Categories
ሥነዉሳኔኛ (About Politics)

የተማሩትን እማትቀበል፤ የተማሩት እማይሆኗት ሀገር

How elites in Ethiopia have suffered from societal clashes in the recent past and how the situation has become today.

bY binyam HAILEMESKEL Kidane, March 23rd 2021 GC.,

ምሁር ዜጋዎች፣ ለኢትዮጵያው ማህበረሰብእ ተገቢ አሽከርነት ማቅረቡን አልበቁበትም። ማረጋገጫዎቹ ሁሉ ቢሰተሩም፤ እየባሰ እሚሄድ ኋላቀርነት መጠጠሩ ዐብዩ ነው።
እነእዚህን ምሁርዎች፤ በሁለት መደብ መክፈሉ ነጥብአችንን የአጠራው አለ። አንደኛዎቹ፤ ጋዜጠኛ ሳሙኤል ጌታአቸው እንደቀነጨበው ሀተታ፣ Ethiopia’s Half cooked graduates, (AddisFortune ጋዜጣ December, 20, 2016 GC.,)፣ በትነሹ እና ሳይሟላ በተዘጋጀው ትምህርት ስርአት በማለፍ የተመረቁት ግን ሲወጡ በአገኙትም እብስልስልታአዊ (intellectual) እውቀት እና ክሂሎት ማገልገል የአልቻሉ ናቸው።
የ አዙሪት ዘአልፋ ደራሲ ከጋዜጠኛነት ወደ ስነውሳኔኛነት (politician) ተሻግሮ የነበረው በላይ ማናዬ፤ ከ አራት ኪሎ እስከ ስድስት ኪሎ (ይህ ትውልድ) በእሚለው ሁለተኛ የመጽሐፍ ሙከራው (2006 ዓም.)፤ የተጠላው የኢህአዴግ. አስተዳደርን እጅግ በትንሹ፣ ሠንጠረዥአዊ ወይም አርእስትአዊ እና ደፈናአዊ ቁንጽል ሙከራ ሲተች፤ አንዱ የአነሳው ነጥብ፤ የኢህአዴግ. ዘመን ትውልዱ ተምሮ እንደተማረው የአክል ማገልገል እና መኖር የአልቻሉ እንደአሉ ይገልጥ አለ።
“ሀገሬን በቴክኖሎጂ ከፍ ወደ አለ ደረጃ አደርስ አለሁ ብየ ዲግሪዬን ጭኜ ከዩንቨርስቲ ስወጣ ዶሮ አርቢ ወይም ድንጋይ ጠራቢ የሆንኩ እኔኮ ነኝ…ይህ ትውልድ።” (ገ.7)
በደፈናው፤ የስራአጥነት ጉዳይ ጋር እሚገናኘው ይህ ጉዳይ፤ ፍችው፤ የተማሩ ዜጋዎቿ በአገኙት መለስተኛም ሆነ ደግ የእውቀት ጥረት አገልጋይነትን ማግኘት ስለአልቻሉ፤ ኢትዮጵያ ለተማሩላት እንደ አልሆነች ይገልጥልን አለ።

ይህ ደግሞ ሁለተኛው መደብ ነው። በተሻለ አቅም ከመደበኛ መማር በላይ ተምረው እና ተመራምረው፤ ለልዩነት እሚመጡ ምሁርዎች አሉ። ዳሩ በመደበኛነት ከእነእሱ ውጭ በሆነ አመክንዮ አይቀናአቸውም። ይህን በሁለት መቼት ከፍለን እንመልከት። ንጉሥ ቀዳማዊ ኃይለስልሤ በትምህርት አበክሮ በማመን ብዙዎችን አብቅተው ነበር። ውጭ ድረስ እሚማሩት ምሁርዎች የሀገርአችንን የዛሬ መሰረት የጣሉ ነገርዎችን ሲከውኑ ነበር። ዳሩ፤ ከአቅምአቸው አቻ ግልጋሎት አላቀረቡም። የእዛ ዘመን ምሁርዎች፤ ለአለመንበልበልአቸው አመክንዮ ሆኖ፣ የተጋፈጡት ማህበረሰብእአዊ ተቀባይነትን ማጣት እና በሂደት ደግሞ የአብዮት ናፍቆት ነበር። ለመጀመሪያው ማረጋገጫ፤ ሁለት ልብወለድዎችን መመልከት በቂ ነው።
የበዓሉ ግርማ ከአድማስ ባሻገር፣ ዋና ገጸባህሪዎቹ ውጭ ተምረው ወደሀገርቤት ሲመለሱ የገጠመአቸውን የማህበረሰብእአዊ መጋጨት እሚነግር እውቅ ትርክት ነው። በተመሳሳይ፤ የዳኛቸው ወርቁ አደፍርስ፣ ዋና ገጸባህሪው አደፍርስ የኢትዮጵያአዊው ማህበረሰብእ አስቸጋሪ እና የተማረን እማይቀበል ሆኖ አጊንቶት በተመሳሣይ ቀውስ ሲንከራተት የአስመለክተን አለ።
[እንደ ወረደ የምሁር ሀሳብዎቹን ከመጠቀም ይልቅ፣ ረጋ ብሎ ሀገርአዊነትን እንዲፈልግ እና ቀድሞ ይህን የአልተማረ ሀገር እንዲመሳሠል መክረውት፤ አቶ ወልዱ አደፍርስን ማናገር ቀጥለው አሉ]፤ “እንድታውቅ እምፈልገው እኔም በዘመኔ የፈረንሳይ ተማሪ እየተባልሁ እንደአጉል ፍጥረት ስታይ የኖርሁ መሆኔን ነው። ጨርሶ የውጭ ሀገር ትምህርት ከሌለአቸው አንዳንድ ሰዎች ይልቅ እኔ ፍላጎትአችሁ እና አላማአችሁ የእሚገጥምአችሁም መሰናክል በይበልጥ ሳይሰማኝ እና ሳይታየኝ አይቀርም። እና የልቤን ለልቤ የአክል የነገርኩ የአክል ነው የአጫወትኩህ።” (ገ.154)
ይህ መቼት ችግር የሆነበት፤ እንደ አለንበት ወቅት የተማሩ ዜጋዎች እና ዝመና በብዛት ማጣቱ ነው። ወደስልጡን አኗኗር የአልተጋለጡ ህዝብዎች ይበዙ ስለነበር፣ መማር አንድም የስቃይ እና ግጭት ምንጭ ነበር።
መውጫ መልሱ ለዛሬውም ሀገርአችን እንደሆነው ግን አቶ ወልዱ፣ አደፍርስን እዛው አካባቢ እንደመከሩት የውጭውን ትምህርት ወደ ዉስጥ ሀገር ሲያመጣ በጥሬው ከእሚሆን፣ ሀገር ውስጥ የአለውን ነገር ፈትሾ ተመሳሳዩን ሃሳብ በመፈለግ በዐዱን በቀጥታ ለቀበለው ህዝብ ከመግለጥ፣ ከውስጥ የተገኘውን አስተሳስሮ መንገሩ ይሻል አለ ብለውት ነበር። ለምሳሌ፣ ወንድምአማችነት ፍልስፍናን ከፈረንሳይ በቀጥታ ከማምጣት እዚሁ የአለህ የእንግዳ ተቀባይነት ልማድህ ነው ብሎ ህዝቡን ማሣወቅ እሚሻል ነው ብለው ነበር። ያ፤ በእርግጥ አሁንም አስፈላጊ ነው። ይህም ብጁአዊነት (customization) ወይም አካባቢአማነት (localization) ይሰኝ አለ። እውቀት እና ጥበብ ድንበር ባይኖርአቸውም፤ ስለአልታወቁ እና በሀገርውስጥ ዳዴ ብለው ስለአላደጉ በዐድ ሊመስሉ ይችል አለ። ስለእዚህ ጥበብ ከአካባቢው ልማድ ተመሳስላ ሀገርአዊነት ተላብሳ መግባቷ፤ ከድንገት መምጣቷ ተያይዞ የእሚቀርብ ግጭትን ቀንሶ ወይም አስቀርቶ እንዲቀበሉት አንድ አማራጭ ይሆን አለ።
ይህን መቼት ዘግተን ወደ አሁኑ ትውልድ እንምጣ። አንደኛውን የተምሮ ስራ ማጣት እንደአየንው ሆኖ፤ ሁለተኛው ደግሞ በደንብ ተምሮ ስራ ፈላጊነት ሳይሆን (የማህበረሰብእ መሪ መሆን ሲቻል)፤ በተለይ በኢህአዴግ. አስተዳደር ያ የአልተሳካበት ነበር። አስተዳደሩ፤ እነእዚህን ከሌላ አደጋ ተደርገው እሚታዩ የዜጋዎች መደብ መሀከል እሚያድንአቸው ነበሩ። እነእዚህ፣ ታላላቅ ምሁርዎች በሙያአቸው ከማገልገል አንሶ፣ በክፍል ውስጥ ከማስተማር እንኳ ሲባረሩ ወይም ጫና ሲደረግብአቸው ነበር።
ልክ አስተዳደሩ ለመውደቅ ሲቀርብ፣ ብዙ ልሂቃንን ወደሹመት አምጥቶ ያንን አመል በጥቂቱ አብርሶ ነበር። ግን፤ የዘገየ እንቅስቃሴ ሆኖ፣ የኃይለማርያም ደሳለኝ አስተዳደር ወዲያው ከእየመመራመሪያው ጣቢያ ተፋጥነው ከተሰበሰቡት ምሁርዎቹ አብሮ ወረደ።

ዛሬ፤ ከአየር የተፈጠረው ብልጽግና አስተዳደር ውስጥ አንዳንድ ምሁርዎችን ወደ ስራ መመለስ እንኳ የተከወነ እንደሆነ እሚሰማ ነው። የ ኢዜማ. መሪ ብርሃኑ ነጋ (ሊቀምሁርዎች/Prof.) በየካቲት ወር 2013 ዓም. ደግሞ፣ ልሂቃንን የሀገርአችን አስተዳደርአዊ ስርአት ኢህአዴግ. ስለወደቀ አበቃ ማለት ሳይሆን ገና ለመለወጥ እየተጀመረ ስለሆነ በአለመፍራት እንዲመጡ እና እንዲያገለግሉ በይፋ ጠይቀው ነበር። በተመሳሳይ ወቅት ደግሞ፤ እውቅ ስነውሳኔኛ እና ደራሲ አንድአርጋቸው ጽጌ፣ በ ኢሳት. ትመ. ሲናገሩ፣ እሚመኙት እንደ እንግሊዝ መንግስት እዚህም፣ የተማሩ ልሂቅዎች መንግስትን ከጀርባው እንዲመሩት እንደሆነ ገልጠው ነበር።
በአጭሩ፤ በሠላሳ አመትዎች ጀርባ የህዝብ ደም እና ትግል ጥቂት አፍርቶ በደንብ ለተማሩት ሀገርን ለማገልገል እንዲችሉ ሁኔታው እየተሻሻለ ነው።
ሁሉም መማር እሚገባው ነገር፣ እነ አደፍርስ እና ከአድማስ ባሻገር፣ የተማሩት ሲማረሩ የአሳዩንን ሁኔታ ማስተካከል እምንችል ማህበረሰብእ እየሆንን መምጣትአችንን ነው። ለነገሩ፤ የተማሩትም በበለጠ ህዝብአዊነት እና እሳቤዎችአቸው መንግስት ሊወድቅ ሲል ግቡ እና አገልግሉኝ ባለ ጊዜ እንደ እነ ሀዲስ አለምአየሁ እነቢኝ ከማለት ወደእሺታ በመምጣት አምባገነንን ሰገልገሉንም፣ የሐይለማርያም ደሳለኝ አስራአንደኛው ሰዓት ምሁርዎች አሳይተው ነበር። በሁሉም ዘርፍ ለውጥ መከሰቱ ደግ ባይሆንም፤ በደፈናው ግን፣ በቀኝ ጎን የአለው ለውጥን ግን ልብ ማለት ይገባ አለ። ቀጣዩ ተመዛኝ መንግስት ሳይሆን በብዙ ማእረግ የተማረ እና እሚገኝ ክፍለ ማህበረሰብእ ነው።
በደፈናውም ቢሆን የእነ በዓሉ እና ዳኛአቸው ጭንቅ ቀንዎች አልፈው የተማረን እማይቀበል ሀገረሰቤ እንኳ እየደበዘዘ ነው። ስለእዚህ፤ ብዙ ዝብ-አረዳድ ይዞ እሚገኘውን፣ “ሀገርበቀል እውቀት” እሚሰኘውን ጭጋግ በመገልገል – ያም ልማድ እንጂ የተለየ በእራሱ እሚቆም እውቀት ለማለት ስለአልሆነ ነው – ወልዱ እንዳሉት ሀገርአዊ ጉዳይዎችን በሀገርአዊ ልማድ አስተሳሥሮ መሰጠንን ማፍጠን እሚገባበት ወቅት ነው። የተማረ እማይረዳት የሆነችው ሀገር፣ በፊትም ሊረዳት ሲገባ የአልተቻለው ምሁር፣ ዛሬ ግን በእርግጥም ጭላንጭል ፈቃድ አግኝቶ አለ። ሀገርን ከእንግዲህ እንደ ደራሲዎቹ መውቀስ አብቅቶ፣ በብዙ ልምድዎች እና ልህቀቱ፣ ለጨለመው ሀገር ብርሃንነት ወደ ዘለንጋ መውጫው መቼት እነሆ መጥቶ አለ። የተማሩትን የእማትቀበለው ሀገር፤ ዞሮዞሮ የተማሩትም አልሆኗትም ነበር። ያ መቀልበስ ከቻለ፤ አሁን ግን የተማሩትን ስትቀበል የተማሩት አለመሆንአቸው ብቻ እሚቀጥል ይሆን አለ። ከአንድ ትልም ንድፍ፣ ወይም ምርምር እና ስራ ጋር ሆኖ እዩኝ እርዱኝ መንግስትም ይደግፈኝ ከማለት ወደ ሁለገብ እና ቡድንአዊ ወይም ሌላ አማራጭዎች በመከተል ነጥሮ መድረሱን ማበርታት ይገባ አለ። አሁን ልዩነቱን ለመሆን የተግባር ፈተና ብቻ አለ። የእነአደፍርስ እና ከአድማስ ባሻገር ወራሽ ስነእናኪነጥበብም ቀጣዩን ችግር ማነፍነፍ አለበት እንጂ፤ ምሁር የእማይቀበል ሀገር ውስጥ ምሁር የመሆኑ ሴራ አዲስ ጭብጥ አይሆንም፨

By Binyamhailemeskel

Hey there! If you want to know about me, I just like fun, commonsense wisdom, and human love. Let us live a bright today changing tomorrow into brighter.
Regards,

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s