Categories
መልካም ጥበብዎች Fine Arts

ስልተ-ተረትተረት፡ የሀበሻ ዋናጅረት (Mainstream) ፊልም ዘርፍ ተራራ-አቻ ችግር

About explaining one of the basic problems in the Ethiopian film making attempts – doing plots only through dialogues of characters – style_of_teret_teret.

bY binyam HAILEMESKEL Kidane, March 09, 2021 GC.,

ብዙ የዘመኑን ሀበሻ-ፊልምዎችን መሄሰሥ፣ ቀላል ስራዎች መሐል ነው። ህጸጽዎቹ፤ የተሰለቸ-ጠቅላላእውቀት ስለሆኑ፤ ተችቶ መሳሳት በድንጋይ ወርውሮ ምድርን መሳት ነው።
አንዱን አስማሪ ችግር ከእነእዚህ – እንደመነሻውይይት – የችግር-መስመሩን ሙሉ ምስል ለመሳል ባንችልም፤ መስመር በነቁጥ ስለእሚጀምር መነሻ ነቁጡን፤ ለማስፈር እንሞክር። ይህ ውይይት ሲቋጭ፤ የፊልም ዘርፉን የሴራ እና ትርክት አቀራረብ (plot and story presentation) ጥንትአዊነቱን እሚጠቁመን ነው። እንዴት እዛ ተደረሰ ሲባል፣ ስልተ-ተረትተረት እምንለው በዋነኛነት ትርክት እና ሴራ አፈጣጠሩ፣ አቀነባበሩ እና አቀራረቡ ነው። ስልተ-ተረትተረት እንዴት ይከወን አለ? ትርክት ነገራን (story telling) በአንደበት ቃልዎች የመዘብዘብ እና የማቅረብ የዋህ ሙከራ ሲሆን እሚፈጠር ነው።
በቀላሉ የውይይቱን ፍሬ-ሚዛን ለመገንዘብ እንዲረዳን ሴራ፣ እና የትርክት አቀራረብ (story presentation) ክሂሎትአማአዊትዎች (techniques) አመጣጥአቸውን በፍፁም ናሙና ደረጃ እንወያይ።
ሴራ የፊልሙ ትርክትን እሚንቀሳቀስበትን ምክንያት እሚሰጠው መንገዱን እሚያነጥፍለት በተለይ ከግጭት ጋር እሚገናኝ ነው። ሴራ እሚንቀሳቀሰው፣ ፊልሙን ለመገንባት ነው። የፊልም እና ተረትተረት አተራረክዎች አንዱ መለያአቸው፤ የተረትተረትን ሴራ አንድ መጽሐፍ ወይም ግለሰብ (አንደበት) እየነገረን ማስተላለፍ ሲችል፣ ፊልም ግን፣ ተዋናይዎቹ ተቀምጠው እሚነግሩን ዜና አይደለም። በመቼት እና ድባብ እየተራወጡ፣ በግጭት እየተፋተጉ፣ ወደአንድ ፍፃሜአቸው በእሚከውኑት ትግል እሚነገረን የሴራ አይነትን የያዘ ነው። ፊልምም፤ እንደ ተረትተረት መንገሪያ ስልት፣ በቀላሉ ተዋናይዎችን አስቀምጦ ሴራአቸውን የአለ እንቅስቃሴዎች እሚያናግረን ከሆነ ስልተ-ተረትተረት ይሆን አለ። ትርክትንም በጥቂቱ እንመልከት።
ትርክትን ከመካከለኛው ዘመንዎች (middle ages) ቀድሞ፤ በተረት መንገድ ማቅረብ የበዛው ክሂሎትአማአዊነት (technique) ነበር። በሂደት፤ መተረክ እየዘመነ፤ በአሳለፍንው ሚሊኒየም መነሻ አካባቢ፤ የ ቢዎፉል (bewoeful) ትርክት ለምሳሌ፤ የዘመንአዊ አተራረክ መነሻ መለኪያ ተደርጎ እሚታይ ሆኖ፤ ትርክት ነገራ መሠልጠኑን የወጠነ መጽሐፍ ይባል አለ። በሂደት፤ ዘመነ ዝማኔ (modern age) ተቋቋመ። ቀጥሎ፤ በጣም በቅርቡ፤ ድኅረ-ዝማኔ (post-modernism) ተፈጥሮ፣ ውስብስብ ታሪክ አቀነባበር እጅግ ከፍተኛ ግርምታን እየቸረ እሚያዝናና እና እሚያስተምር ሆነ።
ይህ በጠቅላላው የስነጽሑፍ አመጣጠጥ መንገዱ ቢሆንም፤ በፊልምም፤ ተነፃፃሪት አለው። ትርክትነገራው፤ በተረትተረት መንገድ ከመፍሠስ የተወሳሠቡ አቀራረብዎችን መያዝ በቅርብ ዘመንዎች ጀመረ። ይህም፤ በተለይ ከጭብጡ ጎን ሴራውን የአስተካከለ ሆኖ እሚጎላልን ዝማኔ ሆኖ አለ።
ሴራዎችን፣ በድርጊትዎች እና ትርክትዎች ማቀነባበር የአለው እውነታ ሆነ። የአንድ ፊልም ፍቺውን ለመረዳት፤ ሴራውን ስንተረጉም፤ ያ በትርክቱ ፍሰት እሚቀርብ ሆኖ እምናገኘው ነው። የኩነትዎች ድርጊትዎች እና እድገትዎች ደግሞ ትርክቱ እሚቀነባበርብአቸው ስልት ናቸው። ዋናው እና ዘመንአዊው ስልተ-ትርክት አፈጣጠር፣ አቀነባበር ወይም አቀራረብ ያ ነው። በእዛ ፍሰት ደግሞ ያለው የግጭት እና አመክንዮአዊነት ትስስር የሴራው ጥንካሬ እና ውበትን ገላጭ ነው። ያ፤ የዘመንአዊ ስልተ-ፊልም ነው።
በተቃራኒው ወደተለመዱ፣ ብዙዎቹ ወይም በተለይ የአለፈው አስርት (decade) ዋናጅረት የሆኑት ምርትዎች፣ እሚያደርጉትን እንይ።
በዋና ውድቀትአቸው መሰረት፤ ትርክትን በድርጊት አያቀነባብሩም። ድርጊት ሲባል፤ የጠብ (action) ጉዳይ ሳይሆን፤ የገፀባህሪዎች ውጣውረድ ነው። እነእዚህ የሀበሻ ፊልምዎች ግን በትርክቱ መሰረት እሚንቀሳቀሱ ገጸባህሪዎች እምብዛም አያስመለክቱም። እጅግ፤ በማውራት ግጭት፣ እና ሴራአቸውን እሚገልጡልን ናቸው። ወሬ እናደምጥ እና፤ በድርጊት ሳይንቀሳቀሱ ትርክቱን ያስኬዱት አለ። ወዲያው ፍፃሜው ይቀርብ አለ።
በተለይ የድራማ ዘውግ ምርት በዘርፉ ስለበዛ፣ ስልተ-ተረትተረትን ተገልግሎ ፊልም አምርቶ ማቅረቡ የበዛ ሆኗል። ለአምራቾቹ ድራማን ከድርጊት ውጭ መረዳቱ የችግሩ ጉዳይ ሆኖ አይታይአቸውም።
ለምሳሌ፤ የአስፈሪ፣ የድርጊት፣ ጦርነት፣ ልብሰቃይ፣ ወዘተ. ዘውግዎች የሉም ማለት እሚቻል ነው። ቢኖሩ፤ ከምልልስ ይልቅ የግድ በድርጊት የመጠመድ እድልአቸው ብዙ ስለእሚሆን ስልተ-ተረትተረትአዊ አቀራረብ ቢያንስ ይቀንስ ነበር። ግን፤ አንድ ዕውቅ እና ትልቅ ሃያሲ የሀበሻ ፊልም ዘርፉን አክብሮ አንድወቅት ችሎ በመመልከት በአንድ ጽሑፉ እንደመሰከረው፤ አፍጊት-ንሁለላ (romance comedy) ፊልምዎች በገፍ ከሁሉ በዝተው እሚመረቱት በወጪአቸው እርካሽ ስለሆኑ ነው። ቢሆንም፤ ድራማ በድርጊት የእሚከወን ትርክት እንጂ በምልልስ ላይ ብቻ አተኩሮ እሚደረግ መሆን የለበትም። ገጸባህሪዎቹ፣ ግጭትአቸው፣ ምላሽአቸው፣ ጉዞ እና መድረሻአቸው፣ በጠቅላላ ትርክትአቸው፣ ድርጊትአቸውን መሻት አለበት። ውሳኔዎች፣ እንቅስቃሴዎች፣ እቅድዎች፣ እና ወዘተ. ብቻ ከአንደበት እሚወጡ ቃልዎችን የተነጠለ እና አጠገቡ በመሆን እሚያግዝ በመሆን መቅረብ አለብአቸው።

ከእዚህ ውጭ፣ አቀራረብ በተለመደው ትርክቱን በገጸባሪዎች በመቀጣጠር እና ተገናኝቶ ተቀምጦ፣ በማነጋገር፣ ጭብጥአቸውን በመሀከልአቸው እየነዱ ወይም እየጎበኙ ሳለ በማወያየት፣ ወዘተ. መገንባት፤ ተረትተረትአዊ ስልት እሚሰኝ ይሆን አለ። እሚያስተላልፉልን መልእክት እና ትርክት፣ በወሬ እሚተላለፍልን በመሆኑ፣ የፊልም ጥበብን ማሳየት አይቻለውም። ጭራሽ፤ በጽሑፍም የቀረበ ቢሆን፣ እጅግ የተስተካከለ የድርጊት ፍሰት እንጂ የውይይት ብቻ አቀራረብ አዝናኝ የመሆን እድሉ አናሳ ነው። በቀረ፤ የፍልስፍና፣ የትምህርት ወዘተ. ጉዳይ፣ ዘመንአዊ ስነጥበብ በተለይ ደግሞ ፊልም፣ ሴራው በድርጊት ሂደት ጥርስዎች ትርክቱን እያኘከ እሚጎነጎን፣ ከውስጡም ተደራሲ እያመሳጠረ እሚመለከተው እንጂ እያደመጠ እሚጋተው መሆን አይችልም። ያ፤ እጅግ ያረጀ ትርክት አወቃቀር እና አቀራረብ ነው።
ይህ ጠቅላላ እይታዎች እንጂ እንደምሳሌ ለመጥቀስ እሚበረታ ጽሑፍ ስላይደለ መነሻነቱም ላይበረታ ይችል ይሆን አለ። ዳሩ፤ በጠቅላላው ግን እሚያስመለክተን እጅግ የተለመደ ባህልን ነው። አሁንም ለደፈና ምሳሌ ግን፣ አንድ ፊልም ላይ፣ አባት ተቀምጠው ለልጅልጅዎች (እና ጓደኛዎቹ) ስለሀገር መውደድ በመምከር እና በመስበክ ፊልሙን ሲጨርሱት እንመለከት አለን። በድርጊት አርበኛው አያት እሚያሳዩን የለም። ተቀምጦ ስለአርበኛነትአቸው በመንገር ግን የፊልሙን ፍሬ እንድንንነገር እንገደድ አለን። ልክ እንደ ተረትተረት። የባሰው እውነታ ጭብጡም፤ እንደተረትተረት የሀገር ብራና መጽሐፍ ከድብቅ ሽያጭ በማስጣል እሚጠናቀቅ እንጂ ምን ማድረግ እና መጠቀም እንደእምንችል አያስመለክተንም። ዋናው ግን፤ በመቀመጥ እሚሰብኩት ገጸባህሪን ትርክት ነጋሪ ማድረጉ እጅግ ሰነፍ አቀራረቡ ሲሆን ለመታገስ ከባድ ነው። ለምሳሌ እንደአማራጭ በወጣትነትአቸው ጣሊያንን ወጋሁ እንዳሉት ሲዋጉ አይታይም፣ ያን ከወንኩ ያን ከወንኩ፣ እናንተም ከውኑ እያሉ ሁሌ ሲዘበዝብ ይታይ አለ። ማንም ያንን እማያቅ የለም። በታሪክ ትምህርት ያልተማረው የለም። ፊልምን ያክል ትልቅ የእይታእናድምጽ መሳሪያ ተገልጋይ ጥበብን ግን፣ እንደተረት ማቅረቢኣ አድርጎ ማስቀረቱ እጅግ ከብልሃት ውጭ መሆን ነው።

አንድ ችግሩን ማከሚያው መንገድ፤ ቃለፊልምን (film script) በጥራት ማዘጋጀቱን መመዘን ነው። ቃለፊልሙ፤ በቁሙ፣ ካለሴራው፣ እና ካለድርጊት አንዳች ነገርን እንደቁምነገር እሚያወራ መደረግ የለበትም። ምልልስ (dialogue) በማቀነባበር ከተጠመደ ግን ተረትተረት የመጻፍ እውነትን እንደሰራ ይገንዘብ። ድርጊትዎችን በንግግርዎች አሰባጥሮ መክተት ከአልቻለ፤ ተረትተረት መተየቡ ገና የአልበሰለ መሆኑን መገንዘብ አጋዥ ነው።
እሚፃፍልን ቃለፊልም፣ ሴራ ሊጎነጉን እንጂ አስተያየትኤዎች (commentaries) ሊያጭቅ መሆን የለበትም። ይህ ለብዙ ፊልም እና ተከታታይዎች እሚረዳ ነው። አስተያየትዎችን በምልልስ ገጸባህሪዎች ማቅረብአቸውን በጣም አብዝቶ ማጨቁ፣ ፊልሙን ለዛ ከመግፈፉ ባሻገር፤ እጅግ የበዛ ስልተ-ተረትተረት ተከታይ እሚያደርግአቸው ነው። ይህ ግን በብዛት እሚዘወትር የአፃፃፍ ስልት ነው።
ይህም፤ ጭራሽ እየከፋ ሄዶ፤ ወደ ሁለተኛ ማከሚያው መንገድ፤ ገጸባህሪ አቀራረጽ ያመጣን አለ። ብዙ ገጸባህሪዎችን በገለጥንው ዘርፉ እምንመለከተው፣ በተመደበልአቸው አንዳች ስፍራ ተቀምጠው ወይም የሆነ ነገር እያደረጉ፣ ብቻ በዋነኛ ተግባርአቸው ለሴራው ተግባር ከማዋጣት፣ በአንደበትአቸው ብቻ የተለያዩ ነገርዎችን በመናገር ትርክቱን ሲያጓጉዙ ነው። ተቀምጠው እየጠጡ፣ እየተጨዋወቱ፣ ተኝተው፣ እየተራመዱ፣ ወዘተ. (ብቻ ለሴራው ምንም በቀጥታ እማያግዘው መደበኛ ድርጊት እየከወኑ) ስለሀገር፣ ስለሌላ ገጸባህሪ፣ ስለሙስና ችግር፣ ማፍቀርአቸው፣ ወዘተ. ይናገሩ አለ። በመናገር ብዙ ይጓዙ እና አንዳች የፊልሙ ጊዜ ላይ ወደድርጊት ገባ ይሉ ወይም ሙሉበሙሉ ለተደራሲ ወሬ አመላላሽ ሆነው የመቀጠርአቸውን እንደተያያዙ ፍፃሜአቸውን ይሰጡን አሉ። ድርጊት ውስጥ ያልተሳሠሩ፣ ገጸባህሪዎች ግን፣ ተረትተረት ከመንገር በዘለለ፤ የከወኑት ዘመንአዊ ጥበብ ነገራ የለም። ይህ፤ በዘመነ ስልተ ልኮት (reference) እየቀረበ በዘርፍአዊ አገልግሎት የበዛ ጥቅም እየሰጠ መቅረብ እሚችል ነው። ዳሩ፤ በደፈና፣ ጥሬ እና ገሀድ መንገድ በአስተያየት በገሀዱ አለም እሚገኙ ተተቺዎችን እየዘነጣጠሉ፣ ገጸባሪዎችን አስተያየት አቅራቢ አድርጎ ማቅረብ የተለመደ ነው። ሴራው ላይ እማያግዝ ጭራሽም ለትርክቱ ታዳሚ እንግዳ የሆነ ምልልስን እያስከወኑ፣ ተረትተረት መሰል አቀራረብን ይከተል አሉ። ያ ከታከመ፤ ገጸባህሪዎች የእሚመለከትአቸውን ሴራ ከድርጊት በተያያዘ ምልልስ ከተናገሩት ብሎም በዘመነ ልኮት አስተያየትኤዎችን ከአቀረቡ፤ መዘመን እሚቻል ነው።

ሶስተኛ፤ አዝማችነት (directing) ላይ፣ አለመብሰሉ ያለ ሲሆን፤ ምልልስዎችን በድርጊትዎች የማቀነባበር ስልትአዊነትን መከተል አንድ አማራጭ ነው። ነካሪ (immersive)፣ እና የጀርባ ዐውድ (background) የተሟላለት ምስልዎች አወሳሰድም ትልቅ መርኅ ነው። እነእዚያ፤ በብልህ አዝማች ከተከወነ እሚቀነስ ችግር እንጂ፤ እሚጠፋ ግን አይመስልም። የገጸባህሪ እና ጽሑፍ መሰረት የበለጠ ቀጥተኛ ተሳትፎ በህጸጹ አሏቸው።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s