Categories
ሥነዉሳኔኛ (About Politics)

Modern Self and የአልተሳካው የምእራብ ስልጣኔ በኢትዮጵያ

About the failed ‘west-civilization’ attempts in Ethiopia, its misunderstandings, and way outs.

bY binyam HAILEMESKEL Kidane, March 01, 2021 GC. (የካቲት ፳፪ኛ ቀን፤ ፪፼፲፫ ዓም.፨)

[Get this article on PDF here]

ምእራብን ወደእዚህ ስለመጎተትአችን ታሪክ (እጅግ ናሙናአዊ እና ቁንጽል ውይይት)

በተለይ ከመካከለኛው ዘመን ጀምሮ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ፣ የምእራብ ስልጣኔን በግዝግቤት (importation) ለመከወን ብዙ ተደርጓል።
ዳሩግን፤ የመሳፍንትአዊ ዘመን ፉክክር እና ብጥጥስ፣ ያንን ሳያሳካ እና ሲያደናቅፍ ቆየ። በተለይ በዐፄ ቴዎድሮስ ዘመነመንግስት፣ መሳፍንቱን ማስገበር እና አንድ ሀገርአዊ አስተዳደር ማበጀት ሲጀመር ግን፤ የበለጠ ይህ ትትረት ወደ ገሀድአችን ተጠራ።
በሂደት፣ ዐፄ ቴዎድሮስ፣ ብዙ ፍላጎትዎችአቸው ውጥንዎችን አመጡልአቸው። የክተት ሠልፈኛ በተቀጣሪ ወታደር፣ በአፍሪቃ የመጀመሪያዋ ዘመንአዊ ከተማ ቅሬዎችን ጭምር ለመጀመሪያ ጊዜ በይፋ ይዛ በጎንደር፣ የጥናት እና ምርምር፣ ማምረቻ መንደር (ጋፋት)፣ ወዘተ. ተጀመረ።
በንጉሡ አለማወቅ፣ ከእንግሊዝ መንግስት ተጣልቶ በውጤቱ ግለጥፋት ከውኖ፣ ይህ ቢቋጭም፣ በተለይ ግን ታሳሪአቸው በነበሩት በዐፄ ምንይልክ ግን የተሻለ ተከውኖ ነበር። ብዙ መነሻ የምእራብ አለም ስልጣኔዎች እንደ አባይን በጭልፋ መዝገን ተቆንጥጠው ግዝግቤት ከውነው ነበር። ታች እንደ እምንመለከተው፣ በተለይ በቀኃሥ. ይህ የምእራብ ስልጣኔን በኢትዮጵያ ምድር የመትከሉ ትትረት ጥጉን የተመለከተበት ብቸኛው ዘመን ነው።
ከእዛ በኋላ ይይህ ትትረት ተገትቶ እንደ አለ ነው። ደርግ፣ ማህበረሰብእአዊነት ስርአትን፣ ኢህአዴግ. የከፋ ሰላምሻጭአዊ አምባግነናአዊ ስርአትን ሲከተሉ፤ ሁለተኛው የቻይና ስነውሳኔአወከ (political) እና ስነምጣኔአዊ ስርአትዎችን እንደሰረቀ ሲሰብክ ግማሽ እድሜዘመን አካባቢ ቢቆይም፣ ምንም የቻይና ስልጣኔ ቀለም ግን ለሀገሪቷ አላወረሰም፤ ለቻይና ህዝብ ስራ እድልዎችን እና ለሀገሪቷ የብድርዎችን ዕዳ ከማስረከቡ በቀረ።
በደፈናው፤ የምእራብ ስስልጣኔ፣ በስርአተ ትምህርት እና አንዳንድ ዝብርቅርቅ መንገድዎች እሚታይ ሲሆን፣ ያም ከበፊቱ የቀጠለ፣ ከዳያስፖራዎች ተፅዕኖ የተላከ፣ ወዘተ. እንጂ እዚህግባ እሚባል ምእራብስልጣኔ ሳይሆን፣ ከመጨረሻ ንጉሡ በኋላ በውዥምብር እና ድፍርስ ስርአት ሀገሪቷ እየሰከረች እንደአለች ነች።

ቆይ ግን፤ ምእራብ-ስልጣኔ ዉስጥ ምን አለ?

In what they call Western civilization, a defining element is employment of history, revolutions, fairer set ups, science, legal and political knowledge, etc. to the end of an establishment of a way of new overarching and detailed systems that enriches privet and public lives, as opposed to the feudal and religious supremacy. It is a process that began very few hundred years back, and got momentum at the Enlightenment and industrialization era. It changed in times and become stronger, finer, more successful and a slingshot towards its succeeding eras. Mainly technological, liberal and AI days, succeeded with equality, and democracy entrenching more. Globalization got more momentum.
Hence, more prosperity, liberty, and modernized systems of protection and production led the way to a lot better standards of lives unprecedented. More rights gained respects, more clarity and public transparency as well as representations earned the finest ways of life where life expectancy, health, entertainment, and movements are possible at higher quality and quantity than ever before. More political and military innovations and influences are obtained and making use of resources and developing richer citizenry classes is succeeding. Most recently, environmental protection and space civilizations are becoming better recognized. Peace, and tolerance is much better and moving to better tomorrow is yet another higher possibility.

The Core of this Success in terms of Basic Citizenry

Modern Self is a type of personality in the history of human race that grew on citizens living in a civilized society. In it, citizens understand basic rights, democracy, humanity, nature, governance, diversity, tolerance and Futurism. They are richer through educations or because of side effects of simply living in a modern and individual-celebrating world. Which all leads into what Trump described during defenses against pressures to pass lock-down orders around 2021 as, impossible to contain in houses because of the vigorous energy of citizens in USA. Citizens are living in productive, powerful, expressive, enriched, and nearly at a human most level limitless life styles.
Hence, this Modern Self, brings the defining element of the ordinary citizens at high levels of modern Western civilizations.

What Determines Success and Failure in the Making of a “Western Civilization”

When, this Modern Self evolved within, it flourishes. It is gradual and thus perpetual. It has roots, thus stems and branches. Most invaluably fruits. This is what happened during the renaissances age in the West. The original fight to set up better system for humans lit itself up. Then, in time, it allowed nations to prosper. Again in time, that equipped these nations more global power.
[seeing that] When it is adopted from others, if with solemn care and devotion, then it roots. For instance in Far Asia. Success has been consistent and culture has evolved with this importation of systems, as they were earnest the most.
But, when it is attempted to mimic without a devotion and series belief, it fails destructively. Like in most Africa or third world countries. Here, the modern way is adopted only with no real and utmost care. Probably commenced only as a factual pressure from the post-colonial state of facts that showed a bit of modernization and infrastructures that required domestic skills and interests to own and run. The rest is global charities, influences, standards and pressures. As said by Dinaw Mengistu, only sports and understanding of precarious politics are understood with most depth and hence mimicked well by Africans. When it comes to modern civilization, it matters very little.

Ethiopian Attempts to Westernize (Cont’d)

In Ethiopia, it is no different. The only relative exception being the last emperor who saw modernization seriously in practical definitions. And real changes occurred in those days. The most important thing being education, apparently then. The emperor taught citizens with out their much interests. And quality was the name of the game, very clearly so when compared to any time after the last King until now.
Still, today, the nation has never reached its prominence as in those ages. All the classic poetry, novels, painting, glass tainted arts, music, theatres, etc. of the nation, are from that era. The emperor himself a devoted reader of the West scholars even as a child, young, and leader in different levels, turned fond of rooted Westernization and believed in education. He brought the most first modern attempts in the Sub-continent, and the country. Wrote many useful prefaces for numerous books he ordered be written and get printed in his printing house, and books others wrote. Scholarly publications and discourses were high and well engaging, more that today. Other institutional and legal reforms were solemn that they are still what the nation use directly or with little amendments. In totality, the country was at least relative to its preceding and succeeding history seeing a modern civilization’s beginning through enrichment of its young citizens. Soon, the demise became from that attempt itself though. From the emperor became old and the educated generations, that even became influential over the globe through pioneering African politics and participation in the global governance, became suicidal to the emperor and sadly to itself as well. First in stirring up further revolutionary changes in the nation, and second when the emperor gave their wishes green lights by refusing to accept in becoming part of his administration. Leading only for a military coup and the worst bloodshed in the history of the over 3000 years old nation. As noted by a writer, it was nearly a tower in sky, an utopian wanted by most, and they died and killed, for series dreams. As soon as closer to two decades of brutal dictatorship lasted, the generation itself faded. Still, the nation that pioneered Africa, led the immediate post-colonial Africa, trained Mandela, built the (Organization of) African Union, participated in the making of the League of Nations, is one of the worst of the worst in the glob.

Post Haile Selassie I and the Demise of Ethiopian Attempts to West Civilize

By the end of our Solomon dynasty, many changes are claimed to have been attempted. And they were fairly great, indeed. But, none have succeeded long after the Socialist government came in. Secession of Eritrea and tribalism became the yoke of the nation. What is going on still now is, thousands are murdered, journalists, academicians, and opposing entities are destroyed, systematic dictatorship reigned, the same in the one political leader after the other. More danger from archaic tribalism lures and rules the nation today. Worsening historical legacies are being made as the Nobel Peace Prize Winner, PM. Abiy Ahmed has kept the nation in the same trap of civilians hatred, inter-ethnic-clashes, as well as his ethnic-based political policies and moves, in his administrative in and outs. Education is too subpar, administrations and citizenry is far from national attempts to hone mental and psychological capacities. The same from preceding two eras continues only with a change in façade approaches, (at least as long as practice is weighed) as the formers ones were having the same moves for themselves as well. The PM, says he can be judged some twenty years later, but that is only ridiculous joke as no one shall wait that long. Enough lawlessness, murders, media, journalism and opposition closures and incarcerations, political assassinations, lack of rule of law, etc., existed in his years. None have hopes, except the plantation and resort building attempts, apparently joked by the nation. Hence, the case is a consistent failure. The attempt to modernize, let alone west-modernize has had no hope in the current regime, as its predecessors.

Does Western Civilization Attempts own Hopes Anymore in Ethiopia

Clear. If it is according to the ways that have been used most recently and their failures, the attempts to see Ethiopian west-modernize is going to keep being the national foil it has been.
The mess that kept springing as those murky trials failed, itself is a body of problems. Our consistent failures have such a nasty side effects that, they require another realm of national extended administrations to heal the troubles. For instance, no planned towns, hubs, and lives have flooding everywhere, no matter attempts were made to urbanize, industrialize, and so on. Generations are also coming from brutally ignored education and cultural backgrounds. Urbanization is a disgust and dirty. Resources are intact or abused. Only, reflections of globalization, in its cheap markets search and humanitarian supports, seem to have brought sanity (basic modernity) of citizens.
Now, national administrations are moving towards the risk of anti-nationalism tendencies and beefing up divisive psyches. The two do not go hand in hand. A bit of modernization is dangerous and not honest. It can clash violently when it has no roots of honest attempts. To do a fresh nation in what they call western concepts is one thing and to re-do a nation in those standards after murky methods that, here and there, made many feel they are finely developing because of some cheap Chinese Techno gadgets and most ridiculously Netela (ነጠላ) garments.
Hence, it is not western civilization that fights its way in Ethiopian future. It will also be an unknown space that have jammed, and is cramming, the nation because of 1) no clear-cut moves by the national administration and history, and 2) because global markets eye even the abyss, let alone poor Ethiopia.
Any one not educated proper alphabets actively uses social networks, and home assembled Chinese androids, and feels politically enlightened. As well, unprecedented access to the internet and many outlets and outputs, has marred the honest clean slates in most citizens. In deed, discipline and teaching has become to require of us double task and efforts than we might wanted if the effort was to be made just few decades ago. The nation also dreams of moving towards building some industrial parks and believes that shall redeem it. Or worse, the current interim administration focuses building few resorts in ten years than keeping peace and stability, or paying attention to the accrued urban population’s miseries.
When concluded, it can be summed as follow. Ethiopia has a mixture of uncivilized space (wanting modern civilization) and a second problem that must solve the erroneous consequences of an unmanaged modernization attempts.

በኢትዮጵያ ከእራሱ ከምእራብአዊ ስልጣኔ ውጭ ተቀራራቢው እንኳ እውነታ የለምን(?)

ነገርዎችን በምእራብአዊነት እና አዲሱ ቅኝግዛትአዊ መንገድ አድርገው ለመከላከያነት በመፈረጅ እሚመሰክሩ ሰውዎች፣ ብዙ አጣብቂኝ አሉብአቸው። በመሀከል እሚገኙ፣ ለምሳሌ ኢትሮጵያንስ እየተባሉ የተፈረጁም፣ በደፈናው ከውጭ የመጣ ነገርን ከእዛ የበቀለ ወደእዚህ መልመድ እሚገባው አድርገው እሚመለከቱ፣ እሚፋጠጡት ገሀድ አለ።
በምእራብ የተገኘ እና የበለጸገ ስልጣኔ፣ ስለምን ለእኛ በጀን? ስለምን ጥቂት በጥቂት የተሳካለት እየሆነ መጣ? ስለምንስ መሠረቱ የኢትዮጵያ ምንጭነት አለው እየተባለ፣ ለምሳሌ በሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን ለዌንዲ ቤልቸር እንደተገለፀው ሀበሻ የውጭ ስልጣኔ ሁሉ መሠረትአችሁ ነው እየተባለ እሚነገር ሆነ? የምእራብ ስልጣኔ እሚሰኘውስ፣ ሙሉ በሙሉ እዛ ፈልቆ የአደገ ነውን?

ስልጣኔ፣ ምእራብ እና ምስራቅነት የለውም። የዘረሰው መሰረተ ህይወት ነው። ገሀድ የተፈነተወ ለአልታወረ እኩል የተገለጠ ለአልተመለከተው ብቻ የእሚያመልጥ፣ ነው። ገሀድን፣ ተቀብሎ በመሠረቱ ለተጓዘ፣ ስልጣኔ ሁሉ ወጥ ነው። አመክንዮው፣ የዘረሰው አቅም፣ ፍላጎት እና ተፈጥሮ ተመሳሳይ መሆኑ ነው። ስለእዚህ፣ መሰልጠን፣ እማይለዋወጥ የአኗኗር ማሻሻል ስነስርአት ከሆነ፣ የትም የተለየ መሆን እሚችል አይደለም ማለት ነው።
በምእራብ የተነሳው ስልጣኔ፣ ከሐይማኖት የተነጠለ እውቀት አሠሳን በዘመነ አብርኆት (age of enlightenment) አቅርቦ ስነስርአትዎችንም በእዛ መሰረት በማቀንቀን ስለተሳካለት የተገኘ ነው። የትም፣ እምነት እና መደበኛ አመለካከትን በጥበበምርምር (science) ከተኩ፣ ጥበበምርምርአዊ (scientific) አገነዛዘብ ወደምእራብአዊ ስልጥኔ እራሱ እሚወስድ ሀቀኛ ጎዳና አለው። የቋንቋ፣ ልማድ፣ እና ፍልስፍናዎች፣ ወዘተ. ልዩትዎች ከአልሆኑ በቀረ ሁሉም እሚገነቡት ተመሣሳይ የሽልፍኖት (technology) እና ስነስርአትአዊ አርነትዎችን ነው። እነእሱም፣ በቀለም ከአልተለያዩ በቀረ፣ በመሰረቱ ተመሳሣይ ስልጣኔዎች ናቸው።
እንዲሁ ለመደምደም፣ እነ ሎሬት እንዳሉት፣ እንዲሁም፣ ኩራትን እእሚወድደው መደበኛ ሀበሻ ጭምር እንደእሚመሰክረው የስልጣኔ መሰረት እኛ ነበርን – ከእኛ የሄደው ግዕዝ ነው እዚህ ያደረሰአቸው – ወዘተ. መባሉ፣ ብንቀጥረው እሚመሰክርልን ቢኖር፣ የምእራብ እሚሰኝ ስልጣኔ አለመኖሩን ነው።

የምእራብ ዓለም እሚሰኝ የስልጣኔ አይነት ከሌለ፣ እኛ ሀገርስ ያሉ ሀገርበቀል እሚሰኙ ወይም በነባር (by default) እምንመለከትአቸው የአኗኗር መንገድዎች በስልጣኔ መሀከል ስፍራአቸው ምንድን ነው? በብዛት ያሉን ጉዳይዎች፣ እንደ ሀገር ሳይሆን እንደ ማህበረሰብ (community) በጥንትአዊ አኗኗር ለመኖር እሚበቁ ናቸው። የባህል ህክምና፣ አስተሳሠብ ትልም፣ ልማድ፣ ወግ፣ የአልተፃፉ እና ኢቅፅአዊ ግን ተከባሪ ደንብዎች፣ መሠረትአዊ መከባበር፣ አመጋገብ እና አለባበስ፣ ስራክፍፍል፣ ደስታ እና ሀዘን፣ የመዝናኛዎች ስርአት፣ ወዘተ. ጉዳይዎችን እሚገዙ የባህል ስነስርአትዎች የእሚገኙ ናቸው። ማንም ግለሰብ፣ በጥንትአዊ ወይም መሰረትአዊ መንገድ፣ በእነእዚህ መኖር እሚችል ነው። ያሉ ደንብዎችን ያክብር እንጂ፣ የዘመንአዊ ምድርን ሳይቀላቀል፣ በሀገርበቀል ህላዌ እንዲህ መሰንበት “ወግ ማእረግ” እሚሰኘውን የህይወት እርምጃዎች ማለፍ እና መኖር እና ማለፍ እሚችል ነው።

የኢትዮጵያ ምእራብአዊ ስልጣኔ እና የነበረው ነባር አኗኗር ግጭትአቸው እንደ አሁኑ የመዝረክረክአችን ምንጭ፣ እንደ ኋላቀርነትአችን ምንጭ፣ እና ለዔሊ አስንቅ (ገና ባይከሰትም) ለውጥአችን ዋና መታከም ያለበት አሁንአዊ ችግርነቱ ሲገለጥ

የመጨረሻው የምእራብ ስልጣኔ የጥቂት መቶ አመትዎች ጉዞ ነው። ሀገርአችን የተለያዩ ማህበረሰብእዎችን ይዛ ብዙ ዘመንዎች ቆይታ አለች። ከምእራብ ስልጣኔ መተዋወቅ ቀድሞ በጠቀሥነው የኦሪት ዘመን መሳይ የአኗኗን መንገድ (በተለይ በብዛተወ በባህል እና ልማድ እሚገለጠው) ሲኖር ተመጥቶ አለ።
ሁሉም ነገር እሚጋጨው፣ ልክ በአዲሱ መንገድ መዘመንን ስንፈልግ፣ ነው። ወይም ከጥንትአዊው መንገድ ለመሻሻል መሰልጠንን ስንመኝ። የምእራብ አለም ስልጣኔ በሀገሩ አባትዎች እና ጎልማሳዎች እሚመራ፣ እዛው የበቀለ ነው። ልክ የእኛን አኗኗር መንገድዎች ሀይማኖትዎች፣ እናት እና ሽማግሌዎች ከላይ ሆነው እንደእሚመሩት፣ በምእራቡም ነፃ ተቋማት፣ ፈርቀዳጅዎች እና አዛውንትዎች እሚመሩት ሆኗል። እንደእኛ ከነበሩበት ጥንትአዊ አኗኗር ውስጥ ዘቅጦ መኖሩን አባትዎችአቸው (ለምሳሌ የአሜሪካ መስራች አባትዎች እንደእሚባለው) የአስተውት እና ታላላቅዎችአቸው ማህበረሰብን እየመሩ የመሰረቱት ነው። ሠፊ ወለል እና ባህል አለው። ታላላቅ ፈጣሪዎች፣ ፀሐፊያን፣ ዳግተመራማሪዎች፣ ነጋዴዎች፣ ከጥንት ጀምሮ ታላላቅ ዕድሜን የኖሩ ነበሩ። ልጅዎችን እና ወጣትዎችን የአንቀሳቀሱት እነሱ እንጂ ሌላዎች አልነበሩም። ስነስርአትዎችም ከእምነት እየተነጠሉ ጠባቂ በመሆን ቀኝ እጅ ለለውጡ ሆኑት። ስለእዚህ፣ ሁሉም በሀቅ እሚጓዝ ሆነ። አማራጭ ወይም መወላወል የለም። ስልጣኔው በእራስሠር (authomatically) እራሱን እየገነባ እሚጓዝ ሆነ። በተለይ የነፃ ገበያ ስርአት የሰራን መሸለሙ፣ እና ባህል መደረጉ፣ መንግስት ህግ እና ስርአት (ለምሳሌ የትምህርት) መመገብአቸው፣ ሁሉን ወደ ጫፍ እሚያገሠግስ አደረገው።

እዚህ የአለው የእኛ እውነታ ግን፣ የተዘበራረቀ ነው። ሀቅን ማዳበር አልተሳካለትም። ስለእዚህ በጠቅላላውም አልተሳካለትም።
የመጀመሪያ ችግሩ፣ የማህበረሰብእ መሪዎች እና ሽማግሌዎችን አግላይ ነው። የቱም ማህበረሰብእ በታላላቅዎች እንጂ በታናናሽዎቹ አይመራም። በተለይ በተለይ በጥንትአዊ አኗኗር ለሺህ እና ሺህዎች ዘመን የሰነበተ ህዝብን እሚመራው ታላላቅዎቹ፣ እና እሚያስኬዱት ልማዱ ናቸው። እነእሱ መሀከል መንገድ በእግርዎች ዳና ብዛት ሳሩ እየተላጠ ቢወጣ፣ ወይም የተደላደለ መልክአምድር ከሆነ፣ የሰመረ መንገድ ይሰኝ አለ እንጂ እማያልቅ ተሳትፎ ተደርጎበት በመላ ማህበረሰቡ እሚገነባ የዘመንአዊ መንገድ አረዳድ እንኳ የለም። ህክምና በዘር እና በባህል እንጂ ሙሉ ማህበረሰብእን እሚያሳትፍ እና ሁሌ እየዘመነ እና እየተሻሻለ እሚጓዝ አይደለም። አፈቃል እና ትውፊት እንጂ መተየብ እና ማህደርአዊነት አይታሰብም።
በእነእዚህ አካሄድዎች መሀከል ሳለን፣ ማለትም ሀገር በቀል ስልጣኔን ሳናዘምን፣ ሌላው አለም ያንን ከወነ። እንደጠቀስንው፣ በቅኝአገዛዝ የተነሳ፣ ቀደም ብሎ ደግሞ የዐፄዎቹ እንደ እነ ቴዎድሮስ ለምሳሌ በመስተጋብርአቸው አለሙን እየተመለከቱ መማማር ጀመሩ እና ከአለበት መምዘዝ ማቀድን ወጠኑ። አንዱን ሽልፍኖትአዊ (technological) መሳሪያ ግዝግቤት ሲከውኑ፣ ሌላውን ሲያስከትሉ፣ ሁሉም በአድ ሲሆን እና በትክክል አልለምድ፣ በትክክል ወጪውን መቀነስ አለመቻል እና ማክሰር፣ ለሙስና እና አምባግነና እሚያበቃን ብቻ ሆነ።

ስነስርአቱ ሀቅን ያጣ ሆነ። ለምሳሌ ንጽስነውሳኔ (democracy)፣ የተመነደገው በአብዮትዎች እና በታላላቅ ትግልዎች ነበር። በሂደቱ ሁሉ ከእንግሊዝ ምድር ያ ያነሰ ቢሆንም። (ለምሳሌ መሰረትአዊ አቻ አስተዳደጉ በ ጣምራመንግስት (federal) ስርአት ጥንስስ በኢትዮጵያ ውስጥም በዐፄ ዮሐንስ ፬ እና ምንይልክ ፪ ተከውኖ ነበር፤ አፈግፍጎ ቀጥሎ ደግሞ በእዛው በመጥፋት ቀረ እንጂ።) ዞሮዞሮ፣ የኢትዮጵያ ጉዳይ ግን በህግ፣ ደንብ እና ዘላቂ ስርአት አይመራም። የእንግሊዝ ጭሰኛዎች ግን ከዘመነ አብርኆት ቀድመው በህግ ነፃነትአቸውን በማሳወጅ ብቻ ፈረንሳይን ለመከላከል በማስገደድ፣ መሰረትአዊ የህግ ስርአትን አስጀምረው ነበር። እነ ዐፄ ዮሐንስ፣ ምንይልክ ግን፣ አባ ጅፋር፣ ወይም ሌላ ባላባትዎች እና ጭሰኛዎች ግን፣ ሲሞቱ አብሮአቸው እሚሞት ጣምራመንግስትአዊ ነፃነትዎችን በተራ መፃፃፍ እና መነጋገር እንደፈጸሙ ነበሩ።
በሂደት፣ የምእራቡ ስልጣኔ ከጦር ቁሳቁሶች እየተነሳ ወደ ቅንጦት የንጉስ ቤተሰብ እቃዎች እየተረማመደ፣ ወደአለንበት ዘመን ለመሻገር በቃ። በተለይ በምንይልክ ዘመነ መንግስት፣ የተለያዩ የምእራብ ስልጣኔዎች በተውሶ እዚህ ሲጠነሠሱ፣ መሰረትአቸውን ሳቱ። በእርግጥ፣ በተለይ ዐፄ ምንይልክ ካቢኔትዎችን ሠርተው በሞት ሲለዩ ጥቂት የጠነከረ ወራሽ አመራር እንዲኖር ሞክረው ነበር። ዳሩ፣ ወንድ ልጅ ስለአጡ እንጂ አስመኪ ወራሽ ካለ ያ እሚታሰብ አይደለም።
ዛሬም፣ አብዛኛው ህግ እና ስርአት እንኳ በእየመንግስቱ እሚቀያየር እና ምንም ወለል የአልጨበጠ ነው። እነ መራራ ጉዲና እንደእሚሰብኩት ገሀድ፣ ገና በዘመንአዊነት የአልተመሰረተ ሀገር ያለን ነን። ይህ ትልቅ ነጥብ ነው። የአልተመሰረተ ዘመንአዊ ስልጣኔ ቀላል ነው። የአልተመሰረተ ዘመንአዊ ሀገር ግን ከባድ ነው። እጅግ እስከአሁን የቆየንው በኋላቀርነት እና ዝብርቅርቅ ብቻ መሆኑን ፈንትዎ እሚያስመለክተን ነው። በአጭሩ፤ የጀመርንው ዘመንአዊ ስልጣኔ የለም። የእምንሰርቅአቸው ቅንጥብጣቢዎች ብቻ አሉን።
በተለይ ግን በቀኃሥ. ጥቂት የተሻለ ነበር። ደራሲ፣ ሀያሲ፣ እና ፀሐፊ ዳለጌታ ከበደ እንደገለጠው፣ ከበደ ሚካኤል አንድ መጽሐፍ ለመፃፍ ሲነሣሣ ቀኃሥ ሰምተው፣ ስለ መጠቀ ነገር ከመስራትህ ቀድመህ ስለ ስነምግባር ፃፍ፣ ሃገሩ የአልሰለጠነ ህዝብ አለው እና ስልጣኔ ብታመጣለትም ስነምግባር ገና ስላልተማረ ያጠፋው አለ፤ ስለእዚህ ስነምግባር ማስተማሪያ ፃፍ ብለውት የንጉስ ትእዛዝን ለማክበር በእሚል ሳይደሰት ቢሆንም ትምህርት እና ምሳሌ በሁለት ክፍልዎች አዘጋጅቶ ስለመልካም ገፀባህሪዎች ትውልዱን ሰበከ። በጠቅላላው፣ ይህ መነሻ እሚያሳየው፣ ንጉሱ ስልጣኔ እንደአልነበረ ተረድተው ነበር። ስለእዚህ ስለሀገሩ መለወጥ በትምህርት ዘርፍ ይታትሩ ነበር። በእየዘርፉ ከነበረው ብዙ ለውጥ በበለጠ፣ የአስተማሩት እና የከዳአቸው በእዛም ሀገሪቷን ለደርግ ሰጥቶ የከዳው ትውልድ በታሪክአችን ሁሉ የተሻለ ስልጣኔ ጫፍ የደረሰ ነበር። ቢሆንም፣ አንደኛ በጥቂት ተፅዕኖ ተገትቶ አፍሪቃን እንደሰበሠበ እና ኢትዮጵያን በዘመንአዊነት እንደመሰረተ ወዲያው መልሶ ጠፍቷል። ሁለተኛ ከቶ ሙሉ አልነበረም። ማረጋገጫው፣ የደርግ መሰረተ ትምህርት ነው። ያም፣ በገጠር የነበሩ እና ምንም ዝማኔ እማያውቁትን በማስገደድ ለአንድ አመት አስተምሮ ማስፈረም እና ማስፃፍን የሞከረ ነበር።
በደፈናው፣ እንደ ደርጉ የሰመጠ ማህበረሰብአወከ እውነትን የአልጠረበ የመሰልጠን ሙከራ ሀገሩን እሚልጥ እና እሚያቆስል እንጂ እሚያሳድጋት አይደለም። ልክ እንደ አልሆነው። እሰከ አሁን እንደ አልተሳካለት።

በእነእዚህ አመክንዮዎች የተሳ፣ የምእራብ ስልጣኔ እምንለውን ገሀድአዊ እና ወጥጣ ስልጣኔን፣ ኢትዮጵያ መቀበል ሳይቻላት ቆየች። አንድ ወቅት የቀድሞ ጠሚ. ኃይለማሪያ ደሳለኝ፣ እኛ ዘግይተን በመነሳትአችን የተሻለ የዘግይቶ-መጪ (late comer’s) ልዩጥቅምዎች አሉን ብለው እንደገለጡት የተሻለ ስልጣኔን ከብዙ ሀገርዎች ጀርባ በመሆንአችን በቀላል እየተመለከትን ተነስተን እንደእነሱ ከባዶ አየሩ ወደ ምእራብ ስልጣኔ መጓጓዝ እውነታአቸው መማር ስለእምንችል፣ ለምሳሌ ጃፓን እንደምን ሰለጠነች ብለው ከበደ ሚካኤል ለማስተማር እንደሞከሩት፣ ይቀልለን አለ ብለው ነበር። ዳሩ፤ ተቃራኒው እንደሆነ ነው። ባለማቋረጥ።
ዘመንአዊ ስልጣኔን ይህ ሀገር ከመገንባት፣ ወደማስመሰል እና የአለ ሀያሲ ስነውሳኔውን እና ስነምጣኔውን ወደማዝረክረኩ እንደቀጠለ ነው። እርካሽ የአለም ምርትዎች እንደተደፉበት፣ መሰረተ ስልጣኔ እንዳመለጠው፣ ስነውሳኔው የዘመንአዊ ጭሰኛነት ስርአት እንደሆነ (በተፅዕኖው (virtually) መሬት እና ተፈጥሮ ሀብትን እንኳ በባለቤትነት እሚይዘው መንግስት ነው)፣ ዘመኑም እንደአለፈ እና በስህተት የተዘበራረቀ የስልጣኔ አረዳድ እየተበተበን እና ለወደፊትም ለማጽዳት እሚጠይቀን ዝርክርክነት እንደተቀመጠልን እየሆንን ነው።
የዛሬ የሀገርአችን ቁንጮ እንዲሁም ሁሉን አቃፊው (ስርሰደዱ/አንክሮትአዊ) ችግር በስልጣኔ የመጀመር ፍላጎት ስም ይጠነሠስ አለ። መሰልጠንን ቁሳቁስዎች ከማምጣት እና በቻይና መሰረተ ልማትዎችን መገንባት ተደርጎ በዋነኛ መገለጫው እምንመለከተው ነው። ይህም፣ ሌላ መገለጫ የለውም ሳይሆን እሚለን አብይ መገለጫው ነው ነው።
የመሠረት መጣል ስራው ሳይከወን – ቀኃሥ. እንዳሣሰቡት ስነምግባር፣ ስነልቦንታ (psyche)፣ ትምህርት፣ ወዘተ. ሳይከወን፣ እሚደረግ የስልጣኔ ግዝግቤት ለአጉል የነገረ አለሙ ሁሉ ግጭት የዳረገን ነው። በምላሹ የተረፈን፣ የምእራቡን ስልጣኔ ፈርጀን መስደብ እና ወረራ ብሎ ማመካኘት ነው። ሊቀምሁርዎች (ዶ/ር) ሂሩት ወልደማርያም የባህል እና ጉዞጉብኝት (tourism) ምኒስቴር እንደገለጡት የባህል ወረራ እየተፈጸመብን ነው እሚል የእማያግዝ አረዳዱ ብቻ እሚቃጨልልን ሆኖ አለ። በሌላ ጎን የከፋው ነገር፣ የምእራብ ስልጣኔን እንደ በዐድ ወይም ለሆነ የሰው ክፍል የተፈበረከ ከማድረጉ ጎንለጎን፣ ለእሚነሱ አንዳንድ የሀገርበቀል ቀለም ማላበስ ስራዎችም አልተከወነም። የምእራብ ስልጣኔ ሁሉም እንደወረደ እሚጨለፍ እእና እዚህ እሚፈስስ መስሎን ለብዙዎች፣ ሀገርን እረሳን ለማለት ያደፋፈረአቸው ክፍተት ምልከታን አግኝተውበት አለ – ቢያንስ ለአንድ አንጃዎች ያ እውነት ሆኖ እሚታይአቸው እንደሆነ ይነገር አለ። በደፈናው ግን፣ የነገርዎችን ሀገርአዊነት አላብሶ ማቅረብን፣ አንዳንድዎች በእሚጠይቁት መሰረት፣ ለማሰናዳት አለመሞከሩም አንዱ ችግር ነው። ይህን ግን፣ ለእሚነሳው ተደጋጋመከ ወሬ እንጂ፣ ይህን መነሻ ጠቅላላ እና ደፈናአወከ ጽሑፍ ፀሐፊ አያምንበትም። ሀገርአዊነትን እሚያላብሱት ስልጣኔም ሆነ ምእራብአዊ እሚለት ስልጣኔ የለም። ለምሳሌ የባህል ሙዚቃን አለመዘንጋትከ የባህል ፊልምዎችን ማምረት፣ ሀበሻ ልብስዎችን ማዘውተር እና ስራም ላይ መልመዱ፣ የአክሱምን ግትር ድንጋይ አስመስሎ ህንፃዎችን ማቋቋም፣ ባለጌ እሚሰኙ እንደ ሐመርዎች አጠር ያሉ አለባበስዎችን እና ሀልዎቴዎችን (attitudes) አለማስመልከት፣ እንግሊዝኛን አለመጠቀም፣ የግእዝ ቁጥርዎችን ልብስ ላይ አሳትሞ መገኘት፣ ሰፌድ እና አገልግል ወዘተ. ቁስዎችን በግድግዳዎች መስቀል፣ ዐፄ ቴዎድሮስ እና ምንይሊክን በምስልዎች ማራባት፣ የወዘተ. የሀገር ቀለም የለበሰ የምእራብ ስልጣኔን ማልመድ ተደርጎ እሚታይ ነው። (ይህም በሌላ ጦማር እንደአብራራሁት፣ ተምኔትዮጵያ (uto-Ethiopia) እሚሰኘው ቅዠት አካባቢ እሚገኝ (ከገሀድ ውጭ ያለ) ፍብርክ ብሔርአዊ የምቾት አይነት ነው።) ቢያንስ በደፈናው እና ለመካከለኛው አመለካከት ይህ ገሀድ ግልጥ አረዳዱ ነው። እነእዚህ ግን፣ የምእራቡ ስልጣኔ እዚህ ቢመጣ አብዝቶ እና ሰምጦ እሚደረጉ ነገርዎች እንጂ ከቶ ሀገርአዊነትን ለምእራብአዊ ስልጣኔ የማስቀለም ጉዳይ አይሆንም። ከቶም። የአኗኗር ዘዴን በገሀድ ለማስመልከት መጣር ነው። ያ ደግሞ በሰለጠንን ቁጥር እሚበዛ እራሱን የቻለ ገጽታ እንጂ ምንም የስልጣኔን ማባበል አይሆንም። ለምሳሌ፣ የቀለም በልብስ ላይ ማቅለም ጥበብን፣ አስመጥተን ብዙ ዘመንአዊ መንገድ የተከተሉ የልብስ ምርትዎችን እናመርት አለን፤ እንደ ሀገር። አቀስቃሽአዊው መሳሪያው (the machinery tool) እና ክሂሎቱ ከእዛ ተገዝቶ መጥቶ ሳለ፣ ልብሱን የዐፄ ቴድሮስ ምስል ቢያቀልሙበት፣ ምኑም ይህ ስልጣኔ ሀገርአዊነት አልለበሰም። በቀጥታ ለአገልግሎት ብቻ ነው የዋለው። ልብሱን ሳይሆን አ1ስቃሹን መፈተሽ ብንችል በውጤቱም፣ የስሪቱን ማሳደግ፣ የማምረት ሂደቱን ማሻሻል፣ የሀገር በቀል ሽመና መስሪያውን አብሮ ወደአቀስቃሹ መክተት እና አመራረቱን ከመጣበት ሀገር የተለየ ማድረግ ቢቻል፣ ወዘተ. የተገዛው ሽልፍኖትአዊ ቁስ (technological material) ሀገርበቀልነትን አቀለምንው እሚሰኝሠ ነው።
እንዲህ እሚሰኙ ነገርዎችን ሳንከውን፣ ከቶ ሀገርበቀል የምእራብ ስልጣኔን ማግኘት አይቻልም። መልሰን ደግሞ ሀገርበቀልነት የአሳቀፍንውን የምእራብ ስልጣኔ እንመልከት። ለምሳሌ፣ መሸመኛ ወይም አረቄ ማውጫ የባህል ስራአችንን፣ አዘምነን፣ በአለሙ ሁሉ እየሸጥን ብዙ አተረፍን። ይህ ሀገርበቀል ስራ እንጂ፣ ምእራብአዊ ከመሆን እሚከለክለው አይኖርም። ምእራብ እምንለው ስልጣኔ፣ እጅግ ኅዋአዊ ነው። ምንንም ግርምታ እሚከትት ነው። ገሀድን የአሠሰ እና የአገኘ እሚባለው ለእዛ ነው። በምእራብ እሚገደብ እማይሰኘው በዋነኛነት በእዛ አመክንዮው ነው። እኛስ የከወንንውን ደግመን እንመልከተው። የአመረትንው የተሻሻለ ማምረቻ በአለም ተሸጠ። እዚህ እምንሰበስበው ገንዘብ፣ ዝና፣ ክብር፣ ኃያልነት፣ እና ስም ወዘተ. አለሙን አሻሻለ፣ እኛንም አሻሻለ። በቀኑ ማብቂያ፣ ስልጣኔ ኑሮ አሻሻይ ክሂሎት፣ ስርአት አይነትዎች፣ እና ቁስዎች እንጂ ምንም ብሔር የሌለው ነገር ሆኖ እንመለከተው አለን። መነሻው፣ ትርፉ፣ ክብር እና ዝናው ወዘተ. እንጂ ኑሮን ማቅለል ብቸኛው የስልጣኔ መሠረት እና ዘ ሆኖ እንመለከተው አለን። ማለትም፤ ሀገርበቀል ስልጣኔ እንኳ በመጨረሻ ኅዋአዊ ገፀባህሪ ያለው ነው። ማረጋገጫው ደግሞ፤ ኢትዮጵያ የአንዳንድ ጥንትአዊ ትትረትዎች መነሻ ናት እሚሰኘው ነቢብ ወይም ሀቅ ነው። እዚህ የተጠነሠሰ ወደ እየ አለሙ ከተዛመተ፣ አሁን የአለው የምድር ስልጣኔ ማህፀኑ እዚህ ከነበረ፣ ምእራብ እና ሰሜን እሚሰኙ አግጣጫዎች በስልጣኔ እንደሌሉ ነው።

ወደዋና ጉዳይአችን ተመልሰን ስንደመድም፣ የኢትዮጵያ መሠልጠን ሙከራ ከመነሻው ጀምሮ፣ በቁሳቁስዎች በመቅናት እና በመመኘት የተጠነሠሱ እንጂ ስርነቀልነትን የጎመዡ አልነበሩም። ዘመንአዊነትን በሞካከሩ፣ ዐፄ ቴዎድሮስ፣ እና ዐፄ ምንይልክ የነበሩት እጅግ መጠነኛ የምእራብ ስልጣኔ ቁሳቁስዎችን የመፈለግ ጉዳይ ሲሆን፣ አንዳንድ ስርአትዎችንም በተለይ በሁለተኛው ንጉስ ለመኮረጅ ተጥሯል።
ከምንም በላይ፣ በብዙ ዘመን ታሪክአችን፣ ብቸኛ ጫፍ ሀቀኛ ሙከራ የተከወነው በብዙዎች እንደእሚመሰከረው በቀኃሥ. ነበር። ይህ በውጤቱም የተመሰከረለት ነው። አፍሪቃን እና አለምንም በስነውሳኔ (politics) የተቀላቀለ እና ዛሬም የሀገሪቷን ምርጥ ምሁራን፣ ፈላስፋዎች፣ ልዑኬዎች (diplomats)፣ ህግ ባለሙያዎች፣ ዳግተመራማሪዎች፣ የስነእናኪነ (art) ባለሙያዎች እና ብሉይ (classic) ምርትዎች፣ ስነስርአትዎች፣ ወዘተ. የአፈራው በአንፃርአዊነት ፍሬአማ ዘመን ነበር። የተከተለው የቀደመውም፤ አቻ ወይም ተቀራራቢ ስኬት አልታየም። ቢሆንም፤ በንጉሡ መውደቅ፣ እና እንደ ኢትዮአሜሪካአዊው ጸሐፊ ዲናው መንግስቱ አተያይ፣ ኮሎኔልዎች ስልጣን አሳብሮ በመግባት እና በመስረቅ አምባግነናን እያቋቋሙብን፣ እንደ ህዝብ፣ እና ሀገር ባለማቋረጥ በጨለማ አኗኗር ለመቀጠል የተተውን ሆነን አለን።
ከእዚህ በአሻገር፤ የእምንመለከትአቸው የስልጣኔ ገዝቶ ማስገባት ስነስርአትዎች ዛሬም የአልተሳኩት እና የመለወጥ ጥሬ ፍላጎትአችን በ እድሜጠገቡ የአልተቋረጠ አወዳደቅአችን መሳለመሳ የአስኬዱት ምንጩ ሆነውት ነው። ዝብ-ስልጣኔ የማልመድ ክወናአችን ዛሬም የሀገር መቅሰፍት በሽታአችን ነው። በንጽውሳኔ፣ ህዝብአዊትነት (republicanism)፣ አምራችአዊነት (industrialization)፣ ባህልአዊ ስልጣኔ፣ እና ትምህርት ወይም ንቅዐተህሊና ልማት የአልተቀደሰ ሙከራ ሁሉ፤ እጅግ እንደአጎሳቆለን ነው። ከምንም በላይ ለለውጥ ለማገልገል አሽከርነት እሚቀጠረው ስነውሳኔአችንም እጅግ በሙስና የተላወሰ፣ እና በመንደር ካድሬዎች ሰንሠለት ከጓዳ እስከ ቤተመንግስት የደረሰ በመሆኑ፣ ተስፋው እጅግ ቀጫጫ እንዲሆን እየተደረገ ይገኝ አለ። እሚከወነው ሁሉ ዝርፊያ እንጂ አስተዳደር በአለመሆኑ፣ ተረኛነት እሚሰኝኛ ነቢብ እስከመፍጠር እና በእለት አንደበት እስከመለመድ ደርሶ አለ። ሲደመደም፤ የተገባ ስልጣኔን ማጎንቆል ወይንም ማምጣት ባለመቻሉ፤ ስነውሳኔ ከቶ ሀገርን ማገልገል ባለመቻሉ እና አላሚአዊ እንቅስቃሴን ባለመከወኑ፣ እሚገቡ ስልጣኔዎች እጅግ ከንቱ እና የእማያተርፉ ሆነዋል። ባሹ እውነታ ግን፣ ጎጂ እና አደናቃፊ የትርኪምርኪ ስነስርአት እየተቋቋመ፣ ባህል እና ስነልቦና፣ እንዲሁም በደፈናው የህላዌአችንን መቼት እያጎሳቆለ እሚገኝ ሆኖ አለ። ከምንም በላይ ደግሞ፤ መከወን እና መድረስ እሚቻልበት የጅማሮ ከፍታ በአለማቋረጥ እየተገደለ እሚገኝ ነው።

እንደሆነው፤ ዛሬም ተስፋ አለ። ከቶ፤ ተስፋ አይጠፋም። የተከወነ እለት እሚቦግግ ነው እና። መሠረትን የፈለጓት ጊዜ ገሀድ ሆና እጅ እምታቀርብ ናት እና። እስከእዛ ግን፤ ምንም የመከፋፈል፣ የአለመሠልጠን፣ እና አንጃአዊነት ፈተናዎች እንደ ዘለአለሙ ታሪክ ዛሬም ቢቀጥሉ፤ ጥቂት በዘገየን ቁጥር እምናክምአቸው እነእሱን ብቻ አይሆኑም። በስመ ስልጣኔ፣ በአስተዳደርዎችአችን ሁሉ እሚከወኑት፣ ተዘርዝረው እማያልቁ ዝብርቅርቅታ አፈጣጠርዎች ናቸው። ከተፈጥሮአችንን ማጥፋት (ለምሳሌ ዝዋይ ሀይቅ እና አበባ ምርትዎች)፣ አለመንከባከብ፣ እና ለሌላ ሀገርዎች የግብርና እና ቁሳቁስ ምርትዎችን ማምረቻ ማእከልነትን በመከወን እንደስልጣኔ መሰረት መቁጠር፣ የውጭ ገንዘብ መሰብሠብን እንደ ጀብዱ እየቆጠሩ ከወረቀት ብር ጀርባ ማብሰልሰልን አለመከወን፣ ወዘተ. እንደተዛቡ እምንመለከትአቸው የስልጣኔ አተያየትዎችአችን ሲሆኑ፣ ባሉበት እየቀጠሉ መሰልጠንን እሚያጨቀዩ አረንቋነትአቸው እየሰፋ መቀጠሉ አይቀሬ ነው። ማምረቱንም ሆነ የግብርና ምርትዎችን ግዝዉጤት (export) በተገቢው መንገድ ሀገር እንዲያለማ አድርጎ መከወን፣ እንጂ አይከወኑ ማለት እንዳልሆነ ማወቅ እሚገባ ነው። ለምሳሌ፤ የሀገር ሽማግሌው ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ እንዳለው፤ ሰሊጥ ለውጭ ገበያ ሸጦ በውጭ ምንዛሬው ዘይት መግዛት ቅወሳ ነው። እንጂ፤ ንግዱን አስፋፍቶ መከወን፣ እንደእሚገባ ሳይታለም የተፈታ ነው። ብቻ፤ የድንበርየለሹን መዘመን ከሀገር እምብርት (አዛውንት እና ሀገረሰቤዎች) ጀምሮ፣ ከአልተወለዱት እና ከአሉት ዜጋዎች ሁሉ አንፃር መወጠን እና ሀቀኛውን መንገድ መከተል እሚገባ ነው።

ስልጣኔ፣ Modern Self, እና የእኛ ነገር ሲደመደም

በቀኑ መጨረሻ፤ አሁንም የቱንም ሀገር ማዘመን Modern Self አማካዩ የአኗኗር መንገድ እንዲሆን ማድረግ ነው። ዘረፍጥረትአችን (our species) Modern Self ከአበጀ፤ የትም እንደ ተከበረ ሰው መኖር ይቻለው አለ። በጥንቱ አኗኗር፤ አብረን እንኖር የነበርን ቢሆንም፤ ኑሮ እንደ መዘመን ዘመን ቀላል በአለመደረጉ እና ስውሳኔአችን እኛን ከማገልገል መገልገል በመምረጡ፣ Modern Self, ባለበት ሳይነቃ በውጥዎችአችን እሚከሽፍ ሆኖ አለ።
Still, to civilize as a nation, modernizing the citizens through a committed enrichment of the citizenry is the way of the beginning. Unless, we keep marching the opposite root, so unpaved as it is, figuratively and in reality.
We hope, and yet, for a day that is bright [to come].
—— & —–

—– & —–

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s