Categories
ስለ ቋንቋ አማርኛ (ወይም ይልቁንም አማሊዝኛ) Amhalish

የፊደልገበታ ጉዳዩ ዳግ-ቅኝት

A review of Amharic’s Alphabet problems in relation to its claimed connection with astronomical codes.


bY binyam HAILEMESKEL Kidane, የካቲት 17 ቀን 2013 ዓም.፨


አሁንም፤ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ፤ የፊደልገበታው ፍሬጉዳይን አግበስብሦ የመነካካት ግብዣ እንደቀረበ ይታይ አለ። ይህም፤ ስለ ስነፈለክ በ “ፊደል እና አስትሮኖሚ” እሚሰኝ የ መጋቤ ሀዲስ ሮዳስ ታደሰ (ሊቀምሁርዎች) ተም. (ተንቀሳቃሽ ምስል) – በ2012 ዓም. ማብቂያ እንደወጣ የእሚገልጥ ነው – በ Youtube የተመለከትኩት አጭር ያልተሠናሰለ ክርክርቴ አቅርቦትን የተመለከትኩበት ውስጥ ያገኘሁት ሃሳብ ነው።


በስነፈለክ እና ፊደል፤ ሀ እና ዘሩ እንደ አንድ፤ ለ እና ዘሩ እንደ ሁለት እስከ በ እና ዘሩ አስር፤ ተ እና ዘሩ ሃያ ቸ እና ዘሩ ሰላሣ እያለ በመውረድ፤ መቶ፣ ሁለት መቶ እያለ ቁጥር ለፊደልዎቹ እንደእሚሸለሙ ነውታ (claim) አለ።


እየቀጠለ፤ በፊት እሚፃፉ የግእዝ አፃፃፍዎች በቁጥርዎችአቸው እሚሰሉ ነገርዎችን በመቀመር ይገኙ እንደነበር ይነገር አለ። ለምሳሌ፤ “ሰማይ” ሰ ሰባት በመሆኑ ሰባት ሰማይዎችን ይወክል አለ ስለእዚህ ሰማይ አይባልም እሚል ህግ ነበር።


ሁሉም ነገር ሲፃፍ በቁጥር እንዲህ ምስጢሬ (code) ቁጥር መያዝ እንደእሚችል ይነገር አለ።


ይህን በመያዝ፤ የፊደል መቀነስን እንደእሚቃወሙ፤ እሚከራከሩ አሉ። አብሮ፤ የተዛማጅ ቋንቋዎችን፤ እንደ እብራይስጥ፣ ግሪክ ወዘተ. ያሉትንም በተመሳሳይ ፍልስፍናአቸው ከግዕዝ በማቀራረብ እበጀው ፊደል አለመቀነስ መሆኑን ይከራከሩ አለ።

በብዙ መንገድ ይህ አሁንም፤ አዲስ የስነቋንቋ መከራከሪያ ያልሆነ ነው። እጅግ በአጫጭሩ እሚዘነጉ ነጥብዎችን ባለመታከት ደግመን ከእዚህ አንፃር በመዳሠስ እንመልከት።


አንደኛ፤ ቋንቋን ከኅዋአዊ የአልጀብራ ቀመር ጋር ማስተሳሠር ጥቅሙ ከአቅም (energy) አረዳድ ጋር እሚያያዝ ነው። ያ፤ ለቋንቋ ተግባቦት (language communication) እሚሰጠውን ቀጥተኛ ግልጋሎት ማስተሳሠር አይቻልም።


ሁለተኛ፤ አማርኛ ከእዛ ህግ የከፋ ፊደልገበታ የተሸከመ ነው።


ሦስተኛ፤ እንዲሁ እንዳለ የተፋለሰ ፊደልገበታአችን ቢቀመጥም፣ ይህንን ለመከወን ብቁ እሚያደርግ ልማድ የለንም። ማንም ሠው ወይም ሰው ብሎ ይጽፍ አለ። ግን ሰው ማለቱ ተገቢ እንደሆነ ሰ ሰባት መወከሉ ከአራቱ ባህሪያተ ስጋ እና ሦስቱ ባህሪያተ ነብስ የተያያዘ እንደሆነ ይነገር እንጂ በተግባር ግን ሰው እንጂ ሠው እሚል ጽሕፈት ማግኘት እጅግ ነሲብአዊ በመሆኑ፣ በተሞክሮአችንም የተፋለሰ ነው።


አራተኛ፤ የሶስተኛው ችግር ስላልተቀረፈ፤ ወጥ ጽሕፈት ያጣን ግን ፊደል የተሸከምን የግለተቃርኖት (oxymoron) ሀገር ሆነን አለ። ስለእዚህ፤ በእየመስሪያቤቱ ስንሄድ፣ መሠረት እሚል ስም ስንናገር በመረጃ ቋት ወይም ማህደር መሰረት በእሚል በማሠስ አገልግሎት እንዳናገኝ እምንደረግ ሆነን አለን። የፊደል ችግር ባለፊደል ሆነን ያላጠራን ሆነን አለ። በመረጃ አሠሳ እና ማጋራት መሰረትአዊ ሰብእአዊ መብትም፤ እንዲሁ፣ ወጥ ፊደል መጠቀም እምንችልበት ዘዴ ባለመኖሩ፣ መብትአችን ተጥሶብን ባለማቋረጥ እንደተበደልን አለን። በምሳሌነት በቀደመ ልጥፍ የተመለከትንአቸው የምስክ ማስረጃዎችን ማጣቀስ እሚቻል ነው።


አምስተኛ፤ ለፊደልገበታአችን ጨለምተኛ መከላከል ቆሞ ገበታፊደል በቋንቋ ህጉ መሰረት ለመግባባት ማሻሻሉ ቢቀር እንኳ የዘመንአዊ አያያዝ መንገድን ለመከተል ግን እሚኬደውንም መንገድ እሚዘጉት ሆነው አሉ። ለምሳሌ፣ እንደ እንግሊዝኛ፣ call እሚለወን koll, kol, col, coal, koal, ወዘተ. እማንል እንደሆነው፤ ህገወጥ የአማርኛ አፃፃፍን በህግ ለማስቀረት ወደ ስነስርአት ያለውን ፊደልገበታም ማዘመን አስፈላጊ የሩቅ አማራጭ ነበር። ዳሩ፤ የክፋት ሃሳብ እንጂ ቅንነት በተከላካይዎች ወገን የለም። ስለእዚህ፣ ፊደልገበታው በተለያየ መንገድ ሊቀርቡት እና ሊረዱት እሚችል የኅዋ አቅምን ከቀመረ በህግ እንዲከበር በስነስርአትዎችአችን ሁሉ መጠቀሚያ እንዲሆን ማድረጉን መግፋት አለብን፤ በተለይ አለብአቸው። በቀረ፣ ይህን ስነፈለክአዊ ዉሂብ አቅፎም ሳይገለገሉትም የተግባቦት እና ሰብእአዊ መብትዎች ጸር መሆን፣ በሁለት መንገድ የእሚያጣ የሰነፍሰነፍ ህዝብ ያደርገን አለ።

ስድስተኛ፤ ፊደል ያለው ቋንቋ ሁሉ ሆሄዎቹ ይቆጠሩ እና የቃልዎችን ቁጥር በተመሳሣይ በመግለጥ፣ ቁጥርን ተሸክመው አለ ማለት ነው።


ያ ከሆነ፤ ግዕዙን አልፈን አማርኛን ብናስተካክል ከባለ ሰላሳአራት ፊደል የእሚቀረን አጠር ያለ ፊደልገበታ ይኖረን አለ። ያው የልጅዎች አልጀብራ ቤትስራን ለመደማመር እሚያንሰን አይሆንም። መልሰን ደግሞ ድሮ ይህን ቁጥር በእየፊደሉ በታትነው የቀመሩ ሊቅዎች እንደነበሩን አሁንም እሚቀምሩልንን ባለሙያዎች የዝማኔው አንድ (ይህ) ፍሬጉዳይ ተካፋይ በማድረግ፣ በሁለት መንገድ መጠቀም እንችል ዘንድ፣ ይህም ክፍት፣ አመክንዮአዊ፣ ሙያአዊ እና ጠቃሚ እጅግ ደግሞ ግንባርስጋ መንገድ ነው። ለምሳሌ፣ እንግሊዝኛም በአቅሙ ቀመሩን ይዞ ያለ ፊደልገበታ ያለው ነው ይባል አለ። ግን እንደአማርኛ ድግግሞሽ እና ኢአመክዮአዊነቱ እጅግ የኮሠሰ ወይም የሌለ ወይም አይጠናም እሚሰኝ ነው። ስለእዚህ፣ እንዲህ በቀላሉ በንጽጽርም ብንፈልግ እማናጣውን የቀላል አልጀብራ አያያዝ በአማርኛ አጥተን ግን ከጎስቋላ የቋንቋ አገልግሎት ላይ የወደቅን ሆነን አለን።


ሰባተኛ፣ በቀኑ መጨረሻ ይህ የተዘበራረቀ የጥንት ቀመር፣ ለኢትዮጵያ ዛሬ የበጃት ምን አለ? ቀመሩን እማይገለገሉ እንደ ጃፓንኛ ያሉ አስቸጋሪ የመፃፊያ ደንብ ያሏቸው ቋንቋዎች ለምሳሌ የአለም ቁንጮ ሆነው አሉ። ቀመሩ ለእኛ ምን አክሎ ከምን አስጣለን። የኅዋ አቅምን በሌላው አለም በስልጣኔ የተነሳ፣ በስነፈለክ እና ተያያዥ ወይም እሚመለከትአቸው ሙያዎች ስር መመርመር እና ለአገልግሎት እንደአግባብነቱ መጠቀም የተቻለ ነገር ነው። በፊዚክስ፣ የእየአይምሮ ጥናት ሰፋፊ የተለያዩ ዘርፍዎች፣ ስነፈለክ እና ተያያዥ የዳግምርምርዎች ዘርፍዎች፣ ሃይማኖትዎች እና አስተምህሮትዎች፣ ወዘተ. ይህንን፣ የኅዋ ቀመር ለመገንዘብ እና ለመገልገል ሙከራዎች እንደተደረጉ አሉ።


አማርኛን ከግእዝ ቋንቋ ፊደልገበታ ተዋሽነቱ የተነሳ ግን፣ በግእዝ ገበታፊደል ደንብዎች አፍኖ በመያዝ ይህንን የአቅም ምርመራ ዘርፍ ለብቻው እንዳይበረታም አድርገንው አለን። አማርኛም ስለእዚህ የተነሳ በዘርፍአዊ ችግር ተዘበራርቆ (=ኢክዊኖክስን አዛብቶ ህገደንቡን በመጣስ፣ ገናም ዳግመኛም እንዳየንው ቢሠፋም በተዘበራረቀ መንገድ በጥንቱ የታሰበለት ህገደንብ ስለእማይፃፍ) ኅዋአዊ አገልግሎቱን እማይሰጥ ሆኖ እንዲሁም ደግሞ ከቋንቋ ተግባቦት ስነምጣኔአዊነት እና እቅጭነት ተፋትቶ አለ።


ስምንተኛ፤ የፊደል ገበታአችን (ልብ በሉ አማርኛ እንጂ ግእዝ አይደለም) ከስነፈለክ የግድ እሚያያዝ ብቻ አይደለም።


ቻይና እሚለውን እምንቆጥረው እንዴት ነው? በኢክዊኖክስ ቀመር መሠረት የተቀመረው ግእዝ ፊደልገበታ የ ቸ ፊደል ዘርን አያውቅም። ወይም ቸነፈር እሚለውም ተመሣሳይ ነው። ይህ ማለት፤ አማርኛ እና ግእዝ ገበታ እኩል የኢክዊኖክስ አገልግሎት የሌልአቸው ናቸው። ምንም ተጨማሪ ማረጋገጫ አያስፈልግም። እንዲሁ፤ የ ቨ ፊደል ዘር አዲስ ሲሆን በግእዝም በአማርኛም አገልግሎት የሌለው ነው። ቋንቋው አይገለገለውም። ግን፤ እንግሊዝኛን በአማርኛ ለመተየብ አጉል ለጋስ ፊደልገበታ ስላለን የተቀመረ ነው። አማርኛ ፊደልገበታን እንደ ድምፅ ሁሉ ተያቢ ሙዚየም መመልከት እሚቻል ነው። ብዙ የአማርኛ ቋንቋ የቱም እሚታወቅ ቃል እማይጠቀምአቸውን ድምፆች እሚተይብ ገና ያልዘገመ ጉዳይዎች ያፈኑት ነው። እንደ ፗ ያሉ ድምፅዎችን መወከል እና ለህፃናት ማስጠናት፤ ጠያቂ ስለሌለን እንጂ፣ እጅግ ቅወሳ ነው። ሀበሻ አማርኛ አጥንቶ ወይም አፉን ፈትቶበት በመቶ አመቱ ቢሞት ፗ’ን እና ቨ የመሳሰሉትን መፃፍ ተምሮ፤ ግን አንዴም በአማርኛ ቋንቋ እማይገለገለው ነው። ሸክምን ለምን በነፃ ፈልጎ መሸከም አስፈለገን? አንጎልን በኮረኮንች ፊደልገበታ ማስጨነቅ ለምን ተፈቀደ?


ተመሳሳይ የእነ ጀ፣ ቸ፣ ሸ፣ ኸ፣ ዘርዎች በግእዝ አይታወቁም። ስነፈለክም አልቀመረአቸውም። ልዩነትአቸውም፤ የዘዬ ብቻ ነው። እናቸንፍ አለን እና እናሸንፍ አለን፤ ጭቂት እና ጥቂት፣ አፍሪቃ እና አፍሪካ፣ ወዘተ. እንደእሚባለው፤ የዘዬ (ቀበልኛ ድምፀት / pronunciations) ልዩነት ብቻ የተሸከሙ ናቸው። ያ፤ ማለት የፊደልገበታ ጉዳይ አልነበሩም። አንድ እንግሊዝኛ ስር፤ color እና colour ተብሎ በአሜሪካን እንግሊዝኛ እና በእንግሊዝ እንግሊዝኛ እንደእሚፃፈው፤ የዘዬ ልዩነት ብቻ ነው። የቋንቋው ፊደልገበታ ግን በዘዬ የተነሳ አልተትረፈረፈም። ምክንያቱም፤ ብዙ ዘዬ መፈጠር እሚችል ነው። በዘመንዎች ሂደት፤ ለምሳሌ ወጣትዎች፣ አራዳዎች፣ ወዘተ. የእየራስአቸው ዘዬዎችን ማዳበር እሚችሉ ናቸው። ለእየዘዬው ፊደልገበታአችንን መፈልቀቅ እና ማስጨነቅ ሊኖርብን ነው። ከዘዬው ተናጋሪ ውጭ ያለን፤ እኛ በእሚገባ አብረን እንጨነቅ አለን። ግን ከቶ እሚገባን እና እሚያገባን ነገር አይደለም። ጎልማሳአዊ እና ጥበበምርምርአዊ (scientific) አመክንዮ ሳንይዝ፤ እንዲሁ ብዙ አማራጭዎችን በፊደልገበታው በትነን እምንጨናነቅ እና እምናስጨንቅ ነን።


አመክንዮአዊነት (reasonableness) የሌለው ማብራራት እማይቻል ነፈዝነትን እሚሰጥ ገበታ በመሆኑ፤ ከኢክዊኖክስ እና የአቅም ቀመር ነውታ (claim) ውጭ ተጨማሪ ተግበስባሽ ችግርዎች አሉት።


ሲደመደም፤ በደፈናው የፊደልገበታ ከስነፈለክም ጥያቄዎች ውጭ የ ኢአመክንዮአዊነት ጥያቄዎች አሉት። በስነፈለክ የነውታ ዉሂብዎች መከላከል በቂ አይደለም።


ዘጠነኛ፤ የእምነት ጉዳይዎች፣ የርእዮት ጉዳይዎች በፊደልገበታው እሚገኙ ናቸው። ይህን የግድ ከቋንቋ አገናኝቶ መከራከሩም ገለልተኛነትን ያጠያይቀው አለ።


አስረኛ፤ እሚሰሙት ነገርዎች ላይ ብዙ ቀላል ዝብርቅርቅታዎች አሉ። ለምሳሌ፤ አቡጊዳ፤ አ አልፋ ብሎ ለማስቀመጥ ጀምሮ በ ኦ ኦሜጋ ብሎ ለማስቀመጥ እንደሞከረ ገልጠው፤ ፊደል መቀነስ ይህን እንደምታ (implication) ያዛባል ይሉ አለ። ግእዝ ገበታ ፊደል፣ አቡጊዳ ፊደልገበታን፣ ሌላዎችም ገበታፊደልዎች ካሉ ሁሉም፣ እነእሱ መነካት የለብአቸውም።


እጅግ ግልጥ ግን እሚሳት ነገር ስለሆነ እሚያስፈልገን ግልጥ ነገር፤ የአማርኛን ጉዳይ እንደ አማርኛ ነጥሎ መመልከት ብቻ አለመቻሉን ዝብአረዳድ መሆኑን ማሳሠብ ነው። ስለእዚህ፤ ነፈዝ ካልተኮነ በቀረ፤ አማር፤ ፊደልገበታ ይስተካከል ሲባል አቡጊዳ ይነካብን አለ፤ ግእዝ ይፋለስብን አለ፤ ወዘተ. እሚሰኙ ክርክርቴዎች እጅግ መጥራት ያለብአቸው መነሻ ስህተትዎች ናቸው።

አስራአንደኛ፤ አማርኛን ማሻሻል ታሪክን ግን ማጥፋት አይደለም። የተፃፉ እና የተቀመጡት ሁሉ በቀደመ አማርኛ ተብሎ መታየት እሚችሉ ናቸው። ልክ እንደ ቻይና የቅርብ አስርታት ፊደልገበታአቸው ከማንዳሪን ወደ ሲምፕሊፋይድ ማንዳሪን እንደዞረው፤ የበፊቱን ማጥፋት ሳይሆን፤ ዘመንአዊነትን ከአንድ ወቅት ወደእዚህ ማስጀመር የአማርኛ ፊደልገበታ ማሻሻል ጥያቄው እና ተፅዕኖው ብቻ ነው።


የበፊት ጽሕፈትዎችን፣ ከተቻለ ለቀላሉ ተግባቦት ማስተካከል፣ ካልተቻለ የበፊት ወይም አሮጌ አማርኛ ብሎ ማስቀመጥ እሚቻል ነው። አዲስ ዘመን ግን፤ በቀለለ አማርኛ ወይም አዲስ አማርኛ ብሎ መገልገል እሚቻል እና እንደ ቻይና ስልጣኔን ማጧጧፍ እንዲቻል ቋንቋንም ቀላል እና ወጥ ማድረግ እሚቻል ነው። የበፊቱ ስለእዚህ አደጋ የለበትም።


ከእዚህ ተያይዞ፤ አንድ ነገር ቢገለጥ፣ ሌላ ማንኛውንም የማሻሻል ነገርም፤ ወደ ቋንቋ፣ የቆዩ ቋንቋዎች ጥናትዎች እና ዳግምርምርዎች፣ ወደ መዛግብት ማህደርከ ወዘተ. ማምጣት እንጂ እንዲረሱ እና እንዲጠፉ ምንም ጉዳይዎችን ማድረግ እማያስፈልግ መሆኑን መረዳት ያስፈልግ አለ።


ማሻሻል፤ አመክንዮ እና መርኅ ከሙያአዊነት ጋር እሚከተል እንጂ፤ አደጋ እና አጥፊ አለመሆኑን መገንዘቡ አስፈላጊ መረጃ ይሁነን።


በተረፈ፤ የፋርስ ቋንቋን ጉዳይዎች እያነሱ ሞክሼዎቹ የተለያዩ ናቸው እሚለው በአማርኛ ውስጥ ፋስር ስለሌለ፤ እንደ ተለመደው ከመልስምት ክርክርቴ (counter arguement) ይልቅ በማዘን መሻገሩ እሚሻል ነው። አማርኛ ቋንቋ ዉሃ’ን ክክኀ ብሎ አይጠራም። የመጨረሻው የ ሀ ፊደል አይነት “ኀ” እንደ ሌላዎቹ ሀ ሳይሆን “ክክሃ” ተብሎ እንደ ፋርስ (ኢራን) ቋንቋ ይነበብ አለ ብሎ ማሳሰብ እና አማርኛም ቋንቋ በገበታው ስለእዚህ አይንካው ማለት፤ የትኛውም ስነአመክንዮአዊነት (rationality) እማያውቀው ነው። ዘወር ያለበት ብቻ እሚቀበለው እና የጉዳይአችንን ነገር ምንያክል ቸልታ እንደተቸረ እሚያስመሰክር ስላቅ መከራከሪያ ነው።


በመሰልጠን፣ በሰብእአዊ እኩልነት፣ በዝማኔ፣ በተሻለ አረዳድ እና የመተማመን አቅም ወይም እምነት እሚነሳ ዘመንአዊ ኢትዮጵያ እስኪፈጠር፣ ይህን መሠል የጸረ-አርነት እና ኋላቀርነት ጉዳይዎችን አቅፈን እንጓዝ ይሆን አለ። ያም፤ አለመከወኑ፣ እስከአሁን ግራ ለማጋባት የተፈቀደውን ፊደልገበታ ይዘን አለመለወጥአችንን ያተመው ነው። እነሆ፤ ይህን ከመፀየፍ ብዛት ግን፤ የባሰ ስህተት ግን የተሻለ ጤነኛነትን እንደ መውጫ ዛሬም እንጠቁም።


አስራሁለተኛ – ከላይ ስንቀጥል – ስለአማርኛ ፊደልገበታ ምንም እንፍረድ ምን፣ ይሁን ብለን አንድ ነገር እንከውን። ይህም፤ በህግ እና ደንብ እንደከሁም በስነስርአት ታቅፎ፣ ቋንቋው የእሚከተለው አካሄድ ድንጋጌን ያግኝ። ከመቶ አመት በላይ ይህን ክርክርቴ ዳናውን ማደን ይቻል አለ። አንድ መዘመን ቢያቅተው አንድ ህግ ግን አስሮት ትውልድ እንዳይጨቃጨቅበት እገዛን እንኳ ይከውን።


ከኢክዊኖክስ ቀማሪው ግእዝ ፊደልገበታአችን ባንጠቀመውም ስለተነገረን ብቻ የወረስንው የኅዋ አቅምአችንን በመከራከር አናባክነው። ለነገሩ፤ ቢኖር ኖሮ፣ የተሻለ ማስረጃው የተሻለ ማህበረሰብ መሆንአችን ነበር። ያንንም አልሆንንም። ያ አቅም ከምድር ወገብ በኩል ወደፊደል ገበታ ከእዛ ወደዬት እንደእሚጠፋ እግዜር ይወቀው። ግን፤ ህግ በየቱም መንገድ ካላሰረው፤ መንታ ድህነት ነው፨

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s