Categories
ሥነዉሳኔኛ (About Politics)

ጸረ-ምእራብአዊነት እንደ ጸረ-ኢትዮጵያአዊነት

Letting remember that boundaries are imagined, as opposed to truth, humanity, nature, discoveries, laws and most important things to us. While it is of the essence to allow self-focused attempts and customizations, it is too archaic to hear catagorization of human’s knowledge and reality as European or such.


bY ቢንያም ኃይለመስቀል ኪዳኔ፤ የካቲት ፲፫ ቀን ፪፼፲፫ዓም.፨

ምድር ቁንጽል ፈለኬ (planet) ናት። ዘረአዳም በመሠረቱ አንድ ነው። (መሠረተ) እውነት ገሀድ እና ወጥ ነው። አምላክ፣ እውቀት እና ጥበብ፣ ከአለ ልዩነት፣ ለሁሉ አንድ ነው። የሰው ልጅ አኗኗርም ሆነ መስተጋብርዎቹ ሁሉ በመሠረትአዊነት አንድአይነት ናቸው።


ብዙ ጊዜ፤ በኢትዮጵያአዊው ማህበረሰብ ችግርዎች መፍትሄ አሠሳ፤ አንድ መስመር እንደ ተቃውሞ እና ማስጠንቀቂያ ይቀርብ አለ። “ያ፤ የአውሮፓአዊያን አተያይ፣ ፍልስፍና፣” ወዘተ. “ነው!”። ያ፤ ትክክል እና ስህተት መንገድዎች አሉት።


ከተገቢው ለመነሳት፣ ሦስት ነገርዎችን እንመልከት።

፩) ሀገርበቀል (ዐውድአዊ) አተያይዎች፣ ፍልስፍናዎች፣ ጥናትዎች፣ ወዘተ. ለምድረ-ሀበሻ ከውስጡ ማብቀል አስፈላጊ ነው። ያ የአልተከፈተ የስልጣኔ አንዱ በርአችን ነው። ስለ ወግዎች፣ አኗኗር ዘይቤዎች፣ ታሪክ፣ መልክአምድር እና ተፈጥሮ ሀብት፣ ወዘተ. ምርመራአችን፣ ዉሂብአችን፣ መረጃአችን፣ እውቀትአችን፣ ጥበብአችን፣ ትርክት አቀማመርአችን፣ ወዘተ. ዐውድአዊነትን (contextualization) ማከም አስፈላጊአቸው ነው።


በእዛ ሚዛን ሲመዘን – ብዙ እና ገና እጅግ ብዙ – የአልተጀመሩ የትትረትዎች በሽበሽ አሉን። ዉዝፍ መሆኑ ከመጥናቱ፤ መሰረትአዊ ጉዳይዎች እንኳ በእዛ ትልም ገና አልታዩም።


፪) የእዚህ ማህበረሰብን ለማስተካከል እና በጨለማ መወረሱን ሊገፉለት፤ ከውጭ ሀገርዎች እሚመዘዙ የስልጣኔ ትትረትዎች፤ በቀጥታ ግዝግቤት (import) ከእሚደረጉ ብጁአዊነት (customization) ማድረግ እና፣ ሀገርአዊነትን ማጣባት አስፈላጊ ነው። ቢያንስ በአቀራረብ እንደ አካባቢው እንዲመስሉ ይህን መከወኑ አስፈላጊ ይሆነን አለ።


፫) መንታ እሚሆኑ፤ የመጡ እና እዚህ ግን የነበሩ እና በብሔርአዊ አርማአችን አለማወቅ አመክንዮነት የተዘነጉ ነገርዎችን፤ ማስተካከልም የመጨረሻው የእዚህ ጉዳይ አያያዝ ይሆነን አለ።

ከእዚህ በዘለለ ግን የበዛ እና እጅግ እሚዘገንን የአውሮፓ ወይም ይልቁንም የሌላው አለም ጥላቻ አለን። ያንን ማከም አስፈላጊ ነው።


በምን ጉዳይዎች?


፩) እውነት፣ እውቀት እና መሰረትአዊ የሰው እና ተፈጥሮ ኑባሬ (existence)፣ (ወይም ገሀድ) ወጥ እና በአንድ ህግ እሚተዳደር ነው። ለሀበሻ ሲባል እሚከረበት እውነት በምድር የለም። ያ ከሆነ፤ እማይቆጠሩ እሚሆኑ ነገርዎችን፤ ግዝግቤት መከወን አስፈላጊ ነው። አቋራጭ መንገድ በመሆኑ ጭራሽ ልዩ-ጠቃሚ እሚሆን ጭምር ነው። እውነትን እንደእየወገኑ መስራት ካልተቻለ፤ ሀቅን ከአንድ መንደር ጎልብቶ ስላገኙት የአንድ ጎራ እውነት ነህ ማለት፤ ግልጥ ጭፍን-ህፃጼ ነው።


፪) ሀበሻ የተለየ ጥያቄ ለተፈጥሮ የለውም። የተለየ መልስ፤ ተፈጥሮም ለሀበሻ አታቀርብም። የሰውዘር ፍላጎት እና ከተፈጥሮ ምላሽ ማግኘትም እምብዛም አይቀያየርም። ጤና፣ ምቾት፣ እርካታ፣ ደህንነት፣ አርነት፣ ትለቃ፣ ስልጣንን ወሳኝነት፣ ወዘተ. የማህበረሰብ እና ግለሰብእ ሁሉ መሠረትአዊ እና አንኳር አሠሳዎች ናቸው።


፫) ከስልጣኔ እና ስነምግባርአዊ ጥያቄዎች መሀከል መስመርን ማበጀት አስፈላጊአችን ነው። ከውጭ ከእሚገባ ከአንድ አመለካከት፣ ስልጣኔ፣ ወይም አንዳች አጋጣሚ ጋር እሚያያዝ እና እሚጫሩብን የምግባር ጥያቄዎችን እሚያጭሩ ጉዳይዎችን መመልከት ያለብን እንደ ምግባር ጉዳይ እንጂ እንደ ቀረበልን እድል አይደለም።


፬) ምን አልባት የይዘት ግንኙነቱ ምንም ባይታየኝም፤ ሎሬት ጸጋዬ ከላይ በተጠቀሠው ቃለመጠይቅአቸው ለዌንዲ ቤልቸር እንደተናገሩት፤ የሀበሻ ስልጣኔን እናነተ አሜሪካአዊያን ወስድአችሁ ሽልፍኖት (technology) አበጅአችሁለት እንጂ እኛ የሁሉ መሠረት ነን እና እኛ መሠረትአችሁን አጥኑን” እሚሉበት ማሳሠብያ አለ።
በእዛ መንገድ፤ የውጭ የሆኑ ብዙ ነገርዎችን ከእዚህ እንደተሣሰሩ መመልከቱም፤ ምንም ቢለይብን ምንም ለሁሉም ኧረ ለአብዛኛውም ከቶ ባይሰራ ብቻ መነሻው ከእዚህ እንደነበር በማስተዋል ለቀላል አቀባበል እንድንበቃ እንዲህ በብልሃት መመልከት አንድ አማራጭ ነው። ምንም የተመረመረ አካሄድ ባይሆንም፤ የነጥብ መሠረት እሚጥል ጉዳይ ነው። ብቻ፤ ስልጣኔዎች ወይም ሙሉለሙሉ እንደ እሚጓዙ ወይም እንደነገሩ ተደርገው እንደእሚበጁ፤ ከእኛ የተወሠዱ እሚባሉ ነገርዎች ካሉ የጉዞውን ነገር አስተውሎ አሁንም እሚኮረጁ ነገርዎችን መልሶ አቻ አድርጎ በመመልከትም ማስተናገድ እሚቻል ነው።


፭) ከእኛ የጉዳዩን አያያዝ ጎዳና ይቀላቀል እንጂ፤ ሙሉበሙሉ ከእኛ አይቀራረብም ስለእዚህ ይቅርብን፤ ብልህ አይደለም።

በጠቅላላው፤ የስልጣኔ መንገድ እንኳ ቢዘገይ የመሰረተ-ህላዌ ጉዳይዎች፣ ለምሳሌ እንደ ምግብ ዋስትና፣ መጠለያ እና ዘመንአዊ አስተዳደር፣ ንጽውሳኔ (democracy)፣ ወዘተ. ከየትም ቢመጡ፣ ያው አስፈላጊ እና አገልጋይ ናቸው። እኒህን መሰረተ ነጥብዎች ወገን ማበጀት ገደብ እማያውቀውን ሰብእአዊ ተፈጥሮውንም መገደብ ነው። ያ ፍብረካ ነው።
የተሻሻለ አለምን መናፈቅ፤ በእራሱ ብቻ ኩነኔ አይሆንም። ያ፤ ከመልክአምድር አንፃርአዊነት በራቁ ስፍራዎች መገኘቱ ምንም ሀጥያት አያደርገውም። እንደ ግለሰብእም ሆነ ማህበረሰብእ ተመሳሣይ ኑባሬአዊ ፈተናዎች እና ፍላጎትዎች ከብበውን አሉ። በልእለ-ብዙሃኑ አጋጣሚዎች፣ በሌላው አለም የተፈለጉ መልስዎች የትም እሚሠሩ እና ማገልገል እሚችሉ ናቸው። የአንድ ክፍለአህጉር አብዛኛዎቹ መልስዎች፣ የተገኙት የመንደሩን መልስ ፍለጋ ተወጥቶ አይደለም። የሰውን እና ምድርን ነገር በመመርመር ነው።
እንደ ሀበሻ ለእኛ ብቻ እሚሆን መፍትሄ ብናስሥ፤ ማስታገሻ ካልሆነ በቀር፤ ቋሚ ህክምና ለመመስረት አንበቃም። ለሀበሻ በእምናልመው አለምም፤ ቋሚ እና እማይነካውን ወጥ የተፈጥሮ ኑባሬአዊ መገለጥን ማወያየት አለብን። አዙሪት ይሆንብን አለ። ምክንያቱም፤ ያንን መከወን፤ አህጉር የለውም። ሁሉም ስፍራ፤ ከቀለም እና አቋቋም ውጭ፤ ሰው፣ ተፈጥሮ፣ የምድር አሠራር እና ታሪክ፣ የማህበረሰብ መሰረትአዊ ባህሪያት እና ታሪክ (ለምሳሌ ሁሉም ሀገር ጥንትአዊ፣ ከእዛ የንጉስአዊ፣ ከእዛ ወታደርአዊ፣ ከእዛ አብዮትአዊከ ከእዛ ንጽውሳኔአዊ፣ ወዘተ. አመጣጥን በአስተዳደር እና ታሪክ አልፏል።) ወዘተ. እማይለያዩ በመሆኑ፣ እምናዳብረው ምላሽ በብዛት፤ ከቀረው አለም ተመሣሣይ ነው።
የተቀረው አለምም፤ ለምሳሌ በምስራቅ ምድር፤ ከሌላው አለም የወረሰአቸው እንዲሁ ብዙ ናቸው። እዚህ፤ የበዛ ግልዮሽአዊነት (individuality) እሚጠየቅ አይሆንም።
ቢሆንም፤ አንድም እጅግ ብዙ ጉዳይዎች የግድ እና የግድ ከእዚሁ መጽደቅ አለብአቸው። ሁለትም፤ የበዛ የይዘት ጥቅም ባይፈጥሩም፤ አንዳንድ ተውሰንአቸው የአሉትን በሀገርበቀል መስተንግዶዎች መለወጥ እሚቻልብአቸው መንገድዎችም አሉ። እንዲሁም፤ እሚመጡትን የእዚህን መንደር ማለማመድ እንጂ ከቶ መከልከል መንታ ኋላቀርነት ይሆናል።


በቀረ ከእነእዚህ ያግንታዎች (exceptions)፤ እራስን በእራስ ላለመጥለፍ፤ ገሀድን ተንጠላጥሎ የተሻለ ገሀድን የመሠረተ ምእራብአዊ ሥልጣኔን አንጻረር። ያ፤ ጸረ-ምእራብአዊነት፤ ከስሜቱ አንፃር ጥንትአዊ ጭፍንነቱ እንደ ተዘለለለት፤ በደፈናው ጸረ-ኢትዮጵያአዊነት ጭምር ነው። እንኳን ከውሥጥ ማብቀልን ብዙ አስኪዶ መገልገል፤ የተዘረጋ ቀኝ እጅን እና ድጋፍን ለእረዥም ጊዜ መጠቀምም አልተቻለም፨

By Binyamhailemeskel

Hey there! If you want to know about me, I just like fun, commonsense wisdom, and human love. Let us live a bright today changing tomorrow into brighter.
Regards,

One reply on “ጸረ-ምእራብአዊነት እንደ ጸረ-ኢትዮጵያአዊነት”

በመጋቢት 05፤ ክፍል አንድ ስርጭትአቸው፣ የ ለብአዊት መርሐግብር በ አርትስ ትመ. ላይ ታላቁን ጸሐፌተው አያልነህ ሙላት አስተናግደው ሲያወያዩ ነበር። ዋና አንዱ ነጥብ የሀገርበቀል እውቀት ጉዳይ ነው። ያም፤ ሀገር ውስጥ የተገኘ በማለት ገልፀውት ነበር።
ሀገርበቀል እውቀት ከውጭ መጣበቅ እንጂ የሀገርበቀሉን እውቀት መተው ከቶ የለበትም ብለው አብነት የገለጡት ደግሞ፤ የቤተክህነት አጻጻፍን ነው። ሀዲስ አለምአየሁ የቤቤክህነት እውቀቱን ከዘመንአዊ አገናኝቶ በመጻፍ ፍቅር እስከመቃብርን አስውቦ ሰጥቶን ሳለ፤ እንደእኔ ያለንው ግነ ከውጭ በተማርንው እምንሰራ ነን ብለዋል። ዳሩ፤ ፍቅር እስከ መቃብር ራሱ ከሼክስፒር የተሰረቀ እንደሆነ እሚሰማ ነው። (ሳምሶን ታደሰ (ቤቢ) በተወነበት ተከታታይ ድራማ በ2012 ዓም. እየተቸ እንደገለጠው)። ብቻ፤ የቤተክህነት ጽህፈት የአፃፃፍ ዘዬ እንጂ፣ የአጻጻፍ ሀገርበቀል ስልጣኔ አይባልም። ስልጣኔ ምንጭ ሀገር አለው እንጂ፣ ይዞ የእኔ ብቻ እሚላት ስለሌለ፤ የሀገርበቀል እሚባለው ተለምዶ ዘዬ ከእሚለው እሚስማማ ነው። አማርኛ በጎጃም እና ወሎ ዘዬ አንድነቱን እንደእማያጣ ግን ቀለሙ እንደእሚለያይ፤ ስልጣኔም ፍሬነገሯ አኗኗር ማቅለል፣ እና ማሰልጠን እንጂ፣ መለያየት የለባትም። አጻጻፍ ከተፈበረከበት ሀገር በቀለ አይባልም። የሰው ሁሉ ጥበብ ነው። ቀድሞ አብቃይ ሀገር ግን አለው። ቀድሞ በቻይና ስለተፃፈ፣ የመጻፍ ጥጥበብ ሀገርበቀል እውቀቴ ብላ ቻይና አትናገረውም። አብሮ፤ ግእዝ ነው የጀመረው ቢባልም፤ ለሌላ ፍፃሜዎች ከአልሆነ በቀረ፤ ሀገርበቀል እውቀት ማለቱ እማይታሰብ ነው። በሀገር ውስጥ የተነሳ ጥበብ እንጂ፤ ሌላ ቦታ የሌለ አይደለም። ወይም ስነጽሑፍን የ አርገን ኦፍ አቃድ ልጅ ብትጀምረውም፤ የኢራን ሀገርበቀል እውቀት አይባልም። በምድር ሁሉም በእየመንገዱ ስነጽሁፍን በተለያየ ጊዜ ጀምሮት አለ።
ይህ ሁሉ አያያዝ፤ ፍፃሜው፣ እውቀት ሰው ሁሉ እሚያስሳት እንጂ በድንበር እምትገደብ አለመሆኗን ለመቀበል እንድንችል ነው። እውቀት ከተሞክሮ ወይም አመክንዮ፤ እምትታፈስ አረዳድ ናት። እውነት እንዴት እንደሆነ መገንዘብ ናት። የአለባበስ፣ የአሰራሩ፣ ስነስርአቱ ወይም ሂደቱ፣ ወዘተ. ይለያይ እንጂ – ያም ዘዬ የአልንው ነው – ፍሬነገሩ ግን ከቶ አይለያይም። እውቀት የጥበብ መረማመጃ አሽከር ናት። የእሚጀምራት እና የእሚጠቀማት ቢለያይም፤ ዘዬዋ ቢለዋወጥም፤ በእውነት ግን አንድ ናት። አኗኗር አመቻች፣ ነገን አሻሻይ፣ የሆነች አገነዛዘብ ናት።
በመሰረቱ እውቀት ሀገርአዊ ድንበር አይዛትም። ቀዳሚ አብቃይ ሀገር እንጂ፤ ጠባቂ የላትም። ያም ቀድመን ጀማሪ ነበርን እንደእሚባለው ነው።
ይህ እሚያግዘን ነገር አለው። ያም፤ ሀገርበቀል እውቀት ብለን ዝብአገነዛዘብ ከመከወን ወደ ተገቢ ሀገር በቀል ጥናት እንድንመለስ ነው። ሀገርአችንን አላጠናንም። አልመረመርንም። እውቀትን ከአለበት እና ዘዬ ከአገኘበት አምጥተን እምናግበሰብስ ብቻ ነን። እውቀትን አንዳንዴ በሀገር ዘዬ ማላበስ ጠቃሚ ሲሆን እና ከምንም በላይ ሀገርን ማወቅ ደግሞ ያስፈልገን አለ። ያ ማለት ከዘዬ ወይም ለምሳሌ የባህል መዳኒት ወይም የባህል ፍትህ ስርአት ጥናት ጋር አይገናኝም። ያ፣ ያለንን ዘዬ ማወቅ ነው። የትም ሀገር ባህልአዊ ህክምና፣ የፍትህ ስርአትም አለ። ዋናው የፍትህ እና ህክምና አገልግሎትዎቹ ስልጣኔ መሆንአቸውን እና ወጥ ከመሆንአቸው የተነሳ የሰው ወይም እውነታ ስልጣኔ ብሎ መገንዘቡ ነው። የቀረው ዘዬ ነው። ያንን ሀገርበቀል ብሎ ከማንቆለጳጰስ፤ ወደ ሀገር ማወቅ እንሻገር አለን። ሀገር ማወቅ እንዳልንው ዘዬውን ማወቅ ሳይሆን፤ ማጥናት እሚያስከትለው ነው። ለምሳሌ፤ በስነመክንዮ፣ የእራስአችንን ሀገር መመርመር፣ መልክአምድር እና ታሪክ ማወቅ እና መገልገል፣ አኗኗርአችን ከዘዬአችን ቀጥለን ማዘመኛውን መንገድ መፈለግ፣ ሀገርበቀል ከእምንለው (ዘዬ) ስልጣኔአችን በላይ መራመድ መቻል ወዘተ. ላይ ልናተኩር የአስፈልገን አለ።

Like

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s