Categories
ሥነዉሳኔኛ (About Politics)

መንደርምስረታ፡ ዛሬም የአርነቱ አንድ ተስፋ

About reminding basic urbanization process is still the hope for Ethiopia’s better future.


bY ቢንያም ኃይለመስቀል ኪዳኔ፤ ጥር 30፣ 2013 ዓም፨

ካስተናገደአቸው የዘመንአዊ ስልጣኔ ተግባሬትዎች (projects)፣ የወርቅ-ደረጃ ታሪክ ለኢትዮጵያ እሚሆነው በእርግጠኛነት ታላቁ መንደርምስረታ ነበር።
ይህ በብዙ አመክንዮዎች አንክሮትአዊ (critical) በመሆኑ፤ የስልጣኔ-ሥር ጉዳይ ነው። እጅግ ማራኪ እና ተፅዕኖአማ አሻራው ለዛሬም የመሀከልሀገር ኢትዮጵያ የቀረ ነው።

 • ትልምአግጣጫው
  በመሠረቱ፤ የማህበረሰብአዊት ፍልስፍናዎችን መተግበሪያ መንገድ ነበር። ለገበሬው ክፍለ-ማህበረሰብ የከተሜ አኗኗርን እንዲቀላቀል ማድረጊያ መንገድ ነበር። የእሚሰበሰቡ ገበሬዎች፣ የተለያዩ የአውታር አገልግሎትዎችን ለመገልገል ይጠቅምአቸው ነበር። የኢሰፓ. አባል የሆነ እየተመለመለ ወደ ገጠር በመጓዝ ቤትዎች በማስፈረስ ይቆዩ ተመልሰው ደግሞ በአንድ መንደር ያስገነቡ ነበር። ምንም እንኳ ገበሬዎች ደርግ ሲወድቅ ወደእየገጠሩ ቢመለሱም፤ ደርግም እንዲወድቅ ህዋሃት.ዎች ተገድዶ መንደር መመስረት አይኖርም እያሉ ያባብሉ እና ድጋፍ ይፈጥሩ እና የሀገር ዑደትን ያሥጣሉ ቢሆንም፤ ትልቅ ማእዶት ግን ነበር።
 • ጥቅምዎቹ
  የዛሬዋን ኢትዮጵያ ዘመንአዊ ማእከልዎች መልክአምድር-ወ-ህዝብ (geo-population landscape) በእማይናቅ ደረጃ የጠነሰሠው ይህ መንደር ምስረታ ነው። ዛሬ፤ ያኔ በተጀመረው እየተስፋፋ የሄደ የህዝብ አኗኗር በከተማዎች ዙሪያ ምስረታ እና እንቅስቃሴዎች እንመለከት አለን። አሁንም ያንን ጥቅም ማብዛት እሚቻል ነው። የባህል፣ አኗኗር እና ስነምጣኔ ኢምንት መዛነፍዎችን አቅርቧል። ያ ከሆነ ምን ምን ይማሩበት አለ? እሚሰርቁት ትምህርትዎች አሉት።
  ፩) የዘመነ አምራችነት (industrialization) መሠረት እና ጓደኛም (መሳለመሳ እሚሄድ) ነው
  ጥንትአዊነቱን አቅፎ በዝማኔ በአልሠለጠነ ሀገር፤ መሠረተ ስልጣኔ ገና መግባት እና መቋቋም አለበት። በዘመነ ኅዋ (አሃዝአዊ ሽልፍኖት/digital technology) እና ሰውሰራሽ አይምሮ (artificial intelligence)፤ ገና ዘመነ ግብርና ላይ ያለን ነን (አብዛኛው ህዝብ ለመኖር እና ስነምጣኔ ፍለጋ የተሰማራበት፤ መንግስትም (ብሄርአዊ ስነምጣኔው) የሰማይስባሪ ገቢውን እሚሰበስብበት፤ መስክ ከመሆኑ አንፃር)። በቅርቡ፤ ከበሬ-ተኮር ጥንትአዊ ግብርና ወደ ዘመነ ግብርናም ሳይገባ የአምራች ዘመንነት (age of industrialization) ላይ ፊጥ ለማለት ጥቃቅን መፍጨርጨርዎች ተደርገው ነበር። ለምሳሌ አንዳንድ ስፍራዎች የተበታተኑ፣ በቻይና መንግስት ድጋፍ እና ሽርክና ንግድ፤ ማምረቻ መናፈሻዎች ለመቋቋም ተሞክሯል። ያ ግን፤ አምራችነት ዘመንን አይመሰርትም፤ አልመሰረተምም። ዘመነ አምራችነት (industrialization age) ሁለንተናአዊ ስልጣኔ ነው።
  አንድ የሀዋሳ ማምረቻ መናፈሻ ሲመረቅ፤ የህንድ አምራች ተቋም አንድ ተወካይ “እዚህ የመጣንው እጅግ ነፃ ማለት እሚቀልል የሰው ጉልበት እና ብዙ የመንግስት ጥቅማጥቅምዎች ስለእሚሰጠን ማምረት እርካሽ ወጪ ስላለው ነው” ብሎ ነበር። ማለትም፤ የባህል ለውጥ፣ መሸመት አቅም፣ እና የማምረቱም ልማድ እና አቅም ሀገር ዉስጥ ገና አልተፈጠረም። የድኅረ-ቅኝ ግዛት ርካሽ ስነምጣኔአዊ ወጪ ፍለጋ እና ብዝበዛ ብቻ ነው። መንግስትም፤ ስራአጥነት እና ሽልፍኖት እና እውቀት ሽግግር በእሚል በቀላሉ ያታልልበት ነበር።
  እንጂ፤ ዘመነ አምራችነት፤ ግብርናውን አጠንክሮ በመደገፍ፣ በጥራት የተማረ ማህበረሰብ በማበልጸግ፣ የስነምጣኔ ዘርፉን በእየፊናው በማበልጸግ የመግዛት አቅሙን ህዝቡን በማብዛት፣ ከተማአዊነት በማበልጸግ፣ ወዘተ. ሁለንተናአዊ የልማት መስተጋብር እንጂ የተራ ሀብትን እና ድህነትን ማስበዝበዝ ሂደት አይደለም።
  መልሶ እሚያባክኑት እና እሚመዘብሩት የውጭምንዛሬ ማግኛም እሚሰኝ አናሳ ትርክት ማሟያ ሳይሆን፣ ዘመነ አምራችነት ማለት የግዝግቤት መተካት (import substitution) ማለት ነው። ሮዳስ ታደሰ (ሊቀምሁርዎች) በ ኢቲቪ. መዝናኛ “ፈታኝ ሣጥን” መርሐግብር ለወጣቱ እይት አሳላፊ (Show host) እንዳሉት ለምሳሌ፣ እንደ ሳምባቆልፍ-፲፱ (COVID-19) ወረርሽኝ ተከስቶ አለም ድንበሩን ቢዘጋ፣ መድኃኒት እንኳ በብቃት ስለማናመርት እንቸገር አለን፤ ቢያንስ የሆነ ያክል ምርትአችንን እዚሁ እናምርት እንዳሉት፤ ዘመነ አምራችነት በሀገር ዉስጥ ቢያንስ ብዙውን የማምረት ሂደት ስራ መስራት እና ምርትን ለአገልግሎት ማመቻቸት ሲበረታ እና ሲጠነከር ግዝዉጤት (export) መከወን ማለት ነው።
  በጠቅላላው፤ መንግስት ሀገርን ከጥንትአዊነት ወደ ዝማኔ (ለምሳሌ አምራችነት) ለመመለስ፣ ከእሚልግአቸው ሂደትዎች አንዱ፤ የተበታተነውን ነዋሪ ወደ ከተማዎች ማምጣት ነው። አብሮ የአገልግሎት ዘርፍ ይመነጠቃል። በፍፃሜው አኗኗር ይቀየር አለ። ያንን ከደርግ መማር አስፈላጊ አንዱ ነገር ነው።
  መዘመን፤ ሀገርን ማሠልጠን፣ ድህነት ቅነሳ፣ እና ወዘተ. በከተማአዊነት ይሳካል።
  ፪) ለኢትዮጵያ አማራጭየለሽ ጎዳናዋ ነው
  ሀገርአችን፤ ከአለም ድሀድሀዎች የመጨረሻ ጎራ ናት። የህዝብ አኗኗር ለማዘመን ከባድ መገዳደር አለ። አቅምም የለም።
  አቅምን አሟጥጦ ግን ስኬት ለመሠብሰብ፣ ብሔቆርአዊ ቆጣቢነት አስፈላጊ ነው። ከተማአዊነት ደግሞ ያን በማገዝ በአጭር የአስተዳደር ወጪ አገልግሎትዎችን ለመጨረስ ያስችላል። ከንቲባአዊ አሽከርነትን እና መሰረትአወከ የልማት አገልግሎትዎችን እንደ ተበተነው ህዝብ በታትኖ ከማቅረብ እና የአጀማመር እና አያያዝ (eastablishing and running) ወጪዎችን ከማናር፤ ያለ የሀብትን ውስንነት በምርጡ መንገድ ለመቀየር ከተማአዊነት አስገዳጁ መንገድ ነው።

መደምደሚያ


ይህ እጅግ መነሻ-ጥቂት ጽሑፍ፤ መንደር ሰፈራን ለኢትዮጵያ አስፈላጊነቱን ለማሳየት ጥሯል። የጥንት ስልጣኔን ወደ ዝማኔ አቻው ለማምጣት ገሀዱ መታየት መጀመር አለበት። የተበታተኑ ኢትዮጵያአዊያንን በማሰባሠብ ማጠንከር ይፈለጋል።
የባህል፣ አቅም፣ ህግ፣ ፖለቲካ፣ ዲሞክራሲ፣ ዝማኔ፣ ወዘተ. ጉዳይዎች በተሰባሠበ እና በተቀራረበ ህዝብ መሀል ይሳለጥ አሉ። እስከ እዛ ግን፤ በእሚዘገይ ሂደት እምንተበተበውን ሁኔታ ማስቀጠል ይሆን አለ።
ጭራሽ ዘመነ ስልጣኔ ቢቀር፤ የአምራችነት እና የተሻሻለ ነዋሪነትን እንኳ ማምጣት በእዚህ መንገድ እሚቻል ነው፨

By Binyamhailemeskel

Hey there! If you want to know about me, I just like fun, commonsense wisdom, and human love. Let us live a bright today changing tomorrow into brighter.
Regards,

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s