Categories
መልካም ጥበብዎች Fine Arts

ማስመሠልን አለማሥመሠል እና ትክክለኛው የአኗኗር እና ኑባሬ ሥልጣኔን ፍለጋ

About the errors and opportunities in the super-crawling yet-no-matter-how-backward [#Recent_but_backward] attempt of civilized culture making by some Ethiopians.

bY ቢንያም ኃይለመስቀል ኪዳኔ፤ ጥር 2013 ዓም፨

አንድ ሰሞን፤ በተለይ ዘጠናዎቹ መጨረሻ፣ የአኗኗር ፍልስፍናን በመሀከልሀገር ውስጥ የነበርን በስንዝር በመቀየር ላይ ነበር። በደንብ ባይመዘገብም፤ አንዱ ነገር ግን የአኗኗር ጥበብን ከአንድ ነገር አንፃር መረዳት ነውጥ የታበት ነው። ይህም፤ በማህበረሰብዊ ግንኙነትዎችአችን “ማሥመሰልን” መልመድ እንደእሚገባ ብዙዎች ይገነዘቡ ጀመር።
ስለእዚህ የአመለካከት እድገት መስካሪ ሆና፤ ኩኩ ሰብሥቤ፤

ቻልኩበት፣ ዘንድሮስ ቻልኩበት፤ የኑሮ አያያዙን ሁሉንም አወኩበት…ማባበሉን፣ ሳቅሳቁን፣

ወዘተ. እያለች ትዘፍን ነበር። እንዲሁ፤ ጥበቡ ወርቅዬ፣

ገባኝ አሁን ገና ገባኝ አሁን ገና፣ ከሰው ጋር ለመኖር አቋራጭ ጎዳና፣ ማስመሠል መሆኑ እያደረ ገና…

እያለ ተመሳሳይ የሆነ ነገር ይነግረናል።
ደህና የስነእናኪነ (art) ጥረትዎች ናቸው። አሁንም የበለጠ መንበልበል ከእሚገባአቸው የሀበሻ ችግርዎች መሀል አንዱ ይህ የባህል ትርጓሜ ነው።

ባህልን ገና በዘመነ መንገድ አልገነባንም። ብዙ ስምጥ እና ሠፊ ክፍተትዎች እንዲሁም ግጭትዎች ሁሉ በእዛ አሉን። ይህም፤ ባህልን ከጭፈራ፣ እና አለባበሥ ወይም ምግብ፣ አበላል፣ የዕድር፣ እቁብ፣ መረዳዳት፣ ወዘተ. ትውፊት፣ ልማድ እና ወግዎች በማዘለል የመመልከት አስገዳጁ ጉዳይ ነው። በእኛ የባህል አረዳድ፣ ግለሰብአዊ የአኗኗር ጥበብዎች ተካትተው አይታይም። በወል እምንከውነው ዳንስ አለባበስ እና መሰል ጉዳይ ለመንግስት ባህል ነው ብሎ ማስወራቱ ከስነውሳኔአዊ ትርፍ አመቺ የሆነለት ነው። ሰዎች ባህልን እንደ ማንመሆን ምስጢር እንዳያውቁት ያ እረድቷል። ባህል በጋራ እሚገኙ ዘይቤዎች ብቻ እንደሆኑ አስተምሮ፣ የመከፋፈልን ሴራ አበልፅጓል’። ለተጠይው ከርፊ የስግብግብነት እና ኢሰብአዊነት መገለጫ – አምባገነንነት – አመቺ ስልት ሆኗል።

ዳሩ፣ ባህል ማንነት ከሆነ፣ ማንነት ሰውነት ላይ ሀ ይላል። ሰውነት ላይ ብዙ ተሠርቶ ወደ ወልነት ይመጣል። በተቃራኒውም በትክክል ቢከተሉት ያው ነው። ከጋራ መሆን ወይም ጋርዮሽ እሳቤም ወደ ግል ምን መሆን መመለስ ይቻላል። አካሄድ ሳይሆን ቁልፉ፣ መድረሻው ነው። በመንግስት እና አለመዘመን የተነሳ የለመድንው መድረሻ ደግሞ፣ የግለሰብአዊ ብልፅግናን ለማደናቀፍ እና ዋናውን የሥልጣኔ መስመር መዝጋት በምላሹ አምባግነናን ለማትረፍ ስለነበር ይህ የባህል ዝማኔ አረዳድአችን አፈርድሜ በልቶ በአንድ መንግስት ስር ቆይቷል። ዛሬም።
ዛሬም፤ ያ እዉነታአችን (our reality) ቁልፍ ነው። ሀገርአችን፤ ባህልን ሆን ተብሎ በእዚህ መንገድ ብቻ እንደተረዳች ናት። ይህ የአምባገነንዎቿ አለመብቃት እና የተዳከመው የጠቢባን (intellectuals) ድህረ-ደርግ የመጣው ክፍፍል ያወረሰን አስተዋፅዖ ነው። በሌላ ጎን የባህል ዝማኔን አምጭው፣ የአምራችአማነት (industrialization) አለመንሰራፋት የሰጠን ክፍተትም ነው።
ብቻ፤ ባህልን ከሥልጣኔ መሰረት አባልነቱ በመቀነስ፣ የጥንት ተርታ የባህል አገነዛዘቡ እንዲቆይ ዉጤት-አፋሽ ስራዎች ተከውነዋል። ባህልን ዝብ-አገነዛዘብ አልብሠን ብሔረሰብዎችን ለማፈን ብንጠቀምበትም ግን፤ ትክክለኛው የዘመነ የባህል ጥናት እራሱን በስንዝር ለመግለጥ በዘጠናዎቹ ዘፈንዎች በጥንጥ ብልጭታ መጠን ተገደደ።

ባህል አኗኗር መንገድን እሚመሰርት በመሆኑ ኑሮ እና ስኬትን እሚወስን ነው። እነእዚህ ከያኒዎች ደግሞ ማስመሠልን ባህል አድርገን እንድንኖር ሰበኩን። መልካም ጥረቱ ሁሉ እንዳለ፤ ገና መስፋት እና መብዛት እንደሆነ፣ ብዙ ጉድለትዎች ግን አሉ።
እጅግ የሀበሻን ዋናዋና ጉዳይን ሁሉ በእየዘርፉ ገላጭ የሆነ አንድ ማብራሪያ ሰጭ ያን ሲያደርግ ደግሞ ጥምቆራጭ የሆነ ግጥም አንድ አለ። ይስማእከ ወርቁ፤ የወንድ ምጥ ላይ፤ ትክክለኛው በር ላይ የደረሰ ሰካራም ግድግዳውን እንጂ በሩን አያንኳኳም ይላል።

አሁንም፤ የከያኒዎቹ ምርትዎች እና ይህ ትዉልድ፣ በበለጠ ያንን አሻሽሎ መገንዘብ አለበት እንጂ በማስመሠል (ደርሶ ደርሶ በሩን በአለማንኳኳት) ፍልስፍና መሸወድ የለበትም።
ኢትዮአሜሪካአዊው እውቅ እና ተሸላሚ ደራሲ፤ ዲናው መንግስቱ፣ በመቀደሻ (debut) ልብወለዱ CHILDREN OF THE REVOLUTION፣ ላይ ናኦሚን ብልህ ታዳጊዋን ሲሥል እንዳስቀመጠው፣
የኑሮ ጥበብ ከላይከላይ (face value) እንደሆነ ገብቷት አለ፤ (ገ.45)
እያለ ይናገራል።

ይህን እነ ኩኩ እና ጥበቡ ያነሱት እና “ማስመሠል” ያሉት ነው። ቃሉ፤ ሀሳቡን በደንብ ግን ቆንጥጦ አይዝም። ሰነፍ ነው። ለእዛ ነው የይስማእከ ግጥም ደወል እሚያቃጭለው። ከማስመሠል፣ ይልቅ ማስመሠልን አለማስመሰል ይሻላል። ዲናው የተሻለ እንደነገረው እና ሌላው እንደሱ ያሉትን እሚከተለው ተደራሲ እንደእሚረዳው ማስመሰል ሳይሆን “አቅልሎ እያዩ” መኖርን መገንዘብ አለብን።
ነገርን፣ ህይወትን፣ ኩነትን፣ እራሳችንን፣ በእሚገባ ከላይከላይአዊ እይታ መዉሰድ መቻል አለብን። እንጂ አስመሳይነት ወደሽንገላ እና ቁምነገረኛነት ላይ መድከምን ያመጣል። ትክክለኛውን ሀቅ ስንደርስበት አዛብተን ማየት ያክል ነው። ከማስመሠል፣ ሀቀኛነትን ማጥበቅ ተገቢ ነው። ዳሩ፣ ብዙ ከሰው አለመጠበቅ፣ ቀድሞ ለእራስ መሆን (በኋላ በልብ እንዳይሰበሩ)፣ መከበር፣ ግልዮሽአዊነት (ሁሉን ለእየግሉ ፈቃድ አክብሮ መተው እና ከእዛም የተነሳ አለመበሳጨትን ማግኘት)፣ ወዘተ. የመሰሉ አበልፃጊ አስተሳሰብዎች ይከሰቱልናል። በማስመሠል ፍች ያን መገለጥ ከተረጎምን ግን፣ ቅኔውን ሳትን።

አስመሥለን፣ ሳቅ ሳቅ ብለን፣ ገጠጥ ገጠጥ ብለን ወደጓሮአችን እስክንዞር መኖርን፤ ያ ዝብ-አረዳድ ይሰጠናል። እንደ ግል እንደእሚሆነው እንደ ሀገር እንዲሁ፣ አክሳሪ ነው። ሀገር ማስተዳደር እና ህዝብ ማገልገል ድረስ ሳቅ ሳቅ በእሚል ፊት እያስመሠለ ሁሉም ይከዳናል፤ ወደ ግል ጥቅም ብቻ ይኬዳል፤ ፍቅር እና መተሳሠብን ያርቅብን አለ። የቻይና ሠራተኛዎች ሲገነቡ ንብረት ተዘርፎ፣ እንደቀለዱብን እና፤ ‘የመንገድ ዳር ብረት እሚሰርቁት ሌላ ሀገር አላቸው እንዴ?’ እንዳሉት፣ አስመስለን እምንኖረው ሌላ ምስጢርአዊ ህይወት ያለን ስለሆንን ነው እንዴ? ሀቀኛ እምንሆነው መቼ እና የቱ ጋር ነው? ልዩ አለም የለንም። ካልሳቁ ገዳይ ያለ ይመስል ለመሰንበት በእሚል አስመሥለን ስንቀራረብ፣ ሳቅሳቅ ስንል አኗኗርም፣ አስመሳይ’ ይሆንብናል። አለባብሰን ኑሮን አንኖርም። በአረም መመለስ ይሆናል። አደጋን ማብዛት ነው።
ይልቁንም፣ ሀቅን እና ማስመሠልን-መጠየፍን መልመድ አለብን። ለሥልጣኔአችን፤ በእየቦታው ሀቀኛ መሆን እና አንድ መሆን፣ ግዴታአችን ነው። በዉሸት ሳቅ ደግሞ ግንኙነት ሁሉ ዶሮ ማታ ነው እና ምንም የተሻለ አናተርፍም።

ይህ የሰረቀን እምቅ (potential) እድል ግን፣ ዘግናኝ እጦት ነው። በማስመሰል ከመጠመድ ሀቅን በመውደድ፣ ማድረግ እሚገባን ግንኙነትን በደንብዎች እና ህግዎች፣ በአዲስ ሀቀኛ ባህል እና ኑሮዘዴ ነው። ግንኙነት በሀቅ፣ በሥራ፣ በዉጤት፣ እና ማግኘት መመስረት አለበት። የሽንገላ ፈገግታ ዉጤቱ ያሰነብተኛል ብቻ ከሆነ ተታልለናል። ዓስተኔ-ሰብእ (mankind)፣ ያን “የማስመሰል ዘመን” በዘመነ ሥልጣኔ መሰረት’ ታልፎ ታልፏል። የሰው ልጅ በዝማኔ ታፍሯል፤ ተከብሯል። ቀና ቀና ብሎ፣ የውሸት ሳይኖር፣ በህግ እና ዘመንአዊነት ተከባብሮ በፍቅር እና ገሀድ እሚያግዘው ፍላጎት ብቻ ግንኙነትዎች መስርቶ እና እያስቀጠለ እየኖረ ነው። ያ ስኬትን ሰጥቶታል። የሰውልጅ አንገት ደፍቶ መኖሩ ሰብአዊ ባህሪው ባይሆንም፣ አስመስለን እንኑር ማለትአችን አንገት ደፍተን የከፋ ኋላቀርነትአችንን እናስቀጥል እሚል ልአለ-ኋላቀርነትአችንን ገላጭ ነው። ጥንትአዊነት ጥንት ሊያስቀረን አይገባም። ሀቅን እና ዝማኔን እናልምድ። ቀና ብሎ ሳያፍሩ በግልጥ መኖርን ለመማር ሩቅ የዘመነ ሀገር እንኳ ባንሄድ፤ ወደእነ ሀረር፣ ድሬዳዋ፣ ዙምራ፣ ኮንሦ፣ ወዘተ. ዘምተን የተሻለ ሀቀኛ እና ግንባርስጋ (straightforward) ፍልስፍና እንኮርጅ። ለማስመሰል አንሳቅ። ነውር ነው። ማንም ካስከፋ አቦ! እሚሉ ወይም አፍረጥርጠው እሚግባቡ እንደሆነ በወሬ እንኳ እንድንሰማ ይነገራል። በግልጥ እና ገሀድ መኖርን ከተማርን፣ ተጩኾበት ጭራ በወርችዎቹ መሀከል እንደቀበረ ዉሻ ተሽቆጥቁጦ መኖሩ ያብቃ። ጉዳቱ በስነዉሳኔ (politics)፣ ሥነምጣኔ፣ ጠቢአችን (our future)፣ እና የኑሮ ጥራትአችን ትልቅ ሆኖ አለ። በመሳቅ ካልተሸነገለ፣ አገልግሎት መስጠት ግዴታው እንደሆነ እማይረዳ እና ኮስተር ካሉበት ለምቦጭ እሚጥል እና እሚያጉላላን የኪስአችንን ፍርፋሪ አጠራቅሞ ደመወዝ ተደግፎ እሚኖር መንግስት እና ግል ሰራተኛ መልሶ-ማጥቃቱን ይከውንብናል። እንደህዝብ በዘመንአዊ ፍልስፍናዎች እና ሁሉን የማክበር ስሜት ተከባብረን ከመገናኘት ይልቅ በመሳሳቅ-ሽንገላ እና ማስመሰል የተገናኘን እና የሰራን በመሆኑ፣ ጥራት ያለውን ሀቀኛ ሰራተኛ አግልለን ያልተገባ ጥራት ያለው የህዝብ አገልግሎት እና አስተዳደር ፈጥረን ያ ክፍተት ዞሮ ያንገበግበን እና ይገርፈናል። እኛም፣ አለሀቅ በዉሸት በመሣሳቅ እምንጠቀም እና ህሊና-ለምኔ ብለን እንደ ዉራጅ-ፍጥረት “በባወጣያውጣው” ያረጀ እንስሣአማ ደንብ እምንሰነብት ያደርገናል።
ከአንገት በላይ ስንኖር እና ስንኗኗር ሀቀኛው አምላክ የቸረን ኑሮ ይሳለቅብናል። በማስመሠል ይሳካል ስንል፣ መታተር ይረሳን እና በትክክለኛው መንገድ ራስን መገንባት ያመልጠናል። ከጥንት-ቀር የዴርቶጋዳ እና ተከታታይዎቹ ልብወለድዎች ጭብጡ ተሻሽሎ በቀረበበት ደህንነቱ ልብወለዱ ይስማእከ እንደሰበከው ቀድሞ እራስን ነፃ ማውጣት እና መቻል እሚለውን እናመልጠዋለን። እራስን ከመገንባት፣ በአቅም እና ሀቅ ከመጠቀም ወና ፍትህን ከመኖር ይልቅ፣ በአንገት አስደፊ አስመሳይነት-ሽንገላ-ሳቅ በድህነት እንድንጃጃል ያደርገናል።
በግለሰብእ መብትዎች እና ግዴታዎች፣ በህግ እና ዘመንአዊ ባህልዎች ከመገናኘት እና አክብሮ-ተከብሮ ከመኖር፤ ያንን ስነስርአት እና የመብትዎች መከበሪያ አለም ከመፍጠር የእሚያስቀረን ግለ-ወጥመድ ይሆንብን አለ።
በጠቅላላ፣ ሀቅ እና ቀናአዊነት፣ ግልጠኝነት እና ተጠያቂነት ባለበት አኗኗር እንድንኖር እና በመበልፀግ ጎዳና እንድንመለስ፣ የማስመሠልን ጉዳይ ቸላ ማለት አለብን። እንኳን አስመስለን ሳናስመስልም አልተሳካም። መንግስት እንኳ ሁሌም አሁንአዊ (live) ድራማ እየሰራ፣ ጠፍናጊ በዓል፣ ምርጫ፣ አገልግሎት ወዘተ. ምርጥ እንደሆነ እያስመሠለ እንዲኖር አብቅተንዋል። ሀቁን ሳናገኝ በሽንገላ አፈፃጸም ሳቅሳቅ እየታከለ ማእዶትን ማደን አይቻልም። አስመሳይ ህዝብ አስመሳይ መንግስት እና አስመሳይ ከባቢ ይፈጥራል።

አንድ ወቅት አኗኗር ከላይከላይ (face-value) እንደሆነ የነጥበቡ ወርቅዬ ተዋዳጅዎች (fans) ተገነዘቡ። ያም፤ እጅግ መሠረትአዊ ነው። (የህላዌውን ደንብ መርምሮ ሲፈጽም) የሰውልጅ የዝማኔ-መነሻ ጥበብዎችን አስሦ ይፈጽማል። እና በግኝትዎቹ መሰረት ደንብ ሠጥቶ ይጨርሳል። ያን እሚከውን ዘመንአዊ ማህበረሰብ ስኬት ያገኛል። አንድን ነሰረትአዊ ነገር ሰው ከዘለለው ግን አለሙ ሙሉ እና ስኬትአማ መሆን አይችልም። ሰው ሆኖ ግን በእርጋታ እየተደሰተ ወይም በአበጀው ገደብ ይቆይ እንጂ እንዳሻው የመኖር ዕድል አለው። ያ፤ የአኗኗር ፍልስፍና አንዱ ነጥብ ሆኖ ሳለ፤ እሚከወነውም፣ ግንኙነትአችንንም ደንብ በመስጠት ብቻ ነው። ግንኙነትን ማስመሠል በእሚሉት አገላለፅአቸው እነእዚህ ተዋንያን እንደተወኑት፣ አንድ ጥያቄ እንጠይቀው። ማስመሠል ሰውን ስናገኝ፣ ከእዛስ? ብቻችንን ስንኖርስ? ያ፣ የነጥቡን ስፋት፣ እና ጥበብነቱን ያሳየናል።

ሰው ማንነቱ ዉስጥ፣ እንዲሁ እርጋታ እና ቁጥብነት ያስፈልገዋል። ረጋ ያላለ ቸኳይ ነው። የተሰማውን ቶሎ ይገልጣል። ያ ደግሞ መልሦ ወይም በመልስምቱ ሊነክሰው ይችላል። ታዲያ ቆጠብ ብሎ በእርጋታ የመኖር ጥበብ ሰው ፊት ስንሆን ፊጥ አድርገን እምንቀጥረው ፍልስፍና አይደለም ማለት ነው። ግለሰብአዊ የአኗኗር መንገድ ነው። የማንመሆን አንድ አላባአዊው ነው። እንጂ እንደ ማስመሰል ብቻ ተብሎ የሚጠቀለል አይደለም።
ባለማስመሠል፤ ከላይከላይ ኑሮን በመቀበል፤ ሀቀኛነትን በስነስርአት (system) በመደገፍ፣ እንደማህበረሰብ ከወደቅንበት አፈር አብረን እንነሣ፨

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s