Categories
ሥነዉሳኔኛ (About Politics)

መንታ ኢትዮጵያ

About underscoring the persistently underrated Ethiopian duality or runt-like twin-ness (urban and countryside) discourse.

bY ቢንያም ኃይለመስቀል ኪዳኔ፤ ጥር 30 ቀን 2013 ዓም፨

“ኢትዮጵያ ሲባል ፳እጁን ብቻ ሣይሆን የገጠር ህዝቡንም እንደሆነ መታወቅ ይገባዋል።”

በቀለ ገርባ፤ መምህር እና ስነውኔኛ (politician)

ታሪክአዊ መነሻ

ምርአዊ የዘመንአዊ ከተማአዊነት (Modern urbanization) ፈርምግባር (initiative) አህጉሩ ያስተናገደው፤ የጎንደር ከተማ ለአፍሪቃ ታሪክ ፈርማህደር (record) ሆናው ስትቆረቆርለት ነበር።

ቀጥሎ፤ ኢትዮጵያን የወቅቱ (እና ምንጊዜውም) አፄ ካሳ፤ ዘመንአዊት ኢትዮጵያን ጠንሥሶ ግሉን ሲገድል፤ አፄ ምንይልክ ፪ ትንሿን አዲስአበባን አለሙ። ዐብይ ለውጥ፤ ቀኃሥ. ዘመንአዊዋን አዲስአበባ አበረቱ። በቀረ እሚሻለው ቀኃሥ.፣ ሁሉም፤ በከተማአዊነት የሞከሩት እንደ አንክሮትአዊ መሰረት (critical base) አልነበረም። ደርግ፤ መንደርሠፈራን እስኪጀምር። ያ፤ ከተማአዊነትን በአንድ እና ሁለት ስፍራዎች ከመመልከት፤ በደቦ (mass) ከተማአዊነትን በእየስፍራው ማጎንቆል ጀመረ። በገጠር በገፍ ለእሚኖርበት ሀገር፣ የአንዲት ከተማ ማልማትን መተው በመሳካቱ፣ በታሪክአችን (በተለይ የቅርብ) ከትልልቅዎቹ የዘመንአዊነት ሙከራዎች እጅግ አጓጊው ነበር። ከእነችግርዎቹ፤ ከእነተቃውሞዎቹ፤ ከእነዳግ-ማፈግፈጉ፤ ብዙ ስኬትን ግን አመጣ። ጭራሽ ዛሬም እሚጨበጥ የሆነ ነው። ወታደር እና ህግዘብ (police) አስገድዶ እሚከውንአቸው መንደር ከገጠር እያፈረሡ ህዝቡን ወደእየተሰበሠቡ ቦታዎች እና መንግስት በእሚነድድ የስልጣኔ ፍቅሩ በእራሱ ገንብቶ ወደአበጀአቸው ሠፈርዎች ጭምር ማምጣቱ በብዙሃን ቢጠላም ዉጤቱ ከፍተኛ ሆነ።

ብዙዎችን ከጨለማ ገጠር ወደ ከተማ አገልግሎት እሚገኝበት፣ የባህል እና ስልጣኔ መሰረት እሚታይበት፣ የስራ እና ስነምጣኔ ዉስብስብ እድልዎች ወደእሚፈስሥበት ከተሜነት ብዙዎችን አፈለሠ። ደርግ እንደወደቀ ቤትአቸውን አፍርሰው ወደ እየገጠርአቸው የተመለሡ (ለተግባሬቱ /project) ማፈግፈግ፤ ቢኖሩም፤ ዛሬም ሠፊ አሻራው ግን በኢትዮጵያ ከተማአዊነት ቀርፆ አለ።

ከደርግ መንደርሠፈራ በኋላ፤ በኢህአዴግ. እና ብልጽግና፣ ምንም የተለየ የከተማአዊነት ትትረት አላስመለከቱም። በብልጽግና በእርግጥ የከተማዎችን ማስዋብ ወቅትአዊ (ለጊዜው የተሳካ) ስራዎችን መመልከት ተችሏል። ያ፤ ስለ ህዝብ ከተማ መኖር ሳይሆን አንድ ሁለት ከተማዎችን ጥቂት ከአቅለሽላሽነት ለማስታገስ የተከወነ በመሆኑከህዝብ እና ከተማአዊነት ፍሬጉዳይ አንፃር እዚህ ግባ አይባልም። በተለይ በኢህአዴግ. ግን ያ ቸልታ ነበረበት።

እቅድ-አለቃ (master plan) እንደ ቅኝግዛት የተከፋፈለች ሀገርን በእየስፍራው ብዙዎችን እሚያበሳጭ እንቅስቃሴ ነበር። ያም ወደተግባር እምብዛም ለውጥ ሲከወን አልታየም። አኗኗር በመቀየሩ እና በመረጃ እና መሰረትአዊ ትምህርት መስፋፋት የተነሳ፤ ህዝቡ ከተሜነትን በመውደዱ እና የገጠር የመሸከም አቅም በመሟጠጡ፤ ስራ ፍለጋ እና ለውጥ ፍለጋን ወደ ቸል የተባሉ ከተማዎች እና መንደርዎች እንደአሻው እሚፈልስብአቸው እንጂ እስከአሁን ልዩ ተግባርአዊ የከተማአዊነት ስኩ ጉዳይ በገሃድ አልተስተዋለም። የታሪክ አጭር ቅኝቱ ይቋጭ። በጠቅላላው፤ አጭር የከተማአዊነት ትትረትዎች ታሪክ ሲኖረን፤ ደርግ የተሻለ ህዝብአዊ ትልምአግጣጫ (policy) ለመተግበር ሲሞክር፣ በቅርብ ደግሞ በብቸኛነት ማለት ይቻላል፤ ህዝብ እንደአሻው ከተማአዊነትን እሚገነዘብ እና እሚቆጣጠር ሆኖ ያለ ነው። ዛሬም፤ የኢትዮጵያ እጅግ ልእለ-አብላጫ (super majority) ህዝቧ በገጠር መንደርዎች እሚገኝ ነው። በእየራሱ የሰላም፣ ጸጥታ፣ አገልግሎት፣ ወዘተ. አያያዝ እሚኖር ነው። ከተማ ውስጥም፤ እጅግ ድሃ የከንቲባ-አገልግሎትዎች ሲገኝ ገና ባልጠነከረ ከተማአዊነት ውስጥ አታካች እና ያልተቀረፉ፣ እየባሱም እሚገኙ ችግርዎች አሉ።

ኢትዮጵያ፡ መሀከልሀገር እና ሀገረሰቤ

ማለት ይቻላል በመደበኛነት፣ ስለኢትዮጵያ የተነሣ ነገር ምንጊዜም ልኮቱ (its reference) ከተማ ኢትዮጵያን እሚያደርስ ነው። በቀረ ሁለት ያግንታዎች ወይም አይደሉምታዎች (exeptions) ሀገረሰቤ ኢትዮጵያን ገለጥኩ ብሎ ካልዘረዘረ ወይም ከከተማ ውጭ እሚገኙ ቅርስ እና መስህብዎች ካልተገለጡ። ከእነእዚህ ውጭ፤ ህዝብ፣ መንግስት፣ አስተዳደር እና ብሄርአዊ ስነልቦንታ (national psyche) መሀከልሀገር ኢትዮጵያን እንጂ ሀገረሰቤን የዘነጋ ነው። እቅጩን ልክ እንደዋዛ። መግለጥ በእሚቻልበት መንገድ ሁሉ፤ የኢትዮጵያ ሀገረሰብ እና ሀገረሰቤ እንደ ሁለተኛ ሀገር እሚታይ ነው። በመደበኛው ዜጋ ልብ፣ ገጠር ኢትዮጵያ ለመዝናናት እሚኬድበት፣ ለጉብኝት እሚሠነበትበት፣ ከዋናው የኢትዮጵያ ኑሮ የተገነጠለ፣ ከእንስሳት እና የሩቅ ዘመድ በቀረ ምንም ነገር እምብዛም እማይገኝበት ተደርጎ እሚታይ ነው። በመገናኛብዙሃንዎች እና ብሔርአዊ ርክትዎች ጭምር፤ ሀገረሰቤ ግለሠብዎቹም፣ የባህል ምልክት፣ የየዋህነት ምንጭ፣ የመስተንግዶ እናትዎች፣ እንዲሁም ከድኻድኻ ተደርገው ይታሰብ አሉ። ሲከፋ ኋላቀር እና ያልዘመኑ፣ ግብርና ብቻ እሚያቁ ሰነፍዎች፣ ከተማ ለግርድና ብቻ እሚገቡ፣ ምንም እማይገብአቸው፣ ያልተማሩ እና ምንም እውቀት የሌልአቸው፣ ወዘተ. ሆነው እሚሳሉ፣ እጅግ እጅግ ሲከፋ ሊፀየፉአቸው ሁሉ እሚያገዱ ልዩ በአድ ፍጥረት ናቸው። ልዩ የሆኑ አንዳንድዎች፤ ያንን ያፈርሳሉ። የሀገር ስነምጣኔ ዋልታ፣ የዕድ እና ባህልአዊ እውቀት (hand craft and traditional knowledge)፣ መደበኛ ዘረሰው፣ የሀገር ዋና ወይም እኩል አባል፣ ከከተሜው የበለጠ በመንግስት እሚጨቆኑ ተጠቂዎች፤ ወዘተ. አድርገው ከመንጋው ስነልቦና እና እይታ-አሠሳ – ይልቁንም እይታ-ድርቀት – በመነጠል ይህን ገጠሪቱ ኢትዮጵያ በቁምነገር እየጨላለፉም ቢሆን ያያሉ። በእዛ መሠረት ቢሆንም፤ በቂ አመለካከት እንደሌለ በመገንዘብ ይህን ይዳሥሳሉ።

ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን (ጸገመ.)፤ “ማነህ ባክህ?” እሚለው አንጀት እሚያላውስ ግጥምአቸው፣ በእየጉራንጉሩ ከእየዘርማንዘሩ እሚገኘውን የተገለለ እና የተናቀ፤ በመሀከል ሀገር ዜጋ ስነልቦና እና አመለካከት እንዳለ የተዘነጋን ሀበሻ ዜጋን እንደ እማይታወቅ ያሳብቃሉ። ህዝቡ ስለእማይታወቅ ስለእዚህ፤ (እና) “አንተ ማንነህ?” እያሉ ይገጥም አሉ። ማንነቱ እንኳ ያልተቋቋመ፤ የተዘነጋ ምስኪን ፍጥረትነቱን (በቅኔ) ያሳብቅ አሉ።

ተስፋዬ ገብረአብ፤ የ ስደተኛው ማስታወሻ ላይ፣ ወደ ራያ-ትግራይ መስመር ሲጓዝ እና ሲተርክ እንዲሁ አንጀትን በአጭር ጉዞ ማስታወሻው ይበጥሳል። ምንም እሚያቁት የሌሉ የሀገረሰብእ ወጣት ምስኪን እመቤትዎችን እዛው ገጠር ተወልደው አድገው ፍፃሜአቸውም በተገደበ የህይወት ሙከራዎች፣ እድል እና ዳሠሳ እዛው እንደእሚሆን ሲተርክ የሰብእአዊ መብት እንደተዘነጋ እና አስተዳዳሪዎች በእነእሱ ስም ብዙ እንደእሚያደርጉ እያሳበቀ ይገልጣል።

በዕውቀቱ ስዩም፤ በአንድ ግጥም እንዲሁ እጅግ አስጨናቂ ገሀዷን ስለ ገጠሪቱ ምስኪን እመቤት አንስቶ ልክ ንደ ተስዬ ገብረኣብ አይነትመባባቱን ይቀኝ አለ። ጊዜ ከጭንቀቱ እንደእሚተዋት እና እህል በዕድ-ወፍጮ መከካት የዘመንዎቿ ክልል ተሞክሮዎች ቁንጮ ማብቂያዋ እንደሆነ በትንሹ ኖራ እንደእምታልፍ ወዘተ. ያወጋ አለ። ፋንታሁን ጥሩህነ በ ደርግ አስተዳደር በአዱደ የነበረውን ስህተት በመሀል እና ዳር ሀገር ክፍፍል አጥቶተ መለከተው አለ።

እንዲህ ያሉ እና ተጨማሪ ጥቂትዎች፤ የኢትዮጵያ ሀቀኛ ገሀዱን አይተው በጥቂቱ ብዙ ማለትአቸው እንዳለ፤ በአጭሩ ግን፤ የንአቸው ብቻ እንኳ ምን ያክል የተዘነጋች እና የተገነጠለች እኩል የአልኑ መንትያ (runt) ኢትዮጵያ እንዳለች ያስመለክቱን አሉ። አሳፋሪው ሀቅ እንደ መደበኛ ዜጋ “ኢትዮጵያ” ሥንል ገጠርን መዘንጋትአችን ሳይሆን፤ ከተርታው ህዝብ እኩል፤ መንግስትም እማይጨነቅለት ባለ-ትልቅ ደረጃ ዝብ-አረዳድ መሆኑ እና ሁለት አይነት ዜጋዎች በአንድ ሀገር የመገኘትአቸው ነገር ነው። ይህን የሀገር ሀቅ፤ ቢያንስ በአመለካከት ደረጃ፤ መቀየር ለሀገር መሠረትአዊ ሠፊ ጥቅም አለው። – ስነውሳኛአዊያን (politicians) እና ትልምአግጣጫዎች (policies)፣ ህግዎች፣ አፈፃጸምዎች፣ እና የስልጣን ፍተሻዎች እንደከተማው (ምንአልባት ግን በበለጠ) ስለገጠር እንዲያተኩሩ ያስፈልግ አለ። ስለ እጅግ አጭሩ የ ሀበሻ ክፍል (ማለትም ከተሜው ኢትዮጵያ) በማተኮር እሚመጡብን ስነውሳኔኛአዊያን, (politicians) እጅግ ሊቀበሉአቸው እሚሸግጉ ናቸው። የእኛ የከተሜዎቹ ኢትዮጵያአዊያን መሰረት እና ወደፊት ጭምር ሀገረሰቤዎች ናቸው።

የስነምጣኔ መምህሩ (በቅርብ የ ኢዜማ. ድርጅት እጩ ሆነው የተቀላቀሉት እና ስለ ሀገርአችን ስነምጣኔ እና ሁኔታ የተሻለ ሙያአዊ ትንታኔዎችን በ ትመ.ዎች (Tvs) ሲያቀርቡ በአለፈው አመት እና ዘንድሮ እሚደመጡት) ፈቃዱ በቀለ (ሊቀሊቃን/ Prof.) ለ ወጣቷ ፍቅርተ ተመስገን በ ኢሳት. ትመ. ኢኮኖሚአችን መሐርግብሯ (2013 መግቢያ አካባቢ) እንዳወያየችአቸው፤ መንግስት ግብርናው ብዙ “ውጭምንዛሬ” ይሰበስበት አለ። ብሩ በዛእው ይቀር አለ ሌላ አላማ ቢያገለግል እንጂ ወደ ግብርናው ተመልሶ ስለ ዝማኔው የተለየ ድጋፍ ግን በምላሹ አያቀርብም። ያም፤ ገጠሩን አላሳደገውም። ያ ቢስተካከል፤ ግብርናው ይዘምን ነበር፤ እሚል ማብራሪያ አቅርበውላት ነበር።

የገጠሩን ህዝብ እንዳያድግ ቸላ ያለ መንግስት በተከታታይ በመኖሩ፤ የከተማው ህዝብ በኑሮው የተጎዳ ሆኗል። የሀገር ስነምጣኔም እንደእሚችለው አልተራመደም። ተቃዋሚዎች እንኳ ቢቀሩ፣ መንግስት መስራቹ ኢህአዴግ. (ብልግና ድርጅት) ጭምር፣ የገጠር ኢትዮጵያን ዘንግተውት አለ። ከማዳበሪያ ዕዳ በዘለለ ቸልታ እንጂ የተለየ ቢያንስ እዚህግባተባይ መንግስትአዊ አቅምን በገጠር-ኢትዮጵያ ሲከወን አንመለከትም እሚለው መደበኛ ትርክት እና ወደገጠር ገለለራ ሲሉ እሚመለከቱት ሀቅ ነው። ያ፤ እንዲለወጥ፣ ኢትዮጵያ ስንል በተቻለሁሉ ዝርዛሮት (specification) እንዲኖረን ወይም አካቶአዊነት ቢኖረን ይመረጥ አለ።

ይህን ጨለም ያለ የኢትዮጵያ ገጠርን አትከትትም ግልጽ እንደምታ የያዘ አመለካከት ማፍረስ ለሁሉም ጠቃሚ በመሆኑ፤ እሚገባው (በተለይ ስነውሳኔ አካባቢ) ስፍራ ሁሉ እንድንመለከተው እንድንሰራ ያስፈልገናል።

ጠቅላላ እውቀት ወይም መሰረትአዊ መረጃ ነው

የኢትዮጵያን ሁኔታ በገጠር እና መሀከልሀገር ብሎ እንደእየስነልቦናው፣ አቅሙ፣ እድሉ፣ ችግርዎቹ፣ ወዘተ. መገንዘብ መቻል እና አመለካከት-ክወናን በእዛ መረጃ ላይ መቅረጽ ለሁሉም ዜጋ የንቃተህሊና መዳበር ጠቃሚ ጉዳይ ነው። በንግድ፣ ትምህርት፣ ወዘተ.ውስጥ የመረጃ እና አተያይ ነገር ትልቁ ዋጋ ነው። የተንሻፈፈ እይታ መኖሩ የተዛነፈ አመለካከት ያሏቸው ተማሪዎችን አስተምሮ ወደ አስተዳደር እና ግል-ግንባታ ማምጣት ነው።

በመክሸፍ የተለመደውን ‘ገጠር ኢትዮጵያዊነት ውስጥ የውበት ዋጋ ብቻ አላት፤ አትጨነቁላትም’ እሚለውን ሰነፍ ጉዞ አማራጭ አድርጎ እንዲቀርብልን ማድረጊያው የስህተት መንገድ ነው። ያለፈው እና ዛሬው ቢቀር የመጪ ዘመኑ ሀገር ለውጥ ትትረቱ እንኳ እሚፈለገው ፍፃሜ ላይ ሀገርን አያደርስም። ሀገርን፤ ገጠር በጭለማ እና ከተማ (ከሞላጎደል ቢሻልም በብዙ ስቃይ ያለበት) ብሎ ለሁለት መክፈሉ እና በንቃት ሁሌ እንዲተረክ እና እንዲታወቅ ማድረጉ በመሰረትአዊነት ደረጃ መነሻ መረጃ ሆኖ ለምድሩ እጅግ አስፈላጊ ነው።

የትውልዱ የመፍትሄ አፈላለግ፣ ኑሮን አገነዛዘብ አቅሙ እንዲጠነክር፣ እጅግ መነሻ አንዱ ጉዳይ ከባቢውን ዘሎ ድንበሩ ድረስ እንኳ በንቅአት መረዳት መከወኑ አንዱ ነው። እዚህ ላይ ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድህን ለዌንዲ ቤልቸር “ኢትዮጵያአዊነት ምንድር ነው?” ስትልአቸው የገለጡላትን እናክል። ያ፤ የአፍሪቃን ስልጣኔ፣ የኢትዮጵያን ስልጣኔ፣ አካባቢውን ወዘተ. ሁሉ በንቅአት ማወቅ ማለት ነው ነበር መልስአቸው። ይህን፤ በገሀዱ ማየት ቢከብድም እንደ ድድላጎት (aspiration) እና አስፈላጊ ግዴታአችን አድርገን ግን እንየው። የማንነት ንቃት ገጠርን ኢትዮጵያ፤ “ኢትዮጵያ”ን መሀከልሀገር ከማለት ይጀምር አለ።

ለ ኢትዮጵያአዊነት አረዳድ ማስተካከያ ከላይ እምንቀጥለው ይሁን።

ኢትዮጵያአዊነት መልካምነት፣ ደግነት፣ ተቀባይነት፣ የጥቁር ሰው አይነት ስልጣኔ ምንጭነት እና መመኪያነት ወዘተ. ከተባለ፤ ያ ተራ የወሬ፣ እድል ወይም ታሪክ ደረጃ ላይ ሆኖ እንዳይቀር አካሄዱን ለመቀየር፤ ገጠሪቱ ኢትዮጵያን በሁሉ እይታአችን መክተት አንዱ ነገር ነው። ኢትዮጵያአዊነት አሁን ሲፈታ “ገጠርን አግላይነት” ነው። ያንን፤ የተማረ ገና ያልወለድንው ትውልድ ሲፈጠር እሚያፍርበት እና ገና ታግሎ እሚቀይረው ከማድረግ ይልቅ፣ አሁንኑ ያንን ኃላፊነት መወጠን ያስገድዳል። እንደ ደርግ እና ገጣሚዎችአችን፤ ኢትዮጵያን በእዚህግባ እሚሰኝ የገጠር እንቅስቃሴ ወደ ዋናጅረት (mainstream) ብሄርአዊ ትኩረት እና ትትረት ማምጣት ያስፈልጋል። ኢትዮጵያአዊነት፤ ቢያንስ እንደሆነው ወይም እንደነበረው ዓለምአቀፍአዊነትን ቢያጣ፤ ህዝብዎቿን ሁሉን የከተተ አመለካከት ግን መደረግ አለበት። ያንን ማስቀጠል በፊት የተገባ ግዴታ ነበር። አሁንም መጀመሩ የትላንት ቤትስራ ነው።

ዘውግ ፍልስፍና ወዳጅዎችን መግቻ አማራጭ እና አንድነትን ፈንጣቂ ብልሃት ነው።

በ ኢትዮጵያ ከእሚገኙ ዋናዋና ስህተትዎች አንዱ ሁሉም ድሃ ሆኖ አምባሲገነንበት፣ ተከፋፍሎ በእየ አንጃው በተለይ ደግሞ በዘር ተከማችቶ እርስበእርስ መቀራረኑ ነው። በዘር ልዩነትዎች መብዛት ደግሞ የተነሳ፣ ዘውግን አቀንቅኖ በኢትዮጵያ ስነውሳኔ ሁለገብ ድል የለም። ዘውግአዊ ድ እንኳ ሀሰት ነው። ቶሎ ጠፊ፣አስመሣይም ጭምር ነው።

ከእዚህ ይልቅ ግን፤ ኢትዮጵያን በሁለት መክፈሉ ተጨባጭ እና ረጂ ነው። በ ጎን-ሀገር የአለው ተመሳሳይ ህዝብ ነው። ሁሉም የተገለለ ነው፤ ቢያንስ በመሰረትአዊነት። ከመነሻ አገልግሎትዎች አንፃር እንኳ በወጥ መሰል ብሄርአዊ ቸልታ እና ንቀት እምብዛም ስልጣኔ የሌለ ነው። ይህ የተገለለ ሀገረ-ክፍል፤ በአንድ ጎራ ቢሰበሰብ ለትግል ወይም ውክልና እሚያግዘው ሲሆን፤ የመሀከልሀገር ህዝብ ደግሞ በጎን እሚተው ይሆን አለ። ያ ደግሞ በብዛት ከስብጥር የተመሰረተ ነ። አንድ እና ሁለት ዘር(ዎች) ብቻ የአሉበት መሀከልሀገር የለም። ያ ማለት በተለቀ ከተማ በዘር የተደራጀ የመብትዎች መከላከል ሂደት ጎጂ እንጂ መጥቀም አይችልም እሚል ድምዳሜን የአስጮልቀን አለ። ሀገርን ለመገንባት እና ህዝብን ባባለ ልዑዋላዊነት ለማድረግ አንዱ ትልም ነው።

ለዘመንአዊ ማህበረሰብአዊነት ስነልቦና

ይህም ከቀደመው ይመዠረጣል። የቀደመው አንድ ጎን ተፅዕኖ (Corollary impact) ጥናት ነው። የሀበሻ ህዝብን ንጽዉሳኔአዊ (democratic) አመለካከት አቅሙን ለመጨመር፣ ታጋሽ እና ስነስርአትያለው (disciplined)፣ ማህበረሰብ ለማድረግ፤ የህዝቡን መሰባጠር እና ልዩልዩ ባህልን እና አተያይን ለምዶ እንዲኖር ማበረታታት ይገባል።

ከእኔ ብሄረሰብ ውጭ አልይ እሚል የኢ-ዜጋአዊያን (uncivilian) አመለካከት ከመደበኛነት ወይም ያግንታአዊነት ሁሉ ለማጣላት፣ ሁሉን በአዲስ (ዘመንአዊ) የኢትዮጵያአዊነት አይንዎች በሰብእአዊነት እና እኩልነት ማስመልከት ለማስጀመር፣ በህግ የበላይነት መተማመንን ለማምጣት፣ ወዘተ. በአጭሩ የዜጋዎች ስነምግባርን መርጃ መንገድ ነው። መሠባጠር መኖሩን፤ በግልአዊነት እንጂ በቡድንአዊነት መንቀሳቀስ እማይገባ መሆኑን፣ ወዘተ. ይህ የሀቀኛ ከተማአዊነት ስነልቦናን ያፈልቃል። ከተሳካ፤ በመሰባጠር እና በከተማ በመሰብሰብ የኋላቀር ቡድንተኛነት ስነልቦና ስለእሚፋቅ፣ የጥቅም አመለካከት ስለእሚበዛ፣ የተሻለ ዘመንአዊ ስልጣኔን ለመመስረት ያግዘናል።

በልዩነት መጠንከር፣ በመንደር ከማሰብ ህግ (የበላይነት) ላይ ወደመተማመን፣ ይሄ የኔ መሬት ነው ከማለት እና ከመጣላት፣ ወደ መከባበር እና በጥቅም ተሳሥሮ ወደመጠባበቅ፣ ብሎም መከፋፈልን ቀንሶ በመተባበር መንግስት ላይ የልማት እና ንጽውሳኔ ጫና ለማሳደር እጅግ መሰረትአዊ ግብአት ነው። በጠቅላላው፤ የልዩነት ትእግስት እና ዘመንአዊ አመለካከት እሳቤዎችን በህዝብ ለማብዛት፣ ይህ የማህበረሰቡን በገጠር እና ከተማ ተከፋፍሎ የመገኘት እና እኩል ህዝብ ሆኖ (ኢትዮጵያአዊ) እንደእዚህ የተለያየ መሆኑን ማስተማር ጠቃሚነቱ ይጎላል።

የፋንታሁን ትንታኔ ዛሬ በከልፊ ህያው ነው

በኢትዮጵያ ውሥጥ ያሉ እና የነበሩ ቅራኔዎች ጠባይ በተሰኘ አጭር ጽሑፍ፤ (በ ቀኃሥ. አስተዳደር ዙሪያ የገመገመውን እውነታ አዝምሞ በማተኮር የተፃፈ) ፋንታሁን ጥሩነህ (ሊቀምሁርዎች) የዳር ሀገር እና የመሀል ሀገር ጽንሰሃሳብ (ሰምና ወርቅ ጽመሔት፣ ልዩ እትም 1983 ዓም.) እሚል ጽንሰሃሳብ አበለጸጉ። በተለይ ዘር፣ ቋንቋ እና እምነት ላይ የተገነባ የመሀከልሀገር የበላይነት በእየ ዘውገ-እንቅስቃሴው ሲገኝ፣ በእየ ተጓዳኝ ዘርፉ (ስነጥበብ፣ ስነምጣኔ፣ ስነውሳኔ፣ ወዘተ.)፣ የዳር ሀገር ኢትዮጵያ የተገለለ፣ መሀይም እና አቅመቢስ ተደርጎ አለ፤ ያም ቅራኔዎችን ወልዶ፣ ሀገር በሁለት ጠቅላላአዊ ጽንፍዎች እየተቋቋመች ነው እሚል ስለእዚህ የፍትህአዊነት ክርክርን እንመስርት አሉ። የግፍተራ ፖለቲካ የአሉትን (ዳር ሀገርን አንጓልሎ መሀከል ሀገር የአለው አስተዳደርን የአጠረበትን አረዳድ)፣ ያ እውነት ከወነ ብለው ተከራክረው አለ።
ከአነሱአቸው ሃሳብዎች ዛሬ በእኛ ውይይት ተገቢው፣ ዘር እና መሀከል ሀገር ከስነውሳኔ ረብየአለሽ ተፅዕኖ-ፈጠራ በእርግጥ የተገለለ መሆኑን ነው። ኢትዮጵያአዊነትም እራሱ ከአዲስአበባ ዙሪያ ከመገኘት የእሚበልጥ ስሜት ነው ብለውት አለ። ዳር ሀገር የአሉት ከሀገሩ ጥቅም ተካፋይነት የአነሱ በመሆንአቸው ኢትዮጵያአዊነት ለእነእርሱ አናሽ ስሜት የአለው ነው። የስነውሳኔ ፍላጎትዎችአቸውም የተለዩ ናቸው። በተለይ በእነእዚህ ዙሪያ የቀረቡት ሃሳብዎች፤ አንድ ዘርን እና ቋንቋን መሰረት ማድረግአቸው በኢህአዴግ. (ብልጽግና) የተዘበራረቀ ቢሆንም፣ ዞሮዞሮ፣ የዳር ሀገሩን ማግለል፣ ዴንታ አለመስጠት፣ የአለ ነው። የእነእሱ አኗኗር፣ ጥያቄዎች፣ እና ነገረሁኔታ የተሰነጠቀ ሲሆን፣ መሀከልሀገር ደግሞ በእራሱ በተለዩ ችግርዎች እና ድበቧባብ እሚኖር ነው።

ገጠርም መሀከልሀገርም ኢትዮጵያን እምንመለከትበት መንገድ ቢሰነተር ይጠቀማሉ

ለምሳሌ ኢትዮጵያ በማለት መሀከልሀገርን ብቻ መግለጥ፤ ለመሀከል ሀገር ጎጂ ነው። የኢትዮጵያ ፍላጎትን እና ጥያቄዎችን በሁለት ሳይሰነትሩ በደፈናው ማቅረቡ ከፍተኛ የሀሳብ፣ ኢላማ እና ድርጊት መዛባትን እና አለመጠጠርን አምጪ ነው። በእዛ ጠቅላላአዊነት እንቅስቃሴን አስልቶ ስላላነጣጠረ ግብ እንዳይመታ ጎጂ ይሆናል። ለመሀከልሀገር “የኢትዮጵያ መሀከል ሀገር ጥያቄዎች እና ችግርዎች (በተለየ)” ተብሎ ትልምአግጣጫዎች እና ህግዎች መታሰብ እና መቅረብ አለብአቸው።

ጠቅላላው፤ የኢትዮጵያን ችግር፣ እድገት፣ ወዘተ. እሚል አተያይ ስር መሀከል ሀገሩን ማስተናገዱ ደፈናአዊነቱ ጎጂ ነው። የገጠር ኢትዮጵያ ችግር እና እድገት (ነገረ አለሙም) የተለየ ነው። የከተማውም። በደፈናው፤ መሰረተ መንገድ፣ መነሻደረጃ ጤናማእከል፣ መነሻደረጃ ትምህርትቤት፣ መብራት እና ንፁህዉሃ፣ ግብርና አገልግሎት፣ ከንቲባ-አገልግሎት፣ ማእከልአዊ እና ወጡ ህግ እና አስተዳደር፣ ወዘተ. የገጠር ችግርዎች እና መፍትሄ ዙሪያዎች መነሻ ናቸው። የከተማ ችግርዎች ደግሞ በቅርጹ ዘወር የማለት ነገሩ እሙን ነው። የዘመነ ከተማ አስተዳደር፣ ኑሮ ዉድነት፣ ጥራት አገልግሎትዎች፣ መሠረተ-ልማት፣ ስልጣኔ እና ንቃተህሊና፣ ንጽውሳኔ፣ ወዘተ. ወዘተ. ናቸው። (የከተማው የገጠሩም ችግር ቢሆንም፤ የገጠሩ ግን ፋታየለሽ ችግርዎቹ መቅደም እሚገባአቸውን ያስቀድማል)። ስለእዚህ፤ ቢያንስ እንደ መነሻ፤ ሁለቱ ክፍለ ኢትዮጵያዎች፤ እንደ ጥያቄዎችአቸው እድገት ካስመለከቱም በእየፊናአቸው እንጂ ከቶ አይቀራረቡም።

በእነእዚህ መለያየት አመክዮዎች የተነሳ፤ ሰማኒያ እና ሃያ እጅ ሀበሻን ሰንጥቆ መመልከት አስገዳጅ፣ ገና-መሰረትአዊ፣ እና ብልህ ነው። መደባለቁ፤ እጅግ ደፈናአዊነት እና ለሁሉም ጎጂ ነው። ይህንን አተያይ ወደ መደበኛ ልውውጥ (conversation/exchange) ሁሉ ማዝመት፣ የሀገር ችግርን በምርአዊ አያያዝ ለመጠንሠስ አስፈላጊው ጉዳይ ነው። ሲደመደም፤ መሀከልኢትዮጵያ ወይም መሀከልሀገር፤ ከትንሽ እስከ ትልቅ የከተማ አስተዳርዎችን ሲሸፍን፤ የቀረውን ሀገረሰቤ ብለን አየን። እንዲህ፤ አስቀድማም የተከፈለች ኢትዮጵያን ነጣጥሎ መክፈሉ ብዝሃ-ጥቅም አለው።

የትልምአግጣጫዎች (policies) እይታን፣ ጥራትን ያግዛል። የስነውሳኔ እንቅስቃሴዎችን ያግዛል፣ ይመራል። ስነምጣኔአዊ እድገትን ለመፈለግ ያግዛል። የብሔርአዊ የስነልቦና እና ከባቢ አገነዛዘብን በማኮለል ለሀገር ዜጋው ሁሉ ንቅአት እና የዕድል አሠሳ አቅሙ መጨመር ያግዛል። የባህል እና ዝማኔን እድል እና አረዳድ ያስፋፋል። የሀገር እድገት ትትረትዎችን በእየዘርፉ እንደእየፍላጎቱ ለመቅረብ ያግዛል። [ለምሳሌ በአጭሩ የትምህርት እና ባህል ለውጥ ጉዳይዎችን በሌላ አጭር መነሻ ጽሑፍ ተመልሰን ለማየት እንሞክር አለን]። በደፈና፤ የሀገር ዝማኔን በእረዥምጊዜ እና ምርአዊ አቀራረብ ለመያዝ – ጎልማሳአዊ (a grownups) አስተዳደር ለመከወን – እና ንቁ ህዝብ ለመሆን፤ ገና መነሻ ቢሆንም፤ ልዩነት ፈጣሪ ነው። ቢያንስ፤ ልዩነት እንዲከፈት ፈቅዶ ወጣኝ ነው። ኢትዮጵያ አዲስ ሆና አታውቅም። ያው ራሷ ናት።

ለምሳሌ፤ ስለ ከተማዎች እና መሰረተልማትዎች ችግር በተደረገ እርእስ የኢዜማ. ድርጅት (party) ተወካይ ኪነህንፃኛ (architect) ዮሐንስ መኮንን በ ሚያዚያ 27 ኛው ቀን 2013 ዓም. ስርጭት (ዳግ-ስርጭት = re-run)፣ ለ 2013 ዓም. 6 ኛው ሀገርአዊ ምርጫ በአደረጉት የምረጡኝ ዘመቻ ፉክክር፣ ከተማዎችን የኢህአዴግ. እና ብልጽግና መንግስት አስተዳደርዎች፣ በዘር ፍልስፍናው፣ ከተሜነትን ዘንግቶት አለ። ከተሜነት የስልጣኔ መሰረት እና የግሉ ቀለም የአለው ሲሆን፣ በብሔር እና ዘር የተመለከትንው ብቻ በመሆኑ፣ የተዳከመ ሆኖ አለ ብለው ነበር። (የተቀነጨበውን የአድምጡ።)

ግን ለንቃተ ህሊና እና ስልት ዝሙን (ፈጣሪ ፈር ጭምር) አተያዩ፤ መሀከልሀገር እና ሀገረሰቤ ኢትዮጵያ ማለት ግድ ይላል፨

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s