Categories
ሥነዉሳኔኛ (About Politics) ስለ ቋንቋ አማርኛ (ወይም ይልቁንም አማሊዝኛ) Amhalish

የኢሳቱ. ዕለትአዊ ዝግጅት፡ የጋዜጠኛዎች አማርኛ ቋንቋ ተግባቦት መሻሻል ESAT’s Eletawi Zigijit: Enhancement of Journalists’ Amharic Language Usage

Calling for attention towards modernization or at least betterment of Amharic language through ESAT’s እለትአዊ ዝግጅት፣ as an important contemporary development in the field.

bY ቢንያም ኃይለመስቀል ኪዳኔ፤ ጥር 2013 ዓም፨

ESAT ዕለትአዊ ዝግጅት Logo.

[በዕውቀቱ ስዩም፤ አማራጭየለሽ የነበረውን የተም. (ተንሳቃሽ ምስል መገናኛ ብዙሃን ተልክቶ) ጨክነው ኢቲቪን ባለመዝጋት ሲመለከቱት፤ (ግማሽ ሌሊት ስርጭት ዘመኑ ላይ የገጠመው ነው) እኩለሌሊት ላይ ቲቪው እራሱን አጠፋ ይላል።]

ከገጽማያ ግራ ወደ ቀኝ፦ ጋዜጠኛዎች መሳይ መኮንን፤ ወንድምአገኝ ጋሹ፤ ሲሣይ አጌና፤ እና ፋሲል የኔዓለም፨

፩) ቋንቋ አማርኛ እና ጠላቱ መንግስት (1983 – አሁን)

በ ኢህአዴግ. እና ብልፅግና አስተዳደር፤ በእየዘርፉ አምባግነናአዊ አፈና አለ። ጋዜጠኛነት እና መገናኛብዙሀን ደግሞ፤ አምባየተገነነበት ቁልፍ ዘርፍ ነው።
በመገናኛብዙሀንዎች እሚፈሠው ቋንቋ አማርኛ፣ ከህዝብ የማብሰልሠል አቅም እንዲሰልብ፣ በ ጆርጅ ኦርዌልአዊ ቀመር መርዝአማነቱ ተቀምሟል። በእዛ መሠረት የሆነው ይህ ነው። 1) ሁሌ አንድአይነት፣ እና ተደጋጋሚ፣ 2) ኢአንክሮትአዊነት (Being uncritical) እሚያበዛ 3) አጭር፣ 4) እንደገደልማሚቶ በሁሉም የታሰረ መሀናኛብዙሀን፣ ጭንቅላት እና ህዝብ ወጥ ተደጋግሞ እሚስተጋባ፣ 5) ለቅፅበት እማይዛነፍ፣ 6) ከፈጠራአማ ተግባቦት እና አመለካከት-ክወና (creative communication and thinking) ይልቅ፤ ብቻ-እሚፈለግ ፕሮፓጋንዳ እሚያመላልሥ፤ 7) አማራጭየለሽ፣ 8) እድገት እና ለውጥ እማያሳይ፣ 9) አቅም እና ባህሉ እንዲሻሻል እማይሰራለት፣ 10) ከመደበኛ አንደበት እራሱ የተለየ፣ 11) ጉልህ ዴንታ እና እንቅሥቃሴ ባይወልድም፤ በህዝብ በደፈናው እሚጠላ ነው።
ከእዛ ቀመር የተነሳ፤ በስነውሳኔው (Politics) እና ሌላም ስፍራ እሚደመጠው አማርኛ፤ የዜጋአዊያን (Civilian) ቁምአሸልብነትን ይፈጥራል፤ ያቆያል። ሌላ ወይም የቆነጀ ሩህአማዊነት (Consciousness) በቅድመንቃት በመፃረር ስልጣኔን እማያግዝ – ጭራሽ እሚያመክን – ነው።

በአጭሩ፣ በብዙ መንገድዎች፣ አማርኛን (ሌላ የሀበሻዎች ቋንቋዎችንም)፣ የመገናኛብዙሀን መሳሪያ ቋንቋዎች፣ መንግስት በጥብቅ ከጎዳቸው ዘርፎች መሀከል አንዱ ዐብይ ነው።
ይህ፤ አንድ በማድከም (Negative duty በመጣስ) ሁለት ደግሞ በህገመንግስትአዊ ግዴታው መሠረት ተንቀሣቅሦ በ አለማበልፀግ፤ (Positive duty በመጣስ) ተከውኗል። ከእዚህ በተጨማሪም፤ አማርኛ 1) ሲጀመርም የደከመ አቅም ስላለው፤ 2) ብዙ የመሻሻል ጥያቄዎች የተሸከመ ከመሆኑ የተነሳ፤ 3) መሳለመሣ እሚወዳጀው ስነእናኪነ (አርት) አብሮት ስለደከመ፣ 4) የእንግሊዝኛ ተኮር ትምህርት የዝማኔውን ጉልበት ከመሻማቱ እና ሲከፋ ከማስቀረቱ የተነሳ፤ እና 5) ወዘተርፍ. አመክዮዎች፤ አማርኛ የፈጠራ አቅም፣ እና ፍቱን ተግባቦትአዊ መሳሪያነትን እንዳጣ እና እያጣ በመጓዝ ያለ ሆኗል።

፪) በቀረአዊነት (ያግንታ) (Exception) በ ኢሳት. እለትአዊ ዝግጅት በኩል

ይህ የጠራ-ተግባቦት ዉድቀት ከብቦን እንዳለ፤ ተቃራኒ የሆነ አንድ ጉልህ እውነት (real) ኩነት ግን አለን። በዕለትከለዕት ተራ ግንኙነት ተገድቦ በአልጎመራ አቅሙ ለደንቡ ያክል ለመለስተኛ ልዉውጥዎች በእየመገናኛብዙሃንዎችአችን እምንገለገለውን የአማርኛ ቋንቋን ዓለም፤ በ ኢሳት. ትመ. (የኢትዮጵያ ሳተላይት ትእይንተመስኮት) አንድ ዝግጅትአቸው ላይ በተለይ በአንፃርአዊነት በምንም ሚዛን ቢመዘን ድንቅ እሚሰኝ አቅም አጊንቶ በልዩነት እናገኘው አለን።

በብቸኛነት በአለት የተገነባውን አምባገነንአዊ መገናኛብዙሀን እና ደካማ አማርኛ፤ የበረቱት ጋዜጠኛዎች እንደአዳኙ ማዕረግ ሆነውለታል። ይህ የ ኢሳት. ትመ. የመንግስት ተቃዋሚ ድምጽ ሆኖ የቆየ ነበር። በተለይ በሀገርአዊነት እና ፀረ-ኢህአዴግአዊነት ቀለም እስከ ቅርብ ቆይቷል። አሁን ደግሞ መወዛገብ እና መከፋፈል ደርሦበት አገልጋይዎቹ ከተሠነጠቁ እና ከተለያዩ በኋላ የብልጽግና-ዘመም መውጫ-ኬላ (outlet) ሆኗል። እስከእዛ ድረስ፤ የተጋጋለ የተቃውሞ የጋዜጠኛነት አገልግሎት ወይም ይልቁንም ትግል በውጭ ሀገርዎች እየተንቀሳቀሠ ሲከወን ቆይቷል። በእዚህ መርሐግብር ላይ እሚገኘውን የአማርኛ ቋንቋን፣ ማድመጥን እንመርምር።

ለእዚህ ኢላማ የይዘት (content) ፍሬጉዳይአቸውን ሳንነካ፣ በአማርኛ ቋንቋ ስልትአቸው ዙሪያ ብቻ እንዘዋወር። ማስተዋል እሚገባንን ሌላ ነጥብም እንግለጥ። የሙሉ የ ኢሳት. ዝግጅትዎችን አማርኛ ቋንቋ አጠቃቀም ይህ ዳሠሳ ከቶ አይሸፍንም። ሌላዎቹ የተቋሙ ዝግጅትዎች እምብዛም ከተሰለቸው ንትብ አማርኛ ልዩነት የላቸውም። ዳሩ፣ ዕለትአዊ ዝግጅት መርሐግብርአቸው ግን ተለይቶ እምንመለከተው ልዩ ጎን ነው።
ዕለትአዊ ዝግጅት በኢትዮጵያ እጅግ ወቅትአዊ የሥነውሳኔ ዐብይ ጉዳይዎች ላይ እሚደረግ የዐምደኛዎች (Columnists) ዉይይት ሲሆን፤ በሳምንቱቀናት (Weekdays) አልፎአልፎ ደግሞ የሞቀ ጉዳይ ካለ ለመሸፈን በሳምንቱማብቂያዎች (Weekends) ጭምር እሚቀርብ፣ ነው። ዝግጅቱ እንደሁኔታው ከአንድ ሰዓት እስከ ሁለት እና በመሰል ወቅትን ተንተርሶ ተለዋዋጭ ርዝመት እሚከወን የይዘት ፈጠራ (Content creation) ነው። መቼቱን በተመለከተ ማታ ሦስት ሰዓት ሲጀምር፤ ከኢትዮጵያ ዉጭ በተለያዩ ከተሞች እሚገኙ ጋዜጠኞቹ በከፍተኛ ፍቅር እና ጉጉትአቸው ከእያሉበት ሆነው እሚታደሙበት ነው። ዝግጅቱ፤ ለረዥም ጊዜ በገጽማያ (Screen) የቆየ ሲሆን፤ በ ኢህአዴግ. መንግስት ተባርረው እና ተሠድደው በእየክፍለዓለሙ የተሠደዱ ጋዜጠኞችም እሚቀርቡበት ነው።

፫) ቋንቋ አጠቃቀም

ዝግጅቱን ካስተዋወቅን፤ ወደ ቋንቋ አማርኛ አጠቃቀምአቸው እንሻገር። ጋዜጠኛ ሲሣይ አጌና እና መሳይ መኮንን በተለይ ነቅሰን በጠቅላላ እነ ፋሲል የኔአለም፣ ወንድምአገኝ ጋሹ፣ ጴጥሮስ መስፍን፣ እና ግዛው ለገሠን የስነዉሳኔ ዐምድአቸውን ወደአንድ አግጣጫ ለመጥረብ ሲወያዩ እንይ።
በተለይ የቀደሙት ሁለቱ፣ በአማርኛ ቋንቋ አጠቃቀም፣ ከአሁኑ ወቅት ወደኋላ ላለፉት ሁለት አመታት የቀረበ ጊዜ ያክል ብቻ እንኳ ካደረግኩት የቋሚ ታዳሚነት ትዝብቴ፣ ሁሉም የአማርኛ የምስል-ወ-ድምጽ መገናኛብዙሀንዎችአችን ቋንቋ አቅምን ልቀው፤ ከፍተኛውን እና በግልጥ እሚለየውን ጉልበትአማ አማርኛ ሲጠቀሙ ባለማቋረጥ አስተውያለሁ። ሌላ አቻ የድምፅ እና ምስል መገናኛብዙሀንዎች፤ ያነሠ፣ የተለመደ፣ ልዩነት የሌለው፣ ወዘተ. አማርኛን ሲያሳልፉ በጠቅላላው መታዘብ ችያለሁ። ስለእዚህ ዝግጅት በመቅረጫ የመዘገብኩት የዳግ-ምርምር (Research) መረጃ መረጃ የለኝም። መደበኛ ትዘብት (Observation) ግን በበቂ የከወንኩበት ነው። ዳሩ፤ ያንን ገሀድ ለመገንዘብ በቂ እለትአዊ ምርቶችአቸውን መርምሬ አለሁ።
በእዚህ መሰረት፤ ምንምን እሚለያቸው፤ ለሌሎቹ እሚያስተምሩት እራሳቸውም አብልጠው በመጠቀም እጅግ እሚልቁበት አንኳር የቋንቋ ፍሬጉዳይ ዝርዝሮች አሉ?
፩) ቅፅአዊ (formal) አማርኛ በዝግጅታቸው የተሻለ አቅም አለው። ይህ በሁለት መንገድ አለ። አንድም፣ የመከባበር እና ኩሩ እና ትሁት ስሜትን ገላጭ ቃልዎች ዝግጅትአቸውን እጅግ ቅፅአዊ ተግባቦት ያደረገላቸው ነው። ሁለትም፣ የአዋቂ እና ምርአዊ አጠቃቀም እንጂ የመንደር፣ መደበኛ፣ እና ተራ ልዉዉጥ ማጣቱ ነው። እራሱን የለየ እና በእዛ ያቋቋመ የቋንቋ የግሉ ቀለም አለው። ሦስተኛ፣ በተቻለ ሁሉ እንግሊዝኛን አለመጠቀም እና ሲያስገድድ ደግሞ ቃሉን በእንግሊዝኛ ተጠቅሞ በውይይቱ የማክበር ስሜት ተሸብበው በማክበር ቃሉን ለመተርጎም መሞከርአቸው ይገኛል።

ይህ ሲደመደም፤ እጅግ የዝግጅት፣ ሙያ፣ ሀገር፣ ገጽማያ እና ታዳሚ ማክበር፣ እሚሠሩት ስራ በመሆኑ የመጣ ይመስላል። በስራው አልፈለ ለራስ ክብርን የመታጠቅ፣ ምራዊነትን (Solemness) መላበስ፣ በደንብ ተዘጋጅቶ በግለትምምን (Self-confidence) መቅረብ፣ ባልደረባ እና አየሩን እንዲሁም ህገደምቡን (Protocol) በዘመነ መንገድ በስነምግባር በመከተል፣ ምናልባት ልምድም በማካበት፣ ወዘተ. የተነሣ፣ ቋንቋውን ቅጽአዊ አድርገውት አሉ። ቅጽአዊነቱ ደግሞ መልሶ ሸልሞአቸው አለ። እጅግ ትሁት፣ ሙያአማ፣ እማይበጣጠስ፣ አማርኛ አድርጎላቸው አለ።

መገለጥ ካለበት፣ ሌላም እይታ ይህን ወልዷል ማለት ይቻላል። ይህን መሰል የአቻ (peer) መርሐግብር በአማርኛ አለመለመዱም ተፅዕኖ አለው። ማንም በአማርኛ ያለ መገናኛብዙሀን ታዳሚ፣ የአቻ-ባልደረባዎች የውይይት በእዛ መልኩ ወጥ እና ቋሚ ሆኖለት ምርትን መገልገል አልቻለም። የእነእሱን ሁኔታ ያ የበለጠ ያጎላልአቸው አለ። ሲደመደም፤ አንድም እሚነፃጸር ዝግጅት ስለሌለ አንድም አቀራረቡ የባልደረቦች አቻ-ውይይት (Peer-discussion) ስለሆነ፤ ቅፅአዊነቱን እንዲሁ በቅፅ (form) ወይም አቀራረብ (structure) አልብሦታል።

አያይዞ ግን፤ የድባብ ሚና ወይም ተፅዕኖውን ቸላማለትም ይከብዳል። እርስበእርስ ድባቡን አክብረው እና ተከባብረው በዝግጅቱ ሁሉ ስለእሚያልፉበት ለቋንቋውም የራሱን ሚና ያ የድባቡ ቅጽአዊነት ዉለታ ያበረክትለታል። ድባቡን አክብረው መረጃ በመሰብሠብ እና በመዘጋጀት ስለእሚቀርቡ እና ለተደራሲ ያላቸው ክብር ትንሽ ስላልሆነ ነገረስራው ሁሉ ሰምሮ ለእይታ ይቀርባል። የተለያዩ ፍላጎት እና አቅምአቸው በእዛ ተጠያቂ ቢሆንም፤ ለእሚጠቀሙት ለቋንቋ አረዳድአችንም አንዱን የመጨነቅ እና የመተለቅ እድሉን እንደ ተያያዥ ቀዳሚእንደምታ (Impression) እሚያግዘው ነው።

፪) የፈሊጥ፣ ምሳሌ፣ ልኮት (References)አጠቃቀም ነው።

ቋንቋአዊ ተግባቦትን ማሠልጠኛ እና ተፅዕኖአማ ማድረጊያ ናቸው።
በተለይ መሣይ መኮንን፤ እጅግ አስገራሚ የቋንቋ ብቃትን ከእዚህ አንፃር እሚጠቀም ነው። በእየእሚከታተሉት ወይም እማይራራቁት አረፍተነገሮች ዉስጥ አስውቦ ፈሊጥ እና ምሳሌ መገልገሉ እጅግ ከፍተኛ የቋንቋውን እመርታ እሚያሰጎነጨን ነው።
ብዙ ቀንዎችን ዝግጅትዎቹን ዘግቦ መመርመር ብዙ የእሚያሳየን ቢሆንም እንደ ተራ ምሳሌ ጥቂት እንግለጥ። እእንዳልንው፤ ሰፊ ትዝብት እና የታዳሚነት ሂስ እንጂ የፀና ዳግምርምር (Research) ስላልሆነ በአጭሩ እንደ ጥቆማ እምናልፈው ነው።

ዝርዝርዎች፦

ከገጽማያው ግራ ወደቀኝ፦ ጋዜጠኛዎች ወንድምአገኝ ጋሹ፤ ግዛው ለገሠ፤ ሲሣይ አጌና እና ጵጥሮስ መስፍን፨

“ሱሪ ባንገት የሆነ እርምጃ ዉስጥ ከመግባት…
“ሰርግ እና ምላሽ ሆኖልአቸዋል…”
“አስራአንደኛው ሰዓት ላይ…”
“የእናቴ መቀነት ጠለፈኝ በእሚል ለማለፍ ማሰብአቸው….

(ሲሣይ መኮንን፤ ዲሲ፤ ህዳር 2013 ዓም.)

“ፍርደገምድል የሆነ…”

(ፋሲል የኔአለም ከአምስተርዳም ጥር 12 ቀን 2013 ዓም.)

“እንደወንድማማቾች አብረን መኖር እንማር። አለበለዚያ እንደሞኞች አብረን እንጠፋለን።”

(ጴጥሮስ መስፍን ከቪርጂንያ፤ ተመሳሳይ ስርጭት)

“ጆሮ ዳባ ብለው ከርመው ዛሬ…
“አውቆ የተኛን ቢቀሠቅሱት….
“መሪዎቹ የሞቱበት ህዋሃት. አፈር ልሦ እሚነሳ ይመስል በዉይይቱ ይሳተፍ ሲሉ…

(ጴጥሮስ መስፍን፤ ቪርጂንያ፤ ጥር 22 ቀን 2013 ዓም)

“ብልፅግናን የደገፉት ፀያፍ መፈክር አሰምተዋል። አንዱ ቦታ እርኩስ አንዱ ቦታ ቅዱስ መሆን አይገባም። አብንን ደግፈው የወጡም አቻ ፀያፍ መናገራቸው…”
“ምርጫ ቦርድ ጥርስ አውጥቷል እየተባለ ነው እንዴት ታዩት አላችሁ?”
“የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዳሸን የፈሉበት”
“ብርቱካን ሚደቅሳ ለአንዳንዱ ፓርቲ ሆደ ቡቡ ናት…”

(ሲሣይ መኮንን፤ ከዋሽንግተን ዲሲ.፣ ጥር 27 ቀን 2013 ዓም.፨)

“የባንዲራው ስር ቁማርተኛዎች…”
“ሁለት ሺህ የድጋፍ ፊርማ ሳያገኙ፣ እየተሻሻለ ያለ ምርጫቦርድን መተቸት መንጠራራት ነው።”

(ጴጥሮስ መስፍን፤ ከቪርጂንያ፤ ተመሳሳይ ዝግጅት)

“ሲጀመር ዘረኛ ግርዶሽ አለበት። ሀገር ሲያስብ እየለቀቀለት ይሄዳል።”

(ሲሣይ አጌና፤ ከዋሽንግተን ዲሲ. ተመሳሳይ ዝግጅት)
ወዘተ.

እነእዚህ እጅግ ቁንጽል አብነትዎች እንጂ፤ መርሀግብሩ በጠቅላላው እሚቀጥርአቸው የአማርኛ ፈሊጥ፣ ዘይቤ እና አባባልዎች፣ ቋንቋውን እርካብ ያስረገጠ አድርጎ ለታዳሚ ያቀረበ ነው።

፫) የማይሠባበር የአማርኛ ንግግር ፍሰት ነው።

ይህ በእርግጥ ትንሽ ግር እሚል ነው። የተፃፈ ማንበብ ካልሆነ በቀር፤ ብዙ አማርኛ እሚነግሩን የአደባባይ ሰዎች እንትንታ (Stuttering) አለብአቸው። ቋንቋውን አስብቶ አለመገልገል የተለመደ ማህበረሰብአዊ ገሀድአችን ነው። ሀበሻ ዝምታን መራጭ እና አምላኪ ብሎም በዘመንአዊ ሚዛን ያልሰለጠነ በመሆኑ በደንብ መናገር እና ተግባቦትን አትግቶ መጠቀም ባህሉ አይደለም። ቢያንስ ይገልጠኛል እማይለው ነገር ነው።

በኢሳቱ. ዝግጅት አማርኛን ያለማቃሠት፣ ያለማማጥ እና ለመግለጥ አለመቸገር፣ ሲጠቀሙት እሚያሳዩት ቀላል ያደረጉት እና የተካኑት የተግባቦት ስኬታቸውን ነው። አማርኛው ስለእዚህ በቀላሉ እሚያፈስስላቸው ነው።

እንዳልንው የዘመኑ አማርኛን ስለነተበ ለምርጥ ግንኙነት ባለማቋረጥ እየለፈለፉት ለመቅጠር እጅግ ትልቅ ቤትስራ ነው። በቀጥታ ዝግጅት ቀርቶ፣ በፅሑፍ እንኳ ቋንቋውን መግራት ለብዙ አድካሚ እና ሲሣካ ያልተለመደ ነው። በእነእዚህ ጋዜጠኛዎች ከእሚቀርበው የምርአዊ የዝግጅቱ ይዘት እና ፈጣን ዳሠሳአቸው አንፃር ስለእዚህ የበዛ ቸብቸብ እዚህ ሁሉን አማርኛ አድማጭ ያስገድድ አሉ።

፬) በአንፃርአዊነት ሠፊ መጠነቃልዎች (Vocabularies) እና የቃልዎች ፍካሬአዊ ፍች አጠቃቀም አልአቸው።

የለመድንው መደበኛ አማርኛ የአመለካከት አቅምን ማቆርፈድ ተሳክቶለታል። ምክንያቱም እጅግ የተለመዱ ቃሎች ካልሆኑ ማንም አይናገራቸውም ማለት ይቻላል። የብዙ ቋንቋ ተናጋሪ ስብጥር ህዝብ ከመሆናችን፣ የመንግስት እማይዛነፈው መገናኛብዙሀን ዋናው የህዝብ ፍጆታ በመሆኑ፣ እና ቋንቋው ወደጓዳ ተብሎ የዳግ-ምርምር እና ትምህርት ቃሎችን ካለመጠቀሙ የተነሣ፣ ወዘተ. የዕለት ከዕለት ተግባቦት እንጂ ብዙም ውስብስብ ነገር አይገልጥም። “ምንማለት ነው?” እምንለው አዳዲስ ቃልዎች በእየ መቼቱ (Spacetime) አይገጥሙንም።

ከእዚህ ሀቅ አንፃር፣ የ መርሐግብርአቸው አቅም እማይከፋ ነው። ሁሌ የተለየ ቃል የለም፤ በእርግጥ። የሚያብረቀርቅ ስኬትም እዚህ የለም። ግን፣ በአንፃርአዊነት ያላሰለቹ ቃሎችን እና እጅግ ባልተራራቁ ሁኔታዎች ደግሞ እምብዛም የማይሰሙ ቃሎችን በመገልገላቸው፣ ይህ አገላለጥ ሊቀርብላቸው እሚችል ነው።

፭) ቀጥተኛነት ያለው የቋንቋ ውል ወይም ጥራት።

የአብዛኛው መደበኛ አማርኛ ከፍተኛ የተግባቦት ደንብ መጣሥ እና የሰዋሠው መሠባበር ያለበት ነው። እንደ ‘ስኪዞፍሬኒያ’ በሽታ ታማሚ፤ አቅም ያለው እና ስነምጣኔአዊ (economical) ልውውጥ አንለውንም።

ለምሳሌ፤ “ማለት የፈለግንው፣ መንግስት…ሰላም ያስከብርልን… ካልሆነ እኔ ምን ግራ ይገባኛል ነው ማለት የምፈልገው።” መሰል አረፍተነገሮች እጅግ የአማርኛ አሳዛኙ ገሀድ ናቸው። በመደበኛ አማርኛአችን፤ አረፍተነገሮች ቢመረመሩ ሠዋሰውአዊ ችግሮችአቸው እንደተግበሰበሱ አሉ። እንዲሁ ልብለልብ በመግባባት እና ባለመጨነቅ እምናልፈው የአማርኛአችን አንዱ ዕብድ ህጸጽ ነው። የ ኢሳቱ. ዕለትአዊ ዝግጅት ግን፤ በእዚህ ዘርፍም መበርታት ይሻል። አነረፍተነገርዎች ተጀምረው በተዛባ መንገድ ሲቋጩ ጆሮ ቆንጠጥ አድርገው እንደ ቀረው መገናኛብዙሃን አይከነክኑም። የቅርጽ (Structure) ብላሽ አይደሉም። አንድ ሀሳብ በአንድ አረፍተነገር ተጀምሮ በእዛው ሳይበላሽ ይሸመጠጣል። እንጂ፤ የቋንቋው አጠቃቀምአችን ድክመት ማሳያ የሆኑት ተዘውታሪ ማምለጫዎች እነ “ማለቴ” “እምልህ” ወዘተ. መሰል እግሬአውጭኝታዎች (scapegoat) እዚህ አይገጥሙንም።

የቋንቋው ተስተካክሎ አለመቀጠርን የተከተለ መዝረክረክን በልዩነት ካላሳዩን ደግሞ ያም ተቆጣሪ ማዕዶትአችን (Transformation) ነው።

፮) የፕሮፓጋንዳ አንደበት መጥፋት።

ከየትኛውም መገናኛብዙሀን የቋንቋ አጠቃቀም የአመል አቅጣጫ የተፋለሰ ስኬት አለው። በብዙ ሌላ መውጫዎች ወደ ጆሮአችን እሚመጡ ጋዜጠኛዎችአችን የካድሬ ቋንቋን እያስተጋቡ እንደሚያሰለቹን እንደሆነ ይታወቃል። ተቃዋሚ ቢሆኑ እንኳ የጠራ አማርኛ አማራጭ ስለሌ ጭምር ተገድደው ለተለመደ ፕሮፓጋንዳ ቋንቋ ይዳርጉን አሉ። ለምሳሌ፤ “የእንትን…ስራ ተሰርቷል። የእንትን ስራ መሠራት አለበት…” ወዘተ. ኢህአዴግ. ሊወድቅ ሰሞን ያሰለቸ አገላለጽ ነበረ። በብልጽግና ደግሞ፤ “ተሞክሮ ተወስዶበታል” “እንደ ልምድ ይጠቅመናል” “ተምረንበታል” በእየጉራንጉሩ እሚደመጥ የሆነ ነው። የመንግስት ማታለያ አንደበት የህዝብም የመገናኛብዙሀንም ሲከፋ ቢከፋንም የስነጥበብም ጭምር ናቸው። በእየስፍራው ሰዎች ተመሳሳይ አገላለጥ እንጂ አዲስ ስልት ወይም ቃል እንኳ አይጠቀሙም።
ኢሳት. በሌላዎቹ ዝግጅቶቹ ጭምር – ማለትም እንደ ተቋም – ባይሳካለትም፣ በእዚህ ዝግጅቱ ግን ይህን ሰብሮታል። ከቶ በተለመደ ትርክትአዊ መስመር የተጠመደ ህዝብ እንደእሚያወራው የራሱ ድባብ ያመው አማርኛ ከመጠቀም በደግ መጠን የበለጠ አቅም ያለው ሁኔታን ፈጥረዋል። የእራሱን የቋንቋ ድባብ አንጥፎ እሚተኛበት መርሐግብር በመሆን እራሱን አኩርቶ አለ።

፬) መደምደምያ

ሲጠቀለል፤ በሙያአዊነት፣ ቁምነገር እና ስሜት እሚቀርቡበት የአማርኛ ዝግጅት በመሆኑ ትልቅ ቋንቋአዊ እመርታን እሚያስመለክት አማርኛ የተሻሻለበት መርሐግብር ነው። ቢያንስ ከየቱም መገናኛብዙሃዎችአችንን የአማርኛ አቅም ከአለጥርጥር የተሻለው ነው።
ከመከፋፈልአቸው በኋላ የብዙዎች ተዋዳጅነት (Fan-hood) በ ኢሳት. ቢቀንስም፤ ዛሬም ግን ስለ አማርኛ ቋንቋው ዉብ አቅም ተመልካችነቴን ማቋረጥ አልችልም። ጥርጥር የለውም። ትልቅ የሙያ፣ ትግል እና ስሜት ትጋት መርሀግብሩን አስውቦት ለዛሬ አብቅቶታል። ከቋንቋ አንፃር ደግሞ፣ የእራሱን ስኬት እጥፍድርብ እንዲሆንለት አድርጎታል።
የዘመነ አማርኛ ብዙ ችግርዎች የታከሙለት ነው። የበዛ ልዩ-ልሂቅአዊ (Esoterica) ወጥመድዎቹ እና መሠረትአዊ-ዝግመቱም የተሸነፉለት ነው። የዘመነ ፍሬነገርም (Substance) መሸፈንን ያኔ ሲለምድ ቋንቋው ወደ ፳፩ ኛው ምዘ. መጣ ማለት ነው።

እስከእዛ፣ ስለስልቱ መንግስት ቋንቋውን በአፍጢሙ ዘርፍጦት በድብቅ ይስቅ ይሆናል። እንደማህበረሰብ፤ ማለት ይቻላል መደበኛ ልዉዉጥአችን ሁሉ ዝግመተለውጥ አጥቶ ቀርፋፋ፣ አቅለሽላሽ እና አመለካከት-ገዳቢ አድርገንው ይሆናል። እንግሊዝኛ እና ትምህርት፤ አማርኛን ከበለጸገ አእምሮ መገንቢያነት ለመከልከል ብለው አቅሙን ዕለትአዊ መግባቢያነት ዙሪያ አጥረው ቸንክረውት ይሆናል። ስነእናኪነም (Art) አንቀላፍቶ እህቱ አማርኛን አላግዝ ብሎት ይሆናል። ጭራሽ ከእነ ዳኛቸው ወርቁ እና ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን አማርኛን የተረከበ ስነእናኪነጥበብ አልመስል እንኳ ብሎ የወረሰ ቋንቋውን ክዶት ዘወትር-ተወቃሽ እና ሁሌ-ተሰልቺ እንደሆነ ይሆናል። መንግስትም ተሳክቶለት ህዝብም አሸልቦ የታፈነ የሥነውሳኔ አሽከር ቋንቋ ብቻ ተደርጎ ይሆናል። እነ ስብሃት ገብረእግዚአብሄር እና ሀዲስ አለምአየሁ በፊትም እንዳሉት ሳይዘምን በመቅረቱ፣ የመሀከልሀገር አማርኛን አሁን ባለበት ሁኔታ ለብቻው አሽከርነት ቀጥሮ ለመርቀቅ ይከብድም ይሆናል። የአማርኛ የዝማኔ ጥያቄውም ስልጣኔን አላስቀድም ኋላቀርነትን-ሙጥኝ ባሉ ተጠልቶ የተከለከልንው ብሔርአዊ አንድ ዕድል ይሆናል። ጋዜጠኛነት አከርካሪቱ ተሰብሮ በመናኛ አቅም እንዳሰለቸ እና ሩህአማአዊነት፣ አመለካከት-ክወና እና የመግለጥ ነፃነትዎች ላይ ቋሚ ፈንጂ ሆኖብን ይሆናል። ዳግምርምር፣ ምሁርነት እና ትምህርት ከስልጣኔ-አባልነት አጥር ዉጭ ምንዱብ’ አማርኛን ዘግቶበት ይሆናል።
በሁሉም አግጣጫ የጭለማ-እሾኽ የከበበው አማርኛ፣ ታሪኩን ዞሮ ሲያይ አብዝቶ በእሚጠላው ይህ ዘመን መሀከል ግን፤ እንደ ቴዎድሮስ ገብረዓብ የስነጽሑፍ ጀብዱአዊ(Adventurous)-አማርኛ፤ ዘመኑ የ ኢሳት. ዕለትአዊ ዝግጅትን፤ ጥቁር ዝይ (Black swan) አድርጎ አጊንቶት ስለልዩነቱ ይኮራበት ይሆናል። ዕለትአዊ ዝግጅትን፤ ስለእዚህ ዉለታአማ እና ዉሮታአማ ልዩነት-ፈጣሪነቱ፤ ከበአድ ሀገር እየተንቆረቆረልን ሲያረሰርሰን ልንሸልመው እና በትልቁ ጫር ልንል ግድ ይለናል። ስለጠቢአችን (Our future)፣ እና ስለእሚጨነቁ ከተጨነቅን እነእዚህን የአማርኛ ዐምድአዊነት ፈርቀዳጅ ታሪከኛ አምደኛዎች ቆመን በጭብጨባ እናመስግን፨

By Binyamhailemeskel

Hey there! If you want to know about me, I just like fun, commonsense wisdom, and human love. Let us live a bright today changing tomorrow into brighter.
Regards,

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s