Categories
ሥነዉሳኔኛ (About Politics)

ከተምኔትዮጵያ ወደ ለአንድሠው-ደራሽ-ዮጵያ ወይም የዘመንአዊ ኢትዮጵያ ሥልጣኔ አንድ አላባአዊን ስለማስወጠን

About revisiting the perfectly (utopian) understood Ethiopianism to include what it lacks – incorporation of and care for the last Ethiopian, i.e., Ethiopia. A country is like exactly how the weak and vulnerables are.


bY ቢንያም ኃይለመስቀል ኪዳኔ፤ ጥር 10 ቀን 2013 ዓም.፨


እዚህ እሚኖረው እንኳ በአረጀ ነሲብአዊነት (Archaic intellect) ነው። “ባወጣያውጣውአነዊት” መገለጫ የህላዌ ትድድር (management of existence) ዘይቤ (Style) ነው። እንጂ እንደ “ሀገር” አይኖርም። ከቶ። (ቢሆንም፤ ሲቋጭ ይህ ጽሑፍ እንደ ሀገር መኖርን ለመጸነስ አንዷን ቁንጽል አዋጭ’ አላባአዊ (Element) ያሳየን አለ።)

ወሳኝ ወይም ኢ-ወሳኝ ገሀድዎችአችን – በተለይ በእዚህ መወጠኛጽሑፍ እንደእምንመረምረው አንድ የኑሮ-ዘይቤ“አችን” ያሉ ነውታዎችአችን (Our claims) – በ ተደራሽ-ስድር-ማህደር አይመዘገቡም አይገኙም፤ እሚለው አንዱ የእዛ በእርጅና-መቅረት-እይታ አብነቱ ነው። ያም በዘመንአዊ ዛሬ ስለእማናልፍ ዘመንአዊ ነገን ስለማንጠብቅ ነው። ብቻብቻ (Anyways)።


ለብዙጊዜ፣ ብዙ ጥበበኛዎችን በልተን፤ ያው በጨለማ አለን እና ሳንዘምን በደፈናው እያለፉ ከእማንመዘግብአቸው ወይም እዚህ እንደምንሞክረው ከእማንወያይአቸው ልውውጥዎችአችን እና የሀገር ስነልቦናአችን መሀል በእየተገኘው አጋጣሚ እንደተለፈፈ ያለው ግን ያልጠራው “የኢትዮጵያአዊነት መገለጫ” እሚሰኘው ዐውደ-ሀሳብ አንዱ ነው።


አብሮታ፣ መከባበር፣ አስተናጋጅነት (hospitality) ወይም ተቀባይነት፣ እንጠጣ-እንብላ፣ ቤትእንግባ፣ እንግዳ ክቡር ነው፣ እንዲሁም እንዲያእንዲያ ያሉት ቀኝአዊ የኢትዮጵያአዊነት ማብራሪያ ናቸው። ያንን በተርታ ትረካው ከመደጋገሙ ውጭ፤ ያ ኑሮ-ባህል እንደእሚገኝብን ለማረጋገጥ በመሰረትአዊ አንክሮትአዊ (Critical) ሀሠሳ እንጠይቅ። ያሳዝነናል። በዘመንአዊ ደረጃ ባህሉ አለመኖሩን ለማወቅ በመጨረሻ እንገደድ አለን። ያ ነውታአችን (Claim) እዉነታ (reality) አይደለም። ተምኔትዮጵያ ሆኖ እናግኘዋለን።

ይህ ባህል በዝማኔ የሌለ በእርግጥ አንዳንዴ፣ ጭራሽ የለየለት ተምኔትዮጵያ ብቻ ነው። ተምኔትዮጵያ፤ ማለት ከእሚከተሉት ሁለቱ አንዱ ወይም በጋራሁለቱም ነው።
አንደኛው፣ የኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያአዊነት ምናብቴአዊ (Fantasy) አረዳድ ነው። እኛ ኢትዮጵያአዊያን እና ሀገርአችን ሁሉ ያለን፣ ሁሉን ጥንት የከወንን እና ያሸነፍን ማለትም የድሮ ሥልጣኔን እስከ ሰማይ ጥግ ሠልጥነን የነበርን፣ ከቶከቶ ቅኝያልተገዛን፣ ደግደግ ባህል ያጥለቀለቀን፣ መልካም የሆንን፣ ወዘተ. እያልን ከታሪክ እና ባህል ኩነትዎች መርጠን እየመዘዝን እምናወራቸው ግለ-አንቆለጳጳሽ ነገርዎች ዉስጥ ሠምጠን የምቾት-ሰጭ አተያይ እና ትርክት ተከታይ ሰዎች በመሆን በተጨባጭ እና ዛሬ ግን ኋላቀርም ነን እሚለውን ሀቅ የዘነጋንበት ስት-አረዳድአችንን ገላጭ ነው። ማለትም፣ የእምንገልጠው ታሪክ/ባህል የለንም ሳይሆን፣ የቅዠት ጎጆ አድርገንው ዉስጡ ግለ-አታሎት እየፈጸምን እምንኖርበት አድርገንዋል ወይም እምናደርገው ክፍል አለን እሚለን ነው። ቢሆንም እንኳ፣ “ታላቅ የነበርን”/ “ባህለኛዎች”፤ ዛሬ አብዝቶ ተምኔት ወይም ምናብቴ፣ እንጂ ገሀዱ አይደለም፤ ስለእዚህ ተምኔትዮጵያ ነን። ሁለተኛው፤ እንዲሁ ተመሳሣይ እሚሆነው ዝብ-አገነዛዘብአችንን ስለእሚገልጥ ነው። እዚህ ደግሞ፣ ኢትዮጵያ አላት እያልን እምንሳሣተው የሌለንን ነው። እንደ ዘመንአዊ ሀገር ገና አልተመሰረትንም። ታዲያ ብዙ እንዳለን እንናገር፤ ይልቁንም እንወሸክት፤ ከእዛ እንረካ አለን። ዝማኔ ወንፊት ከሆነ ግን ያ ሁሉ ወንፊቱ እሚያንጓልለው ቆሻሻ ሆኖ እናፍራለን። (በኋላ በእዚህ ጽሑፍ እምንመለከተው ይኽኛውን ተምኔትዮጵያ ነው። ያም፤ በበቂ ወይም ምንምአይሌ ደረጃ ያልመሰረትንውን አንድ መገለጫአችን እምንለውን “ባህል” ብጤ ነው።) ሃሳቡን ግን ለማጉላት ለምሳሌ እንቀንጭበው። አዛውንትዎች እንደማህበረሰብ እናከብር አለን፤ ብለን እንኩራራ አለን። ዳሩ፤ እነሱን በባህል ብናፍር ማለትም ብንወድድም በዘመንአዊ ማህበረሰብ ሚዛን ያ ዘይቤ ሲታይ ግን ብዙ አዛውንትዎች እሚኖሩት በእየመንገዱ ዳር ወዳድቀው፣ መሀከለኛ-መደብ (middle class) ሆነው ካገለገሉም ካለ በቂ ማህበረሰብአዊ ዋስትና ጥቅማጥቅምዎች ነው። አንድ ቢንያም ዘ ሜቄዶኒያ ከፈጠርንው መንግስት የተሻለ ለአዛውንትዎች አለሁባይ ነው። በተመሣሳይ እንግዳተቀባይ ነን ብለን ብንኩራራም፤ ከገጠር የመጣ ቤተሰብ እንኳ በከተማዎችአችን አይከበርም። በሀገሩ፤ ሀበሻ ባደገ ሀገር እንደእማይስተናገደው እንደ ባዕዳን (alien) ይስተናገድ አለ። በብዙ መንገድዎች፤ እንደሀገር ነን እምንልአቸውን በጎ ነገርዎች እንደ ተምኔትዮጵያ “ለራስአጭበርብር” ፍፃሜ እንጂ እንደገሀድ ብንፈትሽ የማናገኘው ነው።
በጥቅላላ፤ አንደኛ ዛሬ መንገድዳር ወደቅን እንጂ ታሪክአዊ ፍጽምና የተላበስን እኛ ምርጥ ነን እና ሁለተኛ ዛሬም ይሄይሄ-አችን ዛሬም ምንምአይወጣለት፤ እናም ያልጎደለን ነን፤ እምንላቸው በሁለትበኩል የተሳለ ብሔርአዊ ቅዠት እምንስማማብአቸው በጎ ጎንዎችአችን ናቸው እምንል ከሆነ፣ የ“ኢትዮጵያአዊነት”አችን ላይ ኩራት ሳይሆን የ ተምኔትዮጵያ በሽታ ይዞን አለ ማለት ነው። ገሀዱ፤ ኢትዮጵያ ዩቶጵያ አይደለችም። የሦስተኛው አለም ጅራት ናት። ያንን ግን በመሠልጠን መለወጥ ይቻል አለ። አንዱን የእዛ መሠረት – ማለትም ጭብጥአችንን – በእይታ እንጨልፍ።


ተምኔትዮጵያ፤ (Uto-Ethiopia)፤ አእምሮዕጥበት ለተፈረደፈበት ትውልድ የተመቻቸለት የአንጎል በሽታ እንደሆነ ከገለጥን፤ ከላይ ያልንውን ይህንን “የመተሳሠብ ባህል” ነውታ (Claim)ን ባይኖርም ካለን እንፈትሸው።
የመተሳሠብ፣ መጠራራት፣ እና በችግር የመደራረስ ባህል እንዳለን ይዘከር አለ። ሲጀመር፤ ዋናውን የእሱ ጉዳይ እንደ ሦስተኛ እንየው እና ሁለት ችግርዎችን ይህ እራሱ ተጋፍጧል። አንድ፤ አሁንአሁን ቀንሷል ይባላል። ሁለት፤ ዘመንአዊ ስልጣኔ በጥፍሩ ረግጦ እጅግ ጥቂት ብንወሳሠብም አብሮ መገለጫአችን እየተወሳሠበ አላደገም። ዛሬ ላይ ህይወት በእዛ ባህል የቆዩ መገለጫ መንገድዎቹ ብቻ ተገልጦ ስኩ ይሆን አለ ወይ? ቢያንስ የ፳፩ ኛው ክዘ. ዘመንአዊ አኗኗር፣ የቀደመውን መገለጫአችንን እንደተለመደው እንደልብ ለመከወን የተቀየረው ኑሮዘዴ (Lifestyle) አይፈቅድም። ስለእዚህ ለምሳሌ፤ የስነስርአት (system)፣ የህግ፣ የማህበረሰብ፣ ቡድን፣ ክበብ፣ ወዘተ. መስተጋብርዎችን ይዞ ባህሉ አብሮ ስላልዘመነ፤ ለምሳሌ በስራ እና አኗኗር አፍታየለሽነት (Busy-ness) የተነሣ የባህሉ አብሮ አለማደግ እና በእዛም የመቀነሱ ነገር ተከስቷል።


አያይዘን ወደ ዋናው ውይይት እንቀጥል። ምንምን ችግርዎች በእዚህ ባህል“አችን” አሉ? አንደኛ እንብላም፣ እንግባብም፣ ያለኝን-እንኩም፣ ወይም ሁሉንም ሁሉንም መሰልዎቹን እሚገልጠው፣ አንድ ነገር ቢኖር ቅጽበትአዊነት እና ኢ-ዋስትናአዊነት ነው። የአጋጣሚ ልማድ መገለጫ እንጂ ዘላቂነት ያለው ጥቅም አዙሮ ለአስተናጋጁም (ጋባዥ) ለተስተናጋጁም እሚሰጥ አይደለም። መተማመኛ ወይም ዋስትና የሌለው እና ወደስነስርአትነት ያልታቀፈ ልማድ በመሆኑ ትልቅ ዘመንአዊ ፍሬጉዳይ አይሆንም።
ሌላው፤ ብሔርአዊ ይፋነት ወይም ቅፅአዊት (Formality) ያጣ ነው። እንደ መንግስት እና እንደ ማህበረሰብ፣ ለሁላችን እሚሆን የእዛ ብሂል አቻ ስርአት፣ ደንብ እና ህግ የለም። ዝማኔ ያጣ ባህል ባለመሆኑ፣ ወደ ዝሙኑ ማንነትአችን አልተሻገረም።

በትልምአግጣጫዎች (Policies)፣ ህግዎች እና አፈፃጸም አይገለጥም። መከባበርአችን፣ መተባበርአችን፣ ወዘተ. ለአንዳንዱ ሳይሆን ለሁሉ ዜጋ መክፈትአችን በገሀድ አላተምንበትም በአስተዳደርአዊ እና ጋርዮሽአዊ ስርዓትአችንም የለም። በትልቁ ዣንጥላአማ መገለጫችን፣ የሌለ ብሂል ደግሞ መደበኛ ሆኖ በዘመንአዊ አኗኗርአችን እማንዳሥሰው ነው ማለት ነው።
የአዳም ዘረፍጥረት (Species) ህይወቱ ገደቡ ነው። ህይወትን ማን ይገልጣታል? ለእያንዳንዱ ልዩልዩ ነች። በእዛ ስምጠት ገደብ ሳታበጅ እንግዳተቀባይነት፣ አለሁልህባይነት፣ አክባሪነት፣ ወዘተ. ካለ፤ ያኔ ብቻ ሀገርአዊ ባህሪ ያልንው እዉነትም ይሆንልን አለ። በማስረጃ አስደግፈንዋል እና።

ስለእዚህ፣ በአንዳንድ ልማድዎችአችን መተሳሠብ ስላለ በህይወትአችን ሁሉ ያ አለ ማለት አይደለም። ይልቁንም፤ በዘመነ ሚዛን አንደፋም። ባዶ ስለሆንን እንንሳፈፍበትአለን። የምርም፣ እምንተሳሠብ እና በመቻቻል እና መቀባበል እማናኮራ ነን ማለት ነው። የስነዉሳኔ (Politics) ሂደቱ፣ የፍትህ ማጣቱ፣ መከፋፈል እና ጎሪጥእይታው፣ አሰልቺው ተረኛነት የተባለው ስልጣን-ብልግና-ድግግሞሽ፣ እልፍእልፍ ንፁህ እየተገደለ ጭጭታው፣ ድህነት ቅነሳ አልሳካ ማለቱ፣ ገሀድ የወጣው በቀላሉ እሚከወነው ዘመንአዊ ስሪቱ የቅኝወረራው ስኬት፣ ሁሉምሁሉም ብቻ አለመዘመንአችንን እና ይህን ብሂል የተምኔትጵያ በሽታ ያደርግብናል። ነገ እንዲርበን የምግብ ዋስትና ሳይኖረን፣ ምርትአማነት ሳያስጨንቀን፣ አየርንብረት ቢዛባስ ግድሳይለን፣ የእሚወለደው ትውልድ የመቀንጨር ዕዳ ዴንታ ሳይሠጠን፣ ማህበረሰብአዊ ደህንነት (Social Securities)፣ የድሀድሀነት ድጋፍ፣ ወዘተ. ምንም ሳያስጠብበን፣ አንድ እንጀራ አጋርተን አንድ ቀን አሳድረን ልዩ ህዝብ ነን ብንል እዉነትም ተምኔትጵያ ነን።

እምናስበው በጎ ጎን፣ መንገደኛን ከማሳደር፣ ዉሃ ከማጠጣት፣ ለጠፋው መንገድ ከመጠቆም፣ አንዳንዴ እጅግ ሲዘገይም ቢሆን ገንዘብ ከማዋጣት፣ ወዘተ. ብዙም አይዘልግም። ይህ ግን ዋና የብሂልአችን መገለጫ ነው መባል ያለበት፣ የስነሥርዓት አገልግሎት ወይም ነፀብራቅ ሲሆን ነው። እንደ ዋናው ማህበረሰብአዊ መገኛ ሀቅአችን (fact)፣ እኒህን አመልዎች ማስመልከት አለብን። አንድን ግለሰብ፤ አለአንዳችቅድመሁኔታ፣ ማክበር፣ መውደድ፣ መቀበል፣ እንደእራስ መመልከት፣ ወዘተ. ስንጀምር፣ ያ ያልንው ባህል ዘመንአዊ ነፀብራቁ ያኮበኩባል ማለት ነው።
ስንኖር፤ በአንድ ጉርሻ፣ በአንድ በሞቴ ይቺን ደረጃ ሳይሆን፣ በህይወት ደረጃ እምንገልጠው አመለካከትአችን ከሆነ፣ ይህን ከተምኔትጵያ ወደ ዘመንአዊት ኢትዮጵያ እምንገልጠው ራስአችን ሆኖ እምናገኘው ነው።


ለአንድ ሰው ደራሽ አመለካከትን እናዳብር። ሁሉን የዉሸት ምቹ ቀፎ ተምኔትአዊነት ትተን፣ አንድ ዘመንአዊ ሀገር እንገንባ። አንድ ሰው እንኳ ቢቀር እንዋጋለት አለን። እንደ ሰው በክብር እናኖረው አለን። ይህንን በብሂልአችን ካልን እና በተግባር ከከወንን፤ ያኔ ዘመንን።
ይህ የእራስአችን፤ የእያንዳንድአችንን እድል ማበልፀግ ነው። በቀኑ መጨረሻ፤ የስኩ እና ብልፁግ ማህበረሰብ ምስጅት (recipe) ነው። እኛንው እሚገነባው፤ ለአንድ የመጨረሻው ሰው እንኳ ደራሽ ለመሆን እምንከፍለው ዋጋ ነው። የመጨረሻውን ሰው እምናስተናግድበት መስተንግዶ፣ የተሻልን ዜጋዎች ነን እምንልን እምናስተናግድበትን መንገድ አብሮ ይገልጣል። በአንድምሌላም መንገድ።


“ለመጨረሻው-አንድሰው-ደራሽ” ዝማኔ በቀረ፤ ይህ የታላቅነት ባህል ቱሪናፋ እንጂ ገና እንዳልተጀመረ እሚያስረዱን ብዙ ማስረጃዎች እንዳሉን ባለመጨነቅ በቅዠት እምንንከራተት ነን። ስለ ሁሉየተዋጣለት ኢትዮጵያአዊነት ከእምንዘከዝክአቸው የቅዠት ቅርፊት እራሳችንን ስንልጥ፤ ከዘፈቀደ እና ትውፊት የግራመጋባት ጦስ ተቅበዝባዥነት እንባንን አለን። እና፤ ለዘመነ ኑሮ፤ ለሀገር መኖር እንጀምር። ስለእዚህ ዳግ-እንጠይቅ። የተረሳው፤ ከሁልአችን ለመጨረሻው አንድሰው ደራሽ ለመሆን ስንነሣ መቼም ቀድመን መጠየቅአችን አይቀርም፦ “ያ የመጨረሻው ሰው ማንነው” እንበል? እያንዳንድአችን፨

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s