Categories
Uncategorized

የህንፃ ጥላ እና የህፃኑ ችግኝዎች፡ አንድ ቁንጽል ኪነህንፃአዊ ግርምት

An attempt of asking how an architectural structure’s shadow infringes property right by blocking sun rays is treated.


bY ቢንያም ኃይለመስቀል ኪዳኔ፤ የሆነ ሰሞን፤ በርግጠኝነት 2013 ሲጀማመር አካባቢ፨


ሙዐዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት፤ እራሱ እንደ ግርምት እሚታይ ወግ ደራሲ፤ አንድ ወጉ የታሪክ አተረጓጎም ፍልስፍናን እሚያረሠርስ ዐብነት የነበረበት፤ የአክሱም እና ላሊበላ ኪነህንፃዎች፤ አለምን እሚያስገርሙት በቅርጽአቸው ብቻ ሳይሆን ከቶ ባልተገኙት የተጠረቡት የድንጋይዎችአቸው ቆሻሻዎች የትም በምርምር አለመገኘት ማለትም የጽዳት ጥንቃቄ ምስጢር እና ግርምታአቸው እንደሆነ ነግሮን – ታላቅ ነበርን ትልቅ እንሆንአለን ተራ ፕሮፓጋንዳ (የህልምቅቤ) – እንጂ የከተማዎችአችን ቆሻ መስጠት እንጂ ማስወገድ የእማይችል አገነባብ ባህል ከእዛ ታሪክ እንደእማይከተል ይናገራል።
ይህን ያነሳሁት ስለሀውልትዎቹ ለመናገር ነው። ሌላም ያስተማሩን የተባለው የኢክዊኖክስ አረዳድአቸው ነው። ሮዳስ ታደሠ (ሊቀምሁርዎች) በዝብ-ህፃጼ አመክንዮ አገላለጡ እንዳቀረበው፤ የግዕዝ ፊደልገበታ የኢክዊኖክስን ቁጥርአዊ ዉሂብ (data) በሩቁ ቀምሮ [ሰባት ሆሄያት ከሃያስድስት ፊደልዘርዎች ጋር መቶሰማኒያ ይሆናል፤ ያም ግማሽ አመት ነው፤ ያም ፀሀይ 12 ሰዓት ወጥታ 12 ሰዓት እምትጠልቅበት ብቸኛው የአመቱ አጋማሽ በጠቅላላው ሁለት ኅዋአዊ ትእይንት (መስከረም እና መጋቢት ዉስጥ)] አለ፤ ስለእዚህ ግዕዙን ፊደልገበታ የተዋሠው አማርኛ ምንም አፋልሶት ቁጥሩን በማብዛት ቢገኝም መሻሻል ግን የለበትም እንዳለው፤ ይህ የፀሐይ መውጫመግቢያ ነገርን እያዩ እሷን እረፍት መንሳቱ እነእዛም ሀውልትዎች ላይ አለ።
እነእክሱም እና ላሊበላ ሀውልትዎች፤ ጸሐይን እሚመለከቱበት የተለየ ልዩልሂቅአዊ ኪነህንፃአዊ (esoterica architecture) ጥበብ እንደተሸከሙ ይነገራል። ብዙ አይገርምም።
ወደግርምት ግን ያመጣል። ፀሐይ የሰው ልጅ የጋራ ሀብት ብትሆንም፤ እንደ ሙዐዘ ጥበባት ወግ ጭብጥ፤ እምታከራክርበትን ስነመሣ (analogy) አዙሮ ግን፤ በኪነህንፃ ዙሪያ መማር ወይም መጥየቅ እሚገባን አለ።
በተለምዶ፤ የዘመንአችን ኪነህንፃኛዎችን (architects)፣ ከእነአክሱም እና ላሊበላ ተነፃጽረው እሚተቹአቸው እሚነግሩን እኛም እንደ ተርታእናመደዴ (mediocre) የእምናየው፤ ህንፃዎች የባህል እና ታሪክ ቅርስዎችን አለመመሣሰልአቸው ብቻ ሳይሆን፤ የፀሐይን አገልግሎት የእሚቀጥሯት የማጥበርበር ክፉ አገልግሎት በወጪወራጁ እና በእየጎረቤቱ እንድታቀርብ ነው። እረባሽ ግንባታ በእየመንደሩ አለ።
አላማ አሁን ለጽሑፌ የለኝም እና፤ ብቻብቻ የጋሽገበየሁ (layman’s) ከእዚነህ ተያይዞ የፈለቀ ግርምታዬን ጥያቄ ልሰትር እና ልቋጭ።
በአንድ መኖሪያ ቤት፤ ጎረቤት የሆኑት ሌላ ነዋሪዎች፣ ባለአራት ፎወለል ህንፃ መደርደር ጀመሩ። ኪነቅርጹ ልክ መልበስ ሳይጀምር ይህ ተከሠተ። የህንፃው ጥላ ልክ መስከረም ሲገባ ጀምሮ ወደ ነዋሪዎቹ ቤት እየዘለለ ገባ። እነእሱ ቤት ያለው ህፃን፤ የተለያዩ ተክልዎችን ጥግ ላይ አጎንቁሎ እያለማ ነበር። ነገርግን፤ ሌላጊዜ ፀሐይጨረር እሚሠበስቡት እነእዚህ ተክልዎች፤ አሁን የኪነህንፃው ዣንጥላነት በልቶ ከማደር ስለእዚህ በተፈጥሮአቸው ማደግ አስቀረአቸው።
ህፃኑ እጅግ ተማረረ። ምንም መፍትሄ አይኖርም አለ። ግን ሲያስበው እና ሲናገር ሃሳቡ ተረፈኝ።
ሀቂትዎቹ (facts) እኒያ ናቸው። በአመቱ የኢክዊኖክስ ዑደት መሠረት፤ ምድር (በዛቢያዋ) ስትሾር፤ ማጋደሏ የእሚፈራረቅ ጥላን በህግ ባልያዙት ይልቁንም በሌላ ሰዎች ንብረትነት በተመዘገ ንብረት ላይ ለመጣል ዳረጋት። ድንበር እየዘለለ እሚረብሽ የንብረት ሀብት ላይ እሚከሰት ሁከት የተከሠተ ሆነ።
ይህን በህግ መዳኘት አንድ ጉዳይ ነው። ለምሳሌ፤ ለልጁ ቢያንስ የጉዳቱን ልክ ካሳ ከይቅርታ ጋር ማስከፈል፤ ለከንቲባው መስሪያቤት፤ የግንባታ ፈቃድ ሲሠጥ የህንፃዎችን ሁኔታ በአግባቡ በተቻለ ሁሉ እንዳያጣሉ አድርጎ እንዲመረምር ማስጠንቀቅ እና ማሳወቅ፤ ህፃኑ ለምሳሌ አስፈላጊ እና ጠቃሚ ነገር እሚያጣ እና ከህንፃው ዋጋ በላይ እየተጎዳ ከሆነ (ለምሳሌ ለማህበረሰቡ ከእሚሰጡት ጥቅም አንፃር) “ለልማት ተነሺ” እንደ እሚባለው ብዙ ስህተት ያለበት የዴንታየለሽ የስነውሳኔ መርኅ ማስፈረስ ድረስ ሊኬድ ይችላል።
ነገርግን፤ በኪነህንፃ አስተምህሮት፤ የንብረት መብትን በፀሐይ መከለል እና አለመከለል ደረጃ ያሉ ጉዳይዎች እንዴት ይታይ አሉ? ለአንዱ መጨነቅ ለሁሉ መጨነቅ ነው እና፤ ያም የአኗኗር ጥራት እና የስልጣኔ ምልክት ነው እና (የጃፓን አንዲት ተማሪን ለማመላለስ ከመዘጋት አመት የቆየ ባቡር መስመር እንደማሰብ) ትላልቅ ጉዳይዎች ስር ይህን ለመሻጥ እንደምን ጉዳዩ እሚታይ ይሆን? የስነኪነህንፃ ፍልስፍና፤ ከእሚመሠረትብአቸው እሳቤዎች አንዳንድ ጥቃቅንዎች መሀከል ይህ መግቢያ (አቃፊ) ያገኝ ይሆን ወይ?

By Binyamhailemeskel

Hey there! If you want to know about me, I just like fun, commonsense wisdom, and human love. Let us live a bright today changing tomorrow into brighter.
Regards,

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s