Categories
መልካም ጥበብዎች Fine Arts

የሀበሻ ስነእናኪነ (Art) አቅም አቅጣጫ እንዴት መሆን እንደአለበት

Simple talk on direction of contents of the drowning Ethiopian art world.

bY ቢንያም ኃይለመስቀል ኪዳኔ፤ ጥር ፲፩ ቀን፣ ፪፼፲፫ ዓም፨


፩) በዝቶ’ መስረግ


እንደ ንጥረነገር ዳግ-ምርምር ባይሆን እንኳ፤ ብዙ አቅም ያለው የህይወት አንድ ዘርፍ ስነእናኪነ (art) ነው። በኢትዮጵያ፤ ዘመንአዊ ጥበብ አጭር እድሜ ቢኖረውም፤ በተለይ በመጨረሻው ንጉሥ ዘመን ከመቼውም አቅም ያለውን ማንነት ገንብቶ ነበር። ዛሬም ዋናዋና የጥበብ ብሔርአዊ ቅርስዎችአችን፤ ከወደእዛ ዘመን እሚመጡ ናቸው።
እራሱን የተካው ደርግም፣ በአንፃርአዊነት በተገቢ የዘርፍ ዉርስ አቅሙ ይጠራል። ከእነጉድለትዎቹ፤ ከምርጡ የጥበብ አቅም፣ አሁን ድረስ እሚመዘዝ ምርት ያበረከተ ዘመን ነው። ልክ ድህረ-ደርግ፣ ዘርፉ በአፍጢሙ ተወረወረ። ጭው ያለ የጥበብ በረሀ እና መታነቅ ተፈጠረ። እስከአሁን፤ የጥበብአችን ምርት አንገት አስደፊ፣ ከስድሳዎቹ እና ሰባዎቹ ዞሮ ምርጥ እሚለውን ጨላፊ ነው።
ዳሩ፤ በገፍ እና ቅፅ (form) ግን፤ ድኅረ-ደርግ እስከአሁን ትንሽ እማይባል እየተመረተ ነው። ህገመንግስትአዊ የብሔርብሔረሰቦች ባህል ድጋፍም፣ የተለያዩ ደካማ ቢሆኑም፣ በተለየ በሙዚቃ ዙሪያ ጥበብ ምርትዎችን እያስመለከተን ነው። በፊልም እና ሥነጽሑፍም የበዙ ምርትዎች አሉ። በአአዩ. ትያትር ትምህርትቤት፤ መቻል ደጀኔ፤ የመመረቂያ ጽሑፉ ላይ በ 2007 ዓም. በቅርብ የተሰሩ ወደ 700 ፊልምዎችን በእርእስ ለመሠብሰብ ሞክሮ ነበር። የመብዛት እና ብዙ እድል የማግኘቱን ያክል ግን፣ ስነእናኪነአችን ይዘትአዊ እና አቀራረብአዊ ጥራት ጋር ተኳርፏል። እማዕዶትአዊ አቅሙም እጅግ ደካማ፤ አቀራረቡም አታካች እና ሠነፍ ነው። ሁለተኛው የሆነው፤ በተለይ ከሙዚቃ እና ዳንስ አንፃር፣ የብሄረሰብዎች እንደምንም “እራስ-አገላለጽ” በትልምአግጣጫ (policy) ስለተደገፈ የበዛ ነው። ከአቅም ወይም ፍሬጉዳይ ይልቅ የድግሞሽ ልማድ ነጸብራቅነት መገለጫው ሆኗል።
የቀረውም፤ ይመሳሠላል። የተፅዕኖ ጉልበት-አጥ ነው። ሌላው መገለጫ፤ የሂስ እና ዳግምርምር ጥራት እና ብዛት እምብዛም አይታይም። በስነእናኪነ ዙሪያ እሚሠሩ ተደራሲዎች ያሏቸው ሂሰኛዎች እና መገናኛ መዉጫዎች (outlets) አልበቀሉም።
ሲደመደም፤ የስነእናኪነጥበብ ምርትዎች በጠቅላላው፣ ማደግ ሳይችሉ ቀርተዋል። ጭራሽ፤ ከአሁን ወደጀርባ በሠላሳ አመትዎች የኋሊት ተጉዘዋል። ስለእዚህ መቋጫው፤ ፩) የጥራቱ አለመኖርን አሠመርን፤ ብሉይ (classic) ምርትዎች ከበዛው መሀከል ከመመረት እና ይኹንታ ማግኘት ሠንፈዋል። ፪) ያሉትም እሚያበዙት እጅግ መናኛ፣ ተደጋጋሚ፣ እና ያልፀና አቅም ይዘው የመግለጥ (expression)፣ ልዩነት ወይም ወጥ (originality)፣ እና አስማሚ ሳቢነት ያጡ ናቸው። ፫) የደከመ ግምገማ ዘርፉን ይጓደነዋል።

ይህን ሀቅ (fact) ካቋቋምን፣ ቀጣዩ ተመዥራጭ ነጥብን አስግጎ እናያለን። ወደኋላ ስንሻገር የተሻለ አቅም የነበረው ለምነድር ነው? ምን አማራጭ አካሄድ ለእዚህ የትውልዱ የጥበብ በረሀ መልሥ ይሆን ይሆን? መቀልበሥስ እሚገባው ዝብ-ጉዞ እያደረግን ነው ወይስ አይደለም? ምን ያክልስ አጥተን (ተጎድተንስ) ይሆን?


፪) ሀቀኛ መሠረት እንደ ስኬት


የቀደሙ ሁለት ዘመነ-መንግስትዎች የነበሩት ስነእናኪነ ምርትዎች፤ የተሻሉ የነበሩት፤ የማህበረሰብን ችግርዎችን አብዝተው ይዳሥሱ ስለነበር ነው። በልዩነት የቀረቡት፤ በአስተምህሮት ጭብጥዎች ከቤተክህነት እየተሰነጠቁ ወደ አለምአዊነት እና የማህበረሰብ ችግር ነቃሽ እና አስመልካችነት ላይ ስለእሚያተኩሩ ነው። እነ ሃዲስ አለምአየሁ፤ መስፍን ወልደ ማሪያም፤ ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድኅን፤ ዳኛአቸው ወርቁ፤ በዓሉ ግርማ፤ ወዘተ. ከፍተኛ ማህበረሰብአዊ ሂስን በስራዎችአቸው እና የህይወት ትግልዎችአቸው የጨመሩ ነበሩ። ከድህነት፤ እረሃብ፤ ፍትህ እና እኩልነት መጥፋት፤ ኋላቀርነት፤ ሙስና፤ ወዘተ. አንፃር ስራዎችአቸው አብዝተው እሚያተኩሩ እና እሚሟገቱ ነበሩ።
የተከተለው የደርግ ዘመን ላይ እሚሰሙ ዘፈንዎች፤ ብዙ የወቅቱን እና ቋሚ ጭብጥዎች ዕለትአዊ ቋንቋ እስኪሆን ያደረሱ ነበሩ። እንደ ቀደመው ዘመን ስነጽሑፍ፤ በማህበረሰብ ጥልቅ ችግርዎች ዙሪያ ዘፈን እና ሌላውም ጥበብ ምርት ከህዝቡ ጉያ ይገኝ ነበር።
እነእዚህ፤ የማህበረሰቡን ሁኔታ ያንጸባረቁበት ሙከራ ጠንካራ የነበሩበትን ጥበብ ፈጥሯል።

፫) ፍሬነገርን ማጥራት

በጠቅላላ፤ ይህ ተዋዳጅ-ሀያሲ (fan critic)፣ እሚያምነው የሀበሻ ስነእናኪነ ጉዳይዎች መሀል አንድ ነጥብ አለ። የሀገርአችን ጥበብ ምርት፣ ከሌላው ያደገ ሀገር ጥበብ ለመቀራረብ ለእራሱ ህዝብ እንዲሆን መለየት አለበት። ያ፤ አመክዮዎች አሉት። እንደመነሻ ግልጥ ነጥብ ይነሳ። እኛ ገና በዘመነ መንገድ አልተመሰረትንም። የድሀድሀም ነን። ከቶ ያልሰለጠንንም ሉልአዊ ተመጽዋች ነን። ጊዜ ከማሳለፍ፤ ወደ ጊዜ ማሳደድ መራወጥ እሚገባን ነን። አሁንም ቢሆን መጪውን በማስላት ያ እሚያስገድደን ነን።
ይህ ከሆነ፤ ጥበብን አመረትን ካልን፤ ውስጡ መግለጥ እሚፈልገው ሀቅ ያንን እንደሆነው ሌላ መሆን የለበትም። የቀደሙት፤ ለጊዜ ማሳለፊያ አማራጭነት አልቀረቡም። በተገለጡ ቁጥር የጠና እና የጋራ ወሳኝ ችግር ገልጠዋል። ስለእዛ፤ ተወዳጅ፣ አጓጊ እና ሳቢ ሆነዋል። አሁን፤ ያ ታጥፎ፤ በተራ አገላለጥ እሚቀርብ “ጊዜ ማሳለፍ”ን እሚተኩ የብርጭቆ ሻይ አቻ ተደርገዋል። ያንን ከዘርፉ ለመላጥ፤ የተቋጠረ ግንባር ያለበት ምርት አንዱጎዳና እንደሆነ ግልጥ ይሆንልን አለ።
ሌላው ደግሞ፤ የእምንጠቅሰውም የቀደመ ዘመን ስራ ሆነ የአሁኑ ከደመሩ፤ ለዘመነ እና ያረጀ ማህበረሰብ በቂ የጥበብ ግዛትዎች አይደሉም። ገና ያልመሰረትንአቸውን ዋናጅረት (main stream) አመለካከትዎችም በእሚገባ መመስረት ይገባናል። ለምሳሌ፤ ገና የእኛ አኗኗር ጭብጥ ሁሉ በጥበብአችን ሽፋን አላገኘም። ብዙ የመተባበር፣ የመስራት፣ ራስንየመቻል እና ማበልፀግ፣ ከወደቁበት ተነስቶ ዳግማሸነፍ፣ ብሄርአዊነት፣ ወዘተ. ብሉይ (classic) እምንልአቸው ስራዎችን አላመረትንም።
በእነዚህ ሀገርአዊ አረንቋዎችአችን አነሳሽ እና አንፋሽ (inspiring)፣ ልኮት (reference)፣ ዘመንአይሽሬ ስራዎች ማከማቸት ይጠብቁናል።
በእዚህ የዘመንአዊ ስልጣኔ ምድረበዳአማ ገሀድ፤ እና ሀገርአዊ የጥበብ ክፍተት መሀከል፣ የጥበብ ምርትዎች ዝባዝንኬን መጨቃጨቅ የለብአቸውም። ይህን ደጋፊ ሁለተኛ ችግር አለ። የማንበብ እና ምርት በገበያ አሽከርክሮ ለተደራሲዎች በቀላሉ የማቅረብ ባህሉ እጅግ ትነሽ ነው። ተደራሲነት አብዝቶ ቁብ እማይሰጥ እና እጅግ ኋላቀር ነው። እንዳየንው፤ ጊዜማሳለፊያ ወይም የተገደቡ ጥቃቅን ነገርዎችን እንጂ የበዛ ቁምነገር በጥበብ እንደእማይጠበቅ፤ ትክክል ተኾኖ በቀላሉ ይገመታል።
ስለእዚህ፣ ይህን ቀይረን እንደ ቀደመ ነቃ እንዳለው እና እነ ኦሮማይ፣ እሳት ወይ አበባ፤ የህሊናደወል፣ ፍቅር እስከመቃብር፤ ወዘተ. በማንበብ ስለጋራ ችግር ይነሳሣ እና ሀሳብ ይለዋወጥ እንደነበረው ትውልድ፣ የሀበሻ የአሁን ኪነእናስነም እንዲሁ መበርታት እና ትውልዱን መምራት ይገባዋል። እንጂ፣ መቃረን አይጠበቅም። ከቶ። በሙዚቃ ዙሪያም፤ ኢስልጡን መንግስትን በመደገፍ ትውልድ እማያነቃ እና የጥበብን አቅም እሚያስረሳውን ማለት ይቻል አለ ዋጋ ያለውን የብሄርብሄረሰብ መገለጫ ምርት በአዋቂነት መግራት ይገባል። እነእዛ ጥበብ ሳይሆኑ ባህል እና ዘይቤ ማስተዋወቂያ፤ ሲከፋም መንግስት እንደእሚያታልልበት የማንመሆን ጥያቄ ናቸው። ከታላቁ የማስመረጅ እና ማስተማር ጥበበ ጥበብ የተራራቁ ናቸው። ከሀይማኖት እና ባህል ወደ ማህበረሰብ ኑሮ ጉራንጉር መንፋቀቅን ደግሞ ለሀበሻ ጥበብ እነ ሎሬት ጸጋዬ እና ዘመንአቸው ጀምራው አለች። ለተደራሲዎች ዝብአረዳድ የቦረቦረው “ጥበብን” እየሞጀሩ እና በአነሰ ደረጃ ሌላም ክወናዎችን እያቀረቡ፤ የተገደበውን ተደራሲነት እና ገበያ መጋራት ይልቁንም እንዳሳዛኙ እውነት የማያግዝ ሀገርአዊ ቅንጅትን መፍጠር እና መቆጣጠር አይገባም።


፬) መደምደሚያ


ጥበብ አቅሟ ከፍተኛ ነው። ለቱልቱልቴ (propaganda) እንኳ ከፍተኛ አገልግሎት ታቀርባለች። እንዲሁ፤ ለዝማኔ እና ማዕዶት እጅግ አኩሪ መሪ ሚና ማቅረብ እምትችለው ነች።
ምርትዎች ንቃተህሊናን ሳያረኩ እንዳሉ ግን እየተቆጠሩ፤ እሚተዉት የትውልዱ አሻራ፤ ወደፊት ለማየት ሲዞር እማያስደስት መሆኑ እየቀጠለ ነው። የወደፊቱ መጨፍገግ ዛሬ እየተፃፈ ነው፨

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s