Categories
ሥነዉሳኔኛ (About Politics)

ኢትዮጵያ ትልቅ ነበረች፡ ዐዉድአዊ የሥልጣኔ ፈርቀዳጅነት ኦና አተራረክ እና እይታ-ከልል ጉዳትዎቹ Ethiopia Used to be Great: Contextual Civilization Pioneering Nil Storytelling and its Obstructing Harm

About Ethiopian’s errors in mis-contextualizing prides in ancient Civilizations.

በ ቢንያም ኃይለመስቀል ኪዳኔ፤ ጥር 2013 ዓም.

ይስማዕከ ወርቁ፤ የወንድ ምጥ ዉስጥ “ልናነጋ ተኛን” በእሚለው አሀድ (piece)፦


“…ልንውል ተነስተን ልናነጋ ተኛን፤
በድሜጥሮስ ኩፋል፤ በገማ ጭንቅላት ጨለማ እየቆጠርን፤
እንደ ወፏ ሞረሽ በማያነጋ ድምፅ ሁሌ እየተብላላን፤
አንድ ቀን ሳንውል ሦስት ሺህ አመት ሞላን፨”

በሺህ እና ብዙ ሲደመሩ ዘመንዎች፣ የተከማቸ ታሪክ ኢትዮጵያ አላት። ማለትም፤ ቅርብ ዉስጥ አልተመሠረተችም።
በሽማግሊትነቷ ምክንያት፤ ቡራቡሬ ሥጦታዎችን ታሳቅፈናለች። አመክዮዋ፤ ከፍታ እና ዉድቀት (roller coaster)፤ ወይም ተቃርኖት (oxymoron) መሀከል መክረሟ ነው። አንድብቻ የእዚህ መገለጫ፣ ሠፊ ዕለትአዊ-አንደበት (common parlance) የሆነው እድሜበቂጥ ሥልጣኔ ወርሰናል እሚለው ወሬ ነው።
በእርግጥ፤ ወደ ዘመንአዊ ሥልጣኔ ኢትየጵያ ድርሽ አላላችም። ያን ማዕዶት (transformation)፣ ማለት ይቻላል፣ ከቶ ከእማያውቁት እና የገፀምድር እጅግ የኔብጤ-ሀገርዎች-ተርታ ግንባርሥጋ ግንባርቀደሟ ሀገር ናት፦ ድኅረ-ድንበርዘለል ጉብኝቱ፣ ዐብይ አህመድ (ጠሚ. እና ዶ/ር) “ያው እንደምታቁት ለምኜላችሁ መጣሁ” እንዳለው። ይሄን ልክ አሁን እዚህ ስናነብብ፤ ልዕለ-ብዙሀኑ ህዝቧ ከድሀመሆን በታች ሆኖ እንደ እትብት እና ሸለፈት ከዘመኑ ሉል ተሸርፎ በተጣለ አኗኗር እየማቀቀ ነው።
በእዚህ ምክንያት፤ ምንም እንኳ ጥንታዊቷ ሀገር በእዛው አረጀች ተብላ ከመታማት እሚያስጥላት አጥታ የድሮቀርነት ቅርቃር እያጠነዛት አሁን ወትሮአዊ ሠፊ አሳርበዪ ሀገርነቷ እንደ ደንብ ቢቋቋምም – እነ ጆርዳን እና ቤት ግእዝ እንዳሉት “የዛሬን አያርገው እና” [ከኛ] – በጥንት-ቀር አንዳንድ የሥልጣኔ ዘርፍዎች ዉስጥ የትልም-ጥንስሥ የጣለች ማህበረሰብ ነበረች። ስለእዚህ በእርግጠኝነት፤ በጨለመው ዛሬዋ ዉስጥ፣ ጥንት-የቀሩ “ስኩ” ትትረትዎቿን ማነሳሣት ለአንዳንድ ጠቃሚ ኢላማዎች ያገለግላታል።
ዘርፈኁልቁዏ መልእክትአማ አሽከርነትዎችን ያስረክባታል። ሊያውም በአረቦ-ወላድ (interest-bearing) ጎዳናዎች። ለዐብነት ያክል፤ ቀኝአዊ ወል ስነልቦንታ (positive common psyche) አቀነባበር፣ ብሔርአዊ አንድነት፣ አንፋሽነት (inspiration)፣ ትምህርት ቀሠማ፣ ለትውልዶች መመዘኛ ልኮት-ክወና (reference-making)፣ ገቢምንጭ፣ ድንበር ዘለል ኩራት፣ ክብር እና መሠል ጥቅሞችን መሠብሰብ፣ ወዘተ. ዙሪያ፤ ይህ ዘመንጠገብ ታሪክ ቢገላለጥ አጋዥ ይሆናል። እኒህ ሁሉ፣ ለዘመነ ወይም ለሚሞክር ማህበረሰብ ወሳኝ ሁለንተናአዊ ግቤትነትን መዋጮ ያደርጋሉ።
ዳሩግን፤ ያጠመዱን የነዚህ ተቃራኒ ሀቅዎች (facts) አሉ። አንዱ፤ ልኮት ተደርጎ መነሣት እማይገባበት ዝብ-ዐውድ (missed context) ዉስጥ፣ የድሮስልጣኔአችንን ማንሳቱ ነው። ያንን፣ ኩምሽሽ ብለን በማፈር እምንጋፈጥበት ኋኝነትአዊነቶች (possiblities) የለሽፋታ (busy) ማሻቀብ ዉስጥ ተጠምደዋል። አንዳች ሰውነት-ያለው-አካል (entity) የሆነ፣ አንድ ነገር ስለእዚህ’ ማድረግ አለበት። ከጥርጥርዉጭ! ምክንያቱም፤ ቂላቂልነት እና የገዛአታሎት (self-deception) ሲፈለግ እሚደረግ ዝብዘባ ሆኗል። ያ ስት የልኮት ዐውድ ድግግሞሹ ካልጠፋ፣ ቢያንስ እንኳ መቀነሥ አለበት።
ከእነእዚህ አንዱን ዐዉድ አስከትለን ቀጣይ እንመልከት እና አርእስታችንን ወደተገቢው መጨረሻ ጥበቱ እናቀጥነዋለን’። ይህም ሁለት አቻ-እማይጣፍጡ ነጥብዎች ላይ ሌባጣት ይቀስራል።
እነእሱም፤ አንደኛው እጅግ ሞኝ የሆነው ዝምብሎ ድሮ እኮ ትልቅ ነበርን እሚለው በተርታ (እማያስፈልግ) ዐውድ ላይ እሚደመጠው አገላለጥ ነው። ያ፣ የለሽ-ረብ ነው። ከቶ። ባለፈክረምት ጤፍ እንደእማይዘራው፤ ለጉንጭአልፋ ፍፃሜ ብቻ፣ እማይረባ ዐውድ ዉስጥ፣ ያንን መመረጡ ጎጂ እና በዝብ-ህጻፄነቱ (missing the point fallacy) አታካች ነው። ሁለተኛው፤ ያ፤ የጥንት-ቀር ሥልጣኔአችንን፣ መንግስት ባለመታከት በዐውደቱልቱልቴው (propaganda platform) እሚቀጥረው አግባብነት-አጥ ዐውድ ነው፤ በገዛ ገንዘብአችን በእያንዳንዳችን ጥማድ-ጆሮችአችን እሚያሠቃየንበቱ። ምክንያቱም፣ ለምሳሌ ሠላሣ አመቶች ያለፋታ ትልቅ ነበርን ትልቅ ልንሆንም ነው ስንባል ብንከርምም፤ በመጨረሻ ሲለዩን ከቶ ትልቅ ባለመሆናችን፣ ማታለያነቱ ግማሽዕድሜዘመን አርጅተንም ቢሆን የገባን ጥቂቶች አለን። ዳግመኛ፣ ምክንያቱም፤ ከዛሬ ኮሦ ገሀድአችን አልመሣሰል አለን እንጂ፤ በተገደቡ መስፈርቶች ሲመዘን እንደምንም ምንምአይሌ (somehow fair) እሚባል፤ እንደ ግሪክ እና ሮም ወደ ዘላቂ እና አዲስ-ዝማኔ እሚልክ ብሉይ (classic) ባይሆንም፤ ድሮአማ ስልጣኔ አበው ዘ ሀበሻ (forefathers of Habesha) እንደነበራቸው እማያውቅ የዛሬ የድሃድሀ ሀበሻ የለም። ያንንስ፣ ዝብርቅርቅ ፊደል የቆጠርን ሀበሾች ቀርቶ፤ እንደ ተጠቅመህ-ጣል ወይም ተጠዪ ሁለተኛ ዜጋዎች ተሽቀንጥረው ከትርጉምአማ ህዝብ-አላባአዊነት የተሰረዙት ገጠር ያሉን ሀገረሰቤዎችአችን እንኳ – የስኳር እና ሲባጎ ሥልጣኔ ቀንሙሉ ኧውአስብል መንገድ-ቅዠቶች (awe-inspiring mirrages) ቢመስሏቸውም – በእቅፋታቸው እሚያስተናግዷቸው ዉብ ኪነህንፃአዊ ግርምቶች (architectural wonders)፣ የእምነት እና ልዩ-መካንዎች (special sites)፣ ወዘተ. ዉርስዎች፣ በነበር የቀረ ታሪክ-ቀር ጉድጉድ ዉጤቶች ወራሽ መሆናቸውን ያሳውቋቸዋል። በጠቅላላው፣ ሁላችንም ያረጀ ሀገር ዉርስ አባል እንደሆንን በበቂ ሁኔታ ለማወቅ አኗኗርአችን ዳርጎናል። ጥንት-ያለፈ የሆነ ትትረት አሻራውን እንደፈረመብን በጠቅላላው አልተሰወረብንም። በወጉ ያ መደበኛ ዕዉቀታችን ሣይበዘበዝ (capitalized)፣ ዳሩ፣ መረጃውን ብቻውን፣ በእየስብሠባው፣ ስልጠናው፣ የአንዳችነገር ምርቃ-መርሐግብሩ፣ ድርጅትአዊ ስብከቶቹ፣ ዉይይቱ፣ ኩነቶቹ፣ ክብረበዓላቱ፣ ወዘተ. ወደ ገሀድ ለእማይሻገር የስነዉሳኔ ፍጆታ (political consumption) ተደጋግሞ አሁንምአሁንም እሚነሳብን ሆኗል። በከፍተኛ አምባግነና እና እማይዛነፍ የቱልቱልቴ አፈፃጸም፣ ያን የመንግስት ቋንቋን በእየተቋሙ እና መገናኛብዙሃንዎች – ብቻ በመላ ሀገሪቷ – እንደገደልማሚቶ ማስተጋባት ደግሞ አማራጭ-አጥ ባህል ሆኖ ሠላሳ አመቶች ስላለፍን ጥንትአዊው ስልጣኔአችን ቋሚ ረብየለሽ ወሬአችን ነው። አንዳንዴ በእዚህ ያለፈ መረጃው አቀጣጠር፣ ለዛሬ ተግባርአዊነት እግሬአውጭኝታ (scapegoating) ግንባታ ሆኖ የተላመድንው ነው። የተግባር እንደራሴ ስልተ ቱልቱልቴነቱ ዘወር እማይልባቸውን፣ ማንም እሚያውቀውን ድሮቀር ስልጣኔአችንን ለፍፎ የአንዳንድ ዜጋአዊያን (civilian) ጥማድ-ጆሮዎችን ያረሠርስበታል። ይህን በተደፋው ኢህአዴግ. ዘመን እና በተለይ ደግሞ ሳይወድቅ ወልዶ ባስዳኸው ልጁ – አብይ አህመድ እና ብልፅግናው – መጀመሪያ-ሰሞን ለእየጉራንጉሩ የተቀነባበረ “ጥምቆራጭ” እንዲያ-ታላቅ-ብጤ-ነበርን፤ አሁንሣ ቢሆን – ኧረ ናችሁ እኮ አሁንም-ታ! ጤዛዲስኩር፣ ዛሬ ድረስ እየተቀያየረ እና ባለመቋረጥ፣ ጊዜአዊ የተርታእናመደዴ (mediocre) ስሜት በመኮርኮር እና መጋለብ ላይ ነው። ካስተዋልንው፤ የቀደመ ስልጣኔም ሆነ አብዛኛው ታሪክአችን፣ የወሬ አንጀት ማርካት አላማን ብቻ ተወጥቶልናል።
እነዚህን ሁለት የተሣሳቱ የድሮ ስልጣኔአችንን ወሬ-ዐውድዎች እዚህ ከቶ አናነሳቸውም። ምንያረጋሉ። ዋናውን ነቁጥአችን፦ ሦስተኛ ባለጌ ዐዉዱን ግን እናቅጥን እንዳልንው እንደ አርእስት ጭብጥአችን ቀጥለን እንወያየው።
ያም፤ እዚህ እምንጠቅሠው በጠቅላላው፤ የተቀረውን ዓለም ስልጣኔን ለመናቅ እና ማንቋሸሽ እምንጠቀመው መንገድ ስናደርገው ያለው ነው። ያን ለመዠለጥ እንሞክር። ለእዛ ነጥብ ግንባታ ደህና ከሆነ፤ (ነብስ ይማር) ብሔርአዊ ልእለ-ቅርስአችንን (super-treasure) ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኅንን እንጥቀስ።
በታመሙብአቸው መጨረሻ ቀንዎችአቸው አካባቢ፤ ፕሪንስተን ኅዋአዊከተማ (university) የሀበሻ ታሪክ ዳግ-ተመራማሪት (researcher)፣ ፀሐፊት፣ እና መምህርቷ ዌንዲ ሎውራ ቤልቸር ጋር አዲስአበባ ዉስጥ ባደረጉት ቃለመጠይቅ መሀል፤ አንዱ ጥያቄዋ ላይ ደረሡ። አንድ አሜሪካአዊ(ት) ስለኢትዮጵያ በእራሱ ሃሳብዎች ይዞ አብሮን እዚህ ቢመጣ እና ቢኖር ስለኢትዮጵያ ምን ይሉታል አለችአቸው። በአጭሩ “እኛ ነን መሰረተ ስልጣኔ፤ እናንተ ኮርጃችሁን አለ” እሚል ይዘቱን አላማአችን ስላልሆነ ብንዘልለው እምንወያይበትን ሃሳብ ግን አናጣውም። እጅግ ቁጡ ድምፀት በአመላለሡ ድባብ እና ቅንጅት ግን ነበር። በማሽተት እንኳ ደረጃ ክብረት-ስጡኝታ፣ ሌላውን የመናቅ እና ማሳነሥ (ንቀት) እና ማንቋሸሽ ይገኝበታል። የእኔ ሀገር እና የጥቁር-ግብፅአዊ ህዝብዎች ጥንትአዊ ስልጣኔን በምድር ከማንም ህዝብ ቀድመው ወልደውታል። ለዓለም የመጀመሪያው ሥልጣኔ ማህፀን እኛ ነን። ዛሬ እምናየውን ዘመንአዊ ምድር፣ የመሰረትንው እኛ ነን። እዚህ ኑና መሰረትአችሁን አጥኑ ወዘተ. እለዋለሁ ይሏታል።
ሎሬት እሚያነሱት እምብዛም ስህተት የሌለው የታሪክአዊ ዉሂብ (historical data) ትንታኔው ነበር። ያስከተሉት ክፍለ-ፍቺው እና እንደምታው ግን መረር ያለ እና ወጣ ያለ ነው። (አንዳንዴ በአውቆታ (intentionally) ያንን ረብየለሽ እና በእንዲያው-በደፈናው እሚኮፈስ ‘የዛሬ ዜሮ-ቀር ወደድሮ ይሮጣል’ አንጎልአዊነት (mentality) ለማጋለጥ የጠየቀችው ሁሉ ይመስላል። እሚመስለው፤ መልሱን ባትገምተው አስቀድማ አትጠይቀውም ነበር እና።)
ገሀዱ ቢካድም ያው ገሀድ ነው። ምድረቀደምቷ፤ የቴዎድሮስ ካሳሁን ዉብ አገላለጥ “የአዳም እግር አሻራ”ዋ፣ ድሮቀሩን ሥልጣኔ ድሮ በአባይ መስመር እንደፈሳሹ ለሉል አፍሳለታለች አለች። ደህንነቱ ላይ ይስማዕከ ወርቁ ከታሪክ ዳና-አዳኝ እንደቀነጨበው ተመስጦ (meditation) እንኳ ከእዚህ ወደሽቅብ አፍሪቃ፣ ከእዛ ወደመካከለኛምስራቅ፣ ብሎ ሩቅምስራቅ፣ እያለ እየተራመደ ወደምዕራብ ሉል የላክንው ነው። እንደ እራሳችን ማለትም ዘረፍጥረትአችን (species) እና በእርግጥ የማይናቁ የተቀሩ መሰረት እሚሰኙ ግዝ-ዉጤት (export) ነገርዎችአችን። ሰለእዚህ፤ እንኳን ጥርጣሬ እሚያጭረው አዳም፤ ደናክል ሥምጠተምድር ሳለች ከአንድ ቅርንጫፍ ተፈጥፍጣ መሞቷ የተረጋገጠችው ድንቅነሽ ከወተት ወደ ቅጠል ለመዞር ጥርስ ከነቀለችበት ሀገር ግን ያ መመዘዙ በኢአድሎአዊነት ቢሾፉት አብዝቶ አይገርምም። ቀድሞ የነበረ ሀገር፣ ቀድሞ ጥቂት ቢራቀቅ ስሜት-ሰጭ እንጂ ጊዜአይሽሬ ተዓምር መሆን አይችልም። ቢያንስ ፳፩ ኛ ክዘ. ዉስጥ። ብቻ ግልፁ ነገር በቅርብ ዘመንዎች ጭምር፤ ዛሬም እና ነገም፤ ብዙ የአቢሲኒያ ጥንትአዊ ሥልጣኔ በእየዘርፉ ለአደገው ዓለም ልክየለሽ የጉጉት (interest) ግዛት አንድ አባል ነው።
ዋናው ጉዳይ ያንን ታዲያ፤ ለምን ብዙዎች በለጡን እኛም ደግሞ በእዛው ለምን አሸለብን በእሚል ህቡዕ ብስጩ ስነልቦና መሽገንበት ለምን በጭስማውጫ ሂሳብ እንጠቅሰዋለን? ያን ስናደርግ፣ አመክዮአዊ ትሥሥር የለንም። ድሮ ፈርመቅደድ፤ ለዛሬ መንፈላሠስ ተጨባጭ ዋስትና አልሆነም። አይችልም። ለምሳሌ እንደ መጋቤ ሀዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶ/ር) ቅጥየለሽ ኩራት፣ አራት ሺህ ዘመኖች ገደማ በፊት የክዋክብትን መሠረት ማጥናት፣ ዛሬ ኅዋ ዉስጥ በዕደኅዋ (space-craft) እንዳሻ የመንቀባረር ያክል አይደለም። ሰማዩን በዓይን ከመዳሠስ ሄደው እዛው ውለው እያደሩ ማዕድኖቹን ወደመቦርቦር ያረጀ ሥልጣኔ ውስጥ እንደተደረሠ ማድመጥ እንኳ አለብን። ያኔ በቂ የዳጎሠ ሥልጣኔ አልነበረንም፣ አላለምንም፣ አልቆሰቆስንም ከምንም በላይ ዛሬ እንኳ አልቀጠልንም። ሌላው ዓለም፣ በእየቅጡ (dimention) – በብዛት፣ በስምጠት እና በጊዜ – ብልጣብልጥነት እና እልህአስጨራሽ የሥልጣኔ ፍልሚያዎች ዉስጥ ተጉዞ፣ ዛሬ በጥቂቱ አድርሶን እምንቀማመሳትን ዘመንአዊ ሥልጣኔ መስርቷል። አሁንም ሳይበቃ ይህ ፈለክ (planet) ስልጣኔን አንበልብሎ እያራወጠም ነው። የፍራንሲስ ፉኩያማን ነቢብ (theory) ተቃርኖ፣ ታሪክ በነፃነትአዊ ንፅውሳኔ (liberal democracy) አይቋጭም በማለት ያስፎረሸ የተወሳሠበ ሽልፍኖት (technology) እውነታ ገና ከፊታችን አለ፤ ባህል እና ሌላው የየዘርፉ ስልጣኔ ቢቆረፍ እንኳ።
ከዘመንአዊው ስልጣኔ መብራት፣ መንገድ፣ ህክምና፣ አሀዝአዊው ሽልፍኖትዎች (digital technologies)፣ ደህንነት እና ጦርነት መሳሪያው፣ መድኀኒቱ፣ መገናኛብዙሃን አማራጩ፤ እጅግ ብዙ እማያልቀው ምኑቅጡ ሁሉ፤ ወደእኛ የመጣው እና ትውልድአችን ጨልፎ እየተጠቀመ ያለው ከእዚህ ዘመንአዊ እንደ ተመላሽ-ለአባይ የተንጠባጠበልንን ስልጣኔ ነው። ያም፣ በበጎ አድራጎት፣ ልመና እና መሟጠጫ ንግድዎች አማካይነት ያካፋልን ሲሆን፤ ምንጩም ቢበዛ በአንድ ጎራ ያሉ ማህበረ-ዘርፈሀገራት (league of multi-nations) እንጂ አንዲት ሀገር የማይመሰረት እና ማይጠቀለም ነው። የድህረ ጨለማ-ዘመን (dark-age) ሥልጣኔ የግድ ምንጭ ይመደብለት ከተባለ የብዙዎች ትትረትዎች መዋጮ፤ ግን በተሻለ እቅጭ፣ በብርሆት (enlightment) የበሩት የዘመንአዊ ታሪክ ፈርቀዳጅ ሀገሮች ሀብትነት ነው። ቢሆንም፣ ማንም እኔ ብቻዬን አበቀልኩት፤ እያለ እማይሸልልበት ነው። ያንን ከባቢ-ወሬ ለንግድ ማስታወቂያ ካሎነ እምብዛም እሚዘከዝክ ሞኝ-አቅራሪ የለም። ምክንያቱም፤ ሁለተኛም፤ ከእዛ ባሻገር፣ የዛሬን ሉል፤ ከአንድ ሥልጣኔ በተሻለ ታሪከኛው ዓስተኔ-ሰብዕ (mankind)፣ የገለጠው እውነትአዊነት (reality) ነው። ሦስተኛ ደግሞ፤ ከእኛን አይነቱ እዛው የቀረ የድሮ-ፈርቀዳጅ ይልቅ ከእኛ ተዋሰም ቀደመም አቻ-ሆነም ተከተለ፤ ለዘመንአዊው ዓለም ቀኝእጅ ያዋሰው ለምሳሌ የእነ ግሪክ-ወ-ሮምአዊ ስልጣኔ በመሆኑ የምድርአችን የዛሬ-ዝግመት-ወላድ እቅጩ ማህፀን ነው። በየታሪክ እርምጃው የመጡ ብዙ መሪ እና አቀብሎ-ሀላፊ፣ ተቀባይ፣ ብሎም እንደ ሀበሻ ስልጣኔ በጣም ቂጥ-ዘቃጭ ወይም እንደ ማያዎች ጠፊዎች አሉት። ከእኛ ጥንት ስልጣኔ ይልቅ እነእዚህ ገለልተኛ ሀቆች ለአሁኑኗ ምድር እጅግ ተጨባጭ እና ቀጥተኛ እናት እና አባት ናቸው። አንዳንዴ፤ እንዲህ በቀላሉ ሲባል ከባድ ጅልነት (የእንቁራሪት እና ዝሆን በጋራ ሲሻገሩት፣ የእንቁራሪት ፐ ድልድዩን አቀጠቀጥንው ተረት) ቢመስልም፤ እንደ ምድራዊያን ግን ብዙ በጋራ እየተፈራረቅን በመሠልጠን ዓሥተኔ-ሰብእዎች እዚህ ደርሰናል። ያ ማሳረጊያው (bottomline) ነው። ስለእዚህ፤ የእኛን ድሮ-ቀር ሙከራዎች አለጤና አግዝፈን ይህን እጅግ ዝሙን ምድር በሀልዎታ (attitude) መናቅ መላ-አጥ ጅሌት (goof) ሠሪነት ነው። ከታች እንደእምናየውም ተጨማሪ ቂል ህጻጼዎችም ነው።
በእኛ ወገን ግን፤ የአላደጋችሁም አስተያየትኤ (commentary) በተላለፈልን ቁጥር ሌላውን ዝሙን ሀገር ለመፎካከር እምንመዠርጠው ዘላለምአዊ-ስኬት አድርገንዋል። የረቀቀውን ትርፍራፊው የሚረዳንን የወቅቱ ድንቅ ሥልጣኔ በባዶ ሜዳ ሆነን እኛም የጥንት ሀያላን ነበርን እያልን እሚገባውን ክብረት እየነሳንው ነው። እንደጠቀስንው፣ ዛሬ እያገዘን ያለውን ዘመንአዊ ሥልጣኔ እንደ አበርካች መቀላቀል ቢሣነን እንደ ተናቀ ተጠቃሚነትአችንም ቢሆን ራሱ ማክበር ግን አለብን። የግዴታ። የጨዋ-ደምብ ተጠባቂ-አመል (convention) ነው። ሥልጡን ልቦና እና ስነምግባርአዊነት ነው። እራስ-አቂያቂያይነትንም ማብረሻ እና ከጋጠወጥ ወደ ተቆንጥጦ ያደገ የሀገር ስነልቦና ተመልሰን፤ በአንገት መድፋት የበለጠ እንዳንገለል እምንነሳበት አንድ መንገድን ነው። ሎውራ ቤልቸር በሌላ ለተርታ (mediocres) ታልሞ በተፃፈ ኢትዮጵያ መነሻ ነበረች ጽሑፏ እያንዳንዱ ኢትዮጵያአዊ ሲናገር “3000 ዓመት በፊት ብሎ ይጀምራል” እንዳለችው፤ ምን ታሪክ ቢነሳ፤ ለዓለሙ ዴንታ ከእሚሰጡ መሀከል ዛሬ ስለሌለን፤ ኮረጁን እምንልአቸው የምድር በአንዴ እሚናፈስ ዜና መሠረት በመሆንአቸው፤ “Humble” Kendric Lamarን እምናደምጥበት ወቅት ይሁን።

ቢያንስ በምናልባት፣ ብንገምተው፤ ይህ ስለገባቸው ይመስላል፤ እራሳቸው ሎሬት በ ‘90አችን መነሻ፤ ኑው ዮርክ ሲታከሙ የፃፉት “Dialysis” እሚለው አንጀት-በል ግጥም፤
ከሁሉም ጥንትአዊው የአፍሪቃ እንጦሮጦስ/ስምጠት በእርጅናዬ የመጣሁትን እኔ የእግዜር ፈዋሹ እጆች የሆናችሁ፤ ከምሞት ይልቅ ቢያንስ እንደ ነፋስ ስር እንደተቀመጠ ሻማም እንኳ ቢሆን እንድሆን “ቅዱስ በርናባሶች” አደረጋችሁኝ
እንዳሉት፤ ያ ለዌንዲ የተቆጧት የሥልጡን ነበርን ዐውድም እራሱን ማከሚያ ያበጁለት ይመስላል። እኛ ጥንት በቀረ ዝማኔ እንደ ስሎዝ’ አውሬ ብንኮፈስም ዛሬም ድኅረ-አይኤስአይኤስ ‘ሀበሻ-ዝግነናው’፤ ለአስቂኝ ፍልሰት (በሌሊትም) እማናንቀላፋ ነን። ለመራር የምድረበዳ (አረብ) ጉልበትስራዎች (iom) እና ጠቅላላ ስደት (ብዙ ቤተሰብዎችን ባለቤት እና ባለንግድ፤ መንግስትን እሚተነፍስበትን ዉጭምንዛሬ ለመበዝበዝ እምንሮጥበት እና እምንጠለልበትን አለም፤ ለመሰረትአዊ ነብስ አድን ህክምና፤ ከእየድኻው ወጪወራጅ አስጨንቀን ለምነን ከሞላልን እየተሰደድን እምንወዳቸውን እምናተርፍበት፤ ወዘተ. የሆነውን የሌላውን የዝሙን-ዓለም ስልጣኔ እጅ ከመንሳት መቆጠብ በምኑም ጡትነካሽነት አቻ አግባብ-ቢስነት ነው፤ ደግነቱ እንደ ዌንዲ ጽሑፍ መግቢያ ቀልድ ከመቀለጃነት ብዙም እየዘለለ አይታይም። አንዱ ዘርፍአዊውን የጥንቱን ከፍታ ዛሬ መቀራረቢያ መንገድ፤ ይህን ሃልዎቴ (attitude) ገርፎ በአዲስ መንፈስ፤ የድሮ ስልጣኔአችንን እንዳመለክንው ያንን አራብተን የዛሬውን (የእኛ ባይሆንም) በሀቀኛነት ማክበር መልመድ ይሁነን።
በስነምግባር እና ሀልዎታ ዉይይቱ ስንገፋ እና ስንደመድም፤ በአጭሩ፤ ያን ክብረት አሻፈረኝ ስንል ትልቅ ብልግና ነው እንበል። ብሔርአዊ ጋጠወጥነት። ያም ሽማግሌየለሾች አስብሎ በሽማግሌዎች በእሚመሩ ያሰድበናል። ማወቅ ያለብን፤ ገና አሁንም ጭምር እና እየተቆለሉ ለመጡ ዘመኖች ባለማቋረጥ ተሠድበናል። አንድ ጋዜጠኛ በስራው ደንብ መሆኑ ነው ብቻ ፋታ ነስቶ በማበሳጨት ያናገረው የውጭ አምባሳደር፣ አንድ ተራ አንቀሳቃሽ (machine) ብጤ እዚህ ገብቶልን በድኅረ-ተግባሬት-ጊዜ (post project timeline) ተገጥሞ እነሆ ተመርቋል ስለሀገርአችን በል ተናገር ብሎት ነበር። በስላቅ “ታቃለህ! ሀገራቹህ ዓለምን ማስደመሟን ቀጥላለችi” ነበር እየሳቀ ያለው እና በኋላም ቢሆን የመረመረው በማይመስለው እና በቀናነት ደጋግሞ በማስመር ባስተላለፈው ግብረመልሥ የቦረቀው። እንዲህ በማንፈጥረው ወይም በማንመራው ወይም በቀጥታ እና እዚህግባ በእሚባል መልኩ በእማናበረክትለት፣ እጅግ በገሀድ የራቀን ሥልጣኔ ዉስጥ፤ የድሮ-ሀያሎች-ነን እያሉ ፊጥ-እንጣጥ ማለቱ እንዲህ ንቀት እንጂ ምስጋና አይገዛልንም። ሀገርአዊ የዝማኔ ምድረበዳነትአችንን ጭቂት ትርጉም እምናፀድቅለት፣ በብዙ ቀላል መንገዶች ቢሆንም፣ በገዛቂል (self-ridiculing) ዐውድ ተንተባትበን ግን አይመስልም። እስካሁን ይሰራ ነበር። ጥንት ቢሆንም እንኳ አድገን ነበር ብሎ ነጭዎች እና ምስራቅዎችን ወይም ከውጭ የመጣን ሁሉ በተለይ ጥቁር እንግዶችን በለጥናችሁ እያሉ መቆጣት እና መጠራጠር፤ በእርግጥ ኢትዮጵያአዊ ስለሆንን አለመመርመር እምንዘለው ስለሆነ በጎልማሳ ኢትዮጵያነት እራሱ ብንፈትሸው ሚጡአዊነት ነው። ባነሳው ሃሳብ አድክሞን ሲያበቃ በጥንካሬው ከእማይቋጨው እመጓ እንኳ ተምረን “ቢኖረንም ጭምት ሀገር ነን” ብለን እንደ እመጓ (ወይም ቆርንቶስ ተራራዋ፤) የትሁት ዝምታ መምረጡም እሚሻል አማራጩ ነው። ያ ሙያ በልብ ነውን አያካትትም። መሰረትአዊ ስነምግባር ብቻ ነው። ዛሬም መሰልጠን ከታለመ፤ ወደ ሙያ በልብነት መጓዝ ይቻላል።
ስንሻገር፤ ድሮ ትልቅ ነበርን እምልበት ስት-ዐውድ የታሪክ ማስተዛዘኛ ሎተሪ ያክል ዋጋ ነው ያለው። በላጭ አቅሙን በመሣት ታሪኩን በእማይገባ መንገድ ገልበን እራሳችንን እምናሳፍርበት ነው። ለእኛ ዕውቅ- ትረካ (narration) ሆኖ የሀገር-ወሬአችን ሁሉ ዣንጥላ ቢመስልም፤ ክፉ እምቅ ጉዳዩ ደግሞ፣ በህቡዕ እና ግንባርሥጋ ስንፍናችን ማቶት አድርጎ እሚሸከም አወራርአችን ነው። ማለትም፤ በስት-ዐውድ ምትኩ ሊኖር የእሚገባ ዳግ-መመርመር (research)፣ አልሚ ትንታኔ እና ፍች ሊመደብለት እሚገባውን ጥንት-ቀር ሥልጣኔአችንን ያቆረቆዝንበት ድሀ አያያዝ ነው።
ሌላው ከቀደመው ተመዥራጭ (corollary) ጉዳት ደግሞ በሆነውአዊነቱ (objective) ገሀድ መሰረት እንደሆነው ሠፊው የስነምግባር ጋጠወጥነቱ አይደለም። ያ፤ የትዝብት እና ስነምግባር ጉዳይነት ላይ የተቀመጠ ነው። ይህኛው ከእዛ በመጉዳት ይርቃል። በአሁን ታሪክአችን እሚጎዳን ነው።
ይህም፤ የድሮ ከፍታችንን በትክክለኛ ዕንቁ መጠቀሻ ዐዉድዎቹ እንዲነሣ አለማስቻሉ ወይም ያንን መሻማቱ ነው። ይህ የድሮ ታላቅነት ወሬአችን፤ በእማይገባው ዐውድ ባለማቋረጥ ሲዘከዘክ፣ የድሮ ታሪክአችንን እምናይበትን ትክክለኛ ማለትም ፈያጅ መንገድ ይወርስብናል። የወረሰን አተራረክ ግን መናኛ መደዴ ነው። ጎዪውን እማያጎዝፍ፤ ጎዳዪውን እሚሞላ ጥሪ አያንጽም። የሠላ እይታም ባለማዋስ አያለማንም። እኒያን አድራጊ ብልህ አተያየቱን ይጋርደናል። የድሮ ሥልጣኔ ክብሩን እንድናጎድፈው ብቻ ያግዛል። በከንፈር ማንቀሣቀሻ ፍፃሜነት ብቻ እሚቀር የራስ አተያይ ምትኩን ፈታጊአዊ (thorough) አገላለጽ ለካ ይከልላል፤ ዓይንም ሌላ እንዳያይ።
ከአልባሌ ዐውድ ጠቀሣው እምናጣው ስለእዚህ በሆነባልሆነው እምናነሳው የድሮሥልጣኔአችን ተገቢውን እና ልዩነትፈጣሪውን የጠቀሳ ዐውድ መሰረቅን ነው። ያ፣ ባለማፈር ብዙ ልሁን እሚል እምቅአደጋ (risk) አለው። ዋናውን የመጠቀሱን አላማ ያዘነጋናል። ከአለፈው የመማር፣ መመርመር እና መቅሰም ጉልህ ጥቅምዎቹን ብሎም ምናልባት አፍ ማሞቂያውን የኩራት ወይም አንፋሽአማአዊ (inspirational) ምንጭነቱን ሁሉ አጥብቦ እና በድግግም እና ተርታነት አኮስምኖ እንዲሁ ይገዳደረዋል። ተፅዕኖአማነቱን (effectiveness) ይሠርቃል። ይህን ስህተት ብንገድብ ምትኩ ብልህ ስለእሚሆን አትራፊ ነው። ያ ምን ሊሆን እንደሚችል ገና ስላልሞከርን አናቅም። ግን፤ ገንቢ አስተዋፅዖ መኖሩ አያጠራጥርም ብለን ምሳሌ ግን እንሞክር።
ለዐብነት ያክል፣ እንደታተመ ወዲያው ተቀንጭቦ ተሰርቆ “መፍትሄ ስራይ” በእሚል የኪስ (A5) የእምነት መጽሐፍ ረዥም መግቢያ ተደርጎ በከፍተኛ አንዴማጥቃት ሽያጭ ስልት በተንቀዠቀዠ ችኮላ ተቸብችቦ ደራሲው በቂ አትርፎበት ወደ አሜሪካ እንደገባበት በጭምጭምታ የእሚነገረው መጽሐፍን ያዋሰው፣ የምህረት ደበበ የተቆለፈበት ቁልፍ ዉስጥ፣ የመላኩ ድኅረ የኢትዮጵያ ታሪክአዊ ሀብትዎች ጉብኝት ሀሳብዎቹ ወልጋዲት (italics) ፅሑፍ፤ ወይም የሙዐዘጥበባት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ተረፈምርት ቆሻሻቸው በትንግርትነት ዛሬም የጠፉት የእነላሊበላ እና አክሱም ግንብዎች እና የአሁን ከተማ አገነባብ ቆሻሻ አወጋገድ ችግርዎች ንጽፅር ወጉ፤ እና እንደ ሁለቱ ያሉ፣ የድሮሥልጣኔአችን አንክሮትአዊ (critical) ትንታኔዎች፣ ትልቅ ጥቅምዎች አሏቸው። ጥር 06 ቀን 2013 ዓም. ሙዐዘጥበባቱ እራሱ በ ኢሳት. ትመ. (Tv) ወቅትአዊ ሀገርአዊ አጀንዳ እሚስተናገድበት አንደምታ መርሐግብር ላይ “ዓለምአቀፍ ማህበረሰብ እና የተዛባ ምልከታ እና ቀጣዩ የቤት ስራችን” በተሰኘ ዉይይት ዳግ-እንደገለጡት፣ ይህ የጥንቱ ብቻ ሳይሆን የቅርቡም የእኛ ችግር የእሚያሳየው ከታሪክ መገንዘብ አለመቻል ነው። እረኛ የነበረው ቅዱስ ዳዊት ትልቁ ሳዖልን በጣለ ጊዜ ከመፎከር እንዴት ይህ ታላቅ ወደቀ? እንዳለው እና አወዳደቁን እንደመረመረው፣ እንዴት ትልልቅ ሥልጣኔዎች ወይም አካልዎች ወደቁ እና ተዘነጉ እሚለውን በአንክሮት መጠየቅ እና ገንቢ ዳግ-ምላሽ (reaction) ማቅረብ ይገባናል፤ ካልሆነ እኛም ወዳቂ ነን፤ አለ። እንደእዛ ጮማ የታሪክ የአጠቃቀስ ዐውድዎች ብዙ እሚጠቅሙን ሆኖ ሳለ እምብዛም እማይደፉ አገላለጥዎች ግን እኒያን ፍሬአማ ዕድልዎቹንታ ያመክናሉ። ለምሳሌ፤ ፅዱ ከተሞች ገንቢ ነበርን፤ ዛሬም እንሁን! እሚለው መፈክር ከተጠቀሰው መበጀት ይችላል። በባህልነት ለልጆች እንዲያ ደግደጉን ሳንገነባ ረብየለሽ እና ደፈናውን ትልቅ ነበርን መፈክር መዘርጠጡን እኒህ ዐብነቶች ያስተኩሩልናል። በማይረባ አያያዝአችን፣ እጅግ ጊዜዘለል የማንሆን – ለእየእከቱ እምንቦርቅ – የዘላቂ ሥልጣኔ ጠንቅዎች ያደርገናል። ያ፤ የሥልጣኔ መውደቅ ምስጅት (recipe) ነው። የታሪክ ዋዛያልሆነ አጠቃቀስ ዐዉድዎቹን በእየአጋጣሚው አሥሰን፣ ቀጣይነትን እና ሀገርፍቅርን እናልማ።
በዝርዝራችን መጨረሻ ደግሞ አንድ እናክል። ያም፤ አጨፍጋጊ ነው። በተለይ ትልቅ ነበርን እሚለውን የህልም ቅቤ መጥቀሱ ብዙ ጊዜ እሚነሳበት ዐውድ ከቶ ስህተት መሆኑ ነው። ለምሳሌ፤ ትልቅ የነበርንበት ዘመን ላይ፣ ሰብዓዊመብቶች፣ ንፅዉሳኔአዊ መብቶች፣ እኩልነት፣ ባህልአዊነት፣ ወዘተ. የሉም ነበር። እኒህንም ጉዳዮች ስንዳሥሥ ወደእዛ ዘመን ዞሮ እንመስለዋለን ስንል እኒህ ግን ያኔ ሌላ ዓለም ላይ በለፀጉ እንጂ በምናነሳው መቼትአችን አልነበሩም። ይህ በጠቅላላው።ድ ስልጣኔአችን ሁሉ የዛሬ ስልጣኔ የነበረ እና የኮሠሰ አድርገን እምንመሰርተውን ዝብ-ዐውድ ያስጠንቅቅልን። ሥለድሮ ሥልጣኔ እናትነትአችን እሚገባውን አገላለጥ አለመጠቀም፤ ያንንም ጅጁ እመርታ፣ ዞሮ መጉዳት ነው። እንደ ትንሽ ወሬ ቢመስልም፤ የድሮውን “ታላቅነት” ለማሻሻል – ቢያንስ ለመቀጠል አለመቻሉ ቢቀር – አጠቃቀሡን አለማወቅም ግን የመረረ አሁንአዊ ኋላቀርነት ነው።
ሁሉም ሲደመደም፤ የአንድ ሩቅ ክንፈዘመን (era) ሥልጣኔአችንን እንደነገሩ ወርሰናል። እስካሁን፤ የቻልንው እሱን በእየአጋጣሚው በተናኝ-ዲስኩርዎች መሀከል መግለጥ መሞከር ነው። ከብዙ መወለጋገድዎች ጋር። ምክንያቱም፤ እንደሀገር እንኳ እማንስማማበትም እየሆነ መቅረቡ በእነእዚህ ቀኖች ተለምዷል። የመለስ ዜናአዊ ወላይታ በአክሱም ሀውልት ምንም አያገኝም እይታ፤ ወይም የምንይልክ ደግ/ክፉ መሪነት ወዘተ. አወዛጋቢነትን እያጧጧፈ ተመልክተናል። ገና ያም ሳይጠልል እንዳለ፤ ይህንን እምንከራከርበት እና የጥንት ዘመን ዓለም የነበረ ሥልጣኔአችንን ግን፤ ሌላውን የዛሬ ዉብ ዝማኔ ለመናቅ እና ተንቀንም ሳለን ላለመሸነፍ ስናስብ ጊዜ አንቅጠረው። በተገቢው ሥልጣኔአችንን ማንሳቱ ብሎም በእማይገባው አለማንሳቱ፤ ሀገርአዊ ዘርፈ-ገፀበረከትዎች አሉት። የጎልማሳ ህዝብነት ምልክት ነው። ሙያ በልብ ብልሀት ነው። ጭምት ሀገርነትም እማይናቅ ነው። የተራ ፉከራ ስንኝ ማድረግ ከገሀድአችን ግጥመቴ (docking) እማይከውን ስንፍና-መገለጫ ነው። ተገቢውን እና አንክሮትአዊውን የመገለጫ መቼቱን (space-time) እሚያስተወን፣ እሚቀንስብን፣ እሚያስተን እና እሚገዳደርብን ነው። የተኛው እና በተሻለ ክብር ሊወረስ የተሰደደው፤ አንዳንዴም በሆነነገር መመለሱ እኮ አይቀርም እሚባለው፤ የጥንት ሥልጣኔአችን፣ በነበረበት እየተከበረ እና እየታፈረ እንዲያገለግል፤ ብዙ ጉዳት ያለውን እማይገባ ወይም ቢያንስ መናኛ እና ባዶክብ (overrated) አጠቃቀም እንድንቀንስ፣ ቢቻል እንድንተው ቢሆንልን፣ ያኔ አንድ እሚጠልል ገሀድ ይታየናል። ባናብላላውም፤ ሣናስበው፤ በድሮው ሥልጣኔ ዛሬ ተዋርደናል፨

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s