Categories
ስለ ቋንቋ አማርኛ (ወይም ይልቁንም አማሊዝኛ) Amhalish

የቋንቋ-አማርኛ ዝማኔ ጥያቄ፣ መሰረትአዊ የሰብእአዊመብትዎች ጥያቄ ነው

About letting you remember Amharic’s modernization is a Human Rights Issue.

በ ቢንያም ኃይለመስከል ኪዳኔ፤ ጥር – የካቲት 2013 ዓም፨

በተለይ ድኅረ-ኩኒፎርም፤ የሰው ዘረፍጥረትን (species)፤ ቋንቋው፣ ከአምላኩ ስር ከእሚታወቅ ማንም እና ምንም ሁሉ ለይቶታል። እንደእዛ ብቸኛ የስነፍጥረት (Creation) መለያው ባይሆንም ከእዛ ሁሉ የተሻለው ያደረገው መለያው ግን የማሠብ ስጦታው ነው። አሁን ሁለቱ አይለያዩም።
እብስልስል (Thinking) እና በጠቅላላው ቋንቋ እጅ እና ጓንት ናቸው። ቋንቋን ተጠቅመን እናስብ እና ዓለሙን እንገነዘብ አለን። ዓለሙን እና ግልአችንንም ለእራስአችን እናስገነዘብ፤ ለታሪክም እንተው አለን። የስልጣኔ መነሻ፣ ሂደቱ እና መጪ-ተስፋው፣ ብርቱ ቀኝእጅ ይህ የቋንቋ ግብዓት ሆኗል። አማርኛም ለብዙዎች ሰው በመሆን ሂደት አፍ መፍቻ፣ ስለሁሉም ነገር መማሪያ፣ መነገጃ፣ ስነእናኪነጥበብዎችን መቀመሪያ እና መሸመቻ፣ የህዝብ አገልግሎት መስጫ እና መቀበያ፣ መተረኪያ፣ ወዘተ. ብሔርአዊ ብጤ ቋንቋ ነው። አፍመፍታት ማንነትን መፈለጊያ (ሰው መሆንን) እና ስልጣኔን መልመድ ያክል ነው። ይህ ሁሉ ምን ማለት ወደመሆን እሚዞር ነው?
በሌላ ጎን፤ ይህ ሰው እሚያደርገን እና ጠቢአችንን (Our future) እሚወስን መሳሪያ (ቋንቋ) በመሆኑ ለእዚህ ቁምነገርነቱ፣ አቻ ምርአዊ የሆነ መስተንግዶ ይሻብን አለ ማለት ነው።
ለአየንአቸው ወሳኝ አመለካከት እና ተግባቦት (Thinking and communications) ክወናዎች በምርጡ መንገድ እንዲረዳን በእሚያስችል መንገድ መበልጸግ፣ መዘመን፣ እና ዝግመተለውጥ መከወን፣ ወዘተ. እሚገባው ነው።
በቀረ፤ የስልጣኔአችንን እምቅ (Potential) እንዲሁም የሠብአዊነት ጉዳይአችንን እሚያሰናክል ይሆንብን አለ። ሁለቱ ደግሞ የሰብእአዊ መብት አይነተኛ ክፍልዎች ናቸው። በስልጣኔ ስር የብዙ መብትዎች ተያያዥነት አሏቸው። በግለሰብአዊ አቅም ብልጸጋ ደግሞ እንዲሁ፣ ብዙ መብርዎች ተሳሥረው አሉ። ቅድሚያ፤ እንዴት የቋንቋ አለመበልጸግ ሰብእአዊ መብትዎችአችንን እንደእሚገዳደሩ እንመልከት።
አንደኛ፤ አመለካከትን መገደብ። አመለካከትአዊ ነፃነት ኅዋአዊ ሰብእአዊመብትዎች (Universal Human Rights) መሀከል የለየለት ቁንጮ ነው። ከቋንቋ መበልጸግ ነጥሎት ደግሞ፤ መብቱን ማክበር ዘበት ነው። ቋንቋው ያለበትን ሁኔታ መርምሮ እና በመከታተል አበልጽጎ ስለእዚህ፣ ገደብ የሌለውን የማብሰልሠል አቅም ለዜጋዎች ማበርከት ህዝብን በማሰብ ነፃነት (ሰብእአዊመብት) ያገኘው ክብረትን መለኪያው አንድ ገሀድ-ሚዛን ነው።
ሁለተኛ፤ የአገላለጥ ነፃነት (Freedom of expression) ቋንቋን በአይነተኛነት ይገለገል አለ። ያልተስተካከለ ቋንቋ፤ የእዚህ ሰውአዊ መብት ጥሠት መከወኛው ነው። በጥበብ እና ዳግምርምር ወይም ማንኛውም መንገድ የመግለጽ ነፃነት የቋንቋን ጥራት ካገኙ የበለጠ እሚከበሩ ናቸው።
ሦስተኛ፤ የባህል እና ማንነት መከበር መብትዎችን ይፃረራል። ማንነት በዋነኛነት የስነሰብእ ፍልስፍና ነው። ባህል ማንነትን ከማግኘት መልስ እሚገኘው ዉስብስብ የህላዌ እና አኗኗር መስተንግዶ መስተጋብር ዉጤት ነው። እነእዚህ ሁለቱ፤ ያለ ጽኑ ቋንቋአዊ አቅም ጥራት ይዘው አይከወኑም።
አራተኛ፤ የመማር እና መሰል ሰብእአዊመብትዎች ይከለላሉ። ካለ ጥሩ ቋንቋአዊ አቅም፤ ያ እንዲሳካ አይታሰብም። ካልተገደበ የአመለካከት አቅም ላይ ደርሶ፤ ሰው እና አንጎሉን ለማልማት፤ የቋንቋ አቅምን ማስተካከል አስገዳጅ ነው።
አምስተኛ፤ የመጭ ትውልድ መብት ይደናቀፋል። ቋንቋን አዘምኖ እና አሻሽሎ አለመገልገል፤ መጭ ትውልድን ለአልጠነከረ የዕድገት ፍልሚያ እሚዳርግ ቸልታ ነው። መጪ ትውልዱ፤ እንደ በበለጠ የስልጣኔ ሜዳ እንዲታገል የስልጣኔ ግብአትዎችን እና ተፈጥሮ ሀብትዎችን ማውረስ እሚያስፈልግ ጉዳይ ነው።
ስድስተኛ፤ የሰብእአዊ መብትዎች ባይሆንም፤ ንጽውሳኔአዊ (Democratic) መብትዎችም እንዲሁ በቋንቋ እሚከወኑ በመሆንአቸው፣ እነሱን ማክበር የበለጠ ነፃ ማህበረሰብ የመገንባት ሌላው እውነታው ነው።
ሰባተኛ፤ አንዳንዴ እሚጠፋ እና የጠፉ ቋንቋዎችን ማዳን እና መጠበቅ የታሪክ እና ቅርስ አጠባበቅ ክፍለ-ግዴታ በመሆኑ፣ በእዛ ዙሪያም የታሪክ መመዝገብ እና ቅርስ መጠበቅ መብትዎች የሰብእአዊ መብትዎች ቅጥያዎች ይሆን አሉ። በተጨማሪ፤ በብዙ መንገድዎቸደ ሰብእአዊ መብትዎችን መንከባከብ፣ የቋንቋ ጉዳይን በንቃት እስከ ተቻዩ ጥግ ደረጃ ድረስ ማስተካከልን እሚጠይቅ ነው።
ከእነእዚህ የመብትዎች እና ቋንቋ ጥብቅ የትስስር እውነታ የተነሳ ምን ግዴታዎች ለመወለድ በቁ?
መንግስት፤ ቋንቋን የመጠበቅ፣ ማልማት፣ መመዝገብ፣ መስፈርት የማውጣት፣ በአግባቡ የመጠቀም እና አገልግሎት ማብቃት፣ ይፋ መመዘኛ ማውጣት እና መተግበር፣ ዝግመቱን መመርመር እና ማዘመን፤ ወዘተ. ግዴታዎች አሉበት። በቀረ ከእነእዛ ግዴታዎች፣ የተዘረዘሩት ሰብእአዊ መብትዎቹን ለመንከባከብ መቻሉ ቅርቃር ውስጥ ይጠመድ አለ።
ስለእነእዚ፤ ብዙ የመብት ማክበር እና ስልጣኔን የመንከባከብ ትትረትዎች፣ መንግስትን በብዙ ግዴታዎች መጠየቁ ህግአዊ መሰረት ቢኖረውም፤ የኢትዮጵያ መንግስት በቋንቋ ዙሪያ ደካማ ግዴታ አፈፃጸም እሚግት ሆኗል። በተለየ፤ ከደርግ መውደቅ ጀምሮ እስከ አሁን።
ዋና ዋና መንገድዎችን ለማሳወቅ፤ ትምህርት እና ዳግምርምርዎች ሀገርአዊ ቋንቋዎችን ቸላ ብለዋል። የቋንቋ መስፈርትዎች የሉም። ለምሳሌ፤ እንግሊዝኛ ወይም ቻይና ማንዳሪንን ማወቅ፤ በተለያዩ ይፋ ዘዴዎች (TOEFEL, HSK ወዘተ.) መስፈርትዎች እሚመዘን እና በትምህርት፣ ስራ፣ እና ዳግምርምርዎች፣ ወዘተ. የተፈተነ እና መስፈርት ያለፈ የቋንቋ ብቃት ማበጀት እና በእዛ መገልገል ይገኝ አለ። በሀገርአችን ቋንቋዎች በደፈናው ከመልመድ በቀረ ምንም ይፋ እና አስገዳጅ መመዘኛዎች የሉም። ቋንቋዎቹን በነሲብ የመጠቀም ሁኔታዎች ደንብ ሆነው እመርታዎች ጎደሎ ሆነዋል።
ስነእናኪነ ወጥ ብቃትን ማሳየት ሳይችሉ፣ በጠቅላላው ደካማ ዘርፍ እንደያዙ በመቀጨጭ ቀርተዋል። አገልግሎትዎች እና መስተንግዶዎች መስፈርትየለሽ እና ያልዘመኑ በመሆን ቀርተዋል።
በተለይ በአሃዝአዊ ሽልፍነለትዎች (Digital technologies) አገልግሎትዎች ወጥነት እና ቀላልነትን አጥተው ቀርተዋል።
በደፈናው የቀረቡት ቁንጽል አብነትዎች ጉዳትዎቹን ያስጮልቃሉ።

ለምሳሌ፤ ከታች ያሉት ሰባት የገጽማያ ምትዎ (Screen Shots) በሰከንድዎች ልዩነትዎች የታሰሡ ናቸው። በተመሳሣይ የኢላማ ግቤት፤ ተለያዪ ዉጤትዎችን እናገኝብአቸው አለን። በሞግሼ ፊደልዎች አለመስተካከል የተነሳ ከእምንሰቃይብአቸው ቅጣትዎች ዉስጥ ከእሚነገሩ ችግርዎች አንዱን ማስጮለቂያ ነው። የመረጃ እኩልነት፣ ነፃነት፣ ቅልጥፍና፣ ዝማኔ፣ ወዘተ.ን እሚፃረሩ የሆኑበት የኢስልጡንነት ዉጤትዎችን ማሳያም ቁንጽል አብነትዎችም ናቸው።

ይህ አላማአችን ስላልሆነ በእዛ እንቋጨው።

ተከትለዱን ጉዳይ ብናጠብብ፤ የአማርኛ ዝማኔ ጥያቄዎች የሰብእአዊ መብትዎች ጉዳይ ናቸው ማለት ነው።
የቋንቋው መዘመን እና መቅለል የእየዘርፉን እድገት በሁለንተናአዊ ግብአትነት ቢያግዝም፤ ቸልታው ግን የህዝብ መብትዎችን መፃረር ነው።
የተጠቀሱትን ሰብእአዊ መብትዎች ለመንከባከብ እና ጉዳትዎቹን ለማከም፤ የሀገር አቀፍ (አማርኛ) ቋንቋ ችግርዎች ጥናትዎች፣ ዉይይትዎች፣ በመጨረሻ የህግ እና (ትልምአግጣጫዎች/ፖሊሲስ) ደንብዎች፣ ወዘተ. ለውጥዎች አስገዳጅ ናቸው።
የነገሩ መክደኛ ነጥብ፤ አማርኛ ለምሳሌ በፊደልገበታዎቹ አይዘምንም ከተባለ እንኳ፤ (ያም እስካሁን ያለው ሀቅ ነው) ያንንው ዉሳኔ በህግዎች እና ደምብዎች በዳግ-ማጽናት የህግአዊነት እውነታን በቋንቋው አለም ማብቀል አስገዳጁ፣ ታናሹ ቅድመሁኔታ ነው።
ሲደመደም፤ መንግስት የሰብእአዊ መብትዎቹን ለማክበር እነወዲቻለው፤ አመለካከትን እሚያበለጽግ ቋንቋ ማበልፀግ እና መንከባከብ መቻሉ፤ በግዴታው ለመከወን ከተቋቋመልአቸው አመክንዮ-ዘ-ህላዌ (Reason d’etre) መሀከል የለየለት አንዱ የግዴታ-ግዴታው ነው። መንግስት ሆይ ጥራት ባይኖረውም፤ ግዴታህ የነበረውን አሽከርነትህን የበላው ጅብ ባለመጮኹ እነሆ እየተገረሰሥን ምን እንበል?

One reply on “የቋንቋ-አማርኛ ዝማኔ ጥያቄ፣ መሰረትአዊ የሰብእአዊመብትዎች ጥያቄ ነው”

[…] አራተኛ፤ የሶስተኛው ችግር ስላልተቀረፈ፤ ወጥ ጽሕፈት ያጣን ግን ፊደል የተሸከምን የግለተቃርኖት (oxymoron) ሀገር ሆነን አለ። ስለእዚህ፤ በእየመስሪያቤቱ ስንሄድ፣ መሠረት እሚል ስም ስንናገር በመረጃ ቋት ወይም ማህደር መሰረት በእሚል በማሠስ አገልግሎት እንዳናገኝ እምንደረግ ሆነን አለን። የፊደል ችግር ባለፊደል ሆነን ያላጠራን ሆነን አለ። በመረጃ አሠሳ እና ማጋራት መሰረትአዊ ሰብእአዊ መብትም፤ እንዲሁ፣ ወጥ ፊደል መጠቀም እምንችልበት ዘዴ ባለመኖሩ፣ መብትአችን ተጥሶብን ባለማቋረጥ እንደተበደልን አለን። በምሳሌነት በቀደመ ልጥፍ የተመለከትንአቸው የምስክ ማስረጃዎችን ማጣቀስ እሚቻል ነው። […]

Like

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s