Categories
መልካም ጥበብዎች Fine Arts ሥነዉሳኔኛ (About Politics)

ደርሦ ደርሦ፤ መች ደርሦ(?)

ጠልቆ፣ አስፍቶ፣ አርቆ (በ፫ቅ. = 3D) መርምሮ፤ ነገርዎችን በተገቢው እቅጭ (exact) ምንጭ ይዞ ሀቀኛውን ጥቅም ስለመገልገል። ወይም ከአጭር ፍለጋ ወደ ስርነቀል (#አንክሮትአዊ) መፍትሄ ስለ መረማመድ፨

፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

ይስማእከ ወርቁ፤ የወንድ ምጥ፤ ላይ ካሉት እጅግ አገልጋይ ግጥምዎቹ፤ [ለእዚህ ጽሑፍ] አንዷ ግጥሙ በእየአውዱ ለጋበዛት ብዙ ታስተምር አለች። በሰካራም ቢመስላትም፤ ፩) [ማንም ሊሰክር ስለእሚችል] ለማንም ትሆንአለች በእሚል። ፪) ስካርን በብዙ መፍታት ስለእሚቻል። ለምሳሌ፤ አንድ አዝማሪ፦ “አሁን ለኔ ማንሰጠኝ ጠጅ፣ እንጀራ አዞረኝ እንጂ!” ብሎ ስካሩ ድህነት መሆኑን አሳውቋል። ፫) ስካሩን ያስጀመረው በ “ጥንስሥሶች” በመሆኑ፤ በአጭሩ ጽሑፍአችን እንደእምንመለከተው (ለማመሳከር በኋላ ተመልሰው ይህን ይዩት) በጥንስሥ ማለት በዉጥን፣ ጅማሮ ወይም መነሻ ነገር መስከር እና በተብላላ ነገር አለመስከርን እሚያስመለክት (ደርሦ አለመድረስ) ሊሆን ይችላል።
ስለእዚህ፤ ተቀንጭቦ ይስማዕከ ወርቁ ይቀጠር።

“…በውሉደ ጌሾ—በጥንስሶች ሠክሮ፤

ቤቴ ካላት ጎጆው—ከበር ተገትሮ፤

አይከፈትልህ ሲለው ለሰካራም፤

ግድግዳውን እንጂ በሩን አያንኳኳም።”

“የእማይከፈት በር” ፤ (ገ.፲፭)፤ አስተኩሮት (emphasis) የታከለበት።

ወደ መነሻጽሑፉ አጭር ኢላማ አሁን እንገስግሥ።
ዋናው የእዚህች ሀገር አሁንአዊ እና ታሪክአዊ (መነሻ) ችግር፤ ከአምባግነና የተሻለ ችሎታ ያለው መንግስት አለመገኘት እና ንቃተህሊናው እና የሀገር-ፍቅሩ በትርጉም-ሰጭ (ንቁ ተሳትፎ) መንገድ እሚመነዘር ህዝብ ማፍራት አለመቻሉ ነው። ቢሆንም፤ በኢትዮጵያ ዉስጥ ብዙ ጊዜ፤ የመሰልጠን ወይም አንዳች ጉዳይ ላይ ለውጥን የማሻሻል ዕድል ተፈጥሮ ያውቃል።
እነእዚህ አጋጣሚዎች ግን ባለማቋረጥ፤ እንደከሸፉ ናቸው። አሁንም፤ አንድ ጉዳይን አንስተን ይህ ዳግ-ሲደገም እና እኛም ስንሸወድ እናስተውል።
በኢትዮጵያ፤ የማህበረሰብአዊ ጉዳይዎችን መቀየር እሚችል አንድ አጋጣሚ የኢህአዴግ. መንግስት መውደቅ ወቅትም መጥቶ ነበር።
ታዲያ፤ ዕድሉን ከመገልገል፤ ወደማሾፍ ወይም መዘባበት እና አናሽ ነገርዎችን መቅሰም ተከውኗል። ያንን ምንም ጠንካራ ነጥብ ቢሆን ከቶ አንዘረዝርም። እናጥብብ እና እምናነሳው፤ ከአጋጣሚዎች ጋር ተከትሎ በእሚፈጠር የአመለካከት ወይም አተያይ ለውጥ ሂደት፤ አብሮ ግን መሣሣትን ብቻ እምንመለከተው ነው።
ለመቀየር ሲባል፤ መተው እሚገባውን ነገር ሲያነሱ እማይገባውን መተቸትን ይመለከታል። ልክ በአይጥ የተነሳ ዳዋዎች እንደእሚሰቃዩት፤ መልካሙን ወይም ቢያንስ መቀየር እማይገባውን መንካት እና ወይም በተሻለ እንግሊዝኛ ምሳሌው “ህፃኗን ከመታጠቢያ ዉሃው ጋር ዉጭ አብሮ መድፋት” አይነት ክወናዎችን ስለመመልከት ነው።
አንዳንድ ያንን እሚገልጡ ጉዳይዎችን እንዘርዝር። በለውጡ ሰሞን፤ መተሳሠብ እና መፈቃቀርን አስተኩረው እሚያስመለክቱ፤ ዘፈንዎችን አደመጥን።
“አራት ኪሎ” እሚሰኘው ደግ አዝናኝ ክወና የነበረበት ዘፈን፤ ፍቅርን አስቀድሙ ሊለን ይነሳል። ዳሩ፤ አብሮ ግን መማርን ከፍቅር ማጣት አጣምሮ፤ መማርን እሚረግም ያስመስለዋል። ልክ ሙዐዘ ጥበባት፤ ዳንኤል ክብረት (ዲ/ን)፤ በሁለት ሀውልትዎች ወግ ላይ፤ የአውራ ዶሮ ዲግሪ ባለው ወጉ ላይ፤ ተምሮ መክሸፍን እንደተቸው ነው። ይኽኛውም፤ ፍቅርን አለማስቀደም እንደ እሚጥል ይሰብከናል። ዳሩ፤ እንደ ሙአዘ ጥበባቱ፤ እሚያወዳድር እና እና በተሻለ አገላለጽ ከመገሠጽ ይልቅ፤ ይኽኛው ግን ተዘባብቶ መመለስን እና ማላገጥን እሚላበሰው ቀለሙ ወይም ድምጸቱ ነው። ስለስርአት መቀየር፤ ስለነገርዎች መሻሻል፤ ስለ ተያያዥ ብዙ ነገርዎች ከመንገር መቆጠቡ የተማረው ለለውጥ አናሳ ግቤት በመሆኑ አስከፊ ያደርገው አለ።

ቀጣይ፤ ተወዳጁ አብነት አጎናፍር፤ “የጥሪ ደወል”፤ ንጥል ላይ፤ አንድነት እና መተሳሠብን ማስቀደም እንደእሚያምንበት ይገልጥልናል። በተቃራኒው ኩራት እና ትእቢትን ወይም መሰል ክፉ ምግባርዎችን አልስማማም እያለ ይተውአቸው አለ።
ዳሩ፤ እንደ ሀሳብ በእየራስአቸው ነጣጥሎ አያነሳአቸውም። የተማረን ሁሉ እሚተች አድርጎ መማር እና መመራመርን፤ እማይጠቅሙ (ቢያንስ በአንደምታ) ወይም የክፉ ምግባርዎች ተያያዥ ወይም ዋስ አድርጎ ያስብአቸው እና ግብዝነት፣ ራስወዳድነት ወይም እራሴ ልስራው ባይነትን (bootstrapping) እዛ እንዳሉ ይጠቁም አለ። ከእዛ በእዛ እንደእማይስማማ ያሳውቀን አለ።

ምስል ማብራሪያ፤ ደግ አዝማችነት (Directing) ያለበት የሙዚቃው ተም. (ተንቀሳቃሽ ምስል) ላይ፤ “ከትእቢቱ” እያለ ሲናገር እሚጠቁመው የትምህርትን እና ዳግ-ምርምርዎችን (researches) መከታዎች መጽሐፍዎችን ነው፨


በናይጄሪያ፤ ቦኮ ሀራም የተሠኘው አማፂ፤ እንዲሁ፤ “መጽሐፍ ዉጉዝ/ሀጢያት” ነው በእሚለው ዶግማው ያልሰለጠነ ጽንፈኛነቱን ይጠቁመን አለ። ከምረራቡ ዓለም መየያገናኝአቸንው መጽሐፍት፤ ክፋትን ያስተምራሉ፤ ስነምግባር ይሸረሽር አሉ፤ የምእራብ ቅኝ አገዛዝ ወዘተ. ናቸው በማለት ይጸየፍ አሉ።
የቦኮ ሀራም ፍልስፍና፤ ከ Equilibrium ፊልም ጸረአቀንቃኝዎች እና የተዋጉለት ትልምአቸው የተቀዳ ይመስል አለ። ሰብእአዊ ስሜትዎችን መንካት እሚችሉ የትምህርት ነገርዎችን ሁሉ ከማህበረሰብ ማስወጣት እሚያልም ደካማ አያያዝ። ያ ፍፃሜው ወደ ጨለማው ዘመን እንሽርትት ነው።
እንዲሁ፤ አውራዶሮ ዲግሪ እያሉ፤ እሚገልጡልን በተማሩት ልክ ስነምግባርም ብርቱ ያለመሆን ነገርን ሲሆን፤ አጣምረው ግን፤ ከመማር ስህተት ጋር መመልከቱ ስህተት ነው። ከመማር ትእቢት፤ ክፉ ምግባር ወዘተ. አይገኝም። በአጭር ምልከታ ግን፤ እንደ ቦኮ ሀራም ወይም “The Father” መጽሐፍተን እና እውቀትን መገደብ እንጀምር ማለት፤ መማር እሚገባንን አለመለየት ነው። ያልተማረም አጉል ኩሩ፣ ትእቢተኛ፣ ሰነፍ ምግባር ያለው ወዘተ. ነው። ማህበረሰብአዊ ለውጥ ደግሞ፤ ዋናው የእዛ ጉዳይ መንሸራሸሪያ እንጂ የአንዳንድ ሰው ውድቀት የጀርባአቸው ያለ ሁለው ገሀድ ክፉ ነው አያሰኘውም።
መማር እና ዳግ-መመራመር፤ የህይወት እና ስልጣኔ መንገድዎች ናቸው። በአጭር፤ ለምሳሌ እንደ ስነልቦና እና ስነስርአትዎች (systems) ባሉ ነገርዎች ማስተካከል እሚቻሉ ነገርዎችን ከመማር የተነሳ እሚመጡ ሀጢያት ወይም ህፀጽዎች አድርጎ መመልከት የከፋ አወዳደቅ ነው።
የቀደመው ኑባሬ፤ መማር እና ግን መውደቅ፤ ተከታታይ ስለሆኑ፤ መማርን እና መመራመርን መኮነን፤ ልክ እውነትን ሲያገኙ፤ ከመቀበል ዳርዳር ወደማለት መሄድ አይነት ስህተት ነው። በትነሽ (ጥንሥስ) ሰክሮ፤ ሙሉውን አለማት። በሩ ላይ ደርሦ በሯን ሳይሆን ግድግዳዋን አለማንኳኳት።
እንጂ፤ አንድ የአውራዶሮ ዲግሪ ትርክትን ተመልክቶ፤ ተዘባብቶ እንዲሁም ፍቅር ይበልጣል ብሎ ወደ ተለመደ አኗኗር መመለስ፤ ዕድልን ደግሞ ማባከን ነው። ደርሦ አለመድረሥ።
ወደቀደመ ቆሻሻ አኗኗር ከመመለስ፤ ይህንን ያለመሳካት አኗኗር መገዳደር፤ መቀየር፤ መሻሻልዎችን ማንበልበል፤ ወዘተ. ሲገባ፤ እጅግ ባነሠ “ድል” “መማር ለምንአችን” መሠል ማፈግፈግዎችን መከወን እማይጠቅም አካሄድ ነው።
ነገርዎችን አጥርቶ ሰልጥኖ ለመኖር፤ መልካሙን ሲፈልጉ፤ አንዱን እርምጃ ከውኖ ዋና ግብን ሳይመቱ መመለስ፤ ደርሦ አለመድረሥ ነው። የስነስርአት ለውጥን ከማጎንቆል፤ የአጭር ትርፍን መሠብሰብ አዙሮን እሩቅ አያደርሰንም። ሁለንተናአዊ የመገለጥ ስካርን እንጂ የጥንስስ መገለጥ ስካርን መግታት እንጀምር። በረዥሙ እና በስምጡ እናስብ። ያም፤ ገደብ የለውም። ገደብ እማያቅ ለውጥ ከሁኔታው ሁሉ ተምረን እናንሳ። እንጂ፤ ነቅሰን አንማር። ያ፤ ሌላውን ያስለቀወቀን አለ እና። ተጉዘንም ግን ባለመድረስ እምንቀጥለው፤ እስከመቼ?

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s