Categories
መልካም ጥበብዎች Fine Arts ሥነዉሳኔኛ (About Politics)

የባህል እና ማንነትን እውነተኛ ጽንሰሃሳብ መገንዘብ፡ የሰብአዊነቱን ደረጃ [Understanding the real Notion of Culture and Identity: the Human Level]

About Ethiopias missunderstanding of Identity and Culture; Someone needs to do countable thing.


bY ቢንያም ኃይለመስቀል ኪዳኔ፤ የካቲት 04፤ 2013 ዓም፨

በአሁኑ የኢትዮጵያ መደበኛ አኗኗር፤ መብል-መጠጥ፣ አለባበስ፣ አደናነስ-ሙዚቃ፣ ወዘተ. ባህል እና ማንነት ናቸው። ምንም ትክክል ስላይደለ፤ ያ ግን የአለመታደል አይነት ነው።


ባህል እና ማንነት፤ ብሄረሰብአዊነት አይደለም። የዘር እና ወል አኗኗር ደንብም አይደለም።

ማንነት እና ባህል፤ እንደቅደምተከተልአቸው ሰብእአዊነት እና ስልጣኔ ማለት ናቸው። አንዳንዴ ማንነት ቀዳሚ ባህል ተከታይ ቢመስልም፤ ተያያዥ እና ለመነጠል ከባድ ጭምር ናቸው። በአጭሩ፤ ፈንክቶ ማየት ቢከብድ በደፈናው ቀጥሎ ይታዩ።


መጀመሪያ፤ ማንነት ምንምን አይደለም? ፩) ፍልስፍና እንደሆነው ሌላ ምንም አይደለም። ፪) ከምንም በላይ፤ የጣምራመንግስት (federalism) ዝብ-አገነዛዘብ (misunderstanding) እንደቀረጸብን የአንድ መንደር በቃይነት እና በእዚያው ስነልቦና እና ስነምደር (geography) ተገዳቢነት አይሆንም። እናስ?


ማንነት፤ ምን እንደሆንን አስሠን፤ እንዴት እራስአችንን፣ ተፈጥሮን፣ ማህበረሰብን፣ አምላክ ወይም ሐይማኖት፣ እና እማይታወቀውን (ኅዋ ጭምር)፣ ወዘተ. ከእራስአችን እምናስተሳሥርበትን መንገድ፤ እና በእዛ ሂደት እና ፍፃሜ እምንወስነውን ሁሉ ገላጭ ነው። ማንነት ሰው መሆን ምን ማለት እንደሆነ ማወቅ ነው። ስለእዚህ፤ ሂደቱም ማብቂያውንም የግድ አንድላይ ከታች ነው። ማንነት፤ ሰው አድራጊአችን ስነስርአት እና ዉጤቱ ነው። የእራስ-ትርጓሜ፣ አኗኗር ደንብ፣ ህላዌ (existence) አገነዛዘብ፣ የአመለካከት (አተያይ) ቋሚ ባህል፣ ወዘተ. ላይ ያደርሳል።
ሲጠቀለል፤ ዘረፍጥረትን (species) ፈልጎ የማግኘት ስነስርአት ነው። የሰው ዘረፍጥረት፤ ሰው ብቻ ነው። ያ ማለት፤ ማንነት ሁሉ በመሰረትአዊነት አንድ ወይም ወጥ ነው። እጅግ ወጥ ከሆነ፤ ሌላ ቅርጸቱ እማይቀያየር መሆኑ ነው። በመቼት (space-time) ከቶ አይዛነፍም። ልክ ከእማይታወቀው ልጅነት እየተጠረቡ ወደመጎልመስ መቀየር ነው። በደፈናው ስንገልጠው ወደ ሠው መሆን ከተመጣ፤ ማን ወደመሆን ተደረሠ ማለት ነው።
በስፋት ባይሆንም፤ እጅግ ረብ ያለው ተከታይ ክፍሉን እናክል። በግል ሁሉም ያንን ከከወነ፤ ቀጥለን ስንጣመር በጋራ እንደ ህዝብ ማንነትን እምንመለከትበት መንገድ ምን ይሰኝ ወይም ወደምን ያደርሰን አለ? ወደ ባህል። በመጀመሪያ፤ ባህል ማንነት ሳይሆን ማንነት ባህል ነው።


ማንመሆንን ስናስሥ፣ ሰብእአዊነትን እናገኝ አለን። እኛ ሠው ነን። ስለእዚህ ሰው መሆን ማንነትአችን ነው። ያንን በተፈጥሮ እና ሃሳብ (ፍልስፍና) ጫካ ተተክሎ አስሠን አገኘን። በአመለካከት እና ግንዛቤው ጠርበን ቆረጥንው። ወደ መንደር ይዘንው ተመለስን። በእዛ መሠረት፤ እያሳየን እምንኖረው የተገነዘብንውን ማንነት ነው ማለት ነው። ያ፤ ባህል ነው። መወጠኛው የማንነት ግንዛቤአችን ሆነ ማለት ነው።
ማለትም፤ ማንነትን እንደተረዳንው፣ እንኖር እንጀምረው አለን። ሂደት፤ ባህል ያደርገው አለ። ማንነት ባህል ከተደረገ፤ በእምናውቀው ሁሉ ያ የተገኘ የማንነት ዕውቀት ወደቀጣይ ለውጡ ይሻገር አለ። ያም፤ የስልጣኔአችን አይነት ወይም ቀለም ወይም መሠረቱ ይሆን አለ።
የመሠልጠን መሠረት መሠረተ-ማንነት ነው። ሰው እራሱን በተረጎመው ልኬታ፤ ስልጣኔውን አበጀ።
የሠብእ ሁኔታን ከተፈጥሮ፣ ታሪክ፣ ንጽጽር፣ እና ሌላ ግብአትዎች ዘረሰው ከተረዳ – ማንነቱን ያ ከአበጀ – ያ ስርአት እሚኖርበት ዘዴ ይሆንለት ከሆነ – ስልጣኔው ሌላ አይደለም፤ ያ በደፈናው ነው። የዘመኑን ህይወት ማሻሻያ ሽልፍኖት (technology) ዉስብስብነትን ከቀነስን፤ ያ የ መሠረተ-ስልጣኔ ፍቺ ነው። ማለትም፤ መሠልጠን ተጨማሪ ቢኖረውም ከማንም እና ምንም በላይ (እጅግ በትልቁ) ባህል ነው ማለት ነው። ያ (=ስልጣኔ) ማንነት እና ባህልን የተሳሠሩበት ዐውድ ሆነ።
ከእዚህ በመነሳት፤ የሰብእአዊ መብት፣ የአመለካከት እና አገላለጥ ነፃነት (freedom of thought and expression)፣ የግለሰብእ አርነት (freedom)፣ የሃብት ወይም ስነምጣኔ ነፃነት፣ የመንግስት እና ማህበረሰብ ግዴታዎች፣ በጠቅላላው የተለያዩ መብት እና ግዴታዎች፣ ይመሰረት አሉ። በእዚህ ደንብ፤ አኗኗር ይቀረጽ አለ።
ከማንነት ፍለጋ ሰብእአዊነት፤ ከሰብእአዊነት ወደ ባህል፤ ከባህለወ ወደ ስልጣኔ፤ ከስልጣኔ ወደ ዘመንአዊነት ይደረስ አለ። እማይዛነፍ ግንኙነት (ማለትም ልዩአዊነት) እና አንድአዊነት (ማለትም አለመነጣጠል) በእነእዚህ አለ።
ማንነትን ዝብ በማድረግ፤ ባህልን አደናቃፊ አድርጎ በመረዳተደ፣ ከመሠልጠን መቅረት እሚቻል ነው። ልክ እዚህ፤ በተለይ በአለፈው ከሩብ እየጨመረ በመጣው ምእመት፣ በኢትዮጵያ የሆነው እንደሆነው።
ማንነት፣ በተለይ በፕሮፓጋንዳ ተደጋግሞ ተዛብቶ ስለተነገረ በሀገርአችን ገደብን ተላብሷል። ዝብ-አፈታቱ (misinterpretation) ወደ ቁማር አምጥቶ ስልጣኔን እና ሰብእአዊነትን ከሀገሩ ቀንሷል።
ሲደመደም፤ ሦስት ስህተትዎች አለን። አንደኛ ሰብእአዊነት ማንነት ነው። ያንን ስተን በዘርአዊነት-የማንነት-ትርጓሜ እንደምታ ዜጋዎችን እናሳድግ አለን። በእዛው ትልም እንጎለምስ እና በአመለካከት እና አቅምም እንገደብ አለን። ከማንነት እና ባህል ፍችአችን ዉስጥ፤ ያን ሰብእአዊነት እና የስልጣኔን መሰረት-ሃሳብ መከልከሉ ትልቅ ዞሮ-ተኳሽ ጥፋት ነው። ሁለተኛ፤ የቱም ዘር፣ የቋንቋ እና ኑሮዘይቤ (lifestyle) ልዩነትዎች አሉት። ያ፤ ከማንነት አንዱ አላባአዊ እና ኢምንት መገለጫ እንጂ ሙሉ ፍቺ አይደለም። ይህን መሳት ተያያዥ ጥፋት ነው። ሦስተኛ፤ በአለም የትም ያሉ ዘመንአዊ ብሄረሰብዎች ሁሉ የዘር ክፍለ-ማንነትን ሲያስተምሩ የጋራ ጉዳይ አሉአቸው። ሰውነትን እና ስልጣኔን ማስተማር እና አብሮ ማበልጸግ ይኖርአቸዋል። ዘር ቢኖርአቸውም፤ ሰብእአዊነት እና ስልጣኔ አይደናቀፍም። ነገርግን፤ በእዚህ የእኛ ትውልድ የማንነት ግንዛቤ፤ ትኩረት በዘርነት እንጂ ሰብእአዊነት ፍለጋ ላይ የለም። ማንነት ዘርነት፤ ባህል ደግሞ አኗኗር ዘይቤ እና ደንብ (norm) ተደርጎ ጠቃሚ መንገድ ተስቷል።

በመጨረሻ አንድ ነጥብ። እንደብዙሃኑ የምድረገፀ ሀገርዎች፤ ኢትዮጵያ የተለያዩ ህዝብዎች ስብጥር ናት። ዉስጧ፤ የቋንቋ እና የአኗኗር ዘይቤ (life style) መለያየት አለ። ትክክለኛው የባህል እና ማንነት ፍቺ ግን በእዛ ዙሪያ የተቋቋመ የለም።
ዘርነት (being/doing a race)፣ በማንነት ፍቺ ተለውጧል። ባህል እንደ አለባበሥ፣ አጨፋፈር፣ ሰርግ ስነስርአት፣ አመጋገብ፣ ወዘተ. ያሉ የእለትከእለት እንቅስቃሴዎች አላባአዊያን ወይም በጠቅላላው የአኗኗር ዘይቤ (life style) ፍቺ ተቀይሯል። እኒያ፤ በታሪክ፣ ሀብት (resource)፣ እና ከባቢ (environment) ወዘተ. እሚወሰኑ ናቸው። ለምሳሌ በቆላ ነዋሪ ህዝብ ቀለል ያለ አለባበሡ፣ በእንስት አብቃይ አካባቢ የእንሰት ዉጤትዎች አመጋገቡ፣ ወዘተ. ባህል እና ማንነት ሳይሆኑ፣ የተፈጥሮ ሀብቱ እና ከባቢው ተፅዕኖ ናቸው። ማንነቱ እና ባህሉ የአመለካከት እና የህላዌው አረዳድ እና ከተገለጡት እነእዚህ አጋጣሚዎች በይበልጥ የረቀቀ ግን የስልጣኔው ወደብ ላይ እሚጥለው ነው።
ወደእኛ ስንመለስ፤ ይህ ሁሉ መሰረትአዊ ስህተት በኋላቀርነት ተቋቁመን ያለመሰልጠንአችን መሰናክል ነው። ከእዛ ባሻገር፤ የጠብ፣ ክርክር፣ ጥላቻ፣ ክፍፍል፣ ወዘተ. ምንጭአችንም ሆኗል።
ዘመነ ማንነት እና ባህልን፤ ማለትም ሰብእአዊነትን እና አብሮት እሚሄደውን ነፃነቱትን፤ ማልመድ ከመሠልጠን ቀድሞ አስፈላጊ ግቤት ነው። ያንን ከማስተካከል በተጨማሪ አንድ ነጥብን እናክል።
ሁሉም በእየዘሩ ዉስጥ ማንነት እና ባህልን እየሻጠ ከሆነ፤ ዘርነትን ያላተሞረ ከባህል እና ማንነት ዉጭ በኑባሬ ኦናአዊነት (existence vacuum) ሊጣል ነው። ስለእዚህ፤ መሀከል ሀገር ለእሚገኙ ዜጋዎች፤ የተሟላ ቢያንስ አማራጭ ማንነት እና ባህል ማብቀል እና (ካለ) ማጠንከር ይጠቅማል። ያ፤ ተባራሪ (corrollary) ጥቅም አለው። በሀገረሰቤ ዘንድ ባህል እሚባለውን ወይም የተባለለትን የአኗኗር ዘይቤን በተሻለ ዘመንአዊ አረዳድ ለመተካት ወይም ባለው ላይ ለማከል እንደ መንደርደሪያ ይሆን አለ። አብሮ፤ በመሀከልሀገር እሚያድጉትን ከባይተዋርነትን ለማስታገስ እና በሂደት ፍቱን አድርጎ ለማከም ጠቃሚ ነው። በእርግጥም፤ የእየዘሩ “ባህል እና ማንነት” ካለ፤ ከእነእዛ ርቀው በከተማዎች እሚያድጉ፤ “ባህል” እና ቋንቋ እማይገነዘቡ፤ ከሆኑ ማንናቸው?፤ ባህልአቸውስ?፤ ስንል መልሱ ግርታ አለው። ምክንያቱም፤ ማንነት እና ባህል ዘርነት ከሆነ፤ (ለዘርነት ተከታይዎቹም ጭምር) የሀገር ማንነት እና ባህልስ እንዴት ይገኛል? መንታ ማንነት (double identity) የስነልቦና በሽታ ነው። አንድ ቋሚ ባይሆንም ማለዘቢያ ሳናብራራ በአጭሩ እንጠቁም።
ቢያንስ በአብዛኛው ወይም በብዙው ዘር የጋራ የሆኑትን የማንነት እና ባህል አገነዛዘብዎች ወደሀገር ማቅረብ እሚገባ ነው።
ስንጠቀልል፤ የተማረ የማንነት እና ባህል አመለካከትዎችን መገንባት ግድ ይለናል። በቀኑ መጨረሻ ማንነት፤ እንዳልንው ከሰብእአዊነት ከተያያዘ የስነምግባር (ethics)፣ የህላዌ ደንብ (existence’s norm)፣ ወል ስነልቦንታ፣ የአመለካከት አግጣጫ፣ የአተያይ ልማድ፤ ወዘተ. በመሆኑ እኛ ወደ ዘርነት ስላወረድንው፤ ከጥንትአዊ የማንነት አረዳድዎች ሁሉ አንሰናል። ሰውን ሁሉ ማክበር፣ መፈቃቀር፣ ብልህ መሆን፣በአስተዋይነት፣ እርጋታ፣ ታታሪነት፣ ታጋሽነት፣ ወዘተ. እሚሰኙ ብሉይ (classic) የማንነት እና ባህል አገነዛዘብዎችን እማናተኩር ወደ ጭፈራ፣ ልብስ፣ አበላል ወዘተ. የታጠርን እና መሠልጠንን ያራቅን ሆነናል።
ይህ ሁሉ የባህል እና ማንነት ዝብአመለካከትአችን ሁሉ ሲታይ፤ ዘመንአዊ ሰብእአዊነት እና ስልጣኔ፤ መሀከልአችን ተሰምጦ ቢፈተሽ አለመኖሩ አያስገርምም። መዉጫ መንገዱም ግን እነሆ እንደእዛው፨

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s