Categories
ሥነዉሳኔኛ (About Politics)

ረብ-አምጣ-ዝም ታላቅነት እንደ የስልጣኔ ታናሹ መሠናክል

Regarding the insufferable, and mismanaged, utterances of Ethipian old civilizations as obstacle to the present-day common psyche and benefits.


ጥር 2013 ዓም፨

“ትልቅ ነበረን፤ ትልቅም እኖናለንi”

ታላቅ ነበርን…
በእየቀኑም ቢርበን፤
ትልቅ ነበርን…
መቶሚሊዮን+ ድሃዎች ነን።
ታላቅ ነበርን…
ዛሬም አብረን ተኝተን።
ትልቅ ነበርን…
ለዓለም ለማኙ ነን።
ታላቅ ነበርን…
ትልቅ ነበርን?

--- & ---

ቢንያም ኃይለመስቀል ኪዳኔ፨

እጅግ ቢያንስ አማካኙ – ከኢትዮጵያ ህዝብ – የጥንትአዊ ሀገሩ ስልጣኔ ወሬ ከተነሣ፣ ‘ልቡ ቅልጥ፥ ወኔው ልጥጥ ፥ ምድርአለሙን ላነዋውጥ” ይልበታል። በመሠረቱ፤ ደግ እና አጋዥ እውነታ።
ዳሩ፤ እኒህ የሀገርአችን የድሮ መደብአዊ ትትረትዎቿ፣ ከታሪክ መዝገብ ፈትልከው ወደትውልዱ እሚነፍሱት በትዝታ-ዘፈን-ደንብ ነው። ታሪኳ የታሪክ-ማስተዛዘኛ-ሎተሪነት ዋጋው ብቻ የናረባት ሀገር፤ በእዚህ የታሪኳ አረዳድ-ባህሏ ሠፊ ጉዳት – እንዳልንው ጥቅምም ጭምር – አላት። ጥቅምዎቹ፤ የዜጋአዊያን (civilian) የሀገርፍቅር ስሜት እና ተነሳሽነት፤ ህብረት እና ዉህደት፣ ናቸው። ተደጋግሞ እንደእሚተቸው፤ ታሪክአዊ ትምህርት-ቀሠማ ግን እጅግ ኢምንት ሆኗል። ቢያንስ በደንብ ስላልተማርን’ መካከለኛ ደረጃ እናድርገው።
ከእነዚህ ዉጭ፤ የኢትዮጵያ ድሮ-ቀር ስልጣኔ ዛሬ በተለመደው መንገድ በእየስፍራው ሲወራ፣ እጅግ ሠፊ ጉዳትን እያስከተለ ያለ ነው። እንዴት?
(ነብስ ይማር) መስፍን ወልደማሪያም (ሊቀልሂቃን/Prof.)፣ እንጉርጉሮ ን እንዳንተራሷት ጠቅላላሃሳብ፤ በዘመንአዊ እና ሰብእአዊነት ስልጣኔ እና አኗኗር ሚዛን፣ ኢትዮጵያ ጥንስስ አጥታ እንደ አንቡላ ሰርጋአለች።
ልክ እንደ መጽሐፍአቸው ሽፋንስእል (ተመሳሳይነት ያላቸው አልወለድም ሽፋንስእል ጭምር) የሀገርአችን ደካማ ሁኔታዋ ተካዥ አድርጎን፤ አበሳጭቶን “ተስፋ-አስቆራጭ” ሆኖ ያገኘናል።
በእዚህ ብሔርአዊ እድሜጠገብ አረንቋ፣ ባለማቋረጥ ተከብበን፤ በጥንት-ቀር ስልጣኔ ባለማቋረጥ የመብከንከን ጉዳይ ምርጡ የሀገር ስሜት መንገድ እማይሆንበት አጋጣሚ አለ። ተራማጅ፣ የተራመደ እና አንክሮትአዊ (Critical) አረዳድ በድሮ የታሪክአችን አረዳድ መጨመር አለበት።
ያ ለነን አይሆመም?
ብዙ ተቃዋሚዎች፣ መሪዎች፣ ሐይማኖተኛዎች፣ ተጽዕኖ-ወላጆች፣ ጸሐፊዎች እና በእየዘርፉ ወደአደባባይ እሚቀርቡ እና መደበኛ ሀበሻዎች፤ በትልቅ ነበርን – የህልምቅቤ – እጅግ የታጠሩ ናቸው፤ ሊሻገሩትም አይሹም። ከየትከየትኛዎቹ አመክንዮዎች ጀርባ አሉ? አራት ጎራዎችን እንይ።
አንደኛ፤ በደፈናው፣ በያ ነጥብ ዙሪያ የተንበለበለ ደጀንነትን አስመልካች ስሜትአቸው፣ መደበኛ የአብሮታ (belongingness)፣ ማንነት (identity) እና ወል ስነልቦንታ (common psyche) መፍጠሪያ – እና ጭፍን ቢሆንም የፍቅረ-ሀገር ምንጭ – ስለሆነልአቸው ነው። ለእነእዚህ፤ ድሮቀር ስልጣኔው የሀበሻን እና እራስአቸውን ጥንትአዊ ታላቅነት እሚመዙበት አንጡራ የብሔርአዊ ካዝና ጎተራአቸው ነው። ማለትም፤ ለእነሱ በምንም መንገድ ጥንት-ቀር ስልጣኔው መንቆለጳጰሱ አይነኬ እና በቂ መሆን ያለበት ጉዳይ ነው። ምድረቀደምትነት የአሁን ምድረቀዳሚነት ሆኖ ያጠግብአቸዋል።
ለሌላዎቹ፤ በመምራት እና ማስተዳደር ክሂሎትአማአዊ (technical) ጥበብ ነው። በአሉታ ወይም አዎንታ፣ ያንን የድሮ-ታሪክ እየነቀሡ፣ በተለይ ከላይ የቀደመውን መንጋ አይነት ግለሰብ(ዎች) አረዳዱን በተለመደ ታላቅ-ነበርን ትርክት መግበው በ ማነሳሣት፣ አቃርኖ-ማስነሣሳት፣ ማስተባበር፣ መሸወድ፣ ብቻ ተከታይ በማድረግ እንዲቆይልአቸው እሚያነሱት አንድ የአመራር ዘዴአማአዊነት (strategy) ነው።
ሦስተኛው፤ አዲስ ለውጥን ጠዪዎች ናቸው። የተለመደውን የጉዳዩን አረዳድ ሳይዛነፍ በማስቀጠል እጅግ ልዩ እሚያገኙት ወይም እሚያስገኙ እሚመስልአቸው አሉ። ወይም አዲሱ ነገር ያስፈራአቸው ወይም አስጊ ሆኖ ይታይአቸው አሉ። ወይም ሳያስቡት የመሪዎች በተለይ ፕሮፓጋንዳ አገልጋይ የሆነ አተራረክ ይንፀባረቅብአቸዋል ወይም አዲስ አሊያም የተሻለ መፍጠር ያቅትአቸዋል። ስለእነዚህ በማለት – በተለያዩ አመክንዮዎች – አዲስነገርዎችን (በጽንፈኝነት) በመጸየፍ ብቻ ያለፈ ታሪክን ጤናቢስ-ዘብነት ይቆሙለት አለ። አዲስ ዝማኔ መመስረት የድሮውን ከቶ መደምሠስ ብሎም መዳፈር ለስእዚህ ጋጠወጥነት ይመስልአቸዋል። ከታሪክ የራሱ የታሪክአችን ምስክርነት በዘለለ እነሱ ሌላን በመከልከል እሚከላከሉት ካልሆነ ዋጋየለሽ ተደረገ አንደምታአቸው ነው። እነእዚህ፤ በደፈናው፣ የዋህ ወይም በቆየው አረዳድ ለግልአቸው ተጠቃሚ የሆኑ፤ ግን በጠቅላላው ለለውጥ እማያግዙ ናቸው።
አራተኛ በመጨረሻ፤ በተለይ ከስነውሳኔ (politics)፣ እና መደበኛ ዜጋዎች በተለየ፤ የእምነት ጉዳይዎች ላይ እሚገኙ ጥንትአዊ ስልጣኔአችንን አፍቃሪዎች ደግሞ የጥንቱን ስልጣኔ እሚናፍቁት እና እሚንከባከቡት በተለየ መንገድ ነው። አንዳንዴ፤ ጭራሽ የጥንቱ ዛሬ ወይም በጠቢአችን (our future) ዳግም እሚመለስ ነው ብለው እሚያምኑ አሉ። ይህኛውን፤ ይዘትነቱ ከእምነት ከመያያዙ አንፃር ከመኮነን ቢዘሉት ይመረጥ አለ። ዳሩ፤ የመጨረሻው አስተያየትኤ (commentary) የሀይማኖት እና ተያያዥ ስልጣኔ፣ እንደ ወቅቱ የግሪክ ወይም ሮም ጥንት ስልጣኔዎች ሁለንተንአዊ እና ዘመንአዊነትን ጠንሳሽ እንዳልነበር ተረድተው ስለእዚህ ፍፁም አድርገው መውሰድ እንደእማይገብአቸው ቢያውቁት መልካም ይሆነናል። ዞሮዞሮ፤ እንደ እይታ፣ መሀከልአችን ያለ፤ የድሮስልጣኔአችን አንዱ (ምንምቢሆን አትንኩኝባይ) ፍቺአችን ብለን እምንወስደው ነው፤ ተወደደ-ተጠላም።

ሲደመደም፤ እነእዚህ፣ ጥንትአዊ ስልጣኔውን በቀና ተመልክተው፣ ወይም በአንዳች የጉዳይአቸው ሹፈራ የተነሳ፣ ጥንትአዊት ኢትዮጵያን በታሪኳ አግዝፈው ያያሉ፤ ይሰብካሉ፤ ያስተምራሉ፤ አማራጭ ወይም የተለየ አተያይ ብሎ ነገር አይስማማአቸውም።
ጠቅላላ የፍቅረ-ታሪክ ስሜቱ ብቻ ሲታይ፤ ያ፤ በአንዳንድ መሰረት ደግ ነው። ዳሩ፤ ብንከተልልአቸው ችግር አብረው እሚሰጡን ናቸው። ወርቅአማ የተምኔት (utopia) ድባብ ከእሱ አመንጭተው በመሳል እና በሀሰተኛ ከፍታ በእሚያሰርጉ ተጽዕኖዎች አጥምደው ሊያስቀሩን ይችላሉ።
እሚከላከሉት ታሪክአችንን ሳይሆን፤ በእሱ አረዳድ ስር አሁንአሁን የተቋቋመ የስካር መንፈስ መሰል ውስጥ የእሚጥል እማያድግ ቆይታአችንን ነው። የምናብቴ ሐሴት (fantasy joy) ከገሀድ እይታ ዘግቶ እንዲያጥረን። አብሮም፤ ለውጥን እሚከላከል፣ (የአለፈ) ስልጣኔ-አምላኪ የስልጣኔ-ከልካይ ያደርጉናል። በምድረበዳ (Arab) የተመሰረተ የ50 ዓመት ስልጣኔ የምድር መናኸሪያ እና በአለም አምስተኛው ማርስን የጎበኘ ወይም በ300 አመት ታሪክ አለምን እየመራ ያለ ወዘተ. የዛሬ ስልጣኔ አይደለም። ዳሩ በእነእዚህ አተያይ እንዲሁ ከእነዛ እኩል አራት ሺህ አመት ዞረን በደፈናው በማት በደፈናው አለቅጥ መርካት አለብን።
ለእዚህኛው ቀንአችን፤ የጥንትአዊ ስልጣኔን አሁን በተለመደው በተለይ የሁለተኛዎቹ ጎራዎች (ፕሮፓጋንዳ) መንገድ እየጠሩ ዝምብሎ እንደዋዛ ጥንትአዊነቱን በማንቆለጳጰሥ እና በእዛ ፍቺ የዛሬን ተጨባጭ-ገሀድ ጠቅልሎ በመዝለል ለተካኑት፣ እንዲያ መጠቀሙ ያለውን ጉዳት ከጥቅሙ ለመሠንተር እንዲችሉ እይታ ፈልቃቂ ጥያቄ እናብቅልልአቸው።
“በጣም ተለምዶ ከተሰለቸው የስሜት ማንቃት እና የተያያዙት ጥቅምዎቹ ባሻገር፤ የእዚህ ጥንትአዊ የስልጣኔአችን በተለመደው መንገድ ደጋግሞ ጥሪ እና ምልኪያ (cult) ማስከወን ምን ተጨባጭ ረብ አለው? በእዛስ ይቁም ወይ?”
እሚመስለው፤ ምላሹ ረብየለሽነት አለው ነው። ከተለመደው ጥቅም በላይ ከሌለው፤ ትረካው ሁሉ ረብ-አምጣ-ዝም ነው። ያ፤ ወደፊት ለመራመድ አንድ መሠናክል ነው። በእርግጠኝነት፤ አሁን የተለመደው ሀገርአዊ የታሪክ አተያይ አካሄድ መቀየር አለበት። እስከአሁን ያደረሰን፤ የድሃድሃነት ላይ ብቻ ነው። ከእዛ በላይ በዝብዘን ልንጋልበው ግን የእራስአችን የሆነ ነው። እሱን ከማምለክ የበለጠ የማከሉን ነገር ማስቀደሙ አስገዳጅ ነው።
የሀገር ሹፈራ መንገዱ የዉጤትአምጣአማ (tactical) ስልትአማነትን በጉዳዩ እንዲጨብጥ፤ ረብ-አምጣ-ዝም ጥንትቀር ስልጣኔን ማስመለኩ መቀየር ያለበት አካሄድ ነው። አንድም ረብየለሽነቱ በዘመንአዊ እና አንክሮትአዊ አተያይ ረብእንዲያቀርብ አንድም የዝግመተለውጥ ጉዞን ለማሠናከል እንደ ደፈጣ ተዋጊ እሚወረወር ፈንጅነቱን ለማስቀረት ወይም ቢያንስ ለማስታገስ።
መቋጫው፤ ማታለያነት፣ ዝማኔ ከልካይነት፣ ሀሰተኛ ተምኔትአዊ ምቾት መፍጠሪያነት፣ ተራ-ቅጽአዊነት (formality)፣ እና ነገ ሳይደርስ እየተነነ እሚቀር የስሜት ደረጃ ላይ፣ የድሮ ታሪክአችን ልኮት (reference) እንዲውል ብቻ መዋል የለበትም። በምትኩ፤ አንክሮትአዊ አተያይ፣ የዘላቂ ለውጥ መነሻነት፣ እና ጸር ሳይሆን የዝማኔ-ጓደኛ እንዲደረግ፣ ወዘተ. ምሁርአዊ የታሪክአችን አተያይዎቹ ወደ መደበኛዎቹ ዜጋአዊያን (civilians) ይወረድ። የአኗኗር ዘይቤ ባህል፣ ተጨባጭ እንቅስቃሴ፣ ምሉዕ ምስጢር ብተናው፣ ጠቃሚ ግኝትዎቹን ፀሐይ-ፊት ለሁሉ ዜጋ ዝርጋታው፣ ዘመንአዊነት-አጋዥነቱን፣ ጉድለት እና ክፉ ጎኑን ጭምር መማሪያነትን ማገልገሉ፣ አንክሮትአዊ ትንታኔን፣ ቅጥያ ፈላጊ እንጂ ፎክረው እሚያልፉት ማብቂያ ያልነበረነቱን፣ ለእየ ኩነት መርሀግብሩ ማሟያነት ወይም ማማሟቂያነት እሚቀጠር ለመሆን ብቻ እንደእማይገባው፤ በጠቅላላው ረብ-አምጣ-እንኩ አሽከርነትን እንዲችል እና የጨፈገገ ገሀድአችንን መርዳት ባለበት መንገድ የጥንትአዊነት ትረካ ከአዲስ ይወለድ፨

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s