Categories
መልካም ጥበብዎች Fine Arts

አማርኛ ጭምቅ በ ዲናውመንግስቱ፤ አምላክ እሚሰጥአቸው ዉብ ነገርዎች | Amharic Summary of Dinaw Mengistu’s, The Beautiful Things that Heaven Bears [በ እንግሊዝ “የአብዮቱ ልጅዎች” (Children of the Revolution) ተብሎ የታተመ።

የዲናው መንግስቱ እውቅ መቀደሻ ልብወለድ አማርኛ ጭምቁ፨

ትርክት ጭምቅ (story summary)፤

[አበልሺ ደወል | Spoiler Alert]


በ ቢንያም ኃይለመስቀል ኪዳኔ
ታህሣስ ፣ 2013 ዓም. ፣ ወልቂጤ፨

አጭር መግቢያው፦


ሠፋ እሥጢፋኖስ በለጋ እድሜዎች ከደርግመንግስት በማምለጥ ወደ አሜሪካ ተሠድዶ፣ በድሀ መንደር በሥደተኛነት ሲኖር፣ አጠገቡ የገባችን ነጭ ሴት እና ጓደኞቹን ህይወት እየዳሠሰ እሚራመድ የትርክት ጉዞ ነው፨


፪) ክፍል አንድ፦ የትርክቱ ጭምቅ በእየምዕራፉ


 ምእራፍ አንድ

ሦስት አፍርቃአዊ ፍልሰተኞች (ኢሚግራንትስ) አሜሪካ ዉስጥ እኩል ከዛሬ አስራሰባት አመቶች በፊት ደረሡ። ብዙሳይቆይ፣ ተመሣሳይ ስራ ተቀጥረው በእዛ ተዋወቁ። ነጩ ቤተመንግስት ፊትለፊት ባለው የጣሊያኖቹን የሜዲቺ ቤተሰቦች ህንፃን ለማስመሰል ተሞክሮ በተገነባው በ ካፒቶል ሆቴል፣ እንደ ተንከባካቢ-ሰራተኛ (ቫሌት) ተቀጥረው ነጩን ቤተመንግስት ከቅርብርቀት ለመመልከት እሚመጡ ብዙ ተሥተናጋጅ ቱሪስቶችን ሲያስተናግዱ በሚገባ ተግባቡ እና እጅግ የተቀራረቡ የልብጓደኛሞች ሆኑ።
ዛሬ ላይ፣ ኢትዮጵያአዊው እስጢፋኖስ የልእለሱቅ (ሱፐርማርኬት) ባለቤት ሲሆን፣ ኬን (ኬኔት-ኬንያአዊው) መሐንዲስ እና ጆይ/ጆ-ጆ (ዮሴፍ ካሃንጊ-ኮንጎአዊው) ደግሞ አስተናጋጅ ነው። እሥጢፋኖስ በከፈተው ልእለሱቅ (ሱፐርማርኬት) መደበኛ ሸቀጦች እሚነግድ ሲሆን ቀለልአድርጎ እንዳሻው/እየተዘናጋ እንጂ በጥርስነክሶ-መታተር እሚሰራ አይደለም። በተለይ በቅርቡ እጅግ ሠንፎ በወር አስርቀኖች ያክል እሚዘጋበት ጊዜ ሁሉ ሲኖር፣ በደንብ የሠራ ቀን ቢሆንም ከአራትመቶ ዶላሮች በላይ ገቢ አያገኝም። ይህ ትልቁ ገቢም ከሳምንት አንዴ በ ሎጋን ሰርክል ዙሪያ በታደሱት መንደሮች ለሚኖሩት አዛውንቶች እና እሚያመጧቸው ጨቅሎቻቸው ከሚሸጣቸው ሸቀጦች ነው። ይህ ንግዱ እንዲህ ደህና በሚያገኝለት ቀን ደስ ብሎት አሜሪካን እየወደደ፣ ተስፈኛ ሆኖ፣ የከፋም ስላለ ይህ ሃገር ምርጥ ነው በማለት እያንቆለጳጰሠ ሲመለስ፣ ሌላዎቹን በዢ ቀኖች ደግሞ ጥቂት ወይም ዜሮ ሲሸጥ አሜሪካንን እየረገመ ይመለሳል። ጓደኞቹ በተለይ ኬኔት ጠንክር ብለውት እንደመከሩት እና እንዳበረታቱት እንደተሟገቱት ነው። በተለይ ጁዲት ከሠፈሩ ከለቀቀች ጀምሮ ግን አለመክፈት፣ ወይም ደንበኛ በማይመጣበት ሠዓት ከፍቶ ወዲያው መልሶ መዝጋት እየለመደ ነው። እና፤ ገንዘብ ጠፍቶ አጥሯል፣ ደንበኛም እየጠፋ ነው።
እስጢፋኖስ ግን ህልሙ ይቺን የሸቀጦችመሸጫ ይዞታውን ወደ አንድ ደረጃ-ትንሽ-መብልመሸጫ (ዴሊ) መለወጥ ከእዛ ደግሞ በርትቶ ዴሊውን በማስፋት ወደ ሬስቶራንት ማሳደግ እና በእሷ-ኮርቶ-ተደስቶ-መኖር ስለሆነ፣ በ ተበደረው ሁለትሺህ ዶላር ጥቂት ሰማጭ-ወንበሮች ገዝቶ ዴሊውን ከሱቁ ጀርባ በመሞከር ላይ ነው-አሁንም ከግዴለሽነት እና ደንበኛየለሽነቱ ጋር።
ኬኔት ደግሞ፣ ደህናአትራፊ መሃንዲስ ለመሆን እና ሃብት ለማካበት የምንጊዜም ምኞቱ ሆኖ፣ ‘እንደ ትጉህ አሜሪካአዊያን ከተተጋ ብዙ ይገኛል!’ ብሎ ስራውን ካገኘ ሁለት አመቶች ጀምሮ እሚተጋ ሠራተኛ ነው፣ እንዳሰበው በናጠጠ መጠን ተሳክቶለት ግን እማያውቅ ነው። ጆይ ደግሞ፣ በመሀከልከተማው ዉድ ሬስቶራንት ዉስጥ አስተናጋጅ ሲሆን፣ ሁሌ ሲያፀዳ የሚሰበስባቸውን መጠጦች ለራሡ ሳይጨልጥ ዕቃዎቹን ወደ መታጠቢያው አያደርስም።
ከስራሰዓት በኋላ ዘወትር ማክሰኞ-ማክሰኞ ሦስቱም የልብወዳጆች መሠብሰቢያቸው ወደ ሆነው ይህ ልእለሱቅ፣ ዛሬም በወርሃ ሜይ ሁለተኛ ቀን፣ ባለው ሙቀት መሀል ተገናኙ። በጓደኛአዊ ጨዋታዎች ህብረታቸውን አጣፍጠው፣ ሂወትን ለብዙጊዜ እንደሚኖሩት፣ በሀሴት ወደ ጨዋታው ዛሬም ገቡ። በሱቋ ጀርባ የሬስቶራንቱን ህልም ጥንስስ ባደረገበት ዴሊው፣ ዴሊ ወንበሮቹን ከሚተጣጠፉበት አውጥቶ አሁንም ተቀመጡ። ጆይ ውስኪ አምጥቶ ስለነበር ሱቁን ጭራሽ ዘግተው ጓሮ እንደለመዱት ተቀምጠው በሞቀ ጨዋታ ይዝናኑ ጀመሩ።
ሠሞኑን ከአመት በላይ የተጫወቱት አንድ ጨዋታ ነበራቸው። የአፍሪቃ አንድ አምባገነን መሪን አንዳቸው ሲጠቁሙ፣ ሌሎቹ ደግሞ የሀገሪቷን ቦታ ከካርታው ማውጣት አለባቸው። ጨዋታው አድጎ አምባገነን መንግስትን፣ ግልበጣ ሙከራን፣ አማፂን፣ ወዘተ. አክለው በመጥራት እና በመመለስ ይፎካከሩ ነበር።
በቀረ፣ ምሽቱን እስጢፋኖስን እንደለመዱት ስለ አሜሪካ አኗኗር መከረጀት። በእዚህ ሀገር እድል እንደተገኘ ካልተጠነከረ እሚጎዳ እንደሆነ አሳውቀውት፣ አበረታትተውት እና ተጨዋውተው ኬኔት ሁሌ እሚለውን ካለቃው እሚነገረውን እና የለመደውን ‘መልካሙን ዉጊያ መዋጋትህን ቀጥል’ ብሎት፣ እኩለሌሊት ሲል ተነስተው በጆይ ካልዕ-እድ (ሁለተኛእጅ) ያረጀች እና አሁን ላይ ሦስት አመቶች የነዳት ከእስጢፋኖስ ጋር ቪርጂንያ ድረስ ተጉዘው ሊያጋዛው ሲደርሱ ለመስተንግዶው በነጮቹ ሻጮች ስላልተከበሩ ጥለው ተመልሰው ኬኔት ከሌላ ቦታ በገዛት እና ወደ መካከለኛ ገቢ አሜሪካአዊ ባቀረበችው መኪና ሳብ ወደ አንድ ሠፈራቸው፣ ልክ ከከተማው ወጣ ብሎ ባለው ትልቅ ትመ. (ቲቪ.) እና ምንጣፍ እንጂ ምንም ሌላ ወደሌለው ከተማዳር (ሰብኧርብ) አፓርትመንቶች ለመጓዝ ወጡ።


 ምእራፍ ሁለት
አመት ከአምስት ወሮች በፊት፣ ጁዲት ከእስጢፋኖስ ቤት ጎን ያለው ከአስርታትዎች (ዲኬድስ) በላይ ያለነዋሪ የቆየውን ባለአራት ፎቅ ባዶ ልዕለቤት (ማንሽን) እሱም የ ፖርትላንድ አናርኪስቶች ቡድን፣ ቤትየለሾች እና ድረጊስቶች መደበቂያ የነበረው ዉልቅልቁ የወጣለት ነበር፣ አሳድሣው፣ በጎረቤትነት ገባችበት። የጁዲት በመንደሩ መግባት የእሚያምኑት የእነሱ የህይወት ገሃድ (ሪያሊቲ) አባል-ለውጥ አልመሰላቸውም። አንድ ሦስት እሚሆኑት አንድጊዜ የታዋቂዎች መኖሪያ የነበሩት ልእለቤቶች፣ በ ሎጋን ሰርክል ሲኖሩ፣ የእስጢፋኖሱ ማንሽን ግን ተከፋፍሎ አፓርትመንት በመሆን ቁሽሽ እና ዉልቅልቅ እንዳለ በበረሮ ተከብቦ ለእጅግ ደካሞች በርካሽ የተከራየ ነው።
ጁዲት አንዱን ሙሉ ልዕለቤት ባሳደሠችበት ወቅት ብዙ ሰራተኞች ሲቀጠሩ፣ ሰፈሩ ከተረሳ እና ካረጀበት እየተቀየረ ስለነበር ከለውጡ እኔም ልጠቀም በሚል ገቢ ለማግኘት፣ እስጢፋኖስ ዴሊውን ከፍቶ ጀንክ ምግቦችን ለአብዛኞቹ አዳሽ ሰራተኞች ምሣአቸውን ይሸጥ ነበር። ከእነሱ፣ ስለ ጁዲት መረጃ ይጠይቅ ነበር። እሷም፣ በጣም ቀበጥ የነበረች ሞልቃቂት፣ ላጤ ሴቴአዊት (ለዝቢያን) ሴት ነበረች። በየፎቁ ባኞ ቤት፣ ቅጥየለሽ ሠፋፊ ክፍሎች፣ ግማሽ ወለል ደግሞ መጽሐፍቤት፣ ወዘተ. ታሰራ ነበር።
በበሠበሰ እና የተዘነጋው መንደር የሚመጡት ነጮች ወንጀል ለማጣራት፣ ማስታወቂያ ለማስተላለፍ እና መሰል አልፎአልፎ ጉዳዮች ብቻ ስለነበር የሷም አኳኋን ስለ ሠፈሩ ቤቶቹን ማፍረስ ወይም ተያያዥ ጉዳይ ለማጥናት ነው የመጣችው ብሎ ቢያስብም፣ በመጨረሻ ግን ነዋሪ እንደሆነች ከመስኮቱ አኳኋኖቿ ሲገጥመው ተመልክቶ አወቀ። አንዴ ከአባቱ ስለምትተዋወቅ ብቻ ዝምድናውን ለመጠበቅ ሲል ብዙ ባያቃትም ዮዲት ከምትሰኘው የአስርአመቶች ታናሽ ከዝኑ ሰርግ ሊታደም አለአቅሙ፣ ለልዩሁኔታው ሲልብቻ ታክሲ ተከራይቶ ወደ ቧልትአዊ እርዝማኔ ከያዙት የ ናሽናል ቦታኒካል ጋርደን ፎቶ ለመነሳት ሊጓዝ ሲል አጊንታው ተዋወቀችው፣ ከ ኖአሚ እምትሰኝ፣ መልኳ ወደ እስጢፋኖስ እንጂ ወደ እሷ ከእማይቀርብ ልጇም አስተዋወቀችው።
ኦክቶበር ላይ እድሳቱ ስለበሠለ፣ ለመኖር ሙሉኛ ሳይቋጭ ገባችበት። በ ኖቬምበር እድሳቱ አበቃ። ወዲያው ከገቡት ነጮች በላጭ እዉቅና አገኘች፣ ጠይሟ ልጇ ከነጯ እናቷ ጋር በአንድነት መዘዋወሯ ለእይታ አበቃቸው። በ ጀነራል ሎጋን የፈረስ ላይ የአደባባይ ሀውልቱ አጠገብ ልጇን ይዛም ጋዜጣ በማንበብ ታዘወትር ጀመር። ወዲያው፣ ወደ እስጢፋኖስ ልእለሱቅ ወተት እና ለልጇ ከረሜሎች ለመግዛት ስትመላለስ ቀስበቀስ መጨዋወት ጀመሩ። በየመንገድም ሲወጡ ሢገቡ ከተገናኙ ሰላምታዎችን አዘወተሩ።
ከእሱ ክፍል አንድ ወለል ዝቅ ብሎ ያሉት ወይዘሮ ዴቪስ፣ ስምንት አመቶች ፊት ባለቤታቸው ሞቶ የእርጅና ብቸኝነት እጅግ እሚያሰቃያቸው የሆኑት ጎረቤቱ፣ ከጁዲት ደጋግመው ስለተመለከቱት ‘አብራቹህ አየኋቹህ’ ብለው ስለእሷ እንዲነግር ጠየቁት። በጠቅላላው መልካም ለውጥ በሠፈሩ እየመጣ እንደሆነ አስረዳት። ልክ ጁዲትን በመከተል ደግሞ የብዙ ነጮች መግባት ሆነ። የከተሜነት ሽታ አምጭ ንግድ ማእከሎች እየተከፈቱ መብዛታቸው ሆነ።
በሂደት ጁዲት እና ልጇ ሱቅ እየተመላለሡ ተለማምደው፣ ናኦሚ ጭራሽ ከናቷ እየተደበቀች ሱቁ ትመጣ እና ትደበቃት ጀመር። በሂደት ግን፣ ከትምህርትቤትም ስትመለስ እግረመንገዷን አንድፊቱን እሱሱቅ ገብታ እየቀረበች ታናግረው ጀመር። ይበልጥ ይቀራረቡ ጀመሩ። ስለሠፈሩ ወሬ ቃርማ ታሰማው ነበር። ስለ ፖለቲካ እዉቀቷ ልታስመሰክር (ስለ ሪፐብሊካን የዓለምአቀፍ ግንኙነት ዉድቀት፣ በ ኤድስ ላይ ዓለም ስለመስነፉ እና በቂ ገና ስላለመደረጉ፣ ወዘተ.) በኩራት ተንትና ታናግረው ነበር። በምትኩ ከረሜሎች ይሰጣት ነበር። የአስራአንድ አመት ልጅቷ፣ የረቀቀ እና የአዋቂ የአኗኗር ጥበብ ነበራት። እንዳዋቂ ሲጨዋወቱ እና ሲቀራረቡ ቆዩ። በሂደት የምናብቴ (ፋንታሲ) ዓለም ፈጥረው ሀብታም እንስሦች ያሉበት ፈጠራ ሰሩ። ሄነሪ እሚሰኘውም ሾፌር የቅዠቱ መሪ ሆኖ በሱ ስም በእየቀኑ ብዙ ያወሩ ጀመር። ከትምህርት መልስ እናቷን ቶሎ ማግኘት ባቶድም ግን፣ እናቷ አንድ ጥቁር በመንገድላይ ብልቱን አውጥቶ ጥቁርቁላ መጥባት ከፈለገች በመጠየቅ ወሲብአዊ ትንኮሳ ስላደረሰባት ለልጇ ሰግታ ሳይመሽ በጊዜ በአስራአንድሰአት መገናኘቱን ግድ አደረገችባት። ከዛ ከረፈደ፣ መጥታ ከሱቁ ትወስዳት ጀመረች። ላስቸጋሪነቷ የበለጠ ትወዳት እንጂ አስቸጋሪ ልጅ ብላ አትጠላት አትቆጣትም ነበር።


 ምእራፍ ሦስት
አስር አመቶች ወደ ቆየው ሱቅ እንዲሄድ እና እንዲነግድ ኬኔት በንጋታው ሜይ 3 ማለዳ ከቢሮው ሆኖ ለእስጢፋኖስ ደወለ። እሺ በማለት ግን አርፍዶ ወደ ሱቁ ተራመደ። አብሮ ሎጋን ሰርክል ከ ሠላሳ አመቶች በፊት በመውደቅ እና በድህነት ተመትቶ ቆይቶ ከ አስር አመቶች ወዲህ ግን እየተለወጠ እንደሆነ በደንብ አስተዋለ። በሱቅጠባቂነቱ ግን ደንበኛ እስኪመጣ ከፍተኛ ብቸኛነቱ ዋጠው። ለእዚህ መሠል የባይተዋርነት ጊዜ ደግሞ፣ ከድሮ ጀምሮ እሚከራያቸውን መጽሐፎች የማንበብ ልማድ ስለነበረው፣ አሁንም ያን ማድረግ ተያያዘ። ጆይ በስጦታ የሠጠው የ ቪ. ኤስ. ናይፓውል ልቦለድን በማንበብ ብቸኛነት እና ፈተናውን ለማስወገድ ይጥር ነበር። ወደ እዛ የተናቀ ቆሻሻ መንደር ሱቅ መስርቶ የገባው ከአጎቱ ብርሃኔ የተሠጠውን የሁለት ክፍሎች የከተማ መኖሪያ መንደር ያለ ስጦታን እንቢ ብሎ ነው። ያን ያደረገው እንዲህ ብቸኛ ሲሆን ብዙ ለማንበብ አስቦ ነበር። ገና በልጅነት ወደ አሜሪካ ሲመጣ፣ ‘ቆይ ብቻ፣ አባትህ ቢሞት፣ ባያይህም እንኳ ሐኪም ወይ መሐንዲስ ነው እምቶነው። ብቻ ጠብቅ!’ ይል ያበረታታው ነበር። አሁን ግን፣ አላማው እንደ ስደተኛ የነበረውን የትልቅነት ህልም ትቶ ህይወቱን ሰው ሳይመለከተው ተደብቆ መኖር ብቻ ሆነ። እንደ ጥቁርነቱ፣ የተረሳ እና የተናቀ ሠው ስለሆነ ለእዛ እሚረዳው ነበር። እስካሁን ያ እየሆነለት ነበር። ለእናቱ እና ወንድሙ፣ ወደ ኢትዮጵያ የገንዘብ እርዳታ በጥቂቱ ቢሞክርም፣ እነሱ ግን አይፈልጉም። ኑሮው በ የባሰምአለና እይታ በወረደ ደረጃው በምስጋና እሚያየው ሆኖታል።
ጓደኞቹ በጊዜ መጥተው ሱቁን ዘግተው እንደለመዱት ተዝናኑ። ኬኔት የተለመደ የአለቃውን ‘ተፋለም እና ህይወትን በደንብ ለውጥ፤ ይቻላል’ አባባል እየደገመ እስጢፋኖስን አበረታትቶ ውጭ ወጥተው በመጠጣት ሲዝናኑ፣ ሴቶች ይመጡ እና ይቀላቀሏቸው ጀመር። ያም፣ ወጪ አበዛባቸው። እስጢፋኖስ አዝኖ የቀን ሙሉ ገቢው ሊያልቅ እና ልከስር ነው ሲል፣ ሌሎቹ ከፍለው መዝናናቱን ጨርሰው በእኩለሌሊት ሰፈር ቀየሩ። የነጩን ቤተመንግስት ሲመለከቱ፣ የኔ አይደለም፣ ብዙ ከእዛ መጠበቄም ተገቢ አልነበረም በእሚል እስጢፋኖስ ያስብ ጀመር። ወደ ሌላ መሸታቤት ሲገቡ፣ ከ ሠላሳ አመቶች በኋላ መንደሩን የተቀላቀሉ ነጭ ወጣቶች እና የናይጄሪያ ወጣቶች ሲጠጡ አስተዋሉ። ተቀምጠው፣ በብርክፍያ ዘፈን ከፍተው ሲያጫውቱ የአብዮቱ ልጆች እሚለውን ዘፈን ከፈቱ። ተዝናኑ። እንደመጡ በሁለተኛው አመት የአቢዮቱ ልጆች ነን እሚለውን ዘፈን ሰምተው እኛም የአቢዮቱ ልጆች ነን ይሉ ነበር። “ታላቅ ለመሆን እንዲሁም የጭቆና መንገዱን ለማሸነፍ” በሚያረጉት ጥረት ይህ እንደእሚሆን በማሰብ ይህን ሙዚቃ ይወዱት ስለነበር አሁንም ደጋግመው ሰሙት።


 ምእራፍ አራት
በታንክስጊቪንግ ቀን ዋዜማ፣ እስጢፋኖስ በጁዲት እና ናኦሚ የእራት ግብዣ ጥሪ ተደረገለት። ሱቁን ከለመደው ለመጀመሪያ ጊዜ ሳይመሽ የዘጋው ያኔ ነበር። ቤቱ ሲዘገጃጅ እና የለሽእንከን ምሽት ለማሳለፍ ተፍተፍ ሲል፣ ያባቱን ዉርስ፣ የቤተሰብልብስ-እሚመስል የኢትዮጵያ ባንዲራ የለጠፈ ሱፍ ለብሶ መልኩ ግን ወጣት አልሆን፤ ግንባራምነቱም ከፈለገው መጠን አንሶ አልገኝ፤ አለው። ግን ተቀብሎ፣ ተለማምዶ በቅርበት ባለው ቤታቸው በጊዜ ገባ። መንደሩ ሁሉ የሃብታም-ሀብታሙ ቤት ምርጥምርጥ እይታ እንደነበረው፣ አሁንም የእነጁዲትም ምርጥ ቤት ነበር። ናኦሚ ሌላ እንግዳ ስለማትወድ እና የመጀመሪያው የአዲሱ ቤታቸው እንግዳ ስለነበር አመስግኖ ተቀላቀላቸው።
የፖለቲካል ሳይንስ አስተማሪ እንደነበረች፣ ባሏ ከልጃቸው ጋር ትቷት እንደጠፋ እና ከከተማ ከተማ ተዛውራ አሁን ሎጋን ሰርክል እንደመጡ እና አስተማሪነት እንደሰለቻት እና አስተማሪነት መምረጧ እማያረካ እና እሚገርማት እንደነበረ እና እንደጠላችው አሳውቃው ተጨዋወቱ። ግን፣ እስጢፋኖስ ከቶ የደመቀ እና የሀብታም ቤት ገብቶ ነገር ላለማበለሻሸት፣ አበላሉን ለማሠማመር፣ ነገረሁኔታውን አሠማምሮ ለመገኘት ይጣጣር ነበር። ቀጥላ ስለ አሜሪካ የታሪክ ጠይነት ታስተምረው ጀመረች። ‘የታሪክ ፈር በመቅደድ (በቦንብ፣ በባቡር ሀገሪቷን መሰንጠቅ፣ ወደ ጨረቃ በመመንጠቅ፣) አንደኛ ነን፣ መልሰን ታሪኩን በመንገሽገሽ ነው እምንመለከተው፣’ አለች። ተመግበው ቆይተው፣ በመጨረሻ ቤቷን አስጎበኘች እና ብዙ ክፍሎች መኖራቸው፣ ናኦሚ ስትበሳጭ መሸሽ ስለሚቀናት እና ስለምትሰጋ፣ በአዲሱ ቤት ብዙ ክፍሎች አዘጋጅተው ሲከፋት በፈለገችው ቤት ልትደበቅ እንጂ ከቤትውጭ ልትደበቅ እንደማይገባ ስለተስማሙ እንደሆነ ነገረችው። በመጨረሻ፣ ለቅጽበት ሳም አደረገችው። ከዛ ሸኘችው። ደስ ብሎት ቢወጣም፣ እቤቱ ሲገባ ግን የሱ ዉልቅልቅ ያለ ኪራይ ቤት እጅግ አስጸየፈው። እንደምንም ተቀበለው።
በንጋታው ኬኔት እና ዮሴፍን አጊንቶ፣ በቼዝ ጨዋታዎች መሀከል ስለ ዮዲት ጋር መሳሳሙ ሲናገር፣ ግዴለም በአሜሪካ ስትኖር ሃያ አመቶች ሊሆንህ ነው ነጭ መጥበስ አለብህ ብለው አበረታቱት። ጆጆ በኮንጎ የሃብታም ልጅ ሆኖ ሲኖር፣ ሞቡቱ ሙሉኛ እስኪያከስራቸው ከድሃ የቼዝ ተጫዋች ጓደኞቹ ሁሌ ይጨዋወት ነበር። አሁንም እሚችለው የለም። ኮንጎ ሳለ ፒስ ኮርፕስ ከመጣች የቦስተን ነጭ ጋር ጥቂት ጓደኛነት እንደሞከሩ ነግሮ አበረታታው። አሁን ግን፣ ወፍሮ ብታየውም አታቀውም፣ መቀጠሉንም አላሰቡትም ነበር። እና በጁዲት ጉዳይ አበረታትተውት ብቻ ተለያዩ።


 ምእራፍ አምስት
በንጋታው ሜይ 4 ላይ ጠንክሮ እና በርትቶ ለመስራት ቆርጦ ተነሳ። ወደ ሱቁ ለመጀመሪያ ጊዜ በማለዳ ሲገባ ግን ደብዳቤ አገኘ። የጠበቆች ማሳሠቢያው፣ የ ሦስት ወሮች ያልከፈለው ኪራይ ስላለበት እንዲለቅ እሚነግር ነበር። ለኬኔት ደወሎ ሲናገር ተቆጣው። ቸልተኛ ስለነበር ቀድሞም ያንን ነው የፈለገው በእሚል ተናደደበት። በስልክ እንዳሉ የለመዱትን የአፍሪቃ አንድ አምባገነን መሪ ጨዋታ አነሱ። የልጆች ፊት ክፍልዎችን በመቆራረጥ እሚቦጫጭቅ መልአክዎች እሚያናግሩኝ ናቸው ይል የነበረ የዩጋንዳ አምባገነን መሪ ላይ ተወያይተው በመጨረሻ፣ ጆጆ ጋር መደወል ይሻል ነበር በማለት ተለየው እና ሱቁን ገመገመ። እጅግ ያረጁ፣ ተሽጠው እማያቁ፣ መኖራቸውን የማያቃቸው ሁሉ እቃዎች ነበሩ። ገምግሞ ሱቁን አርፍዶ ሲከፍት፣ ሽማግሌ ባልናሚስት እንደ እግረኛ ራስ-ጎብኚ (ቱሪስት) ሆነው መጡ። ጥቂት እቃ ገዝተውት ስለከተማው ጠየቁት። መንደሩ እንደእዚህ ወደ ዝቃጭነት ከመፍረሱ በፊት የፕሬዝዳንት አጎት እና ሃብታም ወይም ትልልቅ ባለስልጣን ብቻ የነበረበት እነበደነበረ ነገራቸው። ጀነራል ጆን ኤ. ሎጋን ታላቅ የአሜሪካ እርስበርስ ጦርነት ጀግና መሆኑን አብሮ አወጋቸው። በተለየ፣ የካሮሊና እና ራሌይን ከመቃጠል እና መውደም በማስቀረቱ ትልቅ ሰው ነው አላቸው። አመስግነው ወጥተው በድል ፊትእግሮች ወደ ሰማይ የላከች ፈረሱ ላይ ያለውን የሎጋን ሀውልት ከካርታቸው እያስተያዩ ተመልክተው ሲጨርሱ አብረው ካርታ እያዩ አደባባዩን ከሚገናኙ መንገዶች እስጢፋኖስ የበለጠ ወደ እሚወደው ወደ ፒ መንገድ መጓዝ ጀመሩ። እስጢፋኖስ ሱቁን ክፍት ትቶ ወጣ። ባዶውን ትቶት እንግዳዎቹን በርቀት ተከተላቸው። ፒ መንገድ እጅግ ከሁሉ ዉብ የሆነው፣ ወደ ጆርጅታውን እና ዱፖት ሲያደርስ በጣም ቤቱ ሁሉ እየተዋበ እና መንደሩ ገነት እየመሰለ ስለሚሄድ ነው። ወደ አስራአራተኛ መንገድ ሲሻገሩ፣ ዩም እሚሰኝ የቻይና ዶሮ ቤት በፊት ገና በ 19 አመቱ አሜሪካ እንደገባ እዛ ገብቶ ጥጋት ላይ የበላው ሁሌ በዛ ካለፈ እንደሚታወሰው አሁን ምግብ ቤቱ ባይኖርም ታወሰው። ያኔ ሲመገብ የሆነ ነጭ ሽማግሌ ሰው ሳንቲም ደጋግሞ ይለምነው ነበር። ሰፈሩን አልፈው ሲያሻቅቡ፣ በሩቅ መከተሉን እየቀጠለ የጥቁሮች ሰፈር ተመለከተ። እዛ አቅም የሌላቸው የተለያዩ የወሲብ ስራዎችን ማታ ይሸጡበት የነበረ ነው። ስጋቤቶቹም እሚሸጡት ሥጋ ይበሰብስባቸው እና ይሰቃዩ ነበር። በ አስራስድስተኛ በኩል ነጩን ቤተመንግስት አይተው በመቀጠል ደግሞ ወደ አስራሰባተኛ ዐዉራመንገድ ወጡ። ሳሙኤል ካፌ አጠገብ፣ እስጢፋኖስ ጥንዶቹን ሊወስድ ተመኘ። ያ እሚወደው ስፍራ ነው። ቆነጃጂት ስራፈት ወጣቶች እየተላፉ መደሰቻቸው ነው። ጆሴፍም ይህን አካባቢ ይወደው ነበር። ‘ፈረንሳይ ፓሪስ ይመስላል፣ ብቸኛው የ ዲሲ ከተማ ጤነኛ እና ዘመናዊ ሰፈር ነው’ ይል ነበር። አንድ ቀንም ሰክሮ ባመሻሹ፣ የመብራት እንጨት ተደግፎ እስካርፕ አርጎ ሲዝናና አጊንቶት ነበር። ወደ ዱፖ አደባባይ ደረሱ። ያም ምርጥ ዉበት የተጣለበት ነበር እና አድሚራል ዱ ፖን ተመልሶ መጥቶ ቢያየው በስሙ ስለተሰየመ ይኮራበት ነበር ብሎ በአካባቢው አረንጓዴ መንደሮች እሚያነቡትን ወጣቶች አልፎ ጎብኚ ጥንዶቹን አሁንም እየተከተለ አለፈ። በአንድ ወንበር ሲቀመጡ እና ሚስቱ እንድትተነፍስ ባልየው ሲያነጋግራት የሆነ የጤና እክል እንደተነሳባት ልብእየሳለ በልቡ ሰላምታ ሰጥቷቸው ተለየ። ወደ ሱቁ አሳብ አደረገ። ንብረትን በቀላሉ እንዲህ ክፍቱን ለቅቆ መዉጣት እሚያያዘውን ፍልስፍና እሚሰብኩትን ሰዎች በንብረቱ ለመንገደኛ መከፈት እሚሰማውን ሊያጤን ያን አደረገ።


 ምእራፍ ስድስት
በንጋታው፣ ሱቅ ይመጣሉ ቢልም፣ ናኦሚም እናቷም ቀሩ። እየተጨነቀ፣ የተሣሳምንው ምን ፍች በሷ አለው ብሎ ሲያስብ ቆየ። በንጋታውም ተጨንቆ ቢውል፣ ማንም ግን የለም። ተስፋ ቆርጦ፣ እኔ ከንቱ ድሃ ምንምየለሽ፣ እሷ ትልቅ ሀብታም፣ አንገናኝም አለ። ቤቷ ተጋብዤ የነበረውም፣ የተበላውም ምርጥ መብል እና የሀብታም ቤት ምሽቱ ተረት ነበር፣ ሌላ አይገባኝም፣ ብሎ የባይተዋርነት ስሜቱን ወደ ቁጣ ብሎም ቁጣውን ወደ ተሸናፊሀዘን (ፒቲ) ቀየረ። በመጨረሻ፣ በሦስተኛው ቀን በድንገት ቤቷን ዘግታ ስቶጣ አገኛት። ለረዥም ደቂቃዎች ቁልፍ ፍለጋ ስትራወጥ ቆሞ ተመለከታት። አተያየቱ አይታው እንድታናግረው ነበር። እያየ ቢጠብቃትም ግን ፀጥ ብላው ገባች። ተስፋ ቆርጦ ቆየ። በሦስተኛው ቀን መጥታ ማታ ቤቱን አንኳኳች። በርዷት በረዶው እያንዘፈዘፋት ተቀምጣ ቆየች። መጠጥ አምጣ አለችው። ሲጀመር ሰከር ብላ ነበር። የቆሸሸ የድሀ ቤቱን አይከፋም ስትለው ተደሰተ። አጠገብ ላጠገብ ተቀምጠው ሲጨዋወቱ ልጇን አስተኝታ እንደመጣች ነግራው እና ቆሞያያት ጊዜ እሷ ቁልፍ ስትፈልግ ለምን ፀጥ እንዳላት ጠየቀችው። የቸኮለች መስሎት እንደሆነ ዋሽቶ ተናገረ። ዳግ-መቀራረባቸውን ወደደ። ደረቱ ላይ ተኛችበት። ቆይታ ነቅታ ወደልጇ ለመመለስ ተለየችው።
በንጋታው ኖአሚ ሱቁ መጣችበት። ለክረምቱ የሁለት ሳምንቶች እረፍት በዛ ያሉ ገፆች ያሏቸው መጽሐፎች ይዛ ልታነብብ እንደሆነ ነግራ አመጣች እና የቱን እናንብ ብላ በመጠየቅ አስደመመችው።


 ምእራፍ ሠባት
ከሱቅ ወጥቶ አዛውንት ጥንዶቹን ከመሬት ተነስቶ እንደተከተለው፣ በ ዱፖ ሰርክል እንዳለ ትልቅ ባለስልጣን በአጀብ ሲያልፍ ተመልክቶ፣ የሊሞዚን እና መኪና ጥበቃ ሽርጉድ እና ወከባው ከሰርክሉ አካባቢ ከነበረው ድሀ ህዝብ የተመልካችነት ሚና አንፃር እየገረመው ታዘበ። ወዲያው የሳንቲም ስልክ ዘንድ ቀረበ። አጎቱ ብርሀኔ ጋር ደወለ። አጎቱ፣ በአሜሪካ ቆይታቸው፣ ለከፋ ጊዜ ጭምር እሚቀራረቡ የሆኑ ተደጋጋፊ ቤተሰቡ ናቸው። ዛሬም ጋሼ ይለዋል። ሲደውል ስላላገኘው፣ እና ‘መልእክት ይተዉ’ እሚል መልስ ተቀድቶ ስላገኘ፣ ‘እመጣለሁ’ እሚል መልእክት መተው አሰበ። ድንገት ሰፋ ሳይደርስ አጎቱ ቤቱ ገብቶ መልእክቱን ሲሠማው ደረሰአልደረሰ ብሎ ከእሚጨነቅ ብሎ ስልኩን ያለመልእክት-መተው ዘግቶ፣ ዮሴፍ ጋር ደወለ። ኮሎኒያል ግሪል ሬስቶራንት አስተናጋጅ አንስታ አገናኘችው። ዮሴፍ ‘በእኔ ተራ ና እና እንደ ኢትየጵያ ንጉሥ ልንከባከብህ!’ ቢለውም፣ ተሳክቶለት ሄዶ አያውቅም። ስልኩን ዘግቶ ወደ ኬኔት ደወለ። ቫለንቲን ስትሬሰር፣ በሃያ አምስት አመቱ ከሁሉ ወጣት መፈንቅለ መንግስት የከወነ ሰው የሆነውን ሰው ሊጠይቀው አሰበ። መልሶ የቅርብ ጊዜ ትዝታ እንጂ ጨዋታ አይሆንም በሚል ዘጋው። ስልኩን መልሶ በመክፈት፣ ሁለት ሰዓት ቀድሞ ትቶት ለወጣው የራሱ ሱቅ ስልክ ቁጥር ደወለ። ተረባብሾ፣ ልጆች እየተንጫጩ፣ ሰማ። ያነሳው ሰው ድምጽ ግን የለመደው ነበር። መዉጣት መግባቱን፣ አለባበሱን፣ ጫማ አወላወሉን፣ ወዘተ. እሚቆጣጠርለት፣ ይዘንባል/አይዘንብም? ብሎ ግምት እሚጠይቀው፣ በረዶ ሻይ እሚያዘጋጅለት፣ ቤተክርስትያን እንዲሄድ እሚያበረታታው፣ በቅርቡ ደግሞ ብቸኛነት እና ተስፋማጣቱን አሽትቶ፣ በእጆች መያዝ እና በጉንጮች መሳም እሚያጽናናው ድምጽ ነበር። የጎረቤቱ ወይዘሮ ዴቪስ።
ስልኩን ትቶ ወደ አጎቱ ሜሪላንድ የድሀዎች መንደር ተነሣ። በኢትዮጵያ ሳለ፣ አጎቱ ከአዲስአበባ አቅራቢያ ይኖር ነበር። ከእናቱ ጋር ምን እቅጭ ግንኙነት እንደነበረው ባያቅም አጎት ሲባል ነው እሚያቀው። የራሱን መኖሪያ ቤቱን የሰራው ከተፈጥሮው የተንጣለለ መሬት እና መልክአምድር እማይለይ እና እሚመሳሰል አድርጎ ነበር። ያ የኪነህንፃ ፍልስፍና የተቃረመው ከ አርኪቴክቸራል ዳይጀስት አንድ እትም ላይ ከቀረበ የ ፍራንክ ሎይድ ራይት ፒሬሪ ኪነህንፃ ስእል ነበር። አጎቱ አንድ ምሽት የቤቱ አገነባብ ፍልስፍናው ስለስብእናው እንደጠቆመው በሌሊት ድንገት እራሱም ተሰወረ። ማንም ምንም እሱ ሠወር አላወቀም። ከመቅጽበት ሲጠፋ፣ ቤት ንብረቱን ሠራተኞች እና ዘበኞች ወረሱት። የደርግ ወታደሮች ፈልገውት ቢመጡ፣ እና ያገኙትን ቢደበድቡ እንኳ መልስ አልተገኘም። ከእስጢፋኖስ ሁለት አመቶች ቀድሞ አሜሪካ ገብቶ ነበር።
ዛሬ እሱ ወደእሚኖርበት ሰፈሩ ሊደርስ፣ ባቡሩን ሲይዝ፣ የ ቪርጂኒያ ኮሚኒቲ ትምህርትቤት ማስታወቂያን በባቡሩ ተለጥፎ ተመልክቶ፣ የተማረበት ትምህርትቤት ስለነበር ማስታወቂያው ባለመለወጡ እጅግ አደነቀ። ነጭ፣ ሂስፓኒክ፣ ኤዢያአዊ፣ አፍሪቃአዊ አራት ተማሪዎች በደስታ በአረንጓዴ ሳር ተቀምጠው ይታይ ነበር። ማስታወቂያው እንጂ እዉነቱ እምብዛም ነው በማለት ሲመጣ የነበረውን አስታወሰ። ለመትረፍ የተሠደደ ቤተሰብ፣ ሲተርፍ የመትረፍ አላማው ሲሣካ፣ ሂወት ደግሞ በቅጡ መኖር ያምረዋል። እሱም እዛ ሲማር፣ ለቤተሰቡ የተሳካለት መሰለ። እና የስደተኛው ዘመድ ሁሉ የራት ሰአት የመወያያ ዜና ወይም መደሰቻ ሆኖ ነበር። ይህ ኮሌጅ፣ በተለይ በጆሴፍ ተወዳጅ ነበር። በአረጀ የድሮ ተማሪነት መታወቂያው እያታለለ እስከቅርብ ወደ ጆርጅታውን ካምፓስ ይገባ እና ይዝናና ነበር። የወጣቶቹ ፊት፣ ያስቀናው፣ ያስደሥተውም ነበር። እንዲሁም ገብቶ ወደ ቤተመፃህፍቱ በመግባት ብዙ መፅሐፎች አውርዶ በጠረጴዛው ላይ በመደርደር፣ አዋቂ ለመሆን እማያደርገው ጥረት አልነበረም። በፊት ጀምሮ ብሩንም፣ የተለያዩ ተጨማሪ የምርጫ ትምህርቶችን ለማጥናት ይከሠክስ ነበር። ዛሬም፣ ኖቶቹን ያነብብ አለ። ግን ብዙ አዋቂ ጆሴፍ አልሆነም። ቢሆንም፣ ሁሌ የዳንቴን አንድ ግጥም ከተፃፉ ግጥሞች ሁሉ ምርጡ ይለው ነበር። ‘አምላክ እሚሠጥአቸው አንዳንድ ዉብ ነገሮች’ እሚለውን፣ የዳንቴ ከሲኦል (ኢንፈርኖ) ሲወጣ የተናገረው የተስፋ ስንኝ። ከአፍሪቃ ስለወጡ፣ ለእነሱ ምርጥ ገላጭ ነው ባይ ነበር። ምንም ሲወራ፣ አያይዞ፣ አፍሪቃ ይመስላል ማለት ይወድ ስለነበር፣ በተለይ ኬኔት ያንን አፍሪቃ ናፋቂነት ይጠላበት ነበር። መመለስ መቼም አትወድም፦ ‘እዛ ሄዶ አፍሪቃን እየጠሉት ከመኖር፣ እዚህ በምቾት ሆኖ ቢናፍቁት ይሻላል’ ነው እምትለን መቼም ይለው ነበር።
ሰፋ ተጉዞ ወደ አጎቱ ቤት ተዳረሰ።


ምእራፍ ስምንት
ናኦሚ መጽሐፍ የመረጠችው የፍዮዶርን ዶይኮቭስኪን ዘ ብራዘርስ ካማራዞቭ ሲሆን፣ ለመጡት ሦስት ቀኖች በመቀጠል እስጢፋኖስ አነበበው። የመጀመሪያው ቀን፣ አብረን ነው ምናነብበው በሚል ግን አንተ ጀምር በሚል ታስነብበው ጀመረች። ተራውን ሲጨርስ ቆይ አንድ ገጽ ብቻ እያለች ታስጨምረው እና ታደምጥ ቀጠለች። አባቱ ተረት መንገር ስለሚወድድ፣ ገፀባህሪዎችንም አግዝፎ እንደእውነት ይቀበላቸው ነበር። እስጢፋኖስም፣ እንደሱ ገፀባህሪዎችን የእውነት አድርጎ መሳሉን ቀጠለ። ሀምሳ ገፆች አስነብባው፣ ሲረፍድ፣ ቤት አሌድ በማለቷ ስራ ፈጠረላት። ማፅጃ ሰጣት። ቤቱን ፀድቶ በማያቅበት ደረጃ አፅድታ አስደመመችው። ረፍዶ ከሰአትበኋላ እናቷ መጥታ ስቶስዳት፣ ለእስጢፋኖስ ለእሱ ብላ እንደሆነ እንጂ ያን የጠጠረ ያዋቂ መፅሐፍ ለግሏ ምታነብ አለመሆኗን ጁዲት አሳወቀችው። ሰፋ ከናኦሚ በተደረገለት ፍቅር በደንብ ተደነቀ። በስልት እንዲያነብ አደረገችው እንጂ ለራሷ አስባ አልነበረም እና ኩራት ተሰማው። ‘ነገ የፈለግሽውን ያክል ቆይ፣ አሁን እኒድ’ ብላ አስገድዳ ቤት ወሰደቻት፣ እስጢፋኖስ ዮሴፍን አማከረ። ‘እንዳሻሽ ነገ ቆይ ማለቷ አንተን መዉደዷ ሳይሆን አይቀርም፣ እኔ አስተናጋጅ ሆኜ ብዙ ያሜሪካ ሴቶችን ተመልክቻለሁ። በርታ ግፋበት፤’ አለው። በቀጣዩ ጧት ሦስት ምእራፎች አንብበው፣ ከናኦሚ ጋር ሱቁን ማፅዳት ቀጠሉ። በደንብ አመረበት። ያረጁ እቃዎች ተጣሉ፣ የተነቃቀሉትን ገጣጠመ፣ ሁሉም አማረበት። ጁዲት አመሻሽታ ሻይ ይዛ መጣች እና ‘ልናነብብ ከሆነ ሻይ ብንጠጣ ምንአለበት’ ብዬ ነው አለች። ‘እኛ’ በማለቷ ተደምሞ ለዮሴፍ ሊናገር ቋመጠ፣ እየጠጡ፣ ጁዲት እና እሱ በየተራ ለግማሽ ሰአት ሲያነብቡ፣ ናኦሚ እየጠጣች አድማጭነቷን ማስመሠል ቀጥላ ቆየች። ‘ከእዚህ በላይ በሆንን ብዬ ከእምመኝ፣ ብልህ ከሆንኩ፣ ይህ የግማሽሰአት ቆይታዬ በቂው ነው እና በእዛ በቃኝ ብዬ ልረካ ይገባኛል’ ብሎ አሰበ።


ምእራፍ ዘጠኝ
በባቡሩ ወደ ሲልቨር ሮክ ኮምፕሌሥ የአጎቱ መኖሪያ እያስደሰተ በእማይጋብዘው ጉዞ ተጉዞ ደረሠ። መንገዱ የተራቆተ፣ አስቸጋሪ እና ቸላ የተባለ የድሃዎች መኖሪያን እሚያስመለክት ነበር። ላብ አልቦት ደርሦ በሃያስምንት ፎቆች አፓርትመንቱ የአጎቱ ወለል ላይ ለመሄድ ገባ። እስከዛ ግን፣ ለአጎቱ እሚለውን ነገር ይሥል ነበር። ሱቁን ለመሸጥ መዘጋጀቱን ቢነግረው ‘ህይወትህ ሊሻሻል ነው’ ብሎ እሚያስብ እንደሆነ በመገመት ሱቅ የመሸጡን ሀሳብ ሊነግረው እና ሢደሰት እና መልካም ሲሠማ ሁሌ እንደሚያደርገው አምላክን ሊያስመሰግነው አሰበ። አጎቱ፣ ሁለት አመቶች ብቻ የሠጠውን ቤት በእዚህ አፓርትመንት ተጠቅሞ የወጣው፣ ሃያስድስቱን ፎቆች በደርግ ስደት ከኢትዮጵያ ተሰደው የመጡት ሀበሻዎች እንደ አዲስአበባ ቅጥያ አድርገው አፓርትመንቱን ስለተቆጣጠሩት ደብሮት ነበር። አማርኛ እንጂ እንግሊዝኛ ማውራት እና ማድመጥ እንኳ አልነበረም። መብሉ የሀበሻ መጠራራቱ፣ አብሮ ጊዜ ማሳለፉ እና አኗኗሩ፣ ልጆችን መቆጣጠሩ፣ ሁሉም የታፈነ የኢትዮጵያ መንደር ስለሆነበት ነበር ሊለቅ የተገደደው።
አጎቱ ከቀኃሥ. ዘመነመንግስት ልዑልዎች እና ካቢኔቶች ጋር ስሙ ይያያዝ ስለነበር፣ ሃብታም እና የተከበረ ነበር። አሁን ግን ሁሉ ሀብት አልፎ፣ ጠፍቶም፣ በብቸኛነት በ ሲልቨር ሮድ አፓርትመንቶች ሃያአራተኛ ወለል ላይ አንድ ቤት ይዞ እሚኖር ነው።
አሁንም ድሀዎቹ አፓርትመንት ዉስጥ አንዱ አሳንሠር ብቻውን እየሰራ ስለነበር ከብዙ ኢትዮጵያአዊ ተሳፋሪዎች ጋር ወረፋ ጠብቆ ታጨቀበት። ዉሥጡ እሚያወሩት አላግባብ ጮክ ብለው ሰው እንዲሠማ ሲሆን ስለ ሀበሻው መንደር ነበር። ስግብግብ ያሎነ ወሬውን ይቀላቀላል፣ ስለ ማህበረሰቡ አንድ ጉዳይ ይወራል እና። በተለይ በዕፅ፣ ስራአጥነት፣ ትዳር-ዉስልትና፣ ወዘተ. ሁሉም ያወራል። እንደእስጢፋኖስ የተገኘ አዲስ ደግሞ ብዙ ይገመታል። ምን እንዳገኘ፣ አሳካ ይጠየቃል። ሁሉም ግን፣ ሀገርቤት ይናፍቃል፣ በሂደት ደግሞ ምንም ኢትዮጵያ አትኖርም፣ ሁሉም አሜሪካአዊ እየሆነ ነው እሚሉ ወሬዎች ናቸው።
ከአሳንሠሩ ወጥቶ ወደ አጎቱ ክፍል ሲደርስ፣ አብረው ስለኖሩ የራሱ ቁልፍ ቢኖረውም፣ ከወጣ ስለቆየ ሰተት ብሎ አይገባም በማለት አንኳኳ። አጎቱ ብርሀነ ሥላሴ የለም። ከፍቶ ገባ። ቤቱ በፊት ሲኖርበት እንደነበረው ነበር። ገፅታውን ለመቀየር ቢዝትም አልተሳካለትም ማለት ነው። እስጢፋኖስ እራሱ ይተኛበት የነበረው ሶፋ ነበር። በእዛ ተኝቶ ህልምዎች እና ቅዠቶች ሁሉ ከውኖ ነበር። አባቱ በወታደሮች በመወሰዱ፣ የገጠመውን እንኳ አያቅም ነበር እና በእዚህ ሶፋ ተኝቶ በልቦናው፣ ምርጥ የእርጅና አሟሟት እንደወሰደው ስሎ፣ በነበረበት የአዲስአበባ አቅራቢያ መንደር መልካም ቀብር እንዳገኘ ይስል ነበር።
አጎቱ እጅግ እቃ እሚንከባከብ እና እስጢፋኖስንም እሚወድድ እና እሚንከባከብ ነው። ስለግሉ ግን ሊጠይቀው አይፈቅድለትም፣ በከፍተኛ ወግአጥባቂ ደረጃ ‘ታላቅህ ስለሆንኩ ስለእኔ አታውራ’ እሚልበት ጊዜ አለ። በሀገሩ ራሱን ነድቶ እማያቅ ክቡር የነበረ ቢሆንም አሁን አሜሪካ ከመጣ ጀምሮ ከመኪና ጋር ኑሮው ተሳሥሯል። በካፒቶል ሆቴል መኪና ማረፊያ አስተናጋጅ (ፓርኪንግ አቴንዳንት) ሲሆን፣ በቀንቀን ደግሞ የአሽከር ታክሲ ንግድ እሚሠራ ነው። ይህን ምፀት ግን ሲቀልድበት፣ ‘ኢትዮጵያ ብመለስ በራሴ የገነባሁት ቤት፣ ዛሬ መንግስት ወርሶት የሚኖርበት ወታደር-ጀነራል ስለሆነ፣ ለሱ መኪና እየነዳሁ አገልጋይ ሆኜ በመቀጠር ገና የመጀመሪያው ቀን ላይ ከራሴ ጋር አብሬ እገድለው ነበር’ ይላል።
ብርሀኔ ብዙ ገንዘብ የሌለው ሲሆን፣ ከገቢው ኩርማኑን ሀገርቤት ሲልክ የቀረው በመጠኑ በድህነት ሂሳብ ያኖረዋል። ወደ አሜሪካ ሲመጣ፣ በምሽት-ምሽት ለወር ተጉዞ አብሮት ያሉት በየበረሀው እየሞቱ እና እሬሳዎቻቸው በአውሬ እየተበሉ ሱዳን ደርሰው በስደተኛ ካምፕ ቆየት ብለው ነበር። እዛ ሲሠነብቱ የተኟቸው ምሽቶች ለብርሀኔ የህይወቱ ምርጦቹ ነበሩ። ለእስጢፋኖስ ደግሞ፣ እዚህ አፓርትመንት ዉስጥ በበጋ መስኮት ከፍተው፣ በሥስ ብርድልብስ ሆኖ፣ ቬንትሌተር አጠገባቸው ከፍተው የተኙት ሃሳብየለሽ እንቅልፎቹ ምርጦቹ እንቅልፎቹ ናቸው።
ብርሀኔ የሱን ድርሻ ብሩን በቁምሳጥን ይከትታል። አጠገቡ አሜሪካ ከገባ ጀምሮ ለተለያዩ መንግስት ኃላፊዎች እሚፅፋቸው ደብዳቤዎችንም አጭቆ ይከትታል። መጀመሪያ ለፕሬዝዳንት ካርተር መፃፍ የጀመረ ሲሆን በጠቅላላ ይል የነበረው ‘የኢትየጵያ ስደተኛ ነኝ፣ ሀገራችን በወታደሮች አለህግ ብዙዎች ንፁሖችን በመግደል ላይ ነች፣ ምንም ያላጠፉ ብዙዎች እየሞቱ ዜናውን እየሰማን እዚህ ሆነን እየሰማን ነው፣ ሀገራችንን ይርዷት እባክዎን’ ወዘተ.። በሀገሪቷ የነበረው ሁሉ ዋጋ እንዳጣም ወዘተ. ይነግራቸዋል። ደጋግሞ ለተለያዩ ተቋሞች፣ ለፕሬዝዳንት ሬጋንም ጭምር ብዙ ይፅፋል። ግን ግዴለሽ ወይም ዝምታ መልስ ያገኝ ነበር። ብቻ ምላሽ ሲያገኝ ደብዳቤዎቹንም እንዳጠራቀመ ነበር።
ሽብሬው እስጢፋኖስ፣ የሰፋ እስጢፋኖስ አባት፣ ከቤቱ በሌሊት ወጥቶ የነበረው ወታደሮችን አምልጦ ነበር። ያኔ ልጁ ሰፋ እስጢፋኖስ አስራሁለት አመቱ፣ ታናሽ ወንድሙ ዳዊት ደግሞ ሰባት አመቱ ነበር። እስጢፋኖስ ባላደገ ልቡ ዉጤትአያመጣብኝም ብሎ በበጎፈቃደኛነት ያመላለሠላቸውን ‘ተማሪዎች ለዲሞክራሲ’ እሚል በራሪወረቀቶች፣ ቤቱ አጊንተውበት ልጁን ለማዳን አባቱ ‘የኔ ወረቀቶች ናቸው’ ብሎአቸው በወታደሮች እራስ እስኪሥት ተደብድቦ እና ደማማ። አለሙያአዊ ኢህገወጥ በነበረ ምርመራ አላግባብ እናትየዋንም ሲያሰቃዩ ቆይተው አባቱን ይዘውት ሲወጡ፣ በንጋታው የቤተሰቡን የወርቅ ሀብት ሰብስባ እናቱ ወደ ኬንያ እንዲጠፋ ሰፋን ሸኘችው። ገና በልጅነት፣ ወርቁን እየሸጠ በመክፈል ድንበሩን ተሻግሮ ኬንያ ሲደርስ የተረፈው እጅግ ትንሽ ብቻ ነበር።


ምእራፍ አስር
ማምሻውን ጁዲት አምጥታ ሻይ በጠጡበት ማግስት በጧት ጁዲት መጥታ እራት እሚያቀደው ካለ ጠይቃ የለኝም ሲል፣ ተመልሳ አብስላ ወደ ሱቁ ከናኦሚ ጋር ማታ መጣች። ምሽቱ ሳይቀዘቅዝ በጊዜ ሱቅዘግቶ ተመገቡ እና ወደ ሞል በጁዲት መኪና አቅንተው ብሔራዊውን የገና ዛፉን ጎበኙ። ሲመለሡ ቤታቸው ያለውን ገናዛፍ ለማየት በናኦሚ፣ ሻይ እንዲጠጣ በጁዲት ግብዣ ተሠጥቶት ወደእነሱ ቤት ጎራአለ።
የናኦሚ ከፊልየጠፋ አባቷ እና የቀድሞው የጁዲት ባሏ፣ ከጀርመን የላከላትን ስጦታ ናኦሚ አሣየችው። ይህ የናኦሚ አባት እንደ ጁዲት ፕሮፌሰር ሲሆን፣ አምና ግሪክ ካቻምና ናይሮቢ፣ ስነምጣኔ ሲያስተምር ነበር። ሁሌ ተሽከርክሮ እሚያስምር ነው። ባስተማሪነታቸው ከሞሪታኒያ ሲመጣ የተገናኙ ነበሩ።
ጁዲት ቤቱን በአለቅጥ ዉድ ስጦታዎች እና ዛፍ ለልጇ አስጊጣ አሳይታው ሲያበቃ በወሬያቸው መሀል ‘ተለቅ ያለ ነገር እወዳለሁ’ ስትል ‘ርካሽ እና አነስ ያለ ስጦታ እወድድአለሁ’ በማለቱ ሳታስበው ‘የተሳሳተ ቤተሰብ ነው የመረጥክው’ አለች። ክው አለ። እስካሁን የጥቁር ባሏ ምትክ ነበር አድርጋ ያሠበችው ማለት ነው። ሴቶች እሚወዱት ጠየም ያለ፣ የተማረ፣ ሊቅ፣ ግለትምምንአማ፣ አፍሪቃአዊ፣ እንደነበር ያን ባሏን ሳለው። ‘እኔ ላይ የሱን ምትክ ፈልጋ ከሆነ ተሳስታለች’ ብሎ ሻዩን ሳይጠጣ ተናድዶ፣ ለመሄድ እንዳሰበ አሳወቀ። በንፁህ ማንነቱ አለመወደዱን እና በመልኩ መገመቱን በመጥላት፣ ‘ሁሌ እራሴን በመስታወት እያየሁ ከእሷ ራሴን ማወዳደር የለብኝም፣ ያን ባደርግ እንኳ አንዴ አንድ ነገር ልክ እንዳሁኑ ሲፈጠር ርካሽ እና ትንሽ ስጦታዎች እወዳለሁ ብል ሮጣ ለቤተሰቤ አቶንም ብትል የነገሩ ማብቂያ ይሆናል’ ብሎ ተናደደ እና ነገረሁኔታው ተረባበሸ። ዳግ-ደንግጣ፣ ‘ቆይ!’ ስትል ‘እንቢ መሸ’ በማለት ችክ ሲል ተስማምታ ትሸኘው ጀመረች። ‘እንደወትሮው ትስመኝ ወይስ በምን እንለያይ ይሆን?’ ሲል ጨብጣ ብቻ ሸኘችው።
ወጥቶ በአደባባዩ ዙሪያ ባለው አንድ አግዳሚ ላይ በቀዝቃዛው አየር ተቀመጠ። ሴተኛአዳሪዎች እሚወጡበት ሰአት ነበር። እስጢፋኖስ ወደሱቁ ከሚመጡት ሴተኛአዳሪዎች ሁሉ ይተኛ ነበር። ሊገዙት ሲመጡ ‘ማታ ተመለሱ እና በነፃ ግዙ’ በማለት አመሻሽተው ሲመለሱ ለግማሽ ሰአት ያክል በአካሉ አጨዋውቶ በነፃ በመሸጥ ይሸኛቸው ነበር። አሁንም አንዷ ቅሬ ‘የምትፈልገው ካለ!’ ሲሉ ከጨለማው መልእክት ላኩለት። ‘ቤትገብ ነኝ’ ብሎ በመመለስ ወደቤቱ አዘገመ።


 ምእራፍ አስራአንድ
አሜሪካ እንደደረሰ፣ በእዚችው አፓርትመንት ክፍሉ ብርሀኔ አስገብቶት ‘ሁሉ የኔ የሆነ ያንተ ነው! ተደሰት’ ቢለውም፣ ስለሀገሩም ብዙ ምክር ቢመክረውም፣ እስጢፋኖስ ግን በከፍተኛ ሀዘን እና ወደሀገር ወዲያ መመለስ ሀሳብ የተጠመደ ነበር። ከቤቱ መዉጣትም ሆነ ከሰው ተቀላቅሎ ማውራትም ቀልድ መስሎት ሀገሩን ዳግ-ማግኘት ይናፍቅ ነበር። በሦስተኛ ሳምንቱ ግን፣ ካፒቶል ሆቴል አጎቱ ወስዶት ስራ አስቀጠረው። አለቃው ‘ሰፋ’ ወይም (ለቅለት) ‘ስቲቭ’ በለው ተባለ፣ ሰፋ ደግሞ ‘ሰር’ ብለህ ጥራው ተባለ። ‘ታማኝ እና ቢቀጭጭም መስራት እማያቅተው ነው’ ብሎ አጎቱ እንዲያ አስተዋውቋቸው ወደ ሜሪላንድ የከተማ ጠርዝ ቤቱ ተመለሡ። ስራውን እየሰራ አጎቱ በመረጠለት ትምህርትቤት መማር ጀመረ። ለራሱ ምንም ወስኖ አያውቅም ነበር። ሦስት አመቶች ቆይቶ ግን፣ አንድ ምሽት ሁለት ተራዎች (ሺፍትስ) አስራሦስት ሰአቶች ሰርቶ ድክም ብሎት ማታ ሲወጣ እና በፖቶማክ ወንዝ ዳርቻ ለማይሎች ተስፋአጥ ሆኖ ሲጓዝ ቆይቶ ለራሱ ለመጀመሪያ ጊዜ በራሱ ወሠነ። ‘ከእንግዲህ እንዲህ መኖር የለብኝም!’ አለ። አባቱ በመሞቱ እና እቃ አውራጅ እና ጫኝ ሆኖ እዚህ በመቅረቱ እሚኖርለት አጣ። በማግስቱ ካፒቶል ሆቴልን ተሰናበተ። ጓደኞቹ እጅግ ደነገጡ። በመጨረሻ ጆሴፍ ‘ደግ አደረግክ’ አለው። ‘ሁላችን ከእዚህ አስተናጋጅነት ወጥተን ሀብታም ሆነን እዚህ ብንመጣ የኛን እቃእሚያራግፉ እና ወደፎቁ እሚያደርሱልን ይሆኗታል ቆይ!’ እያለ አበረታው።
ባመቱ ደግሞ ከአጎቱቤት ወጣ። ዉሳኔዎቹን ወደደ። ፀረገሀድአማአዊ (ኢምፕራክቲካል) ስለነበሩ ደግሞ ጭራሽ የበለጠ ወደዳቸው። በሎጋን ሰርክል ባዶ ቤቶች ብዝት ብለው የነበሩ ሲሆን፣ ቶሎ አገኘ እና መኖሪያውን በእዛ አበጀው። ሱቅ መክፈቱን ደግሞ፣ ኬኔት ከመንግስት ጥቂት ብድር አመቻችቶለት በፊት መጠጥ መጋዘን በነበረበት እና በመንደሩ ብቸኛው የተዘጋ በሆነው ቤት ላይ በመከራየት ፈፀመው። ኬኔት በትዕግስት እንደአባት ብዙ ስለሂሳብ አያያዝ ሲያሥተምረው፣ ኬኔት ደግሞ ብዙ ነገሮች በማገዝ ከወነለት። ማንም ባይጠቀመውም፣ ‘ሎጋን ማርኬት’ እሚል የሱቅስም አበጅቶ ብዙ የመክፈቻ ማስታወቂያዎች እና መፈክር ወረቀቶችን አበጀለት። የምረቃው ቀን ጆሴፍ ቀኑን ፈቃድ ወስዶ ሻምፔይን ገዝቶ ወደሱቁ ተቀላቀለ። መጥተው ሁሉም ከጥንጥ ከፋዩ፣ ብዙ እማያኮራው፣ የስራ ዓለማቸው የማደግ መጀመር ሙከራቸውን ፍች አደረጉ እና አከፋፈቱን አደመቁት።
ከአሁን ሦስትአመቶች በፊት ድረስ ግን ምንም ሳይለወጥ፣ ኬኔት በባዶ ቤቱ እሚኖር ነበር። ጆሴፍ ተምሮ ዶክትሬት መያዝ፣ ኬኔትም ምህንድስና ዲግሪ እና ማስተርስ ሠርቶ ሀብታም ሆኖ ኬንያ ሄዶ ድንቅ ህንፃዎች ገንብቶ ማስደመም የእሚያልሟቸው ነገርዎች ነበር። ኬኔትንም ለእስጢፋኖስ ‘ሱቅህን አስፋፍተህ የፍራንቻይዝ ባለቤት ሁን’ ብሎ ቢያበረታታውም፣ እሱ እስጢፋኖስ እጅግ እሚያስበው ግን ቀላል ሱቅ ከፍቶ፣ ዉስጡ በዝምታ ጭምት ሆኖ እስኪሞት እያነበበ በቀላሉ መኖርን ነበር።
አሁን ሱቁ ሊወሰድበት ደርሶ በተስፋ መቁረጥ ሳለ ኬኔት እንዳለው የሆነነገር ማድረግ አቅቶት ‘ዘገየሁ’ ማለት እና መፀፀት ጀመረ። ከወጣ አምስት ሰዓት ወደሆነው ክክፍት የለቀቀው ሱቁ ዳግ-ሲደውል ያረጀ ሰው አነሳ ከጀርባው ወጣተ ሴት በድምፅ ትሰማ ነበረች። ዘግቶት የአጎቱን ደብዳቤ ጎን ያለ ብር ማጠራቀሚያ ፈትሾ አንድሺህ ዶላሮች አገኘ። ሊሰርቅ እና ደብዳቤ ሊተውለት አሠበ፣ የሱቁን ኪራይ ሊከፍል ወይም እናት እና ወንድሙ ጋር ሊሄድ ቲኬት ሊቆርጥበት አቀደ። መልሶ ግን ከተተው እና እንደደረሰ ሳይታወቅ ቶሎ አጎቱ ሳይመጣ ደብዛውን ከመንደሩ ሊያጠፋ ተጣደፈ።


 ምእራፍ አስራሁለት
ከጁዲት በተቀያየመ ምሽት እየቃዠ አድሮ ሲነጋም ሱቅ መሄድ ደብሮት ቀረ። በቀጠለው ጠዋት ዘግየት ብሎ ሱቅ ሲከፍት ናኦሚን ሱቁበር ላይ ስትጠብቅ አጊንቶ ትላንት በመቅረቱ ማዘኗን ገለጠች። ‘ይቅርታ’ ብሎ ገብተው መፅሐፍአቸውን ሲያነብቡ አረፈዱ። ከሰአት በኋላ ክሪስማስ ዛፍ ለሱቁ አበጁ። አልሸጥ ያሉትን ወረቀት እና መሳያዎችን ሠጥቷት አገለገሉት እና ማሸብረቂያዎችን ሳለችለት። ቤቱን እጅግ አስዉበው እና ተዝናንተው፣ ጥቂት ስጦታ ሊያዘጋጅ አስቦ ለእናቷ ይቅርታ ብሎ ደብዳቤ አስይዞ ላካት። የገና ስጦታ ለመግዛት ሲያስብ አዲስ ባህል የማዳበር እና አሜሪካአዊ የመሆኑ ነገር እየጠጠረ፣ ህይወትን በእዛ መንገድ መልመዱ እየበዛ መጣ። የሀገርቤት ኑሮን መዘንጋት በአያሌው ጀመረ። በፊት ለገና ይደውል ነበረ። አሁን ግን የሀበሻ ቀንመቁጠሪያን እየረሣ መጣ። እናቱ ግን ብትቆጣም፣ ወንድሙም ጭምር ከአይኑ እየራቁ እንደ እንግዳ እየሆኑበት ሄዱ። ለአደጋ ያጠራቀመው ሁለትመቶ ዶላሮችን አንስቶ ለናኦሚ የጠፋ አባቷ ከላከላት የተሻለ፣ ለጁዲት ርካሽ እና ትንሽ ስጦታ እወዳለሁ ሲላት እንደተጣሉበት የምወደው ቀላል እና ከበር ያለ ነገር ስላለችው ያንን መሰል ነገር ሲፈልግ፣ ለዳዊት ቀደም ሲል መሆን የነበረበትን ደግ ወንድም ሊሆንለት፣ ለእናቱ መቼም የተማመኚብኝን መልእክት እና ካርድ ሊልክ እና ሊደሰት በእዛም ሊያስደስት ቆርጦ በ ፒ ጎዳና ወደ ጆርጅታውን ሞል ይህን ሁሉ ሊሸምት አዘገመ።
ለወንድሙ ነጭ ልብስ፣ ለእናቱ እምቶደውን ሽቶ፣ ለጁዲት ማክማስተርሰን በአስተማሪነቷ የደረሰችውን አንድ መፅሐፏ ‘አሜሪካስ ሪፑዲዬሽን ኦፍ ዘ ፓስት’ እሚል እና ጥቂት መሰል መከራከሪያ አጫጭር ፅሑፎቿን (ስለታሪክ እና ፖለቲካ መከራከሪያዎቿ ናቸው) መሳይ ለየት ያለ – ታሪክ እና ፓለቲካ ግጥምአዊ አድርጎ እሚያወራ – መፅሐፍ ሊገዛላት አሰበ። ጁዲት የፃፈቻቸውን ፈልጎ አየትአየት ሲያደርግ፣ ጨካኝ እምትሠኝ ወይም ጥብቅ ሊቅአዊ (አካደሚክ) ነበረች። ከአፃፃፎቿም ለማለት የፈለገችው እንደሆነ የተማረው የአሜሪካ ታሪክ ምኑም እሚበቃ አይደለም እሚል ሀሳቧን ነው። የኤመርሰን እና አስራዘጠነኛው ክዘ. በጠቅላላው ወዳጅ ነች። ጥቂት ጎረር እና በግሏ አተያይ በኩል አተኩራ በመፃፍ እምትከራከር ነበረች። ከመፅሀፏ የወደደው ክፍል ነበር። ኤመርሰንን እንዲሁም ዴሞክራሲ ኢን አሜሪካ እሚለውን መፅሐፍ ለ አራትመቶ ገፆች ከበታተነች በኋላ፣ የመጨረሻ ምእራፏን ለእማይታወቅ ሜሪ ኦር ስሌቨሪ ኢን አሜሪካ ብቻ እሚል ልብወለድ ለፃፈ የቶከቪል ጓደኛ እና የሱን ፅሑፎች ያሳተመለት ፈረንሳይአዊ ጉስታቭ ዲ ቤይሞንት እሚሰኝ እማይታወቅ አንድ መፅሐፍ ብቻ የደረሰ ደራሲ በክብር መታሰቢያነት ያቀረበችው ምእራፏን ነበር። የ ቶከቪል መፅሐፎችን ሊያሳትምለት የወረሰ እንጂ በራሱ ታዋቂ ያልነበረው ይህን ደራሲ፣ በመዝጊያዋ ጁዲት ያለችለት፦ “ስለ ዘርማንነት እና የሴቶች ሚና በማህበረሰብ ዉስጥ እሚሠብክ ሲሆን፣ የአሜሪካንን መጪ 100 አመቶችም ቀድሞ ያየው ይመስል ነበር። “እንዴት እዚህ ደረስን/how did we ended up here?” እሚለውን አንድቀን ለመጠየቅ ለደፈሩ ማብራሪያ ሊያስይዝ የተፃፈ አሥመስሎታል። ታሪክም በፍጥነት እየተተወ እሚረሳ በመሆኑ የቀደመው ትዉልድ ፈጠራ እሚዘነጋ ሆኗል።” ብላ ነበር።
በጠቀሰቻቸው መፅሐፎች ንባብ፣ እስጢፋኖስ ምንም አዲስ አሜሪካንን አላወቀም። ግን፣ ጁዲትን ተረዳበት። አሜሪካ የወደቀችበትን ዐውዶች እጅግ ከምሯ እንዴት እንደምቶስዳቸው እና ጀግኖቿንም እጅግ እሚማርኳት መሆኗን ተረዳ።
ብር ባይኖረውም፣ የጋዝ እና መብራት ክፍያዎቹን የኤምሊ ዲከርሰንን ግጥሞችን ገዝቶ፣ ለናኦሚ ደግሞ በአስራአንድ አመቶቿ እንዳደገችው የበለጠ እሚያሳድጋትን ስጦታ አስቦ ማስታወሻ መዘገቢያ ልዩደብተር ገዛላት። መቼም ይዛው ተዘዋውራ ብዙ ድንቅ ሀሳቦቿን ሁሉ እንድትፅፍበት አቀደ። ቤቱ ሲደርስ ግን፣ ጁዲት ‘እህቴ ጋር ለበአሉ ሄደናል እስክንመጣ ይቅርታ መልካም በአል’ እሚል መልእክት ትታለት አገኘ። ለብቻው ስጦታዎቹን ሲጠቀልል ቆይቶ፣ ሲመሽ ለግል እርምጃዎቹ ወጣ። አንዲት ሴት የገና የፍቅርቀጠሮ (ዴት) ከፈለገ ስትጠይቀው ተቀብሎ ቤቱ ይዟት ሄደ። አብረው በአንድነት አደሩ። ስትወጣ አንድ ስጦታ ዉሰጅ ሲላት፣ ለወንድሙ ከገዛው በቀረ ያሉትን ስጦታዎች ዘርግቶ፣ ሽቶውን መረጠች። ከተጠቀለሉት ሥጦታዎች የመረጠችው ሽቶነቱን ስታውቅ ግን ‘እኔ አልጠቀምም ለምታውቀው ስጠው’ ብላ ተለየችው።


 ምእራፍ አስራሦስት
ወደ ጆሴፍ ጋር በባስ ለመሄድ ቀደም ብሎ ከአጎቱቤት ወጣ። ተሳፋሪ ጭንቅንቅ ማለቱ፣ መተንፈሻ እንኳ ባለመኖሩ፣ እጅግ የወደደውን የድሮ የአዲስአበባ ሂወቱን አስታወሰው። ያኔ፣ በባስ እንዲሁ ሲሄድ ‘እኔ’ እንዲሁም ‘ብቻዬን ነኝ’ እሚለውን ሀሳብ ያጠፋለት የነበር አስደናቂ ማህበረሰብአዊነትን ያገኝበት ድባቡ የባስ ሂወት አስተምሮት ነበር። ወዲያው ያ ፍቅር፣ ተሣፋሪዎቹን ተወ። ባሦቹ የደርግ አስፈሪ ወታደሮች በማመላለሥ፣ ቀጥሎ ወጣት እስረኞችን ወደ አዲስአበባ ጠርዝ በማመላለስ ብቻ ተጠመዱ። ያ የባስ ፍቅር ተወግዶ፣ ከተማውን ምን አስጨክኖ ባሶቹን ወደእዛ ሽብር እንደለወጠ ይገርመው ነበር።
ጆሴፍ በኮሎኔል ግሪል አስተናጋጅነቱ፣ በግልፅ ባይናገረውም፣ የእሚኮራበት ስራው ነው። የስራውን ስፈደራ ሲገልጥ የሚለው፣ ‘የትልልቆች መብልቤት ነው!’ ‘የልሂቃኖች (ኤሊትስ) መመላለሻ ደጅ ነው!’ እሚሉ አድናቆቶችን ስለሆነ፣ በስራው ይኮራል ማለት ነው ብሎ እስጢፋኖስ አመነ። ሴናተሮች፣ ጠበቆች፣ ሎቢስቶች ወዘተ. ምሳ እና ራት እሚበሉበት ሲሆን፣ ጆጆ የመቶ ሴናተሮቹን፣ የተወካዮች ም/ቤት ደግሞ ግማሾቹን ያውቃቸዋል፣ ፊታቸውን ለምዶታል። ሁሌ ይገመግመዋል። በሳምንቱማብቂያ ቀኖች በተገናኙ ቁጥር የፊትአቸውን ሁኔታ ለሁለቱ ጓደኞቹ ይተነትነዋል። የፖለቲከኛዎቹን ፊት ካወቀ እና ከገመገመ፣ ፖለቲካውን በደንብ አጠናቅቆ የተረዳ ይመስለዋል። ከፊትአቸው ጀርባ ያላቸውን የፍሬነገር ነጥብዎች አይመለከትም። መጀመሪያ ወደ ዲሢ. ሲመጣ፣ እንደ ባስቦይ፣ ቀጥሎ የሆቴል እንግዳ ተንከባካቢ (ቤልሆፕ)፣ ቀጥሎ አሁንደግሞ እንደአስተናጋጅነት እየሠራ ነው። በሥራው ተስፋ ሳይቆርጥ ሦስተኛ ተከታታይ ዲግሪዎች ሊሠበስብ እና ዶክተር (ሊቀምሁርዎች) ሊሆን ሁሌም እንዳሠበ ቆይቶ ነበር። አንዴ ግን ተስፋ በመቁረጥ ዘረሁኔታ (ሞድ) ሆነ እና ‘በከተማው ቤተመፅሐፍቶች በቂ ተደራሽነት ስላለ ከፍሎ መማሩ አያስፈልግም በግል መማር ይቻላል!’ አለ። አንዴ በታዳጊነቱ ያነበበው አንድ ግጥም፣ ናፈቀው አፈላልገው አገኙት። ስለኮንጎ ሲሆን፣ በስልሳዎቹ ተስፋ መጥፋቱን ከዳንቴ አሊጌሪ ዲቫይን ኮሜዲ አገናኝቶ፣ ግን ያንን ከሲኦል ሲወጣ ገነት ያየ ቀናአዊ አጨራረሥ ሳይከተል፣ የተረከ ግግጥም ነበር። በሂደት በአስተናጋጅነቱ አመቶች፣ በካፒቶል ሆቴል እና በኮሎኒያል ግሪልም፣ ግጥምን እራሱ እያስተካከለ ይፅፍ ነበር። በሂደት የግጥም ነገሮች ሰልችቶ ካመቶች በኋላ፣ እየጠጣ እና እያጨሰ በመናቅ የተስተናጋጆቹን እረባሽነት እና ተናድደው እንዲወጡ ያልሞከሩት እንዳልነበር ብቻ ያወራ ጀመረ። ኮሎኒያል ግሪል ማለቱን ትቶ ኮሎኒያል ይለውም ጀመረ።
ወደ ስራቦታው ሲደርስ፣ አብረው ብዙ ሳይቆዩ ለማስተናገድ ጆይ ሲሯሯጥ፣ አዘነ። ጆይ ጓደኞቹ በስራሰዓት ሲጠመድ እንዳይመጡበት ይሻ ነበር። አሁንም፣ በአስተናጋጅነት መቅረቱን ለጓደኛው ሲያሥመለክት አዘነ። ሠፋ ሁኔታውን ተረድቶለት አኳኋኑ አላምር ብሎት ሊያስተናግድ በሄደበት በሩቅ ቻው ብሎት ወደ መንደሩ አዘገመ፤ ያም ከኮሎኒያል ግሪል እስከሎጋን ሰርክል ሀያ ብሎክዎች ነበሩ። መንደርዎቹ፣ ከቶ በረዥም ጊዜ ያልተቀየሩ፣ ሌላው ሲመነደግ የቀነጨሩ ነበሩ። ወደተወው ሱቁ እየተመለሠ ብዙ የከፉ ነገርዎች ይገጥሙት እና ይዘረፍ ወይም ይቃጠልበት እንደሆነ ሳለ። በእዛ ያልተለወጠ መንደር በቋሚነት መኖር መወሠኑን በከፍተኛ ኩነት ስላልወሠነ ዳግ-ያስብ ጀመረ። የመጀመሪያዎቹ ሁለት አመትዎቹ እጅግ የአዲስአበባ ብጤ ሆኖለት ነበር። ብዙ ቤተሠብዎቹን ያናግር፣ ይጨዋወት ነበር። ያልበለፀገ መንደር ሲመለከትም አዲስአበባን አቻ አድርጓት ያስብ ነበር። በተለየ፣ አባቱን ማሥታወሥ እና በሀሳቡ እሱን ማውጋት ትልቁ መንገዱ ነበር። ከቤት መራቁን መልመዱ አባቱ ከሀሳቡ ከመራቅ ጋር የተቆራኙ ሆኑበት። ሁሉም ከአባቱ ጋር አብሮ ሄደበት።


 ምእራፍ አስራአራት
በገና ማለዳ፣ ስደተኛ አገልጋይ ነው እንጂ እሚያከብረው በዓል አደለም በእሚል ሡቅ ከፈተ። በብቸኝነት ተደብሮ ሲነግድ እና አመቱን ሙሉ ሊራራቅ ይጣጣር የነበረን ለበአል የተሰበሰበ ቤተሰብን እቃ እየቸረቸረ አገለገለ። በተለይ አሉሚነም ፎይልን ከግማሽአመት ሽያጩ የበለጠ ያን ቀን ሸጠ። ለዓይንሲይዝ፣ ጆይ ጋር ደወለ። ኬኔት ለብቻው በበዓል ሥራ ሊሠራ እና ቢሮ ለማስተዳደር ሊቀበል እንደታመነ በአለቃው ተነግሮት፣ ለብቻው ሥራ እንደገባ ተነገረው። ጆጆ ‘መሀንዲስነቱ ቀርቶ ጅል በመሆን ስራ ገብቷል!’ ብሎ ነበር የገለጠለት። ቀጥሎ ከተማዳር ለመጠጣት ተቀጣጠሩ፤ ለግሉ የበዓል ስጦታ ሙሉ ታክሲ ለራሱ ቀጥሮ ተጓዘ። ዘግይቶ ጆይ ሲደርስ እስጢፋኖስ ሠክሮ ጠበቀው። እሱም እርካሽ ወይን አልሸጥ ሲል ቀጣሪዎቹ ለበዓል-ሥጦታ ሰጥተውት ስለነበር ቀማምሶት ሲጨዋወቱ አመሹ። ኬኔት በሥራው ዉሎ እና አምሽቶ፣ የከበደውን ሰው በዓል ሲያከብር እሱ የደረሰበትን የሁኔታ ገሀድ ተጋፍጦ በተበላሸ ስሜት ሲገባ ቀልደውበት ተቀላቀለ። ‘ባሪያ ነህ’ ብሎ ጆጆ ቀለደ።
እየጠጡ፣ ሁሉም ሲሠክር የለመዱት ጨዋታ መጥቶ ስለ ጁዲት ተነሣ እና የሞሪሸስ ዜጋ የነበረው የተለያት ባሏም ተነሥቶ በእዛው የሞሪሸስ አምባገነኖችን ሲያወሩ ቆዩ። ኬኔት ነገ ስራ ‘ስለምገባ’ ብሎ ሊመለስ ሲያስብ ደግመው በባሪያነቱ ቀለዱበት። ጠንክሮ መስራት እና መለወጥ ነው በማለት ስለሁሉም ወላጆች ሁለቱንም ጠየቀ። ጆጆ ነጋዴ፣ እስጢፋኖስ ጠበቃ አባት ነበራቸው። እሱ ያልተማረ ድሀ የጆሞ ኬንያታ ስእልን ብቻ ያወረሰው አባት በኬንያ እንደነበረው እና አሁን እሱ ሰርቶ አንድ ሺህ ዶላር እና ሱፎች ከመኪና ጋር እንዳለው ተናግሮ በመናደድ ጥሎአቸው፣ ከፍሎ ወጣ።


 ምእራፍ አስራአምስት
የቀረውን የድሴምበር ወር፣ እስጢፋኖስ እነዮዲት እና ናኦሚን እጅግ ናፍቆ ሲጠብቅ ቆየ። በወጣበገባ ቁጥር ቤቷን አሻግሮ እንቅስቃሴ ካሳየው እየፈለገ ከረመ። አሁን የህይወት መሠረት እንደሆነችው አምኖ እጅግ ናፈቀ። ዘ ብራዘርስ ካማራሶቭን በግሉ አንብቦ ጨረሠ። በመጨረሻው ባለ ትርክቱ ደጋግሞ አልቅሦ፣ ለናኦሚ ተማሪበት አንድ ትዝታ ማኖር ህይወት ያድን አለ እሚለውን አሠመረበት። አክሎ በእየቀኑ ምርጥምክርዎች (አፎሪዝም) እያከለ ፅፎበት ቆየ። ከአዲስአመት ማግስት ኪራይ ሊከፍል ሢሄድ ገንዘቡ እማይሞላ እንደሆነ ተገነዘበ።
ሎጋን ሰርክል እጅግ ከፍተኛ የመለወጥ ሁኔታ ስለነበረው፣ የህንፃዎች አይጠቅሙም ብሎ ሠዎችን አፈናቅሎ ማፍረሥ፣ እና የገበያአው መቀነሥ ሆነ። ሲመሻሽም ሴተኛአዳሪዎች መንደሩ ወደመታፈር በመቀየሩ እየቀነሱ ገበያ ስለጠፋብአቸው የእሱም ገበያ አያስመሽም። እስከ ቅርቡ ከኪራይ ወጪው ቀጥሎ ጥቂት ለድንገተኛ የቢራ እሚያወጣው በለጥያለ የብር ቁጠባ-ዝግጅት ነበረው። የገና ሰሞን ግን ያንን አዛብቶ ልዩነቱን መመለስ ስላቃተው አሁን እሚከፍለው ጠፋ። የገና እለት (ጃንዋሪ 7) እናቱ ጋር በላከችለት ብር አማካይነት ብቻ መልሦ ወደእሷ ደወለ። ስለግጥም መፅሐፍ ስጦታው፣ ዲኪንሰንን እንደእምትወድ ስለእሚያውቅ መላኩን ነገራት። በገጠርአማ የማሳቼሴት መንደር በባይተዋርነት ሳታገባ ኖራ በሞተችወቅት በቤቷ መሣቢያ ዉስጥ የታጨቁ ግጥሞቿ ተገኙ። እናቱ እምትሰማውን ትርክት ሁሉ በቅርበት በግልዮሽአዊነት (ፐርሰናሊ) ስለእምታስብ እጅግ ለገጣሚዋ አዘነች። በግል ተነጥሎ መኖርን እሚያሣምሩ ብዙ ግጥሞች የያዙ መሆኑን ገለጠ እና እንደእምትወደው አሣወቃት። ገጣሚዋ ለብቻዋ በግጥሞቹ ብቻ መኖሯን አሳወቃት። መነሻ ግጥም እንድታነብብ፣ “for each ecstatic instant” እሚለውን ምረጭ እና ለምን እንደእምትወጂው ይገባሽ አለ አላት። ዳዊትም ልብሱ ሆኖት አለ አለችው እና ስልኩን ዘጋ።
የነዋሪዎች ማፈናቀል በሰፈሩ ቀጠለ። ከፍተኛ የሰዎች እና አፍራሾቹ ጠብ እና ጩኸት ሲሆን፣ ህግዘብ መጥቶ የማፍረሱን ሥራ በማስከበር አስቀጥሎ ሰላምን በጎን ለማስጠበቅ መጥቶ ማረጋጋት ጀመረ። በቀጣይም ቀን አንድ ሁለት ቤተኛ እንዲለቅቅ ሲገደድ አንዳንድ ሠራተኛ ግጥም ብሎ በኬኔት ሀሳብ መሰረት በተከፈተው ዴሊ ምግብ መመገብ ጀመሩ። በሰሞኑ፣ ሰው መሰብሰቡ እና ተፈናቃይ መብዛቱ ቀጥሎ ገበያው ደርቶለት ቆየ። ማታ የፈረሡ ቤትዎችን እሳቤ ለማግኘት ነጥሎ አንዱን የተለቀቀ ቤት ሆንብሎ ጎበኘ። የተዉት ዕቃ የተቀደደ እና የቆሸሸ ቲሸርት ነበር። ድሀ ሳሉ ለመባረርአቸው አዝኖ ለራሱም አንድቀን እንዳይመጣበት ፈርቶ ተመለሠ።
ሚስስ ዴቪስ በሱቁ መጥታ ተመጋቢዎች በሱቁ ሲያወሩ እንደሰማው ‘የመንደሩ የነዋሪዎች ማህበር ስብሠባ ሊያደርግ ነው!’ አለችው። በእጅየተፃፉ የስብሠባጥሪ በራሪወረቀትዎች ይዛለት መጣች። ወደሱቅህ ለመጣ ሁሉ አድል ብላ ሰጠችው። መንደርተኛው ‘ሰፈሩ ከመፍረስ ይቁም!’ ብሎ ሊሰበሠብ መሆኑን ዳግ-ገልጣለት የጃጁ አጥንቶቿን እንዳይብሱ እንደእምትፋለምላቸው ልማዷ ወተት ይዛ ወጣች። እሱ ግን መጨነቅ አልፈለገም። በርካሽነቱ የተነሣ ወደ ሠፈሩ ተማርኮ መጣ። አሁን ካስወጡት ተቀብሎ ሊወጣ አቅዶ ተወው እንጂ በስብሰባውም በመፍረሱም መጨናነቅ አልፈለገም።
የእሚለያዩ የክርስትና እምነት ቤተክርስትያንዎች የነበሩ የተለያዩ የአምልኮ እምነትዎች እየተተካኩ መቀመጫአቸውን ባደረጉበት አሁን በተተወ እና ቅርስ ሊደረግ በታቀደ፣ ከቅርብጊዜወዲህ ባይተዋርዎች እና አዛውንቶች እሚሰበሠቡበት ብቻ የመሰለው ዕድሜ ጠገቡ ግንባታ ስብሠባው ተገናኘ። ሲገባ መቶ በላይ ሰዎች ነበሩ። ከጀርባ በሩ ገብቶ እንደቆመ ሲቃኝ ጁዲትን ብቸኛ ነጯን ሲመለከት ሊመለስ አሰበ። እና ልክ ሊመለስ ሲል ወይዘሮ ዳቪስ በዓይንዎች ከመድረኩ ሆና ያዘችው እና ተቀመጥ ተባለ። ጁዲትን አይቶ ፈገግታ አቅርቦ አልፏት ‘የተማረችው የእነ ኤመርሰን እና ዲሞክራሲ አሰራር ያለ ከመሰላት ትገርምአለች!’ ብሎ በልቡ እያሾፈ ፊትለፊት ተቀመጠ።
ስብሰባውን ሚስስ ዴቪስ ስለመንደሩ በአልሚዎች የመነሳት እና ረዥም ዘመን የኖሩ ተነሺዎች መኖርአቸውን ችግር ብላ በመጥቀስ ከፍታ መፍትሄ ፍለጋ እንዲተባበሩ በመጠየቅ መድረክ ከፈተች። ብዙዎች የሸመገሉ ተነስተው ተቃውሞ ሰጡ። ጁዲት ‘ስድስት ወርዎች ብቻ ብቆይም የሰፈሩ ጉዳይ ገብቶኝ አለ እና እኔም ይሰማኝ አለ!’ ብላ ስትጀምር አንድ ድምፅ ‘አፍሽን ዝጊ’ አላት። ወዲያው ተቀመጠች። አቤቱታ (ፔቲሽን) እንዲዞር ደግሞ ተበተነ። አልሚዎች ቆመው ነዋሪዎቹ መኖር ይቀጥሉ እሚል ነበር። ፌብሩዋሪ በቂ አቤቱታ ፈራሚ ቢገኝ ከከንቲባው ጋር ለቀጣዩ ሥብሰባ ሊመጡ ቀጥራቸው ወጡ። ዴቪስን አብራው እስከሰፈር ልትጓዝ ቀረብ እያለች ሥትዳዳ አምልጦ በመሄድ ጁዲትን ሰፈር አገኘ። ‘ከመጣሁ ጥቂት ቆየሁ። ፋታየለሽ (ቢዚ) ሆኜ አላገኘሁህም!’ ብላ ናኦሚ ከእህቷ ልጅዎች ጋር ተደስታ ሥትቆይ በእዚያ እሚገኝ አዳሪ ትምህርትቤት እንደከተተቻት አሳውቃ አስደነገጠችው። የአባቷን ስጦታ ‘ስጪልኝ’ ብላት ስለነበር ልታስረክበው ቤቷ ገቡ። አባቷን አታቀውም ሲገናኙ ከፍተኛ አጫሽ ስለነበር አፍጠረኑ አስጠላት። አትወደውም። ስጦታው ሲከፈት የቆየ ታይፕመፃፊያ ሲሆን የቁልፎቹ ፊደልዎቹ የተቀረፁት በእንሰሣት እና ቀለምዎች አሸብርቆ ነበር። ሰፈሩ ሲፈርስ የደራለትን ንግድ እንድትመለከት እና ጣፋጭ ሳንዱች እንድትመገብ ጋብዞ ተለያዩ።
በማለዳ ጧት ወደሱቂ ሲወጣ፣ ጁዲት መኪናዋ በድንጋይ ተመትታባት አየ። ሲቀርባት፣ መስኮቷ ተሰብሮ የተሰረቀ ግን ስለሌለ መስታወት ማፍረሱ ብቻ እንደታለመ አስተዋለ። ገብቶ ሊጠራት ሲል ከበሯ ወንድ ወጣ። ፊቱ ጠይም፤ አረብ-አፍሪቃ ድብልቅነቱ የጎላ፤ ስለነበር ዕዉቅ የስነምጣኔ መምህሩ እንደሆነ አስታወሠው እና እማያቀው ቢሆን ካቀደው ሁሉን ትቶ መመለስ ታቀበ። ዜናውን አረዳው። ጁዲት በማያቃት መልኩ ጯኺ ሆና ‘ማነው?’ ብላ ተጣራች። በፈረንሳይአዊ (ፍሬንች) ‘አንድ ሰውዬ መኪናሽ ተሰብሯል ይልሽ አለ’ አላት። ሮጣ ወጥታ ሰፋን ስታይ ረጋ አለች። ከቤቷም ሮጣ በመዉረድ የሆነውን ስትመለከት ደንግጣ መጮህ ወይም ማልቀስ አቃታት። ባሏ አያድ፣ እንደ ፈረንሳይዎች በእርጋታ ሲጋራ መለኮስ ወይም እሷን መርዳት አቅቶት ቆሞ እንደእሱ ሲመለከት ተናደደ። እንደ ፈረንሳይአዊ (ፍሬንች) ሄዶ በማቀፍ ማፅናናት ሆኖ ለጆሮዎቿ ‘C’est la vie’ በማለት ወይም ሲጋራ አውጥቶ በመለኮስ ዳግ-ምላሽ (ሪአክሽን) መስጠት አለበት ብሎ ሳለ። ግድየለሽነቱን ተመልክቶ በመናደድ ተለይቶአቸው አዘገመ። ዞሮ ሲመለከት ያው እሷ ክው ብላ የቀድሞባሏም ለብቻው ነበር። ተናድዳ እሱም እንደራቀ፣ እየዞረ እያያቸው መበሳጨት ቀጠለ። ወደ ሱቁ ሲያዘግም፣ ከፍተኛ ቅያሜ ይዞ አላስችል ብሎት እየዞረ ተመልክቷት ክውታዋን እየተጋራ ከእይታ ጠፋ።
በሱቁ፣ ስለ ጁዲት መኪና ወሬው ግሎ አረፈደ። ከምኑም በላይ ስለእሷ ሲወራ የተረሳውን ያማረ የሆነውን ትልቅ ቤቷን እማያደንቅ አልነበረም። በመንደርተኛዎቹ ምንም እንዲህ ያለ ቤት ዉስጥ መኖር እሚቻል አይመስልአቸውም ነበር። ከሰዓትበኋላ ድንጋዩ ቀጥሎ ወደቤቷ መስኮት ተወረወረ። ወረቀት አብሮት ተገኝቶ ሲታይ ‘ወጪ’ ወይም ‘ልቀቂ’ እሚል ተፅፎ ተገኘበት። በመጨረሻ፣ ፖለቲካአዊ ጉዳይ እየሆነ መጣ። አንድ አዛውንት በሱቁ አካባቢ እሚንቀዋለል፣ ‘ሁሉን አየሁ ወጣትዎች ናቸው፣ ወርውረው በእርጋታ ዘና ብለው ሄዱ’ አለ። ዴቪስ መጥታ በወሬው ተጠምዳ እንዲሁ ሰፋን መሰል ወሬ አወራች።
በማግስቱ፣ በ ኒውሀምፕሻየር አቬኒው እና 12ኛ ጎዳና ጥጋት እሚገኘው የኒውሀምፕሻየር ታወር መስኮቱ ተመትቶ ተገኘ። በ 1920ዎቹ የስነምጣኔ መበላሸት ወቅት ተገንብቶ የተረሳ እና በበቀለበት ቁጥቋጦዎች ሴተኛአዳሪዎች ከ ‘ዲር ጆንዎችአቸው’ ጋር ፈጣን ስራዎችን እዚያው እሚሠሩበት የሆነ ነበር። በሱቁ የተስተናጋጆቹ ወሬ ቀጥሎ ዋለ። የሁለተኛው ጡብ ወረቀት ደግሞ ‘የስድስት ሰዎች ቤተሰብ ስላፈናቀሉ የተወረወረ ቅጣት’ ይል ነበር። ሁለተኛ የእለቱ ወሬ ደግሞ፣ በ 13ኛ መንገድ ቆሞ የነበረ መርሴዲስ መኪና ጎማው ተቀድዶ ተገኘ እሚል ሆነ። ማታ አምሽቶ ሱቁን እየሰራ ሰፋ ወሬዎቹን አደመጠ። ወጣት እና ትልልቅ ሰዎቹ ሰፈርአቸውን በተሳትፎ ለመቆጣጠር ብለው ተሰብስበው ብዙ ማውራት ጀመሩ። አፍሪቃ እና አዲስአበባ እንዲህ ባሉ በማህበረሰብአቸው ለመሳተፍ ፈልገው በእሚያምፁ ወጣቶች እንደተሞላ እና ከእነኬኔት፣ ጆ፣ እና እራሱ ዕውቀት የበለጠ ያ የከበደ ሀቅ ሆኖ እንዳለ አሰበ። ጥቁርበጥቁር ለባሽ ጡብ ወርዋሪዎቹም እንደተባለው ሊኖሩ እና ሰባሪዎቹ ሊሆኑ ይችል አሉ። እኩለሌሊት ድረስ ሰርቶ ቤት ሲመለስ፣ ጁዲት ቤቷ በመብራት አብረቅርቆ አያድ ጋር በከፍተኛ ጩኸት ስትሰድበው እሱም ሲመልስላት አደመጠ።
ጧት ሱቁ ሲመጣ ጡብ ቤቱበር ላይ ምንም አደጋ ሳያመጣ ተጥሎ አገኘ። በርከፍቶ አስደገፈበት። ወዲያው ጁዲት ገባች። የናኦሚ ደብዳቤን አስረክባ ‘ያን ቀን መኪናዬ ባይመታ አቀብልህ ነበር’ አለችው። የተማሪቤት ጦማር አድራሻዋን ሰጥታው ጦማር በመፃፃፍ ሊመልስላት ተነጋገሩ። ጁዲት ባሏ ጋር እስኪነጋጋ አካባቢ ስትጣላ ነበር። እሱም በመስኮት ሲያደምጥ ነበር። ግድየለሽ እና ለልጁ እማይጨነቅ፣ በልጁ እሚጠላ መሆኑን ጁዲት ስታነሳበት አያድም እየጮኸ ምላሽ ይሰጥ ነበር። የተለመደች አሜሪካአዊት ሴት እና ሆንብላ ያማለለችው እንደሆነ፣ ልጁን ደግሞ እሚጠላት በከፊል ከጁዲት የመጣውን የማንነቷን ጎን ለይቶ ብቻ እንደሆነ እንደሆነ አሳወቃት። እንዲህ ሰሞኑን ንብረቶቿ በተጠቁበት ቆሻሻ በሆነ ሰፈር ህፃን ልጇን ማምጣቷንም ጠቅሶ ከሠሰ። ሲጨቃጨቁ እንዳደመጠ ነጋግቶ አሁን ጁዲት አዝና ለሰፋ አያድን ከ ኮኒክቲከት በማምጣቷ እና ከእሱ ጋር በመገናኘትአቸው አዝና ለእራት እንዲቀጣጠሩ አሳሠበችው። ማቅማማት አቃተው እና ለነገ ማታ ተቃጥረው ወጣች። የናኦሚ ደብዳቤውን ሲያይ እንዳሰበው ናኦሚ እሱ ጋር ስትመላለሥ የኑሮው አካል ሆና በእሱ ዋጋአጊንታ እንደነበረደ ተረድታው ነበር። ‘አሁን ብቻህን እንዳልሆንክ ተስፋ አለኝ!’ አለች። ቀጥላም፣ ‘እዚህ ባለሁበት ሰው ቢኖርም እንደአንተ ምርጥ ግን አይደሉም!’ በማለት ቀጥሎ እንዲፅፍላት ገልፃ ተሰናበተች። በመዳፍብር-(ካሽ)-ዘጋቢው (ሬጂስተር) ቂጥ አኖረው፤ ‘ደግሜ ካነበብኩት እዚችው ስፍራ ቆሜ ላነበው ነው የምፈልገው’ ለራሱ አለ።


 ምእራፍ አስራስድስት
በሎጋን ሰርክል እና እሱ መሀከል ሦስት ብሎክዎች ብቻ ቀርተው ነበር። የሎጋን ሰርክል ራቅ ብለው ሲያዩት ያለው ድባቡ ሰፋ አዲስአበባ ከአባቱ ጋር ከቢሮው ሲወጣ ከሰዓትበኋላ እሱን ይዞት ይራመዱበት ከነበረው መናፈሻ ይቀራረብ ነበር። ያ ሎጋን ሰርክልን የመረጠበት አመክዮ ነበር፤ አባቱ ከቢሮ ይዞት ከሰዓቱን ሳይነጋገሩ በፀጥታ ሆነው በመንገድዳሩ ጭንቅንቅ ገበያ እና ግፊያ አልፈው በፀጥታአማው የንጉሱቤተመንግስት ጥላ ስር የነበረው መናፈሻ ይደርሱ እና አረፍ ብለው ፀጥታን አስተምሮት ወደቤት ይጓዙ ነበር። አባቱ ፀጥታን ሲመጣ ሳይሆን ጋብዘህም በህይወትህ ልመደው ይለው ነበር። ግን አባቱ በመናፈሻው ሲቆዩ ሀሳብ ሲበዛበት ለራሱ ያጉተመትም ሁሉ ነበር። የሞቱ ዘመድዎችን ስም ይጠራ ነበር። ከሰፋ መወለድ በደህና ቀድመው ያረፉትን እናት እና አባቱንም ይጠራ እና ያጉተመትም፣ ህፃኑ ሰፋ ደግሞ ያደምጥ ነበር። ጃንዋሪ 23፣ 1977 (ጂሲ.) ላይ የመጨረሻ ጉዞአቸውን ወደመናፈሻው አደረጉ። በስድስት ወሩ አካባቢ አባቱ ተገደለ። አባቱ ጋር የመጨረሻ ጊዜ ወደመናፈሻው ሲመጡ መንግስቱ ኃይለማርያም (ኮሎኔል) ቀይሽብርን አውጆ በጠርሙስ ቀይ ቀለም በመወርወር የጠላትዎቹን ደም በምሳሌ በመግለጥ ግድያዎቹን አዝዞ የአብዮት ጠላት መገደል የተጀመረበት ሰሞን ነበር። ያኔ፣ በመናፈሻው መጨረሻ ቀን ሲደርሡ ከጭቃ እግርዎችአቸው ጋር እንደክብሪት የተደረደሩት ታዳጊዎች በአንገትዎችአቸው በወረቀት ‘ከሀዲ’ እሚል ተፅፎብአቸው ተገድለው በመንጋለል ተሰትረው ነበር። ጠባቂ አንድ ዘብ እሬሳዎቹን እየጠበቀ ሰው ከመጣ እንዲጎበኝ ተደርጎ ነበር። አባቱ ይዞት መናፈሻ እንደደረሡ የሞቱትን አየ። ላለመመለስ ግን ወሰነ። ከቶ ዘቡም ሟቾቹም በመናፈሻው እንደሌሉ ያክል አድርጎ ልጁን ይዞ ወደዉስጡ ዘልቀው ገቡ። ያንን ያደረገው አብዮቱ እንደሌለ ለመካድ የግሉ እርምጃ መዉሰዱ ስለነበር ነው።
እኩለቀን ሲል፣ ሱቅ ከመሄድ ወደቤቱ ተመለሰ። ማታ፣ በጁዲት ቤት መቃጠል ጊዜ፣ እነኬኔት እና ጆ መጥተው ጆ የሰረቀውን ወይን እና ያዘጋጁትን ተርኪ ሳንዱች እየተመገቡ፣ ሰፋ የመንደሩን ሁኔታ አብራራ። የጡብ ዉርራዎቹን፣ ጥቁር ለበሱ እሚባሉት ሰዎች፣ የአያድን ሁኔታ ወዘተ. ነገራቸው። መጥፎ ምልክት ነው ሲሉት ገበያዬ ግን ጨምሯል አለ። ግን አሁን ቀንሶበታል። ዛየር ሰው ሲጨነቅ ወጪ ያወጣ ነበር ብሎ ጆ ያንን ያብራራ ቀጠለ። አማፂዎች መጥተው ‘ጨቋኝዎችአችሁን ይኸው ያዝን!’ ሲሉ የመንደሩ ሰው ይገረም አለ። ‘ጨቋኝ ነበረን እንዴ?’ ሲል ለማረጋገጥ አንድ አምስት ሰው እዚያው ይረሽኑላቸው ነበር። ‘አሀ ተጨቋኝ ነበርን!’ ብለው ተደስተው ብር ይከፍላሉ፤ በጣም የተደሰተ አንዱ ሚስት እና ልጁን ሁሉ ሰጣቸው። ‘የአፍሪቃ ጉዳይ እንዲህ በልጅዎች እሚደረግ ጦርነት እና አመፅ ይበዛው አለ’ ብሎ ጆ አብራራ። በስድሳዎቹ ድሮ ተስፋ ነበረን፣ አለም እና አፍሪቃ ነፃ ወጥቶ ወደአንድ ነገር እየተጓዘ ነበር። ዛሬ ግን እኒህ እሚረብሹት ምንም የሌልአቸው ልጆች ናቸው። ጆጆ የሩዋንዳ ማጭድ፣ የፖኪስታን ድንጋይ፣ እዚህም የተነሱት እና ሰፋ ዘንድ የደረሱት ጡብዎች ‘የእኛ መገለጫ ናቸው!’ አለ። ጡብ ነን እሚለውን ሀሳቡን አሳበቀ። ሲወያዩ፣ ድንገት የእሳት ማጥፊያ፣ ህግዘብ (ፖሊስ) እና አምቡላንስ መኪናዎች ጩኸት ሰፈሩን ቀወጠ። ጆጆ የአፍሪቃ ጦርነትዎች በህፃናት መከወኑን ሊያሳይ የሠላሳ አመትዎች ጦርነትዎችን መረጃዎቹን ሲያሠላ የአደጋው ድምፁ ከውጭ ወደሱቁ መግባቱ ከባድ ሆነ። የአፍሪቃን መንግስትዎች ግልበጣ፣ እረሀብ እና የልጅዎች ዉጊያ ተሳትፎ ሲወያዩ አፍሪቃ ድረስ ያልሸሸ፣ እዛው የእራስአቸው ህይወትም ትራጄዲ እንዳለው በተግባር ለመመልከት መገደድ ጀመሩ። የእሚነጋገሩት ሁሉ የአህጉሩ መከራ በመጨረሻ የእራስአቸውን መከራ ለመርሳት የተደረገ ሆኖ ሰንብቶ አሁን ሁለቱም (የአፍሪቃ እሚሉትም የእነሱም ገሀድ) ችግርዎች ወደ መጋጠም (መመሳሠል) ጀመሩ።
ጁዲት ከባልደረባዎቿ እራት መከወን ላይ ሳለች፣ ቤቷ መንደድ ጀምሮ፣ ሰው ተሰብሥቦ እየተመለከተ ነው። ምንም አልዳነም። እሳትአጥፊዎቹ ሱቁ ገብተው የተናገሩት ቢኖር፣ የቀረውን ወለል፣ እሷ ስላልነበረች እንዳላዳኑት ነው። አምስት አመትዎች ቀድሞ ሰው በሎጋን ሰርክል ተተኩሶበት ተገድሎ የመንደሩ ሰው እንደተሰበሰበው አሁንም ሰው ተሰብስቦ ይህን ልእለቤት ሲምቦገቦግ ተመልክቶ፤ ሁሉም አራት ወለል ወድሞ ጁዲት ደረሠች። ተስፋቆርጣ ስትንቀሳቀስ እሚደርሰውን ይህን እምታውቀው የነበር ይመስል ነበር፦ ጊዜዋ በሎጋን እማይዘልቅ ጊዜአዊ የነበረ እንደነበር እና ሌላ መኖሪያ ስታስብ እንደነበረ አሳበቀ። ስለቤቷ ሰፋ ማዘኑን ገልፆ ተለያዩ። በመንደሩ ቆይታዋን የአምስት ወርዎች አካባቢ የረዘመ መጥፎ ህልም ያክል፣ ልትተወው እንደምትችል አሰበ። እነኬኔትም ከሱቁ አዝና ስትወጣ አይተዋት በአይን አወቋት። ምሽቱን ጉዳይዎች ሲያወጡ እና ሲያወርዱ በሱቁ አመሹ። ያን ማን እንደከወነ ሲጠያይቁ ቆዩ። በማግስቱ ፍራንክሊን ሄነሪ ቶማስ የተሰኘ የቅንጡ ቅኝገዥ ስም የያዘ አዛውንት ወንጀሉን እንደከወነው በይፋ ተነገረ። ጥቁርለበሽዎቹ ወይም ሌላዎች የተባሉት አሉባልታዎች ቀርቶ፣ የጡብ እና እሳቱ አደጋ ፈጣሪ የሆነው ይህ ሽማግሌ ሰው፣ የተሰረቀ የትመ. (ቲቪ) ግንኙነት ለመንደሩ ይሸጥ ነበር። በሎጋን ሰርክል ድሀ እና በሀምፕሻየሩ አፓርታማ ከሁለት ልጅዎቹ እና ሚስቱ ጋር ለአስራስምንት ዓመትዎች ይኖር የነበረ ነው። አብሮ የተለያዩ የጥገና እጅስራዎችን በመሠራራትም ይታወቅ ነበር። ያን ባለ አንድመኝታ ቤቱን ባለፈው ዲሴምበር ሊዝ አለቀበት ብለው ሢሶ ዋጋ ጨምረውበት ሂሳቡን ክፈል ሲባል ነበር ያቃተው። ሲያስለቅቁት እጅግ ተናደደ። ወደ ጊዜአዊ መጠለያ እሱ ሲገባ ሚስቱ እህቷ ጋር ልጆቻቸውን ይዛ ተለየችው። የጁዲት ቤቷን አቃጥሎ ከወጣች በኋላ በሳምንቱ የእጅስራ እቃዎቹን በሻንጣው ይዞ የተቃጠለ ቤቷ ተደብቆ ሲገባ ህግዘብ ያዘው። ቤቱን አድሶ ሊኖርበት በማሰቡ ቀውስአዊ-ቅዠት (ዲሉዥን) ነበረበት። ህግዘብ ሲጠይቀው ‘ሰው አለመኖሩን አረጋግጬ ነበር ክብሪቱን የለኮስኩተደ’ ብሎ ተናዘዘ። በ ዋሽንግተን ፖስት የወጣውን ይህን የአደጋውን ወንጀለኛ ዘገባ ሰፋ አንብቦ ሲጨርስ ከተለጠፈው ከሰውየው ፎቶ ጋር እራሱን ተመሳሥሎ አገኘው። መላጣነቱ እሚያመሳሥለው እና እድሜው እንደእሱ ጥቂት ሲገፋ በተለይ እንደእሱ እሚመሥል መሆኑን አስተውሎ ምስሉን አጠገቡ አቆየው። ህግዘብ በሎጋን ሀውልት ጎን በመኪናው እየቆየ መንደሩ ጥቂት ቀኖች ያን ሰሞን ጠበቀ። ብዙ ሳይቆይ ግን መኪናው እና ህግዘቡ ተነሡ። ሎጋን ለብቻው ቀረ። ከእሳቱ በኋላ ሱቁን ያለደንብ ባሻው ጊዜ ለአንድ ሰሞን ከፈተ። እንደ ኬኔት አባባል ሊያዘጋው ወይም ደንበኞቹን ሊያጣ ብሎ አልነበረም። ለናኦሚ እንደፃፈው እና የአጎቱን ደብዳቤዎች መሰለ ብሎ እንዳልላከላት ደብዳቤው፣ በስርአቱ እማይከፍተው ናኦሚ እና ጁዲት ስለሌሉ ነበር። እነሱ ፈፅሞ በሌሉበት ሰፈር ጧት መንቃት ደብሮት፣ ሱቁንም ከእኔ ሌላ አንድ ሰው እንኳ ካልወደደው መክፈት እንደእሚደብረው ገለጠ።
በመጨረሻው የመንደሩ ጉብኝቷ፣ ጁዲት ቻው ልትል ጊዜ አመቻችታ ሱቁ መጣች። ከሰዓቱን ብቻዋን የወደመ ቦታውን ላለማየት ስለፈለገች ሱቅ ዘግቶ አብረው ሄዱ። ‘ዳግ-ገንቢው’ (ሪቢውልድ) ብሎ ለማለት ያክል ቢነግራትም ‘ያለፈጊዜዬ ላይ በወጥመድ መያዝ ነው’ ብላ ስለአዲስ ህይወት በማለት እንቢ አለች። ከ ዴሞክራሲ ኢን አሜሪካ እሚለው ተከታታይ ፅሑፍ ጥቅስ – በፅሑፏ የተጠቀመችበት – ሰጣት። እምትወደው የተጠቀመችበት ጥቅስ ነበር። በጠቅላላው፣ ‘በ ዲሞክራሲ ሀገርዎች መሀከል፣ አዳዲስ ቤተሰቦች ያለማቋረጥ ይፈጠራሉ፣ እንዲሁ እሚጠፉም ደግሞም አሉ። ብቻ የቀረው እሚለውጥአቸው ነው። የጊዜ ሚዛን ግን የጠፉትንም የተሰበሩትንም እሚከትት ነው!’ ይላል። ጥቅሱን እምቶደው የተጠቀመችው ነበር። ‘አንድ ጊዜ ለጊዜውም ቢሆን አዲስቦታ አጊንቼ ስሠክን መጥተህ ትቀላቀለን ይሆን አለ’ አለችው። ድጋሚ በሚገናኝ የህይወትአቸው ሃሳብ ተስማምተው ጉዳዩን ዘጉት። ተለያዩ።
‘በሁለት ዓለምዎች መሀከል የተያዘ፣ ብቻውን ኖሮ ብቻውን ይሞት አለ!’ ብሎ በአባቱ ትዝ ያለው ተረት ላይ ጨመረ። አባቱ ‘በዛፍ ቅርንጫፍ የተያዘች ወፍ ሁለቱንም ክንፎቿን ትበላለች!’ ብሎት ነበር። አሁን ግን፣ የሁለት ዓለምዎች ህይወት ስላሳለፈ የእሱው ህይወት ከሁለቱም አለመሆኑን አየ። ሱቅ ስላለው እና የእኔ እሚለው ንብረት ስላለው ያም ንብረቱ ፍፁም እሚባል ባይሆንም እንደመንደሩ አንድአንድ ሰዎች ስላልፈረሰበት እና ዛሬም አብሮት ስለቀረ መደሰቱን ግን ለራሱ ገለፀ። ነገርን እንደመረጥንው መመልከት ወይም መተርጎም እንችል አለን በማለት ወደቤቱ ተለይቷት ሲሄድ በቀና መንፈስ ሊያዘግም መረጠ፨
— === —
፪) ክፍል ሁለት፦ የእኔ እንግሊዝኛ ጥቅስዎች በእየምዕራፉ፨

2 replies on “አማርኛ ጭምቅ በ ዲናውመንግስቱ፤ አምላክ እሚሰጥአቸው ዉብ ነገርዎች | Amharic Summary of Dinaw Mengistu’s, The Beautiful Things that Heaven Bears [በ እንግሊዝ “የአብዮቱ ልጅዎች” (Children of the Revolution) ተብሎ የታተመ።”

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s