Categories
መልካም ጥበብዎች Fine Arts

አቡሽ ዘለቀ ታመናል ሙግ (ሙዚቃግጥም) Lyrics

Abush Zeleke “We are Sick” lyrics.

(ፕሮፌሰር አንድ ጥያቄ ነበረኝ
ዌል መጀመሪያ ሂድና በዘርህ ተደራጅተህ ና
እንዴ ፕሮፌሠር?)


ታመናል ታመናል ታመናል በጣሙን
ሃያ ሠላሳ ዓመት ፊደል ቆጥረን አውቀን
የተሻለ ሃሳብ እንዴት ማምጣት አቃተን
ዛሬም የዘር ሀረግ ገመድ የሚጠልፈን
አዎ
ታመናል ታመናል ታመናል በጣሙን (2)

ሁሉም የየራሱን ገንብቶ ካጠረ
ሁሉም የየራሱን ዘር ከመለመለ
ያብሮነቱን ካባ ማን ሊያለብሰን መልሦ
ለሩብ ክፍለዘመን የበረደን መች አንሦ
ከየትኛው ክልል ነው ከየትኛው ከተማ
ከዛኛው ሰፈር ነው ከእዛ ሰፈር መጣ
መቼ ነው እሚለቀን እናስተውል ላንድ አፍታ

ታመናል
እርም እርም እርም
ስንት ሺህ አመት ልኖር
እርም እርም እርም
ከህሊናዬ ርቄ
እርም እርም እርም
በቀል ተንኮል ክፋት
እርም እርም እርም
ለትውልድ አውርሼ
ከጎዳናው ልውደቅ ልለምን አንጥፌ
እርም እርም እርም
ሆዴን ከምሞላው ሰውከሰው አራርቄ
ይራቀን እንራቀው ይህ ክፉ በሽታ
መቼ ነው እሚለቀን እናስተውል ላንዳፍታ

ታመናል ታመናል ታመናል በጣሙን (2)

ታመናል ታመናል ታመናል በጣሙን
ሃያ ሠላሳ ዓመት ፊደል ቆጥረን አውቀን
የተሻለ ሃሳብ እንዴት ማምጣት አቃተን
ዛሬም የዘር ሀረግ ገመድ የሚጠልፈን
አዎ
ታመናል ታመናል ታመናል በጣሙን (2)

ምክንያት እየፈለግን ሰበብ እየፈጠርን
በትንሽ ትልቁ ጦር እየተማዘዝን
አይደለም የሚበጀን አይደለም የሚጠቅመን
በቀን ሦስቴ እንኳ መብላት እያቃተን

የማን ዘር ነው ከእሳት ከመብረቅ የተሰራ
የማን ዘር ነው ከጭድ ከሰበዝ የተሰራ
አንዱን እያሳነስክ አንዱን አታግዝፈው
ሆድ አምላኩ አትሁን ፍቅር ስበክ አንተ ሰው

እርም እርም እርም
የትነው የተማሩት
እርም እርም እርም
እነዚያ የአድዋ ጀግኖች
እርም እርም እርም
ከራሳቸው አልፈው
እርም እርም እርም
ምሳሌ የሆኑት ለዓለም
እርም እርም እርም
ለሰው እንጂ ለፀብ ስለታገሉ አይደለም

ታመናል ታመናል ታመናል በጣሙን (4)

By Binyamhailemeskel

Hey there! If you want to know about me, I just like fun, commonsense wisdom, and human love. Let us live a bright today changing tomorrow into brighter.
Regards,

One reply on “አቡሽ ዘለቀ ታመናል ሙግ (ሙዚቃግጥም) Lyrics”

[…] ተወዳጁ አቡሽ ዘለቀ፤ “ታመናል”የኢትዮጵያ መሀከልሀገር ዋናጅረት (mainstream) ሙዚቃ፣ ላለፉት ሠላሳ አመትዎች አካባቢ፤ እጅግ ግንባርስጋ መገለጫውን ለመመስከር ምንም የሙዚቃ ሂሰኛነትን አይጠይቅም።በጣም በአይነተኛነት እየተሽከረከሩ የበዙት፣ አንደኛ፣ የእየአይነቱ የፆታ-ፍቅር ጉዳዮቹ አሉ። ሁለተኛ፣ የብሄረሰብዎች ባህል እሚሰኙ በ ኢህአዴግ. ፍልስፍና ወደ ዋናጅረት የተጠሩ ሁሉ-ብሄረሰብ ያለውን ከተማ/ገጠሩን፣ ቆነጃጂትዎቹን፣ ቅርስ እና ታሪኩን ወዘተ. አንቆለጳጳሽ ዘፈን አለ። በፍፁም አይነተኛነት እነእዚህ ዳንኪራ-ወዳድ የእየዘርማንዘሩ ዘፈኖች ናቸው። ሦስተኛ፣ ደፈናአዊው ጭፍን ወይም ባህልአዊ-አርበኛ-ዘመም ሙዚቃዎች ስለኢትዮጵያ “በደፈና-ፍቅር” አለንአለን እያሏት ይቀርብ አሉ። አራተኛ፤ ባይሰምጡም እና በደፈናአዊነት ቢመቱም፣ ስለ አንዳንድ ስነውሳኔ (politics) ጉዳይዎች ሞካከሩ እሚባሉ ጥቂት ዘፈንዎች አሉ። በመጨረሻ አምስተኛ፤ በተረፈ እሚሰኝ፤ የተዥጎረጎሩ ጠቅላላአዊ ጭብጥዎች፦ ለምሳሌ አንፋሽአማአዊ (inspirational)፣ የተለያዩ ምክር-መካሪዎች፣ ወዘተ. ትልምዎችን ዳሳሽ የሆኑ አሉ።ሲደመደም፤ አንድ መሀከልሀገር አድምጠኝ ያለ አማርኛ ዘፈን፣ የለየለት ስነውሳኔአዊ እና ማህበረሰብአዊ ጉዳይዎችን አንስቶ ኋላቀር ሀገሯን ሲመራ አይደመጥም። በቀረ አንድ ጠቃሚ ችግር የነቀሱትን “የኛ” ዎችን።አንድ ሙዚቃ ግን፤ ይህንን አስገራሚ ጭው ያለ የዘፈን ፀጥታ ሰብሯል።በ2012 ዓም. አቡሽ ዘለቀ ያስደመጠው፤ ታመናል።ይህ፤ መሠረትአዊ የሀበሻ ዘፈንዎች ጭብጥ መሆን እሚገባው ግን በአሳፋሪነት በእያንዳንዱ የተዘነጋ ዐውድን፣ ለእራሱ ሳይጨነቅ ያቀረበ ትውልድ-አንድ እሚሰኝ ብጤ ነው።የገፀምድር ጭራ ሀገር፤ ስለምሠሶ ችግርዎቿ በግልጥ ቋንቋዎች ዘፍና ለመሀከልሀገር ዋናዋና እምትልአቸው ዜጋዎቿ ፍጆታ እስክታቀርብ ይህ ታሪከኛ እና ፈርማህደር (record) የእሚያሰቦርቀው ዘፈን ነው። እሱም፤ ዓይንን ለመግለጥ እንዲችል ህዝብን ስለአንድ አረንቋው ምግባር እና ንቃት ያስተምረው ዘንድ በቂ መነሻ ነው፨እሚከተለው ሙጉ. (ሙዚቃግጥም lyrics) ነው። […]

Like

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s