Categories
ሥነዉሳኔኛ (About Politics)

የበስመአብ ቢስሚላሂ ስነውሳኔ፡ መንግስት እና ሐይማኖት ተጋቡ፣ ሀገርም ወጥ-ረገጠ

How recent years have receded Ethiopian politics through involvement of religious leaders in government-led public events.

በ ቢንያም ኃይለመስቀል ኪዳኔ፤ ጥር 2013 ዓም፨

ሠላም-ሻጭ ስነውሳኔ (politics)፣ አምባግነናን እሚከውንበት አንዱ መንገድ ነው። ዉስጡ፤ ሠላም ሀሰተኛ የዋጋ ንረት ተሰጥቶት፣ በከፍተኛ ፍቅር ይዘመርለታል። ሠላም እጅግ ዋጋው መሰቀሉ፣ አምባግነናን ያኖረዋል። ስልጣኔን እና ንፅዉሳኔ (democracy) መገንባት ስለማይችል፣ ሠላምን በማስተከለር፣ እየጠበቀው ሊቆይ ይሻል። ያ፤ የ ሠላም-ሻጭ ስነውሳኔ (peace-selling politics) ይሠኛል።
ባለማቋረጥ፤ ከኢህአዴግ. ጀምሮ እስከ ብልፅግና፤ ሠላም-ሻጭ አስተዳደር እና ሠላም-ገዢ ሀገር በስነውሳኔው እሚራወጡ መሆናቸው ቀጥሏል። ይህን በገሀድ ከእሚከውኑበት አንዱ መንገድ ደግሞ፤ ትእይንተህዝብ በማስከወን “ሠላም ዋጋ አለው፤ ሠላም ይሰጠን!” እሚሉ መፈክሮችን እና ጥያቄዎችን ማስመልከት ነው።
ያ፤ ተሠልችቶ ያለ የሀገር ስነውሳኔ ጭለማ አንድ መገለጫው ሆኖ ሳለ፤ በሠሞኑን የተከናወኑት ትእይንተህዝብ ግን ከተፈበረከው የሠላም-ፈላጊነት ትእይንት በተጨማሪ አዲስ ጋጠወጥነትን ተመልክተናል። የሀይማኖት እና ስነውሳኔ ህገመንግስትአዊ ስንጥቃት ህግ ተጥሶ ተገጣጥሟል።
በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ከተማዎች (እንደ እነ ፍቼ እና ሞጆ ጭምር) ትእይንተህዝብ በተከታታይ ቀንዎች ተደርጎ ነበር። በእነእዚህ ትእይንተህዝብ እይቶች ኢላማአቸው፤ ጠሚ.ሩ’ን በእንቅስቃሴዎቹ በመደገፍ ነበር።
አቶ ጌታአቸው ባልቻ፤ የኦሮሚያ ተግባቦት ጽፈትቤት ራስ (Communication Bureaue Head) ለ ኢሳት. ትመ. (የኢትየጵያ ሳተላይት ትእይንተመስኮት) ጥር፣ 26 ቀን 2013 ዓም. በዜና መሀከል ለሲሣይ መኮንን እንዳብራሩት፤ የተለያዩ መካንዎች የተከወነው ትእይንተህዝብ፤ አላማው አብን. (አማራ ብሄርአዊ ንቅናቄ)፤ ባልደራስ (ለእውነተኛ ዲሞንራሲ) እና ኦነግ ሸኔን ጽንፈኛ በማለት ለማውገዝ፤ እንዲሁም ለ ጠሚ. አብይ አህመድ (ሊ.ም./PhD)፣ የ ህዋሃት. አመራሮችን እያሳደዱ መግደል እና ማሰር ዘመቻው፤ እሚሰጡት ድጋፍ እንዳላቸው ለመግለጥ ነበር።
ይህ የመንግስት ህዋሃት. መሪዎች ላይ ሰብ-አደና (manhunt)፣ በአሳፋሪ መንገድ እና የቅርብ ታሪክም ዳግም ዉድቀት በመሆን ተከውኖ ሞላጎደል ሙሉበሙሉ የተቋጨ እና የቀረው እጅግ ኢምንት ሂደት እንደሆነ ቢጠበቅም – ስለእዚህ ግልጥ የሆነ እጅግ ዘግይቶ የተከወነ ትእይንተህዝብ ቢሆንም – ብቻ ስነውሳኔአዊ (political) እንቅስቃሴ ነው። ተቃዋሚ ድርጅት እና አማፂ ቡድኑንም የመቃወሙ ጉዳይ ከመጠን በላይ የዘገየ ነው። በተለይ፤ ተከታዩ (ኦነግ ሸኔ) ለዓመታት ንፁሐን ሲያግት እና ሲገድል በይፋ ሲዘገብ ነበር። በእነዚህ ስፍራዎች ተቃውሞ እና ውግዘት በይፋ ሳይታይ አሁን የመጣ ነው። ቢሆንምግን፤ ያ የዝብ-መቼት ቂልነት የአሁን እቅጭ ጉዳይአችን አይደለም።
ይልቁንም፤ በትእይንተህዝብ ስርጭትዎቹ በደንብ የተመለከትንአቸው የሀይማኖት ተወካይ መደብዎች ነበሩ። በአንድ ተራ (የሐይማኖት መሪዎች ተራ) ከህዝቡ አንድ ክፍል ፈጥረው በነቂስ በመውጣት ሲቃወሙ እና ሲደግፉ ነበር።
አስተያየት ለመገናኛብዙሃንዎች በመስጠት፣ መፈክሮችን በማስተጋባት፣ አብረው በእየመንገዱ ከፊትከፊት ተከማችተው በከተማ ዋናዋና መንገዶች እየዞሩ በመትመም እና ወደ ትእይንተሜዳ (stadium) በመሰሠብ፣ ስነስርአቱን በማገዝ እና በመካፈል፣ በእየእየቱ ንቁ ኑባሬን በመፍጠር ሲውሉ ተመለከትን።
ፍፁም የሐይማኖት አገልግሎት እሚያደርሱባቸውን – በእምነቶች ፍቺ እሚሰጣቸውን እና በምእመን እሚከበሩ – አልባሣትን ለብሰው ይህንን ድርጊት መከወንአቸው፤ የሐይማኖት ተወካይዎች ያስመስልአቸው ነበር።
እምነት እና መንግስት፤ በ ኢፌድሪ. ህገመንግስትም ሆነ አለምአቀፍ ህጎች፤ እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል ህገመንግስት፤ የተነጣጠሉ ግለግዛት ያሏቸው የህይወት ገጽታዎች ናቸው። አንዱ የእዚህ መርኅ መፍቻው ደግሞ፤ ሃይማኖት በመንግስት ጉዳዮች ጣልቃ አይገባም እሚለው ነው።
ዳሩ፤ ይህ ተግባር፣ ሐይማኖትን በስነውሳኔ ጉዳይ ቀንደኛ ቀጥተኛ ተሣታፊ አድራጊ ነው። የተጠቀሱትን ተቋሞች መቃወም፣ ድንገት ከቀጭን አየር ተወልዶ በመንግስት መሪነት ቆይታ የተፈጠረው ብልፅግና ድርጅትንም፣ የመደገፍ እውነታ አለበት። ስነውሳኔ ድርጅትን መደገፍ ደግሞ የለየለት ኢ-ሐይማኖትአዊ እንቅስቃሴ ነው።
ይህን ለምእመን እና ሐይማኖት ክብር አለመስጠት፤ ከሀሳብአዊ ልዩነቶቹ በላይ ተጨማሪ ግጭት እና ክፍፍል አብዢነት፤ ተገቢያልሆነ እና ኢፍትህአዊ አስጠቁሞት (endorsement) ወይም ጫና ማሳደር ወዘተ. ተብሎ እሚታይ ብሔርአዊ እክል ነው።
በመደበኛነት፤ እኒህን መሠል ትእይንተህዝብ ኩነቶች በመንግስት ስነስርአቱ የተጠፈነገ ሠራተኛ፣ ነጋዴ፣ አገልግሎት ሻጭ እና ዜጋው በመገደድ እሚከውነው እንደሆነ እሚገመት እና በእየሠፈሩ እሚወራ ነው። ሁለትቀኖች ቀድሞ፤ ባለማቋረጥ ይጎነተል የነበረ መሪው ታስሮ ምርጫ ቀድሞ እንዳይለቀቅ ሻጥር እየተሰራበት እንደሆነ እሚገልጠው የ ባልደራስ ተቃዋሚ ድርጅት፣ ትእይንተህዝብ የመከወን ሙከራው በፌደራል ህግዘብ (police) አስተዳደር ተከልክሎ እንዲቀር ተደርጎ ነበር። ስለእዚህ፣ የመንግስት የሐይማኖት መሪዎቹን እንዲካተቱ ከህዝቡ ጋር የመጥራቱ ጉዳይ እንዳለ ይገመታል።
መንግስት ያንን ከከወነ እንዲሁ ህገመንግስትአዊ ጥሠት ነው። ሐይማኖት መሪዎቹም ያንን በነፃ ፍቃድ ከከወኑ፤ አቻ ህገመንግስትአዊ ጥሠት ነው።
ከእዚህ ቀደም፤ መንግስት ሠላምን ሲያስሸጥ እንደእዚህ ያለ ነገር አይስተዋልም ነበር። ቢያንስ በእዚህ መጠን። እንደ ኦነግ ሸኔ ወጣ ያሉ ተቃዋሚዎችን ወይም እንደ አብን ያሉትን ተቃዋሚዎች እያስወገዘ “ሠላም አሳጡን፤ ሠላም መንግስት ሆይ ሥጠን!” ተብለው እሚኮነኑ ተቋማት የደካማ ሂደቱ ማብቂያ ነበሩ።
ዛሬ፤ ከእዛም ባሽ ዝቅጠት ተመለከትን። እምነት በመሪ አገልጋዮቿ በኩል በስነውሳኔ እንድትካፈል ተገድዳ አለች ወይም እራሷን እሷው ለእዛ ዝቅታ አድርጋዋለች።
በእዛም አለ በእዚህ፤ የሐይማኖት ለስነውሳኔ ማብቂያ በመንግስት ጫና ውስጥ መቆየቷ እንዳለ፤ የ በስመአብ ወ ቢስሚላሂ ስነውሳኔአችን ገሀድ የተገለበበት አንድ አጋጣሚ ነው። በሁሉም ወገን፤ ማንአለብኝ ብሎ ወጥ-እርግጥግጥ ማድረግ ነው። ታሪክ ባይጨነቅ ወይም ቢኮንንም፤ ያየ እሚገድደው ያስታውሰዋል። ለእሚታዘብ፤ ይህ ታላቅ ነኝ እያለ እሚኮፈስ ህዝብን፣ በተጨባጭ የገለልተኛ ስነውሳኔ ድንበር የማይታወቅበት እጅግ ቅድመ-አብርኆት (pre-enlightenment) ጨለማ ዓለም ዉስጥ እሚያሽቀነጥር አጋጣሚ ነው፨

[በእርግጥ አሁንአሁን፤ ማለት ይቻል አለ ምንም የስነውሳኔ ኩነት ወይ እንቅስቃሴ እሚከተለው ጉልህ ልማድ ቢኖር፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሀይማኖት አባትዎችን ምርቃ ማስቀደም እና ማሳረጊያ ማድረግ ሲሆን፣ ጉዳዩ ምንም ገለልተኛ (secular) ይሁንም አይሁ እምነት ተከታይዎቹን ወክሎ የእምነት መሪዎቹ በዝግጅቱ በዝግጅቱእና መሳተፍ ነው። ይህ ተገቢ አይሆንም። ለመመረቅ እና ለመጸለይ፣ መርሐግብሩን ለመመረቅ፣ በእየእምነቱ ተወካይዎች አሚከወን ስነውሳኔአዊ (political) እንቅስቃሴ ነው። በደፈናው የድርጅት እና ይህን መሰል ተሳትፎ ባይሆንም፣ እምነትዎች በሩቅ በአሉበት ሆነው ለሀገር እና መሪዎች ዘወትር ይጸልይ አሉ። ለአብነት የአክል፤ ከ ዐብይ ፆም መጀመሪያ ሁለት ሳምንትዎች እንኳ ለመንግስት እና ሀገር እሚከወኑ እንጂ ስለ ነብስ ምእመኑ እሚከውነው አይደለም። ብዙ ሌላ ስርአትዎችም እምነትዎች ለሀገር እና መንግስት መቃናት እሚጠመዱበት ነው። ከቅርብ ጊዜዎች ወዲህ ግን፣ በእየ ዝግጅት መድረኩ ከእምነት ድንበር በመዝለል ወጥቶ ከዘፈን እና ሌላም አንድ ሃሳብ የማስኬድ ዝግጅት ቀድሞ በአምላክ ስም ሀይማኖትዎቹን ወክሎ መፀለይ እና መድረኩን መቀላቀል መልመዱ እንግዳም ሆኖ መገኘት እና መካፈሉ፣ ይህ ሁሉ ኋላ ማፈግፈግ ነው። የእሚካሄድ ዝግጅቱን እና ኢላማውን እሚቃወም ዜጋ በእምነት መሪዎቹ የዝግጅቱ እና ሃሳቡ ደጋፊነት (endorsement) ግራ የመጋባት ነገር ይገጥመው አለ። ተፅዕኖም የእማይደግፈውን ሃሳብ እንዲቀበል ይደረግበት አለ፤ ከተነሳው ጉዳይወይም ፍልስፍና ወይም ጥቅም ወይም አመክንዮ ወይም ጥራት ሳይሆን ከእምነት እና እምነት መሪዎቹን ማክበር የተነሳ እማይደግፉትን ለመደገፍ ወይም ለአለመቃወም መገደድ አለ። ይህ ሁሉ፣ በአጭሩ ሲደመደም አስተዳደርአችን ለእምነት ግድየለሽ በመሆን በአገኙት መሳሪያ ሁሉ በህዝብ ተኩሶ ስነልቦናውን ለመቆጣጠር እሚያልሙ መሆንአቸውን፣ የሃሳብ የበላይነት እየጨፈገገ በእምነት መሪዎች በኩል ተፅዕኖ ለመከወን እሚደረገውን ህገወጥ አካ እና የእምነትን ወደ ስነውሳኔ እንቅስቃሴ ተደባልቆ ለመካፈክ የመመለስ ዘመነ-ጨለማ እሚከውን፤ በ ምኑም ስልጡን የአልሆነ አያያዝ ነው። ሀገርአስተዳደር እና እምነት መለየትአቸው መብዛት ሲገባው፣ ሃሳብዎች በሁሉን የማሻሻል አቅምአቸው መሸጥ እና መገዛት የእሚገባአቸው ሲሆን በእምነት ደጅ አልፈው ለሽያጭ መቅረብአቸው፣ይህ ከቅርብ ጥቂት አመትዎች ወዲህ የበዛ ማሽቆልቆል ነው። እምነት ዋጋዋ በገዘፈበት ሀገር፣ አስተዳደር እና እምነት መለያየትአቸው እጅግ አስፈላጊ የዝማኔ ቅድመሁኔታ ነው። እድገትን እና ዝመናን፤ ብሎም ስልጣኔን ከእዛ ውጭ ማቀድ ቀልድ እንደሆነው፣ የእየስብሰባው እና ህዝብአዊ ኩነቱ እምነት ግለሰብእዎችን ማካተቱም ያው ስህተት ነው፨]

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s