Categories
መልካም ጥበብዎች Fine Arts

ደመረ ለገሠ እና አስረበብ ታደገ፤ በላ ልበልሃ ፤ ሙግ. (Lyrics)

አስቂኝ የአማርኛ ሙዚቃ ግጥም (ሙግ.)፨

https://m.youtube.com/watch?lc=UgxTIGCrhdQ5UoFu5V54AaABAg&v=p_a-Am0UEnE

(ኧረ እሳቱ እሳቱ ኧረ ተቃጠልን ኧረ ዑው ድረሱልኝ
ያገር ያለህ ወገን ኧረ ተቃጠልን ተቃጠልን)
(ኩኩሉ)

ጥርግ በልልኝ
ጥርግ በይ አንቺ
ኧረ ሠልችተኽኛል
(ኡፍ ኡፍ)

ኧረ እኔንም ልቀቀኝ ጥርግ በልልኝ በቃኝ
ኧረ ሰልችተኽኛል በቃኝ በቃኝ

(እሃሃሃሃ)
(እሷም ተይ አንተም ተው)
በሉ እናንተ ጥንዶች ይሰማ ድምፃችሁ
እውነተኛ ዳኛ ፈራጅ ካገኛችሁ
(ይዳኟ እንግዲህ)
(እኽኽኽኽኽ)

በያ ልበልሻ በያ
በላ ልበልሃ በላ
(ተባባሉ)
በያ ልበልሻ በያ
በላ ልበልሃ በላ
(2)
(መስማትማ እንሰማለን)

ኧረ ተይ አንቺ ሰው
ልቤ ባንቺ ደማ
መቼም አንስማማ
ከሰማኸኝ ካደመጥከኝ
ልንገርህ በይፋ
ዉስጤ እንደተከፋ
ኧረተይ አንቺ ሰው
ይብቃሽ ምነው
ጨካኝ ነሽ ቂመኛ
ልኑር ሂጅልኛ
ከሰማኸኝ ካደመጥከኝ
(አውሪው)
በዝቷል የበደልከኝ
መቼም ለኔ አልሆንከኝ
(አመት አታወሪ እንሰማለን)

ለስጋሽ አድልተሽ አመቻችተሽ ኖሮ
የኔ ገንዘብ አልቋል ባንቺ ተመዝብሮ
ስጋ ፈራሽ ከንቱ አይደለም ተጠዪ
አበላልጦ ማየት አይወድም ፈጣሪ
አንቺ ወገንተኛ
የለሽም መዳኛ

ዉርስ ቅርሴን የእናቴን ንብረቴን በሙሉ
ሳልሰማ ሳላይህ ታሸሻለህ አሉ
አንተ *** ሆነህ ስታግበሰብስ
እድሜህ ተጋመሰ በልተህ ሳትጨርስ
(ኧረ ተናገረችው)
በቀን በጨለማ
አለሁኝ ስቀማ

ሜዳውም ፈረሱ ሆኖ ያንቺ ብቻ
ትጋልቢኛለሽ ወዳሻሽ አቅጣጫ
(***ው የለም እንዴ)
አንቺ ካልሽው በቀር በኃይል ሁሉም እምቢ
በጉልበትሽ ትተሽ ባእምሮሽ አስቢ
(ሃሃሃሃ)
አይጠቅምም ዘመኑ
ሰልጥኚ እንደቀኑ

በጉልበቱ አዳሪ የእናት ጡት ነካሽ
ከራስ በላይ ንፋስ ብለሃል ጭራሽ
አትሰራ አታሰራ ብቃትህ አናሳ
ቀኑ ያንተ ሆኖ አያለሁ አበሳ
ሠለቸኝ ግዞቴ
በል ዉረድ ከአናቴ
(ባል እና ሚስቶች አይደልአችሁም እንዴ?)

አንቺዬ ሳታሰፊ እንጀራ
ድንቄም እማወራ
አንተዬ ሳተዘምር አዝመራ
ድንቄም አባወራ

ድስቱን በየጓዳው ስታገነፍዪ
ባግባቡ ሳይበስል አሮብሻል እዪ
(ሃሃሃሃ)
ጉልቻ መለወጥ ወጥ አያጥም ንቂ
ባለሙያ ይምጣ ማጀቱን ልቀቂ
አትማሪም ገልቱ
ስራሽ ሁሉ ከንቱ
(ወየሁ ጉዴ ወየሁ ጉዴ)

እርፍ እና ሞፈሩን ሳታዋድደው
(ወይ እርሻ)
ድንግሉን ለም መሬት ፆም አሳደርከው
(አው እንደእዚህ ልክልኩን ንገሪው)
አንተን ካፈቀርኩኝ ረድኤት አጥቶ ኑሮ
ስጋም ሳይቀመስ ጣሪያ ነካ ሽሮ
(ስጋ ***)
አንተዬ ሁሉም ቀረ ድሮ
(ስጋ እማ ድሮ ቀረ)

የእኔ እና አንቺ ችግር ሳያገኝ መቋጫ
ይኸው እስከ ዛሬ አለን በፍጥጫ
ሰው ሁሉ ያማሻል ቆየሽ ባልጋ ብሎ
(እውነት ነው)
ተነሽ ዉረጅ እና መልስ ስጪኝ ቶሎ
ብርሌ ከነቃ
ከቶ አይሆንም እቃ
(ልክልኩን ንገራት)

ምሽት ያቀድክውን የምትሽር ሳይነጋ
አንተን አምኖ መኖር ያስከፍላል ዋጋ
ቻልኩት ያንተን በደል ሆኜ ሆደሰፊ
ጊዜ እና ቅዝምዝም ዝቅ ሲሉ አላፊ
አንተ ቆርጦ ቀጥል
ስራህ ሆኗል ማበል

ከአናቴ
(በይ ዉረጅ)
ከራሴ
(በይ ዉረጅ)
(2)
(እኔ የለሁበትም)

ኧረተይ አንቺ ሰው
ይብቃሽ ምነው
ጨካኝ ነሽ ቂመኛ
ልኑር ሂጅልኛ
ከሰማኸኝ ካደመጥከኝ
በዝቷል የበደልከኝ
መቼም ለኔ አልሆንከኝ

የበዪ ተመልካች አርገሽኝ በቤቴ
ጠግበሽ አንቺ ተርፎሽ ታጥፏል እኔ አንጀቴ
የፍቅርሽ ሚዛኑ ባግባቡም አይለካ
(እውነቱን እኮ ነው)
ጊዜ ወደሠጠው ያጋድላል ለካ
በቃ በቅተሽኛል
ጉዳትሽ አይሏል
(ታዲያስ)

አመልክን በጉያ ጓዝኽን በአህያ
ይቀደድ ፊርማአችን በቃ እንለያያ
ካለፈው ስህተቴ ተማርኩኝ ብለኽኝ
አንተ ከርሞ ጥጃ
(ኧረ እንደእዚህ ልክልኩን ንገሪው)
ዘንድሮም አወከኝ
ከርሞ ጥጃ?)
ዉሽክትክት *
ምን ይሉኝ ***
(አይ አነጋገር፤ ቂቤ ያለ አነጋገር)

የፈጠራ ታሪክ ዉሸት ቀምረሽ
ቤተሰቤን ሁሉ ታዋክቢያለሽ
(እውነቱን እኮ ነው)
ምነው ብታስቢ ሁሌ ቀናቀና
(መበጠር አይቀር)
መሰፈር አይቀርም በሰፈሩት ቁና
(እውነት ነው መሰፈር አይቀርም)
ሰፍተሽ የሀሰት ካባ
መቼም አንግባባ

ምክር አትቀበም ስራህ አሰቃቂ
(ሁለትአችሁም እኮ እውነት ነው)
ከኔ ወዲያ ላሳር የለም አልክ አዋቂ
በቤቴ ነፃነት ክብር ነፍገኽኝ
በግምት በመላ ያስተዳደርከኝ
ሰለቸኝ ግዞቴ
በልዉረድ ካናቴ
(አንቺም እውነትሽን ነው)

አንቺም ብሶተኛ እኔም ብሶተኛ
ከንግዲህ ይፍረደን የላይኛው ዳኛ
(4)

ተይተይኝ አንቺዬ
ቅሪብኝ አንቺዬ
ሂጂልኝ አንቺዬ
ታክቶኛል አንቺዬ

በልተወኝ አንትየው
ቅርብኝ አንተዬ
ሂድልኝ አንተዬ
ልቀቀኝ አንተዬ

(ይዳኟ እንግዲህ
እኔ ምን አውቃለሁ፣ ህም?)

—– & —–

ሙግ. እና ዜማ፡ ደመረ ለገሠ
ፊውቸሪንግ፡ ኮሜዲያን ሚሊዮን አበበ እና አርቲስት ታጠቅ ንጋቱ
ዳይሬክተር እና DOP፡ ናፖሊዮን አለሙ
ኤዲተር፡ አጋር ባለሙ
ማሲንቆ፡ እንድሪስ ሀሰን
ማስተሪንግ፡ ክብረት ዘኪዮስ
ሙዚቃ ቅንብር እና ሚክሲን፡ እዮብ ካሳሁን
ካሜራ፡ በሱፍቃድ ያዘው
ድሮን፡ ሚካኤል ድሪባ እና ዳባ አብዲሳ
2017 እኤአ.

—— & ——

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s