Categories
ስለ ቋንቋ አማርኛ (ወይም ይልቁንም አማሊዝኛ) Amhalish

አማርኛ ፊደልገበታ፡ መሣሣይ ችግር፣ ተመሳሳይ ጩኸት፣ ተመሳሣይ አግበስብሦ ማምለጫ መልስዎች

አማርኛ ፊደልገበታን በማዘመን ጉዳዩ፣ ቅፅአዊ (formal) አልሆን ባለው ውይይት ላይ፣ አንዳንድ ሃሳብዎች፨

ቢንያም ኃይለመስቀል ኪዳኔ፤ ጥር ቀን፣ 2013 ዓ.ም.፨

ቋንቋ አማርኛ ዉስጡ፣ ብዙ ችግሮች እንደተበተቡት ግንባርሥጋ ነው። ከእነዚህ አንዱ፤ የፊደልገበታ ጉዳዩ ነው።
በአንድ የሀልዮት (thought) ዣንጥላ ስር እሚከማቹ ሀሳብዎች፣ ገበታው ይዘምን፦ ቀላል የጽሕፈት እና ንባብ አገልግሎት ለዜጎች እናቅርብ፣ ብሎ ይመከራል። ተቃራኒ ዣንጥላ ስር ደግሞ፣ ፊደልገበታው ባለበት ይቀጥል በእሚል ሃሳብ ተሰብሠበዋል። የቀደሙት የዝማኔ (ለ)ውጥን ሲያራምዱ፤ ሁለተኛዎቹ፣ የ“ስታተስኮ”ውን መከላከያ ይጠብቃሉ። በእርግጠኝነት ንቅ አንድ የኢትዮጵያ ችግር ቢሆንም፤ ይህ ዕድሜ እያግበሠበሰ እዚህ የደረሰ ችግር፤ እስካሁን በሀገር ቤተእንደራሴ (Parliament) እና ባለድርሻዎች ብሔርአዊ ጉዳይ ተብሎ እልባት አልተሠጠውም።
ወደእዚህ አጭር ጽሑፍ መነሻ የሆነው ኩነትአዊ አጋጣሚ እንሻገር። በተለያዩ ዐውድዎች፣ በቅርቡ ይፋ ሳቢስሜትነትአቸውን (public sensation) ያቋቋሙት መጋቢ ሀዲስ ሮዳስ ታደሰ (የጥንት ታሪክ መዛግብት መርማሪ ሊቀምሁርዎች)፣ የአማርኛ ፊደልገበታውን ባለበት መቀጠል አስፈላጊነት በወቅቱ በይፋ ከእሚያቀነቅኑት መሀከል ዐብይ ሆነው ሃሳብአቸውን ደጋግመው ነግረውናል። ለመጨረሻ ጊዜ ያደመጥኩትን፤ በነብስ ወከፍ አንድ-አንድ ምሪንዳ የበዛው ለሥላሳመጠጥ እንዲጎነጩ በተከፋፈለላቸው እና እግሮቻቸው ጎን ባስቀመጡት ታዳሚዎች ፊትለፊት፣ አዲስ ፓርክ ላይ፣ ጳጉሜ ፮ ቀን፤ ፪፼፲፪ ዓም.፤ ካቀረቡት አጭር የ “ሀገርአችን-ትልቅ-ነበረች-እኮ!” ብጤ የህልም-ቅቤ ንግግር ይህን ሲያስተላልፉት ቃልበቃል እንቀንጭብ።


“ፊደልአችን አስትሮኖሚ ነው። ብዙዎች ፊደል ይቀነስ ሲሉ ያስቁኛል። ጥበብ አይቀነስም። ጥበብ ይቀጥላል። ሰው ሂሳብ ካልቻለ ሂሳብ ይማራል እንጂ ሂሳብ ይጥፋ አይልም። ወደታች 26 ወደጎን 7 ነው።
“ምስጢሩ ምንድነው? ሰዎቹ አላስተዋሉትም። 26 ሲባዛ 7፤ 182 ነው። 182 ትልቅ ምስጢር አለው በሳይንስ። በአሙት ሁለት ጊዜ፣ 182 ሲደመር 182፤ 364 ይላል። የሄኖክ ካላንደርን ነው የቀመሩት።
“ይህ ብቻ አይምሰልአችሁ። ልክ በ 182 ቀን አንዴ፣ ‘ኤክዊኖክስ’ ይከሠታል። መስከረም እና መጋቢት ፖሊ-ኢክዊኖክስ (ቨርናል ኤክዊኖክስ ለማለት) እና ኦተምናል ኢክዊኖክስ፦ ፀሐይ እኩል በምስራቅ ወጥታ ምእራብ አቅጣጫ እምትጠልቀው መስከረም ላይ እና መጋቢት ላይ ነው። ከእዛ ዲግሪዋን ዝቅ ዝቅ ዝቅ….እያደረገች ትሄዳለች።
“ስለእዚህ ፀሐይ ከምስራቅ ወጥታ ምእራብ እምትጠልቅበትን ‘ኢክዊኖክስ’ ስለተረዱ ፊደልአችንን 182 አደረጉ። ፊደል ከተቀነሰ ‘ኢክዊኖክስ’ ይበላሻል ማለት ነው። ይህን ቀመር ማወቅ ያስፈልጋል። …”


በአጭርበአጭሩ፤ በእነእዚህ መከራከሪያዎች መሰረት እሚገነቡ የግብረመልስዎች ነጥብዎችን ለውይይት እነሆበእዚህወዲያ (nowhereby on) እንቀስቅስ።

 1. እጅግ መሠረትአዊ ወንፊት ፩
  አንደኛ፤ እንደተመለከትንው፤ አሁን የተነሳው መከላከያ፤ ከተግባቦት (communication) አመክዮ በግንባርሥጋነት የተጣረሰ ነው። ፊደልገበታ የመግባቢያ ቋንቋ አላባ-መሣሪያ (component tool) ብቻ እና ብቻ ነው። ስነፈለክ (astronomy) እና ቋንቋ የትየሌለ እጅግ እርቀትን የተራራቁ ናቸው። ስነፈለክ የክዋክብት ጥናት፤ ቋንቋ የሰዎች ተግባቦት ናቸው። ዘመነ-አብርኆት (enlightenment) የከፈተው ዘመንአዊ ዓለም፤ የሁለቱ አስተምህሮቶች (disciplines) ተገነጣጥለው በገዛነፃነት (self-independence) የተቋቋሙ ናቸው።
  ፊደልገበታአችን ዉስጥ ስነፈለክአዊ መሠረት መረጃ የመገጥገጡ ትንተና ስለእዚህ ጥንት-ቀርነትአችንን አስመልካች ነው። የቱም (ዘመንአዊ) ፊደልገበታ ስነፈለክን ግን የማንፀባረቅ ባርነት የለበትም። ስነፈለክ ከዘመንአዊ ቋንቋ እና ተግባቦት፤ አመክዮአዊነት (reasonableness) እና መርኅ ምንም አይገናኝም። የምድር እና ሰማይ ያክል መለያየት በእነዚህ ሁለት ግለ-ብቁ (self-sufficient) ዘርፈ-ምርምርዎች አሉ። በአጭር ሲደመደም፤ የስነፈለክ የመረጃ ምስጢሬ (code) በገበታፊደል ሊኖር እንደእሚችል ተገምቷል።
  ስለእዚህ፤ ፊደልገበታን ከስነፈለክ ከመቀላቀል፤ መሠረትአዊ ወንፊትን በመጠቀም፤ ጥበብን ከጥበብ ማንገዋለል እንጀምር። እጅግ ቢዘገይም፤ ሰው ይማራል እንጂ የጥንቱን ልጣባ ብቻ አይበል።
  በእዚህ መጨረሻ ከረዱን ጥቂት ጥያቄዎችን እናዥጎድጉድ። እጅግ ቀላል የጋራነሲብ (commonsense) ቢሆኑም፤ እጅግ በቀላሉ ያግዙ ይሆናል።
  መጋቤ ሀዲስ፤ “…ፊደል ከተቀነሰ ‘ኢክዊኖክስ’ ይበላሻል…” ሲሉ፤ ምድር እቅጭ የፀሐይ እኩሌታ ጉብኝቷን እምታስተናግው፤ በፊደልገበታአችን በኩል ነው እንዴ? ፊደልገበታው በኢዛና ዘመነመንግሥት አካባቢ እስኪዳብርስ ድረስ የ ‘ኢክዊኖክስ’ ጥበቡ የት ነበር? በየትኛው ጥበብ ‘ኢክዊኖክስ’ ፊደል እስኪበጅለት ሳይበላሽ ቆየ? ወይስ ‘ኢክዊኖክስ’ ከገበታፊደል ቀድሞ አልተጀመረም ነበር? ‘ኢክዊኖክስ’ በምድር ዲግሪ እየተስተካከለ እንደእሚከሰተው በፊደልገበታ ለመጨመር እና ቋንቋአዊ አገልግሎትን ተጣብቆ ወስፋት ለመሆንስ ለምን አስፈለገው?
 2. እጅግ መሰረትአዊ ወንፊት ፪፤ ወይም በአማራጭ እርእሱ፦ ግእዝ ይለያል ከ አማርኛ ፩
  ሁለተኛ፤ በክርክርቴ (arguement) ንግግሩ አዲስ ያልሆኑ ሁለት ግለ-ተጣርሶዎች (self-contradiction) አሉት እና ለመቀበል አይቻልም። አንደኛ፤ እስካሁን ኢትዮጵያዎች የሰማንው፤ የግእዝ ፊደልገበታን ይሻሻል ያለ ወይም ያለን የለም። ካለም፤ እዚህ ዣንጥላ መሀከል አይካተትም። ይህ ውይይት ቅጥያነቱ፤ በግእዝ ጉዳዮች ሳይሆን አማርኛን በዝማኔ በመደገፍ ትግል ሂደት በተከመረው ቸላ-የተባለ የነጥብ ክምር መሀከል ፊደልገበታውን የተመለከተው ጎራ ላይ ታካዩ እርብራብ ሆኖ ነው። ሁሉም ክርክር እና ውይይት አማርኛ ፊደልገበታን እንደዘመነ ማህበረሰብ ቋንቋ አሻሽሎ ስለማጠንከር ነው።
  ወደጉዳዩ ስንጠልቅ፤ መጋቤ ሀዲስ ስለ አማርኛ እና ግእዝ ፊደልገበታ ሲጋጭባቸው እዚህም ተደግሞ ተስተውሏል። አማርኛ 26በ7 ፊደል የለውም። ከቶ።
  አሁን ያለው 34 ዋናዋና የፊደል ዘር ነው። ወደጎን ደግሞ በብዛት በዲቃላ ቃሎች እንደ ‘ኢክዊኖክሱ’ አለበቂ አመክዮ ስለእሚገጠገጥ፤ ብዙውን ጊዜ፤ ቢያንስቢያንስ 8 ነው። በሰባት ቢወሰድ እንኳ ግን፤ 34በ7 ወደ 182 ከመምጣት፤ 238 ነው። 467 ደግሞ 364 ለአንድ የምድር ዑደተ-ፀሐይ ስለማይቀርብ፤ ሔኖክንም መቀመር ሳንችል ነው ያለንው። የቆጠሩት የ 26በ7 ፊደል ከአማርኛው እጅግ በዢ ፊደልገበታ ተለይቶ አልታይ ማለቱ፤ ምንያክል በዝብ ነጥብ ላይ አለፍትህ እና ዴንታ-አለሽ አካል እንደእምንወያይ አስመልካቹ ነው።
  ሁለተኛውም ግምባርስጋ ነው። ያሠለቸን እና እየጎዳን ያለው አማርኛ ፊደልገበታ እና ‘ኢክዊኖክስ’ ከቶ አንድ አይደሉም። ምንአልባት ግን፤ ይህን ጉዳይ አብዝቶ ተዋዳጅ (fan) ለሆነለት፤ ‘ኢክዊኖክስ’ እና አማርኛ ፊደልገበታን ለማቀራረብ ማራጩ ግን ጭራሽ ይህኛው ዣንጥላን መቀላቀል የተሻለ መፍትሔ ነው። ‘ኢክዊኖክስ’ እና አማርኛ ፊደልገበታ በቁጥር እንዲቀራረቡ፤ 238 የደረሱትን የገበታ ፊደልዎቹን ብቻብቻ (anyways) መቀነስ ነው። ግለተቃርኖትን በማስወገድ፤ 26 ካስፈለገን እና ትርፍ ፊደል 26ን ቢበልጥም አይቀነስም እሚለው እንኳ ግንባርስጋ መጣጣም ያስፈልገዋል። ታዲያ ለምን ለአማርኛ 26 ፊደል ዘር ያለበት ባለ 182 ሆሄዎች አናበጅም? ያ በአያሌው ከእልፍ የአማርኛ ጉዳይዎች አንዱን ይረዳዋል።
  ዳሩ ይሄ ለመጋቤ ሀዲስ እሚሆን አይመስልም። ያ፣ ከሁን ወታች በሦስተኛው ሚሊኒየም ጅማሮው ሰሞን በፊደልገበታ የተቀመረ የስነፈለክ ዉሂብ አሀድ (piece of data)፣ አሁን ዘረሰው ብዙ በዝማኔ ተጉዞ ተራ የስነፈለክ ዘርፉ ወሬ ያደረገው ‘ኢክዊኖክስ’ን በአማርኛ ፊደልገበታም እንዲሁ ጨምረን ተከትለን ለመገልገል እንዳንችል፤ ሞክሼ እና አላስፈላጊ ፊደልዎች መቀነሡን መከላከላቸው አንዱ ነጥብአቸው ነበር። ያንን በሌላ መቼት (space-time)፣ መጋቤ ሀዲስ እንዲሁ ሲከላከሉት፤ ለምሳሌ “ኀ” የ ፋርስ ቋንቋ ፊደል ስለሆነ ከ “ሀ” ተለይቶ በእነእሱ (ፋርስ) ቋንቋ “ክክሃ” ተብሎ ስለእሚነበብ፤ ከአማርኛም ቢሆን ከቶ መጥፋት የለበትም ብለዋል። በስነፈለኩም በቋንቋ-ፋርስ-ዘበኝነቱም፣ ከመተብተባቸው ባሻገር፤ በጉልህ ሀገር ገንቢ ለውጥም አይደግፉም።
  ይህ ግለ-ተጣርሶት እንደ ሆነ ነው። የሰውንም ልጅ አክብሮ፤ በዝማኔ አምኖ ተማምኖ፤ የሰውን ልጅ ወደፊት የማድረስ ልዑል ኢላማንም እሚጣረስ ነው። ያም፤ በጥበብ አለመተማመን ነው። በእየዘርፉ በመንቦጫረቅ፤ ፊደልገበታውን በባሌም በቦሌም፤ እንደ ጥንትአዊ አገኛኘቱ (ኑባሬው) ለማስቀረት እንጂ፤ ቋንቋውን ኢትዮጵያአዊን ለመደገፍ ቀና አመለካከት በእዛ አመለካከት የለም። ወጥ የሆነ አቀራረብ እና ለጉዳዩ ታማኝነት የለም።
  ሲጠቀለል፤ አማርኛ እና ግእዝን በመሰረትአዊ ወንፊት ፪ ነፍተን እናለያይአቸው። ተነፊ እና ተንጓላይ ወንፊቱን እኩል አያልፉም። የተለያዩ ናቸው። ግእዝ እና አማርኛን በ ጥር፣ 2013 ዓም. በአለመለያየት መገንዘብ፤ ትርጉምየለሽ ጥንክንክነት ነው።
  አራተኛ፤ ዛሬ ዘመኑ የዘመነ ቋንቋ ካላገኘ፣ የቋንቋ ክፍተት ለሌላ ዕድገትዎች ጸር እሚሆንበት እድል ከፍተኛ ነው። መረጃ እንኳ ለማግኘት የገበታፊደል አጠቃቀሙ ብሔርአዊ ደረጃ ስለሌለ፤ ከፍተኛ ቀውስ አለ። ታዲያ፤ እራሱን ችሎ የቆመ ስነፈለክ ጥናት ለእዚህ የቋንቋ ዝማኔ እና መቅለል ጥያቄ ሲባል አሁን ቀርቶ ድሮም አልቸገረውም እና ዛሬ እራሱን ቢችልስ? ቀጥሎ መብራራት ያለበት፣ ‘ኤክዊኖክስ’ን ከፊደልገበታ ጥገኝነት መለየቱ እና ተግባቦትን ከስነፈለክ ብዝበዛ-ምርኮኛነት አስጥሎ ራስ ማስቻሉ ምን አደጋ እሚቀሠቅስ ነው – በቀረ ከዝማኔ?
 3. ዋናው መመዘኛ ሚዛን፡ የቋንቋ ፍልስፍና እና መርኅዎች
  መጠቅለያውን በጠንካራ መንገድ ለማንተራስም ጭምር፤ ሌላውን ፍሬጉዳይ እናንሣ። ያ፤ የስነቋንቋ መከራከሪያ ነው። እድሜ ባስቆጠረው እና ምድር በምትገለገለው ዘመንአዊ የጥናት ዓለም፤ የቋንቋ እና ተግባቦት ወለል በዓለትአማ-ፍልስፍናዎች የተገነባ ነው። እነእዚህ ግልጥ መርኆዎች ችግሮችን በመቀነጣጠብ፣ ቋንቋን ከድንጋይ ስእል ደረጃው አቅልለው በማምጣት ሰውን ለንቅ-አኗኗር እሚያግዙት ናቸው። በእዚህ መሰረት፤ በቋንቋ ጥናትዎች፣ የቋንቋም ሆነ ንዑስ ክፍሉ መፃፊያ ስነስርአቱ፣ በመጨረሻ በዓስተኔ-ሰብእ እሚቀጠረው ግን፤ የአንዱን አዕምሮ (መልእክት አመንጭ) ከሌላው አቻ አዕምሮ (መልእክት ተቀባይ) ከሁሉ በተሻለ መንገድ መግባባትን ማመቻቻ መሣሪያ ነው። ሌላ የቋንቋ እና ፊደል ምክንያት እና ጥበብ በዘመንአችን የለም። በእነእዛ መስፈርቶች መሠረት፤ የአንድ ቋንቋ ፊደልገበታ ወደታች 26 ወደጎን 7 መሆኑ፣ ለዘመንአዊ ተግባቦት (communication) አንዳች እንኳ ፋይዳ አለው አልተባለም። በዘመነ የቋንቋ እና ተግባቦት ዳግ-ምርምር (research)፣ ስነምጣኔአዊነት (economical) ግልጠኛነት (clarity) እና ተፅዕኖአማነት (efficiency) ወይም እጥርምጥንነት (bravity)፣ ወዘተ. እንጂ የስነፈለክ አንዲት ቁንጽል ዉሂብን በሩቅ ሂሳብ ለማካተት መሞከር ምን ያደርጋል? ዳግመኛ፤ ያንን መከወን ምንም ያድርግ፤ ዳሩግን፣ የዘመንአዊ መግባቢያ መርኅዎችን ከተጣረሠ፣ ያ የተሟላ ዕብደት ነው። የቋንቋ መርኅ እሚቃረን የአማርኛ ፊደልገበታን አስቀጥሎ መገልገል በእርግጥ ስለነበር እና ስላለ – እስጊዜ እሚቀጥልም ስለእሚመስል – በእርግጥ ይህ ዕብድ ውድቀት አብሮን እንደነበረው አለ፤ ይኖራል።
  ያንን ዕብደት፤ ማከም እሚችለው ትውልድ እስኪታደል እና ሀገር ፍቅር በእውነተኛ (አቅላይ እና ረጂ) ጥበብ መገልገል እስኪችል፤ አንድ ነገር ይገለጥ። እምንጠቀመው እቅጭ ይኅው ፊደል፤ የቋንቋ መርኅዎችን እጅግ እየጠረሠ እና እያወደመ እሚገኝ ነው።
  በደፈናው ለመኮነን ያክል፤ የመርኅ ተቃራኒ እውነታአችንን (reality) እሚከላከለው ዣንጥላ፤ ጥያቄዎችአችንን በቀጥታ እሚመልስ እንዳልሆነ መገንዘባችንን ቀጥለናል። ጉዳዮችን በመልሳቸው ፈቺ አድርጎ ከመመለስ ይልቅ፤ የሚቀርበው መከራከሪያ ሁሉ ቋንቋአዊ ፍሬነገሮችን እሚይዝ አይደለም። ከተቀየረ…. እማይገለጥ የጥርጣሬ መንፈስ ሀሳብ ይገባናል እና ባዶ-ቁጭትን አስመልካች ነው። ጥበበምርምርአዊ (scientific) አመክዮ የለውም። የቋንቋ ጥበብ ነጥብ ካለ ማቅረብ እንጂ፤ ያንን መከላከያ እንጂ ማስተዛዘኛ ማቅረብ አይበጅም።
 4. ግእዝ ይለያል ከ አማርኛ ፪፤ ወይም በአማራጭ እርእሱ፤ አቅጣጫ ለመጠቆም በእሚል ድምበርዘልሎ እገዛን በልግስና ስለመከወን
  በብዙ እውነት፤ አማርኛ ከግእዝ ይለያል። እድሜ (ጥንት እና የቅርብ)፣ የዛሬ አገልግሎት-ሜዳ (በአይነተኛነት ቤተክህነት እና ማህበረሰብ)፣ እና ገና እንዳየንው፣ የ ‘ኢክዊኖክስ’ ዉሂብን በፊደል ገበታው እንደሆነ-እንደሆነው አድርጎ በመደበቅ ከተሸከመ፤ ግእዝን ለእዛ ፍላጎቱ መተው እና የስነፈለክ አንዲት መረጃ ጥምን ማርካት ከተቻለ ያ አንዱ አማራጭ ነው። አማርኛውን ለይቶ፣ በእራሱ ሙሉለሙሉ እንደቆመ ለማስቻል፣ ያለውን ፊደልገበታ ማስተካከል እሚቻልበትን መንገድ በሌላ አግጣጫ ደግሞ መወያየት ይቻላል። ይህ በተለየ፤ የ182 ጉዳይ የተለየ አስፈላጊ የልሂቅአማ ምስጢር (esoterica secret) ወይም አገልግሎት ካለው ደግሞ፤ በአይነተኛነት ለልሂቆቹ (elites) የተተወውን ግዕዙ በእዛ መንታ-ኢላማ መገደብ ይቻላል። ይህም መዉጫ መንገድ፣ ከእዚህኛው ዣንጥላ ወደሌላው እሚላክ ስጦታ ትንታኔ ነው።
  ከዓለም ቂጥ በተሰነቀረ ህዝብ መሀከል ተወልዶ ለዘገየ የሀገር ለውጥ አማርኛ እሚገለገለው ትውልድን፤ ቋንቋአዊ ባሎነ አመክዮ ቀረፈፍ ቋንቋ እና አምታች ተግባቦት መንገድዎች ማስታጠቅ፤ የቋንቋ እና አመለካከት-ክወና አቅሙን አድካሚ ነው። በእየዘርፉ እሚጠበቅበትን ትግል ስለእዚህ ጸረ-ስኬት ሆኖ መውጋት ነው።
  የድብቅ ኢላማ፤ የልዩ-ልሂቃን መገልገያ፤ ወይም አንዳች ማንኛቸውም ማብቂያን የፊደሉ መትረፍረፍ ካገለገለ፤ ግእዝ ላይ ያንን “ጥበብ” ለጥፎ የቅርብ ጊዜ የሆነውን አማርኛን ግን ልክ ይፋ እንደተደረገበት የአፄ ቴዎድሮስ ኢላማ እንደ ሀገር መገንቢያ ብቻ በመውሰድ፣ አሁንም ለእዛ አላማ አጋዥ እንዲሆን ለዝማኔው ብለን ከቋንቋ መርኅ ዉጭ ባለ ምክንያት የታፈነበትን ቤት በግሉ እንዲተነፍስ በሩን መክፈት ተገቢ ነው። ስራ፣ ንግድ፣ ባህል፣ አመለካከት እና ማንነት መቅረጫ እና መከወኛ ቋንቋ በመሆኑ፤ ይህን ከሌላው በመነጠል፤ አማርኛ ከዘመነ፤ በተሻለ የነቃ ነጋዴ፣ “ምርምር”፤ የሀበሻ አመለካከት መገልገያነት፣ ማሰናዳት ይቻላል። በአዲስ ዘመንአዊ እና ምክንያትአዊ አበጃጀት፤ የግዕዝ መቀነት እሚሰኝ የለሽፍች (nonsense) እየጠለፈው መውደቅ የለበትም።
  ከግዕዝ ሺህ እና ሺህ አመትዎች ወዲህ፤ አማርኛ ከተፈጠረ አጭር ስለእዚህ እንጭጭ ዘመን ነው ያለው። ገበታፊደሉም፣ አፄ ቴዎድሮስ ካንድአንዴ ባያስተካክለውም፤ የስነፈለክ ጉዳይን የቀመረበት ግን አልነበረም። ገና አማርኛ ሲፈጠር፤ ያንን የስነፈለክ ነውታ (claim) አፍርሶ ከ26 ዘር በላይ በመሆን የተገነባ ፊደልገበታ ነበር። ገና እዛ ዘመን የተኮላሸ ድብቅ ቀመርን ዛሬ ከታሪክ ባህል ሰምጦ በመጎርጎር መከራከሪያ ማድረግ ትርኪምርኪ መለቃቀም ነው። ያኔም ሆነ ዛሬ፤ የግዕዝ ቋንቋ ‘ኢክዊኖክስ’ን ከቀመረው፤ አዲሱ ቋንቋ አማርኛው ግድ ያን ማድረግ አይችልም። አብረው ያልተፈጠሩ፤ በእየተፈጥሯቸው የተለያዩ፤ ናቸው እና።
  ሞላጎደል፤ የአዋቂዎች (elits) ሆኖ የቀረው ግዕዝ ቋንቋ፣ የስነፈለኩን መረጃ መሸከም ወይም ማሳበቅ ከፈለገ – የተባለውን በቀጥታ እንዳለ ብናምንለት ማለት ነው – ለምን ታዲያ ያ ተገልብጦ ለአማርኛ ይሁንለት። ማብራሪያ ለእዚህ ያሻል። የግዕዝ ፊደልገበታን ያወያየ እስከእማውቀው የለም። አማርኛን ግን በእየትውልዱ እሚነሱ ቢያንስ ቅን፣ እና አመክዮአዊ አሳቦች ያሏቸው ዜጋዎች፣ ትርጉም የለሽ ሆኖ አግኝተውታል። ባለበት ያንን ማስቀጠል፤ ክፉ ብሔርአዊ ስንፍና ነው።
  ሲሲደመደም፤ ‘ኢክዊኖክስ’ን በፊደልገበታ የቀመረ ሌላ የሰማሁት ቋንቋ የለም። ዞሮዞሮ ያንን ከማድረጉ እምናውቀው ለእኛ ብቻ የተለየ ጥቅሙ ምንድነው? የ ‘ኢክዊኖክስ’ን ሩቅ ጉዳይ በራቀ መንገድ በፊደል መዝራት ምኑንም የቋንቋ መርኅ ወይም ትርጉም ረብ ሲሠጥ ግን አንመለከትም። ግዕዝ በግሉ ያንን ኢላማ በጥንት ዘመን ካሰበ ደግሞ፤ ዛሬስ? የዘመንአዊ ስነፈለክ እራሱን ችሎ እሚገኝ ሆኖ ሳለ፤ በፊደልገበታው አሁን በእዚህ ዘመን ስነፈለክአዊ መረጃን መበታተኑ ለምን አስፈለገ? አንድም ለራሱ ማወቅ። አንድም በዘመነ የቋንቋ አገልግሎት አሠሳአችን ላይ እራሱን የቻለ የክዋክብት ጥናትን ዛሬ ካለ ተግባቦትአዊ አመክዮ በፊደል እምንሸከምበትን ቅጣት እና ኋላቀርነት ለማብራራት። ስለእዚህ፣ ለምን፤ በአስገዳጅ መንገድ ዛሬም የአማርኛ ፊደልገበታ ላይ ያ አሁን ገሀድ የወጣ እና ብዙ ከእዛም አልፎ የዘመነ ግልዮሽ (individual) የሙያ ቀመር በእየአታካች ልውውጥአችን እንዲጣባ እሚያስፈልገን ሆነ?
 5. እንግሊዝኛ፤ ወይም፤ የእማይመከር ምክር፤ ወይም የመጥነክነክ ጥግ በስላቅi
  በአማርኛ ቋንቋ እንግሊዝኛ እንደ መልካም ቤተሰብ ነው። ከአማርኛ፤ በመሀከልሀገር ወደ አማሊዝኛ ከተሻገርንም የቆየን ነን።
  አንድ ነገርን አሁንም እናዳብር። አማርኛ ቋንቋን፤ ለአእምሮ በእሚከብድ መንገድ አንድአንድ ጉድለቶቹን ረጭ አድርግን እንፍታለት። የእንግሊዝኛ ፊደልገበታ፤ ተብሎ እንደሚታወቀው ከሆነ አልፋቤትን፤ ለአማርኛ መፃፊያ እና ማንበበከያነት እንጠቀም።
  Yhiem askedmom beteleyayu mengedoch emngelegelew new; biihonm gin bebizu mknyatoch lemqebel kebad new. Daroo, Englizigna kalew bzu liyu-tiqmoch yetenesa and mewucha menged new.
  መስፈርቶች ወጥተውለት ማደግ ከቻለ፤ በአሃዝአዊ አገልግሎቶች ወጥ አገልግሎትን ለማግኘት እሚያስችል ነው። ዳሩ፤ እዚህ ያለውን ማስተካከል እንጂ ሌላ አይገባም። ነገርግን፤ እንደ ኦሮምኛ እና ሲዳምኛ ያሉ ቋንቋዎች ወደ እንግሊዝኛ ለመፃፍ እና ማንበብ እሚሻገሩበት አንዱ አመክዮ ግልጥ ነው። ኢአመክዮአማ ፊደልገበታን ከመማር እና (የወፍ) ድምፅን ሁሉ በፊደል ከመወከል እና በቋንቋው እማያገለግሉ ወይም እሚደረቡ ሆሄዎችን ለዘመኑ ህፃን ማስጠናት፤ ራሮት-አላቅም ጸረ-ሀገርነት ነው።
  ከእዚህ እምንማረው፤ የእንግሊዝኛን ፍቅር አይደለም። በቋንቋአዊ ሚዛን እሚደፋ ነገር ለመሠብሰብ ብንሻ ግን እማይታሰበውን እንግሊዝኛን ለአማርኛ መጠቀምን እንኳ የተሻለ አድርጎ እሚያቀርብልን ገሀድ ላይ መሆናችንን ማስመልከት ነው። ማለትም፤ በሌላ ቋንቋ፤ የአማርኛ ፊደልገበታ የጸና-በሽተኛ ጉዳይ የሀገር ሌላ ቋንቋዎችን አላገዘም፤ ለእራሱ አማርኛም ከባዳ (እንግሊዝኛ) የባሰ ጸር ነው።
 6. መጠቅለያ ፩፦ ፊደልገበታአችን እንደእሚወራለት አይደለም
  ይህ ገበታፊደል እንደእሚወራለት ፍፁም አይደለም። ቁጥር አለው። ግን ለምሳሌ ዜሮ ቁጥር የሌለው እና አሁንም ሀገር ግድ-ይለኛል ባይ መንግስት ህግአዊ ብይን አጥቶ፣ በእየፊናው ሁሉም ምሁር ፍቺ እሚያበጅለት ነው። ለምሳሌ ፬ ቁጥርን ቆብ እና እግር አንስተው O ብጤ ወይም እንደ ሂሳብ “ያልተገለጠ” (undefined) ምልክት ዜሮን በሠረዝ ደርበው እሚያዘጋጁ ገጥመውኝ ነበር። “የቋንቋው ገበታ እድሜጠገብ እና ሀገር-በቀል በመሆኑ አይቅለል-አይዘምን” ለእሚለው ጭፍን መከራከሪያ ይህ ጉድለት መማሪያ መሆን ይችል። ካለ ዜሮ፣ ገበታው እጅግ አቂያቂይ (ridiculous) በሆነ መንገድ ጎደሎ ነው ማለት ነው። ይህ እሚጠቁመን እጅአዙር መረጃ (circumstancial evidence) አለ። ያም፤ ሌላ የመዘመን ጥያቄዎችም ሊኖሩ ይችላሉ ማለት ነው እሚለውን ነው። ነገሮች፣ በገበታውም ሆነ በቋንቋው ፍፁም እና ለውጥ እማይፈልጉ አይደሉም። ያንን በር እንክፈት እና ለአንዱም ዣንጥላ ሳናደላ፤ ብቻ ጎደሎዎችን እየጣፍን በዝሙን መንገዶች ሀገር-በቀል ስልጣኔአችንን እናዘምን፤ ያልኩት ከገብአችሁ።
  ወደአማርኛ ስንመለስም ያንን ጠንክሮ እናያለን። ሳይሻሻል በመዘንጋቱ፤ ድምፅን እንዳገኘው በማይረባው ፊደል እያጨቀ በማጋበስ የመጣ ነው። አፍሪቃ እና አፍሪካ እንደእሚባለው፤ ቀ እና ከ፤ እናሸንፋለን እና እናቸንፋለን እንደእሚባለው፤ ቸ እና ሸ፤ ጭቂት እና ጥቂት እንደእሚባለው ጨ እና ጠ፤ ወዘተ. ፊደልዎችን እንዳዳበልን እና እኒህም የድምፀት-መንትያዎችን መቀነስ እንደእሚቻል እሚናገሩ ምሁሮች አሉ። አብሮ፤ በአማርኛ ከቶ ባያስፈልግም፤ የ“ቨ”ን ዘር ለምሳሌ በቅርብ ዘመን የቀላቀለ ገበታ ነው። ሌላ ቋንቋዎች ግን፤ የሌላ ቋንቋ ድምጽን ለመተየብ ገበታፊደልአቸውን እንዳሻአቸው አይነካኩትም። ይህ ግለተቃርኖት ይሆን አለ። አንዴ አይነካም፤ አንዴ ደግሞ መነካካት አለ። አብሮ፤ እድሜዘመንአችንን ብንደግም እማንጠቀምአቸው እና ቋንቋው እማያውቅአቸው ከቶ በአማርኛ የሌሉ ፊደልዎችን ህፃናት አስጨንቀን እናስጠና አለን። “ፗ” “ቯ” “ዟ” “ዧ” ወዘተ. በአማርኛ ቋንቋ ቃል ተሰምተው አይታወቁም። ቢያንስ በመደበኛነት። መኖርአቸው የወፍም ይሁን የምናምን ድምጽን ሁሉ በፊደል የመግለጥ የፊደል ተቅበዝባዥነት ነው። ቀጣይ እሚፈጠር ፊደል ካለ አናቅም። ገና አይዘምን ቢባልም በማስተካከል ሳይሆን በማበላሸት ግን በመሄድ ያለ ነው።
  በጠቅላላው፤ ገበታው ምን ቢራቀቅ፤ ከክፍተት ነፃ ነው እሚል እንደምታን ለማውለቅ በቂ የጎን ማስረጃዎች አሉ። የጥርጣሬውን ጥቅም (benefit of the doubt)፣ ለገበታው ችግር አለው እሚለው ዣንጥላ መሆን ይገባዋል። ይህን መካድ፤ ጨለምተኛነትን ብቻእናብቻ መከተል ነው። አመክንዮን አለማክበር።
 7. መጠቅለያ ፪፦ ንጽጽርአዊ ጥናት (comparative studies)
  ሞኝ ከራሱ ብልህ ከሌላው ማራል። ሀገረ ሀበሻ መዘመንን አልችልም እሚል ስነልቦናውን ጥሎ፤ እንደ ምድር-ገዢ አዳም በነፃነቱ ተገልግሎ ምድሩን ዘምኖ ሊኖርበት ይቻለዋል። መርምሮ ዉሳኔ በመበየን እና ለእዛ በመታመን መጓዝ፤ ዋናዋናው ደረጃዎች ናቸው።
  በገሀድ እሚጠይቅብን የመዘመን ቅድመሁኔታ እጅግ አንዱ ዝማኔ-አማርኛ ነው። ይልቁንም፤ ይህን ትተን፤ የቻይና ማንዳሪንን ለመጎብኘት እና ምክር ለመጠየቅ እንጓዝ። እስከ 1950ዎቹ አካባቢ እድሜጠገብ ፊደልገበታውን የታቀፈ እንደ እኛው ፊደልገበታ የጃጀ ቋንቋ ነበር። የምስራቋ ሀገር፤ እድገቷ ከተንበለበለ በኋላም ግን፤ እዛ ድረስ ያደረሳት ቋንቋ፣ ዝማኔ በመፈለጉ ቢዘገይም ስለመጪው ጊዜዋ እና ትውልዶቿ ክብር እና ምቾት ቋንቋዋን ማሻሻሏ አልቀረም።
  ዛሬ፤ የቻይና ቋንቋን በበይነመረብ አገልግሎቶች ለመጠቀም፤ በስፋት እሚደረግ ልዩመስተንግዶ አለ። ያም፤ ብሉይ ማንዳሪን ወይስ የቀለለው (simplified) ማንዳሪን እሚል አማራጭ አለ።
  እዚህ የተደረሰው፤ ዕድሜጠገቡ ማንዳሪንን መንግስት በቅርቡ በስፋት አዘምኖ በማደሡ ነው። እራሱን ስላዘመነ፤ ላልተማሩት ዜጎች በቀላሉ የመቁጠር (literacy) አገልግሎትን አልምተውበታል። እና፤ ብዙ ቻይናአዊያን ከአዲሱ የገበታፊደል መቅለል የተነሣ ለምተው ሀገር ማልማቱን አግዘዋል።
  አሁንም ብዙ እማያነብቡ እና እማይፅፉ ዜጎች ባሉባት ኢትዮጵያ ሀገርአችን፤ ተቀራራቢ እርምጃ ለተቀራራቢ ዉጤት አስፈላጊ ነው። ይህ እጅግ ጉልህ ነው። እንደ መሠረተ ትምህርት እንቁ እሚባል ልዕለ-ታሪክአዊ የደርግ ስኬት፤ በአጭሩ እጅግ የቀለለ ፊደልገበታ ማሰናዳቱ፤ የሀገራችንን ትምህርት ዘርፍ እሚያቀና ነው። ይህ በቀጥታ እሚገናኝ አስተዋፅዖ ያለው ነው። ከጥንት-ቀር፤ አመክዮ-ጣሽ፤ ከቶ-ግድየለኝም-ባይ ጎራ ወደ ዝማኔ ረጂነት በማምጣት፤ ያረጀውን ከመከላከል የሚመጣውን ብሩህ በመመሥረት እኛም እንደ ትውልድ ትውልድ ተነታርኮ ብቻ ያሳለፈልንን ችግር ፈታትተን የገዛ-ታሪክ እንፃፍ።
 8. “ነገር በ፫ ይፀናል”፡ መጠቅለያ ፫
  እንቋጭ። በጠቅላላ፤ ቋንቋ አማርኛ ብዙ ጉዳዮቹ በብሔርአዊ እና ሰብአዊመብቶች ጉዳዮች እሚጠቀለል ከባድ መሰረት ነው።
  አማርኛን ማዘመን ካስፈለገ፤ በስነቋንቋ መርኅዎች ብቻ ማጎልበት ያስገድዳል። በህግ፣ ለስራ እና ንግድ እሚውል ቋንቋም በመሆኑ፤ ዝማኔን እና ወጥነትን እንደእዛው በህግ ማስቀመጥ አለብን። ያንን ማድረግ ከሞከርን ደግሞ ከሌላዎች መሀል ወደእዚህ እድሜጠገብ ችግር ይጠራናል። ገና ዘመንአዊ ትምህርት ከተጀመረበት ቀን ጀምሮ እየተንከባለለ አለአስተዳዳሪ፣ ተራማጅ-አለሁባይ እና ሰሚ እዚህ የመጣ እና ባለማቋረጥ ቀጥሎ እየተንከባለለ ያለውን የሀገር አንድ መሰረትአዊ የቋንቋ ጥያቄ፣ የተማረ መፍትሄ መስጠት ግድ ነው። ያ በግልጽ እሚገባ ብሔርአዊ እርምጃ ፈላጊ ጉዳይ ሆኖ ሊታየን እሚገባ አለበት።
  አንዱን ጎራ ከጥናት ጀርባ በህግ አለማስቻላችን፣ እንደትውልድ የሰነፈ ብልሀትየለሽነትአችንን አስጮላቂ ነው። እነእዚህ ጥያቄዎች፤ በብዙ ምሁራን እና አሳቢያን (thinkers) ከ ሼክስፒር ኮረጁ እሚሉ ሂሶች ቢሸከሙም ተወዳጅ የሆኑት እነ ሀዲስ አለምአየሁ ጭምር፤ ሲንከባለሉ እዚህ እንደደረሱ፤ ሲያናቁሩን ከርመዋል። ገና እንከርምም ይሆናል።
  ያረጀው ጥያቄ መሀል አንድ አላቢ ተግባር ጠፍቶ፤ ገና የምናሳድገው እና ጠቢው (ፊውቸር) ትውልድም፤ አንድ ብሔርአዊ ጭቅጭቅ እንደእሚወርስ ተረጋግጧል። ያንን ወርሰን ፍቺ ሳንሠጥ ዳግ-በማውረስ፤ በዉጤቱ ያልነበረ ትውልድ ያክል ሆነን እንቆጠራለን።
  ከእዚህ እንቅስቃሴየለሽነት ወይም በድንነነት ለመላቀቅ፤ እነ መጋቤ ሀዲስ ወይም ቋንቋውን ከእነብዙ ችግርዎቹ እንቀፈው እሚለውን ሀልዮት እሚያሽከረክሩ ምሁራን ሁሉ፤ አንድ ጉዳይን ግን ማስተዋል እንዲጀምሩ፣ ግብዣ በግልፅ ይቅረብ። አማርኛን ለዘመነ ጥበብ ለማሰናዳት ባይቻለን እንኳ፤ ከመከራከሪያነት ለማስጣል፤ ሀሳብአቸውን የህዝብ እንደራሴዎች በህግ እና ደንብ በእሚፈልጉት መስመር አውጀው እንዲጠብቁላቸው መግፋት መጀመር አለባቸው። ከተራ ተከላካይነት፣ ወደ ማጥቃት ይምጡ። በየቱም ዘርፍ ያሉ ብሔርአዊ ንግግርዎችአችንም ተገቢ መቋጫ ማግኘትን እና ላቂ ዳግ-ቅስቀሣን ያግኙ። “ጥበብ አይቀነስም፤ ባለበት ይቀጥላል” እንዳሉት፤ ጥበብ አላማዋ ማዘመን እንደሆነ ከዘነጉት እና ካልዘመነችም ከጥበብነት ወደ ሸክምነት እና በትእግስት-ጥበብ ወይም ቸልታ ብቻ የተነሳ ወደ ተጧሪነት መዞሯን ካላስተዋሉት፤ ቢያንስ፤ ከአረጀ ጥበብ ወሬ ዉጭ በእንቅስቃሴ ግን ፈር እንቅደድ፦ ወደ ትርጉምያለሽ መልህቅ ዝርጋታ፤ ምንም ላይ እንድረስ ምንም ላይ፣ የህግ እና ደንብአዊ አሳሪነትን ስለምንፋለምላቸው ሃሳብዎች ወደተግባር እንዲለወጡልን እንግፋ።
  አሁንም፤ ከገበታው ክፍተቱ አቻ ይህ የዉይይት አካሄድ ክፍተቱን በአንድ ወገን አጥንቶ ቋሚ ብይን አለመስጠቱ፤ ከእሚጠቀሱት ችግሮች እኩል ባይሆንም፤ ትኩረት ፈላጊ የሀገር እንቅስቃሴ እናድርገው፨

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s