Categories
ሥነዉሳኔኛ (About Politics) ስለ ቋንቋ አማርኛ (ወይም ይልቁንም አማሊዝኛ) Amhalish

ትልቅ ነበርን ትልቅ እንሆናለን፡ የህልም ቅቤ

የትክክለኛ ስፍራ መዛባትን ምርመራ በ አጭር መፈክር ዙሪያ፨


ቢንያም ኃይለመስቀል ኪዳኔ፤ ጥር፣ 2013 ዓም፨


ባልተስተካከለ እና ሲጀመርም ዴንታአችን ባልሆነ ስነውሳኔ (ፖለቲካ) ታንቀን፤ ትልቅ እንደእምንሆን ግን ከመስበክ አናርፍም።
እንደ ዜጋዎች ገና በሀገርአችን አንስተናገድም፤ ግን ያንንም አናይም። በሰብአዊ መብት እማንበረታ፣ ለመጭው ትውልድ (ሀገርግንባታ) በቅድሚያመስጠት ደንብ እማንታትር፣ እንደ ፱ ኛው ሺህ ተከታታይ ሲትኮም መግቢያ ዘፈን ስንት እያለን ወደእርስለእርስ እምንመላለስ ነን። ግን ትልቅ እኖናለን ብለን እንዲሁ እምንፎክር ነን።
“የድሮው ትልቅነት” በዘመኑ ነበር። ብዙ የእኛን ዘመን ጉዳይዎች አባርሮ፣ ሳያውቅ፣ ወይም ንቆ የነበረ ዘመን ነው። አፈፃጸም ቢቀር፤ ሰው በሰውነቱ በአዋጅ እና ሀሳብ እንኳ ደረጃ ያልተከበረበት ዘመን ነበር።
እንደለመድንው ያንን መከባበር የተማርንው ከአድማስባሸገር ሄደን ነው። የእያንዳንዷ ኢትዮጵያአዊ ነብስ እኩል ዋጋ እንዲሰጣት ያደረግንው፤ ከዘመነ ዓለም እና ከምንም በላይ ጫና በኋላ፤ በእነ ማህበረ-ሀገራት (ሊግ ኦፍ ኔሽንስ) አቀንቃኝነት ፍሬማግኘት ነው። ሆኖ ዛሬም፤ ዜጋዎች በዘመኑ ዘምኖ የመኖር ዕድል ንፍገት በአለም ጭራ ናቸው። ያም አያገባንም፤ ትልቅ ነን እንሆናለን ለማለት ግን ያገባናል።
እንደ ጎልማሳ እሚቆነጥጥ አብዝቶ ባይኖረንም፤ በምንችለው አቅም መኮሳተር ግን አስፈላጊ ነው። እማይዘረዘሩ፤ የትልቅ-አለመሆን ጉድፍዎች አጨቅይተውናል። እነእሱን መመልከት እና መታተር ግድ የሁሉ መነሻው ነው። ከእነእዛ ጉዳይዎች፤ ጆሮ ዳባ ቀጥሎ ይሄ መፈክር ከእማይገባ ስእል መሀከል ነው። ዋጋ እንኳ ለባለቤቱ በማያሠጠው የእየሙዚቃው ግብዣ እና ዕለትአዊ ወይም አዘቦት ልዉዉጥ እና ተራ ትንቅንቅ መሀከል፤ በኩራት ረክቶ፤ ይህን መፈክር ማሯሯጥ አሸባሪነት አለበት።
ወደእዛ የድሮ የአንድ-ወገን ከፍታ ታሪክ ለመፈክር ከመበርበር፤ ከእዛ የተሻለ ሁለንተናአዊ እና ዘመንአዊ ለውጥን ዕቅድ ማድረግ አለብን። ብሔርአዊ መናኛ እቅዶች፤ አዘቦት ወሬዎች፤ ቢያንስ ወደ መካከለኛ ጥራት ያለው ጠቢብነት (ኢንተለክት) መሻገር አለብአቸው።
“ዘመንአዊ አይደለንም፤ ዘመንአዊ እንሁን” “ኢትዮጵያአችንን ወደፊት፤” “ሀገርአችን ትቅደም፤” “ኢትዮጵያ ትገንባ፤” ወዘተ. አይነት መፈክሮችን ብንተካ እና ብንደጋግም ዘርፈብዙ ጥቅም ከእዛ ይኖረናል። ለእራሳችን ቁጭት፣ ማንቂያደወል፣ አንፋሽአማነት (ኢንስፖይሬሽን)፣ ትጋትአማአዊነት (ኮሚትመንት)፣ በእውነትአዊነት (ሪያሊቲ) ግጭተደ አለመሳቀቅ እና ትክክለኛ መስመር መቅደድ፣ ወዘተ. እናገኛለን።
መታወቅ ያለበት፤ ይህ ዉይይት፤ የተራ ልውውጥ (ኤክስቼንጅ) አጓጉል መዛኝ መሆን አይደለም። ወይም የአዘቦት ተራ ስህተት አየር ሰንጣቂነትም አይደለም። ዕድል እና እውነትን ከመመልከት የመጣ ነው።
የጠንካራ ወል ስነልቦንታ (ኮመን ሳይክ) ጉዳይን በአግባቡ መጠቀም ስለእሚቻል ይህን የመፈክር ሁኔታ እና ዐዉድን መተቸት ተገቢ ነው። እንዲሁም፤ በእየሚዛኑ ከእሚወድቁ ግን ለመፈክሩ ከእማይደክሙ የትልልቅ ሰዎች (አስተዳዳሪዎች) ንግግሮችንም ከመታዘብ ነው።
ከምርአዊ ነጥብ መሀከል በትልቅ አውድ እና በዋጋ ያለው መልእክት ዋጋ እሚያገኝበት መሀል፤ እነእዚህን አይነት ተርታ (ሜዲዮክር) ወሬዎች ማድመጥ የመዠለጥ (“ዠ” ጠብቆ) ያክል ነው።
ከምንም በላይ፤ አጠገብ ያለውን በላጭ እና ቀዳማአዊነት ሻች ጉዳይ አንቅሮ ተፍቶ ትልቅነትን በተምኔት መድረስ አይታሰብም። ያለብን ድህነት እና ኋላቀርነት ምናብቴ (ፋንታሲ) አይደለም። መዉጫውም፤ ምናብቴ አይደለም።
ምናልባት፤ ገሀዱ ትንሽ አድርጎን ሲጨንቀን፣ እንደ መዉጫ ቀዳዳ አድርገንው በእዛው ስለተለመደ ጆሮአችንን እያጠቃ የቀረ ለበጣ ሊሆን ይችላል። በተግባር ያልተደገፉ ምኞቶች እና ቀዳሚዎችን ያላቀዳደሙ ትርክቶች መሀከል ያንን ማውራቱ፣ ከጉድለቶቹ ተጨማሪ ጭንቀት አይሁንብን፨

By Binyamhailemeskel

Hey there! If you want to know about me, I just like fun, commonsense wisdom, and human love. Let us live a bright today changing tomorrow into brighter.
Regards,

One reply on “ትልቅ ነበርን ትልቅ እንሆናለን፡ የህልም ቅቤ”

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s