Categories
Uncategorized

የጡመራገጽ ቅድመገጽ

A preface to the blog.

ሀገረ ኢትዮጵያ ዉስጥ፣ ዘመንአዊ ሥልጣኔ እንዲመሠረት፣ ብዙዎች ደገኛ ትትረትዎች፣ ዕድሜዘመንዎች፣ ነብሥ ጭምር አስረክበዋል። ይህ ከስልጣኔ ፍልሚያ ጎን፤ በሀገር መከላከል፣ አቆያየት እና ወረሣ ወሳኝ ስኬታቸው እሚዘመርላቸውን ጀግኖች እና መልካም ምኞትዎችአቸውንም ይጨምራል። በሁለቱም፣ ታሪክዎች አሉ፨
ዳሩግን፤ የእዚህ ደገኛ ትትረት ደቦው፤ መጠኑ፣ ከምንም በላይ በእርግጠኝነት ተፅዕኖአማአዊነቱ (its effect)፣ ብቻ-አበሳጪ ብቻ ነው። ተቀምጠን ይህን እዚህ ስንቀድ፤ ይህስብጥር ህዝብ ጥንትአዊ ስልጣኔ ከተባረረ ወዲህ፣ የዓለም ጭራ ነው። ፈለኬ (planet) ጁፒተር ላይ ብንስተናገድ ኖሮ፣ ፈለኬዋ ከቦርጯ ወደ ቀለበቷ ታባርረን ነበር። እግዜር ይመስገን። ምድር ከሆዷ ዉጭ ገፍቶ-ማባረሪያ የላትም። ዘን ዊ አር ሴፍ።
የቴዲአፍሮ የአዳም እግር አሻራ፣ ዘመንአዊ ሥልጣኔ ማህፀን ያልተገጠመላት ያክል በእዛ ረገድ ንዑስነት አላባራ ብሎን አለ። ይህን ማህበረሰብ፤ ሁሉም መስደብ የቻለ አለገደብ ሰድቦታል።


“የኢትዮጵያ ህዝብ ቢያጠፋም ባያጠፋም በቀን ሦስት ጥፊ ይገባዋል! ጧት ከቤት ሲወጣ፣ ለምሣው እና ልክ ከመተኛቱ ቀድሞ!” ማን እንዳለ እንጃ። “በኮከቧ ከምንከራከር፣ የባንዲራ እና ብሔርአዊ አርማችን እናት አህያ ትሁነን። “ለሀገሩ ከእምታበረክተው ወሳኝ አሽከርነቷ እውቅና መስጠት በዘለለ፣ እኛንም ትወክለናለች” አሁንም ማን ያን ጨክኖ እንዳለው አላቅም።
“ኢትዮጵያውስጥ የሆነ አንቀሳቃሽ (ማሽን) ነገር ሰሞኑን ገባ ምን ትላለህ በጣም ጨምቀህ አስተያየት ተናገር ሲባል ‘Uh…! You know what! Ethiopia kept surprising the world!’” ያለ የሆነ የአንደኛ-ዓለም-ሀገር-በእኛ አምባሳደር እንደተናገር አላቅም።
“ኢትዮጵያዎች እግሮች እንጂ ጭንቅላት የላቸውም” ያለ እሯጭን አላቅም።“ኢትዮጵያዎች ጠግበው እንጂ ይሄ ሁሉ መበላት እሚችል ተፈጥሮ እማ እያለ ድርቅ-ገባ አይባልም።” ያለውን አላቅም። “Humanity is DE…AD here!!” ሲል “What is being a human?” ሲባል “Read the Bible?! ሰብእአዊነት መሰልጠን ነው። It’s to master!!! Human, he masters everything! This people are masters of only their stupidity!! They do not know the difference between tomorrow and their shit!” ይህን እራሱ ማን እንደ አለው…ዳግመኛ ሰላም የአምባገናኝ-ፖለቲከኛዎች ደንበኛ ለሀገር የእሚሸጥ ሸቀጥ እና ቢሰፍንም እንኳ ለነገ የእማይቆጠብ ነገር (የቅጽበት ፍሰት እውነት ብቻ) ሆኖ ሳለ፣ “እኛን ሰላም አትንሱ ያሻችሁን ውሰዱ…”፣ “ግድየለም ሀገሬ አንድቀን ይነጋ አለ…”፣ “ዋናው ነገር ሰላም…እናያለን ብዙ እናያለን ገና…(እያለ የአለም ስልጣኔ ለውጥ ተመልካች በመሆኑ ተገርሞ እሚዘፍን)”…ዘፈንዎች በዋናጅረት የኪነጥ. ምርት አብዝቶ አምርቶ በመሸመትም ላይ የአለ ጠቢ (posterity) በተተኪ-ሚናው ለማለፍ እየአዘገመ እናገኘው ዘለን… ቀና ብለው ስለተስፋ ወደ አሉት አባትዎቹ ሲመለከቱ፣ ዕድርለእድር ተሯሩጦ ጎልማሳነትን በከርፊ የእከሌ-ቀብር አደን ውሎ እድሜውን ገፊ፣ ቸልተኛ ሀገር-በመፈንባት ተፈጥሮአዊ ግዴታዎች ፈር-ያዥ/ጎህ-ሰርሳሪ ቢሆንም ትውልድ እየመራ-የማይበራ፣ “ሠርግ አብላኝ” ብሎ የእድሜዘመን መብሉን ቋምጦ እሚጠብቅ ትውልድ ሊያልፍ እና ኦናነት ቅርሱ ሊሆን ሲል ይታይ አለ…፤ ደንግጠው ጭራሽ ዝቅ ሲሉ ማንም ምንነቱን አጥርቶ የእማይመለከተው እምቅ-ጠቢ (potential-coming-generation) በመዝረክረክ መጎንቆል ላይ የአለ ነው…”በ2035ዓም. 250ሚ. ዜጋዎች ስንሆን ያኔ እግዜር ይሁነን!” የአለውንም…

በአጭሩ፤ እንደ ንብእሾክ ጠዝጠዝ እያደረገ የወንድ ምጥ ላይ እንደተቀመመው፤ በድሜጥሮስ ኩፋል ቀን ስንቆጥር ብቻ ሦስትሺህ ዘመኖች አልፈን በተመሳሳይ የድባብ ቅንብር እንዳለን አለን። ያ እሚለን፤ እንደ Lucy (2014 GC) ፊልም አንድ ሞኖሎግ፣ “ህይወት ቢሊየንዎች አመቶች ቀድሞ ተሰጥቶን ነበር። እኛስ ምን አድርገንበታል?” ነው። ከድንቅነሽ ዘመን የተንፏቀቅንው ከማጥገብ’ ከቶ የራቀ አዳዳኽ ብቻ ነው፨
ዛሬ፤ በ፳፩ ኛው ክዘ. ህይወት ለብለብ ያለ ሞቅታ እምትቸር ቀለምአማ ተደርጋአለች። የክፍለዘመንዎች የተለያዩ መቼትዎች (spacetime) ጥበብዎች ሁሉ ተቆልለው፣ ተሰባጥረው፣ ተጣብቀው፣ እና መልሶ-ማለካካት (ክሮስ-ቼክ) ከውነው፣ ምትሃት መሠል ዉበት በህይወት እሚገኝ ሆኖ አለ። ሰብአዊነት ለምለም አብቦ አለ። ታሪክ ተገቢ ወራሽ አጊንቶ፤ ለብያለ ጣዕም በእየአቅጣጫው አለ። ላልተቀላቀለው፤ በማዘን እሚያለቅስ ሌላ አለው። ሁሉ ሳለ፣ ገንብቶ አለመጠቀሙ መራር ጥንትቀርነት ሆኖ ሆድ ያባባል እና፨
ምን ዐምደ-ሥልጣኔ ጎደለን። ዣንጥላአማው (overarching) ዉድቀትአችን እሳት ወይ አበባ አልሆንንም። ዛሬም። ብዙ ምሰሦዎች ደግሞ አሳፋሪው የሀገር ምሰሦነትን እንደያዙ ናቸው። አምባግነና፣ ሙስና፣ ኢባህልአዊነት፣ ኢህግየበላይነት፣ የድሀድሀነት (ከድህነት ወለል በታችነት)፣ ያልቆጠረነት (illiteracy)፣ እማይታገሱት (insufferable) ኢሩህአማአዊ (unconscionable) ኢንቅነት (unconsciousness)፣ ኢዴሞክራሲአዊነት፣ ኢሰብእአዊነት፣ ጸረ-ልሂቅአዊነት (anti-technocracy)፣ ወደፊት ባወጣያውጣውአዊነት ወይም ቸልታ ዘ ወደፊትአዊነት (none-futuristic)፣ ኢማህደርአዊነት እና ትውፊትአዊነት፣ ኢወለልአዊነት (unfoundede-ness) ወይም ከ ዜሮ ጀማሪነት፣ ታጋሽነትየለሽነት ወይም ልዩነትን በዘመነ ጥራት መጠን የማስተናገድ ድካም፣ ቡድንአዊ ወገንተኛነት ወይም ጸረ-ዉህድአዊነት፣ ፍቱን ወልአዊ መሠረትአጥነት፣ ድሮቀር ወል ስነልቦንታ (common psych)፣ የሥልጣኔ እና ባህል ግጭትዎች አለማስተናገድ እና ግድየለሽነት፣ ሀገርበቀልነት ጠልነት፣ ዝርክርክ ግድየለሽነት እና አለመቀናጀት፣ የትትረትዎች ግለሰብአዊነት፣ እረሀብ እና ጠኔ ወይም ችጋር ወዘተ. ናቸው። ከብዙዎች መሀከል፨
እነእዚህ የመከራ ቁልሎች ሀበሻ ከሀበሻ ለሀበሻ ያበረከተለት ራስ-ሠር (self-made) ማህበረሰብአዊ ዳሸን-ቆሼው ናቸው። ባለማቋረጥ ቢወድቅም፤ ለማሻሻል እና ለማበልፀግ ማከሙ፣ ታሪክአዊ እና ብሔርአዊ ቤትስራው ነው። ባለማቋረጥ የወደቀበት። ችግሮቹ የራሱ ስለሆነ ያ፣ ግልጥ ነው። ዳሩ፣ ችግሩ እና የመድኃኒት ሀሠሳ መሰናክሉ የተንበሸበሸ ነው።
እናስ? ሉሲዎች መዉጫአችን በር የቱ ነው? በጨለማ ታሪክ (አለመዘመን)፣ በተዝረከረከ ኑባሬ (existence) እንደመታቀፍአችን በቀላል ስነአመክዮ (ሎጂክ) እሚመሥለው ጠቢያችንም (our future) ተጣጣሚ አለመጣፈጥ ነው፨

ከዘጠናዘጠኝ ጨለማዎች፣ አንዱን ብርሀን ይዞ መበርታት ግን የለሽአማራጭ መንገዱ ነው። ተስፋመቁረጡን መተው ግዴታዉዴታ ነው። ጥቂት እምነት ዋናው እርሾ ነው። ጓጊነት አስፈንጣሪው ነው። ሽማግሌ-መርነት ደጀኑ ነው። ስሌትአዊ ትትረት ጎዳናው ነው። ኢምንት ፍቅር እና ጥቂት ኢጎም ቢቻል አጋዥ ናቸው። ገና ከብዙዎች መሀከል፨
ቀጥሎ ደግሞ ትትረትዎችአችንን ወይም አወዳደቅዎችአችንን፤ ብቻ-ያሳለፍንውን አንጠልጥሎ ስለቅብብል ማለፍ ነው። አሳልፎ’ ማለፍ። የምናቆመው ሂደት፤ ዘመንአዊውን ሥልጣኔ በደግ ወለል ሊያበቅልልን ይችል አለ።
በእሚቆጠሩ ዘመኖች ኗሪው አስተኔሰብእ (mankind) እሚቆጠሩ’ ዘመኖች እንዲኖሩት፣ የሥልጣኔ አስነጣቢነትን ማሸነፉ ዐብይ ግዴታው ነው። አንድፊቱን፤ ይህ ሀገርአዊ እስራት መበጠሻው መንገድም ያው እራሡ ነው። ግንባርሥጋ።
ይህ ዐዉደ-ጦማር በመቃኘት መታዘብ ደረጃ ቢገኝም፣ ባለመላቅ እና ጠቅላላአዊነት ቢመታም፤ ዉስጡ እሚችለውን ያክል እንዲታይ አጭር ጠቋሚጣት ይቀስራል። ሌላ የለም። መብሠል፣ ሽማግሌአዊ መሆን፣ እዚህግባነት ላይ መድረስ፣ እና ሙያአዊ መሆን በሂደት መድረስ እሚፈልግአቸው ናቸው።
ሲደመደም፤ ገፀጦማሩ ሌላከሆነው ይልቅ የተዋዳጅ ትትረት ነው። አልፎአልፎ የግል ትግልዎቼ አንድ ኬላዬ ነው። እማሰፍራቸው ነቁጥዎች አለረቂቅ ጭንቀት፣ መጋራት ስለእሚፈልጉ ብቻ፣ በተገደበ አቅም፣ በተለይ እንደመነሻነት እንዲሆኑ፣ እማፈራቸው ናቸው። በአላፊአግዳሚ (bypasser) ተዋዳጅ (fan) ደንብ ጉዞ ህይወትን እና ማህበረሰብአችንን እሚጎበኝ ነው። ባለማፈር’ ለተደረገው የተዋዳጅነት ሞላጎደል ንዑስ ጥረት እነሆ። ብቻ የእምነት እንጣጤ (leap of faith)፤ የበለጠ እሚያስፈልገን፨

እርሥዎ ተወድደው አሉ፨
ከሁሉ መልካሙ ቆይታን ተመኘሁ።

By Binyamhailemeskel

Hey there! If you want to know about me, I just like fun, commonsense wisdom, and human love. Let us live a bright today changing tomorrow into brighter.
Regards,

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s