Categories
ሥነዉሳኔኛ (About Politics)

የህዋሃት. መሪዎች ኢ-አፍጊት ፍፃሜ እና ዋናው ብሔርአዊ የአሳሣቢ ዉርሡ

የህዋሃት መሪዎች ግድያ ዉርሡ አሳሣቢ ፍሬጉዳይዎች አሉት፨


ቢንያም ኃይለመስቀል ኪዳኔ፤ ጥር 08 ቀን 2013 ዓም፨

በቅርቡ የአምላጭዎቹ (ፉጂቲቭስ) አምባገነኑ ተቋም ህዋሃት. መሪዎች ሞት እና ቅፍደዳ በብሔርአዊ ወታደሩ እና ኮንፌደራል መሰል የክልል ተቀራራቢ ልዩ ሀይልዎች ተከውኖ እየቀረበልን ያለ ዜና ነው። በተለይ በጥር መግቢያ፣ እነ ሥዩም መስፍን፣ አባይ ስብሀት፣ እና አስመላሽ ወልደስላሴ ከቤተሰብ አከል የምልጫው ባልደረባ እና ጥቂት ደንገጡር መሰል ቡድንአቸው ጋር አብረው መገደልአቸው ከተሰማ በኋላ፣ ብዙ የአደባባይ እና መደበኛ ዜጋአዊያን (ሲቪሊያን) ዳግ-ምላሽ (ሪአክሽን) ተስተውሏል። አንዱ፤ የ አሌክስ ዴ ዋል፤ ግብረመልስን እንምዘዝ።
ዳግ-ተመራማሪው (ሪሰርቸር)፤ በተለይ በ ኢሳት. ዕዉቅ ዉጭእሚገኙ ዐምድአዊ-ጋዜጠኛዎች የህዋሃት. ተላላኪ ተብሎ በብዛት እሚፈረጅ ነው። በጥር 07 የዕለቱ አበይት ዜናዎች ዝግጅትአቸው የእዚህ ፀሐፊ አስተያየትን ሲተነተኑ የነበረውን ድምፀት ላሥተዋለ ግን አንዳች ነገር ያጨፈግጋል።
በአፍሪቃ ቀንድ የረዥም ጊዜ ዳግ-ተመራማሪው አቶ ሥዩም መስፍን የእርጅና ጡረተኛነት እና የጀርባ ህመም እንደማያስጉዛቸው፤ የአቦይ ስብሀት የቅርብ ጊዜ ልብቀድዶ ህክምና እና መሰል እርጅና፣ አስመላሽ ወልደስላሴ ደግሞ ሙሉ አይነስውርነትን አንሥቶ መገደልአቸውን በእሚገባ ተቸ።
መንግስት ሲዋጉኝ ተገደሉ ብሎ መረጃውን ሰጠን። እሱ ስላለን ማመን የለብንም። እንዴት እንደተገደሉ አናውቅም። ምናልባት በትግራይ ህዝብ ተፅዕኖ ፈጣሪ ስለሆኑ ይሆናል እንጂ ተዋግተው መሞትአቸው አልተረጋገጠም፤ በማለት ለማቅረብ እሚገደድበትን የምሁር መላምት አቀረበ። ታሪክ፣ የሁኔታው ጥናት እና መደበኛደመነብስ (ኮመንሴንስ)፣ ያንን የተማረ-ግምት አስገደደው። ደምሮ፤ ስዩም መስፍን ህዋሃት ሲያሸንፍ የደርግ ብዙ ባለስልጣኖችን ከህግ ዉጭ ከመገደል አድነው ለህግ ፍርድ አትርፈዋል ብሎ አስታወሰ። ታሪክ ዘቅጦ እንደ ደርግ የእነ ምርጡ ስቴትስማን እና የህግሰው (ጁሪስት) ቶማስ ወልድ ወይም አክሊሉ ኃብተወልድ እና ከፍተኛ ሌላ የንጉሡ የተረሸኑ ባለስልጣንዎች አለህግ እንደተገደሉት አቶ ስዩም መስፍንም መገደላቸውን አነፃጽሮ ህዋሃትዎች. የሠጡትን የመዳኘት እድል መነፈጋቸውንም ገለጠ።
ይህን አጭር ፅሑፉን፣ የዘረዘሩበት ዜና፤ ድምፀት ግን በቀደሙ ዕለትአዊ ዝግጅትዎችአቸውም እንደተገለጠው፣ በገለልተኛ ሥሜት ሳይሆን በአድሎ ነው።
ዋናው ግን የሆነውንታውን (ኦብጀክቲቭ) እውነትአዊነት (ሪያሊቲ) እና እና ስነምግባርን ሚዛን አድርጎ ነገርዎቹን ማጤን ነው። ገሀዱ፤ የህዋሃት. አምባገነን ቡድን፣ ለሀገር እና ጠቢው (ፊውቸር) በጂ ያልነበረ ነው። እጅግ ሰቅጣጭ የሀገር ጠላት ነበር። እንደ ተቋም በመዉደቁ ከፍተኛ ድል እና ሀሴት እንጂ ምንም አማራጭ ዐውደ-ድባብ መፈጠር የለበትም።
ነገርግን፤ ግለሰብአዊ ጉዳይዎች ላይ፣ የህግየበላይነት፣ ስነስርአትአዊ ፍትህ፣ ዘመንአዊነት፣ አርቆ አስተዋይነት፣ ሰብእአዊነት፣ እና ሀገርአዊነት መስተዋል (ኦብዘርቭድ) አለብአቸው። ስነምግባር፣ ርህራሄ፣ ሀገርአዊ እና ጠቢአዊነት (ፊውቸርስቲክ) እርምጃ ደግሞ፣ እጅግ አስፈላጊው እና የሰራዊት እና ሀገር ታሪክም ዉርሱ ነው።
አሁንም፤ የገለልተኛ መረጃ ማደርጀት በተከለከለበት እና ዉዥንብር ለመቀነስ እኔ ብቻ ልናገር እሚል አምባገነንአዊ ፈሊጥ ብቸኛ መረጃ አውጭ በተቋም ምስረታ በተገኘበት ወቅት፣ የመንግስት አንደበትን ብቻ ማመንን ማንም ፍትህአዊ ቢያንስ ዴንታሰጭ አመክዮአዊ (ሪዝኔብል) ሰው እሚቀበለው መሆን አይችልም። እንኳን በእዚህ ተራ የእየጢሻው ስር አምላጭዎች (ፉጂቲቭስ) አሠሳ ቀርቶ፣ በተጋጋለም ጦርነት የዉጊያ ጋዜጠኝነት ባለበት፤ አሁን ግን መንግስት መገናኛብዙሃንዎችአችንን አክስሞ አለኦዲተር እና ታማኝ እንደራሴቤትም ለብቻው ፈንጪ እንዳሻው ሆኗል። ቴቴዎድሮስ ሞሲሣ ዛሬ ቢሆን ጋዜጠኛው ልቤን ነካውን መዝፈን እማይችልበት የ ፕረስ ሪሊዝ ስቱዲዮ ወስዶ አንባቢነት እና ፃፊነትን አሥርጿል።
ቢሆንም፣ ተፈጥሮአዊ መርኀ-ሕግጋት (ፕሪንሲፕልስ ኦፍ ናቹራል ሎ) በአምባግነና እና አፈና አይቀለበሱም። እማይገረሠሱ ግለአስረጂ (ሰልፍ ኢቪደንት) ናቸው። ከእነእዚህ ዘላለምአዊ እውነትዎች፣ አንዱ ግልፀኝነት በሌለበት ህግ እና እዉነት-መርህ፤ ለመንግስት (ስቴት) የጥርጣሬውን ሚዛን አለማቅለል ነው። እሚያጠራጥር ካለ ወይም እንደ ገጠመን ጉዳይ ተጠቂ ማስተባበል እማይችል (ለምሳሌ ሟች) ከሆነ፤ ብሎም መረጃ ክፍት ካልተደረገ፤ ለተባለው ነገር መንግስትን የመጠርጠር እና ተጠቂዎች (አሁን በእዚህ ጉዳይ ሟችዎች) ደግሞ የጥርጣሬ ተጠቃሚ የመደረግ መብት እና ድጋፍ አላቸው።
እዉነትን ከእዚህ አካሄድ ዉጭ ማግኘት አይቻልም። ግልፀኝነት (ትራንስፓረንሲ)ን ከእዚህ በቀረ ማፋፋት አይቻልም። ተጠያቂአዊነት (አካውንትኤብሊቲ) መገንባትን ማለም አይቻልም። ሥነውሳኔን (ፖለቲክስ) እና ያልተገደበ አቅሙን ከእዚህ መርኅ ንቁ ትግበራ ዉጭ በሀቅ ሚዛን ስር መቆጣጠር አይቻልም። የታሪክ ንፅህናን አለማጉደፍ እና የቁርሾ እድል እንደ ተጠመደ ፈንጂ መቅበርን ማስቀረት ከእዚህ ዕንቁ አካሄድ ዉጭ መከወን አይቻልም። የህግ መተማመን እና የዘመነ ሀገርአዊነት ስነልቦናን መመሥረት አይቻልም። የማሳደድ እና መልሶ-ማሳደድ ተረኛነትን ማስቀረት እንዲከብድ ተስፋ ማስቀመጥ ነው።
የተከወነው እና እሚከወነው የኋላውስታ (ፕሪሲደንት) ሆኖ እሚቀመጥ ነው። ልክ አሌክስ ዴ ዋል እንደጠቀሱት፣ የደርግ ሰዎች ተይዘው ከግድያ እንዲተርፉ መደረጉ አንድ የተውንው የኋላውስታአችን ነበር። ያ ሚዛን ዛሬ ግን አሸነፈን፤ አታልለንው አፈረስንው።
ዛሬ፤ ለነገው የተተወ አስቀያሚ አዲስ የኋላውስታ አለ። የአምባገነንዎችን ሁኔታ፣ ፍትህ፣ ተጠያቂነት እና እውነት ብቻ ሊመራው ይገባ ነበር። ያንን ለመከወን ሀቅ እና ግዴታ የነበረበት አገልጋይአችን መንግስት እና ሰራዊቱ፣ በኢሙያአማአዊ (ኧንፕሮፌሽናል) እርምጃዎችአቸው፣ በተከታታይ አሳፋሪ ዜናዎችን እንዲያቀርቡልን እየፈቀደላቸው ነው።
ምክንያቱም፣ በታህሣስ ጭምር በመቀሌ ጠቅላይ ኢታማዦርሹም ብርሀኑ ኡጁላ እንደተሳለቁት ያረጀ ዝንጀሮ ገደል አይዘልም፣ በእየጫካው ተደብቀዋል ግን እናገኛቸው እና ቶሎ ወደመደበኛ ቀን እንመለሳለን ሲሉ በሌላ ቀንም ዝንጀሮ እማይደፍረው ገደል እና ዋሻ አገኘንአቸው እያሉ የወታደር አመራርዎች ከአሠሳ ተልኮ ያሰሯቸው እነ ስብሀት ነጋን እና አውንዲሁ አጭር ቡድኑን አይተናል። በእርግጠጸ ጸረ-ኢትዮጵያ ህዋሃት. መሪዎችም ተሸንፈው ከእየከተማው በማምለጥ ጫካለጫካ እና በእየገደሉ እና ገዳማቱ እንዳሉ የተቋቋመ ሀቅ (ኢስታብሊሽድ ፋክት) ነው። ብዙዎች ሊፀልዩ ነው እያሉ እስኪቀልዱ፣ በእየቀላሉ ስፍራ ሲደበቁ ብቻ በሂደቱ የተሰማ ነበር።
ስለእዚህ፣ በምንም ሚዛን የተገደሉትን ዜና በእዚህ ቀዝቃዛ ያልተፋፋመ እና ማለት ይቻላል ጭጭ ያለ አደና ሂደት መስማት የለብንም። በእየሰውየለሹ ዋሻው ጥቁት እየሆኑ በመደበቅ ከተገኙ፣ እና ለመከላከል እንኳ ፍልሚያ ቢከውኑ፣ ምእመት ያለፋቸው የኋላውስታዎች ዘረዘዴዎች (ስትራቴጂስ) አሉን። እቴጌ ጣይቱ የጣሊያንን ወራሪዎች ዉሀክልከላ እንዳንበረከከች፣ ጁሊያን አሳንጄ ከኢኳዶር ኤምባሲ ለቅቆ ከወጣ እሚቀፈደድ እንደነበረ እና ክፍሉ መታሰሪያው ሆኖ መጨረሻ እንደተያዘው፣ እንደ ምንይልክ ካልዕ ወይም የሱዛን ኮሊንስ ካቲነስ ኤቨርዲን በንብ ወይም መሰል ክሂሎትአማነት (ቴክኒክ) ጠላትን ከይዞታ ማስለቀቅ እና መማረክ ሲቻል፣ ይህ ሰራዊት በጨዋነቱ እና ገለልተኛነቱ ቀጥሎ ዋሻዎቻቸውን ከምግብ እና ዉሀ ወይም ግንኙነት በመከልከል እንዲማረኩ እና በህግ ተጠይቀው የላቸውንም ህገወጥ እሚባል ሀብት እና መሰል ጠቃሚ ነገርዎች መቀበል እንዲቻል ይህን ሁሉ እንዲያደርግ እንጠብቅ ነበር።
በትንሽ ቡድን የለየለት የመጨረሻ ሽሽት ላይ ሳሉ፣ በገሀዱ በሽተኛነት፣ ጅጁነት፣ አካለጎደሎነት፣ ቡድንአዊ ቀውስ እና ሽንፈት የተንበረከከን ገድሎ መመለስ ከቶ አስጠርጣሪ ነው። በክፋት እንኳ ባይሆን ቢያንስ በምህረትየለሽ አለመብቃት እና ድክመት። ስለእዚህ፣ ክፍተቱ ሀገር ጥላሸት ልቅለቃ ነው።
በህግ፣ ፍትህ ተቋም፣ ሀቀኛ ስነዉሳኔ፣ ተጠባቂ የህግ ሥነስርዓት (ዲው ፕሮሰስ ኦፍ ሎው)፣ ቅን አስተዳደር፣ የህዝብ ይቅርባይነት እና ጠላትንም በስርአት ይዞ የመኖር አቅም፣ ወዘተ. አለመተማመን፣ ሆኖም በግንባርስጋነት መታየት እሚችል ድክመት እና ጥፋት ነው። ይባስ ብሎ፤ አሌክስ ዴ ዋል እንደተነተነው በከፍተኛ የአምባገነን መንግስቱ ቁልፍ መሪ የግለሰብዎቹ አሁንም የመምራት እና ተፅዕኖ አቅም ፍራቻ የተከሰተ ግድያ ከሆነ የበለጠ ብሔርአዊ ስድብ ነው። ሀገርአችን እነሱን በህይወት ይዛም የማስተናገድ አቅም አላት። ከሌላት፣ እንደእነሱ ያሉ ግለሰብዎችን እምናስተናግድበት መንገድን አጠያያቂ ያድረገዋል። የዝማኔ መጠንአችንን በእየተራ አለዳኝነት መበላላት እና ሁነኛ ጨካኝአዊነት (ባርባሪክ) ልማድአችንን፣ ጸረ-ዘመንአዊነትአችንን እና ዓለምአቀፍ ክብራችንንም ይራገጣል። በጠቅላላው ግን፣ በምሁሩ እንደተተነተነው ተፈርተው የተገደሉ እንደሆነም ለመጠርጠር በቂ የደረጃ-ማስረጃ (ሰርከምስታንሺያል ኢቪደንስ) ሆኖ ይህን ሁሉ የኩነቱ ዐውድን እናገኘዋለን።
ሲደመደም፤ ለአጥፊዎች እና ማንኛውም የተለየ ክፍለ ማህበረሰብ እምናቀርበው መስተንግዶ፤ ዶይስቶይቨስኪ እንዳለው፤ የማህበረሰብ እድገት እውነተኛ መለኪያችን እና የማንነትአችን መገለጫው ነው።
ጥቂት መራመድ በቀር የማያውቁት የሰባ አንድ አመት አምላጭ አዛውንት የእነ ታጋይ፣ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር እና አምባሳደር፣ አቶ ስዩም መስፍን እና መሰል አካልአዊ ድክመት እና በድብቁ ስፍራአቸው የመከላከያ ፍፁም ዉስንነት ያለብአቸው አብሮ ሟችዎችአቸው “በሀገር-መከላከያ” መገደል፤ ለሠራዊቱም፣ ለሀገርአችንም፣ ለስነዉሳኔውም፣ ለዓለምአቀፍ ምስሉም፣ ለገለልተኛ ተቋምዎችም፣ ለአንዳች ስንኳ ቅድመሁኔታ የለሹ ሰብአዊመብት አክባሪነት ፍላጎት እና ግዴታአችንም፣ ለታሪክአችንም፣ ለአለው አመራርም፣ በጠቅላላው ለማንም እማይበጅ ብልህነት የጎደለው እንደ ሀገር እጅግ ወደኋላ የተራመድንው ጉዞ ነው። ማንኛውንም የስነውሳኔ ከሀዲ፣ ሀገር በፍትህ ተቋምዎቿ በህግ እና ስርዓት ልትጎበኘው ይገባት አለ። ትውልድ እና ሀገር እንዳይሆን አድርገው በአምባገነንነት ይቅር እማይባል ጥፋት የከወኑትም ዜጋዎች፣ ከቶ ኋላቀር ባልሆነ ስነስርአትአዊ ጎዳና መስተናገድ ነበረብአቸው። ለወሬ አላማም ያ ምፀት መመፃደቅ እና ማደግን እንዲሁም ብሔርአዊ ኩራትን እሚያመነጭልን ይሆን ነበር።
የመበዝበዝ እና ቃል እማይገልጠው የደረሰብን በደልአችን፣ በጋዜጠኛዎችአችንም ሲከወን የነበረው ግድያ፣ እስራት እና እማይገለጠው ማሳደድ እና ንቁ ጸርነት፤ ወይም ማንኛውም ስቃይአችን ምላሹ የተማረ እና ወደፊትን ያስተዋለ ሙያአዊ ጋዜጠኛነት መሆን ይገባዋል። እንደእነ ሙአመር ጋዳፊ በደቦ ፍትህ (ሞብ ጀስቲስ) የተያዙ ምናልባት ሊድኑ ይከብድ ይሆናል። የአሜሪካን ታሪክ አንድ ጥበብ እና ዝማኔ ምስጢሩ የሸሪፍ ሥልጣን አመጣጥም ይህ ነው። ማንንም አጥፊ ከደቦ ፍርድ ማስጣል እና ወደ ህግ ማቅረብ። እዛም በመረጃ እና ተመጣጣኝ፣ አስተማሪ፣ የተመረመረ፣ ተጠያቂ አሠራር የእጅን ማግኘት። ይህ የአሜሪካም ሆነ በእሳቤ ደረጃ እሚገኝ የሪፐብሊካኒዝም ሀሁ ነው። ይህ የሀገር ዝማኔ፣ ንፅስነውሳኔ (ዴሞክራሲ) እና ተስፋ ተርጓሚ (ዲፋይኒንግ) ምልክት ነው።
እነዚህን ሟችዎች ህዝብ በንቃት (አክቲቭሊ) አላሳደደም። በስልጣንም በአምባገነንነት ሳሉ እንኳ ተጨቁኖ በመኖር መሰንበት በእሚለው ማህበረሰብአዊ መገለጫአችን አንገት በመድፋት የተዋቸው ነው። ከሀገር ለማምለጥም ሆነ ለመሰወር ሲፈልጉም የሸሹት ከህዝብ አይደለም። ከመከላከያ አደና ብቻ ነው።
ታዲያ ትተው ሲሮጡ ቀርቶ ሲበዘብዙት እና ተስፋውን ሲያጨልሙበትም ግድ ያላለው ህዝብ አሳድዶ ወይም ባጋጣሚ አጊንቶ የደቦ ፍርዱን ካልሠጣቸው፤ ምትክአቸው መከላከያ ሰራዊት ሙያአዊ ስራውን እንደእሚከውን ይጠበቃል። ዞሮዞሮ ግን እንደ ጥንትቀር የወሮበላ መንጋ ሰራዊቱ የደቦ ፍርድን ማሳየቱ እጅግ ብሔርአዊ ዝቅጠት ነው።
ተጠባቂው ነገር ገለልተኛው ሰራዊት በተጠያቂነት፣ ሰንደቅ አገልጋይነት፣ እና ገለልተኛነት ሀገር ከሀዲዎቹን ከሁሉ በአናሹ እርምጃ ማሰቃየት እጅዎች አስሮ ለዘመነ የሀገር ስርአት አጋዥ ሆኖ ማቅረብ አለበት። ባዷቸውን በዋሻ የተጠለሉ ያረጁትን ባይተዋር ሽማግሌዎች ቢከፋቢከፋ እግር መትቶ እሚይዝ አልሞ ተኳሽ ከጠፋ ብዙ መጠርጠር በእርግጥ ግድ ይላል።
እነሆ ያ የዝማኔ እና ሰብእአዊነት እድል አመለጠ። የከሸፈ ታሪክ የቀደመውን ዘመንዎች ተመሳሥሎ እየቀጠለ ተፃፈ። ቤተእንደራሴው በማብራሪያ እና ማጣራት አይጠመድ ይሆናል። ሰብአዊ መብት ተቋምዎችአችንም ሆኑ ጠቅላይ አቃቤ ህግአችን፣ ይጣራልን እኛም ነገሩን እንደስራአችን ዋጋ ሰጥተን እንመርምር ላይሉ ይችላል። ጋዜጠኛዎችም ሆኑ መገናኛብዙሃዎችአችንም በብሉይ ደምመላሽ (ብለድ ፊው) ስሌት የወደቀ አምባገነን አሁን ደግሞ አፈርገባ በማለት የወደቀ ጥንት-ቀር ቡረቃ ተያይዘው ይሆናል። ለቀሩ ጥቂት የህዋሃት. ጨካኝ ከሀዲ እና ፍፁም ተጠዪ አምባገነንዎች፣ ከግልጥነት የተደበቁት ሰብእ-አደናዎች (ማን ኻንት) እንዲሁ ጭፍን ዘግናኝ እርምጃዎች ያቀርቡልን ይሆናል። የተደበቁ ጥቂት አይጦችን ሀገርአቀፍአዊው አንበሳ ስብስብ መማረክ አቅቶኝ መግደል ብቻ ተቻለኝ ይል ይሆናል። እና ድኃረ-ሀፍረቱ እና ጠቋራ ታሪክአችን ቤተኛነቱ አዝጎን እሱም የዛገ ይሆናል።
ከተራ ዜና በኋላ ግን ታሪክ እና ተራ ያልሆነ አዲስ ዜና ተፈጥሯል። ሙዐዘጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በ ኢሳት. ትመ. አንደምታ ዝግጅት ሁለት ቀን ቀደም ብለው እንዳስጠነቀቁት የወደቀ ሲወድቅ እንዴት ወደቀ ከማለት እና መመራመር፤ እንደ እሚንተከተክ ሽሮ መንጫጫት ይቀናን ይሆናል። እንደ መካሪው ሀገር አባት መጠበብ’ የእዛ አለመዘመን አቻው ዑደትም በትዉልድ ይደገም እና ማፈርአችንም ይቀጥል ይሆናል። የይቅርታ እና የፈለገቢሆን አንድ ነን እንሠብሰብ የጠሚ. አብይ አህመድም ስሜታይት (ቪሴሪያል) የጉንጭ-ስብከት ተራ እየተደረገ በግለ-ጥሰት (ሰልፍ-ቫዮሌሽን) ምግባር እንዲሁ ይፎርረሽ ይሆናል። በምትኩ ፈሪ እና ስልጣን-ሙጥኝ ባይ እርምጃዎችም የወቅቱ ተተንባይነት መስመሩን ይቀጥሉበት ይሆናል። ተስፋአችን እንደህዝቡ ተስፋአጥነት በመንግስትም በኩል የወደቀ ይሆናል። ህዝብአዊ አደራ ይበላል። ተርታ (ሜዲዮክር) ህዝብ እና አደባባይአችን፣ ጫፍን ተመልክቶ በኢሙያአማ (አንፕሮፌሽናል) እና ክፉ-ተፅዕኖ-ወላጅ ግድያዎቹ ላይ ትንሽ ዴንታ ወልዶ በይመለከተኛል ይፈነጥዝ ይሆናል። ይልቁንም ወይም፤ ምንአገባኝታው እና ዜግነትአዊ ዕዉርነቱ በቆዪነቱ ይረዝም ይሆናል።
በአሌክስ ዴ ዋል እንደተባለው፤ ለእነእዚህ አምባገነንዎች ሞት ኢትዮጵያ ግን ባንዲራዋን ዝቅ አድርጋ ሀገርአዊ ሀዘን ቀን ማወጅ የለባትም። የበለጠ ሀዘን አለ። ቋሚ ለቅሦ። ያም፣ የበለጠ ባንዲራአችን አስቀድሞም (ኦልሬዲ) ዝቅ አድርጓል። እሚተልቅ ሀገርአዊ ኋላ-ማፈግፈግ እና ቁም-ማንቀላፋት አሳዝኖናል። ላመለጡን እድልዎች፣ ላየንው ተርታ የሰራዊት አገልግሎት፣ ኢሀቀኝነትአዊ (ኖ-ኢንተግሪቲ) ሥነዉሳኔ፣ እና እንደሌለን ላሳየንው ኦና ተስፋ ወይም ማህበረሰብአዊት ንቁተሳትፎ፣ ባንዲራችንን እስከጫፉ አንስቀል። ዝቅ ብሎ ይውለብለብ። ምንአልባት፤ በህግ እና ዝማኔ ለማመን እስክንዘምን በቋሚነት፨

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s