Categories
ሥነዉሳኔኛ (About Politics) ስለ ቋንቋ አማርኛ (ወይም ይልቁንም አማሊዝኛ) Amhalish

የፈረንጆች እንትን… ባህል፣ አዲስ ዓመት ወይም…በቃ ቅብጥርሴ፦ ተርታ-መደዴ አማርኛ አንደበት

“ፈረንጅ” እሚለውን ገላጭ-ቃል በመወያየት እያከከ፣ የአማርኛን እድፍገላ ማየት እሚጥር ቁንጽል አሀድ፨


ቋንቋ አማርኛ አልዘምን ያለ ነው። የሰው ዘመንአዊ አኗኗሩ ከመዘነው፣ አሰልቺ ብዙ ችግሮቹ ይደፋሉ። ምናቸውንም እዚህ አናነሣሳም። ከአንዱ እጅግ መደዴ-ጥንጥ መደበኛአፍ (ኮመን ፓርላንስ) ነቁጥ በቀር። ሲያልቅ ግን ይተልቅልናል፤ ምክንያቱም፣ ከበዛ አሠቃቂ አጠቃቀሞቹ ቀጥሎ፣ ይህ ትነሽ ችግር እሚያስመለክተው ዋጋው በዛ ያለ የሆነ አማርኛአዊ ጉዳዮችን ነው። የቃሉ ብቻም ዉዳቂ ሁናቴን፣ “አንድ ተራ ነው” ብለው ቢንቁት የእሚንቅ፣ ያን ጋን-አቋሚ-ዕውቅ-ጠጠር አይነት ችግር ነው።
“ፈረንጅ”። ይህ ፈረንሳይአዊ (ፍሬንች) እንደነበር እሚነገር የፋርስ (ፐርሻ)ም ነው እሚባል ሴሜቲክ ቃል፣ አማርኛን ከረገጠ ጀምሮ ነጭ ቆዳ ሰውን መወከል አልቦዘነም። ለሀበሻዎች ጣፋጭ ቃል ነው። አለጥርጥር በቋሚነት።

ግን፤ የአጠቃቀም ስህተቶቹስ? ልክ እዛጋ፤ ጭብጣችንን ያዝን።


በመደበኛነት ቃሉ ኢመደበኛ ነው። ከቶ ቅፅአዊ (ፎርማል) ተግባቦት አይፈልገውም። የመደበኛው ተርታእናመደዴ (ሜዲዮክር) አፍ ድንበሩ ነው። ያ ማለት ቅፅአዊ አማርኛ አካባቢ ድርሽ ማለት የለበትም። ግን በእየስፍራው እየቦረቦረ ሲመጣ በእየቀኑ እናየዋለን። ብርቱ ጋሻ የያዘ ህገወጥ ዘላን።
ለምሳሌ፣ በ ፋና ትመ. (ትእይንተመስኮት) ታህሳሥ 23 ቀን፣ ምሳሠዓቱ ዜና “የፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ካለአደባባይ ተሳትፎ ተከበረ” በእሚለው መሪዜና (ሊድ) ረዥሙን ግልጥ ተከታይ ሀተታ ዘረገፈ። ፈረንጅ እሚለው ቃሉ፣ ባለነጭ-ቆዳሰው-ሁሉ ፍቺአችንን እንደያዘ ተቀጠረ። የነጭ ሰው በዓል ሳይሆን የግሪጎሪያን ካሌንደር ተገልጋዮች እና ሞላጎደል ዓለምአቀፍ በዓልነቱን ተሳተ። መሬትን ወርዉሮ መሣት። ነጭ ሁሉ እና ነጭ ብቻ ያከበረው በዓል ሳይሆን በድሀ አማርኛ ግን ተገዶ መሰለ።
ፈረንጅ ለቅፅአዊ አማርኛ አሽከርነት እማይመከረው አንድም በእዛ አመክዮ ነው። ዘመንአዊ ማህበረሰብ፣ በ21ኛው ክዘ. ከምስራቅ እስከምእራብ ካሉ አስተኔ-ሰብእ (ማንካይንድ) ስብጥር የቆመ እንጂ። (በኋላ ያነሳንው ወግ ላይ፣ ኦፕራ ዊንፍሬይ ከነጭ አራት ጠባቂዎቿ ጋር ሀበሻን ልትጎበኝ መጥታ-ስትቆይ፣ ቅጥር-ደገጡሮቿ የበለጠ መስተንግዶ እና እንክብካቤ ማግኘታቸውን በቅያሜ እና ሀፍረት ማሳወቋን፣ “እንኳን! አሹ! ያ እንዳልሽው ሀበሻን አላሳፈረውም! አያሳፍረውምም! እሚል መንፈሳችንን እንደያዝን እሚያሳይ ይመስላል።)
ፈረንጅ አንዱ ተራ ምሳሌ ነው። በእየቦታው አማርኛ፣ ፈረንጅ ን አለቅጥ ሲያገለግል ሰምተንዋል። የጠነከረ፣ መደበኛ፣ ብሉይ፣ ወዘተ. ቃልዎችን መገልገል የቅፅአዊ ተግባቦት (ፎርማል ኮሚኒሜሽን) ደንቡ ነው። ይህ ኢመደበኛ ቃል እኒያን አያሟላም። ካልቆጠሩ (ኢሊትሬት) ከህፃናት ወይም መኪና ያላዩ ሀገረሰቤዎች አንደበት ማለፍ የለበትም። የስደተኛው ማስታወሻ ላይ እንዳለው፣ በስማቸው ይበላል እንጂ እነሱ ሉልአዊነት ወይም ስነምድርን እንኳ አያቁም፤ ገና አላጠኑም። ወደበመደበኛ ተግባቦተት መዝለል አይገባውም። ለቅፅአዊ ልዉዉጥ (ኤክስቼንጅ)፣ ፈረንጅ ን ደጀ-ትምህርት በረገጠ ወይም ጎልማሳ አፍ ደንብ መተካት ግድ-ተመካሪው ነው። በምንዝር (ስፔሲፊኬሽን) ፍቺውን እሚተኩ ቃልዎች ልናበጅለት ይገባል። አመለካከትን ከተደፈነ ወይም ጠቅላላ ሀቅ (ፋክት) አሳሣል ለማብለጥ፣ እንዲያ ነቃያለ-ቋንቋ መገልገል አንዱ ዋልታው ነው።
ኢተገቢ አቀጣጠሩ፣ ጉዳዩን አሳሣቢ እሚያደርገው ጭፍግግ እንደምታዎች (ኢምፕሊኬሽንስ) ስለእሚጠቁም ነው። በአንድነት የበለፀገች ሉል ወቅት፣ የሰማይቤት ያክል ነጭሰውን በልዩነት አርቀን መመልከታችንን ሊያሳይ እሚችል ነው። ቃሉ ወደእዚች ሀገር እግሩሲረግጥ ነጭንበጠቅላላ በልኮት (ሪፈረንስ) እንዳገለገለ፣ ዛሬ ስንት ስነምድር (ጂዮግራፊ) ተምረንም ከአለሙ እንደተዘጋን እና ነጣያለ መልክ ያለውን ስናይ እሱን አረዳዳችን ግርታ እንዳለበት አስረጂ መረጃው ነው። በእርግጥ፤ የ ሙዐዘጥበብ ዳንኤል ክብረት (ዲ/ን)፣ እኛ እና የመጨረሻዎቹ፤ ደግ ትናንሽ ወጎቹ፤ “ፈረንጅ ነውኮ!”-በደንብ-አክብሩት-ከራሳቹህ-ዕድል-በመቀነስ-ወግን ያወጋን ከእዚህ አመለካከት እሚያያይዘን ያየው አንድ ክርም ያክልየቀጠነ የሆነ መንገድ ቢኖረው ነው።
በእዚህ የአንድ ተወዳጅ ቃል ላይ ብቻ ሀሣቦች በአንቀፆች ደርድሮ ሐተታ ማዳበር ደባሪ ይመስላል። ምክንያቱም ችግሩ የህፃን ጨዋታ ይመስላል። ቢሆንም ሽምቅ ተዋጊ ደፈጣውን በእየአዋቂ ስፍራው ስናገኘው፣ እኩል መጠን ያለው ቂልነት ይገጥመናል።
ከእዚህ አንድ ቃል ብዙ ሀሳብ ተያይዞ ደግሞ ሠፊ ተመዥራጭ ነጥብ ማፅደቅ ይቻላል። ይህም፣ አንደኛ፣ ቅፅአዊ አማርኛን መፈለግ፣ ማልማት እና ማልመድ ተዘንግቷል። ያ፣ ይወሰዱታው (ቴክአዌይ) ነው። ከጠጠር አከል ህፀጽ፣ ቁልል ችግር መገንዘብ። ይጠቅማል።
የይፋ ወይም ቅፅአዊ አማርኛ ህላዌን፣ በይፋ የእንቅስቃሴ ተግባሬቶች (ፕሮጀክትስ) እንድንጠቀመው መች መንግስት ሲንቀሣቀስ ሰምንተናል፤ ለነገሩ? መደበኛ (ኮመን) ተግባቦትዎችን ከቅፅአዊ ለሁለት ሰንጥሮ በልዩነት እሚያስተምረን የአማርኛ ትምህርት ፍሬነገር (ሰብስታንስ) ረብአለሽነት አልገጠመንም። ከመማር የዘለለ አጠቃቀሙ ይቅር፤ ሲጀመር የተማርንው ለህይወት አገልግሎት ስንቀጠር በአኗኗራችን በየቱም ሙያ እምብዛም የማንታይ ህዝብ ነን። በአማርኛ ትምህርት፤ እንደ ሸመታ-ሀልዮት እንኳ፤ የቆየንው መናኛውን አስተምህሮት ስናጋብስ ነው። ምናልባት፤ ፈረንጅ ን ተወት አድርጎ በእዚህ ኮስታራ ሀሳብ ነጥቡን መከርቸሙ የምርአዊነት ስሜቱን አጋብቶ የእሚጠቀልልን ነው።
ይህን ካልን፤ አንድ ማከል ደግሞ አያበሳጭም። ተመሳሳይ የአማርኛን ቋንቋ አንድ ጠቃሚ ችግር ልናነሳበት እንችልአለን። በቂ ለውጥ ሊገዛልን ቻይ ነው። በኢመደበኛ ተግባቦት አልበገር ብሎ የቆየን እና የምርአዊ አማርኛን እሚያጠቃብንን አንድ ቃል ጀርባውን እንዲህ ማጉላት ከተያያዝን፤ ከትንሽ ትልቅ መማር፤ እንቀጥል። ያም፤ የቅርብጊዜ መሀከልሀገር አማርኛ (ድህረ-ደርግ) ቃልዎችን በዘመኖች እምብዛም እማያድስ፣ ያረጁትን በጡረታ ማግለል እሚከብደው በጠቅላላው የከበደ ችግር የያዘ መሆኑን ነው። አማርኛ በመሀከልሀገር እንደእምንጠቀመው አቅሙ የሻፈደ ሆኗል። ጆርጅ ኧርዊል፤ 1984 ላይ የአምባግነና ጫፍ ስልቶችን ሲያሳይ ያስጠነቀቀን ዘንግተናል። ቋንቋችሁን እንደማህበረሰብ ሁሉ እየተከታተላችሁ አዘምኑ ያለንን መርሳታችንን ያስረዳል። አማርኛን መንግስት አቆርቋዡ ሆኖ ሥጋዎቹን ግጦብን በአጥንቱ አገርጥቶ የተወው መግባቢያችን ሆኗል። ለቁምአሸልብ የአጀዝቦ-መግዛት ክሂሎትአዊነት (ቴክኒክ) ስኩ ምስጅት (ረሲፒ) ሆኖ አገልግሏል። ኪነእናስነ ጥበብዎች በኢህአዴግ. ታፍነው ለማህበረሰቡ ረብያለሽ ትንፋሽ አልሰጡም። እሚገለጡበት ብስል ቋንቋአቸውም በእዚህ የጊዜ እረድፍ አልተሸተተም።
ጋዜጠኛነት እና ይፋአዊ (ፐብሊክ) ስራ ወይም አገልግሎት፤ ሆንተብሎ ድሀ አማርኛን በአንድ መንገድ ብቻ ሲግት ኖሯል። መንግስት-እቅፍ መገናኛብዙሀኖችም አንድአይነት እና የወል-አመለካከትን (ማስ ሜንታሊቲ) ተቆጣጣሪ ቋንቋ ብቻ በመሆን አዘውትረዋል። ያ ቱልቱልቴ (ፕሮፓጋንዳ) ለመስራት እሚያግዝ በመሆኑ ጭምር ነው።
በእዚህ አጭርወቅት (እነሆ ሠላሣ አመቶች) አማርኛ እራሱን በስኬት አመንምኗል። አምባግነና ለምልሟል። በዳያሌክቲካል ማቴሪያሊዝም የተነገረን ትውልዱ ሁሉ የእራሱ ቀለም እና ቅርፅ አለው ማንም አይደገምም እሚለው እውነት ከሆነ፣ የእዚህ ዘመን አማርኛ አለቅጥ አንገት ደፍቷል። አዳዲስ አለምዎችን የሰውዘር አምርቶ ባለፉት ጥቂት አስርታት (ዲኬድስ) ብዙ ሲቀየር፣ ቋንቋዎችም በእየዘርፋቸው ዘምነዋል። አዲሱን አለም አንፀባርቀዋል። አማርኛ ባለበት አፍጢም ዉድቃት እንዳለ አለ። በምርጡ ሙከራው፤ አማሊዝኛ መገለጫ መሸሻው ሆኗል። ከ ፈረንጅ ተነስተን እኒህን መነጋገር በምርጡ አተራረክ መንገድ አይመረጥ ይመስላል። ዳሩ፤ የቅፅአዊ እና ዘማኝ አማርኛ አበለፃጸግአችንን ግን ወደእነዛ እሚያስጮልቅ ይሆን ይሆናል።
የቀለለው ሀሳብ በችግሮች አነባበሮ ወፍሮ፤ ወደከበደ ያደርሰናል። ፈረንጅ እሚለው ስም የምራዊነቱ ቢያንስ በስሜት እነሆ ቀጨመ። በ ፈረንጅ፤ በቋንቋአችን በስፋት ሊኖር እሚችል ኋላ-ኗሪ ሀልዮታአችንን (ኧቲቲውድ)፣ የአንደበታችንን ኢዝሙንነት፣ እና ኢህግአዊ የኢቅፅአዊነት ተግባቦትአችንንም ማማተር ቻልን። እነእዚህን በዝርዝር እስክናጠነክርአቸው እና መዘርዘር እስክንችል፣ በቂ ጥርጣሬ ጫሪ ይህ ይሁነን፨

ቢንያም ኃይለመስቀል ኪዳኔ
ታህሰሥ 23፤ 2013 ዓም፤ ወልቂጤ፨

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s