Categories
ሥነዉሳኔኛ (About Politics)

ምርጫ እና ቀልድ፤ ብልጽግና ከ. ኢዜማ

የቀልዱ መነሻ ማህበረሰብአዊ-ንፅዉሳኔአዊው (ሶሻልዴሞክራት) ኢዜማ. (የኢትዮጵያ ዜጎች ማህበር) እና አንድ ጥረቱ ነበሩ። ድርጅቱ፣ በታህሳሥ 2013፣ በምርጫዓመቱ፣ አንድ ስራውን በይፋ በሳምንቱ ማብቂያቀኖች፣ ታህሳስ 10 እና 11 ላይ፣ አስመረቀ። የተለያዩ ሰባት የትልምአግጣጫዎች (ፖሊሲሥ) አዘጋጅቶ ይፋ ሲያደርግ እነአማንይሁን ረዳ የትልምአግጣጫዎች ኃላፊውን ጨምሮ እና ሌሎችም ንግግር ከውነው ትልምአግጣጫዎቹን አብራሩ። በመቀጠል፣ የድርጅቱ መሪ ብርሀኑ ነጋ (ሊቀሊቃን = ፕሮፌሰር) ማብራሪያ ለተሰበሠበው ዘጋቢ ስብሥብ አቀረበ።
በኢትዮጵያ የ ትህነግ. መሸነፍ አንድ ደግ ምእራፍ ነው። አሁን ካለጥይት ለመታገል መንገዱ ክፍት ተደርጓል። በሀገራችን ያሉ ልሂቃን ወይም ኤሊትስ ወደ ስነዉሳኔአዊው (ፖለቲካል) መድረኩ መምጣት አሉባቸው። እኛ ሀገር ያ ተዳክሞ ቆይቷል። መስተካከል አለበት። ይህን የትልምአግጣጫዎች ጥናት እንኳ ከውኑልን ብለን ብዙ ምሁሮችን ሄደን አነጋግረን ነበር። አብዛኛዎቹ ድንግጥ-ድንግጥ አሉ። እኛ ስነውሳኔ ውስጥ አንገባም እንፈራለን ብለው መለሱን። ዳሩ፣ በተለይ ድሀ ማህበረሰብን ከፊት ሆኖ እሚመራው የልሂቃን ቡድን መሆን አለበት። ያደጉ ሀገሮች እንደሆነው ምሁሩ ትልቅ የአስተዋፅዖ መዋጮ ይጠበቅበታል። ስለእዚህ ልሂቃን ወደፊት መድፈር አለባቸው። ምሁሮች እና በመጠኑ ገንዘብም የያዙ ግለሠቦች ብቅብቅ ማለት ከቻሉ የተሻለ መንቀሳቀስ እሚችል ስነዉሳኔ (ፖለቲክስ) ይኖረናል።
ይህ ያለቀው አንቀፅ፣ በጠቅላላው የመሪውን ጥቅል ሀሳብ ያስቀምጥልናል። ያም ገሀድ እና እነአንዳርጋቸው ፅጌም እሚገልጡት እንዲሁም የተደጋገመ የኢትዮጵያ አንዱ ህልም ነበር። ከካድሬነት ሰንሰለት-መር ወደ ዕውቀት አስተዳደር መምጣት። አንዳርጋቸው እንደገለፁት (ጥቂት ሳምንቶች ቀድሞ ለ አሀዱ ትመ. (ቲቪ) በሰጡት ቃለመጠይቅ)፣ እንደ እንግሊዝ የተማረ ብቻ ሳይሆን በልዩ መልኩ ከ ብቁው የ ለንደን ስነምጣኔ ትምህርትቤት ብቻ ተምረው የተመረቁ ከመንግስት ጀርባ ሆነው በዕዉቀት የሀገሪቷን ጀርባ መምራት እንደእሚያግዙት በኢትዮጵያም የልሂቃን አመራር ከጀርባ ሆኖ ድርጅቶችን ሲያግዝ ማየት ህልሜ ነው፤ በማለት ተናግረው ነበር።
ይህ የ ኢዜማ. ዜና በእየ መገናኛ ብዙሀኑ ተዘገበ። ወዲያው በንጋታው የብልፅግና ድርጅት መልስምት በአጋጣሚ አዘጋጅቶ አቀረበ እሚያሰኘው ጉድ ተፈፀመ። እየተጨነቁ ነበር ማለት ነው። ከ 1984 የጆርጅ ኧርዊል ልብወለድ ዉስጥ ባለችው ፍፁም አምባገነን ሀገር ዉስጥ እሚገኝ እሚመስለው የሰላም ሚንስቴር ብሔርአዊ የህዝብ ዉይይት ዝግጅቱን ለጀመር እንደተነሳ እሚገልፅ ዜና ለህዝብ በዘጋቢዎች በኩል እንዲሁ በይፋ አቀረበ። ሙፈሪያት ካሚል በአትሮንሱ ቆማ በእርጋታ መናገር ጀመረች። ሚኒስቴሯ በመሀል አጋጣሚውን ለመጠቀም አልቦዘኑም። ወደ ኢዜማ. የልሂቃን የጥሪ ሀሳብ መልስምት አያይዘው ተናገሩበት።


“ልሂቃን ብቻ እንዲሆን ያልፈለግንበት እና መሰረተሰፊ እንዲሆን የፈለግንበት ምክንያት መገንባት የምንፈልገው ዴሞክራሲ ጥቂቶች ብቻ የሚጫወቱበት ሜዳ ብቻ ሳይሆን ብዙሀንን የእሚያሳትፍ እንዲሆን ይፈለጋል።…”


ይህ ቃልበቃል ከ ኢቲቪ. ሰኞ ምሽት ዜና የተወሰደ የሚኒስቴሯ ጥቅስ ነው። ዉይይቱ ተራ እና የተለመደ በእየሰፈሩ ለዓበል እሚከወን የትም ሲደርስ ያልታየ እና ማታለያ እንደሆነው እሚከወን ነው። ታዲያ ይህን ዝግጅት ሚኒስቴሯ ፊሽካ ስትነፋለት፣ የቀደመውን እለት አብይ ዜና ያጠቃች መስሏት ልሂቃንን እናሳትፍ ሲባል አይ እኛ ሁሉንም ነው እምንይዘው በእሚል መልእክቷ የድርጅቷን ዝብአተያይ አንፀባርቃበት አለች።

ይህ የቅድመ ምርጫ የስነዉሰኔ ንፍንፍ ያስመለከተን አንድ ቀልድ ነው። ሌላ ምን ይገጥመን ይሆን? ምርጫ እና ስነውሳኔ በተለይ በፉክክር ወቅቶች ዝነኛ የቀልዶች ምንጭ ናቸው። እነሆ የሰወነውሳኔ ሳቁ ሳይጀመር አይቀርም!

By Binyamhailemeskel

Hey there! If you want to know about me, I just like fun, commonsense wisdom, and human love. Let us live a bright today changing tomorrow into brighter.
Regards,

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s