Categories
ሥነዉሳኔኛ (About Politics)

ያልተንጠለጠለው ሥልጣኔ፡ የኢትየጵያ ሥልጣኔ ምኞት/እንቅስቃሤን ዘመንአዊ ፈር ስለመስጠት

ዘመንአዊ ሥልጣኔ ቆይ ምንድነው? እጅግ ልቡ የሆነውን ሥልጣኔን የመመስረት እና ማስቀጠያ ነጥቡን እንወያይ። ያለ እዚህ፣ ወጥ እና ከራሚ ሲጀመር ሙሉ ሥልጣኔ የለም እና፨

ይህን አጭር ፅሑፍ በ ተአዶ. (PDF) አግኙ፨

ቅንጭብ (ኤክሰርፕት) ከ Interstellar ፊልም ስክሪፕት።


[ኩፐር ለናሳ ዕደህዋ (ስፔስክራፍት) በማብረር ፍኖተሀሊብ (ሚልክዌይ) ቤተክዋክብት (ጋላክሲ)ን ተለይቶ አዲስ ፈለኬ (ፕላኔት) ፍለጋ ሊዘምት ተዋውሎ እቤት በተመለሰበት ምሽት፨]

EXT. PORCH – NIGHT
Donald looks out at the night, taking it all in.
DONALD
This world never was enough for you, was it, Coop?
COOPER
I’m not gonna lie to you, Donald – heading out there is what I feel born to do and it excites me. That doesn’t make it wrong.

Donald considers this. Turns to Cooper.
DONALD
It might. Don’t trust the right thing done for the wrong reason. The ’why’ of a thing? That’s the foundation.

(CHRISTPHER NOLAN, “Interstellar”, 2014 GC)

“ኢትየጵያ እምብዛም ዘመንአዊ ሥልጣኔ እንደሌላት ይታወቅ አለ። የሌለውንም ገሀድ፤ ያለውንም ትትረት እንኳ፣ ማንጠልጠል ግን፣ ሥልጣኔን ለመገንባት አስገዳጁ አንድ ቅድመሁኔታው ነው።”

፩. ስለ ሥልጣኔ ምን መሆን፡ አጭር መሠረትአዊ መግለቢያ
በዘላቂነት ሠፊው የኑሮ ዝግመት እሚቀልባቸው ጎዳናዎች የክምችታው-ዉስብስብነት ከፍታው እሚፈጥረው እዉነትአዊነት (ሪያሊቲ) እሚባለው ሥልጣኔ ነው። ይህ ሥልጣኔን እንዲመሠርቱት፣ ሦስት አስገዳጅ ቅድመሁኔታዎችን ፈተና ያደረገ ፍች ነው። ከእነዚህ አንዳቸው ቢቀነሡ፣ ሥልጣኔው የለም ማለት ነው። በሌላ ቃል፣ የሥልጣኔ ኑባሬ (ኤግዚስተንስ) አስገዳጅ መሥፈርቶቹ እነዚህ ናቸው።
አንደኛው፣ አኗኗር ቀልሎ አለ ማለት ነው። በሠብሳቢ ቃል፤ አቅላይነት የሥልጣኔ ባህሪ ይባላል። ይህም ከዉስብስብነት እሚወለድ ነው። ሁለተኛው፣ ሥልጣኔ አለ ለማለት፣ የህይወት አቅላይነቱ ደረጃው አጀብ መሆን አለበት። ማለትም፣ አንድ ቁንፅል የህይወት ገፅታ ብቻ መቅለሉ አይደለም። ይህ እሚሰኘው፣ የሥልጣኔ ኢተነጣጣይአዊነት ወይም ሁለንተናአዊነት ባህሪ ነው። ሦስተኛ ደግሞ፣ ሥልጣኔ በራስሠር እራሱን እሚያክም፣ እሚያሾር እና ለትዉልዶች እሚዘልቅ ቆዪአዊነትን (ሠስቴይናብል) ባህሪ ይላበሣል።
ስለእዚህ፣ ከመነሻው ትርጉም፣ የሥልጣኔ ህላዌ፣ በዐብይ ሦስት ካስማዎች ተጨፍቆ የሚዘረጋ ነው ማለት ነው። ቅለት፣ የቅለቱ ህብረት እና የእዚህ ህብረቱ ለወቅትዎች መትረፍረፍ (ዘላቂነቱ) ናቸው። እነዚህ ዐብይ ሦስት ሥልጣኔ አምዶች፣ በዛ ያሉ ንዑሥ ነጥቦች እሚያደልቧቸው ናቸው። ከደለቡ፣ ሥልጣኔ እዉነትአዊነት ወይም ይፋ ሆነ ማለት ነው።
ከእነዚህ አንደኛው ሁለንተናአዊነት ነው። መሠልጠን፣ በህይወት አንድ ወይም ዉስን አንጃ አካባቢ ብቻ አይከወንም። ለምሳሌ፣ ሰዎች እንዲንቀሳቀሡ ብዙ አማራጮችን በመፈብረክ እና በቅለት በማድረስ ትልቅ የሥልጣኔ አንድ ዘርፍ ተሳክቷል ማለት ነው። ነገርግን፣ በሌላ ዘርፎች፣ ህይወት መቅለል ካልቻ ይህ ለዉጥ በሥልጣኔ ስም ለመሠየም ኢብቁ ነው። ይልቁንም ቁንፅል-ሥልጣኔ ይባል አለ። የመጓጓዣ ሥልጣኔ እንጂ ሥልጣኔ አይባልም። ይህ ቅፅልአማ ሥልጣኔ ይሰኝ አለ። ሁለንተናአዊነቱ የተቦደሠ እንጂ ያልተሟላ ነው። በሌላ ቋንቋ፣ የሥልጣኔ ባህሪ ዘርፍአዊ ስኬትዎች መኖሩ ነው።
በሁለተኛው ካስማ ደግሞ፣ ቆዪአዊነት፣ በሰፊ ዘርፍዎች የተመሠረቱ የሥልጣኔ ምቾትዎችን በአለት ወለል አድርጎ በትዉልድዎች ጥቅምዎቹ እንዲወሠድ ማድረጉ ነው። ይህ ራስሠር ማድረጉ ነው። ራሱን የቻለ ሥልጣኔ፣ በአለፈው ትውልድ ብቻ አይቆምም። በቀረ፣ ቀጣይአዊነት ጎድሎት አለ። ይህ ዕዉቅ ትርጓሜ የተመዘዘለት ሰፊ ነጥብ ነው። ተፈጥሮ ሀብት (ሪሶርስ) አለማሟጠጥ ለምሣሌ፣ መጭትዉልድ እንዲኖርም እንዲሰለጥንም፣ ከስንበታ (ሰርቫይቫል) እስከ ዘላቂ ልማትድረስ የተመነዘረ ጉዳይ ነው።
ሦስተኛው፣ ዋናው መቅለል እሚለው ነው። ዊንስተን ቸርችል እንዳለው፣ “ከጋሉ ዉስብስብነትዎች እጅግ ቅለትዎች ይወጣ አሉ”። ሥልጣኔ፣ ከፍተኛ ጭንቅንቅ የከተቱ ሂደትዎች በዕለቱ መጨረሻ ፈታ አድርጎ ሰብ-አሥተኔን (ሂውማንካይንድ) እሚያሥደስት ምድርአዊ መጨጊያው ነው። ከእሳት መገኘት፣ እስከ ጠፈር አሠሳ፣ ጥድፊያ እና ጭንቅንቁ መቅለልን ለመውለድ ነው። በጠቅላላው፣ ስልጣኔን አለ ለማለት፣ እሚያስፈልጉን መሠረትአዊ ነጥብዎችን ተመለከትን። ወደ ዋናው ጭብጥ ሳንገባ ቀድመን ይህን እንይ። ታዲያ ሥልጣኔ፣ እንዴት መሠረቱ ይፈጠራል? በአጋጣሚም፣ በሆንብሎንታም፣ በአጭር ጊዜም፣ በእረዥም ጊዜም፣ አሰሣ ተደርጎለት ወይም በመቅዳት እና ማላመድ መሠረቱ ይገኛል። የምድር ዘመንአዊ ሥልጣኔ ከተለያዩ ሥልጣኔዎች በመዋሥ እና በከፍተኛ አሠሳ፣ ሙከራ እና ግኝትዎች ወዘተ. ተከውኖ ዛሬ ባለበተደ የደረሠ ነው።ይህ የሥልጣኔ አንድ ወይም ሙሉ (ሰፊ) ፍኖት፣ ሲገኝ፣ የመኖር መንገድን ካሻሻለ፣ ምንም መንገድ ያግኘው ምን፣ አንድ ነገር ግን ግድ ሆኖ እንደ ትልቅ እሳቤ ይወለዳል። ይህን በቀጣዩ ክፍል እምንመለከተው ሲሆን፣ ለእዚህ ፅሑፍ ቁልፍ ኢላማው ነው። ‘ሥልጣኔን ማንጠልጠል’።
፪. ሥልጣኔን ማንጠልጠል፡ የኢትዮጵያ የመሠልጠን ፍላጎት የዘነጋው ዐብይ ሌላው መሠረት
‘ሥልጣኔን ማንጠልጠል’ ምንድን ነው? አጠንክሮ ያንን ለመመለስ፣ ፅንሰሀሳቡ የተወለደበትን ምንጭ እናጥና። ያም ዘላቂአዊነት እና ሁለንተናአዊነት የሥልጣኔ ክፍልዎች አካባቢ የእሚገኝ ነው። በተለይ፣ መጪትዉልድ ጋር የእሚኖር ግንኙነትን መሠረት ያደረገ ነው። ምክንያቱም፤ ሥልጣኔ በተፈጥሮው ማእከለትዉልድአዊ (ኢንተርጀነሬሽናል) ነው። ለጊዜው እሚባል ሀገርአዊ ሥልጣኔ ታሥቦ አያውቅም።
ይህን ማብራሪያ ለመቋጨት ያክል፣ አንድ ሥልጣኔን ለመመሥረት፣ ለማግዘፍ፣ እና ለማስቀጠል፣ ከምንጠቀምብአቸው ብዙ አውራመንገድዎች አንዱ፣ በሥልጣኔው ሂደት እና መሀከል ያሉ ትዉልድዎችን አንድ አድርጎ ማገናኘት መቻል ነው። ከአልመጣው ትዉልድ፣ አሁን ያለው፣ ለመገናኘት ድልድይ መገንባት መቻሉ፣ ከአለፈው ትዉልድ ደግሞ አሁን ያለው መሠረቱን መቅዳት መቻሉ፤ ማለትም ቀጥተኛ የላይ፣ ታች እና አሁን ትውልድዎች ግንኙነትዎች መመሥረትአቸው፣ የሥልጣኔ ማዕከለትዉልድአዊነት መገለጫው ነው።
ማዕከለትዉልድአዊነት መንትያ ፍች አለው ማለት ነው። መሥራች እና ተካፋይ (ቀጣይነትአዊነት) ላይ አባል የሆነ እሣቤ ነው። አሁን ለእሚገኘው ሥልጣኔ ወርድአዊ (ቨርቲካል) ሁለንተናአዊነቱ ነው። በእየህይወት ዘርፉ መሠልጠን የስፋት (ሆሪዞንታል) ሁለንተናአዊነት ሆኖ፣ ሙሉ ሥልጣኔን ሊመሠርት አይችልም። ሙሉ ሥልጣኔ የእራሱን እና የመጭውን ጊዜያት፣ ዛሬ አካትቶ እሚይዝ ሥለሆነ፣ ለመሟላት፣ ያንን ማዕከለትዉልድአዊነቱን መክተት አለበት። ገና ላልመጣ ትዉልድ በእዚህኛው ሥልጣኔ ቦታ አለመሥጠት፣ የእዚህኑው ሥልጣኔ አለመሟላት መስካሪ ጭምር ነው። ሁለተኛ፣ ተሟላ እሚሠኝ ሥልጣኔ እንኳ የዘላቂአዊነቱ ምሰሦ ጭምርም ነው። ማለትም፣ የተሟላ እሚሰኝ ሥልጣኔ በጊዜ እንዳይዳከም፣ ማሸጋገሪያ ዐውታሩ ነው።
ይህ የሥልጣኔን ማንጠልጠል መፀነሻው ሥፍራ ነው። አንድም አሁን ያለው አንድም መጪው ትዉልድ የሠለጠኑ እንዲሠኙ፣ ትዉልድአዊ ትሥሥር ያስፈልግአቸው አሉ ከተባለ፤ ይህ እንዴት ይከወን አለ እሚለው ጥያቄ ደግሞ፣ መልሡ ነው። በሠለጠነ ማህበረሰብ፤ ሥልጣኔን በማንጠልጠሉ፣ ያለፈው ትዉልድ ይህን ትዉልድ የመልእክት አካል ትቶለት ሄዶ አለ። ይህ ትዉልድ፣ አንድም መጪውን ለመክተት አንድም በጊዜው በጊዜው ሲደርስ ለማገዝ፣ እንዲሁ እሱም መልእክተ ሥልጣኔን ይልክለት አለ።
ይህ መተላለፍ ሲከወን፤ ሥልጣኔ አልተሸሸገችም፤ አልጎደለችም። ተንጠልጥላ አለች። መጪትዉልድን ስታበራለት አሁኑንም ታሟላው አለች።
መነሻሀሣቡ ሢጠቀለል፣ ዛሬ የተገኘን ሥልጣኔ በተለያዩ መንገድዎች ለማስረከብ፣ የማሣለፍ ብሔርአዊ ክሂሎትአማአዊነት (ቴክኒክኒክ) ነው። ታዲያ፣ ምን ጥቅምዎች ሰጪ ነው?
አንድ እንደ አሀድ የምንቆጥረው ሥልጣኔ ከተፈበረከ፣ የእዛ መንጠልጠል ማለት ሠፊ ትርጓሜ አለው። ሥልጣኔው ገሀድ ተገለጠ ማለት ነው። ይህ የህዝብን አንጎል የሥልጣኔን አንድ አሀድ እንዲመለከት እና እንዲጠቀመው ይጠራው አለ። ስለጉዳዩ እንዲያውቅ እና እንዲነጋገር እንዲሁ ያደርገው አለ። ማለትም፣ ሥልጣኔ አንዱ የህዝብን ህይወት እሚቀላቀል ይሆን አለ። በሂደት፣ አኗኗር የሥልጣኔ ከታች እንጂ ተዘንጊ መሆን እንዳይችል ያደርገው አለ። ይህ እሚከሠተው፣ ሥልጣኔው ሲንጠለጠል ከሆነ፣ ያ እሚከወነው ስለተደረሠበት የሥልጣኔ አሀድ ለህዝብ እሚሠበክ ከሆነ ነው። በእየመገናኛብዙሀንዎችአችን፣ መሥሪያቤትዎችአችን፣ መንገድ ዳር ማሥታዎቂያዎችአችን፣ ዕለትከዕለት እንቅስቃሴዎችአችን፣ ግንኙነትዎችአችን መሀከል፣ ሥነጥበብ ዉጤትዎችአችን፣ አለባበስ እና አኳኋኖችአችን፣ የልጅዎች እና ወጣትዎች ትምህርትቤትዎችአችን እና ስርአተትምህርትዎችአችን፣ ጨዋታ እና በጠቅላላ አኗኗርአችን፣ ይህን አሀድ ያወጣ እና ያወርድ አሉ። አሀዱ በሰፊው ማህበረሰቡን ተቀላቀለ። ህይወትን አቀለለ። ቀልሎ አልቀረ፣ አሀዱ ተንጠልጥሎ አለ ማለት ተጨማሪ ጥቅምዎች ይከተል አሉ።
እንዳልንው፣ ከተራ አሀዱን መጠቀም በመዝለል የሥልጣኔው መንጠልጠል የህዝብ ወሬ መደረግ ስለሆነ ሌላ ነገርዎችንም ለመፍጠር መነሣሻ እሚሆን ነው። አሀዱን በስፋት መገልገል እና መጠቀም፣ ለሌላ ተመራማሪዎች ጥሪ፣ ፉክክር፣ እልህ፣ ወዘተ. እሚያመነጭ ነው። ማሻሻል፣ ማስመሠል፣ መፎካከር ቻይ አሀድዎች መወለድ እሚጀምሩ ይሆን አለ። ማለትም፣ የሥልጣኔው አቦል ለእይታ፣ አንፋሽአማአዊነት (ኢንስፓይሬሽን)፣ እና አሽከርነት ሲባል መንጠልጠሉ፣ እንደ በረዶኳስ (ስኖውቦል) ተፅዕኖ ጎንዮሽአዊ ነፃ ዉጤትዎችን ወላጅ ሆኖ ያ ደግሞ ተጨማሪ አሀድዎችን መዛዥ ይሆን አለ።
አሁንም የሥልጣኔው አሀድ አንድ ሁለት አሀድዎች እንዲመጡ ማድረጉ ብቻ የማንጠልጠሉ በረከትማብቂያው አይደለም። የእረዥሙን ሥልጣኔ ልዉዉጥ ጠንሣሽ ይሆን አለ። ማእከለትዉልድአዊ (ኢንተርጀነሬሽናል) የአሀድዎች ልዉዉጥ ይከሰት እና ያ ሀገሩን እሚያዘልቅ የሥልጣኔ ጎዳና ይጠርግለት አለ። ለመጪው የሥልጣኔ ሙሉ ዉርሥ ይከወንለት አለ። ሌቋሆ. (ሌሎችነገርዎች ቋሚ ሆነው)፣ ሥልጣኔ ዘላቂነቱን እሚያገኝበት መንገድ ነው።
ይህ ሲከወን የእዚህ ኢላማዎች መሳካት ምሥጢርአቸውን ይገልጥልን አለ። እነእዛን ለማሣካት የእሚያስፈልጉን ጉዳይዎች ምንምን እንደሆኑ እየተገለጡ ይመጣ አሉ። ሥልጣኔን ለማንጠልጠል፣ የተገኘው ሥልጣኔን እና ሥልጡን ስርኣቱን የህይወትአችን አባል ማድረጉ እንዳለ ሆኖ ተዘርዛሪ ጉዳይዎች በገሀድ ይወለድ አሉ። ይፋ (ፐብሊክ) ማህደር አያያዝ፣ ፈርማህደር (ሪከርድ) አዘጋገብ፣ ይፋ አግጣጫትልም (ፖሊሲስ)፣ ወዘተ. በሥልጣኔ ማንጠልጠል ዙሪያ ይሾር አሉ። እነእዚህ ዘርፍዎች በብሔርአዊ ደረጃ ሲዘሩ እና ሲበረቱ፣ ከፍተኛ የእድገት ጎዳና እሚገለጥ ይሆን እና ማንጠልጠሉ እሚንቀሣቀስ ይሆን አለ።
በጠቅላላው፣ የሥልጣኔ መንጠልጠል፣ የሀገር ሥልጣኔ እንዲሰፋ እንዲሠምጥ፣ ለዘመኖች እንዲሻገር፣ ሌላውም እንዲነሣሳ፣ ወዘተ. ያደርገዋል። የልኮት (ሪፈረንስ) አመልአችንን ያበለፅግ አለ። በገሀድ እና ግልፅነት፣ ታማኝነት እና ሀቀኛነት ማህበረሰብአዊ ግንኙነትዎችአችንን ሁሉ እንድንመሠርት ያገደን አለ። የባህል ለዉጥ አምጥቶ መሠልጠንን የሽምጥ ግልቢያ ያስረክበው አለ። የሰፊ ሥልጣኔው መሰረት አንዱ መነሻን ማበጀት ስለሆነ፣ ይህን ሁሉ ለማድረግ መሰረቱ ሥልጣኔን ማንጠልጠል ነው።
ይህን ማድረግ፣ ከአንድ እርግማን ይከለክለን ነበር። ይህም፣ ከዜሮ መጀመር ነው። የኢትዮጵያ ብሔርአዊ አንዱ ቀታይ (ሌታል) አባዜ ነው። ከኋላ ዳግ-መነሣት (ሪ-ስታርቲንግ) የእኛ ሀገርአዊ መገለጫ ነው። የማንም ወዳቂ የሥልጣኔ ትትረት መንገዱ ያ ነው። ፈሪ፣ ሰነፍ፣ እማይሳካ፣ ማጭበርበሪያ። ሥልጣኔን ማንጠልጠል ግን ያን ከአዲስ መጀመርን ልክሎልን፣ የሥልጣኔአችን መርዘምን እና መስመጥን መሰረት ይሆንልአቸው አለ። አንዱ ሥልጣኔ ቀድሞ ዛሬ ካልተገኘ፣ ሲገኝ ደግሞ ጊዜ፣ አለመካተት እና ቸልታ ሳይሸረሽረው ነገ ካልደረሠ እሚሰምጥ ሥልጣኔ አይገኝም። ታጥቦጭቃአዊ መዳከር እየተደጋገመ ሀገርአዊ ቅርቃር ይጎዳ አለ።
በምንምን ዘዴዎች ሥልጣኔን እናንጠልጥል? አንደኛ፣ በሊቅአዊ (አካደሚክ) አለም። ያለደተቋረጠ፣ ስምጥ፣ ተደራሽ፣ ቀላል፣ የጥናት እና ዳግ-ምርምር (ሪሰርች) አካል መኖር ግድ ይለው አለ። ይህ ቅፅአዊው (ፎርማል) የሥልጣኔ ምንጭ ነው። አንዱ ሀሳብ ሲነሣ በገሀድ ለሁሉም በቀላሉ በሰፊው መገለጥ እሚገባው ነው። ተቋምዎች በሠፊው የማሳተም፣ የማጥናት፣ እና የመዘገብ ሀላፊነት አለብአቸው። መገናኛብዙሃዎችአችንን በእየአመቱ ከእሚጠኑት እየመረጡ የመዘገብ እና ምርምርን ወደ ህዝብ ልብ የማቅረብ ግዴታዎች አሉብአቸው።
ሁለተኛ፣ ሙሉ የሥልጣኔ መረጃው በመንግስት እና ህዝብአዊ ተቋምዎች ለህዝብ አሽከርነት ባለማቋረጥ፣ ዝርዝር፣ መብት ደረጃ ወዘተ. ይዉጣ። ካልሆነ፣ ለምሳሌ ምንም የሥልጣኔ መፍጠሪያ መንገድን ልንማር አንችል፣ ብንችል ደግሞ ደግመን በመርሣት ደግመን ልንሠራው ብለን ልንባክን ይሆናል። ስለእዚህ የሠመጠ መረጃ በሀገርአቀፍ ደረጃ በአሠራርዎች ሁሉ ተበራክቶ መለቀቅ እና ያ ባህል መሆኑ ግዴታ ነው። ያ በተደረገው እማሬ የማከል እና ከዜሮ ያለመጀመርን አጋዥ ነው። ያየንአቸው ብዙ ተጨማሪ ነጥብዎችም አሉት። ለምሳሌ፣ ሰር አይዛክ ኒውተን ይህን የስህበት ህግ አገኘ ብቻ ብንል፣ እና በእዛ ቅርፀት ብቻ እዉቀት ቢተላለፍ ኖሮ፣ የበዛ ተነሳሽነት አናገኝም። ለምሣሌ፣ The Big Bang Theory ተከታይ ላይ ሸልደን ኩፐር፣ እዉቀት ከትንንሽ ነገር ሊገኝ እንደሚችል ተረድቶ እሚነሳበት ክፍል አለ። እንደ ጎረቤቱ ፔኒ ተርታ ስራ ሊሠራ ይሞክር እና በሬስቱራንት ስተናጋጅነት የምሁር ግኝቱን ያገኝ አለ። ሰር ይስሀቅ ግኝቶቹን ከትንንሽ ነገርዎች እንደመዘዘ ታሳቢነት እምናደርገው እዉቀት ነበረው ማለት ነው። ብዙዎች ከተገኙ ሃሳብዎችአቸው በተያያዘ፣ የሊቀጎበዞች (ጂኒየስ) የግኝት መንገድን የእሚነግሩን እኛም ከእዉቀቱ ዘልለን፣ የእዉቀቱንም መንገድ ብንረዳው ብለው ጭምር ነው። ያ እንደውም ከእውቀቱ አቻ ወይም በላይ አስገራሚው ነገር ሆኖ እምናገኘው ነው። ቢያንስ አስደሳች ነው። እንደአዚህ አገልጋይ ነጥብዎችን ለሥልጣኔአችን ላለማጣት፣ መንግስት ከፍተኛ የመረጃ መዘገብ እና በቀላሉ ተደራሽ ማድረጉን ሊጎብጥበት እሚገባው ነው።
ሁለተኛ፣ በይፋ አደባባይአዊ ግንኙነቶች ሁሉ። በተለይ፣ በአደባባይ (ፐብሊክ) ልዉዉጦች፣ መገናኛብዙሃኖች፣ እና ተመሣሳይ ዐምዶች ዉስጥ የተጋ ሥልጣኔአችንን የመጥቀስ፣ ማሳወቅ፣ ማበረታታት፣ ማነሣሳት፣ መንገድ መኖር አለበት። ያ ባህል መሆን አለበት። በመጨረሻ፣ ጠቃሚውን የእማይወርድ ሥልጣኔ መካብን ያረጋግጥ አለ።
ሦስተኛ፣ በመደበኛው አኗኗር እና መስተጋብር ሁሉ መንፀባረቅ አለበት። አንድ ተመራማሪ እና ደራሲ፣ የአዲስአበባን ዩንቨርስቲ ተመራቂዎች ትምህርትቤት (ግራጁዌት ስኩል) ቤተመጽሐፍ በአስቂኝ መንገድ ገልፆት ነበር። በ 2012 ዓም. ማብቂያ አካባቢ በ ኢትመ. (ኢትዮጵያ ትእይንተመስኮት = ኢቲቪ.) የቀረበ አንድ ደራሲ እና ተመራማሪ፣ የተማሪዎች የምርምር ዉጤቶች፣ መጽሐፍቤቱን ሲሞሉ፣ ከሁሉ ያረጁትን እያወጡ ይጥሏቸዋል ብሏል። ይህም፣ ተራቸው ደርሶ እስኪጣሉ፣ ለአዳዲሶቹ፣ ቦታ ለማበጀት ነበር። ይህ ዳግምርምርዎች ቢሞካከሩም ወደ ህዝብ እና ተቋምዎች እንደማይደርሱ አስረጋጭ ነው። ዳሩ፣ ሀገር እንዲሠለጥን ጥናትዎች ባህል እንዲሆኑ፣ ወደ ህዝብ፣ ተቋምዎች፣ ትትረትዎች ሁሉ ዳግምርምርዎች መፍሠስ አለብአቸው።
አራተኛ፣ በስነ እና ኪነጥበብ ትርክቶች ማጨቅ። ሲጀመር ግን፣ የእኛ መደበኛ አያያዝ በቀልድ እና የፍቅር ተርታ ትርክቶች መጠመድ የትውልዱ መገለጫ ስለሆነ፣ የህይወት መንገድን ለመስበክ የምንጠቀምበት ዘርፍ አይደለም። እስከአሁን ያ ቢሠግግም፣ ጥበብ የደረስንባትን ወይም ያጣናትን ሲለማም ልንደርስ የምንችልባት ሥልጣኔን በመግለጥ ቁልፍ አጋዥ ናት።
፫. ዉጥነ-ሥልጣኔ፡ ለምን የሥልጣኔ እናትን እናክብር?
መነሻ የሌለው አምላክ ብቻ ነው። በቀረ፣ በተለይ በቅድመንቃትአዊ ትትረት እሚፈለግ እና እሚገነባ ተጨባጭ ነገር፣ ሀሌታ አለው።
ሥልጣኔ፣ እንዲሁ፣ እሚጀምርበት ነቁጥ አለ። የጥንቱን ትተን ዘመንአዊ ማህበረሰብን ግን ስንመለከት ገሀድ የወጣ፣ የተሞከረ እና የታወቀ መነሻዎች አሉት። ምንጊዜም፣ ሥልጣኔ ሠፊ እሚሆነው፣ በእነእዚህ መነሻዎቹ ላይ ተጀምሮ፣ በመቀጠል ደግሞ ተደራርቦ አዳዲስ ቅለት እሚሆኑ ክዋኔዎች እና ስነልቦናዎች ሲከማቹበት ነው። ከካፊያ ወደ ዶፍ ሥልጣኔ ለመድረስ፣ መነሻው መለቀቅ የለበትም። በእዛ መንገድ የሠራ ዘመንአዊ ስልጣኔ የለም። ይህ የሥልጣኔ ክምችት፣ እናቱ መነሻው ነቁጥ፣ ዉጥነ-ሥልጣኔ እንበለው።
በዉጥነ-ሥልጣኔ፣ የሥልጣኔ ዉስብስብነት ወይም ክምችትዎች ይደራረብ እና መሠልጠን እዉነትአዊነት (ሪያሊቲ) ይሆን አለ። አዳዲስዎችን ማከል ግን እሚፈልገው አንድ ጉዳይ አለ። የቀደመው መነሻን እሚመለከት ምሉዕ-መረጃ ማግኘት መቻል። ምሉዕ-መረጃ፣ መረጃ ብቻ አይደለም። የዉሂብ (ዳታ) ስብሥቡ፣ መረጃውን ይፈጥር አለ። ግን ምሉዕ-መረጃ፣ ተጨማሪ ግቤትዎች (ኢንትሪስ) ከታች ነው። ከመረጃው በተጨማሪ፣ ስለ ሸልደን ኩፐር እንዳወራንው ለምሣሌ አብሮ እንዴት ያ መረጃ እንደመጣ፣ ማን ምን እንዳበረከተለት ወይም እንዳለበረከተለት፣ ምን ዐውድ ላይ እንደተመሠረተ፣ ወዘተ. መኖር አለበት።
የዉጥነ-ሥልጣኔ ምሉዕ-መረጃ እና የጠቀስንአቸው ስነልቦናአዊ፣ አስተዳደርአዊ፣ ህዝብ (አደባባይ)አዊ ትርታዎች፣ መሀከለትውልድዎች ወዘተ. ሲዋሃዱ፣ ወደ ትክክለኛ የሥልጣኔ ትልም እሚደረስ ይሆን አለ። ሥለእዚህ በማለት፣ የሥልጣኔ-እናት ያም ዉጥኗ ነው ልትከበር ይገባት አለ። ዉጥነሥልጣኔ ወይም የሥልጣኔ እናት ከተከበረች እንዳትፈርስ እና እንድትፋፋ ይደረግ አለ። ያ በሥልጣኔ ማንጠልጠል እሚከወን ይሆን አለ።


ዐውድ
የኢትዮጵያ ሥልጣኔ ጉዳይ በመሀልሀገር መገናኛብዙሀን በተራ ድንፋታ እንጂ በሠለጠነ መንገድ ሲቀርብ አይዘወተርም። ሥልጣኔ ካለን፣ በመደበኛ ትርክት ፍሰት መንቆርቆር አለበት። የባህል መዳኒቶች፣ የባህል ፍልስፍናዎች፣ የታሪክአዊ ሁነቶች እና ግዑዞች፣ በቋሚነት ወደጀርባ እሚሻጡት ሀገርአዊ የሁነት አሁንአዊ ሂደቶች ወዘተ. በወጥ ማህደርአዊ ስልቻ መቀመጥ አለባቸው። ይህም ሲሆን ሂደትአዊ እና ፍሬነገርአዊ ይዘቶቻቸው ሙሉ መሆን አለባቸው። በገለልተኛነት መረጃዎች መቅረብ፣ መያዝ፣ መጠበቅ፣ ወደ ህዝብ መፍሠስ እና ከመደበኛ ኑሮ እና ስራው መተሣሰር አለብአቸው። ሥልጣኔን ከስነዉሳኔአዊ (ፖለቲካል) ቱልቱልቴ (ፕሮፓጋንዳ) ፍቆ መለየት ግዴታ ነው። ይህም ከህዝብ ንቃተህሊና ማነስ የተነሣ ለአስፈፃሚአካል ሙሉ-ዘመም መንግስትዎችአችን የተተወ ብሔርአዊ ያልተዘጋ ስህተት ነው።
የኢህአዴግ. (የኢትዮጵያ ህዝብዎች አብዮትአዊ ዴሞክራሲአዊ ግንባር = አሁን ብልፅግና ድርጅት) እናቱ እና አባቱ፣ ትህነግ. (የትግራይ ህዝብ ነፃአውጭ ግንባር) ሦስት አንኳር ሥህተትዎችን ከእዚህ ነጥብ ረገድ ሰርቶ ሀገር ካጅ ነበር። አንደኛ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት-ደርግን እየገለበጠ እንደገባ፣ እልፍ የህዝብ አገልግሎት ማህደርዎችን ከእየመሥሪያቤቱ እየሠበሰበ ማቃጠል ተያያዘ። ብዙ ይፋ እና ታሪክአዊ ማህደር ወደመ። ሁለተኛ፣ በቆይታው ደግሞ፣ ምንም እሚረባ እሚሰኝ (ግልጥ እና የረዥም ሥልጣኔ ተገቢ መሠረት እሚሆን) የባህል ለውጥ፣ ማህደር አያያዝ ስነስርኣት ወዘተ. ለሀገርአችን አላመጣም፤ አልተወም። የህግ ድንጋጌዎች እና የዉይይት መዛግብትዎችአቸውን እንዲሁም ትልልቅ ዉሳኔዎችን እንኳ በዘመነ መንገድ ማግኘት ዳሸንን ከመዉጣት በላይ ነው። መረጃ በመደበቅ ኢተጠያቂነትን ለመደገፍ ተበቅቶ ነበር። የሥልጣኔ ፈር ደግሞ ያን በመቃረኑ ኢህአዴግ. እና ሥልጣኔን ማንጠልጠል እማይዋደዱ ሆነው ተለያይተው አሉ። ሦስተኛ፣ በአምባግነና መንገድ፣ የተፈለገው ትርክት ብቻ እየተነገረ ዉሸትን እና የተገደበ እዉነትን በህዝብ እና ትዉልድ አንጎል የማስረፅ ከፍተኛ ክፉ እሚሰኝ ነገርን ከወነ። አብሮ፣ ታሪክ ማዛባት እና ትምህርት መፅሐፍዎች እንኳ ዋሾ መረጃዎችን እንዲሠጡ አድርጎ ቆየ። በቂ ፀረ-ሥልጣኔአዊነት በእነእዚህ እጅግ መሠረት ሀሳብዎች ታይተው አሉ።


መሠረተ መፍትሄ
ዳግም ለማስመር ያክል እኒህን አንቀፅዎች እንይ። ሦስት መንገድዎች ሠግገው አሉ። አንደኛው፣ እንዳየንው በእየዘርፉ ሥልጣኔን ለገሀድ እና ጋራ አገልግሎት ሲባል እንዲንጠለጠል በማሰብ መዘገብ። ሁለተኛው ባህልአዊ ለውጥ በሂደቱ ማምጣት እና ማስቀረት። ሁለት ነው ይህ በዋናነት። ያለልኮት እና መረጃ ልዉዉጥ አለመጠቀም። ያለፈውን ወደአሁን እያመጡ በመዉሰድ መጠንከር። ሁለተኛ፣ አሁንን ምንጊዜም ወደ ተዘገበ የአለፈጊዜነት እየከተቱ የመኖር እና ማዝገም ባህል ማልመድ።
ሦስተኛ ዜጋዎች፣ መንግሥት፣ ሀገር፣ ተቋምዎች፣ እና የነገውትዉልድ ኢተነጣጣይ ባለመስተጋብርዎች እንደሆኑ መቀበል፣ እና አኗኗርን በእዛ ቅኝት መክተት። ያኔ፣ መንግሥት ታሪክ አያጠፋም። አይቀይርም ወይም አያዛባም። ቀጣይነት ያለው ትትረት ይመሠረት አለ። እንደእዛው፣ ጎንዮሽ ጥቅምዎች ይበዛ አሉ። ሀገርአዊ ግልፀኝነት፣ ተጠያቂነት፣ ይወለድ አለ። ቀጣይነት ያለው ወጥ ሀገርአዊ ገሀድአዊነት ይወለድ አለ። መጨቆን፣ ኢፍትህአዊነት፣ ወዘተ. እሚቀንሡ ናቸው። የሥልጡን አኗኗር አንዱ መሠረቱ ይኼው እራሱ እሚጫወተው መስተጋብር ነው እና መሠልጠን ይቀና አለ። ሙዐዘጥበብ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት እንደፃፈው፣ አንዱ የሀበሻ በሽታ ‘አሉ’ ነው። ከ አሉ፣ አሉባልታ ወጥተው ገሀድን ተሸክመንው እምንጓዝ ማህበረሰብ ያደርገን አለ። በአጭሩ፣ የሞቀ ዘመንአዊነትን በማንጠልጠል ዉስጥ እና ጎንዮሽ ሂደትዎቹ ተሰርቶ እናገኝ አለን።


መቋጫ
የ ክሪስቶፈር ኖላን Interstellar ፊልም ላይ, የኩፐር ሟች ሚስት አባት (የእሱ የህግአባት) ዶናልድ፣ ኩፐር ወደ ህዋ ከመብረሩ ቀድሞ ባለው የዉጭ-ቀረፃ-ትእይንት፣ ቁምነገር ሲያጨዋውተው እንመለከት ነበር። “Do not trust the right thing done for the wrong reason.” እሚለው መስመር፣ እጅግ መሳጭ መልእክት-እጭቅነው። በተለይ ከሙሉ ትርክቱ አንፃር ከፍተኛ መልእክት እሚያስተላልፍ መስመር ነው። ያ መስመርም የእዚህ ገና ያልተብላላ መነሻፅሑፍን መነሻሃሳቡን ያገኘሁበት ነበር። በአጭሩ፣ የዶናልድ ምክር ይሄ ነው።
የሰውልጅ በፈለገው አንድ ሃሳብ ዙሪያ እጅግ አጥርቶ ማሠብ ይገባው አለ። ለምሳሌ ደግ ምግባርን ሲከውን፣ ጀርባው ግን ደግያልሆነ ሀሳብ ካለ፣ ምግባሩን ያበላሽበት ይሆን አለ። ስለእዚህ እኛን አንጎልአችን እሚሸውድበት ሁኔታ እንዳለ ይነግረን አለ። ይህም፣ ለምሳሌ አንድ በጎ ነገር አስበን ሳናቀው ግን መጥፎ ስሜትን አብረንው እናክልበት እና እንጎዳ ወይም እንሣሳት አለን እሚለውን ፊልሙ ያስመለከተው ነው። ለሰውዘር አንድ ነገር ማበርከት እሚያቅድ እና ቀንሌሊት እሚለፋ በጎአድራጊ ግለሰብ፣ ባላስተዋለው መንገድ የፉክክር መንፈስ ይዞት ያንን በጎምግባር ይከውን ከነበረ፣ ተሸወደ እንደማለት ነው። ተታለለ። በጎምግባር ያሠበ፣ ምግባሩ በመጥፎ ጀርባአዊ ዐውድ አይርከስበት እሚለን ነው። እንዲህ ያሉ የሰቡ ጥንቃቄዎችን ከህይወት ተሞክሮ የቀሠመ እና ከፍተኛ ደረጃ የደረሠው ደራሲ አጉልቶ በትርክቱ ጭምር እየነገረ እሚሰብከን ሆነ።
በህዝብ አመፅዎችም ለምሳሌ፣ ሰው ስላመፀ ብቻ እሚያምፁ አሉ። የዉሥጥ አመክዮዎችን አለማጥራትአችን እንቅስቃሴዎችአችን ጠርተው አንድ የስኬት ወደብ እንዳይደርሱ ያደርጉአቸው አሉ። ይህን አበክሮ ለማስተማር የሰመጠ ዳግ-ምርምር ኖላን መከወን ነበረበት። ዳሩ፣ ይህ ጥበብ ለተመልካቹ ስለዝርዝር አስተሳሰቡ እንዲጠነቀቅ እሚጋብዘው ሆኖ ለሀገር እና ተመልካች፣ ያ የሥልጡን አኗኗር አንድ ግኝት በይፋ ለእሚሻው ተንጠልጥሎ አለ ማለት ነው። ይህንን መቼም ፈልጎ መመልከት፣ ማብራሪያ ማሰሥ እና በእዛ ጉዳይ መዘመን እንዲቻል አድራጊ አንድ ትልቅ ጉዳይ ነው።
በእዛ ሥር፣ አንድ ተያያዥ ሀሳብ አገኘሁ። ይህም አንድ ሌሊት ሁሉ ረጭ ባለበት ነቅቼ ዉሻዎች ሲጮኹ እና ሲያላዝኑ የሰማሁ ጊዜ እና ይሄ ሐተታ በተመሳሣይ ወቅት የመጣልኝ ጊዜ ነው። ዉሻዎቹ ሲጯጯኁ፣ ልብ ብዬ አልሰማሁም ነበር። በሆንብሎንታ ያልሰማሁት ደግሞ በእዚህ ፅሑፍ የመጣውን ዋና ሀሣብ ሳብላላው ስለነበር ነው። ግን፣ ከቆየ በኋላ፣ አንድ ቅጽበት ላይ፣ መንጋቱ ገፍቶ የዉሻዎቹ ጩኸት በወፎች ጫጫታ ተተካ። ጎህ መጣ። የዉሻዎቹ ድምጽ በቀኑ ሲሠርግ፣ በአዉቆታ ሳልሰማው ግን ከፍተኛ የስዉር ማድመጥ ስከውንበት እንደነበር ገባኝ። ፅሑፉን ሳሥብ፣ ዉሻዎቹን ከጀርባዩ እያደመጥኩ ነበር። ልዩነቱ በቀጥታ ወይም ሆንብዬ ሳይሆን በጎን ያደረግኩት መሆኑን ነው። ወዲያው ወደ እዚህ ሃሳብ ተመለስኩ። የ ኖላን ወርቅ ቢያፈሱ እማይገኝ ድንቅ ስልጣኔአዊ ነብስአድን ሃሳቡ ወዲያው ቀጥሎ መጣብኝ። ይህ በምክንያት ሆነ።
ኖላን የነገረን ዉስጣችን አንድ ነገር ሲያደርግ፣ ከጀርባ አንጎላችን ግን ሳናስተውለው እሚያደርግብን አለ፤ ያን መመልከት ከቻልን ለህሊናችን ነፃነት እና ብሩህመሆንአችን ትልቅ ግብአት አገኘን ነው። ለምሳሌ፣ የፊልሙ ገፀባህሪ፣ ኩፐር ከምድር ወደ ህዋ ዕደህዋ (ስፔስክራፍት) መንኩራኩሯን ሊያበርር ተስማምቶ ሲመጣ፣ የሟች ሚስቱ አባት እሚመክረውን ዐዉድ ዳግ-እንይ። ወደ ህዋ ሂድ፣ ተመራመር። ግን፣ ቤተሰብ በመጥላት፣ እራስክን ለማሳየት ያክል ብቻ፣ ወዘተ. ብቻ በመለወጥ ከማመን ዉጭ ለአንዳች አመክዮ አትከውነው ማለቱ ነበር። ይህን መልእክት ግን፣ ለሰውልጅ ሁሉ እሚያስተላልፈው ትልቅ፣ የህሊና ስንቅ ለማሸከም ነው። ለማንም እና የትም እና ምንም እማይከሽፍ ሰብአዊነትን ማበልፀጊያ ሃሳብ ነው።
ሰው ለመርዳት ሚሊየኖች ማፍሰሥ፣ ከኋላ ግን ሰው መርዳት ሳይሆን፣ የመቅበጥ ሃሳብ፣ ሃብትን የማሳየት ሃሳብ፣ ባዶነትን የመድፈኛ ሃሳብ፣ የመኩራራት ሃሳብ፣ የመኩሪያ ሃሳብ፣ ሰውን የበታች ነው እኔን ግን እዩ የበላይ ነኝ እሚል ሃሳብ፣ ወዘተ. ሊያጠቃን ይችላል። የኖላን ጣልቃገብነት ወርቃማ የሆነው፣ ይህን ሆንብለን ስናደርግ ደግ አይደለም ስለእሚለን ነው። በቅንነት ሰው ለመርዳት ያደረግንው፣ በገሃድ ባልፈተሽንው ስዉር አመለካከትአችን ግን በኋላ ሊጠልፈን ይችል አለ። በደንብ ያልታሰበበት ሀሳብ አድጥ መሰረት ነው። በበቂ አመክዮ እንጠንቀቅ ባይ ነበር።
ይህን ከሌሊቱ ዉሾች እና ድምፅዎችአቸው አገናኘሁት። በሃሳብ ስንዋጥም፣ በእርግጥ፣ በአካባቢያችን ያለን እዉነት በተለየ ደግሞ ድምጽን ቸላ እንለው አለን። ያን አይነት ድምጽ ግን፣ ነቃ ብለን ባልተቆጣጠርንው ልቦና እንመዘግበው እና እንጨነቅበት አለን። ይህ በኋላ ከፍተኛ ዋጋ አስከፋይ ሊሆን እሚችልበት ዕድሉ ነው። የአንጎል ነፃነትን ማዳፈኛ መንገድ እሚሆን ሁሉ ይሆን አለ። ምርጥ አብነት አለ። የ Get Out ፊልም፣ አቀንቃኙን በአመነአቸው ቤተሰብዎች ሲታገት እንመለከተው አለን። ሳያጠፋ ንፁህ ሳለ የህይወት አደጋ የወደቀበት ይህ ታሳሪው ገፀባህሪ፣ በመጨረሻ ያመለጠው በአንዲት ጥንስሥ ጥበብ የመዉጫ በሩን አበጅቶ ነበር። በጆሮዎቹ ጥጦች ወትፎ፣ ስነልቦናአዊ እስራት ያደረሡበትን ፀረአቀንቃኞች ሳያደምጥ ጆሮውን ዘግቶ ቀረ። በእዛም፣ ከአንደኛው ወሳኝ የእስራቱ ቅጽበት አምልጦ፣ ነፃ መዉጫ መንገዱን መዘየድ ተያያዘ።
ይህ ኪነጥበብአዊ የክወና ፈሊጥአዊ ነው። በጠቅላላው፣ እሚጎዳ እና እሚያስር ድምጽን አለማድመጥ ከተቻለ፣ በእዛ አሣሪ ድምጽ እሚመጣ ባርነትን ማኮላሻ መድሃኒት ነው። እንደእዛው፣ የዉሻዎች ጩኸት የሰማ፣ ያንን ማድመጡን በትልቅ ትጋት ሳይሆን፣ በመሰረትአዊ አረዳድ ግን ሊቀበለው ይገባ አለ። በቀረ፣ በንቅዓት ያልተመዘገበ እዉነትን አንጎል ይላመድ አለ። ይህ ደግሞ፣ የቅጽበትአዊ ሁነቶች ታሳሪ ሊያደርገን ይችል አለ። ሂወት በክፉው ይቀየር አለ። እንደ ኖላኑም ባይሆን። ይህም፣ “በሃሳብ ተይዘን፣ በጎን እሚደረጉ ነገሮችን፣ በተለየ ድምፆችን፣ ካላስተዋልን፣ በስውር ልቦናችን ያንን ነገር ፈልገናል ወይም እውር ሆነንለት ተቀብለንዋል’ እሚለውን ትልቅ ጥበብ እሚመክረን ነው። ይህ ስለ ንቅአትአዊ አኗኗር እሚናገር ነው። ሰው በንቃት ለመኖር፣ አጠገቡ እሚሰማውን ማወቅ አለበት። ካልሰማው ግን፣ ከባድ ቁምአሸልብነት ላይ ነው።
እንደእዚህ ያሉ ጠቅላላ ያልሆኑ (የሠመጡ) ሀሳብዎችን ሀበሻ ገንብቶ እሚያስረክበው በምንምን መንገድዎች ነው? በእየፊልምዎች፣ ዝርው እና ፈጠራ መፅሀፍዎች፣ ክወና ጥበብዎች፣ ዳግ-ምርምርዎች እና ሊቅአዊ ልዩልዩ ዝግጅትዎች፣ መደበኛው አኗኗር፣ ወዘተ. ስራአቸው ሌላ የሆነ ያክል ቁብ እሚሰጡ አይመስሉም። መደበኛ አኗኗርአችን ያወቅንውን ለማንጠልጠል ከመሞከር የራቀ ነው።
ዛሬ ብዙ የለን ይሆን አለ። ብዙ አልተራመድንም። የሆነው ይሁን፣ ያልተሳካልንንንኗም ጉዞ እንኳ በተከሸነ አያያዝ አቅርበን ለመጭው ትዉልድ አንድ ድጋፍ ማድረግ አለብን። የእኛ ከባዶ መነሳት እንዳለ መጪው ትዉልድ እንዲሁ፣ ከዜሮ ጀማሪ ነው። በዕዉቀቱ እንዳለው ዳዶ ድስት ልጣድ ከመንፈግ ባዶነትን ማካፈል እንዳለው፣ የታለፈው ጊዜ በደንብ ተዘግቦ በአንድ ወጥ አካልነት መወረስ ካልቻለ የከፋው ወደኋላ ማዘገም ገና አልተከፈተም እና በላጭ ትኩረት እሚሻ ጉዳይ ነው።
ኢአዋቂነት እርግማን ነው፤ ግድየለም ከዜሮ እንጀምር። አንድ ሥንል ግን፣ ቢሳካልንም ብንወድቅም፣ ምሉዕ-መረጃውን አንጠልጥለንው እንለፍ። ቀጣዩ ሥራ ከዜሮ አይነሣም። ወይም የቀደመው ከወደቀበት አያያዝ አስመሳሥሎ አይነሳም። መሀከለትዉልድአዊዋ እምንናፍቃት ስኬት አንድ እርምጃ ቀረብ ትል አለች። መቼም ቢሆን፣ ትዉልዱ ምሉዕ-መረጃ ከተተወለት፣ ከዜሮመነሳት ዘመኑን አይጨርስበትም። ዞሮ አይራገምም። ሁለት እና ሦስት በአንድ ላይ ይከማች አሉ። በአጭርጊዜ ሀቀኛ መሠረተ-ሥልጣኔ ይሆንልን አለ። ብሔርአዊው የኢአዋቂነት – ያነቀን ቅርቃርአችን – ይሰበርልን አለ። ዉጥን-ሥልጣኔን በተገቢው ማንጠልጠል፣ ሥልጣኔን ሁለንተናአዊ፣ ዘላቂ፣ ክቡር፣ ተፈታሽ፣ ማድረግ ነው፨

—————- ሐ —————–

By Binyamhailemeskel

Hey there! If you want to know about me, I just like fun, commonsense wisdom, and human love. Let us live a bright today changing tomorrow into brighter.
Regards,

3 replies on “ያልተንጠለጠለው ሥልጣኔ፡ የኢትየጵያ ሥልጣኔ ምኞት/እንቅስቃሤን ዘመንአዊ ፈር ስለመስጠት”

[…] አለ። መፍራቱ እንደ አለ፤ የአቅተንም አለ። አንደኛ ስልጣኔን ማንጠልጠል የለም። እንደ ቀረው የበሰለ አለም የሰራንውን እሚቀጥልበት […]

Like

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s