Categories
ሥነዉሳኔኛ (About Politics)

ኢትዮጵያ ሀገረሠው እንድትሆን ሀገረሠላምነቷ ያብቃ፡ ግማሽ እድሜ የፈጀው የሀገር ነቀርሣው ‘ሠላምተኛነትአችን’

“እኛ ሠላም ነው ምንፈልገው!” እሚለውን የተገደደ የሰላም-ሻጭ መንግስት የሀሰት ሰላም-ፍለጋ አመራረት ለሰለቸው ሀበሻ እሚሆን አጭር አሀድ፨

ቢንያም ኃይለመሥልቀል ኪዳኔ

ይህን የመነሻፅሑፍ በ ተአዶ. (PDF) በእዚህ ጠቅታ ያግኙ፨

ክፍል አንድ

ያልተቋረጠ ድህረ-መንግስት-ለዉጥ-ክሽፈቶች እና የመጨረሻ ደቂቃ እማይሳኩ ጭንቅንቆች
እጅግ ጉጉነት በደርግ መንግስት ላይ ነበር። ከሁሉ፣ ‘ኢትዮጵያ ትቅደም’ አላማው፣ ምርጡ ፈርማህደሩ (ሪከርድ) ነው። ያልተሳካለት መንግስት ሆኖ እንደኳተነ፣ በመሠናበቻዘመኖቹ፣ ብዙ ማሻሻያዎችን ከውኖ ለመስተካከል የመሯሯጥ ጥረቶች ነበሩት። ቢሆንም፤ ገና የቅርብ እና ያላረጀ ታሪክ፣ እራሡን ያኔ ደገመ።
ቀዳምአዊ ኃይለሥላሴ (ቀኃሥ.)ን ለመገልበጥ ደርግ በ1968 ሲሞክር፣ ቀኃሥ. እንዲሁ የመጨረሻ የማስተካከያ የለውጦችን አራወጡ። ብዙዎች የለዉጥ ጥረታቸውን ባለመቀላቀል፣ ዉድቀታቸውን አፈጠኑብአቸው። የመፍጨርጨር ለዉጦች ቀኃሥ.ን እንዲሁአላዳኑትም። ቀኃሥ.ን ደርግ አስወጣ።
ዳግመኛ፣ ያ ታሪክ ነበር ጊዜ ጠብቆ በኢትዮጵያ የታሪክ ማህደር ሳይቆይ የተደገመው። ቀኃሥ.ን የመጨረሻ ጥረቶች እንዳላዳኑት፣ እነሆ ደርግም ሠዎች መረሸኑን እና ህብረተሰብአዊት ሥርአቱን መኮምሸሹ፣ የአስራአንደኛው ሰዓት መፍጨርጨር ሆነ። ምኑም ለዉጥ፣ ሱሪባንገት ሆኖ ከመዉደቅ አላተረፈውም። በኋላ ኢህአዴግ. የተሠኘ፣ የተገንጣይዎች ማህበር፣ በተመሣሳይ ሥልጣን አባራሪነቱ ገዘፈ። በተራው ተሳክቶለት፣ ደርግን ለመትረፍ ተፍጨርጭሮ ያልተሳካለተደ ደርግን ወረሠው።
የኢትዮጵያ ታሪክ አዲስ ስነዉሳኔአዊ (ፖለቲካአዊ) ምእራፍ ያኔ ዳግ-ገለጠ። ያኔም፣ እንደቀደሙ የለውጥዎች የተወረወሩ ዕድልዎዎች፣ አዲስ ተስፋ ነበር። ንፅዉሳኔአዊ (ዲሞክራቲክ) አስተዳደር፣ ህዝብአዊ ልዑዋላዊነት፣ ከበርቴአዊ የስነምጣኔ ስርአት፣ የህግየበላይነት፣ ወዘተ. ይፋ ዶግማ ፍልስፍናዎች ሆነው ቀረቡ። ነገርግን፣ ወዲያው ርእሰብሔርአዊው (ፕሬዝደንሺያል) የሽግግር መንግስቱ እንደተጠቀለለ፣ የርእሰመንግስአዊው (ፖርላመንትአሪ) አምባገነን መንግስት ተጠነሰሠ። ይህ እንጭጭ የለዉጥዐዉድ ሙሉኛ (ፉሊ) ወደአየሩ እንደለመደው ሠመጠ። ለዉጡ የወረቀትላይ አንበሣ ሆነ። በሃያአምስት አመቶች በሁሉ-የተጠላ አምባግነናአዊ የአገዛዝ አሌድባይነቱ ኩርማን ዕድሜ-ዘመንን ላፈ። ሀገሪቷ በጎ ነገር ሳትለቅም ቀረች። ጭራሽ ክፉ ዉርሥ ዛሬ ድረሥ ተወርሦ፣ ነገር ከቀኃሥ. እና ደርግ ዘመኖች ባሽ ሆነ። በአጭሩ፤ የደርግ መነሣት፣ በተተኪ ሽብር፣ ትውልድአዊ መጥፋት፣ እና የለሽነፃነት ብሔርአዊ ክስረት ተተካ።
ለተከታታይ ሦስተኛ ጊዜ፣ ኢህአዴግ. በደምቀቢ አዲስ ህዝብአዊአመፅ ካሠበው የቆይታ ዘመን ቀደም ብሎ በደንብ ተንገጫገጨ። ብዙ የጥድፊያ ለዉጦች፣ እንደ ደርግ እና ቀኃሥ. ተመሳስለው ተከወኑ። በንቀት እና በግዴለሽነት ሲናቅ እና ከቶ ሲተው ለነበረው ወጣት ዜጋ፣ ፲ ቢሊየን ብሮች እንደ ቆሎ ግብዣ መርጨት፣ ከከፍተኛትምህርት ተቋሞች ምርጥምርጥ መምህሮችን ድንገት መንጭቆ በማዉጣት ሚኒስቴሮች ማድረግ እና የሱሪባንገት ሹመት ማንበሽበሹን እንደ ቀኃሥ. ተያያዙት። ይህን ድርጅት ከገሀድአዊ መድረክ መባረሩን እና መንጠፉን አላስቀረውም። እንደቀደሙት መንግስቶች፣ በሙስና ተዘፍቆ እንደሰነበተ በሂደቱ በግድየለሽነት የጣለው የታዳጊትውልድዎች እሚቀመስ ማጣት ችግር ከሁሉ አብልጦ የጎዳው ሆነ። ወቅትአዊ ሥህተት ሳይሆን ቀድሞ የከወነው ቂላቂል ኢምሁርአዊ ምህረትአይገቤ የጥፋት ቁልል እና የእነሱ ቀፋፊ መስተጋብር እንደሆነ አላስተዋለም። አልተጨነቀምም። ሦስተኛው፣ የሀገርአቀፍ ስልጣን ማዳን ሩጫ እንደአትሌትዎችአችን ሳይሳካ ቀረ።
ነገር ግን ከጊዜ ወደጊዜ የኢትዮጵያ መንግስትዎች አወዳደቅ እና ቀጣይ ወዲያው እሚመጡ ተስፋዎች እየቀጨጩ ነበሩ። ቀኃሥ. ሲወርድ ከፍተኛ ተስፋ እና እምነት ነበር። ደርግ ሲወርድ አነስ ያለ ቢሆንም ተስፋ እና እምነት ነበር። ኢህአዴግ. “ሲወርድ” ግን ነገር እየባሰ በመሄድ፣ መቶበመቶ አልወረደም። ጭራሽ የማስመሠል ጨዋታ እየጠነከረ ጥርስአውጥቶ፣ አርቴ ርእሰመንግስት መሾም ቀጠለ። ብሔርአዊ አመፁ፣ እንደቀደሙት ጊዜ በምሁርዎች እና በተስፈኛዎች አልተሞላም ነበር። ቢያንስ ሙሉበሙሉ። የ 2010 ዓም አመፁ፣ ከቀደሙት እህት መሰል አመፅዎች አናሽ አቅም እና ዉጤት ይዞ ተቋጨ። ያም፣ ከምኑም ሂደት እና ይዘት ይልቅ በዉጤቱ እሚሾፈተር ገሀድ ሆነ።
ፀረኢህአዴግ አመፅ፣ ዉጤቱ ዘወር ያለ ነበር። ከዉስጡ፤ ከአመፁ እና ኢህአዴግ. (ኦህዴድ = አሁን ኦዴፓ)፣ አዲስ የበቀለ ንዑሥ-ካድሬአዊ አንጃ፣ ደገኛ የነበረ ህዝብአዊ አመፅን እንደ ደርግ ጠልፎ ያዘ። አጋጣሚዎችን መጠቀም ሆነ። እንደ ደርግ፣ በኮሎኔልዎች የተመራው ይህ ለውጥ፣ ህዝብአዊ ስልጣን መዝለጉን በመካድ፣ በድርድር መንግስት-መንበሩን ወሠደ። ብዙዎች፣ መንግስትን ጠልተው በሀገርም በዉጭም የተቃወሙ፣ በመሪዎቹ ሁለት ግለሰቦች (አብይ አህመድ እና ለማ መገርሣ) እምነት በመጣል ተስፋ አኖሩ። መጋረጃው ጀርባ ግን ኢህአዴግ. እንደነበረ ሆኖ፣ ኢትዮጵያን ማስተዳደር ቀጠለ። እንደታሪክአዊው ልማድ፣ ማንም ንቁ ድርጅት እንዲያብብ ስላልተደረገ እና ህዝብአዊነት ስላልወረሠ፣ የመንግስት መዉረድ እንጂ በተገቢ መጭጊዜ መተካቱ ብዙ ተርታ እና መደዴውን (ሜዲዮክር) አላስጨነቀም። ድጋሚ፣ ህዝብ የታሪክ ስህተት ተሠርቶ፣ ልክ አምባገነን መንግስት እጅሲሠጥ፣ አመፁ ከሙሉ አብዮት አደባባይ ሳይደርስ ባልተፋፋመ ለዉጡ እረክቶ ወደመደበኛነት ተመለሠ። ፈረስ ያደርሳል እንጂ አይዋጋም፤ ተከታታይ የኢትዮጵያ አመፆችም እንዲሁ። እጅግ ያውጠነጠኑ ሰዎች እና ቡድንዎች እሚቆሰቁሱት እና እሚፈፅሙት አንድ አብዮት መሆን አልቻለም። መንግስት ያባርራሉ እንጂ፣ ህዝብአዊ መንግስት አያቋቁሙም። ዋናውን መፍትሄ መንካት በታሪክ አልታየም። ለተከታታይ የታሪክ ስህተቶች ይህ እነሆ አሁንም ቀጠለ።
በባህርዳር ትእይንተሜዳ (ስታዲየም) አንዲት ካድሬ በይፋ ለህዝብ እንደጠየቀችው፣ አብይ እንደተሾመ ሠሞን፣ ቀጣዩ ስራ የሽግግር መንግስት ማቋቋም ነው ወይንስ? ብትልም፣ ተመልካችም በሆታ እና ከፍተኛ ድምፅከልካይ የተደጋገመ አጀብ ቢያግዛትም፣ የእዚህ አመፅ ግን፣ ዕድለኛ አለመሆን ከድንገት ስልጣን ያዢዎቹ መልስ ሆኖ ቀጠለ። አመፁም እንደለመደው ሠረገ። እንደ ደርግ አደራ የወሰደው አዲሱ አንጃ ለስልጣን ፍቅር ጥያቄውን በዝምታ እና ማታለያዎች አለፈ። አዲስ ቀለም የተቀቡ የቀድሞዎቹ የኢህአዴግ. መስራች ክልልአዊ ድርጅቶች ይህን ቡድን ለአንድ ‘አዲስ ድርጅት’ ባለቤትነት አበቁት። ብልፅግና። የተሯሯጠ ከልቡ ያልተቀየረ ነገረስራ ሊቀጥል ገሀድ በመድፈር በወርዎች ልዩነት ተመስርቶ መጣ። ይህ ግን፣ ከፍተኛ የመጋረጃ ጀርባ ጥል አመጣ። ህዋሃት. አብሮ እንዳልከረመ፣ በሂደት፣ ኮሎኔል አብይ አህመድ (ዶ/ር) ህዝብአዊ እና አለምአቀፍአዊ ድጋፍ እንዳለው ስለተገነዘበ፣ ከመሀከልአቸው ወጥቶ ህዋሃት.ን ማስጠላት እና ማግሸሽን በረታበት። ይህ ቀድሞም በህዝብ የተገለበጠ ድርጅት እና አብይን ያመጣ ተቋም፣ በቀጥታ መምራት ስለእማይችል፣ ፊት ያስቀመጠው ቡድን ስለከዳው ሸሸ። በሂደት፣ ቀድሞ ህዝብ በባዶ እጅዎች መስዋእት ሆኖ ያባረረው ትህነግ. እና ታድጎ አቆይቶት የከዳው እና ዞሮ የነከሰው ብልፅግና መሀል ጦርነት ተደረሠ። የህዝብ አመፅ ግን፣ መንበር ነቅንቆ ህዝብአዊነትን ወደስልጣን መክተት አቅቶት፣ መመለሡ፣ ደግ ተምሳሌት፣ መውደቁን አሁንም ቀጥሎ፣ አጣ። ከአየር እና ከቀጥታ ዉርሥ፣ አንድ ከስልጣን መጨበጥ እና ማስተዳደር በኋላ የተወለደ ድርጅት ሁሉን ወርሦ ክፉ ታሪክ እንደአዲስ በሀገሪቷ ዳግ-ተሰየመ።
ጊዜአዊ ያልተተረጎመ አስተዳደር ብጤን እድልሰጥቶት ይህ አመፅ ተመለሠ። ወዲያው፣ ኢህአዴግ.ን እንዳባረረ በማድረግ፣ ይህ አንጃ ህዋሃት.ን ብቻ ከአስተዳደሩ በማግለል በራሱ የቆመ አስመሥሎ ፖለቲካአዊ ስእል (ፕሮፓጋንዳ) ሠራ። ብልፅግና እሚል የድርጅትን ስም (አዲስ ድርጅት አይደለም) በኢህአዴግ ሙሉ ቅርፀት እና ከምንም በላይ ሙሉ ዉርስ (አስተዳደር፣ እህት ድርጅቶች፣ የካድሬ ስርአት እና ካድሬዎች፣ ወዘተ.) ላይ ለግሉ በአዲስ እንደሠራ በማስመሠል ልዩ መሆኑን አረጋገጠ። ይህ ማታለል እንጂ፣ ዛሬም ድረስ የተሟላ አበቃቀል ያላገኘ ጥረት ነው። አንዳንዴ፣ የመንግስት ችግሮችን የብልፅግና ችግር አይደለም አመራር እስክንለውጥ ነው በማለት ሲናገሩ፣ በተዘዋዋሪ እሚያምኑት የተሟላ ድርጅት አለመሆናቸውን ነው። ይህ ሲጀመር፣ ተጨባጭ የተስፋ ጭላንጭል እንኳ አልነበረውም። ምክንያቱም፣ ይህ ድርጅት ሣይወለድ፣ የህዝብ አመፅ ጉልበቱ ፍፃሜው ንጽስነዉሳኔአዊ ጅማሮ መዉለድን ስለፈለገ፣ በእዚህ አመፅ የተነሣ ተቃዎሚዎች ተጠርተው መገናኛብዙሃኖች ነፃነት ተሰጥቷቸው፣ ነገሮች እንዲፍታቱ ተደረገ እንጂ፣ የእዚህ ድርጅት ድካም ወይም ተስፋ እነዚህን ለውጦች አላመጣም ነበር። ግን፣ የህዝብ ጥያቄ ለዉጥን ቢቆሠቁስ እና ቢያበስልም፣ በእሱ እይታ ስር የተከወነው ይህ ስራ ተገቢ ዘመንአዊነት እንኳ የያዘ መንግስትአዊ ስራ አልነበረም። የተለወጠው ለዉጥ ሁሉ በህግ የተከናወነ ሳይሆን፣ በወከባአማ የስነዉሳኔ ጥድፊያ እና ከጉራንጉር የበቀለ አፈፃፀም ያክል የተከወነ ነበር። ምንም ዝርዝር ህግ ሳይወጣ፣ ጠቅላላአዊ ድንጋጌዎችንም ሳይሠራ፣ በእዚህ ባዶ መንበር የጠለፈ ቡድን እነዚህ ጉዳዮች ለማረጋጋት በእሚል የተፈቀዱ እንደሆነ ብቻ ተነግሮ የተከወነ ለዉጥ ነበር። ይህ ለዉጥ ግን ወሮች አልቆየም። ብዙ ጥቃቶችን ወዲያው ተቀበለ።
ይህ አዲስ መንግስት መሠረትኩ ያለ ቡድን፣ አብይ አህመድን እንደግለሠብ በመደገፍ ብቻ ህዝብ ተስፋ ቢያኖርም፣ እንደ መንግስት መስራች ቡድን ግን በከፍተኛ ችግሮች ተተበተበ። አንደኛው፣ ወደጦርነት በሂደት የደረሰው የኢህአዴግ. እራስ እና አካል የነበረው ህዋሃት. ነው። አብሮ፣ ይህ ባለእድሜ ድርጅት ያመጣው እሚባለው የወኪል (ፕሮክሲ) እረብሻ እሚጠቀስ ወይም እሚያያዝ ነው። ሁለተኛው፣ የእዚህ ቡድን (በኋላ ብልፅግና የተሰኘ ቀለም የተቀባ)፣ ምንም የራሱን ነገር ያልመሠረተ በመሆኑ እና እንደ ጨርቅሠፊ የገጠመውን ወዲያውአዊ ፖለቲካአዊ ጉዳይ በመጣፍ ብቻ አዲስ ድርጅት ለመምሰል የጣረ ስለሆነ እና መንግስትአዊ አሠራሮችን የመከወን ልምድ እና ብቃት በማጣቱ ነው። አራተኛ፣ ከእዚህ አቅም እና ዕዉቀት ማጣት የተነሣ፣ እንዲሁም ከእረዥሙ የሠላምሻጭነት ዕቅድ የተነሣ፣ (ሁለተኛውን በኋላ እናያለን)፣ ህግ ማስከበር ያለመቻል እና ምናልባት ያለመፈለግ ነው። ይህ፣ እጅግ ሠፊ የአፈፃፀም ችግሩን እሚያብራራ ነው። ጭራሽ የአስፈፃሚ (ኤክሰኪውቲቭ) ክንፍ ሙሉ የመንግስት አካል በሆነበት ሀገር፣ የተራ መደበኛ ሠላም ማስከበር አለመቻል፣ ኢተጠያቂነትን ያስኬደበት ጎዳናው ነበር። ይህን ያለመፈለግ ወይም አዉቆታአዊ ቸልታ (ኢንቴንሽናል ኬርለስነስ) እሚያሰኘው በሂደቱ እና በዉጤቱ፣ ሰው ብልፅግናን በመደገፉ እና የሰላምን አስፈላጊነት እንዲረዳ እና ይህ ድርጅት ሰላምን ለመሸጥ እንዲቀናው ስላስቻለው ነው። በእረዥም ሂደት ሲታይ ይህ ተቋም ተጠቃሚ እና ወደ ቆንጣጭነት የዞረ ስለሆነ ነው።
መግቢያውን ለመቋጨት ያክል፣ ይህ ሁኔታ የተቋጨበትን ፍፃሜ ማየት ተገቢ ነው። ብልፅግና እራሱን እንደ ድርጅት አጎልብቶ ስልጣን ላይ ለመዘግየት ከፍተኛ ጥድፊያ መከወን ጀመረ። በሂደት ግን፣ ምንም የአስተዳደርአዊ መብቃት ስላላስመለከተ ከማእከልአዊ ሀገር ባመለጡ በህዋሃት. ባለስልጣኖች እንኳ ተጠያቂነት እንዳለበት እና በማላከክ እነሱን እሚያሳድዳቸው ማስተዳደር ስላቃተው እና ኢተጠያቂነትን ስለሚመኝ እንደሆነ ፖለቲካአዊ አምላጮች (ፉጂቲቭ) እንኳ ሆነው ሀቁን ግን መሰከሩበት። ቀኖች ገፍተው፣ በኃይል እርምጃ እየተጎዱ እና የመጥፋት ደረጃ ላይ የደረሱ ሆነዋል። ከክልል አምባገነንአዊ ማስተዳደር በተጨማሪ ወጪ እና ዜጋዎች ህይወት መስዋእትነት ተባርረው አሉ። በአጭር ጊዜ ይፈፀማል የተባለ ዘመቻም ከታሰበው በላይ ወስዶ ብዙዎችን ጎድቷል፤ አሁንም አፈፃጸሙ ከብዶ መቋጫው በመርዘም በሂደት ላይ ነው። አብሮም፣ በተለያዩ ስፍራዎች ከእነሱ ወገን ወይም እርዳታ አገኙ የተባሉ አካሎች የኃይል እርምጃዎችን እያስተናገዱ በመቀጣት ላይ ናቸው። ቀደም ብሎ ደግሞ፣ በተለያዩ ጊዜዎች፣ እንዲሁ አዋኪ-ሰላም ተብለው ብዙ ተቃዋሚ ዜጋዎች ታስረዋል፣ ብዙ መገናኛብዙሃንዎች በእዚሁ እንጭጭ መንግስት ተዘግተዋል። ማለትም፣ በህዝብአዊ አመፅ የመጡት የመገናኛብዙሃን እና ንፅዉሳኔአዊ ቀና እርምጃዎች በእጅግ አጭር እድሜአቸው ወዲያው ከስመዋል። የተለመደ ጠቅላላ ህግማስከበር እሚሰኝ አመክዮ መስጠት በቂነቱ ሳይታጠፍ በታሪክአችን ቀጥሎ አለ። ይህም የተከወነው አጥፊዎችን ለመቅጣት በእሚል ስነዉሳኔአዊ እርምጃዎች ነው።

ክፍል ሁለት

ተጨባጭ ሚዛን
ዛሬ፣ የብልፅግና ድርጅት እና የወለደው አብይ አህመድ፣ የያዘው አዝማሚያ ከሦስት አካባቢ አመቶች እነዚህ እንቅስቃሴዎች አንፃር ምን እሚያስመለከት ነው? ይህን መፈተሽ እና መልስ መፈለግ የእዚህ ፅሑፍ አላማ ነው። በመጨረሻ የተገኘውን መልስ፣ ከቅርብ ታሪክዎች ማወዳደር እና ተያያዥነት ካላቸው እና ምን እሚመስል ግንኙት እንደያዙም ማየት እንዲሁ።
ሀገረሠላምነት፡ ምንአልባት የመጨረሻው የኢትዮጵያ መሠናክል
ደርግ ከወደቀ ጀምሮ፣ ኢህአዴግ. መንግስትን እሚገልጥ አንድ ዋነኛ ቀና ነገር አለ። ይህም፣ ኢህአዴግ. የወደደው፣ ቢያንስ ኢህአዴግ.ን በአስጊደረጃ ያልተቃወመ ሰው ወይም ቡድን፣ ሠላም ዉሎ ማደር እሚችል ነበር። በሀገር ደረጃም፣ ኢትዮጵያ ሠላምአዊ ሀገር ሆና ቀዣቃዣዋን አፍሪቃቀንድን ያኮራች ጭምር ነበረች። የአፍሪቃቀንድ የሠላም ደሴት እስከመባል ደርሳ ነበር። ምንም መንግስትአዊ ተቃውሞ እንዳይገኝ በማጥፋት፣ በፈላጭቆራጭነት መሀከል፣ የቀረው የመጨረሻ በጎ ስጦታ፣ ይህ ኢህአዴግአዊ ሰላም ነበር። የድርጅቱ ቅድመሁኔታዎች ከተሟሉ፣ ሰጥለጥ ከተባለ፣ ሠላም ከሞላጎደል፣ አየሩ እሚሠጠው እማያስከፍል ስጦታ ነበር።
ኢህአዴግ. በአቂያቂያዩ የልማትአዊ-መንግስት ስብከት እሚከውነውን ያልተቃወመ እና ለአምባግነናው ቆፍ ያልሆነበት በሰላም እንደኖረ ሁሉ፣ የሀገሪቷን እድገት እና ቀና ለዉጦች ግን በቅን ሚዛኖች መዝኖ እሚጨነቅ ከአደባባዩ ተሠልቦ ቆየ። እንዳይችልም በብዙ አፋኝ ስልት እና ዘዴአማአዊነትዎች (ስትራቴጂስ) ተደረገ። ቢመዘን ግን፣ ፍትህ፣ የህግ የበላይነት፣ እድገት፣ ንፅዉሳኔ (ዲሚክራሲ)፣ ተጠያቂነት፣ መጪውትዉልድአዊነት፣ ከቶ ቁብ እማይሰጣቸው ምሰሦአዊ ጉዳዮች ነበሩ። የተከወኑ ቀና ምግባራትም በቆይታው፣ በተሰጣቸው የጊዜ እርዝመት፣ በእሚሰበሠቡ ድር እና ድጋፍዎች፣ ወዘተ. ከተመዘኑ እጅግ ሀገርን እሚያሳፍሩ እንጂ ምንም ቀናነትን እሚጨብጡ አይሆኑም። በመጨረሻ፣ ይህን ድርጅት የጣለውም ይህ ከፍተኛ እና መሠረትአዊ ለሀገር ያለመበጀት ሸለቆው ነበር።
አብይ አህመድ አለኝ ያለው አስተዳደር እና የተቀየረው ብልፅግና የተራመደበት አዝማሚያ ደግሞ፣ ካልሆነውየሆነው፣ ወደእዚህ ተመሳሳይ መንገድ ነው። ለሀገር ሠላምን በመቸርቸር ስልጣንን በምላሹ የመግዛት “ልዝብተኛው የአምባግነና መንገድ” ነው። ይህ ጎዳና በጥሞና መቃኘት ያለበት አምባግነናአዊ አንድ ቀለም ነው።
ሠላምሻጭነት፣ የሀገር መንግስት ስልጣንን፣ ሠላምን በመጠበቅ ብቻ መያዝ ማለት ነው። ሰላምአስከባሪ ዕዝነት የመንግስቱ ዋና እና ዐብይ ፍፃሜው ነው። ብልፅግናም እንዲሁ፣ በአንዳንድ ጉዳዮች የተነሳ የአለምአቀፍ እና መደበኛ ህዝብአዊ ወይም የተርታእናመደዴ (ሜዲዮክር) ድጋፍን በመጎንጨት፣ ሠላም የመሸጥ እና የስልጣን ቆይታን በምትኩ መሸመት፣ ሆንብሎ፣ በቸልታ ወይም ቢያንስ ካለመብቃት የተነሳ፣ መከወን ላይ ወይም ወደ ክወናው ለመግባት በቂ አዝማሚያ ላይ በመድረስ ላይ እሚገኝ ሆኗል። በሀገር እና ዉጭ ያሉ ዜጎች፣ ሰላም ማስከበርን ይህ ተቋም እንዲከውን አጥብቀው እና ደጋግመው ጠይቀዋል። በሳምባቆልፍ-፲፱ (COVID-19) ዘመን በመሠብሰብ እና ትእይንተህዝብ በመከወን ሰላም ማስከበርን መንግስት ትርፍ ስራው ይመስል እንዲሰራ ሲለምኑት ቆይተው አሉ። የብዙዎች ህይወት እና ንብረት በቀጥታ ገሀድአዊ ሀገር-ሽብሮች የተነሳ ጠፍተው አሉ። የህዝብን ስነልቦና ይህ አዲስ አንጃ እንዲሸበር ቸላ ማለቱ እንደአቀደው ወጥመድ ሆኖለት ስኬትን ማምጣት ላይ ገባ። ሁሉም በአንድድምፅ፣ ሰላምን ከእዚህ መንግስት መለመን ጀመረ። አሁንም ግን ይህ መንግስትነት በድንገት እየሮጠ የታጠቀ ተቋም፣ በኩራት ቆየ። ማድረግ እሚችለው የተዘጋጀበት የሀገር አመራር በቂ አቅም ስለሌለው፣ በተለመደ የኢህአዴግ መዋቅር እና ካድሬዎች እንደሆነ መከወን እሚችለውን ማመቻቸት ቀጠለ። ያም፣ ሰላምን ማስወደድ ይጠይቅ አለ። ሰላምን የወደደ በበዛ ጊዜ፣ ሰላም ዉድ አቅርቦት ተደርጎ፣ በብልፅግና በዘገየ መልኩ መከበር ጀመረ።
ሲደመር፣ ጠንካራ ተጨማሪ ነጥብዎች የእዚህ ድምዳሜ አጋዥ ናቸው። ሀገርአዊ እና ግልአዊ ተቋሞች ነፃነት ማግኘት አልቻሉም። በህዝብ መታፈን የመጣው የኢህአዴግ. መውደቅ ወዲአውአዊ ሽልማትዎች ነበሩት። ተቃዋሚዎች ለነፃነት ትግል ሀገርቤት መግባትአቸው እና የመገናኛብዙሀንዎች ነፃነት መደረጉ፣ እንዳየነው፣ የእዚህ ህዝብ ትግል እና ዉጤት ነው። ግን በሂደት አንዳንዴ ሊቀመንበሩ የእሱ እና ከአመት በላይ ቆይቶ የፈጠረው የድርጅቱ ስኬት መሆኑን ሲሠብክ ነበር። በሂደት ግን፣ በህዳር 29 የኢትዮጵያ ጋዜጠኛዎች ማህበር እንዳወጣው ማስታወቅያ ኢትዮጵያ የጋዜጠኛዎች መብትን ለቅፅበት ኢህአዴግ ሲወድቅ አክብራ በሂደት አፈናው እየበዛ መጥቶ አለ ሲሉ ገልጠው ነበር። የተሰሩትም ቀንደኛ እሚሰኙ ጋዜጠኛዎች እና እምቅ (ፖቴንሻል) ደግ ተፎፎካካሪዎች ተከርችመው አሉ። ሙስናዎች እና አድሎአዊነት ገሀድ ወጥተው የተረኛነት (በተራ ስልጣን ላይ መባለግ) ጉዳይን ብዙዎች አንሸራሸሩት። የተረኛነት ስነዉሳኔ በሀገርአችን ደንብ ሆኖ በዛብን በእሚል ብዙዎች ትችቶችን ሠጥተዋል። ሦስተኛ፣ የተከፋፈለ ሀገር አስፋፍቶ በመሰነጣጠቅ እና በመከፋፈል አዳዲስ ክልሎች ማበጀት እና የቀደመውን የሀገርአዊነት ጥያቄ በፀርነት በመግጠም ይህ በህዝብ ያልተመረጠ መንግስት የኢህየዴግን. አያያዝ አለህኝ ብሎ ተያይዞት አለ። ገና በእጅግ አጭር ጊዜው። አራተኛ፣ ቅፅአማአዊ (ፎርማሊቲ) እና ስነስርአትአዊ ህጎችን እሚያከብሩ እርምጃዎች እየደበዘዙ፣ በድርጅት ዉሳኔዎች አስፈፃሚው አካል በመስገግ ብዙ በመንቀሣቀሱ፤ የህግ እና ህግየበላይነት ጉዳዮች እየቀነሡ በመሄዳቸው ይህ ጥርጣሬ አሁንም ይጠነክር አለ። ግለሰብአዊ ዉሳኔዎች እና ኢተቋምአዊነቶች ቀጥለዋል። ተጠያቂነት በገሀድ የማይታይበት የሹምሽር አለማቋረጥ እየፈሠሰ ነው። ተጠያቂነት ወዲያው አፈርድሜ በልቷል። መገናኛብዙሃኖች እየተጨፈለቁ፣ ተጠያቂነትን መፈተሽ እማይቻል ተደርጓል። ቀድሞም አቅም የሌላቸው እና ፕረስሪሊዝ እንደዜና እሚያቀርቡ ያልበቁ ባለሙያዎች ባሉበት፣ ይህ ወዲያው የመጣ አወዳደቁን አከርፍቶት አለ። አምስተኛ፣ መቅደም እማይገባቸው ጥቂት ተግባሬቶች (ፕሮጀክትስ) ስም መግዣ ተደርገው በስፋት ይሰበካሉ። ድርጅቱ የፈበረከው የተግባሬት አይነት ሳይኖር፣ ኢህአዴግ ያቀደው፣ የነደፈው፣ በጀት የያዘለት፣ የጀመረው፣ ብዙ ተግባሬትዎች፣ እንደ እንጦጦ መዝናኛ፣ የቤተመንግስት አዲስ ተግባሬት፣ ወዘተ. ያሉ ጉዳይዎችን፣ በመጨረስ ብቻ የሁሉም ጀግና እንደሆነ ድርጅቱ በገሀድ ይሰብክ እና እራሱን አስገድዶ ይሸጥ ቀጥሎ አለ። ስድስተኛ፣ የጥድፊያው እና ያልተጠናው ሁኔታ መገለጫው የዉሳኔዎች መብቀል እና ወዲያው መክሰም ናቸው። ትእዛዝዎች ወዲያው ይከሽፋሉ፤ ለምሳሌ፦ አየር መንገድን ለመሸጥ ተሯሩጦ፣ ልክ ጫረታ ሲደርስ አትራፊ ስለሆነ መሸጡ ታጥፏል ማለትን ያክል ያልተዳሠሰ ቂልነት እና መሰል የአጭርተመልካችነት (ሾርትሳይትድነስ) እና የጊዜአዊ ጥድፊያ ጉዳዮች መብዛቱን አስመልካች ሌላ የለም። ያልበቃ የሀገር የመለወጥ አቅም ስላለ ለማሳመን ብቻ መጣደፉ በእዚህ ይገለጥ አለ። መቅደም እሚገባቸውን መንግስትአዊ ጉዳዮች በማመሰቃቀል መያዝ በአይነተኛነት (ቲፒካሊ) አለ። በመጨረሻ ግን፣ ለህይወት፣ ኑሮ እና ንብረት ጥፋቶች ሁሉ፣ መንግስትን እሚጠይቅ የጠፋ መሆኑ፣ መንግስት ግን ሌሎችን ለመጠየቅ እና ለማሠር ፈቃድ ማግኘቱ፤ ሲደማመሩ አንድ ፍንጭ እሚፅፉ ነጠብጣቦች ናቸው። እነዚህም ሁሉ ሲደማመሩ፣ የብልፅግና መንግስት እየሰገገ የመጣበት አንድ ዐውድ ግን እርግጥ እና ገሀድ እየሆነ እሚሳል ነው። ይህም፣ ምርጡ አቅሙ፣ ከደርግ መዉደቅ ጀምሮ እንደሆነው፣ ሰላም ለህዝቡ ማደል እየሆነ መታየት መጀመሩ ነው። ብቃት፣ ፍላጎት እና ትጉህአዊነት (ኮሚትመንት)፣ ሀቀኛነት (ኢንተግሪቲ)፣ በእዚህ ድርጅት የለም።ሠላም ማስከበር ደግሞ፣ አስፈላጊ እንዲሆን በቂ የሀገር ማሸበር ስራ ተከውኖ አለ። አለመብቃቱ እንዲሸፈን በእዚህ ትልም ተቀይሮ አለ። ሰላምን በመሸጥ መንግስትን መመስረት እና አለተጠያቂነት መቆየት።
እሚቃወምን ማሰር፣ መግደል እና ማግለል ደግሞ ለሰላም ማስከበር ቅድመሁኔታ ተደርጎ እንዲለመድ ኢህአዴግም የተወው ልማድ ስለሆነ፣ ለድርጅቱ ጠቅሞት አለ። አብሮ የቆመን መተው ያያልደገፈን በሰላም እረሻሽነት መቅጣት፣ ሀገርን መጨበጥ። ህግን ማስከበር ደግሞ ነፃነትን መግፋት ነው ብሎ ሀሰተኛ አጣብቂኝ ከፍቶ ህዝብን ማታለል ነው፤ እየሆነ እንዳለው። በመጨረሻ፣ ሰላምን ማስወደድ እና የሠላምን ዋጋ ማናር ኢላማው ሆኖ ለገሀድ እይታ እሚገለጥ ነው። ህዝብ ሠላም ሲናፍቀው፣ ሠላምን ሻጭ ሆኖ የመገለጥ በምላሹ የመንበር ኪራይ ማርዘም፣ አምባግነናአዊ የተለመደ ክህደት ነው። የተዘረዘሩት በቂ ፍንጮችዎቹ ይህን ለመገምገም አስቻይ ናቸው።
የቀረው፣ በጥቂት ትግል ፀጥ እረጭ ያለ ሀገርአዊ ዐውድ፣ በእራስሠር እሚመጣለት ስለሆነ፣ ይህ ሰላምሻጭነት አጠያያቂ አይደለም። በስኬትአማ ቀመር እየተመራ በመገለጥ ላይ ስላለ። ከእንግዲህ፣ ሰልችቶት ኢህአዴግ.ን እንዳባረረው፣ ይህ ህዝብ የሠላምን ዋጋ አለፍትአዊ አካሄድ እንዲያንረው ዳግ-ተደርጓል። ባለመከላከል፣ (ነጌቲቭ) ፈቃድ ወይም ቢያንስ ቸልታ የተነሳ፣ ሀገር ሰላም እንዲያጣ እና እንዲሸበር ሆኗል። ከእዚህ እጅግ ከፍተኛ የሰላም እረሀብ ተወልዷል። ይህ፣ የዉሸት ስነዉሳኔአዊ (ፖለቲካል) ፍላጎት የማምረት ሂደት ነው። የዉሸት ፍላጎቱ፣ ህዝቡን እና ሀገሩን፣ ሠላም ገዢ አድርጎ እሚያስጠብቅ ነው። የሀገርን ችግር በሰላም ዙሪያ የመጠፍነግ እና የማሰር የኢትዮጵያ የቅርብጊዜ እርግማኗ ቅጥያው ነው። አስተዳደርን በላቀ ጥራት ላለመለካት ሚዛን እሚያበላሽ የረዥምጊዜ ዕቅድ የያዘ መርዝአማ ሴራ። ዋናው የህዝብ ጥያቄ ይህ ሰላም እስኪሆን መንግስት ከፍተኛ ገለልተኛነትን እና ኢመደበኛአዊነትን ሲከውን ሰንብቷል። ከአካሄዱ በራሱ ጊዜ ደግሞ፣ ጥቂት የመጨቅጨቅን ነገር በማሳበቅ ጭምር፣ የሰላም አስከባሪነት ጉዳዩን ብቸኛ ጉዳዬ ብሎ መከወን በይፋ ጀምሯል።
ህዝብ፣ መደበኛ ሠላም የጠበቀለትን ኢህአዴግ.ን ቢያባርርም፣ መልሶ ግን፣ በተጨባጭ ሚዛን ሲታይ፣ የኋሊት ተጉዞ፣ ሠላም ሸመታ ወደ ስነዉሳኔ ገበያው እንዲወጣ ሂደትበሂደት ተጋብዟል። በሂደት፣ በስፋት እሚፈልገው አስተዳደርአዊ ሸቀጥ፣ ሰላም እና ሰላም ብቻ መሆኑን ብልፅግና በእዚህ ስራው አረጋግጧል። ብዙዎች ለሰላም እርሀብ አሳይተው በመንጫጫት ላይ እንዲገኙ ተደርጓል።
ይህ ለአየር-ወለዱ ብልፅግና ከፍተኛ እድል ነው። አብይ አህመድ እንስቶችን በትልቅ ሹመትዎች ከመሰብሰብ እና ማበረታታት በዘለለ፣ አስደሣች አንዳንድ እንቅስቃሴዎችን ከመጨረስ ወይም መጀመር በዘለለ፣ መቅደም እሚገባቸውን ተገቢ ነጥቦችን ግን ቸላ በማለት እንደቆየ ወደ ለየለት ሰላምሻጭነት ጎራ ተቀላቅሏል። ሠላምን ለሀገር በመስጠት፣ ትንሿን ስነዉሳኔአዊ (ፖለቲካል) ስፍራ ማጨናነቅ ደግሞ፣ የሀገር ችግርን መፍታት አይደለም። ቀድሞም፣ ሀገርን ሰላም በማድረግ፣ ኢህአዴግ. ያልተሳካ ፈርማህደር (ሪከርድ) የተወው ከሦስት አመቶች ባነሰ ታሪክ ዉስጥ ነበር።
የሠላም ማረጋገጥ፣ የሀገር መረጋገጥ አይደለም። ሰላም በተፈጥሮ እሚገኝ መሰረትአዊ ነባር (ዲፎልት) ጉዳይ ብቻ ነው። ሠው ሲወለድ ሠላም አብሮት በተፈጥሮ የተቸረው አምላክአዊ ስጦታው ነው። የመንግስት እሱን መጠበቅ አንዱ እጅግ የድሮው መነሻ ነጥቡ እንጂ ዐብይ ድርጅትአዊ ጥያቄው አይደለም። ሰላምን መሻት፣ በቸልታ፣ ብቁ ባለመሆን ወይም በአውቆታ ሆንተብሎ እሚፈጠር ብሔርአዊ-ጉድጓድ መሆን የለበትም። ሠላምን ሸምቶ መግባት፣ ለህዝብ መክሰር እሚሆነው ለእዚህ ነው። ሰላሙ አብሮት ያለ፣ ለስነዉሳኔአዊ ጥቅም ተነጥቆ እሚፈበረክለት እንጂ፣ የሀገር የፍፃሜ ግብ አይደለም። ዳሩ፣ ሰላም ላይ ማተኮሩ፣ ስለሰላም ወይም ሰላም መጥፋት በእየመገናኛብዙሃኑ መስበኩ፣ በሂደት ስልጣንን ብቻ ከማለም እማይዛነፍ ትልቅ ቀውስነት ነው።


የእምንክድአቸው መንገድዎች እና አሁንም ብሔርአዊ ችግርዎችአችን እና መፍትሄዎችአችን
አማራጩ፣ ያልተኬደበት፣ ዛሬም በመካድ ላይ ያለው ገሃድ ግን አለ። ታዲያ ሰላም ሻጭነት እና ገዢነት የውሸት ለስልጣን እምንፈጥረው ችግር እና መፍትሄ ከሆነ፣ ሀቀኛ ችግርአችን እና መፍትሄዎችአችን ምንምን ናቸው?
የኢትዮጵያ ችግር እና መፍትሄዎችን እሚመለከተው ሀቅ ብዙ ነጋሪ አያሻም። ብዙ አያከራክርም። ሁሉም ደህና ሀገር ድሀ ነበር፤ እስከእሚያድግ ድረስ። በዘመንዎች ስልጣኔ ተሞክሮዎችን አምጥቶ ለሉል በሙሉ ነፃ እዉቀት ብርሀን ነው። ኢትዮጵያ እንደ ዘመንአዊ እንግሊዝ መነሻ ዘመን የህግየበላይነት ፅንሰሀሳብን መፍጠር እና መመራመር አይጠበቅባትም። የአሜሪካን የህዋአዊ ምርጫ (ዩንቨርሳል ሰፍሬጅ) ይጀመር፣ ማንማን ያካትት ይሆን ብላ አትጨነቅም። ተጠያቂ እና ዕዉቀት-መር አመራር እምታበለፅግ አይደለም። ለመጭትዉልድ አልሞ ብሔርአዊ ትጋትን መንከባከቡን እምትፈጥረው ጉዳይ ነው። በአጭሩ፣ የድሀድሀነቷ ያልተቋረጠው ኋላቀር ሀገር የዘመነ መንግስት እና ማህበረሰብ አገነባብ ችግሮቿም መፍትሄዎቿም ናቸው፤ ምንም ጠቅላላ አገላለፅ ቢሆን።
ከምንም ቀድሞ ግን የባህል ቅያሬ አስፈላጊ ነው። እሚገነባ ሀገር የትትረት እና የመለወጥ-ትጋትአማአዊነት (ኮሚትመንት)፣ መቻቻል፣ ነፃአመለካከት ማበረታታት፣ ሀገርአዊነት እና ብሔርአዊነት ስነልቦና፣ አፍሪቃአዊነት፣ ዘመንአዊ ሀልዮታ (አቲትዩድስ)፣ ሰብአዊነት (=ህፃናት፣ አረጋአዊያን፣ ባእድአዊያን (ኤሊየንስ) ወዘተ. መቀበል፣ መከባበር እና ያለችግር መኖር፣ መሠል ባህሪዎችን መደበኛ ማድረግ)፣ ግልፀኝነት፣ ታታሪነት፣ የሀገርባህል አዘማኝነት እና አጠንካሪነት፣ የመማርላይ እምነትን፣ በጋራጉዳይዎች ፍፁም አንድነት፣ ወዘተ. እጅግ በስፋት መጥለቅለቅ ያለብአቸው የባህል መሠረትዎች ናቸው። በተለያዩ ይፋአዊ መሳሪያዎች (ፐብሊክ ቱልስ)፣ ስርአተትምህርት፣ አስተዳደር፣ ትልምአግጣጫዎች (ፖሊሲስ)፣ ህግዎች እና አተገባበርዎች፣ ወዘተ. እነእዚህ በአዲስትዉልድ መሥረፅ እና የተንጣለለ ባህልአዊ መብቃት ቀድሞአስፈላጊው ነው። ይህ፣ ለስልጣኔ ደግ ወለል ይሆነው አለ።
በመቀጠል፣ ወደ ስነዉሳኔአዊ፣ ስነምጣኔአዊ፣ ሽልፍኖትአዊ (ቴክኖሎጂካል) ወዘተ. ጉዳይዎች መመለስ ተገቢ ነው። የድሀድህነት ጉዳይዎችን፣ በአስቸኳይ እና ቁርጥ አሠራርዎች፣ በተለይ በቀላሉ ተጠያቂነት በማኖር የደርግን ለህዝብአዊነት-የአመራር-ተጠያቂነት እማይዛነፍ ስርአት ማምጣቱ በቂ መሳይ ነው። የካድሬ ፈላጭቆራጭነት እና ድርጅትአዊ ልዑዋላዊነት የህግየበላይነትን ስለጨፈለቁ፣ ከድህነት ለመላቀቅ ጉድጓድ ሆኖ አለ። በሂደት እጅግ ተያያዥ እና በጠቅላላው የተቀነጨቡትን ጉዳይዎቹን ማስተካከል የማደግ ጉዳይን እሚያስተካክሉ ናቸው።
ብሄርአዊ አለመታደሉ ግን እንደቀጠለ ነው። የቱም መንግስት ስልጣኔን ሳይጨነቅበት፤ ሰላም በመሸጥ ብቻ በኢትዮጵያ ዛሬ ማስተዳደር ይችል አለ። የታሪክአዊ ተጠያቂነት ቢቀጥልም፣ ሠላም ለመሸጥ የቆረጠ ግን ታሪክን አክባሪ አይደለም። ህዝብን አያስተዳድርም፤ ብቻ ጊዜአዊ ስልጣኑን ያስጠብቀው አለ። ህዝቡ እንዲተዳደር የአመለካከት እና ሀልዮታ (አቲትዩድ) ሰፊ መዘመን እና መንቃት ይፈልጋል። ይህ፣ ከምንም እሚቀድመው ገሀድ ስራ ተቆልሎ እንዳለ ዛሬም አለ። የጠሩ ትምህርቶችን፣ ህዝብአዊ የገሃድ (አደባባይ) የጋራ ዐዉዶችን፣ ሀገርአዊ ስነምግባር እና ስነልቦናን ወዘተ. በመፍጠር፣ የአንድነት እና ዘመንአዊነት ትግልን አስቀድሞ መረባረብ ይጠይቃል። የመንግስት ከፍተኛው ጣልቃገብነት ከሰላም መሻሻጡ ጨዋታ በላይ፣ የስነምግባር እና ስነልቦና ዘርፈብዙ ስብከት መሆን ይገባው አለ።
ሁለተኛ፣ የህግየበላይነት እና ህግአዊነትን መረባረብ ያስፈልጋል። ዉሳኔዎችን፣ ተቋሞችን፣ እርምጃዎችን፣ በህጎች እና እጅግ ሰፊ ዝርዝር ደንቦች የመምራት እንቅስቃሴዎችን ለህዝቡ ማስመልከት ትልቅ ቀዳሚነት ሊሰጠው እሚገባ ጉዳይ ነው። ይህን ሠላምሻጮች አይጨነቁበትም። ቢጨነቁ ደግሞ ደግ መዉጫ አላቸው። በህግ-መምራት (ሩል ባይ ሎው) እንጂ የህግየበላይነት (ሩል ኦፍ ሎው) አያስጨንቅአቸውም። ግን፣ ያ እጅግ ሀቀኛአዊነት (ኢንተግሪቲ) ፈላጊ እጅግ ወለል ነው።
ሦስተኛ፣ ሀገርን መሰብሰብ እንጂ በመከፋፈል ማዉደም ከሁሉ ኢተፈላጊው ጉዳይ ነው። የግለሰቦችን ጉዳይ በማግዘፍ፣ አሃድን በዜግነት ጉዳዮች መጠንሠስ እጅግ ወለልአዊ የኢትዮጵያ ጉዳይ ነው። የህዝቦች መሰባጠርን፣ በሠፊው ትርጉም ደረጃ ተቀብሎ መጓዝ ግድ ነው። አመክዮው፣ እነሱን በስነውሳኔአዊ አውድ መሰነጣጠሩ ከሰላምሻጭነት ለመላተም እንጂ ለሀገርአዊነት ረብየለሽ ስለሆነ ነው። የሴራ ጓደኝነት ከአንድ ብሔረሰብ እና ሌላዎችም ማብዛት ለስልጣን ማሰቡን ብቻ አስመልካቹ ነው። ማንም መገለል እና ጠላት መደረግ የለበትም። እንኳን በኢትዮጵያ ያለ ዉድ ዜጋ እንግዳ እንኳ መገለል የሌለበት ነው። ያ ግን የስርአት ካለመኖር የተነሳ የጎደለ ነው። ስርአትን በአልንአቸው አንድነት፣ ህግየበላይነት እና ሀገርአዊነት ከመመስረት እሚመዘዝ ብቻ ነው። ለሥልጣኑ ግብግብ እሚያያዝ ተቋም ያንን አይጨነቅበትም። በእዚህ የተነሣ ክፍፍል ካለ፣ አደጋ ወይም የአደጋ የቤትስራ በዉሸት ይፈበረካል ማለት ነው። ይህን ለማከም ብቻ፣ መንግስት እራሱን የአስፈላጊነቱን ምስል ከስቶ እሚያገዝፍ፣ እሚያንቆለጳጵሥ፣ እሚኩራራ ይሆን አለ። ሀገርን በተለይ ህዝብን፣ አንድ አድርጎ በመቀበል፣ የዘር ልዩነት የሀገር ምስረታን እንደማይሸርፍ አድርጎ፣ ስነዉሳኔን መቅረፅ እጅግ ተቀዳሚ እሚሆን ሥራ ነው።
አራተኛ፣ ምንም ይሁን ምን፣ መገናኛብዙሃኖችን መደገፍ፣ ማስተማር፣ ለእነሱ ማዳላት ያስፈልጋል። ገና ያልተመሠረቱ ክፍለማህበረሰብ ናቸው። ቢያጠፉ እንኳ ከአንዴ ቅጣት፣ የማስተማር እና ማብቃት እንጂ፣ ርህራሄየለሽ ቅጣት የመስጠቱ ነገር፣ ተስፋ እሚያስመለክት አይሆንም። ከፍተኛ ትእግስት፣ ተቋምአዊ፣ ህግአዊ፣ እና መሰል እገዛዎችን ገና በቅጡ ሳይመሠረቱ፣ ወደ ደምሳሽ ባህል ሮጦ መመለሱ ከፍተኛ የሰላምሻጭነት እርምጃ ነው።
አምስተኛ፣ ከፍተኛ የስነምግባር እና ስራ እደል መፍጠር ወዲያውአዊ ፍላጎትን በከፍተኛ ጥንቃቄ፣ ለመከወን ያስፈልግ አለ። ይህ ሳይደረግ፣ ከፍተኛ የታዳጊዎች መምጣት እየተደራረበ ስለሚገኝ፣ ይህም በተገቢ ሳይሰለጥን እሚመጣ ትዉልድ ስለሆነ፣ ያለውን ችግር ወደ ማጥ እሚሽጥ ስለሆነ፣ የበዛ ሥህተትን በእዚህ ከመድገም አስቀድሞ በቶሎ ቀና ጉዳይዎችን መከወን እሚገባ ነው።
ስድስተኛ፣ የቀድሞ ጠሚ. ኃይለማሪያም ደሳለኝ፣ አቃተኝ-ስልጣንበቃኝ ከማለታቸው ቀድሞ ብዙ የተለመደ የአስራአንደኛሠዓት እሩጫን ተንደፋድፈው ነበር። የመጨረሻው መፈራገጣቸው ግን፣ ከትልልቅ የትምህርት ተቋሞች፣ መሪ ምሁሮችን ሠባስቦ ስልጣን መመደብ ኩርማን ፍፃሜው ነበር። ያ ዘግይቶ የተደረገ ስለነበር ሳይሳካ፣ ረብየለሽ እንደሆነ ቀረ። የወጡት ምሁሮች ከአስተማሪነትም እንደተፋቱ የቀሩ እና ምንም ማገልገል ያልቻሉ ሆነው ባከኑ። ችግሩ፣ የተቆለለ የአስርታትዎች (ዲኬድስ) ችግር ነበር። ሰላም በመቸርቸር መንግስት ጀግኖ ሀገር ሳያቀና በመኖሩ፣ የመርገጥ አቅሙ ሲበለጥ የተከሠተ ገሀድ ነበር። ያ ትንሽ የዘገየ ጉዳዩ፣ ከመቅፅበት በእሚደረግ ምሁርአዊ ሹመት እሚስተካከል አልነበረም። ድህረጊዜአዊነት (ሪትሮአክቲቪቲ) እሚፈልግ መፍትሄ በማንም ሊወለድ አይችልም። ዛሬ፣ በተተካው መንግስትም፣ ያ ስህተት ግን አለ። መሠረትን ከመገንባት፣ ቦዝኖ በመፈንገያ ወቅት መቻኮል በአየንአቸው ተከታታይ የቅርብ ሀገርአዊ ታሪክዎች ያለማቋረጥ ያለ የነበረው ለእዚህ ነው – አሁንም ብቅብሎ እየተጓዘ ባለው ችግር የተነሣ – ሰላምሻጭነት።
በአጭሩ ቢገለፅ፣ ይህ፣ የወቅትአዊ ኢትዮጵያ ከሁሉ ትልቁ ችግር ነው። ስልጣን ለሠላሳ አመቶች እና ዛሬ ጭምር እሚሰጠው ለመንደር-በቀል ካድሬዎች ብቻ ነው። የመማር ጥያቄ ከህዝብ ብዙ ያልተቋረጠ ትችቶችን ሲያመጣ፣ የይስሙላ ትምህርትአዊ ማእረጎች ተሸክሞ ለስልጣን መቅረቡ አሁንም ምርጡ የማታለያ ጥረት ሆኖ፣ ሀገር እያታለለ ነው። ለሰላምሻጭ ያ ዴንታአይሰጥም። የተማረ፣ ሰላምን እንደ ተፈጥሮ አድርጎ ፍትህን፣ እድገትን፣ እኩልነትን፣ ህግን፣ ወዘተ. ያበለፅግ አለ። ያ ደግሞ ለመስረቅ እና ላለመጠየቅ እሚመች አይደለም። ሰላምሻጭ ብቃቱም ፍላጎቱም በእዚህ ሀገርገንቢ መንገድ አይደለም።
ካድሬዎች ከመንደር ተነስተው፣ የስነዉሳኔ መሰላል በመረጋገጥ ጫፍ ድረስ ይደርሳሉ። ሰላምን ለማስጠበቅ አይተኙም። ያ ደግሞ መጠፍነግ ነው። ተፈቅዶልአቸው፣ በመርገጥ ሰላም ሲያስከብሩ፣ መንግስት የሰራውን ድርጅት እንጂ ህዝብ እና የነገውን ተፈላጊ ሀገር አያገለግሉትም። መንግስት፣ ድርጅት እና አስተዳደር ለሀቀኛ ምሁሮች የተከፈተ አልሆነም። ከእዚህ የተነሳ፣ ተቋምዎች እና ስነስርአትዎች አሸልበው፣ ረጋጭ አስፈፃሚአካል መንግስትን ሙሉበሙሉ የያዘ ሆኖ አለ። በሌላ ቋንቋ፣ ያ አምባግነና ነው። ስልቱ፣ ሰላምሻጭነት። በተለይ፣ ህግ አዉጭ እና ተርጓሚ ሽባ በሆነበት የአስተዳደር ድባብ፣ ህግአስፈፃሚው በመንደር-በቀል ካድሬዎች ብቻ በመገጥገጡ፣ ከስልጣን ቆይታ ትግል በቀር ምንም እማይሻገር አስተዳደር እንዲተካካ ያደረገው አመክዮ እንደሆነ አለ። መታወቅ ያለበት ትልቅ ነጥብ ግን፣ ትልልቅ አስተዳደርአዊ ስፍራዎች ሳይሆኑ፣ ከስር እሚገኙት ከሁሉ ንዑስ አስተዳደሮችን በእውቀት መምራት እሚያስፈልግ ሆኖ ጭራሽ አለመታየቱ ነው። ድርጅትአዊ አሰራር ላይ ቢሆንም፣ ቢያንስ የቻይና ድርጅትአዊ አሰራር ላይ እሚገኘው እና እሚያስመካቸው፣ የገዳ መሰል የአስገዳጅ የልምድ መሰላልነትን የመጠቀም አሰራር እንኳ አለመኖሩ ትልቅ ክፍተት ነው። አሁንም፣ እነ አንድአርጋቸው ፅጌ እንደእሚከራከሩት፣ ከጀርባው በምሁሮች እሚመራ ድርጅት መንግስትን የመምራቱ ነገር፣ ይህች ሀገር እሚበጃት እጅግ ቁልፍ ነጥቧ ነው። ይህም፣ በከፍተኛ ደረጃ ችላ የተባለ ነው። ዛሬም፣ የኢህአዴግ. አስፈፃሚ ግለሰቦች በእየስፍራው በካድሬ ፍልስፍና ብቻ ሀገሪቷን በበላይነት እንደተቆጣጠሩ አሉ። በህዝብ የመመረጥ እና የመምራት በህዝብ ከስልጣን የመጠራት እና የመዉረድ፣ በፍትህ አካሎች የመጠየቅ እዉነትዎች፣ በብዙ ሺህ አመት ታሪክአችን እንደናፈቁን፣ በከፍተኛ (የባሰ) የመረሣት ደረጃ ላይ እሚገኙ ሆነዋል። ንፅዉሳኔን (ዴሞክራሲ) እሚጠይቅ እየደበዘዘ፣ ሠላምን እንደናፈቀ ተደርጎ እሚነገረው ትውልድ በዝቶ አለ። ብልፅግና ከእዚህ አካሄድ፣ ዝንፍ ሳይል መቆየቱ፣ የኢህአዴግ. ካድሬዎች ትከሻ ላይ መንጠልጠሉ፣ ኢገለልተኛነት እማያውቁ የመገናኛብዙሀንዎችን ጨባጭ መሆኑ፣ ሰነጣጣቂ እና አብድነት አምጭ አለመሆኑ፣ ወጥነት እና ሀቀኛአዊነት (ኢንተግሪቲ) አለማስመልከቱ እና ዛሬ አንድ እንሁን ነገ ሰላም ላስከብር ልሰር ላጥፋችሁ አይነት ጨዋታዎቹ መብዛትአቸው፣ ወዘተ. ከላይ የተመለከትንው ሁሉ አዲስ ያለመሆኑ እና ከምንም የከፋው ሰላም ለመሸጥ የማተኮሩን ጉዳይ አጉዪዎቹ ናቸው። ሰላም ማስከበር ብቻ በእሚያቁ ደጀን በእሚሆኑለት ካድሬዎቹ ላይ የሚተኛ መንግስት፣ አላማው በነሱ ሰላምን ሲቸረችር መኖር ብቻ ነው። ተቋሞች አያቀኑም፣ ህግ አያስከብሩም። አይጠየቁም። ሳይመረጡ እና ያለድርጅትአዊ ወጥ ደንብም እንደ ዓሣ በሀገሩ እየተመደቡ ይሽከረከር አሉ። እሚጨበጥ እና እሚመረመር ቡድን በአንድ ሥፍራ አይገኝም። ይፋ እና በህዝብ የእሚመረጥ አስተዳደርን ቦርቡረው እሚፈስሡ የድርጅት ተላላኪ እንጂ የህዝብ ያልሆኑ አስተዳዳሪዎች ብቻ ናቸው። ሰላምን ግን አለመተኛት ሆነው ይጠብቁልን አለ። በመጨረሻ፣ አንድ ትዉልድ አሳልፈው እነሱ በልፅገው፣ የገቡበት ይጠፋል አብዮት ወይም ቢያንስ አመፅ መንግስቱን ያፈርሰዋል። ይህን፣ ሰላምሻጭአዊ የካድሬ መንግስት፣ ኢትዮጵያ ቅርብ ሆነው ከተደረደሩ ስህተቶቿ ተምራም፣ ከነቢብ (ቲዎሪ) ጥናቶች ተምራም፤ በባሌምበቦሌም፤ ፈፅማ ልትፋታው እሚገባት ጉዳይ እንደሆነ አለ።
እነዚህ እንደ አባይን በጭልፋ እና በነሲብ ጠቋሚ አርእስቶች፣ የስልጣኑ መንግስት ማሟላት እሚገባቸው መነሻዎች ብቻ ናቸው። ገና በሂደት እልፍ ሰፊ እና ጥልቅ ጉዳይዎች በእራስሠር (አውቶማቲክአሊ) እሚገለጡ ችግርዎች እና መፍትሄዎች አሉብን። ግን፣ ሀቀኛው የተሰወረው ፍላጎት እኒህን ቢፈልግአቸውም ግን፣ አሁን አልተገኙም። የመገኘት ፍንጭ አላሳዩም። እነዚህን በሀሰተኛ የሰላም ረሀብ መቅበር ግን በተሳካለት አዝማሚያ ላይ የደረሰ ጥረት እየከወነው ያለ ሆኗል። በሠላም አስከባሪነት ደረጃ፣ ወደ ኢትየጵያ መንግስትነት መምጣት፣ ከፍተኛ የታሪክ ዳግ-ስህተት፣ የሀገር ዉርደት እና ቆሻሻ አዙሪት ነው። ይህም፣ ብሄርአዊ አዚም፣ ከፍተኛ ተጠይ ፍፃሜ እሚገጥመው፣ መጨረሻው የታወቀ ዉድቀት ሲሆን፣ ዛሬም ግን እንደሀገር እያኮበኮብንለት ያለው እዉነት ሆኖ እየጠለለ ያለ ሀቅ ነው።


መቋጫ
ከደርግ መዉደቅ ወዲህ፣ ሰላም በማስከበር እሚያተኩሩ መንግስቶች በኢትዮጵያ ቆይተዋል። ብልፅግናም፣ ሰላምን ማስከበር ትልቁ አጀንዳ እንዲሆን ገና ከመምጣቱ አድርጓል። የሰዎችን ሰላም ከሰዎች ወስዶ መልሶ መሸጥ ግን፣ የለዘዘ የአምባግነና አይነት ነው። የተለመደ የኢህአዴግ.ም መዉደቅ መሠረቱ የነበረ ነው። ኢትዮጵያ ሰላም እምትሻ ሀገር አይዘለችም። ሰላም የዉሸት ስነዉሳኔአዊ ሸቀጧ ነው። በኋላቀርነት እእድትዳክር ስግብግብ መንግስት መስራችዎቿ እሚያያዙት ቀንደኛ ትኬትአቸው ነው። ዕድል አለው። የበቃ ትዉልድ ካለመኖሩ በዘለለ የደከመ እና የተከፋፈለ የህዝብ ማንነት ለእዚህ ኢላማ በመመረቱም፣ ይህን ሰላምሻጭነት መታገሉ የበለጠ ቆፍ ገጥሞት አለ። ከሁሉ ገሀድ ወይም ትንታኔአዊ ጥቆማ፣ ሰግጎ እሚገለጥልን ሰላምመሸጥን የመፈናጠጡ ጉዳይ የበለጠ እንደሆነ ነው።
መሠረትአዊ ለዉጥዎች ሀገርን አንፆ ለቀጣይ ዋና ስራው አበጅተው ማቆም በሚገባቸው ትዉልድ እና ወቅት፣ እነዚህ መሠረትዎችን መጠንሰሥ ግን በግፍ ግድየለሽነት ቸላ ተብለው አሉ። የአንድ ግለሰብ ጉልበት፣ የዜግነት በላጭ ዋጋውም እንደተረሳ እንዲቀጥል እየተሰራ ይገኝ አለ። ሰብአዊነትን በዘመነ ዓለም እና በብዙ ጀብድ እና ታሪክ መሀከል ተገኝተን የእምናረክስ ሆነን አለን። ይህ፣ አዋጪነቱ፣ ለአምባግነና እንጂ ለህዝብ አይደለም። እጅግ ድሃ በሆነች ሀገር፣ ዛሬም፣ የሀገር አስተዳደር ከመንደር ካድሬነት አሽከርነት ተነስተው ጫፍ በሚሰበሰቡ ካድሬዎች እሚከወን እንደሆነ አለ። በእዛ ሂሣብ፣ የሚገኘው እሚወራረድ ዉጤት፣ ሲበዛ ሰላምሻጭነት ሲከረፋ ሙሉ አምባገነንነት ነው። ምንም የሀገር ሀቀኛ ግንባታ ጭላንጭል የለበትም። ሀገራችን ያየችውን ቅድመ-ብልፅግና መፈንቅለ ግለሰብዎችን ወይም የካድሬዎችን አንጃ ግልበጣ ያመጣው፣ ኢህአዴግ.ን ያበሣጨው እና እጅ ያስሠጠው የህዝብ አመፅ እንጂ ይህ በኋላ ዘግይቶ ብልፅግና እያለ እራሱን የሠየመ ቡድን አልነበረም። የእዚህ ድርጅት አዝማሚያ፣ ሰላምን በማስከበር ስልጣን ላይ መክረም እንጂ፣ የተመለከትናቸውን መቅደም እሚገባቸው ጉዳዮች ማስቀደም አይደለም።
ይህን ዝብ-አካሄድ በመከወን እሚገኘው አየር-ወለዱ ብልፅግና ዛሬም፣ የኢትዮጵያ ክፉ ታሪክ ዳግ-እንዲመጣ በመሯሯጥ ላይ ያለ ነው። ዛሬም በኢህአዴግ. አመራርዎች ከታች እስከ ላይ ተሞልቶ እሚሰራ ከሆነ፣ ኢህኣደግ. ሲጨመቅ ሰላምሻጭ አምባገነን ከነበረ፣ አሁንም አዲስ ነገር የለም። በቀረ፣ የተለመደው ከፊል ዉጤትአማ ህዝብአዊ አመፆችን መጥለፍ ካሎነ በቀረ። ይህም አዲስ የመሬት ስርወለል እንጂ፣ በራሱ አዲስ እማይሆን ነው። አዲሡ እና ያረጀው የሀገር ተስፋ ምንም ያልተኬደበት ነው።
መንገዱን በማቆሸሽ፣ ብልፅግና መቀጠሉ እሚያበሳጭ እንደሆነው ሁሉ፣ አሁንም ሀቁ አንድ ነው። የሰላም ሀገር መሆን አይገባንም። የሰላም ሀገር ከሆንን፣ ቀጣይዎቹ ጥያቄዎች የፍትህ፣ ዘመንአዊነት፣ እንደማህበረሰብ የመጠንከር እና የመብቃት ተጠያቂነት፣ እኩልነት፣ ወዘተ. ያልንአቸው የመሰልጠን ነጥብዎች ናቸው። ሰላም ያጣ ግን፣ ሰላም በመሸመት ይጠመድ አለ። ይህን የመሳሠሉ የስልጣኔ ጉዳይዎችን እሚያስብበት ፋታ የለውም። ንፁህ ዉሎአዳር አላገኘም። መሠንበትን አላረጋገጠም። ሀገሩ እንደምታሳድረው አላወቀም። የመኖሩ የህይወት ዋስትናው የለም። የሀገር መገንባት እና መላቅ ጥያቄውን በተሳካ ሁኔታ ይህ የሰላም መታወክ ይሰልብበት አለ። በምትኩ፣ መንግስትን የስልጣን ሾፋሪነቱን እድል ይተውለት አለ። ያልከበደ ወጪ በማውጣት፣ በካድሬዎች በመንጠላጠል እስከ ጉራንጉሩ የጠበቀ ቁጥጥር ይደረግ አለ። የህዝብ መስሪያቤትዎች፣ ሰላም አገልግሎትዎች፣ ሙያ ተቋምዎች፣ ገለልተኛ አካልዎች፣ እንዲሁም የፍተሻ እና ማመዛዘን (ቼክ ኤንድ ባላንስ) እንዲሁም ንፅ ስነስርዓቶች መሠረት የሆኑትን የፍትህ እና ህግሠሪ መንግስተደአዊ አቋቋሚዎች ጭምር በእነእዚህ የድርጅት አገልጋይዎች መምራት አሽከር ለማድረግ አስፈላጊው ቅድመሁኔታ ነው። ሁለተኛው በይፋ ትልምአግጣጫዎች (ፖሊሲስ) ህግዎች እና አፈፃፀምዎችም እኒህን የመንግስት ክንፍዎች የአስፈፃሚው አሽከር የማድረግ ስልትአዊ እና ገሀድ መመዘኛ እሚያቁለጨልጨው ክወናው አለ። ብቻ፣ ከመንደር በቅሎ ሰላም በማስጠበቅ ያም መንደርን በድርጅት ትእዛዝዎች መሰረት ጠፍንጎ መያዝ እና ተቃውሞ ማድረቅ ነው እስከ ጫፍ ተጠያቂነት ሳይኖር የማደግ ዕድል ለካድሬዎች መኖሩ እና ልዩልዩ ኢህግአዊ እና ኢስነምግባርአዊ ጥቅምዎችን ማግበስበሡ፣ ለሀገር ከመስራት ለአምባገነኑ የማገልገሉን ኢህሊናአዊ ጉዳይ እሚያጠነክርለት ነው። በተጠፈነገ የካድሬ ድር፣ ጫፍ ድረስ ሀገር ከመተንፈስ በቀር እንዳይጠይቅ ተደርጎ ሀገር መገንቢያው ስልጣን አለተጠያቂ ከህዝብ ይሰወር አለ። በእዚያ መጋረጃ ጀርባ ሆኖ መንግስት ያሻውን ማድረግ እንደእሚችል የቀደመው ታሪክ ምስክር ሆኖ፣ ዛሬም ያለው የካድሬ-ብቻ መንግስትአዊ ስነስርኣተ ወሳኝ የሀገር ግንባታ ዋልታዎችን ከቁብ ሳይቆጥር ገሀድ አያያዙ ይፋ ሆኖአለ። ያም፣ ሰላምን መሸጡ አዋጪው መንገድ እንደሆነ መገንዘቡ፣ ሌላ አለማወቁ ወይም አለመቻሉ ወይም ቢበዛ አለመድፈሩ አለ።
የእዚህ አጭር መነሻ ፅሑፍ አላማው፣ ፖለቲከኞችአችን ይህን ቁማር ያቁታል ብሎ መከራከር ነበር። ስላወቁት፣ በታሪካችንም መንገዱን ይህ ሰላምሻጭነት አበጅቶ ስለሄደ፣ የተተካውም ከአብራኩ የወጣ ድርጅት ስለሆነ፣ በተጨባጭ ነገርዎች በአጭር ጊዜም ቢሆን እየጠለሉ ያሉት ሀገርን ለሰላምሽያጭ እና ሸመታ መልሶ በሂደት ማመቻቸት ላይ መጠመድ ብቻ ነው። ሰላምን ባለማቋረጥ መሻት ግን፣ እጅግ ብሔርአዊ መሸወድ ነው። ሰላም አብሮን ሳለ፣ የተነጠቅንው ከእዛ በላይ ማቅረብ እሚችል መንግስት ስለሌለን ነው። ሰላምን በመሻት ከተጠመድን ግን፣ ያንን ማቅረብ አይከብደውም። የኢህአዴግ. አቀራረፅ እና አሠራርም ከእዛ የዘለለ ስላልነበረ፣ ከዉስጡ ሙጥኝ ብሎ ወጥቶ ዛሬም ደግሞ የተተወለትን በመቀበል እና በመጠቀም የተጠመደው ዞሮዞሮ ዳግምአዊ ኢህአዴግን. ለመሆን ነው። ተጨባጩ ሚዛን አንድ ነገር ካረጋገጠም፣ እንዳየንውም፣ የሆነው ይህን የእዉነት አዝማሚያ ብቻ ነው። ሰላም እያለ ከሰላም ተጨማሪ የፈለገ ህዝብ ኢህአዴግን. ካባረረ፣ በሂደትበሂደት ደግሞ ሰላም የተለመደችዋ ከሁሉ ዋና ሸቀጥ በወራሽ መንግስት-መስራች ከተደረገች፣ ይህ ድምዳሜ አስጊነቱ እንዳለ፣ እዉነት ግን ብቻ ነው። ያልተሰበረውን፣ የኢትዮጵያ ሀቀኛ ጥያቄ እና መፍትሄ እሚነካ መንግስት ማቋቋም እስኪቻል፣ ዳግ-ማፈግፈጉ እና በሀገር አፍሮ መኖሩ እሚቀጥል እንደሆነ እናይ አለን። ለዉጡን ግን፣ ማንም ያንሳው፣ ይምራው፣ ይቆስቁሠው፣ ኢትዮጵያ የከወነችው ዕለት፣ ሰላም ሻችነት ሀገርአዊ እስራትአችን እንደሆነ እንገነዘብ አለን፨
ወልቂጤ፤ ኢትዮጵያ
ጥቅምት ፳፰ ቀን ፪፻፻፲፫ ዓም

ግርጌ ፅሑፍዎች

፩ ለምሳሌ እነ ሀዲስ አለምአየሁ፣ የሹመትን ግብዣን እንቢ አሉ።
ከቀኃሥ. እሚለየው ሀቀኛ ለውጥ እንፈልግአለን እንጂ ለድንገተኛ ስልጣን የማቆየት ዕቅድ አባል አንሆንም እሚል ምሁር ግን በይፋ እምብዛም አልተጠመደም። ዘመኑንበሙሉ ቀንደኛ ምሁር-ጠል እና አሳዳጅ የነበረው ኢህአዴግ. ድንገት ስልጣኔን አድኑ ሲል በጄ መልስዎች ብዙ ነበሩ። በዉጤት ግን ጥቂት ወርዎች ለአምባገነኑ ከመሸመት የዘለለ ስኬት አልነበራቸውም።
ኢትዮአሜሪካአዊው ዲናው መንግስቱ፣ Children of the Revolution, (2007 GC), ገፅ፣ 147፣ መጀመሪያ ታታሚ (ዴቢው) ልብወለዱ የአፍሪቃን አምባገነንነት ባብጠለጠለበት ትርክቱ እሚያነሳው ቁምነገር ከህትመቱ በኋላ ነጥቡ የተደገመበት ነበር። የአፍሪቃ አምባገነንዎች እና ስልጣን በግርግር ያዥ እሚሆኑት ኮሎኔልዎች ናቸው፤ የበላይዎችአቸው ሲዘናጉ እነሱ ግን የበለጠ የስልጣን ጥም አሉአቸው።” በማለት ገልፆ ነበር። ይህ ታላቅ ፀሐፊ እንደተነበየው፣ በአንድ ትውልድ ለሁለተኛ ጊዜ ኢትዮጵያም ሁለተኛ የኮሎኔል መሪ እንዲመራት ሆነ።
፬ ስለ ሠላምሻጭነት አምባግነና የቀደመ የፀሐፊውን አጭርፅሑፍ ይመልከቱ። “ሠላም ሻጭነት እና ሠላም ገዢነት፤ ያልተዳፈነው አምባግነናአዊ ጎዳና በኢትዮጵያ ዳግ-ነብስ ሢዘራ”፣ ወይም ተአዶ. (PDF = ተንቀሳቃሽ አሀዝአዊ ዶሴ) ስሪቱን ያግኙ፦ www.academia.edu/,
ቢበዛ ጥቂት የአንድ ቡድን ዉስጥ ጠጠር ያለ መለያየት እንጂ፣ የተቃዋሚነት መደብ አልተፈጠረም ነበር። በመሀከልአቸው፣ ብልፅግና የተሰኘው ቡድን አገልጋይ ህዋሃት. እስኪፈነገል ደግሞ የበላይ ነበሩ። ስለእዚህ፣ የድርጅት ዉስጥ ያሉ ቡድንዎች የመገለባበጥ ጨዋታ አመፁን ጎርሦት አለ ማለት ነው። ግልበጣ መንግስት ወይም ሙሉ አብዮት እንዳልሆነ ዘርዝረን አይተን አለ። የካድሬዎች ቡድን ግን ሌላውን እዛው በዛው ተክቶ አለ የአንቀፁ መልእክት ፍላጎት ነው።

One reply on “ኢትዮጵያ ሀገረሠው እንድትሆን ሀገረሠላምነቷ ያብቃ፡ ግማሽ እድሜ የፈጀው የሀገር ነቀርሣው ‘ሠላምተኛነትአችን’”

[…] again peace, although that is not going to exist alone. Hence the idea of peace-selling being the curse of the nation for the past three decades. Before that the nation lost close to a million citizens for pure […]

Like

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s