Categories
መልካም ጥበብዎች Fine Arts

መግቢያ ሆሊውድ ለጀማሪው ተመልካች፡ ጎንዮሽ ወይም የጀርባ (ባክግራውንድ) እይትዎችን (ሲንስ) ተገቢ ትድድር (ማናጅመንት) ሠጥቶ ምርጡን አገልግሎት ስለማግኘት

የሆሊውድ ምርትዎችን ከመጠቀም ቀድሞ ጀማሪ ተመልካች በጥቂቱ ማወቅ ካለበት ጠቅላላ እውቀት፤ ስለ ጀርባ ዐውድ (background) እሚወያይ፨

ይህን አጭር ፅሑፍ በ ተአዶ. (PDF) ለማግኘት ይህን ጠቅታ ይከውኑ፨

፩) አጽሕሮተፅሁፍ
[ይህ መነሻፅሑፍ ያልዳበረ ነው። ማጠንጠኛሀሳቡ፣ በኪነጥበብ ምርት ሸመታአችን፣ እንደ መደበኛ ጀማሪ ሀበሻ ተመልካችነት፣ በእርጋታ እንድንገለገል ማሳሠብ ነው። እምቅአደጋ (ሪስክ) በአልተረዳ መገልገልአችን አለ ብሎ በማሣየት፣ የጥንቃቄ ጎዳናውን ለመጠቆም ያስብ አለ።]

፪) መነሻ
ታላቁ የ friends ተከታታይ፣ አይነተኛ ምሣሌ ነው። ብዙ ተከታታይዎች፣ እጅግ በተለይበተለይ እንደእሡ ያሉ sitComs ምርጡ ምሣሌዎችአችን ናቸው። ይህ ስለእዚህ ፅሑፍ ጭብጥ ነው። በኪነጥበብ አዕምሮ እሚሸወድበትን ሲከፋም ተታልሎ እሚጎዳበትን አንዱን መንገድ ነቅሦ ስለመመርመር እና ለዘመነ አኗኗርአችን ጉዳይዎችን ስለማፅዳት እሚያትት ነው።
እና፤ የመዝናኛ ዘርፉ ምርትዎች እሚተውብን የጎንዮሽ ችግር ካለ የእዛ መሠረት ሊሆን እሚችለው ነገር ምንድን ነው?
በተለይ በ sitCom ተከታታይዎች ተዋንያን አንድ እይት (ሲን) ሲጫወቱልን፣ ከጀርባአቸው እጅግ የበዙ የሠውዎች፣ እንሥሳት፣ የቁሣቁስ አና መሠል ምስልዎች እና ቁሣቁስዎች እንደ ጀርባ ሽፋኖችን እያገለገሉ እንመለከት አለን።
ለጥቂት አመክዮዎች ታስቦ ይህ እሚከወን ነው። አንደኛ፣ ገላጣ እና ወጥ ጀርባ የድራማውን ዉበት ይቀንሥበት አለ። ሁለተኛ፣ የጀርባው ዐዉድ ከፊት የሚታየው እይት-ትርክት አካሉ ወይም አጋዡ ነው። ሦስተኛ፣ ግልቻይ (ሰልፍሰፊሺየንት) መልዕክት ለማስተላለፍ ታቅዶ አለ። አራተኛ፣ ለአዕምሮ የበለጠ ቁጥጥር ስለመብቃት እና ትርክቱን በከበደ መጠን ስለመሸጥ ተብሎ እሚደረግ አለ። አምስተኛ፣ ከእነእዚህ ሁለቱ ወይም ተጨማሪዎች ሊደባለቁ እና ሊከወኑ እሚችሉ ይሆን አለ።
ከእነእዛ በላይ ያሉ ምክንያትዎች ሊኖሩ ይችል አሉ። ቢሆንም፤ ዋናዎቹ እነእዚያ ናቸው። ቀጥለን ሣንዘልቅ፣ እነዚህን ቀድመን ጥቂት እንዘርዝርአቸው። አንደኛ፣ ተከታታይ አስቂኝዎች፣ ሠፊ የቦታ መቼት መለዋወጥን አይከውኑም። ተዋንያን በብዛት ከአንድ ቤት፣ መስሪያሥፍራ፣ ወይም አንዳች እንዲህ ያለ በጣም ዉስን መካን ላይ ተገድበው እሚከውኑ ናቸው። እንደ ሌላ ዘውግ ተከታታይዎች የመቼት (ስፍራ) ስፋት አይሠጥአቸውም።
ይህ ማለት፣ ከጀርባአቸው፣ ብዙ እሚለዋወጥ ምስል የለም ነው። ያ ደግሞ አንድ ግልፅ ነገር አለው። ጀርባውን፣ ተንቀሣቃሽ ምስሉ እንደእሚቻለው አድርጎ ካላንቆጠቆጠ፣ ወይም ቅብዝብዝ ወይም መልእክት ሰጭ ካላደረገ፣ እንደ መጋረጃ (ወጥ ጀርባ) ፊት ሆኖ ድራማውን መጫወት ይሆን አለ። ያ ክወና ደግሞ፣ ቶሎ ሊሰለች፣ ስበት ወይም ስህበቱን ሊቀንስ ይችልበት አለ። በእዛ አመክዮ፣ ለተከታታዩ ተተኩሮ የመታየት አቅሙ መሻሻል፣ ከጀርባአቸው ያለውን ምስል በሙሉ ከፍተኛ ዋጋ በመስጠት አንዳች ክፍለ-ጥበብ አድርገው ይገለገሉበት አለ። ሲደማመር፣ ተከታታዩ ዉበቱን እና የመታየት፣ የመማረክ፣ አቅሙን እሚጨምር ይሆን አለ።
ሁለተኛው፣ ተከታታይ sitComs፣ እሚዋቀሩት፤ ከሌላ ነገርዎች መሀከል፤ በትርክት፣ ጭብጥ፣ ትልም፣ መቼት፣ ወዘተ. ነው። ተከታታዩ፣ ከእነእዚህ አላባአዊያን ጋር ተያያዥነት ያለውን የጀርባ ምስል ሊያስመለክት ይችላል እሚለው ይህኛው ነጥብ ነው። ይህ የጀርባዐዉድ ትትረት፣ ጭብጡን ወይም ትልሙን መደገፍ እሚችል ሲሆን፣ ወይም ቀለል ወይም ቆፍጠን ያለ መልእክትን በምልልሥዎች እና ድርጊትዎች መሀከል ሊያግዝ እሚችል ሲሆን ያንን እገዛ እሚያሣካ ነው። ለምሳሌ፣ አንድ ገፀባህሪ መኖሪያቤቱ ዉስጥ እሚያውጠነጥን ተከታታይ sitCom አለ እንበል። በመኖሪያቤቱ የተሠቀሉ ምስልዎች፣ እቃዎች፣ ጌጥዎች፣ ቁሳቁስዎች በተደጋጋሚ ከተመለከትንአቸው፣ የገፀባህሪውን ማንነት፣ ህልም፣ ፍላጎት ወዘተ. ሊገልጡለት እሚችል ነው። ለምሳሌ፣ ሁሉም ከባህልአዊ ምስል፣ ቁሳቁስ፣ ጥቅስ ወዘተ. የተበጀ ጀርባዐዉድ ቢሆን፣ ገፀባህሪው ባህልአዊነት ከዘመንአዊነት ኑሮቅጥ (ላይፍስታይል) ያሸንፍ እሚል ሀሳብ ይዞ እሚንቀሣቀስ ግለሰብ ቢሆን፣ ይህ የጀርባዐዉድ ተጨማሪ የማንነቱ አካል ሆኖ እሱን እንድንገነዘበው ላቂ (ኤክስትራ) ገለፃን ለተደራሲ አቅራቢ ይሆን አለ። የጀርባዐውዱ፣ ገፀባህሪ እና ትልምን አጋዥ ሆኖ ከመደበኛ መማረክ ኢላማ በዘለለ አሽከርነት እየፈፀመ ነው።
እዚህ ላይ አንድ በብዛት በጀርባ እሚከወን ያልሆነ ግን በጀርባ ዐዉድም አልፎአልፎ እሚከሠት ሁናቴ እንግለጥ። ለምሳሌ አንድ ትርክት ወደተደራሲ በምልልስ በመሸጋገር ላይ ሳለ፣ ተቀጣዩ መልእክት ግን ከጀርባ ባለ አንድ ድባብ እሚገለጥ እና እሚሟላ ሊሆን ይችል አለ። ያኔ፣ ፍፁም በግሉ፣ ይህ የጀርባ ዐዉድ የትርክት አባል ይሆን አለ። እንደተጠቆመው፣ እንዲህ ያሉ ቀጥተኛ የትርክት ፍሠትን በእዛ መልኩ እምንመለከተው ግን በጎንዮሽ እሚሰኙ ፍንጭዎች ጭምር እንጂ በጀርባድባብ ብቻ አይደለም። ለምሳሌ፣ አንድ መልእክትን የተናገረ ገፀባህሪን ቀጥሎ ወዲያው ለምሳሌ በጣት፣ በጥቅሻ፣ በአንድአች ፍቺ የለውም በእምንለው ድርጊት እሱ ግን ትልቅ እሚሰኝ የትርክት-ቅጥያ ሊሰጠን እሚችል ነው። ይህ ከተምሳሌት፣ ዘይቤ፣ ወዘተ. የአተራረክ ጥበብ አይነትዎች እሚቀራረብ ነው። እነእዛ ሠፊ እና ከፍተኛ የተለየ ኪነጥበብአዊ ዘርፍዎች ናቸው። ይኽኛው ግን፣ ሥዉር ሊሰኝ እሚችል የጎን መልእክት ብጤ እና እጅግ ቅፅበትአዊ ሲሆን ከምልልስ የተነጠለ ግን አግዞ እሚመጣ ነው። ምንምእንኳ ይህ የጀርባድባብ ቀጥተኛ ፍች ላይሆን ቢችልም፣ እጅግ ተቀራራቢ ነው በእሚል መወያየቱ አስፈላጊ ሆኖ አለ። ለምሳሌ፣ አንደኛ፦ ሁለቱም የጎንዮሽ እና ጀርባድባብ መልእክትዎች አጭር መሆንአቸው (በአንድ ቅፅበት እምንገነዘብአቸው አንጂ እረዥም ይዘት እማይገፈትሩልን በመሆኑ)፤ ሁለተኛ፦ ስነልቦናአዊ ወይም በብዛት ታካይ (አዲሽናል) መልእክትዎች ያሉአቸው በመሆንአቸው፤ እና ሦስተኛ እንደ ድብብቆሽ ወይም የፋሲካእንቁላል (ኢስተርኤግ) እሚደበቁ ስለእሚሆን፤ ሞላጎደል፣ ተመሣሣይነት አሉአቸው። ለምሣሌ፣ አንድአንድ ፊልም ወይም ተከታታይዎች ላይ፣ አንድ ምልልስ ሲካሄድ በስውር የተባለው ሹፈት መሆኑን እሚገልጡበት መንገድ ይኖር ይሆን አለ። ብዙ ተመልካች አይነጥበውም። ግን በትንሽ ጥቅሻ፣ ምላስ በማሾፍ በማውጣት፣ በጣት ምልክት፣ በግንባር ቆዳ፣ ወዘተ. የተለያዩ መልእክትዎችን አጋዥ ምልክትዎች ሊሠጡ ይችል አሉ። እነእዚህን በበለጠ ገሀድነት መጠን ወይም እጅግ በስዉር እና ጥንቁቅ አኳኋን ልንመለከት እንችል አለን። ለምሳሌ፣ Ex Machina, Alex Garald, (2015 GC) ፊልም ላይ፣ ካሌብ በመስታወቱ ፊት ፂሙን ሲላጭ እንመለከት አለን። በመደበኛ አተያይ ፂም ላጭቶ ማብቃቱን እንመለከት ብቻ አለን። ግን፣ እጅግ የተደበቀ ድምፅ በማደን እንዳለ እንጂ መላጨቱ ተራ ማመካኛ እንደሆነ የስክሪፕቱ እዉነታው ይነግረን አለ። አያይዞ፣ ከቶ በመደበቅ ብልሃት በእርጋታ ወደመስታወቱ ቀረብ ብሎ ከመላጨት በዘለለ የመታጠቢያ ክፍሉ ድብቅ መቅረጫ እንዳለው ያረጋግጥ አለ። መደበኛው ተመልካች ሁለቱንም ነገርዎች የአማግኘት እድሉ እጅግ ጠባብ ነው። እርእሱን እማላስታውሠው አንድ ፊልም ላይ ደግሞ፣ የተቀመጠ ገፀባህሪ የቀረበች እንስትን ሲመክር እንመለከት አለ። አንድ የጥንት ምስራቅ ፈላስፋን ጠርቶ ‘ዝንብን ለመግደል መድፍ አትጠቀሙ!’ ብሏል ይላት እና ወደጉዳይአቸው ይገቡ ነበር። ያንን አድምጦ በቀናነት ተገንዝቦ ማለፍ ግን መደበኛው ተመልካች ሁሉ እሚከውነው ነው። ዳሩ፣ ያንን የተናገረው በማልመጥ ወይም ማሾፍ ነበር። በጥቂቱ የመናቁን ነገር ለማረጋገጥ እየጠቀሰ ያንን ይነራት አለ። ይህን ለመጠቅለል፣ አንድአንድ እይትዎች ላይ አጋዥ መልእክትዎችን እንመለከት አለን። እንደ እነዚህ ያሉ። እነእዛ፣ የክወናው አባልዎች የጀርባዐዉድ ወይም ድባብ አባልዎች አይደሉም። ነገርግን፣ ተቀራራቢ ናቸው። ዳሩ፣ የጀርባዐዉድዎችም በእዛ የተቀራረበ አኳኋን ሊገለጡበት እሚችሉበት መንገድ አለ።
ሦስተኛ፣ አልፎአልፎ ደግሞ፣ ግልአዊ (ፕራይቬት) መልእክትን አስተላላፊ ምስል ሊፈጠር እሚችል ጀርባን ማበጀት ነው። ይህ ለምሣሌ አንድን ጉዳይ እሚሰብክ ነገርን መግለጥ ሲሆን፣ ከቀጥታ ጭብጡ ወይም ትልሙ ግን ብዙ ላይገናኝ እሚችል ነው። ከትርክቱ ወይም ገፀባህሪው ሊያያዝ እሚችልበት አጋጣሚ ላይኖር ይችል አለ። ለአንዲት ቀጭን ወጥ መልዕክት ወይም እንደምታ ወይም ድባብ ፈጠራ ብቻ ሊያገለግል እሚችል ነው። ለምሣሌ፣ ገፀባህሪው አስተናጋጅ ቢሆን እና ዉጣዉረዱን እሚያስመለክት ትርክትን እምንመለከት ቢሆን፣ ከእሚያስተናግድበት ቤት ግድግዳ ላይ ሁሌም የኢትዮጵያ ባንዲራን ወይም የቅድስት ማርያምን ምስል ብንመለከት፣ ከቀጥተኛ ትርክቱ ምንም ግንኙነት አያያይዘውም። ዳሩ፣ በግሉ፣ ይህ የጀርባ ድባብ ግን መልእክት አለው። ሥለሀገር ወይም ሀይማኖት ጠቋሚ እንጂ ስለትርክቱ እምብዛም ቀጥተኛ ተያያዥነት የለውም።
አራተኛ፣ ተደራሲ አዕምሮ አተኩሮ እና ተመሥጦ፣ እንዲቆይ ለማድረግ እሚያስችሉ ጀርባዎችን መጠቀም ነው። ይህ፣ ሆንተብሎ የተመልካች ትኩረት ላይ አንዲት ጨዋታ ለመጫወት ሲሆን አብሮ ግን አመለካከት ላይም አንዳች ህቡዕ ተፅዕኖ ለመዉለድ እሚከወን ሁሉ ሊሆን እሚችል ነው። ለምሣሌ፣ እጅግ የተጨናነቀ የግብዣ ማህበርን (ፓርቲ) ከተዋናይዎቹ ጀርባ መሣል እና ግርግር ማብዛት፣ አዕምሮን በድባቡ መሥጦ ለማሣመን እና የበለጠ ቅቡልነትን ለማግኘት እሚረዳ ነው። በተለይ ድምፅዎች ሰምተን ተስተናጋጅዎችን እንድንከታተል ድረስ ሳብ ያደርገን እና ወዲያው ግን ምንም እማይጠቅም ድምፅ መስማትአችንን አስተውለን ወደ ዋናው ድምፅ እንመለስ አለን። ያ ማለት፣ እጅግ አትኩሮትን ለመፈተን እና በእዛ ዋጋ የአስተማማኝ ገብቶ-ምሠጣ (ኢመርሽን) ልንፈጥር እንችል አለን። በእርግጥ ይህ እንደምሳሌው ከሆነ የትርክቱ ነገራ አካል ሊሆን እሚችል ጀርባዐውድ ነው። ድባቡ መሣል አለበት። ግን፣ በሆንብሎንታአዊ (ኢንቴንሽናል) እንቅስቃሴዎች እና ድምፅዎች ግን አትኩሮትን የመቆጣጠር ኢላማ እሚይዝ ስለሆነ አዕምሮን የማስጨነቅ እና የመጠቀም ቢያንስ ጎንዮሽአዊ ተፅዕኖ ሊያገኝ ይቻል አለ።
የመጨረሻው ራስአብራሪ (ሰልፍኤክስፕላናቶሪ) የሆነ ነው። ከአራቱ ዉህድዎች ሊገጥመን እሚችል ነው። ይታለፍ።
መነሻ ሀሳብአችን ሣይጠናቀቅ ግን፣ አንድ ጉዳይ ይጨመር። የጀርባዐዉድ፣ ምስል ብቻ አይደለም። ድምፅም ጭምር ነው። ከንግግርዎች፣ ከእንቅስቃሴዎች፣ ክክወናዎች፣ ወዘተ. ጀርባ ፊልም እና ተከታታይዎች ዉስጥ ብዙ ድምፅዎች እናደምጥ አለን። የጀርባዐውድ ከዋናው የምልልስ ድምፅዎች እና የጀርባ ድምፅ ማጀቢያነትን አይከትም። እነእዛ የፊትለፊት ድምፅዎች ሲሆኑ፣ ከእነሱ ጀርባ ግን እምናደምጥአቸው የጀርባድምፅዎችን በተመሳሣይ መንገድ ማስተዋል ተገቢ ነው። በእርግጥ የድምፅጀርባዐውድን በ sitCom የተለየ ሆኖ አናገኝም። እንደምስል ጠንካራ ልዩነት ከሌላ የተከታታይ ወይም ፊልም ጉዳይዎች የሉትም። በአንድምሆነሌላ ግን፣ ማጀቢያ ድምፅዎች ከፍተኛ ማስተዋል ያስፈልግአቸው አለ። እንደምስልዎቹ፣ ከጀርባ እሚፈስሡት ድምፅዎች ለዉበት፣ ለመልእክት፣ ለትርክቱ ወይም እይቱ አባልነት ወይም ማሟያነት ወዘተ. ይችል አሉ። ልክ እንደ ቀደመው፣ ተነፃፃሪ አላማ እና ባህሪዎች አሏቸው።
ግን፣ እንደአልንው የመደበኛውን ድምፅ አይደለም። የማጀቢያ ለማለት እሚከብዱ፣ የተለያዩ ድምፅዎችን በተለየ መመልከት እሚገባ ነው። በቀላሉ ከጀርባ እማይታዩ ሰዎች ወይም ቁስዎች እሚሠጡት ድብቅ ለማለት እሚያዳዳ የድምፅ አይነተደ ነው። ከላይ ብለንው አለን። ሌላው ግን፣ ከተለያየ እይታ ወይም አመለካከት ወደ ተመልካች እሚላከውን ከሞላ ጎደል ስዉር ድምፅ አበጥሮ ስለመመልከት ነው። ለምሣሌ፣ በ troy ፊልም ዉስጥ፣ ወደ ትሮይ ከተማ ግንብ ደርሠው፣ ከተደራደሩበት ጦርነት አስቀሪ አማራጭ ፍልሚያ አለመከበር በኋላ የጦርነት ዉጊያውን ሲጀምሩ፣ ከፍተኛ ቀታይ (ሌታል) የሠልፍ ትዕይንት ይሆን አለ። በእዚህ ክወና መሀከል እሚሰሙ ድምፅዎች አንዱ የፊልሙ ማጀቢያ ድምፅ ሲሆን ሁለተኛው፣ ደግሞ የተለያዩ የጦር፣ ቀስት፣ ማቃሠት፣ የጋሻ ምከታ፣ ጩኸት፣ ወዘተ. ድምፅዎች ናቸው። እነእዚህ መሀከል እሚሣልብን የዉጊያ ጠቅላላ ድምፅ ነው። ነገርግን፣ በቀውጢው የፊልሙ ትዕይንት ሂደት ሦስተኛ የተደበቀ አንድአንዴ እሚጎላ ብዙ እማናስተውለው ድምፅ አለ። የዓሞራዎች ማንዣበብ እና ድምፅአቸው በእየመሀከሉ በጥቂቱ ገባወጣ ሲል እናስተውል አለን። ይህ፤ ማለት ይቻል አለ፤ ስዉር ድምፅ ነው። ከከፍተኛ ቀዉጢ እይት መሀከል ብዙ ማስተዋል ከሌለ ባለማስተዋል እማያደምጡት ድምፅ ነው። የእራሱ ተፅዕኖ እና አተያይ ያለው በመሆኑ፣ እንዲሁ ሊተዉት እሚገባ አይደለም። የጎን ድምፅነቱ ከፍተኛ የመረሣት አጋጣሚን እሚሰጠው ቢሆንም፣ ማስተዋሉ ተገቢ ነው። የ Ex Machina ፊልም ላይ መስታወት አጠገብ እየቀረበ እሚሰማት ድምፅ፣ ተመሳሣይ አትኩሮት ብትፈልግብንም፣ የጀርባዐውድ ድምፅ አንለውም። የትርክቱ አካል ናት። ገፀባህሪው እሚጎረጉረው አንድ ጉዳዩ ነው። የትሮይ አይነቱ የተገለፀው ድምፅ ግን፣ ከፍተኛ የጀርባዐውድነት የተሸከመ ነው። ከትርክቱ አይገናኝም። ማስተዋሉን ግን በአቻ ደረጃ ፈላጊ ነው።
ስለእዚህ፣ ፊልም እና ተከታታይ በመመልከት ወቅት፣ የጀርባዐውድዎች፣ በምስል እና በድምፅ ሆነው፣ የተመልካችን ዐብይ አትኩሮት የመስለብ፣ የማጠንከር፣ የማጣፈጥ፣ የማከል እና መገንባት፣ አለቅጥ የማስጨነቅ ወዘተ. አቅም ስላሏቸው፣ ተገቢ አተያይን መከወን እሚያስፈልግ ነው። የበለጠ ይህ በቀጣዩ ክፍል እሚብራራ ነው።

(አፍታ የንባብ እረፍት)
(መመለሥ)

፫) ሥነልቦና
ቀጣዩ ነጥብአችን፣ እነእዚህን ነጥብዎች እንደምን እንመልከት ነው። ከጀርባዐውድዎች አንፃር ምንሥ ተፅዕኖ በእኛ የተዛባ የአተያየት አያያዝ ሊገጥመን ይችል አለ? እምንመርጠው አተያይ፣ አዉቀንም ሣናቅም፣ እሚነጥቁን ወይም እሚጨምሩልን ነገርዎች ይኖሩ ይሆን?
ቀድመን፣ አንድ ሥነልቦናአዊ ዕውቅ ሃሣብን እንወያይ። እሡ፣ ነገርንም ሆነ ኪነጥበብን በእምንመለከትበት ባህልአችን፣ ያለውን አንድ ነገር ያብራራልን አለ። የምንመለከተው ነገር (ይዘቱ ወይም ፍሬነገሩ) እንደአለ ሆኖ)፣ ከአተያየት አያያዝአችን ብቻ ተነሥተንም ግን እምንጠቀም ወይም እምናጣ መሆንአችንን እሚያስመለክተን ነፀብራቅ ሆኖ እሚቋጭ ትንተና ነው። ይህም የአመለካከት ልማድ ስለእሚሆን፣ አጋጣሚአዊ አተያየት ብቻ አይደለም። በእዛ አመክዮ፣ በሥፋት መዳሠስ ያለበት ነው።
እንደእየሁኔታአችን፣ ተመሣሣይ ነገር አይተን እምንገነዘበው ግን ይለያይ ይሆን አለ። ይህ አጋጣሚ ሊሆን፣ ወይም ወቅትአዊ ሀልዎታ (ኧቲትዩድ) ሊሠኝ ይችል አለ። ወይም፣ እንደ ግማሹ ብርጭቆ፣ ወይም ዳክ-ራቢት ስዕል አንዱ ትርጓሜ፣ የጉዳይዎች አተረጓጎምአችንን እና ከእነዛ ዉስጥ የምርጫ መወሠን ብቃትአችንንም ይገልጥ ይሆን አለ።
ለምሳሌ፣ በዝይ(ዳክዬ)-ጥንቸል ዕዉቅ ስእል ላይ፣ ዝይ ብቻ የተመለከተ እና ያንን የዘገበልን፣ ጥንቸሏን ዘግይቶ ተመለከተ እንበል። “ኦ! ዝይ አይደለም! ጥንቸል ነች!” ይለን እና ዳግ-ይመዘግብልን (ሪ-ሪፖርት) አለ። ቀደም ብሎ ዝይ እንዳላየ ያክል። ሌላው ተመልካች ደግሞ፣ “ጥንቸሏን አይቼ አለሁ፣” ካለ በኋላ “አሁን ግን ዝይም እያየሁ ነው” ይለን አለ። አተረጓጎም፣ እንደ እይታ እሚከተለን ሲሆን፣ የአገነዛዘብ ባህልአችንን እሚያሰምር ሁሉ ሊሆን ይችል አለ። ብዙጊዜ እምንመለከተው ያንን በመሠለ መንገድ ሊሆን ይችል አለ። ገሀድን ማንሻፈፍ ለማንም ሰው ይገጥመው አለ እሚለው የእዚህ ትንታኔ ነጋሪትነገር (ስቴትመንት) ነው። በአጭሩ፣ ነገር ምልከታ እና ነገር እምንፈታበት መንገድ፣ ከአተያይአችን እና ከእብስልሥልአችን ካለንበት ሁኔታ እና ልማድአችን፣ የተሞክሮ ክምችትአችን መጠን፣ ያለን አትኩሮት ወይም ፍላጎት ወዘተ. እሚያያዝ ነው። ግን፣ ባህል ሲሆን፣ አንድ ጨለምተኛ ነገር በመመልከት፣ ወይም ደግ ነገር በመመልከት አንዱን ምስል መተንተነደ እንደእምንጀምር፣ የተደጋገመ ጨለምተኛነት፣ ወይም ቀናአዊነት በህይወትአችን ሙሉ (ደረጃ) ሊፈጠርልን እሚችል ነው።
የእዚህ ነጥብ ጠቃሚነቱ በከፍተኛ መጠን ነው ይባልአለ። ቀናነትን፣ ብልሀትን፣ እርጋታን፣ ወዘተ. ለመቆጣጠር እና ለማግኘት፣ ረብየለሹን፣ ደስታየለሹን ኢሰብአዊ አተያይ ለማስወጣት ወይም መቀነሥ፣ ሊያግዝ እሚችል ነው። ስለእዚህ ዉጤት በማለት፣ አተያይን ማሠልጠን አንድ ቅድመሁኔታ ነው። ይህን ሥልጣኔ አምጥቶ አሥተሣሰብን ባህልአማ (ካልቸርድ) ለማድረግ፣ በጎ ሥነስርዓት (ዲሲፕሊን) ለመከተል ተመካሪ መሆኑ አያጠራጥርም።
ይህ ግን ጠቅላላ ጉዳዩ ነው። ወደ ፊልም እና በተለይ ተከታታይዎች መመልከት ጊዜ ደግሞ እንመለሥ። የጀርባዐዉድዎችን ከዋናው የእሚታይ እይት (ሲን) ምን ያገናኛቸው እና አረዳድአችን ጋር ሊነካካ እሚችል ሆኖ አለ? እንደአልንው፣ መልእክት ሊነግሩን፣ ዉበት ሊጨምሩ፣ አእምሮአችንን አብልጠው ሊቆነጥጡብን፣ ወዘተ. ይችል አሉ። ታዲያ ይህን ጥቅም በተገቢው መንገድ ማግኘት እና ጎንዮሽጉዳትን ግን ማስወገድ እምንችለው እንዴት በማስተዋል ነው? ሆሊውድንም ሆነ ማንኛውንም ኪነጥበብ ከእዚህ ጉዳይ አንፃር በምርጡ መንገድ መቅረብ እምንችለው እንዴት ነው? አተያይአችን እምንገነዘበውን ከመሠረተ፣ እንዴት አድርገን የኪነጥበብ አተያየትአችን ምርጡን አገነዛዘብ እንዲያጋብስልን እናድርግ? ምንአልባት፣ እምናተኩረው በጀርባዐውድ ምስል እና ድምፅ ላይ አለእሚገባው መጠን፣ ፍቺ፣ ቸልታ፣ አትኩሮት፣ ወዘተ. ከሆነ እና ተሞክሮአችንን እሚቀንስብን ከሆነስ? ጥቂት አላማአችንን መላሽ ጥያቄ ነው የጠየቅንው።
አንደኛው፣ ግድ እና ግድ ከሁሉም መቅደም ያለበት ጎዳና፣ በተዋንያን ቀጥታ እንቅሥቃሴ (ዳይሬክት አክሽንስ) ላይ አይኖች ማተኮር አለብአቸው እሚለው ነው። ትርክት፣ ጭብጥ፣ ትልም ወዘተ. በዋናው የተዋንያን እንቅስቃሴ እና ምልልስዎች እሚመሠረት ነው። ጀርባዐዉድ ከእዚህ ጋር እሚመጋገብ እና እሚቀላቀል ጭምር ቢሆንም፣ እሚጣረስ ሆኖ ግን ልናገኘው እንችል አለን። ያም እኩል እናተኩርብህ ስንለው ነው። ስለእዚህ፣ ከመጣረሱ መዉጣት ያለበት መልስ መቅደም ያለበትን ማስቀደም ነው። ያኔ፣ ቀጥተኛውን ትረካ አይንዎች ማደን አለብአቸው እሚለውን መሠረት ሆኖ እናገኘው አለን። ዋናውን ካለመልቀቅ ወደቀጣዩ መዞር እንጂ ግንድ ሳይኖር ቅጠል ማለም ኢስነአመክዮአዊ (ኢሎጂካል) ነው።
የጀርባዐውድ፣ የአተያይ አትኩሮቱን ከተዋናይዎቹ ክወና ሊቀንስ አንዳንድ ጊዜ ሊሞጨልፍ ይችል አለ። ማለትም፣ በጎ አላማውን እና ክፍሉን፣ ጀርባዐዉድ መሆኑን፣ በመጣል አሣሳች ሊሆን ይችል አለ። ይህ ሢደረግ፣ የኪነጥበቡን ዋና አላማ እና ጭብጥ፣ ከክወናው አብሮታ መፈፀምን፣ ከተመልካቹ ሊያጎድልበት እሚችል ነው። ክስረት። ጥቅምዎችአቸው እንዳለ ሁሉ፣ ጉዳትም አላቸው እሚለውን እሚያሠምርልን ይህ ነጥብ ሆነ። ይህ ቢያንስ በእኛ አተያይ አቅም ወይም ትኩረት መጠን እሚገጥመን ቢሆንም፣ በመጨረሻውደቂቃ አተያይ ግን ለእኛ ጎጂ ሆነ ማለት ነው ይለን አለ።
የእሚተላለፉ መልዕክትዎችን እንዳናተኩር፣ የጀርባዐዉድዎች ትኩረት አዛቢ ሊሆኑብን እሚችል ነው። የትርክት፣ ክወና፣ ትልም እና መሠል ኪነጥበብአዊ መስተጋብርዎችን አንጎልአችን እንዳያገኘው፣ የጀርባዐዉድዎች ትኩረት ሰራቂ ሌባዎች ሊሆኑብን እሚችል ነው። ይህን ካቋቋምን፣ ምን ዉጤት እንዳለው በነገርንው ጨምረን እንሞክር። ሌላው ነጥብ፣ ከቀናአዊነት መረማመጃ ሊያስት እሚችል ነው እሚል አንደምታ ያለው ተፅዕኖን እንመልከት። አንድ ነገርን እሚያሣስቡ፣ እሚያሣስቁ፣ አስፈሪ፣ የለሽፍቺ፣ ፍቺአማ፣ ወዘተ. የሆኑትን ጀርባዐዉድዎች በትኩረት እሚመለከት ተመልካች፤ ከዋናው እይት ቦዘን እሚል አይን፤ አንድ ሥህተትን እሚጎትት መሆኑ አይቀሬ ነው። እነእሱን ለመገንዘብ በመጣጣር ሂደት፣ ዋናውን ግብ፣ የቀጥታ መልእክት መሣቱን እሚያገኝ ነው። ማለትም፣ ሞላጎደል፣ ክወናውን እና አላማውን የመልቀቅ ሁኔታን ሊወልድብን ይችል አለ። በመጨረሻ፣ የተዛባ ስሜት፣ አገነዛዘብ ወይም ፍቺ፣ የተሣሳተ ነጥብ፣ ረብየለሽ ድባብ ወዘተ. ይዘን ልንወጣ እንችል አለን። ከመዝናናት እና መደሠት፣ ወይም ቁምነገር ከመጨበጥ፣ የተበላሸ ገበያ ይሆንብን አለ። ከፊው ነገር አያበቃ ከሆነ ደግሞ፣ በላጭ ጉዳት ኋኝነትአዊነት (ፖሲቢሊቲ) አለው። ለምሣሌ፣ ይህን ስህተት እምንደጋግመው ቢሆንስ? እንዳየንው፣ የዝይ/ደንቸል ስእልን በተለያየ መንገድ እንዳየንው እና የረዥም ጊዜ አተያየትአችንን እሚመሠርትልን ከሆነ፣ ማለትም በልማድአችን ምርጡን አተያይ ካልከወንን፣ ከፍተኛ አደጋ አለ። በእየፊምም እና በተለይ sitComs፣ ጨብጠን እምንወጣው ያልተገባውን አተያይ ሊሆን ይችል አለ። የተደጋገመ ተሞክሮአችን፣ የጀርባዐውድን ከዋናው ትእይንት ሳያሰባጥር ወይም ሳያስቀዳድም ከተቋጨ፣ የተደጋገመ ስህተት ሆነ ማለት ነው። ያ፣ የተደጋገመ ስህተት፣ የማይደገፍ ነው። ከሆነ፣ አስቀዳድሞሽ (ፕራዮሪቲ) ለዋናው እይታ በማድረግ መንቀሳቀሥ ግድ ነው። በሂደት ወደ ማሠባጠር ችሎታ መድረስ ተመካሪው ነው። ለእዛ፣ ከባለሙያዎች፣ ሂስአዊያን (ክሪቲክስ)፣ አዋቂ እና ተሞክሮአማ ግለሰብዎች ምክክር ተጠቅሞ፣ ነገርዎችን ማሠላሰያ አቅምን ማዳበር እሚገባ ነው። ከመሬት ተነስቶ፣ የፊልም ወይም sitComs ተከታታይ ከመሆን እሚገኘውን ይህን እምቅአደጋ (ሪስክ) ማሸነፊያው እንግዲህ ይህ ጥንቃቄ ሆነ። እነእዚህ ኪንዎች፣ በብዛት በክሂሎት በታጨቁ፣ በገንዘብ እና አቅም በሠለጠኑ እና በተማሩ እሚሰሩልን ናቸው። ገንዘብ ማግኘት ወይም አንድ አተያይ መሸጥ አንዱ አብይ ኢላማአቸው ነው። ያ ማለት፣ ያሉ አቅምዎችአቸውን ሁሉ በመጠቀም፣ እኛን በተፅዕኖ ለመክተት እሚጥሩ ናቸው ማለት ነው። ለእኛው የተዛባ አተያይ፣ ለእማይገባው አተያይ ለመሸነፍ ወይም ለእሚረባው አተያይ ላለመሳተፍ እሚያበቃንን ይህን ስህተት እንዳንከውን፣ ይህን ቅድመጥንቃቄ መከወኑን መውደድ ሳያስፈልገን አይቀርም። ይህ አንቀፅ ይጠቅለል። እንዴት የጀርባዐውድን መያዝ እንዳለብን በመሠረትአዊነት ሳንገነዘብ ወደ ተደጋጋመ እይታው ብንጠልቅ፣ አደጋ እንዳለብን አስምረን ተመለከትን ማለት ነው።


፬) መደምደሚያ
በከፍተኛ መጠን ሠፊ የሆነውን ይህን ነጥብ በከፍተኛ መጠን አጥብበን፣ መነሻ አንቀፅአችን ላይ ዳግ-እናተኩር። ከጀርባዐዉድዎች፣ መልእክትዎች አሉ። ጠቃሚ እና አተያየትአችን እንደፈጠረው መስተጋብር ደግሞ ጎጂ እምናደርግአቸው ናቸው። ከእነዚህ፣ በጎውን ላለመሳት፣ ወደመጥፎውም ላለመሳት፣ ተመሣሳይ ነገርዎች ያሥፈልጉን አለ። ጥንቁቅ፣ አስተዋይ አይንዎች። ከምንም በላይ በተሞክሮ እና ምክር የተዘጋጀ አይን። መብል መብላትን፣ ቀላሉን የሰው እለትአዊ ክወናን፣ ካለእጅመታጠብ በመደበኛነት እንደማንደፍረው፣ የተወሳሠቡ ሃሳብዎችን እና መዝናኛዎችን እሚሸጡትን መዝናኛዎችንም፣ እንደእጅ መታጠብ ባለ ዝግጅት መቅረብ አለብን። በቀጥታ ይህን ዉስብስብ ምርት በመሸመት እምቅአደጋ አለ። እንደ ሂስአዊያን የተጠበበ እውቀት እና ስል አይን ባይኖረንም፣ እንደ አንድ ንቁ ወይም የተማረ-መደበኛ-ዜጋ፣ ለእዚህ አገልግሎት ኢምንት እውቀት እና ዝግጅት ያገደን አለ። ያንን አስፈላጊነት፣ በመጨረሻ፣ ጭራሽ ከአተያየት ባህል አገናኝተንም የጉዳዩን ከፍተኛ አቅምነት አስተዋልን። መነሻፅሑፍአችንን እንጠቅልለው።
መጀመሪያ፣ አትኩሮትን በቀጥተኛው ወይም ቀድሞ ሊታይ የታለመ ክፍለ-ምስል ወይም እይታ ማተኮር ነው። ቀጥሎ፣ በእርጋታ እና በሰከነ አተያየት፣ የተረጋጋ ቅኝትን ጀርባዐዉድ ላይ መከወን እሚቻል ነው። ከምኑም እሚልቀው፣ የቀደመውን መከወኑ ነው። ያንን ላለማጣት፣ ሁለተኛውን ማለትም የጀርባዐውድዎችንም ለመቃኘት ከተፈለገ፣ የተመለከትንውን ደግሞ ወይም ደጋግሞ መመልከት እሚመከር ነው። እንጂ፣ ዋና ኢላማውን ለእማይቀድም ጎንዮሽአዊ ግብ መበተኑ አስከፊ ኪሳራ ሊሆንብን ቻይ አደጋ ነው። በማየት የወረወርንውን ልፋት ከመልስ ጥቅም አቅሙ ሊቀንሥብን እሚችል ነው። ሌላው ከፊ ነጥብ፣ በተቀላቀለ ወይም ጀርባዐዉድ ላይ ባተኮረ አተያይ ያለፈን እይት፣ ካልደገምን እና አሥተካክለን ካላየንው፣ በእዛው የእሚገጥመን ዝብአረዳድ (ሚስአንደርስታንዲንግ) ከእኛ ጋር እሚቀር ሊሆን ይችል አለ። በጠቅላላው፣ ጥቂት ዝግጅትን፣ እንዲሁም የሙያ ምክርዎችን በቀሉ በማደን፣ መግቢያ እዉቀት ይዘን እንድንገለገል፨

ቢንያም ኃይለመስቀል ኪዳኔ፨

ህዳር፣ 2013 ዓም.

By Binyamhailemeskel

Hey there! If you want to know about me, I just like fun, commonsense wisdom, and human love. Let us live a bright today changing tomorrow into brighter.
Regards,

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s