Categories
ስለ ቋንቋ አማርኛ (ወይም ይልቁንም አማሊዝኛ) Amhalish

በአማርኛ የእንግሊዝኛ መደባለቅ አስፈላጊነት ለኢትዮጵያ አዲሡ ሥልጣኔ፡ እንደ ሁለተኛው ጎዳና

አማሊዝኛ ቀኝአዊ እይታ ካለው ለማሰሥ እሚጥር አሀድ (ፒስ)፨


ቢንያም ኃይለመሥቀል ኪዳኔ፤ ህዳር 2013 ዓም፤ ወልቂጤ፨

ይህን አጭር መነሻፅሑፍ በ ተአዶ. (ተንቀሳቃሽ አሀዝአዊ ዶሴ =PDF) ለማግኘት፨

መግቢያ
ቋንቋ አማርኛ፣ ወጣቱ እና ባይተዋሩ ፪ ፣ ኁልቆመሣፍርት ጉድለትዎቹ ሀምሳእግር ትል ቢሆን አርባዘጠኙ የተቆረጡበት አንካሣ ያስመሠሉት፣ የመሀከልሀገር ዐብይ መለዋወጫው ነው። ተቻይ-ምርጥ ተግባቦትአዊ መብቃቱን ብዝ ጉድለትዎቹ ሥለአሠረጎዱ፣ ተፈጥሮአዊ መራራ ሠንካላነቱ ሳይታከም ኢዝግመተኛ (ኧንኢቮልቭድ) እንደሆነ በጉሮሮዎችአችን ተቀርቅሮ አለ።
እንደሆነው ሆኖ፣ የቱም የእዚህ ፅሑፍ ነቁጥ ያን እጅግ መሠረትአዊ ሸንካላነቱን እሚያስጠረጥር ጉድለቱን ዳሣሽ አይደለም። ያ ደረጃ አንድ ስምጠት እሚሻ ጥናት ለጊዜው ተዘልሎ፣ ገና ቀላል ፍፃሜ አሁንበእዚህ ታልሞ ተይዞ አለ። ቀጣይዎቹ አንቀፅዎች፣ ይህን መሠረትአዊ ነጋሪትነገር (ስቴትመንት) ለማቅረብ ሞክረዋል።


የፅሑፉ ነጋሪትነገር
የአማርኛ ተፈጥሮ፣ በአቶገበየሁ (ሌይማን) መሥፈርት እጅግ ያልከፋ እንደሆነ ታማኝ ነው። መቼትአዊ ዐውድዎች፣ በእዛ ሚዛን እጅግያልከፋ እሚባል ችግሩን ግን ጭራሽ አዝቅጠውት አሉ። ጭራሽ አዝቅጠው መክፋት ላይ አድርሠውት እሚገኝ ነው። እነእዚህም፣ ግርጌፅሑፉ እንደጠቆመው፣ አንደኛ ዘመኑ ወይም መንግስትአዊ አምባግነና እና ሁለተኛ በተሻገረበት የመሀከልሀገር ግዛቱ እንደእሚነገረው ናቸው። ጉዳይአችን መወለድ ጠቅላላ አመክዮው ያ ነው። አማርኛ፣ ዛሬ ላይ፣ በመሀከልሀገር እንደእሚነገረው፣ በአግባቢነት አቅሙ ብዙ ህፀጽዎች ፅልመት አጥልተውበት አለ።
ዛሬ፣ ዘመን ወይም አምባግነና እሚሠኘው በተለይ በአለፉት ሠላሳ ዓመትዎች የነበሩትን ድክመተ-አማርኛ ጫፉን ጥግ ያደረገበት ገሚስዕድሜን ገላጭ ነው። ይህም ከአምባግነና ስነዉሳኔ (ፖለቲክሥ) እና ቸልታ ጋር ተያይዞ የመጣ ነው። እስከዘመነ ደርግ ማብቂያ፣ የአማርኛ ደግ መብቃት እና በ ቸ እና ሸ እንኳን ከፍተኛ አትኩሮት መሠጠት፤ እና ማደግ ይህም በአንፃርአዊነት ያልተቀደመ እና ያልተደገመ የፍልስፍናዎች፣ ትምህርት፣ ሥነዉሳኔ (ፖለቲክስ)፣ ዕለትአዊ ቋንቋ (ኮመን ፓርላንሥ)፣ ወዘተ. መብቃትዎች ነው፤ ቀጥሎ የመጣ ወቅት ነው። ዛሬ በጠቅላላው፣ ከተሠኙት ችግርዎች እየነቀስን እንውረድ።
ከመሀልአቸው አንዱ፣ የዘመነ ዝርዝር ያለው ልዉዉጥ (ኤክስቼንጅ)፣ ሲከወንበት በመደበኛው ይፋ-አደባባይ አለመታየቱ፣ ሲሞከርበት ደግሞ አለማስቻሉ ነው። ይህን እጭቅ ንባቤ (ቴሢስ) በተከታይ አንቀፅዎች እናፍታታ።
የዘመነ ዝርዝርአዊ ልዉዉጥ ዘርፍአዊ ፍች የከተተ ነው። አማርኛ፣ መናኛ ዕለትአዊ መግባቢያነትን በማጠናቀቅ ያለውን ምክንያት-ዘ-ህላዌ (ሪዝን ዴት) ይጨርስ አለ። ቢያንሥ በከፍተኛ እርግጠኛነት እንደ እሚመሥለው። ሢገፋ፣ መናኛ ኩነትአዊ ልዉዉጥዎች ላይ ኢግጥምአዊ (አንፖይቲክ)፣ ሥኑፍ፣ መደዴ አሽከርነት ብቻ አጠንክሮ ይግት አለ። እነዚህ ስኬትዎቹ፣ ሙሉ ቋንቋአዊ ሙሉነትን አላስገበሩም። መሥፈርትዎች ተጓድለው አለ።
በተቃራኒ፣ የኢትዮጵያ ማህበረሰብእ፣ እንደ ሀገር መሠልጠንን እሚፈልግ ሆኖ፣ በእዛ እና መደበኛውም እረሀብ ጭምር እየተንገበገበ ነው። መሠልጠን ደግሞ፣ ቋንቋአዊ ግብዓቱ ልህቀትን መሸፈን፣ እና ዉስብሥብ ምስጢርዎችን ለማስተናገድ ልዉዉጥ ማመቻቸት፣ ዝርዝርዎችን (በተለይ በሙያአዊነት) ማብቃት እንደ መረማመጃዎቹ ናቸው። ዳሩ፣ አሁንአዊዉ መሀከልሀገር አማርኛ ዉስጥ፣ እነእዚህ ሀይቀአስፓልት (ሚራዥ) አቻ ናቸው። በዉጤቱ፣ ቋንቋው እጅግ፣ ዕለትአዊ ልዉዉጥዎች፣ ከዉበት እና ሠፊ የአመለካከት አድማስ የተቆራረጠ፣ የመንገደኛ (ሌይማን) ደረጃ-ታች አንደበት ብቻ ሆኖ አለ። ቢያንስ ማለት ይቻል አለ።
ይፋ-አደባባይ ማለት ደግሞ፣ በጋዜጠኛዎች፣ በመገናኛብዙሀንዎች፣ በህዝብአዊ (ፐብሊክ) ልዉዉጥዎች፣ ወዘተ. እሚደመጠው እንደማለት ነው። ይህ፣ የተለመደ መሀከልሀገር ዜጋውን መደበኛ አማርኛ ልዉዉጥንም ማካተት እሚችል ነው ብለን መዉሠድ እንችል አለን። አንድም፣ ያ የተነገረው የአማርኛው አካል ሲሆን፣ ሁለተኛ ደግሞ፣ የቀደሙት የይፋአደባባይ ልዉዉጥዎች ፍፃሜ፣ ወደ መደበኛው ዜጋ መድረስ ስለሆነ፣ በቀኑማብቂያ፣ ይህን መደበኛ ዜጋ እና የአማርኛ አቅሙን ገላጭዎች ወይም ጠቋሚዎች ናቸው።
ሥርችግሩን፣ የፅሑፍአችንንም እምብርት ከፈታታን ወዲህ፣ መሟሻአረፍተነገርአችንን (ፕሮፖዚሽን) ለመጠቅለል፣ አማርኛ ዝሙን መለዋወጫነቱ እንደተጎዳ አስመለከትን እንበል። ታዲያ፣ ለእዚህ የትኛው መዉጫው መንገድ ጉልህ ሆኖ አለ? አንዴት? መንገር አያስፈልግም፤ ግንባርስጋነቱ አያጠያይቅም። ሥልጣኔ መር አማርኛ መወለድ፣ ከተፈላጊው ሥልጣኔም አብሮ እና ቀድሞም አንዳንዴም ቶሎቶሎ ተከትሎም ቢሆን፣ ወደፊት – ወደ ዝሙን ቋንቋነት – መራመድ አለበት። ሠፊ ሸለቆ ችግርዎቹ፣ ምህረትየለሽ አቅምማነስ እንደአለበሡት፣ ከፍተኛ አቻ-መልሦ-ተፅዕኖ ሊቀበሉ ይገባ አለ። ከነቁጥ፣ ነጠላሠረዝ፣ ወዘተ. ጉዳይዎቹ እስከ ወጥ የቋንቋውን መስፈርት አዉጪ ሥነዉሳኔአዊ (ፖለቲካል) እርምጃ መከወኑ፣ ምንአልባት የአንቀፅ (አርቲክል) ጉዳይዎቹን የመፍታት እና መሠል ጉዳይዎቹ፣ ወዘተ. ድረስ፣ እማያልቀው የችግር ቋቱን ሁሉ፣ በከፍተኛ መፍትሄ የማቅለሉ ዐብይ ጉዳይ ስኬት፣ መደፈን አለበት። ይህ፣ በመደምደሚያው ክፍል እሚበልጥ ተብራርቶ አለ።
ሌላውን፣ አንዱን መንቀስን ቀጥለን ግን፣ እንደ አሁንአዊው አላማአችን፣ እንመልከተው። እጅግ ንዑሥ ጎዳና ነው። የአማርኛ ጠዝጣዥ ኢሥልጡንአዊ አቆያየት እስኪጠመዘዝ፣ አንድአንድ የጊዜ-ብጁ ጎዳናዎችን መከተል እሚመከረው አንድ የምንአልባት አማራጭ ነው። ሂደትአማ መፍትሄ፣ በወጥ እና ቋሚ መፍትሔ ስለእሚተካ ኢዘላቂአዊ (የተገደበ) አፈፃጸም ነው። ይህ ጎራ እንዲህ እሚሠኘው፣ አማርኛ ሸለቆ ችግርዎቹን ሲሞላአቸው እና የላቀ አንደበትን ሲያጓጉዝ፣ መወገድ ወይም መቀነስ እሚችሉ ወይም ለዉበት ብቻ እሚቀመጡ ታንኳዎች ስለሆኑ ነው። አንዳንድ ጊዜ፣ አጋጣሚ ተጠቃሚነት (ኦፕርቹኒዝም) ሊባል ይችል አለ። ግን፣ ሆንብሎንታአዊ (ኢንቴንሽናል) አጋጣሚ አሣሽነትንም በተገቢ አመክዮ መከወን እሚፈቀድ ይሆን ይሆን አለ። በእርግጥ ቀጥተኛ እና ጥንትአዊ (ኦሪጂናል) ምላሽ መስጠት ተገቢው ነገር ነው። ያ እስኪሣካ፣ ለቃቂ ግን አመቻቺ ጉዳይዎችን መመርመሩም እማይከፋ ነው በእሚል የታሠበ ፅሑፍ ነው።
እነእዚህን አማርኛን መገንቢያ ወጥ እና ዘላቂ መንገድዎች አንዘረዝርም። አካሄድ እና ጥናት እሚያመጣአቸው ናቸው። ከቶ የእዚህ ፅሑፍ አካል አይደረጉም። የመዳረሻ ጊዜአዊ መንገድዎች ቢሆኑም ሁሉም አይዘረዘሩም። የእዚህ መጠነስፋቱ (ስኮፕ) አንዱን፣ መመልከት ብቻ ነው። ይህም፣ እንግሊዝኛን ለዘመንአዊ ልዉዉጡ ጊዜአዊ የሠመጠ ተባባሪ ማድረግ፣ እሚለው ነጥብ አላማአችን ነው። አስቀድሞም፣ እንግሊዝኛ ለአማርኛ ቀኝ እጁን ዛሬ በመሀከልሀገር ያዋሠ ነው። በእየአማርኛ ልዉዉጥ፣ እንግሊዝኛን አጋዥ ማድረጉ የተለመደ ነው። ነገርግን፣ የእንግሊዝኛ አጋዥነቱን፣ አማርኛ ስላልዘመነ በደከመበት ስፍራ ማድረግ ስለእሚልበት ሁኔታ ብቻ መወያየቱ የእዚህ ጭብጡ ነው። በእዚህ መሠረት ጥያቄአችን አሁን ይህ ነው። አማርኛ እስኪዘምን፣ እንግሊዝኛን በአኳኋኖች በጠራ መጠን መጠቀም እና ያልላቀ ክፍሉን በእንግሊዝኛ እየጣፉ ዝሙን ልዉዉጥ መከወን እሚቻል ከሆነ ያ እንዴት እሚሆን ነው?
ከላይ የተብራራ ነጥብ ላይ እንቀጥል። ዘመንአዊነት የሥልጣኔ አንዱ መሠረቱ ነው። መዘመን ግን፣ ዘርፈአዊ (መልቲፋሴትድ) ነው። በቋንቋም ይህ ሁኔታ አለ። በሁለት መንገድ፣ ቢያንስ በወጪወራጅአዊ ምልልሥ እንኳ፣ ይህ ይከወን አለ።
አንደኛ፣ በስልጣኔ ጅማሮ እና ጫፍ ሠፊ የልዉዉጥ ዉስብሥብነት አለ። ህይወት የእንቅስቃሤ ፈርጇ ይሠፋል። ገናም በያለበት እሚከወነው ህይወት እጅጉን ሥለእሚዘረዘር የቋንቋ ልዉዉጥ ይሠምጣል። ታዲያ ይህ ምሉዕአዊ መስተጋብር ሲፋፋም፣ ቋንቋው በአቻነት እሚግም ነው። ከእዚያ ገሀድ በቀረ፣ መሠልጠኑ፣ ኢእዉነተኛ ነው። በአማራጭ እይታ፣ ወይም በተነጠለ እይታ፣ የቋንቋን መሠልጠን ደግሞ እንይ። በታሣቢ ጎንዎች ሁሉ ቋንቋ በአቅምዎቹ ሲጠነክር፣ የተናጋሪዎቹን አንጎልን ይሠላው አለ። አመለካከት ይሞረድበት አለ። ያ ሲሆን፣ የሠላ አንጎል፣ አምጭስልጣኔ ስለእሚሆን፣ የቋንቋ ወደስልጣኔን ግለዝግመት ይከውንልን አለ። በስልጣኔ ቋንቋ ሠፍቶ፣ እንዲሁ በቋንቋ መዘመን ደግሞ ሥልጣኔ ተወልዶ፣ ነገርዎች ተተካክተው እንደእሚሠሩ በእነእዚህ ሀሳብዎች ተመለከትን።
ወደ እኛ ጉዳዩ ስንመጣ፣ በዘመንአዊው ሥልጣኔ አልተመነደግንም። አማርኛ ከእዛ እሚገኘውን መንገድ አልተጓዘም እና አላደገም። አማራጩ፣ በእራሡ የሥልጣኔ ፈርቀዳጅ መሆን ነው። ለእዛ ብዙ ደንቃራዎች እንደአቆሙት አለ። ዳሩ፤ አማርኛ በእግርዎቹ እንዲቆም እና ሥልጣኔ እንዲዋሃደው፤ ተናጋሪዎቹ ያንን እስኪፈቅዱለት፤ ሠንካላ አማርኛን በጊዜ በእሚለወጥ፣ ማለትም ሂደትአዊ፣ ህክምናአችን ወደእንግሊዝኛ እንጎትተው። እሱ፣ አይሠንፍም። ምርጡ የሥልጣኔ ቋንቋነቱ ማማዎች ጥሦ የተንበለበለ ሆኖ አለ። የአማሊዝኛ ጉዳይ ሢነሳ፣ ምንአልባትም፣ ከየቱም ቋንቋ በላይ፣ እንግሊዝኛ አማርኛንም እንደሽምግልና ከዘራ ደግፎ እንደያዘ፣ ሳይታክት ያለ መሆኑን አስረጂ ነው። ይህ፣ እንዳልንው የቋንቋዎች ዉህደት፣ ብዙውን ጊዜ እማይመከረው የሆነው፣ በአማርኛ አብዝቶ ሢከወን አማሊዝኛ ተብሎ ይጠራል።
በአማሊዝኛ፣ እንግሊዝኛ ከአማርኛ ተጣምረው አሉ። በእዛ፣ እንደ ‘የትላንቱ ባክ አፕ ለዛሬው በጀን’ መሰል አረፍተነገርዎች አሉ። ‘ሞባይሌ ጠፋ’ እሚለው የተዉሦ እንጂ የዉህደት አይደለም። ተዉሦ እና ዉህደት፣ በእየእራስአቸው ህፀጽ እና ጥንካሬዎች አሏቸው። ፲፩ የእዚህ ጽሑፍ ፍላጎት ግን፣ አማሊዝኛ ዉሥጥ ያሉትን እጭቅ አሉታአዊ ተፅዕኖዎች ትቶ፣ የነጠለውን ጥቅሙን በተብራራው መሠረት መሣል መሞከር ነው።
ይህን ምክረሃሳብ፣ በምን መንገድ ምክር አደረግንው? ነጥቡ፣ በከፍተኛ ጥንቃቄ፣ ይህም በልዩነት ታች የተብራራ ነው፣ ማሠባጠሩን በሥልጡን መንገድዎች አማርኛ እስኪነሣ መከወን ነው። አሥፈላጊ በሆኑ የቅድመሁኔታዎች መሟላት፣ አማሊዝኛን መገልገል፣ አማርኛ ከሥነዉሳኔአዊ (ፖለቲካል) ሻጥር ወይም ቢያንስ ልዑል-ቸልታው የሠጠው ክፍተት ሁሉ ታክሞለት እስኪወጣ፣ ይህ መልስ አስገዳጅ ወይምቢያንስ ተመካሪ ይመስል አለ። በምንቅድመሁኔታዎች እሚከወን ይሁን? አንድ፣ ለመዘመን በእሚደረግ ትትረት ጉልህ አጋዣ በእሚሆን ጊዜ። ሁለት፣ መደበኛ ጠንካራ አማርኛ በጎን እስኪለምድ፣ እስኪሠርፅለት። ማለትም ቅድመሁኔታ አለ። ሁሌም አማራጭ ሲገኝ ከተቻለ መተው ከአልተቻለ አብዝቶ አማሊዝኛን አለመከወን ይገባ አለ።
የቀደመውን ጥቂት እናብራራ። እንዳልንው፣ የቋንቋ ማደግ፣ የአንጎል ብሩህነት አንድ ምንጭ ነው። ያለን አማርኛ፣ ዛሬ በተግባር እንደእምናገኘው፣ ዕለትአዊ መግባቢያነቱ በመጉላቱ እና በዐድነትን መጋበዝ ለመዘመን በእሚደረግ ጥረትዎቹ ስለአለበት፣ ፲፪ ይህን ማእከለጨዋታ (ኢንተርፕሌይ) ጠቃሚ ሆኖ እናገኝበት አለን። በአማርኛ አቅም አለመልማት እና ጭራሽ ማሽቆልቆል ብዙ ጉዳት በተናጋሪዎቹ አንጎል ስለአለ፣ ይህንን ማሸነፊያ አንዱ የአጭርጊዜ መፍትሔ ነው።
ለምሣሌ፣ እንደቀደመ ደግ መነሻ ዘመን እሚሰኝ፣ በአስገራሚ ሁኔታ ደግሞ ተተኪ ባላገኘው፣ የቀኃሥ. (ቀዳምአዊ ኃይለሥላሴ) እና ህብረተሰብአዊው (ኮሚውኒስት) ደርግ ዘመንዎች፣ ዘመንአዊው አማርኛ ደህና-ጫፍ እመርታውን ገንብቶ ነበር። ጥበብ፣ መደበኛ አኗኗር፣ ጋዜጠኛነት፣ ስነዉሳኔ፣ ስነምጣኔ፣ እና ፍልስፍና ደግ የቋንቋውን አቅም መቅመስ ጀምረው ነበር። ከምሁርዎች እና ባለሙያዎች በዘለለ፣ በመደበኛ ዜጋዎች አንደበት በአማርኛ መጠነቃልዎች (ቮካቡላሪ) እና ሠዋሰው ላይ ደግ አቅም ይዞ የመሀከልሀገር አማርኛ አገልግሎ ነበር። ዛሬ የእዛ ትዉልድ ከፍታው ተሠልቦ አለ ማለት በአያሌው እሚቀና ነጥብ ነው። በእዚህም የተነሣ፣ ከአማርኛ ጠቅላላአዊ መላሸቅ የተነሣ አመለካከትአዊ አቅምም አብሮ በአቻነት እና በባሽነት እንደከሸፈ አለ፤ በማያጠያይቅ አይነተኛነት። ፲፫
የእነዚህን ክፍተትዎች ለመሙላት ተመካሪው አማርኛን ዳግ-ማበልፀጉ ነው። እንግሊዝኛው ሠፊ ድጋፍ አይሠጥም። በግርጌ ፅሑፍ እንደተገለጠው፣ እማሬ እንጂ፣ ፍካሬአዊ አቅሙ፣ በወጥ ቋንቋ ከነበረው ይልቅ በድብልቅ ቋንቋ ስለሌለ፣ ይህ ምክር ከሁሉ አስገዳጁ ሆነ። ከተብራራው ቋንቋአዊ ነጥብዎች በተጨማሪ፣ ዳግመኛ፣ ሥነልቦናአዊ እና የልዑዋላዊነት ጥያቄዎች በእዚህም እሚነኩ ስለሆነ፣ ይህን በአንክሮ ማሥተካከል ተገቢ ነው።
እስከእሚወሠደው ደረጃ ስለአሽከርነቱ አማሊዝኛ ሲወሠድ፣ ምን ጥቅሞች መቀበል እንችል አለን? አንደኛ የመንግስት ቋንቋአዊ ንቀት ከፍተኛ ያመጣውን አንጎልአቅም መዉረድ፣ በፍጥነት እና ቶሎ ለማቅለል መንገዱ ነው። አንድም፣ አማርኛን ስላላሸቁት ነው። ሁለተኛ ደግሞ፣ ዘመንአዊ ዕዉቀት እና ልዉዉጥ፣ እሚገኘው ከጊዜው የመሀከልሀገር አማርኛ ይልቅ በእንግሊዝኛ ሥለሆነ፣ ለእዚህም መሠረት የሆነው በእንግሊዝኛ የተቀረፀ እና የእሚከናወን ስርዓተትምህርት ስላለን ነው፣ ይህን መከወን ጥቅሙ በላጭ እርግጠኝነት አለው። እንግሊዝኛ የበለጠ አቅም ከተለመደው አማርኛ በላይ አለው። ሦስተኛ፣ እንደተገለጠው ገና በዘመንአዊነት እሚለመድ አማርኛ፣ በዐድአዊ ቆይታው የዘለገ እንደሆነ በመደበኛነት ይገመት አለ። ማንሠራራቱ ጊዜ ፈላጊ መሆኑ ግልጥ ነው። ይህንን በሂደት ለመርታት እስኪቻል ይህ የአስፈላጊ እንግሊዝኛ መቀጠር ተመካሪ ነው።
ጎንዮሽአዊ ጥቅምዎች በእዚህ ዘንድ አሉ። አንደኛ አስፈላጊ የባህል ለውጥ ካለ፣ ከእንግሊዝኛ ጋር እሚገለበጥ ከሆነ ይህን ማግኘት ይቻል አለ። ሁለተኛ፣ በዓለምአቀፍ ደረጃ የእንግሊዝኛን አቅም ለአማርኛ ተናጋሪዎች እሚያሳድግበትን እድልም ሊያጋብስለት ይችል ይሆን አለ።
ቅድመጥንቃቄ አንድ ሠግጎ አለ እና ይገለጥ። እንግሊዝኛን አማርኛ ዉስጥ ደባልቆ የመናገር ጉዳዩ፣ እሱም እሚባለው አማሊዝኛ ነው፣ እዚህ ላይ እረጂ ቢሆንም፣ አማሊዝኛ ግን ለእዚህ አንቀፅ አላማ፣ ሁለት ይደረግ። አንደኛው እና የተመከረው፣ የተበረታታው፣ አማሊዝኛ፣ ገንቢ እና ጎህቀዳጅ ሚና አለው። ይህ የሆነው ወደሽሉ የሥልጣኔ አንደበት ሀገርን መምራት አላማው ስለያዘ ነው።
ዳሩ፣ መደበኛ አማሊዝኛ መሀከል ከፍተኛውን መጠን ያዥ የሆነ አለ። ይህ ከያዝነው ነጥብ አንፃር ገንቢነቱ ኩርማን የሆነው፣ የቅምጥል እና ስንፍና ብሎም ግድየለሽነት አማሊዝኛ ነው። ለምሣሌ፣ ሞልቃቃ፣ ቅጥአማ (ስታይሊሽ)፣ ዳያስፖራ፣ ምሁርልምሰልባይ፣ ወዘተ. ተናጋሪዎች፣ ይህን አማሊዝኛ በቄንጥ ከአንደበት ይወልዱታል። አማርኛን መጠቀም ሲችሉ እንግሊዝኛውን በሆንብሎንታ ያስቀድሙት አለ። ያ፣ ለዋናው አማሊዝኛ እራሱ ለተመረጠበት አላማ፣ አማርኛን በሂደት ለማዘመን እሚለውን የሣተ አተኳኮስ ነው።
ይህኛውን አማሊዝኛ፣ ከቀበሌኛ እዉነት መደመር እሚችል ነው። ወይም ከወጣትነት ወይም አንድ የዘዬ ዘርፍ ወይም የሠፈር አኳኋን አዝልለን አንመለከተውም። ጥንካሬአማ ይዘት፣ አረፍተነገርአዊ ብርታት፣ ብዙም አያስመለክትም። ይልቁንም፣ የአንድ ጎራ ዘዬ ቢባል እሚቀልል የአማሊዝኛ ዓይነት ነው። እንጂ የቋንቋ ምልዓት የሞላው የሥልጣኔ ፈር አይደለም። ዳግ-ይልቁንም፣ የሀልዎታ (ኧትይትዩድ) መገለጫ እንደሆነው ያክል፣ የቋንቋ ግልአዊ ማንነትአልባ ግን የሌለው ነው። ይህኛውን አማሊዝኛ ዘረሁኔታ (ሞድ)፣ ይህ ፅሑፍ የሸፈነው አይደለም። የአማሊዝኛ ተመካሪው አካሉ፣ በእዚህ ፅሑፍ የተካተተው፣ የዛሬ አማርኛው እማይደርሥበትን የሀሳብ ጉራንጉር ለማገዝ እሚነካካውን፣ በጎንም የተገለጡትን ጥቅምዎች እሚሠጠውን ነው።
ሢደመደም፣ አማሊዝኛ እንደድልድይ ሲወሠድ፣ ያየንአቸው መንደርአዊዎቹን ቅጥ ግን እዚህ ምክረሀሳብ ያላደረግንው ነው።አማርኛ እንደቀደመ ዘመኑ በዘመንአዊ ዕዉቀት አሽከርነት ችሎ እስኪፀናልን ወይም ከእዛም በስኬት ተሽሎ በልዑል ቋንቋነት እስኪገፋ፣ እና ሀገርበቀል ፊደል ስላገኘ የአፍሪቃ መኩሪያ ከእሚሰኝበት ደረጃው በይዘትም ያ ተገብቶት እንዲቆም፣ አማሊዝኛ ዳስ ዉስጥ መሻገሩ አስፈላጊ እንደሆነ ማስመልከት ነው።


መደምድማት
ቋንቋ የሥልጣኔ አንዱ ዐብይምሠሶው ነው። በሁለት እኩል መንገድዎች ተመስክሮ አለ። አንድም፣ በዘመነዋሻ፣ ቋንቋን መጠቀም፣ ዓስተኔሠብእን (ህዩማንካይንድ) ዉስብሥብ ዝማኔን ኮትኩቶለት ነበር። ብሉይ (ክላሲክ) ሥልጣኔን አመቻቺው አንድ ካሥማነቱ በእዚህ አለ። ሁለትም፣ በተለይ ከአምስትመቶ አመቶች ሉልአዊ ለዉጥ (ዘመነ ኢንላይትመንት) አንፃር ጀምሮ፣ እና ዛሬ፣ እንዲሁም በእርግጠኝነት የዘመነውን ነገን ጭምር፣ ቋንቋ ዘመንአዊውን ዓለም ያሣደገ አንድ ዕደ-አንደበት ነው። ሠፊው የሥልጣኔ ዣንጥላ፣ ከሌላ አቋቋሚዎች መሀከል በቋንቋ፣ በሠለጠነ ምድር የተዘረጋ ሆኗል።
ወደቀጣይ ነቁጥ ስንሻገር፣ በመሀከልሀገር እሚነገር የዛሬ አማርኛን የተዘነጋ ሆኖ፣ ሀገር ግን መሠልጠንን ከአየሩ እሚጨለፍ ይመስል ፲፬ ሥታልም እምናገኝአቸው ኢተገጣጣሚ ጉዳይዎች ሆነው ነው። በመሀከልአቸው፤ ግጥመቴ (ዶኪንግ) ከቶ ኢኋኝ ነው። የመደዴ ሥነዉሳኔ አረማመድ፣ በተለይም በሥልጣኔ ሀቀኛ መሠረት አጣጣል ከእነእዚህም አንዱ በሆነው በቋንቋ ላይ፣ ያም እስከ ግማሽ ትዉልድ፣ በኢትዮጵያ ሀይባይየለሽነቱ አለ። ማደግን በሠፊው መሥበክ በቂ የካድሬአዊ (ኤክሰኪውቲቭ) የተጫጫነው የመንግስትአዊ ስነሥርዓትአችን ቆሻሻ ጨዋታ የእነእዚህ ቋንቋ ጥያቄዎች እና ሁሉም የኢትዮጵያአዊ ጉዳይዎቹ ሁሉ ቀታይ (ሌታል) ነቀርሣው ነው። ሀገርን ልናሣድግ ነው እሚለው ቱልቱልቴ ብቻ ለመንግስትቀጣይነት በቅቶ፣ እጅግ እንዲሁም እጅግ፣ የእዛ ሀቀኛ ግንባታ ወለልዎቹ ግን ተሽቀንጥረው እና ተንቀው፤ ተረስተውም አሉ። ከእነእዚህ አንዱ፣ ለሀገር መንግሥት ጭበጣ ቋንቋዎችን፣ አማርኛን ጨምሮ፣ መዘንጋት እና አቅሙን ጭራሽ መግፈፍን፣ እማይነቀፍ የማድረጉ ቀፋፋ ጉዞው ነው።
ይህን ብሔርአዊ ገደል፣ በስነዉሳኔአዊ (ፖለቲካል) ትንተና መኮነን እንዲቻል፣ በመዝለል፣ ቋንቋአዊ መድኃኒትዎቹ መሀከል በሁለት ዐዉድአዊ ረድፍዎች ተወያየን፤ አንዱን መርጠን ኢምንት ዝርዝር መነሻሀሳብ አበጀንለት። አንዱ፣ ሠፊ እና ዘላቂ የቋንቋ አዘማመን መንገድዎችን መከተል መንገድዎቹ ናቸው እሚለው ነበር። ቋንቋ አማርኛ ሠፊ፣ ስምጥ፣ አንገብጋቢ (መሰረትአዊ) ችግርዎቹ በሠለጠነ ሙያአዊ መንገድ ከታከሙለት፣ አሥመኪ የሥልጣኔ አንድ ግብዓትነቱን ለሀገር መዋጮ ያቀርብ አለ። ይህ ጠቅላላአዊ ምርመራ፣ ሁሉንአቀፍ ቁሥሎቹን ከሻሩለት እሚደርስ ሥጦታ ነው። በእዚህ ሳንነካው፣ ይህንን ትልም ዘለልን።
ሁለተኛው ደግሞ፣ ያሠፋንው እስከአሁን፣ ንቅሣት ነው። እሚነቀሡ ነጠላ የሆኑ የተለያዩ ጉዳይዎችን በእየዐዉድዎችአቸው መንከባከቡ እና ትንፋሽ ማበጀቱ ነው። ወደ መቋጫው የቋንቋው ደግ አቅም ብቅታ መከወኑን በጊዜያዊነት እሚያግዙትን ስለመመርመር ነው። የእንግሊዝኛን ድጋፍ፣ ለጎደሎ አማርኛ አቅምአችን መቅጠሩን ከእዛ እሣቤ መሀከል ነቅሠን ደግሞ ተመለከትን። በእዛ፣ የሂደት መልስ ሲኖር፣ ከፍተኛው የአማርኛ ቀዉስ አንድ መዉጫውን ድል እስኪያደርግ፣ ይህ ከእነስጋቱ አንዱ መንገዱ ሊሆን እሚችል ነው፨

ግርጌፅሑፍዎች

በሦስት አመክዮዎች ወጣትነቱ አለ። አንድ፣ በእማሬአዊነት (ሊተራሊ)፣ ገና አንድ ሺህ አካባቢ አመትዎችን የቆጠረ ዕድሜ ያለው የቅርብ ጊዜ መግባቢያ ስለሆነ ነው። ሁለተኛ፣ በፍካሬአዊነት፣ ወይም ጥራት ነው። አምልቶ የሥልጣኔ አባል መሆን ገና ስላልጀመረ በአገልግሎቱ አንጋፋነትን ያላካበተ ቋንቋ ነው። የቀደሙ የሀገርአችን ታሪክዎች በግዕዝ ሲፃፉ፣ አማርኛ ከመደበኛ ልዉዉጥ እምብዛም አትሻገር ተብሎ አለ። ለምሣሌ፣ ዛሬ የሥራ ቋንቋ እንደሆነ ቢቀጥልም እንኳ፣ የልሂቃን ቋንቋነትን አልተሾመም። ምሁርነት እና የትምህርትም ሂደት ማለት ይቻል አለ ሙሉኛ እንግሊዝኛ ተገልጋይ ነው።አማርኛ ታሪክ ላይ ያልጎላ አሽከርነት ይዞ ሳለ፤ በዝማኔ ትትረት ደግሞ እንደእዛው የተገለለ በመሆኑ፣ ገና የአገልግሎት ወጣት ቢባል ቢበዛበት እንጂ አላነሠውም። ጉዳዩ ከእዛ የራቀ ነው። ወጥ ዘመንአዊ ሥራዎች በቋንቋው መቶ አመቶችን እምብዛም ሳይዘሉ እሚገኙ ናቸው። ሦስተኛ፣ ቋንቋው ላይ መሠረትአዊ ጭቅጭቅዎች ያልጠለሉ በመሆንአቸው፣ አንዳንዴ፣ ከይዘት እና ገለልተኛ ሚዛን አንፃር፣ ፍካሬአዊ እንጭጭነትን ልንለጥፍለት ሁሉ እምንገደድ ነን።
ባይተዋርነቱ ሁለት አመክዮዎች ያመጡበት ነው። አንድም ከስልጣኔ ጎዳና እሚገባውን ፍላጎት ማግኘት አለመቻሉ ነው። አንድም ደግሞ ምስኪን ቋንቋ መሆኑ ነው። ይህኛው ባይተዋርነት በሁለት መንገድዎች ነው። አንድም በከተማ ስለእሚነገር እና ምንጩ ገጠር ሆኖ ሳለ እዛ ያለው አማርኛ በአለበት በመቅረቱ ከተማ ያለው አማርኛ ስርመሠረቱን ስለእረሳ ወይም ስለሣተ እና ስላደገ ነው። ሁለተኛው፣ ገጠር ያለው አማርኛ፣ ጥንትአዊ መሠረቱን፣ ታሪክአዊ እና በበዙ መስፈርትዎች የተሻለ አቅሙን ቢይዝም፣ ከዘመንአዊ ስልጣኔ ግን እሚከትተው ባለመኖሩ ነው። ይህኛው ሲጠቀለል፣ የገጠሩ እሚሻል መሠረት እና አቋቋሚዎች (ኢለመንትስ) ቢይዝም ዘመንአዊነትን ግን በተመለከተ ሌጣ ነው የከተማው ደግሞ በራሡ ቀለም ጥቂት ዘመንአዊነት ለራሱ ቢያለምድም የገጠሩን አላብአዊያን የተመለጠ ስለሆነ፣ ባይተዋርነቱ ከመገኛሥፍራዎች አንፃርም የተፈፀመ ይሆን አለ ማለት ነው። በተለየ ግን፣ ይህን እሚዳስሥ አርዕስት ለብቻው ለመፃፍ እምሞክር ቢኖርም፣ ይህ የባህል ክፍተት (ቮይድ) ጭምር ነው እሚለውን እግረመንገድ ልጠቁም። ሁለቱም አርዕስቶች በእየግላቸው በጥቂት ተወያይተው አሉ።
በአዲስአበባ ዩንቨርሢቲ ህግ ትምህርትቤት፣ በአስመራ ጭምር በዳኝነት ያገለገሉት ዕዉቅ የህግ የመጀመሪያው ሀበሻ ሙሉ ፕሮፌሰር ጥላሁን ተሾመ የመማሪያ ክፍልዉሥጥ ቃል ነው። አቶገበየሁ ማንኛውንም መንገደኛ እሚወክል ስም ነው።
በከፍተኛ ደረጃ ሲመዘን ቋንቋው በሁለት ጎራዎች ኋላቀር ነው። አንደኛው፣ ሠዋሰውአዊ ወይም ቅፅአዊ ድክመቱ ነው። ለምሣሌ፣ ‘በቤትህ ዉስጥ ቆይ’ እሚለው ትዕዛዝአዊ ዐረፍተነገር፣ መንታ መንትያ ስህተትዎች አሉት። ይህም ድግግሞሽ ነው። ‘በቤትህ ቆይ’ ወይም ‘ቤትህ ዉስጥ ቆይ’ እሚሉት ሙሉ ከቀደመው የበለጠ ዐረፍተነገርነት አላቸው። ‘በ’ እና ‘ዉስጥ’ አንድ አገልግሎት ሰጪዎች ናቸው። መተካካት ቻይ ናቸው። በዘመነ ቋንቋ ግን እንዲያገለግሉ ይህ መደጋገሙ፣ የቋንቋውን ቀልጣፋነት ቀንሦበት አለ። ይህ ብቻ አይደለም። መንትያው ተመሣሣይ ድግግሞሽ አብሮ አለ። ‘ቆይ’ ሲል፣ አንተ እሚለው ሁለተኛ ወገን ወንድ ንጥል ተዉላጠሥም በዉስጠአዋቂነት (ኢምፕላይድሊ) አለ። ‘ቆይ’ ብለን አንቺ፣ እናንተ፣ እሷ፣ እኛ፣ እነሡ፣ አለማለትአችን፣ ይህን ልዩ ተዉላጠሥም ብቻ እሚያመጣልን ስለሆነ ነው። ግን ይህ ቋንቋ በሠመጠ ደረጃ ስላልተመነደገ፣ ይህ አንተ በአረፍተነገር ግንባታ ሂደት ግን እሚደጋገም ነው። እጅጉን ብዙ ጊዜ ይህ ህፀጽ በሠፊው አማርኛ ላይ ተጣብቶ አለ። ለምሳሌ፣ በእዚህ አረፍተነገር፣ ‘በቤትህ ዉስጥ ቆይ’ እሚለውን ‘በቤትህ ቆይ’ ወይም ‘ቤትህ ዉስጥ ቆይ’ ብንለው እና ከመንታ ችግሩ አንዱን ብንጥል፣ የቀረው መንትያ ችግር፣ ይህ የተዉላጠሥም ድግግም ነው። ‘በቤትህ’ እሚለው በአንተ እሚለውን ገልጦ አለ። በእሷ፣ በእናንተ ወዘተ. እሚል ፍች የለውም። ሁለተኛ ወገን ንጥል ወንድ ተደራሽን የደረሠ መልእክት ነው። ግን፣ ቆይ እሚለው ሲመጣ፣ ተመሳሳዩ አንተ እሚለው ተዉላጠሥም ይደገም አለ። ይህ ግን ባሽ አደጋም አለው። ሦስተኛ አንተ ደግሞ በገሀድ ሊገባ ይችል አለ። ለምሳሌ ‘አንተ በቤትህ ዉስጥ ቆይ’ ቢል ኖሮ፣ ሦስት ጊዜ አንተ እሚለው ተገልጦ አለ። አስፈላጊ እማይሆንበት ሁኔታ ውስጥ ይህ ከተገለፀ ችግሩን ያወሣስበው አለ። በጠቅላላው፣ ይህ ኢስነምጣኔአዊ (ኧንኢኮኖሚካል) ቋንቋነቱን፣ በአንድ አረፍተነገር እንኳ ያለውን ያልተመቻቸ አገልግሎቱን እና የአንጎል ብሩህነትን መቃረኑን አስመልካች ነው። ሁለተኛው ችግሩ ደግሞ፣ ዘመንአዊ የልሂቅነት (አካዳሚክስ) እና ጥበበምርምር (ሳይንሥ) አቅም አለመሸከሙ ነው። የልሂቅዎች እና ምሁርዎች አማርኛ በማንም መደዴ መንገደኛ እንኳ እሚታወቅ መደበኛ ቋንቋ ነው። ከመደበኛ መለዋወጫነት ዘልሎ፣ የሠላ ዘመንአዊ የልሂቃን (ቴክኖክራትስ) እሚዘውሩት ቋንቋ አልሆነም። በተለይ፣ ከቀኃሥ. ጀምሮ እስከ ደርግ መዉረድ ግን ይህ የተገመሠ ችግር ነበር። አማርኛ የጎለበተ የጥበበምርምር ቅጅዎችን የቻለ አቅም በይፋ መሠብሰብ ላይ ነበር። በዋናው ፅሑፍ ይህ ዉይይት ገፋ ተደርጎ አለ።
በ ቸ እና ሸ ተጋደሉ ብለው ብዙዎች የደርግ እና ተቃዋሚዎቹን አመፅ እና ግድያን አቅልለው ወይም በስህተት ይገልጥ አሉ። ዳሩ፣ ያ የቋንቋ ጉዳይ በወቅቱ ዋጋ እንደነበረው እንጂ ሌላ እሚያስመለክተው የለም። ጉዳዩን ግን በማሣሳት የድንገት አመፅ ዉጤት ወሳጅ ሆኖ የተሾመው አብይ አህመድ (ኮሎኔል፣ ሊቀምሁርዎች)፣ በ2010 ክረምቱ ላይ “…በ ቸ እና በ ሸ መበላላቱ ያብቃ…በ ሸ እና ቸ ተከፋፍሎ መገዳደሉ ባይኖር ኖሮ…” ብሎ በመናገሩ ከፍተኛ ዉግዘትን ተቀብሎ ነበር። (“በ ቸ እና ሸ ሞቱ??? በግጥም መልስ” ን ተንቀሳቃሽምስል ይመልከቱ። ፍኖተ ርዕይ፣ https://m.youtube.com/watch?v=y385biNur-E, ህዳር 2013
መደበኛው ሥነ እና ኪነ ጥበብዎች፣ የሚታወቀው ሥነዉሳኔ በሞላ ማለት ይቻል አለ፣ አደባባይአዊ ልዉዉጡ ሁሉ፣ እና የትምህርት እና ዳግ-ምርምር (ሪሰርች) ክፍሉ፣ ወዘተ. ከፍተኛ የቋንቋ አቅም መደበኛአዊነትን እንደአጨቀ እሚስተዋል ችግር ነው። የድምዳሜው ነቁጥ እሚጎተተው አዳዲስ ቃልዎች ከመጥፋትአቸው፣ ተርታ አማሊዝኛ ከመብዛትአቸው፣ ምሁርአዊነት እሚሸት ቀለምአማ አማርኛ ባለማደጉ እና በዘመነ ቀኃሥ. እና ደርግ የነበረውም በመክሠሙ፣ ወዘተ. አማርኛ ቀጥኖ አለ ነው።
ባለማባራት፣ አምባግነናአዊ ዘረዘዴ (ታክቲክ) ስለሆነ ብቻ፣ ኢትዮጵያን እንደጥንቱ ሀያል ማድረግ በእሚሠኙ ወይም በእሚያያዙ ቱልቱልቴዎች (ፕሮፓጋንዳ) ህዝቡን መዘብዘቡ እንዳለ ነው።
በጊዜ ዐዉድ የተነሣ፣ የተስተካከለ እና የቀረበ ነገር እንደማለት ነው።
ይህ የአማርኛ እና እንግሊዝኛ መደባለቅ፣ አማሊዝኛ እሚሰኘው፣ በጠቅላላ ያለ የመደባለቅ እዉነትን ገላጭ ነው። እንግሊዝኛውን ለቅንጦት፣ መደበኛ አማርኛ ባለማወቅ ወይም በመስነፍ በመዝለል፣ ወዘተ. የእምንደባልቀውን መደባለቅ ይህ ፅሑፍ እሚደግፈው የሆነው ነጥብ አይደለም።
የቋንቋዎች ዉህደት ሢባል መዋዋስን እሚገልጠው አይደለም። ቋንቋዎች የተለያዩ ቃልዎችን ከሌላ ሊበደሩ እና ሊያስቀሩ ቢችሉም የአማሊዝኛ ፍች ግን አማርኛ ቋንቋን እየተጠቀሙ፣ አብሮ እንግሊዝኛን መቀላቀል ነው።
አማሊዝኛን በተመለከተ እሚነሡ ችግርዎች ከዉሠት ጋር አንድ አይደሉም ማለት ግን አይደለም። ዞሮዞሮ፣ ሞላጎደል በዉጤት ተመሣሣይ እሚሆኑበት ጊዜ ስላለ፣ ብዙ ችግርዎችን አብረው ይጠነሥስ አሉ። ለምሣሌ፣ የፍካሬ ፍችን፣ የአንድ ቋንቋ መብሠል እና መሥፋትን፣ የአንጎል ወጥ መልእክት አሣሳልን ወዘተ. እሚያኮመሽሹ እንደሆነ ክርክርቴዎች (ኧርጊመንትስ) አሉ። ሥለ እዚህ ለግሉ የታቀደ ፅሑፍ እስኪደርሥ፣ ለጊዜው ይህን መግቢያ ብቻ በእዚህ እንዲህ ተገልጦ እንለፈው።
፲፩ ለምሣሌ የተለያዩ አዳዲስ አማርኛ ቃልዎች በእዚህ ፅሑፍ አሉ። መደበኛ አማርኛ ዉስጥ ከትተንአቸው እነሡን መልመድ እሥኪከወን ድረሥ፣ አሁን በጠቅላላው እሚሠጡት ድባብ ጉደኛ (ዊርድ) አቻ ይመስል አለ። ይህ ግን ቋንቋውን በግል አቅሙ ለማወፈር አስገዳጅ ተግባር ነው። ዳሩ፣ በአንድ ወቅት አማርኛ ያጣአቸውን ቃልዎች መዉለድ እና ወዲያው ወደ አማርኛ ከቶ ማቋቋም ሂደት ፈላጊ ነው።
፲፪ በአንድ ወቅት መከወን እሚችል እንዲሁም ወዲያው ወደ መደበኛው አማርኛ መስረፅ እሚቻለው አይደለም ብቻ ሣይሆን፤ የተሞከሩ አዳዲስ ቃልዎች እንኳ ገና እሚሻሻሉ እና በእየምርምሩ እየተሻሻሉ እሚገነቡም ጭምር ናቸው። ሲጠቀለል፣ ገና ያልተወለደው ዘመንአዊ አማርኛ በሂደት ብቻ እሚካብት ነው። ለነገሩ፣ አንድመነሻነጥብ የሆነን ይህ ጊዜፈጂ፣ አቅም ፈላጊ የአማርኛ መዘመን እስኪከወን አማራጭ የማምጣት ፍላጎት መሆኑ ዳግ-ይጠቆም።
፲፫ የቋንቋ እና አመለካከትን እጅለእጅ መጠባበቅ ለማብራራት መድከም አስፈላጊ አይደለም። የተወሠነ ቋንቋአዊ አቅም የተወሠነ የማሠላሰል አቅም ነው። ከቋንቋ ጥናት በዘለለ፣ ይህ ስነጥበብ እና ስነዉሳኔን የማረከ መረጃ ነው። ሀገርዎች ለማደግ አንድም ቋንቋን ሲያዘምኑ፣ መንግስት መስራች ተቋምዎች እዉቀት ሲያጥርአቸው ወይም አምባግነና ሲያያዙ፣ ቋንቋን ማላሸቅ አንዱ ምግባርአቸው ነው። ለምሣሌ፣ የ ጂየርጅ ኧርዊለ 1984 ብሉይ (ክላሲክ) ልብወለድን መመልከትም በቂ ነው። አብሮም፣ የኢትዮጵያን ዝቅተኛ የማስተማር እና የአስተዳደሩ ቋንቋ ቸልታን ማያያዝ ተገቢ ነው። ብዙ ጥናትዎች፣ ፅሑፍዎች፣ ዘገባዎች፣ ትልምአቅጣጫዎች (ፖሊሲስ)፣ ክርክርዎች ወዘተ. የትምህርት ጥራትን እሚናፍቁ እና የኢትዮጵያን የዘርፉን ከፍተኛ ዉድቀት እንሚያረጋግጡ ናቸው። ለምሳሌ የከፍተኛ ተቋምዎች ተማሪዎች ኢብቁ ሆነው መመረቅን በተመለከተ፣ Ethiopia’s “Half-Cooked” Graduates, ሣሙዔል ጌታአቸው፣ አዲስፎርቹን ጋዜጣ፣ https://addisfortune.net/columns/ethiopias-half-cooked-graduates/, (ህዳር 2013) እሚለውን ጠቅላይሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ እንኳ የለብለብ ተማሪዎች እንዳሉን ያመኑበትን ፅሑፍ መመልከት በቂ ነው። አማርኛ በግሉ፣ እንዲሁም የሁሉም ትምህርትዎች መጨረሻ መግባቢያነቱ እና የስራ ቋንቋነቱ ላይ አብሮ ከእዚህ መዉደቅ ቀማሽ ነው።
፲፬ የኢህአፓ. ከፍተኛ አመራር የሆኑት ለ ፍኖተ ርዕይ ትመ. (ትእይንተመስኮት) በሰጡት ቃለመጠይቅ እንደገለጡት፣ የጥሀም. (ጥቅል ሀገርአዊ ምርት = GDP) ስላሻቀበ እና ትንንሽ መንገድ እና ህንፃዎች ስለተገነቡ የኢህአዴግ. መንግስት ሀገር አለማ ብሎ ለመቀበል አይቻልም። የአፍሪቃ እና ጥቁርዎች መኩሪያ እንደነበርንው፣ በነፃነት፣ በዕዉቀት እና ፍትህ ስንኖር እና ተሰርቆ ከተረፈ እርዳታ እና ብድር የተገነቡ ጥቂት ነገርዎችን በቀናአዊነት መቀበል ከባድ ነው። ኢትዮጵያ ኋላቀር በመሆኗ በስፋት እና ፍጥነት ማደግ ይገባት ነበር። አንዳንድ ጊዜ፣ ደርግ ቢቆይ የብራዚል ስነምጣኔ ይኖረን እንደነበረም እሚናገሩ አሉ። ደመልከቱ፦ “የዛሬ 24 ዓመት ኢህአዴግ አዲስ አበባን ባይቆጣጠር ኖሮ ዛሬ የኢትዮያ እድገት ከብራዚል ጋር ይስተካከል ነበር፤” ጉዳይአችን ጡመራ ወይም ዘሀበሻፖስት፤ http://www.zehabesha.com/amharic/archives/41799, ህዳር 2013።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s