Categories
ሥነዉሳኔኛ (About Politics)

የህልምአችን ኢትዮጵያ፡ እንደ ጠባቂያዊያን ስላለመዘናጋት

እንደ ህልም አጋሪዎች ወይም አላሚአዊያን ሳይሆን እንኳ ጭራሽ እንደጠባቂአዊያን ስላለመበላሸት ስለመስበክ፨

የ ተአዶ. (ተንቀሳቃሽ አሀዝአዊ ዶሴ = PDF) ስሪቱን እዚህ ያግኙ፨


ኢትየጵያን በመልካም ጥበቃ እሚጎመጇት ብዙ ልጆች አሏት። ተስፋ ቆርጠውባት አያውቁም። ማለት ይቻላል እነዚህ ሁሉም ሀበሻዎች ናቸው። ያደገች ሀገር ብትኖረን ብለው ባለማቋረጥ በመመኘት የሚጠመዱ።
ብዙዎቹን ስለእዛ ህልም፣ ዝርዝርአቸውን ሲጠይቋቸው፣ መልሳቸው ‘አንድ ቀና መንገድ ከተከትልን ይህ እድገት መጥቶ፣ መልካም ኢትዮጵያ እምትባል ሀገር ይኖረናል’ ባዮች ናቸው። ከቀናአዊነትአቸው የተነሳ በልቦቻቸው የተለያዩ ምኞቶችን ከመወሸቅ ጀምሮ ለህልሙ እጅግ መደበኛ ትግልን እሚያደርጉም አሉ። ትንሽ እማይባል ጊዜም እስከ አንድ ዘርፍአዊ መታገል ዉስጥ እሚገቡለት እና ሀገርአዊ መስዋእትነትን እሚከፍሉለት ጭምር ሁሉ አሉ።
ለምሳሌ፣ አንድ ዘፈኑ ላይ ቴዎድሮስ ካሣሁን እነዚህን የኢትዮጵያ መልካም አላሚዎች ወክሎ ያቀነቅናል። እህል ይዞ ምድሩ አረንጓዴ ሆኖ፣ ሆዱ ዉስጥ ግን እረሃብ ብቻ ስላለ ተናዶ ይጠይቃል። በእርግጥ፣ በታሪክም ሆነ ባላሥጣልንው ሀገርአዊ ሂደትአችን ላይ፣ ጠኔያምነታችንን እሚሸፍንልን ነገር ከቶ ተሣክቶ አልተገኘልንም። እንዲያውም መራብ እና መቸገር እየበዛብን ነው። ሳይቋረጥ ለረዥም ጊዜ፣ በቋሚ የምድር የከፋ ረሀብተኞች ዝርዝር ቁንጮ ላይ በቋሚነት አለን። ስለእዚህ፣ ትክክለኛ መነሾ አተያይ ተከውኗል።
ቴዎድሮስ መራባችንን ነቅሶ፣ ግን በማብራሪያ ፍለጋው፣ ሠው መውደድ አለመቻሉን እንደ ‘አስራቢ አመክዮ’ ይወቅሠዋል። ይህን ጭብጥ፣ ይህ ዘፋኝ በዚህ ነጠላ ዘፈን ምርቱ እሚነካካው አይደለም። ዘወትር እሚጎትትብን መገለጫ የሆነው ሃሳቡ ነው። በኢትዮጵያዊያን መሀል መፈቃቀር ሥላልተቻለ፣ በመሀከላችን መተሳሠብን ስላራቅን፣ ዘረኝነት ስላበዛን፣ ሀገር ማፍቀር ወይም ማስቀደም ስላልተሳካልን፣ እነእዚህ ሁሉ፣ የማደግን መንገድ እንደሚዘጉብን እና እንደሚያሥርቡን እሚነግረን ሁሌም ነው። ባለማቋረጥ፣ ያቀነቀናቸው ሃሣቦች መተሳሠብ፣ ቀና ማሠብ፣ አብሮነት፣ ወዘተ. መዉጫ ጎዳናችን ናቸው ብሎ ነው።
ሲጠየቁ እና ሲመልሡ፣ ይህ ጥቅልል ሃሳብ ብዙዎችን የሀገራችን ደግ አላሚዎች እሚያስማማአቸው ፍሬጉዳይ ነው። ወደ ቀናአዊነት እንድትለወጥ፣ ሀገራችን የጎደላት ይህ በአንድ ቅርጫት እሚከተት የመዋደድ-ጥያቄ አጀብ ነው ባዮች ናቸው። የስሜት ጉዳዮችን ማሠልጠን እንዳለብን አዉቀውታል።
ነገርግን፣ ይህ ለተርታ እና መደዴው (ሜዲዮክር)፣ የሚታይ ያልበሠለ ትልም ብቻ ነው። የሀገር ጉዳይን አደብዝዞ ማየት ያስመለከተው መዉጫ ነው።
ስለእዚህ፣ በዉጤቱ፣ ይህ ወገን፣ የጠባቂያዊያን ጎራ ነው። ለመደበኛዎች የችግር አፈታት መነሾአቸው፣ ደራሽ ካላገኙ፣ ማብቂያአቸው፣ የሆነ እይታ ነው። በጠቅላላው፣ አይነተኛ ሣቢስሜት (ቲፒካል ሰንሴሽን) ብቻ ነው። የመነሸጥ እና ‘የአቦ በናትህ አትጨናነቅ’ ሀልዮታ (ኧቲትዩድ) ነፀብራቅ፣ ተርታ ስሜትአማዊነት (ቪሤሪያሊቲ)፣ የጎተተው የመፍትሄ ክር።
ጠባቂያዊያን ሀገር እንድትለወጥ፣ ስሜትአማአዊ መሠናክሎች እንዳሉብን በማስረዳት፣ እነዛን መሻገር መዳኛችን ነው ባይ ናቸው። ልክ የስሜት ጉድጓዶችን መድፈን፣ መሬቱን እንደሚያስተካክለው እንጂ ቤቱን እንደማይገነባው፣ ከሌላውም አፍራሽ ጠላት እንደማይጠብቀው ያልታየቸው ይመስል። ወይም ተደብቆባቸዋል ነው ነጥቡ፤ በእርግጥ።
ሥንተሳሠብ፣ አንድነትን ስናዘምምበት፣ ፍቅር ይኑረን ስንል፣ ወዘተ. ምድሩ፣ ስነዉሳኔው (ፖለቲክስ)፣ ሽልፍኖት እና ፈጠራ (ቴክኖሎጂ ኤንድ ኢኖቬሽን)፣ ስነምጣኔው (ኢኮኖሚ)፣ ህግ እና ፍትሕ ዘርፉ (ሎው ኤንድ ጀስቲስ ሴክተር)፣ የወጣት እና መጪ ትዉልድ ጥያቄዎችን እና ፍላጎቶችን፣ እየባሰ የመጣው አየርንብረት እና ተፈጥሮ ሀብት መመናመን፣ ዓለምአቀፍ ግንኙነት፣ ማእከለትዉልድአዊው (ኢንተር ጀነሬሽናል) የግንባታ ሥራዎቹ፣ የታሪክ አተረጓጎሙ፣ ዋናው ባህልአዊ ለዉጡ፣ ወዘተ. አፍከፍተው የኛን ጉርሻ እሚጠብቁን ቁልጭ ያሉ ጉዳዮችአችን ናቸው። ለማያልቁት ቀመርአዊ ጥያቄዎች፣ አንድ የስነልቦና ወይም ስነምግባር መፍትሄ እሱም መፈቃቀር እና አንድንት ተብሎ የተጠቀለለ መፍትሄ፣ መጠቆም፣ ገደል ከታችነት ነው። ለሃጃቹህ ማለት ደግሞ፣ የእነዚህ ጎራዎች መንገድ ነው። እንዋደድ እንጂ ከሠማይ ወይም ከከርሠምድር የሥራፈጠራ እና ስነምጣኔ ጥበብ ሁሉ ይፈልቅልናል ከግዴለሽነት ጀርባ የመጣ ነው። ጥያቄ ሁሉ በፍቅር ይፈታሉ ማለት እነዚህ የሀገር እድገት ምሠሰዎችን ሰይጣን አድርጎ መሳል ነው። በፍቅር ሰይጣን ቢሸነፍም፣ ሀገር ግን አይገነባም። በመፈቃቀር፣ በመተሳሠብ ወዘተ. ግንኙነት ያምራል እንጂ፣ መፈቃቀር ወደ ግንብ እና ሀኪምቤት አይለወጥም። መፈቃቀር ወይም አንድነት በሀገር ግንባታ ሂደትአዊ ዉበቶች እና ግብዓቶች እንጂ ከቶ እና ከቶ ፍፃሜ አይደሉም። ምክንያቱም፣ እርምጃ አንድ፣ የጠባቂያዊያን መፍትሄዎች ማለት ነው፣ የብልፅግና መቋጫ ከቶ አለመሆናቸው ነው። የማደግ ምስጢርን ፈፅሞ አለመመለሳቸው እንዲያውም አለማወቃቸው ነው። ተርታ እና መደዴ የሀገር ናፍቆት እና መዉደድ እንጂ፣ ይህ የዋናጅረት (ሜይንስትሪም) ሀገር ትልም አይደለም።
ነገርግን፣ የልሂቅአዊያን (ኢንተለክቹዋልስ) ፈር፣ ሌላኛው መዉጫ ነው በማለት የኢትዮጵያን መለወጥ ከዕዉቀትም እሚያቆራኙ ክንፎች አሉ። የእነዚህ ጎራ ደግሞ፣ ሁለንተናአዊ ስሌትን ወደጨዋታው መጥራት ብቸኛው መንገድን አድርጎ መረዳት ነው። ለተራ ስንበታ የሚሸነፉ መደዴዎችን፣ የቀደሙትን ጎራዎች፣ እነዚህኞቹ ደግሞ ይፀየፉታል። አንድ መሆን፣ መፈቃቀር፣ መከባበር፣ መተዛዘን፣ የሠው ፍጥረት ተፈጥሮ አድርገው ይመለከቱታል። በባህል ለውጥ ቅርጫት ብቻ ይከቱታል። እንጂ፣ ሙሉ መፍትሄው ከእዛ እንደሚዘልግ በማሠላሰል ተገቢ ብለው ያሠፉታል። ለተቸገረች ኢትዮጵያ ደገኛ መፍትሄ ማሠስ ሲገባ፣ ከባህል አንዱን የአብሮነት አመለካከትን ነጥሎ በኢፍትህአዊነት በማጎላት መሥበክ፣ ሀገር መሣደብ ነው ይሉታል። በተፈጥሮው፣ አምላክ ሠውን አብሮ እንዲኖር፣ እንዲዋደድ አድርጎታል። የተፈጥሮ ህግ ነቢብአዊያን (ቲዎሪስትስ) እንደጨረሱት፣ ሠው ተፈጥሮ-ሜዳ (ስቴት ኦፍ ኔቸር) ዉስጥ እሚፋቀር ፍጥረት ነው ይሉታል። የመከፋፈል እና መጠላላቱ ነገር እጅግ የረከሠ ስነዉሳኔ (ፖለቲክስ) ዉጤት እንጂ፣ የተፈጥሮ ጉድለታችን አይደለም ይሉታል። ጊዜአዊ ሴራ እና ቀድሞ አለማሠብ ሀብትን በፍትህ ያለማዳረስ የፈጠሩት አለመስማማቶች እንጂ፣ ህያው ያለመዋደድ ችግሮች ስለሌሉብን፣ ስለፍቅር እና አንድነት መሥበኩ ተራነት ነው ይሉናል። በኋላ ማብቂያ ላይ እንደምናየው፣ ይህ የስሜት አሻሽሉ እንድትለወጡ ስብከት፣ ሀብትን ያከማቹ፣ ወይም በሥልጣን እሚገኙ፣ ይዞታአቸውን ላለማስነካት በቀመሩት ወይም እነሡን ገሀዱ ስለተስማማአቸው ቸልተኛ በመሆናቸው የሚያንፀባርቁት ሥብከት ነው እሚሉንም አሉ። ቴዎድሮስ ‘ኢትዮጵያ’ አልበሙን ለጋዜጠኞች ሲያብራራ እንዳለው፣ ከረዥም በዘር የመከፋፈል ስነዉሣኔ (ፖለቲክስ) ቆይታ በኋላ ሀገሪቷን ማከም ስለሚያስፈልግ፣ ሀገራዊነትን ማቀንቀን በመፈለጉ በሀገር ስም ስራውንም አልበሙንም መሠየሙን እና ‘ኢትዮጵያ’ ማለቱን አብራርቶ ነበር።
ይህ የጠባቂያዊያን ጎራ እይታን አብራሪ ነው። ህክምናው፣ ቴዲ እንዳለው፣ ከተፈበረከ በሽታችን ለመፈወስ እንጂ፣ በሽታውን ፈጥሮ ካስተላለፈው ከኢህአዴግ. ቀድሞም፣ ከነበረው ከረሀብ፣ ኋላቀርነት፣ ጋርዮሽ-አስተኔነት እና ቤተኛው የድህነት በሽታዎቻችን እሚያክመን አይደለም። እንዲያ ያልተብራራውም፣ እንዲያ ስላልሆነ ነው።
ሊቅአዊያን፣ ሀገርን ማከም በዘመንአዊ ሀገርአዊ ስነልቦና ፍብረካ፣ ቁጥጥር፣ እና እላይ የተዘረዘሩት ሠፊ እና ጥልቅ ጥበበምርምርአዊ (ሳይንቲፊክ) መንገዶች ነው ይላሉ። ቀደም ብሎ ዛሬ በእነዚህ ጉዳዮች ላይ በመነሳት፣ ትዉልድአዊ ዳናን መፈብረክ ነው እንጂ በወዲያውአዊ መፍትሄ ላይ ሁሉን አቅም ማባከን አይደለም ባዮች ናቸው። ሁሉ ፍላጎት፣ አቅም እና ሀብት፣ ለእረዥሙ ጉዞ ዛሬውኑ መነሳት አለበት። ከአለምቂጥ ተኾኖ፣ ብዙ ፍልሚ አለ። የተርታ ስነዉሳኔ ችግሮችን በፍቅር እና አንድነት ነጥቦች ብቻ ተክቶ የህልሟን-ኢትዮጵያ ጉዞን ማቀጨጭ፣ እንደ ተሳሣተ ጉዞ እሚቆጥሩ የእዚህኛው ጎራዎች ናቸው።
በእዚህ ፅሑፍ፣ የኢትዮጵያ ቀና ለውጥን እሚመኙ ጠባቂያውያን እና ሊቅአዊያንን ገነጣጥለን ለመተርጎም ባንችልም ፍቺያቸውን በንዑሥ መዝገበቃልአዊ አቀራረብ ግን አየን። ይህም፣ አሁን እንደተረዳንው ተራ አረዳድ እንዲወለድ ለማስቻል አይደለም። አስጊ እዉነትን ለመጠርጠር እንድንችል ነው። እነዚህም ሁለት ሥጋቶች አሏቸው።
አንደኛ፤ የሀገር ስነዉሳኔ (ፖለቲክስ)፣ በእነእዚህ የጠባቂያዊያን ወገኖች ሀሳብ እንደተያዘ በመቅረቱ፣ ትውልዱን ወደ ሊቅአማአዊ ጎራ እሚያዘምት ፊትወራሪ በአያሌው ከስሟል እሚለው ነው። የእረዥሙ ጎዳናአችን ጭራሽ ተዘንግቶ፣ በተራ፣ ማለትም ገና መነሻ በሆነ፣ የአንድነት ጥያቄ ናላችን እየዞረ በአጭሩ ቀረን ወይ ነው። ቀድሞ፣ በቅርብ ታርሪክአች ሁሉ፣ የሀገር ፍቅርአችን ንፅሥነዉሳኔ (ዴሞክራሲ)፣ ፍትህ፣ የህግ የበላይነት፣ ወዘተ.ን ለማስተካከል በእሚደረጉ ትግሎች የሚገለጥ ነበር። ይህ ተገቢው መንገድ ሆኖ፣ የህዝብ የበላይነት እና ልዑዋላዊነትን፤ የአዋቂዎች ሀገር እና አስተዳደርን መጓጓቱ እሚያጋድለን ለኢትዮጵያ እምንከውነው የትግልአችን ቀለሙ ነበር። ስለእዚህ የመጀመሪያው ሥጋት፣ ሀገርን እምናልምበት ሚዛን ተዛብቶ፣ ለነፃ፣ ፍትህአዊ እና ስነምጣኔአዊ ብርቱ መንገዶች እምንፋለመው፣ በተራ አንድ የመሆን ፍላጎት አሽቆልቁሏል ነው። ሀገረመንግስትን እሚቆጣጠሩም፣ በፀረ-ዘር ክፍፍል ጥያቄዎችአችን እየተጨዋወቱ፣ እረዥሙን የስልጣኔ ጠኔ-ማስታገስ ጉዞ በአመቺ ደረጃ ሊዘነጉት በቅተዋል። ህዝብን ቸላ ብለውት አለመነካትን አሥርፀዋል። መንግስት እና ተቃዋሚዎች፣ በንገድ፣ ህግ፣ ፍትህ፣ ሽልፍኖት (ቴክኖሎጂ)፣ ባህልአዊ ለውጥ፣ ሀያል ሀገር የመገንባቱን ፍሬነገር፣ ወዘተ. ከመወያየት እና ስለእነሱ መፋለምን በመገሸሽ እና ባለማንሳት ላይ ናቸው።
ሁለተኛው ሥጋት፣ ስለዘረኛነት እሚያቀነቅኑ ዘውገኞች ወይም አንድነት እሚቆጠቁጠን ነን ባዮች፣ ስለ ዘረኛነታችን ወይም ሀገር ወዳድነት መሆን እሚያስፈልገን መሆኑን በመናገር ብቻ፣ እኛን እሚያሾሩን በቆሸሸ ጎዳና ሆኗል እሚለው ነው። የመልካሟ ኢትዮጵያ ህልማችን፣ ጥንት በብዙ መንገዶች ፈረኛዎች (ፓዮኒርስ) የነበርንባቸው ምሠሶዎች መገንባቱ ቀርቶ በሌጣ መቦጫጨቅ ህክምና ላይ ስለማተኮር እየተስማማን አሁንአሁን ሠንብተናል። ሀገር ግንባታ እሚሠኝ ሀረግ እና ጓደኞቹ በመሪዎች እንኳ አይዘወተርም። አንድነት እና መከፋፈል እሚሉ ነቁጦች ጆሮ አደንቁረዋል። ታዲያ ሁለተኛው ጉድለት፣ በአንድ እንሁን ወይም እንከፋፈል ፈሊጥ አመቶች እየተራመዱ እንደቀልድ ሲያልፉን ይኸው ከስረናል ነው እሚለን። ይልቅም፣ ለከፋፋይ እና አንድ አድራጊዎቹ፣ በቂ የመጨዋቻ እና የፊትአዉራሪነት ክብርን መቀዳጃ ብቻ ሆኗል፣ በመሀከልየህልሟ ሀገር ጉዳይ ተሠርቋል ነው።
እንደ 1984፣ ጅዎርጀ ኧርዊለ፣ እሚመሥለው ጥቅሞችን ለመጋራት እና ሀብትን ለመቆጣጠር ሆንተብለው የተፈጠሩብን ነጥቦች ናቸው ባይ ነው። አንድ እንሁን፣ አአይ ይቅር፣ በሚሉት ክንፎች አስብቶ መጓተቱ፣ ለላይኛው አካሎች፣ የዉስኑን ሀገር ማስተዳደር ስፍራ እና ጊዜ (መቼት)፣ ስጦታ አድርጎታላቸዋል ባይ ነው። ዘረኛዎች እና ሀገርተኛዎች። በእየዘርፍአቸው፣ ስለዘረኛነት ወይም አንድነት ጥቅም እና አስፈላጊነት ያቀነቅኑልናል። በግዙፍ ዘርፎችአቸው፣ ስለ ጉዳዩ ሁሉ መገናኛብዙሃዎችአችንን ይሸፍኗቸዋል። ዉሎ አዳር፣ ነጋጠባ ከብሉዩ (ክላሲክ) የህልም ኢትዮጵያ ግንባታ ፍልሚያው ተፈልቅቀን፣ በመሀከል ስልጣን መግዣ የሆነ የአንድነት እና ክፍፍል ጭብጥ ወርሮን አለ። ሁለቱ ያያፈኑን ጎራዎች፣ እና በየትኛውም የቀረ መሀከል ስፍራ የተንጠለጠሉ፣ ወይም እሚያገለግሉ፣ የሥልጣን ሥፍራዎችን፣ ጥረቶችን፣ ፍሠተንዋይ (ኢንቨስትመንት)፣ ትኩረት (አቴንሽን)፣ አይምሮታ (ማይንድሴት)፣ ብሔርአዊ ስነልቦና (ናሽናል ሳይክ)፣ ወዘተ. ሁሉ ሸብበውብናል።
ለእዚህ ጥረቶችአቸው ምላሽ ሀገር መገንባቱን ማፍረሳቸው ዐብዩ ምላሽ ቢሆንም ያ ግን አይታያቸውም። እነሡ፣ በመሀከላቸው፣ የሠሩት ድንበር በራሣቸው ህግና ደንብ (በተለይ በስውር ያሉ) በያሉበት የበላይ አድርገው ይጠብቋቸዋል። ብዙ ጥቅሞችን ያገኛሉ። የአስገብቶ አብሮታዊነት (ሙቹዋሊ ኢንክሉሲቭ) በመሆን አብሮ መሰንበት የህቡዕ ደንብአቸው እምብርቱ ነው። ማንም ዘልሎ በስፋት አያጠቃም። በተመጣጠነ መጠን ለጨዋታ ያክል ግን መጎሻሸም አለ። ዉጤቱ፣ ሀሰተኛ ጠላት መፈብረክ ማለት ነው። በያሉበት እየተጎሻሸሙ አደጋ በማንዣበብ፣ ለመከላከሉ ግን እሚያስፈልጉ እንደሆኑ ስእል ይስላሉ። በመሀከል፣ እነሱ ይጠቀማሉ። ህዝብ በጨለማ መኖሩ ሳይሠበርለት ይቆያል።
በሁለተኛው ሥጋት መሰረት፣ አንዱ የአምባግነና ጫፍ፣ ይህ ስለመሆኑ፣ ኧርዊል ሲናገር እነዚህ ሀያላን ጉልበቶች ለመጣጣል አይነካኩም። በያሉበት ተከባብረው ግን ጠላቶች ናቸው። በእዚህ ኑባሬአዊነት (ስታተስ ኩዎ)፣ እኛን ግን ይይዙበታል ይለናል። በተለያዩ የእሚያሸብሩ ነጥቦቻቸው፣ ሀገር ተጠፍንጎ እሚቀር ይሆናል።
አሁንም ይህች ድሀ ኢትዮጵያ ሀገራችን እንደማንኛውም የምድር ሀገር ተስፋ አላት። ተስፋው በመሬቱ ላይ አይደለም፣ በእኛው ላይ ነው እና፤ እኛ ከታጠቅን ደግሞ ስለእማያቅተን፣ ስለእዚህ ተስፋውን እኛውን እራሳችንን ካደረግን፣ እውነትም ተስፋ አለን። ሦስተኛውን ዓለም ከስር ሆና ብትመራውም፣ ያም ሀቅ እየተረሳ ቢመጣም፣ በእርግጥ ምሽት ሁሉ ነጊ ነው።
እንጠቅልል። የሀገራችን ብሔርአዊ ትርክት ሁሉ፣ ተስፋ አለን ከተፋቀርን ወይም አንድ ከሆንን እና ተስፋ የለንም እንበጣጠስ ላይ ታስሯል። እጅግ፣ አታካች ሁለት ቆሻሻ ጉዳዮች ላይ። አንድ መሆንን ማሳካት ሁሉም መፍትሔ አይደለም። መፈቃቀርም የስብእና እንጂ የሀገርአዊ ስነዉሳኔ ቀጥተኛ፣ ከምንም በላይ ብቸኛ፣ መልስ አይደለም።
የሀገር ግንባታ ትግል ግን በእዚህ ኋላቀር ጎዳናዎች ተፋፍሞ መዝቀጡ አይቻለውም። ሆንተብለው በሂደት የተወገዱ ብዙ እና መነሻ ጥያቄዎች አሉ። እነእሱ መፍትሄ ስለሆኑ፣ የህዝብ አይኖች ግን በቆሻሻ ጉዳዮች እንዲጠመድ ተደርጓል። ዓለምአቀፍ የመቻቻል ታሪክን ገና ጥንትአዊው የታሪክ ዘመኖች ዉስጥ ያፋፋምን፣ እርስበእርስ እንድንቻቻል እንደዋና ጉዳይ ሆኖ በቀጣይነት ተጠይቀናል። ይህም፣ ለእዚህ ዉድቀት መቀጠል በሚኳትኑ እና ያንን ትልቁ ስራቸው ባደረጉ በሀገር ጉዳዮች ፊትለፊት በምናያቸው ሰዎች የተሰጠን ክህደት ነው።
ዘረኛነቱን ያንበለበለው፣ እጅግ ተራ የወጣቶችን አቅም አስቀድሞ ያለመመልከት ኢአዋቂነት ሲሆን፣ እሱን በቀላሉ ከማከም፣ ችግሩንም ሆነ ሀገሩን ወደ መዋዋል ተኪዶብናል። ወዲያው የቀደሙት መሪዎች፣ ለችግሮቻችን ቁብ ባለመሥጠት ወይም ቢያንስ በመዘናጋት ሀገርን በመበዝበዝ እረዥም ወርቅአማ እድሜዎችን ወስደው ሄደውልናል። የመጡት ደግሞ ተገቢውን መንገድ ከመዉሰድ እና ተምሮ ከመምራት ላይ አልታዩም። የተተወውን በሽታ በማስመልከት፣ እናክመው ብሎ በመስበኩ በመጠመድ፣ በተራቸው የስልጣን እና መሪነትን መቼት/መካንጊዜ (ስፔስታይም) በመስረቅ ላይ ናቸው። ይህን ካመንን፣ ሀገርአዊው ያልተቋረጠ ክህደት፣ እጅግ የባሠ እየሆነ እንደመጣው፣ እሚታየን ይሆናል።
ቀጣዩ ዐብይ ጉዳይ፣ ዘረኛነት ይዉደም፣ ስለሀገር እናስብ ከሆነ፣ እነሆ ይህ ስልትአዊ ሙስና (ሲስተሚክ ኮራፕሽን) እንዳታለለን እንወቅ። ኢትዮጵያ ጥያቄዋ አንድነት፣ ፍቅር ወይም ዘረኛነት አይደለም። ያ የተመረተ እንጂ ገሀድአዊ ወይም ነባር ወይም ቢያንስ የህልምአችን-ሀገር-ግንባታ ሂደት የመጨረሻው ጥያቄ አይዘለም። ዓለም የድሃድሃ ህዝቦች ነን። ማለትም፣ የስነልቦናአችንን ዉስን መድረክ የተቆጣጠሩብንን ጥያቄዎች መፋለም አለብን። ከእዛ የባሡ መሰረትአዊ ጉዳዮችን አልፈን ብዙ እምናብላላቸው ነገሮች እንዳሉን ማሥታወስ ግዴታ ነው። በእዛ መስመር ስንገባ፣ ይህ የብሄርተኛነት፣ ተፈቃቃሪነት፣ ወዘተ. ነጥቦች በእራስሠር (አዉቶማቲክአሊ) ይስተካከላሉ። ለምሳሌ፣ በቂ የስነምግባር፣ እዉቀት እና ስነልቦና ስልጠናዎች እና ስራ ዕድል ለወጣት ዜጎች ማስፋፈቱ ብቻ የዘውገኞችን አካሄድ በአያሌው እሚያጠፋ ነው። ማለትም፣ ዋናዋና ጉዳዮችአችንን ክደናል። በምትኩ፣ ይህ የጠባቂአዊያን አተያይ ወጥመድ አድርጎ ይዞናል።
ሀገርን ከስሩ ለእዚህ ትዉልድ ተስማሚ አድርገን ገና አልመሰረትንም። እጅግ ጥልቅ እና ሰፊ ቀዉሶች አሉን። ስለእዚህ፣ ከፊት እምናያቸው፣ ፍቅር እና ጥላቻ ሲሠብኩ እንዳታለሉን እንወቅ። አንድ ስንሆን እና ስንፋቀር፣ ሁሉ ጥያቄ ያገጣል፣ እሱም ተረስቷል እና። ግን፣ እነዚህን እሚያሳሥቡን መሪዎች ሲያታልሉን፣ እኛም በጠባቂያዊያን ጎራነት አብረን ተስማምተን የሀገር መለወጥ ተስፋን በእዛ ብቻ፣ በአቂያቂያዩ ‘መፋቀር እና አንድነት’ ጉዳዮች ነሁልለን፣ ከሳልን፣ የወደቀው የታሪክ ክፍላችን ለመቀጠሉ እሚጠራን አንዱ አመክዮው ነን።


ቢንያም ኃይለመስቀል ኪዳኔ
ወልቂጤ፣ ህዳር 05፣ 2013 ዓም።

By Binyamhailemeskel

Hey there! If you want to know about me, I just like fun, commonsense wisdom, and human love. Let us live a bright today changing tomorrow into brighter.
Regards,

2 replies on “የህልምአችን ኢትዮጵያ፡ እንደ ጠባቂያዊያን ስላለመዘናጋት”

ልክ አሁን (ታህሳሥ 03፣ 2013፤ በ ኢሣት. ትመ. (ትእይንተመስኮት) የ የኔታ ቲውብ፣ ይነጋል ሀገሬ እሚሰኝ ዝግጅት ላይ (ህዳር 25 ቀንዎች ቀደምብሎ የተቀረፀ) ተንቀሳቃሽ ምስል የሆነ ዝግጅት እያየሁ ነው። ዳኛቸው ወርቁ (ዶ/ር) አትሮንስ ላይ ቆሞ ፖለቲካ ፍልስፍና በአማርኛ ለታዳሚዎች ሲናገር አደመጥኩ።

ከተናገሩት ጥምቆራጭ ጭብጥ መሀከል፦

ቀኃሥ. ከስልጣን ሲወገድ፣ አበቃ የኢትዮጵያ ችግር ተባለ። ግን የእኛ ቋጠሮ ንጉሡ ላይ ብቻ አልነበረም። ደርግ መጥቶ አልተስተካከለም። የኛ ችግር ደርግ ላይ አልነበረም። ኢህአዴግ. ሲወድቅ እና ትህነግ. ሲደመሠስ ‘አሁን አረፍን’ እሚል ነገር ስሠማ ያለፈው የተደገመ መሠለኝ! መፍትሄው ትክክለኛ አቢዮት መከወን ነው። ያ ደግሞ አንድ ፈላስፋ እንዳለው የተቀየረውን መንግስት መለወጥ አይደለም። ተረኛነት አምጪ ሁኔታውንም መቀየር ነው። አብዮት እሚሳካው፣ ሀገር በ ንፅስነውሳኔ (ዴሞክራሲ) እሚመሠረተው ቀጣይነት ያለው ንግግርዎች (ኮንቨርሴሽን) ሲከወን ነው። አሁን ገና ሥራውን መጀመር ነው ያለብን ለሀገር እንነሳ እንጂ መዘናጋት አይገባም፤”

(ቃል በቃል አልተቀነጨበም)። ብቻ ሀሳቡ፣ ያልተቋረጠ ኢትዮጵያ መፈንገል ያቃታትን ብሔርአዊ መክሸፍን ስለማክሸፍ ነው። ዘወትር በእየትውልዱ፣ አብዮትን የእየትውልዱ ክብረበዓል ከማድረግ፣ ተገቢውን ስራ መከወን ያለመዘናጋቱ ትርጓሜው ነው። ንቅዓተ ህሊና በማበልፀግ፣ ሀገርአዊ እና ሰብአዊ ዉህደትአችንን በማግዘፍ፣ ስነምግባር እና ሀቀኛነትን ከጓዳ ወደ ፖለቲካ በመሰተር፣ አንድ ሀገር በመንፈስ እና ስነልቦና (ሳይክ) በመስራት፣ ባህልአዊ ለውጥ በመከወን፣ የገዘፈውን በእራስ እጅዎች (የህሊና ደወል ላይ በዓሉ እንደሰበከው) እና ተጠያቂ እና ልዑዋላዊ አስተዳደር ሀገርን በዘመንአዊ ስልት ማቋቋም መጀመር አለብን። ገና ባልተጀመረ ስራ መጠበቅ በመቀጠል እና ባለመንቀሳቀስ፤ የጠባቂአዊያን ብሔርአዊ ዕዳ ጉዞን እናክሽፍ፨

Like

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s