Categories
ሥነዉሳኔኛ (About Politics)

ሠላም ሻጭነት እና ሠላም ገዢነት፤ ያልተዳፈነው አምባግነናአዊ ጎዳና በኢትዮጵያ ዳግ-ነብስ ሢዘራ

ሰላም እየተሸጠ እና እየተገዛ ሙሰኛነት በኢትዮጵያ እንዴት እንደቀጠለ፨

Peace Selling and Peace Buying: Resuscitation of the Unclosed Road of Dictatorship in Ethiopia
A brief note
Binyam Hailemeskel kidane

አጭር መነሻፅሑፉን በተአዶ (PDF) ይዉሰዱ፨

አጭር ጽሑፍ
በ ቢንያም ኃይለመስቀል ኪዳኔ
binyamael@gmail.com
ጥቅምት፣ ፪፼፲፫

የአለመታደል አይነቶች ብዙ ናቸው። የአምባግነና አይነቶችም። ከሞላጎደል፣ ብዙዎቹን የአምባግነና አይነቶች፣ (በተለይ በእዚህ ዘመን የበዙትን)፣ አንድ የመጨረሻ የእስትንፋስምንጫቸውን ግን በደንብ ማወቅ ይቻላል። ከሌላዎች ነገሮች መሀል፣ በመገለጫቸው ሠላምሻጮች ናቸው። የአምባግነና ተሸናፊ ህዝብም ሠላም ገዢ ነው። ሠላምሻጭ አምባገነን መንግስት፣ ህዝብን በኦሪቱ አምባግነናአዊ ሠንሰለት በታላቅ ጭካኔ እና በለየለት ፈላጭቆራጭነት እሚይዝ አይደለም። ያ የአምባግነና ዘመን በአለምአቀፍ ስልጣኔ እና ተቋሞች ተሸንፎ፣ ቢያንስ ለይስሙላ ብዙዎቹ አምባገነኖች፣ ዘመናዊ ስነስርአትአዊ ግብአቶችን ያካትታሉ። ስለእዚህም፣ እነእዚህን አጭበርባሪ አምባገነኖች፣ ጭምብላቸውን ገፎ አምባግነናአዊ ማንነነታቸውን ለመግለጥ በብዙ መንገድ መመዘን እና መኮነን ያሻል። ከእዚህ አንዱ መንገድ ደግሞ፣ ሠለምሻጭነትን እሚጠቀሙ እንደሆነ መመልከት እና ማጋለጡ ነው። ሠላምሻጭ መንግስት ማለት፣ አምባገነን ለመሆን በእጅአዙር እሚሠየም ሲሆን፣ የስልጣን ቲኬቱ ደግሞ፣ ሠላም አቅራቢነቱን በአስተማማኝነት መግለጡ፣ መስበኩ፣ እና ማድረጉ ነው። በስልትአማ ጎዳና አምባነንነትን አጠንክሮ እሚያቆይ ይህ ሠላምሻጭነት ምን እንደሆነ፣ መገለጫዎቹንም ጭምር እሚከተለው አጭር ጽሑፍ እሚዳሥስ ይሆናል።
ይህ ጽሑፍ ይህን እሚያደርገው ግን፣ በተለይ፣ ስለ “ቅናሼ-ሽቃቤነት” በማወያየት ነው። ይህ ደግሞ፣ በጉልህ እንደምታው፣ ሠላምሻጭነትን ለግንዛቤ አብቅቶ እሚያስከትል እና ጭብጡን እሚያስምግ ነው። እነሆበእዚህወዲአ ይኸው።

ቅናሼ-ሽቃቤነት

ሠላምሻጭአዊ የአምባግነና ስነዉሳኔ (ፖለቲክስ) ጎዳና ዉስጥ፣ አንድ ታላቅ መርኅ መቆሚያ ወለሉ ሆኖት አለ። ይህ በእጅግ ሠፊ ገላጭ (ቃል) መብራራት ይችላል፦ ቅናሼ-ሽቃቤነት። ቅናሼ-ሽቃቤነት ማለት አንድ ህልውኑባሬ (ስታተስኮ) ን ላለመቀየር ወይም ለማምጣት ሲፈለግ እሚወሰድ ዉጤትአምጣአዊ (ታክቲካል) የአምባገነኖች ወይም፣ በእዚህ እንደምንመለከተው ቀይመብራት ላይ ያሉ የእጩ አምባገነኖች እርምጃ ነው።
እሚሠራው ደግሞ፤ የወረደ ወይም ኢተፈላጊ እዉነትን ለህዝብ በቋሚነት በማስተማር ወይም ደጋግሞ እና ደጋግሞ፣ በማሣሰብ፣ ይህ ያለው ኢተፈላጊ ሁኔታ እንዲቀጥል ማድረጊያ ነው። ወይም እንዲመጣ መፍጠሪያው ነው። ኢተፈላጊ ሁኔታው በእርግጥ፣ አምባገነን መንግስትነት ነው። ይህ እሚወለደው፣ ቀድሞ ህልውኑባሬ ዘብ (ስታተስ ኮ ዲፌንደር) እሚሰኝ አካል ወይም ሁነት እንዲለወጥ ግፊት ሲበዛበት ነው። የእዚህ አካል ወይም ሁነት ምላሽ ግን፣ ህልውኑባሬው መልካም እንደሆነ መስበክ ወይም ሌላ ጎዳናዎችን በመጠቀም ማሣመን፣ ነው። ለእዛ ዉጤት ጫፍ እሚጠቀመው መንገድ፣ አናሽ እዉነትን መጠቆም እና ማሳመን (እሰኪገዛ ድረስ መሸጥ) ነው። ይህ ተሳክቶ ከተቀናበረለት፣ ህልውኑባሬ ዘቡ አዎንታአዊ ለውጥን ከለከለ ማለት ነው።
ይህ በሥነውሳኔ እና በተለየ ደግሞ ሠላምሻጭነት ላይ፣ ከፍተኛ የአምባግነና አሣኪነትን መጥራት ቻይ ነው። ሠላምሻጭ፣ ሠላምን ለህዝብ በገፍ አቅርቦት ያመጣለታል። ሠላም ፈላጊ ህዝብ ደግሞ ወዲያው፣ ከመንግስት እና ህዝብ ገበያው አቅርቦቱን ያጋብሣል። ይህ የሠላም እና ስልጣን ልዉዉጥ ሆነ ማለት ነው። መንግስትነት፣ ሠላም በመሸጥ ተቀላጥፎ ተጨበጠ። እልፍ መንግስትአዊ ጉልበቶች በመናኛ እና በዜሮ አፈፃጸም፣ ቅርጽ እና ደንብ ቸላ መባል ይችላሉ ማለት ነው። ብቻ ቁምነገሩ፣ ዋናው ሸቀጥ፣ የመንግስት ሠላም ጠባቂነት (አስከባሪነት) እና የህዝብ ሠላም ገዢነት ነው። በሠላም ወጥቶ መግባት ይጀመር አለ። ነገርግን፣ አምባገነን፣ ሠላም ከመሸጥ ዘሎ ለስነውሳኔ ገበያው የተለያዩ ፍትህዎች፣ እኩልነትዎች፣ መብቶች፣ ንጽስርዓት (ዴሚክራሲ)፣ እና እድሎችን፣ ለህዝቡ ወይም ለሀገሩ አምራች፣ መሪ፣ አቀነባባሪ፣ ተቆጣጣሪ እና አቅራቢ አይሆንም። ከአንድ መንገስት፣ ወደህዝቡ ብቻውን ሠላም መሸጥ ግን፣ ለህዝብሁሉ ባዶ ድስት ማቅረብ ነው። ምንም እንኳ፣ በዕቀዉቀቱ ስዩም፣ ባዶ ድስቴን በእሳት ልጣደው፣ ማጣቱን ያካፈለ ንፉግ አይባልም ቢልም፣ በእዚህም ስሌት ሠላም ማቅረብ ደግ ነው ቢባልም፣ ሠላም ግን ለማንም ሰውልጅ፣ ሰብአዊ ፍላጎቱን እሚቋጭለት በቂ መንግስትአዊ አገልግሎት ሆኖ አያውቅም። የበቂ ሃብት እና ፍትህ፣ የአኗኗር አዎንታአዊ ለውጥዎች፣ የነገን አቅዶ በላጭ አቅም መገንባትና ሀገርአዊ ዘላቂዋስትና ማቅረብ፣ ባህልን መጠበቅ እና ማሳደግ፣ ተፎካካሪ እና አለምአቀፍ መሪ መሆን፣ ወዘተ. እሚሠኙ ሰብአዊ ፍላጎቶች ሠላምሻጮችን የማርጃቀን (ኤክስፓየሪንግ ዴት) ያመጣባቸዋል። ሠላምሻጭ ደግሞ፣ የመጨረሻ አቅሙ ላይ ደርሶ ያለ ነው። ከሰላም ሌላ ማቅረብ እሚችለው ምንምን ብቻ ነው። መጨመር እሚችለው ነገር ከቶ የለውም። ብቃቱም፣ እዉቀቱም፣ ፍላጎቱም፣ ፈቃደኛነቱም የለውም። ቢያንስ፣ በተጨባጭ አንዱ ጎድሎት፣ ከሠላም አቅራቢነት መዝለል እማይችል የለዘዘ አምባገነን መንግስት ማለት ነው።
እንደተባለው፣ እሚሠራው በቅናሼ-ሽቃቤነት ነው። ያም፣ ያነሠ ነገርን በቀጥታም ሆነ በእጅአዙር በማስረጽ፣ ሠላምን በገበያው ማስወደድን ያደርጋል። ህዝብ ከዳቦ፣ ፍትህ እና መበልጸገ ይይልቅ፣ ማደሩን፣ ነብሱን ይጠይቅ ይጀምራል። በሁኔታው መደፍረስ፣ መንግስት ዜጋዎችን ማንነነታቸውን፣ ፍላጎታቸውን፣ አቅማቸውን፣ ያዘናጋል፣ ያስተዋል። በምትኩ፣ በሠላምገዢነቱ እንዲያተኩሩ ብዙ ያደርጋል። በመጨረሻ፣ ህልውኑባሬ ወደ ሠላም ሐሠሳ ያመጣቸው ዘንድ ይህ ቅንብር ያረጋግጥለታል። ያኔ እሚቸበቸበው፣ የተዘረፈው ሠላም ነው። የተሠረቀ ህዝብአዊ ሀብት – ሠላም – ተመልሶ ይሸጣል። መንግስት አይከስርም። ሠላም በመደልደል፣ በስልጣን ይደላደላል። ስለእዚህ፣ ሁኔታዎችን ወደታች ማዝቀጥ መነሻው ክሂሎትአማነት (ቴክኒክ) ሆነ ማለት ነው። ልክ የዘቀጠ ማህበረሰብአዊ ስብእና ከሠላም መናፈቅ ሲደርስ፣ ሽቃቤ (መሻሻል) የተፈጠረ ያክል፣ ሠላምን መስበክ ይጀመራል። መንግስት፣ ይህ ሲሳካለት፣ በቅናሼ-ሽቃቤ (ወደታች ወርዶ ወደነበረበት በመመለስ ወደላይ ተጨምሮ የተወጣ ማስመሠል) ይከውናል። ይህ ማለት፣ በቅናሼ-ሽቃቤነት ሃሰተኛ ለውጥ ማለት ነው። የመጨረሻው፣ የአምባገነን የማታለያ መንገድ ነው ማለት ነው። ወደላይ ባለመረማመድ፣ ሰርጎ በመመለስ፣ ለውጥ እንዳለ ማሣመን ማለት ነው እና። በእርግጥ፣ ይህ በስነልቦናም የተረጋገጠ፣ የመከራከሪያ እና ማሳመኛ ዘዴአማአዊነት (ስትራቴጂ) ነው። በመቶ እሚገዙትን ሃያ ልግዛው ብሎ ተስፋ በማስቆረጥ፣ ሂሳቡን በማጣጣል፣ ብቻ ዋጋውን ከመቶ በታች መግዛት አይነት ነው። ይህ ዘዴአማአዊነት ታዲያ፣ በቅናሼ-ሽቃቤነት፣ አዲሱ የአምባግነና ዘረዘዴ (ሞድ) ሆኖ በመሀከላችን እየጎነቆለ አለ። ይህም፣ እጅግ አንገት አስደፊ ጅማሮ ነው። በጽሑፉ መጠቅለያ፣ ይህን ከመወያየቱ ቀድሞ፣ ጥቂት ባጫጭሩ እሚነቃቀሡ ነጥቦችን አይተን፣ ሀሳቡን አጠጥረን እገንዘብ።

የሠላምሻጭ-ሠላምገዥ ሥነዉሳኔ መኖር ምልክቶች ወይም መገለጫዎች

 • ሠላም በሀገሩ በተለመደው ሚዛን ሲለካ በአስተማማኝ መንገድ ለህዝብ አለ።
 • በቀረ ከሠላም አቅራቢነት፣ ይህ መንግስት ግን መስራት ቢፈልግ እንኳ እሚችለው ግን ሌላ የለውም። (የራሱ አወቃቀር እና ተፈጥሮ አያስችለውም እና)።
 • ምንጊዜም ወለልአዊ ለውጥ ለማድረግ ፈቃደኛ አይደለም። ስርነቀል ለውጥ ምን እና እንዴት እንደሆነም እንኳ አያቅም። ቢያቅም አይተግብርም፣ አመክዮውን እና ዉጣዉረዱን አይችለውም።
 • መጨረሻቸው ከቶ ኢ-ዉብ ብቻ እንዲሁም ብቻ ነው። (በአቢዮት የመውደቅ እድሉ ከፍተኛ ነው፣ ከሰላም በላይ መኖሩን ዜጋዎች ዘግይተው መረዳታቸው አይቀሬ ነው እና)።
 • ሚዛኑ ተግባር ሲደረግ፣ (በተለይ) ቅኝገዢ አስተዳደር መሠል እንጂ ሀገርበቀል መሪ አይመስልም።
 • ኢአላሚአዊያንነት (ነን ቪዥነሪስ) አለ።
 • መደበኛውን ህይወት ባለማፈናፈን ጠፍንጎ መቆጣጠር ላይ መበርታት።
 • ገለልተኛ፣ ተጠያቂነት፣ ባለህግየበላይነት፣ ንጽስርዓትአዊ (ዴሞክራሲያዊ) ወዘተ. አስተዳደሮችን ማቅጠን፣ ማስመሠያ ያክል ማድረግ፣ ወይም አጥፊነት።
 • የድርጅት የበላይነት (ከህግ፣ ሀገር፣ ማህበረሰብ፣ መጭጊዜ፣ ወዘተ. የበላይነት በተቃራኒ ሆኖ) አለ።
 • ሙስና። (ኢተጠያቂነት የተንሠራፋ ነው። ምንም መከታተል እንኳ አይቻልም)።
 • የካድሬ ሠንሰለት እንጂ፣ የተወካዮች እንደራሴነት ዜሮ ወይም ይስሙላ ነው። (ሰዎች እሚመርጧቸው አያስተዳድሯቸውም። ስነውሳኔአዊው (ፖለቲካል) ድርጅቱ (ፓርቲ) ግን ይሾማል፣ ይሽራል፣ ያሸጋግራል፣ ያንሳፍፋል፣ ጡረታ አስገድዶ ያሶጣል፣ ይተካካል፣ ወዘተ.። በአጭሩ፦ አምባግነናው እንዲሰምር እና ህዝብአዊ ድምጽ እንዲነጠቅ ወይም እንዳይሠራ፣ ሹምሽር ሁሉ በድርጅት እሚከወን እንጂ የህዝብ ድምጽ የለም ወይም ቢያንስ ለይስሙላ ብቻ ነው)።
 • ከፋፋይነት። (ለስልጣን አመቺ ከመሆኑ አንፃር ብቻ ሳይሆን፣ ለሠላም አሻሻጡ አስተማማኝ ግብአት እሚሆነው በመከፋፈል ወይም ልዩትን በመስበክ የአደጋ እምቅ (ፖቴንሻል) ን ቢያንስ በህቡእ ኋኝነትአዊነት (ፖሲቢሊቲ) በማሳበቅ፣ አደጋውን ለመከላከል፣ መንግስትአዊ ህግአማአዊነት (ሌጂቲሜሲ) ማናሪያ መንገድ ነው።

ምንምን ሃቂቶች (ፋክተርስ) ሠላምሻጮችን ሊረዳቸው እሚችል ይሆናል?
ለሠላምሻጮች በስልጣን መጠንከር፣ ከእነሱ እና ጥረቶቻቸው በጨመረ፣ የጎንዮሽ ድጋፍ እሚሠጡዋቸው ተነባባሪ ምክንያቶች አሉ።

 • የኢንጽስነውሳኔ (ዴሞክራሲ) ፈርማህደር (ሪከርድ)
  ያለፈ ታሪክ ለዛሬአችን ጭራው ነው። አካሉ እንጂ ከቶ የተለያየ አይደለም። ስለእዚህከ የቀደመው ሀገርአዊ፣ መንግስትአዊ ወይም ህዝብአዊ ጊዜ፣ ታሪኩ በድሃ አስተዳደር የተበደለ የነበር ከሆነ፣ ብዙ ጭንቀት በቀጣይነት ባለማቋረጥ ሆኖ ነበር ማለት ነው። ይህ የወደቀ አኗኗር፣ የኑሮ መንገዱ ሆኖ ተለምዶ ከነበር፣ ባንድ ጊዜ ሊቀየር እሚጠጥር ማህበረሰብአዊ ዳገት ነው። ይህ የአሁንን ሠላምሻጭ እሚያግዝ፣ አንድ የኋሊትአዊ (ባክዋርድ) ሃቂት (ፋንተር) ነው።
 • የመደበኛ ስነዉሳኔአዊ (ፖለቲካል) ሩህአዊነት (ኮንሸስነስ) አናሣ ወይም ያሸለበ መሆን።
  ዓይነ-ግቡ የዜጋአዊያን (ሲቪሊያን) የመማር፣ እና ማወቅ መጠን ያነሠ መሆን ትልቅ ድጋፍ ለሠላምሻጮች ገድ ነው። ዘመናዊ ማወቅ ምን እንደሆነ ዜጋዎች ስለማያውቁ፣ ለአብዮትአዊ፣ አመፅአዊ፣ ትግልአዊ፣ ፍተሻአዊ፣ ተሳትፎአዊ፣ ወዘተ. ተካፋይነት ወይም ተሟጋችነት አቅም፣ የማይበቁ የሩህአዊነት (ኮንሸስነስ) ምንዱቦች ናቸው። ልእለብዙሃኑ ዜጋ፣ ከመሠረትአዊ ትምህርት ዉጭ ስለሆኑ፣ የተማሩትም በጥራት ስለእማይገኙ፣ ከምንም በላይ ደግሞ ትምህርት ከማህበረሰቡ የተደባለቀው ለቅጽአዊነት (ፎርማሊቲ) ያክል እንጂ እንደ ባህል ስላልተዋሃደ የምሁርዎች ሽባነትን (መደንዘዝን ወይም ስትራክቸራል ዲስፈንክሽን) በገሃድ ስላለ፣ ንቁ የምሁርዎች አደና በመንግስት ዘንድም ስለሚካሄድ፣ ወዘተ. የመደበኛ ዜጋው ሩህአዊነት የደረቀ ነው። ሠላም በመሸጥ ለሚገዛ መንግስት ገድ እሚሆንለት ግብአት የሆነው፣ ዜጎች ከሰላም በላይ እሚገባቸው እንደሆነ ስለማይረዱ እና እሚያስረዷቸውም ሆነ እሚሟገቱላቸው ስለማይኖሩ ወይም ስለማይበዙ ነው።
 • የተከፋፈለ ህዝብአዊ ታሪክ፣ ማንነት፣ ወይም ኑባሬ
  እዉነትም ይሁን ሀሰት፣ በህዝብ አእምሮ እና አረዳድ፣ የሀገሪቷ ህዝብ ወይም ወገን መከፋፈል ያለው ከሆነ፣ ጭራሽ ለሠላምሻጭው ጠቃሚ ነው። ወጥነት፣ ካልሆንም በልዩነቶች አንድነት ከተለመደ ግን፣ ሠላምሻጭንበቀላሉ ለመልቀቅ እማይታሰብ ይሆናል። ግን፣ በክፉው ስነሁኔታ (ሲናሪዮ) መንግስት በቀላሉ በማቃረን፣ በማጣላት፣ በማፎካከር፣ ወዘተ. በጋራ ግን ሁሉም ከምንም በላይ እሚሹት ሠላም እንደሆነ ያረጋግጣል ማለት ነው።

ቢሆንም፤ ዋናው የሠላምሻጭ ጉልበቱ ግን፣ የካድሬአዊ ስርአት፣ ሙስና፣ ጉልበታምነት፣ እና ጭካኔው ናቸው። ሃገርን በፈለገው በራሱ ምርጫው መሠረት ከማስተዳደር ይልቅ፣ እሚመረጡትን በይስሙላ የውክልና ትግበራ እና ዉጤት በማሽከርከር፣ ዋናውን ስልጣን ግን በድርጅትአዊ ታማኝነት ለካድሬዎች በመዘርጋት፣ የካድሬዎች ሠንሰለት ከቀበሌ እስከ ጠቅላይሚንስትርነት እንዲደርሡ ማድረጉ ነው። ይህ፣ የስልጣን ጥንካሬው መሠረቱ ነው። እነእዚህ ካድሬዎች፣ ለህዝብ የማገልገል ግዴታ የለባቸውም። ካጠፉ፣ እሚጠይቃቸው የለም። ቢበዛ ሲያጠፉ ተነስተው ወደ ሌላ ሹመት ይቀየራሉ እንጂ ተጠያቂነት ወይም የህግየበላይነት አሊያም ሌላ የንጽስነውሳኔ ማስተማመኛዎች የሉም፣ አይከወኑም። ድርጅታቸውን እንጂ ህዝብን ወይም ሀገራቸውን፣ ካድሬዎች ደግሞ አያገለግሉም። ስለእዚህ፣ ዘላቂ፣ ከድርጅት (መንግስት) የተሻገረ እና ሀገርአዊ፣ አስተዳደር ከቶ የለም። ከእዛ እሣቤ መፃረር የእነዚህ አካሎች ቆይታ መሠረታቸው ነው። ሠላምሻጭ ካለ፣ ይህ ሁሉ አለ እንጂ አይለወጥም።

ጠቅላላአዊ አገላለጽ እና አሁንአዊ ዐዉድ
መስከረም አልቆ፣ ዛሬ ጥቅምት አንድ ቀን ፪፼፲፫ (2013 ዓም) ኢትየጵያን አገኘናት። ባለቀው ቀን ግን የብልግና ድርጅት ኢህግአዊ ነው በማለት ህዋሃት እና አንዳንድ ሌሎችም ኢትዮጵያ የለሽ-መንግስት ትሆንበታለች ያሉበት ቀን አበቃ። መንግስት፣ ባለበት ግን ቀጠለ። ብልጽግና የሃገር መንግስት መሪ እንደሆነ አለ።
ይህ እንደሆነ ግን፣ በሃገርነት መቀጠሉ ቢጠቅምም፣ ከተንፋሹ ድርጅት እሚፈነጥቅ ተስፋ እንዳለ አንዳንዶች እሚናገሩ አሉ። ቢሆንም፣ የእዚህ ድርጅት አያያዝ ግን ጮራ ያስመለክት ከሆነ በተገቢ የሚዛን መስፈርቶች መመልከት እሚገባ ነው፤ ይህን መጠራጠርም አያስፈልግ ከቶ።
ታዲያ፣ የብልጽግና ድርጅት፣ ተስፋ እሚቸረው እንዲሆን የምን መስፈርቶችን አሟልቶ ነው? መልካም ነገሮች እንዳሉ ሁሉ ግን፣ እሚገዝፉት አስጨናቂ እና አንገብጋቢ አያያዞቹ ናቸው። በተጨባጭአማዊ (ቨርቹዋል) ወንፊት፣ የእዚህ ድንገተኛ ተቋም አያያዝ ሲነፋ፣ እሚወድቀው ተስፋ ለመሆን አይችልም።
የብልጽግና አያያዝ የደንበኛ አምባግነና ጎዳና ሆኖ ከታየው በላይ የበለጠ ምንም ሌላ አልሆነም። ሰላምሻጭነት ደግሞ፣ ከሌሎች ማታለያዎች ጋር ተነባብሮ፣ የእዚህ ድርጅት አዝማሚያ እየሆነ በጉልህ እያደገ ስለሆነ፣ ይህ ነገር በላጭ አስጊ ነው።
በመላው አለም፣ የሀበሻአዊያን ድጋፍ ለእዚህ መንግስት መሠጠቱ ከሃገር ፍቅር እንጂ ከድርጅቱ ድጋፍ አንፃር አይደለም። ነገርግን፣ ብልጽግና ይህን ፍቅረ-ሀገር መስኖ አድርጎ ወደ ድርጅትአዊ ጥቅም በመምጠጥ ላይ ነው። ወደ ሠላም አስከባሪነት እንዲመጣ እየተጎተጎተ እንደሆነ እና ሣልወድ በግድ አምባገነን ሆንኩ በእሚመስል አተያይ እሚመለከተው እንደሆነ እየተገለጠ ነው። የተለያዩ የጉልበት እርምጃዎች ወደ ሰላም አስከባሪነት እያዞሩት እና ያንን በቂ እያስመሠሉለት ነው። ዳሩ፣ ሠላምሻጭነት የአምባግነና ወለል እንጂ የተስፋ ፍች አይደለም። አካለ መንግስት፣ የተወደደ እእና የተፈጠረ ሠላምን በመሸጥ ብቻ ማተኮሩ፣ የአገልግሎት ቀለሙን እሚያጠቁርበት ነው። በተጨባጭአዊ ስሌት፣ እስከአሁን ያለው ሲደማመር፣ ቀሪው እየተሸጠ ያለው ሠላምብቻ እንደሆነ ጎልቶ እሚታይ ነው። የፈሣሽ (ፍሉይድ) ካድሬ መሠላል ከቀበሌ እና ወረዳ እስከ አምባሳደርነት ተዘርግቶ፣ ያለ ምርጫ፣ በፈላጭቆራጭ ድርጅት፣ ሠዎች ድርጅቱን ያገለግላሉ። ምንም ለውጥ በእዚህ የለም። ህዝብአዊነት የተረሳ መስፈርት እንደሆነ አለ። ብዙ መመዘኛዎችም አልተስተካከሉም። እንዳለ የቀጠለው ግን፣ ስርአት ከማቋቋም ይልቅ፣ ጊዜአዊ ጉዳዮችን ብቻ በማከም መጠመድ (ማታለል) እና ከምንም በላይ ህዝብ ሠላም እንዲያጣ ቸላ በማለት፣ ለሠላም እንዲጮኽ ማድረግ ነው። ይህ የተሳካለት ድምር እንደሆነ በመታየት ላይ ነው። ብዙዎች ሠላምን እንደሸቀጥ መንግስት እንዲሸጥላቸው በማልቀስ ላይ መሆናቸው የቀጠለ ነው። ይህ ግን፣ በተጨባጭ መስፈርት፣ ለአምባግነና ምስጅት (ረሲፒ) የሆነለት ነው።
ድርጅቱ፣ ሠላም እንዲደፈርስ በመተው፣ ወይም ስልጣንአዊ ግዴታውን ቸላ በማለት፣ ዜጋዎች በመጨረሻ ያሳኩትን መንግስትአዊ ለውጥ፣ የኋሊት እየከተተው ነው። መንግስት እንዲለወጥ ተደርጎ፣ አመጽ ሲያሸንፍ እና ኢህአዴግ አብይ አህመድን (ሊቀምሁርዎች) ሲሾም፣ ፍትህ እና ስርአትአዊ ለውጥ ተፈልጎ የመጣ ሀገርአዊ ትግል ነበር። ይህ ግን፣ ሂደት-በሂደት፣ መንግስት ሠላም በመሸጥ ብቻ ልዑል አሽከርነቱን በማደፍረስ አግበስብሶ እንደሚቀጥል ገሃድ ማሳያ ሆኗል።
ሀገርን፣ ሠላም እንዲርበው በመጋበዝ፣ ሠላምሻጭ ብቻ ሆኖ ተፅዕኖአማውን መንበር አባክኖ መቀመጥ፣ ግን የለዘበው አምባግነና ብቻ ነው። ሠላም አብሮ እንደተወለደ፣ በህዝብም መሀል እንዲሁ በነባር (ዲፎልት) እንደሚገኝ፣ አጥፍቶት ወይም እንዲጠፋ ቸላ ብሎ፤ ወይም በማናቸውም መንገድ፤ እኔ እየሸጥቁት ልቀመጥ አምባግነናአዊው ቋንቋ ማለት ነው። ሃገር እና ሰው፣ ከሠላም በላይ ብዙ ጥያቄዎች እንዳሉት ማን ያውቃል?!

By Binyamhailemeskel

Hey there! If you want to know about me, I just like fun, commonsense wisdom, and human love. Let us live a bright today changing tomorrow into brighter.
Regards,

One reply on “ሠላም ሻጭነት እና ሠላም ገዢነት፤ ያልተዳፈነው አምባግነናአዊ ጎዳና በኢትዮጵያ ዳግ-ነብስ ሢዘራ”

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s