Categories
መልካም ጥበብዎች Fine Arts

ድህረ-ገጽ (post-script) “መሥፍን፡ ጎንለጎን” ልብወለድ ላይ

ድህረገጽ (ፖስት ስክሪፕት) ለ መስፍን ጎንለጎን ልብወለድ፨

ይህ ቁንጽል ጽሑፍ በጎንለጎን ልብወለድ ላይ አጭር ተያያዥ ማብራሪያ ነው። አበልሺ ደወል (spoiler alert) እነሆከእንግዲህበእዚህወዲአ (nowhereby) ተሰጥቶ አለ፤ እነሆ። የእዚህን ውይይት ለመሳተፍ፣ ቀድሞ ልብወለዱን ማንበብ ተመካሪ ነው። ካልሆነ፣ የትርክት እና ትልም ዳሠሳው እሚነካካ ስለሆነ የቀዘቀዘ ንባብ ይሆናል። ለልብወለዱ ተአዶ. (ተንቀሳቃሽ አሃዝአዊ ዶሴ = PDF) ስሪት ይህን ማስፈንጠሪያ ጠቅአርጉ፨

ማስፈንጠሪያ አንድ።

ማስፈንጠሪያ ሁለት።

ትዉዉቅ፤
ጎንለጎን በ 20012 ዓም. መጨረሻ ለንባብ የወጣ ልብወለድ ትርክት (story) ሲሆን መነሻው እና መድረሻው የሀበሻዊያን አንድ አንኳር መሆን እሚገባው የስነልቦና ጉድጓድ ነው። ይህም፦ ቅድመ-ንድፍ የታዳጊዎች ማደጊያ መንገድን ማበጀት እና ተፈላጊ ዉጤት በቅድመንቃት የመታተር ፍልስፍናን እሚሰብክ ነው። ስለእዚህ፣ መጽሐፉ በአንድ ገሃድ ሃገርአዊ ችግር፣ ማነፍነፍ አድርጎ ያበቃ፣ ከብዙዎች መሀል ዐብይ ብሎ የተመለከተውን አንድ ማህበረሰብአዊ ስንጥቃት ከቅድመገጽ ቀድሞ (በታሳቢነት) አንስቶ ትርክቱን እሚጀምር ነው፨

ይህ ትርክት አጭር እሚሰኝ ሲሆን የዕድሜ-አወጣጥ (coming of age) ትርክት ነው። መሰረቱ ግልዮሽአዊነት ማህበርተኛነት ዉስጥ (individualism within socialism) ሲሆን ታዳጊዎች በመነሻ እድሜዎቻቸው ኃላፊነት በመዉሰድ እንዲያድጉ እና ሲያድጉ አመርቂ የማህበረሰብ አባል ሆነው ወደ አዋቂነቱ መደብ እንዲቀላቀሉ እሚከራከር ነው ማለት ይቻላል። ለምን? ማስመሪያው፣ ሰው እንደግል የማህበረሰብ አሃድ እና መነሻ ስለሆነ ነው። ማህበረሰብን ለማወቅ፣ አውቆ ደግሞ – ‘ወይ ማወቅ ደጉ’ – ለማሳደግ ከተፈለገ፣ ወደ ተተከለበት ስሩ መግለጥ ስለእሚያሻ ነው። ከግል ተነስቶ ግልዎች ሲደማመሩ ማህበረሰብ ስለእሚገኝ ማህበረሰብአዊ ቀመርን በእዛ መጠን እሚፈታ ሆነ። እና አንዱን ዜጋ ብቁ አድርጎ መልሶ ለጋራው እይት ዳግ-መደመሩን ደግሞ በግልጥ ታሳቢነት እሚጨምር ነው። ሁሉም ዜጋ ለየግሉ ብርቱ ከሆነ፣ ማህበረሰቡ በሚደመር ጊዜ ብረትአማ ነው። ስለእዚህ፣ በመሠረተ-ሀገር የሆነው ግለሰብ እና ወዲያው ከባቢው ቤተሰብ ዙሪያ መፍሠስ እሚያልም ትሁት ትርክት ነው፨

በስምንት ምዕራፎች እሚጠናቀቀው ትልም እሚወስደን ጉዞ ሲቋጭ፣ የጎንለጎን መርኅን አጥርቶ መመልከት እምንችልበት ስፍራ ላይ እንድንደርስ በማለም ነው። መቼቱ ሞላጎደል ዉሱን ሲሆን፣ ምናብቴ (fantasy) እና ገሃድ አርኪ ባልሆነ ዉህደት ባይሆንም ብቻ እንደ ነገሩ ግን “የተደባለቁበት” ነው ለማለት ይጋብዛል። ማለትም ግን፣ ገሃድ እና ምናብቴ፣ መደባለቅ እና መከሸን እሚገኝበት የአተራረክ መንገድ አይደለም፨

አጭር ዉይይት፤

የሰው ልጅ እና ስነፍጥረት (ክሪዬሽን)፣ መስተጋብር አላቸው፦ እንደ አቻ-ጓደኛ እንዲሁም አለቃ/ምንዝር። በየቱም አገነዛዘብ፣ ሃቅዎች ግን ገለልተኛ ናቸው። አንድ ገለልተኛ ሃቅ፣ ልክ ሰው ጣልቃ እስኪገባ ተፈጥሮ መለወጥ አትችልም እሚለው ነው፨

ማለትም፣ ሰው ሃቅን ለመለወጥ ከቻለ፣ ማህበረሰብአዊ እዉነትንም ለእሱ እንዲጥም አድርጎ ማጣመም ይችላል ማለት ነው። የእዚህ ለውጥ ትርታ ደግሞ የራሱ የዘረሰው ገጸባህሪ እና ማህበረሰቡ ያላቸው ህይወትአዊ ጠባይ ሲቀየር ነው። ይህ በተፈጥሮው ሲገኝ፣ ኢስልጡንነትን የያዘ ነው። በስልጣኔ በረራ ግን፣ ለምሳሌ ዘረሰው ባሪያ-አሳዳሪነትን፣ ፈላጭቆራጭነትን፣ መሃይምነትን፣ እሳት/ብርሃን የለሽ ጨለማን፣ ህግአልባነትን፣ ወዘተ. በመቀየር አዲስ ሽል-አኗኗር አልምዶ-ለምዶ ይገኛል። ይህ ወጥ የተደረገ ገሃድ፣ ሰው በልምዱ እና እውቀቱ፣ ተፈጥሮአዊ ገሃድን ወይም ሃቅን፣ ጣልቃሲገባበት፣ ህይወት (ለግለሰብ እና ማህበረሰብ) እሚለዋወጥ ሃቅ ነው ይለናል፨

ይህ ቀላል የሆነ፣ ከመለመዱ የተነሳ፣ የሰው ጥበብ ማስረጃ ነው። ታዲያ፣ በታሪክ የተረጋገጠ ስንኩል አኗኗር የመቀየር አቅም፣ በዘርፍ እና ጥልቀት፣ ከቦታ እና ጊዜ ወደ ሌላ ቦታ እና ጊዜ ቢለያይም፣ እሚቻል ሆኖ ገሃድነቱ ከታየን፣ ለእሚፈለግ ለውጥ ሁሉ ይቻላል መንፈስን ተከትለን እንነሳለን ማለት ነው፨

በእዚህ ሲሳካልን፣ ሠው ሠው የመለወጥ አቅሙን እራሱ ዘረሰውን እንደ ተፈለገው ለማሰልጠን ዕድል አገኘ ማለት ነው። ተመዥራጪው ተጽዕኖ ደግሞ – ማህበረሰብም እንደ ግለሰብእ መዋጮነቱ – አንድ ነጸብራቅን ሰልጥኖ ለሂወት አረዳድ እና አቀማመስአችን ማስመልከት ይችላል እሚለው ነው። ማለትም መሰልጠንን፨

ዘረሰውን ወደ አንድ የመሰልጠን ትልም ማስገባት ደግሞ በቀላል ስሌት፦ ስነልቦናውን መቆጣጠር፣ ከምኑም አስቅድሞ ይጠይቃል። እንደአለመታደል ቢያንስ ይፋ አኗኗራችን ዉስጥ፣ ዘመንአዊ እና ንቃተህሊናአዊ (ፕሮአክቲቭ) ጥረት ለእዛ ዉጤት ከመከወን አኳያ ገና እጅግ ለውጥን ያልተመሠረትን ሃገር ነን ማለት እሚቻል ነው። ሳይማሩ እሚያስተምሩ የሽማግሌዎች እና አዋቂዎቻችን አመራር፣ በስልጣኔ ቁሳቁሶች እና ዉስብስብ መስተጋብሮች መንገስ የተነሳ፣ ጨርሶውን ወጣት እና ታዳጊ ዜጋውን፣ በስልጡን ስነልቦና አማራጮች የመምራቱን ዕድል ደግሞ ተደርቦ መንትፎበታል፨

ታዳጊዎች ብቻቸውን ሆኑ ማለት ነው። ከሁለቱም፦ ከስልጣኔ ጣዕም እንዲሁም ጎንዮሽ ጉዳቶቹ በሙሉ፣ በሌጣ ተሞክሮ እና ዜሮ ብስለት ተፋጥጠውት አለ ማለት ነው። ፍልሚያው የታዳጊው እና በሃገራችን መሠል ተሞክሮ በማጣቱ ምክር እንኳ እማይሰጠው ወላጅ እንደመሆኑ ብዙ ስራዎች በታዳጊዎች እርካብ ላይ ካልፈሠሰ መዳረሻ አድማሱ ኢተተንባይ እና ዉዥምብርነት አለው። ከከፋ ደግሞ አሉታአዊነት ብቻ ነው። ማለትም፣ ሁሉም በጎ እና ክፉ ሥራ ሁሉ፣ ታዳጊዎችን እየጠበቀ ነው፤ በእነሱው እየተፈጸመም ነው፨

እንግዲህ ይህ ክርክርቴ (አርጊመንት) ዉሃ ከቋጠረ፣ አንዱ የዘመኑ ጭብጥ ታዳጊዎች የራሳቸው የነገ አለቃዎች ይሁኑ አንዱ መንገድ ነው እሚለው ነው። የታዳጊዎች ሙሉኛ (ፉሊ) ግለ-ኃላፊነት መዉሰዱ አማራጭ አካሄድ ስላልተወልን፣ ይህን መራር ኢትዮጵያአዊ ገሃድ መገዳደር የሁሉ ኢትዮጵያአዊ እና ባለድርሻአካሎች ግዴታ ነው።

አምባግነና ላይ እዉቅና ያገኘ ኢህአዴግ. እንዲወድቅ ዋነኛው መነሻ መሠረትአዊ እሚሰኝ ሠላም መጥፋቱ አልነበረም። ጭራሽ በብሔር የተከፋፈለ ሃገር፣ በአምባግነና እግር ሥር ወድቆም፣ ምንም ዴንታ ሳያሳይ ለሙሰኛ እና አጥፊ መንግስት እሚሰግድ ነበር። ነገርግን፣ ይህን የጭሰኛ ፖለቲካ፣ መሠረትአዊ ሰላም መኖሩ ብቻ እንዲቆይ አድርጎት ነበር። ሰላሙ ሲጠፋም፣ አምባግነናውን እሚጠይቅ አልነበረም። ብቻ ምኑንም ነቀርሳአዊ አመራር ሃገሪቷ ብትታገስም፣ አንድ ነገር ግን ይህን አምባገነን ጣለው። ይህም፣ ታዳጊዎች ቸላ ተብለው ማህበረሰብአዊ ዉጥንቅጥ ገሞራው ስለፈነዳ ነበር። ይህ ደመነብስአዊ አብዮት ነበር። እጅግ አስቀያሚው። ይህ ንጽስርአት (ዲሞክራሲ)፣ ፍትህ፣ ልማት፣ ደህና ሃገር መናፈቅ፣ ለልጆች ማሰብ ወዘተ. ያመጣው ስልጣን-ወገዳ አልነ አልነበረም። ይህ በደመነብስ፣ ሽሮ ልሶ ማደር ያቃተው ወጣት ስለበዛ ከመሞት ቀድሞ የፈጸመው ጣር ያመጣው ለውጥ ነው። ይህ በእርግጥ፣ የአለም-ጭራነት ነው። የተራበ፣ ፍትህ እና ልማት ነገንም እማያማትር እጅግ ያልተማረ ማህበረሰብ ፈርጣማ እና ለማድ መንግስት ሲገፈትር ጉድ ነው። የማህበረሰብአዊ እንጦሮጦስ ደረጃነት ማስረጃው ነው። የእዚህ ነጥብ መፍትሄው ታዲያ ዛሬም በዜሮ ተስፋ አለ፨

ይህ ስር-መሰረት የሆነ ነጥብ በብዙ መንገድ መታየት አለበት። ወዲያውአዊ (ኢሜዲየት) እና ረዥም-ጊዜ መፍትሄዎች ሊበጁ ይገባል። በረዥሙ እሚያዘው አንዱ መፍትሄ፣ ዛሬን ሳይሆን ነገን ቀድሞ መሳል ነው። ነገ፣ ይህን ጸረ-ኢህአዴግአዊ መሰል አብዮት እንዳያሳይ ለማድረግ የስልጡን ስነውሳኔውን ሀሁ ስለመጀመር በትልሙ ተነስቶ አይተን ነበር ማለት ነው፨

የሃገራችን ስነዉሳኔ (ፖለቲክስ) እንዳንቀላፋ እና አያያዛችን ከቶ እንደማያምር ማስረጃው ይህ አቢዮት በቂ ስለነበር ይህ መንገድ የተወያየ ነው። አሁንም ቢሆን፣ ወላጆች ከማሳደግ እና ዕድል ከመጠበቅ በቀረ ኃላፊነት ለመወጣት እሚያስችል የለሽ-ዕዉቀት ናቸው። እንዲሁም የፈጣን-ለውጥ ዘመኑ አኗኗር ደግሞ ተሞክሮ ስለሌላቸው ልጆችን ስኩ ወደፊት ላይ ለመጣል እሚያስችል አቅም የላቸውም። ከሃይማኖት እና ስነምግባር በዘለለ፣ ምስጥ አስተዳደግ መስጠት አይችሉም። የማያቁት ዘመን ላይ እነሱም ሳያልሙት ድንገት ስለደረሱ፣ ምንም ረብአዊ ድጋፍ ቀድመው መስጠት እሚችሉ አደለም። ወላጆች እኩል ከልጆች ለዘመኑ ባዳ ናቸው፨

ማለትም፣ መንግስት፣ ምርምር ተቋሞች ጥበበኛዎች እና እሚቻለው ሁሉ ፈጣኑን ተገቢ ምላሽ አትክልት አድርጎ ዛሬ መትከል አለበት። ታዳጊዎች ኃላፊነት ለምደው፣ ግልዮሽአዊ አርነት ተላብሰው፣ መጪጊዜን መተንበይ ተለማምደው፣ አንድ የሂወት መስመር አልመው፣ በስኬት ለመቋጨት መነሣሳት እንዲችሉ እሚገባው ሁሉ መደረጉ ስነዉሳኔአዊ ብልህነት ነው። ችግራችን ታውቋል። እሚበለጽግ የታዳጊ ጭንቅላት አይነተኛው የሀበሻ ጭንቅላት ሆኖ እያሳደገ ያለ ስርኣት የለንም። መፍትሄው ደግሞ፣ ከእዚህ አንኳር ቀይስህተት አንፃር፣ ይኸው መፍትሄ ነው፨

ቁም-አሸልብ ስነዉሳኔአችን ነቅቶ፣ የተገኘውን ስልጣን ተቆጣጥሮ አመቶች ከመቁጠር የዛገ ስነስርኣት እምኖደው ሃገር መፈልቀቅ አለበት። የተጣባን መሃይም ስነውሳኔ (ፖለቲካ) መፍረጥ አለበት። ነገን በመመልከት፣ ነገን በፈለግንው መንገድ ለመቀበል፣ ዛሬ መስራት ይጀመር። የእዛ መጨረሻ ደግሞ፣ ከነጥባችን አንፃር፣ ወጣቶች በጉልበት ወጣት እንዲሆኑ፣ ራስመቻልን ከታዳጊነት ይማሩ እሚለው ነው። በተፈለገው መንገድ ይህ ሊጠና፣ ሊታሰሥ፣ ሊተገር እሚችል ነው። ከእዚህ ትርክት አንፃር ደግሞ፣ ማንም የሌላቸው ድሃ ሄበሻዎች ይህን ሃላፊነት ለማልመድ ሲሞክሩ እንመለከት አለን። የወደፊታቸውን ከታዳጊነት ጀምረው መቆጣጠር እሚገባቸው ታዳጊዎች እንደ ህፃናት ክሩሴደርስ ሙሉ ኃላፊነቱን መዉሰድ፣ የጠበቃቸው እውነት ነው። እነናሆም፣ ብሩ እና የናሆም ጓደኞች ይህን ሃላፊነት ሲጋተሩት እንመለከት አለን። በግል እና በግል። ማንም እሚረዳቸው ተቋም የለም፦ በቀረ ቤተሰብ። ግን በአላቸው የነገ ስእል ዛሬ ዉስጥ በመሳል ሲጨነቁ እንመለከታለን። ግን በምክንያት ይህ ተከውኖ፣ በመጨረሻ ክፍያ ሲጎነቁል እንመለከት አለን። ሰሚ ከተገኘም፣ አልተማርንም እሚሉ እናቶችም ሆኖ አዋቂዎችንም እንደ መሰረተ ትምህርት በጥቂት አካቶ መንገድ አለ እሚል ስብከትም እሚአመጣ ነው፨

እግዚእአብሔር መልካም እድል ለእሚወለዱልን ሁሉ ይስጥ፣ ታዳጊዎችአችንም መልካሙ የመታተር እና መለወጥ ትልም ይገለጥልአቸው፤ ይቅናቸው። ከወላጆች በጊዜ ተላቅቆ የስኩ አኗኗር መስራች ያድርጋቸው፨
ሌላ እሺ ምን ይባላል፨

መጠቅለያ፤

ለመጠቅለል ያክል፣ ጎንለጎን በትርክቱ፣ ወጣቶች እሚሆኑ ታዳጊዎች ስኬትአማ እንዲሆኑ እገዛ ከዐዋቂው ክፍለ ማህበረሰብ ይፈልጉ አለ ብሎ ይነሳ አለ። ይህ እገዛ ደግሞ ትልቅ ባይገኝም፣ በተገኘው መንገድ ሁሉ ይሞከርበት እሚል ነው። መነሻነጥቡ፣ ስለእዚህ፣ ስኩ ወጣቶች፣ መልካም ስነስርኣት እና ባህል ዉስጥ እንዲአልፉ ማድረግ እና የስነልቦና ድጋፍ እንዲያገኙ ማድረጉ ግድ ነው ብሎ እሚከራከር ነው። ወላጆች ስላልተማሩ እና አዲሱ ትዉልድ በአዲስ ዘመን ዉስጥ ያለመሪ ለብቻው ስለቀረ፣ ለእዚህ ፍጥጫ ማሸነፍ እሚያግዝ፣ አንድ የማህበረሰብ ብልህ መንገድ መዘየድ አለበት። ድህነት ስለተቋቋመ፣ ልጆችን ማሳደግ እንጂ ደግ ነገር ማውረስ አይታሰብም፤ ቢያንስ እንደ ማህበረሰብ። ስለእዚህ፣ ቀላሉ ዉርስ መታሠስ አለበት። የስነልቦና አርነት፨

ያለ ስነልቦና ነፃነት እሚያድጉት እና፣ ወጣቶች እየሆኑ ያሉት ዜጋዎችአችን ስራ በመፈለግ እና በድንገት አድጎ ኃላፊነት ዉሰድ በመባል ቀውስ ዉስጥ በመስመጥ ላይ እሚገኙ ናቸው። ይህ ከመቶ ሃምሳ አመቶች ጀርባ ከተፈታልን፣ መፍትሄው ዞሮዞሮ ይህ የተባለው ነፃ እና ኃላፊነት ወሳጅ ወጣቶች የማሳደግ ሁኔታ ነው። ማለትም፣ መቼም እሚጠብቀንን ስራ ዛሬም እንደዘላለሙ አንተኛበት የሃሳቡ መሠረት ነው።

በመጨረሻ፣ ላገዙኝ ሁሉ ምስጋናዬ ይደገም። አመሰግንአችሁ አለሁ። ቻው፨

ቢንያም ኃይለመስቀል ኪዳኔ።

By Binyamhailemeskel

Hey there! If you want to know about me, I just like fun, commonsense wisdom, and human love. Let us live a bright today changing tomorrow into brighter.
Regards,

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s