Categories
My Outlet (የግል ኬላ)

ምእራፍ-፰

መስፍን ጎንለጎን ምእራፍ ፰፨

፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
፰ እናት ከብራ ልጆች ፈር ሲይዙ ወይም የመጨረሻው መጀመሪያ

የመጨረሻውን ምእራፍ በ ተአዶ. (PDF

የወቅቱ ድባብ መገለጫ፣ የቤቱ ግርግር እና አባታቸው ወሬ ሆኖ ነገሩ ሁሉ በሾረ መልኩ እየፈጠነ ሲከናወን ሰነበተ። ግርግሩ በመብልቤቱ ሲፋፋም ሌላ አዲስ ዜና ተቀላቀለአቸው። ብሩ ከጓደኛው ዮስ ጋር የ አአኅ. ጤና መካነዕዉቀት (ኮሌጅ) ዉስጥ እንደ ተመደበ ታወቀ። እሚ ማንባትን ተያያዘች። ብሩ እናቱን አቅፎ አበረታ። የመጀሪአ ልጇ ተለይቶ ወደ ሃኪምነት ለመለወጥ የመጨረሻ ጉዞውን ሊጀምር ሆነ። በአንድ ጎን ደስታ እና ስኬት በሌላው ደግሞ አአሟ ስለ ተፈተነ አለመርዳት መቻሏ ሆድዋን አብሶ አለቀሰች። ማረጋጋቱን ከውኖ፣ ብሩ ብዙ ድጋፍ እንደ እማይፈልግ እና በግል ብርታቱ እሚማር መሆኑን አሳውቆ መማሩ ብዙ ወጪ እንደ እማይጥልበት ገለፀ። የአያያዝ ጉዳይ እንጂ ለበቂ ተምሮ መዉጣት በቂ ሁኔታ እንደ አለ በግልጥ ሃሳቡን አሳወቀ። እሚ አማራጭ ስለ ሌለ በመራር እልህ ሆና በመመረቅ እና መልካም መመኘት ሁሉን ተቀብላ አለፈችው፨
ቤተሰቡ በተሰማው ደስታ ሲደሰት ቆይቶ አመሻሹ ላይ የተለመደ ቤተሰብ ጨዋታ ላይ መስ መመለሻው እንደ ደረሰ አሳወቀ። “ሦስት ቀንዎች ብቻ ቀሩኝ!” እራሱም ተገርሞ ሁኔታውን አሳወቀ። ክረምቱ ሲገፋ በመጠነኛ ንግድ መላመድ ሰንብተው አዲስ አመት ባልተለመደ አኳኋን ሊደርስ ሆነ። የእሚ ምርቃት፣ ልዩ አሸኛኘት እና መስተንግዶ ለወንድሟ በቀሩት ሦስት ቀንዎች ሲንከባለል ሰነበተ፨
የ መጨረሻ ሰሞን ድጋፍ ማድረግ ከቻለ መስ ናሆምን ከመሄዱ ቀድሞ ምንም ጉዳይ እንዲጠይቀው አሳወቀ። ናሁም ምስጋና ብቻ ቸረ። “ሁሉ ተሟልቶ ሁሉ በፈጣን ሃዲድ መስመር ጉዞ መግባት ላይ ነው!” መስ ይህቀረሽ እሚባል እርካታ ለ ማግኘት ሁሉን ፈትሾ ክፍተት አሰሰ። በእርግጥ በስተቀረ ከ ተግቶ መስራቱ ብዙም መጨነቅ አሁን የለም። ናሆም ያደረገው ስኩ ቅድመዝግጅት ደግ ደንበኛ ቁጥር እየሰበሰበለት ነበር። የተሳበው ደንበኛ በሂደት እየ ለመደ እና ሌላ እየተጠራራ ተወዳጅነቱም በዛ በዛ ብሏል። ይህ ደግሞ በቅድመዝግጅት ብቻ አልመጣም፤ ያን ብቻ ይዞ አልተጓዘም። ልክ መስ እንደ አሰበው ነ ትግበራ ው ወዲአው ወዲአው ክፍተትዎች ከ አሉ ናሆም ተጨማሪ አጢኖትዎችን በአካሄዱ ላይ አድርጎ ማሻሻልዎችን አደረገ። አብሮ ተተኪ ከማስተማር ጀምሮ በመነሳት፣ የእርሱን የአገልጋይነት እና ተቆጣጣሪነት ኢዘላቂነት አሰበ። ቢግን፣ ሁኔታውን እና ነገረ ጥበቡን ማስጠናቱን አልቦዘነም ነበር። ቀድሞ የደረሰበትን እርግጠኛ አያያዝዎች እና ነገርዎች ሁሉ ያስተምረው እና አብሮ ይሳተፍ፣ ጭራሽ በ ቀድሞ በመለማመድ ቢግ በእይታ መቆጣጠር ሥር ሆኖ ገልገል እና መወሰኑን ይከውን እና መድረሱን ይመዘን ነበር። ይህም አንዱ የንግዱ ስኬት ማስቀጠያ መንገድ ነበር፨
ደግሞ ብዙ ሌላ ጉዳይዎችን ጨምሮ አሻሻለ። ለ ምሳሌ፦ ከተማ ትንሽ ከሆነ ለእኛ ሃገር ንግድ ብዙ እንደምታ አለው። በአዲስአበባ ወይም ዓዉራ ከተማ፣ ነጋዴ አንድ ልዩጥቅሙ ሰው ሳይጨነቅ ከ የትም ይገባለት አለ። በአነሰ ከተማ ግን ነዋሪ አንዴ አንድ ስሜት በሻይቤቱ ከተሰማው አይመለስም። ማኅብረሰብተኛነቱ የጎላ ስለሆነ ነፃ አነጋገዱ ያነሰ ነው። ደንበኛ መያዙ በትንሽ ከተማ ፈተና አለበት።
ይህን ናሁም አስቦ ሁለት ነገርዎች በአነጋገዱ አደረገ። በትንሽ ከተማ ዉስጥ መነገድ ለስኬቱ ከትልልቅ ከተማዎች ይልቅ በማስተናገድ ጉዳዩ ላይ በከፍተኛነት እሚወድቅ እንደ ሆነ ተረዳ። ስለ እዚህ ደንበኛዎችን ለትንሽ ከተማ ሃቂትዎች በእሚጎዳኝ መንገድ መከወን ድርድር የለበትም ብሎ ወሰነ። አንድኛ ሥፍራዎችን መከለል እና ለብቸኛነት እና ለመደበቅ እሚጓጓ ህዝብን ለማበረታታት ሞከረ። ትነሽ ከተማ መተያየት ስለ እምታበዛ ሁሉም እንደ ልብ ሻይቤት አይጓዝም። የመተያየቱ አጋጣሚ ይበዛ አለ። ስለ እዚህ ጠረጴዛዎች በመከለያ ቅርጽዎች ዉበት ተጎናጽፈው በመጠቅለል ህዝቡን ለግሉ አገልግሎት አበረታቱት። የትንሽ ከተማ ስነልቦናን በመደገፍ ሁለትኛ ደግሞ ማታ ብርሃንዎች መደብዘዝ አበዙ። ጨለማ በማታ፣ ግልአዊነት (ፕራይቬሲ) በቀን ግልዮሽአዊነትአዊ (ኢንዲቪጁዋሊስቲክ) ሥፍራዎች እዉነትም ለብዙዎች በራሳቸው መንገድ ሹክ ብለው ጥሪ አደረጉ፨
ሦስትኛ፣ ማንም ምንም ቢሆን ባለዓይንዎች ማፍጠጥ፤ በትሁት ማቀርቀር ታዛዥ የአስተናጋጅነት እና መስተንግዶ አቀራረብ ይቸር ነበር። አንድአንዴ ማን እንደ ሆኑ ጭራሽ ሳይመለከት ናሆም በብልሃት የአስተናግድ ነበር። የከተማው ብዙ ሰውዎች ይህን እንደ እሚወድዱ ስለ ተረዳ አገልግሎቱ “በአለቃዬ፧ እመስቴ፣” እሚል ሰላምታ ብቻ ይጀመር አለ። ትህትናው አይቋረጥም። ይህም ስኬት ሳበ። አበዛ። መኮነን እማይፈልግ ስነልቦና እና ልክኖታ አስፍቶ እሚሻ ክፍለ ዜጋ በዝቶ እንደ አለ በጎን በናሆም ተረጋግጦ ተደረሰበት። መመላለሱ እና እንክብካቤ ተችሮ በአግራሞት መኮምኮሙ የናሆም ጉርሻ እና እሚ ገቢን አወፈረ፨
ቀጥሎ ትንሽ እንደ ቆየ አሁንም ደግሞ ናሆም አንድ መላ አገኘ። የእነ እርሱ ከተማ የፋሲካይት ኅዋአዊከተማ በምግብ መስተንግዶዋ ብዙ ችግር እንደ አለባት ይወራ ስለ ነበር ለተማሪዎቹ ብቻ የቀነሰ አገልግሎት በፈለጉት ድርድር መሰረት እስከ ጊቢው በር እንደ እሚአደርስ አሳውቆ አስነገረ፣ ለጠፈ። ጥቂት የቀነሰ ዋጋ እና የ ቷጤና ጉዳይ ደግሞ ባስፈለገአቸው መልኩ መስተንግዶ እንዲሰራ እና በ ወርሃዊ ቅድመ ክፍያ እንዲ መጡ አደረገ። ብዙ ትእዛዝ ስለ ነበር በአንድነት በተስማሙበት ሰዓት በመዉሰድ ያከፋፍል ነበር። በሂደት መንጠባጠብ ሲበዛ ዘበኛዎች ጋር ተነጋግሮ በሃምሳ ሳንቲም ብር ክፍያ እየአንድአንዱ ሳህን በእየ ቀኑ ከእነእርሱ ተመዝግቦ መብል መዉሰድ እና እርሱ ለዘበኛዎቹ በሰዓት የሁሉን የተመዘገበ የመብል ምርጫ አሰናድቶ በአንድ ጉዞ አድርሶ መመለስ ለነለት። የመብሉ መለየት፣ ደግ አልሚነት እና ጣዕም፣ የድህረመብሏ ስነልቦና ብዙ በጊቢው መብል የተሰቃየ ተማሪ አነሳሳ። በቀላል ከጤናጣቢያዎች ድጋፍ አስጽፈው በሂደት ብዙዎች ገንዘብ ተክተው የጊቢ መብል በመተው ወሰዱ። ወደ ናሆም የደረሰ ትእዛዝ በዛ። በቀን ሦስት ጊዜ በሰፊ ዉል ዝርዝር ስምምነት፣ ፍርርም፣ መሰረት ሦስት ጊዜ በቀን መመላለሱን እና ሳህንዎች ቀይሮ ከዘበኛዎቹ መመለሱን ተያያዘ። ይህ ከፍተኛ ስም እና ትልቅ ገቢ ሆነልአቸው። ተማሪዎች ለመፈተሽ ወይም ትእዛዝ ለማስተካከል መጥተው ይጠቀሙ እና ይመለከቱ ነበር።

አስተያየትዎችንም በማበረታታት እና በመቀበል እንደ ሰዉ ስሜት ማስተናዱ አንዱ ብልሃት ስለ ነበር ተወዳጅነቱ በ እዛም ጨመረ። ገቢ ደግም አብሮ ናረ። ናሆም አያያዙ ጥበብ ስለ ነበረው እሚ ከፍተኛ ገቢ አጊንታ መደመሙን እና ከቶ አለማመን ድረስ መድረሱን ጀመረች።
ስለ እዚህ ማጤን እና ነገርዎቹን ፈር መያዝ አስተዉሎ መስ በ እርግጥም ብዙ እሚአደርገው እንደ እማይኖር አሰበ። ሰኞ ለመመለስ አጽንቶ ሲቆርጥ እና ሲአሳውቅ ከንግዱ ፋታ ወስደው ለመተንፈስ፣ ቅዳሜ ከሰዓትን ናሆም ወደ ተለመደ ካፌአቸው እንዲሄዱ ሁኔታ አመቻቸ። “ጀምበርን እንደ እዚህ በማስተዋል እምደመምበት ሥፍራ አዲስአበባ እንደገባሁ እምፈልግ እንደ ሆነ እወቅ!” እንደ ገቡ መስ በፀሐይግባት ጥበብ ቋሚ ታዳሚነት ደረጃ ላይ መማረኩን አሳውቆ ነገረ ው። “ጠዋት ወይም ማታ እምትታይበት ከፍታ በየመንደሩ ይጠፋል ብዬ አላስብም!” ናሆም ጠቅላላ ሃሳቡን አቀረበ። የተለመደ ጤናአማ ምርጫ እሚሉትን ያለወታሸገ ጭማቂ መጠጥ በ ማዘዝ ተቀመጡ። ቀዝቃዛ አየሩ እና የክረምት ማብቂአ ንፋስ ዐጀቡ የበለጠ እርካታ ለድባቡ አጎናፅፎት ተቋደሱት፨
መስ ያሰበውን ማመስገን በ ቀላል ቃልዎች አስረከበ። “ዉድ መብራቱ! በሂወት ጎን አዲስ የነገ ሂወት ማበጀት መማር እንድከውን ከጭቃ እስከ ቃልዎች ቀምረህ ስለ አነፈስክብኝ ምስጋናዬ ትልቅ እና ትልቅ ነው!” ዝቅ ብሎ ቀኝ እጁን በማሽከርከር ወደ መስ አቀረበ። መስ ፈገገ። ትልቅ ምስጋና የቀረበለት እንደ ሆነ አስተዋለ። ታዳጊ ወጣት ሁሉን አስተውሎ፣ ነገን እንደ እዚህ ዋጋ ሰጥቶ ሲታትር ስለ ተመለከተ እና ምስጋና በተገቢ መካንጊዜ ማመቻቸት ሲቸረው ያድናቆቱ ጠረፍ ልቅ ሆነ። የማድነቁን ነገር መልሶ አስረከበ፨
“እግዚእአብሔር ይስጥልኝ! እኔ ም ከዐዋቂ ታዳጊ ጋር ተቀራርቤ በሂወት ጉዞ መጓዙ ብቻ ሳይሆን የነገ መዳረሻን መጥረብ እና መቅረፅ እንደ እሚቻል አምኖ ለአሳመነኝ ታዳጊ ወጣት ትልቅ ምስጋና አለኝ!” መልሶ እጁን እንደ ተደረገለት አድርጎ ዝቅ በማለት አከበረ። ተያዩ እና በሣቅ ሁለቱም ፈነዱ። የጀንበርዋን ጨዋታ እያስተዋሉ በመሳሳቅ እና ጨዋታ ቆዩ። ‘አንቺን መሆን አንችልም ጀምበር! ምን ብታምሪ – እኛ እኛ ነን! ብቻ ዉበትሽን በመዝረፍ ለመቅመስ ማን ከልካይ አለ? ቅኔዎችሽ ስ!’
መስ ፀሐይግባት ላይ እማያልቅ ዉበት እየተመለከተ ዉበት በማጣጣም ወደ ልዩልዩ ጭማቂዎች መጠጡ ጣዕምም ተመለሰ። ጎኑ የናሆም አብሮታ ምቾት ጭምር ጣዕም ሆኖ ተስማማው። ፈገግ አለ እና ሰማዩ ለራሱ ካካበጀው ድንበር ተመልሶ ዉድ ዲሞሱን በነሆለለ ፈገግታ ሆኖ መልከት አደረገው። ናሆምም ከሰማዩ ዳርቻ ወደ ዉድ አጎቱ መጠጡን ወደ አፉ አቅርቦ ነገርግን በልዝብ ፈገግታ ከንፈሮቹን ገጥሞ ተመለከተ። “ምን?!..” የደከመ ጨረር ፊቱ ላይ ስትተኛ ነብሱ ሞቅታ ለብ አድርጓት እንዳለች ላጎቱ ሣቅ አለ። ፍቅር መሀከልአቸው ሆነ። መስ በመልሶ መሣቅ ተመለከተው። ናሆም አብልጦ ሣቀ። መስም ተከተለ። አመክዮ ጠፋ። በሣቅ ወደ እማይደረሰው ሰማይ በመመልከት ከሰማዩም ልቀው ግን ከነፉ። እንኳን ሰማይ ምንም እማይመክተው ጠረፍን ሁሉ ጣሽ ደስታ ፈካ። ጭርታ ጋር የተዋደደ መንደሩን በበዛ ሣቅ አናጉት። ሁለቱም በመሣቅ ተግባበተው የተለዋወጡት ሰፊ ልዉዉጥ ያለ ይመስል ሲግባቡ መሣቁ በቂ ነበር። እጅግ በእርግጥ፨

በ ማግስቱ መልካም ማለዳን አሳለፉ። ከሰዓት በኋላ፣ናሆም መስን ይዞ ወደ ፍኖት ማህበሩ ወሰደው። ለመሳተፍ ባይሆንም የማህበሩን ነገር ከሰማ ጀምሮ መስ በማድነቅ አስተያየቱን ይቸር ስለ ነበር በጓደኛዎቹ ፈቃድ ሊጋብዘው ተፈቅዶለት እንዲከታተል ጥሪ ሆኖ አብረው ሄዱ፨
ናሆም በማህበር በመስራት መማማር እና መጠንከር እንደ አለ በፊትም ያስብ እና ይደሰት ነበር። ከገጠር ሲወጣ ሁለትኛ ክፍል ጨርሶ ወደ ሦስትኛ ክፍል ተሻግሮ ነበር። በሁዳዱ የደብረ ብርሃን ቅድስት ፅዮንን ማርያም ገዳም በመመላለስ ዉዳሴ ማርያም ከ መልክአ ማርያም እና መልክአ እየሱስ ጋር አጠናቅቆ ዳዊት መድገም ሊለምድ ደርሶ ነበር። ከተማ ሲገቡ ትምህርቱን ሊቀጥል ቤተክርስቲያን ገባ። ግን የከተማ ታዳጊዎች ለማስተማር የተቀጠሩት ቄስ እንደ ደቀደመው ገጠር ገዳም ምርጥ አልነበሩም። የጠራ ትምህርት በገጠር ከከተማ ይልቅ እሚገኘው መንፈስአዊ ው የቤተክህነት ትምህርት ሲሆን ብቻ ነው። ማንም የከተማ ታዳጊ ዉዳሴ ማርያምን ከ እረቡዕ ዘልሎ ስለ አልጨረሰ ናሆም ብቻውን ሆነ። ጭራሽ መምህሩ የኔታ ደጉ ለማስተማር ናሆምን ይጠቀሙበት ጀመረ። ነጋሪት ተብሎ ተሰየመ። ወደ ፊት እንዲሄዱ ያሉበትን ቀጥሎ እሚመጣ በመንገር ሁሉን ተማሪ መንገር፤ ነጋሪት መሆን ጀመረ። ግን በተፅዕኖአዊነት (ቨርቹዋሊ) አስተማሪ ነበር። በመመላለሱ ባይተዋርነቱ እየባሰበት ሲሰማው፤ ሲደብረው፤ አመቱን በመመላለስ ብቻ ጨርሶ ዳዊቱን ገና በጊዜ ተወ። መሰባሰብ እና አንድነገር እነኳ ማድረግ ግን ይወድድ ስለ ነበረ እና በከተማ መሰባሰብ ደግሞ በሰንቤትትምህርትቤት እሚዘወተር ስለ ነበር ሰንበትትቤት በቀጣዩ ዓመት ገባ። የልጆች ተብሎ በተከፈለ ክፍለ ሰንበትትምህርትቤት በመዘመር እና በማገልገል እስከ ስድስትኛ ክፍል ቆየ። መደበኛ ምስጋና መዝሙር መዘመር አጠና፣ በተቻለው አገለገለ። ሰባትኛ ክፍል ሲገባ ወጣቶች የሰንበትትምህርትቤት ክንፍን ተቀላቅሎ በቡድን-አዛርያ ተመድቦ ገባ። በላጭ ነገርግን መሰል አገልግሎት ሰጠ። በጥምቀት በተለየ ለቡድኑ በአዉደዓመትዎች ብር ሰብስበው መንፈስአዊ-ቤተመጽሐፍ ከጓደኛዎቹ ጋር አበጁ፤ ዛሬ በሰንበት ቀንዎች ለማንም ክፍት ማንበቢያ ሆኖ በከተማ ው ከተማሪቤትዎች ዉጭ እሚገኝ ብቸኛ ክፍት ቤተመጽሐፍዎች ሆኖ ቆመ፨
ግን ሲአድጉ ሰንበት ተማሪዎች እየተንጠባጠቡ ቀሩ። ዓለምአዊነት ሳይሆን፣ ሰንበትትምህርትቤት የልጆች እና ታዳጊዎች ተደርጎ ስለ እሚታሰብ በ አጭር ሂደት ባዶ ሆነ። ሰንበት ሲደርስ በ ማስቀደስ ብቻ እሚቋጭ ሆነ። ዘጠነኛ ክፍል እስኪፈጽም ድረስ ለመቆየት ታገለ። ብቻውን የሁለትኛ ደረጃ ተማሪ ሆኖ መሰንበት ግን እማያስደስት ሆነበት። በመጨረሻ ምትክ ማህበርተኛነት እሚገልፅበት የ እኩያ (ፒር) ማህበርተኝነት ግድ ነው በእሚል ስለ እሚአምን የተቀነሱትን ሰንበት ተማሪዎች በመሰብሰብ እና ግል ድርድር አሳመነ። የ ቅ. ጊዮርጊስ ዝክር በቡድን መጠጣት ጀመሩ። በየወሩ ይሰባሰቡ እና ሊቀሰማዕትዎቹን አስበው ይዉሉ ጀመር። በሂደት ወርኅአዊ ስብስብ ስለ አላረካው የበጎአድራጎት ማህበር ሰራ። ብዙ ሰው የለበትም። በመንደሩ እየዞሩ ብቸኛ ግለሰብዎችን ለመደገፍ ስድስት ልጅዎች ብቻ ተስማምተው በአስራአምስት ቀን አንድ ቅዳሜ ጠዋት ለብቸኛ የከተማ ነዋሪዎች ልብስ ማጠብ እና ቤት ማፅዳት ጀመሩ። ብዙ ሳይቆይ ተበታትነው ልጅዎቹ ቀሩ። በአዲስ ጥረት ደግሞ ተማሪቤቱን አንኳኳ። ከዓሊ እና ሩት ጓደኛው ጋር በመመካከር የንባብ ማህበር ለማቋቋም አቀዱ። ሲአውጠነጥኑ ማህበሩ በቆራጥ ፍላጎት ለእሚነሳሱ ካልሆነ እንደ እማይዘገይ ከልምዱ አንስቶ በመናገር የማንበብ ባህል እና ፍቅር ያለቻቸውን ለይተው በመረጃ ማሳደድ ማጥናት እና በማሳመን አስር የአስረኛ ክፍል ተማሪዎችን ትምህርት እንደ ጨረሱ ሰበሰቡ። በመደበኛነት ልብወለድዎችን በማንበብ እንዲጀምሩ አደረጉ። መምህርዎችም በቡድኑ ተመርጠው ድጋፍ አዋጡ። በመጨረሻ ህገደንቤ (ፕሮቶኮል) ተዘጋጅቶ ሲዘረዘር ደግሞ የብርሃኑ ዘርይሁን የ ሥነፅሁፍ መሠረትአዊያንን ማንበብ እና ሥራውን መጀመር ግዴታ ሆነ። በመሰረትአዊ አገነዛዘብ ተመስርተው በማንበብ ቆይተው ሃያአንድኛ ቀን መገናኘት ይወያዩ እና የጋራ ነጥብአቸውን በቡድኑ የጦማር አድራሻ ፍኖት-ንባብ-ማኅበር.ብብሎግስፖት.ኮም ላይ በመለጠፍ ወደ ቀጣይ ንባብ ይሸጋገሩ ነበር። የናሆም ማህበር መመስረት በመጀመሪአ አንድ ሰው አንድ መፅሐፍ አንብቦ በማብራራት እንዲወያዩበት እና በእየተራ እንዲደረግ ታስቦ ቢጋፈጡትም፣ በእራሱ አብሮ ማንበብ ሃሳብ መጨረሻ አሸናፊነት ደግ ልምድዎችን ከትምህርት ጎን እየቀሰሙበት ቆየለት። ከዝክር ማህበሩ እኩል ይህ ፍሬው አድጎ በእዚህ ወር አዳዲስ አንድ የአስራአንድኛ እና አንድ የአስረኛ ክፍል፣ ሁለት ተማሪዎች ዓመቱን አብሮ በመቆየት ክበቡን ለመውረስ በመስማማት ቀርበው ነበር፨
ናሆም እና መስ ወደ ተዋበው እና ሰፊው የሁለትኛደረጃ ቤተትምህርት ገብተው መስ በጊቢው ማማር እየተገረመ ደስታን በማጣጣም ወደ ተለመደ ክፍልአቸው አዘገሙ። በክፍሉ ሲገቡ ሰዓቱ ደርሶ ስምንት ሰዓት ስለ ነበር ሁሉም ተገኝቶ ነበር። ወደ ፊት ማኅበርተኛዎቹ ከብበው ሲቀመጡ ከሩቅ ጀርባ ላይ ሁለቱ እንግዳዎች ተጋብዘው ጎንለጎን ተቀምጠው ነበር። መስ ወደ እንግዳዎቹ ከጎንአቸው ተቀመጠ። ናሆም በመሪ ወንበሩ ተቀምጦ ሰላምታ ሰጠ እና ዝግጅቱ ተጀመረ፨
ለ አለፈው ማኅበር በድምፅ ብብልጫ የተመረጠ የነበረውን አደፍርስ፣ ትርክት ጭምቅ፣ በአብዛኛው የተፃፉ ምርጥ ፲ ጥቅስዎች፣ የእሚነሱ የመፅሐፉ ሃሳብዎች መንሸራሸሪአ ጉዳይዎች ምን ምን እንደ ሆኑ መጠቁም (ኢንዴክስ) ያወጡትን፣ ከአስተያየትኤዎች ጋር እባሪ አድርገጎ የሁሉንም ሃሳብዎች በመቀላቀል ናሆም የአዘጋጀውን ዘገባከፊሉን አነበበ። የቀረውን የሠብለ ጓደኛ ቀጠን እና እረዘም እምትለዋ ሣቂታ እና ተጫዎቿ ራሔል አግዛ ው አነበበ ች። አብዛኛዎቹ ያነሱት ነጥብ ተጨምቆ በጋራ ዘገባው ስለ ገባ በመስማማት በአንድ ድምፅ አፀደቁት እና ለፊርማአቸው ዞረ። የማኅበሩ አንድ ጦማር ተደርጎ ሊለጠፍ ወደ ሰኞ የናሆም ሥራነት ዞረ፨
የ ቀኑ ማኅበር በ እመጓ ላይ ስለ ነበር፣ መፅሐፉን ናሆም አስተዋወቀ። እትም፣ ዋጋ፣ ገፅዎች፣ ወዘተ. አብራራ። በ እየ ተራ መፅሐፉን እንዴት እንደ አገኙት እና ገመገሙት አሳውቀው የትርክት ጭምቅአቸውን በአጠረ አገላለጥ የአስደምጡ አለ። በጠቅላላ ስለ ገፀባህሪው የአምላክ ክርስቶስ መስቀል ላይ ደም መቀበያ ጽዋ ፍለጋ እሚኳትን ሃበሻን ተከትሎ እንደ እሚጓዝ አብራሩ። ሞገስ፣ አጠር ለፍጠን ያለው ስካርፕ እማይለየው ድምፀ ጎርናና ተሳታፊ ግን ስለ ኢትዮጵያ አየር መንገድ መስበክም የትርክቱ ጭምቅ እንደ ሆነ አክሎ ሲናገር ሁሉም ሳቀ፨
ሁሉም በእየ ተራ ያዘጋጀውን አንብቦ ምርጥ ጥቅሶች ያሉአቸውን ዘረዘሩ። ሴራውም ቀረበ፤ ከትርክቱ ተቃቃፊ ነበር በእሚል ቋጩ። የፍለጋው ልብአንጠልጣይነት (ትሪለር) ላይ ተስማምተው ወደ ተጨማሪ ትችት ዘለሉ። ገሚሱ ግን ከልብ ማንጠልጠሉ በተጨማሪነት የየመልእክቱ መነሳት ከ አልሆነ በቀረ ስስነፅሑፍአዊ ዉበት እንደ ጎደለው ኮነነው። አንዱ ተማሪ፣ ኤፍሬም፣ ጫጫታ ለመሆን በቀረበው ክርክር መሃል፣ ተቆጣ እና ድጋፉን አሰማ፨
“ደግ ልብአንጠልጣይ ትረካ ነበር። ምርጥ ስልተአተራረክ ተከትሎ በልብ ማንጠልጠል ሲአጫውተን ነው የቆየው። መልእክቱ የተዘነጋ እና መታወቅ የነበረበት አንድ ዐብይ ጉዳይ ነው። ምን ጎደለበት ታዲኣ?” የሃሳቡ መቅረብ ገሚሱን አሁንም አስደስቶ ድጋፍአዊ ጫጫታ ሆነ። ኤልሻዳይ፣ የረጋ ስብእናዋ ጠፋ ብሎ በጮኸው ክርክርቴ ፋም የ አለ አንደበት ዋ ተቃራኒ ነጥብዋን አቀረበ። “ሃያአምስት ወይም ሠላሳ እጁን፣ ስለ ኢትየጵያ አየር መንገድ ነው እሚተርከው እሚመስለው። ግን ብርሃኑ ዘዘሪሁ፣ ሁላችን ቀድመን ለሦስት ሳምንት ያነበብነው እና አማሪኛ መምራችንን ለይቶ ስለ ልብወለድ ለአራት ቀን እንዲአስተምረን ያስቸገርንው ስለ ማንበብ እና ንባብ መበለት በብልሃት ለማወቅ ነበር።”
ሁሉም ሃሳቧ እንዲገባው አተኩሮ አፈጠጠ። አትኩሮት ስትስብ ክርክርቴዋን ገነባች “ታዲአ፣ ከ አስታወስን፣ ደራሲ ወደ ህዝብ አንድ ትርክት ይዞ ሲአቀርብ እሚይዘው ትርክት አዲስ ወይም ገሃድ ታሪክ ሊሆን ይችል አለ ብለን ነበር። ብቻ ግን እሚታወቅ ገሃድ ነገር ከተነሳ አዲስ ነገር መታከል አለበት።”
የ ነጥቡ አዝማሚአ ከወዲሁ ስለአልተገለጠላት ሄለን ተቆጣች እና “ከእመጓ ጋር አገናኚዋ።” አለች “ታገሽ።” ናሆም ጣልቃ ገባ። ኤልሻዳይ ፀጉሯ ወደ ፊቷ ወደ ክፍሉ ድንገት በነፈሰ ንፋስ ሲራወጥ ወደ ጀርባ ሸኘት አድርጋው ተመቻችታ ነጥብዋን ቀጠለች። “ስለ አየርመንገድአችን ታላቅነት አሁንም አሁንም ደጋግሞ ያወራ አለ። ሁሉም አንባቢ ግን የአን ያቅ ነበር። ስለ እዚህ አዲስ ነገር ጠበቅን። ግን ምን አዲስ ነገር ገነገረን። ሁሌ አፍሪቃን እንደ እሚመራ በ ትመ.ዎች ያለመታከት ስለ ተቋሙ ሃያልነት ሰምተን አለ። ልብወለድ ይህን መደበኛ ወሬ ደጋግሜ ልተርክህ ከአለ መሰል አደንቋሪ ወሬ ከ ማተት እና ጆሮ ከ መጠለዝ ለምን መዝለግ እና ነጥብ መጨመር አለበት።” ዓሊ ፈገግ አለ። ነጥብዋን ተረዳ እና ሊአግዛት ፈልጎ “ለ ምሳሌ ምን?” አላት። “ለ ምሳሌ ሃብታም እና ስኬታማ እንደ ሆነ የታወቀ ታላቅነቱን አንስቶ፣ በምን አሠራሩ ስኩ እንደሆነ ቢተርክልን ስ? አፍሪቃን በእድገት ጭራዋን ወካይ ነን፣ መቀየር እንሻ ግን አለን። ታዲያ አየር መንገዱ አፍሪቃን ከአኮራ እንደ አየር መንገዱ ምን ብንሰራ ነው በቀረ ሥራአችን ሁሉ እሚሳካልን? አመራር ጥበቡ ልዩነው? ምሁሮች ስለ አሉበት ነው? ሲጎበኝ ገፀባህሪው ለምን ስኬትን ሲመለከት የስኬቱን ጀርባ ማሰስ ጠላ? አፍሪቃአዊያንን ከበለጥን እና በዓለም ከአኮራን አመክዮው በ ደንብ ተጠንቶ ወደ ሌላ ነገርዎች እንዲዞር መነሳት ነበረበት። ለምን ጓደኛው ኢትዮቴሌኮም ባፍሪቃ መሰል ሆኖ አንድኛ አልሆነም? ለምን እምናውቀውን ከመደጋገም በምናውቀው ትርክት አዲስ ነገር ከትቶ’ አይናገርም። ለምን ዳግምርምር! (ሪሰርች) ሰርቶ አልከተተም?” የኤልሻዳይ ነጥብ ሲዘረዘር ዓሊ ይህ እንደ ነበር ገምቶ ፈገግ አለ። ማኅበሩ በአየር መንገዱ ተደጋጋሚ መንቆለጳጰስ ጀርባ አንድ ነገር ከአልተጨመረ አታካች ነበር ባሉት ቡድንዎች አብዛኛዎቹ ተደባልቀው ተስማሙ፨
ተሰማ፣ ዝምተኛው የማኅበሩ አባል አሁን ወደ ዉይይቱ ገባ። “ግን አየርመንገዱ የተሳካለት ከአፍሪቃ ቀድሞ ስለጀመረ ነው ብዬ አስብ አለሁ። እድሜ ለ ቀኃሥ. ብዙ ነገሮች ከማንም ቀድመን ኮርጀን ነበር የአኔ።” ተሰማ ሲናገር ከአደፈጠ በኋላ ብዙ አስቦ ስለ ነበር ጉዳዩ ወደ ደግ መወያያ እርስነት ሲለወጥ ማውራት እሚጀምር ነበር። ሁሉም በአትኩሮት ሲመለከቱት ነጥቡን ቀጠለ። “አፍሪቃ ቅኝ ግዛት ወቅት እኛ ግን ደግ ነገሮች መጠንሰስ ተያይዘን ነበረ እኮ። አየርመንገዱም በተዓግ. ድጋፍ ስለተመሰረተ ያኔ ደግሞ መማር በጥራት፦ በወተት እና ማር፣ በልመና ስለ ነበረ፣ የፈለገ ብቻ ይቀጥል እና ይገፋ ስለ ነበረ፣ እንጀራ እንደእሚአወጣ በቅርብ ዘመኖች አይተን ‘እንጀራ ይውጣልህ ተማር’ ከማለት የቀደመ ዘመን ስለ ነበረ፣ መምህሮች ከውጭ እንደ ዛሬው ሳይሆን በጥራት ተመዝነው ይመጡ ስለ ነበረ፣ ምሁርዎቹ ሲመረቁ ድንቅ ነበሩ። እንዲህ እንደ እኛ በየገጠሩ ለብሄረሰብ ጥያቄ መልስ ፍጆታ ብቻ በእሚል ባዶ ህንፃ ክቦ ሥራ-አጥ ትውልድ ለመቀነስ በሚል የወደቀ ተማሪ አስተማሪ እንዲሆን በኦና ቤተሙከራ ለብለብ አድርጎ ማስወጣት ከዛ በርቀት መማር እያጭበረበሩ ትልቅ ቦታ መድረስ ስለ አልነበረ፣ ከፍተኛ ጥራት ያለው ምሁር እየወጣ እሚሰራበት ተቋም ነበረ።” እነ ሄለን በተነሳው ሃሳብ የበለጠ በደራሲው መዳሰስ የነበረበት ሰፊ ክፍል እንደ ነበረ ተስማሙበት። ተሰማ ትንታኔ ማዉጋቱን ቀጠለ። “አፍሪካ ልዑዋላዊ አልነበረችም። እኛ ግን ብዙ ሀገርዎች። ቀድመን በደንብ መብረር ጀመርን ማለት ነው። ከእንግሊዝ እና አሜሪካ ለንጉሱ ወይ ልዑክዎችአቸው እሚላኩ በራሪቅርፅዎች ቀንሰው በሀገራችን ተቋም መብረር ተጀመረ። የቀኃሥ. ድንቅ ዲፕሎማቲክ ስኬት አንዱ መገለጫ ይህ አየርመንገድ መበር። እና ሌላው ግልፅ ይመስለኝ አለ።” አስተዋለ እና ለመጨረስ ያክል ቀጠለ “ዘርፉ ሃገር ማቋረጥ ስለ ሆነ፣ ዉድ እና አትራፊ ሆነ። ምንሰበስበው በዶላር ስለ ነው፤ በእዛ ላይ ከፍተኛ ፉክክር እና ድጋፍ ከበራሪቅርፅ አምራቾች አለ። ገበያው፣ እንደ ትርፉ የደራ ነው። አንዴ ከተገለበጠ ስለ እሚጎዱ ቀድመው እና በተከታታይነት ይደግፉን አለ ብዬ እገምት አለሁ።” ሄለን በሃሳቡ ተማርካ አድምጣ አንድ ተጨማሪ የመሰላት ነገር ሲከሰትላት አከለችው እና የማኅበሩ ቆይታ መጣፈጡን ተያያዘ።
ዓሊ የተሰማን የቀኃሥ. ፍቅር ስለ እሚረዳ ለመተንኮስ ብሎ አፈነገጠ። “ቀኃሥ. “እኮ ብዙ ትልቅ መሪአችን አልነበሩም!” በርግጥ ከንፈር አያያዙ የሹፈት ፈገግታውን አስመልክቶ ጨዋታ እንደ ነበር ቢገልጥም ሁሉም የቀኃሥ. አክባሪ እና ደግ ልክክፍልዎችአቸውን እሚአንቆለጳጵስ ስለ ነበር የወል ድምፅ ገሰፀ ው። ተሰማ ቱግ ብሎ ቀኃሥ. ደግሞ ምን መሰረት ጣሉ?” ተሰማ ደግሞ በመደመም ከምር የቀረበ በመሰለው ጥያቄ አርእስትነት መልሶ ለመገንባት ሲል ጠየቀ። ጣትዎች በመቁጠር እንደ ተሰማሪ (ታሊ) እየተጠቀመ በስሜት ጩኸት ዘረዘረለት፨
“ሁሉንም ነዋ! የሃበሻ የመጀመሪአው ኅወአየዊ ከተማ፣ የመጀመሪአው መንግስትህግ፣ የመጀመሪአው ፍርድቤት ስርኣት፣ የመጀመሪአው አየር መንገድ፣ የመጀመሪአው ከተማ አዉቶባስ፣ የመጀመሪአው መስኮተድምፅ ጣቢአ እና ተቋም፣ የመጀመሪአው ትመ. ጣቢአ እና ተቋም፣ የመጀመሪአው ቤተአእምሮ ህክምና፣ የመጀመሪአው አንድ መቶ ትልልቀ እና ትንንሽ የአባይ ግድብዎች በመላ የኢትየጵያ አባይ መስመር መስራት ማስጠናት እና መፈፀሙ፣ የመጀመሪአው ማተሚአ ቤት፣ የመጀመሪአው ምሁር ሚኒስቴርዎች፣ የመጀመሪያው ጥቁር ሆኖ በአሜሪካ ትልቅ አቀባበል እና ትብብር የተቸረ እና የአሜሪካን ጥቁሮችን ያነቃቃ መሪ፣ ብቸኛው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ማዕከል እና መስራች፣ የመጀመሪአው መኪናአዊ ትላልቅ ግብርና፣ የመጀመሪአው ቤተመዘክር፣ የመጀመሪአው ይፋአዊ (ፐብሊክ) ቤተፊልም፣ የመጀመሪአው ዓውራዕቅድአዊ ከተማአችን፣ ስለ ዘመንአዊነት ሲባል በዘመንዎች ያልተቋረጠ የዜጋዎች ባርነትን የመጀመሪአው ሰብእአዊ መብት ህግአዊ ልክኖታ ሰጥቶ እስከ ባሪአ ንግድ ማቆም ዐዋጅ መከወን፣ የመጀመሪአው ሉልአዊ ተቋም መስራችነት እና አባልነት፣ እልፍ ነገርዎች በ ቀኃሥ. ተመሰረተ። ያ ብቻ አይደለም፣ እንደ አለ ማለት ይቻል አለ መሰረቱ የእርስአቸው ሆኖ ዛሬ ያለ የሃገሪቷ ቅርጽ የርስአቸው ነበር። በማንም ያልተስተካከሉ የዘመንአዊነት ጉዞ ሃቀኛ መሰረትዎች ነበሩ።”

“በ እግጥ ቀኃሥ. የሰሩት ሁሉ የዘመንአዊ ኢትዮጵያ ምርጡ ወለል ነበር።” ኤልሻዳይ በአናት መነቅነቅ አክላ ተናገረች። “ልክ ‘እወድሃለሁ የእኔ ፍቅር ፍቅር…’ ብሎ አቤል ተስፋዬ በሉልአዊ ዘፈኑ አማርኛ ከተናገረው የሃበሻነት ማሸነፍ ቀጥሎ!” ሞገስ በመቀለድ ስሜትአዊነትዋን ሊአበርድ አስቦ ሲናገር ሁሉም ፈገገ። ሣቁ ዉጥረቱን ሲአረግብ ወደ ነጥቡ መቋጨት እንዲመለሱ ሞገስ ቀጠለ፨
“የ ሃገርአችን መደበኛ ነዋሪ አየርመንገዱን እረስቶት ከብሔር እና ዘር ዉጭ ስላለ ይጠቅመው አለ ባይ ነኝ። ከስነዉሳኔ የህዝብ ወሬዎች ዉጭ ነው። ሲጀመር መደበኛ ህዝቡ አይጠቀምበትም እና ማንም አይረብሸውም። አገልግሎቱ ለቀረው ዓለም ይበዛ አለ። ሰፊዋ አፍሪቃ ደግሞ እንደ አልክው ቀድሞ በተቆጣጠረው ክሂሎትአማአዊ (ቴክኒካል) እና ስነገበያአዊ የበላይነት አልደረሰችበትም። ስለ እዚህ አየርመንገዳችን ስኬታማ ሆነ።” የተጫዋች፣ አላጋጭም፣ ኩሩ እና ቁምነገረኛው ሞገስ ሃሳብ አከለ። በወረደው ጠቅላላ የወጣትዎቹ ምናብአዊ ጭዉዉት፣ መልሰው አተያየት አግጣጫዎችአቸውን ወደ ብስል አገነዛዘብነት መሞረድ እየቻለ ስለ ነበር፣ ሁሉም በቅንነት፣ አክብሮት እና ይዘትአዊ ተሳታፊነት እንደ አቅሙ ይገባበት ነበር። “ግን ሰው በማባረር እና በፈላጭቆራጭ የተሞላ ነው ይባል አለ። ቢሆንም ማንም መደበኛ ሀበሻ አይጨነቅም። ገብቶ አይገለገልበትም፤ አይወራለትምም። ስለ እዚህ ጉድ ወይም መኣት በስኬቱ መንጣለል ጎን እንደ አለ አናውቅም። ደራሲው ብዙ መናገር ይፈልገው የነበሩ ነገርዎች ነበሩ ማለት ነው። ከጀርባ በእርግጥ ደራሲ መፈተሽ የነበረበት ጉዳይዎች ነበሩ።” ሩት እጅ በደረት አድርጋ ጡትዎችዋን ድጋፍ በመስጠት ከማድመጥ ወደ ተሳታፊነት ለመግባተደ ተናገረች። “ሰው ስለ እማይመለከተው ነፃነት እንደ አገኘው ተጠያቂነትም ሊአመልጥ ይችል ይሆን አላ! ቅሬታ ሲኖር የሰራተኛ ማህበሩ ሰራተኛ አይደግፍም እንጎዳ አለን እሚሉ ብዙ ነጥብዎች በእርግጥ አሉ! ወይም ደግሞ ይህ ስኬቱ እና ብሔራዊ አርማነቱ እና የገጸባህሪው ኩራት አየርመንገዱ ግልዮሽአዊ (ፕራይቬታይዝድ) ይደረግ ስለእሚባል እንደእሚጠፋ እየተነሳ ስለእሚገኝ ይህንንም አላነሳም። ማለቴ የስነምጣኔሃብት ሊቀሊቆች በፍቃዱ ድጋፌ እንዳለው አየርመንገዱ ቢሸጥ እንደ ኬንያ እና ደቡብአፍሪቃ አየርመንገዶች፤ እነእሱ የመንግስት ሳሉ የእኛ በላይ ሁሉ ነበሩ፤ እሚያሽቆለቁል እንደሆነ ከሚሟገቱት ቢሆንም ደራሲው ይሸጥ እሚሉትን አንጃዎች የገሠጸበትም አጋጣሚ የለም፤ ከተራ ተጓዥ ፈንጠዚያ በቀረ። እነእዚህብ ነጥቦች ስለዘለለ፣ እና መጓጓዣውን ስላፈቀረ ብቻ አንዳንዴ በበራሪቅርጽ መሄድ ብርቅ ነው እንዴ? ያያስብላል በርግጥ።” አብርሃም፣ አጠር ያለው አባል አከለ። ሁሉም ፈጠጥ ብለው በማድመጥ ነበሩ። ልክ ሲጨርስ የከበባቸው ዝምታ መናገሩን ቀጠለ፨
በእርግጥ ጠቅላላ መረጃዎች እና መደበኛ አመክዮ በመጠቀም እንጂ ተገቢ ዳግ-ምርምርዎች ከውነው እሚነጋገሩት አልነበረም። ለመወያየት ባህል እና ለአተያየት አቅም ማጥራት፣ አጢኖት አመሰራረት ጥበብም ግን እንደ መነሻ ደግ ግብዓት ሆኖ ዉይይቱ ሁሉን ያነቃቃ እና ያነፍስ ነበር። ኤልሻዳይ ቀጥላ በዉይይቱ ገፋችበት። “ሌላው ከእመጓ ትልቅ ክስረት ሰነፍ አጨራረሱ ነው።” ስትል አብዛኛዎቹ ተስማሙ። “ተገቢ አይመስልም በእርግጥም። ሃቅ መርምሮ ከአገኘ፣ ሽንጥ ገትሮ መናገር እንጂ ማፈግፈግ ስነፅሑፍአዊ ክህደት ነው። ግልፅ ነው ልክ ወይም ስሕተት መሆን አለ። ግን አንድ ወገን መያዝ እና መሟገት ግድ ነው። ተደራሲ በ ቀረበለት ሃሳብ አምኖ እንዳይጠነክር የሴራ ሽባነት ፈጥሮ አለ። እኔስ በግሌ አምንአለሁ ብሎ መጨረሱ ትርክቱ ሁሉ የ አንድ ሰው ግምትን በመንገር ያጠነጠነ የ አክል መጨረሻው ላይ ይቆረፍድ አለ።” በሃሳቡ እሚመዘዝ ሌላ ሃሳብ መነሳቱ ቀጥሎ ዓሊ “የይዘት ዓርታዒዎች በማስመልከት ስለ እማንበረታ እንጂ በእርግጥ ይህን አስተካክለህ አንድ ወገን ያዝበት እና በእርግጠኛ አቀቋም ተደራሲ አበረታታ እሚል አስተያየትኤ አያጣም ነበር።” ብሎ አከለበት፨
ሠብለ ጨዋታውን አስፍታ ሌላ ነጥብ አነሳች። “ባለፈው እመጓ ለአንድ ቀን ጉዞ ሄጄ ነበር። በገዳሙ ምስሎች ሲሸጡ፣ ደፋሲው የፃፈውን የእመጓ ትሁት ዝምታን በምስልሉ ጀርባ ከትበውት ነበር። እና ማን ነው የቀደመው? እሱ ከኮረጀ ስነፅሑፍአዊ ወይም ሊቅአዊ ሌብነት ነው።” ተሰማ ጉዳዩን ለማጣራት “መች ነው ምስሉ ላይ የፃፉት? የድርሰቱን ጊዜ እናቅ አለን እና መወዳደር ይችል አለ” ሠብለ አዘነች። “አልጠየቅኳቸውም።… ብቻ ከገዳሙ የማሞገሻ ማብራሪአውን ከወሰደብአቸው ከዛ እንደ ወሰደ መግለጽ አለበት። ቀጣይ ስንሄድ መች እንዳተሙት እንጠይቅ አለን ና!” ሩት የሠብለን ጉዳይ ታውቅ ስለነበር “ወይ ደግሞ እመጓ ስኔድ ቀድመን እመጓን እናንብ።” ብላ አስተካከለች። ምስሉን ስንመለከት ቀድመው ከፃፉት በእራሱ ጊዜ ጥያቄ ሆኖ ይከሰትልን አለ በእሚል እንደምታ አብራራች። ያስኬዳል በእሚል ሠብለ ፈገግ አለች፨
በተመሳሳይ ጉዳይዎች ተወያይተው፣ በመጨሻ በሴራው አፈፃጸም ድክመት፣ በሙሉ ድምጽ ተስማሙ እና እሚከተለውን የወል ሂስ ድምዳሜ ተስማሙበት። ናሆም በመፃፍ መልሶ አነበበ። “ምርጥ የሃገር አኩሪ ታሪክ ቢጨልፍም፣ በአተራረክ ደግ ማንጠልጠል ቢአገኝም፣ ሴራ አዘጋግ ወሽመጥ ቆራጭ ሆኖ ከ ተያያዥ ጉድለትዎች ጋር እሚቋጭ ልብወለድ ሲሆን፣ ደግ ልብአንጠልጣይነቱ ከስንኩልናው እንደ ከዘራ ሆኖ አላስመለጠውም።” በእዚህ ማኅበሩ የሂስ ነጥቡን ደመደመ። በእርግጥ የለሁበትምታ አንዱ አንቀጹ ‘የአማካይ ምዘና እንጂ ይህ ጽሑፍ ፍጹም የግል ሂስ እና ሥራ አያመለክትም’ እሚል ነበረበት። አብዛኛው ተስማምቶ፣ ፭ ከ ፲ እሚለው አማካይ ዉጤትአቸው ተገልፆ ናሆም የእየ ግል ወረቀትዎችአቸውን፣ የንባብ-ጥርዝዎች፣ ተቀብሎ ለቀጣዩ ማኅበር ቀጠሮ እሚለጠፈውን የመጨረሻ ቅጅ ለማዘጋጀት የተለመደ ኃላፊነቱን ወሰደ፨
በቀጣይ በበአሉ ግርማ ከ አድማስ ባሻገር ለመወያየት ሁሉም እንዲአነብቡ በአብላጫ ድምፅ ዉሳኔ ሆነ። የንባብ-ጥርዝ እሚሉትን ከትርክት ጭምቅ፣ ጥቅስ፣ እና አስተያየትኤዎች አብረው ለማቅረብ ተስማሙ። የአዲስ ገቢ እንግዳዎች ትዉዉቅ ቀጠለ እና ለቀጣዩ የእነርሱ ሥራ የብርሃኑ ዘሪሁን መግቢአቸው መጽሐፍ እና ከናሆም እሚተላለፍ የአማርኛ መምህርአቸው አሃዝአዊ የስልጠና ዶሴ ማንበብ እና ለመሰል ሹፍተራ መምጣት ብቻ ሆነ። መስ ከጀርባ ራቅ ብሎ ዉይይቱን ሲመለከት እንደ ጨረሰ ናሆም ቤተሰብ እንደ ሆነ ተናግሮ አስተያየት ሊሰጥ ጋበዘው። መስ በመደነቅ እንደ ተከታተለ እና እንዲበረቱበት ብቻ ተናግሮ አበቃ። ሁሉም ተለያይተው ወደ እየ ቤትአቸው ለማዝገም በንዑስ ቡድንዎች ተሰብስበው ወጡ።
አንድአች ጉዳይ አንስተው ከመስ ጋር ሲጨዋወቱ እየተጓዙ ቆዩ እና መስ እግረመንገዱን ወደ ተስ.ዎች ሱቅ ይዞት ሄደ። መካከለኛ የ አባይአዊ ዘመንአዊ ተስ. ገዝተው እዛው መስ ለናሆም በሥጦታ አስረከበ። ዘመንአዊ የንክኪ ተሱ. ደግ አቅም የነበራት በቻይና ነጋዴዎች እዚሁ ተመረትኩ እምትል ነበረች። ናሆም በመደነቅ እና መደሰት መረጃዎችዋን አየትአየት አድርጎ በአክብሮት ደገመ እና አጎቱን አቅፎ ሳመ። ‘ትልቅ ትንግርቴ’
ሻጯ የሁኔታው ደስታ ተካፋይ ለመሆን መጨረሻ የተከራከሩበትን እና ያስከፈለችአቸውን፣ የሃያአምስት ብር ክፍተት በመመለስ ጨምራ አደመቀችአቸው። ስሜት ሲንሳፈፍ ጥቂት የፍቅር ድጋፍ ሲታከልበት ይበልጥ ደምቆ ይንበለበል አለ። እንጂ የድጋፍ ወይም ስጦታው ማነስ መተለቅ ሌላ ጉዳይ ባይሆን ድጋፍ ዋ ኢምንት ይሆን ነበር። በተደረገልላአቸው፣ ከገንዘብ በላይ ስሜትአዊ ድጋፍ ተነክተው አመሰገኑ። በመልሱ ፈገግታ እና መልካም ዕድል ሲቸሩ፣ አመስግነው በእጥፍ የአብሮታ ደስታ ወጡ። “የቤቱ መገንባት ይብስ አለ ብዬ እንጂ የግልህ ተስ. እንድታገኝ ያሰብኩት ገና ስመጣ ነበር። ብቻ ዕቅዱ ከመኝታቤትነት ወደ ሽያጭ ቤትነት ተለዉጦ በማደሩ፣ ከታሰበው በላይ ቢጨርስም፣ ለሁሉም ለሁሉም አላማ እና ሚዛን፣ ይህ ይገባህ አለ!” መስ አመክዮ እና አስተያየቱን በናሆም ደስታ እራሱ በመርካት ፈግጎ አከለ። በማስጨነቁ መልሶ ናሆም አዘነ። ሃሳቡን ም አቀረበ። መስ በደስታው እንደ እሚጠግብ አሳውቆ በመጠነኛነት በተገኘው የ ተስ. አገልግሎት እንደ እሚደገፍ እንደ እሚአምን አሳወቀ እና በሌላም መጨዋወትዎች ሆነው ወደ ቤት አዘገሙ፨
እሚ የሥጦታው ውድ መሆን አሳስቧት ተጨነቀች። ለሁሉ ድጋፍ እና መነሳሳት፣ አጎትአቸውን በልጆቿ ፊት አመስግና መረቀሠ። በወንድሟ መባረክ እና የቤተሰቧ አዳኝ ሞገስ ስለሆነ ትልቅ አክብሮት እና ፍቅር ቸራ በተለመደ ምርቃት እና መልካም ምኞቷ ጀርባ ጥቂት ዕንባዎችም ከለሰች፨
የ ሽያጭ ንግድዋም እየበረታ ሲሄድ መስ በመልካም ምኞት ቀጣዩ ዓመት የሰላም እና ስኬት እንዲሆን ተመኝቶ ቤተሰቡን በትልቅ ሃዘን ጊዜው ደርሶ ተሰናበተ። መንደሩ የሞቀ እና የደመቀ ነበረ። መንደሩ አዲስ ቀለም እና አዲስ ዓለም የገመረ ነበረ። መንደሩ አባት እና መሪ ያስተናገደ ነበረ። መንደሩ ዓዉራውን መመለሻ ው ደርሶ ነበረ፨
የ ባቤ ሰዉነት ሙሉበሙሉ አገግሞ፣ ለአጥንት እና ወለምታ ታካሚ እንደ እሚታዘዘው፣ የፍየል ሥጋ እንዳይበላ በመመከሩ እና የፍየል ሥጋ ሲጀመር ድርሽ ባለማለቱ የመዉደቁን አጋጣሚ፣ የሃኪምዎቹን ማዳን ጥረት፣ በፍየል ትልቅ ስእል ጎን አዋዝቶ ክረምቱን በሞነጫጨረበት እና አመሰግንአለሁ ብሎ በሰየመው ስእል ለሁለትኛ ተከታታይ ዓመት የመለያያ ስእል ሥጦታ እንዲሆነው አድርጎ አቀረበ። ጢኖ አቅፋ በረዘመ መሣም ቆይታ በማነቅ እና ወዲአው ለቅቃ በማኩረፍ ፍቅርዋን ቸረች፣ ገለፀች። ቢግ በመሰል ትልቅ ፍቅር እና አጭር ዓመት ቆይታ እንዲለያይአቸው አበክሮ በመመኘት ፍቅሩን ገለፀ። እሚ በመሸኛው ጊዜ በተለየ በማልቀስ የተለመደ ፍቅሯ ተገለጠ። በመጨረሻዎቹ ቀናት በመደጋገም አወሩት መሰረት የሚስት አጋር ለመሞከር ቃል እንዲገባ ተደረገ። በማሰብ እንደ እሚበረታበት ገልፆ መጨነቁ እንዲቀር ደግሞ አሳወቀ እና በተካነችበት እሚመስል የጠላ እና አረቄ ንግዱም እንድትበረታ ናሆምን በምስጢር እየተመለከተ አሳወቃት። ብሩ እና ናሆም ያለችውን ሻንጣ በመሸከም ለመሸኘት ወጡ፨
ሆድሆድ እሚብስ ቆይታ ሆኖ በተረበሸ መንፈስ ሲጓዙዙ እንደ ነበር ሳያስተዉሉ ወደ መናኸሪአው ደረሱ። ብሩ ጨዋታ በማምጣት መለያየቱን አናሽ ቅዝቃዜ አላብሶ በመጨረሻ መለያየት አይቀር ሆኖ ተሰነባበቱ። “ሰልም ግባ አባትአችን!” ብሩ በተለየ በልጅዎቹ ላይ የመስን ተፅዕኖ አስተዉሎ ስለ ከረመ የአባትነት ማዕረጉን በመጨረሻው ሰዓት ቸረው። መስ በትልቅ ክብር እና ደስታ ተሰናብቶት “በብዙ ሃሳብዎች እና ፍሬነገርዎች መዘብዘብ አስጨንቄህ ከሆነ ትልቅ ይቅርታ!” ወደ ናሆም ዞሮ ቅሬታውን ገለጠ። ናሆም ከቶ የከበደው የሃሳብ ጉዳይ ኖሮት እንደ እማያውቅ እና በማደጉ ላይ የጨፈገገ ስሜት ብቻ እንዳይኖር፤ በአዉቆታ የተረዱትን በመግለጥ እና ሃሳብ በማጥለል እንደ ተጠቀመ ብቻ አሳወቀ። ‘አገነዛዘብ በጥሬ ቃልዎች ጠልሎ እንደ ባቤ ስእል መታየት ከአልቻለ፣ አገነዛዘብ ብቻ ሳይሆን፣ ደመነብስ ብቻ ነው፤’ “እማይተካ ሥጦታ በይቅርታ ሳይሆን አመስግነኝ በማለት ነው እሚገለጸው!” ናሆም ፈገግ ብሎ በማመስገን መንፈስ ሁኔታውን አረጋገጠ። “የሜነጋገርንውን የ ፌስቡክ ጠላ ነገር አስብበት!” በመጨረሻ የጀምበር ኩምኮማ ወቅት እየተሣሣቁ ሲአመሹ ከደረሱበት አንድ ሃሳብ ላይ እንዲበረቱበት ለናሆም ማሳሰቢአ አክሎ የሃዘኑን ድባብ ለመስበር ሞከረ። ናሆም በመስማማት እሺታውን ገለፀ። በመጨረሻ ተሰነባብተው ሲተቃቀፉ፣ ናሆም ወደ ማዘኑ ተመልሶ ዓይንዎቹ አለ ፈቃዱ እረጠቡ። በአክብሮት እና ፍቅር ስሜት ፈገግ ብሎ ሸኘው እና ወደ መኪናው መስ ገባ። ወንድምማማችዎቹ መመለስ ሲጀምሩ ብሩ የናሆምን ጥልቅ ስሜት ስለ እሚአቅ እና አሁንም ሃዘን ብጤ እንደ ሸበበው ተመልክቶ፣ ለማጫወት ያክል “እንደ አባት ነው! እንግዲህ ተራርቆም መቀራረብ ይቻል አለ!” ወንድሙ ስሜትአዊ እንደ ሆነ ተገንዝቦ ለማረጋጋት እና ማፅናናት ሞከረ። ናሆም ከሁኔታው ለመመረቅ በመጣር መሄዱን እስኪለምድ እንጂ ለመቀበል እንደ እማይከፋ እዉነት አድርጎ አረጋገጠለት። ‘ስንት ብንማር ብንመራመር አባትአዊ ምቾትን ግን ማጣቱ መተኪያ የለውም!’ መስ ብቻውን እንደ ጓደኛ፣ አባት፣ አጎት፣ ተንከባካቢ፣ መካሪ እና ተመካካሪ፣ እጅግ የቀረበው እና በቅርበት እሚአቀው ጀግና የሆነው ዐዋቂ ሲለየው የተሰማው ወደርየለሽ አጊንቶ ማጣት ስሜት ለራሱም አስገራሚ ሆኖ ታየው። በመለያየት እሚፈጠር ድንገቴ ስሜት ትንግርት ሆኖ ሲጠነክር ደግሞ አስተዋለ። ብቻ ማዘኑን ለወቅቱ በመልመድ እስኪቆይ እንጂ፣ የከፋ እንደ አልሆነ ብሩም እርሱም ተረዱ። ብሩ በሙሉ ቅርበት ከአብሮ ማደር እና፣ ዓለሙን ሁሉ አብሮ ለመገንዘብ መታተሩ እና ተጨማሪ የዝምድና ጥያቄዎች ጋር የነበረ ግንኙነትአቸውን አስተውሎ ስለ ነበር በናሆም ዳግ-ድርጊት (ሪአክሽን) ልክታ እንጂ ያን ተከትሎ ስህተት አላስተዋለም። ወደ ቤት ተመልሰው እሚን ማገዙን እና ማስለመዱን ቀጠሉ፨

የ ቤተሰቡ ነገረሁኔታ በእሚ መጠመድ ተቀይሮ፣ ጮለቅ እና ጢዩ ብዙ ጊዜ አብሮ በማሳለፍ፣ በመቀያየር ወንድዎቹ ሻይቤቱን እያገዙ ማገልገሉን ተያያዙት። በትጋት እሚሰሩት ንግድ ሥራም ከቶ አለ መክሰሩ በሂደት ፈጽሞ ተረጋገጠ። ትርፉ ደግ ነበር። ሙሉኛ፣ ወጪ በገቢ ይጣፋ ነበር። መስከረም ላይ ነገሩ እንደ እሚሻሻል እሚ ታወቃት። ሰራተኛዎች ወደ ጓሮ ዞረው ከመንገዱ ማዶ የለው የእምቅ ገበያ መንደር እንደ እሚተምም ገመተች። በጋውም ሰው ሲአንቀሳቅስ እና ኢትየጵያ በመስከረም ወደ መደበኛ አኗኗር ወከባ ስትገባ፣ የእርስዋም ንግድ ሊጠቀም እንደ እሚችል ተገነዘበች፨
ናሆም ጋሽ ተሻገር የሰጡትን ሢሶ በመንከባከብ የገበያ ሰንሰለት ክፍተት፣ የግብርና እንክብካቤ ሀሁ፣ እና መጠነኛ እረወዳታ ለእሚ ንግድ አቀረበ። የአሸተ ጤፍ ጎን የሰላጣ ምርቱን ሰብስቦ በጊዜ ለአገልግሎት አደረሰ። እግረመንገዱን መጠነኛ ሥጦታ ለጋሽ ተሻገር አድርጎ አስደመመአቸው። ሌላዎቹም አትክልትዎች ማደጉን እና መድረሱን ተቀራርበው ነበር። በአስርኛው ቀንም ሰላጣው ለ ተከታይ ዙር ቅጠልዎቹን አስፍቶ በማሳደግ ደረሰ። እሚ በቀረበው ልዩነት ተደምማ ንግድዋን የሂወቷ መሰረት ለማድረግ በረታች። በሂደት የናሆም ልዩልዩ መብልዎች ተወዳጅ እና ወጪ ቆጣቢ እንደ ሆኑ በጉልህ መታየት ጀመረ። መጠነኛ ትርፍ ብጤ ተገኘ።
ብሩ ወደ ትምርቱ ለ መሄድ ሲዘገጃጅ እሚ መጠነኛ ትርፋን አማጥጣ ብዙ ባይሰኝም ድጋፍዎች አድረጋ ለመሸኘት በቃ። ወደ አዲስአበባ ሲደርስ መስ አስተናግዶት መለማመድን ከወነ። ናሆም ተክልዎቹ ደርሰው ባገኘው ዉጤት ታላቅ መደነቅ ዉስጥ ገባ። ከፍተኛ የምርትአማነት ዉጤት እንደ ነበረ አሰበ። ነገርግን የተሰበሰበው አንድ ጆንያ ካሮት እና ቀይስር፣ አንድ ጆንያ ነጭ ሽንኩርት፣ ግማሽ ማዳበሪአ ቃሪያዎች፣ ግማሽ ማዳበሪአ ቲማቲም እና ተከታታይ የ ቆስጣ ቅጠልዎች ነበሩ። በ ግል መሬት ላይ ሥራው ቢከወን ብዙ ብልሃትዎች ተጠቅሞ ትርፋአማነት እንደ እሚዘልግ ተገነዘበበት። በቤት ጓሮ እንኳን ቢተከል ብዙ እንደ እሚገኝ ከ ሰበሰበው ብዙ ምርትም አስዋለ። የነጭ ሽንኩርቱ መድረቅ እና ማገልገል ከቻለ፣ ዓመት ሙሉ ማገልገል ሲችል በወጪ ከ ሦስት ሺህ ብር በላይ እንደ እሚሆን ሙያአዊ ግምት አደረገ። በአጭር ስፍራ የተሰበሰበ ሽንኩርት በ እርግጥ በገበያ ዉድ ዋጋ ነበረው። ሌላዎችም ምረወትዎች ብዙ በ ማዳን ለእሚ የብዙ ሺህብርዎች ማርያምመቀነት ሆኑ። አሁን ወጪ በ ከፍተኛ መጠን አሽቆልቁሎ ማለት ይቻል አለ ገቢ ሁሉ ወደ ትርፍነት ለ መዞር እሚፈቀድለት ሆነ። ከንግድ ሰንሰለት ክፍተት ይልቅ ግን የግብርና ሙያን በ ሙሉልብ አንድ ገጽታውን ተመልክቶ ወደ ዘመንአዊ ግብርና ዳግምርምር መግባት መቻሉ እንደ እሚረዳው እና እንደ ብዙ አስተማረው ተረዳ። ትልቅ የ መብሰል እና የ ዉጭ (ከ ምናብ) ዓለሙን መቆጣጠር መልመዱን እንደ አገዘለት ተገነዘበ። የ ጋሽ ተሻገር ምርትን በመንከባከብ የ ደገልግሎት ዋጋውን እየአጣጣ እና ተያያዥ የጤፍ ስዳውን በመማርም ሰነበተ። ማጨዱን እና መከመሩን፣ አፈር ከእበት አደባልቆ መሬት አበጅቶ መዉቃቱን፣ እበቅ ከገለባ አንጥሮ መለየቱን በ አያቅተኝም ስነልቦና እና እሚቻል ምርምር እየአገዘ በጋሽ ተሻገር መሪነት ነገሩን ሁሉ በስኬት አጠናቀቀ፨
የ ዓመቱ ሩብ ወቅት፣ ከመዋእለህፃናት ትዉዉቅ ዉጭ የነበረችው እና በአንድኛነት አንድኛ ክፍልን ያለፈች ውጢዩ ሁለትኛ ክፍል ገብታ መማር የ ጀመረችበት፣ ባቤ እና ቢግ በመማር እና ግል ጥናትዎች እና ተያያዥ ሥራዎች ያደጉበት ሆነ። የናሆም አለቃነት የሰገገበት እና እሚ የጥቂት በአሰራሩ ተክና በመጨረሻ አንድ አጋዥ ተመላላሽ ሰራተኛ የቀጠረችበት ሆነ። በቂ የገቢ እና ወጪ ልዩነትዎች ተመልክተው በናሆም ክረምት ሙከራ ገጸበረከትዎች ንግዱ የትርፍ ቀስቱን የአሻቀበበት ሆነ። እሚም በጎን አረቄ ባዘጋጀች ጊዜ ናሆም በፌስቡክ እና ትስስርአዊ ድረገጽዎች የንግድዎቹ አገልጋይ ገጽ ከፍቶ በታለመ ማስተዋወቅ ብዙ የአዲስአበባ እና አካባቢው ደንበኛዎችን ለ ሙከራ አድርጎ ሳበ። የእሚ አረቄዎችን ምስል በመለጠፍ እና ሁነትዎች በእኛ አረቄ አማሩ በማለት ብዙ ተከታይ ማፍራት ቻለ። አሃዝአዊ ስነገበያ ጥቂት ጥናትዎች አድርጎ በታዘዙ ጊዜ በመስ አማካይነት ማድረሱን እና ደግ ጥራት መጠጡን እሚ ከ ሰጋችው የአካባቢ ገበያ መስከን አሻግረው መቸብቸቡን ተያያዙት። እሚ በአገኘችው መበረታቻ ለሰርግዎች እና ዝግጅትዎች፣ ለልዩልዩ ትዕዛዝዎች በናሆም በእሚላክ ትእዛዝ አሃዝአዊ መቀመጫዋን ከቤቷ አድድርጋ ትርፍ እና ዕዉቅና ማግኘቱን ወጠነች፨
አንድ ምሽት እሚ ናሆምን ጠርታ ለማነጋር እንደ እምትፈልግ ገለፀች። “አትቆጣ!” ብላ ጀመረች። ናሆም ግራ በመጋባት ተመለከተ። “ንግዱ ማትረፉ ከተረጋገጠ፣ እንዲህ ብዙ ከተገኘ…እባክህ ሌላ ምን ይፈለግ አለ ትምህርት ብለህ ሩቅ አገር አንተም አትሂድ!” ናሆም በሃሳቡ ከቶ አለ መዘየድ በቀለለ ስሜት ሆኖ አሳወቀ። እሚ መልሳ ሃሳቡን ተወት አደረገች። “ግን ደግ ማትረፉ ካለ ማስፋቱ ከተቻለ ምን ይፈለግ ነበር?” ባልተዋጠላት የናሆም ዉሳኔ የነፃነቱ ጉዳይ ግን አስተማምኗት ለጊዜው ሃሳቡን ፈታች፨

ብዙ ሳይቆይ አቶ በረከት በድንገት ወደ ቤተሰቡ ተቀላቀለ። እሚ በእንባዎች ስትታጠብ ልጆቹ ሁሉ ደስታቸው ማብቂያ አላገኘም። አቶ በረከት በአደረጉት ለውጥ ተደምሞ ሁሉንም ይቅርታ ጠይቆ እና ቀና ሆኖ በመቀላቀል አስደመማቸው። መልካም ጊዜን ይህ ፈጠረ። በቆይታ መለማመዱም ሆነ፨


ዓመቱ በየፊናአቸው ለቤተሰቡ አላባውያን የሂወት መስመር ወርዉሮ ሲአንቀሳቅስ ቆየ። አቶ በረከት በባለሦስት እግር መኪናዎች አከፋፋይነት ደህና ንግድ ለመጀመር እሚጥርበት እና ወደ መስመር እሚገባበት እየሆነለት ሄደ። እሚ ከበረታችበት ንግድ ብዙ ተምራ በናሆም እርዳታ ስኬትአማ የመሆን ጉዞዋን ቀጠለች። ብሩ ስኬትአማ ቆይታ በመጀመሪአ ዓመት አድርጎ በዮስ ጋር አብረው ሲመለሱ አንድ ብስራት አቀረቡ። የስዊድን መንግስት ነፃ የትምህርት እድል ተጠቃሚ ለመሆን በእየዓመቱ ከእሚጓዙ ወደ ሦስት መቶ እሚጠጉ ኢትዮጵያዎች መሀል ሁለቱ አሸናፊዎ ሆነው ለ ክረምቱ ተመለሱ። ዜናውን ለእሚ እሚአስረዳበት መንገድ ግራ ገብቶት ናሆምን ቀድሞ ለማሳወቅ በማሰብ ተረጋጋ። የብሩ ቤት መድረስ በሆነበት ዕለት ደግሞ ናሆም የብሔርአዊ ፈተናው መፈጸም እና የፍኖት ማህበር ለተተኪዎች የመሻገሩ ነገርን በተመለከተ ከ ጓደኛዎቹ ጋር ተሰብስቦ ወደ ተከታታይ ዝግጅትዎች ለመሳተፍ ወጥቶ ነበር። ጓደኛዎቹ በፈተና መጨረሱ ስም ከሁለቱ የማህበሩ አዲስ ተተኪዎች ጋር በአንድነት በትምህርትቤት የተሰባሰቡት በፈተናው ማብቂያ ማግስት ነበር፨
በ ፈተናው ብዙ የተከፋ ሳይኖር ሁሉም በመሰብሰብ፣ በመሰብሰቢአ ክፍልአቸው ከተጨዋወቱ በኋላ ጊቢውን ለመሰናበት እና ወደ ቀጣይ ዝግጅትአቸው ለመሻገር አሰቡ። በአስራሁለት አባልዎች ማህበሩ በጩኸት ማስተጋባት ጀመረ። ሠብለ በመሀል ሆና ተከበበች። ሁሉም የእምታወጣውን መሪ ድምፅ ይጠባበቅ እና ለመቀበል በ ተቀባይነት ይዘጋጅ ነበር፨
የ ቀጠነ ድምፇ በጩኸት ወጥቶ ጮኸ፤ “ፈተና የለም!” መሪውን ቃል አወጣ ች። ሁሉም በህብረዜማ እኩል ቃልዎቹን አዝልገው በመጮኽ ደጋገሙ። “ከ እንግዲህ! ከ እንግዲህ! ከ እንግዲህ!”
በ ተመሳሳይ ዜማ የ ሠብለ ዜማ አስተጋባ። “ፈተና የለም!” የወል ዝማሬ ተደገመ። “ከ እንግዲህ! ከ እንግዲህ! ከ እንግዲህ!” ሦስትኛ ጊዜ ደግማ ስትጮኽ ወደ ጊቢው ዋና መናፈሻ ተቃረቡ። በወል ተቀባይነት አፀፋውን ወየ መለሱ ወጡ። ሠብለ በጩኸቷ ቀጠለች። “ይቺ ትምህርትቤት የለችም!” “ከ እንግዲህ! ከ እንግዲህ! ከ እንግዲህ!” “ወደ ጊቢ ነው!” “ከ እንግዲህ! ከ እንግዲህ! ከ እንግዲህ!” “በርማታ ቲቸር የለም!” ድምጽ ዘልጎ መዉጣት ቀጠለ “ከ እንግዲህ! ከ እንግዲህ! ከ እንግዲህ!” ተጮኽ። በርማታ በብዙዎች ከቶ የእማይወደደ ወግአጥባቂ እና የተቃርኖት ፍች ተደርጎ እሚወሰድ መምህር ነበር። ሠብለ ደግማ “በርማታ የለም!” ስትል ጩኸቱ ወደ ኹካታ ተለዉጦ ጉሮወሸባው በዛ። “ከ እንግዲህ! ከ እንግዲህ! ከ እንግዲህ!” “ፍዮኖት የለም!” “ከ እንግዲህ! ከ እንግዲህ! ከ እንግዲህ!” አዲስ ገቢዎቹ ግን ከ መጮኹ አሁን ዝም አሉ። አፍ ለጉመው ም ቢሆን ግን በመተያየት ተሳሳቁ። “ጊቢ ነው!” “ከ እንግዲህ! ከ እንግዲህ! ከ እንግዲህ!”

ከጊቢው ሲወጡ ዓሊ እና ናሆም ደጉ ደጉ ሩቅ ሆኖ ሲመለከትአቸው አዩት። ቤተመጽሐፍአዊ ባህሪው የመጽሐፍትል ያስባለው ደጉ በፈጣኒት-ጭንቅንቅ (ሃይፐር-ዎሪይንግ) እሚታወቅ ሲሆን ትንግርተኛ ጉዳይዎችንም እሚአነሳ፣ ብዙ የጥናት ግኝትዎች አሉኝ እሚል፣ ከማንም የእማይቀራረብ፣ ለሰው ሁሉ እጅግ ፈሪ መሳይ ሰው ነበር። ተማሪዎች በመጫወት ሲቀልዱበት መምህርዎች እንደ ንቤ (ድሮን) እሚአስተናግድ ቤተመጽሐፍተኛ (ላይብራሪያን) ብቻ ይመለከቱት ነበር። ከወጡ ሃሳብዎቹ መሃል ለምሳሌ ለህፃንዎች፣ ኤቢሲዲ፣ ሀሁሂሃ ከመማር እንደ ካት፣ ቦል፣ በግ፣ እጣን፣ ያሉ ቃልዎች በማንበብ ፊደልዎቹን በወል በማስተኮር በቀጥታ ወደ ፊደል ሰፈከ ስራው ማስገባት እና ማስተማር ተመራጭ እና ተገቢ ነው። ፊደል ላይ ከፍተኛ ማፍጠጥ አንጎል ይጎዳ አለ። ዝብፍሰት ላለበት በተለየ የወደፊት በሽታ ይሆነው አለ። ብሎ የአምን ነበር። ሌላ ጊዜ ናሆምን ድንገት አቻኩሎ ጠርቶ ጣትዎቹን አስመልክቶት ከናሆም ይልቅ አለንጋ ከሆኑ ተወዳደረ። ሌላ ጊዜ የጣና ሃይቅ ዓሣዎች ጎን አጥንትን ለመመርመር አራት መቶ ብር ለ ዓሊ ሰጥቶ እንዲአመጣ አዘዘ። ብዙ ምርምር እሚአረቅቀው መምህር ትንግርት ፀባይዎቹ ለብዙዎች መሳለቂያ ሲሆን እነ ናሆም ግን በመረዳት መርዳት አይተውም ነበር። እንደውም የኢትየጵያ ጭራ-ደረጃ እድገት እነ እዚህን ስለ ዘነጋች ነው ብለው ያምኑ ነበር። እነ እዚህ በሰመጠ ቅዠት ሲአስቡ የእማይመስልን ወደ ገሃድ ለዉጠው ችግርዎች ወይም ይፈቱ አለ ወይም ለሌላ ግኝት መሰረት ይሆኑ አለ ብለው ያምኑ ነበር። ለ ምሳሌ የእንግሊዝ የዓለም ጦርነቱን ማሸነፍ በጀርመንዎች ድብቅ የጥቃት ትእዛዝዎች ስለላ ነበር። እንግሊዝ በመሽመድመድ ስትሸነፍ፣ ጀርመን የት እንደ እምታጠቃ እምታስተላልፈውን መረጃ አነፍንፎ መድረስ ስለ አልቻሉ ነበር። ነገርግን የመረጃውን ማነፍነፍ የበቃው የሂሳብ ሊቅ በሽተኛ እና የስነልቦና ቀውስዎች የነበሩበት ነበር። ያመረታት አንቀሳቃሽ (ማሽን) መኪና መረጃ ጠልፋ ትተረጉምም ጀመረ። እንግሊዝ ጦርነቱን አሸነፈች። ይህ በሽተኛ ዜጋ ዘ ኢሚቴሽን ጌም እሚሰኝ ፊልም ሲሰራለት እና ሂደት በሂደት እስከ ቅርብ ድረስ የእንግሊዝ ታላቅ ዜጋ ተብሎ ሲከበር ግን ወዲአው ነበር የሞተው። አንድ በሽተኛ የሃገር ወሳኝ ታሪክአዊ ድል የወርቅ ቁልፉ ነበር። እልፍ የዓለም ኃያልነትዎች የተመዘዙት በተናቁ እና የተዋረዱ ደጉን መሰል ተንገላቺ አዉጠንጣኝዎች በፈበረኳት አንዲት ፈርቀዳጅ ግኝት ነው። የእዚህ ቤተመጽሐፍ አንዱ በአለሙያ ግን ናሆም እና ዓሊን በቀር እሚአናግረው እንኳ የሌለው እና ስነልቦናአዊ በሽተኛነቱን ሰው እንደ ሰው እንደ አይቆጥር ያደረገው በቂ እና ፍትሕአዊ ሃቅ ነበር። ደጉ የሁለቱን ልጅዎች መመረቅ አስመልክቶ በግሉ ጠርቶ ትልቅ ሰላምታ የሰጠው ገና በፈተናው ማለቅ ማግስት ነበር። በባዶ የቤተመጽሐፉ ክፍል ተጋብዘው መልካም ምኞት ተሰጥተው ተሸኛኝተው ነበር። አሁን ግን በይፋ ሲለዩ ደጉ ደፍሮ ወደ ዉጭ ወጥቶ መደባለቁን ከቶ ባያስብም በእሩቅ ግን በሰፊው ይፈግግ እና ሰላም ይል ነበር፨
አሁንም ከአለበት የቤተመጽሐፉ በረንዳ ላይ በማጨብጨብ እየአጀበ ከ እንግዲህ እሚሉትን ጨዋታ ማገዝ ቀጠለ። ወደ መዉጫ በሩ ሲቀርቡ ተመልሶ ወደ ቤተመጽሐፉ ተፈተለከ። በመጨፈሩ መልሰው በማተኮር ሲራመዱ፣ ወደ መዉጫ በር ጋር ደረሱ። ዘበኛው ይሄይስ በተደበላለቀ ስሜት ተከብቦ ቀረበአቸው። ከጊቢ እየወጡ ዘፈኑለት። “ይሄይስ ዘቡ የለም!” ሠብለ እየተመለከተችው ወደ እርሱ ጠቁማ በጩኸት አወራች። “ከ እንግዲህ! ከ እንግዲህ! ከ እንግዲህ!” ሁሉ በሣቅ ጮኾ እየከበበው አስተጋባ። ይሄይስ ተደስቶ የዘበኛ ኮፍያዉን አዉልቆ በማንጠልጠል ለጭፈራ መሀከልአቸው ገባ። ሠብለ ጎን ሲቆም ጨዋታውን በጩኸቱ ቀጠለችለት። “አንተ ኑርልን!” “ከ እንግዲህ! ከ እንግዲህ! ከ እንግዲህ!” ዘበኛው ታላቅ ደስታ ው ሰማይ ነካ። ሁሉን እየሳመ በመልካም ምኞት ተሰናበተ። በተለየ ናሆም የብዙ ንግድ አማራጭዎች አቅርቦ ተቀምጦ ሲውል እንዲሰራ ከንግድ ድር አመሰራረት እና ተግቶ ታግሎ መስራት ሰበካ ጋር ስለ አነሳሳው እና ጠቀም ያለ ጉርሻዎችን በጎን ሥራዎች ማግኘት ስለ ጀመረ፣ ናሆምን በመመረቅ እና አቅፎ በመሳም የተለየ ክብር ገለጠለት። አብረው በመጮኽ ሁሉም አጀቡት፨
ወደ ውጭው ሲወጡ የከንግዲህ ዝማሬውን በሩ ላይ ተረካከቡ። አዳዲስዎቹ ልጅዎች ተከበቡ። ተጨፈረ። “ወሰዱት!” በመጮኽ በይፋ ፍኖትን ለማሻገር፣ ሠብለ ብዕር አስረከበችአቸው። ሁሉ አጀበ። “ከ እንግዲህ! ከ እንግዲህ! ከ እንግዲህ!” እየ ተጨፈረ በቅጽበት ቆይታ ከፊል-ይፋ መሳይ መጨዋወቱ ቀጥሎ በግሩም ሃሳብ አቅራቢነት በትምህርትቤቱ ፊትለፊት ብዙ ሳይርቅ ወደ እሚገኘው የ መኑ ልጅዎች መጠጥቤት ገቡ። የጃምቦ መጠጥ ተከፋፍለው አንድ እርጅም ሸጓጣ ስፍራ ወርረው መመጠጥ እማይወስድ ሁሉ ደፋፍሮ ሲጎነጩ ቆይቶ ሁሉም በየተራ መቆም እና ፅዋ ማንሳት ጀመረ፨
ለፈለጉት እና ለመሰለአቸው ፅዋ በማስነሳት ደስኩረው፣ ስለ ክብር ፉት ብለው በማጣጣት መቀመጥ ሲቀጥሉ፣ የሠብለ ተራ ደረሰ። ለደስታ በተቻኮለ ቃልዎች ምርቃትዋን ከሚጮኸው ኹካታ እና ዘፈን አስበልጣ በማነብነብ አቀረበች፨
“ለእኛ ወላጅዎች፣ መምህርዎች፣ ሀገር እና ከተማ ምስጋና ይድረስአቸው!” ሁሉም በኹካታ “አዎ!” “አዎ!” “በማለት አገዛት። “ቆይ! አታስተካክሉኝም? ከ እግዚእአብሔር ቀጣይ መች አልኩ?!” ወዲአው እርማት ሰጥታ ጥርስዋን አስመለከተ ች። ትንሽ ሞቅ ይላት ጀምሮ ኖሮ ለ ሰከንድ ፈዘዝ አለች። ዓሊ “ዝብ ፍሰት አለባት እንዴ ይቺ ልጅ?” ለግሉ በ መገረም ጠየቀ። ሲሰክር እንደ በረዶ አንድ ቅጽበት ላይ ቀጥ እሚል የዝብፍሰት ህመም እንደ አለበት በ ግሉ የ ደረሰበት አገነዛዘቡ ነበር። “ ነገሩ በሰው ልጅ ሁሉ ከዓይንዎች መኖር እኩል እሚገኝ ተፈጥሮአዊ ህመም ነው! እንደ ስኳር በሽታ ወይም ጤናአማ መጠን ሊአገኝ ወይም ሊከፋ፤ ከምንን በላይ በወቅት ወይም ሁኔታ ደግሞ ከፍ ዝቅ ብሎ ሊለዋወጥ ይችል አለ እንጂ በጠቅላላው ግን በሰው ሁሉ አለ!” ለእራሱ አዉርቶ ወደ ዉጭው ከባባቢ ዓለም ሲወጣ፣ ሁሉም “ለ እናትሽ! ለ እናትሽ!” እየአመሰገኑላት ደረሰ። ተቀላቅሎ “አዎ ለእናትሽ!” “ብሎ ዐጀበ። ፅዋዋን አሁንም ነሣ አድርጋ ዝቅ በማድረግ ወደ ሌላ ተመስጋኝ ቀጠለች፨
“ከ ትምህርት ጎንለጎን ብዙ እንደ እሚቻል ለአስተማረን ናሆም በረከት!” “ለ ናሆም! ለ ናሆም!” ሁሉም አዉካካ። “በፍልስፍና ሁሉ ይደገፍ አለ እሚሰኝ የ ጎንለጎን ነቢብ ይዘው ከጓደኛዎቹ ጋር ሲንቀሳቀሱ እንደ ነበር ጭምጭምታ ይሰማ አለ።” አንድ ቀጫጫ ድምፅ አቋረጣት። “ምን ማለት ነ..ው?” ለማብራራት አልፈለገችም። “ለእኛ ኢኢትዮጵያዎች አኗኗር ብቻ የእሚሰራ አንድ ተጨባጭ ገሃድአማአዊነት (ፕራግመቲካል) አካሄድ ከተማሪዎች አንፃር ተበጅቶ ሊዘምት ይገባ አለ። ልጅዎች ከትምህርት ሃላፊነት ጎንለጎን እራስ ችለው ወይም በመነገድ ሙከራዎች ከፍተኛ የመንቃት እና ሃላፊነት የመውሰድ ጥበብን ከተግባርአዊ ተሞክሮ እንዲቀምሙ እና ለሥራ እንዲበቁ እንዲችሉ… ከትምህርት ጎን መነገድ ቢችሉ…ግለትምምን መገንባት…ኡፍ! ብቻ የእኛ ጀግናዎች በጊዜአቸው ያብራሩበት ይሆን አለ!” በአጭር መነካካት እንደ ተረዳአችው ተናግራ በተቻኮመው አስተያየትዋን ቀጥላ አሁንም ፅዋ ነሣ ዝቅ አደረገች። “ብቻ ግን ለናሆም ነው ያልኩት!” ሁሉም ጠረጴዛ መታመታ አድርጎ በአንደበትም አገዘ። “ናሆም! ናሆም!” ድምፅዎች ተንጫጩ። መልሳ አሁንም “ለ ዓሊ!” ስትል ሁሉ የበለጠ አዉካካ። “ዓሊ! ዓሊ! ዬ!” የግንኙነትአቸው ጥግ የታወቀ መስሎአት ደነገጠች። ጥቂት የሰመጠ መቀራረብ ስለ ጀመሩ በ ፍራቻ ልትዋጥ ዳዳት። መልሳ በሁኔታው ሁከት ተዋጠ ች እና ሳትገፋበት ተመለሰች። ለነገሩ ሁሉ አሁን እሚአከትም ይመስል አለ። መለያየቱ አይቀሬ እየለነ ነበር። በመገረም ስትመለከት እና ስትቃኝ ራቅ ብሎ ሠብለ ጋር ያለው ዓሊን ተመልክታ ተጋጩ። ናሆም ሃሳቧ ስለ ገባው ፈገግ ብሎ ፅዋ አነሳ እና ብቻውን ጮኸ። “ዓሊ!” ሁሉም በኹካታ ፈገገ። መልሳ “እና እና እና … ለ ፍኖት!” አለች። ሁሉም ደግሞ አዉካካ “ለ ፍኖት!” “ፅዋውን እናንሳ ለተመረጡት!” ብላ ላመሰገነችአቸው ሁሉ በአንድነት ፉት አለች በመጨረሻ። “ለ ተመረጡት!” ሁሉም ፉት አለ። ጨዋታው ቀጠለ። በኹካታ ቆይተው በእየተራ መሰል ፅዋ ማንሳትን አደረጉ። ሁሉም ተመሳሳይ ምስጋና ለመረጡአቸው ቸሩ። ፉት በማለት በስማቸው ስለ ክብር ጠጡልአቸውም። የናሆም ተራ ሲደርስ ኹካታው በረታ እና ፉጨት ሁሉ ተከተለ። “አመሰግንአችሁ አለሁ ጓድዎች!” በወሮች ልዩነት ፂም የወረረው ፊቱን አቅርቦ ሲቆም ሁሉም አጨበጨበለት። ከአምላክ እስከ ቤተሰብ አመሰገነ። “ከአንተ ጋር የነበረኝ ጊዜ ደግሞ መቼም አይረሳም! ከቶ! ከቶ! የመሸታ ፈተና ሰሞን ንባብ! የፍኖት እልህ አስጨራሽ ግን ስኬትአማ ጉዞ! የምኞት እና ህልም ስብከቱ! የጨዋታ ቀኑ!…በጣም እማያልቅ ትዝታ አለን እና አመሰግንአችሁ አሁንም አለሁ!” ሁካታ ሆነ። ቀጥሎ ተናገረ። “ከ ትዝታ ማስቀመጥ አንፃር ጥሩ ዘመንዎች ስለ ነበሩን ብቻ ግን አይደለም ስለ አወቅኳችሁ እምኮራው። ስንመለከት ዞረን አንድቀን እምንጠቅሰው ስራዎችም ስለ ተውን እንጂ!” የፍኖት ጦማር ገጽ የደለበ ልጥፍዎችን በመደመም እየአስታወሰ ተናገረ። ፉጨት እና ጩኸት ቤቱን አደባለቁት። “ጎንለጎን? ጎንለጎን?” አንድ ጥጋት ላይ የመሪ ጥያቄ ድምፅ ጮኾ ተሰማ። ጩኸት ተከትሎ አገዘው። ናሆም ቀጠለ። “ጎንለጎን ከ ጓደኛዎቼ ጋር አምና የአጠራንው አብሮን ግን ጥቂት ቀደም ብሎ የነበረ ሃሳብ ነበር። ወደ ነቢብ (ቲዎሪ) ስናሳድገው ግን ትላንት፣ ዛሬ እና ነገን በጠቅላላው ስገልፀው ማለት ነው፣ ሰድረን የተመለከትንበት ነበር።” አንድ ድምፅ አሁንም ከጥጋቱ ጮኸ። “ጊዜአንፃርአዊያንዎች!” ሁሉም ፈገገ። ወደ ናሆም ሲመለሱ ፈገግ ብሎ ወደ ጉዳዩ ተመለሰ። “ትላንት ጎርፎ ሆኖ ዛሬ ላይ ጣለን። ነገ ደግሞ ጎርፍ እኛን ያደርስለት አለ። ዛሬ መኪናነቱ ሲአረጅ። በእየቀኑ በመጫን ስንኖር ወደ መቃብር እንጂ ወደ ቦግ ያለ ዕለት እንደ እማንነቃ ተገነዘብን!” ከፍተኛ ፉጨት የጣሪአውን ሰላም ድብልቅልቁን አወጣው። ሳቅ አለ ናሆም። “እና በዛሬ የተውንው እራስአችንን ነገ ስንነቃ እምንቀላቀል እንቅልፍአማ’ ዘረፍጥረትዎች ነን። ስለ እዚህ ከመተኛት ቀድሞ በማስላት ብናቅድ ነገን በምንፈልገው ገሃድ ከብቦ እንዲቀሰቅሰን ማድረግ እንችል አለ ማለት ነው።” “ኡ….ው!” ጩጩኸት ሌላ ሰው ደስታውን አስተጋባ። መልሶ ሳቅ በማለት ናሆም ቀጠለ። “እና ከ ድሃድሃቤተሰብዎች የበቀልን ነን። ግን ነገ በትምህርት ሊበራ ብለን እምንማር ተስፈኛዎች ነን። የጓደኛዎቼ እና እኔ ሃሳብ፣ ድሃ ሆነን በቤተሰብ ጥላ ሃላፊነት መማር ስለ እማንችል፣ ስንመረቅ በፍራቻ እና አቅም ማጣት መንግስትን እንዳናስቸግር፣ ዛሬ፣ ከትምህርት ጎንለጎን፣ ኃላፊነት የለብአችሁም ተማሩ ስንባል በአለመዘናጋት ስንመረቅ እምንፈልገውን በማቀድ ቀድመን በሙከራ እንድንበረታ እና የእምንመረቀው እኛን ወደ ስራ እንዲገባ የሙከራ መንገድ ዛሬ እየላክንለት ነው!” ፉጨት እና ጭብጨባ ሲሆን ሞገስ ቆፍጣናው በሞቅታ ተስፈንጥሮ ተነሳ። እጁን በድራፍት ፅዋ እንደ ደገነ ሌላውን ወደ ናሆም ወንጭፎ ሰነዘረ እና ወደ ታዳሚው ቡድን ዞረ። “የ ኢንተርስቴላር እና ተርሚኔተር ወዳጅ ናሆም ይህ ነው!!” ብሎ መልሶ ተዘረፈጠ። ሁሉም ተደመመ። ኢንተርስቴላር ላይ ኩፐር ምድርን ነፃ ሲአወጣ ተመልክተን በመጤዓለምዎች (ኤሊየንስ) ተረድተን ነው ሲባል ለካ ኩፐር እና መሰልዎቹ፣ በዕዉቀት፣ ትጋት እና እማይተነፍስ ተስፋ፣ ተሞልተው በቀደመ ዘመን የሰሩት ነበር ለእዛ ቀን የምድር መዳን አመክዮ የሆኑት። ወደ ፊት እሚገኝ እራስን ስኬትአማ አድርጎ ምንጩን በ መደበቅ እንዲገኝ በገጸባህሪው ማሳደድ እና መልሱ ለካ ተስፋ ሳይቆርጥ በትጋት ስለ ሰራ እራሱ የእራሱ የወደፊት ደጀን እንደ ነበረ ማስመልከት የክሪስቶፈር ኖላን እና ብዙዎች ትርክት ነጋሪዎች (ስነ እና ኪነጥበብ ሙያተኛዎች) ጭብጥ እና ትርክት ነገራ አንድ ዓዉራ ጎዳናአቸው ነበር። ነገርግን፣ የኖላንም ሆነ መሰሎቹ የእንስራ እና እንለወጥ ትረካ መልእክት አንድ ማስጠንቀቂያ አለው። እንድን ነገር ወይም ሌላ፣ መስራቱን እንስራ፣ መመወጡንም እንለወጥ፣ ነገርግን፣ ቤተሰብዎችን እናክብር፣ እንዲሁም ጉድለትን ለመደበቅ ወይም ማምለጥ ያክል እንዳይሆን እምንንቀሳቀሰው እንጠንቀቅ ነው። ሃሳብ ሊደራረብ ይችል አለ። መልካም አስበው ስዉር ሃሳብ አብሮ እንዳይኖር መጠንቀቅ፣ ይህ ለእንደግ፣ እንለወጥከ እንዘምን፣ ጥያቄ ሁሉ አንዱ ቅድመጥንቃቄ ነው። ምክንያቱም፣ ተሳክቶ ሃብት ሲመጣ፣ በሃብት ባዶነት ይኖር ይሆን አለ። ይህ ቅጽበት ለምሳሌ በሚስቱ አባት፣ ኩፐር ከመብረሩ ቀድሞ
ናሆም በክሪስቶፈር ኖላን አድናቂነቱ ስለ እሚታወቅ በተሰነዘረው አስተያየትኤ ሁሉም ተደስቶ ናሆም እንዲደሰት በመጠበቅ ተመለከተ። ናሆም በእርግጥ ደስታውን በፈገግታው አስመለከተ።
“እና የነገ ሀበሻ ወጣት ዛሬ በትምህርቱ ጎን በግሉ በርትቶ አንድ ነገር ቢአደርግ፣ ያ ለነገው እራሱ እሚፈልገው የትምህርቱ መመረቂአ ወቅት ቅጥያ እሚበጅለት ከሆነ፣ ግማሽ ምእት ሙሉ በበዓሉ ተሰድበንበት በአለማቋረጥ የአፈርንበትን የቤተሰብ ጀርባ ተከትሎ መንግስት ጀርባ መንጠልጠሉን ማስቀረት እና…” ሁሉም በፉጨት እና አድናቆትአዊ አጯጯኽ ቤቱን በስሜት አነደዱት። ናሆም በመድከሙ ለመጨረስ ያክል ጮኽ ብሎ በመታገል ሃሳቡን ጨረሰ። “እና! ዛሬ አንድ ነገር እናድርግ ነገ እንቀጥልበት ነው! አመሰግንአለሁ ውድ ጓድዎች። ኮርቼ አለሁ በእናንተ!” ሁሉም በመነሳት ቆመ። ጩኸት እና አድናቆት በዛ። ለማክበር የፈለጉት የሃሳቡን እንጂ የእርሱን ነገር በአለመሆኑ ናሆም አብዝቶ በግልዮሽአማነት ደስታውን ሊጣበቀው አልፈለገም። ግን ታግሎ ታግሎ ተሸነፈ። ምትሃትአዊ ጉልበት ከስሙ መጠራት እና አድናቆትአዊ ጩኸቱ ተከትሎ ወደ አንጎሉ ተማገ። እ…ርከት አለ። ‘ወይ ካንቶና ኤሪክ! የልምዣት መሰል ኦልትራፎርድ ሲጮህልህ ያን ኩራት ማሳየትህ ይነስህ?! ጉረኛ ማለቴ ለእዚህ ቅጽበት ይፋቅልኝ!’ የልብልብ ተሰምቶት ቆየ። ሁሉም ለናሆም ፅዋ አነሳ። ተጎነጩ። ተቀመጡ፨ አንድ ወጣት ግን፣ መላኩ ቀጫጫ ሰዉነቱን እየጎተተ ተነሳ። “ግን ይህ ነገር..” ቀጫጫ ጆሮ ሲበሳ ሁሉ ፈገግ አለ። “ዉይ ይሄ ድምፅ” ጉረሮ ጠራርጎ አወፈረ ድምፁን። “ዛሬ ከእሚነገረን ቀደም ሲል ቢነገረን ይሻል ነበር። ዛሬ እኮ ኅዋአዊከተማዎች ገባን!” በተቃውሞ ተቀመጠ። ብላ ተነሳች። ወደ እርሱ እየተመለከተች በፌዝ አየች እና ጮኸች። “ጎንለጎን የደረጃ ነቢብ ከአልሆነ ስቅላት አለው ያለህ ማነው?!” ኹካታ ነብሱ ሲነጠቅ ትልቅ ጨዋታ ተገበረ። ነብስ ሰከረች። መበሻሸቅ ተጀመረ። መላኩ ስለጊቢ ምናብ ሰርቶ ሲአስስብ መልስ ፍለጋ ቆየ። አልተገለፀለትም። ሠብለ ከት ብላ ስትስቅበት ሁሉም ተከተለ። መልሶ “አሃ!” ሲል የባሰ ጩኸትአዊ ሳቅ ሆነ፨
በፍልቅልቅ እና ወደ ኹካታ ያመዘነ ጨዋታ ዉስጥ በጠቅላላው ድንቅ ድባብ ዉስጥ ቆይተው ወደ መደነስ ተያያዙ። በሁሉ ፊት ሁሉ እየወጣ ትንሽ ወገብ ማንቀሳቀስ እና እሚችለውን ማሳየት ግዴታሆኖ ነበረበት። ለታዳሚ ዓይንዎች በቂ ክፍያ ማቅረብ ግድ ነበር። የሁሉም ዙሩ ሲአልቅ ሰዓቱ ጨለማን ጠራ። ወጣትዎቹ ጨዋታ ላይ መሽቶ አንድ ሰዓት ሆነ። ሁሉም ተነስቶ በአንድነት መጨፈር ደግሞ ተያያዘ። እንደ አቅሚቲ ሁሉም ማስነካቱን ጀመረው። አንዱ እግር አንስቶ ሲአንቀጠቅጥ ሌላው እጅ የአወናጭፍ ነበር። ፍትዎች ኩራት ፊት ሆኑ። የላይኛው ከንፈር በዉይታ ዳር እና ዳሩ ወደ ታችኛው ሰርጎ ገባ። ታችኛው ከንፈር ወደ አፍንጫ ገፍቶ ተሟገተ። አፍ ስሜትን ሰብስቦ ኩራትን ወደ ጣሪአው ወረወረ። ሁሉ በቅጥ ሳይገደብ አስነካው አስነካው። ዱካአጫዋቹ ቀወጥ እሚሉ ከፍተኛ ቅውጥ (ተምፖ) ዘፈንዎቹን ፈልፍሎ በዘርፈአዉታሩ (መልቲሜዲያ) አጫወተ። በላብ መዘፈቅ እና ቁናቁና በነፃ መሳብ ተጀመረ። ጩኸት እና ዳንስ ወደ ለየለት ነፃቅጥ ዳንኪራ ገብቶ እንደ ለየለት የደስታ መንደር አዲስ ዓለም ተፈበተከ፨
ቆየት ብሎ በአንድአንድዎቹ መስከር ሲታይ ናሆም እና ዓሊ ከሠብለ ጋር ሂሳቡን አወራርደው ቡድኑን በማረጋጋት ይዘው ለመዉጣት ሞከሩ። በተለየ፣ ስንዱ ግን አለቅጥ ሰክራ ለመዉጣት እንቢ አለች። ብትለመንም ከፍተኛ ስካር ወርሷት ባለማፈር መሳደብ እና በእንቢታ መጨፈር ፈለገች። ጎተት ቢአደርጓት ተመናጭቃ እማይታወቅ ቅጥ በማውረግረግ ከጥፍረእግር እስከ ፀጉር ብቻ በስሜት ስልት እርካታ በፈቀደላት መስመር ገብታ አስነካችው። ናሆም ሁሉንም ወደ ዉጭ እንዲወጡ አድርጎ ጥቂት እንዲታገሱ ነግሮ ከዓሊ ጋር ዳግ-ገብቶ ተመለከታት። ኹካታው ጎደል ብሎ አልሞቅ ቢላት እና ብትናደደድም ስካሩ በቂ ሆኖ ግን አላስችል ብሎ በዳንኪራ ዘወራት። በመጨረሻ እነዓሊ ተሸክመው ወደ ዉጭ አወጧት። “እናትአችሁን ልብዳ!” ለማምለጥ በመሞከር ጮኸች። በዓሊ ፊት ላይ ከፍተኛ መደናገጥ ሆነ። እንደ ታረደ ዶሮ ተንደባልላ ልትወድቅ ስትል በተዓምር ጨምቀው በመጨበጥ ያዟት። መሬቱ ላይ ከቤቱ መግቢአ በር ዉጭ በመጨረሻ ረጋ ብላላቸው ተንጋለለች። ድንገት መኪና ቢመጣ ብለው ሰጉ። አንስተው በእየትከሻዎችአቸው እጅዎችዋን ተካፍለው ወጠሩ እና ዳግ-አንጠለጠሏት። ይዘዋት ጥቂት ሲራመዱ ለግማባቸው ተንፏቀቀች። ወዲአው ግን የበላችሁ ሁሉ አስመለሳት። ፊትአቸው የነበረችው ሠብለ በመፀየፍ “ኤክ!” ስትል ጭራሽ እራስ በመሳት ላይ የገባችው ሠብለ ግን ሽንትዋን ሁሉ ጨምረችው እና ሸናች። በእግሮቿ ስር በጫማዋ ላይ የፈሰሰ ው ሽንት ሁለት እግርዎችዋን አዝናንቶ እሚከብብ ኩሬ ሰራ። አሁንም ሰብለ እጅ በአፍ ጭና ተፀየፈች። አፈረች። “ምን አዲስ ነገር ነው ይሄ ሠብለ? ሳትሸኚ ዋልሽ?” ዓሊ የስንዱ ደረትን በሌላ እጁ ይዞ አረጋጋት። ሠብለ እረጋ ብላ ተፀፀተች። ዓሊን አግዛ ደረትዋን ይዛ ረጋ ስታረጋት ማስታወኩን ካቆመበት ቀጠለች። ወደ ተለየአቸው በሬ ናሆም ሲመለከት፣ “በርይሁን ቀረ?!” ። ወዲአው፣ ሠብለ ገብታ ሳትፈትሸው በሬ ከመጠጥቤቱ ተመልሶ ዉሃ ይዞ መጣ። አናትዋን አርሠው ጥቂት በደመነብስ ፉት አደረጓት። በትዉከቷ ላይ የቀረውን አፈሠሱ። ሦስት እግርዎች መኪና ተከራይተው ወደ ሩት ቤት እንድታድር ተወሰደች። ዓሊ እና ናሆም አድርሰዋት ለቤተሰቦቿ ሩት አብራት እንደምታድር መልእክት አስተላለፈች። ብዙም ጫና አልደረሰም ነበር። አባቷ ሰካራም እና እማይጨነቅ ስለ ሆነ፣ እናትዋም እቤት ስለ ሌሉ የቀሩት ሁለት ጨቅላ ታናናሾች ጉዳዩም ብዙ አልገባቸውም ነበር። ሩት ዘንድ በክፍሏ አስተኝታት እነ ናሆምን ተሰናበተች። አደራ በ ማለት አስረክበዋት ብዙ ፈሳሽ እንድታገኝ በመምከር ወደ እየ ቤትአቸው ቀደም ብለው እንደ ተበተኑት የቀሩት ጓጓደኞቻቸው እነሱም ተበተኑ፨
ዓሊ እና ናሆም በመጠጡ ጉልበት ተደመሙ። የታመቀ እልፍ ሃዘን ያለባት ስለ ሆነች እራስ መቆጣጠር ደግሞ ስለ እሚሰለች፣ በድንገት ሰክራ ባደረገችው ሁሉ መልሶ ሰብእአዊነት ተሰምቶአቸው ተጨዋወቱ። ነገ ጠዋት ተገናኝተው ሁሉን ጓደኛ ሊከታተሉ ተስማምተው ተለያይተው ወደ እየመንደርአቸው መመለስ ገቡ። ናሆም አንድአንዴ የመጠጥ ጉልበት ምትሃት እንደ እሚአክል በራሱ ላይ አስተዋለ። ሞቅታው ላለመጨነቅ ገፋፊ ነው። ስሜት ብቻ ሳይሆን ስብእናም የአራግፍ አለ። ነገርግን ዋናው ከሠከሩ፣ ሚስጥሩ ቢያንስ በስካር እንደ አሉ እንዳይረሳ ማድረጉ ነው። ቢያንስ አለመርሳት ደግሞ ከባድ አይደለም። ቀላል ነው። ‘ግልን መቆጣጠር እስከ ሞት ነው፤’
በምሽቱ ጉዳይ በመደመም እንደ ተጓዘ ወደ ቤት ደርሶ ብሩን አገኘ። ሰላምታ ተሰጣጥተው ተጨዋወቱ። ብሩ ናሆምን ይዞ ወደ ሻይቤትአቸው ሄደ። ብዙም ሰው ስለ አልነበረ፣ አንድ ጥጋት ላይ ተቀምጠው መጨዋወቱን ብሩ ነፃ የትምህርት እድሉን እንደ አገኘ ገልፆ ጀመረ። ናሆም አቅፎ ደስታውን ከአዲስ ገለጠ። በማብራራትም ዓምና ከ ዮስ ጋር ነፃ ዕድሉን ለመሞከር ገንዘብ ከአዲስአበባ ለዉጭ መላክ ስለ ነበረብአቸው እንደ አዘገዩ እና የእሚልኩለትን ገንዘብ በመቆጠብ ወደ ሁለትሺህ እና አምስትመቶ ብርዎች ወደ ስዊድን ነፃ ትምህርት ዕድል ወጥ እና አንድ ተቆጣጣሪ ተቋም እንደ ከፈለ፣ በህክምና የ ስቶክሆልም ኅዋአዊከተማ እንዲቀበለው በፃፈው አጭር ማብራሪአ እና በአገኘው ልኮት ጦማሪት (ሪፈረንስ ሌተር) መቀበል እንደ ተደረገለት እና ዮስም አብሮ በመሰል ሂደት እንደ አለፈ አብራራለት። ወዲአው ለነፃ ትምህርት ዕድሉ ቀድመው ዓምና በተዘጋጁት መሠረት የነፃ ትምህርት ዕድሉ እንዲገባአቸው እሚአትት ፅሑፍ ከቀበሌ ያዘጋጁት ያቅም ማነስ ድጋፍ ደብዳቤ ትርጓሜ ጋር እንደ ላኩ እና ልኮት ጦማር ከሌላ መምህርዎች አስጨምረው ለነፃ የትምህርት ዕድሉ ብቁ ተብለው እንደ ተመረጡ አሳወቀ። “አንተ እና እሚ በላክአችሁልኝ ድጋፍ እንጂ ይህ ሁሉ ጊዜ በመጠበቅ እሚዘገይ እና እሚቀር ነበር!” በ ማመስገን ተደምሞ አክብሮቱን ሰጠ። “እኛ ምን አደረግን? ዓምና ጀምረህ ታግለህለት የኳተንክ እና ተገቢነቱን የያዝህ አንተው!” በ ትህትና አስተባበለ። “ከአሰብኩት በላይ እንዳልጨነቅ በማድረግ ጭራሽ የገዛችሁልኝ ጭንመቀመሪአ ከሰው እኩል አድርጎኝ ኮርቼ ነበር የተማርኩት!” ናሆም መስ በላከለት ምርጥ የጅቡቲ ርካሽ እቃዎች አምስትመቶ እና ሺህ ብርዎች እየአተረፈ ያጠራቀመው ገንዘብ መደለብ ሲጀምር እሚ “የወጣት ተማሪዎች መጫወቻ ለብሩ ብንገዛ ስ?” ብላ አምስት ሺህ ብር መቆጠብዋን ስታሳውቅ ናሆም የነበረውን ሰባት ሺህ በቀናነት አከለ። መስ አዲስ የዴል ጭንመቀመሪአ ከጅቡቲ በረከሰ ዋጋ አምጥቶ ከአስረከበው በኋላ፤ የብሩ ሂወት ልጓም አልነበረውም። በሁሉ ስኬት በማግኘት ከጓደኛው ጋር ከፍተኛው አስር ዉጤት ዉስጥ አሻቅበው በ መሀኘት የሊቀጉባኤ (ዲን) ክብር ጦማር በሁለቱም ትምህርት መንፈቅዎች ተሰጥቶአቸው አጠናቀቁ።፨
በ ተከሰተው ሁሉ ተደስተው ለ እሚ በማናገሩ ናሆም አግዞት እሚ ተነገረች። በደስታም ሃዘንም ሲቃ ወደቀ ች። ፊቷ በዕንባ ሲርሱ በአፍታ ዝምታ እንድትረጋጋ ተውዋት። ማዘኗ ሲበዛ ናሆም ጣልቃ ገብቶ አፅናና። “ከ እኛ ከ እዚህ ገጠር ወጥተህ ስዊድን ህክምና መማር እና ሃኪም መሆን እሚቻል አደናጋሪ ነገር ነው። አዲስአበባ በቅጡ ሳትረጋ ዉጭ ሃገር ግር ብሎህ ብትጨነቅስ?!” እሚ ልቅሶዋ ስለ እማይታወቀው ሆነ፨
በ ስዊድን ብዙ ሃበሻዎች እንደ አሉ፣ አብረውት ሁለትመቶ በላይ ሰውዎች እንደ እሚጓዙ እና ከ ወጣት እስከ ዐዋቂ እንደ እሚኖር፣ የዩሱፍ አብሮ መገኘት፣ ብዙ ጉዳይዎች እንደ እሚቀልል ብቻ ዘርዝሮ አብራራላት። በመጨረሻ ተደስተው ወደ ጉዳዩን መመልከቱ ዞረው መጨዋወቱን ጀመሩ። በመስከረም አጋማሽ ስለ እሚጓዙ የነብሩ እና ዮስ ጉዳይ ቤተሰቡን ሲአስተክዝ እና ሲአስደስትም ሰነበተ። መብል ቤቱን በመቆጣጠር እና በ ጠነከረ አየቀቀዝ ቀጠሉበት እና እሚ የጠነከረ መሰረት ለቤተሰቡ መገንባትዋን ቀጠለች። የበረከት ጉዳይ ጠፍቶ መቅረቱ ሲታወሳት ብቻ ዘወትር ልቧ ይሸበር ጀመረ። በደፈና ው መለያየቱ እንደ እማይገባ እና መፈላለጉ ቢገኝ እንደ እሚቅም አሰበ ች። “ሌላ ቦታ ቤተሰብ መስርቶ ልጅ ከልጅ እማይተዋወቅ ሆኖ ድንገት ግን ቢገናኝ ስ? እንደ ተሳካልን መመልከቱስ ለእርሱ ምን ያክል ትርጉም የለሽ ቢሆን ማየቱ ግን ተገቢ ነበር!” በጉዳዩ ያላት አቅም ምንም ስለ ነበር፣ ወሬው እስኪሰማ በመልካም ምኞት ልትዘልለው እና ልጆቿ ላይ ልታተኩር ነበር። ብቻ የከሸፈ ቤተሰብ ላለፈው ቁስል መሆኑ ሳያንስ ለመጪው አሜኬላ ሲሆን መከንከኑ በስውር አጥንት ይሰረስ አለ። የእሚ ሃሳብ ም አልፎአልፎ እየመጣ ቢሆንም የበዛ እና መረር እሚላት ነበር። የቤተሰብ መጪን አጥርቶ አለማወቅ በምትኩ ደግሞ አጠራጣሪ ጊዜ መኖሩን ማወቁን ያክል ለእናት እሚከብድ ምናብአዊ ፈተና የለም፨

በ ማግስቱ አመሻሽ ላይ ቤቱን ዘጋግተው ወደ ዋና ቤትአቸው ሊመለሱ ሲል አንዲት እንስት ወጣት በሩን አንኳኳች። “ዘግተን አለ!” የተመላላሽ ሰራተኛዋ መልስ ተሰጠ። እንስቷ ግን መልሳ አንኳኳ ች። “እንደው መንገደኛ ነኝ ባክአችሁ አንቆይም አስተናግዱን! መንገድኛ ነን እንደው!” እሚ ለተስተናጋጇ እራት እንዲዘጋጅ እና እንድትስተናገድ ማድረጉ ደግነት ጭምር ሆኖ ታያት እና እንድትገባ አዘዘች። አብሯት ከአለ ው ተጓዥ ጋር እቃዎች ተሸክመው ገቡ እና ወንበርዎች ያዙ። ኮፍያ እና መነፅር ያደረገው ተጓዥ ከቀጭን እና ዘለግ ያለች የቀይዳማ ወጣት አጋሩ ጋር የበዛ እሚመስል የጉዞ ኮተት፣ በሻንጣ እና ጉልህ ፍራፍሬዎች እና ሸንኮራ ቤቱን ሲአጭቅ፣ አስተናጋጇ ስለ መሸባት እነ ናሆምን ጠርታ በመተካት ወደ ቤቷ ወጣች። ናሆም ወንድምዎቹን እና ዩሱፍን ትቶ ለመታዘዝ መጥቶ ቀረበ፨
“እራቱ ምን ይሁንልአችሁ ጌታዎች?!” እንስቲቱ በምንአሌ መቅረብ ሃሳብ ሰጠች እና ፈገግታዋን ቸረች። ናሆም በቀረው ተስተናጋጅ ማድፈጥ እና መደበቅ የእሚደብቅ ጥቁር ሰፊ ጃኬት መልበስ እና የገዘፈ ሰውነት ከአፍጣጭ እንስቷ ነገረሁናቴ እና አለ አመክዮ መሣቅ ፍራቻ አደረበት። መልሶ የተሸከሙአቸው እቃዎች ብዙ እና እማያቀላጥፉ ስለ ነበሩ ለመሰረቅ እንደ አልቀረቡ አመነ። ትእዛዝ በመጠበቅ እጅዎች በጀርባው አዙሮ በማጣመር ለደቂቃ የያክል ቆሞ ጠበቀ። የተባዕቱ ተስተናጋጅ በቀዩ ምንአሌ ላይ ማፍጠጥ በዛ እና እንደ አቀረቀረ፤ “እስቲ የዓይጥ ወይም ጅብ ያልሆነ ጥብስ አዘጋጅልን! አደራ! የእሚበላ እንስሳ ይሁን!” አለ። እንስቷ ከት ብላ ስትስቅ ቆማ በዘገየ መታዘዝ ከእሩቅ ጓዳው ስትመለከት የነበረች እሚም ተደነጋገሩ። ናሆም ግን ድምፁን ለየ!
“መስ!?” እንግዳው ኮፍያውን አውርዶ ቀና አለ። እሚ በእልልታ ወደ ዉጭ ስትቸኩል ወጣች። ትልቅ ሞቃትአማ ድባብ ተወደለ። ሁሉም በሰላምታ ሲዋሃድ ከዋናው ቤት እልልታ የሰሙ ተምመው መጡ። ያደገች እና የቤተሰቡን ስምዎች መጥራት የለመደች ጮለቅን ያቀፈ ብሩን ጨምሮ ሁሉም ተቀላቅለው ትልቅ ጨዋታ ሆነ። በአገባቡ ሲደመሙ፣ “መድሃኒት የእኔ እጮኛ ናት!” በማለት ተጨማሪ ትንግርታ (ሰርፕራይዝ) አከለ። ቤተሰቡ መድሃኒትን በመቀበል በልጆቹ ደግሞ መጯጯኽ በዛ። ቤቱ ተዘግቶ የደመቀ ጨዋታ ሆነ። አቶ በረከት ከስራ ተመልሶ ደስታውን ተቀላቀለ። ጢዩ ትልቅ ዉጤት አምጥታ ሁለትኛ ክፍል እንደ ገባች አሳውቃ ትኩረቱን ለግል ለማድረግ ጣረች። “ሳድግ እኮ መምህር ልሆን ነውስ!” ጨዋታውን ሁሉ በእድሜዋ የትኩረት መፈለግ እና ትኩረቱን እሚቸር አባት ፊት እንደ ቀረበ ሆና ቀጠለች። እሚ የቢግ ቡና እዛው እንዲፈላ አስደርጋ መጨዋወቱን በተለየ ከሃይማኖት ጋር ለመተዋወቅ እና መግባባት በመጣር ቀጠለች። ጢዩ አሁንም በማቆራረጥ፤ “እሚ ላም ቤት እና ሁለት መኝታ ቤት ጓሮ ልታስገነባ ነው!” ማስመረጅ (ኢንፎርም) ቀጠለች። መስ በደስታ እራሱን ነቅንቆ የራሷ ወጪ ይመስል የምትኮራ ጢዩን አበረታታ። ቡና ተፈልቶ፣ የቤቱ ልዩ ተፈጥሮአዊ ዉበት ከረዘመ አካሉ ዉስጥ ቀዝቃዛን አጭቆ በመቸር የሞቀ ቤተሰቡን አቀፈ። በጨዋታ እና ደስታ እራት ቀርቦ ሲጨዋወቱ የብሩ ጉዞ ወሬ ሲነገር መስ ቀድሞ እዛ እንደ ሰማ እና ከመስ ጋር በእሚቻል ሁሉ እሚገናኙ እንደ ሆነ ገለፀ። መድሃኒት ጋርም ትዉዉቅ እንደ አደረጉ እና መስ እና ብሩ መግባባትአቸው እንደ ጠነከረ መሰከሩ፨
ለጫፍ ቤተሰብአዊ ደስታ የቀረ ምንም ታሳቢ ነገር ሳይኖር፣ የጢዩ የመብራት ቁጥጥር እና መሰል ጨዋታዎች ከባጥ የቆጡ እና ቁምነገር ጨዋታው ሁሉ ተደበላልቆ ምሽቱ ፈጠነ። የሁሉም ልጅዎች ሰውነት ገዘፍ ገዘፍ ብሎ በተሳካ ትምህርት ዓመት ተጠናቅቆ ደግ ቤተሰብ በደግ ንዋይአዊ ወለል መቆም ጀመረ። አብሮ የመፋቀር እና በሥራ አተኩሮ የመከባበሩም ነገር አንድአች ድባብ አከለ። የደመቀው ምሽት በዕሁድ አድካሚነት ሲጨፈለቅ ወደ መኝታ ዞሩ። አዲስ መኝታ ለእንግዳዎቹ – ግን ቤተኛው መስ ጭምር – በጊዜአዊነት ተበጅቶ ወደ ሰላምአዊ እረፍት ጨዋታ ሳይቋረጥ ተገባ። ጢዩ ሳትታይ በ እንግዳዎቹ መሀል ተገኝታ ነበር፨


ጎኁ እማይታክት ሥራውን ቀጠለ። ሌሌም ጽልመት አባረረ። አዲስ ሰኔም አጋማሹ ላይ ባዲስ ቅዝቃዜ ተመለሰ፨
ሌላ ሰኞ ዛሬ ነው። የዛ ሰኞ ጧት ደግሞ አሁን ሊጠባ አለ። አብሮት ዉስጡ፣ የእሚ ልጥጥ ቤተሰብ ነበር። ጨለማ መቅደዱን የሰኞ ጎኁ ሲጀምር፣ ማንም አልነቃም። ናሆም ግን ልክ ነቃ። አንጠራራ። ‘ኡኽ አዲሱ ዕለት። አቀፈኝ። ከ አልተሞተ፥ እንቢታ የለ። እኔም በሁለትኛ ማንጠራራት እና መመቻቸት፣ የነፍስ እጅዎቼን ዘርግቼ ገቢ ቀኑን አቀፍኩት።’ ከተኙት ቀድሞ፣ ቀን ሲአንኳኳ የዕድሜውን በር ከፍቶ እሚቀበል፣ ቀን-ተቀባይ ይባል አለ። ቀን-ተቀባይ ከ ቀን-ተቀላቃይ ይለይ አለ። ሌቋሆ. ሁለትኛ ው ከቀደመ ው አናሽ የቀን ፍቅር አለው። ስነፍጥረት ደግሞ ለአፍቃሪው ፍቅሩ እንዲከፈለው ያስገድድ አለ። ቀን-ተቀባይ ከቀኑ በላጭ ክፍያ ስለ እዚህ አለው፨
ተንጠራራ። ሁሌ እንደ ለመደው። መስ አልነቃም። ወታደርአዊ አተኛኘት እንደ ተኛ ነው። እንደ ሁሌው አጠገቡ አልነበረም። ራቅ አድርጎ በወለሉ የተዘረጋ ስነድርድርአዊ መኝታ ተመለከተ። መስ ወታደርአዊ አተኛኘት ተኝቶ የእጮኛው አናት ደረቱ ላይ ተጋድሞ ወደ ናሆም ሲመለከት ታየው። ፈገግ አለ፤ ፈገግ ተባባሉ። ራቅ ብሎ እሚ እና በረከት ከጮለቅ እና ጢዩ ጋር አሉ። በሌላ አቅጣጫ ደግሞ እነብሩ ተከማችተው አሉ። ወደ ራሱ ዞረ እና ጣሪአውን እየተመለከተ በስሱ አንድ ሥራ ጀመረ፨

፨ተፈጸመ፨

By Binyamhailemeskel

Hey there! If you want to know about me, I just like fun, commonsense wisdom, and human love. Let us live a bright today changing tomorrow into brighter.
Regards,

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s