Categories
My Outlet (የግል ኬላ)

ምእራፍ-፬

መስፍን ጎንለጎን ምእራፍ ፬፨

፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
፬ የ ዱብዕዳ መከንከን ብልጭታ ወይም ገሃድን መቀበል

ምእራፍ አራት በ ተአዶ. (PDF).

ማታው ሳያረጅ መተኛት የቀንተቀባይነት ቅድመሁኔታ ነው። ለስኩ አኗኗር የስልት ጮራ ስለሆነ፣ ያ ደግሞ ግድ ነው። ከማለዳ ድባብ ተቋድሶ ቀንን መጀመር፣ ከቀንተቀላቃዩ ባዶ ጣት ይዞ ወደቀን መምጣት እሚለይ ነው። የጂም ዴቪስ ጋርፊልድን መቼም ማለምም አይታሰብም። በእርግጥ ድመት እንቅልፋም ስለሆነ፣ የእሱ ስብከት ህጸፅ የለውም። ድመት ከመተኘት ወዲያ ምን ያውቅ አለ። ሰው ጋርፊልድን ልሁን ካለ ግን አንጎሉ ተዛብቷል ማለት ነው። በቀንተቀባይነትአችን የህይወት ሽልማት አለን። በሂወትአችን አንድ ጣት ላይ ቀለበት አርጎ ሲያጌጡ እንደእሚውሉ እመስቶች መመረቅ ያክል ነው። ለተፈጥሮ መስህብ በቋሚነት በመጋለጥ፣ በቋም የግለትምምን ላይ ተፈናጥጦ መዋል ነው። ይህ በእርግጥ የስብእና ማዘመኛ አንዱ ጎዳናው ነው፨
ይህን በምልዓት ያስተማረው መስ፣ ምሽቱ ቤተሰቡን በደግ መቀላቀል ቀጥሎለት አልፎ ሲመሻሽ ወደ ሦስት ከኩርማን ሰዓት ገደማ፣ ደካክሞት፣ ሁሌም እንደ እሚደሚያረገው፣ ከናሆም ጎን ወደ መኝታ ወጣ። ካሳለፉት ማለዳ ተስፈንጥረው የተገኙበት ማታው ድረስ የነበረ አዋዋልን እሚፈትሽ የአኳኋን ቅኝት በእየፊናአቸው ልክ ከማሸለቡ ቀድሞ አደረጉ። መስ አዲስአበባ ጧት ሲነቃ፣ ሲጓዝ እና ቤተሰቡን ፋሲካይት ተቀላቅሎ ሲውል፣ ከናሆም የበለጠ ሲቀራረብ እና ደከምብሎ ሲገኝ ሳለ። ናሆምም የቀኑን ዉሎ በአስር ሰከንድ ጠቅለል አድርጎ አሠበው። ሁለቱም ደስተኛ ነበሩ። ቅሬታ ከነበረብአቸው መረመሩ። ዋናው ያ ነው። በደስታ ለመኖር ስዉር ቅሬታን እንዳይቀበርብን መፈለጉ እና ማወራረዱ ተገቢ ነው። ምንም አሁን ያሳሰባቸው ነገር ስላልነበር ይህቢሆን ያሉት ነገር ሳይኖር ደስታን ብቻ አገኙ። ቅር ያሰኘ ሰውም ሁኔታም የለም። እሚያሳዝን እና እሚያስከፋ ሁኔታም አልገጠመም። ስለእዚህ በደስታ ተንሳፈፉ። ይህ የዳበረ እና ስለተዘወተረ ቀላል የሆነ ጸባይ፣ የዕለት ዉሎ አርኪ ከነበረ፣ እሚገፈፍ ከነበረው ይፈልግ አለ። በጠቅላላው የአኗኗር ዝብርቅርቅ እሚአጠልል፣ ስስ ግለቅኝት ነው። ግን ከስኬትአማ አኗኗር ምክርነቱ በዘለለ የስነልቦና ሰባኪዎችም እሚያነሱት ምርጥ ተሞክሮ ነበር። ጭንቅላት በአዋዋል ዉጣዉረዶች እንደ ተሸበበ መተኛት ጎጂ ነው። በቀጥታ ድሃ አድራጊ ነው። ከገንዘብም ከጤናም አው በቀጥታ እሚተሳሰር ነው። ምክንያቱም፣ ሰው ቢአንቀላፋም፣ ተመርምረው ያልተዘጉ ጉዳይዎችን አንጎል በስዉር ያመነዥክ አለ። እየተብከነከኑ ወደ እንቅልፍ ቢኬድ አርኪ እንቅልፍ ማጣት ሆኖ፣ አካል አርፎ አልነቃ ብሎ፣ እንዲሁም ጤና-ነስነት ይፈጥር አለ። አካል ሲተኛ ጆሮ ካልተጮኸ አያደምጥም፣ ቢሰማም። ሌላውም አካል እንደእዛው እሚተኛ ጊዜ እሚዘጋ ነው። ሰው እስከ 80በመቶ አካሉ ሁሉ እንደ ሞተ እሚከረቸም ነው። ግን አንጎል ከተብከነከነ፣ ሰላም ካልተያዘ፣ መተኛቱ ያነሰ አካልአዊ እረፍት ሰጪ ነው። ያም የእልፎች ሂወትን አቆርቋዥ በይፋ ግን እማይጠና ነው። በተለይ በድሃ ሃገር ለመሃይም መሪዎች ቅንጦት ስለሆነ ህዝቡ ዳቦ ስለእሚያልም ማንም አይነካውም። ቢሆንም፣ ሃቁ እንዳጠቃን መኖረጀ አልቀረም። እነናሆም ይህን ደርሰውበት አሁንም እረጂ መሪ በሌለበት ሃገር ግለመሪነት እሚያሠማሩ ሆኑ፦ በግል እና ቤተሰብዎች ላይ። ይህን ስስ አሠሳ አድርገው ከጭንቀት እረፍት እንደ አገኙ ሁለተኛው ቀላል እና ሂወት አፍጋጊ ክወና (በተይ ለሀበሻ) ደግሞ ቀጥሎ ይተወን አለ። ይህም፦ ከራስጸጉር እስከ እግርጥፍር፣ አካልዎችአቸው፣ በሞላ ምቹ እረፍት ላይ እንደ ሆኑ ይፈተሻሉ። የአልተመቸ የከንፈር አቀማመጥ ካለ፣ የክንድ ላይ ጫና ማብዛት ካለ፣ የመደበቅ ስነልቦና ካለ፣ ጉልበት አቀማመጡ ከተጨናነቀ፣ አንገት እና አናት ዘና ያለ አቀማመጥ ካጡ፣ ትራስ ካስቸገረ፣ ብቻ ሁሉም አካላት ላይ መፍታታት እሚገኝ እንደሆነ ይፈተሹ አለ። በተለየ የሰውልጅ ፊቱ በመቶ ምናምን ፊትገጽታዎች (ጀስቸር) በእየሰከንዱ ስለእሚገለጥ እና አንድ የስሜት ነጸብራቅ የሆነ ቅርጽ በማንኛውም ቅጽበት ሰርቶ የሰውንልጅ ስለእሚአስቸግር፣ ሰው ሁሉ ሲተኛ ነብሱ አብሮ ዘና እንዲል፣ የፊት ስሜት እንደ ተስተካከለ ማረጋገጥ ያስፈልግ አለ። በቀረ፣ ሰላምአዊ እንቅልፍ ያሳጣ ዘንድ የተጠና ጥበብ ነው። መስ ይህን በእሚገባ ሲአስተምረው፣ ናሆም መጀመሪያ የምር አልመሰለውም ነበር። ግን ተወራረዱ እና ተኝተው ፊቱን በመረመረ ጊዜ አንድአች የስሜት ገጽታ በፊቱ ወዲአው ወዲአው እየተለዋወጠ ይገኝ እንደነበር ፈትሾ አገኘ። ፊትን ከፈተሹት የሚቀያየር ገጽታ እንደስሜትአችን እሚያስመለክት ነው። በበይነመረብም አሠሳ ብዙ ጉልጎላዎች አድርጎ ተገረመ። “አርኪ እንቅልፍ ስምጥ ፍልስፍና አለው። ሌላ የስኬትአማ ሰውዎች ዐብይ ምስጢርም ነው።” መስ የአስተምህሮቱን ነጥቡን ለተገነዘበ ናሆም እንደመጠቅለያ አክሎ ወደ አካል ፈትሾ አመቻችቶ መተኛት ዘወትርአዊ ባህሉ አደረሰው፨

በመኝታው አዲስ አንሶላ በማንጠፍ እንደተኙ በልማድ ተግባብተው አሁንም ለእዚህ ጭንቅላት እና አካል ምቾት አሠሳ ትንሽ የወሰዷትን ዝምታ ገፍፎ መስ ተናገረ። “በእረዥሙ ጉዞ ጥቂት መጫጫን ስለደረሰብኝ መተኛት አለብኝ!” ሌላ ጊዜ ግን መኝታ ላይ ጥቂት ሳይወያዩ እና የእነርሱን ካባቢን እና ህይወት በበላጭ ግንዛቤ ለመረዳት በእሚል ስለአንድ ትንግርትአዊ ወይም ሰብአዊ ምስጢር አስምጠው ሳይጨዋወቱ ዝምብሎ መተኛት አልለመዱም። የአንን ምሽት ግን ሁለቱም፣ እራቅ እራቅ ብለው ለመተኛት ከተሰናዱት ቤተሰብዎች ጋር በመሆን ለጥ ብለው በሰመጠ እንቅልፍ ወዲአው ወደቁ፨
እሚም ብዙ ጭንቀት ከሰዓቱን አጥለቅልቆዋት የነበረ ቢሆንም ወደ መኝታው ስትሄድ ግን፣ ልጆችም ስለከበቧት ፈታ ለ ማለት ሞከረች። ‘በልጅ ፊት ሳይገልጡም ቢጨነቁ፣ ጭንቀቱ ፈጽሞ ከመንፈስአቸው አይደበቅም፤’ ብላ አክስቷ አስተምራት ነበር። ልጅ ስትወልድ ደግሞ ስለ ልጆቿ ብላ አምናበት የእማትዘነጋው ጉዳይ ሆነ። በልጅዎች ፊት ምንም ቃል ሳይወጣ በ አኳኋን፣ አረማመድ፣ አበላል፣ ፊት አያያዝ፣ አነጋገር፣ የመንፈስ ሁኔታ፣ በምኑቅጡ ብቻ ዝግመተለውጥአዊ (ግራጁዋል) ንጽረት አድርገው አንጎል እና ስብእና እሚገነቡ፣ እሚግባቡ እና ሰው መሆንን በስውር ከከበበ ቤተሰብ እሚማሩ ስለሆነ አቅራቢያቸው መጨነቅ አደጋ ማስተላለፍ ነው፨
ይህ አገነዛዘብዋ ነበር ለእሚ ጥንቃቄ መዉሰድ ላይ የተዋት። የሐረግን ነገር ዋጠችው እና ሃዘኑ ቢከነክንም ለመቀበል ወስና ብቻ ሲታወሳት ንድድ ይላት ነበር እንጂ ከመርዶው መቺነት ግን ተመርቃ ነበር። ወደ ቀጣዩ የመፍትሔ ግብረመልስ (ፊድባክ) ጉዳይ ስትገባ ያንን ሃዘን ጣለች። የኑሮ ወጪው ባህል መጠጥ በመነገዱ እና፣ ኮፍያ በመታታቱ፣ ይጠነሠሳል፤ በሆነ ቅጽበት ወስና ነበር። የቀረ ሌላው ደግሞ፣ ለነገ ይታሰብበት! ይህን ብላ በአእምሮዋ አዋዋሉዋን አጠለለች። እንደ እነናሆም አዉርታ፣ አውጥታ-አዉርዳ በሆንብሎንታ ያዳበረችው ልማድ ባይሆንም፣ በእንቅልፍ አክብሮትዋ የተነሳ እሚከነክን ነገር ሳታጠልል ፈጽማ ይዛ ስለእማታድር በአጋጣሚም ቢሆን ይህንን የእነእርሱን ምሁርአዊ እና ዘመንአዊ ልማድ አዳብራለች። ይህ ግን እሚከወነው እንደ እነመስ እና ናሆም በአዉቆታ በእየ ሁልጊዜም አይደለም። ልክ እንደዛሬው ጭንቀት፣ ትዝታ ወይም ሃሳብ መጥቶ ካልናጣት፣ ቀጥታ በደስተኛነቷ ‘አምላክ ሆይ ተመስገን’ ብላ እምትተኛ ናት። ጭንቀትም አይገጥማትም። ከልጆቿ በቀር ሌላ አታውቅም። ሠላም ዉለው ከተኙ ምንም ሌላ ነገር አይታያትም። ዓለሙ በምህዋሩ እስከዞረ ተደስታ ታንቀላፋ አለች። በቃ። ጭንቀት ለእማይገጥመው ደግሞ ስለጭንቀት ማስተማር ማስጨነቅ ነው። ጉዳይ ግን አእምሮዋን ከጨበጠባት፣ በቂ ልማድ አላት። መልሱ አንድኛ ‘አሁን የእንቅልፍ ጊዜ ነው’ ሲሆን ሁለትኛ ‘ከአስፈለገ ነገ እመለስበትአለሁ፣’ ነው። አተኛኘቷ ምንም እንዳልተከሰተከ ዓለም ዘጠኝ ነው ይሆንላት አለ፤ ያም ለሰው ድንቅ ችሮታ ነው። ስለ እዚህ እንቅልፍዋ በድንቅ ስምጠት እሚከወን ሆኖ፣ ጧት ልጅዎች ተደስተው፣ እርስዋም በበራ ስነልቦና እና ቀለለ መንፈስ እምትመለስ እንድትሆን ይህ ልማድ እረድቷት አለ። ይህ ለሰው ሁሉ እሚያኗኑር ወርቅአማ ልማድ ነበር፨
ሌሊቱ በእራስ-መርሳት እና ዳግ-መታደስ ሰዓትዎች ተጨርሶ፣ በማለዳ ናሆም እንደ ሁልጊዜው ቀድሞ ነቃ። አዲስ ማክሰኞ ገባ። ባለበት ተንጠራርቶ አቅምን ከአዲስ ሰላም ብሎት አዳበረ። በሦስት አንጃዎች የተሠነጠቀውን የቤቱን ያተኛኘት አሠላለፍ ተመልክቶ ሃሳብ መታው። ‘የፋሲካይት ከተማ ትንሽ አደለችም ለካ’ ብሎ ድንገት ሰሞኑን የረበበት ጥያቄን በማረጋገጥ መልስ ሠጥቶ አሰበ። ‘የከተማን ስፋት ከመናቅ በፊት እየ አንድአንዱ ቤት አንድአንድ ቀን አድረህ መርምር፤’ የእሚ እና ብሩ መራሹ ቡድን በእዛ ጓዳ መንደር መንደር አቅፎ ከእራሱ ቡድን ጋር ተደምሮ የሃገር ያክል ሆኖ ታየው። ህዝብ ቁጥሩ በዝቶ የትንሽ መንደር ቁጥር በዘንድሮ በስነልቦና ተናቀ እንጂ ጥቂት ሰው ሆኖ መሠብሰብ እራሱ ክቡር እና ሰፊነት ነው ብሎ አሰበ። ‘ለነገሩ አንድ ሰው አንድ ሃገር አይደል፤’
ናሆም ግሉን ሲያነጋግር አፍታ ቆይቶ በአዲስ ቀኑ አዲስ ጉልበት ይዞ በመንጠራራትዎች ሲጠመድ መስ ተከትሎት ነቃ። የጧት ሰላምታ ተለዋወጡ እና ሁለቱም ጥቂት በዝምታ አስተዋሉ። እሚአደርጉትን አመል ሁለቱም ስለ እሚአውቁ በምንም አልተረባበሹም። ‘ሩት እና ዓሊ’። መስ ዋና የክረምት ዕቅዱን ቶሎ ስለመወጠን አሰላሰለ፨
ከአልጋው ወርደው ወደ ዉጭ ሲወጡ በተለመደ ማለዳ ዉርጭ የሰኔ ኩርማን፣ መጠነኛ ካፊአ አድርጎ ማብቃቱ ነበር። በመጠነኛ የአካል ለጥጦ መንጠራራትዎች እና መንቀሳቀስዎች ሰውነት በማፍታታት እየከወኑ፣ ግማሽ ሰዓት የአክል ታተር አርገው፣ ጸጉር እና ፊት ተታጠቡ። ቀጥለው ጥርስ በማጽዳት ታጠቡ። በተለየ የማለዳ አንዱ ተግባር ጥርስ ማጽዳት እና ከመጽዳት የተነሳ እሚመጣ የአፍ ትምምን መጨመር ነው። በማለዳ ከመነሳት ብቻ የተነሳ በተማገው የአሸናፊነት እና ነፃነት ስሜት ላይ፣ አፍ ተቦርሾ ማጽዳቱ ሲደመርበት፣ ቀኑን አብልጦ በትምምን መቆጣጠር እና በደስተኛነት መዋል ይቻል አለ። በአፍ አለመጽዳት የሰው ሂወት እሚበላሸው በስውር ስለሆነ እና ማንም እሚረዳው ከተጎዳ በኋላ ስለእሚሆን፣ መስ ናሆምን እና ቤተሰቡን በእየእለቱ ጥርስ እሚቦርሹ አድርጎ እንዳለመዳቸው ነበሩ። ሰኞ ግን ሁሌም ከመደበኛ ጥርስ ማጠብ የበለጠ ከፍተኛ የጥርስ ማጽዳት ይከዉናሉ። መቦረሽ ፍጹም አይደለም። የጥርስ ሃኪምቤት በከተማዋ ስለሌለ በመፋቅ እና በስምጥ ፍተሻ መጠነሠፊ ጽዳትን በአንደበትአቸው በእየሰኞው ይከውኑ አለ። በቀረ፣ በተመገቡ ቁጥር መጉመጥመጥ እና በሌባጣት መቦርቦሩ ትልቅ አቅም ያመጣልአቸው ነበር። አሁንም መተጣጠቡን እንደ አደረጉ፣ ገብተው ልብስ ለመለወጥ ተመለሱ። ማንም የነቃ አልነበረም። ሰዓቱ ወደ አንድ ተጠግቶ ስለነበር በፍጥነት ወደ ቤተክርስትያን ለመሄድ ሲመለሱ የባቤ አንድ እግር እና አንድ እጅ በብሩ ላይ ተነባብረው፣ ቢግ ደግሞ በተለየ አግጣጫ በሰፊው አልጋ አንድ ዳርቻ ፈንጠር ብሎአቸው ብርድልብስ በመቀማት፣ ሦስቱም እንደነገሩ አሸልበው እንዳሉ ነበሩ። በአልጋው የተከመሩትን ናሆም ፈገግ ብሎ አይቶ አለፈ። እንደወጡ ወደ መስ ዘወር ብሎ “አንድ አልጋ ማበጀት አለብን፣” ጥርስ ነከስ አድርጎ ናሆም ተናገረ። የጠዋት ጨረር ፊቱ ላይ እንዲአርፍ ዓይንዎች ጨፍኖ በመንቀሳቀስ ሆኖ የሀቡን ምላሽ ጠበቀ። “የኔ ዕቅድ ግን ሌላ ነው። ይህ ክረምት አንድ ያልክውን አቃፊ ነገር ጨምሮ፣ በላቀ ስፋት አዲስ ትርጉም ሰርተንበት እንዲአልፍ ነው ያሰብኩት።” “ከአዲስ አልጋ ማበጀት ሌላ ደግሞ ምንድን ነው?” “እሚ ጋር እንወያይበት እና እነግርህ አለሁ።” “ትደብቀኛለህ ማለት ነው?!” ፊቱን ደካማ ፀሐይ ጨረር ፍለጋ ከማንቀሳቀሱ ወደ ምርአዊ አዞረ። “ከጓሮ አንድ ወይደግሞ ሁለት ክፍልቤት ማከል ብንችል አስቤ ነበር።” ማምለጥ ስለ አልቻለ እቅጭ ሃልዮውን አካፈለው። “ኦ! እዛ እንድናድር ነዋ በሰፊ ነፃነት! ያ እማ ትልቅ ጉዳይ ነው!” በልጦ ጥያቄው ስለተመለሰ ደስታን ሲአገኝ እና አርኪ ጨረር አጊንቶ ሞቅታ ሲሰማው አንድ ሆነ፨
ቤተክርስትያን ደርሰው በኪዳን አገልግሎት መካፈል ቆዩ። ምእመን ተበትኖ ሲወጣ እነ እርሱ ወደቅጥር ሰርገው ፀበል በመጠጣት፣ የግል ጸሎትም አድርሰው ወደ ቤት ለመመለስ ወጡ። ልክ ቅጥሩን ተሰናብተው መጓዝ እንደ ጀመሩ የኔብጤ ጋር ተፋጠጡ። አለቅጥ ቁስልስል ባሉ እግሮቻቸው፣ የዝንብ መንጋ ሁሉ በደስታ እየተመገበ እሚአሰቃይአቸው አንድዓይንአማ አዛውንት የእኔ-ብጤ የሠለለ እጅ ጫፍ በተዘረጋ መዳፍ ላይ ሁለት ሳንቲም ብረትዎች መስ አስቀመጠ። እና ጉዞ ቀጠሉ። እራቅ እንዳሉ ናሆም በቀላል እሚታሙ እና እሚድኑ የመሰሉ ቁስልአቸው አላስችል ብሎት ዞርብሎ ዳግ-ጎበኘው። በማደግ እና ዓለሙን በመገንዘብ ክፍለ-ዕድሜዘመንአዊ’ ጥረቱ፣ አንድ እሚብከነከንበት ትንግርት ማህበረሰብአዊ ኢፍትሕአዊነት ነበር። በተለይ ክረምቱ መጥቶ በተርታ እሚሰደሩት የእኔብጤዎች፣ እላይአቸው ላይ ዘንቦብአቸው በፀሐይ ደግሞ የደረቀብአቸው ናቸው። አደፋ ልብስ እና አካል ተሸክመው የጎሰቆሉ ነብስዎች፣ ሰሞኑን ተደጋግሞ ስለሸተተው እና መልስ ሰጥቶ ያልዘጋው፦ ያልተመረቀበት ሰሞንኛ ነጥብ ሆኖ ጠዝጥዞት ነበር፤ ይህ ትርዒት በዝቶ ነበር እና። ዓይንዎች በስሜት መክሸፍ ሸብሽቦ፣ አንጀቱ በመንደድ ጋል ብሎ ያሰበውን እሚገልጽበት እሚናገረውን አጣ። አቅልሎ ጀመረ፣ “ግን ይሄ ጠቃሚ ነው? ምን የአደርግልአቸው አለ! ባራት አምስት ብርዎች ጠግበው እና ለብሰው አይታከሙ ቤት አይገዙ ወይ አይከራዩ!? ሂወትአቸው በእዛ እንዴት ነው እሚቀየረው!?”
መስ ለናሆም የአዳጊ ምናብ ጥያቄዎች ቸልታ እና ጥራዝነጠቅነት በ “እኔ እንጃ ባክህ!” ሃልዮታ (አቲቲውድ) መልሶለት አያውቅም። ‘የልጅዎችን ጉጉአዊነት በስነስርአቱ እማያብራሩ ነገን እሚአደኸዩ በሽተኛዎች ናቸው፤’ ብሎ ያስብ አለ። የማደጊአ እብስልስልዎች፣ ለልጅዎች ዓይንዎች ናቸው። ለጠየቁት በዐዋቂ መስተንግዶ – በማክበር – እየመለሱ ማሳደግ እሚመልሰው ቅጽበትአዊ የታዳጊ እርካታን አይደለም። የልጅዎቹን ግለትምምን፣ ቁምነገረኛነት፣ ፍቅር፣ ተባባሪነት፣ አክባሪነት፣ ዐዋቂነት እና ሃቀኛነት ስለሆነ ጥያቄዎችአቸውን ዘንጊ እና አኮምሻሽ ሰው እራሱ ዐዋቂነት እንደአልደረሰ አርጎ ይገነዘብ አለ። “ዛሬ ደኽይቶ ነገንም እሚያደኸይ!” ይል ነበር። ባለማስላት አቅሙ፣ የሁለት ቅጥዎች (ዳይሜንሽንስ) ንዑስ ፍጥረት አድርጎ ይረዳቸው አለ። ናሆም በእዚህ ምክንያት ከልጅነት ጀምሮ ለጉጉትዎቹ አኩሪ ፍጆታ ኋኝ አመክዮአዊ ነጥብ እና አንክሮትአዊ (ክሪቲካል) ማብራሪያ እንጂ ነፈዝ መሠል ጥያቄ እንኳ በቁምነገር ሳይስተናገድለት አልፎት አያቅም። የእራሱን የመረዳት ብቃቱን እና አፈቀላጤአዊነቱንም (አርቲኩሌትድ-ነስ) መስ አብሮ ይፈትሽበት አለ፤ በተለይ ናሆም አድጎ ከበሰለ ወዲህ፣ እሚመስለው፣ ጭራሽ ናሆም ሃልዮ-መሪ ወይም አጋሪ ጭምርም ነው፨
አሁንም መስ አንጎሉ ያየውን ወደ አፍ ጎተተ። “ሃገሩ እንግዳ ተቀባይ ነው። የሥነህዝቡ (ዘ ፖሊቲ) ግብር መዋጮ ሸርፎ፣ ማህበረ-ደኅንነት (ሶሻል ሰኪውሪቲ) ስርኣት አውጥቶበት አቅም ያጡ “እንግዳዎች” በቀላሉ መደገፍ እና እንግዳ ተቀባይነት ከፉከራ አዝልሎ እስኪአውቅ እንደ ጠየከው እና አየኽው ትርጉም እማይሰጥ አኗኗር ተግተህ’ መልመድህን ተያያዘው። ይህ ማለት ሀበሻ ነህ ነው ከገባህ። ሃገሯ በተወችልህ ሂወት አትደላህም! አንተ ነገ እንዲህ ልትወድቅ እና እዚሁ ልትለምን ትችል አለህ። ማህበረሰቡ ሠላሳ በላይ መቶ-መቶ ዓመትዎች ኖሮ ለራሱ ግን እንጭጭ ዋስትና እንኳ የለውም!” መስ ተናግሮ የናሆምን ፊት መልከት አደረገ። የከረፋ ነገር እንደተናገረ ያውቅ አለ። ግን የከረፋ ኢትየጵያአዊ አዛውንት አይቶ ስለጠየቀው ነገሩን ለማቅለል አልደፈረም። መልሶ ጠጣር ስላወራ አሰብ አድርጎለት ነበር የተመለከተው። ናሆም በላቆጠው ኢሰብአዊ አኗኗር አለቅጥ ተነክቶ፣ ስነስርአትአዊ (ሲስተሚክ) የነብስ መላሸቅ እንዲደርስበት ስለተተወ መስ ለታዳጊዎቹ ሁሉ ድንገት ስሌት ከውኖ አዘነ። ተስፋመቁረጥ ወደ ሀበሻ ልብ እሚሠርጸው፣ ዉጭውም እንዲህ መንፈስ ሰባሪ ሲሆን ነው። ጨክኖ እውር ካልተኮነ፣ ሀበሻ በሀገሩ አይኖርም። ምክንያቱም ሰብአዊነት አይከበርም። በመብት ጥየቃ ያልበረታው፣ ህዝቡ የነተበ ስለሆነ እና ሰውን በሰውነቱ መመልከት ስላቃተው ነው። በየቦዩ ወድቀው፣ በእየጥጋቱ አዛውንት ተሽቀንጥረው፣ ገብቶ ወደቤት መዝናናት የህሊና እውርነት ይጠይቅ አለ። ያንን ደግሞ ስላሳካን፣ ህሊናአችን ሰብአዊ መብትን መረዳት አልቻለም። ሰውመሆንን ከመገንዘብ እሚመነጭ የመብት አይነት፣ ሰውን ባለማክበር የተከረቸመበት ሆነ። ከርፊው ነገር፣ ይህ ባህል እና ማንነትአችን መሆኑ ነው። ትውልድ እና ሀገር፣ እንዲቀኑ፣ ይህ መፍረስ አለበት። ሰውን በሰውነቱ እንደእንቁ መመልከት፤ ምንም ይሁን ምን። ግን አስተዳዳሪዎችአችን ያንን መመልከት እሚችል አንጎል ከቶ ስለሌለአቸው እነናሆምን ከገሃድ በሽታ ማከም፣ የአዋቂ ሀበሻ ግዴታ ነው። አሁንም፣ መስ ትንሹ ልጅ ጭንቀት ይዞት፣ በስውር-ተስፋው እንደ አበቃለት እና እራሱን እንደ እሚጠላ መደበኛ ነዋሪ ሆኖ ልቡ እንዳይደነድን ጨዋታውን ወደ ቀናአዊነት ቀጠለለት። “መፍትሔ አብሰልስል እንጂ እንደ ጥራዝነጠቅ በመጥላት ብቻ ተጠምደህ አትለፈው። ይህን አይተህ ስታድግ ወደ አዉሬነቱ በመለወጡ ላይ በርቺ አትሁን! መልስ አጢነህ ተጨነቅ አይደለም፤ እወቀው እና ችግሩንም መፍትሔውንም በቀለለ መንፈስ ጎንለጎን ያዝ። ከዛ ቀጥል እና ተመረቅ! እለፈው። ለውጥ መምጣት እሚችል ሆኖ አጋጣሚ ሲጋብዝህ ያንተን ተፅዕኖ ታፈርጥበት አለህ።” መስ ያንን ሲለው፣ በአዎንታአዊነት እንዲወስደው መምከሩ ቢሆንም፣ ሰው እንደ ቀልድ ነትቦ ለሳንቲም እና እምክ ሙቀት ማግኘት ሲል ሠንሰለት ሰርቶ በመቀራረብ ተደርድሮ ሲዋረድ፣ አልፎ መሄድ እና መመረቅ ከበደው። ‘ገሃድአችን ይከረፋል። ኢገሃድአዊ (አንሪያሊስቲክ) የእውነት ወለል፣ ከየት በቅሎ ሃቅ ከልሎ አቆመን? ጥላሸት ስርኣት! አርማጉሳ ዝንጋዔዎች፤’ ጥርሱን ነከሰ እና ሃሳቡን እሱም አመጣ፦ “አንድ ዓመት ‘ያመቱ በጎሰው’ የተባለ ቢንያም፣ ሃገር እና መንግስት በጣጥሶ፣ በመቄዶኒያው አረግአዊዎች-ማስጠለያው ድንቅ እና ብዙ አድርጎ ነበር። ስንት ምሳሌ መንግስት እና ሃገሩ ይፈልጋል ታዲአ?!” መስ ለጥያቄው መልስ አጣ። ሳቅ አለ። አሰበ። አጣ። ደግሞ አሰቦ አጣ። ዳግ-ፈገግ አለ። መልሶ፣ አንድ መላምት ኮተኮተ። ሞላጎደል ጭር ባለው መንገድ እየተራመዱ በዝምታ ሆኖ በማሰብ ቀጠለ እና አስፍቶ ሊአብራራ ተዘጋጀ። “እንግዲህ እንደሃገር ጠዝጣዥ ድህነት ስብእናችንን ይሞነጫጭር፣ ሰላም አላሳድር ይለን አለ፤ በ…እ…የ…ዕ…ለ…ቱ! ስለእዚህ እንዳንተ ክብረነክነት ስናስተውል ወደ መንታመንገድ ሁሌ እንወጣለን።
“ግን የኛ ስብእናዎች እሚነኩ ጊዜ እንደ ቢንያም ‘ሰው ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው!’ መሠል ንጽፅረቴ (ዩውፎሪያ) አርገን ለክብራችን ተፅዕኖ ፍልሚያ፣ ነብስአችን ጋሻ አታነሳልንም። ከመንታመንገዱ ወደ ከረፋው መንገድ እናዘምም አለን። በተለምዶ እና ባህልአዊ ምላሽአችን። ይህን ያየህውን መሰል ሁኔታ ስንመለከት ቢታከም ቢታጠብ ቀለል ያለ ድጋፍ ቢሰጠው ሰው ሆኖ ይኖር ነበር ብለን አናስብም። ያ ቀናአተያይ ነው። ያ ለኛ አልታደለንም። የመሆን እሚችል ቀና ጎን እንደ ስቶይስቶች አይታየንም። የስቶይስት ፊት ያላቸው ጉራጌዎች እንኳ፣ የስቶይስት አኗኗር አቅምአቸው ግን ግዝፈት ስለሌለው በመጠነኛ ገቢ አደና ስለእሚኳትኑ፣ ይህን መሰል ችግር ፈቺ አልሆኑም። የቀረንውም ይህን መሰል ሰው ለይተን ከአደፋ ኩነቱ መመልከት እማናውቅ ከቶ እንቅልፋምዎች ነን። የግረህ ኑር እርግማን እስረኛነትአችን ነገር በነባር ቅርጹ እንዳያምር እና እንዳይጠብቀን አድርጎን አለ። ግን ብልህ ትትረት አምጡ በማለቱ እንጂ እንዲህ ቆሽሻችሁ ኑሩ ሲለን አልነበረም። የእኛ ከመንታው እሚመረጥ መንገድ የቢንያም ተጽዕኖ ነኝ ንጽፅረቴ አይደለም። በተስፋመቁረጥ፣ መልካምነትን እሚክደው ጎዳና ይቀናን አለ። ማለትም፣ ስት-እጥፋት ዉስጥ ገባን ማለት ነው።
“እንግዲህ ሰው ክብሩ ሲነካ፣ ክፍለ ማንነቱ ወደ ትግል እና አልሸነፍባይነት (ጣይቱኛ) ይመርጥ ነበር። ምን አልባት ትላንት እንዳልከው እኛ በተፈጥሮ እና ዕድአዊ-መስህብዎች አሠሳ አናዘወትርም። ስለእዚህ የሂወት ትምህርት አናጎመራም። እና ያለንን ክብር ስለአልተረዳን ደግሞ፣ ተስፋ ስንቆርጥ ገልጠን ባናፍረጠርጠውም፣ አዉሬነት ቀንቶን ደነዘዝን ማለት ነው። እንደ ቢንያም፣ ወይም ሰሎሞን ቦጋለ ያለ ግን፣ ገሃድ መርሮት ከአስከፋው፣ ከአመድ እንደ ፊልቆን ያንሰራራ እና በዳግ-ትትረትዎች አንድ ተፅዕኖአማ መላተም ይሰራል። በሂደት ነጠብጣብ ለውጥ ይከማች አለ። ያ ነው ከነቁጥህ እሚታየኝ። ክፉ አኗኗር አሽትተን ገብተን መተኛት፣ ደንዝዞ፣ በአዉሬነቱ መላመድ አንዱ መንታመንገድ ምርጫ ነው፤ ያልሰለቸን። ደግሞ ተፈጥሮ ዉበቷ እና የእኛ ዋጋ ሲገባን ግን፣ ‘እንቢ ሟች ኑሮዬ አለፍትሕ እና ፍቅር አይኑር’ ብለን፣ የተገታተረንን ለ መግጨት መነሳት እንለምድ አለን!”
መስ በእረጅም ማብራሪአ ይህን ሲል እርሱም እሚከነክነውን ነገር በቃልዎች እሚአፍረጠርጥበት አጋጣሚ ስለሆነለት እረክቶ ነበር። ናሆም አናቱን በመነቅነቅ ግንዛቦት ሲከውን፣ መስ ሙሉ ተስማሚ ስለአገኘ በግሉ ጥረት ፈገግ አለ። በአለመናቅ መወያየቱን ለዚህ ጎንዮሽ ሽልማቱ ጭምር ይወድደው ነበር። አሁንም በጉልህ አረዳድ እየተገለጠ ስለመጣ ይህን ዉይይት ተደሰተበት፨
ናሆም በትኩረት አድምጦ በመስማማት ሃሳብ መከወኑን ቀጠለ እና በቀደመው ጉዳይ ተናገረ። “ታዲአ! በእርግጥ ሃገሩሁሉ ድሃ ስለሆነ ብዙ ሰው ልትሰበስብ ቢከብድም፣ ግን በቅርጽ፣ ለህሊና-ንጽሕና ያክል እና ለይፋ አዛውንትዎች ከበራ ያክል እንኳ፣ ለህሊና እና ማስተማሪያነት እንኳ፣ ያዛውንትዎች ከለላ ተግባሬትዎች ከመንግስት አመትአዊ በጀት ጥቂት ተሰንጥሮ መንቀሳቀስ ይገባው የነበረ አንድ ጉዳይ አይደለም እንዴ።” አሁንም የከበበው ዓለም ስተተኛ እንደ ሆነ ሌላ ክፍተት አምጥቶ ሲያሳይ መስ አሰብ አደረገ እና ተናገረው። “ይህ እና በጣም ብዙ እሱን መሰል ጉዳይዎች ሁሉ፤ ያንተ ዘመን ለመምራት ሲደርስ እሚፈታው ነው።” ይህን ሲሰማ ናሆም በሽሙጥ ሳግ አለ። አጥጋቢ መልስ ስለ አጣ ወደ በታችነት እና ቆሻሻ አቅፎ መኖር የግድ ዞሮዞሮ ሊሰርግ ስለሆነ ተናደደ። “እህ! ነው? ባክህ የኛ ትዉልድ ላይ አትጣበቅ። እራሱ የናንተ ትዉልድ የሀገር ችግሩን ይፍታ።” መስ በተራው ፈገግ አለ። “ይገባኛል። ግን ያንተም ትዉልድ መልሶ አይጨቅጭቀና! በቃ ግማግም አኗኗርአዊ ዐውድ ይከብብህ ዘንድ አቀረብንህ! ተቀበለው!” ፈገግ ብሎ ሲመልስለት ናሆም አፈር አለ። በእርግጥ ወደታሪክ ዞሮ መጮኹ መፍትሔው አይደለም። ናሆምም ያውቃል። ለወደፊቱ መሻሻል ሲል ብቻ እንጂ…፣ እና ለውጥን ትላንት አልጀመርንውም፦ ይህን አምነን በመቀበል፣ ዛሬን ለነገ አገልጋይ እናድርገው ብሎ ለማንፈስ (ኢንስፖየር) ብቻ እንጂ…፣ ያለፈውን ዘመን በደፈናው እሚተች አይደለም። እንደ አለበት የወጣትዎች ትውልድ፣ ነገን በመቀየር እንጂ ባለፈው በመጠመድ እሚሸወድ አይደለም። እንደውም፣ ናሆም ሀገር ስለመለወጥ ሲወራ ስሜቱ ከፍተኛ እና ቅን ነው። እንደ ሺህአዊያን (ሚለኒያ) ትዉልድ አባልነቱ፣ ገጠር ዉስጥ የተወጠነ ልጅነት ላይ ቢሆን እንኳ፣ ዞሮዞሮ ዘግይቶ በለመደው የስልጣኔ ቁሳቁስ፣ ዕዉቀት እና ንፁህ ታዳጊ ስብእና ጋር፣ የድሃ ሃገር ማብራሪያየለሽ አኗኗር ከእሚታሰበው መጋጨት እየፈጠረበት፣ ዓለም ቀዉስ ሆኖበት አለ። በተለየ አንድ ሰሞን አቅሉ ደፍርሶ ነበር። ይህም ልክ፣ ሁለትኛ ደረጃ ሲደርስ መስ በአነቃለት አመለካከት ታገዘ እንጂ ብዙ የዓለሙ አለመጣጣም እና ማብራሪያ እንኳ አለመገኘቱ የተነሳ፣ ወደ ቅወሳዎች አቅርቦት ነበር። መጪ ትዉልዱ በአሃዝአዊ ሽልፍኖት ሲንበሸበሽ፣ በዕዉቀት ዕድልዎች ሲወረር፣ ሰብአዊነት ሲአይል እና ዓለም የተሻለ ሲሆን፣ አብሮ እማይሄድ የመንገድ ዳር ቆሻሻ ትርዒት (የ እኔብጤ እና ቆሻሻ አወጋገድ)፣ ብሔርተኛ ዘዉግ ቅወሳዎች፣ ቲማቲም የለሽ ድሃ መብል ባህል፣ ፍትሕ ነፃነት ጠፍቶ ስለ ብሔር ጨርቅ እና ስለ አፈር በየቀኑ መዘፈኑ፣ አንድ ተስፋ ሰጭ የዕዉቀት ወደፊት ለመገንባት ደግሞ ጥረት አለመታየቱ፣ ብቻ ምኑቅጡ ለሀበሻ ሺህአዊያን የስነልቦናአዊ ውጥንቅጥ-ቁጥር-፩ ነው። ቁጥር ሁለቱ እራስአቸው ይህን አይተው እሚፈጽሙት ግለ-ዉጥንቅጥ ነው። ናሆም በቀደመው ውጥንቅጥ ነብሱ የእዛ ሰሞን በተለየ ልትወጣ ደርሳ ነበር። ቀዉሱ ግልጥ ምላሹ ግን የበለጠ ግልጥ – ክህደት – ነበር። ‘የአን ውጥንቅጥ ማንም አያጤነውም። ከኗኗር ጽንፍ መጋጨቱ፣ ቁስላም ልቦና ቢፈጥርም፣ ቁስል በሚያፈነዳ አኗኗር ዉስጥ ሰላም ስላልነሳን አዉሬዎች ነን። የሰብአዊነት ጫፍ ሳይታየን ስላለን እምንባክን ዘረፍጥረትዎች ነን፤’
ወደ ዋናው የከተማው መንገድ፦ ‘ልዕልት እና እሯጭ ጥሩነሽ ዲባባ ጎዳና’ ላይ፣ እሚተፋውን ቀጠን ያለ ስምየለሽ ጠባብ እና አጭር መንገድ ሲጨርሱ፣ አንድ ወጣት በታላቅ ቅሬታ እንደ አለ እሚመሰክርበት ፊትን ወደ መንገዱ እየወረወረ በያንዳንዱ የአካባቢው አኳኋን እና ነገር ነፈዝ ቅኝት ላይ ሆኖ በዝግታ በእነእርሱ አግጣጫ ሲአዘግም አዩት። ናሆም እና መስ ሞላጎደል ፈጠን በማለት ሲራመዱ ወጣቱ እየተመለከተ እንኳ ማስተዋል ጠፍቶበት ከግዙፉ መስ ጋር ተላተመ።
“አስተውል ዝግተኛው ወጣት ተጓዥ!” ወጣቱን በክንዶቹ ይዞ በማቆም መስ እያረጋጋ ተናገረው። ሲመለከተው በፊቱ ላይ የባዶነት መዓት ተንጣልሎ ነበር። “ሃሳብ ሳይሆን ዉሳኔ እና እራስ መሰብሰብ የአነቃህ አለ! ወጣት!” መስ ሲጋጨው ቆምአድርጎ እንደያዘው አብዝቶ እየተመለከተው በወታደር እና መልካም ዜጋአዊነት ይህን ነግሮት ለቀቀው እና እየተመለከተአቸው ራመድ ያለ ናሆም ላይ ደረሰ። “እንዴት ያን አልከው?” እጅ ሰዓቱን እየተመለከተ ለቁርስ እንዳያስጠብቋቸው እያሰበ ጠየቀው። “ስት-ፍሰት (ዲስኦረንቲየሽን) ነፍሱን ሰርቆት አለ። ገና በ ጧት!! ወይ ደብሮት አለ፣ ወይ ደኽይቶ አለ፣ ወይ ከጓደኛ ው ተጣልቶ አለ፣ ወይ ቅሬታውን ሳያቅ ብቻ የሀበሻ ኑሮ እንደ እምታውቀው…በምን እንደ ከፋህ እንኳ በ ስነልቦናትንታኔ (ሳይኮአናሊሲስ) ማጥራት አትችልም። ግን የእዚህ ወጣት ስትፍሰት የተለመደው የዘመኑ ፉክክር መንፈስ ከባዶነት ጋር ሲላተምበት እሚመስል ነው።” መስ የተናገረው ናሆም በቅጽበት መቅደም ከአወሩት የተገናኘ መሰለው እና ለበለጠ ማወቅ ጠየቀ። “እንዴት?” መስ በተለየ ነጥብ ነገሩን ጀመረ እና ፈጠን ማለቱን አበዙ፨
“ማለት፣ እረዥም ነው ታሪኩ። ብቻ ባሳጥርልህ ዐዋቂ እሚመራ ው ማህበረሰብ አይደለንም። ዐዋቂ ማለት ምራቅ ዉጦ ትልቅነቱ ጋር አብሮ የመምራት ጥበብ የተሸከመ ሽማግሌ ማለት ነው። ማህበረሰብ በመንግስት ይተዳደር አለ እንጂ አይመራም። መሪው ዓዉራዎቹ ሽማግሌዎች እና ዐዋቂዎች ናቸው። የእኛ ሀገር ሽማግሌ ግን ምን አይነት ነው? የዘመኑን ስልጣኔ በውል ስለእማያቅ እንደ ሽማግሌ በዘመነው-ማህበረሰብአዊ-ዕዉቀት ጉልበተኛ የሆነ አይደለም። የእኛ ሽማግሌ ከታዳጊ ዜጋዎች በበለጠ ለዘመኑ እንግዳ እና ባዳ ሆኖ የመምራቱ ጉልበት በስልጣኔው ግርግር ተደምስሶበት አለ። ልጅዎቹ እንዲሰለጥኑ ተማሪቤት ግን ይልክ፣ ይመግብ ያሳድራል። በቀረ፣ ምንም ማድረግ አይችልም። ስልጣኔ ዉስጥ ፈርቀድዶ ለትዉልድ የማስረከብ ነገር፣ ቢአንስ እምብዛም፣ የለም። ሳይማር የአስተምርህ አለ እሚባለው ነገር ይጠቀልለው አለ ማለት ነው። አንተ ትማር አለህ። በእዛ ግን ሽማግሌዎች እማያቁትን እና ምክር ማይሰጡበትን ነገር ማንም ክፉደግ ብሎ ሳይለያይልህ ማወቅ ጀመርህ ማለት ነው። እንደ ቀኃሥ. ኅዋአዊከተማ “ሁሉን እወቁ መልካሙን ጠብቁ” ብሎ በማስተማሩ ደግሞ ስነምግባርም እሚቸር የለም።”
በህይወት የበሰሉ ወላጅዎች ዘመንአዊ ዕዉቀት ሳያቁ፣ ወጣቱ ሲማር ደግሞ ዕዉቀቱ ጋር ብስለት የሌለው ሆኖ ይጠፋፋሉ። ሥራ ስታገኝ ምን ማድረግ አለብህ? ቤተሰብ እና ሀገር ማነጽ አለብህ። ግን እምትገባ እምትወጣበትን እሚአቅ ሽማግሌ የለብህም። ሽምግሌዎች አይቆጣጠሩህም። ያ ያኗኗር ብስለት ይመነትፍህ አለ። ከስር ስለ ቀሩ ወላጅዎች ኖረው እሚአስተምሩት ተመሳሳይ ህይወት ከንግዲህ የለም። እምትገባው ወደ ግል ዐውድ፣ በሽማግሌዎች ወደ አልተሞከረ አኗኗር ነው። በጎኑ ገንዘብ አለህ። ልክ አቤል ሙሉጌታ ‘ገንዘብ እሚገኘው በሃያ ልብ በአርባ አመት’ ብሎ እንዲአቀነቅን እንደ አደረገው ትሆን አለህ። ከላይህ እንዳንተ ተምሮ ገንዘብ ሰብስቦ ቤተሰብ በመምራት አልፎ ይህን አኗኗር እሚአስተምር ቤተሰብ ስለ ሌለህ፣ በብዛት እንደ እሚታየው በግራ መጋባት ስትባክን ሀገር ማቅናት ቀረ ማለት ነው። ቢበዛ ቤተሰብ መስርቶ መቀመጥ እንጂ የስልጣኔ ጥበብን ማሠስ የለም። በአቻ ግፊት እየ ተጎተትህ፣ በአባቶችህ በአልተቀመሰ ንዋይአዊ እና ዘመንአዊ አገልግሎት፣ አንተ ድንገት ተገኝተህበት፣ በነፃነት ተዝረክርከህ ስትንሳፈፍበት፣ የውርስ ጥሪትህ ሲወራረድ፣ ሞላጎደል ለማህበረሰብ እድገት አይበጅም። ሃገሩን ስላባከንክው፣ ይባክናል።
“ይህ፣ የዐዋቂዎች ከትዉልዱ-መሪነት መገለል የአመጣው የሀገርአችን ዝብርቅርቅ ድባብ ነው። ወጣቱ በግሉ ነው። ከአልኩህ አንፃር ከምር መሪ እና ዐዋቂ የለንም። ልክ እሚ አንተን ታሳድር ታሳድግ እንጂ በምንም እንደ እማትመራህ እና ከፍ ስትል ከአዋቂዎች ያልተመለከትክው አዲስ ባህል እንደ እሚገጥምህ ማለት ነው። እሷ ስለእሚገጥምህ አታቅም። አንተ ሸገር ሠራተኛ ልቶን ትችል አለህ። ገና በወጣትነትህ። ማን ሰፋ ያለ ተሞክሮ ይሰጥህ አለ? ማንም! መካሪ፣ አማካሪ ተቋም፣ የመንግስት ተግባሬት፣ ኢመደበኛ ባህል፣ ወጥ የተሞክሮዎች አሰዳደር እና ተደራሽ ማህደር፣ ወዘተ. አይገኝልህም። መኳተኑን መያያዝ ግድይልህ አለ። ማለትም በአጭሩ፣ አዋቂዎች ይህን ሀገር ተሞክሮ እየሰጡ እሚያሳድጉት አይደለም። አዋቂ በጓዳ እና በአነሰ ስፍራ ነው። ወጣት ደግመለ ባዶውን። አንዱ አምድአዊ የስነውሳኔአችን (ፖለቲክስ) አለመሰናዳት አመክዮ ይህ ነው። ሽማግሌዎች እሚቆጣጠሩት ሃገር አይደለም። ወጣት ደግሞ ሃገር ማስቀደም በብልሃት እሚገባው አይደለም። በምርጥ ምሳሌ ብለውጥልህ፣ የገዳ ተቃራኒ ሁኔታ ላይ ነው ያለንው። በቻይናም የገዳ መሰል ስነቅርጽ (ስትራክቸር) በአመራርአቸው አለ። በማደግ ትከተል እና ከሽማግሌዎች ትረከብ አለህ እንጂ በወጣትነት፣ ካለ ልምድ እምትቀበለው ሃላፊነት በገዳም ሆነ ቻይና ኮሚኒስት ድርጅት የለም። በገዳ ሉባዎች ጭራሽ ጡረታ ሲወጡ እራሱ ቁልፍ አማካሪ ናቸው። በሃገርአችን ግን የ አዋቂዎች አካል አለመምራቱ፣ ለስልጣኔ ቁርጥራጮች፣ ለአፍላ-አገነዛዘብዎች፣ መሠረት ለነገ አድርጎ ለማያስጥሉን መንገዶች…ወዘተ. እንድንከስር አደረገን። ወጣቱ ሁሉ ባይተዋር ሆኗል! አንተን ጭምር!” መስ አሁንም አብራርቶ ሲጨርስ ምን እንደተሰማው ለማስተዋል ዞር ብሎ አየው። ናሆም እያስተዋለ አድምጦ በተባለው እየተብሰከሰነ ቆየት አለ እና አናት በመነቅነቅ እህታ ሰጥቶ ተስማማ። ግን ሃሳቡ በእዛ ዙሪአ አልተነሳም ነበር እና ዳግ-ጠየቀ። “ግን ከወጣቱ ልጅ ስትፍሰት ይህን የኢአዋቂያን-መር ማህበረሰብነት ምን አገናኘው?!”
“እረዥም ነው አልኩህ። በአጭሩ አሁን ያልኩትን ከ እዛ ወጣት ባገናኝልህ ግን ወጣቱ በአብዛኛው ስለ እዚህ በሠለጠነ ዓለም ተረፈ ምርት ተዘብዝቦ አለ፤ እድገት በእሚል ፈሊጥ። አጠቃቀሙን ዐዋቂዎችአችን አልጀመሩትም። ጎጂ ጠቃሚ ብለው ህግ አላወጡም፤ የሰሩትም ባህል ዜሮ ነው። ስለ እዚህ ወጣቱ ልጅ ምን የመቀመሪአ ተጠቃሚ ቢሆን በመጠቀም ስለእሚማር ቅኔውን ላያውቀው ይችል አለ። ሲጀምር ማን ይማር አለ። ሳንማር እየተጠቀምንው ባህል አድርገንው አለ እኮ! ለ ምሳሌ በመቀመሪአዎች ብዙ አገልግሎት ሲሠጠን፣ ሃገራችን ግን አገልግሎቱን መቆጣጠሪያ ግን አልነበራትም። በመቀመሪአዎች አገልግሎት ተሰውረህ፣ ለ ምሳሌ በበይነመረብ፣ ህግ መጣስ ወይም ጉዳት ማድረስ፣ ወንጀል መስራት ትችል ነበር። ህግ ያልቀደመው አገልግሎት ስለ ነበር ማለት ነው። በሂደት ቀስበቀስ አንድሁለት የአሃዝ ዓለም መቆጣጠሪአ ህግዎች እየተደነገጉ ነው፤ ገና አሁን። ብዙ ክፍተትም አሁን ድረስ አለ። ለምሳሌ በበይነመረብአዊ ንግድ፣ የንግድ መብትህን ሊነካ ይችል ነበር። ሲነገድ ከርሞ ግን ትላንት ወደ ፋሲካይት ስመጣ በመኪናው መስኮተድምጽ ገና ሰሞኑን የላይ-መስመር ንግድ ደንብ (ኦንላይን ትሬድ ሬጉሌሽን) ብጤ እንደ ወጣ እና በበይነመረብ ለመነገድ ፈቃድ እንደ እሚጠየቅ የመደንገጉን ዜና ሰማሁ። ማለትም፣ የጨበጥንአቸው ዕድልዎች እንኳ የጠለለ አረዳድ እና ዉሳኔ እሚነዳአቸው ዐዋቂነት ቀድሞአቸው የእሚገኝ እና እሚመራአቸው አይደሉም። በባህልም መሳሪአዎቹን እየቀደምን ተዘጋጅተን አልተገኘንም። ለምሳሌ አንተ ስልክ ብታገኝ በአባት-እናትህ ምን እንደ እምታደርግበት አይታወቅም እና ለአንተም ጥበቡ ዝግ ነው። በራስህ ነው ጥቂት እምትማረው። ብዙም እሚገፋ ደግሞ የለም። እንደ እሚሉት ከሆነ ግን የተዓግ. ትልቅ ተቋምዎች አንዱ ‘ናሳ’ የ ‘አፖሎ’ መንኩራኩርን አመንጥቆ ጨረቃን ሲአስረግጥ፣ መንኩራኩርዋን የተቆጣጠረበት ግዙፍ ልዕለ-መቀመሪአ (ሱፐር ኮምፒውተር)፣ ዛሬ በእጅ ከእምንይዝአቸው ትንንሽ ስልክዎች በእልፍ የአነሰ የመቀመር አገልግሎት አቅም የነበረው ነበር። አንድ ተናጋሪ ‘ዛሬ አንድ ተራ ዘመንአዊ ቀፎ ይዝአችሁ ወደ እዛ ዘመኑ ‘ናሳ’ ብትሄዱ አምላክ ትሆኑብአቸው ነበር’ ብሎ ነበር። ግን ያ ጨረቃ ማዉጣት እሚችል አቅምን በኩራት የዘለለ እና እቅጭ መቀመሪአ አገልግሎት በፍጥነት እሚከውን አቅምን በመዳፍዎችአችን ይዘን፣ ምን እንከውንበት አለን? ስራ መፍታት እና መሰዳደብ፣ ግልኛ (ሰልፊ) በመለጠፍ እና በቅሬታ በ መመልከት ስነልቦና ማዛባት! መቀመሪአዎች በተፈለሰፉበት ወይም በቁጥጥር ሆነው ባደጉበት ሀገርዎች በብዙ ዘመንዎች እየዳኸ ባህሉ ከህዝቡ ጋር በሂደት እና በሽማግሌዎች ወይም የማህበረሰቡ መሪ ዐዋቂዎች ተቆጣጣሪነት ስለ አደገ ዛሬ በአገልግሎቱ አቅርቦት ብዙ እንደ እኛ መሳሳት የለም። እኛ ጋር ግን ዐዋቂ እሚመራው ማህበረሰብ ሳይመሰረት ሳተላይት አብራሪ መቀመሪአ በመዳፍዎችአችን ድንገት ተወረወረልን። ባህል ሳይዳብር ለምሳሌ ዜጋዎች የመናገር ነፃነት እና መድረክ ሳይበጅልአቸው፣ ተደብቆ ማውሪአ ተፈቀደ ማለት ነው። ቅጥየለሽ ተፅዕኖ እና ውጥንቅጥ ሆነ! ንግድ ዉድድር ስለ ሆነ በቅኝ ግዛት ምትክ ገቢ ለማግኘት እንድናስችል በስነገበያ (ማርኬቲንግ) ሸፍጥ በገፍ ሲሸጥልን እና ስንፎካከር፣ ዕዉቀት እና ባህሉን መሳለመሳ ሳናድግበት ታዳጊዎችአችን ግን ተወረሩበት። እና ያ ወጣት በድንቅ መቀመሪያው ወይ እሚመለከትአቸው የ ፌስቡክ እና ኢንስታግራም ቆንጅዬ ምስልዎች ‘አንተ ግን እንደ አየሃቸው ምስልዎች እና ሃብታሞች ወይም ቄንጠኛዎች ስለ አልሆንክ ዋጋቢስ ነህ!’ እሚል ስዉር እንደምታ ጭረውበት ወይም የተሱ. ላይ-መስመር አገልግሎት እየጣፈጠው ገንዘብ ጨረስክ ብሎ ከ ቅዠት ስለ ከለከለው፣ ሂወት ደብሮት ሊሆን ይችል አለ። ከፊቱ እሚነበበው፦ ጥቂት ቅሬታ ሠርስሮት የተቦረቦረ ነብስ መሆኑ ነው። እራሱን አጥቶ እሚኳትን ሆኖ ነበር እንግዲህ።” ይህን በመስማት ብዙ እየአብሰለሰለ ናሆም ቆየ። ለእሱም በጎን ለማናገር ብሎ ይሁን ከምር የተነተነለት አሰብ አደረገ። በእርግጥ መስ ያለው ለእኔም ነው። ግን ላንተ ነው ብሎ በግልጥ መንገሩንም ያውቅ ስለሆነ የተሰማውን ለመተንተን እንጂ ለእኔ ያጣመመው አይደለም ብሎ እያሰበ አናቱን አሁንም እየነቀነቀ መገንዘቡን አሳየው። እያሰላሰለ ወደ መንገዱ ዳር ተለየው እና ወጣ። የቸርቻሪት ሎሚዎች ለመግዛት ቆመ እና ማውጠንጠኑን ቀጠለ። በአንድ ብር አራት ሎሚዎችን ሰብስቦ በኪስዎች ይዞ አጎቱን ተቀላቀሎ መራመዱን ጀመሩ እና ጠየቀ፨

“ልክ ነህ! ዘ ፊፍዝ ዌቭ ፊልም ላይ፣ የመጤዓለምዎች (ኤሊየንስ) በ ፌስቡክ እና መሰል አገልግሎትዎች መጥተውብን፣ አሊያም አገልግሎቶቹ እራሳቸው መጤዓለሞች እንደሆኑ እሚአሳብቅ ሲሆን አንጎልአችን ማየት እሚችለው አንድ ነገር ብቻ እንዲሆን እና እርስለእርስ እንድንጫረስ ሊአደርጉን እየሞከሩበት ነው ይለን አለ። ግን ያልክውን ግልጽ የ ስነልቦናውን ጉዳት እንዴት በልጁ እንደ አየህ እርግጠኛ ሆንክ?” መስ ናሆም ባለው ተገርሞ በእርግጥ በብዙ ስዉር ጉዳይዎችን አንጎልአችን እሚአስመለክተን ሌላውን ጠላት አድርጎ እንዲሆን አድርገው የባእዳኖቹ (ኤሊየንስ) ያክል እሚያፋጁን እና እሚቆጣጠሩንም እንዳሉ አስቦ፣ በትርክቱ ተደምሞ ወደ እራሱ ጉዳይ ማብራራቱን ቀጠለ “ከእዛ አይርቅም። ፊት አንብብ እንጂ! ሰው ለምን በ እዛ ዝግታ ይራመድ አለ? በእዛ መፍዘዝ፣ መደንዘዝ፣ እና ግዙፍ ሰው ባለማየት መግጨት ድረስ! ለምን አካባቢን በአኳኋን መልቀቅ ላይ ይደረስ አለ? ለምን ሰው ነቃ ብሎ ዓይንዎች ሰብስቦ አይራመድም፣ ትኩረት በግል ላይ ተደርጎ፣ ነገር ላይ ሳይጨነቅ አይኬድም? ወጣት ልጁ እሚራመደው መሬት፣ ግንባታዎች፣ ወጪ ወራጅዎች፣ ወዲህ ወዲአ እሚለውን፣ ብቻ ሁሉን እሚመለከተው ህቡዕ ቅሬታ ዉስጥ ሰምጦ ነው። ለሻሻ እና አረምዎቹን ሁሉ ይቆጥር አለ። በእየአንዳንዱ ነገር ይጸጸት እና ያስብ አለ። የመሬት ለሻሻ አይቶ መጸጸት ድረስ። ማለቴ ለማህበረሰብ አሳቢ መሆን ቢመከርም የሱ ስሜት ግን ዘልጎበት አለ። አንድ ደስታ ከጥልቅ ሂወቱ ጎድሎት አለ።
“በ ነብሱ ጉድለት ሆኖ፣ ግን በገሃዱ የባከነው፣ አንድም፦ መፍትሔ እሚፈልገው ከዉጭ ስለ ሆነ ነው። ግን መልስ ከራስህ ቆራጥነት ነው ያለው። ትኩረትህ ጉልበትህ ነው። እምትበላውን ነገር ሰዉነትህ ፈጭቶ ንጥረነገር ለይቶ ሲአጣራው ከአገኘው ጥቅም፣ ከ ሰውነትህ አብዛኛውን መቶኛ ነጥቆ አንጎልህ ይወስድበት አለ። በጭንቀት እና ትኩረትማጣት ወይም በ ስትፍሰት መጥለቅ፣ የእምትበላውን ሁሉ ሰርቆ እሚወስድ ስለ ሆነ ለጤና ሁሉ አክሳሪ ነው። ያፈቀረ ጨንቆት እንደ እማይበላው ትኩረት እና ትርጉም ላጣ ሁሉ ጭንቀት በዝቶበት መብል ፍላጎት ይጠፋ አለ፤ የ በላውም ኢፍትሕአዊ ክፍፍል ይደረግበት አለ ማለት ነው። ለስትፍሰት ተጋላጭ ሰው ደግሞ ይህ ሳይታወቀው እሚሠረስረው ስዉር ግለ-ጦርነት ነው።
“ጦርነቱ ክፉ ነው። ይሰልብህ አለ። ሰውን ሣይመለከት እና ሳያገኘው፣ ቶሎ መናቅም እንዲጀምር፣ እዉቀት በበቂ ክምችት እንደ አለው ያክል እንዲንቅ እሚአደርገው አንድም ይህ ጦርነት ነው። ማብሰልሰሉ ይወርስህ አለ። ከሰው መግባባት መጨዋወቱ ይርቅህ ያመልጥህ አለ። ያ ማለት፣ ሰውን ሳታውቀው ያወቅህ እንዲመስልህ ያደርግህ ዘንድ ክፍተት ይፈጥርብህ አለ። ሰው መናቅ ያለብህ ይመስል ያስጀምርህ አለ። ብቻ እየቀጠሉ፣ ከ ብዙ ነገርዎች ላይ ማፍጠጡ ሰውንም አብዝተህ እንደ እምታቀው የአስመስልህ አለ። ግን ነገር ቢአፈጥጡበት መልስ ስለ ሌለው ቶሎ ብለህ እምታቀው ሊመስልህ ይችል አለ። ሰው ግን ምን ብታፈጥጥበት አብረህ ቀርበህ ካላየህው ልታቀው አትችልም። ሰው ፈሳሽ ነብስ አለው። ይቀያየር አለ። አናዳጅ ሰው ድንገት ልብስህ ሊአቀዘቅዘው ይችል ሁሉ አለ። ማለትም ሁኔታ ይገልፀው አለ። ግን ሰውን ስለ አፈጠጥህበት እንደ እምታቀው መስሎህ ወደ መናቁ እና መሸሹ የአደርስህ አለ። ስለ እዚህ በመቀራረብ እማትበረታው ሰው ጭራሽ ከ ሰው መራቂአ ስውር ስነልቦና አከልህ ማለት ነው። እንደ እዛ ልጅ ደሴት ሆነህ በብቸኛነት ከገሃዱ ጠቅልለህ ትጠፋ አለህ ማለት ነው።”
ናሆም በመደነቅ ኮስተር ብሎ ማድመጡን ሲቀጥል መስ ሃሳቡን በ ማዘን ቋጨለት “የ እኛ ሃገር ግን በስነልቦና እና ዐዋቂ መመራት ስለ እማያውቅ ወጣት ሁሉ አባትዎቹ የማያቁት ዓለም እየወረረው ስነልቦናው ተደነጋግሮ በ ስውር እሚጨነቅ ሆኖ አለ ባይ ነኝ። በአብዛኛው፣ በጠቅላላው። ይህ ወጣት ‘ሁሉን ጭንቀት እኛ አልፈንው አለ። በእዚህ በእዚህ ይህ ይሰማህ አለ። በ እዚህ እድሜህ ይህ ተጽዕኖ ይጠልፍህ አለ’ ምናምን እሚለው ተሞክሮ ወይም ምክር የለውም። ግን እሚዘበዝብ ድንቅ አገልግሎት አለው። በዉስጡ መጨነቅ ትርፉ ወይም ቢአንስ ጎንዮሽ ጉዳቱ ነው። ማን አከመው ታዲአ? ማን? ስለ እዚህ በስትፍሰት እሚጠልቅ፣ ወይኔ ይሄንን ተመለከትኩ በእሚል እሚጨነቅ፣ በብርቅርቅ ምስልዎች ብቻ መመልከት እሚደነቁር ልብ እሚሰለብበት ነው። በተስፋ መጨለም እራሱን ተገንዝቦ በተሳሳተ ዓለም እየፈሰሰ ነው። ብኩን ነፍስ! ወደፊት በልምድ ይገባህ አለ።” ሳያስበው መስ ጥቂት ስሜት ነፍሶበት በ መናደድ ሁሉ ሰመጠ። “አይ” ፈገግ አለ ናሆም ጥቂት ነገሩን ለማርገብ በማቀድ። ጥቂት ተጓዙ እና መስ ረገብ ሲል ነገሩን ለመጠቅለል መልሶ መገንዘቡን አሳወቀ። “ባልክው ብቻ ደግ ነገር እየተመለከትኩ ነው። ይገርማል ብቻ። በተስ. ሳንቲም መጨረስ ሂወትን መጥላት ሊሆን ይችል አለ አልክ!” ዝምታ ሆነ፨
ግን በ እርምጃው አይነት አጋዥነት ከቤተክርስትያኑ በአስራአምስት ደቂቃ ጉዞ ወደ ቤት ደረሱ። እሚ በእነ ባቤ እና ብሩ ድጋፍ ከገብስ፣ ባቄላ እና ድንገት በመጠኑ እንዴት እንደ ሆነ ሳታውቅ እጇ በገባው ለውጭ ፍጆታ እሚመረተው ዉዱን የ ማሾ ፍሬ ክክዎች ደባልቃ የ አዘጋጀችው ቅንጬ ቀረበ። በቂቤ፣ ነጭሽንኩርት፣ እና በሶብላ እንዲሁም ሚጥሚጣ መዓዛ ው በእሚደንቅ ሆኖ ተለዉሶ ቤቱን አወደ። እንደ ተለመደው መብል ለብቻ መመገብ ባህልአቸው ስላልሆነ ቢግን ቀስቅሰው በባቤ ጸሎት ወደ መመገብ ተገባ። “ጉልባን ይመስል አለ!” ቢግ በሳህኑ ከአለው አንዴ ጎርሶ ምስክርነት አቀረበ። እሚ በምስጋና መቀበል መልክ “ምን ይደረግ። አዘጋጅ ዋ እናትህ!” ብላ ህፃንዎቹን አስፈገገች። ሎሚውን እንዲጠቀሙ ናሆም አጥቦ በመቁረጥ አቅርቦ ስለ ነበር በሎሚው መጨመቅ ቅንጬው በላጭ ጣፋጭነት አገኘ። የፈለገ ደግሞ በብልቃጥ በተቀመጠው ደረቅ የመጥበሻ ቅጠል ዱቄት ብንብን በማድረግ ቃና መቀየር ተፈቅዶለት ነበር። ባቤ ያን እሚወድድ ስለ ነበር በቅንጬው መጥበሻውን ብንብን አድርጎ አዋኻደው። በተፈላው የማር ሻይ እያወራረዱ መመገቡን ሲቀጥሉ ቤተሰቡ ከእሚ በቀረ ደስተኛ እና የስኬት መንገድን እሚያጣጥም ሆነ። ሁሉም መቋደሱን በከፍተኛ ፍቅር እና መከባበር፣ አብሮነት እያደረገ ቆየ። ከመሀል ባቤ ተነስቶ በትላንቱ ዉሎ በመማረኩ አሁንም መቆየት ሳያስችለው ትመ.ውን አበራ። እሚ መስፍንን ተመልክታ አስተያየቷን ሰጠች። “ለ አንድ ሁለት ቀን እዩት እና ይዉጣልአችሁ በእሚል እንለፍ እንጂ በገበታ መሀከል ትመ. አፍጥጦ መመገብ የለም። መብል ከሰውነት እንዴት ይዋሃድ? በደመነብስ ሰው ይመገብአለ እንዴ! ከሰውነት የይገባም እኮ። የገበታ ስነምግባር!” ብላ ተቆጣች። ባቤ በቅሬታ ሆኖ ብቻ ለተፈቀደውም ለሰሞኑ ልዩ ዕድል ኩምኮማ ተዘጋጀ። ወዲአው ሲጎረጉር በ ኢሳት. የ ኢሳት ዕለትአዊ ዝግጅት ላይ በ ዉጭ ሀገርዎች የኢትየጵያዎች ተቃውሞ ሰልፎች ዜና ቀረበ፨
በ ኦሮምያ ክልል እሚገኝ ነፍጠኛ እና ዐብይ አህመድ ከኦሮሚያ ይዉጡ እሚል የባህርማዶ ሀገርዎች ትእይንተህዝብ የሃጫሉ ሁንዴሳ ሆንብሎንታ ግድያን ተከትሎ መነሳቱን አምደኛዎቹ ጋዜጠኛዎች በሰከነ ዉይይትአቸው አንስተው እየአጤኑት ነበር። በግብጽ መንግስት እርዳታ የመጨረሻ እጅአዙር ብጥበጣ ሙከራ እየተሞከረ እና በብሔር አጣልቶ ትርምስ ለማበጀት የተከወነ እንደ ሆነ እና የ ታህግ. (ታላቁ ህዳሴ ግድብ) ዉኀ መሙላትን ለማቋረጥ የታለመ ሴራ እንደ ሆነ አነሱ። ባቤ የጠጠረ ዝግጅቱን ጠላው። ምንም እሚአስቅ ወይም አዝናኝ ነገር ስለ አልተመለከተ ለእርሱ ፍላጎት እሚሆን ጣቢአ በማሰስ ጣቢአውን ቀየረ፨
መስ በትኩረት የሰማውን የደህንነት መረጃ ስለ ልጆቹ የገጽማያ እፍፍታ ሲል በትመ.ው ተመልሶ እንዲቀጥል አልጠየቀም። ናሆም ፍላጎቱን ተመልክቶ ስለተረዳ ተያያዥ ዜና ከጠቀመው ብሎ ትላንት የሰማውን አወራለት። “ለእንግሊዝ፣ ፈረንሳይ፣ ተዓግ.፣ ኖርዌይ፣ ምናምን… መንግስትዎች ‘ግብር እንከፍል አለን። ነፍጠኛ ከኦሮሚያ ይዉጣ ከአልሆነ እናንተ ትልልቅ ሃገርዎች ግብርአችንን ለኢትዮጵያ መንግስት እርዳታ አታድርጉብን’ አሉ። ብዙ ሌላ የለውም፤ ከእዛ ተቃውሞ ነጥብ ውጭ።” ይህን ናሆም ሲናገር ሳያስበው ወደ ማውገዝ ስሜት ዉስጥ ድምፀቱ መጣ። ጭራሽ ሊጎርስ ያዘጋጀውን አዘግይቶ አስተያየት አከለበት። “እዛ በለየለት “ሰው ሃገር” ግብር ከፍለው ደረት ነፍተው ይኖሩ አለ። ግን እዚህ በሃገሩ ግብር ከፍሎ እንዳይኖር ሃሳብ ያመነጩ አለ። ነፍጠኛ እሚሰኝ ነገር እንደ ዩኒኮርን ባይኖርም፣ በእዛ አማራ ለማለት ነው። ሲቀጥል የሁሉም ብሔረሰብ አባል የነበረ የጥንት ነፍጠኛ እንጂ አማራ ነፍጠኛ ብቻ ኖሮ አያውቅም። ግን አማራ እና ሌላ ብሔረሰብ ከግብር ነፃ ሆኖ ኦሮሚያ ክልል ዉስጥ እሚኖር አይደለም። እንደ ማንም አብሮ በ ሃገሩ ግን እኩል ነፃነት የአጣ ነው።” መስ በታዳገከው ናሆም ግንዛቤ ላይ ምን አቋም እንዳለ ለማወቅ የበለጠ መብራራት ፈለገ። “ኦሮሞዎች በ ህዋሃት. የተመሰረተ መንግስት ላይ ሲአምጹ ልእለቀንደኛ ደጋፊ ነበርክ እኮ፤ ወይስ ድጋፍህ እንደ ዋለልኝ መኮንን ነበር?” ብሎ አምታች ጥያቄ በሆንብሎንታ አቀረበለት። አብሮ ሃሳቡን ማጥለል ከቻለ እና ከአደገ ለመመልከት ይህን አደረገ። “አሁንም ደጋፊ ነኝ። በእርግጥ አዎን ልክ እንደ እዛ ድንቅ ጸሐፊ ሀሰተኛ-ዘውገኛነት ኦሮሞ ህዋሃትን እንዲገፋ እና ነፃነትን በሀገርአቀፍ ደረጃ ለማግኘት አብሮ እንዲያግዝ እንጂ ዘውገኛነትን ማን ይደግፍ አለ? በጠቅላላው ግን ፍትሕ እንደዘመነባርነት በጎደለበት እማይከነክነው የለም። ይከነክነኝ አለ። ለዘውግም ለነ ብሔርአዊ ጉዳይ፣ ለምኑም ሳትል፣ ኢሰብአዊነትን ትዋጋ ወይ እሚዋጋ ማንንም ትደግፍ አለህ። በእርግጥ ዞሮዞሮ ይኸው ህዋሃትም ተሸንፎ የተገኘውን ተቃውሞ ሁሉ መደገፉ ችግሩን ማስወገዱ እንጂ መፍትሔውን መጥራቱን ማወቅ አልተቻለም። ጸረ-ብሔርአዊ ህዋሃት ለቀቀ። ግን ብሔርተኛነት ገና በጎዳና ላይ ነው። እና እነእዚህን መሰል ተቃዋሚዎች ወይም ጥቁር-ልዑክዎች አጨናጋፊ እየሆኑ ነው ማለት ነው። እሚሆን የአንድ ምሩቅ-መሃንዲስ፣ ሃያሲ እና ዐምድ-አርታዒ (ኦፕ-ኢዲ)፣ የለልኝ አቻ እሚሆን ጽሑፍ ባለፈው ስመለከት ዋለልኝ እንደተሳሳተ ሲያሳብቅ ነበር። የእነዛ ጥቁር-ዘውገኛዎች ተቃውሞ ያሰጋ አለ ብሎ ይሰብክ አለ፤ ዘውገኛነት እሚቆይ እና መደብ እሚዘገይ ንቅአተህሊና እንደሆነ ሲናገር ብስጭት ነው ያልኩት። ስንት የአመጽ እና አብዮት ንብብር እንደእምናልፍ እግዜር ይወቅልን እንግዲህ። ብቻ ለጠየክኝ አዎን በሰብአዊነት፣ ሀገርአቀፍአዊነት እና ሀሰተኛ-ዘውገኛነት፣ ማንንም ብሔር እምደግፍ መሆኑን አላቆምም። ማለትም እኔ ኦሮሞ፣ አማራ፣ ትግሬ፣ አፋር፣ ሁሉንም ነኝ! ኢትዮጵያአዊ ስለ ሆንኩ። ግን ህግን ያልበደለ ዜጋ ማባረር የትም መፍትሔ ሆኖ አያቅም። ማሰቡም ውርደት ነው! ማለትም፣ ሴራ አለ ማለት ነው ከምር። ምክንያቱም በሰላም ቀን ማን ያንን ውርደት ይዋረድ አለ? እንጂ አምባግነና (ዲክታተርሺፕ) ብቻ እሚአቅ መንግስት ላይ እማ ማን አይቃወም። ማንም የትም ግብር ከፍሎ ተከብሮ በሰብእአዊነት መስተንግዶ በእሚኖርበት የዘመንክፍል፣ ይህ ተቃዉሞ ሰልፍ በእርግጥ የግብጽ ስራ ሊሆን ቢችል እንጂ ኦሮሞ ነፍጠኛ ሣይል መንግስትን ለይቶ ተቃውሞ አባርሮ፦ በማግስቱ እንደ እዚህ እሚል አይደለም። ለነበረው አመጽ ደግሞ መተባበር እንደታፈነ ዜጋ አንዱ ሃላፊነቴ ነው፣ ይሆን አለም፤ መቼም። ግን እርስበእርስ በመጣላትአችን ጥንካሬአችን ስለ እሚገፈፍ እንደ እዚህ ሃገር ጎጂ ጎረቤት ሃገር ጠቃሚ ነገር ሲገጥም መስከን እና እጅአዙርን ማብረስ እንጂ በእዛ በመስጠም እምንሰበስበው ጠቃሚ ነገር የለም።” ይህን ብሎ ቅንጩውን በማጣጣም ጥቂት ዝምታ ወሰደ። መልሶ ተጨማሪ ቅርቃር ለማበጀት በተከፈለአቸው እሚባሉ ትእይንተህዝብ የከወኑት ሃሳብ ላይ ተጨማሪ ነጥብ ጣለ፨
“ጽንፈኛዎች የሌላ ዘር ነዋሪዎች ይውጡ እሚሉት ቢወጡ በክልሉ እሚቀረው ህዝብ እሚበለጽገው በሥራ እና ዕዉቀት ምርምርዎች እና ትምህርትዎች እንጂ በሌላ በምንድነው? መሬቱ ወዲያው ተወርሮ ወዲያው እሚያጥር እና ፍቱኑ መፍትሔ ያሎነ ነው። ስለ እዚህ ለምን ማንም ሳይፈናቀል፣ አፀፋ-ዉድመት ግብዣንም ሳይጠራ፣ የታሪክ አዎንታአዊ ዝግመትን ጠልፎ ሳያበላሽ፣ ሁሉም እዛው እንደ አለ በመማር እና በዕዉቀት፣ በተጠያቂነት እና ጉልበቱ ተጠምዝዞ በጸረሙስናአዊ ትግል በመብሠክሰክ፣ ትዉልድ እና ሃገር ማልማቱን ይልቅ ተያይዘውት ልዩልዩ ጥበብዎች ከእየ ዘሩ በመሰብሰብ በሥራ ጥበብ መለዋወጥ እሚአድጉ አይሆንም። ዕዉቀት እና ጥበብ ደግሞ ከባህርማዶ እምንቀጥረው ከእኛም ዜጋዎችአችን ሄደው ነግደው እሚበለጽጉበት ነው። ያልኩህን ደግመህ አዉጠንጥነው ዝምብለህ አትለፈው፣ መፍትሔው ከእዛ አይርቅም፤ አንጎልህ ግን።” ናሆም በቀናነት ይህን በማሰብ አስተያየቱን ሲሰጥ መስ በብሩህ ቀናነቱ ተደምሞ አየው። በሃገሩ እልፍ ችግርዎች መብገን ይዞ እሚአድገው ትዉልድ አባል ስለሆነ መልሶ በእርሱ ትዉልድ መፍትሔ ይመጣ ይሆን አለ ብሎ ዳግም በማሰብ ፈገግ አለ እና መልስ ስለ ሌለው በጥያቄው መደነቅ ብቻ ራስቅሉን ዘመም አደረገ። “እኔ እንጃ! እስቲ በሂደት መልስ እናበጅ ይሆን አለ። እስከ መቼ ምርጡ ጎዳና ገሃድ ቢሆንም እንደ ዐዚም እማይታየን ሆኖብን ከደጉ መንገድ እንደ እምንሸሽ እግዚእአብሔር ይወቀው፤” አፍታ ወሰድ አድረጎ ቁምነገሩን ቀጠለ። “ችግሩ አከፋፉ የክብ ሽክርክሪቱ መሰበሪያ ማጣቱ ነው። ዞረን ዛሬም እኮ በስነዉሳኔአችን መዝቀጥ፦ ሰላም-ሻጭ-ሰላም-ገዥነቱ ላይ ተመልሰን አለን እኮ!” ናሆም የተነሳው ሃሳብ በተከታታይ የታሪክ እሾህአማ መሰላል ላይ ያወጣን ሁኔታን ስለነካ እና ትእግስት መከራከሪያ ሆኖ እሚቀርብበት ሆኖ ስለእሚናደድ በአገኘው ድጋፍ ተደሰተ። መስ ትእግስት ከእሚሉት መሀከል ስለነበር እና በቅርቡ ብቻ ወደ ገሃዱ መመለስ ስለጀመረ ናሆም የልብልብ ተሰምቶት የበለጠ ሊስበው አሰበ። እንደ መስ ግን ምናልባት ሙሉ ሃገሩ ቶሎ ላይነቃ እንደሚችል አሳሰበው።
“ተርታ እና መደዴው (ሜዲዮክር) ያንን መመልከቱን እንኳ እሚችሉ አይመስለኝም! የጋሽ አበራ ሞላ ሃሳቦችን ሳያከብር ግን ተራ ልጁ የሆነ ኮትኳች (ጋርድነር) እና ጀማሪ አንፋሽ (ኢንስፓየረር) እንደተለመደው የንጹህ ህዝብ ደም ያወጣውን የአብዮት ነፃ ዙፋን ተቀብሎ፣ የልምምድ ዳዴ ሲጨርስ የለየለት ሰላም ሻጭነት የገነባ ያልተለየ አምባገነን ሆኖ ተቀምጧል። መነሻ ምርኮ (ፈርስት ኢምፕረሽን) ዘግይቶ ይደበዝዝ አለ እና ይህ የበለጠ አደጋ ያለው የአብዮት ክስረት ዙር ግን ሊሆን ይችል አለ። በልብአቅልጥ ወሬዎች ተርታ እና መደዴውን አንፍሶ፣ ያልሰለጠነ-ሀገር እሚባለውን ህዝብ ልብ፣ በበቂ በምኞት መጠን አነሁልሎ አስክሮ አለ። ጠሚ. ዐብይ አህመድ የያዘው ፊት ዛሬም ከቀረበ፣ የእዛ ድንቅ የኢህአዴግ መሸነፍ ሰሞን የነበረው ጥልቅ ስሜት እና የእርሱ ወቅትአዊ የአቢዮቱን መንፈስ መጠቅለል፣ ብቻ ያ ጣፋጭ ቅዠት ትዉስታ እሚረጭ ነው። ይህ መነሻ ምርኮው እንደ ጠልሰም ስእል አስካሪ ነው፤” መስ ከት ብሎ ሣቀ። በእርግጥ የሃያሰባት አመቶች አምባግነና በባዶ መዳፎች የማባረሩ የህዝብ አብዮትአዊ ልእለ-ገድል ቃል እማይገልጸው ስሜቱ ሁሉ የተጠቀለለው በእዚህ ተተኪ ለወቅቱ-ትንግርት-ሰው እና ቃሎቹ ነበር። ይህ መነሻ ምርኮ በቂ ሽያጭ ሆኖለት እስከአሁን ያልተሟሉ እልፍ ቸልታዎች ከፍለንበት በቀላል ታልፈውብን እንደሀገር ከስረን አለን። ይህን እንዴት መግለጥ እንዳለበት አሰብ አድርጎ ቁምነገሩን ለጓደኛው መጨበጥ አስቦ ናሆም ቀጠለ። “እዉነትም ለካ ይህ ሁሉ የሀገር መዉደም ሲከወን ትልቅ ቸልታው ወደ ሰላም ሻጭነቱ ለመፈናጠጥ ነበር። ሻሸመኔ ሲወድም አፍንጫው ስር ድንቁ አግዓዚ ነበር፣ አዲስአበባ እስከ ቡራዩ ለቀኖች ስትታወክ ሁሉም ሃላፊዎች እና ጦር እዛው ለዕዝ ተቀምጠው ነበሩ፣ ብዙ ዉድመቶች በቂ እሚሰኝ ህዝብአዊ ሰቆቃ ከወኑ። ግን ለአብነት የተደረጉ ነበሩ። ከኢህአዴግ. ልዩነት የሌለው ምርጡን የድህረ-ዝማኔ የአምባግነና መንገድ፦ ሀገር አሸብሮ ወይም ለሽብር ቸላ ብሎ (ሁሉም ነብሱ ታዉኮ ሲደነግጥ እና መሰል ጥፋት ከሰፋ ብሎ ሲፈራ) ሰላም-ሻጭ ሆኖ በቀላሉ በዙፋን ጉብ ይባል አለ። ያ ቸልታ የእዛ ጥረት አካል ሊሆን ይችል አለ። የሰላም ሻጭ ስነዉሳኔ ለመሪው ምንም አያከስርም። ሰላም ጠብቅልኝ እንዲል ዜጋውን ወደ አመጽ እና ሽብር መምራት የጥሬዕቃው ወጪ ነው። የታወከ ሰው ሰላሜን ስጠኝ ብሎ ሲጠይቅ ሰላም አስከባሪነት ሰላም አጥፊ እና አዋኪን መቆጣጠር ይሻ አለ ብለው ተቃዋሚዎችን በማውደም ብቻ በጠንካራ ብቸኛነት ስልጣንን መውሰድ ማለት ነው። ዝነኛ ጨዋታ! የስልጣን ማመካኛ በሽታ ፈጥሮ (የንጹሃን መታወክ) ሰላሙን በቀላል ዋጋ ላቅርብ ብሎ ለመሸጥ መቅረብ ብቻ ነው። ድሃ ጭንቅላት ይህን ስለማያውጠነጥነው እንቢ አይልም። ሰላም እንደ እንሰሳ በቂው ነው። የተሸነፈው ንቃተህሊናው ያነሰ የነበረው እና ሲቀጥል የተመረዘበት ዜጋ ይሸነፍ አለ። ወርቅ እና ፈርጡ የሰማይ መላእኮች ሳይሆን የራሱ እንደሆነ ይዘነጋ አለ። ሀገር ሰላም ብቻ እሚጠየቅበት እንዳልሆነ ይረሳ አለ። በጎመን በጤና መርህ ዉስጥ በቶሎ ይታሰር አለ። ይህ በአውቆታ የተሰለበብህ ሰላም ሲጠበቅልህ መሪውን መቀበል ትጀምር አለህ። ለቀላል ጥያቄ ለሰላም ማቅረብ መንግስት መሆን ይጀመር አለ። መንግስት እና ሀገር ግን ከሰላም በላይ ነበር። ከፍትህ፣ ስልጣኔ፣ ወደፊት መጓዝ ወዘተ. መከልከልህን ተቀበልክው፣ ተሽመድምደህ መኖር ጀመርህ ማለት ነው። እና ይህ የሆነ የአምባገነኖች መንገድ ዞሮዞሮ ተመለሰ። ለአምባገነኖች ደግሞ ይቺ ምርጧ ካርድ መሆኗ በታሪክ እርዝማኔ ያበቃ አይመስልም። ‘መች የታሪክ መምህርነትን ፈቀድን፤’ ዐብይም ከመጣ ወዲህ የ አለጂያንት መጽሐፍዎች ወይም ፊልሞች ለሀገሩ ዋና መልእክት መንደመሆናቸው ቀጥሏል። መልእክቶችአቸው ስላልተሰሙ ወደ እውቁ የአሳማዎቹ ወደሰው እርምጃ መራመድ ቋፍ ላይ ያለ መንግስት ጋር ነን።” መስ አሁንም ከት ብሎ ሣቀ። መስማማቱን ከርችሞ አረጋጋጭ እሚሆን ነጥቡን አቀረበ። “ለነገሩ አዎን! አንድም ለሀበሻ መሰረትአዊ ጥያቄ፣ ወይም ዋናውን-ተፈላጊ ነገር የአፍ አዎንታአዊነት በማትረፍረፍ፣ መመለስ አትችልም። በአኗኗር ኋላቀርነት ምክንያት፣ አሉታአዊ ስነልቦናው የኑሮ ባሪያ አድረጎ አስቀርቅሮት ጨለማ ንጽረት እሚቀናውን ህዝብ ነው። ኮሎኔሉ መሪ እንኳ አመድ እሚቀናው ብሎ የሰደበው ህዝብ ነው። በቀላል አደናግሮ የግል ተአማኒነቱን ማፋፍሞ – ማለቴ አዎንታአዊነት ቢርበንም በዝብ አጠቃቀም ቀጥሮት – በጎን ደግሞ ሁከት ቢያንስ በቸልታ በመፍቀድ፣ አወዛገበ፣ አሸበረን። በመጨከን አምባገነን መሆኑን አጠንክር ተብሎ በእሚያስተጋባ ጩኸቶች ከዳርእስከዳር ተደገፈ። ሃገር እሚያክል ሃብት ላይ፣ በመነሾ ማራኪነቱ እና አውቆታአዊ ዝምታው ሰላም ሻጭነቱን ይዞ ብቻ ቀጠለ። የአምባግነና እና ስርዓተ ሙስና የእሚፈልገው ወርቅ ፍፃሜው እየሆነለት ነው። አፈሩን ገለባ ያድርግለት እና መለስንም እንኳ ኧረ ተመለስ ማለት የጀመረ ህዝብ ያለበት ሃገር ያን ያክል ለመሰንበት ብቻ እሚናፍቅ ሆነ። ህዝቡ ሚሊየኖቹ ሃብቶቹ ሲወድምበት፣ ብዙዎቹ ሲገደሉበት፣ ሲፈናቀሉበት፣ እንደታሰበለት ተስፋቆርጦ ተሸነፈ። ወዲያው አቅሙን ቀብሮት በቀላሉ ለሰላም ግዢ ብቻ ወደ ስነዉሳኔ ገበያው እሚወጣ ሆነ። መንግስት እራስህ ተጠየቅ፣ ሳትጠብቀን ቆይተህ ተጎዳን ያለ እንኳ የለም። ሮጦ ወደ ታሰበለት ቀዳዳ ተቀረቀረ፦ ሰላም ሽጥልን እንጂ! ያሻህን እሰር፣ ያሻህን ህግ አውጣ እና ጋዜጠኞች እሰር፣ መገናኛብዙሃኖችን ዝጋ፣ እሚቃወሙህን አጥፋ፣ እሚያስጨንቁህን አስወግድ፣ እሚገመግሙህን አዋርድ፣ ወዘተ. ብቻ ሠላም አስመልስልን ሽጥልን ማለቱን እጅግ አበዛው። ያምባገነን መልሶ-መደራደሪያ (ካውንተር አርጊመንት) ደግሞ፣ በሰላም እጦት ከደገፋችሁኝ፣ ከፈቀዳቹልኝ አዋኪ እምለውን በማሳደድ እገዛ አለሁ ነው። ወዲያው ይኸው፣ ድምጽ የሌለበት ሃገር፣ ስንት ደህና እሚሰኙትን ሄሉ መገናኛብዙሃዎችአችንን ዘጋብን። የተለየ ድምጽ መስማት ከለከለን። የአንድ መንግስት ድምጽ ብቻ ያደነቁረን ቀጠለ። ጋዜጠኛዎች ታሰሩ። ንጹህ መሪዎች ወይም ተቃዋሚዎች እንደ ባልደራስ መሪዎች ያሉት ጭምር እና ያጠፉ አብረው ታሰሩ። አሳማዎች እንደ ሰው ሊራመዱ አጭር ቆይታ በቃአቸው ማለት ነው። ከቶ እንደእሚያሸንፍ በማረጋገጡ እየሰበከ ሲያስፈራራቸው የነበረ እና ባለ ድጋፍ እሚፎካከሩት እንደ እነ እስክንድር ነጋ ያሉትን አደጋዎች ሁሉ አብሮ መቀነሻ መንገድ ፈብርኮ፣ አሁን ሰላም እሚነሱ አጠፋሁላችሁ እዚህ ቆይቼም እጠብቅላችሁ አለሁ ባይ ሆነ። ሰላም ስላገኛችሁ እኔ ወደዙፋኔ እናንተም ወደ ድህነት፦ የራሳቹህ ሰላምን ነጥቄ/አስነጥቄ ሸጬውአለኋ…! ይህ የአምባግነና ሰላም ሽያጭ የመንበር ትኬት እንደሆነ በገሃድ አደባባያችን እየተሸጠ ያለ ጉዳይ ነው በእርግጥ።
“ግን ከአስር ኢትዮጽያአዊ ዘጠኙ፣ አሁን ለዘመኑ አስጊ በሆነ አኗኗር ገጠር እሚሰቃይ ነው። የቀረው ከርፊ ከተማ አቅፎት ስብእናውን ገደብ እሚጥልበት ዜጋአችን ነው። የጋሽ አበራ ፍልስፍና አዲስአበባን በትልቅ ልዩነት ሲሞሽራት ዛሬም መጥቶ ሃሳቡን ከጣለው ሰው እሚለቅም የሆነው አብይ፣ እንደ መሪ ሃቀኛ ቢሆን ኖሮ፣ የለብለብ አካባቢ ኩትኮታ አይያያዝም። እርሱ ሲሄድ አብሮት እሚሄድ፣ ልክ እንደ ሆዱ ያለ አካሉ አድርጎ፣ ሃገር እሚያድን ፍልስፍናን አያስተናግድም አይሰብክም ነበር። ጋሽ አበራ አዲስአበባን በግል ደስታው በውበት ሲያበራት በቂ ግልአዊ አቅም ነበር። መንግስት የነቃ ቀን ግን እንደ ጋሽ አበራ አይሰራም። ትዉልዱ ሁሉ ጋሽ አበራ እንዲሆን ያደርግ እና እልፍ አበራን ይቀጥር አለ። ሌላው ማጭበርበር ነው። ወይም ቢያንስቢያንስ መሃይምነት። አንተ ስከመንግስትነት ስትሄድ አብሮህ እሚገፈፍ ነገር ከሰራህ ብልህ መሆን እምትችልበት ዜሮ ምክንያት ነው ያለው። መንግስትአዊ ሃቀኛ አቅም የበጂ ነገር መሰረቱንከ ለሁልገከዜ መተው እና እንዳይቋረጥ ሆኖ በእራስሰር እሚያድግበትን መንገድ መዘየድ ነበር። ሃቀኛው መሪ አበባ ተክሎ በኮትኳችነት ሞኝ ስነልቦና አይሸውድም። የጋሽአበራ ሽልማት ድርጅትን፣ ፍልስፍናን፣ ትምህርትን፣ አመለካከትን፣ ውድድርን፣ ወዘተ. በትልቅ እማይቀለበስ ስነስርአት ቅንብር ይቀርፃል። እንደ ፈረንሳይ እና እንግሊዝ መካከለኛው ዘመን የመናፈሻ ፍልስፍናን ያሳድግ ነበር። ሀገርበቀል መናፈሻ ፍልስፍናን ያሳድግልንም ነበር። እርሱ ሲሄድ፣ የጋሽ አበራ ስም፣ የመስራት ስነልቦና፣ የአሸናፊነት ሽልማት፣ የማይዛነፍ ስራ እድል፣ የጸዳ ከተማ አንዱ ባህልአዊ እዉነአችን ይሆን አለ። ተቋሙ በብዙ መሰል አያያዞች ሁሉ በሌላ ጥረቶች ይቆይልን አለ። ለእዛ ግን እሚፈለገው ነገር ህግ እና ስነስርአትአዊ መሰረት ነበር። ህግአዊ ባህል! ለሁሉም በጎ ጥረት፣ ህግ መስርቶለት እማይነቀነቅ ባህል አድርጎ ማስቀመጥ ይገባ አለ። በድቡሸት ያልታነጸ ነገ ላይ አንዱ እግር የተተከለ ሆኖ ይህ ዛሬ ይኖረው ነበር። በጠቅላላው ይህ ግን ክሽፈት ነው። መናፈሻዎችን ለመገንባት በኢህአዴግ ወቅት ብዙ ተጠንቶ፣ ተመርምሮ፣ ንድፍ ወጥቶ፣ ተበጅቶ፣ ስራው ተጀምሮ፣ ተጓትቶ ነበር። ግን ይህ ወቅትአዊ አመራር መጥቶ ስለጨረሰው መቶእጅ የእራሱ ስራ እንደሆነ አድርጎ አመት የሆነውን ብልግና እሚሰኝ ድርጅት መስበኪያ አደረገው። ለነገሩ፣ ይህ ድርጅት ኢህአዴግን ያባረረ እና ጥንት የነበረ እንደሆነ እየሰበከም ምረጡን ማለቱን ተያይዘውት አለ። ኢህአዴግ በብዙ አመቶች ትግል በህዝብ ሲባረር፣ ይህ ተቋም ገና ከመወለድ አመቶች የራቀ ነበር። አመጽ እና አብዮት ኢህአዴግን ሸኘ። በጊዜአዊነት ከህአዴግ ተደብቆ ይህን ሰው ሾመ። በአመት ምናምን ህዋሃትን ወደ መቀሌ አባርሮ፣ ይህ አዊ አሻንጉሊት፣ ጥርስ አወጣ። እራሱን ወዲያው ከአዲስ አቋቋመ ደና ብልጽግና አለ። መናፈሻዎቹም እየተከናወኑ የነበሩት ከብልጽግና ቀድሞ ነበር። በአጭርጊዜ ግን ይህ ድርጅት የአብዮቱ ታጋይ፣ የሃገሪቱ መሠረት እና ረዥም ታሪክ እንደሆነ ሲሰብክ እሚሰማ ሆነ። አብዮት ጥምዘዛ። ተመሣሳይ፣ ዓለመ ምድረበዳ (ዐረብ) ዉስጥ እሚሰቃዩ ሀበሻዎችን ተሸክሞ አንድ ሁለቴ በመምጣት ከዙፋን ሲኬድ እሚኬድ፣ ዙፋን እስኪለመድ እሚያለማምድ ጀብድ ይሰራል። ነገም ያ እንዳይከሰት ግን ህግበህግ፣ የሆነ እንቅስቃሴ ከቶ አልተከወነም። ዜጎች በውጭ ሀገር እንዳይጎዱ ከአስተናጋጅ ሃገር ጋር ዘላለም ለተሻለ ነገር መደራደሩ፣ ማንም አረቢኛ ሳይማር መብራት ከሌለበት ገጠር ወደ ቤተመንግስት መሳይ ዐረብ ቤት ገብቶ ባለማወቅ ከመሰቃየት እና መተኮስ እሚባል ነገር እማታቂ ብቶኚም ልብሴን ስትተኩሽ አቃጠልሽው ተብሎ ከፎቅ ከመወርወር፣ ልብስ መተኮስ እና ቤት አያያዝ ዜጎችን ማሰልጠን፣ መብቶቻቸውን ደግሞ ከኮሚኒቲ መሪዎቻቸው ጋር መጠባበቅ እሚያስችሉ ህጎች አዉጥቶ መደገፍ፣ ወዘተ. ይገባ ነበር። ሃቀኛ መሪ እንዲህ ተቋም፣ ባህል እና መሪአቸውን ህግን ይሟገትበት ነበር። በእዛም፣ ከውጭ ዜጎች እሚልኳቸውን ዋናውን የዉጭምንዛሬ ሀገርአዊ ምንጭም ማዝለግ ይችል ነበር። የሃገሪቷን ዳያስፖራ እንደ ቀሩት በቅርብ ያደጉ ሃገሮች ባለበት ሀገር ደህና እንዲሆን ማንቃት እና መገት ይገባ ነበር። ብቻ እያንዳንዱ ጉዳይ በህግ እና ተቋም እንዲሰራ፣ መሰረቱን መተው እና እንደእነ ‘ሚድናይት ጀጅስ’፣ ማርበሪ እና ማዲሰን ጉዳዮች፣ ለስርኣት እሚሟገት ትትረት በቅጽበቶች ሁሉ አበጅቶ ለመሞት ይቻል ነበር። ያን አይነት መዘጋጀት ግን የለም። ነፃ እና አቅመኛ መገናኛብዙሃን እና ፍትሕ አካል ደግሞ ከሌለ አብሮ ይሄ ሁሉ በልጦ እየሞተ፣ እሚጠየቅ እና እሚመረምር ስለእማይኖር ዳግም ገደል መግባቱ ነው። ለእነዚህም ስነዉሳኔአዊ ማእዶት (ፓለቲካል ትራንስፎርሜሽን) ትንቅንቅ ገጥሞት አለ። እና የነገ ነፃነት እና ብሩህ ቀንነት፣ በድንገተኛ ስልጣን ላይ መጤዎች እና ያልተማረ እፍፍታአቸው አደጋ ላይ ሆኖ አለ።
“ሃኪምቤቶች፣ ትምህርቶች፣ እኩልነት፣ ፍትሕ፣ ገለልተኛ እና አስቻይ የባህል ለዉጦች (ከምንም በላይ)፣ ሙሰኛዎችን አለመሰብሰብ፣ ህጎች እና አለትአዊ የማህበረሰብ መሰረት መጣል፣ አንድነት እና አዎንታአዊነት ማስተማር፣ የህብር-ዉህደት ስነልቦና ማፋፋም፣ ሃገር በስርኣት እንድትተሳሠር እና ከመንግስት ገዢአዊ መዳፍ ወጥታ እንደ ጉልበተ-ሰብእ እንድትቆም፣ የንቅ ማህበረሰብ መሰረት መጣል፣ እና እንዲህ ያሉት ብቻ የሃቀኛ መንግስት መሰረት ሆነው ሳለ፣ ወደ ሰላም ሻጭነት መመለሱ ተረኛነት ነው፤ ለአምባግነና እና ሙስና።” ናሆም ሳያሥበው ይህን አስፍቶ በስሜት ሲናገር መስ ያልጠበቀውን የትንታኔ ምልከታዎች ስለተገነዘበ ተደንቆ አፈጠጠ። ናሆም መልሶ ሳያስበው ያወራው እራሱን አስገርሞት ወደ ጠላው ተቻኩሎ ዞረ። በስፋት የገለጠለት ሃሳቡ በመስም አንድ ነው።
“አሁን ይሄ ምኑ ይታይ አለ? ሃገርአችን በቅርጽ እና ቅጽ ፈርጅአዊውን ልዑልነቀርሣዋን ሙስናዋን ሳታጠፋ፣ አድሃሪዎች የሙሰኛዎች አገልጋይ ሆነው የብሄር ቅብጥርስዮ ወኪል በመሰኘት አካባቢያዊ ህዝብን በማፈን አገልግለው በማደግ ወደ ዉጭ አምባሰደር እስኪሆኑ እና ከነዘመዶች እስኪኮበልሉ እና ነጮች መሃል ተጠቃለው እስኪገቡ፦ ከመሬት ተነስተው ከበርቴ (አድሃሪ) እስኪሆኑ፣ በሙስና ማገልገል ከታች በመጀመር በሚሄዱበት ስርኣት ሃገሩ እንደተበላ እነሆ ሌላው አቢዮትም መክሰሙ ነው። እንግዲህ በቀላል እሚከፈተው ብርሃን በረዥሙ እያስሮጠን እና መንከባለል ተጠናውቶን ስለእምንኖር አንድ እድሜ ዘመን አልፎም ሌላው እድል ወደ ገደል እየሄደ ነው። አሁንም ያ፣ ያንተ ትዉልድ አንዱ ራስምታት ነው።” ሣቅ ሣቅ ብሎ ተመለከተው። የእይታውን ነገር እንደ እሚጋራ እና ሃሳቡን መግለጹ እንደማይከፋ በአንድምታ ስነልቦና አሳወቀው። መስ በመስማማት ከንፈር ለጠጥ አድርጎ ግንባር በመሸብሸብ አናት ወዘወዘ። መስም ከጠላው ተጎንጭቶ ወደ ባቤ ዞር እየአለ ባማራጭነት ከቀረበው ትመ. አካባቢ አተኮረ። ባቤ እና ታላቁ ቢግ በትመው አዲስ ተሞክሮ ተጠምደው ከቶ በቤቱ መኖርአቸውን ወደመዘንጋቱ ነበሩ። ይህ ስሜት ተገቢ ከሆነ መስም ተገድዶ አስተዋለው፨
ባቤ ጣቢአዎች መጎርጎር ሲቀጥል ኢሳት ተመልሶ ተከፈተ። ናሆም ሃሳቡን በመጠኑ አጥርቶ ስለነበር መስ ስለ ወጣቱ የ ስነዉሳኔ (ፖለቲካ) ተሳትፎ ሌላ ገጽታ ለማወቅ ስለ ኢሳት ዕለትአዊ አስተያየቱ ምን እንደ ሆነ ጠየቀ ው። ናሆም በዘለገ መንበክበክ ልዕለ-ገር የሆነ ቅንጬውን በጥቂት ጉልበተ ማኘኩን ቀጥሎ የልቡን ተናገረ። “አዘጋጅዎቹ ታሪክ እሚፈልገው የሰው አይነትዎች መሀከል ይመስሉኝ አለ። ጋዜጠኛነት ይልቁንም ዐምደኛነት እንደ እዚህ በአማርኛ ቀርቦ እሚአብበው እኛ ሀገር ከስንት አንዴ ነው። ሊያውም በቀኃሥ. እንጂ እንዲህ ጀግና ጋዜጠኛዎች ማደግ አልተፈቀደልአቸውም ነበር እና በቅርቡ እነእሱን አይነት ሙያተኛ ኖሮን አያቅም። እነ እርሱ ግን በዓለም ተነዝተው ከአዉስትራሊያ፣ አዉሮፓ እና ሰሜንአሜሪካ ድረስ በ አሉ ጽንፍአማ የዕለት ሰዓት ልዩነትዎች ተጽዕኖ ሳይወድቁ በ እየእለቱ የኢትዮጵያ ስነዉሳኔአዊ (ፓለቲካል) ዉሎአዳርን ከእያሉበት በመከታተል በመመርመር እና በሰከነ መከራከር፣ ድንቅ መሆን እንድንችል በእኛ ምሽት ተዘጋጅተው ሁሌ ይቀርቡን አለ። አስበህዋል የሰዓት ልዩነቱን? በ አሉበት ሃገር ሌሊት ነቅተው እሚአዘጋጁት እና እሚከታተሉት ነገር! እኛ ሀገር ቀን ሲሆን እሚከወን ቤተእንደራሴ-ጉባዔ እና የመንግስት መግለጫዎች ለእነእርሱ የሌሊት ጉዳይ ሆኖ መብዛት። ብዙ ለመዘጋጀት ሌቱን ቀን፣ ቀኑን ሌሊት አድርገው በእኛ ማምሻ በግርማሞገስ ተሰይመው ይቀርቡን አለ። ከምንም እሚደንቀው በእዛ ጥረት እና መስዋእትነት ጀርባ እሚመጣው ድንቅ ድባብአቸው ነው። በመከባበር በሠከነ መልኩ ስለሃገር ጉዳይ ገሃድአማአዊነት (ፕራግማቲካል) ጉዳይዎች ላይ ዘመንአዊ ንግግርዎች ሲአደርጉ አማርኛ ‘ኢሃዴግ መመስገን እንደ አለበት ከ ድህረምርጫው ህዝብአዊ ነውጥ በሂወት በመቁሰል ብቻ ያስተረፍንአቸው አንድአንድ የማይመለከትአቸው የጠር ነዋሪዎች ለጣቢአችን ገለፁ’ ከእሚል ጋዜጠኛአዊ አማርኛ ተመንጥቆ እንደ ታደለ ይገባሃል። በአማርኛ፣ ሃሳብ ተፍታትቶ በሰመጠ መጠን ሲገለጽ እና በመከባባር ዉይይይት የአሲከውን ድንቅ ሆኖ እሚያስመለክቱህ ነገር ነው። የእዛ ጫፍ ስኬት ደግሞ ኢሳት ዕለትአዊ ነው፤” ናሆም ኢሳት ዕለትአዊን እንደ አንድ መረጃ ምንጭ ስለ እሚከታተል በተገኘ አጋጣሚ ሁሉ በትምህርትቤት በይነመረብ አገልግሎት ክፍል ከእሚከታተለው ምርአዊ ዝግጅት አንዱ ነው። ከእዛ በቀር ኢሳትን ብዙም አይመለከትም። ‘ውጭ ከአሉት በቀረ ኢሳት ገና ያልተመሰረተ ተቋም ነው፤’ የእነ እዛ ዝግጅት እንጂ ሌላው ብዙም ያደገ አይደለም ይል ነበር። ስምጥ መረጃ ማቅርቡ ላይ ዜናአቸው እንደ ማንኛውም የሀበሻ አማርኛ-ጋዜጠኛነት የተሸራረፈ ሙያ ነው ብሎ ያስብ አለ። በእርግጥ በማፋጠጥ እና መርማሪ ጋዜጠኛነት እዉነት ማዉጣት ላይ ማንም በአማርኛ ሰርቶ ሲሳካለት በቅርቡ ጊዜ አላስተዋለም። ይህ እሚለውም ጋዜጠኛ የለም። ስለ እዚህ የ ኢሳት ዋናው ዝግጅት የዐምደኛዎቹ ትትረት ያለበት ብቻ ነው ብሎ ይገነዘብ አለ። ናሆም ከ ኢሳት በቀረ፣ የጋዜጣዎች ሳምንትአዊ ገረፋ አያመልጠውም። በደረቅ-ቅጂ (ሃርድ ኮፒ) እንደ ቀደመው ዘመን መቶ ዓመቶች ቀድሞ ፈርቀዳጅ ሆነን በዓለም ደረጃ አላባአዊ ሆነ ባቋቋምንው ቤተጦማር (ፓስት ኦፊስ)፣ ዛሬ ባገሪቷ ጋዜጣዎች እንደድሮው ለየከተማው ሲወጡ ተጓጉዘው አይሰራጩም። ነገርግን በየማክሰኞው፣ በትምህርትቤት ጊቢያቸው አንድአንድ ጋዜጣ ስለሚመጣ፣ ከመምህርዎች ሻይቤት በመቀላቀል እራሱን ስላስለመደ እና ማንም መምህር ስለሚአቀው እርሱን መከልከሉ ስለ እማይታሰብ በነፃነት ጋዜጣዎቹን ሁሌ ያሥስ አለ። ይህ ከግል ጥረትዎቹ እጅግ ከፊሉ እንጂ ሙሉው አይደለም፨
በ ሠጠው ሃሳብ፣ መስ በካምፕ ኑሮው በትመ. የዝግጅቱ ታዳሚነቱ ትልቅ ስለነበር፣ አስተያየቱን በመስማማት አቀረበ “አይ እርግጥ የነ ሲሳይ አጌና፣ መሳይ ከበደ፣ ወንድምአገኝ ጋሹ፣ ፋሲል የእኔዓለም፣ ጴጥሮስ መስፍን፣ የመራራ ጉዲና ጓደኛ ግዛው ለገሠ እና በየጊዜው እሚመጡ አቻ ምሁር ወይም በሀገርአዊ እንቅስቃሴዎች ተሳታፊ ግለሰብእዎች በድንቅ ዉይይትአዊ አቅም ሀገርአዊ ጉዳይ ሲአንሸራሽሩ ላገሪቷ መታደል እንደ ሆነእኛም በካምፕ ተሰትረን እምንመለከተው እና እምናወራው ነው። የአማርኛ ወቅትአዊ ስነዉሳኔ ሽፋን ሰጪዎች መሀል፣ በመላ ሀገሪቱ ካሉት እሚልቁ፦ ምርጥዎቹ እነ እርሱ ናቸው። አንድ ቀን ሃገር ሁሉ እሚኮራብአቸው ይመስለኝ አለ። ታሪክ እሚፈልግአቸው ሰውዎች አይነት ናቸው የአልክው ግን እሚገርም ቅጽል ነው። ተመልካችነትህ ተሞርዶ አለ።” ፈገግ ብሎ የመጨረሻውን ነጥብ ሲናገር ተመለከተው።
ሳይታሰብ በሰመጠ ወግ፣ መብሉን እየአጠናቀቁ ሲደርሱ ቢግ በአምላክአዊ ምስጋና መብሉ እንዲቋጭ አደረገ። ሌሎቹም በማድመጥ እንደተሳተፉ መብሉን ጨረሱ፨

ቤተሰቡ በትመ. ምቾት ሲጠመድ መስ እሚ ወደ አለችበት ጓሮ እንደ ምርጡ ሥጦታው አቅዶ ያሰበውን ለመፈጸም ፈቃድ ስለሚጠይቅ ነግሮ የልቧን ለማዋየት ዞረ። እግረመንገዱን ሲያገኛት ትላንት ፊቷላይ ያየውን ስሜት መነሾውን ሊጠይቅ አስቦ፣ አሁን በጊዜው ሲያያት መደበኛ ስለመሠለችው፣ ተራ ነገር ይሆን አለ፣ አጉል ማስጨነቅ እንዳይሆንብኝ ብሎ አለፈው እና ግለነገሩን ብቻ ሊያዋያት ወሰነ፨
እርሷም ቀድማ ገና ከነበረችበት ፊቷን በመታጠብ ሆና እንዳለች ስሴስመለከተው መታጠቡን ትታ ቀና ብላ በመጨነቅ ተቀበለችው። ለብቻው ስታገኘው፣ እንደ ገና በግል ለመነጋገር ብላ በጠቅላላ ስለ እሚአወጣው ወጪ እሚጨነቅ ስለሆነ በማሰቡ ስጋትዋን ገለጠች። መስ ቀላሉን በማየት፣ አጽናንቶአት ወደ ግል ሃሳቡ ገባ። በአጭር ወደገደለው፣ ገለጠው። ባዶ በሆነው የቤቱ ጀርባ፣ አንድ ወይም ሁለት ክፍልዎች ቤት መስራት እንደ አሠበ ገልፆ አብራራላት። እሚ በድንገቴ ሃሳቡ ደነገጠች። ምንም ለግንባታ እሚሆን ገንዘብ በእጇ የለም። የቀረው ብሯ ብሩን ወደ ጊቢ መላኪአ እና ምንአልባት ቢተርፍ የባህል መጠጥ ንግድዋን ካተረፋት በጥቂቱ ለማስጀመሪአነት የታቀደለት ነው። ማገዝ አትችልም። መስ ወጪው አነስተኛ እንደ ሆነ እና በራሱ እንደ እሚገነባ እንዲሁም ፈቃዷ ብቻ እንደ እሚአስፈልግ አበሠራት። የእሚ ዓይንዎች እረጠቡ። “እዴት? አንተ ምን አለህ?” መስ በሁለት ቢበዛ ሦስትሺህ ብር ሁሉን ማጠናቀቅ እንደ እሚችል ነገራት። “በዛ የበግ ግልገል እንጂ፣ በግ እንኳ እማይገዛ ሆኖ እንዴት ሁለት ክፍልዎች ቤት ይገነባ አለ?” መስ በግንባታው ሥራ ብዙ አስልቶ የተዘጋጀበት ስለሆነ በቀላል እንደ እሚሰራው አሳወቃት። “ይህን ካሰብኩ ቆይቶ ነበር። ብዙ ወጭ የለም። እሺታው ያንቺ ከሆነ ስራውን በክረምቱ ሳንቀደም እንጀምር።” እሚ በጭንቀት እንዳይዋጥበት አስባ ብቻ እንጂ፣ በወንድሟ ብልህነት ትምምን ስላላት ለእሚአድጉት ልጆቿ የተለየ ክፍል ብታገኝ ከተቻለም አከራይታ ገቢ ብታገኝ ብላ መልሳ በመደሰት ፈቃድዋን ሰጠች። ወዲአው ግን አንድ ነገር ከነከናት። ይህ ዱብእዳ ትላንት ባይከብባት ቶሎ እሺ አትለውም ነበር። ወይም ትከለክለው ነበር። መጨነቁን ለማስተው ያንን ማድረጓን ግን ድህነት ከለከላት። ከወንድሟ እምቅ (ፖቴንሻል) ጭንቀት ጋሻነት ወደ ግድየለሽነት ስትዘቅጥ ያስተዋለች እንደ ሆነ ገመተች። ድህነት፦ እንዲደፈን ብዙ የኑሮ ቀዳዳ በመቦረታተፍ፣ አንተትብስ-ትብሽን እና መተሣሰብን ከአኗኗር እሚአርቅ ነው። ድህነት ሰብእአዊነት እሚአፈናቅል ፀረ-ፍቅር ነው። ድህነት ኢአፈቃቃሪ ነው። አንገት በመድፋት በዚህ ሃሣብ ጥቂት ተዋጠች፨
መስ የግንባታ ፈቃዱን እንደ አገኘ፣ ናሆም እና ብሩን ጠርቶ ለብቻቸው አድርጎ ዕቅዱን አሳወቀ። ሁለቱም በመጀመሪአ ተደሰቱበት። አደነቁ። በቤት ሃሳቡ ተማረኩ። ቤት ከጓሮ ኖሮ አያውቅም፣ ቢኖር ድንቅ ነው ብለው አሠቡ። ብሩ በአመጣው ወረቀት ላይ መስ እሚደረጉትን ዘርዝሮ በአጭሩ ፃፈ። ዕቅድን ወደ ትግበራ ንድፍ ለውጦ ደግሞ መዘርዘሩን በማስረዳት ቀጠለ። የነ እርሱ መንደር የከተማው ማብቂአ ስለሆነ ከጀርባ ጫካ ብቻ አለ። ከመግቢያው ጥቂት እልፍ እንደ አሉ ብዙ ድንጋይዎች ተከምረው አሉ። ጫካው በእርግጥ የከተማው ወል ባለሀብትነት አለበት። ግን ድንጋዩን እንደማንም መሠብሰብ እንደ እሚችሉ አሳወቀ። ድንጋይዎቹ ዋጋአቸው የሚአያመላልሳቸው የአንድ አህያ ኪራይ ሃምሳብሩ ብቻ ነው። ሁለት ቀኖች ቢዘምቱበት መቶ ብር ማለት ነው። ይህን በቤቱ ዉጭ ቅጥሩን እየተመለከቱ በድንጋይ ምቹ መቀመጫዎች እንደ ጉልቻ ከብበው ተቀምጠው ሲአወያይአቸው ነገራቸው፨
በእዚህ ዕቅድ እነ ብሩ ሃሳብ አጡ። እንዴት ይህን ሊአስብ እንደቻለ ገርሞአቸው ብቻ አለ። ድንጋዩ በእርግጥ ማንም እማይሻው እና በጫካው መግቢያ አካባቢ በቅሎ እና ተቆልሎም እሚገኝ ነው። “መሰብሰቡ ብቻ የእኛ ስራ ነው” መስ ሥራው ቀላል እንደ ሆነ ግን ጥቂት እንደ እሚፈልግ ቀጠለ እና አሳወቀ። ሁለቱም ወጣትዎች ተስማሙበት። ነገ በጎኅ ይህን ለማድረግ ማቀዱን መስ አሳወቀ። ዕቅዱ ፀደቀ። ወደ ቀጣዩ ታለፈ፨
መስ ዕቅዱን ማጋራት እና ለሃሳብ አስተያየትዎች መክፈቱን ቀጠለ። የናሆም ፊት ላይ ጥያቄ ሲመለከት ግን ተመልሶ አብራራ። “እሚጠይቀን የለም። ድንጋይዎቹን አምና በደንብ አጥንቼ ለእዚህ አመት መገንባቱን ስላዞርኩ እንጂ መቼም በቀላል እንሠበስብአቸው አለን።” አናቱን በመነቅነቅ ናሆም ሃሳቡን አጠራ። “አይ ይሄ መሆን ይችል አለ። እኔም ለመውሰድ ባይሆንም አስተውዬው ነበር።” ብሩ ድጋፍ እና ዳግ-ማረጋገጥ (ሪአሹራንስ) ሰጠ። ወደ መስ ዞሮ አድናቆቱን አከለ። “ለእዚህ ማሰብህ ግን ትገርም አለህ! ድንቅ ነው።” መስ ፈገግ አለ እና ወረቀት እና እርሳሱን እንዲሁ አገናኘ። “ችግር ለመፍታት፣ ሩቅ ማየት አያስፈልግም። አካባቢህን ለመለወጥ ብቻ ተነሳ። ብሩህ እና ቀና ከሆንክ ሁሉ ይቀየር አለ።” አስተያየቱን ሲሰጥ ናሆም እና ብሩ ተያይተው ፈገግ አሉ፨
ፍሬጉዳዩን መልሶ ቀጠለልአቸው። “ከድንጋይዎቹ ኋላ ደግሞ ጥቂት ጭቃ እሚሆን አፈር እሚአመጣልኝ እማዘጋጀው አለ። ለርሱ አራትመቶ ብርዎች ከፍለን ያንን እናገኝ አለ። አብሮ እሚቦኩት ደግሞ እምንሸምትአቸው በ ጊዜአቸው ይቆዩን እና፣ ተያያዥዎቹን እንጨትዎች ደግሞ እኔ እምሰበስብበት መንገድ አለ።” “ቆርቆሮስ?” ብሩ ጠየቀ። “ዋና ወጪአችን እርሱ ይሆን እና በጊዜው እምንገዛው ይሆን አለ። በጠቅላላ ሦስትሺህ አካባቢ መደብን።” ፈገግ እያለ የመጨረሻውን በኩራት ጭምር ገለጸ፨
በዉይይቱ መጨረሻ፤ ወደ ነደፉት ተያያዥ ሁለት ክፍልዎች ቤት ምስል ላይ መስ አነጣጠረ፤ “ይህን እንገነባ አለ።” ብሩ በቤቱ ንድፍ የግንብ ግድግዳውን አጤነ። “ካለ ብረትዎች እና ድንጋይዎቹ ግድግዳዎቹ እንዴት ይቆም አለ?” የመስን ሁኔታ በትንግርት ሆኖ ተመለከተ እና በሁሉ ተስማምቶ ድንገት ባገኘው የመጨረሻ ጉዳይ ጥያቄውን አቀረበ። መስ ዕቅዱ እንደ ስነድርድር (ኮምፕሮሚስ) እንጂ በጸና መደበኛ ቅርጽአዊ ምህንድስና እንደ እማይከወን ገለጠ። ቤቱ ጠንካራ እንደ እሚሆን እና ተፈጥሮአዊ ዉበቱ እንደ እሚበዛ አሳወቀ። ግን “ግንብ በብረት ምሰሶ አሽከርነት ብቻ እሚገደብ ነው።” ናሆም ይህን አግዞ ሲጠይቅ ከመስ በቀር ያሉት ጥቂት አቅማሙ። “ሲቢንቶስ?” ናሆም አከለ። መስ ሃሳቡ ትንግርት ቢሆንም እንዲቀበሉት ግዱን አብራራ፨
“እምንገነባው በምሰሦዎች እሚደገፍ፣ መሰረት ላይ እሚቆም፣ ጣሪአ እሚለብስ፣ ምርጥ ደገኛ ቤት ነው። ግን በተለመደው መንገድ በመሄድ በመቶሺህ እሚቆጠሩ ብርዎች ማጥፋት አይጠይቅም። እኛው እምንገነባው ሁኔታዎችን እምናሸንፍበት መንገድ ስለምንፈጥር ነው።”
ወንድማማቾቹ ብዙም ሊአምኑት አልቻሉም። ነገርግን በተለየ ናሆም የመስን ግንባታ ክሂሎት እሚያውቅ ነው። “እመኑኝ። ይህ በይፋ ዲግሪ ስልጠና ባይደገፍ በሙከራ፣ ግል ምርምር፣ እና ዳግ-ምርምር (ሪሰርች) ግን የተደገፈ ነው። በካምፕ ቆይታ ከአናፂዎች እና ግንበኛዎች ጋር ባልዉል ኖሮ በእርግጥ አትተማመኑብኝም ነበር። ግን ደግ ተሞክሮ አለኝ። እናሸንፈው እና ይህን ቤት እናቆመው አለን። ቢአንስ ከእኔ ጋር ሞክሩ እና እዩት።” ብሩ ልክ ከሦስት ሳምንትዎች ቀድሞ ብሔርአዊ ፈተና ተፈትኖ ሲጨርስ ከ ተማሪዎች ጋር በትምህርትቤት አስተዳደሩ ድጋፍ ባህርዳር፣ ጎንደር፣ እና አክሱምን ጎብኝተው ሲመለሱ የተመለከተአቸው ከጭቃ እና ድንጋይ እሚአጋጁ ቤትዎች ድንገት በ ምናቡ ተከሰቱበት። በደብረብርሃን መስመር ወሎ ደርሰው በወልዲያ ትግራይ በመግባት በጎጃም ወደ ፍቼ ከእዛ አዲስአበባ ሲመለሱ ባደረጉት ዙረት ብዙ የሲቢንቶ አልባ ግንብ ቤትዎች ተመልክቶ ነበር። “በእርግጥ ብዙ ገጠርዎች ላይ በጭቃ እና ድንጋይዎች ብቻ ምርጥ ቤት – ጭራሽ ፎቅዎች – አድርገው ይገነቡ አሉ። እንደ እነእርሱ ነው ሃሳብህ?” ግንባር በጉጉት ስሜት በመቋጠር ጠየቀ። “ጥቂት ከዛ ይሻል አለ። ግን እንደ እዛ በለው!” መስ በሂደት ሲያዩት ይመሰጡ አለ በእሚል ለጊዜው ያቀደውን ብሩ በአሳለፈው አጋጣሚአዊ አረዳድ ስለ ተገነዘበ በአጭሩ አሣውቆ ገለጠ። ናሆም ብሩን አንድበል በሚል በኦናነት ሆኖ ተመለከተ። “ምን አይነት ቤትዎች ናቸው የተመለከትህው?”
ብሩ ሻይ ሁሉ ሊጠጡ ገብቶብአቸው የነበሩ ሁለት ቤትዎች ትዝ አሉት። በጉዞው የነበረው ቆይታ አንዱ ድንቅ ጉብኝት እንደአጋጣሚው መሠረት ከሆነ እነ እዛ ቤትዎች ነበሩ። አቻዎቹ ብዙ አላስተዋሉም። ባህርዳርን እና አክሱምን ለመመልከት ብቻ እና ጎብኝቶ ለመመለስ በእዛም የፈተና ድካም ለማቅለል እንጂ ለ ትርፍ ጉዳይዎች አልተጨነቁም ነበር። ብሩ ግን በቤትዎቹ፣ ማህበረሰቡ፣ ነገረ ሁኔታው፣ መልክአምድሩ፣ አየር ሁኔታው፣ ገበያው እና እሚመለከተው ሁሉ ሲደመም እና ሲአጤን ነበር የተጓዘው። ሌላው ከብዙዎች አጢኖትዎች በአንዱ የጭቃ እና ድንጋይዎች ጥምረት የፈጠሩት ግንባታ ትንግርት ማጤን ነበር። እንደውም ከዳንግላ ወጣ ብለው ለጎማ መቀየር ሲቆሙ ከጥቂት ጓደኛዎቹ ጋር ፊትለፊት ሻይቤት አይተው ገባ ብለው ሲቀመጡ የቤቱ ግድግዳዎች ያፈር እና ድንጋይ መጠባበቅ የፈጠሩት ስለ ነበር ስለ ግንቡ ጠይቆ ነበር፨
“ምን ያክል ጠንካራ ነው ግን?” የመናቅ እንዳይሆንበት እንደ ተገረመ እንጂ እንደ ናቀ ሆኖ አልጠየቀም ነበር። ጎልማሳ እመስት አስተናጋጇ የቤቱ ባለቤትም ነበረች። መንደሩ ዉስጥ ሃብታም እንደ ሆነች ጥርጥር የለውም፤ በስፋት ባልተሠፈረበት ስፍራው ምንም እሚሻል ደግ ቤት አልነበረም። “እንዴ! እሄ ዘመንዎች ኢቆየ አለ። ጥንካራ ነው።” በደስታ ሆና ከአንዲት ቡና አፍዪ ቆንጅዬ ልጃገረድ ትልቅ ምስል መለጠፉ በ ዘለለ ብዙ ያላስጌጠችው ግድግዳዎችዋን በመቃኘት ራቅ ብሎ በቆመ መደርደሪአዋ ላይ የሻይ ማስቀመጫዋን ለማስቀመጥ እየ ሄደች ተናገረች። ዞር ብላ ስትመለከተው ወጣቱ ብሩ ግድግዳዎቹን ይቃኝ ነበር። በመረጃ እንዲደሰት ወሬዋ ላይ አክላ፣ አስራአራት ዓመት እንደ ቆየ ስታሣውቅ በአዲስ በላጭ ትንግርት ብሩ አፈጠጠበት፦ ገና ከቶ አዲስ ነበር። የመሠል መለስተኛ መንደርዎች ቤትዎች ሲመለከት እንደ መጣ ከአስተያየቱ ገብቶአት በኪነህንፃ ጥበቡ ተገርሞ እንደ ጠየቀ ገብቶአት ነበር። የእመስቲቱ ዐዋቂነቷ ደግ ነበር። የብሩን መጀመሪአ ስላየው የመነጋገር አጋጣሚ በቀናነት ተገነዘበች እና፣ ትንግርት እንደ ተሰማው አዉቃ ትንግርት ብቸኛነት ስለሆነ ብቸኛነቱን ልትቀፍፍለት እና አንተ ብቻ ይህ አልተሠማህም ብላ ለማገዝ መናገርዋን ቀጠለች፨
“እንደ እናንተ ሲመንት የለውም። ግን ስታወዳድሩት፣ ይህን ወጪም አይሉት፤ የይህ ትንሹ ወጪ ነው። ጥቅሙ፣ አገልግሎቱ እንኳ ብዙም ልዩነት የለው። በኢ ነው! ኧረ በኢ ነው ይህ ለ እኛ መች አነሰ? ስንት ዘመን ሊኖር ነው?!” ብላው ነበር። ከንግግሯ የቤትዎቹን ጥንካሬ እና የእዛ ማህበረሰብ ቀላል አኗኗር ፍልስፍና ተዳብሎ ተገለጠለት። ከፃድቅ አብርሃም “እሜዬ ትንሽ ነው፣ ድንኳን ይበቃኝ አለ” ስነልቦና ብዙ የሸሸ አልነበረም። ተረፈ አገነዛዘብ ሆኖት፣ የከተማ አኗኗር ስልት ዛሬዬን ልጨርስ እንጂ አልጨነቅም ከእሚል ሃሳብ ዘልሎ እንደ ተወሳሰብ አሠላሰለ። ጠንካራ እና ዋጋ ያለው ቅርስ ለልጅልጅዎች መተው ስለ እሚሻ፣ ምቾት እና ደህንነት ስለ እሚአገኝበት፣ ዉበት መገለጫ ስለ ሆነ፣ ርእዮተዓለም መግለጫ ወይም ማንጸባረቂአ ስለ ሆነ፣ አገነባብ ጥበቡ ወደ ገበያ ምንጭነት ዞሮ መገንባት ስለ ቀለለ፣ በሸማችአዊ የፉክክር ስሜት ኪነህንፃውን ተወዳድሮ መግዛት ስለተለመደ፣ የልክኖታ (ሪኮግኒሽን) ማግኛ ሆኖ ጎዶሎነትን በቁስ መሙላት አማራጭ ሆኖ ስለ ቀረበ፣ ብቻ በአንዱ ወይም ሌላዎቹ መንገድ(ዎች) የኪነህንፃ መመንደግ በከተማ እንደ ተወሳሰበ አሠበ። የአኗኗር ፍልስፍና መለያየት ግን የእዚህ ሁሉ መለያየት ኋኝነትአዊነትዎች (ፖሲቢሊቲስ) እንደ ተጠነሠሰ ተረድቶ ነበር፨
ብሩ የእዛ ሃሳብ ጠርቶ ሲታወሰው አሁን በቶሎ የልዩነት አረዳዱ ነገር በእራሱ ሂወት መጥቶ አስተዋለው እና ተደነቀ። በእርግጥ አሁንም አጢኖት በመከወን ጥቂት አሰብ አድርጎ የቤት ምስጢሩን ፈለገ። ዞሮዞሮ ለአናት ኮፍያ እንዲሆን መጠለያ ማበጀቱ መሠረቱ ነው። አሁን በእነእርሱ አኗኗር የዘመነ አገነባብ አገልግሎት መቅጠር እሚቻል አይደለም። አማራጩ፣ ሁለት ነገርዎች አጣምሮ ከተቀበሉት ፍቱን ነው። አንድኛ በቤቱ እሚአሰጋ ነገር ላይኖር እንደ እሚችል ከተረጋገጠ በቂ ነው ብሎ ማመን። ሁለትኛ አኗኗርን አቅልሎ እንደ ገጠርዎቹ ሰውዎች መዉሰድ ይገባ አለ። ሁለቱ ሲጣመሩ በጭቃ ምርጊት ድንጋይዎች እና እንጨትዎች ደንበኛ የግንብ ቤት ሊሰሩ ይችሉ አለ። ስነልቦናም ሊፈቅድአቸው ይችል አለ፨
በሩ ይህን አዉጠንጥኖ ልክ በመስማማት ሲጸና፣ ናሆም መሰል አገነዛዘብ ከ እራሱ አለም አንፃር ይዞ መጣ። “በእርግጥ የጎንደር አፄ ፋሲለደስ መንፈስ አዳሽ ቅጥርጊቢ ዉስጥ የተቀመጡት ቤትዎች በእንጨትዎች የተዋሃዱ ዘመንአዊ ሴመንት-የለሽ የድንጋይዎች መጠባበቅ ነው። እዚ ዘመን ድረስ እልፍ ሰው አለ ማቋረጥ በፎቆቹ እየረገጠው በመጎብኘት ምንም ሳይሆን ደርሶ አለ። በርግጥ አሳፋሪ የቀለም አለመገጣጠም ባለበት እድሳት አንድአንድ ሥፍራዎቹን ሲአድሱ ተመልክቼ አብሽቀውኝ አለ። አሁን ነጥብአችን ግን፣ የኛ ቤትም ከተገነባ፣ ሃያ አመት ቢአገለግል..” ያሰበውን ለመናገር እየአቅማማ ቀድሞ ፈገግ አለ። “እኛ እንደርስለት አለን! አፍርሰን እንገነባው አለን።” አፍርሰን ሲል በሃዘን መስን ተመለከተው እና ዝቅ ብሎ አቀረቀረ። መስ በፍጹም መረዳት ፈገግ አለ። “አዎን!” ብሩ የሃሳቡ ደጋፊ ሃሳብ ሲመጣ ተደስቶ ዳግ-ተስማማ። “ዋናው ጠንከር አድርገለን ለሃያ ሠላሳ አመትዎች ማቆም እምትችል እንደ ሆነ ታምን አለህ ወይ ነው? ማለት ነው!” ብሩ ወደ መስ ነገሩን ጠቅልሎ ጋል ያለች ፀሐይ በመሸሽ ከተቀመጠበት እየተነሳ ጠየቀ። መስ ፊቱን በደስታ እና ወታደርአዊ ምርአዊነት ዉህደት ከትቶ ጥርስ በመንከስ ተናገረ። “ከ አለ ጥ.ር.ጥ.ር!”
በ እርግጥ የገጠሯ ነጋዴ እመስቲቱ እንደ አለችው ሃምሳ አመት ሁሉ መቆየት እሚችል የኪነህንፃ ዉቅር የእሚአገኝ ንድፍ እና ንድፈ ሃሳብ ያለው ነበር የመስ ሃሳብ ም። የአኔ ሻይ ቤቱ ዉስጥ ዛሬ ከተማዎች ከ ሰረቁት፣ በገጠሩ አካባቢዎች ታዋቂ ከሆኑት ክብ መቀመጫዎች – ኩርሲዎች – በአንዱ በቅጽበት ተቀምጦ ተደግፎ ልክ እመስቲቱ ጓዳ የሻይ እና ይዘው እሚሄዱት ጮርናቄ መልስ ይዛ ልትመለስ ስትገባ ሆን ብሎ በመደጋገም በጀርባው በአቅም እየደለቀው በመጠኑ መርምሮት ነበር። እንደ መደበኛ ቤት እማያሰጋ ጠንካራ ነበር። ስለ እዚህ የመስን አማራጭ ከባዶ እሚሻል ቤት ለማለት አልደፈረም። ከተማ ስለዘመነ እንጂ የእዛ ቤት አገነባብ ጥበብ ያነሰ እሚሆን ነው ብሎ አላሰበም። ጭራሽ አኗኗርአቸውን እንዲአጤንበት እና ማንነትአቸውን እንዲፈልግበት አገዘው። ከገጠር በደሳሳ ጭቃ ምርጊት ሣርጎጆ ቤት መኖር ወጥተው ወጡ። ዛሬ ድረስ የተለየ ያጋበሱት ሃብት የለም። ከሃብት አንፃር ከተማ ይግቡ እንጂ ልክ የገጠር ሰው እንደ ነበሩት ናቸው። የገጠር ማህበረሰብ ወደ ከተማ ፈልሶ ሲመጣ አብዛኛው የከተሜ ቤት በመገንባት ተጠምዶ ለከተሜነት መሰላው እጅግ ይቸገር አለ። እርሱ እና እነ ናሆም ምንም ከተማ ቢገቡም፣ ከተማው ደግሞ ከተሜ ኪነህንፃ ቢአስመለክትአቸው እና ባጠገቡ ሲኖሩ አባል ሆነው ከተሜነት ቢሰርጽብአቸውም ያላስተዋሉት ግን ድሃ እንደ ሆኑ ነው። ስለ እዚህ በሰው ቤትዎች እና አጥርዎች መመልከት እራስን ከተሜ ማድረግ እንደ እማይችሉ መረዳት እንደ አለብአቸው አመነ። ከገጠር ወጥቶ ከተማ በመፍለስ ከተማ መግባት እንጂ ከተሜነት የግድ የለም። በዉሸት ግለ-አታሎት (ሰልፍ ዲሰፕሽን) ቤት ደሳሳ ጎጆ ሆና ከተማ እምንገኝ ቢሆንም ከተሜ ግን አይደለንም። ቢአንስ ሙሉኛ። ከተማ የወደቀ ገጠሬ ነን። ከተማ ገብተን ከተሜ መሀከል ከመኖር ወደ ከተማ ገብቶ ከተሜነት መቀላቀል ሙሉ የከተሜ ወግ መሰብሰብ ይገባ አለ። እሚ ግን አቅም ስለ ሌላት ልጆቿ በገነዛዘብ እንኳ ሊነቁ እንደ እሚገባ እና ሃቅ መቀበል እንደ አለብአቸው አመነ። ያንን ሲአደርጉ ይህን ቤት ገንብተው መኖር ማሰብን እና መከወኑን መቀበል ይችሉ ዘንድ ታናሽነትአቸውን ተመልክተው አሉ። መኮፈስ ቢያያዙ፣ ከተሜ ቤት መፈለግ ይከብድአቸው ስለሆነ አለ ተጨማሪ ቤት ይቆዩ አሉ። ግን ማመኑ ለአቅም እሚመጥንን ወደ ማግኘት እንዲደረስ የስነልቦና ገደቡን ይፈለቅቅ አለ። መነሻ እንጂ መፈፀሚአ ያልሆነ ስለእሚሆን ደግሞ ልጅዎች እንቆቅልሽ ሲጫወቱ “አልተዋጠ የእሚዉጥ ምንድነው?” እሚሉት “ኩራት”ን መዋጥ አስቸጋሪ አይሆንም። ናሆምም በግሉ ተመሳሳይ ሃሳብ አዳበረ። ‘ቀላል ሂወት ለቀላል ሰውዎች’። “ዋና ው መገንባቱ ነው!” የግራ እጁን ጠቋሚ ጣት ከታች ወደ ላይ እያወናጨፈ ሙሉኛ ተስማማ። ናሆም በብሩ ሙሉኛ ድጋፍ ደግ አመክዮ ካለ ለማወቅ ሻተ። “እዉነት?” ብሎ ጠየቀ። “አዎን!” ናሆም ኑሮ ማስላት ቢቻል ቀላል ኑሮ እንዳላቸው እና ቀላል እቅድ ይዘው ምንም ነገር መጀመር እንደ እሚችሉ አዉጠንጥኖ ለቤቱ ሳይሆን ለምንም ነገር ምንም የሌለአቸው ስለ ሆኑ ምንም ነገር እሚሻል ከሆነ ከእርሱ እሚሻል እስኪመጣ ደግሞ አመስግነው እና ታግለው መቀበል እንደ አለብአቸው አመነ። ቀኃሥ. ‘ከ ንጉሥ መወለድ ጀብዱ አይደለም። እራስን እንደ ንጉሥ አድርጎ መዉለድ ግን ጀብዱ ነው!’ ያሉትን አሰበ። የእሚ እና ታናናሽዎቹንም ሁኔታ አሰበ። እሚ ብቻዋን ከልጆች ጋር የአለች ናት። እርሱ እና ናሆም በቅርብ ወደ ጊቢ ይቀላቀሉ አለ። ግን ልጅዎቹ ቢአድጉ እንደ እነርሱ በተጣበበ ቤት ባይሆን ብሎ ተመኘ። ነገርግን አቅም ስለ ሌለ በዝምታ ዘልሎት እንጂ አንድ ሰሞን በተለየ ከንክኖት የነበረ ጉዳይ እግር አዉጥቶ አሁን መጥቶ ስለ ሆነ መቀበሉ ግድ እንደ ሆነ አሰበ። “ነገር ሲከብድ እጅአጣጥፎ ከመቀመጥ ለስነድርድር እምንችለውን ለማድረግ እና እምንችለውን ለመቀበል አንስነፍ።” በማለት ጠቀለለው። እና እንደ አልአችሁ በእሚል ትከሻውን እርሱም በመስማማት አንቀሳቀሰ። መስ መስማማትዎቹን ሰበሰበ እና ቀጣይ ነጥቡ በቤቱ ጉዳይ እሚ ብዙ እሚነገራት እና እምትጨነቀው የለም እሚለው ሆኖ በአንድነት ወዲአው ተስማሙበት። ነገሩ በንድፍ፣ ዉይይትዎች፣ እና በከፊል የተገለጡ ዕቅድዎች፣ በቂ ሆኖ እሚበልጥ እስኪገነባ አገልጋይ ሊሆን ታሰበ። ማን ይቃወመዋው አለ? ሁሉም ተስማምተው ለየግልአቸው በደስታ ስሜት ተከብበው፣ ለነገው በቀጠሮ ዉይይቱን ቋጩ፨

ብሩ ወደ ጓደኛው ዮስ ተደዋውሎ በማያረካው ግን ብዙም አማራጭዎችአልባነትአቸው የተነሳ እሚአዘወትሩት የ ፋሲካይት ኅዋአዊከተማ በይነመረብ አገልግሎት ለመገልገል፣ የወጣትዎች አማራጭ ከተማው ስለሌለው እንደ ወትሮው ሰርገው ሊገቡ ተቀጣጠሩ እና ቤት የነበሩትን በሰላምታ ተለይቶ ወጣ። ሰዓቱ ወደ አራት ከግማሽ ሲል መስን እንዲሁ ተሰናብቶ፣ ናሆም ወደ አቀደው ሌላ የክፍለ ዕለት እንቅስቃሴ ተሻገረ። ወደ ጓደኛዎቹ ሩት እና ዓሊ ቀጠሮ ለመድረስ፣ ወደ ሩት ቤት ቀድሞ ለመሄድ አዘገመ። ሁለቱ ጓደኛዎች ከናሆም ጋር፣ ፍኖት ማህበረ-ንባብ ን መስርተው ከሰባት የክፍል-አቻዎችአቸው ጋር በሃያአንድ ቀንዎች አንድ መጽሐፍ በግል በማንበብ ተገናኝተው በእየእሁድ ከሰዓቱ በመወያየት እሚገናኙ ነበሩ። በሂደት፣ ሩት እና ዓሊ ደግሞ ከሰመጠ ጓደኝነት ላይ እራስዎችአቸውን አገኙ። ሦስቱን የበለጠ ያቀራረበ ደግሞ ለወደፊት ያቀዱት ህልምዎችአቸው ጎን የጠነሰሷቸው መስመረ-ተግባርዎች ነበሩ። ሁሉም በግብርና ጥናትዎች ዣንጥላአማነት እሚጠለሉ ጉዳይዎች አካባቢ ትልቅ ተስፋ ስለው የ ነበሩ ታዳጊ ወጣትዎች ነበሩ። ዘንድሮ፣ በዓመቱ የትምህርት ማብቂአ ተገናኝተው ስለጊዜ መንጎድ እና በቃ መለያየትአችን ነው በእሚል ተገርመው ሲወያዩ ወደ አንድ አገነዛዘብ ደርሰው ነበር፨
በ እርግጥ ጊዜ እየነጎደ ወደ አስራሁለትኛ ክፍል ተሻገሩ። እና ምንድነው ብለው በጨዋታው መሀከል ስለቀጣዩ ዓመት ፍቺ በፍራቻ ተወያዩ። አዲስ የህይወት ምዕራፍ ሊከፈት እና የለመዱት የሁለትኛ ደረጃ ሂወት መጨረሻው እና መሪው ሲሆኑ ትንሽ በታዳጊ ስነልቦና ደነገጡ። “የአው ትልቁ ፈተና ቀጣይ ዓመት አለ።” ሩት በእማያረካ አንገትበላይ መልስ መለሰች። በጸጥታ ታለፈች። በተየ ዓሊ ጭንቀቱ አንድ ነገር ዙሪአ እያብከነከነው ነበር፨
ትንሽ ቆየ እና አሁንም ዓሊ ድንገት አንድ የሃሳብ ጠጠር መታው። የላላ ነጭ ቆቡን ወደ ታች ግንባሩ እየጎተተ “ቆይ ጊቢ ስንገባ ስ?” በማለት ወደ አሰበው ነጥብ በመጠየቅ እነእርሱም እንዲደርሱበት በአንጎልመምራት ሊአደርስአቸው አሰበ። ሩት ቀጫጫ ሰውነ፣ ጠይም መል፣ አጠር እሚለው ቁመቷ፣ ከሹፈት እና ማላገጥ ጸባይዋ ጋር ተስማምተው ያሉባት ነበረች። አሁንም ቁምነገረኛ እንደ ሆነች ሁሉ በማሾፍም እሚችላት አልነበረም እና “ከ እዛ እማ መመረቅ ነው ምን አዲስ አለ! ሳትመረቅ፣ ዛሬ መጋባት አማረህ ወይ?” አለች። ናሆም ሲስቅ ዓሊም ሳቀ እና ቆይቶ ጥረቱን ደገመ።
“አስቡት! የምሬን ነው። ተመረቅን! ከእዛ ስ?” ሩት በጠይም ፊትዋ ነጭ ጥርስዎች ብልጭ አድርጋ ጨዋታ ቀጠለ ች። “ቆንጆ ባል መፈለግ ነዋ!” ከሣቀ በኋላ፣ ዓሊ አሁንም በመናደድ ተቆጣት። መልሶ “ማነው ዛሬ ማግባት ያማረው?” ብሎ እየተመለከታት ሳቀ። አፍታ ወሰደ እና ተመለሰ “አይደለም! ከምሬ ነው! የሥራ ጉዳዩን አስቡት። ምንም ብሩህ ነገር የለም። ተመርቀን ግን ሥራ ፍለጋ ነው። ከእዛስ? እቺ እንደ አለችው ድንገት ወደ ትዳር ይኬድ አለ። በቃ አያፈናፍነንም፤ አያልፍልንም። እንደ መንጋው ለሆድ በ መሯሯጥ ልናረጅ ነው።” ሃሳቡን ዓሊ አስተንፍሶ መልሶ ረጋ አለ። አሁን ነጥቡ ሊታይአቸው እንደ እሚችል ገመተ። ለመጀመሪአ ጊዜ ሩትን በፈገግታ ወደ ሃሳብ ስትሰርግ ተመለከተ እና በተራው ፈገግ አለ። በፈገግታው ብቻ እንደ አበሸቃት አሰበ፨
“እና ወደ ሰማይ ማርረግ ፈለግህ እንዴ?” ሩት ከሃሳብ ተመልሳ ወደ ቀልድ ስትሄድ ናሆም ሳቅ ብሎ ግን በቀረበው የሃሳብ ማጥመጃ ተሳበ። ዓሊ ብሽቅ አለ። “ወሽመጥሽ ይቆረጥ!” ዓሊ በመራገም መንፈስ ሲመለከታት ሩት ዓይንዎቹ ሰለምለም ያሉ መሰላት። “እንደ እርሱ አትየኝ ብዬህ ነበር!” በሌባጣት እየተቆጣች ነገረችው። ናሆም አላስተዋለም። “እና ምን ይደረግ ነው እምትለን? እንነግድ እና ሃብት እናፍራ?” ናሆም የሃሳቡ ጉዞ ወደ እዛ ከሆነ ለማወቅ ሲል ለማጥራት ጠይቀ፣ ዓሊ ሃሳብ መልሶ አሰብ አድርጎ አጭር ዳለቻ ሱሪውን ወደ ታች ወረድ ወረድ አደርጎ ሳበ። አሁንም የሩት ጉንተላ ሰለባ ሆነ።
“ምን አሳጥረህ ለብሰህው ገና ትጎትተው አለህ? ፌስታል መሰለህ እንዴ እምትለጥጠው?” መልሳ ወደ ጨዋታ ገባ ች። ዓሊ በከፊል ልብ እየአሰበ በከፊል ልቡ ሳቅ ብሎ “ከአንቺ ዉዬ ለምዶብኝ!” ብሎ በአቻ ጨዋታ መለሰላት። ብዙ ጊዜ ከላይ እምትለብሰው ልብስ ሆን ተብሎ ስለ እሚአጥር ወደ ወገቧ ለጥጦ መጎተቱን ታዘወትር ነበር። በእርግጥ ሁሉም በድርጊቷ ይዝናናበት የነበረ ተግባርአዊ-ፌዝዋ ነበር። እራስዋን ጨምሮ። ዓሊ ክብ ፊቱን በራ በማድረግ ሃሳቡን በቀልድ መሀል ስለ ደረሱበት ቀጥሎ በግልጥ አቀረበው “አይ። እሚመስለኝ በመማር ግን ወደ ግል ዓለም መዉጣት እንጂ ወደ ስራ ፍለጋ መቅለጥ የለብንም ባይ ነኝ።” ሩት አሁን ፈገግ ማለቱን ጉያዋ ከትታ አሰበች። ዉይይቱም ቀጥሎ በግል ለመስራት ሁሉም በጥሬው ማለሙን ተያያዙት፨
በ ንጋታው አንድአንድ ጉዳይዎች ለመጨረስ ወደ ትምህርትቤቱ ሲሰበሰቡ ወሬውን ከአቆሙበት ቀጠሉ። ወደፊት በተማሩበት መስመር፣ የዕዉቀት አገልግሎት የመነገዱ ሃሳብ ከመደበኛው አኗኗር ካወጣ በእሚል ሩትን ጨምሮ አሳምኖ በሁሉም ተብሰልስሎ ነበር። ዓሊ ተንጠልጣይ ሃሳብ አቀረበ። “ዛሬ እማንጀምረው ከሆነ ደግሞ፣ ዛሬ አጥርተን አቅደን እማንፈትነው ከሆነ ደግሞ፣ ይህን ነገር ግን ወደፊት ከመሬት ተነስተን ለ ማማሳካት ይከብደን አለ።” ብሎ ጀመረ። ሩት በምርአዊነት ሆና እንዴት እንደ እሚከወን ስለ አነሳው ጠየቀች። ናሆም ከአሰበ ኋላ አንድ ሃሳብ አቀረበ። “ለምን እምንፈልገው ወደ ግብርና እሚቀራረብ ነገር ስለ ሆነበዚህ ክረምት ስንመረቅ እምንከውንአቸውን ነገርዎች በተግባር አንሞክርበትም? ወደ ጊቢ ስንገባ ተግባርአዊ ልምድም ይዘን ስለ እምንቀላቀል እሚበዛ ጥቅም ይሰጠን እና እንለይበት አለን።”
በ ዓሊ ፊት መስማማት ታየ። ሩት ሴትነቷ ቀጥሎ ከሚነሳው ዝርዝር ነገር እንዳይገድባት በመስጋት ሆና እንዴት ያለ ነገር እንደ እሚሆን ለማወቅ ማብራሪአ ጠየቀ ች። ፍላጎቷ በርግጥ የእንስሳዎች ሐኪምነት ላይ ነው። ነገርግን እንሰሳዎች ለማከም ሳይሆን በሁለት ሦስት ድግሪዎች ፈጣን ልዩአማነት (ስፔሻልአይዜሽን) ክወና ወደ እንስሳዎች ተፈጥሮ ምርምር መግባት ትመኝ ነበር። በእንስሳዎች መመራመሩ የልጅነት ጀምሮ የነብስ መስህቧ ነበር። የዶሮዎች ክንፍ ላባ በመንቀስ ቂፍ ከማለት ቶሎ ወደ እንቁላል መጣል እንዲደረጉ ከአየች ወዲህ እናትዋን በተጨማሪ የህፃንነት እንስሳዎች ባህሪ ጥየቃ ታዝላት ነበር። ብልሃት ጥበብ ሆኖ ታይቷት ብዙ ለመመራመር ታቅድ ነበር። በሂደት ብትረሳውም፣ አሁን አሁን ግን የፍላጎቱ ማነወሰራራት ወደ እንስሳዎች ምርምር እንደ እሚአደርሳት ታልም ነበር። ይህ ሙያ በእርግጥ በዓሊ ሃሳብ መሰረት ወደ ፊት እንዴት በተፅዕኖአቸው ለዉጥአቸው ኢምንት ከሆነው የኢትየጵያ ግብርና ዙሪአ መስሪአቤትዎች መቀጠር ዙሪአ እሚለያት ግለ-ቀጣሪት እንደ እሚሰጣት አላወቀችም ነበር። በበይነመረብ ስትጎረጉር አድራ አንድአንድ ሃሳብዎች ግን አግኝታ ነበር። ናሆም ደግሞ በእፅዋትዎች ግብርና እሚሳብ እና ገበሬ በ መሆን ዘመንአዊ የግብ-ንግድ (አግሮቢዝነስ) ቱጃርነት መመስረት ህልም አለው። ብዙዎች በግብርና ፍሰተንዋይአቸው ቢሊየነር ሲሆኑ አጥንቶ ተመልክቶ አለ። ከበይነመረብ የሰበሰበው መረጃ ብዙ ስለ ግብ-ነጋዴዎች አስተምሮት ነበር። ለ ምሳሌ የቡሽ ቅጠል ያገኘችው እና ለወይን መክደኛ አድርጋ የፈለሰፈችው እንስት በዓለም ወይን ንግድ ጣዕም ሳይበላሽ መክደኛ መንግድ አምጥታ ከ አበረከተችው አስተዋፅዖ በተጨማሪ ቢሊየነር የሆነችበት ሁኔታ የግብርናው (ተክልዎች) ዓለም ከተጠና በአንድ ቅጽበቱ ሂወት እና ሃገር ለዋጭ እንደ ሆነ የተማረበት ነበር፨
ይህን በግብርና ዕዉቀት ወደ ሃብታምነት መቀየር ከአስተዋለ እና አጥርቶ ከአቀደው በእርግጥ ብዙ ቆይቶ ነበር። ገበሬነትን ከምንጩ በልጅነቱ ተመልክቶ እልፍ ያልዘመኑ ጉዳይዎች ተመልክቶ፣ በሃዘን ይታዘብ ነበር። በግሉ በአጠናው የአልተሰደረ ዕዉቀት ደግሞ ብዙ ማሻሻያዎችን አድርጎ በልዩነት ፈጣሪነት ይህን የሀገርአቀፍ በሽታ በልዩነት ሊቀላቀል ገና ከበፊት ይፈልግ ነበር። ገጠር በልጅነቱ ገበሬዎች ከጤፍ እና ስንዴ ወይም ጥቂት ሰብልዎች በቀረ ብዙ እንደ እማያውቁ ተገንዝቦ ነበር። የቀይሥር፣ ካሮት፣ እና ቆስጣ ተክል ፍሬአቸው ከየት እንደ እሚገኝ እንኳ መልስ እሚሰጠው አልነበረም። ጤፍ እና ጤፍ ብቻ ነበር ወሬው። በዉሃ ዉስጥ ብቻ፣ አፈር ያልነካው ሰብል ማብቀል እንደ እሚችሉ አያውቁም ነበር። ምዕራብአፍሪቃ ዉስጥ ደግሞ የተደነቀች አንዲት እንስት በጠባብ ቤቷ መሬት እንደ ናፈቁ ለመብልነት እሚደርሱ ሰላጣዎች በመደርደሪአዎች አሳድጋ ብዙ ገቢ ስትሰበስብ ጎርጉሮ ተመልክቶ ነበር። ገበሬዎች ግን ከብበውት ሌላ ሂወት ይዘው ባያሳዩትም፣ እስቲ ከበቀለ ብሎ ፓፓያ እና ፍራፍሬ ዘርዎች መበተን እንጂ የማጎንቆሉ ጥበብ እንኳ አይገባቸውም። ፍሬው ሳይደርቅ ጤፍ እሚዘራ ሳይሆን ሌላውንም ፍሬ እንደ እዛ አለመመልከትአቸው የጭንቅልአትዎችአቸውን ነገረሥራ እንዲአጤን ጋብዞት የአውቅ ነበር። ብቻ ብዙ ችግርዎች ሲመለከት በገደብየለሽየ መስራት እና ዉጤት የመጨበጥ ፍላጎቱ ተገፋፍቶ፣ ከፍተኛ የዘመንአዊ ግብርና ፍቅር አድሮበት ከልጅነት ጀምሮ አድጎ ነበር፨
ዓሊም በስነህይወት ትምህርት እሚነሆልል ታዳጊ ወጣት ነበር። ትምህርቱ ከመሬት ተነስቶ ይቀናው ነበር። ዕዉቀቱ ከ መምህርዎቹ ይበልጥ እንደ ነበር ብዙዎች ይስማሙበት ነበር። በቡድን እርስለእርስ መማማር መርሐግብርዎች ተማሪዎች ሲመደቡ እርሱ ሁሉም እሚስማሙበት የስነህይወት ትምህርት ማስረዳት ኃላፊነቱን ይወስድ ነበር። ከእዚህ ተያይዞ፣ ወንድ አያቱ የባህል መድሃኒት ልምምድ ስለነበራቸው በለጋ እድሜው በሽተኛዎች አያቱን ፈልገው ሲመጡ እና አመስግነው ሲመለሱ እየተመለከተ ይማረክ ነበር። አያቱ ብዙ ሳይቆዩ በዘጠናስድሥት ዓመትአቸው በቅልጥፍና እንደ ነበሩ ቢአርፉም ያን አድጎም በማስታወስ እና ማስተዋል በግብ-ህክምና (አግሮ-ሜዲሲን) መሳተፍ እሚአቅድ ሆኖ እራሱን አገኘው። ከተክልዎች እሚገኝ መድሐኒትዎች፣ ያመጋገብ ጥበብዎች በመቀመም እና መቅሰም መታከም እሚቻልበት ጥበብ ይመስጠው ጀመረ። ለምን አንድ መብል ስንመገብ እንደ እሚመቸን፣ ሌላው እንደ እሚአቅር፣ ወይም እንደ እማንወድድ ወዘተ. መርምሮ ለመድረስ እሚጓጓ ሆነ። ትልቅ የንዋይ አቅም እና ጉልበት እንደ እሚአመጣለትም አመነ። ለምሳሌ አንዴ የስኳር ወይም አንድ ነቀርሳ በሽታ ማዳን ወይ ጉዳት ማለዘብ ከቻለ እድሜዘመኑን እንደ እሚለዉጥበት እና ባህሉን ከዘመንአዊው ህክምና ዓለም ለማዋሃድ እና ቤተዘመድዎቹን በጥበቡ እንዲአንጹት ለማድረግ መወትወቱን ተያያዘ። ከአያቱ ተግባርዎች በማስተዋል ከስነህይወት ትምህርት ፍቅሩ ጋር በተላከከለት ህልም ጋር ተደስቶ የነበረ ታዳጊ ነው፨
በ ሃሳብዎችአቸው ጥቂት አመንዥኸው ሊገናኙ ለጥቂት ቀንዎች ተለያይተው፣ በቆይታ፣ አሰሳዎች እና ዳግ-ምርምርዎችአቸው ዉጤት ላይ ለመወያየት ለዛሬ ተቃጥረው ነበር – የነገዎቹ መንግስት ቀጥሮን ባንረክስ ባይዎች፨
ናሆም ወደ መሀል ከተማው በሦስት እግርዎቹ መኪናዎች ደርሶ ከሩት ቤተሰብዎች ዳር-መንገድ ሸቀጥ-ሱቅ ተሻግሮ ባለው ጎዳና ደረሰ እና ወርዶ ቆመ። ሩት ትጠባበቀው ስለነበር ለታናሽ እህቷ ሱቁን አስረክባ ወጣች። ብዙም ጭንቅንቅ የሌለውን የዐድዋ ቀኝ-ዘማችዎች መታሰቢአ ጎዳናን ተሻግራ ወደ ሰማይአዊ ሹራብ፣ ከጥቁር ጅንስ ሱሪ እና ጥቁር ሸራ ጫማ የተጫማ ናሆም ቀረበች። ሰላምታ ተለዋውጠው ወደ ዓሊ ቤት በዉስጥ ለውስጥ መንገድዎች እያሳበሩ ተጓዙ፨
ሰዉነት ዋጥቂት ሞላ ብሎ ቁመትም ጨመር ያረገች ያክል ሆኖ ለናሆም ተሰማው። በቀልዶቿ እየተዝናና የባጥ የቆጡን ሲአወርዱ ቆዩ። ከእናቷ ጋር እንደ ናሆም እምትኖረዋ ሩት የቤቱ አራተኛ ልጅ ነበረች። ታላላቆቿ አድገው ሦስቱ ሴትዎች ተድረው በእየሃገሩ ተድረው በመበተን በ ግል ቤተሰብዎች ተጠምደው ነበር። ታላቅ ወንድሟ ደግሞ በ የ ጎንደር ኅዋአዊከተማ ዉስጥ የመደበኛ ምህንድስና (ሲቪል ኢንጂነሪንግ) አራትኛ ዓመት ተማሪ ነበር። ሩት ከሁሉ የላቀ ትምህርትአዊ ብስለት አሳይታ በስኬት አሁን ወደ መሰናዶ ማብቂአ ዓመቱ ገብታ ነበር። በጸባይዋ ተጫዋች ቀልደኛ ቀና እና በሴትነቷ ከሰብእአዊነት ቀለም መዝቀጥ እና መገደብ እማትሻ ስለነበረች በግለትምምን (ሰልፍኮንፊደንስ) ማደግዋን ተይዛ ነበር ከጉርምስና ቀጥላ በእዛው ነፃነት ወደ ሴትዎች የመቀበር ዓለም ሳትቀላቀል በንቅዓት ያደገችው። ጓደኞቿ በተራ መንደርተኛነት እሚብሰከሰኩ ሴትዎች አይደሉም። ከማንም ጋር በነፃነት ትልልቅ ህብረትዎችን በመፍጠር፣ በመመራመር እና በማወቅ እንዲሁም በመዝናናት መንፈስ ነፃነትዋን አዉጃ እና አስከብራ ምትኖር ታዳጊ ወጣት ነበረች። የቤት ዉስጥ እና ቤተሰብ ጫና ስለሌለባት ደግሞ ነፃነቷ አልተነካም ነበር ነበር። ናሆም የነፃነት ስሜቷ ስለእሚማርከው ሁሌ አድናቆቱን ይቸራት እና ትግሏ በትልቅ የሂወት ክፍል እንደ እሚጥላት እና ከመደበኛው ንስት እምትለይ እንደ እምትሆን ጨምሮ ይነግራት ነበር። አያይዞ የነገር ማቅለል ባህሪ ዋ ይመስጠው እና በእዛው በነገራት ነገር ስትቀልድበት ይበልጥ ይማረክባት ነበር። ሁሌ ትቀልድ እንጂ ቁምነገሩን ግን አትዘነጋም። እርሱ እሚላትን ነገር ያው ቀድማም እየኖረችው ስለ ነበር መወያየቱ ብዙም አይታያትም ነበር። ቆፍጣና እና ነፃ ሆና በመራመድ ላይ እንደ እምትገኝ ታውቅ አለች። ብቻ ከስኬትአማ ሂወት አያያዟ ይሻገር እና ናሆም ስትቀልድ ደግሞ የበለጠ ይደሰትበት ነበር፨
ቁምነገር አልፎአልፎ እየተወራ ብቻ እንጂ፣ ጨዋታ ከአልበዛ፣ ከእርሷ ጋር መዋል የለም። አሁንም በቀላል ነገርዎች ሲጨዋወቱ ወደ ዓሊ ቤት ከከተማ ው ደቡብ ጠረፍ አካባቢ ደረሱ። ዓሊ የመጨረሻ ልጅ እና ቤተሰብዎም አብዛኛዎቹ ነጋዴዎች ሆነው ከእናት እና አባቱ ጋር እሚኖረው ብቸኛ ልጅ ሆኖ ነበር። በግንብ የታነፀ ቅጥርግቢአቸው ላይ ሲደርሱ አረንጓዴ ቀለም ተቀብቶ የአሸበረቀ ትልቅ የጊቢ በር ላይ አንቀበቀቡ። ዓሊ መጥቶ ከፈተ እና ሰላምታ ሰጥቶ ወደ ዉስጥ አስገባአቸው። “ቆያችሁ ምንው። ቀጠሮ አይከበርም እንዴ?” ሲል ሩት “ቤት ማንም የለም ስለእምትል መጣንልህ! ሌላ ምን ፈለግህ!” ብላ ሳቅ በማለት ጠየቀችው። “የኔ ባትሆኚ እኮ ይቆጨኝ ነበር ጓዴ! መልስ እማታጪ ጀግና!” እየአለ ዓሊ ወደ ሳሉኑ ጋብዞ አስገባአቸው። በበሩ አቅራቢአ በቤት ዋ እምትኖረው ነጭ ድንክዬ ዉሻ እነ እርሱን ለምዳ ከመጮህ ወደ ማጫወት ተመልሳ በዓይንዎች እስኪገቡ ሸኘችአቸው። ወደ ሳሎኑ ሲገቡ የተንጣለለው ሰፊ ወለል ላይ ያሸበረቀ ምንጣፍ ዉብ ቁሳቁስዎች እና ጣሪአ አቀፈአቸው። ቤቱን ታላቁ ነጋዴ ወንድምአቸው ገንብቶልአቸው ገና ከገቡበት ሁለት ዓመቱ ነበር። እናቱ ሰሚራ የልጇ እንግድዎችን ተላምደው ይጨዋወቱ ነበር። በሂደት ቤተኛ ሆነው ነበር። ዓሊ ወደ ሶፋው አስቀምጦአቸው አብሮ ተቀመጠ እና ባለአርባ ኢንች ገጽማያ ትመ.ውን በሩቅመቆጣጠሪአው አጠፋ። ሰሚራ ከጓዳ መጥታ ሰላምታ ሰጠ ች። ቀይ ድሪያዋ። ተለያዩ ወርቅአማ ቅብ አበባዎች አሸብርቀው በቀይ ፊቷ ላይ ቦግ እሚል ተፅዕኖ አድርጎ የልጅ-ፊት ቢኖራትም እርጅናዋ ጎላ ብሎ ፊትአቸው በንቅዓት ተንቀሳቀሰች። ቤተሰቡ ቢአረጁም በጤና እና እረጅም እድሜ እሚኖሩ አላባዎች የነበሩት ነበር። ወደ ስድሳአራት ዓመት የተዛወረችው ሰሚራ ንቅዓት ግን ያልቀነሰች የአርባ ዓመት ጎልማሳ ነበር እምትመስለው፨
“ሂድ ቆሎ አቅርብ እንጂ! ያሰላም የአንተ ችግር አይጣል ነው ስ! ዉይ ዓሊ…!” ብላ ማውገዝ አደረገችበት። “ገና አሁን ነው ስ ያረፉት እሞ! ረጋ አይሉም ወይ?!” መልሶ በ መከራከር ወደ ጓዳ ሄደ። ሰሚራ “ልብ የለውም የእኔ ልጅ! ሰው በደንብ አያከብርም!” በማለት ራቅ ባለ ኩርሲ ቁጭ አለች። “ኧረ ትልቅ ሰው ነው ዓሊ!” ናሆም ቀላል የሆነ ጨዋታውን አደራ። “እይ! ያርግለት! ያርግላችሁ ስ!” ብላ ወደ ሩት ዞረች። “አንቺ ሱቅ ደህና ነው ወይ?” አለች። ሩት ፈገግ ብላ “ደህና ነው! ግብር በዛብን እንጂ ደህና ነው!” ብላ የእናቷ ግብር ሃዘን ትዝ አላት። “እይ! በዛባችሁ!? ምን ያሉ ክፉዎች። ነግዱ ስ ብቻ በብርታት። ተስፋ አትቁረጡ። ዋና ያ ነው። ግብር ሁሉን ብር አምጡ አይልም ስ! ትንሽ ደግሞ መቆጠብ ነው! አው! ሲገኝ አለማጥፋት!” ዓሊ ቆሎ በሳህን ዘርግፎ ለእናቱ እየአስያዘ ፈገግ ያሉ እነ ናሆምን ተመለከተ እና እናቱ ጋር ጨዋታውን ቀጠለ። “አንቺ ተይአቸው ስ! ገና አሁን ከፀሐይ ነው የተቡት ይረፉበት አትጨቅጭቂአቸው!” አለ። ሰሚራ የዘገነችውን ጥቂት ቆሎ በመዳፍዋ ሰትራ የአልተለቀመ ያክል መልቀም ጀመረች። “ለአሮጊት ቆሎ ይሰጣል ወይ?! ሸፋፋ! ደግሞ አትጨቅጭቂአቸው ይለኛል! እንግዳ ጥለህ መወሸቅ አለ እንዴ?! ያዙ ያዙ ስ ሩትዬ! ናሆም! ያዝ! ባይጠቅምም ያዝ ስ!” በአጫዋቿ ሰሚራ ጨዋታ እየፈገጉ ቆሎ ማመንዠ ተያያዙ። ሰሚራ ወዲአው ዓሊ ሲቀመጥ አስነሳችው። “አንተ ልጅ ቆሎ ብቻ ይቀርባል ወይ? ኧረ ተ ልብህ ዉን! ሂድ ተነስ ሻሂ አፍላ! ጊዶ! ቁጭ ቁጭ ቁጭ!” ዓሊ መልሶማጥቃት አደረገ። “ሻሂ ጥጄ ነው የመጣሁት! እ! እስተከ አሁን ምን ሰዋጥሽ! እ! ጥጃለሁ!” ከቆሎው ቆረጠመ። ሰሚራም ለዉዝዎች ለቅማ በመብላት ሌላውን መለሰች እና አዲስ ዘገነች። “ቅር አይላችሁም አደል? ልጅ ናቹህ ብዬ ነው እሺ! አው! ጥርስ የለኝ እኔ እንደ እናንተ! እናንተ ብሉ እንጂ እኔ ማ ምን…እርጅና መጣና ድቅን አለ ፊትሽ እባክህ ተመለስ ልጅነት በሞትሽ..ነው!” እነ ሩት ፈገግ ሲሉ። ሰሚራ “ቤቤተሰብ ሁሉ ሰላም ነው?” አለ ች። ሁሉም ሰላም እንደ ሆነ ሁለቱም መሰከሩ። “በሉ ተጨዋወቱስ! ማታ ተኛ ብለው እሄ ስልክ እየጎረጎረ ነገ እነ ሩት ይመጣሉ ዳግ-ምርምር ነው ምናምን እየአለ ነው ያመሸ! እኔ ሻሂው አመጣለት አለሁ። ተጫወቱ በሉ። አይዟቹ!” ፍልቅልቅ ስብእናዋን አስጎንጭታአቸው ወደ ጓዳዋ ገባች። ሩት “እናትህ ደስ ሲሉ በእናትህ! እንዲህ እንደ ቀለዳቹ ነው እምትኖሩት አይደል?” ብላ ጠየቀች። ዓሊ የሩት እናትም ተጫዋች መሆኗን ስለ እሚአቅ “ተይ አንቺ ነገረኛ! ሁሉም እናት ተጫዋች ነው እኔን አትተንኩሽኝ” እየአለ ወደ ጠረጴዛው ላይ የተሰተሩ ወረቀታ-ወረቀትዎቹ ማሰስ ገባ። ሩት ዘና በማለት ጫማዋን አዉልቃ በጠረጴዛው ላይ አንድ እግርዋን ሰተረች። ዓሊ እንደ ለመደው ቆንጥጦ ጎነተላት። እጁን በመጠፍጠፍ አስተወችው። ልማድዋን ስለ እሚአቅ ተዋት እና በመገረም ተመልክቶ በይሁንታ “ዘና በሉ ብቻ!” ብሎ አንዱን ወረቀት አንስቶ እንዲመለከቱት ሰጠ እና እናቱን ከ ሥራ ሊከለክል ገባ። በናሆም እና ሩት መሀከል መቀራረብ ሆኖ በ አንድነት ወረቀቱን ተመለከቱ። በሙንጭርጭር የንድፍ ሳጥንዎች እና አጫጭር ቃልዎች ወደ ሌላ ሳጥንዎች በቀስቶች እየተላኩ ተመለከቱ። ብዙም ባይገብአቸውም ብቻ አንድ ንድፈሃሳብ ዓሊ ሞካክሮበት ነበር። ሻሂ አቀረበ እና አብሮ በቆሎ እየተዝናኑ ወደ ጨዋታአቸው ገቡ፨
“ያሰብኩት ምንድነው?” ዓሊ በወረቀትዎቹ ላይ እየአፈጠጠ መነሻ ሃሳቡን ፈለገ። “አው! አንድ ነገር አሁን በ እዚህ ክረምት እንጀምር አለን! ሁልአችንም በ እምንወድደው የወደፊት ሙያ ዛሬ አንድነገር አድርጎ ለ መበልጸግ እና መሰረቱን ለማግኘት ተግባርአማአዊ (ኢምፒሪካል) ግብዓት እንወስድ አለን። ይህ ደግሞ በ ክረምቱ ማሳለፊአነት እምንይዘው አይደለም። በዕዉቀት አንድ መነሻ ሃሳብ ለማሳደግ ነው። ስለ እዚህ መመርመር እና ማጥናቱን አብረን እናስኬድ አለን። ይህ ደግሞ” ሌላ ወረቀት አነሳ። “አው! መስከረም ላይ ብሔርአዊ ፈተና አመት ሲመጣ በመደበኛ ትምህርቱ ስንገባ አንድ ተግባርአዊ መሰረት በእኛ አንጎልዎች ቤተዋይ ተሞክሮ ቆጥበን እንድንቀላቀል የአደርግ አለ። በመጨረሻ ቀጣይ ዓመት ድህረ-ፈተና መሰል ጥረትን በ ተለቀ ምልዓት ከውነን እምንቆይ ይሆን አለ።” ሌላ ወረቀት አንስቶ ተመለከተ። “አዎ! ጊቢ እምንፈልገውን ለማግኘት ከታደልን ወይም ቀይረንም ቢሆን ስንቀላቀል በላጭ ተሞክሮዎች ስለ አሉን ኃያልነትዎችአችንን እናስቀጥል አለን። በየክረምቱ እምንሰራውን ከአቆምንበት እየቀጠልን፣ ከመመረቅ በፊት በእርግጠኝነት ምንፈልገውን ይዘን ከ ተማርን ተያያዥ የሥራ ዓለሙን ደግሞ በሰፊ ጥናትዎች እናስስ አለን። ከመመረቅ ቀድሞ አንድ በሙያዎችአችን እሚገኝ ደግ ተቋም ገብተን በተለማማጅ-ሰራተኛነት (ኢንተርንሺፕ) እንለማመድ እና ድር ማድራት እንለማመድ አለ።” ወረቀት ፈልጎ አነሳ እና በማጤን ማብራራቱን ቀጠለ። “አዎ! በመጨረሻ፣ ማን ምን እንደ እሚሰራ፣ ገበያው ምን እንደ ሆነ፣ ምን እንደ እሚከትት፣ ምን እንደ ጎደለው፣ ምን ማድረግ እና መቀላቀል እንደ አለብን፣ በየት በኩል መጀመር እንደ አለብን፣ ማን ምን እሚአደርግበት እና ማን ምን አቅም እንደ አለው ወዘተ. አጥንተን ወይ ተቀጥሮ ለ ማገልገል እና ለቀጣይ መብቃት መማር፣ ወይ አዲስ ንግድ ይዞ ሰተት ብሎ ለመግባት፣ ወይ ቀጥታ በትምህርቱ ለመግፋት እና ልዩአማነት ለማዳበር ልንሄድ እንችል አለ ማለት ነው። እንግዲህ።” ወረቀትዎቹን ጣለ እና ዘና ብሎ በመንፈላሰስ ሻይ ፉት አለ። ናሆም እና እሩት በቅራርቦቴ (ፕረዘንቴሽን) ው ተደምመው ጥቂት አሰቡ። ቀላል ግን ደግሞ የ እረዥም ዘመንዎች ንድፍ ሙከራ ስለነበረ ሳቢ ነው። መናቅ እና ማቃለሉን ተወት አድርገው መስመጥ እና ማሰብ መነጋገር ከቻሉ አንድ ቁምነገር እሚፈጠር እንደ ሆነ ናሆም ገመተ።“ሃሳቡ ከ ዛሬ ተነስተን ከአልሆነ በቀር፣ ነገአችንን ነገ ስንደርስ ከአየር ዝቀን አናገኘውም ይመስል አለ!” በማለት አብላላው። ሩት አሰብ አድርጋ “አይ እንደ መነሾሃሳቤ (brainstorm) ደግ እና እቅጭ ነው። ግን በዝርዝር ምን ማድረግ አለብን ነው ቀጣዩ ትልቀ ጥያቄ።” በማለት ጉዳዩን ወደ ማጥለል እንዲራመድ አደረገች፨
“እምንፈልገውን መከወን ነዋ። ለ ምሳሌ አንቺ ለምን ወደ ፉሲካይት ኅዋአዊከተማ ገብተሽ ለምን እንስሳዎች ሕክምና ክፍለትምህርትአቸው አትጎበኝም? የአንድ ሳምንት ስራሽ ይሁን እና እሚመጣውን እንመልከት!” ናሆም ሃሳብ አቅርቦ ሲአግዛት ጥያቄ ቀጠለ ች። “እዴት? ማን ነኝ እኔ? የትም ስንሄድ ከትምህርትቤት የትምህርትቤቱ የትብብር ደብዳቤ ተባበሩአቸው ብሎ ደግፎን እንጂ ከመሬት በመነሳት አይደለም! ማን ነኝ? ከየት መጥቼ ነው ቤተሙከራ፣ ቤተመጽሐፍ ምናምንአቸውን እምጎበኘው፣ የቱ መምህር ነው እሚአብራራልኝ እና እሚአስተናግደኝ?”
የ ሩት ጥያቄዎች ቢበዙም አንድ ዐጀብ ስር ስለ አሉ ናሆም በመጠቅለል ሃሳብ ሰጣት። “የሆነ ሰው እስክትሆኝ በ መጠበቅ ማንም ሳትሆኝ እንዳትቀሪ! ስነድርድር ነው ዓለም! ይግባሽ እንጂ! ከ ሰው፣ ባህል፣ ተፈጥሮ፣ ተቋም፣ ምኑቅጡ ጋር ተደራድረሽ ነው ምትፈልጊውን እምታገኝው! ለምሳሌ በይፋ መንገድ ብቻ ስለ እማይሰራ አላማሽን በ ሌላ መንገድ ተደዳደሪው እና ሞክሪ። የአለ ወረቀት ሄደሽ በ ፈገግታ እና በመግባባት መንፈስ ጨዋታ ጀምሪ እና እስቲ መጎብኘት ይቻል አለ እንዴ በይ? ቤተመጽሐፍአቸው ለጊቢው ሁሉ አንድ ነው። ግን ክፍለትምህርት ተብሎ አንድ ቤተሙከራ አያጣ ስለ እሚሆን ያን ብታዪ ሞክሪ!” ዓሊ ሊአግዛት ሃሳቡን ይበልጥ ገነባላት። “እሱ እማ እንደ እዛ እኮ ነው። አንቸኸ ፈታ የ ደልሽ አይደል እንዴ! አትፍሪ! ሄደሽ ስትጠይቂ ለ ዘበኛው ይሁን ለ ምሳሌ!” ሳቅ አለች። ዘበኛ ምን ሊአደርግ ነው በእሚል። ዓሊ ግንኙነትአዊ ዘዴአማአዊነት (ስትራተጂ) ማብራራቱን ቀጠለ። “የምሬን ነው! ዘበኛው ጋር ሄደሽ አባ ብርዱ ከበደኝ በይ! ብዙ ያዋሩሽ አለ። በመሀል እስቲ እንደው እዚህ ጊቢ ገብቼ ለቀጣይ ዓመት መሰናዳት ላደርግ ነበር። ማን ላናግር በይ! ተጫዋች ሰው እና ሰው ሁሉ እሚአስተናግድ እሚወድድ ማነው? በያቸው። የአለ መታከት ሰፊ ዲስኩር ይሰጡሽ አለ! ስለ ተነገረሽ ሰው ማንነት፣ ስም ትርክት ጠይቀሽ መረጃ ሰብስቢ! የተሰጠሽን ተቀብለሽ አመስግነሽ አጫውተሽ እጅ ነስተሽ ወደ ተባለው ሰው ሂጂ!” ሩት ፈገግ አለች። ምን ተጫዋች እና ነፃ ብትሆንም ለካ ገና ብዙ ሰው ጋር ድር ፈጥሮ የመገናኘት እና የእሚፈልጋትን ብቻ ሳይሆን የእምትፈልገውን ግን የእማያቃት ሰውን ሁሉ ማግኘት እንድትችል አድርጋ ብዙ መለማመድ አለባት። ዓለሙ ሰፊ እና ገና እምትለማመደው እንደ ሆነ ተረዳች፨
ዓሊ መማረኩዋን እየተመለከተ ቀጠለ። “ወይ ደግሞ ወደ ሻይ ቤት ግቢ እና ስለ መምህርዎቹ ጠይቂ። አንድ ተረት ፈጥረሽ እስቲ ንገሩኝ ስለ እዛሰው ስለ እዚህ በይ እና አዋሪአቸው። ሻይ አፊይ ደግሞ አይደብቅም። መረጃዎችሽን ይዘሽ ወደ ደግ የተሰኘ ሰው ትሄጂ እና ሰላምታ ሰጥተሽ በጨዋታ ትቀራረቢ አለሽ። በሂደት እንደው ተማሪ ነበርኩ እስኪ ክፍለትምህርቱን ብጎበኝ እና ብነሳሳ ብዬ ነበር። ብለሽ ፈታ በይ እና ጠይቂ። እንደ እሚመችአቸው ልምጥምጥአማአዊነት (ፍሌክሲቢሊቲ) አሳይተሽ ወደ ቤተሙከራሽ ግቢ። ምን እንዴት እንደ እሚሰራ ጠይቂ። አንድአንድዱ በደስታ የአስጎበኝሽ አለ!” ሩት በቀረቡት ግንኙነት-ድር ግንባታው ተደሰተች። መልሳ “ሌላው ስ?” አለች። “እንግዲህ! ጡትሽን አይቶ ፈገግ ካለ ስትጠይቂው ጊዜ አስቢበት እና ወስኝ!” ናሆም ወደ ምርአዊነት ተመለሰ። “አይ አንድአንድ የተበደለ ሰው አይጠፋም። ሰውን እንዴት መገንዘብ እንደ አለበት እማይገነዘብ ሰው ሞልቶ አለ! ግን እንደ እዚህ ያለ ሰውን ከምር እና በቆፍጣና አቀራረብ ስትቀርቢአቸው፣ ጉድለቱ የነፃ አለመዉጣት ስለሆነ አንድ ኃላፊነትአዊነት (አውቶሪቲ) ስር እሚወድቅ ስነልቦና አለአቸው። ስለ እዚህ ቆጣ ከአልሽአቸው ሊሰሙሽ ይዘጋጁ አለ። በእዛ አማራጭም ሞክሪ ከአጢኖትሽ ገፋፊነት ከአገኘሽ!”
ሩት በሃሳብዎቹ ተደመመች። ብዙ ተማረችበት። በዝረወዝር በማፍረጥረጥ ከአወሩ መንገድ እንደ እማይጠፋ አመነ ች። በሁለቱ ሃሳብዎች ተደስታ መጨረሻ ሃሳቡዋን አነሳች። “በሁሉ ካልሆነ ስ?” ናሆም ቀጠለ። “አይ! ይሄን ከአንድ ግለሰብ ላይ እምትሞክሪው አይደለም። አንዱ ሙከራ ሲወድቅብሽ ወደ ሸምገል የአለው፣ ወጣቱ ጋር ሌላ ጊዜ፣ ወንድ እና ሴቱን በየተራ አወያዪ። አንዱ ይሳካ አለ። ግን እንቢ ከአለ፣ መንገድ አናጣም። ለ ምሳሌ፣ ማህበርአችን አንድ የድንች ማህተም ተዘጋጅቶለት፣ ክበብ ሆኖ ደግሞ በይፋ እንዲመዘገብ አድርገን መምህርዎችአችን ማህተሙን ደግመውልን፣ ክበቡ ጥናት ሊአካሂድ ስለሆነ ለሩት በአምላክ የመረጃ ሰፊ ትብብር አድርጉላት ብለን መፃፍ ነው! በደረት መንፋት ሄደሽ በ መመላለስ ማጥናት ትችይ አለሽ።” ዓሊ ሃሳቡ ከአለ ችግር እንደ እሚሳካ ለማስረገጥ የአክል “አዎ! ይህን ሰራሁ ብለው ለመከራከር ማስጎብኘት ነገር ሲመጣ ደብዳቢ ይሰጥ እንጂ መንግስት በግምገማ ባህሉ የተነሳ እንዲረዱን አድርጎ አለ። ተንከባክበው ባይሆንም ለስራአቸው ማስቆጠር እና እድገት ምናምንቴ ሊአስተናግዱሽ ይከጅሉ ይሆን አለ። ያም አንድ መንገድ ነው።” ሩት በሃሳቡ ተገርማ ስታደምጥ ቆይታ ለበለጠ ምርምር ነገውኑ እንደ እምትሄድ እና ስለ ጊቢው እና ክፍለትምህርቱ መምህርዎች እንደ እምታጠና አሳወቀች። ስለ ቀጣይ ዕቅዱ ቀጥላ አነሳች። “እእ ደግሞ ብችል ባህልአዊ መድሃኒቴን ከገጠር ልሂድ እያልኩ እሞን እየጨቀጨቅኩ ነው ከ ተፈቀደልኝ እንደ አንቺ መረጃዎች ሰብስቤ እመጣ አለሁ። ናሆምም አስብበት። ከእዛ ግን አንድም በማንበብ አንድም በአንድ ሙከራ ነገር ስንዳብር ክረምቱን መቀጠሉ እና መፈጸሙ ቀጣይ ዕቅዱ ነው። ከ አልተሳሳትኩ…” ወረቀቱን ፈልጎ አየ። “አዎ! ከዛ በቃ! ፈተና! ቀጣይ ደግሞ አንድ እሚበልጥ ስምጥ ተግባር እንዲሁ ነቅሰን መከወን። ይህ ዘንድሮ ተሞክሮአዊ ዕዉቀት መሰብሰብ ነው። ቀጣይ ግን አንዱን ለይቶ ማጉላት። ከዛ መማር፣ ተለማማጅ መሆን!፣ መመረቅ፣ ወዘተ…” ዓሊ ቆሎውን በ ቅንጦት ወደ አፉ ወርወር እያደረገ ነገሩን ጨረሰ፨
ናሆም በግሉ የአቀደውን ገና ስላላዳበረ፣ ዓሊን ለሃሳቡ አመስግኖ እንደ እርሱ በጊዜ መዉሰድ እሚአዳብር እንደ ሆነ ገለጸ። ሰዓቱ ነጉዶ ስለ ነበር ዓሊ በመደናገጥ “ዉይ! ዉይ! ዉይ! ሶላት ሳልሰግድ! አንዴ ቆዩኝ!” ብሎ የሃሳብ ክሂሎትአማአዊ (ቴክኒካል) ጠብጠቢትዎቹን (ቴምፕሌትስ) አስቀምጦ ሮጦ ወደ ጓሮ ክፍሉ ሄደ። ሰሚራ ወጥታ “እንቅልፍ ወሰደኝ ስ? በስማም! ጭልጥ አደረገኝ እኮ! ዉይ ይሄ ልጅ! ምሳ አያቀርብም ወይ!? ሰዓቱ ሄደ!” ናሆም ለመሄድ ቢነሳም ሩትም እንደ ገባት ሰሚራ በዚህ ሰዓት ቤቷ የገባ ሰውን አትለቅቅም። ምሣ መጋበዝ ግድ ነው። ግድ አስቀምጣአቸው ወደ ጓሮ ዞረች። ከአፍታ በኋላ ተመልሰው ከዓሊ ጋር ጓዳ ማንኮሻኮሽ ጀመሩ። የአትክልትዎች እና ድንች ወጥ ከ ነጭ እንጀራ ጋር ቀርቦ እየተጨዋወቱ ተመገቡ። ደግመው ሻይ ጠጥተው ትንሽ ከተጨዋወቱ በኋላ አቶ ሙባረክ የዓሊ አዛውንት አባት ደረሱ። ሸምገል ብለው በባርኔጣ እና ትልቅ ካፖርት ከከዘራ ጋር በቋሚ ተጠቃሚነት ያሉት ሙባረክ ገብተው ምሣ መንደር ስለበሉ ቡና ብቻ ጠየቁ። ከእነናሆም ጥቂት ተጨዋውተው ቡና ዓሊ አፍልቶ ተጠጣ። ወደ ስምንት ከሩብ ሲል ተሰናብተው እነሩት ወጡ። ዓሊ በር ድረስ ተከተለአቸው። ነጭ ኮፍያው ስር ሌባጣቱን ልኮ አከክ እየአደረገ ቆየ እና “በቃ ሰሞኑን እንገናኛ! ገጠር ከሄድኩ ስለ እማልኖር… ነገ አንቺ ጊቢውን እዪ…ከነጌ ወዳ ዘጋባሽን ይዘሽ እዚሁ እንገናኛ በቃ!” ሩት ድንገት ትዝ ብሏት “ገጠር ከሄድክ እማ የፍኖት ዉይይት ቀጣይ ሳምንት እኮ አለ!” አለች። ዓሊ “ኦ! ለካ ደርሶ አለ። ጊዜው እንዴት ይሮጥ አለ! በቃ ይሄን ሳምንት እዚህ ነኝ! ግን ከነጌ ወዳ እንገናኝ! ተመሳሳይ ሰዓት! ቀጠሮ ይከበር!!” ፈገግ አሉ። ሰላምታ ተሰጣጥተው፤ ሩት ስማ ው ናሆም ጨብጦት ተለያዩ፨
በ ጨዋታ እና መሳሳቅ መንገድ እየአሳበሩ ብዙም በማይጎዳ ዘጠኝ ሰዓቷ ደመናአማ ፀሐይ ታጅበው ሰፈሯ ደረሱ። በመጨረሻ ተሰነባብተው በአጫጫርዎቹ ሦስት እግርዎች መኪና አሽከርነት ወደ ሰፈሩ ተሳፈረ። እሚአደርገውን አዉጠነጠነ። ‘ነገን ዛሬ መለማመድ! ነገ ከአየር አይጨለፍም! ዛሬ ከዛሬ መኖር ጎን ነገን መገንባት የአስፈልግ አለ!’ በ ሃሳቡ ብዙ መጥቶ ሄደ። በእርግጥ እሚአስበው ነገር ይህንንው ነበር። አንድ ነገር ከትምህርቱ ጎን መከወን ነበረበት። እንጂ በእዚህ የእሚ እቅፍ ተደላድሎ ተምሮ በ መጨረስ ወደ አለመው ዓለም መድረስ የለም። ወይም ስኬቱ ያነሰ ይሆን አለ። ዛሬ ግን የተጀመረ ነገር ካለ ነገ አዲስ ቀን ሲመጣ ይህን ጅማሮ መጎንጨት ይቻል አለ። በተለመደው የኢትዮጵያ ስርኣተ ትምህርት ታልፎ ስምን በአግባቡ መፃፍ እማይቻልበት እንደ እሚገጥም ይወራ አለ። ትምህርቱ የሌላ ዓለም እርቢ (ኮፒ) እንጂ አእምሮ አልሚ አይደለም። ተምሮ በድህነት እምትማቅቅ ሃገር ስንት ሥራ መጠንሰስ ሲቻል ዜሮ ተኮኖ መቀጠር ብቻ እሚታለመው በዚህ በዐድ ትምህርት ስልጠና ታልፎ ነው። ይህን ይፋ ስርኣት የተሸከመው እንከን ማሸነፍ የ አለበት ለጊዜው ዜጋ ው እራሱ ብልህ በመሆን ነው። ስለ እዚህ አንድ ነገር በ ማድረግ በላጭ ክሂሎት በማዳበር፣ ነገ እሚታለም ነገርን ዛሬ ለ መሰረቱን ማግኘት መጣር ግድ ነው በእሚል አመነ። ለመስ እሚነግረው እና እሚአበለጽገው ድንገት አንድ ነገር መጣለት። አናቱንን ወዝወዝ ሲአደርግ በሃሳብ ነጉዶ፣ መኪና ዋ ቆማ ነበር። ወጣቱ ነጂ “ምን አሳሳበህ ጓድ!” ብሎ በሰብእአዊነት ጠየቀ። “አይ! ጓዴ እዚሁ ነው! አመሰግንህ አለሁ!” አናቱን ሰበር አድርጎ ሂሳቡን ሰጥቶ ወረደ እና ወደ ቤት አግጣጫ የመጨረሻ ቀጭን መስመሩን ተያያዘ፨

መስ ከ ጓሮ በመተረው ሥፍራ ካስማዎች ለመቅበር እሚአስችል አስር ጉድጓድዎች ቆፍሮ ጠበቀው። በሃምሳ ሳሜ.ዎች ጥልቀት ያሰመጠአቸው ጉድጓድዎች ብዙ ሳይደክም ጨቅየት ስላሉ በታላቅ መታዘዝ ሰምጠው ሰረጎዱለት። ናሆም ሳያግዘው ይህን ሲመለከት “ለምን አልጠበቅከኝም?!” በማለት ተቆጥቶ አሳሰበ። “እሽ! ችግር የለም! የጉጉልበቱን ሥራ ለእኔ ተወው! ከቶ አላስነካህም። ይህ የእኔ ዕቅድ ነው!” “እንዴ! አንተው ትኖርበት አለ ሃ! እንዴት እንዲህ ይባል አለ?” መስ ፈገግ ብሎ ጥርሱን ነከስ ነከስ በማድረግ አጤነ። “ና እስቲ አንድ ስፍራ ደርሰን እንመለስ እና እናየው አለን!” ናሆምን አስከትሎ ወደ ዉጭ ወጡ። ከቤታቸው ብዙ ያልራቀ ቢሆንም ዉስጥለዉስጥ ጥቂት ተጉዘው በሌላ ጫካ አካባቢ መንደር ደረሱ። ናሆም ያሉበትን ሲአስተውል ጭራሽ ወደ ሰመጠ የዳገትአማ ጫካ መንደሩ ገባ አሉ። ጥቂት ጠብቆ ጥያቄውን ለመጠየቅ ሲአቅድ አንድ የእንጨት አጥር ያለበት ቅጥር ተመለከተ። እዛ እንደ እሚሄዱ ሲገምት በእርግጥም እዛ ደረሱ እና መስ አንኳኳ። አንዲት ህፃን በሩን እየአንፏቀቀች ከፍታ እንዲገቡ ፈቀደ ች። “አባባ አሉ?” በማለት መስ ዝቅ ብሎ እየሳማት ጠየቀ። በአናት ማወዛወዝ አዎንታ ገለጸች። ወደ ዉስጥ ሲዘልቁ በበረንዳው ላይ እንዲቆይ ናሆም ነግሮት ገባ። በህፃኗ ራቅ ብሎ መመልከት ታጅቦ ናሆም በወንበሩ ላይ ተቀመጠ። ሰፊ አንገት ማህተምዋን እየበላች ከሩቅ ስትመለከተው ጠራት እና የአጫውታት ጀመረ። ስም ከአላት ጠየቀ። “ብሩክታይት ጎበዜ ታደሰ ዓለምነህ ወለላ በላሳ ከእዛ አላውቀውም!” ናሆም ፈገግ ብሎ “ትማሪአለሽ?” ሲል ጠየቀ። ጨቅላዋ በግንባር መልስ መለሰች። “ስስንትኛ ነሽ?” “አስራስድሥትኛ!” ድንገት ቶሎ ለመደችው እና “እይስ! ዥዋዥዌዬ ተበጠሠ! መብሩክ መጥቶ ተው ስለው እንቢ አለና ወጥቶበት ተበጠሠ። ትሰራልኝ ፈለህ?!” በእጇ ራቅ ብሎ የቆሙ ዛፍዎች ላይ ጠቆመች። ናሆም ተነስቶ ጎበኘላት። አንድ ግንድ ላይ ታስሮ የነበረ ገመድ መሬት ወድቆ አለ። አንስቶ ጎኑ ባለ ትልቅ ዛፍ ላይ በደንብ አሰረላት። በትልቅ ደስታ ወጣችበት እና ጨዋታውን ወዲአው ጀመረ ች። እየተጨዋወቱ እና እየአሳቀችው ቆየ ች። “አንተ! ዋልኮት የባርሴሎና አሰንጣኝ ነው ወይስ የስፔን አሰንጣኝ ነው?” “አአይ!” “ሜሲ ነው እሚአሰለጥነው አደል? እኮ!” ናሆም በፈገግታዎች እየተጫወተ መንገሩን ቀጠለ። ጥቂት ቆይቶ መስ ብዙ ቁሳቁስዎች ተሸክሞ ከሳሎኑ ወደ ዉጭ ወጣ። ናሆምን ሲጠቅሰው የአናፂ ቆዳ ቀበቶ አብሮት kit መጥቶ ተቀበለው። የቤቱ አባወራ አበራ ጥቁር-አረንጓዴ ካፖርት ለብሶ እየአናገረው ወጣ። “ይሄ እንደው ደንበኛ ከሆንን ብዬ እንጂ እና ክረምቱ ለአናፂነት ስለ እማይመች ገበያውም ስለ ሌለ በ ርካሽ ሸጥሁልህ እንጂ እንደ እዚህ አይገኝም! በል በርታ አይዞህ። ጠይቀኝ እየተመላለስህ!” አሉት። “እሺ! ጋሽ አበራ! አመሰግንአለሁ፤ በሉ ግቡ ለብርዱ ወደ ዉጭ መዉጣት አይገባም!” “አይ ልክ ነህ! የ እኔ ብርድ አይችልም ልክ ነህ! የታለ ተጉ? ተጉ ና እንጂ ቶሎ!” ጎረምሳ ልጅ እጅዎቹን በመላስ ከሳሎኑ ወጣ። “ትመለስ ትበላለህ ብዬህ ነበር እኮ! በል ቶሎ አሳይአቸው እና ና!” እነመስ ሲወጡ ትንሽ ዋ ልጅ “አመሰግንህ አለሁ!” ጮኸች። ናሆም በ ፈገግታ ተመልክቶ በ ማጎንበስ አመስግኖ ወጡ። ከቤቱ ጀርባ ጥቂት ወስዶአቸው የጫካው መጀመርን ተያያዙት። “ቀይ እና ነጭ ጨርቅዎች የታሰሩባቸውን ቁረጡ ብሎአል! ቀዩ ብቻ ነው የእናንተ!” አለ እና ጣቱን መላስ ቀጠለ። “አውቅ አለሁ አንበሣ ው። ተመለስ በቃ። አመሰግን አለሁ!” ናሆምን ከልጁ አብሮ እንዲመለስ አሳወቀው “ብዙ አያቆየኝም፣ ጋሪ ከ መቅሱድ ተከራይተህ ና። ሩቅ ስለሆነ አሁን ሂድ!” ብሎ አሰናበተው። ናሆም ሃሳቡ በግልጥ ስለ ገባው ከጎረምሳው ጋር እቃዎቹን አዉርዶ ተመልሶ ሄደ፨
መስ ባህርዛፍዎች በመቆራረጥ ፈጣን እንቅስቃሴዎች ተጠመደ። በመጋዙ ከባህርዛፍዎቹ ቂጥ ላይ በፈጥነት ይገዘግዝ ጀመር። እርጥብ ስለ ነበሩ ከደቂቃ በ አነሰ ፍጥነት ወደ ጀርባ ይገነደሱ ነበር። ብዙ የ ማገር አገልግሎት እሚሰጡ ቀይ ጨርቅ የታሰሩብአቸው ጠን እሚሉ ዛፍዎችን ጥሎ ነጭ ጨርቅ አበራ አስሮ ለእራሱ እንዲቆረጡለት የጠየቃቸውን አምስት ማገርዎችም ቆረጠለት። መጋዙን አስቀምጦ ምቹ አነስተኛ መጥረቢአዋን አንስቶ ለመለመአቸው። በመጥረቢአው በመታገዝ ወደ ቋሚ ምሰሶዎቹ ተሻገረ። ወፈር እሚሉትን ዛፍዎች እንዲሁ እየቆረጠ እና እየገዘገዘ ጥሎ በመለምለም ከመረ። በግዙፍ ሰዉነቱ ታግዞ በቀልጣፋነት በወታደርአዊ ትጋትአማአዊነት እንጨትዎቹን ሰበሰበ። አምስቱን ማገርዎች ተሸክሞ ወደ አበራ ቤት አዘገመ። በናሆም መቆየት እየተገረመ ለአበራ ማገርዎቹን አስረክቦ ከተመረቀ በኋላ ወደ ዉጭ ወጣ። ናሆም አህያ እምትጎትተው ጋሪን በመንዳት ከሩቅ ሲመጣ ተመለከተ። መቅሱድ የአህያ ጋሪ አገልግሎት በመስጠት ትልቅ እውቅና እና መጠነኛ ሃብት ማካበት ላይ የነበረ ሲሆን እማያውቀው ሰው የለም። መስ በ ስልክ አነጋግሮት ስለነበር እና ስለ እሚተዋወቁ አህያዋን በ ሃምሳ ብርዎች ኪራይ ለአንድ ሰዓት አዉሶት ነበር። ወደ ጓሮ ዞሮ እንጨትዎቹን በመከፋፈል በመጠኑ እየተሸከመ አበራ ቤት መግቢአ ላይ መከመር ጀመረ። ናሆም ደርሶ ወደ አህያዋ ጋሪ ጫነ። መስ ከጓሮ ሁሉንም አምጥቶ ሲጨርስ ቁስዎቹን ለማምጣት ተመለሰ። ናሆምን አግዞ ሁሉም እንጨት ሲጫን ወደ ቤትአቸው ማዝገም ጀመሩ። “ዘገየህብኝ እኮ!” “ትራፊክ አስቁሞኝ ነበር!” መስ ከት ብሎ ሳቀ። “ዉሎህ እንዴት ነበር?” ጨዋታ ለመቀየር መስ ጠየቀ። ናሆም በሃሳብ ነጉዶ ወደ መንገዱ መመልከቱን ጀመረ። መልሶ ሃሳቡን ሰበሰበ። “ደግ ነበር። አንድ ነገር ለ መከወን እና ክረምቱን ለማሳለፍ አስበን ነበር።” “ምን መከወን አቀድአችሁ?” “አይ! በጋራ አቀድን እንጂ ተግባሩ በየፊና ነው። እና እኔ ያሰብኩት ለወደፊት እቅዴ ግብርና እንደ ሆነ ታውቅ አለህ!” “አዎን ምሁር ገበሬው!” “ማለቴ…ግን ግብርና ሲባል ዘመንአዊ ምርትአማነት (ፕሮዳክቲቪቲ) ብቻ አይደለም። ሰንሰለት መፍጠር ነው!” “ሰንሰለት? ሰንሰለት ልታበቅል?” ፈገግ ብሎ በሹፈት እንዲብራራለት ጠየቀ። “ማለቴ! የእኛ ሃገር ንግድ አንድ ችግር አለበት። በእርግጥ ከእምናውቀውም ከማናውቀውም ብዙዎች መሀከል! አንዱ ችግር ንግድ ሲነገድ ወጪ መቀነስን እሚአተርበት ነጋዴ የለም! ዋጋ በመጨመር ትርፍ እንዲጨምር ማቀዱ ልዕለ-ልማደኛ አካሄድ ነው። ባንድአች አመክዮ፣ መሸጫ ዋጋ ማናር ትርፍ ማግኛው መንገድ ግን አይደለም፤ ቢአንስ ብቸኛው! እና እምመኘው እንደ ልጅ ቢሆንም ቢሳካልኝ፣ መሸጫ ዋጋ ባለበት ሆኖ ጠቅላላ ገቢን ለ ማናር ሌላ መንገድዎች መጠቀም ነው። ለ ምሳሌ ወጪ ከ ሌላ አቻ ነጋዴ ወጪ መቀነስ። እንደ እዛ ሲሆን ትርፍህ ከብጤዎችህ ይበልጥ አለ።” መስ ይህ እንዴት ሊከወን እንደ እሚችል በ ማሰላሰል ተጠምዶ “እሺ ባክህ! እንዴት?” በ ማለት ቀጣዩ እንዲነገረው ጠየቀ፨
“የ ንግድ ወጪ እንታሳንስ ከሆነ ስነቆጠራ (አካዉንቲንግ) ላይ ማወራረዱ ትርፉን ይጨምርልህ አለ። ስለ እዚህ ጥያቄ ው እንዴት ወጪ ይቀነስ ነው? እዛ ላይ ማውጠንጠን ግድ ነው! እኔ የመጣልኝ አንድ መንገድ የግብዓት ግዢ ሰንሰለቱን መቆጣጠር ነው። ማለትም በአንድ ተያዥ ንግድ ሰንሰለት እየአንድአንዱ እሴት ቢጨምር ባይጨምርም ምርቱን ወደ ቀጣይ ገዢ ስላሻገረ ብቻ ዋጋ እሚጨምርበት ነው!” “መሀልኛዎች (ኢንተርሜዲያሪስ) ናቸው ዋ!” “ብቻ አይደለም! “እነ እርሱን በእርግጥ ማስወገድ ከ ቻልክ ግብዓትህ ከበለጠ ቀጥታ ምርት ምንጩ ከተሰበሰበ፣ ንግድ ወጪህ ቀነሰ። ያ ከሆነ አዎን ሽያጭ ገቢህ ሲቀናነስ ትርፉ ከመሀከልኛዎች እሚሳተፉበት ንግድህ መሻሉ ጥርጥር የለውም። ግን የእኔ ነጥብ፣ የምርት ምንጩን በከፊልም ቢሆን መቆጣጠር እና ብዓት በራስህ ማምረቱ ነው። ብዙ ጥቅምዎቹ አሉት። ግብዓትህ በራስህ ሲከወን የንግድህ ነገር ወጪው ከፍተኛ መሽመድመድ ያሳይ አለ። በተመሳሳይ ዋጋ ሸጠህ ትርፍህ ግን የሰማይ ያክል ይዘልግ አለ። ሌላው ግን ትርፉ መጠነኛ ነው። ጨዋታው እንደ እዛ መደረግ አለበት።” መስ አሰብ አደረገ “ይሄ ማ እኮ የሌላውን ግብዓት ንግድ ወጪ አላገናዘበም። ግብዓት ማምረት ስትያያዝ መልሶ ወጪ አለው።” “ወጪ የሌለው ንግድ የለም! ሃሳብህ ግን ገብቶኝ አለ። መልሱ ግን ግለ-ሰንሰለት ፈጠርህ ወይስ አልፈጠርህም ነው! በእርግጥ ልዩአማነት ጭራሽ አንዱ የንግድ ማድሪአ ቅጥ (ዳይሜንሽን) ነው! ግን ይኽኛው ለ እኛ ሃገር ያልተለመደ ስለ ሆነ ከእዛ መች ተጀምሮ ነው ወደ ልዩአማነት እምናዘግመው። ገና መች ተበዘበዘ? ሰንሰለት ተፈጥሮ ንግዱ ሲበዘበዝ ትርፍ ሲከማች (ሳቹሬት) የአኔ ነው ወደ ልዩአማነት ገብተን የትርፍ ክምችት መቆሙን ለመስበር እምንንቀሳቀሰው። አሁን ግን እዚህ ሃገር ለ ማትረፍ ግብዓትህን ብታመርት ከፍተኛ ጥቅም አለው። ለምሳሌ እኔ የመብል ቤትዎች ሰንሰለት መክፈት ህልሜ ነው። እንደ በቀለ ሞላ ሆቴልዎች ብዙ ቅርንጫፍ የአለበት መብልቤት መክፈት አላማዬ ነው። ግን በግብርና የግል ግብዓትዎች ማምረት እመኝ አለሁ! ዋናው እዛ ነው። ግብርናው ዘመንአዊ አያያዝ ካገኘ ከመሬት ስፋት ጋር አይገናኝም እና አየር እና ግድግዳውን፣ ዉኀ እና ጣራውን ተጠቅሞም በማምረት የገበሬ ትርፍን አብልጠህ መሰብሰብ ትችል አለህ። በመቀጠል ግን ዋናው ለራስህ ፍጆታ የመሆንህ እዉነት ነው። የግል ፍጆታህን ስትቆጣጠር እልፍ መብልቤትዎች በገዙት ሲአገለግሉ ትርፍአቸው ብዙ ልዩነት አያስኬድአቸውም። አንተ ግን ልቀህ ከ እነ እርሱ ትርፍ በ ማብለጥ ልትልይአቸው ትችል አለህ። አሁንም አትሳሳት የንግድ ጉዳይ ብቻ እማስብ አይደለሁም። ዋናው በእራሴ ምርጡን የግብርና ምርት ማምረት ስለ እምፈልግ ነው። ከገበሬ ብትገዛ የተለመደ ነገር ነው። እኔ ግን ብዙ እሚለይ ይዘት ያላአቸውን ምርትዎች ማጎንቆል፣ ማሳደግ እና መንከባከብ እምችልብአቸውን ጥበብዎች እየተመራመርኩ ስለእምሄድ፣ በአጭሩ የረዘመ አልሚ ምርት መሰብሰብ የኑሮ ዘዴ ህልሜ ስለ ሆነ ነው። በእነእዛ ምርትዎች ሃበሻን በልዩነት መመገብ እና ሃብት ማካበት የትምህርት መጨረሻዬ ነው።” የናሆም በልጅነት ይህን ግብርና ለምዶ ከዘመንአዊ ዓለም ሲቀላቀል ወደ አጤነው ልዩነት ለመግባት አልሞ መኖሩ አሁን ደግሞ በበለጠ ተግባርዎች መሞከር መፈለጉ መስን ሁሌ እንዲአደንቀው የሚአደርገው ነበር። አሁንም በማድነቅ አተያይ ከጎኑ ሲራመድ አስተዋለው። ዘመንአዊው ዓለም ወደ ኢትዮጵያ ሲፈስስ በግብርና መስክ ግን ገና አልተያዩም። የሃገሪቱ ምርት ገበያ ተቋም መረጃ ማስመልከቻ ገጽማያዎች እንኳ ገና ሳያገለግሉ በየአሉበት ጠፍተው በግብ-ንግዱም ሆነ በግብርናው ሃገሪቷ ገና የጭራ ጭራ እንደሆነች ናት። የግብርና ሚኒስቴር እንኳ የግብርና ምርምር ተቋም ያሰናዳው በ2008 ዓም. ነበር፤ ዛሬ ድረስ በበሬ ሲታረስ እና የሃገሩ ልዕለ-በላጭ ዜጋ በግብርና ተደግፎ ግብርናውን መመርመር እና ማዘመን ግን ገና ጥቂት ዓመትዎች ቀደም ብሎ ነበር ተቋም ይገባው አለ የተባለለት። በእርግጥ እልፍ የግብርና ማዘመን ኋላቀርነትዎች ስላሉ እልፍ የሥራ ዕድልዎች አሉ ማለት ነው። ናሆም ወደ እዛ ገብቶ ዘርፈሰንሰለት (መልቲቼይን) -ነት ለመቀየር እሚአስበው ኋኝነትአዊነትዎች አዳኝነት ግሩም አክብሮትን እንዲቸረው ከእሚአደርጉት ነገርዎች አንዱ ነበር። አሁንም በመራመዱ ዉስጥ ፀጥታ ሰፈነ እና ደጋግሞ በአግራሞት መመልከቱን ተያያዘው። ጥቂት አለፍ እንደ አሉ “ታዲአ ክረምቱን ምንድነው እምትፈልገው?” ብሎ ጠየቀ ው። “የእማስበው በተለየ ቅድም ጀምሮ ጊዜን ሃይል ነው። ጊዜ ይነጉድ አለ። አንድ ነገር ከአልተደረገበት አንተም በባዶ ትነጉድ አለህ። ስለ እዚህ ይህ ህልሜ በተግባር ሊመስል እሚችለው ነገርን ለመሞከር እና ተግባርአዊ ትዉዉቅ ልከውንበት ጥቂት አቅጄ ነበር!” መስ ደንገር አለው። “ማለት? ግብርና ለመልመድ ከአሁኑ?” ናሆም አጎቱን አየት አደረገ ። “ይገርማል እንዴ? አብሮ መነገድ ነገር አስቤ ነበር። እስቲ አስተያየት ስጠኝ ከጓደኛዎቼ ተመካክረን እነእርሱም ለክረምቱ እሚጀምሩት ነገር አለ። የእኔ ሃሳብ ደግሞ አንዱን ለኔ ተወው አንድ ገበሬ በማገልገል እምለምደው ነገርመኝ አቅጄበት አለሁ። ግን አብሮ ጥቂት ሻይ እና መብልዎችን መሸጥ እፈልግ ነበር። በሩ አጠገብ ሁለት ሜትርዎች ኮሽም አጥሩን ቆርጠን ሻይ ቤት ብጤውን ለመሞከሪአ ብናበጅ ብዬ ነበር። አትቆጣኝ ቆይ ታዲአ!” እእንዳይጨነቅም እንዳይቆጣም ምን ማድረግ እንደ አለበት እየአውጠነጠነ ቀጠለ። “እምልህ ሸራ ነገር መወጠር ብቻ ነው!” ቀለል ብሎ እንዲታየው ጣረ። “አየህ ነገር ሰፈሩ ከከተማ ዉጭ እንደ ሆነ ነው!” ናሆም ስላሰበበት ቀበል አድርጎ ቀጠለ። “ያልታየህ ነገር ብዙ ገበያ አልሻም፤ አጠገብአችን ደግሞ ሰፊ የወረዳ አስተዳደሩ ጀርባ እንደ ሆነም አስብ፣ መዞር እንዲችሉ ከአደረግን በቂ አመክዮ መትተን ከፊታቸው ያሉ የጤና ዴስክ እና ዞን ትምህርት መምሪአ ቤተስራዎችም አሉ! ወደ ከተማም ደርሶ መሸጡን አቅጄበት አለሁ! ዋና ው ድር ነው!” ናሆም ለገበያው እንዳይጨነቅ ለማሳመን ጣረ። መስ አቅማምቶ አሰብ ማድረግ ቀጠለ። ልጁን መደገፍ ይፈልግ አለ። ደግሞ ቢአንስ ይዳክር እና ይየው ቢባል ጥቂት ወጪ መኖሩ አይቀርም እና ስለ ወጪው አሰብ አደረገ፨
“ዋና ው ክረምቱን በአንድ ተሞክሮ ለመለማመድ ስለሆነ ትርፍ ጉዳዩን ትተህ ብቻ እሚን አሳምንልኝ እና ሻይ እና ልዩ መብልቤት ልሞክር። ቀጣዩን ዓመት ከትምህርት ጎንለጎን ቀጥዬ ቤተሙከራ ላድርገው! ያን ስልህ አከስራለሁ ወይም ልቀልድበት አይደለም! ብቻ ልሞክረው ነው እምልህ! ከዛ ጊቢ ተምሬ ወደ እዛው ስመለስ ብዙ ተሞክሮ እና ዕዉቀት ይኖረኝ አለ ማለት ነው!” “እስቲ እናስብበት አለን።” በሃሳቡ ጥቂት ገፋ እየአደረገ መጨነቅ ብጤ ሲከብበው መልሶ ከልኩ አያልፍም በሚል ተወት አድርጎ እንደ ልጅ እሚመለከተው ናሆምን ተመለከተ። በሃሳብ ሰመጥ ብሎ ጎኑ ይራመድ ነበር። ፈገግ ብሎ ወደ እራሱ ተመለሰ፨
“እና እኔ ለምን አንድ ስራ አልጀምርም? አልክ? ግን ትምህርትስ?” መስ ከአፍታ ኋላ ነገሩን ለመወሰን እንዲረዳው ጠየቀ። መልሶ አብራራለት። “ልጅ ነህ ገና። በመማር ብቻ በርታ። ያንተ ፈንታ ያ ነው። በእዛ ስኬት አድን።” ናሆም ለማስረዳት አሰብ አደረገ እና አንድ ጫፍ መዘዘ። “ትዝ ከ አለህ ጧት፣ ልመደው ድሃ ነን ምናምን አልክ እኮ! ተማመንን በእዛ! እና? በድህነት ግን ልጅነት ልጅ በመሆን የለም። ማን እንደ ልጅ ይንከባከብህ አለ? ማን ወላጅነትን ከሰብአዊነት እና ዘመንአዊነት አንፃር ይመለከት አለ? አንተም መልሰህ ሽማግሌነት እራሱ እንኳ እዚህ ሃገር አያምርም አልክ። ታዲአ ለምን እስከ እማረጅ እቀመጥ አለሁ? አርጅቼ ም መፍትሔ ከሌለ፣ ለምን በተገቢ መንገድ ለመጓዝ ዛሬውኑ ግለንቅዓት (ሰልፍአዌርነስ) መከወን ይከብደኝ አለ?” መስ ፈገግ አለ። ሃሳቡ እንደ ስነአመክዮ (ሎጂክ) ስህተት የለበትም ነበር። ግን ለዚህ አረዳድ ጀርባ ሰጥተን እምንኖር ነን ብሎ መስ ስለ እሚአስብ ብዙ መልስ ቢፈልግ አንዱም ትክክል አይሆንም። አመክዮ ቢከዳው ማታለል ግን ሊአግዘው ይችል ከሆነ ብሎ ሌላ ሃሳቡ ላይ አጠነጠነ፨
“እናትህም እምትፈቅድ አይመስለኝም ናሆም። በዚህ ዕድሜህ እንዲህ እንድትሆን አያስችላትም።” መስን አጉልቶ ናሆም ተመለከተ። “አንተ ዋስ ትሆናለህ እኮ! ለእዛ ነው እምጨቀጭቅህ! ገናም በትምህርት ዉጤት ማነስ-አለማነስ ታይቶ ደግሞ በጊዜ ሂደት እንወስንበት አለን። እሺ በል። በእናትህ።” “ቆይ ባይሳካስ?” መስ ሌላ ፈተና ደቀነ።
“እየውልህ! ቀድመን እሚሰራ እንፈልግአለን አይደል? ከእዛ በዝርዝርዎች እናዳብረው አለን። ከዛ እንፈጥር እና አዳዲስ ቀለምዎች እናክልበት አለን፤ ከብጤዎች እንለየው አለን። ከእዛ በትጋት እንተገብረው አለን። ያንድ ጓደኛዬ ሠብለወንጌል ትባልአለች አባቷ ድንቅ ስነንግድ (ቢዝነስ ስተዲስ) ኅዋአዊከተማአችን ዉስጥ አስተማሪ ነው። ሄደን ብዙ ምክርም እንጠይቀው ደግሞ አለን። የይዘቱን ዕዉቀት ከንግድ ዕዉቀት አስማምተን እናለማው አለ። ብቻ ተስማማ። እሺ በል በናትህ።”
“ታውቅአለህ? እንደውም አንድ ሃሳብ መጣልኝ። በጅቡቲ መስመር ባቡር ጥበቃ ተሰማርቼ መስከረም ላይ ሥራ እጀምር አለሁ። ሁለት ሦስት ጫማዎች ልልክልህ እችል አለሁ። ትርፉን ወስደህ ዋናዬን መልስ እንጂ እደጋግምልህ አለሁ! እማታስበላኝ ከሆነ ነው ታዲያ ግን።” አዲስ መላምት ሰጥቶ ጥያቄውን ቀየረ፨
“ዬ! ማን ያስበላሃል። በአንድ አፍ! በትግል የተገኘ እቃ እማ አትርፌ ነው ብድር እምመልሰው። ለማንኛውም እርሱ ብቻ አይደለም። የእኔን ሃሳብ አትገፍትር። የእኔ ‘መማር ጎንለጎን ከነገአችን ህልም እሚቀራረብ አንድ ነገር ማድረግ’ ነው እንጂ ነው። ጎንለጎን እሚሰኝ መርኅ ከጓደኛዎቼ ጋር በፊት በጅተንአ በቤተሰብ እና መንግስት ጥረትዎች ለዜጋ በእሚበጁ መስመርዎች ብቻ ትልቅነት አይከሰትም ብለን ነበር። ስለ እዚህ በጎን ትምህርት ሳናበላሽ አንድ ግለሰብአዊ ወይም ቡድንአዊ ጥረትዎች ለማስኬድ አቅደን ነበር። እስከ ዛሬ በዕዉቀት እና ማንበብ፣ ዕዉቀት በመጋራት እና የንባብ ማህበርአችን ወርሃዊ ዘገባዎች ለህዝብ በበይነረብ አገልግሎትዎች በማስቀመጥ ሌላዎችንም በመርዳት ላይ ነን። ነገርግን በግለአርነት (ሰልፍኢንዲፔንደንስ) በዕዉቀት መበልጸግ ብቻ በቂ አይደለም። ዕዉቀት የግለአርነት አንዱ አላባዊያን ነው። ንዋይአዊ (ፋይናንሲያል) ብልጽግና መሳለመሳ መገኘት አለበት። ለእዛ ደግሞ እንደ አልኩህ ወደፊቱ ዛሬ በመቀመጥ ሲጠበቅ ብሩህ አይደለም። ስለ እዚህ የነገ ንዋይ እና ዕዉቀት ዓለምአችንን በማጣመር ዛሬ አንድ ነገር ለማድረግ እየአቀድን ነው። የወረቀት ዕዉቀት በማሳደድ ብቻ እንዳንቀር ከምናብ ወደ ገሃድ ለመድረስ አቅደን ነበር። እና ያንን ሃሳብ ነው አሁን እርዳኝ እምልህ!” መስ በምርአዊነት የጠነከረ እና የተብሰለሰለበት የናሆም ሃሳብን መከላከል አቆመ። በእርግጥ የክረምት ቁምነገር ለተማሪዎች ጭራሽ እሚረዳ እንደሆነ አምኖ፤ ተነሳሽነቱንም ለማስፈንጠር ብሎ መደገፉን አቀደ። በእርግጥ ሲአስተውል ይህ ጠቃሚ ሃቅ ነው። “እንደ አልኩህ እናየው አለን እስቲ!” በማለት ከመሬት ተነስቶ እሺ ላለማት ያክል መለሰለት። ናሆም እንደሳበው ቶሎ እሺ ላለማለት እና ጉዳዩ ሳይቋጭ ቃል ላለመግባት ብቻ እንጂ ጎኑ እንደሆነ አመነ፨
መስ የናሆምን ፊት በእርምጃዎች እየተንቀሳቀሱ እንዳሉ ደግሞ መልከት አደረገው። መልሶ ደግሞ ሃሳብ ሸምቆ ነበር እና ፈገግ ብሎ ጨዋታ ለመቀጠል በእሚል አዲስ ጉዳይ አነሳበት። “ዲ! ታውቅ አለህ ግን፣ ‘ያመል (ቢሄቪየር) ነው እንጂ ድሃ የገንዘብ የለም’ ይባላል። አዎንታአዊነት እና ቀላል አመለካከት ካለህ ሳትለፋ መኖሩ እሙን ነው።” ናሆም ተገቢውን አጸፋ ፈገግ ብሎ መለሰ። አትስራ አትታትር ለማለት እንዳልሆነ አሰበ። “አዉቅ አለሁ። የታሪክ ግድግዳ አብሮም የተራ ክፉ ደብተራዎች ጓድ እሚመስለውን ሰው ሙግ. አስታውስ አለሁ።” ይህን ብሎ በፈገግታ ፊቱን ቦግ አደረገ። መስን በአክብሮት ደግሞ ተመለከተው። “አመል በመገንባቱ አንተና እና እሚ ስላልተኛቹህ አመላችን ያልተገሩት አመልን አይመስልም። እራስ ማፍቀር እና ግለትምምን፦ መሪነት እና አዎንታአዊነት አለን። ስለእዚህ፣ በማህበረሰብ ፍልቅልቅ ቅጽበቶች በንቃት ተሳትፎ ሰምጠን አለሃፍረት እና አለጥራዝነጠቅነት በቁጥጥር መኖር አልምዳቹን አለ። እናመሰግን አለን። ዘመኑ ካለው ተወለድ ተጠጋ አይደለም። ከእሚያውቅ ተወለድ ተጠጋ ነው። ወደ ቀኝ መንገድ እየወሰዳቹን ነው እና እናመሰግን አለን፤” የፈገግታው ቦግ ማለት ወደ ስዉር መንበልበል ደርሶ አክብሮቱን አበከረ እና ጠምሮ አሻገረ። መስ ፊቱን ቀርቀር አድርጎ አሰብ አደረገ። በእርግጥ ልጆቹ የምርጥ ማህበረሰብ እና ግለሰብእ ፍልስፍናዎች መሀል አልፈው እየተጠረቡ የነበሩ ናቸው። ደግሞ መብሰላቸው ተዉቦ ማወቁንም ተያይዘውት አለ። መስ ዘወትር የእሚያብከነክነውን እያሳካ እንደሆነ እየተመለከተ ነበር። ለሀበሻዎች፤ በእርግጥ ወጥ የማደጊያ ስርኣት፣ በአዎንታአዊነት፣ ማህበረሰብአዊ ንቃት እና ተሳትፎ፣ በእራሳቸው አኗኗር መስፈርት ተመስርቶ አልዳበረላቸውም። የዓለሙን በህቡዕ መመንደግ ብናውቅ በሃገር ደረጃ ያሽቆለቆልንበትን፣ የመሰልጠን ምስጢር ቢገባን የስልጣኔ ጫፍ ቀለም የሆነውን፦ በግል የእማይቋጨው ዓለምን፣ በግል ተንደፋድፎ መበስበስን እንጂ በዘመን ተሻጋሪ አያያዝ በአንድነት ሆነን የነገ እእና መቶ አመቶች ኑሮ ማስተካከልን አናስብበትም፣ አንከውነውም። መስ ከሃሳቡ መለስ ብሎ ናሆምን ተመለከተ። “እንግዲህ ይሁንልህ! ምርቃት እንጂ ተቃውሞ የለኝም!” ፈገግ አለ።
እንደእሚወዱት የጎንለጎን እርምጃ እየተበላ ወደ ቤት መንደር ሲቀራረቡ ናሆም ጨዋታው ያነሳውን ጨዋታ መስጠት ፈለገ። ትዉልዱ ከአመል በላይ ያስፈልገዋል። “ባክህ አጭር ተመልካቾች ግን እንደሚያሰጋአቸው ያመል ብቻ አይደለም ፈተናአችን፤ ለነገሩ ያመል ነው ድህነት ብሎን ወዲያው አረንጓዴ ምድር ይዤ እራበኝ ሆዴን ብሎ አመል ሳይሆን እዉቀት እና የተተግባሪ ማመዛዘን ስልጣኔ እንዳጣን በራሱ መስክሯል፤” መስ ፈገግ አለ። “አመልም የስልጣኔ አንድ ቅልጥም አጥንት ነው እኮ!” መስ ጉዳዩን ትቶ ወደ ቀደመው ለመመለስ ባጭሩ “የመመፃደቁን ክፍል እንጂ የስልጣኔ ሁሉ መሰረት በእርግጥ ገጸባህሪን በእዉቀት እና ምርምር ማሰልጠኑ ነው፤ “የዓለም አለመቆም እና የኛ ቁምአሸልብ ህላዌ መብልን ነጥቆ ይጨርሰን ይሆናል። ምድር ሁሉ ድንገት በፀሐይ ጨረር መዛባት፣ ወረርሽኝ፣ ወል-አዉዳሚ (ማስ ዲስትራክሽን) ጦርነት ምናምን ብትጠፋ ሃገር እና ዜጋዎች ስምጥ ዋሻዎች ወሽቀው ማስቀጠያ ህግዎች እና ዝግጅቶች ያሏቸው ሃገሮች ቆየት ብለውም ባሉበት ዓለም፣ መብል ማምረት በቅጽበቶች እና ያለተለመደው እርሻ እሚከወን ተራ ነገር እየሆነ ነው። እንስሳ ስጋዎች እንኳ ህዋስአቸውን ወስደው በማርባት ስጋ ያመርታሉ። የእኛ ግብርና አንድም ተፈጥሮአዊ ምርት ስለሆነ እነእሱ እንዲመገቡት፣ አንድም እኛ ተመግበንው በአንጎል እና እና አካልአዊ ስነልቦና ያደጉ ማህበረሰቦች መሆን ስለሌለብን፣ አንድም መሬትአችን ተፈጥሮአዊ ምርት አቅሙን አበላሽቶ ይህን የአዲስ ቀላል ሰብል እና ስጋ ዉጤቶች ለመግዛት ገበያ እድል መሆን እንድንችል፣ አንድም በቂ መዳኒት እና ሳቁሶች መግዣ ዶላሮች ስናጣ ያለንን ግብርና ምርት መለወጥ ስለምንገደድ፣ አንድም ግብርና ምርቶቹን ዉጭ በመሸጡ ሰንሰለት እሚበለጸጉ ጥቂቶች ስላሉ፣ ብቻ ነገን እሚያስባት እና በህግ ከትቦ ጭንቀቷን እሚከለክልላት ብርሃኗን እሚያበራላት ስለሌለ፣ የነገው ግብርና ከዛሬው ባሽ ችግሮች በአስጊ እምቅ ደረጃ አሉት።” መስ በቀላሉ አስጀምሮት ብዙ በጎለጎለበት ነጥቡ ግራ ተጋባ። ዓይኖች ጠበብ አድርጎ ተመለከተው እና ናሆምን ማብራሪያ መጠየቁን በብሌኖቹ ተናገረ። ናሆም ባጭሩ ቋጨለት። “ማለቴ ግብርናአችን ነገው አይታወቅም። መንግስት ደግሞ በሬ እየተዋዋሱ ለየፊና ማረሱን እንኳ አላስቀረም። እንዴት ለነገው ዘመንአዊ ቀውስ ታምነው አለህ? አለሙ ብዙ ሲሄድ እዛው ቀርተን አለ። ግን አለሙ ከመመንጠቁ የተነሳ እዛው መቅረትም መንሸራተት ሆኖ አለ። ነጠላ፣ መስቀል፣ የድንግል ማሪያም እና ተክልዬ ስእሎች፣ አበሻ ቀሚሶች… በ ዶላር ከቻይና እየተገዙ ነው። ግን የተማረ ነገን ጠባቂ ስርአት የለንም። ዛሬን በዉጭ ጫንቃ መኖሩ በዝቷል። ብዙ አድገናል እሚል የ ጥሃም. ዘገባ በስነምጣኔ እና እድገት አመላካች መስፈርቶች ዉድቅ የተደረገ ሚዛን ይዘው አደግን ይበሉ እንጂ ወደ ጎንደር ታሪክ እንኳ አልቀረቡም። ጎንደር እራሷን ዘግታ እንደ ነበረው በወረርሽኝ አለም ቢዘጋን እንኳ መሰረትአዊ መዳኒቶች በራስ አቅም ማምረት እማንችል እንደሆንን ምሁሮች ይናገራሉ። እና የግብርናው ጉም ነገው እልፍ ችግሮች ኖሮት ምንም አኩሪ ነገር አለመመልከቱ ነው።”
መስ በአገኘው እይታ ብዙ ነገሮች አብሰለሰለ። አተያየቶቹን እያጋራው እና ብዙ ጨዋታዎችም እየፈጠሩ በመጨዋወት፣ በመሳሣቅ እና በማሰቦች እየተመላለሱ፣ ወደ ቤታቸው ቀረቡ። ‘ጎን ለ ጎን፤’

ጥቂት ተጉዘው ቤት ሲደርሱ እንጨትዎቹን አራገፉ። መስ ሂሳቡን ሰጥቶ ጋሪውን ለናሆም እንዲመልስ አዘዘ እና ወደ ጓሮ በመዞር ቋሚዎቹን በጉድጓድዎቹ አስቀምጦ በገመድ መትሮ ቀጥ ብለው እንዲሰለፉ አደረገ። ለቅስት ማቆም አንድ ማገር ሸርፎ ምሰሶውን ሊአጣብቅ ሲል ሚስማርዎች መግዛቱን እንደ ዘነጋ አስተዋለ። ወደ ጓሮ በሩ አዝግሞ በተከፈተ በሩ ድንገት ሲገባ እሚ ፊት ጋር ተፋጠጠ። ምሣ የተበላበት ዕቃ ታጥቦ ከገባበት አንስታ በመወልወል እሚ ተጠምዳ ልቧ ግን ተሰልቦ ፊቷ ላይ ዕንባ ይዘንብ ነበር። መስ መጥቶ መመልከቱን ስታይ ደንግጣ ፊትዋን በሳህን መወልወያ ጨርቁ ጠረገችው። ፈገግ በማለት ልትመለከተው ሞከረች። “ምንድነው የኔ እህት? ሰላም አይደለም?” ድንግር ብሎት እና ሆድ እየባሰው የትላንት ጭንቀቷ ትዝ ብሎት እራሱን እየረገመ ጠየቀ። “አይ ምንም እንዲሁ ነው መስፍን!” ፊትዋን መልሳ አዞረችበት። “ይህ ግልጽ ሃዘን ነው። ምን ሰምተሽ ነው?! ምን ችግር ገጠመሽ? ለኔ ሰትነግሪ ማን አለሽ? በይ ንገሪኝ አታስቀይሚኝ!” ቆጣ ብሎ መልስ ፈለገ። እሚ አሰብ አድርጋ አንድ ነገር ካልተናገረች እርሱ እንደ ሆነ እሚተዋት አይሆንም። “ያቺ አሰሪዬ አረፈች ብለው ትላንት እንደ ወጣችሁ መጥተው ነግረውኝ ነበር!” “እይ! ይቺ መስከረም እምትያት ወጣት?!” “አዎን! መኪና አደጋ!” ዕንባዋ መልሶ ቸፈፈ። ወዲአው አዘን ብሎ ቅጽበት እንደ ቆየ መስ ጉዳዩ ቀጥሎ ተገለጸለት። “ኡኡ! እና ገቢው ተቋረጠ እንዳትይኝ! የግል ንግድ ሰራተኛ ነገር!” ወደ ጉዳዩ ዘለቀ። “አዬ ማን እንደ እርሷ ሊአስቀጥለው ይችል አለ ብለህ! አሁንም ባለቤቷ ሥራዋን ሁሉ ጠቅልሎ ሲዘጋ ሽኝት ብሎ ጠርቶን እዛ ዉዬ ለምሳ ተጠርተን ገና አሁን መግባቴ እኮ ነው። እንደው ነገሩ አበቃቁ ይህ ሆነ ወይ ብዬ በሃዘን ልክ ስወሰድ ነው የተመለከትክኝ!” መስ በቤተሰቡ የዱብዕዳ ናዳ እንደ ዘነበ ተሰማ ው። “እና ገቢ…ሽ? አይ!” አናቱን ወዘወዘ። “ደህና እረዳት አጊንተሽ ነበር እቴ!” ደግሞ አስተዛዘነ። “ነበር የእኔ ወንድም! ነበር!” ዕንባዋን ደግማ ጠረገች። “እንግዲህ አሁን እዚህ አድርሼ ልጅዎቼን ምን ላድርግአቸው!?” በሰፊው እንባዋ ወረደ። ሣህኑን ወርወር አድርጋ አቀረቀረች። በቀሚሷ እጅጌ ዓይንዎችዋን ጠረገች። “አይ….! አጎደለችው ቤተሰቤን!” መልሳ ወደ ሰማይ ቀና አለች። “አበስኩ ገበርኩ! ነብስዋን ይማረው አምላክ! ገና ከመሞቷ ይህን ስል! ኧረ አፈሩን ገለባ ያድርገረላት! እንደው የልጆች ነገርም ሲታወሰኝ ነው እንጂ ሰው ሞቶ ይህን ማለት ተገቢም አልነበር! እንደው ይቅር ይበለኝ!” መስ በማጽናናቱ በረታ። “አይ ተገቢ ነው! ነብስዋን ይማረው በርግጥ ግን ላንቺ የእንጀራ ጉዳይ አለብሽ እኮ! ነውር አይደለም መጨነቅሽ! እ….” በሃሳብ ሰመጠ። መልሶ አጽናናት። “አይ ኧረ እኔ ከእንግዲህ አልጨነቅም፤ አምላክ አይወደውም። እንደው አስጨነኩህ አንተንም። ኑሮ እንደ እግዚእአብሔር ፈቃድ ይሆን አለ። እጅ አጣጥፎ መቀመጥ በርግጥ የለም። መስራት ይገባ አለ። ምን ይኸው እርሷ ብትታትረው አይደል ከመሬት ተነስታ የናጠጠችው። በመሥራት በመትጋት ነው እዚህ የደረስኩ፤ እናንተ ከእኔ በላይ ዉጭ ሀገርዎች መጓጓዙን ምኑቅጡን ታገኛላችሁ ብቻ በርቱ ትል እና ልጅዎቼን ትመካክርልኝ የነበረው! ከእኛ መንደር አይርቅም የተወለደችበት አይደል እሚሉት። ለሠራ እማ በአየሩ መንገድ አለ። ገንዘቡ አይታፈስ ተሰርቶ ነው። ለሠራ ካልተከለከለ ደግሞ ወገቤን ታጥቄ እኔም የአቅሜን እንግዲህ ጠላውን አረቄውን ልያያዘው እየአልኩኝ ነው። ሌላ እማ ምን መንገድ አለ መብራቱ? ምን መንገድ አለ ይሆን?”
መስ እንደ ሁልጊዜው ጥርሱን ነከስ እየአደረገ አሰላሰለ። ባነሳችው እራስ መለወጥ ሃሳብ መልሶ ተደሰተ። ተስፋ ያለ መሰለው። በባፎ ከመቅረት ቶሎ ወደ አንድ አማራጭ መመለሱ ጥቅም እና አዎንታአዊነት እንዳለው አመነ። “አይ መፍትሔ ከግል መፈለጉ ከፊ አይደለም በርግጥ!” ቀደም ብሎ የገዛውን የሚስማር ኪስወረቀት አንስቶ ወደ ዉጭ ለመዉጣት ተዘጋጀ። “እስቲ እናወራበት አለን። አንቺም ማሰቡን እና መስራቱን እንጂ ማዘኑን ተወት አድርጊ! ልጅዎቹም እንዳይመለከቱሽ ህፃናትዎች ይፈበሻሉ እና ሃዘንሽን አባርሪ! በይ አይዞሽ!” እህቱን አጽናንቶ ርጋታ ሲመለከትባት ተመለከተ። “እሺ! እኔ እማ ድንገት ትዝ ቢለኝ እንጂ ብለዙም ባዝን ለውጥ የለ። ትልቅ ሰው እንደ አልክው ከማዘን ወደ ማሰብ ቢመጣ እንጂ ሌላው ትርጉም የለውም። በል ሂድ እረጋ ብለህ ስራ አንተንም አስጨንቄአለሁ።” ጨለማ ከመርገም ሻማ መለኮስ! በሃሳቧ መስ ፈገግ ብሎ ወደ ሣህኗ ስትመለስ ትቷት ወደ ሳሎን አለፈ። ልጅዎች በቧልታይ (ኮሚክ) እይት (ሾው) ትመ. ስር ተሰድረው በማፍጠጥ ይዝናኑ ነበር። ካስቀመጠበት ሚስማርዎች አንስቶ ሳያስተውሉት እየመራረጠ በገባበት ተመልሶ ወጣ። ጓሮ እንደ ደረሰ እና አንድዋን ሚስማር እንደ መታ ናሆም ደረሰ። ልክ ናሆምን ሲመለከት ግን አንዳች የሃሳብ ጠጠር አናቱን ሸነቆረችው እና ክው አለ። የናሆም ሃሳብ ና የእሚ ሃሳብ የተገጣጠሙበት መሰለው። አንድ መምታት የጀመረውን ሚስማር ተወት አድርጎ፣ አሰብ አደረገ። የአንዣበበ እምቅ የዱብዕዳ መከንከን ፈጥሮ አለ። አንድ መፍትሔ በእራሱ መዉጫነት ሊአስመለከት ወደ ቤተሰቡ ዱብዕዳውን ተከትሎ በማሳደድ መጥቶ ከሆነ ሊመረምረው ዓይኖች አጥብቦ ቆየ። ናሆምን በመመልከት እሚን አሰላሰለ። ብልጭታው ትልቅ ሆኖ ልቡን ሲኮረኩረው፣ መዶሻውን ጥሎ ተራመደ፤ ናሆም ሲአየው “መጣሁ!”፤ ወደ እሚ ገሰገሰ፨

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
፬ የ ዱብዕዳ መከንከን ብልጭታ ወይም ገሃድን መቀበል

<p class="has-text-align-justify" value="<amp-fit-text layout="fixed-height" min-font-size="6" max-font-size="72" height="80">ሳያረጅ መተኛት የቀንተቀባይነት ቅድመሁኔታ ነው። ለስኩ አኗኗር የስልት ጮራ ስለሆነ፣ ያ ደግሞ ግድ ነው። ከማለዳ ድባብ ተቋድሶ ቀንን መጀመር፣ ከቀንተቀላቃዩ ባዶ ጣት ይዞ ወደቀን መምጣት እሚለይ ነው። የጂም ዴቪስ ጋርፊልድን መቼም ማለምም አይታሰብም። በእርግጥ ድመት እንቅልፋም ስለሆነ፣ የእሱ ስብከት ህጸፅ የለውም። ድመት ከመተኘት ወዲያ ምን ያውቅ አለ። ሰው ጋርፊልድን ልሁን ካለ ግን አንጎሉ ተዛብቷል ማለት ነው። በቀንተቀባይነትአችን የህይወት ሽልማት አለን። በሂወትአችን አንድ ጣት ላይ ቀለበት አርጎ ሲያጌጡ እንደእሚውሉ እመስቶች መመረቅ ያክል ነው። ለተፈጥሮ መስህብ በቋሚነት በመጋለጥ፣ በቋም የግለትምምን ላይ ተፈናጥጦ መዋል ነው። ይህ በእርግጥ የስብእና ማዘመኛ አንዱ ጎዳናው ነው፨<br>ይህን በምልዓት ያስተማረው መስ፣ ምሽቱ ቤተሰቡን በደግ መቀላቀል ቀጥሎለት አልፎ ሲመሻሽ ወደ ሦስት ከኩርማን ሰዓት ገደማ፣ ደካክሞት፣ ሁሌም እንደ እሚደሚያረገው፣ ከናሆም ጎን ወደ መኝታ ወጣ። ካሳለፉት ማለዳ ተስፈንጥረው የተገኙበት ማታው ድረስ የነበረ አዋዋልን እሚፈትሽ የአኳኋን ቅኝት በእየፊናአቸው ልክ ከማሸለቡ ቀድሞ አደረጉ። መስ አዲስአበባ ጧት ሲነቃ፣ ሲጓዝ እና ቤተሰቡን ፋሲካይት ተቀላቅሎ ሲውል፣ ከናሆም የበለጠ ሲቀራረብ እና ደከምብሎ ሲገኝ ሳለ። ናሆምም የቀኑን ዉሎ በአስር ሰከንድ ጠቅለል አድርጎ አሠበው። ሁለቱም ደስተኛ ነበሩ። ቅሬታ ከነበረብአቸው መረመሩ። ዋናው ያ ነው። በደስታ ለመኖር ስዉር ቅሬታን እንዳይቀበርብን መፈለጉ እና ማወራረዱ ተገቢ ነው። ምንም አሁን ያሳሰባቸው ነገር ስላልነበር ይህቢሆን ያሉት ነገር ሳይኖር ደስታን ብቻ አገኙ። ቅር ያሰኘ ሰውም ሁኔታም የለም። እሚያሳዝን እና እሚያስከፋ ሁኔታም አልገጠመም። ስለእዚህ በደስታ ተንሳፈፉ። ይህ የዳበረ እና ስለተዘወተረ ቀላል የሆነ ጸባይ፣ የዕለት ዉሎ አርኪ ከነበረ፣ እሚገፈፍ ከነበረው ይፈልግ አለ። በጠቅላላው የአኗኗር ዝብርቅርቅ እሚአጠልል፣ ስስ ግለቅኝት ነው። ግን ከስኬትአማ አኗኗር ምክርነቱ በዘለለ የስነልቦና ሰባኪዎችም እሚያነሱት ምርጥ ተሞክሮ ነበር። ጭንቅላት በአዋዋል ዉጣዉረዶች እንደ ተሸበበ መተኛት ጎጂ ነው። በቀጥታ ድሃ አድራጊ ነው። ከገንዘብም ከጤናም አው በቀጥታ እሚተሳሰር ነው። ምክንያቱም፣ ሰው ቢአንቀላፋም፣ ተመርምረው ያልተዘጉ ጉዳይዎችን አንጎል በስዉር ያመነዥክ አለ። እየተብከነከኑ ወደ እንቅልፍ ቢኬድ አርኪ እንቅልፍ ማጣት ሆኖ፣ አካል አርፎ አልነቃ ብሎ፣ እንዲሁም ጤና-ነስነት ይፈጥር አለ። አካል ሲተኛ ጆሮ ካልተጮኸ አያደምጥም፣ ቢሰማም። ሌላውም አካል እንደእዛው እሚተኛ ጊዜ እሚዘጋ ነው። ሰው እስከ 80በመቶ አካሉ ሁሉ እንደ ሞተ እሚከረቸም ነው። ግን አንጎል ከተብከነከነ፣ ሰላም ካልተያዘ፣ መተኛቱ ያነሰ አካልአዊ እረፍት ሰጪ ነው። ያም የእልፎች ሂወትን አቆርቋዥ በይፋ ግን እማይጠና ነው። በተለይ በድሃ ሃገር ለመሃይም መሪዎች ቅንጦት ስለሆነ ህዝቡ ዳቦ ስለእሚያልም ማንም አይነካውም። ቢሆንም፣ ሃቁ እንዳጠቃን መኖረጀ አልቀረም። እነናሆም ይህን ደርሰውበት አሁንም እረጂ መሪ በሌለበት ሃገር ግለመሪነት እሚያሠማሩ ሆኑ፦ በግል እና ቤተሰብዎች ላይ። ይህን ስስ አሠሳ አድርገው ከጭንቀት እረፍት እንደ አገኙ ሁለተኛው ቀላል እና ሂወት አፍጋጊ ክወና (በተይ ለሀበሻ) ደግሞ ቀጥሎ ይተወን አለ። ይህም፦ ከራስጸጉር እስከ እግርጥፍር፣ አካልዎችአቸው፣ በሞላ ምቹ እረፍት ላይ እንደ ሆኑ ይፈተሻሉ። የአልተመቸ የከንፈር አቀማመጥ ካለ፣ የክንድ ላይ ጫና ማብዛት ካለ፣ የመደበቅ ስነልቦና ካለ፣ ጉልበት አቀማመጡ ከተጨናነቀ፣ አንገት እና አናት ዘና ያለ አቀማመጥ ካጡ፣ ትራስ ካስቸገረ፣ ብቻ ሁሉም አካላት ላይ መፍታታት እሚገኝ እንደሆነ ይፈተሹ አለ። በተለየ የሰውልጅ ፊቱ በመቶ ምናምን ፊትገጽታዎች (ጀስቸር) በእየሰከንዱ ስለእሚገለጥ እና አንድ የስሜት ነጸብራቅ የሆነ ቅርጽ በማንኛውም ቅጽበት ሰርቶ የሰውንልጅ ስለእሚአስቸግር፣ ሰው ሁሉ ሲተኛ ነብሱ አብሮ ዘና እንዲል፣ የፊት ስሜት እንደ ተስተካከለ ማረጋገጥ ያስፈልግ አለ። በቀረ፣ ሰላምአዊ እንቅልፍ ያሳጣ ዘንድ የተጠና ጥበብ ነው። መስ ይህን በእሚገባ ሲአስተምረው፣ ናሆም መጀመሪያ የምር አልመሰለውም ነበር። ግን ተወራረዱ እና ተኝተው ፊቱን በመረመረ ጊዜ አንድአች የስሜት ገጽታ በፊቱ ወዲአው ወዲአው እየተለዋወጠ ይገኝ እንደነበር ፈትሾ አገኘ። ፊትን ከፈተሹት የሚቀያየር ገጽታ እንደስሜትአችን እሚያስመለክት ነው። በበይነመረብም አሠሳ ብዙ ጉልጎላዎች አድርጎ ተገረመ። “አርኪ እንቅልፍ ስምጥ ፍልስፍና አለው። ሌላ የስኬትአማ ሰውዎች ዐብይ ምስጢርም ነው።” መስ የአስተምህሮቱን ነጥቡን ለተገነዘበ ናሆም እንደመጠቅለያ አክሎ ወደ አካል ፈትሾ አመቻችቶ መተኛት ዘወትርአዊ ባህሉ አደረሰው፨ሳያረጅ መተኛት የቀንተቀባይነት ቅድመሁኔታ ነው። ለስኩ አኗኗር የስልት ጮራ ስለሆነ፣ ያ ደግሞ ግድ ነው። ከማለዳ ድባብ ተቋድሶ ቀንን መጀመር፣ ከቀንተቀላቃዩ ባዶ ጣት ይዞ ወደቀን መምጣት እሚለይ ነው። የጂም ዴቪስ ጋርፊልድን መቼም ማለምም አይታሰብም። በእርግጥ ድመት እንቅልፋም ስለሆነ፣ የእሱ ስብከት ህጸፅ የለውም። ድመት ከመተኘት ወዲያ ምን ያውቅ አለ። ሰው ጋርፊልድን ልሁን ካለ ግን አንጎሉ ተዛብቷል ማለት ነው። በቀንተቀባይነትአችን የህይወት ሽልማት አለን። በሂወትአችን አንድ ጣት ላይ ቀለበት አርጎ ሲያጌጡ እንደእሚውሉ እመስቶች መመረቅ ያክል ነው። ለተፈጥሮ መስህብ በቋሚነት በመጋለጥ፣ በቋም የግለትምምን ላይ ተፈናጥጦ መዋል ነው። ይህ በእርግጥ የስብእና ማዘመኛ አንዱ ጎዳናው ነው፨

<p class="has-text-align-justify" value="<amp-fit-text layout="fixed-height" min-font-size="6" max-font-size="72" height="80">ጥቂት ተጉዘው ቤት ሲደርሱ እንጨትዎቹን አራገፉ። መስ ሂሳቡን ሰጥቶ ጋሪውን ለናሆም እንዲመልስ አዘዘ እና ወደ ጓሮ በመዞር ቋሚዎቹን በጉድጓድዎቹ አስቀምጦ በገመድ መትሮ ቀጥ ብለው እንዲሰለፉ አደረገ። ለቅስት ማቆም አንድ ማገር ሸርፎ ምሰሶውን ሊአጣብቅ ሲል ሚስማርዎች መግዛቱን እንደ ዘነጋ አስተዋለ። ወደ ጓሮ በሩ አዝግሞ በተከፈተ በሩ ድንገት ሲገባ እሚ ፊት ጋር ተፋጠጠ። ምሣ የተበላበት ዕቃ ታጥቦ ከገባበት አንስታ በመወልወል እሚ ተጠምዳ ልቧ ግን ተሰልቦ ፊቷ ላይ ዕንባ ይዘንብ ነበር። መስ መጥቶ መመልከቱን ስታይ ደንግጣ ፊትዋን በሳህን መወልወያ ጨርቁ ጠረገችው። ፈገግ በማለት ልትመለከተው ሞከረች። “ምንድነው የኔ እህት? ሰላም አይደለም?” ድንግር ብሎት እና ሆድ እየባሰው የትላንት ጭንቀቷ ትዝ ብሎት እራሱን እየረገመ ጠየቀ። “አይ ምንም እንዲሁ ነው መስፍን!” ፊትዋን መልሳ አዞረችበት። “ይህ ግልጽ ሃዘን ነው። ምን ሰምተሽ ነው?! ምን ችግር ገጠመሽ? ለኔ ሰትነግሪ ማን አለሽ? በይ ንገሪኝ አታስቀይሚኝ!” ቆጣ ብሎ መልስ ፈለገ። እሚ አሰብ አድርጋ አንድ ነገር ካልተናገረች እርሱ እንደ ሆነ እሚተዋት አይሆንም። “ያቺ አሰሪዬ አረፈች ብለው ትላንት እንደ ወጣችሁ መጥተው ነግረውኝ ነበር!” “እይ! ይቺ መስከረም እምትያት ወጣት?!” “አዎን! መኪና አደጋ!” ዕንባዋ መልሶ ቸፈፈ። ወዲአው አዘን ብሎ ቅጽበት እንደ ቆየ መስ ጉዳዩ ቀጥሎ ተገለጸለት። “ኡኡ! እና ገቢው ተቋረጠ እንዳትይኝ! የግል ንግድ ሰራተኛ ነገር!” ወደ ጉዳዩ ዘለቀ። “አዬ ማን እንደ እርሷ ሊአስቀጥለው ይችል አለ ብለህ! አሁንም ባለቤቷ ሥራዋን ሁሉ ጠቅልሎ ሲዘጋ ሽኝት ብሎ ጠርቶን እዛ ዉዬ ለምሳ ተጠርተን ገና አሁን መግባቴ እኮ ነው። እንደው ነገሩ አበቃቁ ይህ ሆነ ወይ ብዬ በሃዘን ልክ ስወሰድ ነው የተመለከትክኝ!” መስ በቤተሰቡ የዱብዕዳ ናዳ እንደ ዘነበ ተሰማ ው። “እና ገቢ…ሽ? አይ!” አናቱን ወዘወዘ። “ደህና እረዳት አጊንተሽ ነበር እቴ!” ደግሞ አስተዛዘነ። “ነበር የእኔ ወንድም! ነበር!” ዕንባዋን ደግማ ጠረገች። “እንግዲህ አሁን እዚህ አድርሼ ልጅዎቼን ምን ላድርግአቸው!?” በሰፊው እንባዋ ወረደ። ሣህኑን ወርወር አድርጋ አቀረቀረች። በቀሚሷ እጅጌ ዓይንዎችዋን ጠረገች። “አይ….! አጎደለችው ቤተሰቤን!” መልሳ ወደ ሰማይ ቀና አለች። “አበስኩ ገበርኩ! ነብስዋን ይማረው አምላክ! ገና ከመሞቷ ይህን ስል! ኧረ አፈሩን ገለባ ያድርገረላት! እንደው የልጆች ነገርም ሲታወሰኝ ነው እንጂ ሰው ሞቶ ይህን ማለት ተገቢም አልነበር! እንደው ይቅር ይበለኝ!” መስ በማጽናናቱ በረታ። “አይ ተገቢ ነው! ነብስዋን ይማረው በርግጥ ግን ላንቺ የእንጀራ ጉዳይ አለብሽ እኮ! ነውር አይደለም መጨነቅሽ! እ….” በሃሳብ ሰመጠ። መልሶ አጽናናት። “አይ ኧረ እኔ ከእንግዲህ አልጨነቅም፤ አምላክ አይወደውም። እንደው አስጨነኩህ አንተንም። ኑሮ እንደ እግዚእአብሔር ፈቃድ ይሆን አለ። እጅ አጣጥፎ መቀመጥ በርግጥ የለም። መስራት ይገባ አለ። ምን ይኸው እርሷ ብትታትረው አይደል ከመሬት ተነስታ የናጠጠችው። በመሥራት በመትጋት ነው እዚህ የደረስኩ፤ እናንተ ከእኔ በላይ ዉጭ ሀገርዎች መጓጓዙን ምኑቅጡን ታገኛላችሁ ብቻ በርቱ ትል እና ልጅዎቼን ትመካክርልኝ የነበረው! ከእኛ መንደር አይርቅም የተወለደችበት አይደል እሚሉት። ለሠራ እማ በአየሩ መንገድ አለ። ገንዘቡ አይታፈስ ተሰርቶ ነው። ለሠራ ካልተከለከለ ደግሞ ወገቤን ታጥቄ እኔም የአቅሜን እንግዲህ ጠላውን አረቄውን ልያያዘው እየአልኩኝ ነው። ሌላ እማ ምን መንገድ አለ መብራቱ? ምን መንገድ አለ ይሆን?”<br>መስ እንደ ሁልጊዜው ጥርሱን ነከስ እየአደረገ አሰላሰለ። ባነሳችው እራስ መለወጥ ሃሳብ መልሶ ተደሰተ። ተስፋ ያለ መሰለው። በባፎ ከመቅረት ቶሎ ወደ አንድ አማራጭ መመለሱ ጥቅም እና አዎንታአዊነት እንዳለው አመነ። “አይ መፍትሔ ከግል መፈለጉ ከፊ አይደለም በርግጥ!” ቀደም ብሎ የገዛውን የሚስማር ኪስወረቀት አንስቶ ወደ ዉጭ ለመዉጣት ተዘጋጀ። “እስቲ እናወራበት አለን። አንቺም ማሰቡን እና መስራቱን እንጂ ማዘኑን ተወት አድርጊ! ልጅዎቹም እንዳይመለከቱሽ ህፃናትዎች ይፈበሻሉ እና ሃዘንሽን አባርሪ! በይ አይዞሽ!” እህቱን አጽናንቶ ርጋታ ሲመለከትባት ተመለከተ። “እሺ! እኔ እማ ድንገት ትዝ ቢለኝ እንጂ ብለዙም ባዝን ለውጥ የለ። ትልቅ ሰው እንደ አልክው ከማዘን ወደ ማሰብ ቢመጣ እንጂ ሌላው ትርጉም የለውም። በል ሂድ እረጋ ብለህ ስራ አንተንም አስጨንቄአለሁ።” ጨለማ ከመርገም ሻማ መለኮስ! በሃሳቧ መስ ፈገግ ብሎ ወደ ሣህኗ ስትመለስ ትቷት ወደ ሳሎን አለፈ። ልጅዎች በቧልታይ (ኮሚክ) እይት (ሾው) ትመ. ስር ተሰድረው በማፍጠጥ ይዝናኑ ነበር። ካስቀመጠበት ሚስማርዎች አንስቶ ሳያስተውሉት እየመራረጠ በገባበት ተመልሶ ወጣ። ጓሮ እንደ ደረሰ እና አንድዋን ሚስማር እንደ መታ ናሆም ደረሰ። ልክ ናሆምን ሲመለከት ግን አንዳች የሃሳብ ጠጠር አናቱን ሸነቆረችው እና ክው አለ። የናሆም ሃሳብ ና የእሚ ሃሳብ የተገጣጠሙበት መሰለው። አንድ መምታት የጀመረውን ሚስማር ተወት አድርጎ፣ አሰብ አደረገ። የአንዣበበ እምቅ የዱብዕዳ መከንከን ፈጥሮ አለ። አንድ መፍትሔ በእራሱ መዉጫነት ሊአስመለከት ወደ ቤተሰቡ ዱብዕዳውን ተከትሎ በማሳደድ መጥቶ ከሆነ ሊመረምረው ዓይኖች አጥብቦ ቆየ። ናሆምን በመመልከት እሚን አሰላሰለ። ብልጭታው ትልቅ ሆኖ ልቡን ሲኮረኩረው፣ መዶሻውን ጥሎ ተራመደ፤ ናሆም ሲአየው “መጣሁ!”፤ ወደ እሚ ገሰገሰ፨ጥቂት ተጉዘው ቤት ሲደርሱ እንጨትዎቹን አራገፉ። መስ ሂሳቡን ሰጥቶ ጋሪውን ለናሆም እንዲመልስ አዘዘ እና ወደ ጓሮ በመዞር ቋሚዎቹን በጉድጓድዎቹ አስቀምጦ በገመድ መትሮ ቀጥ ብለው እንዲሰለፉ አደረገ። ለቅስት ማቆም አንድ ማገር ሸርፎ ምሰሶውን ሊአጣብቅ ሲል ሚስማርዎች መግዛቱን እንደ ዘነጋ አስተዋለ። ወደ ጓሮ በሩ አዝግሞ በተከፈተ በሩ ድንገት ሲገባ እሚ ፊት ጋር ተፋጠጠ። ምሣ የተበላበት ዕቃ ታጥቦ ከገባበት አንስታ በመወልወል እሚ ተጠምዳ ልቧ ግን ተሰልቦ ፊቷ ላይ ዕንባ ይዘንብ ነበር። መስ መጥቶ መመልከቱን ስታይ ደንግጣ ፊትዋን በሳህን መወልወያ ጨርቁ ጠረገችው። ፈገግ በማለት ልትመለከተው ሞከረች። “ምንድነው የኔ እህት? ሰላም አይደለም?” ድንግር ብሎት እና ሆድ እየባሰው የትላንት ጭንቀቷ ትዝ ብሎት እራሱን እየረገመ ጠየቀ። “አይ ምንም እንዲሁ ነው መስፍን!” ፊትዋን መልሳ አዞረችበት። “ይህ ግልጽ ሃዘን ነው። ምን ሰምተሽ ነው?! ምን ችግር ገጠመሽ? ለኔ ሰትነግሪ ማን አለሽ? በይ ንገሪኝ አታስቀይሚኝ!” ቆጣ ብሎ መልስ ፈለገ። እሚ አሰብ አድርጋ አንድ ነገር ካልተናገረች እርሱ እንደ ሆነ እሚተዋት አይሆንም። “ያቺ አሰሪዬ አረፈች ብለው ትላንት እንደ ወጣችሁ መጥተው ነግረውኝ ነበር!” “እይ! ይቺ መስከረም እምትያት ወጣት?!” “አዎን! መኪና አደጋ!” ዕንባዋ መልሶ ቸፈፈ። ወዲአው አዘን ብሎ ቅጽበት እንደ ቆየ መስ ጉዳዩ ቀጥሎ ተገለጸለት። “ኡኡ! እና ገቢው ተቋረጠ እንዳትይኝ! የግል ንግድ ሰራተኛ ነገር!” ወደ ጉዳዩ ዘለቀ። “አዬ ማን እንደ እርሷ ሊአስቀጥለው ይችል አለ ብለህ! አሁንም ባለቤቷ ሥራዋን ሁሉ ጠቅልሎ ሲዘጋ ሽኝት ብሎ ጠርቶን እዛ ዉዬ ለምሳ ተጠርተን ገና አሁን መግባቴ እኮ ነው። እንደው ነገሩ አበቃቁ ይህ ሆነ ወይ ብዬ በሃዘን ልክ ስወሰድ ነው የተመለከትክኝ!” መስ በቤተሰቡ የዱብዕዳ ናዳ እንደ ዘነበ ተሰማ ው። “እና ገቢ…ሽ? አይ!” አናቱን ወዘወዘ። “ደህና እረዳት አጊንተሽ ነበር እቴ!” ደግሞ አስተዛዘነ። “ነበር የእኔ ወንድም! ነበር!” ዕንባዋን ደግማ ጠረገች። “እንግዲህ አሁን እዚህ አድርሼ ልጅዎቼን ምን ላድርግአቸው!?” በሰፊው እንባዋ ወረደ። ሣህኑን ወርወር አድርጋ አቀረቀረች። በቀሚሷ እጅጌ ዓይንዎችዋን ጠረገች። “አይ….! አጎደለችው ቤተሰቤን!” መልሳ ወደ ሰማይ ቀና አለች። “አበስኩ ገበርኩ! ነብስዋን ይማረው አምላክ! ገና ከመሞቷ ይህን ስል! ኧረ አፈሩን ገለባ ያድርገረላት! እንደው የልጆች ነገርም ሲታወሰኝ ነው እንጂ ሰው ሞቶ ይህን ማለት ተገቢም አልነበር! እንደው ይቅር ይበለኝ!” መስ በማጽናናቱ በረታ። “አይ ተገቢ ነው! ነብስዋን ይማረው በርግጥ ግን ላንቺ የእንጀራ ጉዳይ አለብሽ እኮ! ነውር አይደለም መጨነቅሽ! እ….” በሃሳብ ሰመጠ። መልሶ አጽናናት። “አይ ኧረ እኔ ከእንግዲህ አልጨነቅም፤ አምላክ አይወደውም። እንደው አስጨነኩህ አንተንም። ኑሮ እንደ እግዚእአብሔር ፈቃድ ይሆን አለ። እጅ አጣጥፎ መቀመጥ በርግጥ የለም። መስራት ይገባ አለ። ምን ይኸው እርሷ ብትታትረው አይደል ከመሬት ተነስታ የናጠጠችው። በመሥራት በመትጋት ነው እዚህ የደረስኩ፤ እናንተ ከእኔ በላይ ዉጭ ሀገርዎች መጓጓዙን ምኑቅጡን ታገኛላችሁ ብቻ በርቱ ትል እና ልጅዎቼን ትመካክርልኝ የነበረው! ከእኛ መንደር አይርቅም የተወለደችበት አይደል እሚሉት። ለሠራ እማ በአየሩ መንገድ አለ። ገንዘቡ አይታፈስ ተሰርቶ ነው። ለሠራ ካልተከለከለ ደግሞ ወገቤን ታጥቄ እኔም የአቅሜን እንግዲህ ጠላውን አረቄውን ልያያዘው እየአልኩኝ ነው። ሌላ እማ ምን መንገድ አለ መብራቱ? ምን መንገድ አለ ይሆን?”
መስ እንደ ሁልጊዜው ጥርሱን ነከስ እየአደረገ አሰላሰለ። ባነሳችው እራስ መለወጥ ሃሳብ መልሶ ተደሰተ። ተስፋ ያለ መሰለው። በባፎ ከመቅረት ቶሎ ወደ አንድ አማራጭ መመለሱ ጥቅም እና አዎንታአዊነት እንዳለው አመነ። “አይ መፍትሔ ከግል መፈለጉ ከፊ አይደለም በርግጥ!” ቀደም ብሎ የገዛውን የሚስማር ኪስወረቀት አንስቶ ወደ ዉጭ ለመዉጣት ተዘጋጀ። “እስቲ እናወራበት አለን። አንቺም ማሰቡን እና መስራቱን እንጂ ማዘኑን ተወት አድርጊ! ልጅዎቹም እንዳይመለከቱሽ ህፃናትዎች ይፈበሻሉ እና ሃዘንሽን አባርሪ! በይ አይዞሽ!” እህቱን አጽናንቶ ርጋታ ሲመለከትባት ተመለከተ። “እሺ! እኔ እማ ድንገት ትዝ ቢለኝ እንጂ ብለዙም ባዝን ለውጥ የለ። ትልቅ ሰው እንደ አልክው ከማዘን ወደ ማሰብ ቢመጣ እንጂ ሌላው ትርጉም የለውም። በል ሂድ እረጋ ብለህ ስራ አንተንም አስጨንቄአለሁ።” ጨለማ ከመርገም ሻማ መለኮስ! በሃሳቧ መስ ፈገግ ብሎ ወደ ሣህኗ ስትመለስ ትቷት ወደ ሳሎን አለፈ። ልጅዎች በቧልታይ (ኮሚክ) እይት (ሾው) ትመ. ስር ተሰድረው በማፍጠጥ ይዝናኑ ነበር። ካስቀመጠበት ሚስማርዎች አንስቶ ሳያስተውሉት እየመራረጠ በገባበት ተመልሶ ወጣ። ጓሮ እንደ ደረሰ እና አንድዋን ሚስማር እንደ መታ ናሆም ደረሰ። ልክ ናሆምን ሲመለከት ግን አንዳች የሃሳብ ጠጠር አናቱን ሸነቆረችው እና ክው አለ። የናሆም ሃሳብ ና የእሚ ሃሳብ የተገጣጠሙበት መሰለው። አንድ መምታት የጀመረውን ሚስማር ተወት አድርጎ፣ አሰብ አደረገ። የአንዣበበ እምቅ የዱብዕዳ መከንከን ፈጥሮ አለ። አንድ መፍትሔ በእራሱ መዉጫነት ሊአስመለከት ወደ ቤተሰቡ ዱብዕዳውን ተከትሎ በማሳደድ መጥቶ ከሆነ ሊመረምረው ዓይኖች አጥብቦ ቆየ። ናሆምን በመመልከት እሚን አሰላሰለ። ብልጭታው ትልቅ ሆኖ ልቡን ሲኮረኩረው፣ መዶሻውን ጥሎ ተራመደ፤ ናሆም ሲአየው “መጣሁ!”፤ ወደ እሚ ገሰገሰ፨

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

By Binyamhailemeskel

Hey there! If you want to know about me, I just like fun, commonsense wisdom, and human love. Let us live a bright today changing tomorrow into brighter.
Regards,

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s