Categories
My Outlet (የግል ኬላ)

ምእራፍ-፮

መስፍን ጎንለጎን ምእራፍ ፮፨

፮ ወለል እና ምርኮ

ምእራፍ ስድስት በ ተአዶ. (PDF).

ዳግ-በወጣ ጎኅ የቤተሰቡ ዓዉራ የሆነው መስ እና የመንፈስ ደቀመዝሙሩ ናሆም ብሩን አንቅተው ወደ ዉጭ ወጡ። ብሩ ማንንም ታናሽ ወንድም ሳይቀጣ የተገረሰሰ አካሉን ከእስራት በርጋታ ብቻ አስለቅቆ ተከተላቸው። ተገቢ የጉርድ ሱሪዎች በመልበስ፣ ጥርሶች እና ፊት አጥርቶ ከመታጠብ በኋላ፣ ለረዘመ እሩጫ ተዘጋጁ፨
“እሺ! ከዚህ ወጥተን ከተማውን ዳር ለዳር ሰዓትኛ (ክሎክዋይስ) ዞረን መመለስ ነው!” ናሆም ሰውነት በማማሟቅ ሆኖ ለወንድሙ አብራራ። ብሩ ገሸሽ አለው ከመስማቱ ገና። በማይታወቅ ዝግተኛ ስልት ማማሟቅ እየከወነ መሰላቸው እና “እቀረጩ፤ ምን ያክል ነው ግን?” ብሎ ጠየቀ። መስ ወደ አፈሩ ወርዶ የእግሮች ጉልበት ዘርግቶ በመለጠጥ መቀመጫውን መሬት እንዲነካ ካደረገ ኋላ ግንባሩን ከጉልበቱ አጣበቀ። በሌላ እግር መወጠር መልሶ ግንባሩን ደፈቀ እና ቆየ። ናሆም የእጅ ማፍታታትዎች አድርጎ ወደ ወገብ መለጠጥዎች ገባ። ብሩ መልስ ስላጣ እርቀቱ እንደ እሚከብድ ሳለ። አሁንም እጆች በማወናጨፍ ሆኖ ጠየቀ። “ምን ያክል ነው ርቀቱ ግን ይሄ ፊያቶ ወጣን እምትሉት ነገር?” ሲል ደግሞ ጠየቀ። ናሆም አንድ እግር አንስቶ በአየሩ ከአናቱ በላይ በመስቀል ቆየት በማለት ሲለማመድ ቆየ እና “አስር ኪሎ ሜትሮች አካባቢ! ግን ዉስጥ ለዉስጥ ሮጠን ከድንጋይ ማዉጫው በላይ ደግሞ እንቅስቃሴዎች እንቀጥል አለ። ያንን ትተህ ተለይተህን ግባ።”
መስ ተነስቶ እጅ ሰዓቱን ተመለከተ። ቆጣሪዋ አስራሁለት ሰዓት እንደደፈነች ታሳይ ነበር። “እንዉጣ አንበሣዎች!” ዱብዱብ በማለት መራ። ናሆም እና ብሩ ተከተሉ። ከቤትአቸው ራቅ ብለው እንደ ሮጡ ብሩ በከፍተኛ ማለክለክ ተወረሰ። ናሆም ሳቅ ቀደመው። ይባስ ብሎ ቀረት ቀረት ማለት ግን ሲርቅም የብሩ ትትፋሽ ዘልጎ መሰማት ጀመረ። መስም ፈገግ አለ። ናሆም ለር ብሎ ወደ ተጎተተ ወንድሙ እየተመለከተ ወደ መስ በጀርባው መሮጥ ጀመረ እና “ገና ፍጥነት አልጀመርንም! በርታ በርታ በል!” አለው። ብሩ ግማሽ ኪሎ ሜትር እንደ ደረሰ ከቶ ቆመ። አንድ መንደር ገብተው ስለነበር ዉሻዎች በመጮኽ መንደሩን አወኩት። ናሆም ከ መስ በመለየት ወደ ወንድሙ ተመልሶ ሮጠ፨
“በቃ ተከተለን! ይህ መንገድ እስከ ጊቢው ያወጣን አለ!” “ኅዋአዊከተማ ው?!” ብሩ በጩኸት እጅዎች በወገብ አድርጎ ቆሞ ጠየቀ። ናሆም አናቱን ነቀነቀ። “ኧረ! ቅጣት ነው እንዴ?!” “ከእዛ ወደ ጊቢው በር ሚወስደውን መንገድ አትከተል። ከጊቢው ጀርባ ነው እምንከብበው። ጊቢውን ዙር እና መልሶ ሌላ መንገድ ይሰጥህ አለ። እርሱን ይዘህ ስትከተል እዚህ እኛ ቤት ትገባ አለህ። ካልደከምህ ጫካው ጋር ና!” ናሆም የወንድሙን ትከሻ ነካነካ አደረገ። “በርታ! በዝግታ እና በአጠረ ርቀት ጀምር! በአንዴ ቀነኒሳን መሆን የለም! ቀጣይ ታሻሽለው አለህ! ጀምር ጀምር!” ብሩ የልብ ልብ ተሰምቶት ተከተለው። ወንድሙ ግን በዝግታ ሲሮጥ ቢቆይም ብሩ መድከሙ ቀጠለ። ሁለት ኪሎሜትሮች እንደ ምንም እሮጠ። በጉልበትዎቹ እጅዎቹን ጭኖ በመስገድ አለከለከ። ወንድሙ ከ መሮጥ ማሮጥ እንዲሻል ዐዉቆ ዘገየ። እያበረታው ስድሥት ኪሎሜትርዎች ሮጠ። በቆይታዎች እየታገዘ ግን በኅዋአዊከተማ ው አጥር ደረሰ። ብሩ ማመን አልቻለም። እርቀቱ ከቤትአቸው ከፍተኛ ነበር። ወንድሙን ተደግፎ ቆመ። ብዙ ተነፈሰ። “አምስት ኪሎ ሜትርዎች…እ..ህ! አልሆነም?” ናሆም ፈገገ። “አስራ አንድ ኪሎሜትርዎች ሆነ!” ብሩ በጩኸት ቦረቀ። ናሆም ርቀቱን ሸሽጎት ነበር። ብዙ ጮኾ ደጋግሞ ለመለማመድ ወስኖ፣ በዝግታ ልከተል ወንድሙን አሰናበተ፨
ናሆም በፈጠነ እግርዎች አጣጣል ከተማውን በመክበብ ሮጦ ቤትአቸውን አልፎ ወደ ጫካው ደረሰ። መስ የግል እንቅስቃሴዎቹን ሲሰራ አገኘው። “ወንድምህ ባንዴ ቀድሞኝ፣ ደርቦን ቤት ሲገባ አላገኘውም?” ናሆም ሳቀ። “መመለሱም ጀግና ነው!” ናሆም አብሮት አካል አቀልጣፊ እሽክርክሪትዎች ሲለማመድ ቆየ። አምስት አርባ እሚሰኝ አመታት በእሚገባ አዳብሮት ሁለት ሰዓት ሲል ወደ ቤት ተመለሱ፨

ምእራፉን በ ተአዶdrivesdk

<p class="has-text-align-justify" value="<amp-fit-text layout="fixed-height" min-font-size="6" max-font-size="72" height="80">ብሩ ን ጠርቶ ቁርስ በልተው ሲነሱ እነ ናሆም መግባትአቸው ነበር። “በሉ ሰዉነቴ ጓጉሎ አለ! ዕድሜ ለእናንተ እሩጫው ስለ ገደለኝ ጊቢ ገብተን በይነመረብ በመጠቀም መጎለቱ ብቻ ነው አማራጬ! መንቀሳቀሱ እንደሁ አይቻልም!” መስ “ምንም አይደለም!” ብሎ በሽሙጥ፣ በግልፅ መመስገን እንደ ነበረበት አሳበቀበ። “አዎን! ናሆም ዉድ ወንድሜ! አመሰግንህ አለሁ! ቀጣይ ሳምንት እንገናኝ! አስራአንድ!” ድምፅ ጨምሮ ጓደኛውን ሲነግር ዮስም ሳቀ። “ይህ ታሪክ ነው! እንዳልኩህ ብትቀላቀለን ጤናህ ይጠበቅ አለ፤ አታመስግነኝ ምንም የይደለም!” “ሂድ! እና የምር አስራአንድ ኪሎሜትርዎች ሮጥህ!?” “ሀበሻ! አንድ ሲነግሩት አራቴ አረጋግጦ ለመስማት መፈለጉ እና ለማመን ማመንታቱ አይጣል ነው!” “ስለ ክዋክብት እና ዝቅተኛ የአየር ግፊት ስለ እማንጠይቅ እኮ ነው! መደዴ ነገር ደግሞ መጠየቅ ተዋጥቶልን አለ!” በእራሱ የተጀመረበት ነጥብን አጠንክሮ፣ ዮስ በጀርባው አንዱ ትከሻው ላይ ጭንመቀመሪአ (ላብቶብ) አንጠልጥሎ ብሩ በቀረ ትከሻው ተደግፎበት ተያይዘው ወጡ፨
እነ ናሆም ባቤ ታናናሽዎቹን እስኪቀሰቅስ ትመ. ከፍተው አፈጠጡ። ወዲአው፣ ሁሉም ተቀላቅሎ ቁርስ ቀረበልአቸው እና ሁሉም ተመገቡ። የተለመደ ገንፎ በተለመደ ድባብ ተመግበው እየተጨዋወቱ ቆዩ። ቁርስ ሲአበቃ፣ መስ እና ናሆም ተያያዩ። ከዚህ መሰል እንቅስቃሴ መልስ ነብስ አድን መጠጥ ቀምመው ቀን ሙሉ ይጠጡ ነበር። አሁንም ናሆም ወደ ጓዳ ገብቶ ጨው፣ ስኳር፣ ጥቂት ቂቤ፣ ጥቂት በሶ፣ ወስዶ ሁሉን አዋሃደ። በቡና መሰል ቅጥነት አብዝቶ በአምስት ሊትር ባልዲ አዘጋጀ። ሁለት ዝግ መጠጫ ሽንጣም እቃዎች ዉስጥ ነብስ አድኑን ሞልቶ አንዱን ለአጎቱ አስረከበ። በጫፉ መክፈት እና ፉት ብሎ መዝጋት እንደ ዉሃ እየተጎነጩ ተቀመጡ። ትመ.ውን ሁሉም ሲአፈጥጥበት፣ መስ በእንግሊዝኛ ትምህርት ሰዋሰው ማስጠናቱን እንዲጀምር ናሆምን ጠየቀ። ስለ ዉስብስብ አረፍተነገርዎች እየአስጠናው “ሃቪንግ ራን ሰምሃው ኧ ሎንግ ሩት፣ አይ ስቲል ዊሽ ቱ..ጌት አዉት ኤንድ ዎርክ!” ብሎ ማጥናቱን እንደ አሳካ አበሰረው። የለመደውን ቅርፀት እንዳይረሳ እንዲለማመደው፤ እንደ ወትሮው አስጠንቅቆት ወደ ዉጭ መጠጥአቸውን ይዘው ወጡ፨
የቤቱን ወለል በድንጋይዎች መሙላት ተያይዘው አረፈዱ። መጠጡም አልቆ ተደገመ። ሁለት ሊትርዎችን ለእየ ፊናአቸው አጠናቀቁ። “አሁን ሂወት ደሜን ስለመለስኩ ደስተኛ ሆነች!” መስ ረክቶ በምስጋና መልክ ይህን ብሎት ሽንት ለመሽናት ዞረ። ናሆም በቤቱ ወለል ለመጠናቀቅ መድረስ ተደሰተ። ወለሉ በድንጋይዎች ከተሞላ በኋላ አነስ ያሉትን ድንጋይዎች ከላይ በማፍሰስ አሰለጠኑት። በእርጋታ በእላዩ በመራመድ ለአጨራረስ መዘጋጀቱን አስተዋለ። ‘ወለል ካለቀ፣ ምሰሦዎች ከቆሙ፣ ጣራ ከለበሰ፣ ይህ ድንቅ ነው! መስ ምትሃትኛ ሠራተኛ! እግዚእአብሔር ዕድሜ ይስጥህ የእኔ አባት!’
እየ ተደመመ በተከናወነው ተደንቆ ከግሉ ሲወያይ መስ ተመለሰ። የማገርዎቹን ርብራብ አብዝቶ በመደርደር ከመቱት በኋላ ለድንጋይ ድጋፍ እንደ ቀረ በመተማመን ደስታአቸውን አላቁት። ተጣጥበው ወደ ቤት ተመለሱ፨
በትመ.ው ተዘግቶ መጠበቅ ናሆም ተደሰተ። ታናናሽዎቹ ቀን ሙሉ ማፍጠጡን ለመጀመሪአ ጊዜ ተጸየፉት። ወደ ትመ.ው እራሱ ሲመለስ፣ ቢግ ለመሰል እንግሊዝኛ እርዳታ ከወንድሙ ዛፍቤት ወርዶ በመምጣት ወንድሙን ጠራ። የተሰጠውን መፈጸሙን በመፈተን አረጋገጠ። ናሆም የሰባትኛ ክፍል ተማሪ የነበረ ወንድሙን የ ሰር አርተር ኮናን ዶይል “ዘ ሃውንድስ ኦፍ ባስከርቪል” እሚሰኝ አጭር መርማሪ ትረካ ሰጠው። ቢግ ተደሰተ። አሁን ለማንበብ እሚፈቀድለት ፈረቃ ላይ ደረሰ። ከመሰልጠን ጀርባ መዝናናቱ ሲፈቀድ ደስታው በቃል አይገለጽም። ናሆም ከእሚወድድአቸው አጠር ያሉ እና ለታዳጊ ከእማይከፉ አንዱ ያለው መጽሐፍ ስለ ነበር ለታዳጊው ሲሰጠው እሚሰማውን በፊቱ እያጤነ ነበር። ቢግ በመደሰት በአንድ ወይም ሁለት ቀንዎች ሊጨርስ እና እንደ ለመደው የትርክት ጭምቁን ጽፎ፣ ጭብጥ አዉጥቶ፣ የጭብጥ መምረጡን ማስረጃ ጥቅስ አምጥቶ ሊአብራራ እና ቀጣዩን ቤትስራ ሊቀበል ተደስቶ ወጣ፨
ባቤ በመሳሉ ተጠምዶ ተቀመጠ። ጢዩ ከጮለቅ ጋር የህፃን መዝሙርዎች በመዘመር እና መደሰት ተያያዘች። እኩለ ቀኑ በእነ መስ በትልቁ ጠረጼዛ ዙሪአ አለ ማቋረጥ ለጤና መጠጣት እና አዝናኝ ጊዜ ማሳለፊያ ጨዋታዎች ማዝገም ቀጠለ። ጢዩ በመዞር እንቆቅልሽ በመጠየቅ አንጎሎቻቸውን ስትፈታተን ስትደሰትም ቆየች፨ብሩ ን ጠርቶ ቁርስ በልተው ሲነሱ እነ ናሆም መግባትአቸው ነበር። “በሉ ሰዉነቴ ጓጉሎ አለ! ዕድሜ ለእናንተ እሩጫው ስለ ገደለኝ ጊቢ ገብተን በይነመረብ በመጠቀም መጎለቱ ብቻ ነው አማራጬ! መንቀሳቀሱ እንደሁ አይቻልም!” መስ “ምንም አይደለም!” ብሎ በሽሙጥ፣ በግልፅ መመስገን እንደ ነበረበት አሳበቀበ። “አዎን! ናሆም ዉድ ወንድሜ! አመሰግንህ አለሁ! ቀጣይ ሳምንት እንገናኝ! አስራአንድ!” ድምፅ ጨምሮ ጓደኛውን ሲነግር ዮስም ሳቀ። “ይህ ታሪክ ነው! እንዳልኩህ ብትቀላቀለን ጤናህ ይጠበቅ አለ፤ አታመስግነኝ ምንም የይደለም!” “ሂድ! እና የምር አስራአንድ ኪሎሜትርዎች ሮጥህ!?” “ሀበሻ! አንድ ሲነግሩት አራቴ አረጋግጦ ለመስማት መፈለጉ እና ለማመን ማመንታቱ አይጣል ነው!” “ስለ ክዋክብት እና ዝቅተኛ የአየር ግፊት ስለ እማንጠይቅ እኮ ነው! መደዴ ነገር ደግሞ መጠየቅ ተዋጥቶልን አለ!” በእራሱ የተጀመረበት ነጥብን አጠንክሮ፣ ዮስ በጀርባው አንዱ ትከሻው ላይ ጭንመቀመሪአ (ላብቶብ) አንጠልጥሎ ብሩ በቀረ ትከሻው ተደግፎበት ተያይዘው ወጡ፨
እነ ናሆም ባቤ ታናናሽዎቹን እስኪቀሰቅስ ትመ. ከፍተው አፈጠጡ። ወዲአው፣ ሁሉም ተቀላቅሎ ቁርስ ቀረበልአቸው እና ሁሉም ተመገቡ። የተለመደ ገንፎ በተለመደ ድባብ ተመግበው እየተጨዋወቱ ቆዩ። ቁርስ ሲአበቃ፣ መስ እና ናሆም ተያያዩ። ከዚህ መሰል እንቅስቃሴ መልስ ነብስ አድን መጠጥ ቀምመው ቀን ሙሉ ይጠጡ ነበር። አሁንም ናሆም ወደ ጓዳ ገብቶ ጨው፣ ስኳር፣ ጥቂት ቂቤ፣ ጥቂት በሶ፣ ወስዶ ሁሉን አዋሃደ። በቡና መሰል ቅጥነት አብዝቶ በአምስት ሊትር ባልዲ አዘጋጀ። ሁለት ዝግ መጠጫ ሽንጣም እቃዎች ዉስጥ ነብስ አድኑን ሞልቶ አንዱን ለአጎቱ አስረከበ። በጫፉ መክፈት እና ፉት ብሎ መዝጋት እንደ ዉሃ እየተጎነጩ ተቀመጡ። ትመ.ውን ሁሉም ሲአፈጥጥበት፣ መስ በእንግሊዝኛ ትምህርት ሰዋሰው ማስጠናቱን እንዲጀምር ናሆምን ጠየቀ። ስለ ዉስብስብ አረፍተነገርዎች እየአስጠናው “ሃቪንግ ራን ሰምሃው ኧ ሎንግ ሩት፣ አይ ስቲል ዊሽ ቱ..ጌት አዉት ኤንድ ዎርክ!” ብሎ ማጥናቱን እንደ አሳካ አበሰረው። የለመደውን ቅርፀት እንዳይረሳ እንዲለማመደው፤ እንደ ወትሮው አስጠንቅቆት ወደ ዉጭ መጠጥአቸውን ይዘው ወጡ፨
የቤቱን ወለል በድንጋይዎች መሙላት ተያይዘው አረፈዱ። መጠጡም አልቆ ተደገመ። ሁለት ሊትርዎችን ለእየ ፊናአቸው አጠናቀቁ። “አሁን ሂወት ደሜን ስለመለስኩ ደስተኛ ሆነች!” መስ ረክቶ በምስጋና መልክ ይህን ብሎት ሽንት ለመሽናት ዞረ። ናሆም በቤቱ ወለል ለመጠናቀቅ መድረስ ተደሰተ። ወለሉ በድንጋይዎች ከተሞላ በኋላ አነስ ያሉትን ድንጋይዎች ከላይ በማፍሰስ አሰለጠኑት። በእርጋታ በእላዩ በመራመድ ለአጨራረስ መዘጋጀቱን አስተዋለ። ‘ወለል ካለቀ፣ ምሰሦዎች ከቆሙ፣ ጣራ ከለበሰ፣ ይህ ድንቅ ነው! መስ ምትሃትኛ ሠራተኛ! እግዚእአብሔር ዕድሜ ይስጥህ የእኔ አባት!’
እየ ተደመመ በተከናወነው ተደንቆ ከግሉ ሲወያይ መስ ተመለሰ። የማገርዎቹን ርብራብ አብዝቶ በመደርደር ከመቱት በኋላ ለድንጋይ ድጋፍ እንደ ቀረ በመተማመን ደስታአቸውን አላቁት። ተጣጥበው ወደ ቤት ተመለሱ፨
በትመ.ው ተዘግቶ መጠበቅ ናሆም ተደሰተ። ታናናሽዎቹ ቀን ሙሉ ማፍጠጡን ለመጀመሪአ ጊዜ ተጸየፉት። ወደ ትመ.ው እራሱ ሲመለስ፣ ቢግ ለመሰል እንግሊዝኛ እርዳታ ከወንድሙ ዛፍቤት ወርዶ በመምጣት ወንድሙን ጠራ። የተሰጠውን መፈጸሙን በመፈተን አረጋገጠ። ናሆም የሰባትኛ ክፍል ተማሪ የነበረ ወንድሙን የ ሰር አርተር ኮናን ዶይል “ዘ ሃውንድስ ኦፍ ባስከርቪል” እሚሰኝ አጭር መርማሪ ትረካ ሰጠው። ቢግ ተደሰተ። አሁን ለማንበብ እሚፈቀድለት ፈረቃ ላይ ደረሰ። ከመሰልጠን ጀርባ መዝናናቱ ሲፈቀድ ደስታው በቃል አይገለጽም። ናሆም ከእሚወድድአቸው አጠር ያሉ እና ለታዳጊ ከእማይከፉ አንዱ ያለው መጽሐፍ ስለ ነበር ለታዳጊው ሲሰጠው እሚሰማውን በፊቱ እያጤነ ነበር። ቢግ በመደሰት በአንድ ወይም ሁለት ቀንዎች ሊጨርስ እና እንደ ለመደው የትርክት ጭምቁን ጽፎ፣ ጭብጥ አዉጥቶ፣ የጭብጥ መምረጡን ማስረጃ ጥቅስ አምጥቶ ሊአብራራ እና ቀጣዩን ቤትስራ ሊቀበል ተደስቶ ወጣ፨
ባቤ በመሳሉ ተጠምዶ ተቀመጠ። ጢዩ ከጮለቅ ጋር የህፃን መዝሙርዎች በመዘመር እና መደሰት ተያያዘች። እኩለ ቀኑ በእነ መስ በትልቁ ጠረጼዛ ዙሪአ አለ ማቋረጥ ለጤና መጠጣት እና አዝናኝ ጊዜ ማሳለፊያ ጨዋታዎች ማዝገም ቀጠለ። ጢዩ በመዞር እንቆቅልሽ በመጠየቅ አንጎሎቻቸውን ስትፈታተን ስትደሰትም ቆየች፨

እረፍት አድርገው ሲጨዋወቱ ቆዩ። እሚ በትመ. ድንገት አንድ አዝማሚአ አበዛች እና አሳደደች። “ለምን ይህን ቃና እሚባል ጣቢአ አታሳዩኝም?” መስ ትመ. ከገዛ ወዲህ የጢዩ ትመ. ተብሎ ልጂች ብቻ ናቸው የተዝናኑት! እኔ በሂወቴ ትመ. አይቼ አላቅ። ይሄ ቃናን ልመልከት በሉ!”
እነ ናሆም በጠነከረ ፍላቷጎቷ በሥሱ በመሳሳቅ ጣቢአውን ከእማያልቅ ጥቅምየለሽ የዐረብኛ እና መሰል ጣቢአዎች አድነው አገኙ። እሚ በማስተዋል ተመለከተች። “አይ ዘመን! ታቦት አንሶት፤ ነጭ አማርኛንም ሰርቆ አረፈው?!” መስ ከት ብሎ ሳቀ። እጅ በአፍ ጭና ማትኮር ቀጠለ ች። እነ መስ በመጠቃቀስ ጥቂት እንድትደመም አድርገው ከቆይታ ኋላ ታሪኩን አብራሩላት። “አከናፍር (ሊፕሲንግ) ነው የአላችሁት?” ከተብራራላት ኋላም የመነሻ ሃሳቡ ትንግርትነቱ ከንክኗት ስለጠየቀች። የጮለቅ አጫዋች ጢዩ ጣትዎች ዘርዝሮ በማሳየት ጭምር መከዳው ስር ሆና “ኧው! አምስቴ ነገሩሽ እኮ እሚ! አምስት!” ብላ ተናገረች። በፊቷ ደመነብስአዊ ልዝዝ ፈገግታ ሰርታ እሚ አሰላሰለች። “ቃና ሃገሩን ያታለለው የነጭ ተረት ባማርኛ ስላቀረበ ነበራ!” እነመስን ስለጣቢአው እንዲአስቡ አደረገችአቸው። “አዎ! ግን እኔ ጣቢአው ሲከፈት ደራሲ እና ፊልምሰሪ ቡድንዎች ይዘጋ ሲሉ አልደገፍኩም ነበር! እሚ እንደ አንቺ የአለ ይዝናናበት አለ ብዬ ነበር የደገፍኩት፣ ቀን መዋያሽ ነው!” ናሆም በርግጥ በነፃ ገበያ እና ከምንም በላይ በየመግለፅ አርነት (ፍሪደም ኦፍ ኤክስፕሬሽን) አምኖ ቃና እንዲነካ አልፈለገም ነበር። መስ የነበረውን የወቅቱ ጋጋታ አስታውሶ “አንድም ነገር በ ቃና አትመለከትም ነበር እኮ ግን!” ሲል አሳሳበው። ናሆም ቃናን ተመልክቶ አያውቅም። የዳናዊት ሃሽታግ_ታይምን ግን አልጠላውም። በመንደር ዞሮ ስለ አዲሱ ወሬ ከአጣራ በኋላ ጣቢአው የደረሰ እለት የሞተ (ደእሞ. ዴድ ኦን አራይቫል = ዲኦኤ.) እንደ ነበር ተገንዝቦ ነበር። “ከምሩ ማን የማይቋጭ ያታካች ነፈዝ ትረካዎች ይመለከት አለ?” በእሚል አልፎት ነበር። ግን ወዲአው ሃገሩ ተናወጠ። በተለየ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ሲቃወሙ ግን ናሆም ደነገጠ። ይህ የሰሞንኛ እና ማንም እማይከታተለው እሚሆን እንደ ሆነ ያስተዋለው ነበር። ግን ኪነጥበብኛዎች ያዙን ልቀቁን ካልተዘጋ አሉ። ይህ በግል አቅምአቸው ፍራቻ እንጂ አደጋ ሆኖ አልታየውም ነበር። እንደ አሰበውም በሂደት ጣቢአው ወረቱ ቀዘቀዘ። ታዳሚዎቹ ሟሸሹ። ጭራሽ ጣቢአውም ብዙ ገሃድአማአዊነት መከተል ጀመረ። የአካባቢ ጉዳይዎችን እና እሚሰባጠሩ ተለዪ ወይትዎች ማሰራጨት ጀመረ። ምክንያቱም ታዳሚ ሸሸው። ዛሬም ናሆም እሚአስበው፣ ቃና ለእሚ መሰል በመጥለፍ እና በዳንቴል ሥራ ለእሚጠመዱ እና ቤተአዛዉንትዎች (ኤልደርሊ ሆምስ) ደግ አማራጭ ሊሆን እንደ እሚችል ነበር። በንባብ ለእናቱ በአንድ ቁጥር ባታቅም በመንካት መክፈቱን እንድትለምድ አድርጎ ሲደብራት እንድትመለከት ነግሮ ብጁ አደረገው። መስ በሁኔታው ሁሉ ሳቅ አለ፨
ስለ ቤቱ ተነስቶ ሁሉም በእሚ ተመርቀው መጨዋወቱ ቀጥሎ አረፈዱ። መጠጡን ፈጽመው፣ ወደ ጠላ ገብተው በወሬ አረፈዱ። ለነገ ድንጋይ ለመጨመር አቅደው ትመ. ለእሚ በመተው ወደ ዉጭ ወጡ፨

ናሆም ምሣ በልቶ ከቤተሰቡ በመለየት ወደ ተማሪቤት ሰፈሩ ወረቀትዎች በመሸከም አዘገመ። በሰፈሩ የመረጃ እና ግንኙነት ሽልፍኖት (ቴክኖሎጂ) መምህሩ ቤት ጎራ አለ። ስለ እሚተዋወቁ እና ለ እርሱ አክብሮት ስላላቸው፣ መምህሩ የናሆም ኮትኳች ጭምር ነበሩ። መቀመሪያ ቤተሙከራውን ቁልፍ መቼም ሊአውሱት ቃል ገብተው ይህን ዕድል ተጠቅሞ ብዙ አገልግሎትዎችን ያገኝ ነበር። አሁንም፣ ቁልፍ ተቀብሎ ወደ ጊቢው በር ደርሶ አንኳኳ። ዘበኛአቸው ጋሽ ይሄይስ እንዲሁ ተባባሪ እና ተጫዋች ሲሆኑ የእነ ናሆም ቡድን ምንጊዜም አጋዥ ደጋፊ ናቸው። ስለሚደረግላቸው እንክብካቤ ሳይሆን ስለ ቀና፣ ቁምነገረኛ፣ ታታሪ እና ደግ ባህሪዎችአቸው የወጣትዎቹ ተባባሪ ነበሩ። በእሚችሉት ሁሉ። ቀላል ሰውም ስለነበሩ አብረው በመጫወት እና ስለ ስልክአቸው እና አኗኗርአቸው ምክር በመጠየቅ ከወጣቶቹ ከፍተኛ ቀና ቅርርብ አዳብረው ነበር። ለናሆም ትንሹን በር ከፍተው አስገቡት እና ሰላምታ ሰጥተው ወደ ክፍልአቸው ጀርባ የሽመና ስራቸው ተመለሱ፨
ናሆም ለጊቢው ፍቅር ነበረው። እረዣዥም ዛፍዎች፣ አረንዴ አፀድ፣ የተቀጣጠሉ መማሪአ ክፍልዎች፣ አሁን እረጭ ብሎ የግርግር እና ጫጫታ ሰለባ መሆኑ ከቶ ተረስቶ አለ። ድባቡ ዉስጥ ቅዝቃዜ እና ነፋሻማ አየር ብቻ እየአስተዋለ ከጓሮ ወደ ነበረው መቀመሪአ ቤተሙከራ ገባ። አንድ መቀመሪአ አብርቶ ያቋረጠውን የዘገባ መፃፍ ቀጥሎ፣ ወደ በይነመረብ አሠሳ ገባ። የዜና ድህረገጽዎች እልባት (ቡክማርክ) ስላሉት ቶሎ በመስረግ ዜናዎችን ፈተሸ። ሲጨርስ ስለእርሻ ቀላል ማብራሪአዎችን ተመለከተ። በእርግጥ የኢትየጵያ ግብርና ብቻ በበሬ እሚከወን አይደለም። ስለ ብዙ የበሬ እርሻ ጉርሻዎች በፅሁፍ እና ምስልዎች ተመልክቶ አስተማማኝ መረጃ በመሰደር የሰበሰበውን አብላሎት (ኢንተርናላይዝ) አደረገ። ከብትዎቹን ስለ መጥመድ፣ የመሳሪአዎቹን አወቃቀር፣ ከብትዎቹን ስለ መንዳት እና ላፍታ ማቆም ጥበብዎች፣ መሬቱን ስለ መቆጣጠር፣ የእጅ ሥራዎች አስፈላጊ ሥፍራዎች፣ ወዘተ. እንደ ገባው መልሶ እራሱን በመጠየቅ ምናብአዊ ካርታ አበጀ፨
ከቆይታ በኋላ ተመልሶ በመዉጣት ጋሽ ይሄይስን ዳግም አስቸግሮ ጥቂት ከተጨዋወቱ በኋላ ወደ ዉጭ አሰናበቱት። ስለሽመና አንድአች ዘዴ አጥንቶ ምክር ሊለግስ በማቀድ ለ ፈጽሞ ሌላ ጊዜ ጠቅላላ ምናልባትአዊ ዕቅድ አኖረ። ‘እልፍ የዕድ ብልሃት መረጃ ተሰድሮ በበይነመረብ አለ። የቱንም ሙያ እሚነካ አጋዥ መረጃ አይጠፋም። ሂወት በቀላሉ መቀየር እሚችል ድንቅ የመረጃ ባህር አለን። እሚያቀውም በተለይ ቢያንስ ግን እሚነካው የለም! አሁንም ሂወት ግን መለወጥ ይችል አለ፤’ በእዛ አገልግሎት እነጋሽ ይሄይስ ምንም የመጠቀም ወይም አንድ ነገር እንኳ የማድረግ እድል እንደ ሌላቸው በማሰብ ኃላፊነቱ የእርሱ እና መሰሎቹ እንደ ሆነ ገመቶ ዕቅዱን ለቀረበ ቀን መልሶ ሳለው እና ወደ መምህሩ ቤት ተመለሰ። መልሶ ስለቀላል ነገርዎች እና ሂወት መሻሻል እያዉጠነጠነ ወደ ቤቱ አዘገመ። የይሄይስንነገር ሲያሰላስል አብሮ የዘመኑ መረጃ እድል ወደ አንድ ዕድል ማሰስ እና መጠቀም ብሎም ወደ አንድ ከበርቴነት የመቀየሩን ነገር አሰበ። የሁለቱ ሽማግሌዎች ፈጠራ ትዝ አለው። በወረቀት ማስታወቂአ ጽፎ መለጠፍ እና ማስታወቂአው ቀኑ ሲያልፍ ከተለጠፈበት መቅደድ ግድግዳዎች ሲበላሹ ያስተዋሉት፣ ሁለት ሽማግሌ ጓደኛሞች ከመስሪአቤት ጡረታ ሊወጡ ሲሉ አንድ መላ ዘየዱ። ማንም ያልተመለከተውን ነገር ከእዛ ዝርክርክነት ተመለከቱ። የተለጣፊ ጽሑፍ (‘ስቲኪ ኖት’) ፈበረኩ። በአይምሮ ሃብት ተመዝግቦልአቸው በእሚአመርቱት ተለጣፊ ጽሑፍ፦ በተለያዩ ቀለምዎች አማራጭነት የእሚቀርብ በበዙ መትዎች አማራጭ እሚቀርብ ሲሆን በተለየ ግን አጭር ወረቀት ነው። ያንን በመለጠፍ መልሶ ደግሞ ሲነሳ ወረቀት ቀድዶ ስለማይተው ተወዳጅ ሆነ። በበራሪቅርጽ (አዉሮፕላን) ፈጣሪ እድሜ ዘመን ምርምርዎች አቻ እሚሆን ዝና እና የቢሊየን ዶላር ንግድ ለጡረታአቸው ገነቡ። ናሆም ይህን በመደነቅ እሚአስተውል ነው። ይህን ያክል ጥቂት ጨረፍታአዊ አስተዉሎት በመከወን ብዙ ማትረፍ የተፈቀደበት ዓለም ላይ እኛ ግን ጥንት የተለመዱ ምርጥ-ምርጥ የዕድ ዘዴአማአዊነትዎች (ስትራቴጂስ) ባለመጨነቅ ሳንመለከትአቸው ብዙ ማግኘት እየቻልን ትተንው አለን። ይህ የድሃ ሃገር ገሃድ መሆን የለበትም። እያዉጠነጠነ ሲራመድ ሳያስተውለው በሃሳብ ተጨልጦ ወደ ቤቱ ደረሰ፨

በመጨዋወት አረፋፍደው ከሰዓት በኋላ መስ የድንጋይዎች መጨመሩን እንዲከውኑ ናሆምን ጠየቀ። ተስማምተው የመቅሱድ አህያ ግልጋሎትን በመቅጠር ድንጋይዎቹን ሲጭኑ እና ሲአራግፉ ቆዩ። መስ በተሳካ የድንጋይዎቹ መሰብሰብ ተደስቶ ናሆምን ወደ ለመዱት ተወዳጅ ካፌ ለግብዣ ለመዉሰድ አሰበ። የጋሽ አበራ አብዛኛዉን እቃዎች በመያዝ በቤትአቸው በኩል ተጓዙ። የናሆም የማደግ እና የወጣትነት ዘመን ለእልፍ የሂወት አገነዛዘብ ጥያቄዎች ስለሚዳርገው ብዙ ነጥብዎችን እንደለመዱት አንስተው በመወያየት ጎንለጎን እየተራመዱ ጋሽ አበራ ቤት ላይ አስራአንድ ከአርባ ሲል ደረሱ። መስ ናሆምን ዉጭ አድርጎ እንደ መለደው ወደ ዉስጥ ገባ። የአበራ ታዳጊ ልጅ በተበጀላት ዥዋዥዌ ከናሆም ጋር ተግባብታ ለተጨማሪ መጫወቻ ድጋፍ ጠየቀች። የዘለገ ዥዋዥዌ እንዲሰራላት ትልቅ ገመድ አመጣች። መስ ለነገ ጠዋት አፈር እንዲልኩለት የኢሙያአዊ ስዉር ግንባታ ዓለም ዋነኛ ተዋናዩ ጋሽ አበራን አሳምኖ ቀብዱን ከፍሎ ሲወጣ ናሆም በመሰላል ትልቅ ዛፍ ላይ ወጥቶ ገመድ ሲአስር ደረሰ። አብሮ በማገዝ ትልቁን ልዕለዥዋዥዌ አስተማማኝ አድርገው ሰሩ። ህፃኗ በማመስገን እና ቡረቃ ሙከራውን አድርጋ አስደሰተችአቸው፨
ወደ ካፌው ከሃያ ደቂቃዎች በኋላ ሲደርሱ እንደ ተለመደው ብዙም ሰውዎች ባይኖሩም ጥቂት ፈንጠርጠር ያሉ ታዳሚዎች ጀምበሯን ይመለከቱ ነበር። ፀሐይግባት ጋር ለሁለትኛ ጊዜ በሳምንቱ ተያይተው በመዝናናት የለመዱትን ጭማቂ እየወሰዱ ቆዩ። በርግጥ መስ እሚአወራው ቁምነገር ለናሆም የአዳጊነት ጥያቄዎች ምላሽ ብቻ አልነበሩም። የአደገ ሰውንም እሚአቃቁ እና እሚለውጡ ብዙ ነጥብዎችን በማሰስ ይነጋገሩ ነበር። መስ ምስጋና በመቸር ናሆምን እሚአንቆለጳጵሰው ለራሱም በዘመነ ዉይይትአቸው ብዙ ጥቅምዎችን ስለ እሚአግበሰብስ ጭምር ነበር፨
ጀምበሯ ስትጠልቅ፣ ሌላ ሃገር ላይ የማለዳ ጀምበር ሆና ስትነሳ ትንግርቱን እየሳሉ መደመሙን ተያያዙት። የሞቀ ቀለም ጭዉዉቱን በሰማዩ እረጭታ፣ ጀምበሯ መጥለቁን ጀመረች። መስ የጀምበሯ መፍጠን በምትጠልቅበት ወቅት እንደ አለ አስተዋለ። በአካሏ ጫፍ መደበቅ ሲጀመር፣ ከምኔው በእሚአስብል ፍጥነት መስመጥ እና በላጭ ጎኗ መሸፈን ይከተል አለ። ብዙ ሳይቆይ በአፍታ ደግሞ ትነሽ ሽራፊዋ ብቻ ለእይታ ተተወ። “ጀምበር ፈጣን ነች ማለት ነው?” መስ በመደነቅ ሆኖ የልብ ሃሳቡን አነሳ። ናሆም ነጥቡን ቶሎ አስተውሎ ተረዳ። “አይደለችም! ግርዶሽ ወቅትም እኮ በተለይ የሙሉ ፀሐይ ግርዶሽ አንድ ሥፍራ ለአንድ ደቂቃ ተከውኖ ወዲአው ክብ ቀለበቱ መፍረስ ይጀምር አለ። ማለትም፣ ፀሐይ በፈጣን ጉዞ ነው ያለችው። መቼም ቢሆን!” መስ ጉዳዩ ትንግርቱን አባሰበት። “እና እረጅም ቀን ነው ያለን በለኛ!” ናሆም ነጥቡ በተገቢ የጊዜ አረዳድ መንገድ ስለ ጠለለ አልተደነቀም። ፀሐይ ወይም ጀምበር ከዉበቷ ጀርባ የጊዜ ፍችን እምትሰብክ ደቀመዝሙር ናት። መቼም። “አዎ!” ጀምበሯ በቅጽበቱ ጠልቃ የተረፈ ጨረሮቿ በሩቅ ደመናው ብቻ ተቀልቦ ፈዝዞ ተይዞ ነበር ወደ እርስበእርስ መተያየቱ ተመለሱ እና ናሆም ማብራራቱን ቀጠለለት። “ፀሐይ ባየሃት ፍጥነት፣ እየተመለከትሃት በአንዴ እንደ ሰረገች ቀን ሙሉ ትጓዝ አለ ች። ይህ ፈጣን ጉዞዋ ቀኑ ምን ያክል ከፍተኛ እርዝመት እንዳለው እሚአስመለክትህ ነው። ቀንዎች በምድር በእርግጥ እረዥም ናቸው!” መስ አናቱን በመነቅነቅ ትንግርቱን ለመዋጥ ሞከረ። “እና አንድ ቀን አቅሙ ከጀምበር ወይም ግርዶሽ ምልከታ ይገኝ አለማለት ነው?!” ፈገግ አለ። “አዎን! በእሚገባ!” ባለፈው የተጨዋወቱት ትዝ አለው። “የአልክው…ከተፈጥሮ መገናኘት መቻል ያኗኗር ማበልፀጊአ ነው. ..ነገር።” ናሆም እራሱን ነቀነቀ። የጭማቂ አጫዋችም ቀጠረ። “ትልቅ ፍች አለው በ እዉነት! ትልቅ! ሰው ተፈጥሮን እንዲህ እንደ ዘበት ተመልክቶ የቀኑን መርዘም በመመልከት ምን እንደ እሚሰራ በቀኑ ምን እንደ እሚአደርግ፣ ምን ያክል መደሰት እና ደስታውም ምን ያክል እንደ ረዘመ ማየት አለበት! የሰዓት መቁጠሩ ጉዳይ በቂ የጊዜ አገነዛዘብ እና ዋጋ አይሰጠንም ባይ ነኝ!” ናሆም በተነሳው ሃሳብ ተገረመ። በተለየ በሁለትኛው ነጥበ። “የጊዜ ዋጋ በእርግጥ በእምንቆጥረው የእጅ ወይም ተስ. ሰዓት እሚለካ እና ለአንጎል እሚደርስ አይደለም። ጊዜን ለመመተር ያክል እንጂ ዋጋውን ለመንገር የሰዓት ቆጣሪ አያገለግልም! የሰዓት ዋጋ ከእንዲህ ጀምበር፣ ግርዶሽ፣ ወይም ሌላ አጢኖትዎች እሚገኝ ነው!” መስ እጁዎቹን አጣምሮ በጉልበትዎቹ አስደገፈ እና ዓይንዎች አጥብቦ ማሰላሰል ከወነ። “በእርግጥ ስለ ቀንህ ዋጋ ለመገንዘብ ያልክው አንድ ትልቅ አማራጭዎች ናቸው። ግን ህመም እና ሞት ላይ የቀረበ ስጋይ ወደ ጊዜ ዋጋም መገንዘብ የአደርስ አለ።” በስልጠና ወቅት ስለገጠመው በማስታወስ አስተዋለ። በጠብመንጃ ስልጠና ወቅት አሰልጣኝአቸው መኮንን አጠገብአቸው ይተኩስ ነበር። በመናደድ ብቻ ግን አልነበረም። በማስደንገጡ ከፍተኛ ንቅዓት እንደ እሚፈጠር የህመም ፍልስፍና ተከታይ ስለ ነበር የአምን ነበር። የሰው ልጅ ህመም ሲገጥመው ከጭንቀት እና መፍዘዝ ወደ ንቅዓት እና ቅልጥፍና ይመለስ አለ። ለሞት እንደ ቀረበ ሲገባው በተለየ ህመሙ እሚሰብከው ብዙ የአጣው የሂወት ኢላማ፣ ፍላጎት፣ እና ምኞት ነው። መሞቱ እሚፀፅተው ሆኖ ብዙ እንደጎደለው ይማር አለ። ይህን ሲረዳ ግን በመጽሐፍቅዱስም እንደ ተነገረው ምነው ይህን ባወቅሁ ይል አለ።መሞት ላይ ስላለ ምነው በተመለስኩ እና በተስተካከለ መንገድ ሂወትን በመራሁ። ለካ ይህ ያ ነገር ትክክል አልነበረም በማለት ይቆጭ አለ። ይህ የሞት-አጠገብ ስሜት ለአሰልጣኝአቸው መሪ አንድ ፍልስፍና የሆነው በማስደንገጥ ሞት እንደ ቀረበብአቸው ተረድተው ወጣት ሰልጣኝዎቹ ለነቃ እና እንከንየለሽ አኗኗር ይመለሱ ዘንድ ያስመኛቸው አለ ብለው ማመንአቸው ነው። ሳያቅ ለሞት የቀረበ ተለማማጅ ሲድን ጥይትንም ይንቅ አለ ብለው ያምኑ ነበር፨
መስ እግር እግሩ ስር ስድስት ቀለሃ ሲተኮስበት እና የሞተ ሲመስለው ትዝ አለው። የዛ ሰሞን መሞትን አቅፎ በቃተተ ድንጋጤ እንደ ሰነበተ ትዝ አለው። ድንገት ተተኩሶ መደንገጡ ብቻ ሳይሆን ተተኩሶ በአንዴ አለመቋጨቱ ለቋሚ ሲኦል የተዳረገ ያክል ልዩ መከራ ላይ ጥሎት ነበር። በእርግጥ ጥቂት ስነምግባር በኋላ ሁሉ አልፎ አስረድተው እንደ ሰበኩት ተምሮ አግኝቶበት ነበር። አሁንም ናሆምን በህመም የሂወት ዋጋን ማወቅ በዛ ደግሞ ጊዜን በትልቅ ዋጋ ተምኖ መገንዘብ እንደ እሚቻል ሌላ አማራጭ አድርጎ አብራራለት። “ትክክል ነህ!” ናሆም ሃሳቡን እያብላላ አመነ። በዘመን አገነዛዘብ ያሟሟት ጉዳይ መሰማት ሁሉ እንደ አለበት ሲአስበው የተፈጥሮ ለዘረሰው ንቅዓት ትብብሯ በሌላ መንገድ ተገልፆ አስገረመው። በብዙ መንገድ ዘመንን መገንዘብ እንድንችል ዕድል አለን። የዘመን ቋንቋ ሲገባን ደግሞ ሌላ ፍጥረት የመሆን ያክል እንቀየር አለ። መስ እንደ አለው ለተስተካከለ እና እማይባክን አኗኗር ዝግጅት እናደርግበት እና ቃል እንገባበት አለ። ‘ከአላፈገፈገ ሰው የዘመን ትርጉም እንደ ገባው ወደ ፊት ከቀጠለ፣ የአሰበውን ለማሳካት ከልካይ አይኖረውም!’ “ግን የጊዜ ወይም ዘመን ፍቺ ሲገባን እምንደመመው እና የጸባይ ለዉጥ እምናስመለክተው ለምንድነው?” ናሆም ሃሳቡን አጠለለ እና ሌላ ነጥብ ላይ አመጣው። “አንድም ያኗኗር ፍች ባለፈው እንደ አልክው ይቀየር እና ይሳልብን አለ። ተፈጥሮን ስንመለከት እና ስስንደመም ነብስአችን ከተፈጥሮ እንደ አልክው እምትሰማው ማበረታቻ ሳይኖር አይቀርም። ለአኗኗር መዘመን እና ለስኬት ትልቅ መነሳሳት ከእማታውቀው ክፍልህ ይከብብህ አለ።” ናሆም ይህን በመስማት አብሰለሰለ። ስለጊዜ ትንግርት ያልተነገረ ስምጥ ስሜት ሁለቱም ዉስጥ ነበር። በቃልዎች አይገለፅም። ፈገግ ተባብለው ሂሳብ ከፈሉ እና ወጡ። ‘የጊዜ አረዳድህ በሰብእአዊነትህ ይገለፅ አለ። ጊዜን በጥበብ የተገነዘበ፣ ሰው ሆኖ እንደ ተፈጠረ አይቀርም። ወደ ልዕለስብእና ይቀየርበት አለ። ከአረማመድ፣ አዋዋል፣ አሰራር እስከ አገነዛዘብ፣ ከብሔር፣ ከሃገር፣ ከታሪክ፣ ከአንጎል እሚአቀው እና እማያውቀው ሁሉ አነንፃር ትክክልኛነት ላይ ወደ መድረስ በጊዜ አገነዛዘብ ይደረስ አለ! ጊዜ፤’

ምሽቱን በደግ መዝናናት እና ፈሳሽ መዉሰድ አሳልፈው፣ ሙሉ ቤተሰቡ ሲጨዋወት ቆይቶ ወደ መኝታ በጊዜ በመዉጣት አሳለፉት። ጢዩ ወንድሟ ናሆምን እንደ እራሱ የበግ ፀጉር እና ዶሮ ላባ በመስፋት አዲስ ትራስ እንዲአበጅላት ጠየቀች። ትራሷ በ ማርጀቱ ይህን ስታሳውቅ ናሆም ለጥቅምት ቀጠሮ ሰጣት። የሞቀ አየር ንብረት ሲገኝ የተሸለተ የበግ ፀጉሩን ደጋግሞ በማጠብ እና ማድረቅ ወደ ምቹ አገልግሎት መመለስ የተካነበት አንድ ዕደጥበብ ነበር። ጢዩ ጉዳዩን ችላ ብላ በእናቷ ጀርባ ተሸጉጣ ተኛች። ሁሉም ተመሳስለው እራስአቸውን በጀርባ በመንጋለል ዘነጉ፨

<p class="has-text-align-justify" value="<amp-fit-text layout="fixed-height" min-font-size="5" max-font-size="72" height="80">በ ማለዳ ቀድሞ በመነሳት እነ ናሆም የቀጠለ የድንጋይ ማጋዝ ሥራአቸውን ከወኑ። ብሩ ሰዉነቱ ስለ አላስቻለው በጥቂቱ እያገዘ ብዙ ድንጋይዎችን እንደ ህብረት በቤትአቸው ከመሩ። እረፋዱ ላይ ከቁርስ መልስ የጋሽ አበራ መልእክተኛ መጥቶ የተመረጠ አፈሩን ከእሚገነባው ቤት ጀርባ አራገፈ። አህያዎቹን እየ ነዳ በመመላለስ አፈሩን ከአከማቸ በኋላ ሂሳቡን ለመቀበል በጋሽ አበራ ቤት አስርሰዓት ተቀጣጠሩ። መስ ናሆምን አስከትሎ ሱቅ በመሄድ ኖራ እና እንቁላልዎችን ገዝተው ጭቃ ወደ ማብካቱ ገቡ። ጭድ እሚአመጣ አህያም ከጋሽ አበራ ዘግይቶ ደርሶ ማቡካቱን ሁሉ እየተደመመበት በመስ ተከወነ፨
ምሳ ከበሉ በኋላ ናሆም በቶሎ ተለይቶ ወደ ሩት ቤት አመራ። ሩት በፈገግታ ተቀብላው፣ በአዲስ ሙሉ ልብስ አምሮባት ተያይዘው በመለዱት አቋራጭ መንገድ የጨዋታ ጉዞ ዓሊ ቤት ደረሱ። ዓሊ ሰዓት ጥቂት ስለ ረፈደ በመቆጣት አስገባአቸው እና ጨዋታውን በዘገባ ማቅረብ ጀመሩ። የሰሚራ አልፎአልፎ ጨዋታ እየአቋረጠአቸው፣ በሻይ እና ቆሎ ግብዣ የሩት ሁኔታን መገምገም ተጀመረ፨
ሩት በኅዋአዊከተማ ው ደግ መስተንግዶ እንደ ተደረገላት እና ስለእንስሳዎች ህክምና በቂ ትዉዉቅ እንደ አገኘች በመንገር የመምህርዎቹ ለዓመት ማብቂያ ፈተና መሯሯጥ ስለ ነበር ለክረምቱ ግን በማስተማር ስለማይጠመዱ ጉያአቸው ከትተው ጓደኛምዎች መምህርዎች ብዙ ሊያስመለክቷት ቃል እንደ ገቡ እና ስልክ እንደ ተቀያየረች እና እንደ ተግባቡ ተናገረች። ሁለቱም በመደሰት እንኳን ደስያለሽ በማለት አበረታቱ። የጠበቀችው አስጊ ማህበርአዊ ክልልም ባሉት ጥበብዎች እንደ ቀለለላት እና ቀና ቀን ማሳለፏን ገለጠች፨
ዓሊ ለቤተሰብዎቹ አገልጋይ ሆኖ ስለ ተያዘ ጥቂት ቆይቶ ወደ ገጠር ዘመድዎቹ በመመለስ መረጃዎች እንደ እሚቃርም እና የግንኙነትዎች ድር እንደ እሚሞክር አሳወቀ። “እኛን ብዙ አበረታትተህ አንተ ይህን ብቻ ነው ያደረግክው?!” ሩት በተቆጣ ስሜት ዓሊን ገሠፀች። ናሆምም ተግባርአዊ ነገር እንደ ጠበቀ ገልፆ አገዛት። ዓሊ ሩት ላይ በማሾፍ እየተጨዋወቱ ቆይተው፤ አማራጭ እንዳልነበረው በማንበብ እና ማቀድ ብቻ እንደ ቆየ ገለፀ፨
ናሆም ግብርና በተግባር ለማጥናት እና ተያያዥ የሙከራ ቤተመብል ለማዘጋጀት እንደሚሞክር እና የደረሰበትን አብራራ። ሁለቱ ም ባከናወነው ተደስተው አበረታቱት።
ሲጨዋወቱ ቆይተው ሩት በክረምቱ ከማጥናቱ ጋር እንደ እምትከርም ገለጸች። ናሆም በሥራ እንደ እሚጠመድ አሳወቀ። ዓሊ እሚመለስበት እንደ እማያውቅ አሳወቀ። ሁሉም ዋና አላማአቸውን ከዉነው ወደ ጓደኛአዊ ጨዋታዎች ተመለሱ። በልብወዳጅነት ስለ ሁሉ ጉዳይ በመጨዋወት እና ሠሚራ ወጣገባ ስትል በእምታቀርብልአቸው የ ቀለለ እና ጎንታይ ጨዋታዎች ደምቀው በመጨዋወት ቆዩ። ሩት እንደ ወትሮው በዓሊ አድፍጦ ደግ ነገር አዉጠንጥኖ መምጣት አቅም ተማርካ በማድነቅ እየጎነተለችው። “ይኸው መቶ ሚሊየን ገበሬ ባለበት ሃገር ስንራብ መንግስት መኪናአዊ ማድረግ የነበረበትን ግብርና እያያዝአለሁ ብሎ በሞኝ መንግስት እሚአሾፍ ጀግና ተቀምጦልሽ አለ እንዴ! እርሱስ አይደነቅም!” ዓሊ ሲገስፃት ሩት ደነገጠች። ናሆም ሳያስተውለው “አንተን ነዋ 'ምቶደው!” እሚል አመለጠው። ያላቀደው ስለነበር በጨዋታ ስለ ወጣ እሚታሽ ወለምታ አልሆነለትም። በመደንገጥ ሁሉም ተፋጠጡ። የተስተዋለ ስሜት እንደ እዚህ አልነበረም። ግን ሩት ለዓሊ ያላት ስሜት በእዛ መንገድ ከተተረጎመ መልሳ ሁኔታዋ ከነከናት። ጥቂት ዝምታ ሰፍኖ ዓሊ ሁኔታውን ሲአስተውል ሩት “በእዚህ የመረጃ ዘመን ለነገሩ የግብርና መረጃን ከቀረው በመለየት ለግብርናው እሚሟት ብቻ ሳይሆን መረጃ አያያዝን በመምረጥ መከታተል ያስተማረን ናሆም እማ ልዩ ምስጋና ይገባው አለ! በመረጃ እሚደነቆርበት ዘመን ላይ ናሆም መምህር ነው!” በተደመመ አተያይ ወደ ናሆም ዞራ ጉዳዩን ቀየር አደረገች። ዓሊ በአተያየቷ እቅጭነት ተገረመ። ጨዋታውን ለማስፋት ያክል “መረጃ ዘመን የመረጃ መደንቆር ነው እንዴ?” ዓሊም በጨዋታው መቀየር ተደስቶ ጠየቀ። ሩት በጣሪአው ጠየም ያለ ፊቷ ላይ ሲአፈጥጡ በተለየ ንጣትአቸው ዉብ መስተጋብር እሚፈጥሩ ዓይኖቿን ላከች። ፊቷ እሚቆንጅበት አኳኋን ላይ እንደ ቆየች ያሰበችውን አብራራች። “ሰው የመስማት አቅሙ ከትንንሽ ድምፆዎች ወደ ጫጫታ ከእዛ ጩኸት ይደርስ አለ። ግን ከፍተኛ ጩኸት፣ ለምሳሌ አደንቋሪ ሙዚቃ መጠን እንደ እምንለው፣ ጆሮ ይጎዳ አለ። በሂደት ታምቡር ተቀድዶ መድማት አለ። ከተጨረ ድምጹ መሞት አለ አይደል? እና መረጃም ከአቅም በላይ መርጆን ደንዘን አለ። ወደ ሞት ሊቀረብ ምንም አልቀረም። ዘሪቱ እንዳለችው አኗኗር ወደ ዉሸት አምጥቶ ኑሮ እየሞተ ነው። መረጃ ደግሞ መብዛቱ እና አለመመረጥ መቻሉ አንዱ ይመስለኝ አለ።” ወደ ናሆም ተመለሰች። ጀርባውን በጨወታ መታመታ አድርጋ “ይህ ሰው ግን እሚፈልገውን በማደን እንጂ ማስታወቅያ እና ተያያዥ ማጥመጃዎችን በመዝለል አቅሙ ድንቅ የአሃዝ ዘመን አትኩሮት አዳብሮ አለ። መሸለም አለበት!” ምስጋናዋን ቸራ በፈገግታ የጓደኛዋን ፊት ተመለከተች። ናሆም አመስግኖ በጥቂት ዝምታ ተዋጡ። አሁንም ዝምታው ሲጨንቃት “በቃ ገጠር ስትገባ ዳማከሴ እና ጤናአዳም ለእራስምታትዎችአችን አዘጋጅልን እንግዲህ። በእንክብል እና ሽሮፕ ስሪት አቅርብልን። ዱቄት (ፖውደር) አለ ለነገሩ።” ለሩት ይህ ጨዋታ ሆኖ ከአስደሰታት ብሎ ዓሊ ሊያግዝ ብቻ ብሎ ጨዋታውን አሰፋው። “የሮማን፣ እንኮይ፣ እንጆሪ፣ ወይን፣ ወዘተ. ምርትዎች መልክአቸው ተረስቶ አለ። የፍራፍሬ ምንንት ሁሉ ሳይረሳን ናሆም ደርሶ እእንድንቀምስ ያግዘን አለ፤ የኔን ተይው…” ድንገት የቀደመ ሦስታዬ (ትሪአንግል) መመለሱ ሲገባው የጀመረውን አቋረጠ። “ወለምታ ሲይዝሽ ብቻ ነይ ወደ እኔ…!” በእሚል ፈገግታ ጭምር ተመለሰ። መልሶ ዝምታ እንዳይሆን የትመ. ማያገፅን ሩት ተነስታ አበራች። በመሰባሰብ ለመተያየት እና መጨዋወት እንጂ ልቦና ለማመሰቃቀል ስለ እሚዳርግ በጨዋታዎች መሀል ትመ. ወይም ተስ. መጎርጎር አያደርጉም ነበር። አሁን ግን ለጨዋታ ምንጭነት ሩት ተመኝታው ለሎሌነት ተከፈተ። የራሺያ ዓለም ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታ ላዕላይ-እይትዎች (ሃይላይትስ) በናሁ ትመ. ሲሰራጭ ነበር። በእግርኳስ ጨዋታ የዓለም ዋንጫ እና አህጉርአዊ ጨዋታዎች ካልሆነ የመከታተል ልማድ ከቶ የሌለአቸው ወጣትዎቹ በመደነቅ ስለ ጨዋታው ተወያዩ። በተለየ እማይረሳ አንድ የዓለም ዋንጫው ዉብ ትዝታ የጃፓን፣ ቤልጂየም፣ እና ብራዚል ብሔርአዊ ቡድንዎች የክሂሎትአማአዊነት እና ገናኝግንኙነትአዊነት (ታክቲካል) ዘዴአማአዊነትዎች ጦርነትዎች ነበር። ናሆም እና ዓሊ ምናብ ከእግርኳስ ወይም ሌላ ስነእንቅስቃሴ (ስፖርት) በመደመም እሚመለከተው ይህን መሰል ዘዴአማአዊነት ጦርነትዎች ስለነበር ይህን አይረሱትም። ጃፓን በመከላከል ደጀን አፅንታ በደራሽ መልሶማጥቃት ወጉ። ከእዛ ዘዴአማአዊነት በላይ ግን የኩርቶዋ ቆጥ አካልን ለመበዝበዝ ምትዎች በመሬት በማንከባለል ይልኩ ነበር። ይህ ስኬቱ መቶ እጅ ሆኖ ቆየ። ቤልጂየም የማታማታ ግን እንደ እባብ አንሰራርታ ድለኛ (ሻምፒዮን) ሆነች። እነ ናሆም በጃፓን የአካል-ወጥነት (ስታሚና) መስነፍ የተለመደ የሩቅ ምስራቅ ሃገር እግርኳስአዊ ጉድለት ደግመው ዋጋ ሲከፍሉ ተመለከቱ። ቀጣይ የመጣው ግን ሌላ የዘዴ አነፍናፊ አንጎል ምርጥ መብል ነበር። ብራዚል የጃፓን ክሂሎትአማአዊነት እና ገናኝግንኙነትአዊነት ስኬትአማነትን መልሰው በመቶ እጅ ግልበጣ ይዘው ገቡ። የጃፓንዎች ትምፋሽ መድከም በብራዚልዎች ስለሌለ ሁሉም የቤልጂየም መዉደቅን ቀድሞ አመነ። ዘጠና ደቂቃ ግን ኳስ ድቡልቡል እንደ ሆነች ሳይሆን ዘዴአማአዊነት የሂወት መልስ እንደ ሆነች ለአጤነው አስመለከተች። ቤልጂየም ዘዴአማአዊነት ምርጫአቸውን አስተካክለው ለጦርነቱ ፍልሚአ ገብተው ጉድ አሰኙ። ኩርቶዋ በመሬት ፈጥኖ መዘርጠጥን አብዝቶ በቀንዎች ልዩነት ከመስራቱ በዘለለ ብራዚል ግን በጃፓን አካሄድ መልሳ በደራሽ ጥቃት መሬት ለመሬት መምታት እንደ እምትያያዝ ስለታወቀ ቤልጂየም መሬቱን እንደ ተቃውሞ መንገድ መዝጋት ብቻ ለምዳ ጭንቅ ወለደች። ብራዚል የግል የቀደመ ዘዴ ምርጫዋ በስኩው የጃፓን ዘዴአማአዊነት ሊቀጥል አልችል ብሎ በመሸነፍ ወደቀች። የአእምሮ ጨዋታው በስህተትን ማወቅ እና የጠላት አረማመድ ወደ ጉድለት መበዝበዝ እንደ ሆነ ታውቆ እዉቀት ወደ መልስ ዉሳኔነት ተለወጠ። ድልኛነት በእዛ ተገኘ፨
የእነ ናሆም መንፈስ በዘዴአማአዊነት ፍጥጫ እና ጨዋታ ረክታ ነበር። ያን አንስተው ሲጨዋወቱ ሩት እግርኳስ ተራ የክብ ላስቲክ መሽከርከር እንደ አልሆነ ተረድታ በዘዴአማአዊነት ትንታኔው ተደመመች። ለካ ኳስ የሂወት ዘዴ መማሪአ ነው በእሚል ስትደመም እና ስትፈግግ የስነእንቅስቃሴ ላዕላይእይቱ ወደ እሩጫ ተመለሰ፨
ኃይሌ ገብረሥላሴ የአሯሯጥ ብልሃትዎችን ሲዘረዝር እና ከጀርባ ሾልኮ ለፈጣን አጨራረስ ምርጡን አማራጭ ከመሮጫ መም ቅርፅ ልዩጥቅምዎች (አድቫንቴጅስ) አንፃር ሲተነትን እና አንጎል ጨዋታው ከመሮጡ፣ ቢአንስቢአንስ እኩል ዋጋ እንዳለው በይፋ ሲጋለጥ ሩት እሩጫም ተራ የመፈርጠጥ ሳይሆን አእምሮ ዘዴአማአዊነት ፍልሚአነቱን አረጋግጣ ፈፀመች። ሚሊየንዎች እሚዘወሩት በስነእንቅስቃሴኛዎች (ስፖርትስሜን) አካልአዊ ትንቅንቅ ብቻ አልነበረም። ምን አልባት ዘዴአማአዊነት በማነፍነፍ ወደ ስነእንቅስቃሴ ታዳሚነት ለመግባት ዉሳኔ አደረገች። ሰዉነትዋን ሶፋው ላይ አመቻችታ ዘረረችው እና በመንፈላሰስ ከተቀመጠችበት ቀና ብላ ሃሳብ ለማብራራት በምርአዊነት ቀና አለች። ያልታሰበ የሂወት መስመር ከድንገትኛ ጨዋታ መሃል ቀስማ ለትዉዉቅ እንድትበቃ ማብራሪአዎች ለመጠየቅ አቅዳ ፈገግ ስትል፤ ነገን በማቀድ ዉስጥ በመኖር ጥበቡ ወርቅአማ አብነትአዊ ው ግልትምምኑ እና እውቀትን በመመርኮዝ እማያወላዳ ስኬትአማ አብሰልሳይ ልማዱ ስብእናው ከምንጊዜውም የኢትየጵያ ጥበበኛዎች አንዱ ያደረገው፣ እግርዎቹ ሲሮጡ እንደ ድንቅ ትርዒት የእሚሆንለት እና ሉልአችንን የማረከው፣ ሻለቃ ኃይሌ፣ ቀጥሎ ስለ ዩዜን ቦልት ሃብቱን ወዲያው አባክኖ ድሃ መሆን እና እንቅስቃሴ ከውኖ ሃብት ያካበተ ወይም ገቢ ያገኛ እሯጭኛ (አትሌት) ወይም ብቻ ማንኛውም ወጣት ሁሉ በመቆጠብ ንግድ መጀመር እንደ አለበት በምድር ፈጣኑ እሯጭ መቀጣጫነት ተግባርአዊ አብነት አንስቶ የሃገር ሽማግሌነት ምክሩን ድንቅ ትንታኔው ላይ አከለ። ሲጨዋወቱ እና በትመ.ው ደግ ልቦና መዛባት አድርገው ቆይተው፣ ሰዓቱ ሲረፍድ ወደ ቤትአቸው ለመመለስ እንግዳዎቹ ተነሱ፨
ዓሊ እንደ ለመደው ነጭ ኮፍያዉን በተደጋጋሚ ማስተካከል እየሸኘ ጥቂት አስጉዞአቸው ተመለሰ። እነ ሩት መንገድአቸውን ተያይዘው በጨዋታ ተመለሱ። አንድ መንደር ልክ ቀስቱን ሲአጠመዝዙ የሞተ ሬሣ ተሸክመው ለለቅሶ ወይም ቀብር በዐጀብ ሲአልፉ ተፋጠጡ። እጅግ ከፍተኛ ሁከት በልብአቸው ሠረጸ። የሰውዎቹ አለቃቀስ እና የህፃን ልጅዎች በመንገዱ አጠገብ ተቀምጠው በጭንቀት መመልከት አብልጦ ሰላም ነሳአቸው። ህፃንዎቹ ከብይ ጨወታ ወደ መቆም እና በአንጎል ደርማሽ አመለካከት አስተዋሉ። ናሆም የለቅሶው መንጫጫት እና የሰው እየበዛ ከጀርባ መምጣት ሊአይል እንደ ሆነ ሲአስብ በሩጫ በመንገዱ ዳርዳሩን ሮጦ ወደ ልጅዎቹ አዘገመ። “የእናንተ ሰፈር እዚህ ነው?” በማህበረሰብአዊ ይገባኝአለ ስሜት ቆፍጠን ብሎ ጠየቀ። “አዎ! የእነ እርሱ ቤት እዛ ጋር ነው!” አንዱ ቀልጠፍ ያለ የስምንት ዓመት አካባቢ ልጅ መለሰ። ናሆም “ኑ በሉ!” በማለት እጁን በትከሻአቸው ጭኖ ሦስቱንም እየነዳ ትኩረትአቸውን ከለቅሶው ወደ ጨዋታ መለሰ። “ማን አሸነፈ?” ብዩን እየተመለከተ በቆፍጣና ስሜቱ እንደ አለ ጠየቀ። “ገና ነው! አልተበላላንም!” ሌላው መለሰ። ወደ አሳዩት ቤት ሲደርሱ “ሰው አሳልፉ እና ቆይታችሁ ዉጡ እሺ!” በመቆጣት ሆኖ ሁሉም እንዲገቡ አድርጎ መከረ። አናት ነቅንቀው እሺታ መለሱ። አንድኛው በመጨነቅ ተሸብቦ ስለ ነበር በፈገግታ ያደረገው የገባው ያክል የማመስገን መሰል ፊት ሰ ው። ወደ ዉስጥ እንዲገቡ አስጠንቅቆ በሩን አስዘጋአቸው። ወደ ሩት በመመለስ ከሰቅጣጭ የአጯጯኽ ስነስርአት ጎን ሩትን አቅፎ አለፉት። “የሞተ ሰው እንዲህ በመንገዱ ተሸክመው ሲራመዱ እንደ ሰይጣን ልጅዎች ያስፈሩ እንደ ሆነ አይገባአቸውም!” ናሆም አለፍ ሲሉ ለሞተው ነብስ ይማር እየተመኘ አዋያት። “እ! በመኪና ሲሆንም ጥቁር መኪና! ልብስ ጥቁር። መኪናውን ቀለል አድርገው ቢቀባቡት ደግ ነበር። የሰው ልብስ መች ከጠቆረ አነሰ። ማስጨነቁ አይጣል ነው።” ጭራሽ በመኪናዎች ለቅሶ ሲፈፀም ያለውን መቋቋም ላይ ያለ አስጨናቂነት አሰበች። ባለቃቀስ ባህሉ ኩነና እና ለሌላዎች በተለይ ህፃናት አለመጨነቅ እሚከወን ለቅሶ እና ቅብር የታዳጊዎች ስነልቦና ሰቆቃ እንደ ሆነ ሃሳብአቸውን ገልጠው፣ ለቅሶው ከቶ እንደ ራቀ ሩት ፊት ላይ የሞት ጉዳይ ተስሎ ብዙ ጭንቅ ሲወርራት አስተዋለ ች። ናሆም ብዙም በልጆቹ እና ባህሉ እንጂ በግሉ ስለ ሞት አልተጨነቀም። 'የሞት ፍች ሞት አይቀርም እና አኗኗርህ ይህ ቀረሽ እሚሰኝ መሆን የለበትም ማለት ነው። በርትተህ መኖር እስከ ጥጉ መሆን አለበት ነው። መጨነቅ የለብህም። ሞት እረፍት ነው። ሳትፈራ ለመሄድ መዘጋጀት ደግሞ እንደ ግዴታ ሆኖ አለብህ። ሞት በአጭሩ እሚአስተምርህ መኖር እንደ አለብህ ነው። መመለስ እማትችል ስለሆነ በስኬት ወደ ምትፈልገው መጓዝን መልመድ አለብህ፤'
በጨዋታ መቀየር ለመዝናናት አስባ፣ ሩት የኃይሌ ጉዳይ ትዝ አላት እና “እሚናገሩት ነገር ድንቅ ነው! የት ነው በስፋት አጊንቼ እማደምጠው እና እምማርበት?” ብላ ጨዋታ አነሳች። የተሰራጨው ምክር ብልሃት ሲረጭባት ተገርማ ነበር። ማወቅን ደግሞ ፈንትዎ የሚያይ ለበለጠ ማወቅ ይነሳሳ አለ። ችግሩ ግን ይህ መረጃ የት ይገኝ አለ ሆኖ ቶሎ ለሩት ታያት። ናሆም ከመስ ጋር የተወያዩት ትዝ አለው። መረጃ መሰደር እና ማስቀመጥ እኛ ሃገር ከቶ ባህል አይደለም። ወደ ሩት የግል ግዕዝ ገጠመኙን አስታውሶ በማዘን ተመለከተ። ፍላጎቷ ሲንበለበል መረጃ ግን ባይገኝ እና ብትፈተን ስ?
ናሆም ምንም አማራጭ አልታየውም። ተንቀሳቃሽ ምስሉን ለመጎርጎር እና ከበይነመረብ ሊአወጣላት አቀደ። ግን ይህ መጥራት የሃለበት የሃገር ቅሌት ነው ብሎ ቢአንስ በጨዋታ እንድትረዳው ወደ ጎዳናው እየተመለከተ ያወጋት ጀመረ፨
“ኃይሌ ትልቅ ነገር አዉርቶ ነበር! አሁን፣ ለነገ እና አስር አመት ጀርባ አገልግሎትአችን ሆንብሎ፣ ማን ወደ ህዝብአዊ ማህደር ይክተትልን? ልክ ነሽ ጥያቄው ያ ነው። ግን እሚጠይቀው የለም! እኛ ከሊቀ ሽማግሌዎቹ ብዙ አድምጠን የስራ እና ማንነት ክብርን ከወዛም የጨዋታ ፍልስፍና ጋር ተዋዝቶ ሲቀርብ ኮመኮምን።” የሻለቃው እና ጓደኛዎቹ በዓል ጨዋታ ዳግ-ስርጭት በከፊል ሞቅ ብሎ ሲመለከቱት የነበረው ድንቅ ድባብ ትዝ ብሎት አስተዋለ። “አሁን እሚደንቀው የኢትየጵያ ያልመለስንው ግን ግንባርሥጋ ነገር፣ ኃይሌ እና ጓደኛዎቹ በያአመቱ ተነስተው ይህን ጨዋታ እና ምሥጢር ትንታኔ ይንገሩን ነው ወይ። በእያመቱ በየትዉልዱ ይህን ያውሩ እንዴ?” ነጥቡን አሰፋላት፨
ሩት በሃሳቡ ወደ ሌላ ነጥብ ሲገባ ለጨዋታ ያክል ማውራቱ አልከፋትም። የጀርባውን ሹራብ በእጇ ጨምድዳ ወገቡን አቀፈች እና “አንዴ ከተፃፈልን እኮ ለመጭ ዘመን ይገኝ ነበር። ነገርን ከጠቀመን ወይ በመተየብ ሰድረን በማህደር የማስቀመጥ አቅምአችን መበርታት አለብን ማለት ነው፤ ወይም መጽሐፍ ሁሌ እንደ ምልህ ትልልቅ ሰውዎችአችን ሊፅፉልን ይገባ አለ፤ ቁምነገርአቸው እንደ አይጠፋ!” በእብስልስል ወደ ጉዳዩ ሰመጥ ብላ አስተያየት ሰጠች። ዘመም ብላ ቀርባው እንደ አንድአንድ ጊዜው ስሜት ዋ መቀራረቡን ወድዳ ለጠፍ አለችበት። ለናሆም እና እርሷ ይህ መደበኛ ቅርርብ እንጂ ፍች የለውም። በመቀራረብ የእሚፈጥሩት አዲስ ግንኙነት ኖሮ አያውቅም። ከነፃ ጓደኝነት በቀረ። ናሆም ግን በድጋፍ ስትዘምምበት ደስ እሚል ስሜት እንደ እሚወርረው አልፎአልፎ ማስተዋል ይከውን ነበር። ሰውነቱ ፈርጠም ስለ አለ ለድጋፍ ዘመም ሊሉበት ጋባዥም ነበር። ከእርሱ ጥቂት አጠር ከአለችው አናቷ ላይ ዓይንዎች ጣል አድርጎ የአናት ፀጉሯ ወደ ትከሻዎች የተሰነተሩበት የቆዳ ንፁህ ክፍልን በነፃነት አየት አድርጎ ፈገግ አለ፨
“ልክ ነህ። ማን ይህን ትልቅ መልእክት ቀጥሎ ይሰማው ይሆን ግን? አንዴ በበዓል ጨዋታ ተወራ! በቃ! ተደግሞ አይሰማም። ያሳዝን አለ!” ናሆም በምናብ ጉዳይዎች ሲጨዋወት እሚወድደው ካፌ በከሰዓት ድባቡ እንዲታያት ሩትን ወደ እዛ ለመዉሰድ መንገዱን መለወጥ አሰበ። “ግን ዘወትር በ ትዊተር-መርኅ አኗኗር መሰረት ይህ ዉይይት በነጥብዎቹ ሁሉ ሊነሳ ይገባ ነበር። ከዜሮ መጀመር እሚሰኘው አንድኛው የኢትየጵያ ዉድቀት ነቢብ አይደል አንዴ።” ናሆም ሁለት ጉዳይዎች አነሳላት እና ወደ ካፌው መንገድ አሳበረ። ሩት ወደ እሚወስዳት መንገድ ተገርማ “ምድነው ትዊተር-መርኅ እና ከዜሮ-መነሳት ነበብአችን? እና ወደ የት ነን?” ጠየቀች። ናሆም የትእይንት ግብዣ እንደ አለው አሳውቆ ከመራመድ በተሽከርካሪዎች ለመጓዝ አስቦ ሦስት እግርዎቹን ቀጠረ።
በመኪናው ተቀምጠው መጓዝ ሲጀምሩ የእሚረብሽ እሚሰኝ አቀስቃሽ ድምፁን እየታገለ ማብራራት ጀመረ። “ከዜሮ መጀመር ማለት እንደ ኃይለ ቃሉ ግልፅ ነው! ምንም ነገር ሲሰራ፣ ሲኖር እና ሲታደግ፣ ሲረጅም፣ ሁለንተና ሂወት በአጭሩ፣ በቀደመ የታሪክ መረጃ መሪነት አይደረግም። ከአዲስ አፍርሶ መገንባት እና መስራት መሞከር ልማድአችን ነው እሚል ነጥብ ነው። ፍሬሃሳቡን ለማደንደን ተግባርአዊ ምሳሌ ብለው የየመንግስትዎች ጥረትዎች በግል እንደ ተከወኑ እና በቀደመ መንግስት በርትቶ መቀጠል እንደ ሌለ ያብራሩልሽ አለ። መዉጫ መንገድ ብለው ያው ሂወት በቀደመ ተሞክሮ ምሪት ትጓዝ እና እንደግ ባባይ ነቢብ ነው። በቀረ በአዲስ ጥረት ተመሳሳይ እሽክርክሪት ዉስጥ ስንኳትን ትዉልድዎች በከንቱ አለፉ ነው ነጥቡ! ‘ሁሉን ሁሌ ከአዲስ' እሚል መርኅ ይዞን የተሸወድን ነን' ማለቱ ነው።”
“እና ትትዊተር-መርኅ የ አልክው ነገር ስ?” አብራ ሩትም ጮኽ በማለት ጠየቀች። በነገራት ሃሳብ ግልጥነት ታያት። ግልጥ ስለሆነ ግን ቀላል እንዳይመስላት እና እንዳትንቀው ጣረች።
“መጽሐፍ ነገር ይፃፉልን… ሁሌ መልእክቱ በቋሚነት እንዲገኝ … ወደ አልሽው ወደ ነጥብሽ ልመልስሽ እና ቀድሜ፣ ያ መፍትሔው አይደለም። የቀስተደመናአማው መፍትሔ አንድ ነፀብራቅ ነው። በተገቢው መንገድ ስትጓዢ እርሱ አንድ ነፀብራቅ እንጂ ፍፃሜ አይደለም።
ሩት የሃገሪቷ ትልልቅ ሰውዎች ልምድ በመጽሐፍዎች እና ዘጋቢ ፊልምዎች ከተሰደረ፣ ልምድ ወደ ቀጣይ ትዉልድ ይሻገር ነበር። እሚሄድ ዘመን ሲአልፍ ልምዱ ግን ለትዉልዱ ካርታ ይሆንለት አለ ብላ በማመን ስለ እማንፅፍ እና ታሪክ ለትዉልድ፣ ሃገሩ ስለ እማያስቀር የሃዘን ነጥብዋን በዙሪአው ተበሳጭታ ትሰጥ ነበር፤ እድሉ ሲገኝ። ነገርግን የናሆም ሃሳብ ከ እዛ ሲለይባት፣ ምን በላጭ ነገር ቢገኝ ነው ብላ ጆሮ በመክፈት ጠበቀች። ወደ ካፌው ሲደርሱ የበለጠ ተስተናጋጅ ናሆም አስተዋለ። አንድ ወንበር ስቦ እንድትቀመጥ ሰበዘ። ዞሮ በመቀመጥ እሚወድደውን ጭማቂ አዘዘ። እርሷ ትኩስ ነገር በመፈለግ ወተት በቡና ጠቁሮ እንዲመጣላት አዘዘች። ናሆም ያሰበውን በመጠቅለል ካመነችበት በእሚል አብራራለት።
“ምን መሰለሽ። ሂወት አኗኗሩ ከስሩ ይነቃ ዘንድ የተፈቀደ ቀን ነገር ሁሉ በእራሱ አካሄድ ይስተካከል አለ። በእርግጥ መፅሐፍ መፃፍ ወይ ታሪክ በአንድ እና ብዙ አማራጭዎች የመተው ትልቅ ነገር እና ቀዉስ ክፍተት እምናስመለክትበት ቋሚ ስህተትአችን ነው። ግን እርሱን ማከም አንዱ መንገድ ብቻ ነው። በሽቃቤነጥብ፣ ጣሪአ ለመድረስ ወለሉን በመነካካት፣ መድከም ነው። ዋናው፣ ተገቢ ሂወትን በአንድ ሁለት ሦስት ምርጥ መንገድ መቁጠሩ አይደለም። ሂወት ማሻሻያ መንገዱ ተቆጥሮ አያልቅም እና። ልኩ አይታወቅም።" ሩት የታዘዘው ሲቀርብ አተኩራ ማድመጡን ተያይዛ ነበር። በሃሳቡ መማረኳን አይቶ ናሆም ቀጠለ። "ብቻ ግን ሂወት ከቅናሼነጥብ በርቶ – ጣሪአው ፈንጥቆ ቤቱ ቢበራ – እና ያኗኗር አንድ ሁለት ሦስት ገፅታ ቢመነዘር ይሻል አለ። አንዴ የበራ አኗኗር ሲመነዘር እልፍ ስንጥርዎች አንስተሽ ብትፈትሽው፣ አኩሪ መልስ አለው። ለምሳሌ እንደ አልሽው መፅሐፍዎች እና ዘጋቢ ፊልምዎች ስለስኬትአማ ሰውዎችአችን አለን ወይ?፣ ስትይ መልሱ አዉ ይሆን አለ። በእራስሰር ሂወት መስመር ስለ ያዘ ምንም ብትጠይቂ አጥጋቢ ነገር ትትመለከች አለሽ።" በሃሳቡ ወደ አንድ ነጥብ ገብቶ ለመቋጨት ምናቡን በረበረ። በመጨረሻ የ ተነሳውን መጠቅለያ ከብዙ አማራጭዎች መሀል ልኮት (ሪፈረንስ) ሆኖ እንዲአግዘው ጠራ። "አው። ለ ምሳሌ ድረገፁትዊተርን ተመልከች። በቃ የ ትዊተር አሰራር የሂወት ምርጡ መንገድ ነው። ድንቅ ፈጠራ ብዬ ከእልፍ ፈጠራዎች እማስበልጠው ጉዳይ ነው ትዊተር።በ ማለዳ ቀድሞ በመነሳት እነ ናሆም የቀጠለ የድንጋይ ማጋዝ ሥራአቸውን ከወኑ። ብሩ ሰዉነቱ ስለ አላስቻለው በጥቂቱ እያገዘ ብዙ ድንጋይዎችን እንደ ህብረት በቤትአቸው ከመሩ። እረፋዱ ላይ ከቁርስ መልስ የጋሽ አበራ መልእክተኛ መጥቶ የተመረጠ አፈሩን ከእሚገነባው ቤት ጀርባ አራገፈ። አህያዎቹን እየ ነዳ በመመላለስ አፈሩን ከአከማቸ በኋላ ሂሳቡን ለመቀበል በጋሽ አበራ ቤት አስርሰዓት ተቀጣጠሩ። መስ ናሆምን አስከትሎ ሱቅ በመሄድ ኖራ እና እንቁላልዎችን ገዝተው ጭቃ ወደ ማብካቱ ገቡ። ጭድ እሚአመጣ አህያም ከጋሽ አበራ ዘግይቶ ደርሶ ማቡካቱን ሁሉ እየተደመመበት በመስ ተከወነ፨
ምሳ ከበሉ በኋላ ናሆም በቶሎ ተለይቶ ወደ ሩት ቤት አመራ። ሩት በፈገግታ ተቀብላው፣ በአዲስ ሙሉ ልብስ አምሮባት ተያይዘው በመለዱት አቋራጭ መንገድ የጨዋታ ጉዞ ዓሊ ቤት ደረሱ። ዓሊ ሰዓት ጥቂት ስለ ረፈደ በመቆጣት አስገባአቸው እና ጨዋታውን በዘገባ ማቅረብ ጀመሩ። የሰሚራ አልፎአልፎ ጨዋታ እየአቋረጠአቸው፣ በሻይ እና ቆሎ ግብዣ የሩት ሁኔታን መገምገም ተጀመረ፨
ሩት በኅዋአዊከተማ ው ደግ መስተንግዶ እንደ ተደረገላት እና ስለእንስሳዎች ህክምና በቂ ትዉዉቅ እንደ አገኘች በመንገር የመምህርዎቹ ለዓመት ማብቂያ ፈተና መሯሯጥ ስለ ነበር ለክረምቱ ግን በማስተማር ስለማይጠመዱ ጉያአቸው ከትተው ጓደኛምዎች መምህርዎች ብዙ ሊያስመለክቷት ቃል እንደ ገቡ እና ስልክ እንደ ተቀያየረች እና እንደ ተግባቡ ተናገረች። ሁለቱም በመደሰት እንኳን ደስያለሽ በማለት አበረታቱ። የጠበቀችው አስጊ ማህበርአዊ ክልልም ባሉት ጥበብዎች እንደ ቀለለላት እና ቀና ቀን ማሳለፏን ገለጠች፨
ዓሊ ለቤተሰብዎቹ አገልጋይ ሆኖ ስለ ተያዘ ጥቂት ቆይቶ ወደ ገጠር ዘመድዎቹ በመመለስ መረጃዎች እንደ እሚቃርም እና የግንኙነትዎች ድር እንደ እሚሞክር አሳወቀ። “እኛን ብዙ አበረታትተህ አንተ ይህን ብቻ ነው ያደረግክው?!” ሩት በተቆጣ ስሜት ዓሊን ገሠፀች። ናሆምም ተግባርአዊ ነገር እንደ ጠበቀ ገልፆ አገዛት። ዓሊ ሩት ላይ በማሾፍ እየተጨዋወቱ ቆይተው፤ አማራጭ እንዳልነበረው በማንበብ እና ማቀድ ብቻ እንደ ቆየ ገለፀ፨
ናሆም ግብርና በተግባር ለማጥናት እና ተያያዥ የሙከራ ቤተመብል ለማዘጋጀት እንደሚሞክር እና የደረሰበትን አብራራ። ሁለቱ ም ባከናወነው ተደስተው አበረታቱት።
ሲጨዋወቱ ቆይተው ሩት በክረምቱ ከማጥናቱ ጋር እንደ እምትከርም ገለጸች። ናሆም በሥራ እንደ እሚጠመድ አሳወቀ። ዓሊ እሚመለስበት እንደ እማያውቅ አሳወቀ። ሁሉም ዋና አላማአቸውን ከዉነው ወደ ጓደኛአዊ ጨዋታዎች ተመለሱ። በልብወዳጅነት ስለ ሁሉ ጉዳይ በመጨዋወት እና ሠሚራ ወጣገባ ስትል በእምታቀርብልአቸው የ ቀለለ እና ጎንታይ ጨዋታዎች ደምቀው በመጨዋወት ቆዩ። ሩት እንደ ወትሮው በዓሊ አድፍጦ ደግ ነገር አዉጠንጥኖ መምጣት አቅም ተማርካ በማድነቅ እየጎነተለችው። “ይኸው መቶ ሚሊየን ገበሬ ባለበት ሃገር ስንራብ መንግስት መኪናአዊ ማድረግ የነበረበትን ግብርና እያያዝአለሁ ብሎ በሞኝ መንግስት እሚአሾፍ ጀግና ተቀምጦልሽ አለ እንዴ! እርሱስ አይደነቅም!” ዓሊ ሲገስፃት ሩት ደነገጠች። ናሆም ሳያስተውለው “አንተን ነዋ ‘ምቶደው!” እሚል አመለጠው። ያላቀደው ስለነበር በጨዋታ ስለ ወጣ እሚታሽ ወለምታ አልሆነለትም። በመደንገጥ ሁሉም ተፋጠጡ። የተስተዋለ ስሜት እንደ እዚህ አልነበረም። ግን ሩት ለዓሊ ያላት ስሜት በእዛ መንገድ ከተተረጎመ መልሳ ሁኔታዋ ከነከናት። ጥቂት ዝምታ ሰፍኖ ዓሊ ሁኔታውን ሲአስተውል ሩት “በእዚህ የመረጃ ዘመን ለነገሩ የግብርና መረጃን ከቀረው በመለየት ለግብርናው እሚሟት ብቻ ሳይሆን መረጃ አያያዝን በመምረጥ መከታተል ያስተማረን ናሆም እማ ልዩ ምስጋና ይገባው አለ! በመረጃ እሚደነቆርበት ዘመን ላይ ናሆም መምህር ነው!” በተደመመ አተያይ ወደ ናሆም ዞራ ጉዳዩን ቀየር አደረገች። ዓሊ በአተያየቷ እቅጭነት ተገረመ። ጨዋታውን ለማስፋት ያክል “መረጃ ዘመን የመረጃ መደንቆር ነው እንዴ?” ዓሊም በጨዋታው መቀየር ተደስቶ ጠየቀ። ሩት በጣሪአው ጠየም ያለ ፊቷ ላይ ሲአፈጥጡ በተለየ ንጣትአቸው ዉብ መስተጋብር እሚፈጥሩ ዓይኖቿን ላከች። ፊቷ እሚቆንጅበት አኳኋን ላይ እንደ ቆየች ያሰበችውን አብራራች። “ሰው የመስማት አቅሙ ከትንንሽ ድምፆዎች ወደ ጫጫታ ከእዛ ጩኸት ይደርስ አለ። ግን ከፍተኛ ጩኸት፣ ለምሳሌ አደንቋሪ ሙዚቃ መጠን እንደ እምንለው፣ ጆሮ ይጎዳ አለ። በሂደት ታምቡር ተቀድዶ መድማት አለ። ከተጨረ ድምጹ መሞት አለ አይደል? እና መረጃም ከአቅም በላይ መርጆን ደንዘን አለ። ወደ ሞት ሊቀረብ ምንም አልቀረም። ዘሪቱ እንዳለችው አኗኗር ወደ ዉሸት አምጥቶ ኑሮ እየሞተ ነው። መረጃ ደግሞ መብዛቱ እና አለመመረጥ መቻሉ አንዱ ይመስለኝ አለ።” ወደ ናሆም ተመለሰች። ጀርባውን በጨወታ መታመታ አድርጋ “ይህ ሰው ግን እሚፈልገውን በማደን እንጂ ማስታወቅያ እና ተያያዥ ማጥመጃዎችን በመዝለል አቅሙ ድንቅ የአሃዝ ዘመን አትኩሮት አዳብሮ አለ። መሸለም አለበት!” ምስጋናዋን ቸራ በፈገግታ የጓደኛዋን ፊት ተመለከተች። ናሆም አመስግኖ በጥቂት ዝምታ ተዋጡ። አሁንም ዝምታው ሲጨንቃት “በቃ ገጠር ስትገባ ዳማከሴ እና ጤናአዳም ለእራስምታትዎችአችን አዘጋጅልን እንግዲህ። በእንክብል እና ሽሮፕ ስሪት አቅርብልን። ዱቄት (ፖውደር) አለ ለነገሩ።” ለሩት ይህ ጨዋታ ሆኖ ከአስደሰታት ብሎ ዓሊ ሊያግዝ ብቻ ብሎ ጨዋታውን አሰፋው። “የሮማን፣ እንኮይ፣ እንጆሪ፣ ወይን፣ ወዘተ. ምርትዎች መልክአቸው ተረስቶ አለ። የፍራፍሬ ምንንት ሁሉ ሳይረሳን ናሆም ደርሶ እእንድንቀምስ ያግዘን አለ፤ የኔን ተይው…” ድንገት የቀደመ ሦስታዬ (ትሪአንግል) መመለሱ ሲገባው የጀመረውን አቋረጠ። “ወለምታ ሲይዝሽ ብቻ ነይ ወደ እኔ…!” በእሚል ፈገግታ ጭምር ተመለሰ። መልሶ ዝምታ እንዳይሆን የትመ. ማያገፅን ሩት ተነስታ አበራች። በመሰባሰብ ለመተያየት እና መጨዋወት እንጂ ልቦና ለማመሰቃቀል ስለ እሚዳርግ በጨዋታዎች መሀል ትመ. ወይም ተስ. መጎርጎር አያደርጉም ነበር። አሁን ግን ለጨዋታ ምንጭነት ሩት ተመኝታው ለሎሌነት ተከፈተ። የራሺያ ዓለም ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታ ላዕላይ-እይትዎች (ሃይላይትስ) በናሁ ትመ. ሲሰራጭ ነበር። በእግርኳስ ጨዋታ የዓለም ዋንጫ እና አህጉርአዊ ጨዋታዎች ካልሆነ የመከታተል ልማድ ከቶ የሌለአቸው ወጣትዎቹ በመደነቅ ስለ ጨዋታው ተወያዩ። በተለየ እማይረሳ አንድ የዓለም ዋንጫው ዉብ ትዝታ የጃፓን፣ ቤልጂየም፣ እና ብራዚል ብሔርአዊ ቡድንዎች የክሂሎትአማአዊነት እና ገናኝግንኙነትአዊነት (ታክቲካል) ዘዴአማአዊነትዎች ጦርነትዎች ነበር። ናሆም እና ዓሊ ምናብ ከእግርኳስ ወይም ሌላ ስነእንቅስቃሴ (ስፖርት) በመደመም እሚመለከተው ይህን መሰል ዘዴአማአዊነት ጦርነትዎች ስለነበር ይህን አይረሱትም። ጃፓን በመከላከል ደጀን አፅንታ በደራሽ መልሶማጥቃት ወጉ። ከእዛ ዘዴአማአዊነት በላይ ግን የኩርቶዋ ቆጥ አካልን ለመበዝበዝ ምትዎች በመሬት በማንከባለል ይልኩ ነበር። ይህ ስኬቱ መቶ እጅ ሆኖ ቆየ። ቤልጂየም የማታማታ ግን እንደ እባብ አንሰራርታ ድለኛ (ሻምፒዮን) ሆነች። እነ ናሆም በጃፓን የአካል-ወጥነት (ስታሚና) መስነፍ የተለመደ የሩቅ ምስራቅ ሃገር እግርኳስአዊ ጉድለት ደግመው ዋጋ ሲከፍሉ ተመለከቱ። ቀጣይ የመጣው ግን ሌላ የዘዴ አነፍናፊ አንጎል ምርጥ መብል ነበር። ብራዚል የጃፓን ክሂሎትአማአዊነት እና ገናኝግንኙነትአዊነት ስኬትአማነትን መልሰው በመቶ እጅ ግልበጣ ይዘው ገቡ። የጃፓንዎች ትምፋሽ መድከም በብራዚልዎች ስለሌለ ሁሉም የቤልጂየም መዉደቅን ቀድሞ አመነ። ዘጠና ደቂቃ ግን ኳስ ድቡልቡል እንደ ሆነች ሳይሆን ዘዴአማአዊነት የሂወት መልስ እንደ ሆነች ለአጤነው አስመለከተች። ቤልጂየም ዘዴአማአዊነት ምርጫአቸውን አስተካክለው ለጦርነቱ ፍልሚአ ገብተው ጉድ አሰኙ። ኩርቶዋ በመሬት ፈጥኖ መዘርጠጥን አብዝቶ በቀንዎች ልዩነት ከመስራቱ በዘለለ ብራዚል ግን በጃፓን አካሄድ መልሳ በደራሽ ጥቃት መሬት ለመሬት መምታት እንደ እምትያያዝ ስለታወቀ ቤልጂየም መሬቱን እንደ ተቃውሞ መንገድ መዝጋት ብቻ ለምዳ ጭንቅ ወለደች። ብራዚል የግል የቀደመ ዘዴ ምርጫዋ በስኩው የጃፓን ዘዴአማአዊነት ሊቀጥል አልችል ብሎ በመሸነፍ ወደቀች። የአእምሮ ጨዋታው በስህተትን ማወቅ እና የጠላት አረማመድ ወደ ጉድለት መበዝበዝ እንደ ሆነ ታውቆ እዉቀት ወደ መልስ ዉሳኔነት ተለወጠ። ድልኛነት በእዛ ተገኘ፨
የእነ ናሆም መንፈስ በዘዴአማአዊነት ፍጥጫ እና ጨዋታ ረክታ ነበር። ያን አንስተው ሲጨዋወቱ ሩት እግርኳስ ተራ የክብ ላስቲክ መሽከርከር እንደ አልሆነ ተረድታ በዘዴአማአዊነት ትንታኔው ተደመመች። ለካ ኳስ የሂወት ዘዴ መማሪአ ነው በእሚል ስትደመም እና ስትፈግግ የስነእንቅስቃሴ ላዕላይእይቱ ወደ እሩጫ ተመለሰ፨
ኃይሌ ገብረሥላሴ የአሯሯጥ ብልሃትዎችን ሲዘረዝር እና ከጀርባ ሾልኮ ለፈጣን አጨራረስ ምርጡን አማራጭ ከመሮጫ መም ቅርፅ ልዩጥቅምዎች (አድቫንቴጅስ) አንፃር ሲተነትን እና አንጎል ጨዋታው ከመሮጡ፣ ቢአንስቢአንስ እኩል ዋጋ እንዳለው በይፋ ሲጋለጥ ሩት እሩጫም ተራ የመፈርጠጥ ሳይሆን አእምሮ ዘዴአማአዊነት ፍልሚአነቱን አረጋግጣ ፈፀመች። ሚሊየንዎች እሚዘወሩት በስነእንቅስቃሴኛዎች (ስፖርትስሜን) አካልአዊ ትንቅንቅ ብቻ አልነበረም። ምን አልባት ዘዴአማአዊነት በማነፍነፍ ወደ ስነእንቅስቃሴ ታዳሚነት ለመግባት ዉሳኔ አደረገች። ሰዉነትዋን ሶፋው ላይ አመቻችታ ዘረረችው እና በመንፈላሰስ ከተቀመጠችበት ቀና ብላ ሃሳብ ለማብራራት በምርአዊነት ቀና አለች። ያልታሰበ የሂወት መስመር ከድንገትኛ ጨዋታ መሃል ቀስማ ለትዉዉቅ እንድትበቃ ማብራሪአዎች ለመጠየቅ አቅዳ ፈገግ ስትል፤ ነገን በማቀድ ዉስጥ በመኖር ጥበቡ ወርቅአማ አብነትአዊ ው ግልትምምኑ እና እውቀትን በመመርኮዝ እማያወላዳ ስኬትአማ አብሰልሳይ ልማዱ ስብእናው ከምንጊዜውም የኢትየጵያ ጥበበኛዎች አንዱ ያደረገው፣ እግርዎቹ ሲሮጡ እንደ ድንቅ ትርዒት የእሚሆንለት እና ሉልአችንን የማረከው፣ ሻለቃ ኃይሌ፣ ቀጥሎ ስለ ዩዜን ቦልት ሃብቱን ወዲያው አባክኖ ድሃ መሆን እና እንቅስቃሴ ከውኖ ሃብት ያካበተ ወይም ገቢ ያገኛ እሯጭኛ (አትሌት) ወይም ብቻ ማንኛውም ወጣት ሁሉ በመቆጠብ ንግድ መጀመር እንደ አለበት በምድር ፈጣኑ እሯጭ መቀጣጫነት ተግባርአዊ አብነት አንስቶ የሃገር ሽማግሌነት ምክሩን ድንቅ ትንታኔው ላይ አከለ። ሲጨዋወቱ እና በትመ.ው ደግ ልቦና መዛባት አድርገው ቆይተው፣ ሰዓቱ ሲረፍድ ወደ ቤትአቸው ለመመለስ እንግዳዎቹ ተነሱ፨
ዓሊ እንደ ለመደው ነጭ ኮፍያዉን በተደጋጋሚ ማስተካከል እየሸኘ ጥቂት አስጉዞአቸው ተመለሰ። እነ ሩት መንገድአቸውን ተያይዘው በጨዋታ ተመለሱ። አንድ መንደር ልክ ቀስቱን ሲአጠመዝዙ የሞተ ሬሣ ተሸክመው ለለቅሶ ወይም ቀብር በዐጀብ ሲአልፉ ተፋጠጡ። እጅግ ከፍተኛ ሁከት በልብአቸው ሠረጸ። የሰውዎቹ አለቃቀስ እና የህፃን ልጅዎች በመንገዱ አጠገብ ተቀምጠው በጭንቀት መመልከት አብልጦ ሰላም ነሳአቸው። ህፃንዎቹ ከብይ ጨወታ ወደ መቆም እና በአንጎል ደርማሽ አመለካከት አስተዋሉ። ናሆም የለቅሶው መንጫጫት እና የሰው እየበዛ ከጀርባ መምጣት ሊአይል እንደ ሆነ ሲአስብ በሩጫ በመንገዱ ዳርዳሩን ሮጦ ወደ ልጅዎቹ አዘገመ። “የእናንተ ሰፈር እዚህ ነው?” በማህበረሰብአዊ ይገባኝአለ ስሜት ቆፍጠን ብሎ ጠየቀ። “አዎ! የእነ እርሱ ቤት እዛ ጋር ነው!” አንዱ ቀልጠፍ ያለ የስምንት ዓመት አካባቢ ልጅ መለሰ። ናሆም “ኑ በሉ!” በማለት እጁን በትከሻአቸው ጭኖ ሦስቱንም እየነዳ ትኩረትአቸውን ከለቅሶው ወደ ጨዋታ መለሰ። “ማን አሸነፈ?” ብዩን እየተመለከተ በቆፍጣና ስሜቱ እንደ አለ ጠየቀ። “ገና ነው! አልተበላላንም!” ሌላው መለሰ። ወደ አሳዩት ቤት ሲደርሱ “ሰው አሳልፉ እና ቆይታችሁ ዉጡ እሺ!” በመቆጣት ሆኖ ሁሉም እንዲገቡ አድርጎ መከረ። አናት ነቅንቀው እሺታ መለሱ። አንድኛው በመጨነቅ ተሸብቦ ስለ ነበር በፈገግታ ያደረገው የገባው ያክል የማመስገን መሰል ፊት ሰ ው። ወደ ዉስጥ እንዲገቡ አስጠንቅቆ በሩን አስዘጋአቸው። ወደ ሩት በመመለስ ከሰቅጣጭ የአጯጯኽ ስነስርአት ጎን ሩትን አቅፎ አለፉት። “የሞተ ሰው እንዲህ በመንገዱ ተሸክመው ሲራመዱ እንደ ሰይጣን ልጅዎች ያስፈሩ እንደ ሆነ አይገባአቸውም!” ናሆም አለፍ ሲሉ ለሞተው ነብስ ይማር እየተመኘ አዋያት። “እ! በመኪና ሲሆንም ጥቁር መኪና! ልብስ ጥቁር። መኪናውን ቀለል አድርገው ቢቀባቡት ደግ ነበር። የሰው ልብስ መች ከጠቆረ አነሰ። ማስጨነቁ አይጣል ነው።” ጭራሽ በመኪናዎች ለቅሶ ሲፈፀም ያለውን መቋቋም ላይ ያለ አስጨናቂነት አሰበች። ባለቃቀስ ባህሉ ኩነና እና ለሌላዎች በተለይ ህፃናት አለመጨነቅ እሚከወን ለቅሶ እና ቅብር የታዳጊዎች ስነልቦና ሰቆቃ እንደ ሆነ ሃሳብአቸውን ገልጠው፣ ለቅሶው ከቶ እንደ ራቀ ሩት ፊት ላይ የሞት ጉዳይ ተስሎ ብዙ ጭንቅ ሲወርራት አስተዋለ ች። ናሆም ብዙም በልጆቹ እና ባህሉ እንጂ በግሉ ስለ ሞት አልተጨነቀም። ‘የሞት ፍች ሞት አይቀርም እና አኗኗርህ ይህ ቀረሽ እሚሰኝ መሆን የለበትም ማለት ነው። በርትተህ መኖር እስከ ጥጉ መሆን አለበት ነው። መጨነቅ የለብህም። ሞት እረፍት ነው። ሳትፈራ ለመሄድ መዘጋጀት ደግሞ እንደ ግዴታ ሆኖ አለብህ። ሞት በአጭሩ እሚአስተምርህ መኖር እንደ አለብህ ነው። መመለስ እማትችል ስለሆነ በስኬት ወደ ምትፈልገው መጓዝን መልመድ አለብህ፤’
በጨዋታ መቀየር ለመዝናናት አስባ፣ ሩት የኃይሌ ጉዳይ ትዝ አላት እና “እሚናገሩት ነገር ድንቅ ነው! የት ነው በስፋት አጊንቼ እማደምጠው እና እምማርበት?” ብላ ጨዋታ አነሳች። የተሰራጨው ምክር ብልሃት ሲረጭባት ተገርማ ነበር። ማወቅን ደግሞ ፈንትዎ የሚያይ ለበለጠ ማወቅ ይነሳሳ አለ። ችግሩ ግን ይህ መረጃ የት ይገኝ አለ ሆኖ ቶሎ ለሩት ታያት። ናሆም ከመስ ጋር የተወያዩት ትዝ አለው። መረጃ መሰደር እና ማስቀመጥ እኛ ሃገር ከቶ ባህል አይደለም። ወደ ሩት የግል ግዕዝ ገጠመኙን አስታውሶ በማዘን ተመለከተ። ፍላጎቷ ሲንበለበል መረጃ ግን ባይገኝ እና ብትፈተን ስ?
ናሆም ምንም አማራጭ አልታየውም። ተንቀሳቃሽ ምስሉን ለመጎርጎር እና ከበይነመረብ ሊአወጣላት አቀደ። ግን ይህ መጥራት የሃለበት የሃገር ቅሌት ነው ብሎ ቢአንስ በጨዋታ እንድትረዳው ወደ ጎዳናው እየተመለከተ ያወጋት ጀመረ፨
“ኃይሌ ትልቅ ነገር አዉርቶ ነበር! አሁን፣ ለነገ እና አስር አመት ጀርባ አገልግሎትአችን ሆንብሎ፣ ማን ወደ ህዝብአዊ ማህደር ይክተትልን? ልክ ነሽ ጥያቄው ያ ነው። ግን እሚጠይቀው የለም! እኛ ከሊቀ ሽማግሌዎቹ ብዙ አድምጠን የስራ እና ማንነት ክብርን ከወዛም የጨዋታ ፍልስፍና ጋር ተዋዝቶ ሲቀርብ ኮመኮምን።” የሻለቃው እና ጓደኛዎቹ በዓል ጨዋታ ዳግ-ስርጭት በከፊል ሞቅ ብሎ ሲመለከቱት የነበረው ድንቅ ድባብ ትዝ ብሎት አስተዋለ። “አሁን እሚደንቀው የኢትየጵያ ያልመለስንው ግን ግንባርሥጋ ነገር፣ ኃይሌ እና ጓደኛዎቹ በያአመቱ ተነስተው ይህን ጨዋታ እና ምሥጢር ትንታኔ ይንገሩን ነው ወይ። በእያመቱ በየትዉልዱ ይህን ያውሩ እንዴ?” ነጥቡን አሰፋላት፨
ሩት በሃሳቡ ወደ ሌላ ነጥብ ሲገባ ለጨዋታ ያክል ማውራቱ አልከፋትም። የጀርባውን ሹራብ በእጇ ጨምድዳ ወገቡን አቀፈች እና “አንዴ ከተፃፈልን እኮ ለመጭ ዘመን ይገኝ ነበር። ነገርን ከጠቀመን ወይ በመተየብ ሰድረን በማህደር የማስቀመጥ አቅምአችን መበርታት አለብን ማለት ነው፤ ወይም መጽሐፍ ሁሌ እንደ ምልህ ትልልቅ ሰውዎችአችን ሊፅፉልን ይገባ አለ፤ ቁምነገርአቸው እንደ አይጠፋ!” በእብስልስል ወደ ጉዳዩ ሰመጥ ብላ አስተያየት ሰጠች። ዘመም ብላ ቀርባው እንደ አንድአንድ ጊዜው ስሜት ዋ መቀራረቡን ወድዳ ለጠፍ አለችበት። ለናሆም እና እርሷ ይህ መደበኛ ቅርርብ እንጂ ፍች የለውም። በመቀራረብ የእሚፈጥሩት አዲስ ግንኙነት ኖሮ አያውቅም። ከነፃ ጓደኝነት በቀረ። ናሆም ግን በድጋፍ ስትዘምምበት ደስ እሚል ስሜት እንደ እሚወርረው አልፎአልፎ ማስተዋል ይከውን ነበር። ሰውነቱ ፈርጠም ስለ አለ ለድጋፍ ዘመም ሊሉበት ጋባዥም ነበር። ከእርሱ ጥቂት አጠር ከአለችው አናቷ ላይ ዓይንዎች ጣል አድርጎ የአናት ፀጉሯ ወደ ትከሻዎች የተሰነተሩበት የቆዳ ንፁህ ክፍልን በነፃነት አየት አድርጎ ፈገግ አለ፨
“ልክ ነህ። ማን ይህን ትልቅ መልእክት ቀጥሎ ይሰማው ይሆን ግን? አንዴ በበዓል ጨዋታ ተወራ! በቃ! ተደግሞ አይሰማም። ያሳዝን አለ!” ናሆም በምናብ ጉዳይዎች ሲጨዋወት እሚወድደው ካፌ በከሰዓት ድባቡ እንዲታያት ሩትን ወደ እዛ ለመዉሰድ መንገዱን መለወጥ አሰበ። “ግን ዘወትር በ ትዊተር-መርኅ አኗኗር መሰረት ይህ ዉይይት በነጥብዎቹ ሁሉ ሊነሳ ይገባ ነበር። ከዜሮ መጀመር እሚሰኘው አንድኛው የኢትየጵያ ዉድቀት ነቢብ አይደል አንዴ።” ናሆም ሁለት ጉዳይዎች አነሳላት እና ወደ ካፌው መንገድ አሳበረ። ሩት ወደ እሚወስዳት መንገድ ተገርማ “ምድነው ትዊተር-መርኅ እና ከዜሮ-መነሳት ነበብአችን? እና ወደ የት ነን?” ጠየቀች። ናሆም የትእይንት ግብዣ እንደ አለው አሳውቆ ከመራመድ በተሽከርካሪዎች ለመጓዝ አስቦ ሦስት እግርዎቹን ቀጠረ።
በመኪናው ተቀምጠው መጓዝ ሲጀምሩ የእሚረብሽ እሚሰኝ አቀስቃሽ ድምፁን እየታገለ ማብራራት ጀመረ። “ከዜሮ መጀመር ማለት እንደ ኃይለ ቃሉ ግልፅ ነው! ምንም ነገር ሲሰራ፣ ሲኖር እና ሲታደግ፣ ሲረጅም፣ ሁለንተና ሂወት በአጭሩ፣ በቀደመ የታሪክ መረጃ መሪነት አይደረግም። ከአዲስ አፍርሶ መገንባት እና መስራት መሞከር ልማድአችን ነው እሚል ነጥብ ነው። ፍሬሃሳቡን ለማደንደን ተግባርአዊ ምሳሌ ብለው የየመንግስትዎች ጥረትዎች በግል እንደ ተከወኑ እና በቀደመ መንግስት በርትቶ መቀጠል እንደ ሌለ ያብራሩልሽ አለ። መዉጫ መንገድ ብለው ያው ሂወት በቀደመ ተሞክሮ ምሪት ትጓዝ እና እንደግ ባባይ ነቢብ ነው። በቀረ በአዲስ ጥረት ተመሳሳይ እሽክርክሪት ዉስጥ ስንኳትን ትዉልድዎች በከንቱ አለፉ ነው ነጥቡ! ‘ሁሉን ሁሌ ከአዲስ’ እሚል መርኅ ይዞን የተሸወድን ነን’ ማለቱ ነው።”
“እና ትትዊተር-መርኅ የ አልክው ነገር ስ?” አብራ ሩትም ጮኽ በማለት ጠየቀች። በነገራት ሃሳብ ግልጥነት ታያት። ግልጥ ስለሆነ ግን ቀላል እንዳይመስላት እና እንዳትንቀው ጣረች።
“መጽሐፍ ነገር ይፃፉልን… ሁሌ መልእክቱ በቋሚነት እንዲገኝ … ወደ አልሽው ወደ ነጥብሽ ልመልስሽ እና ቀድሜ፣ ያ መፍትሔው አይደለም። የቀስተደመናአማው መፍትሔ አንድ ነፀብራቅ ነው። በተገቢው መንገድ ስትጓዢ እርሱ አንድ ነፀብራቅ እንጂ ፍፃሜ አይደለም።
ሩት የሃገሪቷ ትልልቅ ሰውዎች ልምድ በመጽሐፍዎች እና ዘጋቢ ፊልምዎች ከተሰደረ፣ ልምድ ወደ ቀጣይ ትዉልድ ይሻገር ነበር። እሚሄድ ዘመን ሲአልፍ ልምዱ ግን ለትዉልዱ ካርታ ይሆንለት አለ ብላ በማመን ስለ እማንፅፍ እና ታሪክ ለትዉልድ፣ ሃገሩ ስለ እማያስቀር የሃዘን ነጥብዋን በዙሪአው ተበሳጭታ ትሰጥ ነበር፤ እድሉ ሲገኝ። ነገርግን የናሆም ሃሳብ ከ እዛ ሲለይባት፣ ምን በላጭ ነገር ቢገኝ ነው ብላ ጆሮ በመክፈት ጠበቀች። ወደ ካፌው ሲደርሱ የበለጠ ተስተናጋጅ ናሆም አስተዋለ። አንድ ወንበር ስቦ እንድትቀመጥ ሰበዘ። ዞሮ በመቀመጥ እሚወድደውን ጭማቂ አዘዘ። እርሷ ትኩስ ነገር በመፈለግ ወተት በቡና ጠቁሮ እንዲመጣላት አዘዘች። ናሆም ያሰበውን በመጠቅለል ካመነችበት በእሚል አብራራለት።
“ምን መሰለሽ። ሂወት አኗኗሩ ከስሩ ይነቃ ዘንድ የተፈቀደ ቀን ነገር ሁሉ በእራሱ አካሄድ ይስተካከል አለ። በእርግጥ መፅሐፍ መፃፍ ወይ ታሪክ በአንድ እና ብዙ አማራጭዎች የመተው ትልቅ ነገር እና ቀዉስ ክፍተት እምናስመለክትበት ቋሚ ስህተትአችን ነው። ግን እርሱን ማከም አንዱ መንገድ ብቻ ነው። በሽቃቤነጥብ፣ ጣሪአ ለመድረስ ወለሉን በመነካካት፣ መድከም ነው። ዋናው፣ ተገቢ ሂወትን በአንድ ሁለት ሦስት ምርጥ መንገድ መቁጠሩ አይደለም። ሂወት ማሻሻያ መንገዱ ተቆጥሮ አያልቅም እና። ልኩ አይታወቅም።” ሩት የታዘዘው ሲቀርብ አተኩራ ማድመጡን ተያይዛ ነበር። በሃሳቡ መማረኳን አይቶ ናሆም ቀጠለ። “ብቻ ግን ሂወት ከቅናሼነጥብ በርቶ – ጣሪአው ፈንጥቆ ቤቱ ቢበራ – እና ያኗኗር አንድ ሁለት ሦስት ገፅታ ቢመነዘር ይሻል አለ። አንዴ የበራ አኗኗር ሲመነዘር እልፍ ስንጥርዎች አንስተሽ ብትፈትሽው፣ አኩሪ መልስ አለው። ለምሳሌ እንደ አልሽው መፅሐፍዎች እና ዘጋቢ ፊልምዎች ስለስኬትአማ ሰውዎችአችን አለን ወይ?፣ ስትይ መልሱ አዉ ይሆን አለ። በእራስሰር ሂወት መስመር ስለ ያዘ ምንም ብትጠይቂ አጥጋቢ ነገር ትትመለከች አለሽ።” በሃሳቡ ወደ አንድ ነጥብ ገብቶ ለመቋጨት ምናቡን በረበረ። በመጨረሻ የ ተነሳውን መጠቅለያ ከብዙ አማራጭዎች መሀል ልኮት (ሪፈረንስ) ሆኖ እንዲአግዘው ጠራ። “አው። ለ ምሳሌ ድረገፁትዊተርን ተመልከች። በቃ የ ትዊተር አሰራር የሂወት ምርጡ መንገድ ነው። ድንቅ ፈጠራ ብዬ ከእልፍ ፈጠራዎች እማስበልጠው ጉዳይ ነው ትዊተር።

“ትዊተር የ ፌስቡክ ጓደኛው በምን ከ ፌስቡክ በልጦ?” ሩት መጥዋን አማስላ ናሆምንም ጋብዛ ቀመሰችለት። ደግ የወተት እና ቡና ስብጥር ከመጠነኛ ስኳር ጣዕም ተዋህደውበት ነበር። ደግማ ፉት አለችለት። ናሆምም የሎሚ መደዱን ነገር ስለ እሚረዱ አስተናጋጅዎች ሁለት ሙሉ ሎሚዎች የአቀርቡለት ስለነበር ጨምቆአቸው በፍራፍሬ ጭማቂዎቹ አዋህዶ አጣጣመ። ወደ ፀሐይግባቱ መቀራረብ ሲሆን በራሷ ወደ ጀምበሯ ትእይንት እንድትመጣ በሆንብሎንታ ችላ ብሎት ወደ ነጥቡ ተመለሰ።
“አዎን! መነሻ እና መቋጫ ሃሳቡ ግን እንደ ፌስቡክ ደካማ አይደለም። በርግጥ ፌስቡክ ሰውን በአሃዝአዊ ዓለም ማገናኘት ስለተሳካለት ድንቅ ነው። ግን የ ትዊተር ምርጥነት ሰውን ከሰው ሳይሆን ሃሳብን ከመሰል ሃሳብ መንደር ማገናኘት ነው መርኁ። በ ፌስቡክ ያንተ ግንኙነት ድር ክፍት ይሆንልህ አለ ለመረጃ። በ ትዊተር ዓለም ሁሉ ክፍት ነው፣ በፈለግሽው ሃሳብ ብቻ አስሽ። ማለትም ሃሳብን ስታስሺ በዙሪአው ያሉ ሁሉ ይመጣልሽ አለ። ምትሃተኛው የ ሃሽታግ ፈጠራ የቅርብ ዘመን ምርጡ ፈጠራ ነው።” ሩት በሃሳቡ ተስማምታ ወደ ትዊተር ተጠቃሚነት ለመመለስ አቀደች። ገና የ ፌስቡክ ገፅ ሙከራላይ ነበረች። ደስታ ሊሰጥ እሚችል ግን አልነበረም። ብዙ አዲስ ነገር የለበትም። ምርጥ እሚሉትን ምስል በመለጠፍ መንቆለጳጰስ የሂወት አካል መሆኑ በ ልክኖታ (ሪኮግኒሽን) ስለ እማናድግ የተንሰራፋ ቢሆንም፣ ወደ መጨነቅ የፈዘነበለ እና ትርጓሜው የደበዘዘ ሆኖ እንዲገኘኝ አለቅጥ እንደ በዛ አስተዋለ ች። በ ትዊተር እሚሻል ዓለም ካለ ለመሞከሩ አቅዳ ከወተቷ ተጎንጭታ ፈሳሹን ወደ ሆድ በስሱ ጣዕሙን ደግሞ ወደ ጉሮሮ ሳበች።
“ከሂወት እሚገናኘው እንዴት ነው ታዲየቀ?” ወደ ነጥቡ ተመልሳ ተመለከተችው እና ፈገግ ብላ የግብዣው ስፍራ ደስታ ሲቸር አስተዋለች እና የበለጠ ፈገግ ተሰኘ ች። “እንደ አልኩሽ በ ትዊተር የአሻሽን ፈልጊ። በእዛ ጉዳይ ዙሪአ ሃሽታግ ቀድሞት የተባለ ሁሉ፣ ከዓለም ሁሉ፣ ወደ ገፅማያ ስለ እሚወረወርልሽ ድንቅ የመረጃ ድባብ አታጭም። እንደ እዛ፤ አኗኗርም፣ እምትፈልጊውን ሁሉ ማግኘት በእምትችይበት ቀመር ሊሰራ ይገባው አለ። ነጥቡ በእዛ ነው እሚመሰረተው። አንድ የስነምግብ (ኒውትሪሽን) መረጃ ወይም ዕዉቀት ሰብስቦ አንድአች ነገር መማር እሚሻ ታዳጊ ዛሬ ተነስቶ ከመሀልአችን ስለ ስነአመጋገቡ ልወቅ ቢል ተምሮ ጊቢ እስኪገባ ምን ሊአቅ ይችል አለ? ምንም! ስነምግብን በተመለከተ ግን አንድ ማንኛውም ሰው ሲጠይቅ በሙያው የተፃፉ፣ የተተረኩ፣ ልብወለድ እና ኢልብወለድዎች፣ ታሪክ እና ዳግ-ጥናትዎች በቀላሉ ሊቀርብለት እሚአስችል የገሃድ አኗኗር ትዊተር ሊኖር ይገባ አለ። በህዝብ ቤተመጽሐፍዎች ከማዕከልአዊ ቤተመፅሐፍዎች እና ቤተመዛግብትዎች ለከተማዎች ሁሉ መረጃው መላክ አለበት። ልጁ ምንም አጥቶ ከተስፋ መቁረጥ መድረሱ ይልቅ ቢአንስ አዲስአበባ እከሌ ቤተመጽሐፍ ይህ ይህ በዛ ዙሪአ አለ ሊለው እሚችል መረጃ እንኳ ማግኘት አለበት። ወደ አዲስ አበባ ወይም የተባለበት አቅራቢአ ከተማ ለመሄድ ወይም ሰው ለማስላክ ይጣጣር ያልም አለ። ብቻ ህልሙ አልሞተም። የት እንደ እሚሄድ ያቀው አለ። ማደግን ብቻ ይጠብቅ አለ።” ሩት በሃሳቡ ድንቅ ብልሃት እና ንፅረት (ኢንሳይት) ተደመመች። ግን መልሶ ፍቱን ቢሆንም ችግር ተገለጠላት። ማንም አይተገብረውም። መፍተሔውን እየአሰላሰለች፤ “ግን ይህ በተሞክሮ የለም መሰለኝ እኮ።” ብላ አቻ ሃሳብ ጋበዘ ች። “አዎን። ትዊተራይዝድ የተደረገ ያኗኗር ስልት የለም። አንድ መረጃ ቢጎረጎር የለም። ሃገሪቷ ብትታሰስ ተዘቅዝቃ ብትበጠር የአንድ ወር ቀደመ ዜና እንኳ ይጠፋሽ አለ። ህዝብአዊ የፍትህ ዉሳኔ እንኳ ለማግኘት መከራው አይጣል ነው። ክፍቱ ነገር እንግዲህ።” ናሆም ቀጥሎ አብራራ። እንዲጠጣ እየጋበዘች “እና መፍትሔው ስ?” ከፈገግታ ጋር በአጭሩ ጥያቄ ወረወረ ች። ፈገግ ብላ ዘና በማለት አየችው። “እና በብሔርአዊ ማህደር ነገርዎች አናስቀምጥም ችግሩ ከ ሆነ፣ መፍትሔው ጉዞዎችአችን ሁሉ በይፋ እና ተደራሽ ጥረት ቢቀመጡ እና በብዙ አቀራረብ አማራጭዎች ቢቀርቡ ከዜሮ መጀመር ይቀነስ አለ ነው። ወጣት ተነስቶ በ ወለል ማነፅ እሽክርክሪት አይጨነቅም። ታሪክ ተሰድሮ ቀርቦ ስለ አለ ባለ የሃገርአዊ ታሪክ እና መረጃ ቋት መመርመር ከፍተኛ የቅን ዝማኔ አጀማመር እምርታ ይመጣ ነበር።” ይህን ሲናገር አሁንም ሩት አድምጣ ነጥቡን አብላላች እና ብልህ እንደ ሆነ አስተዋለች። ናሆም መመሰጥዋን አስተውሎ መቋጫውን ሰጠ። “ግን ያ ከፊሉ ነው። ቀሪው ታዲአ አኗኗሩን ባህል ማድረግ ነው። የልኮት ባህል በመደበኛ አኗኗር ገልብጦ ማምጣት ይገባ አለ። በሊቅአዊ መንደር ተወስኖ የእሚገኘ ው ባህል ወደ መደበኛ አኗኗር ዓለም መምጣት አለበት። በመደበኛ መገናኛብዙሃዎችአችንን እና ጉንጭአልፋ ወሬዎች ሁሉ እከሌ እንዲህ ብሎ ነበር ብሎ ነገሩን ያወቀ የመረመረ ሥም መጥቀስ መልመድ ተገቢ ነው። ባህሉ ይሄኔ በመደበኛነት ይዳብር አለ። መረጃ ሲሰማ ስለ እዚህ ለወደፊት ልኮት ልንጠቀምበት እንዲቀመጥ ማድረጉ የዝማኔ መሰረት ሆኖ ይታየን አለ ማለት ነው። ስለ እዚህ እንደ አንድ አብነት ብቻ፣ ለ ምሳሌ ኃይሌ አንድ ነገር ሲናገር የታሪክ ማክበር እና መተንተን ሲከውን ነበር እና የታሪክ ምሁሩ የታሪክ ተማሪውም ያላትን አይረሳትም። በመዘገብ ለጋራ ቋት ያስቀምጣት አለ። ስራው ስለ እሚሆን። በሰው ተጠቅሳ፣ ስትደጋገም ወደ እዛች የአንድ ቀን የኃይሌ ጨዋታ ብዙዎች ልኮት አጊንተው ‘የት አለ እንዲህ ድንቅ አስተያየት የተሰጠበት ወሬ? ዝርዝሩን ላድምጥ!’ ይላሉ። የእሩጫ ዘዴአማአዊነት ትንተናው እንደ አንቺ የማረከውም፣ የተንቀሳቃሽ ምስል ማህደር አይጠፋም፤ በቀጥታ ወደ እዛ መራመድ ይችል አለ። በብሔርአዊ ወይም ተቋምአዊ ቋት ደግሞ ተመሳሳይ አያያዝ ስላለ በእዛ ትንታኔ ከተመሰጡ ይህ ተመሳሳይ ነገርን ይፈትሹ እሚል የ ትዊተርአዊ አሰራሩ ይቀጥል እና አንቺን መመለስ እንዳትችይ በመመራመር እንድትበረቺ ይጠምድሽ አለ። ማምለጫ የለም። ኃይሌ እና ትንታኔው ለአንድ ቀን ተራ ወሬ ስርጭትነት ሳይሆን ለሃገር እና ትዉልድ ስለተመዘገቡ መቼም እሚገኝ አገልግሎት ይሰጡ አለ ማለት ነው! እንግዲህ ከዜሮ መጀመር ለእኔ እሚወድቅልን እሚመስለኝ በእዚህ መረጃ እና ታሪክ መሰደር፣ ተደራሽ ማድረግ፣ ባህሉን መገንባት እና ማከማቸት ሂደት ነው። ትዉልዱ ግን ይህን ስለ አጣ በግል ከመፍጨርጨር እና ከዜሮ መቧጠጥ በዘለለ የሥንት ሺህ ዘመን ታሪክ ባለቤትነት ሁሉን ከአዲስ ከመቧጠጥ አላስቀረውም። የዳማከሴ ጥበብ እንኳ በስፋት በእዚህ ትዉልድ የለም። ዕዉቀት ወደ መደበኛ ፈኗኗር ተሰድሮ አልተባም። ችግሩ እንግባ ስንል እሚጨበጥ አለ መኖሩ ነው!”
ሩት በአደመጠችው ተደምማ ፍቱን ጎዳና ስትመለከት አስተዋለች። መንግስት በተግባሩ እና የባህል ለውጥ ስብከት በማድረጉ እንዲአምን እና በመጭው ትዉልድ አእምሮአዊ ጉልበት መገንባት እንዲአምን በልቧ ፀለየች። ከዛም በላይ ለመታገል እና ሃገር እሚወጠንበት መንገድ እስከሆነ ለወራሪ ምከታ ደም እንደ እሚሰጡት ትዉልድዎች መታገል እንደ አለብአቸው አሰበች። ወራሪ ዘምኖ በድሮው ሠራዊት መንዳት መምጣቱ ከቆመ ዘመን የለውም።

<p class="has-text-align-justify" value="<amp-fit-text layout="fixed-height" min-font-size="6" max-font-size="72" height="80">ምሳሌ አአኅ. ሊከወን እሚችል ማህደርአዊ ቋት ላይ ገብተህ ትመለከት እና ትደመም አለህ ማለት ነው። ግን እንደ አልክው ተፃፈ ወይም አልተፃፈም ብቻ ከአልን ቢፃፍ ተወርዉሮ ወይ ቅጂው ሲአበቃ ወይ ተሽጦ ሲአልቅ አበቃለት ማለት ነው። ግን በአኗኗር የተሰገሰገ ፍልስፍና ሲሆን ሂወት ትዊተር ሆነች ማለት ነው። ድንገት ስለ ቦልት ሲነሳ ኃይሌ እንደ ሳቀበት ሲነገር ትሰማ አለህ። መች አለ ያንን ትል አለህ። እዛ ቦታ መፅሐፍ ላይ ተደርጎ አለ ወይም እንዲህ ቋት ላይ አታጣውም ይልህ ዘንድ አንድ ነገር አታጣም። ባህል ስለ ተደረገ። ሄደህ መፅሐፍ ይሁን ምስል ትመረምረው አለህ። ከ አንድ ቀን ጨዋታው የዘመን ወተት ማለብ እና መጠጣት በብልሃት ተፈቀደ ማለት ነው። ሃገር በቀደመ ጥንቅር ምርጥ ምርጡን መሰብሰብ ትጀምርል አለች። ማደግ መሰረቱ እና አካሄዱም ያ ነበር።
“እና ይሄ የአኗኗር መንገድ ስለሆነ አይጠፋም ማለት ነው። ይደንቅ አለ። አንድኛ ማህደር የ ማዘጋጀት እና ተደራሽ የማድረግ፣ ሁለትኛ ባህል አድርጎ ልኮት ያኗኗር ባህል ማድረግ። ከእዛ ሂወት ይቀልል ነበር። ምን ያክል ቀላል ግን የእማይታይ መንገድ! እዉነትም ለማደግ ሳይሆን ለአጭበርብሮ መቆየት እሚአንገላታን መሪ እሚፈራረቅበት ሆኖ የቀኃሥ. ዉጥን ተሰልቦ አለ!” ሩት የቀኃሥ. ዘመን ያደረገው ዘመንአዊ ጥረት ከሌላ ተነቃፊ ገፅታው ለይቶ በማየት ምርጥ የኢትየጵያ መሰረት ይከተል ነበር ባይ ነች።
“ምን ኢህአደግ. ሲወድቅ በይፋ የተዘመረው ‘ሃያሰባት ዓመት ጅብዎች ገዝተውን አለ፣ በሠላሳ ቀንዎች ዉስጥ ዐብይ ነፃ አድርጎን አለ!’ እየተባለ አልነበር።”
“እ! ጅብ ሲገዛው የተቀመጠ እና በሠላሳ ቀን ነፃ እሚወጣ ምን አይነት ትዉልድ ቢሆን ነው?”
“ያን ማለቴ አይደለም። ያው አሳድግህ አለሁ ብሎ ሰዓት ቆጣሪ ፈንጅ በመትከል እሚሰነብት እንጂ መሰረት እሚጥል እውነትም የለም ነበር ልልሽ ነው። የቀኃሥ. መሠረት ተናፋቂ እስኪሆን አፈግፍገን አለ።”
“ግልጥ! ህዋሓትዎች. ሲገቡ የደርግ ፋይልዎች ማቃጠል የመነሻ ስራአቸው ነበር! ትዊተርአዊ አያያዝ ቢጀመር ግን ለዉጡ ድንቅ ነው። ከዜሮ መጀመር ይቀር አላ። የሰማንው ዉይይት ቢአነሳሳሽም፣ ለዘልአለም ነው ያሸለበው። ማንም ደግሞ አያገኘውምም። ግን እንደ ነፋስ ነፍሶ እንዳይቀር ከጨዋታ ጀርባ መረጃ እሚሰድር የሃገር ጀግና ይሻ አለ። ይህን መሰል የብልፅግና መሰረት ሳይጥሉልን በትንሽ አመትዎች በግ አደልበው በነብስወከፍ በእየ ወሩ እንደ እሚአከፋፍሉ ያክል በተሰለቸ የዋሻ ዘመን ንጉሥ አሰራር 'ሃብታም ልናረግህ ነው በአስር ሃያ ዓመትዎች ታግሰህ ጠብቅ' በእሚል ይጫወቱብን አለ። ትላንት የተነገረ ይፋ ወሬ በመረጃነት ዛሬ የለም። ታዲአ መበልፀግ በአለፈ አኗኗር ጥበብ ላይ ከአልተካበ ከየት ይምጣ?…ማን መቶ ዓመትዎች እንደ ወረቀት ዘርግቶ በምናብ አስልቶት?” ዝምታ ሰፈን ብሎ በማውጠንጠን ተጠመዱ። ናሆም ስለገጠመው ክፉ ነገር አስታውሶ በሃሳብ ነጎደ። በፊቱ የተሳለ ትዝታ ብጤ ጉልህ ሲሆን ወደ አጠገቧ እንዲመለስ አሳስባ ሣቅ ተባባሉ፨
“አንድ ጊዜ ፋሲካይት እንደ ገባን ግዕዝን ከመንፈስአዊ ጥናት አብልጬ እንደ ሙሉ እና ወጥ ዓለምአዊ ቋንቋነት ጨምሬ ማጥናት ፈለግሁ። ማጥኛ አለ ሲባል ሰምቼ ባስስ ባስስ ምንም ነገር በፋሲካይት አጣሁ። ስለ ግዕዝ በመደበኛ ቋንቋ ማጥናት አጋጣሚዎች ማንም አያወራም። ሃሽታግ-ግዕዝ-ጥናት እሚሰኝ በይነመረብ ሃሰሳ ያኔ የለም። ትዊተርንም አላቅም ነበር። ግን ቆየት ያለ አባይ እሚሰኝ ጋዜጣ፣ ትምህርትቤት እንደ አጋጣሚ ሻይቤት እሚአስቀምጠው የጋዜጣ ክምችት በዝቶበት ይሸጥ ተብሎ፣ ከዓሊ ጋር እዛ ለንባብ ስለ እሚአስዉሉን፣ በመሸከሙ ስናግዝአቸው፣ ከብዙ ዓመት በኋላ ከግዕዝ ዘመንአዊ አስተምህሮት ጋር ድንገት ተገጣጠምኩ። በጋዜጣው ጀርባ አንድ የአአኅ. ታዋቂ ግዕዝ መምህር ሳምንትአዊ የዘመንአዊ ግዕዝ መግቢአ ማስተማሪአ ዐምድ ነበረአቸው። ፖሣቁ.ን ይዤ ምክር ከተቻለም መጽሐፍ ብጤ እርዳታ ጠይቄ ‘ልጅ ተማሪ ነኝ እርዳኝ!’ በማለት አክዬ አንፋሽአማአዊ የመሰለኝን ጦማር ላክሁ። ምንም መልስ አልመጣም። በመጠበቅ እስክሰለች ተስፋ ብይዘም መልሱ ዝምታ ነበር። እኔ ስለሆንኩ እንጂ የተሰማኝን ብዙዎች ቢገጥምአቸው እንደ እማይታገሱት አስተዋልኩ። የጓጓሽለት ፍሬጉዳይ ወይ በአካባቢሽ ወይም በአለበት መንደርም ሰሚ የለውም። በሰፋ ጥረት ማሰስ ልምድም ዉጤትም ደግሞ ከባድ ነው። በተለመደ ድሃ አኗኗር ከአልተሸበብሽ፣ መኖሩ አታካች ነው።”
ናሆም በአጋራት ትዉስታ ጎን በተፈጠረው አሁን የተከወነ ጉድለት ያክል በሃዘን ሲዋጥ ሩት አስተዋለ ች። እንዲህ ከ ተሰማው በመናገሩ ከቀለለው ብላ ሩት ለስሜቱ መታከምም ደስ አላት። መልስ በከለከለው ላይ ጥቂት አርስዋም ተናደደች። ከምናቧ ጋር ተወያየች። የልጅ መንፈስን መደገፍ ቢቻል ደግ ነው። የልጅ ፍላጎትን ማቀጣጠል አለ ክፍያ ለመደገፍ በእርካታ እና ቅድመንቃት (ፕሮአክቲቭ) ትትረተደ እምንፈልገው ጉዳይ መሆን አለበት።
ምንአልባት ኑሮ በሁለንተና ሲዘምን አንዱ እሚስተካከል ነገር ከሆነ ብላ በአንድ ቅጠል ህክምና ከመጨነቅ በሙሉ ዛፉ ማከም መጠመዱ እንደ እሚሻል ስለ ተቀበለች ዘለለችው። ናሆም በሃሳቡ ተማርካ የስሜት አቻ እንደ ሆነችለት አስተዋለ። አስቦ ሲፈፀም፣ በማስተዋል ከዛ ከአልተመረቁበት ብዙ ቅሬታ ጫሪ መልስየለሽ የዝማኔ ጉድለት ጥያቄዎችአችን በተለይ መንፈስ ሊሰረስሩ ይችል አለ ብሎ ለእራሱ እየነገረ ተመለከታት። ከስሜት እንድትወጣ መንገድ ለመፈለግ ምናቡ ዉስጥ ጣረ። ገና ስሜት አላብላላችም። ተዋት። 'ለነገሩ ብዙ ኢትዮጵያአዊዎች በዝማኔ ማጣት እና መንገዱ ግን ቀላል ቢሆንም ባለመስተካከሉ አንጀትአቸው በእየቀኑ አርሮ እንደ እሚአድሩ ጥርጥር የለውም። ችግሩ ብቻአቸውን የሆኑ ይመስልአቸው አለ። ሲቀጥል ደግሞ ወደ አንድ ድርጊትአዊ መስመር ቀይረው አይታገሉበትም። አንጀትአቸውን አቁስለው ማለፉ በስዉር ወይም ግልፅ ሁኔታ፣ በቂ መስሎ ይታይአቸው አለ።' ይህ በእኛ ትዉልድ ከተቀየረ በእሚል ናሆም እንደ ለመደው ተስፋ አድርጎ ሃሳቡን በሙሉኛ በመተው ሳይሆን በመመረቅ ስሌት ብቻ ወደ ቀጣይ የሂወቱ ዑደት ተመለሰ። ፈገግ ብሎ ተመለከታት፨
ሩት፣ የፀሐይግባት በደግ መጠን ስትደምቅ ወዲአው ለማስተዋል ተገደደች። ለናሆም እንዲመለከታት በአድናቆት ወደ ጀምበሯ ስትጋብዝ እና ስትመለከት ቆየች። በአስደማሚው ፀሐይግባት ነብሷ ምርኮነት ወደቆ በፈዘዙ ጨረርዎች አዲስ መጨዋወት ሆነ። በመደበኛ እና ምናብአዊ ጨዋታዎች ሳቅ እና ቁምነገር አዋዝተው ፀሐይግባቷ ነብስአቸውን ስትጎበኝአቸው ቆይታ በተለመደ ቅንብርአዊ መጥለቋ የበለጠ እየተገረመች ተሰናበተችአቸው፨
ሂሳቡን ከፍለው ወደ ቤት በተለመደ ተሽከርካሪ ቀጠራ ተጓዙ። የናሆም ሃሳብ ለፀሐይግቷ ሹፍተራ እንደ ነበር በመንገዱ ሳሉ ገባት። የቦታ ምርጫውን ወድዳ ተፈጥሮ በጀምበር እይቷ ነብስዋን ‘በርቺ! በርቺ!’ ማለትዋን በእራሷ ትርጉም እየፈታች አንፋሽአማአዊ ድባብ ውስጥ ሰመጠች። በ ትዊተር፣ ከዜሮ መታገል እና ፀሐይግባት መስተጋብር ትልቅ የቆሻሻ አኗኗር መፀየፍ ሲከብባት አስተዋለች፨
በ እግር ወርደው ጥቂት ተጉዘው፤ ሩት ቤቷ ደረሰች። አመስግና በሃሳቡ አንድ የሃገር ጥቅም እንዲመጣ ኃላፊነት የእነ እርሱ እንደሆነ ገልፃለት ወደ ምናብአዊ ፍፁምነት አደና መማረክዋን ገለፀች። ከሃሳቡ እንድትመረቅ ለመንገር አሁንም አልደፈረም። ከፍተኛ መለጠጥ ነነሷ ላይ አርፎ ነበር። የታወቃት ትልቅ ምስጢር ነበር። ተግባር እስኪተረጉመው ላገነዛዘብ ትልቅ መብራት ነበር። ተብላሎት እስክትከውንበት እና መነሳሳቱ እስኪበቃት ለጊዜው ትሙቀው በእሚል መመረቅን አሁን አልመከራትም። እንደ ተደመመች አመስግና ጉንጩን በመሳም ተለይታው ገባች፨
ናሆም ተለይቷት ቤት ሲደርስ፣ የመስ ጭቃ በላቀ ዉህደት ልሞ እና ላቁጦ በብርሃን ጨረርዎች ኮረብታ ከውኖ አስተዋለው። በመደመም ዞርዞር እየአለ፣ በጣት ለናሙናነት በመጠንቆል፣ መርምሮ አድናቆቱን ቸረ። “ገና ይላቁጥ አለ!” መስ ከጀርባው ደርሶ መደመሙን ቀድሞ ተመልክቶበት ስለ አሰራሩ ጨምሮ አስረዳው። በማለዳ ድንጋይዎችን በግድግዳነት ከወለሉ በጥቂት አዝልገው ሊደረድሩ እና የጭቃውን ለከፍተኛ መጠን መዘጋጀት በጥቂት ጭማሮ መጠበቅ ለቀንዎች ሊተዉት ተነጋግረው ወደ ቤት ገቡ። እየተጫወቱ እና በዉኀ መሞላት የቀጠነ ቅራሬ እየኮመኮሙ ቀሪ ምሽቱን አሳለፉ። ‘የመስ መምጣት ሁሉን ፈር እየአስያዘ ኑሮአችን እንደ ዘበት ሊቀየር ነው!’ ምሽቱ ሥፍራው ተገባደደ፨
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ምሳሌ አአኅ. ሊከወን እሚችል ማህደርአዊ ቋት ላይ ገብተህ ትመለከት እና ትደመም አለህ ማለት ነው። ግን እንደ አልክው ተፃፈ ወይም አልተፃፈም ብቻ ከአልን ቢፃፍ ተወርዉሮ ወይ ቅጂው ሲአበቃ ወይ ተሽጦ ሲአልቅ አበቃለት ማለት ነው። ግን በአኗኗር የተሰገሰገ ፍልስፍና ሲሆን ሂወት ትዊተር ሆነች ማለት ነው። ድንገት ስለ ቦልት ሲነሳ ኃይሌ እንደ ሳቀበት ሲነገር ትሰማ አለህ። መች አለ ያንን ትል አለህ። እዛ ቦታ መፅሐፍ ላይ ተደርጎ አለ ወይም እንዲህ ቋት ላይ አታጣውም ይልህ ዘንድ አንድ ነገር አታጣም። ባህል ስለ ተደረገ። ሄደህ መፅሐፍ ይሁን ምስል ትመረምረው አለህ። ከ አንድ ቀን ጨዋታው የዘመን ወተት ማለብ እና መጠጣት በብልሃት ተፈቀደ ማለት ነው። ሃገር በቀደመ ጥንቅር ምርጥ ምርጡን መሰብሰብ ትጀምርል አለች። ማደግ መሰረቱ እና አካሄዱም ያ ነበር።
“እና ይሄ የአኗኗር መንገድ ስለሆነ አይጠፋም ማለት ነው። ይደንቅ አለ። አንድኛ ማህደር የ ማዘጋጀት እና ተደራሽ የማድረግ፣ ሁለትኛ ባህል አድርጎ ልኮት ያኗኗር ባህል ማድረግ። ከእዛ ሂወት ይቀልል ነበር። ምን ያክል ቀላል ግን የእማይታይ መንገድ! እዉነትም ለማደግ ሳይሆን ለአጭበርብሮ መቆየት እሚአንገላታን መሪ እሚፈራረቅበት ሆኖ የቀኃሥ. ዉጥን ተሰልቦ አለ!” ሩት የቀኃሥ. ዘመን ያደረገው ዘመንአዊ ጥረት ከሌላ ተነቃፊ ገፅታው ለይቶ በማየት ምርጥ የኢትየጵያ መሰረት ይከተል ነበር ባይ ነች።
“ምን ኢህአደግ. ሲወድቅ በይፋ የተዘመረው ‘ሃያሰባት ዓመት ጅብዎች ገዝተውን አለ፣ በሠላሳ ቀንዎች ዉስጥ ዐብይ ነፃ አድርጎን አለ!’ እየተባለ አልነበር።”
“እ! ጅብ ሲገዛው የተቀመጠ እና በሠላሳ ቀን ነፃ እሚወጣ ምን አይነት ትዉልድ ቢሆን ነው?”
“ያን ማለቴ አይደለም። ያው አሳድግህ አለሁ ብሎ ሰዓት ቆጣሪ ፈንጅ በመትከል እሚሰነብት እንጂ መሰረት እሚጥል እውነትም የለም ነበር ልልሽ ነው። የቀኃሥ. መሠረት ተናፋቂ እስኪሆን አፈግፍገን አለ።”
“ግልጥ! ህዋሓትዎች. ሲገቡ የደርግ ፋይልዎች ማቃጠል የመነሻ ስራአቸው ነበር! ትዊተርአዊ አያያዝ ቢጀመር ግን ለዉጡ ድንቅ ነው። ከዜሮ መጀመር ይቀር አላ። የሰማንው ዉይይት ቢአነሳሳሽም፣ ለዘልአለም ነው ያሸለበው። ማንም ደግሞ አያገኘውምም። ግን እንደ ነፋስ ነፍሶ እንዳይቀር ከጨዋታ ጀርባ መረጃ እሚሰድር የሃገር ጀግና ይሻ አለ። ይህን መሰል የብልፅግና መሰረት ሳይጥሉልን በትንሽ አመትዎች በግ አደልበው በነብስወከፍ በእየ ወሩ እንደ እሚአከፋፍሉ ያክል በተሰለቸ የዋሻ ዘመን ንጉሥ አሰራር ‘ሃብታም ልናረግህ ነው በአስር ሃያ ዓመትዎች ታግሰህ ጠብቅ’ በእሚል ይጫወቱብን አለ። ትላንት የተነገረ ይፋ ወሬ በመረጃነት ዛሬ የለም። ታዲአ መበልፀግ በአለፈ አኗኗር ጥበብ ላይ ከአልተካበ ከየት ይምጣ?…ማን መቶ ዓመትዎች እንደ ወረቀት ዘርግቶ በምናብ አስልቶት?” ዝምታ ሰፈን ብሎ በማውጠንጠን ተጠመዱ። ናሆም ስለገጠመው ክፉ ነገር አስታውሶ በሃሳብ ነጎደ። በፊቱ የተሳለ ትዝታ ብጤ ጉልህ ሲሆን ወደ አጠገቧ እንዲመለስ አሳስባ ሣቅ ተባባሉ፨
“አንድ ጊዜ ፋሲካይት እንደ ገባን ግዕዝን ከመንፈስአዊ ጥናት አብልጬ እንደ ሙሉ እና ወጥ ዓለምአዊ ቋንቋነት ጨምሬ ማጥናት ፈለግሁ። ማጥኛ አለ ሲባል ሰምቼ ባስስ ባስስ ምንም ነገር በፋሲካይት አጣሁ። ስለ ግዕዝ በመደበኛ ቋንቋ ማጥናት አጋጣሚዎች ማንም አያወራም። ሃሽታግ-ግዕዝ-ጥናት እሚሰኝ በይነመረብ ሃሰሳ ያኔ የለም። ትዊተርንም አላቅም ነበር። ግን ቆየት ያለ አባይ እሚሰኝ ጋዜጣ፣ ትምህርትቤት እንደ አጋጣሚ ሻይቤት እሚአስቀምጠው የጋዜጣ ክምችት በዝቶበት ይሸጥ ተብሎ፣ ከዓሊ ጋር እዛ ለንባብ ስለ እሚአስዉሉን፣ በመሸከሙ ስናግዝአቸው፣ ከብዙ ዓመት በኋላ ከግዕዝ ዘመንአዊ አስተምህሮት ጋር ድንገት ተገጣጠምኩ። በጋዜጣው ጀርባ አንድ የአአኅ. ታዋቂ ግዕዝ መምህር ሳምንትአዊ የዘመንአዊ ግዕዝ መግቢአ ማስተማሪአ ዐምድ ነበረአቸው። ፖሣቁ.ን ይዤ ምክር ከተቻለም መጽሐፍ ብጤ እርዳታ ጠይቄ ‘ልጅ ተማሪ ነኝ እርዳኝ!’ በማለት አክዬ አንፋሽአማአዊ የመሰለኝን ጦማር ላክሁ። ምንም መልስ አልመጣም። በመጠበቅ እስክሰለች ተስፋ ብይዘም መልሱ ዝምታ ነበር። እኔ ስለሆንኩ እንጂ የተሰማኝን ብዙዎች ቢገጥምአቸው እንደ እማይታገሱት አስተዋልኩ። የጓጓሽለት ፍሬጉዳይ ወይ በአካባቢሽ ወይም በአለበት መንደርም ሰሚ የለውም። በሰፋ ጥረት ማሰስ ልምድም ዉጤትም ደግሞ ከባድ ነው። በተለመደ ድሃ አኗኗር ከአልተሸበብሽ፣ መኖሩ አታካች ነው።”
ናሆም በአጋራት ትዉስታ ጎን በተፈጠረው አሁን የተከወነ ጉድለት ያክል በሃዘን ሲዋጥ ሩት አስተዋለ ች። እንዲህ ከ ተሰማው በመናገሩ ከቀለለው ብላ ሩት ለስሜቱ መታከምም ደስ አላት። መልስ በከለከለው ላይ ጥቂት አርስዋም ተናደደች። ከምናቧ ጋር ተወያየች። የልጅ መንፈስን መደገፍ ቢቻል ደግ ነው። የልጅ ፍላጎትን ማቀጣጠል አለ ክፍያ ለመደገፍ በእርካታ እና ቅድመንቃት (ፕሮአክቲቭ) ትትረተደ እምንፈልገው ጉዳይ መሆን አለበት።
ምንአልባት ኑሮ በሁለንተና ሲዘምን አንዱ እሚስተካከል ነገር ከሆነ ብላ በአንድ ቅጠል ህክምና ከመጨነቅ በሙሉ ዛፉ ማከም መጠመዱ እንደ እሚሻል ስለ ተቀበለች ዘለለችው። ናሆም በሃሳቡ ተማርካ የስሜት አቻ እንደ ሆነችለት አስተዋለ። አስቦ ሲፈፀም፣ በማስተዋል ከዛ ከአልተመረቁበት ብዙ ቅሬታ ጫሪ መልስየለሽ የዝማኔ ጉድለት ጥያቄዎችአችን በተለይ መንፈስ ሊሰረስሩ ይችል አለ ብሎ ለእራሱ እየነገረ ተመለከታት። ከስሜት እንድትወጣ መንገድ ለመፈለግ ምናቡ ዉስጥ ጣረ። ገና ስሜት አላብላላችም። ተዋት። ‘ለነገሩ ብዙ ኢትዮጵያአዊዎች በዝማኔ ማጣት እና መንገዱ ግን ቀላል ቢሆንም ባለመስተካከሉ አንጀትአቸው በእየቀኑ አርሮ እንደ እሚአድሩ ጥርጥር የለውም። ችግሩ ብቻአቸውን የሆኑ ይመስልአቸው አለ። ሲቀጥል ደግሞ ወደ አንድ ድርጊትአዊ መስመር ቀይረው አይታገሉበትም። አንጀትአቸውን አቁስለው ማለፉ በስዉር ወይም ግልፅ ሁኔታ፣ በቂ መስሎ ይታይአቸው አለ።’ ይህ በእኛ ትዉልድ ከተቀየረ በእሚል ናሆም እንደ ለመደው ተስፋ አድርጎ ሃሳቡን በሙሉኛ በመተው ሳይሆን በመመረቅ ስሌት ብቻ ወደ ቀጣይ የሂወቱ ዑደት ተመለሰ። ፈገግ ብሎ ተመለከታት፨
ሩት፣ የፀሐይግባት በደግ መጠን ስትደምቅ ወዲአው ለማስተዋል ተገደደች። ለናሆም እንዲመለከታት በአድናቆት ወደ ጀምበሯ ስትጋብዝ እና ስትመለከት ቆየች። በአስደማሚው ፀሐይግባት ነብሷ ምርኮነት ወደቆ በፈዘዙ ጨረርዎች አዲስ መጨዋወት ሆነ። በመደበኛ እና ምናብአዊ ጨዋታዎች ሳቅ እና ቁምነገር አዋዝተው ፀሐይግባቷ ነብስአቸውን ስትጎበኝአቸው ቆይታ በተለመደ ቅንብርአዊ መጥለቋ የበለጠ እየተገረመች ተሰናበተችአቸው፨
ሂሳቡን ከፍለው ወደ ቤት በተለመደ ተሽከርካሪ ቀጠራ ተጓዙ። የናሆም ሃሳብ ለፀሐይግቷ ሹፍተራ እንደ ነበር በመንገዱ ሳሉ ገባት። የቦታ ምርጫውን ወድዳ ተፈጥሮ በጀምበር እይቷ ነብስዋን ‘በርቺ! በርቺ!’ ማለትዋን በእራሷ ትርጉም እየፈታች አንፋሽአማአዊ ድባብ ውስጥ ሰመጠች። በ ትዊተር፣ ከዜሮ መታገል እና ፀሐይግባት መስተጋብር ትልቅ የቆሻሻ አኗኗር መፀየፍ ሲከብባት አስተዋለች፨
በ እግር ወርደው ጥቂት ተጉዘው፤ ሩት ቤቷ ደረሰች። አመስግና በሃሳቡ አንድ የሃገር ጥቅም እንዲመጣ ኃላፊነት የእነ እርሱ እንደሆነ ገልፃለት ወደ ምናብአዊ ፍፁምነት አደና መማረክዋን ገለፀች። ከሃሳቡ እንድትመረቅ ለመንገር አሁንም አልደፈረም። ከፍተኛ መለጠጥ ነነሷ ላይ አርፎ ነበር። የታወቃት ትልቅ ምስጢር ነበር። ተግባር እስኪተረጉመው ላገነዛዘብ ትልቅ መብራት ነበር። ተብላሎት እስክትከውንበት እና መነሳሳቱ እስኪበቃት ለጊዜው ትሙቀው በእሚል መመረቅን አሁን አልመከራትም። እንደ ተደመመች አመስግና ጉንጩን በመሳም ተለይታው ገባች፨
ናሆም ተለይቷት ቤት ሲደርስ፣ የመስ ጭቃ በላቀ ዉህደት ልሞ እና ላቁጦ በብርሃን ጨረርዎች ኮረብታ ከውኖ አስተዋለው። በመደመም ዞርዞር እየአለ፣ በጣት ለናሙናነት በመጠንቆል፣ መርምሮ አድናቆቱን ቸረ። “ገና ይላቁጥ አለ!” መስ ከጀርባው ደርሶ መደመሙን ቀድሞ ተመልክቶበት ስለ አሰራሩ ጨምሮ አስረዳው። በማለዳ ድንጋይዎችን በግድግዳነት ከወለሉ በጥቂት አዝልገው ሊደረድሩ እና የጭቃውን ለከፍተኛ መጠን መዘጋጀት በጥቂት ጭማሮ መጠበቅ ለቀንዎች ሊተዉት ተነጋግረው ወደ ቤት ገቡ። እየተጫወቱ እና በዉኀ መሞላት የቀጠነ ቅራሬ እየኮመኮሙ ቀሪ ምሽቱን አሳለፉ። ‘የመስ መምጣት ሁሉን ፈር እየአስያዘ ኑሮአችን እንደ ዘበት ሊቀየር ነው!’ ምሽቱ ሥፍራው ተገባደደ፨

By Binyamhailemeskel

Hey there! If you want to know about me, I just like fun, commonsense wisdom, and human love. Let us live a bright today changing tomorrow into brighter.
Regards,

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s