Categories
My Outlet (የግል ኬላ)

ምእራፍ-፫

መስፍን ጎንለጎን ምእራፍ ፫፨

፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
፫ መቀላቀል

ከአዲስአበባ ወደ ፋሲካይት እሚመለሱ አጓጓዥ መኪናዎች በከተማዋ መናኸሪአ ጣቢአ ሲገለገሉ አይታይም። የመኪናዎች መስተንግዶዎች፣ ከደንብ እና ደንብ-አስከባሪ ለመሠወረደ፣ በእየጉራንጉሩ እንደ አይጥ ተደብቀው፣ እሚዘወሩ ናቸው። ‘ቀዉስ ማህበረሰብ፤’ ካሊል ጅብራን “ህግ ደንግጎ በማዉጣቱ ትደሰቱ አላችሁ በመጣሡ ደግሞ አብልጦ ትረካላችሁ፤” ያለው የአልነቃ ማህበረሰብ ቂልነት ማንቂያ ምክረሃሳቡ ትዝ አለው። ዉስጧም ቢሆን ብዙ ዘመንአዊነት እና ህግ የሌለባት መናኸሪያዋ ገብቶ በሩ ጋር ከአንድ ተራ አስከባሪ ጋር ጠጋ ብሎ እየተጨዋወተ መጠበቁን ተያያዘ። የመስ መኪና ምንጊዜም ከመናኸሪአ ገቢዎቹ ናት። ሁሌም በይፋ አገልጋይ ቀጠራ እረግቶ እሚጓጓዝ ነው። ወደ አምስት ሰዓት ተኩል ሲል መቼም እምትደርስ የሌሊት ተመዳቢ መኪና እሚን ሲጎበኝ ሁሌ እሚጠቀምባት ናት፨
እጅግ እረጅምዋ ሰማያዊ መኪና አሁንም እንደ ደረሰች በሽንጧ የሰገሰገችው ሁሉ መዉረድ ጀመረ። መስ ግን ብዙ እቃዎች ስለአጓጓዘ ዘገየ። መኪናው በር ላይ ቆሞ ዓይንዎቹን አማትሮ፣ ተቀባይ ካለ ሲፈልግ፣ ናሆምን ከቅጥር በሩ ወደ እርሱ ሲአዘግም ተመለከተ። ቀለል ያለች ፀሐይ ለብርሃንነት ያክል ብቻ ደብዝዛ ባለችበት እረፋድ፣ ናሆም ፈገግ እያለ በመሞቅ ሆኖ ወደ አጎቱ ቀረበ። ልክ ሲገናኙ በደስታ ተጨማምቀው ተቃቀፉ፨
ከፍተኛ ናፍቆት እንደ ነበረብአቸው እሚአስመለክት መተቃቀፍአቸውን ቀጥሎ ደግሞ በተደጋገሙ የቃል ሰላምታዎች ልዉዉጥ ቆዩ። መጨዋወቱን በሞቀ ልብ ቀጥለው እረዳቱ እያገዛቸው የበዙ እቃዎቹ ሲወርዱ “ይህ ሁሉ ምንድነው? ከዉትድርና ተባረርክ እንዴ?” የበራ ፊቱን የበለጠ እየአበራ ናሆም ጠየቀ። መስ ማራገፉን እየቃኘ ፈገገ። “ምን የመንግስት እንጂ፣ ያገር ሠራዊት የለ። መንግስት ሲቀያየር፣ ተባራሪ-ተቀናሽ መች ይጠፋ አለ!” መልሶ ወደ ናሆም ቀለደ፨
ጥቂት እየተጨዋወቱ የወራጅዎች ጭንቅንቅ ጋብታ ሲአሳይ፣ ባህያ ጫንቃ እሚጎተት ጋሪ አሽከርነት ቀጥረው፣ የወረዱ እቃዎቹ እና የተጓዥ ሻንጣዎቹን አስጫኑ። ለባለጋሪው አግጣጫ ሰጥተውት፣ ከጀርባ ሆነው የተነፋፈቁት ደግሞ በሞቁ ልብዎች እያወጉ ወደ ቤት አቀኑ። የመስ ፈርጣማ እና ትልቅ ሰውነት ግዝፈትን እሚተረጉም ሰውነት እንደ ሆነ፤ ዘንድሮም በላጭ መፈርጠም ሰብስቦ ያስመለክት አለ። ገና የሠላሳንድ ዓመት ወጣት ቢሆንም ሰዉነቱ ግን ከግዝፈቱ የተነሳ ዕድሜው ጋር አይተባበርም፤ እጅግ ትልቅ እና አስፈሪ አስመስሎት አለ። “ከወትሮው ዘንድሮ አስፈሪ ሆነህ አለ። የምን ህግዘብ የምን ወታደር፣ ሰውነት ገንቢ ነህ እንጂ!” ናሆም ያጎቱን መምጣት እየአጣጣመ ሰውነቱን በመቃኘት በፈገግታ ጨዋታውን ቀጠለ። “አካል ማበልጸግ የወታደር አንዱ ግዴታ ነው።” “በማተለቅ?” “በርግጥ በጥንካሬ እና ቅልጥፍና እንጂ በማተለቅ ብቻ አይደለም።” መስ ይህን ብሎ አፍታ ወሰደ እና መልሶ ጨዋታውን በመቀጠል “ግን መከራከር ለመደብህ በቃ!” ብሎ አናት ጸጉሩን አሻሽቶ ካዲስ ፍቅሩን ገለጸለት። “ታውቀኝአለህ፤” ደጋግሞ ትሁት ጸጉሩን እየአሻሸበት አሁንም የናፍቆት ፍቅር ገለጸለት። እንደ ልጁ እሚመለከተው ዉድ ልጅ። “አውቃለሁ ተሟጋቹ። ጠበቃ ሳትሆን አትቀርም!” “አላቅደውም!” “ተው ከ ግብ-ንግድ (አግሮቢዝነስ) ጥብቅና ይሻልህ አለ! እኛ ጋር እንኳ የ ህግ በአለ-ሙያ ከመጣ የአበጡ ደረትዎችአችን ክስም ነው እሚሉት። በህግ ሙያህ ትፈራ ትከበር አለህ!” “ያክብሮት ናፍቆት የለኝም! አመሰግን አለሁ! ግን መብል አሰናጂዎች ፊት ስትቀርቡ ስ? አቢዪዎች አይፈሩ አይከበሩም?” “በቀላል ይተኩ አላ!” “እ!” በመገንዘብ ሆኖ ጨዋታውን ተወት አደረገ። ያባት የአክል እሚቀበለውን አባት እና ጓደኛውን ደግሞ ስለ አገኘ ተደስቶ መመልከቱን ቀጠለ። ዳግም ግዙፍ አካሉ ላይ የተሰቀለውን ያባቱን’ ፊትን ተመለከተው። የተለመደው መልካም ፊት በጠይምነት እሚገለጥ ሆኖ በመጠነኛ የዓይንዎች መሰርጎድ እና መሀከለኛ አፍንጫ ደግ የሀበሻ ወኪል እንደ መሰለ ነበር። ጸጉሩን ጎፈር አድርጎ ጨብረር እንዳይል ከርክሞት እንደነበረ አሁንም ያው ነው። የሀበሻ ራስቅል አነስ ስለእሚል በጸጉር ጎላ ቢደረግ አንድ ደግ አማራጭ ነው በእሚል ስለእሚፈላሰፍ ይህን መከወኑን አያቋርጥም። በሙያው የተነሳ ጸጉሩን ማሳነስ ቢጠበቅበትም በቻለው መጠን ግን አጉልቶ ለማስመልከት እና የአርበኛዎች ሃልዮታ (አቲቲውድ) ስለሆነ በእኛው ፍልስፍና መሰረት እሚገኝ ባህል ስለሆነም መከራከሩን ግን አይተውም። የነቃ እና ስርኣት አክባሪው ገጸባህሪው ዘወትር ከቆፈጠነ፣ ትሁት እና ቀለጠፈ ስብእናው ላይ በግልጥ እና ጉልህ እሚነበብ ነበር። መስ የወደፊት ተስፋውን አዉጠንጥኖበት ህግዘብነት ሲጀምር በከባድ አካል ስልጠናው ጥቂት አካሉ ተጎድቶ በሂደት ግን በያመቱ በመጠገኑ እና ሥራውን በትጋት ከዉኖ በመላመዱ ሰውነቱም እየተመለሰ አሁን ደግሞ ጭራሽ አልፎ እየተላመደ እና እየገዘፈ ነበር። ‘እግዚእአብሔር ይመስገን፣ ዘንድሮ ከድካሙ እንደአለ ተመልሰህ አገግመህ አለ ማለት ይቻል አለ፤’
“ቤት ያሉትስ ደህና ናቸው?” መስ ስለ ቤተሰብዎቹ ጠይቆ ከአህያዋ ነጂ ጀርባ አንዷ ሻንጣ ስትንቀሳቀስ ሰግቶ እየተመለከተ ጠየቀ። ነጂው አስተካከላት። “ሁሉም ናፍቀውህ አሉ። ጮለቅ አድጋአለች። ቢግ እንግሊዝኛው አልፎሃል። ሰሌን መታታት ጢዩ እየለመደች ነው ሰሞኑን። ባቤ ስእል ክሂሎቱን ከወትሮው ተክኖ አላስቀምጥ ብሎን አለ፣ ገና ስትገባ ይስልህ ይሆን አለ።” ፈገግ ብሎ ጠቅላላ ዘገባ ሰጠ። “ይሄ ጭንቅላትህ ነዋ! ወደ ሊቅነት እየነዳህአቸው ነው ሁሉንም!” አሁንም ጸጉሩን እያሻሸ በፍቅር ነካካው። “…እኔንም እንግሊዝኛዬን ታስቀጥለኝ አለህ። እኛ ሠራዊት መሀል እማ እፈራበት አለሁ! ለወደፊት እቅዴም ይረዳኝ አለ!”
እየተጨዋወቱ በናፍቆትአቸው በደንብ ስለ ጤና እና ሁኔታ አተኩረው እየተጠያየቁ፣ ወደ ቤት ደርሰው ሲገቡ መስ ሁሉ ልጆች እኩል ስለ ከበቡት አንድነት ሁሉን አቅፎ ሰላም አለ። ቤቱ በጩኸትአቸው ተናጋ። ደጋግሞ በእየተራ ወደ ጣራ እየአጎነ ታዳጊዎቹን በማስደሰት ሰላምታ የዘለለ ምቾት ተገድዶ አቀረበ። ‘ሁሉ አባትአልባ ታዳጊ እሚናፍቀው ተወዳጁ አጎት።’ ናሆም ድንገት ሆዱ ተሸበረ፦ ልክ ቅጽበት ዉስጥ እንደ ተተኮሰ ድንጋይ ባባት ምትክ ሌላ አባት እንደ አለ ሲታወሰው። እሚ እንደ ወትሮው ግንኙነትዎችአቸው ዕንባ በማፍለቅ በታላቅ ደስታ ተከብባ ፍቅርዋን አሳየች። ዉድ እና ምትክየለሽ ወንድም። በተራ ደም መተሳሰር ሳይሆን በህይወት አጋርነት የነብስ ጓደኛዋ። ከዉጭ፣ እቃዎች ተራግፈው የጊቢው ደሳሳ በር ላይ ተከመሩ። በደስታ በተለጠጠ ሞቃት አንጎል ሁሉ ተሟሙቆ ተናፋቂውን እንግዳ በመክበብ ጨዋታው ቀጠለ። “ይህ ሁሉ ምንድን ነው?” እሚ በመሳቅ እና መጨነቅ ስሜት ተደባልቃ ስለ እቃዎቹ ጠየቀ ች። “ለሚያድጉት ልጅዎችአችን እሚገቡ ናቸው።” መስ በትህትና መለሰ። እሽግዎቹ ዉስጥ ከበድ ያሉ ይዘትዎች እንደ አሉ እሚአሳብቁ ጥቅልልዎች ወደ በሩ ተጋድመው ተመለከቱ። እሚ እንደ ተጨነቀች በብዙ ምርቃት ወንድምዋን አብዝታ አከበረች። መልሳ የፍቅሩ ጠረፍ ሰማይ ደርሶ ታያት። ለብዙኛ ጊዜ። ብቸኛዋ እሚ ባይተዋሩ ልቧ ተነክቶ አለቀሰች። “ምንም ለእራስህ ሳይኖርህ ለኛ ብቻ በመኖር ነህ። እባክህ አትጨነቅብኝ። እራስህን ችለህ ቤተሰብ ያዝ እና የበለጠ ደግሞ አስደስተን።” ጮለቅን ያቀፈ መስ መልሶ አረጋጋት። ናሆም ሃሳቡ ወዲአው ጠፍቶለት ነበር። ይህን ሲአደምጥ አሁንም ተመለሰበት። ወደ ዉጭ ወጣ እና ሌላ ቁስዎች እየፈታታ ዘነጋው። አባቱ እንደ ሆነ መስን በስዉር ልቡ ዳግ-አምኖ ከበሩ ላይ ለቤተሰቡ የመጀመሪአውን ትመ. (ትእይንተመስኮት = ቲቪ) ተሸክሞ ገባ። የቻይና ስሪት ሆኖ፣ ኢትዮጵያ ወታደሮቿ ገጥመንው አለ ብለው እሚንቀባረሩበት ነበር። የኢትዮጵያ አንድ ዋና የሙስና ግንድ እንደ ሆነ በሚነገርለት ተቋምአቸው አልፋ የወጣች ምርት፤ ፋና ትመ. ባለሠላሳ ኢንችዎች ጠፍጣፋ ገጽማያ (ስክሪን) ነበረች። ጢዩ ወርዳ በስጦታው ዙሪያ ከወንድሞቿ ጋር ከበበች። ምን እንደሆነ ስትረዳ በመቦረቅ ጮለቅን ባንድ ጡንቻው አመቻችቶ ያቀፈ እረዥም መስን፣ በእግርዎቹ ስር እንጣጥ እንጣጥ በማለት በልጅ ቋንቋ አመሰገነች። “ካንድ እስከ ሦስት ከወጣሁ ትመ. ይገዛልሻል ተብዬ ነበር! ዬ…ዬ… አጎቴ ገዛልኝ! መስ! መስፍን! ገዛልኝ ዬ….. የእኔ ሽልማት፣ የእኔ ትመ.! የእኔ ትመ.!” ወዲአው ከሳተላይቶች አላማ (ሳይን) ተቀባይ መግላሊት እና አላማ-አስተናጋጅ (ሪሲቨር) ደግሞ በናሆም መዳፍዎች እንዲሁ ተይዞ ከውጭ ወደ ቤቱ ገቡ። ጢዩ የ ግሏ ትመ. እንደ ሆነ ከቢግ ወደ ታች ላሉት ልጅዎች ምስጢሩን በመዘርዘር ቶሎ አሳመነ ች። በአንድ ድምጽ ጥረቷ ሰምሮ የ ጢዩ ትመ.” ተባለ፨
የ እሚ እማይቋጭ ምርቃትዎች እና የታዳጊዎች ጩኸት ቤቱን ሲአሞቅ፣ መስ በተነሳው ጥያቄ ሰሞኑን ምናቡ መልስ እያበጀ ቢሆንም በነገሩ መረሳት ግን ተደስቶ ሁሉን ተመለከተ። እነ ቢግ፣ ባቤ እና ጢዩ እሚከዉኗቸው የግል ዳግ-ምርምርዎች እና ጥናትዎችን በከፊል አምጥተው በመሽቀዳደም አስመለከቱ። ባቤ አንድአንድ ስእሎቹንም አብሮ ለእይታ ጋበዘ። ልክኖታ (ሪኮግኒሽን) እና አድናቆት ፍለጋ ሁሉም ታዳጊ ይህን ሲከውን ሁሌም ከስሜቱ ወደ ገሃዱ የሚወርደው መስ የልጆቹን አድናቆት አሠሳ፣ በማድነቅ እና ሙገሳ አሳምሮ ማስተናገዱን ተያያዘ። ይህ ሲሆን፣ እሚ ወደ የኩሽና መስተንግዶዋን ለማቅረብ ወደ ጓሮ መመላለሱን ስታበዛ፣ ናሆም በጎን ለብቻው ተጠመደ። ምሪተዕድ (ማኑዋል) ወረቀትዎች ከአዲስ እቃዎቹ እሽግዎች አዉጥቶ በማንበብ ሁሉን በጥንቃቄ ገጣጥሞ ለሎሌነት ቶሎ አበጀአቸው። “ብዙ ተጨነቅህብኝ!” እሚ ከጓሮ ስትመለስ በተመለከተችው በመደመም መልሶ ሃሳብ ገብቷት ጭንቀቱን አቀረበች። “ብዙ አልጎዳኝም። የገበያው ምርጥ እንኳ ባይሆን ልጆች እስኪአድጉ ለጊዜው ይበቃ ይሆናል ብዬ ነው።” ጥጋት ላይ በክብ ጠረጴዛዋ ላይ ለግሏ መካን ተቀብላ የቆመችው ትመ. ላይ ዓይንዎች በመደነቅ ጣል አድርጋ “እመብርሃን ትቁምልህ እንግዲህ! ያላንተ ቤተሰቡ በእርግጥ ማን አለው!” እንባዋ ዳግ-ፈሰስ አለ። መስ ማጽናናቱን ቀጥሎ ወደ ልጆቹ በመመልከት እንዳየደረበሹ በእሚል መልእክትም ሊያስጠነቅቅ ሞከረ። ወደ መረጋጋት አሁንም ቶሎ ተመለሰ ች እና ፈጠን ብላ “እመስቴ ትክፈልህ! በል መቆሙን ትተህ ተቀመጥ፣ እነ እርሱ አይደክሙም!” እጁን ይዛ በረዥሙ ወንበር አስቀምጣው ወደ ጓዳ ዘለቀ ች። መስ በ ታናሽነት ፈገግ ብሎ ለራሱ ጮለቅን ይዞ ቁጭ አለ እና አወራ፦ “አሜን!”፨

<p class="has-text-align-justify" value="<amp-fit-text layout="fixed-height" min-font-size="6" max-font-size="72" height="80">ሁሉም ልቡ በሐሴት እየተንከባለለ እንደ ቆየ አዲስ ድባብ ተበጅቶ ቤቱን ተቀላቀለ። ቡና በቢግ ተፈላ። በቤቱ የቤትዉስጥ በአለሙያነት የሌለው በጮለቅ ላይ ብቻ ነበር። እሚ በቡና እቃዎቹ አጠገብ እጣን ማጤሲያው ላይ አጫጫሰች። መዓዛ እና ጭሱ ከብቦ ሁሉን አዝናናላት። በጎን ወደ ኩሽና በመመላለስ እና የቢግ ቡናን በመቆጣጠር መሀከል ሆና የ ምሣው ወጥ ቢደርስም አብዝቶ በመንተክተክ ማስቀጠሉን ተያያዘች። አንዱ የኩሽና ብልሃቷ መብል በበቃ መጠን ቢበስልም አብዝቶ ማንቸክቸኩ ጣዕም ጨምሮ ስለእሚወልድ ያንን ማድረጉ ነበር። ወዲአው ከስንዴ ብቻ የተዘጋጀ እና በጓዳ እርሾ እና ቅመማቅመምዎች የታገዘ ድፎዳቦ ፣ ሎሚ ዳንቴል ለብሶ፣ በእሚ ይሁንታ አናቱ ላይ ባቤ አድርጎት ጫነ እና ወደ ሳሎኑ ከጓዳ ብቅ አለ። ጢዩ ባቤ ዳቦውን እንዳይጥል እግር እግርዎቹ ሥር ሆና በማደናቀፍ በተከታታይ ማሳሰብዋን ተያይዛ ነበር። “እንዳታፈስ ዳቦውን! እንዳታፈስ ዳቦውን!” እግርዎች በእየተራ ወደ ቂጧ በመላክ እየነጠረች በተከታታይ አስጠነቀቀች። “እረፊ ልታስደፊኝ ነው!” እያለ መንገድ ስትገድበው በመሸዋወድ ደርሶ በጠረጴዛው ላይ ጫነው እና ወደ ጢዩ ዞሮ መሟገቱን ቀጠለ። “አትረብሺኝ! ሥራዬን ልስራበት! ተይ ተብለሽ አለ! በኋላ እሚ ትቆጣሽ አለች።” ሁለቱ የዘወትር ባላንጣዎች በጢዩ አልነካህም ብሎ ማብሸቅ የተፋፋመ የልጅ ጠብአቸው ጋር ተመልሰው ወደ ጓዳ ደግመው ዘለቁ፨<br>መስ ሁሉን በማጫወት ሲጠመድ መተንፈሻ ስፍራ ሊያበጅለት ናሆም የልጆቹን ትኩረት ወደ ትመ. አዞረ። ለመስ መቀበያ ከተጠመቀው ደህና ጠላ ባቤ ድጋሚ ከጢዩ በመጨቃጨቅ ሆኖ በመመለስ አቀረበ። በትልቁ ጠረጴዛ ጎንለጎን ተቀምጠው፣ መስ እና ናሆም መብል እስኪመጣ ለጫወታ ያክል ብቻ መቀማመስ ጀማመሩ። እሚ መሰናዶዋን ወጣ ገባ በማለት እያየች ከጠላው በአንድ ትንሽ ጣሣ አንቆርቁራ ቀመሰች። ጣራውን በመመልከት ቅምሻዋን አሰላች። “ነገ የተሻለ ይስተካከልልኝ አለ። ጎሸት ብሏል። ዛሬ እንዲያው እንጠጣው እንጂ…ቱፍ ቱፍ..” እንጨት ጌሾ ተፋች እና በወንፊት ማጥለሉን አስባ “ተጫወቱ! እንኳን ደህና መጣህ እንግዲ።” ብላ ጋብዛ ወደ ጓዳዋ ተመለሰች። ናሆም ስለመቅመስ በእረጅሙ ተጎነጨ፤ በጥርስ መንከስ መምረሩን ከቃናው ደባልቆ አጣጣመ እና ለኩነና ዉጤት አጤነው። የተጠለለ መቆያዋይዛን ይዛ ስትመለስ “ምርጥ ነው እሚ!” ብሎ የቀደመ ሃሳቧ ላይ አስተያየት ሰጠ። “አንተማ ጠላ መች ትጠላ!” እያለች አዲሱን ጠላ ቀዳችልአቸው። “ቄስ ቤት ሲመላለስ ለመደ!” ባቤ ፈንዲሻዎች ከጢዩ ጋር ላለመድፋት እየታገለ ሲአቀርብልአቸው አጋለጠው እና ለራሱም በጎን ባመጣው አጭር ጣሣ አንቆረቆረ። ናሆምን ጨምሮ ሁሉም ሳቀ። ቢግም ባቅሙ ሊሞክር ከቡና ኩርሲው ላይ ተነስቶ አንቆረቆረ እና ወደ ቡናው ተመልሶ በሰሌን እሚ እንዲታታ አስተምራ ባዘጋጀው ድንቅ ባለብዙወለሎች ማራገቢአ አንድ ሁለቴ ፉት ካለ ኋላ ከሰሉን ማራገብ ቀጠለ። ከጮለቅ በቀር ሁሉም ጠላ ጠጪ ነው። እሚም ታዋቂ ጠማቂ ብጤ። መብሉ ሳየይሰየም መጠጡ ቀደም ብሎ ጨዋታውን አደመቀላት። ሁሉን ቃኘት አድረወጋ አሁንም ተመለሰች፨<br>ባቤ ተጠርቶ ከተቀመጠበት ትመ. በመነሳት እንጀራዎች ተቆርጠውለት ወደ ሳሎኑ አደረሰ። አሁንም ጢዩ የወዲያው ታላቋ ጋር አንዱ ግንኙነቷን፣ መፎካከር እና ማብሸቁን፣ ቀጥላ እንጀራ እንዳያፈስስ ታስጠነቅቅ ነበር። ባቤ የእሚ ስንደዶዎች ዉጤት በሆነው ማቅረቢያ እንጀራ አደረሰ እና እየተሟገተ ተመለሰ። የእሚ ሥጋ ወጥ በተለየ መዓዛ እየአወደ እንዲሁ ለመብል ወደ ሳሎኑ በራሷ እጅዎች ቀጣይ ወጣ። መስም የቤቱ ማማር ከተጎዘጎዘው ቄጠማ እስከ እሚንበለበለው እጣን እና የጨዋታው ለዛ መፍለቅ ጨምሮ አስተዋለ። ቤተሰቡ ሽርጉድ እና መጨዋወት ሲጀምር በፊቱ የተዘረጋ ህብረ-ነብስነት ነብሱን አሞቀ። ደምቆ ያለ ቤተሰብ ሲከብበው እና አላባዊም ሲሆንለት ልቡ ፍክት አለች። የሁሉ ፊት በደግ መጠን በርቶ ደስታ እና ኹካታ አብዝቶ ተወለደ። በፍቅር መዋጮ ሁሉ ድባቡን ከመረ። የድምቀቱ መልሶ ተካፋዩ እንዲሁ እራሱ የቤተሰቡ ሁሉ አላባአዊያን ሆኑ። በዚህ የጋራ ስብስብ እና ጭዉዉት ፍቅር መለዋወጥ ሲከወን የቤቱ ዙሪአ ገባ ሁሉ ከድምጽአልባ ተፈጥሮው ወደ ህያውነት ተመለሰ። መስ የልጆቹ ልጅአዊ አጨዋወትዎች፣ ያደጉትም መስተንግዶ እና ፍቅር አስደስቶት ዘና ማለቱን እንደቀጠለ ቆየ እና ደግሞ የተለወጠበትን ከባቢ ለመልመድ ዙሪአውን ቃኘ። በግድግዳው አንድ ጥጋት ላይ ጎላ ባሉ ቀለምዎች እና ወረቀትዎች፣ ባቤ የሳላቸውን አንዱ የ አዉሬዎች መንደር ሁለት ጠብዎች እና ሌላው የ ወፍዎች ጋብቻ ሰዓት እሚሰኙ ድንቅ ስእልዎችን በመቃኘት አጤነ። የስሜት አገላለጽ አቅሙ በማደጉ ባቤ እንደ ሊቀደቂቅ (ፕሮዲጂ) ሰዓሊ ስእልዎቹ አንድ መስህብ ከመሆን አያንሱም ነበር። የጀማሪነቱ እና በዘመነ መንገድ ገና አለማጥናቱ እንጂ ትልቅ ክሂሎት እሚታይብአቸው ነበሩ። በመጀመሪያው የእልህ አስጨራሽ የትልልቅ አዉሬዎች ፍልሚያ ነበር። ፊትአቸው የቆመች ቆንጆ አዉሬ የፍልሚያው መሠረት መሆኗ እና ያሸናፊው መሆኗ በስእሉ ይሳበቅ አለ። ነገርግን፣ የስእሉ ልዩነት እሚገኘው በጎን የነበረችው እንስት አዉሬ በሃሳቧ የነበረው ትግል ከእነእርሱ በልጦ መታየቱ ነበር። ቆንጆዋ ማን ቢያሸንፍ ደስ እንደእሚላት በማስላት ከሃሳቦች ስትፋለም እና ያ ትግሏ ተደብቆ ይታይ ነበር። ደህም መስን አፈገገው። እና የወፍዎች ደስታን ደግሞ በሰርግ ሰዓቱ እንደ እሚበዛ አድርጎ እምታለቅሰውን ወፍ እና እሚያከብራትን ሙሽረ የቀመመብአቸው መንገድዎች ድንቅ ነበሩ። ደግሞ፣ መስ ፈገግ አለ። የስእሉ ሁኔታ ከድባቡ ከማገው የነብስ እርካታው ጋር ተጣበቀ። በዓመቱ መጨረሻ የቤተሰብ አባል ሊሆን፤ ይህ ድንቅ መቀላቀል ሆነለት።<br>ወዲአው ብሩ ከዮስ ጋር እሱም ቀጠን ብሎ ቀይዳማ መልኩ ላይ አዲስ ታዳጊ ፂሙን አሳምሮ መቆረጥ እሚወድድ ከሆነው ጓደኛው ጋር መጥቶ ድባቡን ተቀላቀለ። ጢዩ የንቁው እና አነስተኛ ዓይኖች ባለቤቱ፣ ለዘብ ብሎ አስተዋይ እና ቀና ማንነት የተላበሰው፣ የብሩ እጅግ ቅርብ የልብ ጓደኛን ዩሱፍ ዑመር ናፋቂ እና ከፍተኛ አድናቂ ናት። እርሱ ሲመጣ እንዲአስጠናት በማድረግ፣ የተለያዩ ጨዋታዎችንም እንዲረዳ አድርጋው ደግሞ አብሯቸው እንዲጫወት በመጋበዟ ስለተለማመዱ፣ ተቀራርበው ነበር። እንደ ወትሮው ሄዳ ተወሸቀችበት። ሰላምታ ተለዋውጠው ጠላ በናሆም ለነብሩ በጣሣዎቹ ተቀድቶ ሁሉም አሁን ለሰፋ ጨዋታው ልቡን አዋጣ። በሞቀ መስተንግዶ የጠረጴዛው እራስ እሚ ሆና ሁሉን በግራ እና ቀኟ ተደርድሮ በመመልከት ፈገግ ብላ ለመብሉ ጋበዘች። ዮስ “ልክ ሲበሉ ደረስን!” ብሩን እያየ ተናግሮ እንጀራ ቁርጦቹን አነሣ። እሚ በደስታ ሳቅ ቸረች። በቀኟ መስ ሲቀመጥ፣ ከርሱ በግራው አጠገቡ ናሆም አለ፣ በሁለቱ ተቃራኒ ከእሚ ግራ ብሩ ሲቀመጥ ጎኑ ዮስ አለ። ከእርሱ ጎን ጢዩ ሥፍራ ያዘች። አንገቷ ከጠረጴዛው ጠለል በጥቂቱ የሠገገ ቢሆንም እና ጆኩ ፊቷን ቢስቅበትም ገሸሽ አድርጋ የሁሉን ፊት ለመቀላቀል ሞከረች። ዮስ ሳቅ ብሎ ከአጠገቧ ጆኩን ወሰደላት። ባቤ ከናሆም ጎን ወንበሩን ያዘ እና ጢዩ ጋር መበሻሸቁ እና ጨዋታ መከታተሉ መሀል እየተመላለሰ ሆነ። ቢግ የቀረችው ወንበር ላይ ከእሚ ተቃራኒ ፊትለፊቷ ቡናውን በእሳቱ በመክዳት ለመብሉ ተቀመጠ። እሚ ከሰሉ ቅርቧ ስለነበር ፈገግ ብላ ወደ ጠረጴዛ ድባቧ አተኮረች፨<br>ሁሉም ሳህን በእየፊናው ወስዶ፣ ቀይ እንጀራ ቁርጥ በማንጠፍ አስቀመጠ። ብሩ ቆሎ እሚያካክሉ ቅንጥብጣቢዎች እየቆነጠጠ መቀማመስ ጀመረ። ጣዕሙ ካለቅጥ ከመንተክተኩ የተነሳ እና ሥጋው አለ ቅጥ ተንተክትኮ የደበቀውን ንጥረነገሩ ጨምቆ ያፈለቀው ቅባቱ የእሚአዉድ ያደረገውን ሥጋወጥ ለሁሉም ዞራ በማድረግ፣ አብሮ ከፎሶሊአ፣ ጥቅል ጎመን እና ሥጋ በእርድ እና ቂቤ በእሚገባ ስለተንተከተከ ጣዕሙ የተለየ የሆነ አማራጭ ወጥም በእየግልአቸው እንዲጨልፉ በመተው እንዲዞር ተደርጎ፣ በጎን ጠላዎች ዳግ-ተቀድተው፣ መቁረሱ ብቻ ሲቀርአቸው የቢግ አጭር ጸሎት ደቂቃ ደርሶ ጸጥታ ሆነ። በእሚ ትእዛዝ ቢግ ቆመ። በመመሰጥ አቡነዘበሰማያት ብሎ ባርኮ ሲቀመጥ ሁሉም አሜን ካለ ኋላ መንጫጫት እና መቁረሱ ተጀመረ። መስ ሳህኑን ሲመለከት ሥጋው እና አጥንቱ ስለ በዛ በግ ታርዶለት እንደ ሆነ ጠየቀ፤ መቁረስ ከመጀመሩ ቀድሞ። “እኛ ልጅ ባለበት እንኳን በግ ዶሮ አናርድም! የሦስትሺህ ዘመኖች ታሪክ ታልፎ እንስሳዎች በቤት ማረዱ የልጆች መጭጊዜን በስዉርስነልቦና ማቆሸሹን አለመገንዘቡን ከመንግስት ቀድመን ስለገረዝን በቤትአችን አንከውነውም።” ብሩ ማብራሪያ ሰጥቶ የእንስሳ ሞት እና ጭካኔ በልጆች ዓይኖች ስዉር አስጨናቂ ዋጋ ስላላቸው እና ወደፊትን በአንድ መንገድ ስለእሚያጨልም ይህን ድርጊት ሰብኮ እሚ በመስማማቷ ከአስቆሙት አራት አመት ሆኖት ነበር። በእርግጥ ቀድሞም ቢሆን ዶሮዎች እንጂ በሬ እና በግ አርደው አያቁም። የስልጣኔ መሰረት የልጆች ስነልቦና እና ቀናአዊ አንጎልአዊነት (ሜንታሊቲ) ስለነበር ምንም እረባሽ ኩነት ልጆች ባሉበት አይከወንም ፤ አመከደዮው ደግሞ የስነልቦና ዉድቀት ብቻ ሳይሆን የሙያአዊነት እና ቀላል አኗኗርም ጭምር ነበር። በመንደሩ ባዶ ስፍራውን ተከትሉሏሎ ባሉት መስሪያቤቶች ከአሉት አንዱ የከተማ እቅድ መስሪያቤት ያሉት ዘበኛ በአስር ብር ክፍያ አርደው እና በልተው እሚያቀርቡልአቸው ነበሩ። ይህ ብሩን እሚያስደስት ነበር። እንዲህ ቢደረግ ኖሮ፣ በተለይ በይፋ ንግድ ሰንሰለት ከሆነ፣ በሙያአዊ አያያዝ የተስተናገደ እርድ እና ቀላል ጥሬ ሥጋ ለፈጣን አገልግሎት መገኘቱ የስልጡን ማህበረሰብ ሀሁ ይሆን ነበር። ይህን በመጥፎ ባህሎች እና ድህነት የተነሳ እያንዳንዱን ሥጋ ለማትረፍ በሚል ጭምር በጓሮ እምንለውጠው ነው። እርድ ግን ላለመሰልጠን እና ልጆች በጨቅላ አይኖች ደም በማስመልከት ለክፉ ስብእና ንቅኣት መሰረት ሆኖ በመጉዳቱ ማህበረሰብእ ብዙ እንደ እሚያውክ እና ሰፊ ንግድ ሰንሰለት ግን እሚፈጥር እንደነበር እያሰላሰለ ድንገት በጉዳዩ ሄደ። ታዳጊዎች ደም ሲመለከቱ፣ ጭራሽ እረዱ ሲባሉ፣ የገጸባህሪ እረብሻ እሚያገኝአቸው እና ያ የእድሜዘመን ጠባሳ እሚሀለን መሆኑን እሚያቅልን መንግስት በህግዎች ይከለክለን እና እርድን ሙያአዊ እሚያደርግልን ይሆን አለ። መቼ? የጠቆረ ለግላጋ ፂሙን በሥስ ፈገግታ ገፋገፋ አድርጎ በመመለስ መብሉን ተገናኘ። ሃሳብ ሲመጣበት ቶሎ ይለቅቀው እና ወደ አጠገቡ ኩነት ይገባ ነበር። እንዳይመለስ እና እንዳይብሰለሰል ይህ ይደግፈው ነበር፨<br>ብዙዎቹ በዓይንዎች እረሃብ እንደ አባት እሚመለከቱት መስ፣ በፊት ቋንቋ ፈግጎ ምላሹን ሰጥቶ ሁሉን በማዝናናት እና በመጨዋወት አብሮ ተጠምዶ መመገቡን ተያያዙት። ትንንሽዎቹ ባቤ እና በተለየ ጢዩ ሳህንዎችአቸውን ይዘው ወደ እርሱ በመቅረብ እንዲአጎርስ ስለ አስገደዱ እሚም መከልከል ስለ አልተሳካላት መስ በግሉ መብላት ላይ ብዙም ማተኮር ሳይችል መብሉ ተጠናቀቀ። እነ ጢዩ ሳህንአቸውን በማዋስ አንስቶ እንዲአጎርስአቸው ሲሽቀዳደሙ ደስታአቸው አፍቃሪ አባት እንደ አገኙ እንጂ ሌላ እሚአንስ አልነበረም። አጉራሽ ሌላ አይተው አያቁም፣ ወላጁ የለም። ጢዩ አንድአንዴ ዩሱፍ ይህን እንዲከውን እስከ ማድረግ ድረስ ትጓዝ ነበር፤ በመመገብ ወይም መጫወት ዮስ የተቀላቀለ ቅጽበት ይህን አባትአዊ ሚና በተጫዋች አያያዙ አስደሳች አድርጎ ይወጣላት ዘንድ ደግሞ እርሱ ጎበዝ ዘመንአዊ ሰው ነበር፨<br>ባቤ ደግሞ እንደ ተለመደው የመዝጊአ ጸሎት አደረገ። ከቢግ የበለጠ ማተኮር ባይከውንም በመጸለዩ ግን ጎበዝ ነበር። መስ የባቤን ማደግ አስተዉሎ በልቡ እየመረቀው የጸሎት ማተኮር ነገርን ስለ አስታወሰ ፈገግ አለ። ምንይልክ ካልዕ ግብር ሲአወጡ ለተሰበሰበው እድምተኛ መብል መጠጡ ጎን በሞቀው ጨዋታ እና ኹካታ መሃል የተመስጦ ጸሎትጉዳይ ተነሳ። አንዱ ታዳሚ ከሌላዎቹ አብልጦ የመመሰጥ አቅም ቀላል ነው በማለት ሞገተ። በወጥ ሃሳብ ሆኖ ሳይሰናከል በደግ ተመስጦ አቡነዘበሰማያት ለወረደ አንድ ፈረስ እሸልም አለሁ ብለው ውርርድ ሆነ። ይህ ታዳሚው ተነስቶ አቡነ ዘ በሰማያቱን በልቦና ጀመረ። ድንገት በትልቅ ተመስጦው መሀል ሆኖ እየ ቀጠለ “ኀበንዮም ኅድግ ለነ አበሳነ” ብሎ ወደ ንጉሡ ዞር ጎንበስ በ ማለት አለ። “እምዬ! ፈረስዋ ግን ሌጣ ናት ወይስ ባዝራ እንደው?” ብሎ ጠየቀ። መስ ፈገግ ብሎ የባቤ ትኩረትን በደግ መጠን እንዳለ አይቶ በቂ በእሚል አስተዋለው። ህፃን ከአላፈረ እና ሃላፊነት እንዚህ ቀላል በእሚሰኙ ማህበረሰብእ ኩነቶች ከተወጣ፣ የግለትምምን (ኮንፊደንስ) አቅሙ ብዙ ድጋፍ አይሻም ማለት ነው። ፍቅር ብቻ ነው እሚፈለገው እንጂ ከፍራቻ መፈልቀቁ አይጠየቅም፨<br>ጸሎቱ ሲያበቃ፣ ከጸላዩ ሃሳብ ይልቅ ግን መስ የእሚ ሃሳብ ሲሰረቅ አስተዋለ። እሚ በመደነቅ ሆና ወደ ትመ.ው ስትመለከት መስ አስተዋለ። ጢዩ እና ባቤም ወደ ትመ.ው መቀመጫ አካባቢ አነስተኛ ምንጣፍ አኑረው ቀረቡት። ባበቀለው አዲስ ተፅዕኖ ገብ ተሞክሮ ከገጠር በቅርቡ ለወጣችው እና ገጽማያ (ስክሪን) ከእዚህ ቀድማ ብዙም ለእማታውቀው እህቱ እንደ አመጣ እንዲቃኝ ጋበዘችው። በድንገት ጨዋታውን እየረሳች ሄደች። አጠገቧ ብዙ ሰው ያለ መሆኑን ወደ አለመገንዘቡ ተጠጋች። በትንግርቱ የተቀሙ ዓይንዎችዋን ተመልክቶ፣ ደስታ እና እርካታ አሁንም ተሰማ ው። የመደሰት ስሜቷን ኮርቶ ለግሉ ቀመሰው። በትመ.ው፣ የ ኢቢኤስ ጣቢኣ ቅዳሜን ከሰዓት በእይት አሳላፊዎቹ (ሾው ሆስትስ)፣ ኢትዮጃዝ ፈጣሪው ክቡር ሙላቱ አስታጥቄ ተጋብዞ ቃለመጠይቅ እሚደረግለት ስርጭት ሲተላለፍ ነበር። የአ፣ የቤተሰቡን ትመ. አገልግሎትን የከፈተ ዝግጅት ሆነ። ምግብ ተጠናቅቆ፣ ወዲያው በእርግጥ ጨዋታዎችን ጋብ አድርጎ በገጽማያው ማፍጠጥ ጀመረ። ታዋቂውን ሙዚቀኛ ማድመጡን ሁሉም ተያያዘ። “ማሲንቆ የፈጠረልን ሀበሻ ትልቅ ጥበብመርምሬ (ሳይንቲስት) ነው።” አለ ባለሞገሳማው፣ አትኩሮ ሥራ እሚሰራው እና እንዲሁም ስኬትአማው የሙዚቃ ነብይ። ተፈጥሮው ሻከር ብሎ ልዩአማአዊነት (ስፔሻሊሊቲ) ያስገኘለት ድምጹን ተመራማሪ የሆነው ሙዚቀኛው እየላከ አስተያየቱን ቀጠለ “ግን የኧኧ… ማሲንቆ ፈብራኪ ማን ነው!? ፈልገንው፣ ማንቆለጳጰስ አለብን! እኔ እንኳ በኧኧ… ሙያተኛነቴ፣ ይህን ሰው አላውቀውም! ግን እንደ ሃገር እርሱን በመፈለግ ማክበር እና ስሙን ለታሪክአችን አንድ ግብዓት ማስቀመጥ አለብን። የማሲንቆ ፈጠራ ላስተዋለው ትልቅ ትንግርት ነው።” በግኝቱ ሁሌ መደሙን እና ነገርግን ታሪክ አለመዘገብአችንን ነቅፎ የቅርብ ጥናቱ የደረሰበትን ፍንጭ ቀጥሎ ጠቆመ። “የአረጀ በሬን አርደው ሲበሉት፣ ጭራውን ወደዛ መሳሪአ ቀየሩት እሚል መረጃ ላይ በዳግምርምሬ ተረድቼ አለሁ። ግን እንዴት የአን መስራት ጀመሩት? ለምን? መቼ ነበር? የት ስ? በጠቅላላው፣ ብፈልግም መጀመሪአው ማሲንቆ ታሪክአዊ መረጃን ዘልቄ አላገኘሁትም!” የሙላቱን አስተያየት በአንክሮት እይት አሳላፊዎቹ አናት እየወዘወዙ እና እየፈገጉ አደመጡ። ነገሩ ግን አያስቅም ነበር። መስ ወደ ጠረጴዛው ዞሮ አስተያየት ሰጠ። “የምንጊዜውም ችግርአችን ነው!” ናሆምም ባለሙዚቃውን ሲከታተል ስለ ነበር ወደ መጠጡ ዞሮ በሰፊው ፉት ያለውን ዋጥ አድርጎ ተናገረ። “አዎ! በነፃነት ተናግረን ስለማናድግ፣ ስናወራም ትኩረት እና ተሰሚነት አጊንተን ስለማንከበር፣ በጠቅላላው በአስተዳደግ እና ባህልአችን ሃሳብ መግለጽአችንን ስለ እማናከብር፣ ሌላ ሰው ሲናገር እኛ ዉስጥ ያለው የእዛ ታህታይአዊነት (ኢንፈሪዮሪቲ) በሰው ሁሉ ያለ ይመስለን አለ። ፍትህአዊ ለመሆን የአጣንውን ሌላ እንዳያጣ አንቸር አለን። ሰውን ሳይጨነቅ እንዲናገር ለመደገፍ፣ ምንም ይባል ምን በመሳቅ እና አናት በማወዛወዝ እንዲናገር ማደፋፈር ሀበሻአዊ አባዜ ሆኖብን አለ!” መስ በአስተያየቱ ተደመመ። እርሱ የነካው ነጥብ በጋዜጠኛዎቹ አናት እየነቀነቁ በሃዘንጫሪ ጉዳይ ፈገግታ አለማቋረጥአቸውን አልነበረም። “እኔ እኮ ያለንን ታሪክ እና አቅም አጥንቶ እሚአስተምረን አለመኖሩ ገና ተደረሰበት! ልትል መሰለኝ” ናሆም በመጠነኛ ፈገግታ ወደ ሉልአዊው የሙዚቃ ሰው እና ሃሳቡ ከአሳላፊዎቹ ጉዳይ ተመለሰ እና አደመጠ። 'በእርግጥ ቃለመጠይቅ ሲከውን ሃዘን ሲነገረው ሁሉ በቋሚ ገልፋጭ እና ዥዋዥዌ ፊት መስተንግዶ እማያበላሽ ደግ ጋዜጠኛ ወይም እይት አሳላፊ መመልከት ዘበት እንደ ሆነ አለ' ስለ ሃገርአቀፍአዊ ዕዉቀትአልባ አኗኗር እና ቋሚ ድካምአችን የጃዙ ሰው መልእክት ቀጠለ። እሚ አድምጣ መልእክቱን መጭመቅ ፈለገች። “የቀደመ ዘመን ታሪክ አልተወልንም ስለእዚህ ባለጌ ነው ነው እሚለው?” እሚ ጠየቀች። ናሆም በአባባሏ ከት ብሎ ሣቀ እና ቀጥሎ በመስማማት “አፌ ቁርጥ ይበልልኝ” ከማለቱ መስ ሊአርም ሞከረ። “ታላላቅዎችህን አክብር ዲአቆን!” እሚ አረዳድዋን ተከትላ አስተያየትኤዋን (ኮመንታሪ) ዳግ-አከለች። “አይ ይሄ ዘመን ምን ምን አደረጋችሁልን ብቻ ነው በየጊዜው። እኛን ዞሮ ማየት እንጂ ወደ ፊት አለመመልከት አባዜ ሆኖባቸዋል። አትፍረድብአቸው! ጥንት ጡት ተቆረጠ ምናምን እየ አሉ በካችአምና ለቅሶ አዲስ ድንኳን ዛሬ ሊጥሉ አለ ምክንያት ይኳትናሉ ይባል አለ!” እሚ በአከለችው ነጥብ ናሆም አንድ ስሜት ነካው እና ብቻ በጥረቷ ተደስቶ ፈገግ አለ። ‘ማሲንቆ እና አኞሌን ስታገናኝ እንዴት አልስቅ፤’ ጨዋታው ደራ። “ቢግዬ ይሄ ቀዘቀዘ ትኩስ ወጥ አምጣ እና መስ ልጅ ሲአበላ ስለ አልበላ ይጨምር ትንሽ!” እሚ አያይዛ ስትናገር መስ ግን እንቢታ ገለጸ። ባይጨርሰውም ቤቱ እንደለመደው እና እንደ ሌላው ከሁለት ቁርጥ በላይ መመገብ አልፈለገም፨ሁሉም ልቡ በሐሴት እየተንከባለለ እንደ ቆየ አዲስ ድባብ ተበጅቶ ቤቱን ተቀላቀለ። ቡና በቢግ ተፈላ። በቤቱ የቤትዉስጥ በአለሙያነት የሌለው በጮለቅ ላይ ብቻ ነበር። እሚ በቡና እቃዎቹ አጠገብ እጣን ማጤሲያው ላይ አጫጫሰች። መዓዛ እና ጭሱ ከብቦ ሁሉን አዝናናላት። በጎን ወደ ኩሽና በመመላለስ እና የቢግ ቡናን በመቆጣጠር መሀከል ሆና የ ምሣው ወጥ ቢደርስም አብዝቶ በመንተክተክ ማስቀጠሉን ተያያዘች። አንዱ የኩሽና ብልሃቷ መብል በበቃ መጠን ቢበስልም አብዝቶ ማንቸክቸኩ ጣዕም ጨምሮ ስለእሚወልድ ያንን ማድረጉ ነበር። ወዲአው ከስንዴ ብቻ የተዘጋጀ እና በጓዳ እርሾ እና ቅመማቅመምዎች የታገዘ ድፎዳቦ ፣ ሎሚ ዳንቴል ለብሶ፣ በእሚ ይሁንታ አናቱ ላይ ባቤ አድርጎት ጫነ እና ወደ ሳሎኑ ከጓዳ ብቅ አለ። ጢዩ ባቤ ዳቦውን እንዳይጥል እግር እግርዎቹ ሥር ሆና በማደናቀፍ በተከታታይ ማሳሰብዋን ተያይዛ ነበር። “እንዳታፈስ ዳቦውን! እንዳታፈስ ዳቦውን!” እግርዎች በእየተራ ወደ ቂጧ በመላክ እየነጠረች በተከታታይ አስጠነቀቀች። “እረፊ ልታስደፊኝ ነው!” እያለ መንገድ ስትገድበው በመሸዋወድ ደርሶ በጠረጴዛው ላይ ጫነው እና ወደ ጢዩ ዞሮ መሟገቱን ቀጠለ። “አትረብሺኝ! ሥራዬን ልስራበት! ተይ ተብለሽ አለ! በኋላ እሚ ትቆጣሽ አለች።” ሁለቱ የዘወትር ባላንጣዎች በጢዩ አልነካህም ብሎ ማብሸቅ የተፋፋመ የልጅ ጠብአቸው ጋር ተመልሰው ወደ ጓዳ ደግመው ዘለቁ፨
መስ ሁሉን በማጫወት ሲጠመድ መተንፈሻ ስፍራ ሊያበጅለት ናሆም የልጆቹን ትኩረት ወደ ትመ. አዞረ። ለመስ መቀበያ ከተጠመቀው ደህና ጠላ ባቤ ድጋሚ ከጢዩ በመጨቃጨቅ ሆኖ በመመለስ አቀረበ። በትልቁ ጠረጴዛ ጎንለጎን ተቀምጠው፣ መስ እና ናሆም መብል እስኪመጣ ለጫወታ ያክል ብቻ መቀማመስ ጀማመሩ። እሚ መሰናዶዋን ወጣ ገባ በማለት እያየች ከጠላው በአንድ ትንሽ ጣሣ አንቆርቁራ ቀመሰች። ጣራውን በመመልከት ቅምሻዋን አሰላች። “ነገ የተሻለ ይስተካከልልኝ አለ። ጎሸት ብሏል። ዛሬ እንዲያው እንጠጣው እንጂ…ቱፍ ቱፍ..” እንጨት ጌሾ ተፋች እና በወንፊት ማጥለሉን አስባ “ተጫወቱ! እንኳን ደህና መጣህ እንግዲ።” ብላ ጋብዛ ወደ ጓዳዋ ተመለሰች። ናሆም ስለመቅመስ በእረጅሙ ተጎነጨ፤ በጥርስ መንከስ መምረሩን ከቃናው ደባልቆ አጣጣመ እና ለኩነና ዉጤት አጤነው። የተጠለለ መቆያዋይዛን ይዛ ስትመለስ “ምርጥ ነው እሚ!” ብሎ የቀደመ ሃሳቧ ላይ አስተያየት ሰጠ። “አንተማ ጠላ መች ትጠላ!” እያለች አዲሱን ጠላ ቀዳችልአቸው። “ቄስ ቤት ሲመላለስ ለመደ!” ባቤ ፈንዲሻዎች ከጢዩ ጋር ላለመድፋት እየታገለ ሲአቀርብልአቸው አጋለጠው እና ለራሱም በጎን ባመጣው አጭር ጣሣ አንቆረቆረ። ናሆምን ጨምሮ ሁሉም ሳቀ። ቢግም ባቅሙ ሊሞክር ከቡና ኩርሲው ላይ ተነስቶ አንቆረቆረ እና ወደ ቡናው ተመልሶ በሰሌን እሚ እንዲታታ አስተምራ ባዘጋጀው ድንቅ ባለብዙወለሎች ማራገቢአ አንድ ሁለቴ ፉት ካለ ኋላ ከሰሉን ማራገብ ቀጠለ። ከጮለቅ በቀር ሁሉም ጠላ ጠጪ ነው። እሚም ታዋቂ ጠማቂ ብጤ። መብሉ ሳየይሰየም መጠጡ ቀደም ብሎ ጨዋታውን አደመቀላት። ሁሉን ቃኘት አድረወጋ አሁንም ተመለሰች፨
ባቤ ተጠርቶ ከተቀመጠበት ትመ. በመነሳት እንጀራዎች ተቆርጠውለት ወደ ሳሎኑ አደረሰ። አሁንም ጢዩ የወዲያው ታላቋ ጋር አንዱ ግንኙነቷን፣ መፎካከር እና ማብሸቁን፣ ቀጥላ እንጀራ እንዳያፈስስ ታስጠነቅቅ ነበር። ባቤ የእሚ ስንደዶዎች ዉጤት በሆነው ማቅረቢያ እንጀራ አደረሰ እና እየተሟገተ ተመለሰ። የእሚ ሥጋ ወጥ በተለየ መዓዛ እየአወደ እንዲሁ ለመብል ወደ ሳሎኑ በራሷ እጅዎች ቀጣይ ወጣ። መስም የቤቱ ማማር ከተጎዘጎዘው ቄጠማ እስከ እሚንበለበለው እጣን እና የጨዋታው ለዛ መፍለቅ ጨምሮ አስተዋለ። ቤተሰቡ ሽርጉድ እና መጨዋወት ሲጀምር በፊቱ የተዘረጋ ህብረ-ነብስነት ነብሱን አሞቀ። ደምቆ ያለ ቤተሰብ ሲከብበው እና አላባዊም ሲሆንለት ልቡ ፍክት አለች። የሁሉ ፊት በደግ መጠን በርቶ ደስታ እና ኹካታ አብዝቶ ተወለደ። በፍቅር መዋጮ ሁሉ ድባቡን ከመረ። የድምቀቱ መልሶ ተካፋዩ እንዲሁ እራሱ የቤተሰቡ ሁሉ አላባአዊያን ሆኑ። በዚህ የጋራ ስብስብ እና ጭዉዉት ፍቅር መለዋወጥ ሲከወን የቤቱ ዙሪአ ገባ ሁሉ ከድምጽአልባ ተፈጥሮው ወደ ህያውነት ተመለሰ። መስ የልጆቹ ልጅአዊ አጨዋወትዎች፣ ያደጉትም መስተንግዶ እና ፍቅር አስደስቶት ዘና ማለቱን እንደቀጠለ ቆየ እና ደግሞ የተለወጠበትን ከባቢ ለመልመድ ዙሪአውን ቃኘ። በግድግዳው አንድ ጥጋት ላይ ጎላ ባሉ ቀለምዎች እና ወረቀትዎች፣ ባቤ የሳላቸውን አንዱ የ አዉሬዎች መንደር ሁለት ጠብዎች እና ሌላው የ ወፍዎች ጋብቻ ሰዓት እሚሰኙ ድንቅ ስእልዎችን በመቃኘት አጤነ። የስሜት አገላለጽ አቅሙ በማደጉ ባቤ እንደ ሊቀደቂቅ (ፕሮዲጂ) ሰዓሊ ስእልዎቹ አንድ መስህብ ከመሆን አያንሱም ነበር። የጀማሪነቱ እና በዘመነ መንገድ ገና አለማጥናቱ እንጂ ትልቅ ክሂሎት እሚታይብአቸው ነበሩ። በመጀመሪያው የእልህ አስጨራሽ የትልልቅ አዉሬዎች ፍልሚያ ነበር። ፊትአቸው የቆመች ቆንጆ አዉሬ የፍልሚያው መሠረት መሆኗ እና ያሸናፊው መሆኗ በስእሉ ይሳበቅ አለ። ነገርግን፣ የስእሉ ልዩነት እሚገኘው በጎን የነበረችው እንስት አዉሬ በሃሳቧ የነበረው ትግል ከእነእርሱ በልጦ መታየቱ ነበር። ቆንጆዋ ማን ቢያሸንፍ ደስ እንደእሚላት በማስላት ከሃሳቦች ስትፋለም እና ያ ትግሏ ተደብቆ ይታይ ነበር። ደህም መስን አፈገገው። እና የወፍዎች ደስታን ደግሞ በሰርግ ሰዓቱ እንደ እሚበዛ አድርጎ እምታለቅሰውን ወፍ እና እሚያከብራትን ሙሽረ የቀመመብአቸው መንገድዎች ድንቅ ነበሩ። ደግሞ፣ መስ ፈገግ አለ። የስእሉ ሁኔታ ከድባቡ ከማገው የነብስ እርካታው ጋር ተጣበቀ። በዓመቱ መጨረሻ የቤተሰብ አባል ሊሆን፤ ይህ ድንቅ መቀላቀል ሆነለት።
ወዲአው ብሩ ከዮስ ጋር እሱም ቀጠን ብሎ ቀይዳማ መልኩ ላይ አዲስ ታዳጊ ፂሙን አሳምሮ መቆረጥ እሚወድድ ከሆነው ጓደኛው ጋር መጥቶ ድባቡን ተቀላቀለ። ጢዩ የንቁው እና አነስተኛ ዓይኖች ባለቤቱ፣ ለዘብ ብሎ አስተዋይ እና ቀና ማንነት የተላበሰው፣ የብሩ እጅግ ቅርብ የልብ ጓደኛን ዩሱፍ ዑመር ናፋቂ እና ከፍተኛ አድናቂ ናት። እርሱ ሲመጣ እንዲአስጠናት በማድረግ፣ የተለያዩ ጨዋታዎችንም እንዲረዳ አድርጋው ደግሞ አብሯቸው እንዲጫወት በመጋበዟ ስለተለማመዱ፣ ተቀራርበው ነበር። እንደ ወትሮው ሄዳ ተወሸቀችበት። ሰላምታ ተለዋውጠው ጠላ በናሆም ለነብሩ በጣሣዎቹ ተቀድቶ ሁሉም አሁን ለሰፋ ጨዋታው ልቡን አዋጣ። በሞቀ መስተንግዶ የጠረጴዛው እራስ እሚ ሆና ሁሉን በግራ እና ቀኟ ተደርድሮ በመመልከት ፈገግ ብላ ለመብሉ ጋበዘች። ዮስ “ልክ ሲበሉ ደረስን!” ብሩን እያየ ተናግሮ እንጀራ ቁርጦቹን አነሣ። እሚ በደስታ ሳቅ ቸረች። በቀኟ መስ ሲቀመጥ፣ ከርሱ በግራው አጠገቡ ናሆም አለ፣ በሁለቱ ተቃራኒ ከእሚ ግራ ብሩ ሲቀመጥ ጎኑ ዮስ አለ። ከእርሱ ጎን ጢዩ ሥፍራ ያዘች። አንገቷ ከጠረጴዛው ጠለል በጥቂቱ የሠገገ ቢሆንም እና ጆኩ ፊቷን ቢስቅበትም ገሸሽ አድርጋ የሁሉን ፊት ለመቀላቀል ሞከረች። ዮስ ሳቅ ብሎ ከአጠገቧ ጆኩን ወሰደላት። ባቤ ከናሆም ጎን ወንበሩን ያዘ እና ጢዩ ጋር መበሻሸቁ እና ጨዋታ መከታተሉ መሀል እየተመላለሰ ሆነ። ቢግ የቀረችው ወንበር ላይ ከእሚ ተቃራኒ ፊትለፊቷ ቡናውን በእሳቱ በመክዳት ለመብሉ ተቀመጠ። እሚ ከሰሉ ቅርቧ ስለነበር ፈገግ ብላ ወደ ጠረጴዛ ድባቧ አተኮረች፨
ሁሉም ሳህን በእየፊናው ወስዶ፣ ቀይ እንጀራ ቁርጥ በማንጠፍ አስቀመጠ። ብሩ ቆሎ እሚያካክሉ ቅንጥብጣቢዎች እየቆነጠጠ መቀማመስ ጀመረ። ጣዕሙ ካለቅጥ ከመንተክተኩ የተነሳ እና ሥጋው አለ ቅጥ ተንተክትኮ የደበቀውን ንጥረነገሩ ጨምቆ ያፈለቀው ቅባቱ የእሚአዉድ ያደረገውን ሥጋወጥ ለሁሉም ዞራ በማድረግ፣ አብሮ ከፎሶሊአ፣ ጥቅል ጎመን እና ሥጋ በእርድ እና ቂቤ በእሚገባ ስለተንተከተከ ጣዕሙ የተለየ የሆነ አማራጭ ወጥም በእየግልአቸው እንዲጨልፉ በመተው እንዲዞር ተደርጎ፣ በጎን ጠላዎች ዳግ-ተቀድተው፣ መቁረሱ ብቻ ሲቀርአቸው የቢግ አጭር ጸሎት ደቂቃ ደርሶ ጸጥታ ሆነ። በእሚ ትእዛዝ ቢግ ቆመ። በመመሰጥ አቡነዘበሰማያት ብሎ ባርኮ ሲቀመጥ ሁሉም አሜን ካለ ኋላ መንጫጫት እና መቁረሱ ተጀመረ። መስ ሳህኑን ሲመለከት ሥጋው እና አጥንቱ ስለ በዛ በግ ታርዶለት እንደ ሆነ ጠየቀ፤ መቁረስ ከመጀመሩ ቀድሞ። “እኛ ልጅ ባለበት እንኳን በግ ዶሮ አናርድም! የሦስትሺህ ዘመኖች ታሪክ ታልፎ እንስሳዎች በቤት ማረዱ የልጆች መጭጊዜን በስዉርስነልቦና ማቆሸሹን አለመገንዘቡን ከመንግስት ቀድመን ስለገረዝን በቤትአችን አንከውነውም።” ብሩ ማብራሪያ ሰጥቶ የእንስሳ ሞት እና ጭካኔ በልጆች ዓይኖች ስዉር አስጨናቂ ዋጋ ስላላቸው እና ወደፊትን በአንድ መንገድ ስለእሚያጨልም ይህን ድርጊት ሰብኮ እሚ በመስማማቷ ከአስቆሙት አራት አመት ሆኖት ነበር። በእርግጥ ቀድሞም ቢሆን ዶሮዎች እንጂ በሬ እና በግ አርደው አያቁም። የስልጣኔ መሰረት የልጆች ስነልቦና እና ቀናአዊ አንጎልአዊነት (ሜንታሊቲ) ስለነበር ምንም እረባሽ ኩነት ልጆች ባሉበት አይከወንም ፤ አመከደዮው ደግሞ የስነልቦና ዉድቀት ብቻ ሳይሆን የሙያአዊነት እና ቀላል አኗኗርም ጭምር ነበር። በመንደሩ ባዶ ስፍራውን ተከትሉሏሎ ባሉት መስሪያቤቶች ከአሉት አንዱ የከተማ እቅድ መስሪያቤት ያሉት ዘበኛ በአስር ብር ክፍያ አርደው እና በልተው እሚያቀርቡልአቸው ነበሩ። ይህ ብሩን እሚያስደስት ነበር። እንዲህ ቢደረግ ኖሮ፣ በተለይ በይፋ ንግድ ሰንሰለት ከሆነ፣ በሙያአዊ አያያዝ የተስተናገደ እርድ እና ቀላል ጥሬ ሥጋ ለፈጣን አገልግሎት መገኘቱ የስልጡን ማህበረሰብ ሀሁ ይሆን ነበር። ይህን በመጥፎ ባህሎች እና ድህነት የተነሳ እያንዳንዱን ሥጋ ለማትረፍ በሚል ጭምር በጓሮ እምንለውጠው ነው። እርድ ግን ላለመሰልጠን እና ልጆች በጨቅላ አይኖች ደም በማስመልከት ለክፉ ስብእና ንቅኣት መሰረት ሆኖ በመጉዳቱ ማህበረሰብእ ብዙ እንደ እሚያውክ እና ሰፊ ንግድ ሰንሰለት ግን እሚፈጥር እንደነበር እያሰላሰለ ድንገት በጉዳዩ ሄደ። ታዳጊዎች ደም ሲመለከቱ፣ ጭራሽ እረዱ ሲባሉ፣ የገጸባህሪ እረብሻ እሚያገኝአቸው እና ያ የእድሜዘመን ጠባሳ እሚሀለን መሆኑን እሚያቅልን መንግስት በህግዎች ይከለክለን እና እርድን ሙያአዊ እሚያደርግልን ይሆን አለ። መቼ? የጠቆረ ለግላጋ ፂሙን በሥስ ፈገግታ ገፋገፋ አድርጎ በመመለስ መብሉን ተገናኘ። ሃሳብ ሲመጣበት ቶሎ ይለቅቀው እና ወደ አጠገቡ ኩነት ይገባ ነበር። እንዳይመለስ እና እንዳይብሰለሰል ይህ ይደግፈው ነበር፨
ብዙዎቹ በዓይንዎች እረሃብ እንደ አባት እሚመለከቱት መስ፣ በፊት ቋንቋ ፈግጎ ምላሹን ሰጥቶ ሁሉን በማዝናናት እና በመጨዋወት አብሮ ተጠምዶ መመገቡን ተያያዙት። ትንንሽዎቹ ባቤ እና በተለየ ጢዩ ሳህንዎችአቸውን ይዘው ወደ እርሱ በመቅረብ እንዲአጎርስ ስለ አስገደዱ እሚም መከልከል ስለ አልተሳካላት መስ በግሉ መብላት ላይ ብዙም ማተኮር ሳይችል መብሉ ተጠናቀቀ። እነ ጢዩ ሳህንአቸውን በማዋስ አንስቶ እንዲአጎርስአቸው ሲሽቀዳደሙ ደስታአቸው አፍቃሪ አባት እንደ አገኙ እንጂ ሌላ እሚአንስ አልነበረም። አጉራሽ ሌላ አይተው አያቁም፣ ወላጁ የለም። ጢዩ አንድአንዴ ዩሱፍ ይህን እንዲከውን እስከ ማድረግ ድረስ ትጓዝ ነበር፤ በመመገብ ወይም መጫወት ዮስ የተቀላቀለ ቅጽበት ይህን አባትአዊ ሚና በተጫዋች አያያዙ አስደሳች አድርጎ ይወጣላት ዘንድ ደግሞ እርሱ ጎበዝ ዘመንአዊ ሰው ነበር፨
ባቤ ደግሞ እንደ ተለመደው የመዝጊአ ጸሎት አደረገ። ከቢግ የበለጠ ማተኮር ባይከውንም በመጸለዩ ግን ጎበዝ ነበር። መስ የባቤን ማደግ አስተዉሎ በልቡ እየመረቀው የጸሎት ማተኮር ነገርን ስለ አስታወሰ ፈገግ አለ። ምንይልክ ካልዕ ግብር ሲአወጡ ለተሰበሰበው እድምተኛ መብል መጠጡ ጎን በሞቀው ጨዋታ እና ኹካታ መሃል የተመስጦ ጸሎትጉዳይ ተነሳ። አንዱ ታዳሚ ከሌላዎቹ አብልጦ የመመሰጥ አቅም ቀላል ነው በማለት ሞገተ። በወጥ ሃሳብ ሆኖ ሳይሰናከል በደግ ተመስጦ አቡነዘበሰማያት ለወረደ አንድ ፈረስ እሸልም አለሁ ብለው ውርርድ ሆነ። ይህ ታዳሚው ተነስቶ አቡነ ዘ በሰማያቱን በልቦና ጀመረ። ድንገት በትልቅ ተመስጦው መሀል ሆኖ እየ ቀጠለ “ኀበንዮም ኅድግ ለነ አበሳነ” ብሎ ወደ ንጉሡ ዞር ጎንበስ በ ማለት አለ። “እምዬ! ፈረስዋ ግን ሌጣ ናት ወይስ ባዝራ እንደው?” ብሎ ጠየቀ። መስ ፈገግ ብሎ የባቤ ትኩረትን በደግ መጠን እንዳለ አይቶ በቂ በእሚል አስተዋለው። ህፃን ከአላፈረ እና ሃላፊነት እንዚህ ቀላል በእሚሰኙ ማህበረሰብእ ኩነቶች ከተወጣ፣ የግለትምምን (ኮንፊደንስ) አቅሙ ብዙ ድጋፍ አይሻም ማለት ነው። ፍቅር ብቻ ነው እሚፈለገው እንጂ ከፍራቻ መፈልቀቁ አይጠየቅም፨
ጸሎቱ ሲያበቃ፣ ከጸላዩ ሃሳብ ይልቅ ግን መስ የእሚ ሃሳብ ሲሰረቅ አስተዋለ። እሚ በመደነቅ ሆና ወደ ትመ.ው ስትመለከት መስ አስተዋለ። ጢዩ እና ባቤም ወደ ትመ.ው መቀመጫ አካባቢ አነስተኛ ምንጣፍ አኑረው ቀረቡት። ባበቀለው አዲስ ተፅዕኖ ገብ ተሞክሮ ከገጠር በቅርቡ ለወጣችው እና ገጽማያ (ስክሪን) ከእዚህ ቀድማ ብዙም ለእማታውቀው እህቱ እንደ አመጣ እንዲቃኝ ጋበዘችው። በድንገት ጨዋታውን እየረሳች ሄደች። አጠገቧ ብዙ ሰው ያለ መሆኑን ወደ አለመገንዘቡ ተጠጋች። በትንግርቱ የተቀሙ ዓይንዎችዋን ተመልክቶ፣ ደስታ እና እርካታ አሁንም ተሰማ ው። የመደሰት ስሜቷን ኮርቶ ለግሉ ቀመሰው። በትመ.ው፣ የ ኢቢኤስ ጣቢኣ ቅዳሜን ከሰዓት በእይት አሳላፊዎቹ (ሾው ሆስትስ)፣ ኢትዮጃዝ ፈጣሪው ክቡር ሙላቱ አስታጥቄ ተጋብዞ ቃለመጠይቅ እሚደረግለት ስርጭት ሲተላለፍ ነበር። የአ፣ የቤተሰቡን ትመ. አገልግሎትን የከፈተ ዝግጅት ሆነ። ምግብ ተጠናቅቆ፣ ወዲያው በእርግጥ ጨዋታዎችን ጋብ አድርጎ በገጽማያው ማፍጠጥ ጀመረ። ታዋቂውን ሙዚቀኛ ማድመጡን ሁሉም ተያያዘ። “ማሲንቆ የፈጠረልን ሀበሻ ትልቅ ጥበብመርምሬ (ሳይንቲስት) ነው።” አለ ባለሞገሳማው፣ አትኩሮ ሥራ እሚሰራው እና እንዲሁም ስኬትአማው የሙዚቃ ነብይ። ተፈጥሮው ሻከር ብሎ ልዩአማአዊነት (ስፔሻሊሊቲ) ያስገኘለት ድምጹን ተመራማሪ የሆነው ሙዚቀኛው እየላከ አስተያየቱን ቀጠለ “ግን የኧኧ… ማሲንቆ ፈብራኪ ማን ነው!? ፈልገንው፣ ማንቆለጳጰስ አለብን! እኔ እንኳ በኧኧ… ሙያተኛነቴ፣ ይህን ሰው አላውቀውም! ግን እንደ ሃገር እርሱን በመፈለግ ማክበር እና ስሙን ለታሪክአችን አንድ ግብዓት ማስቀመጥ አለብን። የማሲንቆ ፈጠራ ላስተዋለው ትልቅ ትንግርት ነው።” በግኝቱ ሁሌ መደሙን እና ነገርግን ታሪክ አለመዘገብአችንን ነቅፎ የቅርብ ጥናቱ የደረሰበትን ፍንጭ ቀጥሎ ጠቆመ። “የአረጀ በሬን አርደው ሲበሉት፣ ጭራውን ወደዛ መሳሪአ ቀየሩት እሚል መረጃ ላይ በዳግምርምሬ ተረድቼ አለሁ። ግን እንዴት የአን መስራት ጀመሩት? ለምን? መቼ ነበር? የት ስ? በጠቅላላው፣ ብፈልግም መጀመሪአው ማሲንቆ ታሪክአዊ መረጃን ዘልቄ አላገኘሁትም!” የሙላቱን አስተያየት በአንክሮት እይት አሳላፊዎቹ አናት እየወዘወዙ እና እየፈገጉ አደመጡ። ነገሩ ግን አያስቅም ነበር። መስ ወደ ጠረጴዛው ዞሮ አስተያየት ሰጠ። “የምንጊዜውም ችግርአችን ነው!” ናሆምም ባለሙዚቃውን ሲከታተል ስለ ነበር ወደ መጠጡ ዞሮ በሰፊው ፉት ያለውን ዋጥ አድርጎ ተናገረ። “አዎ! በነፃነት ተናግረን ስለማናድግ፣ ስናወራም ትኩረት እና ተሰሚነት አጊንተን ስለማንከበር፣ በጠቅላላው በአስተዳደግ እና ባህልአችን ሃሳብ መግለጽአችንን ስለ እማናከብር፣ ሌላ ሰው ሲናገር እኛ ዉስጥ ያለው የእዛ ታህታይአዊነት (ኢንፈሪዮሪቲ) በሰው ሁሉ ያለ ይመስለን አለ። ፍትህአዊ ለመሆን የአጣንውን ሌላ እንዳያጣ አንቸር አለን። ሰውን ሳይጨነቅ እንዲናገር ለመደገፍ፣ ምንም ይባል ምን በመሳቅ እና አናት በማወዛወዝ እንዲናገር ማደፋፈር ሀበሻአዊ አባዜ ሆኖብን አለ!” መስ በአስተያየቱ ተደመመ። እርሱ የነካው ነጥብ በጋዜጠኛዎቹ አናት እየነቀነቁ በሃዘንጫሪ ጉዳይ ፈገግታ አለማቋረጥአቸውን አልነበረም። “እኔ እኮ ያለንን ታሪክ እና አቅም አጥንቶ እሚአስተምረን አለመኖሩ ገና ተደረሰበት! ልትል መሰለኝ” ናሆም በመጠነኛ ፈገግታ ወደ ሉልአዊው የሙዚቃ ሰው እና ሃሳቡ ከአሳላፊዎቹ ጉዳይ ተመለሰ እና አደመጠ። ‘በእርግጥ ቃለመጠይቅ ሲከውን ሃዘን ሲነገረው ሁሉ በቋሚ ገልፋጭ እና ዥዋዥዌ ፊት መስተንግዶ እማያበላሽ ደግ ጋዜጠኛ ወይም እይት አሳላፊ መመልከት ዘበት እንደ ሆነ አለ’ ስለ ሃገርአቀፍአዊ ዕዉቀትአልባ አኗኗር እና ቋሚ ድካምአችን የጃዙ ሰው መልእክት ቀጠለ። እሚ አድምጣ መልእክቱን መጭመቅ ፈለገች። “የቀደመ ዘመን ታሪክ አልተወልንም ስለእዚህ ባለጌ ነው ነው እሚለው?” እሚ ጠየቀች። ናሆም በአባባሏ ከት ብሎ ሣቀ እና ቀጥሎ በመስማማት “አፌ ቁርጥ ይበልልኝ” ከማለቱ መስ ሊአርም ሞከረ። “ታላላቅዎችህን አክብር ዲአቆን!” እሚ አረዳድዋን ተከትላ አስተያየትኤዋን (ኮመንታሪ) ዳግ-አከለች። “አይ ይሄ ዘመን ምን ምን አደረጋችሁልን ብቻ ነው በየጊዜው። እኛን ዞሮ ማየት እንጂ ወደ ፊት አለመመልከት አባዜ ሆኖባቸዋል። አትፍረድብአቸው! ጥንት ጡት ተቆረጠ ምናምን እየ አሉ በካችአምና ለቅሶ አዲስ ድንኳን ዛሬ ሊጥሉ አለ ምክንያት ይኳትናሉ ይባል አለ!” እሚ በአከለችው ነጥብ ናሆም አንድ ስሜት ነካው እና ብቻ በጥረቷ ተደስቶ ፈገግ አለ። ‘ማሲንቆ እና አኞሌን ስታገናኝ እንዴት አልስቅ፤’ ጨዋታው ደራ። “ቢግዬ ይሄ ቀዘቀዘ ትኩስ ወጥ አምጣ እና መስ ልጅ ሲአበላ ስለ አልበላ ይጨምር ትንሽ!” እሚ አያይዛ ስትናገር መስ ግን እንቢታ ገለጸ። ባይጨርሰውም ቤቱ እንደለመደው እና እንደ ሌላው ከሁለት ቁርጥ በላይ መመገብ አልፈለገም፨

ናሆም ወደ ጨዋታው ለመመለስ እናቱን እየተመለከተ ፈገግ በማለት ፊቷ ላይ አተኮረ። ብዙ እሚናገረው እንደ አለ በፊቱ የፈሠሰ ከፍተኛ አልገለጽባይ ስሜት መሰከረበት። የጠሩ ዓይኖቹን አስለመለመ። ባቤ እና ጢዩ ተጠርተው ተባብረው ሁሉን እየአስታጠቡ ሳለ አስተያየቱን ቀጠለ። “በመጀመሪአ ሁሉን አታገናኚ። የተነሳው፣ የኢትዮጃዝ ፈጣሪው ያለውን መሰረት ያደረገ ሌላ ፍሬነጥብ ነው። በዛ ላይ፣ ትዉልዱ ቢናገር ባይናገርም ሃቅ ሃቅ ነው! የእኛ ልጅልጅዎች መቶ ዓመትዎች ጀርባ የማሲንቆ ጌታ ማን እንደ ሆነ ሊፈልጉ ይነሳሉ። ዛሬ የእናንተ ትዉልድ ፈልጎ ካላስተማረን በቀር ማለት ነው። ከዜሮ የመጀመሩ ዐዚም፣ አንድ መነሻ መካንጊዜ (ስፔስታይም) ላይ ተሰብሮ፣ ዘመንአዊ አኗኗር አንድ ስለ እማንል፣ ከአዲስ መጠየቁ ገና መቶ ዓመትዎች ጀርባም የአው ነው። ማሲንቆ የእልፍ ክፍት ጉዳይዎችአችን ምሳሌ ይሁነን እና፣ መጠናት የነበረበት እና አወላለዱን ጀምሮ ያለፈበት እድገቱ ሁሉ ለእኛ መቀመጥ የነበረበት ድሮ ነበር። እንጂ ዛሬ ተነስተን የት እንደ ጎነቆለ እምንፈልገው መሆን አልነበረበትም። ሙላቱ አሁን ባይጠይቅም፣ የማሲንቆ ምንጊዜም ምርጥ ተጫዋችአችንስ ማን ነው? ከሴቶችስ የቷ ኢትዮጵያዊት ምርጡን ማሲንቆ ተጫውታልን አለች? ሌላ ሙላቱ ተፈጥሮ ገና እልፍ ባዶ ስፍራዎችአችንን ይጠይቀን እና እሚአፍርብን ይሆን አለ። ገና ወደፊት!” ናሆም በአዉቆታ (ኢንቴንሽናል) እኛ በማለቱ እነ እሚ አፈር አሉ። “ሽሙጥ መሆኑ ነው!” አለ ብሩ ከጓደኛው ጋር ተቀምጦ ጨዋታውን በአትኩሮት እየአደመጠ። እንደ ወትሮው፣ ብዙም በወሬ አድምቆ አይሳተፍም። ለብቻው ወይም ቢበዛ ሦስት ሰውዎች ሲጨዋወቱ በቀረ፣ ቅድመንቃት (ፕሮአክቲቭ) ጥረት በጨዋታዎች እምብዛም አያደርግም። አድምጦ ግን አልፎአልፎ ሰከን ባለመልኩ ይሳተፍ አለ። መስ ወደ ናሆም ወግኖ ስነስርኣት ለማላበሱ ብቻ አሁንም በመጨነቅ ሆነ። እሚም ብሩን ሰምታ በመሳቅ ወደ ናሆም ዞረች። ከነጥቧ የተቀጠለ መከላከያዋ ቀረበ። “እኛ ከገጠር ነው የወጣን እንግዲህ! በቃ! ጨረስኩ ነጥቤን!” ከጠላዋ ተጎንጭታ ፈልሰስ ለ ማለት ባያስችልም ወንበሩ፣ ዘና ለማለት በመሞከር፣ ፈታ ብላ በመከላከሏ ላይ በረታች። ብዙዎቹ ሳቅ ሲሉ ቀጠለች። “ተማሪቤት እንኳ አይተንአናቅ በዘመንአችን!” ከጎኗ ቢግ ደርሶ አዲሱን ወጥ አቀበላት። ለመስ አቀረበች እና አልቀበልም ማለቱን አስታውሳ በእዛው በማለት ደግማ ብትሞክርም መስ ደግሞ እምቢ ስለ አለ መልሳ ለቢግ ሰጠችው። ሊመለስ ሲል አብሮ ቢግን፣ ናሆም ጥቅሻ ሰጠው እና ቢግ ወደ ጓዳ ምሥጢሬ (ኮድ) ተቀብሎ ገባ። ናሆምም ወደ እናቱ ዳግ-ለመከላከል ዞረ። “እና እኛ መናጢ ኢዕድለኛ፣ ለሃገሩ አራሽ ብቻ ነን፤ ከተሜ ብቻውን ሁሉን ይወቅልን ነው! ያ ከቶ ሠነፍ ስህተት ነው። መንግስት ጉዳዩን ማስጠናት እና ለእኛ ወጥ ማስተማሪአ እንዲሆን – በገጠርም በከተማም – ታሪክ እና መረጃውን አስምጦ ማበጀት ነበረበት። የከተሜው ጥፋት አይደለም። ምንአልባት የእምንመራብአቸው መንግስትዎች እንጂ።” ናሆም ሃገረሰቤውን (ካንትሪሳይድ) አብሮ በግልጥ ለመተቸት ባይችልም፤ በግልጽ ገጠሬ እምንለው ሃገረሰቤ ግን ነፃ እንደ መሆን እንደአለበት መስ አሰበ። የስደተኛው ማስታወሻ ላይ ስደተኛው በትግራይ ክልል መግቢአ የገጠመውን የሀበሻ ገጠር ሂወት ተርኮ ከቶ አንድ ዉስብስብ ነገር እንደ እማይገባአቸው አሳምሮ አቅርቦ አንብቦ ነበር። የአልጄዚራ አንድ ዘጋቢ ፊልም ደግሞ የኢትዮጵያ ገጠሮች ያዓለም አንደኛ ድሃዎች ብሎ ያሰራጨው እይትን ለለቅሶ በደረሰ ስሜት አስተዉሎ ነበር። በእዉቀቱ ስዩምም የገጠሯ እንስት ከመፍጨት ተባእቱ አርሶ አግብቷት ከመዋለድ በዘለለ በምድርአዊ ሂወት ሌላ ምንም እንደ እማያቁ ተናግሮ ገጥሞልአቸው ነበር። የኢትዮጵያዊ ስልጣኔ መሠረትን እሚጠቁሙት መሀል የሆኑት እና በትዉልድአችን ነጥብአቸው የተዘነጋው ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህንም፣ ይድረስ ለእማላውቅህ ወንድሜ እያሉ የማንተዋወቅ ያክል ከየገጠሩ ኢትዮጵያ እንደተቆራረጥን ሆድ በእሚያባባ መንገድ ገሃዱን ገጥመው አሉ። አንኮበር በሄደበት አጋጣሚ ደግሞ እራሱ ያንን ማየቱን አስታወሰ። ሰዎቹን ያ ጉብታ ምን እንደሆነ ብሎ ቢጠይቅ መከራከርን ይይዙ ነበር። አጠገብአቸው ካለች ቀዬ ዉጭ አያቁም። አይወጡምም። ሀገር እንኳ አያቁም። ሀገር መንደሩ ብቻ እና ቢበዛ ዘመድ የገባበት ከተማ ነው። ሐመሮችንም ጎብኝቶ ያዩትን ሁሉ አማራ እሚሉ የዋህ እንደነበሩ እና ከቡድኑ ሲንቀሳቀስ የሀመሮቹ አንድ በጎራ እሚሄድ ቡድን አንድ አማራ ሴት ስጡን አንድ ሀመር ሴት ዉሰዱ ብለው የቀለዱትን ሁሉ አስታወሰ። በጠቅላላ ያየው እና ያነበበው ገጠሪቱ ኢትዮጵያ የዋህ እርግብ እንደሆነች ነበር። ከጫፍ እስከ ጫፍ። ይህ ህዝብ በስሙ እሚሰራውን አያቅም ያለው የስደተኛው ማስታወሻ ደራሲ ቃል አሁን ይብስ ብሎ በዐዉድአቸው አማካይነት በዝቶ አንቃጨለበት። የመስ ምናብ ብዙ የገጠር ኢትየጵያን አስሶ ከተጠያቂነት ለማጽዳት መጠየቅየለበትም አለ። “ጸሐፊዎች እንደ አሉት በስማቸው ምን እንደ እሚሰራ መች ከቶ ያውቁት አለ በእርግጥም! የከተሜ እንጂ የገጠሬ ስህተት በእኛ አለመዘመን አመክዮነት የለም! ገጠሬ መንግስትን በደንብ አያቅም፣ ቢያንስ ቢያንስ! ግን ከተሜም ማለት መንግስት መስራች ነው እና የመሰረተው መንግስት እንጂ እኛ አይደለንም!” መስ ለሁሉም ተናገረ።

ባለቀጭን ድምጹ ዩሱፍም በዉይይቱ መሟሟቅ ተደስቶ ለመጀመሪአ ጊዜ ክፍተት ያለውን ተመልክቶ ለማሳወቅ ተሳተፈ “ግን እኮ ህዝብ መንግስትን ከአልጠየቀ እና ከአልገፋፋ በመንግስት ተብዬ ተቋም ብቻ ምን መደረግ ይችል አለ? ህዝቡ እሚሻው ስኳር እና ቢበዛ አንድ ጤናጣቢአ ብቻ ነው። መመራመር እሚባል ጽንሰሃሳብ ወይም የቃሉ ፍችው እንኳ በደግ መጠን አይገባውም። ምክንያቱም የህይወት ትርጉም መመራመር እና ዳግጥናት እንደ እማይጨምር ህዝቡ ያስብ አለ። ዕዉቀት ከሂወት ከቶ እሚቆራኝበት ባህል እና አረዳድ የት አለ? በተለየ ከስቶይክስ አንዱ (ምርጡ እና ብቸኛ ባንዲራአቸው) መርህ፦ የቀድሞ አለምን ከመሳል፣ በመሠረቱ መንቀሳቀስ እና አሸንፎ አንፃር እሚመዘን እና እሚደፋ እዉቀት-መር አኗኗር እምብዛም ነው። ከማህበረሰብ ይልቅ ቤተሰብ ልእለ-ጉልበተኛ ነው። ቤተሰብ ደግሞ መረጃ አሥሶ እና ከምሮ ለትዉልዶች እሚያስቀምጥ ተቋም አይደለም። በምሣ እና እራት ጉዳዮች እሚጠመድ ሰዉነት (ኢንቲቲ) ነው። የባህል መድኃኒት እዉቀት እንኳ ከሰው እና ቤተሰብ ሣይዘልል በባዶ የጥበበ ሀገር ፉከራ ህክምናው በታሪክ እየተሰወረብን ነው እኮ! ዉሎ ማደር ላይ መጨነቅ እንጂ ነገን ማሰብ እንደ ግለሰብእ ዜጋ እና ማህበረሰብ አይቀናንም። መንግስት በተጠየቀው ልክ እንጂ ባልተጠየቀው ሥፍራ ጀብደኛ ለመሆን ስለ እማይነግስ በዕዉቀት አሠሳ እና በማህደር ስደራ በጠቅላላውም ሆነ በማሲንቆ ጉዳዩ መመራመሩ አይመዘንበትምም አይገባበትምም። የዕዉቀት አካሄድ እኮ ለእኛ የተከረቸመ በር ነው።” የህክምና ትምህርት ለመማር ከጓደኛው ብሩ ጋር እሚአቅደው ወጣቱ ዩሱፍ በሰጠው ሰፊ ማብራሪአ ዉስጥ በጎኑ ሌላ እንደምታ ስለያዘ፤ ባህል ህክምናውን ሲአነሳ ዓሊን እየአስታወሰ፤ ናሆምን ጥቂት አሳመነ። ግልጽ ነጥብ ነው በእሚል እራሱን ነቅነቅ አደረገ። ‘እና! ዜጋዎች ነፈዝ ከሆኑ ከእነ እርሱ እሚወጣ መንግስት የህዝቡ ነጸብራቅ ነፈዝ ነው በእርግጥ። ያው አመድ እሣት አይወልድም፦ ፍሬው ቢወድቅ ከዛፉ አይርቅም። በቀረአዊነቱ (ዘ ኤግሴብሽን) እንደ ተዓግ. ‘መስራች አባትዎች’ አርቆ አስተዋይዎች መሪ እና ማኅበረሰብእ አስተዳዳሪዎች ተደርገው፣ ሃገርን ለወደፊት ከአነጹ ብቻ ነው ሌላው አማራጭ። ክፉው ነገር ግን መንግስት እኔው እራሴ መሰረት ጥዬ በአንዴ ሃብታምዎች ተርታ አደርግአችሁ አለሁ ባይ ኢኀፍረተኛ-ሞሽላቃ በመሆን ቋሚ ሸዋጅአችን ነው። የቱም የደግ ማህበረሰብ ሃገርአዊ እድገት በአንድ መንግስት ጥረት አልተገነባም፣ መሰረት በመጣል ብቻ ብዙ መንግስትዎች ያልፉ አለ እና! የኛ ሃገር ቢክድ ባይክደውም። በአንድ መንግስት ዣንጥላ ከታደገም፣ ቅድመ-ምጣኔሃብት የባህል-አብዮት አለ። በቀረ አይታደግም። ለምን? አለማደግ የተነበረበት እዉነት ነበር። ሊለወጥ ብዙ ትዉልዶች ወይም ባህል ለዉጥ በአንድመንግስት ዉስጥ ግድ እሚሆን ይሆን አለ ማለት ነው። መንግስትዎችአችን፣ ቢአንስ ከ ኢአዴግ. ጀምሮ ላሳድግአችሁ በማለት ቁምአሸልብ እና ሸዋጅ እንጂ ሌላ አልነበሩም። ዛሬም ድረስ! ምክንያቱም ማደግ አንጎል ሲበለጽግ እና በስርኣት እና በህግ አባትነትአዊነት ሲተዳደር ብቻ እሚመጣ ነው እንጂ ቻይና በብድር እና ሙስና ያስተረፈውን ገንዘብ ወስዳ አንድአንድ ግንባታ አለ ጥራት ስለ እምትሰራልን ማደግ አለ አይባልም፤ ችግሩ እንደ እኛ ነፈዝነት መንግስትም ነፈዝ መምሰሉ እማያዋጣ አላደረገውም እና ቀጥሎበት አለ፤ ስለ ተገቢ መንግስት ስርኣትን የመጣል መነገር ወደ መጨረሻ እናነሳልአችሁ አለን፤’ “በእርግጥ ዞሮ ዞሮ፤ ግን ዋናው ሥራ የመንግስት ነው።” አለ ናሆም ለደቂቃ ያክል ሲአስብ ቆይቶ ሲመለስ፨
ሃሳቡን ቀጥሎ ልክ ሊአብራራ ሲል ጥቁር ፌስታል አጠልጥሎ ወደ ሳሎን ሲመጣ ቢግን ተመለከተው እና ድንገት ተበሳጭቶ በስውር ተቆጣ ው። ቢግ በአገለገልኩ ተቆጣሁ በእሚል ናደድ ብሎ ግንባር በማኮሳተር ተመልሶ ገባ። እሚ ነገሩ ገባት። ናሆም በግሉ መስተንግዶ ሙዝ መጋበዝ አንድ ዕቅዱ ሆኖ መስን ማስደሰት አስቦ ትንሽ ሙዝዎች ናሆም ወደ ገበያ ወጥቶ በማለዳው ገዝቶ ነበር። ወደ ጓዳ ዘልቃ ሙዝዎቹን ከፌስታል በማላቀቅ፣ መምረጥ፣ መቆራረጥ እና ሳህን ላይ መሰተር አግዛው “እንዲህ ነው እሚቀርበው እንጂ ከእነ ፌስታሉ ትጎትት አለህ!” ብላ በማስተማር አዘግይቶ ይዞ እንዲመጣ በማሳወቅ ተመለሰች። በመናደድ ሆኖ ቢግ አላደመጠም ነበር። ከስሯ ኩስኩስ እያለ ተከተላት እና ጭራሽ ሊቀድማት እየታገለ ጠረጴዛው ላይ ደረሰ። መስ ስርኣት ለመያዝ የተደረገው ጥረት ገብቶት በቅንነት ፈገግ ሲል፣ ቢግ በመቆጣት ሙዙን በማዞር አደለ። “ናሆም፣ ትልቁ ልጅ፣ ስለ እሚወድድህ ለመስተንግዶህ ተጨንቆ የገዛው ነው!” አለች እሚ ሃሳቡዋን በልጅ ድርጊት ላይ ንቀት አድርጋ ወደ ጨዋታ ው በመመለስ እየተቀመጠች። መስ አመሰገነ፨
ባቤ ሩቅመቆጣጠሪአ መቆጣጠር ለምዶ አዲስ ጣቢአ ቀየረ። የአዲስ ጣቢአው ድምጽ ከቀደመው ይልቅ ከፍተኛ ነበር። ያስናቀች ወርቁ ድንቅ ቅንብር ለታዳሚ ሲሰራጭበት በቤቱ ጣሪአም አስተጋባ። “ሀገሬ ኢትዮጵያ ተራራሽ አየሩ፤ ፏፏቴሽ ይወርዳል በየሸንተረሩ፤ ልምላሜሽ ማማሩ።” ዩሱፍ ጨዋታውን አስኪዶ ፉት በማለት ቀጠለ። “ማሲንቆ ው ይቅር። የ አስናቀችን ዘመን ሙዚቃ እንኳ መች አጥንታችሁ አስረከብአችሁን። ሁሉ በፊናው ነው እንጂ የሀገርአችንን ሙዚቃ በሙያ ምክር ማድመጥ እና ማስተናገድ፤ ኧረ ይፋ (ፐብሊክ) ማህደር ዉስጥ መክተት እና ለዳግ-አገልግሎት (ሪዩዝ) መች ማግኛ መንገድ አለ?” ናሆም በጥቂት የቆዩ ሙዚቃዎች ፍለጋ ላይ እሚደርስበት እልህ-ገናዥ ትግል ልክ እንደ እጅግ ጥንትአዊ የዝንጀሮ ቅሪት አሠሳ እንደ ሆነበት ድንገት ትዝ ብሎት ለጨዋታው ብቻ ሳይሆን በማህበረሰብአዊ እንዝህላልነትዎችም ጭምር ተናድዶ ለሃሳብ ማከል “ትክክል” ሲል፤ ግን ለመጀመሪአ ጊዜ ቤተሰቡ ሰው ሲጫወት ሳያደምጥ ቀረ። ሁሉም ማያገጹ ላይ ድምጹ አለ ገደብ በሚንቆረቆረው የ አስናቀች ትግበራ በመገረም እያፈጠጠባት ነበር። ‘አዚመኛ አኗኗር! ቦ ጊዜ ለኩሎ ወደ ኩሎ ጊዜ ገጽማያ ዉእቱ የተቀየረበት፤’
ናሆምም ዩሱፍም ተያይተው በመግባባት ለመመሳሰል ተገድደው ወደ ማያገጹ አፈጠጡ። የቴዎድሮስ ታደሰ ሃገርአዊ ዘፈን ድምጹ ተተክቶ፤ ይፋ ምስል ስለ አልነበረው በተራራ እና ወንዝ ምስል አቀናብረው ‘ቅንብር በ አሃዱ ትመ.’ በማለት ጥጋት ላይ የፃፉት ወዲአው ወጣ። ናሆም በግኖ ጥፋቱን አስተዋለ። ጣቢአው በ አስናቀች ዘፈን ላይም ይህን መልእክት አስተላልፎ ስለ ነበር በትንግርት አልፎት ነበር። አሁን ግን ስህተቱ ታየ። በአስናቀች ዘፈን ቅንብር ወቅት ጣቢአው ከቶ አልነበረም። የተፃፈው፣ ግን የሙዚቃ ትርዒቱን ሁሉ በአንድነት ጨፍልቀው ስለ ነበር ለሁሉም ዘፈን መጨፍለቅ ቅንብር በኛ ነው እሚል መልእክት በወጥነት ፃፉበት። ቀጥሎም የመጣው የትእግስት አፈወርቅ ዘፈን እራሷ ደንሳ የምትዘፍንበት ቅንብሯ ቢሆንም ቅንበሩ በእኛ ነው እኮ እሚለው መልእክት ተመልሶ መጣ። ‘ማሰራጨት ቅንብር ም መሰለአቸው፤’ አስናቀች እራሷ መድረክ ላይ ቀለም አልባ ተንቀሳቃሽ ምስል ጥንት አቀናብራ ነበር። ስርጭት እንጂ የእነ እርሱ ቅንብር አልነበረበትም። ስርጭት ደግሞ የትኛው ጣቢአ እንደ ሆነ ለማስመልከት በተለየ አላማ ጥጋት ላይ ሰቅሎ ወይም በይፋ ማስተዋወቅያ ቅጽበት ብቻ ተገልጦ እሚነገር እና እሚረዱት ነበር። ‘መች ይሆን ህዋስ ግዙፍ አካል እንደ ሰራ አምነን ለ ጥቃቅኑ ነገር እምንጨነቀው?’ ናሆም አንድ የተያያዘ ሃሳብ ጨለጠው። ፊቱን ከትመ.ው ወደ ጣሪአው በመመለስ ማጅራቱን ወንበሩ መደገፊአ ላይ አስተኛ እና በእዚህ ተራ ስህተት እልፍ ነገር ሲበላሽ ምናቡ ዉስጥ ልብሳለ (ኢማጅንድ)። ይህ ትኩረት ማጣት እና አይቶ እራሱ መመርመር አለ መቻል፤ ከነ ስህተቱ ማሰራጨት፤ ልዩነት እማያመጣ ትንሽ ነገር ሊባል ቢችልም ከቶ ሃሰት ነው። ግዙፍ ልዩነት አምጭ ነው። የዚህ አፃፃፍ ስህተቱን በቀላል ተመልክቶ በማናናቅ እሚዝናና ሰው ወደ ሥራው ከመዝናናቱ ቀጥሎ ሲገባ ለጥቂት ወይም ኢምንት ነገር መልሶ መጨነቅን ይተውበት አለ። የተስተካከለ ነገር ተጽፎ ብንገለገል ወይም ደግሞ እና ይህን ስህተት አጉልተን ተወያይተንበት ጥንጥዬ መሰል ነጥቡን እንድናስተውለው ቢደረግ፣ የትልልቅዬ አኗኗር ባህል መመስረቻ ሆኖ እንደ ዣንጥላ (ኦቨርአርክ) ለብዙ ነገርዎች ግብዓት እሚሆን ነበር። እንጂ እንደ ትንሽ ተደርጎ ብቻ በመታየት ከተናቀ፣ ልጅዎችም ክፍተት መተው እና መዘናጋት ይማሩበት አለ። ህጸጽ አልባ ስምጥ የሆነ መጠበብ በተግባርዎችአቸው ሁሉ እንዲቀስሙ ከእዚህ ተገቢ መረጃ አሰጣጥ በተለየ ደግሞ ትችት መማር እሚገባአቸው መሆን ነበረበት። ለትንሹ ነገር በመጨነቅ መዝረክረክን መፋለም፣ የሥራን ክቡርነት ይማሩበት ነበር። ሥራ መጥራት እንዳለበት ሲማሩ ደግሞ ሰውን በሥራው ብቻ መመዘን እና ወደ ሰብእአዊ የእርስለእርስ አገነዛዘብ ይመነደጉ ነበር። ግን እንዲህ ያለ ስህተት እሚቆጣጠር፣ እሚተችም የለም። ትንሹ ነገር ለእኛ ብዙ አያስጨንቅም፣ ትልቁ ነገር ደግሞ ከትንሹ ስለ እሚአድግ ብላሽ አኗኗር፣ ከአለቃቃሽ ባህሪ ጋር ጠቅልሎን አለ። ትልቁን መተቸት መልመድ ማለቃቀስ ያስተምር አለ እና። ትንሹ ነገር ላይ ማተኮር ግን ትልቁን ነገር በእራስሰር እንድንካንበት ይፈጥርልን አለ። ለዛ ነበር ሰው ከሰማይ እና ምድር ወደ እራሱ፣ ወደ አካላቱ፣ እያለ ወደ ህዋስ የደረሰው። የትልቁ መሰረት ትንሹ ስለሆነ። ህዋስ ባይጠና መድኃኒት ለአካል አይገኝም ነበር። ይህ ድንቅ አረዳድ ግን ቅፅ (ፎርም) ነው። ስነቅርጹ (ፖተርን) በአኗኗር ሁሉ መዝመት ነበረበት። ትንንሹን በመስመጥ መገንዘብ እና መተቸት ወደ ዘርፈቀለምአዊ (መልቲከለርድ) አኗኗር ወለል መፈናጠጥ ይቻል አለ፨
ይህን አስቦ ናሆም ከምናቡ መነጋገሩን ሲቋጭ፣ ዞሮ ሁሉን ተመለከተ። የማንም ትኩረት ከእሚቀርበው ድንቅ የሙዚቃዎች ኪን አልተመለሰም ነበር። የጣቢአው ስህተትም። ናሆም በመነሳት እቃዎች በመሰብሰብ ለዳቦ ቆረሳው ዝግጅት እራሱን ጠመደ። ማድቤት ጎን ባለማጠቢአ ጣቢአ ዉሃ በስምጥ ሳፋ አድርጎ ቁስዎቹን ለመታጠብ እንዲቀልሉ ዘፍዝፎ ወደ ሳሎን መቁረሻ ቢላዋ ፈልጎ ተመለሰ። እሚመለከተው ያፈጠጡ ተመልካችዎች እንጂ ከትመ.ው ቀድሞ ፍልቅልቅ የነበሩ ተጫዋቾችን አለመሆኑ ቀጠለ። ወዲአው የአስናቀች ዘፈን የሃበሻ ቀሚስ ለብሳ ስትዘፍን በተለመደ የስርጭት ስህተት ተመለሰ እና በገጽማያው መሮጥ ጀመረ። ማፍጠጡ ግን፣ ማስተዋል አብሮት የለውም። ናሆም ፈገግ ብሎ ዳቦው ላይ አተኮረ። የገጣሚ እና ክፉልብ ባለቤቱን ገጣሚ አንድ ግጥም አስታወሰ፦ አስራአምስት አመቶች አካባቢ በፊት አንድ ትመ. ጣቢያ በብቸኛነት ህዝቡን ሲያቀውስ ዉሎ እኩለሌሊት ሲሆን ስርጭቱን በብሔርአዊ መዝሙር ይደመድም ነበር። ይህ ኢትመ. (የኢትዮጵያ ትእይንተመስኮት (ኢቲቪ)) አቀዋሹ ትመ.፣ ከተመልካችዎች ትግስት አይገባው የነበረው፣ ስርጭቱ ሲቋጭ፣ ‘ጣቢያው ሰልችቶት እራሱን አጠፋ!’ እሚለው የገጣሚው እይት ድንቅ ነበር። ይህን መሰል ሁኔታ አሁን ካለ አስተዋለ። ሁሉም እሚያፈጠው ትመ.ው እራሱን ስላልዘጋ ነውን? ለአዎንታአዊነት መርኁ ሲል፣ ምንም ሃሳብ ሊአጨፈግገው ሲመጣ ቀና ንጽረት ይሸልመው አለ። ‘በርግጥ የ አስናቀች ዘፈን እንደ ዘመኑ ዘፈን ሀገርአቀፍ በተለይ ማዕከለትዉልድአዊ (ኢንተርጀነሬሽናል) እውቅና የለውም እንጂ ድንቅ ትግበራ ከደግ ሙግ. ስንኝዎች ጋር ይዞ ይንቆረቆር አለ።’ ናሆም ለቀናአዊ የድባቡ አረዳድ የነቀሰው ነጥብን ለራሱ ነግሮ፣ የባይተዋርነት ኩነቱ አግዞት ዳቦዋን ከርዝራዥ ብስል ኮባዎች አጥርቶ በማጸዳዳት የቤተሰቡን ሁኔታ ዳግ-አብሰለሰለ። ‘የዘመኑ ቀመር የዚህ አይነት ሁኔታ ሲአቀርብ፣ ተቀምጦ፣ ሙሉ ልቦና ዉስጥ ሆኖ ትርዒትን መቀበል ነው። ወይ ደግሞ መሳሪአውን አጽልሞ፣ ኢቁርፍድ ሰብአዊ ግንኙነት ላይ ግልን መሰካት ነው። በቀረ፤ ‘ሁሉን አዳኝ ሁሉን አብካኝ’ነት ተገባበት፦ ኢአስተዉሎትአዊ ዝግጅት እድመት አንጀት አያረሰርስ፤ በልጨዋወት-ወይስ-ላድምጥ መንታ-ልብ መታደም፣ መረጃ አዛብቶ (ወይም ጫፍጫፉን መቀንጠስ ከውኖ) ጥራዝነጠቅነት ማፋፋት እና ዜሮ ተብላሎት (ኢንተርናላይዜሽን) ላይ መፈንገል ነው። አሊያም ቅዱሱን የሰብእአዊ ግንኙነት በግማሽልብ ማርከስ ነው። ሁሉም እርግማን ነው፤’
የ ቤተሰቡን ሁኔታ ወደ ጨዋታ እና ድፎ ሊመለስ ሲሰናዳ ሁኔታአቸው ናሆምን አረጋግጦ አሳመነው። የአክሳሪ ሁለት ጥረትዎች አጣብቂኝ ረብቦ አለ። ወደ አንዱ የማተኮር አቋሙ ግን፣ ለጊዜው በእሱ ደንብ አውጭነት እሚተገበር አይደለም። እራሱን ግን መርቶ ነፃ ማውጣት ይችል ነበር። ወደ ሙዚቃው አተኩሮ የአስናቀች ድምጽ ማጀቢአ ከበሮውን፣ ጭብጨባውን፣ የእናትዎች እልልታውን፣ የመድረኩን ግርማሞገስ፣ የዘመኑን ግለሰብእዎች ሞገስአዊ ህላዌታ (=የነገረ ሰውነት አኳኋን ሁኔታ)፣ ከትመ.ው አሽከርነት እርሱም ፈጥጦ በማተኮር በስሜት ህዋስዎቹ ሰብስቦ መጠጠ። አጣጣመ። ‘ድንቅ የሙዚቃ እና ህላዌ ዘመን፤’ ቀጥሎ ግን፣ ጫጫታ እና ኹካታው በሆነ በአልሆነ ሲነሳ እና አንዱ አትኩሮት አልነግሥ ሲል ጥቂት ለወረቱ እርዳታ አሰበ። ጮለቅን ከእሚ እቅፋት ወርሶ ወደ በረንዳ አወጣት። የፀሐይ ብርሃኑ ዓይኖችዋን ሲዳስሰው ኩሩ ፊትዋን አጥበረበራት። ወዲአው አዲስ ከባቢ አየሩን ለመታዘብ ሰግላ ዓይንዎች ላይ በመጨከን ብርሃኑን ሳትለምድ ገላልጣ ሾፈች። ወደ ዛፍዎች እና ሰማይ ማስተዋል እና መመራመሩን ግሏን ሸጠችበት። የሽዉዉታ ድምጽ ለበለጠ እምቅ ምርኮ ፍለጋው አንገት አሥሰገጋት። የተደሰተች መስላ ወደ ታዛቢ-ሀሴተኛነት ተለወጠች። ወንድሟ በደስታዋ ማስተዋል ፈገግታ አበቀለ። ዛፍዎች እና አዲስ የዓይን ግድግዳው ሁሉ፣ የጀብዱ ቀዳዳ ሆኑባት። ‘የሰው መሆን መሰረት እና ጉልላቱ፤ ቀለምዎች፣ ቅጥዎች (ዳይሜንሽንስ) እና ድምጽዎች የመኮምኮም ስሜት እንጂ ምን የቀረ አለው? ቀለም አለመለየት፣ አግጣጫዎች ዉስጥ ቅርጽ አለማድመጥ ድምጽዎች አለመፈተሽ…በሰው ቢኖሩ ሰው በከፊል-ኢህላዌ አለ። ሰውመሆንን የናሆም አንጎል እነ እዚህን አስልቶ ሲረዳው፣ የጮለቅ ቅርጸ ሠዉነት፣ ቀላ እሚል ቀለም እና ሰማይአዊው ልብሷ፣ ከመዓዛዋ ጋር ወደ ልቡ ሰረጉ። ዉብ እና ተወዳጅ ታናሽ እህትን አንጎሉ ተረዳ። በስሜቱ ፍቅር ፈለቀ። እጅግ ጨቅላዋን አፈቀረ እና በሰዉነቱ ከፍታ እንደአደረጋት በድንቅ ድድንገቴ ቅጥ እየተወዛወዘ ወደ መሀል ጊቢው አደረሳት። በደስታው ተጨማሪ ደስታ አግኝታ የከባቢውን ዉበት አደመጠች። ዞር ዞር እያደረገ ከባቢው አጫዋችነቱን እንዲወጣ መጋበዙን፣ ከተጨማሪ የራሱ ዝምማለት እና የማስደሰት ብቻ መስተንግዶአዊ ዐጀብ ጋር ቸሮአት አገዛት፨ ‘ድምጽ፣ ቀለም እና ቅርጽ የሂወት አረዳድ አብዛኛው ክፍልአችን ከሆነ፣ የሰው ፊት፣ አካል፣ አቋቋም፣ ድምጸት፣ በማስታወስ እህት ከባዳ መለየት ከተቻለ…ቤት እና ቁስ፣ ዛፍ እና መንገዱ…ብርጭቆ እና በሬው…በቅርጽ፣ ቀለም፣ ከተለያየ…የ ገሃድአዊ ስነፍጥረት መክፈቻ ይህ ከሆነ፣ ለምን የእልፍ ድምጽዎች፣ ቅርፆች እና ቀለምዎች ደልስፍና ሳይጠና ቀረ። ለምን ህዝብ እሚያውቀው መሠረተ ህይወት አልሆነም? ለምን ኪነህንፃው፣ ምህንድስናው፣ አልቀለለንም? ምንአልባት ይህ የህይወት መሰረትነቱ ስላልገባን…መነሻው ስላልተጨበጠን እየሞለጨን ይሆን!’ ጮለቅ ተደስታ ትዝብቷ ወደ ትምህርት ዞረ። ወደ ከባቢውን መልመድ። ከእንግዲህስ እማውቀው ስፍራ ነው እምትል ይመስል ወደ መልመዱ መጣች፨

ከ ሰዓት ኋላውን ለህፃንዎቹ ትመ.ው ተትቶ ዐዋቂዎቹ በደመቀ ጨዋታ ዳግ-መጥተው ዋሉት። አዲሱ ድባብን፣ እነ ጠላ እና የሃሳብ ገልጋይነት ምትሃቱ፤ በመስ የተቆረሰ የድንቅ ኢትዮጵያአዊ የድፎ ምቾት፤ እና የሆድሆድ ማውጋት ጨዋታዎች ለነብስ መስተንግዶ እንዲሆን አብቅተው አጋሉት። በመጨዋወቱ የሂወት የመጀመሪአ እና መንገድአዊው ቃና፦ ሰብእአዊ ፍቅር፣ ተሳስቦ በእየመሀከልአቸው ለሁሉም ተከፋፈለ፨
ድህረእኩለቀኑን ሸኝተው ፀሐይ መዛል ጀመረች። ሁሉም እኩል በጨዋታው ዝሎ ከሣቅ እና ለዛ ለማረፍ ደግሞ ፈለጉ። አብዛኛው ዐዋቂ ከኹካታው ልጓም መያዝ ጋር ተያይዞ፣ የነፃ ጨዋታውን ተከትሎ፣ ነብሱ ቅልል ብሏት መርካቷ ሲታየው፣ አንድ ነገር እንዲረዳ ተጋበዘ። የታመቀ አንጎል እንደ ነበረው እንዲገነዘብ ሆነ። ጨዋታ ሞቅ ሲል እና ሁሉ ሲሳተፈው ፍርሃት አጫጅ፣ ሐሴተህላዌ ፈንጣቂ ነው። ይህ ምትሃት ታይቶ፣ የሆድሆድ ከሆድ ብዙ አራግፎ ባዶነቱ የህላዌ መገጣጠምን አምጭ ሆኖ መደሰት ምንጩ በእዛ ተገኘ። መንጠራራት እና መጨዋወት ከእረፍት ጋብታ ጀርባ መጣ። ለእየፊናውም መዝናናቶች ቀጥሎ፣ አሁን ደግሞ ጊዜ በቀለ። ዉጭ ተገኝተው ደግሞ አየር ለመተካት እንዲችሉ፤ እግረመንገድ ከመስ ጋር ትርክት-አስይዘኝ ሊባባሉ (ቱ ካች-አፕ) ናሆም ቀጥሎ አሰበ። ማሰናዳት እንጂ መጠጣቱን አበክራ ስለማትችል፣ እሚ ደግሞ በገዛ ጠላዋ መጠነኛ ኩምኮማ፣ አናትመናወዝ አጊንታ ወደ ብቸኛው የቤቱ ማረፊያ-ክፍል ስለሸለብታ ተለየች። እነዩሱፍ በአዲሱ የዩሱፍ ሰቤ (አንድሮይድ) ተስ. እሚአራውጡት የበይነመረብ መስተንግዶ መስጦ በአዲስ አጥር ለይቶ አቀፈአቸው። የቀሩት ታናናሾች በትመ.ው ላይ በትጋት የማፍጠጥ ዕድሉን በበቀለው ጊዜ ወረሱ። የትመ.ውን እና ልጅዎቹን ግንኙነት ነገር፣ ናሆም እየአጤነ ተቀምጣበት ሸለብታ የሰረቃት ጮለቅን በመከዳው በጥንቃቄ አኑሮ ጢዩን ጠርቶ ምንጣፍዋ ላይ ተዘርፍጣ በጎኗ እንድትጠብቃት አስረከበ። መስ ጎን ወንበሩን ስቦ ተቀመጠ። ወጣ ቢሉ እንደ እሚሻል ሊናገር ሲል መስ ድካም ያሳየ መሰለው። ጠረጴዛው መሃል ቢግ ካኖረውን የጣሣ ቡድን አንድ መዝዞ በመገልበጥ ጠላውን እስከ ወገቡ መቶ ሚሜ. እሚሆን አንቆረቆረ እና በተነሳበት ብርጭቆ ምትክ አድርጎ ያዘ። ዝነኛው እይት አስተናጋጅ፣ በሃገርአችን የትመ. ዘርፉ ምንአልባት ከሁሉም እረዥም የ ትመ. ህላዌ አስፍቶ የገጽማያዎች ቤተኛ የሆነው እና ደግ የመዝናኛ እይት አሳላፊ የሆነው፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ቁምነገረኛ ግለሰብዎችን አብዝቶ በመጋበዝ ሃገር አንፋሽ (ኢንስፓየረር) የሆነው፣ ዐዋቂ ጋብዞ በትሁት ስብእና ሲአስተናግድ ለታታሪ ህይወተኛዎች እርካታ የሆነው፣ ይህ የትመ. ገፀባህሪ ው ባፈጋጊነቱ የእማይሰወር እየሆነ የነብስ-ዝማኔውን አንድምታ እሚሰብክለት፣ ሰይፉ ፋንታሁን በ ኢቢኤስ ጣቢአ እሚአሮጠው ዝግጅቱ ሙዚቃዎቹን አልፎ ተተካ። መጋቤ እና ሊቀምሁርዎች (ዶክተር) ሮዳስ ታደሰ ቀርቦ እየገስተናገደ ነበር። የጊዜው ሳቢስሜት (ሰንሴሽን)፣ የታሪክ መመዝገቢያዎች መርማሪው፣ ጉያው ዉስጥ የከተተው ቅዱስ እሚሰኝ ሊቀደቂቅ አብሮት ተቀምጦ ተዋወቀ። አንፋሽአዊ (ኢንስፓይሬሽናል) የዕውቀት አደና ትትረትዎችን ለተመልካች ሁሉ የአምስተኛ ክፍሉ ሊቀደቂቅ ከ እራሱ ምሳሌ እየጣፈ ሰበከ። ሰይፉ መደመምን ሲአደርግ፣ “ትክክልኛ ለውጥ እንዲመጣ ከተጠየቀ መልሱ በህፃንዎች ላይ እንስራ ነው!” በእሚል ሊቀምሁርዎቹ ሊቀደቂቁን አግዞ ጨመረ። እና ስለልጆች በዕዉቀት መኮትኮት የጋለ ፍላጎቱን አብራርቶ አከለበት። በወንበሩ ተለጥጦ ዘና ያለ አቀማመጡ ላይ ተንፈላስሶ፤ በመላጣነቱ እሚቀልደው እይት አዘጋጅ እና አሳላፊ አሁንም እየቀለደ፤ ቁምነገር ማዋዛቱን ቀጠለ። ወደፊት ኢትዮጵያ በሊቅ ወጣትዎች እንድትገነባ ዛሬ ለልጅዎች ከመደበኛው ስርአተትምህርት ዘልሎ ማስተማር ይገባ አለ በማለት ካደረገው እና “ኢምንት ጥረት” ካለው ልጅዎች እና ትዉልድ በዕዉቀት መቅረጽ፣ በላጭ የሆነ ትትረት ከንግዲህ በሚመጣው ጊዜ እንደ እሚአመጣ ሊቀምሁርዎቹ በመቀጠል አሳወቀ። ሰይፉ ዕዉቀት በዞረበት ያልዞረ እንደሆነ ከቀለደ በኋላ እንግዳውም ይዞ የመጣውን በሃገር-ደረጃ የእንወቅ ጭብጥ ማስሠበክ እና መስበክ ቀጠለ፤ የኢትዮጵያ ጥንትአዊ ስልጣኔን ደግ ጫፍ አይቶ እንደነበር በቁጭት ሆኖ እየተፀጸተ አብራራ። “በተለየ፣ ስለስነፈለክ የነበረን ስኬት ድንቅ ነበር!” ምስክርነት ሰጠ። የዓለም ሁሉ ጎህዉጪዎች ሆነን እንደነበር፣ ለተቀሩት ጥንትአዊ ስልጣኔዎች የስነፈለክ ድሮአዊው ጥናትአችን ዐብነትአቸው እንደ ነበረ፣ እና ግሪክአዊው ፕሉቶሚ ከሰበሰበአቸው የክዋክብት ካርታ ጥናትዎች መሀከል ወጣኝዎቹ ጥሬ-ግብዓትዎቹ የኢትዮጵያ ግርማአዊዎች (ሮያልስ) የቆረቆሩት ጥናትአዊ አሠሳ እንደ ነበር ከድምጸት ጋር ተናገረ። ቀጠለ እና ወደ እዛ የምድርን ፈር የቀደድንበት ስነፈለክአዊ ኀያልነት እንድንመለስ፣ ያቅሙን እንደ መፍቀሬ ሃገር እንደ እሚታትር ደግሞ በመግለጽ አሠመረበት። ስለጊዜ አገነዛዘብአችንም ስምጠት እንደ ነበረን የሰከንድ ስምጥ ክፍልፋይዎችን እነ ካልዕኢት፣ ሣልሲት፣ ራብኢት፣ ሀምሲት ወዘተ. ብሎ በመዘርዘር ቀጠለ፨
ናሆም በእርጋታ እንደ አለው እና በሃሳብ ስርገተስሜት-አዊነት (ኦቨርዌልም-ድነስ) ሳይገጥመው፣ ኀላፊነት ወሳጅ ብቁ ህላዌ ላይ እንደ ሆነሆኖ ከጠላው ፉት እየአለ ከአደነቀው ጥረት ተያያዥ አስተያየትኤ ሰነዘረ፨
“ሰሞኑን ባለፈው ‘አማርኛ ቋንቋ ዉስጥ እሚነሱ ጥያቄዎችን አንዴ እንዲለይላቸው ጎትጓችዎች አሉ፤ በዐዉዱ የምናብ ሥፍራህ ምን ይልአቸው ዘንድ ያለ ነው?’ ተብሎ ጥያቄ ሲቀርብለት በከቶ ኢስልጡን ስድብ ተማትቶ ነበር ክርክርቴውን የመለሰው፤ ያጠነከረው፤ እና የዘጋው።” ብሎ መስን ተመለከተ። መስ ትመ. በማድመጥ ትኩረት ላይ ነበር። ናሆም ጠላ ተጎንጭቶ መስንም ጋበዘ። “ያዝ!” ጣሣ አጋጩ፤ “ያዝ!”፤ ተጎነጩ፤ ናሆም ቀጠለ፨
“አሳፋሪ ነጥብ ደግሞ አከለበት እና የለየለት ግለሰቤያዊነቱን (ፐርሰናልአይዜሽን) ጭራሽ አጎነው። ከጥንት ጀምሮ በቋንቋው እልፍ የዝማኔ ጥያቄዎች ይሰነዘሩ ነበር። የተመዘገቡት የአማርኛ ላይ ጥያቄዎች እንኳ ትዉልዶች የቀደሙ ነበሩ። አሁንም አንድ ዣንጥላአማ (ኦቨርአርኪንግ) ዉሳኔ በይፋ ይሰጥበት፤ ለቋንቋው በቀጥታ እሚጠየቁ እና ቤተእንደራሴአችን ይህ ኢወሳኝነት እንዲቋጭ፣ አንድ-ይበሉበት ስለተባለ እንደ ተለመደው ወደ ጢሻ እሚሸሽ ሃሳብ ወረወረ። ‘ፊደልአችን በሞግሼዎች ቢገጠገጥም ሁሉም በእየፊናው ፍች አለው፤ ይህን እሚሉት አሉታአዊ አቅም (ነጌቲብ ኢነርጂ) የረበበባቸው ናቸው፤ ሲጀምር ደግሞ እሚአውቁት አንድም ነገር የለም! እኛ ግን እናውቅም ማወቅአችንንም አያይዘንም እናውቅም አለን፤ እነሱን አትስሙ፤ ባለፉበትም ከቶ አትለፉ፤ እኒህን ሰዉዎች አግልሉ፤ እኛን ጠይቁ፤’ በማለት እንደ ክፉመጠን የለየለት መሃይም አብራራ። ጓደኛዬ በብሔርአዊው ጣቢአ ኢትመ. (ኢቲቪ) መዝናኛ አየሁ ብሎ ያን ሲጠቅስ አላመንኩም። ሲጀመር በቱልቱልቴ (ፕሮፓጋንዳ) መናኸሪያው ኢትመ. የተላለፈ እሚታመን የለም በርግጥ። ኋላ ግን ያልተማረው ሃገር ብዙ ትመ ጣቢያዎች ቢይዝም እሚደረግበት ከቶ ምንም ስለሌለ፣ የእድገትበህብረት ዘመቻ ወቅት ይህ አቅም ቢኖር ምን ይደረግ እንደነበረም ስላልተሳለልን፣ እይቱ ብዙ ዳግ-ስርጭትዎች (ሪ-ረንስ) አገኘ። እና በአንዱ ተመለከትኩት። እጅግ አሁን ከሰማንው መቆርቆሩ ጋር ኢወጥ እና እንከንየለሽ-አሳፋሪ መልስ የሰጠበት ነበር።”
መስ ቦዝ እያሉ ስለ መጡ ሙሽሽ ያሉ ዓይኖቹን አብልጦ በቆዳአቸው በመጠቅለል ወደ ቅሉ አሰመጠ እና አጠበበአቸው። ሰመጥ ያሉ ሃሳብ ናሆም ባለው ላይ ከወነ። ትመ.ው ላይ ሲዞር ሊቀደቂቁ አንጎልአዊ ዋጋውን እየአስመሰከረ እና አድማጭ ሰይፉን እያስፈራራ ነበር። መስ ወደ ናሆም ዞረ እና ከአቆመት ጥቂት ቀጥሎ አብሰልስሎ ጉሮሮውን ሞረደ። “ተገቢ ነው ያለው እኮ!” ብቻ ብሎ የሠመጠ ሃሳቡን ጠቀለለ እና ጠላውን በደንብ ተጎነጨው። ናሆም በጠቅላላ አስተያየትኤው ኢተገቢነት እና እስከ አሁን ያ ብቻ ሊባል ታሰበ መሆኑን ሲረዳ ፈገግ አለ። “አስተውል፣ ወታደሩ ሰው ! የተባለው ሁሉም የኛ ፊደልዎች ፍች አላቸው ህዝባር የላቸውም አይደለም። የተጠየቀው፦ ካላቸው፣ እሱም አላቸው እንዳለው፣ ፍች እንዳላቸው እሚነግር ብሔርአዊ ጥናት ተከዉኖ ከትምህርት ስርአትአችን ጋር ተጣብቆ ተገቢ ጥቅም ለትዉልዱ ይስጥ ነበረ። ከሌለው (ወይ ደግሞ ኖሮትም ጉልህ ጥቅም ከ አጣ) – አማርኛ እና ግዕዙ ገበታ በነገርአችን ይለያይ አሉ፤ ለግዕዙ ፍች ካለ ለአማርኛው የግድ አለ አይደለም – ይህ ገሃዱ ይገለጥ እና ብቻ..ብቻ ምንም ይሁን መልሱ ምን በይፋ ግን ይለይለት ነበር። ወጥነት ማጣቱ፣ መነታረኩ፣ ያብቃ ነበር የተባለው። አሁን አማርኛ ላይ ያለው እብት የነገ ሃሳቢ አድበስብሶ እሚያልፈው አይደለም። እሚሟገትለት እንጂ። ምክንያቱም፣ ልክ ኦሮምኛ ቋንቋ በግዕዝ ገበታ ይፃፍ እንደ እሚባለው ቢፃፍ ለ ኦሮምኛም አራት አምስት “ሃ” ይግባለት እንደ ማለት ነው፤ ለአማርኛም የግእዙን ማስቀጠል። ኦሮምኛ ዉስጥ ያ ሁሉ “ሃ” ምን ይሰራ አለ? ያ ከተባለ፣ ነጥቡ ግን፣ ላማርኛውም ያው ነበር። የግዕዝ ፍች ወደ አማርኛ አላግባብ ማቀላቀል አለ ይባል አለ። አማርኛ ያልተጠቀመበት የግዕዙ ፍቺ ቢኖር፣ እርባና ለጥያቄው የለም። ግዕዝ ስታጠና በቀር። ለእየፊደሉ ፍች ያበጀውን፣ በትክክል ማለት ነው፣ የግእዙንም ጉልበት እያደበዘዘበት ነው፣ ይባል አለ። የሆነው ሆኖ ግን፤ በብሔርአዊ ጥናት እና ምርምር ይጠና እና ብቻ መነታረኩ በብሔርአዊ ዉሳኔ መስመር እንዲይዝ ይለይለት ነው አልኩህ። ስሜት ሰጭ በሆነ ስልጡን ፊደልአዊ ጎዳና ዝማኔ እናብጅ ነበር የተባለው። እርሱ ግን ‘ፍች አላቸው፣ አይነኩም!’ ብቻ ብሎ እንደ ፉርስ (ኢራን) ቋንቋ ሆሄዎች፣ አጥንት እንደተሰነቀረበት ጉሮሮ በትልቅ ትግል እየአከ “ሀ” እና “ኀ” ልዩነት አላቸው ብሎ የመጀመሪአውን ‘ሀ’ ያው ‘ሀ’ ነው ብሎ አንድኛው ሞክሼ ላይ ጉብ ብሎ ዘለለበት። ሌላዎቹን ሀዎች ረግጦ፦ ‘ኀ’ ደግሞ ‘ክሃ’ ነው በማለት አስፈሪ ድምጽ ሰጥቶ መለያየቱን አበሰረ። ዋና ነጥቡን ዘልሎ በማሽቀንጠር በሰፊው ወዲያው መሳደብ ጀመረ ከዛ።” መስ ፈገግ ብሎ ብዙ ለ አለመሳቅ የስር ከንፈሩን ነከሰ። ናሆም ም ሳቅ ብሎ ፈሳሹን ተጎነጨ እና ቀጠለ “እሚለያይ ድምጸትአዊ ፍች በግዕዙ አላላቸው ይባልአለ – በእርግጥ። ነገሩግን፣ ያ ጥያቄ ው አይደለም – ሲጀመር። አለ ይባል አለ – ያ ይታወቅ አለ። አይረባም ላማርኛ ደግሞ እሚባል በሌላ ጎን ያለ መናቅ የሌለበት መልስ ፈላጊ ክርክርቴ አለ። ስለ እዚህ እንዘምን እና አብረን እ ጥበብዎች በመጋራት እንራመድ እና ቀጣዩን ነጥብ እንከራከርበት ነበር ጉዳዩ። ማለትም ከስነፍሬነገር (ሰብስታንስ) ይልቅ የዝምን አረማመድ ስነሂደትአዊ ነጥብ ነበር የቀረበው። ነጥቡ ይጥለል እና በተጠና ዉሳኔ አንድ ደረጃ ላይ ይደረስ፣ መላ-ይመታ እንጂ ሌላ አልተጠየቀም እና። ደግሞ ባነሳው ዝብ-ሃሳብ እራሱን እንዳልኩህ መዝነው። እሺ ጥንትአዊ ግዕዝ ገበታፊደል ዉስጥ፣ ሞግሼ ፊደል ፍችው በድምጽ ተለያይቶ ከነበር፣ ጉሮሮ እየአከከ “ኀ” ን “ክክሃ” ማለቱ ባማርኛ የትኛውን ቃል እንድንጠራ ዛሬ ላይ አጋዥ ነው? “ዉኀ” ብለህ ፃፍ ይሉህ አለ። ዉሀ/ዉሃ/ዉሐ/ዉሓ/ዉኃ/ዉኻ ብትል ልክ አይደለም ይሉህ አለ። ለምን ስትል ‘ኀ’ ‘ክክሃ’ ነው ሊሉህ ነው። ግን ከሰባቱ ኋኝነትአዊነትዎች እንዴትም – ለ ምሳሌ አክብረህ – ፃፈው፣ “ዉኀ ልጠጣ” አልክ ማለት ነው። ሲነበብ ያው ‘ዉሀ ልጠጣ’ እንጂ “ክክኀ ልጠጣ!” ወይም “ጠላ አልጠጣም” እሚል አይሆን! ግን ነፍስወከፍ ፍች አለው ብሎ በተለመደ ዳርዳር አግበስብሶ ማለፍ ነው ወይስ ካለውም ከሌለውም አንዱን አጥርተን በመወሰን ነገ ይህ ጥያቄ በጨቅላ ህፃናት ተደግሞ እንዳይነሳ ወደ ተጨባጭ ዝመና በእዚህ በእኛ ቀን እንግባ? ተገቢው ጥያቄ ሁለትኛው ነበር። ዝብ-ፍቅረ-ሀገር-አረዳድ ነው አንዳንዴ ደግሞ። እንደ ሀገር በጉዳዮች ተወያይቶ መላ በመዝጋት ወደ ፊት መራመድ የለም። ገና ፊደል ላይ መቧቀስ ካለ ስንት ጉዳይ አስሠን ተወያይተን አለን? ስልጣኔ ደግሞ በእነዚህ ነጥቦች ማደግ እና ወደ ቀጣዩ አፋፍሞ ለፍልሚያ መግባት ነበር። ይህ የተሰወረበት ምን ቢሀለን ነው?
“እንደ ምሁር እምትቀበለው እና እምታካትተው ከሆነ ደግሞ በምሁርአዊ መስፈርቶችም የረከሠ ዉጉዝ ነጥብ አንሺ ነው። የሱ ክርክርቴ ዝብ-ህፃጼ (ሚሲንግ ዘ ፖይንት ፋላሲ) ብቻ አይደለም። ምታ-ሰብእ ህፃጼ (አድ ሆሚነም ፋላሲ) ሁሉ አለበት እና። ያ የልቀት-ዓለም ዉጉዝ ከመ መሀይም እርጉም ከመ ሌጣ ወረቀት አስባይ ህፃጼ ነው። ነጥብ ያመጣን ጠያቂ ነጥቡን መንካት እና ከቻለ አሸንፎ መመለስ ሊቅአዊ ባህል ነበር። ወይስ ነጥብ አምጭውን በስነልቦና መጨርገድ እና ነጥቡ እሱ ያነሳው ስለሆነ ብቻ ስለዚህ ስህተት ነው ማለት በተገቢነት እሚጠበቅ ነው? ሦስትኛ ህፃጼው ደግሞ ንጽረተ-መሪ ህፃጼ (አፒል ቱ ኦቶሪቲ ፋላሲ) ነው። እኔ ስለ እማውቅ ሃሳቤ ምንጊዜም እፁብ-ትክክል ነው፣ ባይነት ነው። ያም ስንፈተ-ሊቅአዊ እሚባል ነው። እንጂ የኔ ሃሳብ አመክዮው ጠንካራ ስለ ሆነ እሚሻል ነው ዜሮ ነው። በተለየ ከሊቀምሁርዎች እነዚህ ድሃ-ህፃጼዎች ተከማችተው በ አንድ ነጥብ ላይ ሲገኙ እና ነጥቡ ብላሽ ሲሆን አሳፋሪ እሚል ቅጽል ፍችውን መሆን እሚችል ነው፤ ከሩቅ አላሚ አይጠበቅም።”
መስ ናሆም ባቀረበው ሃሳብ በእርግጥ ህፃጼ ሊወጣ እንደ እሚችል ገመተ። የልክነት ጎራ እንጂ፧ በቅናሼነጥብ (ዲዳክሽን) ወይም ሽቃቤነጥብ (ኢንዳክሽን) ነጥበሃሳብ (ፕሬሚሲስ) አላጎነቆለም ነበር። መስም ድጋፉ ከላይከላይ ታይቶ የተሰነዘረ ነበር። በመረታት ግን አለመሸነፍ ስሜት አናቱን ለመስማማት ያክል ወዝወዝ አደረገ፤ ጉንጭዎቹን ባዲስ ጠላ ወጠር አድርጎ በብርጭቆው ስር እየተመለከተ። መስ፣ ናሆም ጎን ሆኖ በመከራከር እና መወያየት የተማረው አንዱ ጥበብ በ ዉይይት እና ክርክር፣ ማመን እንጂ መረታት እንደ ሌለ ማስተዋል ነበር። እሱ የአነሳው ነጥብ በናሆም ቢረታበት የአምን አለ እንጂ ተሸናፊነት ስሜት በመያዝ አይጎዳም። አንድም ስሜት ጋር መጣበቅ አንድም ቀጥሎ አለመወያየት ይጠነሰስ አለ። ናሆምም ፍጹም ትክክል ሃሳብ ዉስጥ እንኳ እሚመራ እንጂ እሚዋጥ አይደለም። አሁን የረትታ የመስ ነጥብም ነገ ሊሻሻል ወይም ሊቀየር ወይም ተሸናፊ ሊደረግ እንዲችል አንድ ነገር ሊፈጠር ይችል አለ። ስለእዚህ የመርታት ስሜትም በእርሱ ዘንድ አይኮተኮትም። መስ ስለ እዚህ የእርሱን የተረታ ሃሳብ ሲተው እና የናሆም ሃሳብን ሲቀበል በልክ-መሆን የተሻለ በእሚል እንጂ ‘ፍጹምነት ላይ በቃ’ በማለትም አይደለም። ይህ፣ ሃሳብዎችን ግለሰቤአዊ (ፐርሰናል) እንዳያደርግ ረድቶት አለ፨
“እና እሚሰራው ሁሉ ገደል ገባ በለኛ!” ጉዳዩን ለመጨረስ ያክል፣ በማያገጹ ከትንሹ ጭንቅላትአማ ልጅ ጎን በስስት ተቀምጦ እየአየው ያለ ምሁርን ተመልክቶ የተቀዳውንም ለመጨረስ የአክል ፉት እያለ ጠየቀ። “አይመስለኝም” ናሆምም አብሮ ተጎነጨ። ሌላ ዙር አንቆረቆሩ እና ዘና አሉ። “ልጅዎች በመገንባት ማመኑ እና ዕውቀት መሪ ማኅበረሰብእ እንድንሆን መሟገቱ እንከንየለሽ፣ ‘ቀን አላፊ ቀን አግዛፊ፣’ እምለው ትትረት መሀከል ነው! ግን አንድም እሚመጡት ምናብአማ ታዳጊዎች በእንከን የለሽ ቋንቋ ማደግ ቢችሉ ተገቢ ነው። እናም፤ አማርኛን ማዘመን አንተን ካከሉት ዐዋቂዎች ንጽጽር ሳይሆን ገና ሀሁ ካልቆጠሩት እና ሃያ ዓመትዎች ጀርባ ሃገሩን ከሚረከቡ” ወደ ሊቀደቂቁ እየጠቆመ፣ “እንደ እነዛ ከአሉት ታዳጊያን አንፃር መታየት ያለበት ጉዳይ ነው። እንዳለው ዉኀን “ክሃሃ” ማለት ካለብን ቶሎ ያስተምሩን። ከሌለብን አማርኛን አቅልለንው አመቺነቱን እንደላደልበት እና ዝማኔ እንቅመስ” “ከእነ ጮለቅ አንፃር በእርግጥ ፍቱን ምናብቴ (ፋንታሲ) መሰል መላምት ነው።” አለ መስ በመገረም ሆኖ “አዎን ከእነ ጮለቅ አንፃር ማየት ተገቢ ነው። እንጂ በቋንቋ-ክፍተት ሆነን እነጮለቅም ወደ እዚህ ንትርክ መግባት የለባቸውም። በምርጡ ቋንቋ ሲጠቀሙ የተመራማሪነት ትኩረትአቸው ቀላል ይሆን አለ። ሲቀጥል እንደ መሪ-ስእል ይህን ታታሪ ስትመለከተው፣ አንድ ጉዳይ እንዲሁ መነሳት አለበት። ጭራሽ መጋቤነቱን ላለማንሳት ነው እንጂ ከሊቀምሁርዎችነቱ አንፃር ብቻ ደግሞ ህፃንዎች ማበልፀጉን አያይዘህ ስትኮንን ከሃሳብዎች አክባሪነት እና ሰውን ከሃሳቡ ነጥሎ ከመመልከት መሰረት ሊቅአዊ (አካደሚክ) ክሂሎት ማዳበር እና ምሳሌ መሆን አለበት። እንጂ ሃሳብ ባለማክበር እና ተናጋሪ በማንቋሸሽ ልጅዎች ምን ሊማሩ ይችል አለ? በአንተ ህፃጼ እና ኩነና (ጀጅመንት)፣ ነጥብ ያቀረበን በስነልቦና እምታሟሽሽ ሆነህ፣ ግሉን እየአጠቃህበት፣ በጎን ደግሞ ምናብቴ መሰል ምናብአዊ (አይዲያል) ትዉልድ ገንቢ መሆን እሳት እና ዉሃ ማስታረቅ ነው፤ ታላሚ አይደለም። የከፋው ስህተቱ ደግሞ እነሶቅራጥስ እንኳ በማወቅአቸው ጡዘት ‘እኔስ እማውቀው አለማወቄን ነው’ ባሉበት ይህ ዓለም እና የርሱ ሥራም ገና የአለፉ ታሪክ ዘጋቢዎችን ማነፍነፍ ሆኖ – ማለት ገና ብዙ አያውቅም ማለት ነው – ሰውን ከፋፋይ መሆኑ የአለማወቁ ስዉርባንዲራ ነው። ‘እሚአውቁ እና ማወቅአቸውን ደግሞ እንዲሁም የእሚያውቁ አሉ፤ እነርሱ መሀከል እኛ አለን’ ማለቱ ከቶ ለዘመናዊ ሃሳብአዊው ዓለም አብነት አይደለም። ይህ በርግጥ ከሙሉ ሊቅአዊ ዳራ የእማይመዘዝ ኢሊቅአማአዊ ስብእና ነጸብራቅ ነው። በሊቅአማአዊ ግዛት ዉስጥ ማንም ሙሉ ዐዋቂ የለም። ከቤተክህነት እሚነሱ ምሁርዎች ግን ይህን የመናድ ስብእና አላቸው። ሊቅአማአዊነት (አካደሚሻን-ሁድ) ከቤተክህነት ሊቅነት እሚጋጭብአቸው ሆኖ ይገጥምሃል። ቤተክህነት ዉስጥ፣ ተቃራኒ ነጥብ ዉጉዝ ስለሆነ እና ስንዝር መቅረብ ስለእማይፈቀድለት፣ የቤተክህነት ምሁርዎች ሊቅአዊ ዓለም ሲደርሱ፣ የሃሳብ መለያየቱ፣ እንደ ሃሳብ ፍጭት እና ምርጡን ነጥብ ማጥለያ መንገድ ሆኖ ወዲያውኑ አንዳንዴ ደግሞ እንደ እዚህ ታታሪ በዘገየጊዜም አያዩትም። የእሚለይ ሃሳብ ሲጋፈጥአቸው፣ የቤተክህነት ተመሳሳይ ዉግዘት መጎንጨት ያለበት ይመስልአቸው አለ። እና ጥረቱ ድንቅ እንደ ሆነው ሊቅአማአዊ ገጽታው ግን የተሸረፈበት ይመስለኝ አለ። አንፋሽአማአዊ (ኢንስፓየረር) እና ሃገር ወዳድነቱ ላይ ግን አንድ ስኬት እሚቀምስ እንደ ሆነ እንኳን ጥርጥር የለውም። እግዚእአብሔር ይባርከው! መንግስት ሳይሆን እንደ እዚህ መጋቤ አርባ የሃገር ፃድቅዎች ቢሰበሰቡ ደግ መሪነት ይሆን ነበር። እና ለ ተለዪ (ደዲኬትድ) መማሪአ ትመ. ጣቢአ ጥረት ላይ ስለሆነ፣ ንቃተንዋይ (ፈንድ ሬዘር) እንኳ ላይ፣ ሃብታምዎች ቢአግዙት ሃገር መዉደድአቸው በርሱ ሊቅአማ አገልግሎት በነእርሱ ገንዘብ ተገልጦ፤ ወደ ፊቷ ኢትየጵያን በደንብ ማገዝ ይችል አለ።”
ናሆም ይህን ሲናገር የቤተክህነት ትምህርት እራሱ ወጥኖ ስለነበር እሚጠቀምአቸው የእንግሊዝኛ ትክ-ቃልዎች ከግዕዝ ፍቅሩ እና ከአማርኛ ተቆርቋሪነቱ፣ ከሠለጠነ አኗኗር ናፍቆቱ እንደ ሆነ መስ ያውቅለት ነበር። ነገርግን ያለው ሊቅአዊ ዝማሜ ከመንፈስአዊ ትምህርቱ ስለእሚለይ፣ መስ እራሱ ብዙ ባልገባው የይጋጭ አሉ ቅርቃር (ዴድኢንድ) እንደ እማይጎዳ አመነ። በእርግጥ ለእርሱ ብዙም የናሆም አዳዲስ መጠነቃልዎች (ቮካቡላሪስ) አይገቡትም። ግን ለቀና እና እማይጨነቅ ሰው፣ የሃሳብን መሰረት መጨበጥ እሚከብድ አይደለም። የናሆምን ግል ጥረትዎች በማጎልበት ስለማገዝ በእሚል የቃሎች ፍች አይጠይቀውም። እንደ እሚያቅ ይሆንአለ። በቀረ፣ ግድ ለመናገር ሃሳብ ሲአጎለብት እሚአስገድደው ቃል ሲገጥመው አብራራ ይለው ነበር። አሁንም በሃሳብዎቹ ግልጠት አግኝቶ ነበር። የናሆም ሃሳብዎች በዕውቅ ጉዳይዎች ላይ ግልጥ ነው። ለምሳሌ ቋንቋን በተመለከተ አማርኛ ፊደሉ ብቻ ሳይሆን አማሊዝኛ ብሎ በሚጠራው ያማርኛ እና እንግሊዝኛ መዳቀል እየተከበበ እንደ አለ እና ተቋምዎች እና ምሁርዎች አማርኛን ወደ ኢልዑዋላዊነት ነድተውት እንዳለ እና የድቃሎሽ (ፒድጊናይዜሽን) ዉጤት የሆነው አማርኛ ባዲስ ዝግመት ደግሞ ከእንግሊዝኛ እየተዳቀለ እንደ እሚሄድ ምሁርአዊ ትንበያ ይሰጥ ነበር። ከግዕዝ አዳዲስ ቃልዎች መዋስ፤ ካማርኛ መዝገበቃልዎችም ብዙ አማርኛ ቃልዎች እያሉ መጠቀም ሲቻል፤ እንግሊዝኛ ቃልዎች ተዘውትረው፣ አማርኛ ዉስጥ እንደ ልበሙሉ አረም እየሰረጹ ነው። ያንን ንዝህላልነት ጠያቂ ሲያጣ፣ ለቋንቋው ወይም ሀገር አለሁባይነት ሲቀር፣ ጉዳዩን አስጊ አድርጎት አለ። ቃል እማሬ እና ፍካሬ ፍች ስላለው እንግሊዝኛ ቃል በመጠቀም ግን እማሬ ብቻ እንጂ ፍካሬ ፍች ማግኘት እየቀረብን ነው ይላል። እንደ ገናም ህፃንዎች እና መደበኛ ዜጋዎች አማርኛ ቃል እንግሊዝኛውን ተክተን ስንጠቀም በየሙያአችን ስናወራ ቢሰሙ አዲስ መጠነቃል ሆኖ ለመልመድ ይጥሩ እና ዕዉቀት በቀላል የእሚንሰራፋበት ሀገር እንሆን ነበር ብሎ ያምን አለ። ግን በእንግሊዝኛ ቃል ተክተን ስናወራ አማርኛ ስላልሆነ ለማወቅ ዴንታ አይሰጠንም። ‘በእንግሊዝኛው አንገደድም’ በእሚል ስነልቦና ሁሉም አዲስቃልን በመተው አ በአዳዲስ ቃልዎች እንዳይበመጽግ አድራጊ ባህል ነው። ለእንግሊዝኛ ደግሞ ብዙ ሰው ተጨንቆ ፍቺውን አይጠይቅም። እማያውቁት አማርኛን ቢሰሙት ግን ፍች እንደ እሚጠይቁ እርግጠኛ መሆን ይቻል አለ። ይህ ሃሳቡ በአማሊዝኛ እንዲበግን እና ሁሌ ኮናኙ እንዲሆን አድርጎት አለ። እሚአዝን የሆነው ግን ወደ ምእት-አመት በተጠጋ የተፃፈ አማርኛን የማዘመን ጥያቄ መሀከል አልፈን ዛሬም ጭራሽ ፈተና በማከል ማጥራቱ እና መወሰኑን ለመጭ ትውልድ መተዉ ነው። ናሆም እንኳ ስልጣኔ አፍቃሪ እንጂ ስነቋንቋኛ (ሊንግዊስት) አይደለም። አይሆንምም። ግን ቋንቋው ዘምኖ በጠራ ግንኙነትዎች ሙያተኛዎች ሁሉ ዕዉቀት ካልተለዋወጡ ወይም ካላገለገሉ እሚሰናሰል እድገት ከዉስጥ ማፍለቅ ትልቅ ጋሬጣ ይጠብቀው አለ ብሎ የአምን አለ። ቤተትምህርት ሲገናኙ፣ ሠብለወርቅ የክፍልጓዱን በቋንቋ ፍቅር ስለእምትንቦገቦግ “ብዙ ሥራ አለብሽ። ችግሩ ግን ሰሚ እንኳ የለሽም!” በማለት እንድትበረታ ከወዲሁ ይገፋፋት ነበር። የቋንቋ መጽሐፍዎችን በግል ትጋቷ በማንበብ የቋንቋ ፍሬሃሳብዎች እምታዋየው ስለሆነ የስነቋንቋ (ሊንግዊስቲክስ) ሃሳቡን ሁሉ አለገደብ እሚአጋራት የመልስም ጎዳናዎችን እምትጠቁመው ናት። መጪው ቢጨፈግግም ያቅምአቸውን ለማበርከት እና ትውልድአቸውን ለማነጽ ከብዙ ክፍል ጓደኞቹ ከወዲሁ በማኅበረ-ንባብ እሚወያዩ ሆነው ገና በድህረ ጉርምስና ወጣትነት መግቢአ ላይ ኀላፊነትዎች በግል በመከናነብ ላይ ናቸው።
በእርግጥ አማርኛ ቋንቋን ሲያስሱ አንደኛው የፊደሎች መሻሻል ጥያቄ ወገን ተገቢ ብቻ ነው አይሉም። አማርኛ ሞግሼ ሆሄዎቹ ምንም ሴማንቲክአዊ ልዩነት እንደሌላቸው ያውቁታል። ቢቀነሱ ደግሞ ምንም ልዩነት ለሴማንቲክስ እንደማያመጣም ያቁታል። ምክንያቱም እንደ ሊቀምሁሩ ማብራሪያ የፋርስ ቃል ነው እኮ ብቻ ብሎ ከቶ እማይታወቅ ድምጽ መስጠት አንዱ ወገን እሚያመጣው የዝሜ-ሞግሼ ገበታ፣ ዓላማው ለምሳሌ ሰባት “ሃ”ዎች ተደርድሮ መገኘቱ ለዓይኖች የፊደል ወጥነት ለማስቀረት ብቻ የታለመ ስለሆነ ብቻ ነው። ዓይኖች ለመፈተን ወይም ለማፍታታት ተብሎ ስለማይነገር ግን ይህን ማብራሪያ እማያውቅ በቀጥታ ኢአመክዮአዊነት ተመልክቶ ይከራከርበት አለ ማለት። ስለእዚህ ገበታው ይሻሻል ወይም አይሻሻል ማንም ስህተት አይደለም። ድምጹ አንድ ከሆነ በዓይኖች ብቻ ሲታይ ከተለያየ የዓይኖች ማፍታቻ ብቻ ተደርጎ በጥንቱ ፍልስፍና የበለጸገ እንጂ የስነቋንቋ ምክንያት ኖሮት አይደለም። ነገርግን፣ ይህ ምክንያቱ በምስጢር ቢቀር እሚፈለግ ሆነ። በይፋ አይነገርም። ያንን ብቻ የእነሠብለ ትዉልድ ይጠላል። በግልጥ በቋንቋው ቃሎች መወያየት አይፈቀድም፣ ባለበት ገበታ ይቀጥል ብሎ ይህን አስፍቶ ማብራራት ወይም ደግሞ በመሰል ደንብ የዓይኖቹ ዘውግ ይቅር እና አለመወሳሰቡ ይመረጥ ተብሎ ማሻሻል ተገቢ ነው። አንድ ወጥ መንገድ ለመፍጠር፣ መጠየቁ እንዲቀር በእዚህ መብራሪያ ማስተማሩ ወይም ደግሞ አሻሽሎ በአንድመንገድ መወሰን ተፈላጊ ነው። በይፋ አንዱን ደንብ መፍጠሩ ታዳጊዎች ጥያቄውን እንዳዲስ እንዲያነሱት ስለሚተው እና በድግግሞሽ እሚተው ወጥመድ ስለሆን ፍቱን መልሱን ስለመጭ ትዉልድ ሲሉ ይፈልጉታል። ይህ አዙሪት ችግርላይ መዉደቁ ከቶ ለሰባዊነት አይመከርም በሚለው ሃሳብ እረግተው ይወያዩ ነበር። ሠብለ አንድ አላማዋ ለናሆም እንዳዋራችው እንደ ሊቀምሁሩ አይነት ማጭበርበሪያ አመክዮ ከሀገርአችን ተሰርዞ መጪው ትዉልድ በጠሩ ከባቢዎች፣ በተቀነሱ የሃገር ችግሮች ተጠምዶ፣ ለመስራት ይደገፍ። ለእዛ ደግሞ የሚፈታቸው ጥያቄዎቹን እንቀንስለት እሚለው ስለነበር ናሆም ሰሚ ብታገኚም ባታገኚም በርቺ እሚላት ለእዛ ትዉልድአዊ ብሩህነት ነበር፨
ናሆም ለወቅቱ የትመ. ትንግርት እንዲለምድአቸው ለልጆዎቹ ምንም ገደብ ሳይሆን ቆየ። ‘እማይገደብን ነገር መከልከል ምናልባት ማስጣል ሳይሆን ማሳመቅ ሊሆን ይችል አለ። ያ፣ ኋላ በታፈነ እና እልኸኛ ነፃነት ዉስጥ ተሆኖ በምልአት እንዲጎበኝ ቆጣሪ-ፈንጅ (ቲኪንግ ቦንብ) ማዘጋጀት የአክል ነው። እንደእሚ፣ እሚገጥምን ነገር ቀድሞ አስተዋውቆ አያያዙ የግል እንደሆነ እና በዉሳኔ ግለ-መሪነት (ሰልፍሊደርሺፕ) ማበልጸግ እንደ እሚገባ ጥርጥር የለውም፤’

መጠጡን ሲኮመኩሙ ጸሐይግባት ተቃረበ። መስ ሲመጣ እና ሲቆይ፣ በተቻለ ሁሉ በወትሮአዊነት እማይቀሩበት ፈርጡን ‘ድግስኛ’ እሚሰኘው የአምባእራስ ካፌን፣ አሁን ከመስ ጋር ለማየት አንዱ ጉጉቱ ስለ ሆነ፤ ዛሬ ላይጎበኙት እንዳይችሉ በመስጋት መስን ቃኘ። ካልደከመው እንዲወጡ አሳወቀው። ወደ ቤተመጸዳጃ በመመላለስ ብዙ ጠላ እየጠጡ በጣቢያዎች ምቾት ካረፈዱበት ከሰዓት በኋላ ቀጥታ ወደ መኝታ ላለ መጓዝ ተያይዘው ወጡ። አብረው እነ ብሩ በመዉጣት ወደ ሌላ አግጣጫ ወደ እነዩሱፍ መንደር ወደ መሃልከተማ አዘገሙ፨
ልጅዎቹ ብርቅ ሆኖብአቸው ባፈጠጡት የ ትመ. ትንግርት አናትአቸው ዞሮ ዋለ። ሦስቱ አዳጊዎች፣ እሚን ላለመረበሽ ድምጽ አሳንሠው፣ በብቸኛነት በማፍጠጡ እንደ አሉ፣ መዝናናትአቸውን እሚገታ ሆኖ ድንገት የዉጭው በር በከፍታ ድምጽ ተንኳኳ። ቢግ ወጥቶ ሲመለከት ሁለት ወጣትዎች ቆመው ከደሣሳው በር ፊት ተገትረው ተመለከተ። ስለእሚአውቅአቸው ቀርቦ ማናገር ሳይፈልግ ወደ ጓዳ ሊገባ ሲመለስ፣ እሚ የበር ድምፁን ሰምታ ስለነበር ወደ ሳሎኑ ሻሽ በማስተካከል ስትወጣ ተገጣጠሙ። ቢግ ወደ ትመ. ሲመለስ ባቤ ብቻ አጠገቡ ነበር። ጢዩ ከአንቀላፋችው ጮለቅ ሥሯ ተቀምጣ አናትዋ መከዳው ላይ አርፎ ትከታተል ነበር፨
እሚ ወጥታ እንግዳዎቹን ተመለከተች። ሰላምታ ሰጥታ ወደ ቤቱ የግድግዳ ስር ደረጃ እንዲቀመጡ አዘዘች። በዕለቱ ከቀጠሮው ቀኑም ዘግይተው የደረሱት የተለመዱ እንግዳዎቿ ነበሩ። ገብተው በተጋበዙት ደረጃ ላይ ተገባብዘው ተቀመጡ እና ግድግዳ ላለመደገፍ በጉልበት ክንድዎች አስደግፈው ዘመም ዘመም አሉ። አንድአቸው ጠና ያሉ ወጣት ሲሆኑ ገና ለግላጋው ወጣቱ አጋርአቸው ደግሞ ባለባርኔጣ ነበር። እሚ ወደ ቤት ገብታ ለቢግ ጠላ እና ዳቦ እንዲአወጣ አዘዘች። ተነስቶ በቀለጠፈ አያያዝ ጠላ በጣሣዎቹ ቀድቶ ከእግርአቸው ሥር ጆክ ሞልቶ አስቀምጦ ዕድልዎችም በዝርግ ሳህን አስይዞ አስቀምጦልአቸውም ወደ ባቤ ጋር ገብቶ ስእልታይ (ካርቱን) ፊልምዎች እድመቱን ቀጠለ። “አቶሚክ ቤቲ እምትሰኝ ልጅቷ መሳሪአውን አገኘ ች ው?” ብሎ ወዲያው የለመዳትን ባቤን ጠየቀ። “አው! አው!” ዝምታ አያይዞ በ እሚጋብዝ መልስ መልሶለት በማፍጠጡ ተደባለቁ። ቢግ እንጂ በእርግጥ ባቤ እንግሊዝኛው ከሰዓቱን ሲፈተን ነበር። ቢግ አብዛኛውን ቃልበቃል እየተገነዘበ ተያይዞት እና ለታናሹም እሚያብራራም እየሆነ ነበር፨
እሚ ብዙ የልቃቂት ፌስታልዎች ይዛ በመዉጣት ወደ እንግዳዎቹ ተመለሰች። አንድኛው እንግዳ በየወሩ እሚመላለሰው ገዛኽኝ ለሐረግ እሚላላክ ወጣት ሲሆን ጓደኛው ባለባርኔጣ እና ያረጀ ዳለቻ ካፖርት ያጠለቀው ደግሞ በቅርብ የተቀጠረ ው ቀጠን ያለ ሰራተኛ መላኩ ነበር። ልቃቂትዎች፣ ፈትልዎች፣ ጥጥዎች እና መሠል እቃዎች ለእሚ እና መሰል ሰራተኛዎች ማከፋፈሉ እና በየወሩ መሰብሰቡ ጋር በተያያዘ አብሮ ሥራውን በትጋት እሚፈጽም ነበር። በቁራሌነት ሲሰራ በደረሰበት የዛገ ቆርቆሮ መቆረጥ አደጋ በበብዙ ህክምና እና ወጪ ስለተረፈ፣ ያንን ትቶ አሁን ኢመደበኛ ተላላኪነቱን እየጀመረ ነበር። ገዛኽኝ እሚ ፊት ቆጥሮ እቃውን ከተረከበ ኋላ እራስምታት ተፈንቅሎ ያልሸሻት እሚ “ተጫወቱ እንግዲህ! ቤቱ እንግዳ መጥቶ ተዝረክርኮ ስለላልተጸዳ ንፋሱ ይሻላል ብዬ ነው! ጠጡ! ጠጡ!” ብላ ጠላውን አንስታ በመቅዳት ልትገባ ተጠጋጋች። “እሺ እናትአችን! እግዚእአብሔር ይስጥልን!” ብለው ከእየቂጥዎችአቸው በጥቂቱ ከፍ በማለት ጣሣዎቹን አስሞሉ። ወደዉስጥ ልትመለስ ስትል ግን ገዛኽኝ አስቀራት። “እናትአችን፤ አንድ ጉዳይ ነበረን!” እሚ መለስ ብላ “ምን?” በትህትና ፈገግ በማለት ጭምር ጠየቀች። ወደ አስረከበችው እቃ ተመልክታ “ጎደለ እንዴ?” ስትል ወደከያው ሰጋ አለች። “አይደለም። ወንበር ይዘው ኑ እና እንወያይ” አለ፨
ግር ብሏት ወደ ሳሎን በሩ ተጠግታ “ባቤ በርጩማ!” አለች። ባቤ በድምድምታ እየተራወጠ በርጩማ አድርሶ ወደ ትመ. ስር ቢግ የአነጠፈው ምንጣፍ ላይ በደረቱ ዳግ-ተነጥፎ ማፍጠጡን ቀጠለ፨
እሚ ፊትለፊት እየተመመከተችአቸው ተቀመጠ ች። “እሺ?” ብላ ግርታዋን ቀለል ለማድረግ ሞከረች። ተባርሬ እንዳይሆን በእሚል ስጋት ልቧ ጠቅ ተደረገ። ገዛኽኝ ዳቦውን አኝኮ ለመናገር በመቸኮል ጠላ ፉት አደረገ። በፍጥነት ተቻኩሎ ሲዉጥ አንገቱ ዳቦውን እንደ ምንም ተቀብሎት በጉሮሮው አንሸራተተለት እና ትንታ መለሰለት። ልክ ሊናገር ስላሰበ ይህ ሲፈጠር ከትንታው ይልቅ እየተሳቀቀ እሚን በኃፍረት መመልከት ከወነ። ወንጀል ይመስል የሰራው ክው ሲል እሱ ሰውነቱ ግን በአደጋ ላይ ተፈናጠጠ። ከዉስጥ ዓይንዎቹ እንባ ወደ ፊቱ ወረወሩበት። ከአፍንጫው ትይዩ ግንባሩ ደግሞ የፊት ቆዳውን ገፍትሮ የ ደምስር ቱቦ አስመለከተ። “ጠጣበት እኔን እኔን!” በትንታው እንደሆነ በመቆየቱ እሚ በመደናገጥ ጋበዘ ች። በትንቅንቅ አንገቱን ከሳምባው እያስታረቀ ብዙ ቆየ እና ጎደል ያለ ጣሣውን ጨለጠ። ወደ ጓደኛው ደግሞ ልኮ እየታገለ “ቅዳልኝ እንጂ!” አለው በዝምታ ሲተወው በመቆጣት። እሚ ተሽቀዳድማ ስትሞላለት ግማሹን ጠጥቶ ጉረሮውን በመደጋገም እየኮረኮረው፣ አንገቱን ለመበጠስ እስኪመስልም እእያሰገገ በፈታጊ ድምጽ መስተንግዶ አጸዳ። ዓይኖቹን እያደረቀ ፈገግ አለ። እና ተንፈስ ብሎ ድምጹን መልሶ ለማግኘት በመታገል ቀጠለ። “አይ ደህና ነኝ…”። እሚ ‘ከዚህ በላይ¡’ በእሚል ፈገግ አለች እና ሞት ወርዉሮበት በጥቂቱ ተስቶ መልሶ እንዲህ ሲል ተገርማ፣ ወንዝ ለጥቂት ሳይገድል እንደ ተፋው የሰመጠ ሰው አይታው፣ ዳግ-ፈገግ አለች። አብራም በዝምታ ጠበቀችው።
እንደምንም ሲረጋጋ ቆይቶ፣ “እና እመስቴ ጉዳዩ ትንሽ አሳዛኝ ነው!” አለ። “ምን? ምን ተፈጠረ? ተባረርኩ?” እሚ ደንገጥ አለች። “አይ! እርሶ ለሐረግ እማ ከእሚወደዱት አንዱ ነበሩ። ያከብሮት ነበር እንደው። መቼም አያባርሮትም ነበር! አይ!! አይ!!” “ታዲአ?” አለች እሚ በይበልጥ ልቧን ሰቅላ ክው ማለቷ እየተውለበለበ። ጓደኛው “አይ እመቴ! እመስት ሐረግ እኮ ካረፉ ሃያ ቀንዎች ሆናት! እንደው ድንገት ነው እኛም የደረስንበት።” የእሚ ልብ በታላቅ ሃዘን ጽን-መብረቅ ተወርዉሮበት ተሰነጠቀ። “ምን! ሐረግ … ይህች ታላቅ ወጣት አረፈ…ች?” እጅዎችዋን በ አፏ በመጫን ዓይንዎች አፍጥጣ ጠየቀች። “አዎን እመቴ! በሰካራም ጫት ይበላ የነበረ ሹፌር መኪናዋ ተገጭቶ ስታሽከረክር… አዲስአበባ ሞተች ብለው ይኸው መስሪአቤትአችን ተዘግቶ ትላንት ነው የተከፈተው።” አለ ገዛኽኝ በእሚ ሃዘን እራሱም ክው ብሎ ዳግም የሐረግ ቀና ባህሪ እና ለሰራተኛዎች ያላት ፍቅር እና ርህራሄ ተመልሶበት ዓይንዎቹ ለሁለትኛ ጊዜ እንባ እያቀረሩ። ሂወት ጨልሞበት ወደ ጎዳና መዉጣት ሲዳዳ ነበር ሐረግ ወደ ድርጅቷ ያስገባችው እና ትልቅ መጽናኛ ከገቢ ምንጭ ጋር የሆነችለት። ዕንባው ሲወርድ በእጁ ጠረግ አደረገ እና እሚ እንባዋ እንደ እርሱ ሲፈስስ መልሶ አቀረቀረ፨
ሐረግ እሚን ደጋግማ አራት አምስቴ መጥታ አይታት ቤትዋን ጎብኝታ ለቅልጥፍና እሚረዱ ክሂሎትአማአዊነትዎች (ቴክኒክስ) በሥራው ዙሪአ እራሷ አስተምራት፣ አግዛት እና ልጅዎችዋን በመማር እንዲጠነክሩ በመጣች ቁጥር መክራላት፣ ለባቤ ስእልዎች አድናቆት ቸራ አንድ መሳያ ቁስሣጥን (ኪት) ገዝታ ከወረቀትዎች ጋር የሰጠችው፤ እና ወደፊት ዛሬ በትጋት ከአጠኑ ብሩህ እንደ እሚሆንልአቸው ደጋግማ በማስረዳት ልጅዎችዋንም ትረዳላት ‘የነበረችው’ ደግ። በሁለገብ እማያልቁ እና ተፅኖአማ በጎስራዎቿ እና ንግድ ትትረቶቿ እምትደነቅባት ‘የነበረችው’። እንዲሁም ደግ ስብእና የነበራት፣ ሃብታም ወጣትን መሞት በዝምታ ክዉ ብላ አዉጠነጠነች። የትሁት ፍቅር እና ተፅእኖአዊው ያገባኝአለ ባይነቷ ፊቷ ተስሎ ከቶ አልጠፋ አላት። ተፅዕኖ ስትፈጥር በቀላሉ እና በሚደንቅ ስፋት እና ፍቺ ነበር። ከቀደሙት ጉብኝቶቿ በአንዱ፣ ድንገት እሚ ቤት ስትመጣ ስልክ መስሎት ገና ስታወጣው መንትፎ በሮጠ ወጣት መንገደኛ የእጅቦርሳዋ ተዘርፎ ነበር። መስታወት አብራ ተዘርፋ ስለነበር እቤት ገብታ ተጫውታ ችግር ካለ ተመልክታ እና ተወያይታ ልክ ልትወጣ ስትል እሚን መስታወት ጠየቀች። መስታወት በቤቱ ግን በቁምነገር ታይቶ ስለ አልተገዛ አልነበረም። እሚ ዝም ብሎ የለም ከማለት “ምን መስታዉት ቢአፈጥጡበት መልስ የለው፣ ዉሸት ሞሽላቃ፣ ነገረ-ሠይጣን ነው!” ብላ በጨዋታ ነበር የመለሰችላት። ከት ብላ የሳቀችው ሣቅ አሁን የሆነ ያክል ትዝ አላት። በእርግጥ እሚ ለጨዋታ ብትለውም በልቧ የመስታወት ነገር ለዓይንዎች ጉድ እሚአፈላ እንደ ሆነ እና በሰው አልታይም ብሎ ሰው መስታወት ፊት በማፍጠጥ እና በምኞት ዉበቱን ሲሾፈትርበት ስነልቦናውን እንደ እሚጎዳ ከምሯ ትገነዘብ ነበር። “ምን ይሰራልሽ አለ ልጄ! መስታወት እስክታዪ ድረስ እና ቁንጅናሽን በሰብእአዊ ጉድለትሽ መልአክ ልምሰል በማለት አይበቃኝም እስክትይ እንጂ እኮ ቆንጆ፣ ዉብ መልክ አለሽ። እንደ መልአክ ነሽ! መስታወቱ ግን ባልታወቀ ስዉር መንገድ መንፈስ ይቆርጥ አለ። ይቅርብሽ መስታወት ላይ ማፍጠጥ ልጄ፤” ብለው ከመጫወት ወደ ማሰብ እና ማስጠንቀቅ ዘልቀው መከሯት። ሐረግ አቅላ ነገሩን በመመልከት አጋጣሚውን ለመቀየር ወዲያው እንዲገዛ ትንሽ ገንዘብ አቀረበች። “ልክ ኖት! ግን በተገቢ መጠቀሙ አይጎዳም! ለምሳሌ የተሻለ መልክ ፍለጋ እና የምኞት አሠሳ ለማድረግ፣ ልክ በመስታወት በሚያፈጡበት ሂደት አንጎልን ልክ ሰው ሲያየኝ ምን ይል ይሆን እያስባሉ ለማፍጠጥ ሳይሆን፣ በእዛም አዎ ልክ ኖት፣ መመኘት ወይም በመልክ ቅሬታ ወይም እንደ ናርሲስከስ ኩራት መፍጠር ሳይሆን፣ ቆሻሻ ለመፈተሽ ያክል ነው እሚረዳኝ …” ፈገግ ብላ መለሰ ች። እሚ “ሰው መስታወት ተመልክቶ መልኩን ይጠላ እና ስነልቦናው ይጎዳ፤ የመስታወት ፊትፊት ምኞት፣ ሰውን አታልሎ፣ ሳያቅ በልቡ ክፉ ስነልቦና ሲአሠርግ፣ አጥንት መሰርሠር ድረስ ወደ መጨነቅ ያደርስ አለ። እና መልክ አወዳዳሪ አድርጎ ሽባ እንደ አያደርገን እሰጋ አለሁ” በማለት ብትከራከርም፣ ሐረግ በቁሟ ሳለች በደረሰላት ትንሽዬ መስታወት እንደ ልብ ሳትጠቀም ለነገሩ ፊቷን መርምራ ብቻ ተመለሰች። በቀጣዩ ዓመት፣ አምና፣ ስትመለስ ግን፣ ነገሩን በመዘከር ሙሉ መዋቢአ ቁስሣጥን ለእሚ ተሸክማ አመጣች። ሁሌ ስትመጣ ለልጅዎቹ መቀየሪአ ብዕርዎች፣ እርሳስዎች፣ ደብተርዎች፣ እንደ እምትሸከመው፤ ለእሚም ትልቅ መስታወት፣ ሚዶ፣ በዛ ያሉ ዘይት ቅባትዎች፣ ጸጉር ጌጣጌጥዎች፣ ኋላ ባቤ በ መሳል የጨረሳቸው ኩልዎች፣ ምላጭዎች፣ እና መሰል መዋቢአዎች አስረከበች። እሚ እንግዳዎቹ ፊት በቁምነገረኛነቷ ትዉስታ ተጠልፋ ሃሳብ ዉስጥ ስትቆይ የእንግዳዎቹ ሹክሹክታን ሰምታ በሃዘኗ እንደ አስጨነቀች ተሰምቷት፣ ዝምታውን ሰበረች፨
“ትልቅ ሰው እናቴ! ትልቅ ሰው አሁንም! ኧረ አይጣል እግዜር!” ቀጥሎ ከመናገር ቀድማ ጨንቋት ተከዝ አለች። “እና አሁን ምነው ቀብር እንኳ ሳልደርስ! ሳትነግሩን እንደው ምነው?” ገዛኽኝ ሃዘኑን አልፎ ቆፍጠን ለማለት ጥሮ ይህን ካደረገ እራሱን በመኮነን እየፈተሸ ቅጽበት ወስዶ በይበቃኝ አለ ስሜት ሆኖ መልስ ሰጠ። “አይ እመስቴ! አዲስአበባ ነበረች እርሷ። አይጨነቁ! ማን ሄደ ብለው? እምታሰራው ሰው ሁሉ እሷ ሰውን ከመዉደዷ ተነስታ የሰበሰበችው ሠራተኛ የነበረ ነው። እንጂ ከእዚህ ሃገር ከወጣች ጠቅልላ ቆየች አደል እሚባለው። እናት አባት ወይ ቤተዘመድ እንኳ በእዚህ አካባቢ መች አላት። ሁሉ ቤተሰብ፣ ቤተዘመድ ዉጭ ሃገር እና አዲስአበባ ነው በእሷ ሳቢያ ከየገጠሩ ፈልሶ ይነለር የነበረ።” ጓደኛው እንደተከዘ ቀበል አድርጎ “አዎን! እኛም በየግል ነው የአዘንንው! እርሶም ይበርቱ እንግዲህ!” የእሚ ሃዘንትኛ ፊትን እየተመለከተ በማስተዛዘን ገለፀላት። “እንዴት ያለ ክፉ ገጠመኝ! ጫት፣ አልኮል… ንጹሑንም ይፈጅ አለ! ሃገሩ ገሃድ ችግር ተመልክቶ ደንብ ህግ ማዉጣት አያውቅ! ከኛ መሃይምዎቹ እማይሻል መሪ እሚአስተዳድርበት ሃገር፤” እሚ እምትወቅሰው ማሰስ ስትፈልግ ተጠያቂ ጠፋ። መንግስት እንደሆነ እሚተች እና እሚጠየቅ እንደአልሆነ በታሳቢነት ታይቶ ንጽስርኣት (ዴሞክራሲ) የማይታወቅበት ሀገር ነው። እልፍ ቢፈጅ፣ አንድ እርምጃ የለም። ባለፈው፣ እነናሆም ሲወያዩ እንደዘበት ያደመጠችውን ብትንቀውም በራሷ ደርሶ ግን ተመልክታ እህታ አሰምታ አናቷን ነቀነቀችብአቸው። ተዓግ. ዉስጥ ጥቁሩ ፒንክ ፍሎይድ በነጭ ህግዘብዎች (ፖሊስ) እያሰርንው ነው በእሚል አንገቱ ተጨምቆ ሞተ። ‘የጥቁሮች ሂወት ዋጋአለው’ እሚል አለምአቀፍ የዜጋአዊያን (ሲቪሊያን) ንቅናቄ ተንበለበለ። የኒውዮርክ ገዢ ክዌሞ አሜሪካ ለምን እንደሰለጠነች ብንጠየቅ እምንመልሰውን ወርቅአማ መልስ አብነት ሆነው ሰጡ። “ህግ ይወጣ አለ! እነሆበእዚህወዲአ፣ ምንም አንገት ጨምቆ ማሰር አይፈቀድም!” ሲሉ ተደመጠ። አበቃ! አንድ ማህበረሰብአዊ መሰናክል ሀገሩን አንድ ዜጋ ቀጠፈ። ሲታሰር ስለተንደፋደፈ ነው እንጂ ሊገደል ለንተብሎ አንገቱ አልተጨመቀም ነበር ቢባል ባይባል! በሰው መቀለድ የለም። በሀገር መቀለድ ነው እና። ስለእዚህ ማንም ህግዘብ አንገት ጨምቆ ማሰር በህግ እሚያስቀጣው ወንጀል እንደሆነ ሊደነገግ ሆነ። እነናሆም እና ብሩ፣ የማህበረሰብ ለውጥ መነሻው በገጠመው ቆሻሻ ነገር ላይ ህግ ማውጣት እና በእዛ ስንክሳር ዳግ-እንዳይወድቅ ማረጋገጡ ነው ብለው ያወሩት ሠረሰራት። መች ስምጥ ህግ መደንገግ፣ መች ሰፊ ህግ ማስከበር አለ? መቼ? ልቧ የሐረግ ሞትን እየሳለ ከሰለ፨
“አዎን! ምን ይደረግ እመቴ? ሹፌሩ ምንም አልሆነ እርሷ ወዲአው አረፈች።” በጸጥታ ሃዘን ተመልሳ እሚ ቆየች። ሐረግን በምሽት እንደ እብድ እሚአሽከረክሩ ሃገርአቋራጭ፣ ሌሊትወፍ-ሹፌርዎች ያደረሱት ንዝህላልነት ከዓለሙ ላይ የሠፈፈ ሰፊ ስራዋ እና ሂወትዋም ጭምር አለያያት። እሚ በማዘን እንደ ቆየች ወደ ገሃዱ ተገድዳ ተቀላቀለች እና ጠላውን እንዲጠጡ አሳሰበች። ገዛኽኝ ማግ አድርጎ ጨዋታውን ቀጠለ። “እና እመስቴ ይኸው ከትላንት ወዲአ ማምሻ ላይ ባለቤቷ ነው ያሉን ሰው መጥቶ፣ ሁሉን ንግዷን እንደ ዘጋጋ እና እንደ ሸጠው አሳወቀን። እና መበተንአችን ሊሆን ነው በቃ!” ከመርዶ ተደማሪ ሌላ ዱብ ዕዳ እሚ ላይ ከመረባት። “ምን! ሥራው ሁሉ ሊቆም?” እሚ በሌላ መደንገጥ እንደ ተመታች ጮኸች። ወደቤት ድምጿ እንዳይራመድ መልሳ ደንገጥ ብላ አፍ በእጅ ሸፈነች። “አዎን! ባሏ እምብዛም እንደ እርሷ ለሰው እሚገድደውም አይደል። በየት እንደ ተገናኙ እግዜሩ ይወቀው። ሰው ሲአናግር እንኳ ቅጥ የለውም። ሁሉ እንግሊዝኛ እሚችል እሚመስለው ሁሉ እሚአቅ እሚመስለው ክውክው እሚል ምሁር ነገር ነው።” ጓደኛው ቀጠል አድርጎ ሊያግዘው በጨዋታው ገባ። “ወደ ዉጭ ጠቅልሎ ሊሄድ ነው መሰል። ሁሉን ንግድ ሸጦት አለ፤ ምንአለፋዎት።” “ለምን ተክቷት አይሰራም? እንደ እርሷ እኛ እንደሁ እንሰራለት ነበር። አትራፊ ነው ብላ አለች ንግዱ እንደሁ!” እሚ በመገረም በአቅሟ ልክ ሁኔታውን አዉጠንጥና ሃሳብ አቀረበች። ይሁን እንጂ ሃሳቧ ግን ከጭንቀት ቁልል አልጸዳም። ብታወራም ምቧ ግን እየከሠለ ነበር። አሁንም በመንታ ልብ ተመለከተችአቸው፨
“አይ! እኛም ትላንት ጠይቀንው ነበር። ‘የእኔ ቢዝነስ፣ በጉዞ ወኪልነት አካባቢ ሆኜ ማማከር ነው። ይህ ዘርፏ ለእኔ አይሆንም!’ ብሎ ሁሉ ንብረት በቀደመ ሳምንቱ እንደ ተሸጠ እና ከእንግዲህ ሁሉ እንደ አበቃ ተናግሮ ጥቂት በህግ መሰረት ብሎ የመልቀቂአ ክፍያ አስልቼ አለሁ ያለውን ለሁሉ እንድናደርስ ላከን።” ከረዥም ልብሱ ያወጣውን አምስትከህ ስድስትመቶ ሰማኒአ አራት ብር ቆጥሮ አስረከባት። አብሮ ምስክር ወረቀት ብሎ የተሰጠውን በማድረስ ሰጣት። አመስግና ተቀበለች። “ከእንግዲህ ያው ሥራው የለም። ነገ ግን መዝጊአ ብሎ አንድ በሬ እንድንጥል ዝግጅት እንዲሰናዳም አድርጎ፣ አንድ ዝግጅት ብጤ አለ።” ገዛኸኝ ጣሣ እየሞላ ተናገረ። የጓደኛውንም እየሞላ ሳለ ጓደኛው ጣልቃ ገባ። “እንግዲህ ነገ ምሣ ሰዓት ላይ በመሃል ከተማው የድሮ ሱቅዋ ላይ ሁሉ ይሰበሰብ አለ። አመስግኜ ነው እምዘጋው ብሏል እና፣ እመቴ እርሶም ኑ እና እንለያይ አለን” ብሎ ሃሳብአቸውን ቋጨ፨
እሚ በማዘን እና ግራመጋባትዎች ተዉጣ የሱቁ ስፍራ እንደ አልጠፋት ለማረጋገጥ ካርታውን ሳለች። ሁለት ጊዜ ብቻ አይታው ነበር እንጂ ሁለት አመት ሙሉ ስትሰራ ከቤቷ ወጥታ አታውቅም ነበር። ብሩም፣ ናሆምም እነቢግ እና ባቤም እንደ እሚአውቁት አስታውሳ ለነገው ቀጠሮ ተስማማች። ወጣትዎቹ ተረካክበው፣ መልእክት አስረክበው፣ በሰላምታ እና በርቱ እንግዲህ በእሚል ሃዘን ጭምር ተለዩ እና አመስግነው መርቀው ወጡ። እሚ እስከ በሩ ዉጭ ድረስ ሸኝታ “እንግዲህ መሰል ሥራ ከተገኘ አስቡኝ” አለች ሊለያዩ ሳለ በመጨረሻ። ገዛኽኝ መለስ ብሎ “አይ እመስቴ! እኛ እንኳ ወደ ሁመራ ለመሄድ እየ ተሰናዳን ነው። እዚያ ወይም ሥራ ይኖር አለ ወይም ከሥራው ጎን አጥንተን አመቺ መካንጊዜ ዉስጥ ወደ ሱዳን መሻገር ነው ያሰብን። እንግዲህ እማ እዚህ አንቆይም!” ባዘነ ድምጽ መለሰ። እሚ “ደግ! በሉ እንግዲህ ይቅናአችሁ እንዲያ ከሆነ እማ!” በመሰል ሃዘን ድምጸት ሆና እሷም ተሰናብታ ወደ ቤት ተመለሰች፨
ወደ መመኝዋ በመዉጣት በሃሳብ ባህር ሰጠመች። ከፍተኛ ቀውስ ዱብዕዳ! ቤተሰቡ በድህነት እንደ ተከሰሰ አሰበች። በመሸነፍ እንደ ተፈረደብአቸው ደግሞ አመነች። የቤቱ ብቸኛ እራስ ነች። ገቢዋ ከእንግዲህ ግን ቆመ። የበልግ ዉጤቱ የገጠሩ ገጸበረከት፣ የመጨረሻውን ጉብኝት ቤቷ አድርሶ ተጠናቅቆ አለ። ምትክ ብላ ያሰበችው የሐረግ ስራ፣ ሙሉኛ እሚገታውን ቃታ ሳይታሰብ ሳበ። መስከረም ደግሞ የልጅዎች ትምህርት ጎን አዲሱ የህይወት ምእራፍ ይከፈት አለ። በረከት ደግሞ፣ ከአዲስአበባ ሁሉ እንደ ራቀ በወሬ ከተሰማ ሁለት ዓመትዎች መሆኑ ነው። ጮለቅ መረገዝዋን እንኳ ሳይሰማ የዛሬ ሁለት ዓመት ነበር ከቆይታ ኋላ መጥቶ በሁለትኛው ቀን የተመለሰ እና የጠፋው። እንደ ክንፋም ህልምዎች ተረት ከገጠር፣ ወደ ፋዲካይት፣ ከእዛ ወደ አዲስአበባ፣ ነሆለለ። አንዴ ደግሞ ወደ ሱዳን ድንበር እንደነበር አንድ ጭምጭምታ አምና ተሰምቶ አይሆንም በእሚል ታልፎ ነበር። ወዲአው የእነገዛኽኝ መሰሉ የሱዳን ምኞት ትዝ ብሏት ወደ ሱዳን መሻገሩን ከምር ሊሞክር እንደ እሚችል ዳግ-አሰበች። የደረሰብአቸውን አዲስ አደጋ መልእክት አድርጎ ለመስጠት እና ቢአገኙት እንዲረዳዱም፣ ማን እንደ ሆነ ገልፃ ለማስረዳት አቀደች። ነገ ሲገናኙ ያንን በዘዴ ለማሳሰብ ወጥና አሰበች። መልሳ “ምን ሊአደርግ?” ብላ ግሏን ጠየቀች። መቼም በሁለት ዓመትዎች ሰው ሃገር ተጉዞ ሃብት አይከመር። አይታፈስ። ቢሰበስብ እና ቢያገኝ እንኳ ከዝርክርክ ኑሮው እሚተርፍ የለም። እንደሁ፣ ታሪክ ምስክር ነው። የገጠሩን ገጸበረከት ያለችው ገቢ ሳታሳውቀው ወዲአው ስለተለየ እሚአቀው ገቢ ባይኖራትም ቤተሰቡ እንዴት እንደ እሚኖር ሳይጨነቅ እሚኖር አዉሬ እንደ ሆነ በልጦ መልሶ ታሰባት። ለመጨረሻ ጊዜ ሲጠፋ እንደወሰነችው ከንግዲህ ቢመለስ እንደ እማትቀበለው አብልጣ አሁንም በማስመር ወሰነች። ብቻዋን እዚህ የደረሰችው እርሱ ከቶ ምንም ሳይደግፋት ነው። የነበረውን የአባቱን መሬት በመሸጥ ጉድ አድርጓት አለ። ፍቅሯ ከእንግዲህ በጥላቻ እንዲቀየር ወሰነች። ለነገሩ ሱዳን የተባለው በወሬ ብቻ ስለሆነ መልሳ ያን በማሰብ ቁጣዋንም ተስፋዋንም አቀለለችው። ካለእርሱ እሱ ድጋፍ እዚህ ተደርሶ አለ፤ ምን አሁን እነሆ ቢከብድም፨
የዱብዕዳውን ነገር መልሳ በንዝህላል ባሏ መፈትፈቱ እሚፈይደው እንደ ሌለ በመናደድ ተመልሳ አሰበች። ደግሞ ሁኔታው እማያስመልጥ ሆኖ አስጨንቋት ጥቂት አሰላስላ ጭንቀት ብቻ ሆነ። “ምን ይደረግ ቀጣይ አሁን?” ከወለል ንጣፉ ፍራሽ ወደ ጣሪአው ከእዛ ወደ ግድግዳው ተመላልሳ አፈጠጠች። መልስ ጠፋ። “አይ ሰካራም ሹፌር!” መልሳ ይህም መልስ እንደ እማይሰጥ ተረድታም መራገሙን ተወች። ጭንቅ፨
ብቻ ወደ እሚደረገው አተኩራ ለማብሰልሰል ወሰነ ች። ዞሮዞሮ አንድ መፍትሔ መምጣት አለበት። ከሆነ ደግሞ፣ መጨነቁ ያ መፍትሔ አይደለም። “እና ምን ይሻል አለ?” ልጅዎችዋን በመሳል እራስዋን ጠየቀች። አናቷ ብቻ ዞረ። መፍትሔ ላይ ማተኮር መፈለጉ የዘወትር ጉብዝናዋ ቢሆንም፣ ይህ ግን መፍትሔ ልፈልግልህ ስላሉት መፍትሔ የአልወለደ ነው። የግል ሥራዎቿ በወር ሦስትመቶ ብር እንኳ አስገኝቶ አያውቅም። ከዓለም ከቻይና ቀጥሎ እርካሽ ይባል በነበረው እና በእጥፍ በተጨመረው የመብራት ኃይል አገልግሎት ብቻ ከአራትመቶ ብር በታች ከፍላ አታውቅም። ዉሃ እና መሰል ከተሜ አገልግሎትዎች ተደማምረው እስከ አምስት-ስድሥትመቶ ብርዎች በወር ሊዘጋጅለት ይገባ አለ። ሌላውም የቀለብ እና ልብስ ትምህርት ወጪዎች ብዙ ሲሆኑ ገና ጨቅላዋ ጮለቅ ደግሞ ታወሰቻት። ዕንባዋ በአዲስ ትልም ተረማምደው ወደ ጆሮዎቿ እምብርት ወረዱ። ጣሪአው መልስ አልሰጥ ሲል አሁንም በገነች። ከእራሷ ይልቅ ልጆቿ አሳሰቡዋት እንጂ እርስዋም እራስዋም አለች። ሃብታም መሆን ተመኝታ ባታውቅም ኢትዮጵያን እየዞሩ ገዳምዎች መመልከት ግን የቆየ የታመቀ ህልሟ ነበር። አሁንማ ያ እሚያንቀለቅል ህልም ቢበተን እንኳ፣ ለሰብእአዊ አኗኗር ልብስ ለመቀየር እንኳ እንደእማትታደል መስሎ ሆነ። መከራውን ባሰበች ጊዜ ጭንቀቱ የነብስዋን ግዛት ወረረባት፨
ወዲያው እራስዋን ታዝባ ስለ ልጅዎች ማሰቡን ቀጠለ ች። ያም መፍትሔ ባይሆንም፣ ወደ ችግሩ ግዝፈት ካስመለከታት ብላ ገፍታ አሰበችበት። ብሩ በወሮች ወደ ኅዋአዊከተማ እሚሰደድ ነው። እዚሁ ከተማ እንዲማር ሃሳብ ግን ድንገት መጣላት። መልሶ ሃዘን ወረሳት። በ የ ፋሲካይት ኅዋአዊከተማ መማር ቀርቶ ጉብኝቱን እንኳ ስለበይነምብ አቅርቦቱ ብሎ ሲከውነው እሚጸየፈው መካን ነው። ተማሪዎች በ ወልቤቴ (ዶርም) -አቸው አጠገብ ሽንትቤት የሌላቸው፣ መታጠቢአ ቦታው ዉሃ አፍስሶ እማያውቅ እና ከፍለው በጀረኪና ከአካባቢው ነዋሪ ገዝተው አንዳንዴ በግድየለሽነት በአየር ላይ ከጣራ ዉጭ ሲታጠቡ እራቁትአቸውን እሚታዩ፣ በወልቤቴዎቹ ስር ከቤተምግብአቸው እሚወጣ የመብል እጣቢ ፍሳሽ በስፋት እየተንቆረቆረ ሽታው እሚሰነፍጥ የሆነ፣ ቤተመጽሐፍአቸው አንድ ሲሆን በፈተና ሰሞን ብቻ ሃያአራት ሰዓት እሚሰራ እና በቂ አቅርቦት እና ወንበር አቅም የሌለው፣ መብሉ በአሰቃቂ ሁኔታ እማይታገሱት የሆነ፣ ብዙ መምህርዎቹ እራስአቸው መነሻ ዲግሪ እንጂ ልምድ እና ዕዉቀት በብዛት የሌላቸው እንዲሁም በዘር እና ግንኙነትዎች የተቀጠሩ እሚበዙበት፣ መምህርዎቹ እና አስተዳዳሪዎች ለተለያዩ ጎንዮሽ ገቢ እሚኳትኑ እና የኃላፊነት ትኩረትአዊ ብቃት የሌላቸው፣ ቤተሙከራዎች እና መዝናኛ አማራጭዎች እማይገኙበት፣ ትምህርት ክፍልዎች እንኳ በግል ነፃነት እማይተዳደሩበት (ለ ምሳሌ ህግ ትምህርትቤት ሳይሆን ህግ ክፍለትምህርት (ዲፓርትመንት) ሆኖ የማህበርአዊ ጥበበምርምር (ሳይንስ) አባል ተደርጎ ህግ ትምህርትቤቱን የስነቁፋሮ (አርኪዎሎጂ) መምህር እሚአስተዳድርበት ሆኖ ለእየ ግል ለተማሪዎች ፍትሐብሔር መጽሐፍ ይገዛ ሲባል በሁለት ቅጅ በቤተመጽሐፉ ተጠቀሙ እሚል እንደ ነበረ እና ሰሞኑን ብቻ እራሱን ይህ ህግ ትምህርትቤት ሆኖ እንደ አደገ እና ሌላዎችም ነፃነት እሚፈልጉ መዋቅርአዊ ዝርክርክነትዎች ያሉበት ስለ ሆነ)፣ ቤተህክምና በአቅራቢያው የሌለው፣ የአቻ ግምገማ መጽሔትዎች (ፒር ሪቪው ጆርናልስ) ለተማሪዎች የሌሉት (ለመምህሮችም እንኳ የሉአቸውም)፣ መስተንግዶ እና የጥበቃ ደህንነቱ ለተማሪዎች በብቃት እማይሰጥ ስለ ሆነ፣ ብቻ በጠቅላላው፣ ክብረነክ ተቋም፣ ተማሪዎች እማያበቃ እና በሽተኛ እሚአደርግ ነው፣ በእሚል አዲሱን ኅዋአዊከተማ ከአሠሰ እና ወሬዎችም ከለቃቀመ በኋላ መቀላቀሉን ከቶ አይመኘውም ነበር። እሚም ይህ እንደታውቅለት ከአመቶች ቀድሞ ጀምሮ እንዳሳወቃት እና እንደተስማሙ ነበር፨
ከከተማው ርቆ ለተሻለ መስተንግዶ መሄዱ ደግሞ ለእሚ የነብስ እርካታ ቢሰጥም የወጪ መዓቱ ግን አሰጋት። ሰሞኑን ደግሞ ይመደብ እና ወጪው አንድ ብሎ ይጀመር አለ። በዚህ ደረጃ ደርሶ የርሷ ድጋፍ መለየቱ ከነከናት። በስሌት አንጎሏ ቢናጥ ቢናጥ መፍትሔ አልወጣ ብሎ እረፍት አጣች። በመጨረሻ አማራጩ ጠላ እና አረቄ መስራቱ እና መሸጡ እንደሆነ አመነች። ግን ጥቂት ገቢ ቢያስገኝ እንጂ በቂ እንደ እማይሆን አመነች። ከተማው በአረቄ እና ጠላ የተንበሸበሸ ነበር። ዋጋው እርካሽ ነው። ከቶ አስተማማኝ ገቢ አይደለም። ድንገት የጮለቅ ድምጽ በጩኸት ማልቀስ ሲሰማት ነብሷ እያለቀሰች አሁንም ዕንባዋ ወረደ እና ወደ ሳሎኑ አናሽ ስቃይ የበዛበት ጡት ከሁለት ጡቶቿ እያወዳደረች ወጣች። ወደ ጮለቅ መኝታው ሽንጣም መከዳ ላይ ስትቀመጥ የተለመደ እማያሳስብ ግን ጌጠኛ ሲጢጥታውን አሰማ። የትርዒቱ አፍታ-እረፍት ሆኖለት፣ ባቤ ከትመ.ው ፊት ተነስቶ ወደ ዉስጥ ገባ። እሚ ጮለቅን ጥቂት ጡት ስታጠባት ቢግ መስታወት ይዞ ተመለሰ። እራሱን አፍጥጦ በመመልከት እንደ ዶሮ ወዲህ ወዲያ ሲል እሚ ጮኸች። “አንተ ይህን መስታወት አትንካ አላልኩም! የከንፈርህ ማበጥ ጉርምስና ስለጀመረህ ነው አትጨናነቅ ተቀበለው፣ መስታወት ተውልኝ አልተባልክም!” ሳታስተውለው በቁጣዋ ጨምራ ስትናገር ግራ መጋባቱ በዛበት። መልሶ ሁኔታውን ለማርገብ ይቅርታ ጠይቆ በከፊል ማንጎራጎርም ወደ ጓዳው ተመለሰ። እሚ ታዳጊዎቿ በመልኮቻቸው አንድ ጉድለት ፈልገው በስዉር ስነልቦና እሚጎዱ እንዳይሆን በሁለት ቀጥተኛ መንገዶች ስለወደፊታቸው ትዋጋላቸው ነበር። አንደኛ መስታወት ላይ ማፍጠጥ ከቶ የተከለከለ ነው። ፊት፣ ጸጉር፣ እና ጥርስ አበክሮ በስርኣቱ ባለማቋረጥ ማጽዳት ከፍተኛ ግዴታ እሚጣልበት እለታዊ ጉዳይ ነው። መስታወቱ ቆሻሻ ለመፈለግ ብቻ እንዲቆይ እሚፈቀደው ለሰከንዶች ነው። ፊቴ ቢረዝም፣ ቢያጥር፣ አፍንጫዬ ባይጎረድ አጠር ቢል፣ ግንባሬ ጸጉር ባያጣ፣ አይኖቼ ቢፈጥጡ፣ ሰርጎድ ቢሉ፣ ጠባሳዬ ጠፋ ብትልነ ኖሮ… ብሎ ማያ ጊዜ የለም። እነእዚህ በስዉር እሚያድጉ አስተሳሰቦች ስለሆኑ የብዙዎች ስልጣኔ መሰረት መስታወት ላይ እሚያጠነጥን መሆኑ አንዱ ገሃዱ ነው። የእኛ ሀገር ዘመንአዊ ስልጣኔው በማህበረሰብ ደረጃ እሚያወራው ጉዳይ ባይሆንም ይህ ግን የብዙ ስልጡን ሃገሮች አንድ የስልጣኔ አካል ነው። ከጥንትአዊት ግሪክ የናርሲስከስ በዉሃ መልኩን መመልከት ተረት ጀምሮ፣ እልፍ ታሪክዎች በእዚህ መስታወት ፊትለፊት ባለው ስነልቦና ዙሪያ አሉ። ለኢትዮዮጵያ እሚገባት አንዱ ድንቅ ስነጽሑፍ የሆነው የቬሮኒካ ሮስ የአለጂያንት መጽሐፍ ወይም ፊልሙም እንኳ እሚጀምረው ትሪስ በልደቷ ዋዜማ መስታወትን በመመልከት/አለመመልከት ጉዳይ ስትጨነቅ ነው። አመክዮ? ሰው ባይቆጣጠረውም፣ በዉስጡ ስዉር ስነልቦና ወደ ቆንጆ ነኝ ወይም አስቀያሚነኝ እብስልስልታ እሚልክ እና እሚያጠምድ እንደሆነ በዘመኖች መረጋገጡ ነው። ግን እሚ በግሏ እእታጋፈጠው፣ ሃገሪቷ ይህን ስልጣኔ ይዛ እማታስፋፋው ስለሆነ ነው። እሷ ከእናቷ እንደተማረችው ግን ይህን ሃሳብ እምታውቅ ነበረች። የመስታወት ነገር ስዉር እንጂ ሰው አላስብም ቢልም እንኳ ካለማሰብ እሚደርስበት አይደለም። እጅግ ስዉር-አዉዳሚነት መገለጫው ነው። መመለጥ እሚጀምሩ በእንቅልፍ ልብ ብርድልብስ ጸጉር እንዳይመልጠው ሲጠነቀቁ እና በ ንዋመእርምጃ (ስሊፕዎክ) ሲሰቃዩ በገጠር ሳለች ገጥሟት ያውቅ ነበር። በባለሙያዎች እና ስነጽሁፍአዊያን ጭምር መስታወት መመልከቱን መቀነሱ ወይም ማጥፋቱ ለእዛ ሲባል እሚመከር የሆነው ለእዛ ነበር። ስዉር ማለት በእንቅልፍ ልብ ሁሉ እሚያጠቃ ነው። ማንም በርጋታ መስታወት አየሁ ቢል፣ በንቅልፍ ልቡ ላሳሰበው መልኩ መጨነቁ የመስታወት ጉድን መቆጣጠሩ እንደእሚታሰበው ቀላል አለመሆንን ማስመልከቻው አንዱ ነጥብ ነው። የተሰጠ ፊት ወይም ሰውነት አንዴ ከአምላክ ተሰጥቷል። በእርሱ መከፋትም፣ መኩራትም ጎጂ ነው። የፊት ፍልስፍና አድዉነት ለመናገር የስልጣኔ መሠረት የእሚሆነው ለእዛ ነው። ማንም ሊቀይረው ስለማይችል፣ ግን ሁሉም ሊበረታበት እሚገባ ስለሆነ። በመስታወት ግን ያ ቢሆን ባይሆን ብሎ ማፍጠጡ በዝነኛው የስዉር ስነልቦና መሰረት አጥንት ድረስ መጨነቅ ማለት ነው። ግን ይህ አይታወቅም እና ችግሩ ሲደጋገም ወደ ነብስን ማሰቃየት ይደርሳል ብላ ለማመን ብቁ ሆና ነበር። አሳቧ በጥንትአዊት በሮምአዊያን ከነበረው የመስታወት ግምት እሚጋጭ እንደሆነ ግን አታውቅም። እነእርሱ መስታወት ላይ ስናፈጥ እምንመለከተው ምስል ሳይሆን ነብስአችንን ነው ይለጀ ነበር። ማን አየኝ? ሰው ሲያየኝ ምን ይል ይሆን! ቂጤሳ? ጸጉሬሳ! እያሉ እንደ መለጠጥ ደግሞ ታዲያ ነብስን እሚወጋ የለም። ምክንያቱም ነብስ በተጨነቂ ቋንቋ እየተሰደበች ነው እና። ይህም ከእኛ ተግባር ተሰውሮ ህቡዕ በሆነብን ሚስጢሬ (ኮድ) እሚተላለፍላት እና እኛ እማናውቀው፦ ስለእዚህ እሚጎዳን ሆነ። ሁለተኛ መፍትሔዋ ደግሞ፣ ስለፊት እና አካል እያንዳንዱ ሰው ማውራት ግዴታው ነበር። ስለእራሱም ስለሰውም። ማን ቀለል አድርጎ ጉዳዩን መያዝ እንደቻለ ታጠና እና ታስተካክልአቸው ነበር። ከከንፈሬ፣ ጥርሴ፣ ጉንጬ ወዘተ. እንዲህ ነው እንዲያ ነው ይሉ ዘንድ ይበረታቱ ነበር። በተገኘ አጋጣሚ ሁሉ። እከሌ ከንፈሩ፣ ጥርስዎቹ፣ ቆዳው፣ ወዘተ. እያሉም መግለጥ እና ስለሌላውም መነጋገር ግድ ነበር። ሀበሻዎች ይህን በግልጥ እና ቀናነት እንዲሁም ባለማካበድ እሚያወሩት ከአልሆነ፣ የስነልቦናው ትግል ቀፋፊ እንደእሚሆን ቤተሰቡ በጋራ ከእዛ የተነሳ አዋቂ ሆነ። መስም በመደወል ብዙ ጊዜዎች ከሚመክራት አንዱ ጉዳይ፣ የሀበሻ መልክ ፍጹም ስለአልሆነ እና በእጅጉ ስለእሚለያይ፣ ልጆችን አንድም ለእዛ ገሃድ አብስሎ ማዘጋጀቱ ላይ ስለሆነ፣ ያንን በሚገባ ሁሉም ይከውን ነበር። ሀበሻ አንዱ ያጣው ነገር በእርግጥም፣ በግልጥ እና አለማፈር ተዝናንቶ ስለመልኮች እና ብዙ ተያያዥ ጉዳዮች መነጋገር ነው። ከእዛ የመልክዎች፣ የመቀንጨርዎች፣ የኢፍጹምአዊነት እና ፍጹምአዊነት መሠናክልዎች ይዘለሉ ነበር። ልክ በእዉቀቱ እንደዘገበው፣ ከመልክ ተሻግሮ መመልከት የወደቅንበት አንዱ ማህበረሰብአዊ ስንኩልናአችን ስለሆነ፣ ይታከም ነበር። ሃቀኛዎች ለመሆንም ይህ በገጽታ አለማፈሩ ይረዳን ነበር። ብዙዎች እማያጠኑት፣ ግን እሚያቁት የሀበሻ ይሉኝታ ይገፈፍ ነበር፣ የመልክ ቅሬታ ልእለብዙሃኑን ይሉኝታ እሚወልድ ነው እና። ኩሩ ግን ለመቃወም እና ለወጥ ሃሳብ እንዲነቃ ይህ የድጠቅመው ነበር። በተለየ እንደእኛ ያለሃገር፣ በመልክ ጉዳይ እንዲህ በይፋ ሰርቶ ካልተሻገረ መሰልጠኑ ከቶ እና አሁንም ከቶ እሚታለም እንኳ አይደለም። ህንድ እንኳ ወደ ማደግ ስትመጣ ይህ የመልክ እና አቋም ጉዳይ ከባህል እና ብሂል ተቀላቅሎ፣ አንዱ የቀደማት መሰረተ ስልጣኔ ነው። የሎሬት ጸጋዬ የመጨረሻ ስቃይ ሰቆቃም ሀበሻን አደፋፍሮ ከከበበው የማፈር እና በእዛም እሳት ወይ አበባ ያለመሆን ችግር ነበር። በእርግጥ፣ ሃገር በጋራ በመሰብሰብ ስንሰራ እና ስናጠና፣ ስንታገል ካደገች፣ በጋራ ለመሰብሰብ የፊት እና አካል አመለካከቶችአችን ስርነቀሉን ለውጥ ቀድመው መከወን አለብአቸው። ካሎነ፦ ይሉኝታ፣ ፈሪነት፣ አምባገነን እሚመቸውነት፣ በመንግስቱ ግርማ እንኳ ይህ ህዝብ አህያ ነው መባል እና ታሪክአዊ ተሰዳቢነት፣ ሆይሆይታአዊነት፣ ፎታችአዊነት፣ አሽሟጣጭነት፣ ይከተል አለ። በየትም ማህበረሰብ ዝማኔ ይቀበል ዘንድ አይሆንለትም፣ አንዱን ትልቅ መሰረት ስላልገነባው ወለሉ ዉሃ ነው እና። እልፍ ቢሰራ ሰማጭ እና አየሁ እሚል ልፋት አይሆንም እና። ይህ ስቶይስቲክ ፊት አያያዝ ክፍለ-ፍልስፍናው ላይ ብቅ ያደርገን አለ። ያም፣ የስልጣኔ ወርቅአማ አንድ ቁልፉ ነው። በእየደራሲዎችአችን የተመሰከረለት፣ የተሰበከ…። የሰው ፊት ወይም ሰውነት አንድ ቅርንጫፍ ላይ ሰውየው ቅር ብሎት ከአለ፣ እራሱን እንደሙሉ አይመለከትም። እራሱን እንደ ጉድለቱ ወይም መሙላቱ መመልከት ይገደድበት አለ። ለምሳሌ ጠባሳ በአንድ ጉንጭ ካለ ሁሌ መስታወት ሲመለከት ያንን እሚመለከት ሰው በድብቅ ነብሱ ትጨነቅበት እና ፊቱን በተፈጥሮው መረዳት ይከብደው አለ። ተፈጥሮአዊው የፊት አገነዛዘብ፣ ፊትን ወጥ አድርጎ መሳል እና መቀበል ነው። አፍንጫ፣ ዓይኖች፣ ጥርሶች፣ ጠባሳ፣ ቅንድብ…የሆነ ክፍል ላይ ነቶ አለማተኮር ግድ ነው። ያ ነባር (ዲፋውልት) የፊት አተያይ ነው። ያ ጤነኛ ነው። መስታወቱ ግን አንድ ጉድለት ካስመመከተ፣ እና ከተያያዙት፣ እንደ አሃድ (ዩኒት) ጠቅልሎ መገንዘቡን ይገዳደር እና ይደፍቀው አለ። ይህ ለአካል ሁሉ ነው። እኛነትአችን ከእራስ ጸጉር እስከ እግር ጥፍሮች አለ። አለባበስ ሁሉ ግልጥ ተጽዕኖ አለው፣ እንኳን አካል። መኖሪያ መንደር፣ ሠፈር እና ሃገር ወዘተ. እያለ ይህ የስቶይክ ፊት አያያዝ መንገድ ይሠፋ አለ። ግን ከፊት አንፃር ብቻ ያለው ፍልስፍና፣ በቂ ክፍሉ እሚጠቁመን ወጥ አረዳድ እንዳይዛባብን እሚያደርገን መንገድ በመስታወት መፋለሱን ማወቁ ነው። ይህ ሲፋለስ እና ሰው ከመልኩ አንድ ሃሳብ ሲዋሃድ፣ አንጎሉ መጨነቅ ይጀምር አለ። እንደእሚባለው ከሆነ፣ የስነልቦና መልስምት በስውር ይፈልግብን አለ። እኛ ሳናውቅከ አንጎም መከላከያ ምሽግ ይፈጥር አለ። ማስጠላት ወይም ማማሩ፣ መጨነቅ፣ ኢገሃድአዊ ክብረኛነት (ፎልስ ግራንዲዩር)፣ ‘ስለእዛ አነሳላችሁ አለሁ ቆየት ብዬ’ ትእቢት፣ ናርሲሲዝም፣ ታእታይአዊነት (ኢንፈሪዮሪቲ)፣ ወዘተ. ብቻ የገጸባህሪ መዛባት ይከስት አለ። ይህን ጠርቶ ደግሞ በባህሪ ለዉጥ ይቋጭ አለ። ካልእአዊነት (ዱፕሊሲቲ) በማንነት ይጠራ አለ። ከአንድአንድ የገሃድ ክፍልዎች እራስን መሰንጠቅ እና ያንን ባህሪ ማድረግ ያመቻች አለ። ይህ ያምተባበረ ገሃድ-ተካፋይነት፣ ማህበርአዊ ቀውስ ይወልድ አለ። ያ ደግሞ ከግል ወደ ሃገር ጉዳቱን ያስለጥጠዋል። በእርግጥ፣ የፊት እና መስታወት ጉዳይ በአለም ትልቅ ስፍራ እሚሰጠው፣ በመሰልጠንአችን እሚንጸባረቅ ስፋት እሚያከማችከ እኛ ጋር ግን በአልሰለጠነ አያያዝ እሚያዝ ነው። ይህም የስነውሳኔአችን ማንቀላፋት-ደረጃ ህላዌ አንዱ መዘዝ ነው። የነቃ መንግስት፣ መንቃቱን በመራመድ አያረጋግጥም። ጦር በማርመስመስም። ባህል በመቅረጽ እና ነገን ብሩህ ሆኖ እንደእሚገኝ ግን በሚያረጋግጥ ማነጽ እሚጠመድ ነው። ይህ እስኪሆን፣ የእሚ ተሞክሮ፣ የመስ ድጋፍ፣ የመንታ ኃላፊነት ጠቅልሎ አለ። ሁሉንም ማስተማር። በእርግጥ፣ በድሃ ሃገር፣ መንግስት በገንዘብ እና ጉልበተኛ ሰላም ማስከበር ዙሪያ ብቻ ነው ያለው። ሲቀጥል፣ በሙስና። እንጂ በልጅዎች ማደግ እሚጨነቅ የዴንታ ፍንጭ እንኳ አያስመለክትም። የቤተሰብ ንቅትቅት ማለት፣ የልጆች ነገ መሰረት ነው፦ በኢትዩጵያ እና ብጤ ሃገር። ቤተሰብ ከመንግስት በላይ፣ ያለ እርሱ ድጋፍ ልጅ ማሳደግ ሙሉኛ ግዴታው ነው። እንደ እነእሚ። እንዲሁ፣ ቢግ ሰሞኑን በደረሰበት ጉርምስና የከንፈሩ መወፈር እና ራስቅሉ ማደግ እንደገጠመው ተወያይተው ስሜቱ እንዲቀልለው ተደርጎለታል። በግሉ አይብከነከንበትም። ከአየሩ ነጭ መሆን እኩል እሚመለከተው ነገር ተደርጎለት ብሩህነቱ እንዲቀጥል ተደርጓል። አሁንም ድንገት የመዘዘውን መስታዋቱን መልሶ አፍታው ሲፈጸም የአፈጋጊውንሻውን ዘ ሺፕ እይቱን ለመከታተል ወደ ትመ.ው ፊት ቀርቦ ተነጠፈ። እሚ ጮለቅን አጥብታ በሃዘን ተሸብባ እንደቆየች ለጢዩ እንድትመግባት እንቁላል ልጣ ጨምራ ሰጥታት ወደ ጓሮ እራት ለማዘጋጀት ጡል ጡል ወደ ማለት ዞረች፨

ናሆም እና ቤተኛ-ግን-እንግዳው መስ በከተማው ምዕራብ ዳርቻ ወደ አለው ከከተማ ወጣ ስላለ ብዙ ሰው እማይጎበኘው ግን እይታአማ (ሲነክ) ዉበት ለፈለገ በተለየ ምርጥ ፀሐይግባት እሚአስመለክት ስፍራ ስለሆነ እሚአዘወትሩት ወደ ሆነው ድግስኛ ካፌ ባለሦስት እግርዎች ተሽከርካሪ ተጠቅመው ደረሱ። ወደ ኮረብታአማው ካፌ ሲደርሱ ብዙም ሰው የሌለው ባይተዋሩ ድባብ ተቀበላቸው። ከነበሩበት በማንሳት ለእየግልአቸው ወንበርዎች ሰብስበው ፀሐይግቷ እምትኮመኮምበት አንድ ጥጋት ላይ በግልአቸው መስተንግዶ ተቀመጡ። በታሸጉ መጠጥዎች ላይ ጠበቅ ያሉ ነጥብዎች ስላሏቸው ተፈጥሮአዊ ነገር እሚአዘወትሩ ናቸው። በተለየ ለድሃው ሀበሻ ማንም ተጨንቆ እሚያስተምረው እና እሚንከባከበው ህቡአዊያን (ሲንዲኬትስ) ወይም ተቋም፣ ወዘተ. ስለሌለ፣ መብል መጠጥ የተበላሸ አያያዙን አስመልካቾቹ አንድ አብነት እሚሆኑት እኒህ የታሸጉ መብል ህዝባር መጠጦች ናቸው ብለው ያስቡ አሉ። ለምሳሌ፣ ድህነትአችን በዓምድር ከፍተኛው ስለሆነ መጠጥዎች በድንቅ ጥራት ሌላ ሀገር እንዳሉት እዚህ የሉም። ቢሆንም፣ ስንጠቀም ስለእማናድግ፣ በነብስ ብርቅታ ብዙዎችአችን ከአገልግሎቱ ጉዳቱ እሚከብበን ነን። በብዙ መንገድዎች። ይህን እሚያጠናልን የለንም። ግን የቻርሊ እና ቸኮሌት ፋብሪካው መጽሐፍ (በ) መጀመሪያ ሲፃፍ በጥቁሮች የመብል ጣዕም መሰናከል ለማስተማር እንደነበር ጋዜጦች ዘግበው ነበር። ዘግይቶ ግን የመብል እና መጠጥ ጉዳይ ሰብአዊ ነው በማለት ነጭዎች ገጸባህሪያት እንዲከውኑት እና ጣፋጭ መብል እንቅፋት እንደእሚሆን ለማስተማር የተረኩት እውቅ እና ተወዳጅ መጽሐፍ፣ የተደጋገሙ ፊልሞች ትርክት ሆነ። እኛ ሀገር ይህ ከቶ የለም። በተለየ በድህነት ስንኖር ግን የመብል መጠጡ ወጥመድን እሚያጠናልን መኖሩ እና ባህልአችን ማንጸባረቁ ግድ ነበር። ብዙዎችአችንን እየጠለፈ ነው እና።ለምሳሌ፣ እነናሆም የሚገምቱት አንድ ጉዳይ የአንዳነደድ መጠጥ ማሸጊያዎች ቁማርን ነው። የዘንዶ ምስሎች የ አሉት ሁሉ አለ፦ ጣፋጭ መጠጥ ላይ። ሀገር የነቃ ቢሆን ይህን ያስወግደው ነበር። ምክንያቱም፣ ልጅዎች እሚያዘወትሩት መጠጥ ነው። ቢሆንም ልጅዎችን ግን በስነልቦና ከመጠጡ ደስታ ጎን አብሮ እሚዋጋ ነው። ልክ ድሀ ሀበሻ፣ ጣፋጩን ተጎንጭቶ ነብሱ በስኳሩ አቅም ስትረካ ዓይኖቹ በደስታ ፍጥጥ ይላሉ፦ ወጥ የሰው ስነልቦና ነው እና። ወዲያው መጠጧን በደስታ ሲያፈጥባት፣ እባብዎች መጠጡን ሊጠጡ ወይም በአንድምታ ወደ ‘ጠጧ’ እየጠቆሙ ይመለከት አለ። ይህ የአጉል እምነት ቢመስልም፣ ብብዙ የስነልቦና ትንታኔ ግን ነበረው። በአንድአንድ አረዳዶች መሠረት፣ በመጠጡ የተወለደ የሰመጠ ደስታ መሀል የጠጪው ልብ ትነቃቃ አለች። ወዲያውኑ፣ በስሜት ስካር መሀል፣ አዉሬትን በማስመልከት እና አዉሬአዊነትን በመስበክ ይጎዱን አለ። በደስታ ጫፍ ላይ ደግሞ የሰው ልብ እሚቀልጥ እንደሆነ ሌላ ትንታኔ መስካሪ ነው እና። ስኳርአዊ ስካር፣ እርካታ ነው። መጣፈጥም ስካር እሚሰኝ አንድ ፍች ነው። በእዛ ስካር ወቅት፣ ሰው ያየውን አቅልሎ ለመቀበል ልቡ ገደቡን ስለእሚንድ እሚሳካለት ነው። ጣፋጭ በሰዎች እርካታን ወግቶ፣ ስነልቦናአዊ አጥርን በመጣስ በመበጣጠስ፣ ቶሎ አጠገቡ ያለውን ነገር ወይም ድባብ ተቀባይ መንፈስን እሚጨምርብአቸው እንደሆነ ይጠረጠር አለ። ታዲያ፣ በደስታ የሀበሻ ድሃ ህፃን ሁሌ እማትገኝ ጣፋጭ ቀመስ አድርጎ ነብሱ ሲፈካለትከ የሰው አንጎል ሁሉ እንደ እሚሆነው፣ አጠገቡን ሊቀበል ይቻኮል አለ። እንደ ሄሮድስ በሄሮዳዲያ ዘፈን እንደ ነሆለለው እና ምንም ነገር ቃል እንደገባላት፣ ወይም እንስትዎች ጭንዎች መሀል ተጋድሞ ምንም ቃል እንደእሚገባው (አድሬሽ አንዴ ሲነጋ ልሙት እንዳለው አዝማሪ)፣ ወይም በመጠጥ ሰክሮ ብዙ ቃል እንደ እሚገባው ሰካራም (ሳሚ ጎ፣ ለመስቀል በዓል ከዘፋኝዎች ጋር በስቶይስት ፊትነት እማይታማው በብርቅርቅታአማው የጉራጌ አይነተኛው ፊት፣ በሃይሉ ፈረጃ ቤት ተገኝቶ፣ በድግስ ተንበሽብሾ ሲሰክር፣ ለስቶይሲስት ፊት ተሸንፎ ስሜቱ ለቀቀች፣ ሰገደች፤ ‘በኢትየጵያ ተወዳጅ እምትሆን ዘፈን ላንተ እሰራልህ አለሁ!’ ብሎ ሰገድ እያለ ለሃይሉ ቃል ሲገባ፣ ስቶይስት ፊቱ ወርቅአማ ጉራጌ የመሆን እድሉ ስለነበር አጠገቡ ሰው ያለ እንኳ ሳይመስለው የሳሚ ጎ ስካርን ከቁብ ላለመቁጠርም ስልጣኔው ከፍተኛ ነበር፤ ምክንያቱም ያውቀው አለ፤ የደካማ ነብስ በልእለብዙሃኑ ኢትየጵያአዊ አለች ከጉራጌዎች ላይ ግን የለችም፤ ማስረጃው፦ ከቁብ ያልተቆጠረው ስካር በመንቀት ወቅትም በሀገር ፊት ቢገባም ቃሉ፣ ብዙ ቆይታን አልፎም የተገባው ቃል ያለጥረት እንደቀረ እና እንደከዳን ታይቶ ነበር እና፤ እስከአሁንም። ለነገሩ፣ ይህ የሀበሻ ሁሉ ስንፈተ-ህላዌ ነው፦ ስቶይስት ፊት ማጣት ደና ሲገኝ ልገዛልህ ብሎ መሸነፉ፣ ቀን እስኪወጣልን!)፣ ብቻ ጣፋጭ እሚጠጣም እሚያመሳስለው ንጥረነገርአዊ ምላሽ አለው። በከፍተኛ የስሜት መለጠጥ ላይ ጣፋጩ በእኩል ወይም ተቀራራቢ ደረጃ አርዝሞ አግዝፎ ይክበው አለ። ያኔ እንደ ሰከሩ ስሜትዎች፣ ልክ እንደ ሌሎቹ፣ አንድ እማይገመት ነገር ለማድረግ ቃል እንደእሚገባ ሰው ይሆን ዘንድ ተመሳሳይ አንጎል ንጥረነገር ላይ ይመጣ እና በኩራት ነብሱ አካባቢውን ያናግረው አለ። ‘በሏ ጠይቁኝ! አለም ከእኔ ምን ትሻ አለች! ጎበዝ ጠይቁኝ! ዓለም ከእኔ ምን ይፈልግ አለ?! ጎበዝ ልስጥ ጸሐይን፣ ልስጥ ጨረቃን፣ ምን ፈላጊ ናችሁ?!’ ይል አለ። ይህ የስካር ቅኔ ነው። የስሜት ቋንቋ ነው። ማንም አላልኩትም አይልም፤ ባይለውም፤ ብሎት አለ። የሰውነት መገለጫ ነው እና። ግን በቁማሩ መሠረት፣ ጣፋጭ ሻጮቹ እባብን በእዛ ቅጽበት ማስመልከትአቸው፣ ጣፋጩ ጎን አዉሬአዊነት የማጣባትአቸው ዴንታቢስ ጉዳይ ጥያቄአቸው ነው ማለት ነው። ለጣፈጠ መብል መጠጥ ሲባል፣ አዉሬአዊነትን የጠጪው ስነልቦናን እንዲከትል አድራጊ ወይም ጠቋሚ ነው። የጣፈጠ ከፈለግህ፣ ልክ ተጎንጭተህ ስትፈካ ዝቅ ስትል እንዳየህው፣ እንደ እዚህ አዉሬ ሁን። ጣፋጭነት አወጀሬአዊነት ይፈልግ አለ፣ ጨክን ለሆድህ፣ አዉሬ ሁን… ብሎ እሚሰብክ ነው። ይህን ምስል ወይም መሰል ምስልዎች እያስመለከቱ የመብል መጠጥ ስካርን ማማስከተል፣ የተኛውን ወይም የተሸነፈውን የሰውን ክፉውን ክፍል ማንቂያ እና ማሰይጠኛ ከፍተኛ ህቡዕ ጦርነትአቸው ነው። እነናሆም በሁኔታው እሚጠቃን እልፍ ሀበሻ፣ በተለይ ህፃንን እያሰቡከ ቢያንስ ትንሾቹ በመረረ መልኩ እሚጎዱ እሚሆኑ እንደ እሚሆን ያስቡ ይወያዩ ነበር። የቱ ታዳጊ? ኧረ ወይም አዋቂ፣ እንደው ተኝተን ማን ይጎዳ ይሆን? በማዘን የታሸጉ ነገሮችን እሚሸጡ በብዛት ክፋት እሚያስተምሩ ስለሆነ፣ አይጠቀሟቸውም፣ ከአልተገደዱ። በጣፋጭ መጠጦች ፍጆታ ወቅት ስሜት ሲነድድ ፈጂው ግለሰብ የልብቅርጽ፣ የመተቃቀፍ፣ ባንዲራ፣ ወዘተ. ምልክቶች እንዲመመከት ቢደረግ ግን ብዙ የመፈቃቀር፣ መከባበር እና መሰል ስሜቶች ይሰበኩ ነበር። ይህን አቅምም አፈርድሜ የከተትንው በጨካኝነትአችን ነው በማለት ድህነትን ሳይሆን አለማወቅን አምርረው ይጸየፉት ነበር። በሆድይፍጀው ትተው፣ የተሻገሩት የቆየ ጉዳይአቸው ነበር። እንደ ለመዱት ወደ መዝናናትአቸው አተኮሩ። የዘይቱን እና ማንጎ ትኩስ (ፍረሽ) ጭማቂዎች ብቻ አማራጭ ስለነበር እነእርሱን ተደባልቀው እንዲመጣላቸው በማዘዝ ወደ ፀሐይግባቷ አዝናኝ እይትአማ ጥሪ አተኮሩ። ደግ ሰዓት ላይ ደርሰው ስለ ነበር ፀሐይግባቷ መንፈስ አዳሽ ሆና መጣች። የደከመ ሙቀት፣ ግን ደማቅ ጨረር፣ ከፀሐይዋ ወደ ደመናው ተወረወረ። ብዙ ቀለምዎች ተሸናፊው ፀሐይ በደመናዎቹ ካብ ደረደረ። የደመናዎቹ ሸራነት አገልግሎት የህብረቀለሙ አሣሳል ጨዋታ ሲአስደስት፣ በራቃቸው ጥጋት ደግሞ ደማቅ ቀይ፣ ደምለበስ፣ ወደ መሆን እየተጠጋች ጀምበሯም አብራ አዝናናቻቸው። ቀይዋ ጀምበር ባልተለመደ ትልቅነት አስደምማ ስታበራ ከኮረብታው ስር ወረድ ብሎ በተንጣለለ ገላጣው የምድር ጫፍ ላይ ሆና ነበር እይቱን ታሰክረው ነበር። ደምለበስ አካሏን ተያይዞ፣ አጠገቧ ደግሞ ወደ ወፍራም ቢጫአማ አክሊል እሚከብባት ብርሃኗ አለ። እርሱን ከፍ ብሎ ወደ ቀረባት ደመናው እሚደርስ ደብዘዝ ብሎ ቡናማነት እሚይዝ ቀለም ነጥሮበት አለ፣ ከእርሱ ከፍ ተብሎ ወደ ምዕራብ ቀና እየተባለ ሲመጣ፣ አናት ወደ ሰማይ ሲንጋጠጥ፣ ቡናአማው ቀለም ጠፍቶ ደመናዎቹ የአህያ ሆድ መስለው ደግሞ ይገኙ አለ። ከእርሱ ጀርባ፣ ወደ ምእራቡ ሲዞር፣ ጭራሽ የፀሐይ ጨረር ተነፍጎ ሰማዩ፣ በሂደት ሂደቱ ጭለማ መሆን የጀመረ ሆኖ አለ። ከጨለማው እስከ ቀዩ ጀምበር የፀሐይዋ ድንቅ ፍንጣቂ እና የደመና መስተንግዶ መንፈስን ሰቅዞ ይሰርቅ፣ አልመልስም ይል ነበር። ‘ዉቧ ፀሐይግባት፤’ ሰማይአዊ ኪነ ተዓምር፤’ በመመልከቱ እንደተደመሙ የቀረበውን ጭማቂ ቀመስ አድርገው ሞከሩ። ናሆም በጭማቂው የሎሚ ጣዕም በሚወደው መጠን ስላልገነነበት አስተናጋጁን ተጨማሪ ሎሚ ቁራጭዎች አዘዘ እና ወደ ጀምበሯ መልሶ ዞረ። ሎሚዎቹ ሲመጡ መስም ተካፍሎ በእራሱ ብርጭቆ ዉስጥ ጨመቀ። በተለየ ናሆም ለሎሚ ትልቅ ፍቅር አለው። ምንም ነገር ዉስጥ ቢገባ ዋኝአዊ (ቨርሳታይል) አገልግሎቱ በፈሳሽአማአዊ (ፍሉይዲቲ) ተቀያይሮ ከቀረበው ጣዕም ጋር በመሰባጠር ድንቅ ጣዕም ሲፈጥር ስላስተዋለ መቼም ችላ አይለውም። በተለየ የበሰለ ጣፋጭ ሎሚ ነፍሱ ነው። ወደ ጀምበሯ ከጉንጭ መሙላት ቀጥሎ ዘና በማለት ተደላድሎ ተቀመጠ እና ወደ መስ መለስ በማለትም ፈታ እያለ ጨዋታ ጀመረ። አናቱ ጀርባ ሁለት እጆቹን አቆላልፎ ትራስ ሰራ እና “እሺ አባት መስ! ኑሮ እንዴት ነው?” በማለት ጨዋታ ጀመረ። መስ ፊቱ ወደ ጀምበሩ ዋ እንደ ሆነ ወደ ናሆም ሳይዞር፣ በመጥለቅ ላይ ስለ በረታች በሥስት ፈዝዞ እያስተዋላት “ደግ ነው! ተያይዘንው አለ!” ብሎ መለሰ። ናሆም ጥቂት ሰመጥ እሚል ዘገባ ይፈልግ አለ። “እና እድገት አገኘህ? ደሞዝ ተጨመረ? ወይስ ሰለቸህ? ወይስ ፍቅርህ ለሥራው ዘንድሮ ጨመረ?” መሪ ሃሳብዎች ዘርዝሮ ለ ሰማጭ ወሬ ኮረኮረው። መስ ማብራራት እንደ አለበት የአውቅ አለ። ግን በናሆም ጎን እንደ አካሉ ልቡ የለም። በጀንበሯ ሙሉኛ መስጠም ፍቅር-አጠገብ ልቡ ይገኝ አለ። ምናቡ እና ሁለንተናው፣ ዝማኔ (አፕዴት) ከተፈጥሮአዊው ትርዒት ሊገጠምለት እንደ ተወሰደ እየተሰማው ነው። በሰማዩ ትርዒት ጭንቀት ቀለል እንዲለው ተደርጎ የታከመበት መሰለው። ስምጥ እርካታ እረብቦበት አስተዋለ። ስብእናው ቀልጠፍ እና ነቃ ብሎ ማእዶትአዊ (ትራንስፎርሜሽናል) ሽግግር ሲሰራበት አነበበ። ንቅዓተህሊናው በጉጉአዊነት (ኪሪዮሲቲ) ተጠለፈ። ሰማዩን አተኮረ እና ጥቂት ቆየ። ናሆምም። እጅግ ቅጽበትአዊ አፍታ በኋላ፣ አሁን ሰርጋ እማትታይ የሆነችው ጀንበር፣ በአድማሱ ጀርባ ጠዋትን ይዛ የጠዋት ጀምበር ሆና እምትነሳበት መንደር መኖሩን አስቦ በማሰላሰል ተደመመ። “እርሱን አቆይ እና የፀሐይ እና ምድር መስተጋብር፣ ነገረ-ሥራው ሁሉ፣ አይደንቅም በእናትህ? የእግዚእአብሔር ነገር!” በተመስጦ ነፍሱ ሰርጋ ተናገረ። ናሆም በመስ መመሰጥ ፈገግ አለ። ተማረከበት። መስ ተመራማሪ ምናብ አጊንቶ ብዙ ነገርዎች ሁሌም ያጠና፣ ለአንጎሉ ድፍኑን ሁሉ ይፈለፍል አለ። በተፈጥሮ እና ከህይወት-ኅዋአዊከተማ (ዩንቨርስቲ ኦፍ ላይፍ) ምሩቅነቱ ያገኘው ዕዉቀት አስደማሚ ነበር። ወደ ሸበበው ትእይንተ-ሰማይ እያተኮረ፣ መልሶ ሃሳቡን ጠረብ አደረገው። “ማለቴ ሰው መደነቅ እሚሻ ነፍስ አለው። ተፈጥሮ ደግሞ መንክር እሚሰኝ እልፍ መንገድ ሰጥታ እምታስደምም ናት። እኔ እምልህ ግን ፀሐይግባትዋን ስሾፍ ከመደመሙ ጀርባ የሆነ የቅለት፣ ፈታ ብሎ ከነፍስህ መሰረት የመደሰት ነገር ዘልጎ ይሰማህ አለ። ለምን ይህ ነፃነት እና አለመጨነቅ ከመደሰቱ እና ማድነቁ ጀርባ እሚፈጠር ሆነ ነው ሃሳቤ?” ሣቅ ብሎ አየት በማድረግ ደመደመለት “በእርግጥ ከተጨማሪ ሃሳብዎቼ መሃል!”
ናሆም በሃሳቡ ትንሽ እየአብሰለሰለ ከፀሐይዋ አድማስ አልፋ መመጥ ኋላ የመጣውን ገጽታ በዓይኖቹ እያስተዋለ ለመደነቅ ዉበቱን አሠሰ። ምእራብአዊው ሰማይ ጨለም ቢልም፣ ከፊሉ የምስራቅ ሰማይ አሁንም በደመናው ላይ ደካማ ጨረርዎች ሰብስቦ ጸሐይ ለሰው ብትገባም ለደመናው ስብስብ ግን እንዳልገባች አሳብቆ አሳየ። ትርዒቱ እንዲዋብ አንድ በራሪጠለል (ኤየርፕሌን) ከአድማሱ እየቀረበ ሲከንፍ የተሰወረችውን ፀሐይ እንደ ደመናዎቹ ልዝዝ ጨረሮቿን ይዞ አንጸባረቀላቸው። ዉስጡ እሚጓዙ በአድማሱ እንደእሚደሰቱ በመገመት እሚሰማቸውን በትክክል ለመገመት ግን አቅቶት ተመኝቶ አለፈው። ወደ አገኘው እና የተፈቀደለት ድንቅ ትርዒት ተመለሰ። በእዛ የመመለስ ዉሳኔው ቅጽበት ግን አንጎሉ ሲሸውደው አስተዋለ። ልክ ሲዝናና የነበረው በድሃ መዝናኛ የሆነ ያክል፣ ልክ እሚበርሩት ሰዎች የደላአቸው ያክል እና መጠላት የእሚገባአቸው ያክል፣ በንቀት ስሜት ዉሳኔው በስውር ሲታጀብ አስተዋለ። የክሪስቶፈር ኖላን ጭንቀት እና እዉቅ ምክሩ ልክክ ብሎ ተገለጠለት። ደግ የመሰለንን የሞራል ዉሳኔ ስንወስን፣ ወይም ማንኛውንም ነገር ስንወስን፣ አንጎል ግን በደፈጣ ዉጊያ የገር ማታለል ባህሪ ይሰጠን ይሆን አለ። ይህም፣ ናሆም ልክ የበራሪዎቹን ሰዎች ሁኔታ ስሎ በመንፈስ አብሮአቸው እረካ። ቀጠለ እና አብሮ ሊሆን እና ለእራሱ ሊመለከት ተመኘ። በእየቅጽበት ክፍልፋዮች ሃሳቡ እየተረማመደ ወደ አሁኗ እይታ አተኩር እሚል ጥሪ አንጎሉ ሰጠው። ልክ ለእኔም ቀን ይኖረኝ ይሆን አለ ብሎ የበረራውን ጉዳይ ሲሻገር ግን አንጎሉ ኖላን እንደእሚለው የወረወራትን እጅግ ቅጽበትአዊ አገነዛዘብ አፈፍ አደረጋት። ይህም በራሪዎቹን መናቅ፣ ማቅለል፣ በዴንራቢስነት መጥላት፣ ምንአልባት መመቃኘት ወዘተ. ስሜቶች እሚገልጹት አረዳድ ጋር አጣብቆ ከአንጎሉ ሲሸኝአቸው አስተዋለ። ያሰበው አንድቀን በርሬ አይ ይሆን አለ ቢሆንም፣ ጨዋ አመለካከት ቢሆንም፣ ልክ ሲተወው ግን የተንሸራተተው እና ያላስተዋለው ሃሳብ የሰመጠበት በህቡዕ ነው። ተደብቆ። ለእዛ ነው ኖላን ስታደርጉ ስትሰራሩ፣ ስታቅዱ እንኳ፣ ከጎን አብሮ እሚደበቅ ስሜትን አስተውሉ። ‘ባቤ የሳለው በእርግጥ ሰው በግልጥ ፍልሚያን እየሾፈተረ ሲተረጉም እና ሲረዳ ግን በግል ጉዳይ ሳይታሰብ መተርጎም ወቅት ነው። እንደ “ዊችስ ሠንበት” እሚሰኘው ዕዉቅ የሰው ሁሉ የአንጎል ፈተና አስመልካች ስእል፣ ሰው በእርግጥ ስለመዶሻ ሲነገር፣ መዶሻ ሳይሆን ወይም ሚስማር ወይም መዶሻ ያሰቃየውን ስቃይ እየሳለ እሚያደምጥ አለ። ይህን ስሜት ፈልቅቆ በስቶይስት ፊት ሆኖ መቆጣጠር መቻል እና ንጽሐ ሃሳብን ወይም ቁጥጥር መከወንን ብዙዎች ይመክሩት አለ። እሚሰማን ገባኝ ከአልንው ተቃራኒ ሆኖ ያለ ስሜት ሆኖ እናገኘው አለ። ለእዛ ነው፣ አሁንም ተቆጣጠሩት አሊያም ይጎዳ አለ፣ ብሎ ይህ ጭምት ፊልም ሰሪ በትሁትነቱ ሆኖ ሁሌም እሚናገረው እሚባለው። ‘ስለ እዛ እናወራ አለን ወደፊት፤’ ቢጠቀለል፣ በአጭሩ፣ አንጎል በሰከንድ ብዙ ሃሳብ እኛ ሳናቅ ይከውን አለ ይባል አለ። ይህ ቀረብ ያለውን አሠራር መቆጣጠር ግን የገጸባህሪያችንን መቆጣጠር አቅም አመልካች ነው። ናሆም ድንገት የእሚያድግበት እና በሰል እሚልበት ትምህርትን አጊንቶ ለእረጋው ህላዌ ተጨማሪ ግብዓት ሆነለት። ያገኘውን ምስጢር ለማመንዠክ አቅዶ ዋጠው እና ወደ ድባቡ ተካፋይነት ከእብስልስሉ ተመለሰ። ግሩም ድንቅ ጸጥታ ከነፋሻአማ አየር ጋር ሲከብብአቸው ወደ አድማሱ፣ ሰማዩ፣ እና ኮረብታው ስር ወደ ተነጠፈው ዝቅተኛ የመሬት ወለል እየቃኘ ተመለከተ። እርግጥ ድንቅ መደመም መስ እንዳለው አለ። እርግጥም እርሱን ተከትሎ የቅልል እና ዘና ማለት ስሜት ደግሞ አለ። ይህን መዝግቦ አስተዋለ። ‘እዉነትም ተፈጥሮአዊ መስህብ ስብእና ዝማኔ ይሰጥ አለ፤’
ያዉጠነጠነውን ጨምቆ መላምት ቀመረ እና ወደ እሚጠብቀው አጎቱ ዞረ። “እሚመስለኝ፣ ሰው ዉበት አድናቂነት እንደ ጣትዎቹ ሁሉ ከአካሉ ጋር ተገጥሞለት አለበት። ይህ ክፍሉ ግን በኛ መደበኛ ወይም ኢመደበኛ አኗኗር ሁሉ፣ ልተገለጸም። የእኛ ሞገደኛ ሙዚቃ ወይም ስነጽሑፍ ዉጤት፣ ዉበት አድንቆ ከማሳወቁ በቀረ፣ ወደ ተግባርተኮር ነብስ መሳጭ መዝናኛ አደና ውይይት ወይም ስብከት አልተቀየረም። ቢበዛ ከእሚሆን ከስነጥበብዎች ላይ ማንፀባረቁ አልፎ፤ በመደበኛነት አይነተኛው ሀበሻ በመስህብዎች ነሁልሎ እማይደሰት ስለሆነ ደግሞ፣ የነብሱ በዉበት ብቻ እምትረካ ክፍሏ ዘላለም ተጨቁኖ ይቀር አለ ማለት ነው። ግን ነብስ ኢአመክዮአዊ (አንሪዝኔብል) ጉጉአዊነት ይነሽጣት፣ ይሞርዳት፣ ይስባት፣ ያስደስታት አለ። የአ፣ በቃ ተፈጥሮዋ ነው። በአጭሩ ሰው ሁሉ መደመም እምትሻ ነብስ ስለ አለችው ነው፤ አንዱ ማብራሪአ።” መስ ወደ ናሆም ተመልክቶ አናቱን በመነቅነቅ ለመገንዘብ በመጣር ከጭማቂው ተጎነጨ። “እየጠጣህ ታዳጊው!” በማለት አሳሰበው። ናሆምም ፈገግ ብሎ ተጎነጨ። “ትንሽ አናናስ ባይጨርሱብን ኖሮ እማ ምን ትሆኝ ነበር!” ብርጭቆዋ ገመስ እንደ አለች ፊቱ ጎን አቁሞ አናገራት። መስ ፈገግ አለ። “እና ተፈጥሮአችንን ተፃርራችሁ ሀበሻዎች አትመሰጡ አትዝናኑም ፤ እና በነብስ ታምቃችኋል እያልክን ነው? ገና ሆድአችን ሳይሞላ ወደ መዝናናት? እ?” መስ በመገረም ጠየቀ። ናሆም ጥርሱን ነከስ አድርጎ እንዴት እንደ እሚአብራራ አሰበ እና መልስ ሰድሮ መተረኩን ቀጠለ።
“ምን መሰለህ? ሆድ ተፈጥሮአዊ ነው። አበቃ! ዛፍም ይመገብ አለ፣ ትልም ይመገብ አለ፣ ሰውም! ግን ሰው ለሆድ ማሳደድ አልተፈጠረም። መጽሐፍቅዱስ እንኳ ዓለሙ የ ተፈጠረው ለአንክሮ ወ ተዘክሮ እሚለን ነው። ማለትም በሆድ ማሳደድ ብቻ እንድንጠመድ ቢታሰብልን ኖሮ ዓለሙ እሚበላ ብቻ ይሆን ነበር። ግን ዓለሙ እንደ እምታየው…” እጁን ወደ አድማሱ የደከመ ብርሃን ጭራ እና ሰማዩ አወነጫጨፈ። ፉት ብሎ ድጋሚ በሥሱ ጉሮሮውን አረጠበ እና ቀጠለ፨
“አንድም ሰው አሳሽ እና ጓጊ ነብስ ተሰጠው፣ አንድም ዓለሙ ያን አንጸባርቆ ባስደማሚ ትርዒትዎች የታጨቀ ሆነ። በሌላ ጎን ደግሞ ለምሳሌ እንደ አልኩህ እንደ እምንደሰተው እና ነብስ እንደ እምናረካው ሁሉ፣ በሌላ እይታ ደግሞ አምላክን እንድናደንቅ እና ጥበቡን እና እርሱን እንድናይበት ጭምር ይህ ሁሉ ሆነ። አንክሮት ማለት እግዚእአብሔር ታላቅ ነው ብሎ በስራው ጉብኝት መደመም ነው፤ ዓለሙ እና ዉበቷ ሁሉ የእጆቹ ሙከራ ናት። ይህን አይቶ ማነከር ደግሞ ለርሱ አንዱ ምስጋና ነው። ለእዛ ነው ዘማሪት ምርትነሽ ‘አምላኬ ሆይ.. በሰማይ የ አለህ፣ አይህ አለሁ በፍጥረትህ ጌጠኛ ሆነህ፤’ ያለችው እና ከዉቅያኖስ እስከ ነፋስዎች እና አራዊት ምልከታ መደመምዋን ገልፃ ዘርዝራ እምትዘምርለት። ለነገሩ፣ በክርስትና እምነት ስትበቃ፣ ምድርን የከበቡዋት ሌዋታን እና ብሔሞት፣ በአንዴ እልፍ እና እልፍ ዝሆንዎች ለምሣ እሚመገብ አህጉር እሚአክል የአዉሬ ዘር ወዘተ. ትመለከት አለህ ተብሎ ይሰበክ አለ። ከየት መጣ ይህ ሁሉ? መብላቸውስ እንዴት ተበልቶ አያልቅም አይራቡም ትል አለህ? ከእዛ እግዚእአብሔር ታላቅ እማይሳነውም ነው እንድትል ነበር እና የተመለከትክው አንክሮት ይመጣ አለ። አምላክ የመመገብ ጥበቡ ይደንቅህ አለ ማለት አመሰገንህው ማለት ነው። ይህ ግን ለበቁት እግዚእአብሔርንም እንዲደመሙበት ቸርነቱን እሚአሳይበት ነው። እና ለእኛም በመጠኑ ከፍተኛ ማድነቂያ መስህብዎች እንዲሁ አሉን ማለት ነው።” ፈገግ እያለ ነጥቡን ጠበብ አደረገለት። መስ በመደነቅ አድምጦ መልሶ ግን ጠየቀ። “ያልክው… ሀበሻ ተጎድቶ አለ ምናምን መሰለኝ?” ናሆም አናቱን ነቀነቀ እና ቀጠለ። “እንደ እዛ ነው። የዘረሰው ተፈጥሮ፣ የመንፈሱን መብል ከሆዱ መሳለመሳነት እንዲያስተናግደው ይጋብዘው አለ። ይህ በአመክዮ ነው። አንድም አምላክህን ታስብ አለህ። አንድም ድንቅ መጀመሪአ ያልንው የስብእና ዝማኔ ይግትህ፤ ያነቃቃህ አለ። በተፈጥሮ ዉበት አሠሳ ነብስህ እርካታ ስትሞላ፣ ጭንቀት ሲገፈፍልህ፣ እምትመለከተው የስብእና ዝማኔው ሲከሰት ነው። ይህ ጉብኝትህ ሲደጋገም ደግሞ ጭንቀት ገጸባህሪህ በቋሚነት ይርቅህ አለ። ስብእናህ ልክ አሁን በቀደመ ፀሐይግባት ቅጽበቱ እንደ አደገው ደጋግሞ እሚአድግ ይሆን አለ። በቋሚነት የሰከረ ሰው ንጽህና ማለትም አለመጨነቅ ገባልህ ማለት ነው። የዓለም ድንቃድንቅዎችን፣ የምድር ተፈጥሮ መስህብዎችን፣ የሰማይ ትንግርትአዊ መስተጋብርን ወዘተ. እምታስስ ትሆን አለ። ይህ ደግሞ እማይቋረጥ እና ቋሚ ጭንቀት አልባ፣ ቀለል ፈታ ማለትን በአኗኗርህ ይፈጥርብህ አለ እና። በሂደት ስብእናህ በእዚህ ቅጽበት ስትደሰት እንደ ወረረህ መቅለል በቋሚነት እሚከብብህ ይሆን አለ ማለት ነው።” መስ በመደመም ምስጢር ብጤ የነጸረ መሰለው እና አናቱን አወዛወዘ። “ዋው! እና መብል በማሳደድ ብቻ ድሃ ስብእና ኖሮን እማንመነደገው ለእዛ ጭምር ነው በለኛ። የሠለጠነ ተነሳሽ መንፈስ የለንማ!” ናሆም ያለውን ስለ ተገነዘበ፣ ተስማምቶ ጥርሱን በመንከስ እራሱን እየቀነቀ፨
“አዎን! ይህ ብቻ ግን አይደለም የቀረብን። ልክ ይሄ ስሜት ሲደጋገም፣ ተፈጥሮአዊ እና ሰውሰራሽ መስህብ አሳድደን ስንመለከት እና በቋሚነት ስንማረክ ስብእና ዝማኔው ወጥ ሆኖ አዲስ ልዑል ስብእና ያድግብን አለ። አንድ ነገር ይለወጥልን አለ ማለት ነው። ይህም በጭንቀት እማይወጠር ሰው አድርጎን ወደ እየ ግል ሥራዎችአችን እና ሂወትአችን ይልከን አለ። ከእዚህ መልስ ወደ ሥራ እና ሰብአዊ መስተጋብር ስትሄድ ከጭንቀት አልባ እና ቀና አተያይ አግጣጫ ሆነህ ሁሉን ትመለከት አለህ ማለት ነው። ምክንያቱም መስህቡ ሲአስደምምህ እና ስትመረምረው ነብስህ አንዱ ፍላጎትዋ ተሟልቶ ማንነትህ ከባህል እና መስተጋብርአዊ ወይም አኗኗር ጭንቅ ወደ ተፈጥሮአዊ ነባር (ዲፎልት) አርነት ተመልሳአለች እና! ለነብስህ ተፈጥሮ ስባት አሰዝናንታት ስትመለስ ቻው ትላት አለች እና። ይህ የተፈጥሮ ቻው ሰላምታ ደግሞ በድንቅ እኛ የእማናውቀው ቋንቋ እሚከናውን ነው። ለምሳሌ ግን ብንተረጉመው አንዱ ጭብጡ እንዲህ ነው።
‘በርቺ በርቺ!
እራስሽን አታሙቺ!
ተፈጥሮ ነው ዉብ፣
እንዲሁ ሁኚ አንቺ፤
በአዎንታአዊነት ተመቻቺ፤
በርቺ! በርቺ!
ናሆም ይህን ሲል መስ ከት ብሎ ሣቀ። “ዉብ ዓለም ዉስጥ በጭንቀት አትሙቱ፤ ነው መልእክቱ?” በናሆም አገላለጽ ተደስቶ ሃሳቡን ደግሞ እንዲሁ አጤነ። እዉነትም በእርግጥ የእሚሰማን ቅለት እንዲህ ያሉ ቋንቋ ተፈጥሮአዊ ዉበት ስለ እምትሾክከን ነው ብሎ መገንዘብ ይቻል አለ ብሎ አመነ።
ናሆም ቀጥሎ “ይህ መልእክትዋን ከእምገልጽልህ በላይ አጠንክራ ለነብስአችን ትነግራት አለ። አንተ ግን አትሰማውም። ግን ነብስህ ሰምታ ያዎንታአዊነት አንሳፋፊ አየር ተሞልቶላት፣ ዉጤቱን ብቻ ከስሜትህ ታይ አለህ። ማንነትህ አዲስ ሆና ታድሳ በደስታ፣ ፍቅር፣ ትጋት ለመኖር ስትዘጋጅ ቆሻሻ ጭንቀትህን ስትነጠቅ ይሰማህ አለ።” ናሆም ይህን ሲል የመስ አንጎል በግልጥ መረዳት ሆኖ አንድ ተሞክሮው ጋር ነጥቡን አስተሳሰረ። ልክ ጎንደር ከተማዋን እንደ ጎበኘ ወደ እውቅ የንጉሥ መንደር ተሻገረ። በምስል የተቀረጸው የፋሲለደስ ቤተመንግስት ከእዉነታው እማይመጣጠን ነብስ አዳሽ ድንቅ ተዓምር ሆኖ ነብሱ ስትቦርቅ በእራሱ መደሰት እና ኩራት ሲርከፈከፍበት ተመልክቶ ነበር። ሂወቴ ድንቅ መስተንግዶ ያስፈልጋት አለ ብሎ እንዲወስን ትልቅነትን እዉነትም በርቺያ በእሚል መልእክት መስህቧ ነግራው እንደ ነበረ አስታወሰ። ላሊበላን ቀጥሎ ሲመለከትም እንደ ወፍ ብረር ብረር እሚአሰኝ ድንቅ ስሜት ወርሮት ነበር። በትንሽ ነገር ለመጨነቅ እና ለመታሰር ከቶ እንደ እማይመለስ እንደ ሆነ አሣስቦት ነበር። በእርግጥ ከፍተኛ ደስታው እንደ እዚህ ዓለምን በመዞር ወይም ሃገርአችንን በመዞር ቢቃረም ቋሚ የስብእና ዝማኔ እሚአዉስ እንደ ሆነ ናሆም ሲአብራራ በመስማማት አስተዋለ፨
ናሆም ወደ ሃሳቡ መደምደም ቀጠለ። “እና እኛ በልዩልዩ ተፈጥሮ እና ሰብእአዊ መስህብዎች ተከብበንም ዞረን እማንጎበኝ እና እማንደሰት፤ እማንነቃቃ ነን። በዛ መነሾ፣ ነብስአችን ተሰውራ ትቆጣን አለ። ስጦታ ከልክለናት አለ። ነብስአችን የመንቃት እና ለካ ሂወት ዉብ ድንቅ ናት እሚሰኝ ዉድ ዋጋ ያለው አረዳድ ካመለጣት ደግሞ፣ የግለንቀት (ሰልፍቢሊትሊንግ)፣ ዋጋችንን አለማወቅ፣ ስብእና ይከብበን አለ። በታደሰ መንፈስ ዓለሙ ዉብ ድንቅ ነው፣ የተሰራው ለእኔ ነው እኔም ዉብ ድንቅ ነኝ እሚል ስነልቦና በስዉር ይሰረቅብህ ስለአለ። አያይዘህ ደግሞ ለ ማፍቀር ለመፈቀር ለመስራት ለመተባበር ትበረታ የነበርህ እንዲሁ ትደነዝዝ አለህ። ግን በጉብኝትዎቹ ነብስህ ስትነሣሳ ሰብእአዊነት ይይዝህ እንደ ሠለጠነ ሰው ትኖር፣ ታስብ፣ ሁሉን ታከብር ታፈቅር፣ አለህ። ዘረኛነት ያስጠላህ አለ። ዘረኛ ጥንብአንሳ ነው እሚለው የነቢዩ መሐመድ ቁጣ ይገባህ አለ። ተፈጥሮ አንድ ናት! ድንቅ ዉብ። መከፋፈል መለያየቱን እንደእስርቤት እንድትመለከተው ደርግህ አለ። ኢሰብእአዊነትን ትጠላ ዘንድ ግን በእዚህ መንገድ እንድትበቃ ተፈጥሮን ከነብስህ አስገብተህ በወጥነት ልትቀምሳት ይገባ አለ። አንተ ስለ ጉንዳንዎች፣ ወፍአንበሪ (ድራጎን)፣ ተኔአንበሪ (ዳይኖሰር)፣ እና ስለ ወፍዎች ባህሪዎች ተነግሮህ ብትማር ተደምመህ ነብስህ ወደ ተፈጥሮ አረዳድ ትገባ እና ሰውን ሁሉ እንደ ሰው ወደ ማየት ሁሉ ትለወጥ አለህ። ይህንን ሁሉ ሰብአዊ አኗኗር ግን አጥተን አለ። ከተፈጥሮ ስለራቅን። ያደጉ ሃገርዎች እንኳን ዜጋዎች እርስ ለእርስ ሊጣሉ እኛን ተቀብለው እንደ ሰማይቤት መሰል ደግ እድልዎች ግብዣ እና ጥበቃ ጋር እሚአስተናግዱን ናቸው። ከእራስአቸው ፈጽሞ ደግ መጠን ይደባልቁን አለ። እኛ በዘር የተለየ ሀበሻን ከምናገለው ያነሰ መገለል አላቸው። በበአድ ምድር። አንድአርግአቸው ጽጌ ለምሳሌ ሃገሩ ስትበድለው እንግሊዝ ግን ዜግነት አጊንቶ ስለ ነበር አፄ ቴዎድሮስን ገድለው ጥቂት ዜጋዎች እንደ አዳኑ እንግሊዝአዊ የተደረገ የእኛንው ዜጋ በመሰል ጥረት ይሟገቱለት ነበር። ከየትም ና፣ ዜጋነትህ ያን የአክል ነው። “እንግዳ ተቀባይ” ሃገር ለእኔ ያ ነው። ግን ተፈጥሮን ባያስሱ፣ ሰውን በሰውነቱ የመረዳት አቅምአቸው አናሳ ይሆን ነበር ባይ ነኝ። እኛ ደግሞ እርስ ለርስ እንኳ አንስማማም። የተፈጥሮ ዉበት ደግሞ አልገባንም። ልክ ሲገባን ግን፣ እንኳን ለ ዜጋ፣ እንኳን ለሃገር ትቶ ተሰደደ ሰው ፍጥረት፣ ለእንሠሳው እና አየሩ መብት እንኳ እምንሟሟትለት ይሆን ነበር። ስለ እዚህ ያጣንው መስህብ መረዳት ብቻ አይደለም። ስልጣኔን ነው። መልሱ ወደ ዉበት አድናቂነት መመለስ ነው። ስብእናህ ዋናውን ሁለንተናአዊ ጥሬ እቃውን አጥቶ አምላክን በስብከት ብቻ መቀበል ተገድዶ አለ። መጨናነቅ እሚከብበን፣ የኑሮ ድባቴውን መገፍተር እሚከብደን፣ እና ለኑሮ በትኩረት አለ መሰናዳት እሚቀናን፣ ለፍቅር እና አንድነት እምንሰንፈው፣ ለምኑቅጡ ውጥንቅጥ እምንሠጠው… ይህ ክፍተትአችን አስተዋፅዖ አድርጎብን ነው።” መስ ተደምሞ አደመጠ። እዉነት እንደ እሚሆን ወይም ተፅዕኖ እንደ አለው አመነ። “ይህ ከባድ ማጣት ነው! ሀገሬ! ይህ ትልቅ ስንኩልና ነው!” አለ። ናሆም ከጭማቂው ጠጣ እና ልቡን ጨምሮ ሰበረበት። “ይህ ብቻ አይደለም። አንድ ደግሞ ብርቱ ማጣት ገጥሞን አለ!” ሲል አከለ እና ወፍራም ፈሳሹን ደግሞ አነሳ። መስም ስምንት ክሬም ኬክዎችን ጠቅልሎ እንዲዘገጅለት እና ሂሳቡን እንዲአመጣመት አስተናጋጁን አዘዘ። ወዲአው በፍጥነት አሽጎ ኬክዎቹን አመጣ። በ ተእግ. (ተጨማሪ እሴት ግብር) ደረሰኙ ላይ ወጪወዎቹን ተመልክቶ ዋጋውን እና የሁለት ብርዎች ጉርሻ አክሎ አስቀመጠ እና ለመንገዱ ወጪ እንዲሆን መቶ ብሩን ሰጥቶ ዝርዝር እንዲመጣለት ደግሞ አዘዘ። “እና ምን ይጨመርብን ይሆን ደግሞ! ያጣንውን እንኳ በቅጡ እማናውቅ ነን ለካ!” አለ ወደ ታዳጊው ወጣት ዞሮ። ናሆም ቀጠለ። “ባጭሩ ብነግርህ ሌላው ያመለጠን ነገር ቢኖር እልፍ ነገርዎችን በምንም ሳይሆን በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ መስህብዎች ማጥናት ነበር እምንማረው! ከተፈጥሮ ብዙ የአኗኗር ማዘመኛ ጎዳናዎችን እንሠበስብ ነበር!” አለ። መስ በፈገግታ ሆኖ መደመሙን አናት በመነቅነቅ አሳወቀ። ዝርዝር-ብሩን ተቀብለው ደንገዝገዝ ብሎ ስለነበር በዝግታ እርምጃ ወጡ እና የባለሦስት እግርዎቹን አገልጋዮች በመጠበቅ መወያየቱን ቀጠሉ፨
ናሆም ማብራራቱን ከ አቆመበት አነሳው። “ለ ምሳሌ፣ ሙዓዘጥበብ ዲአቆን ዳንኤል ክብረት እንዳለው” አሽከርካሪ መጥቶ ሲቆም ተገባብዘው ገቡ። ሲመቻቹ መስ ከአቋረጠበት ሊአስቀጥል “ምን አለ ደግሞ?” አለው። “የ ሰርቆአደርዎች ስብሰባ ላይ” ብሎ ልኮት (ሪፈረንስ) ጠቅሶ ሲጀምር መስ ሁሉን መጽሐፍዎቹን ስለ አነበበለት በማስታወስ አናቱን ነቀነቀ። እዛ ላይ የግል እና ሃገርአዊ አኗኗር ዘዴ-ምክሮች ተነስተው ይንሸራሸሩ ነበር። የነጥብዎቹ መብዛት ግን የቱን ናሆም እንደ እሚአወራ እንዲጠብቅ አስገደደው እና “እሺ!” ሲል ሹፌሩም የሰባ ወግ እንደ አለ ተረድቶ ጆሮውን ጣል አድርጎ መስማቱን እና መንዳቱን ጀመረመ። ናሆም ቀጠለለት። “ለ ምሳሌ የሰው መኖሪአ እማይመስል ደረጃ እሚደርሱ በግንባታ ቆሻሻ እሚያሥጸይፉ የግንባታ አያያዝ ሀገርአዊ ስንፍናአችን አነሳ እና ከእነ ላሊበላ ግንብ አነፃፀረልን። ላሊበላ እና አክሱም ላይ ድንቅዎቹ ግንብዎች ሲገነቡ አንዲት የግንባታ ተረፈምርት ፦ የተጠራረበው ድንጋይ ክምር፣ በተመራማሪዎች ቢፈለግ ከቶ አልተገኘም። የድንጋይ ቆሻሻ ግን ግድ መቼም ከመጠረቡ ጎን ተቆልሎ ነበር። ሁለቱም የተጠረቡ ድንጋይዎች ነበሩ እና። ብናጠና ኖሮ ግን፣ እንዴት ቆሻሻ እንደ አስወገዱ እንማር እና ዛሬ ከተማ ስንገነባ አናቆሽሽም ነበር አለ። ልልህ የፈለግሁት መስህብዎች ስትጎበኝ ነብስ ከማንቃቱ ጎን ብዙ የ አኗኗር መላ መማር ትችል አለህ ነው። ለምሳሌ በዓለም የተመዘገበ ስምጡ ዋሻ አራት መቶ ሜትርዎች አካባቢ ሠርጉዶ በላቲን አሜሪካ አለ። እዛ ዉስጥ የሀር ትልዎች በእሚደንቅ ወጥመድ በራሪ ትንኝዎች አጥምደው መብልአቸውን ሲመገቡ እና ሲኖሩ የተፈጥሮ መስተጋብር እማይዛባ እንደ ሆነ እና ወጥመድ ሰርቶ ተደብቆ አጥምዶ መያዝን በሌላ ጥበብ ደግሞ ሲከወን ተደምመህ ትማርበት አለህ። በፊልቆን (ፋልከን) ወፍ ደግሞ እሚደንቅ ከሞት መነሳት ትማር አለህ። አምስትመቶ ዓመትዎች ኖሮ ወደ ግብፅ ይበርር አለ። ያም ሞቱን ስለ እሚአቅ እድሜው ሲደርስ እሚያደርገው ነው። እና እዚያ ሄዶ በሞትአልጋው አሸዋ ላይ ይተኛ አለ። እራሱን በፈጣኒት (ሃይፐር) ማረጋገብ እሳት ፈብርኮ ያነድደው አለ። ሲነድድ ሞቶ አመድ ይሆን አለ። ወዲያው እማይዛባ በሆነ አምላክአዊ ተዓምር ደመና ደምኖ ዝናብ ይዘንብ እና ይጨቀይ አለ። ከአመዱ ጭቃ አንድ ትል እጭ ይሆን እና ብዙ ሳይቆይ ይወለድ አለ። በቀንዎች ቆይታ ጥንጥ በራሪ ወፍ ከእጩ እንደ እንቁላል ጫጩት አድርጎት ፈልፍሎ ይወጣ አለ። ወፉ አደግ እስኪል እየ አኮበኮበ መብረር ተለማምዶ ከአመዱ ይነሳ አለ። ወደ ሰማይ ከፍብሎ ይወጣ እና በከፍታ ክንፎች እየአማታ ይበርር አለ። ይህ መልሶ ከተቃጠለው ፊልቆን እሚነሳው አዲሱ ፊልቆን ነው። ለሌላ አምስትመቶ አመቶች እራሱን ሆኖ ደግመለ ይመለስ አለ ማለት ነው!” መስ ትርክቱን አድምጦ ስለ ትንሳዔ ሙታን የበለጠ ማብራሪአ እሚደረገውን የፊልቆን ነገርን ተደምሞ አሰበበት። ሹፌሩም በመደነቅ አደመጠ። ናሆም ቀጠለ። “ስለ ፊልቆን አናውቅም። ቤተክህነት ምሁር ብቻ የአውቀው አለ። በአደጉት ሃገርዎች ግን እብድ እዉቀት እና አነቃቂ ትርክት ነው፦ በመደበኛ ባህል ደረጃ። ‘ከአመዱ እንደ ፊልቆን እነሳ አለሁ!’ እሚል ዝነኛ አባባል እንግሊዝኛ ዉስጥ አለ። ማንም ሲደብተው፣ ከስራ ሲባረር ወይ ሲሸነፍ፣ ከሞትም መነሳት አለ ብሎ ሁኔታውን እሚያቀልልበት መደበኛ እዉቀት ሆነ። እንዲሁ እነርሱ ጋር ንስርም ተወዳጅ ነው። ሲዘንብ እንደ ወፍዎች ከመጨነቅ እና ለመጠለል እየተራወጠ ወደ ዛፍ ከመሸሽ ከእሚያዘንብ ዳመና ጀርባ ወጥቶ በመንሳፈፍ ዝናቡን ያሸንፍ አለ። ዝናቡ ሲአበቃ ከደመና በታች ይመለስ አለ። ብቻ ለአብነት እንጂ ምንም የስነፍጥረት (ክሪኤሽን) ዉበት ተዘርዝሮ አያልቅም። እልፍ ጥበብዎችን፣ ብልሃትዎችን፣ ታሪነትን፣ ብዙ መምዎችን ከስነፍጥረት ዘረፍጥረትዎች እና መስተጋብርአቸው ትቀስም አለህ። ብልህ ትሆን አለ። ፈብራኪ ትሆን አለ። ከድንቅ ሰውሰራሽ መስህብዎችም ድንቅ ጥበብዎች፣ በትጋትአማአዊነት (ኮሚትመንት) መስራትን፣ ማቀድ-ማሰላለሰልን እና ይቻልአለን ትማር አለህ፤ ተገድደህ። ጎንደር እና ላሊበላ ጥንት የሰሩት ኪነህንፃ ዛሬ ሲቆም እና ሲአስደምም እኛ በኅዋአዊከተማዎች ለተማሪዎች እምንገነባአቸው ቤትዎች በዘመነ ሽልፍኖት (ቴክኖሎጂ) እንኳ ታግዘን ወዲአው እሚፈረካከሱ እና ወዲአው እሚአሰቅቁን ናቸው። ይህ የራስ ጀርባን እንኳ የመጎብኘት አቅምአችን የአሳጣን ሌላው ዉድቀት ነው ማለት ነው።” ሹፌሩ መዳረሻውን ነክቶ ወሬው ጥሞት ጥቂት ሂሳብ ሳይጠይቅ አደመጠ። ፈገግ ብለው ሂሳቡን ሰጥተውት ወደ ቀጣይ መሰል ተሽከርካሪ ገብተው ወሬውን መጨረስ ተያያዙ። ናሆም ቀጠለ እና ከተሽከርካሪው ሙዚቃ እየታገለ ማውራቱን ተያያዘ፨
“በ አጭሩ ከተፈጥሮ መስህብ ቁርኝት ሲኖረን ግን ሁሉ ወደ ስኬት ያመራ አለ። ባለህበት ሙያ ላንተ እሚሆን ድንቅ ነገር ትማር አለህ። ተፈጥሮ ስትደመምባት አንድም እምትሰጥህ እነ እዚህን ጥበብዎች ዝቃ እና ዝቃ ነው። ስለ እዚህ ከተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ መስህብዎች፣ ሀበሻ ስለራቀ በስራዎቹ እና አኗኗሩ ብልሃት እና ስኬት ተቀንሶበት ወይም ተወስዶበት አለ። ለምሳሌ ቀላሉ ማስረጃ እኮ ከትል ቅዱስ ያሬድ የተማረውን ማየት በቂ ነው። ሰባት ጊዜ ወድቃ መብሏን ባለመታከትዋ ስታገኝ አለመሸነፍን ተምሮ በመማሩ በረታ። ይቺ ትል ባትኖር ያሬድ ተፈጥሮ ‘በርታ በርታ…፣’ አትሸነፍ አትለውም ነበር። ባትለው ደግሞ መንፈስ ከፍቶ መብል ከሰማይ እሚአወርድ የዜማ መዓት አይገኝ ይሆን አለ ይሉ አለ። ሰር ይስሃቅ ኒዉተን ደግሞ የበለስ ፍሬ ስትወድቅበት ስለ መዉደቅ-መነሳት ሳይሆን ስለ ስህበት ተማረ። የኒዉተን እንቅስቃሴ ህግ ተወጠነ። ስንት ግኝት ከዛ እና መሰል ግንዛቤዎች ተከትሎ አደገ። ስለእዚህ ከተፈጥሮ ተምሮ ሂወትህን ማብራት አለመቻሉ ጉድለትአችን ነው። ከስብእና ዝማኔ እና ጥበብ የመቅሰም አለመቻልአችን ጋር እሚታከተለው ድህነት ኢፈጠራአዊነት ነው። አንዱ መርገምአችን የመስህብዎች ቁርኝት ማጣትአችን ነው። ስንቱ ትልቅ ነገር የፈጠረ መነሻው ትንሽዬ ተፈጥሮን መመልነት ነበር!? የመርማሪ እና ፈጣሪ አንጎል፣ በተፈጥሮው፣ መፍጠር መመራመር ይፈልግ አለ። ለዛ ደግሞ ነብሱ ከተፈጥሮ ትማር እና ትዘጋጅለት ነበር። ይህ ግን በኛ ባህል የለም እና በእዛም ፈጣሪዎች አይደለንም። በእዛ ሳቢአ አዉሬአዊነት እሚስማማን ሆንን። አንዱ የእኛ መልስ ከመስህብዎች መታረቅ ነው ማለት ነው። ቅድም በፀሐይግባቷ የተሰማህን አስተውል። ድንቅ ነፃነት እና አለመጨነቅ፣ የተሰማህ ልዩ-ህብረቀለም፣ ነብስህን ነጥቃ ዉበት እና መስተጋብርአዊ ስኬትን ስትሰብከው የተፈጠረ ነው። ልብህ የተፈጥሮ ትያትር ስለ አደመጠ ነው። የኑሮ-ድባቴህ የተገፈተረው፣ ትልቅ ደስታ የተሰማህ፣ እና ልትገነዘበው የሞከርከው፣ ለእዛ ነበር።”
ናሆም ይህን ሲል ሙዚቃውን በ መሃል ቀነስ አድርጎ እሚአሽከረክረውም ሹፌር እንዲሁ የ አደምጥ ነበር። ወደ ቤት እሚወስድ ጎዳናአቸው ላይ ሲደርሱ አስቁመው ሂሳብ አወራረዱ እና ቀሪ አጭሩን መንገድ በግሮች ተያያዙት። “እና ብዙ ነገር አለ። ለምሳሌ ጥንትአዊ ወይም ማእከልአዊ ዘመንዎች መመርመሩ፣ ድብቅ ምስጢርዎች ወይም መልእክትዎችንም ሊሰጠን ይችል ነበር። ምንም ልብወለድ ቢሆን እንደ ናሽናል ትሬዠር ፊልም የቆዩ ቅርስዎች መልእክት እሚተው ሊሆኑ ይችል ይሆን አለ። ግንባታዎች እና ቅርፃቅርጽዎች ብዙ ፍልስፍናዎች እና ርእዮትዎች ሊያስመለክቱን ሁሉ ይችሉ አለ።” ‘ስስለእዛ አንድ እንጠቁምአችሁ አለን ወደፊት፤’ መስ እያሰላሰለ ብዙ የተነሳ ነጥብ ስለነበር ቢብላላ ድንቅ ጉዳይ እንደእሚገኝ አስቦ አመነ። እሚማሩበት ካለ እሚመለሱበት እንደሆነ ባለመጠራጠር ነገሩን በልቡ አሰቀደረ እና ዘለለው። ቀዝቃዛውን አየር በማስተዋል ተመለከተ። ሰማዩን አብሮ ሲቃኝ ግን አንዳች ነገር አስተዋለ። በጣም ጨልሞ አለ። ጨረቃ በምዕራቡ አግጣጫ ብቅ ብላ ሙሉ ለመሆን አንድ ዕለት ቢቀራትም ብዙ ባልጎደለ አካል ሆና ታበራ ነበር። ሰዓት ሲመለከት ግን እጅግ ገና ሆነበት። ትንግርቱን ለውድ ታዳጊው አጋራው። “በጣም ጨልሞ አለ። ግን ገና አንድ ሰዓት አልሆንም። አስራሁለት ከሠላሳ ነው! ይገርም አለ! አይደል?” መስ እየተደመመ ያስተዋለውን አካፈለ። ናሆም ማብራራቱን ጀመረ። “በእኛ ሃገር ስነምድርአዊ (ጆግራፊካል) አቀማመጥ ሳቢያ፣ ብዙ እምናስተውለው ልዩነት የለም እንጂ እንደ ዋልታ ረገጥ ሃገርዎች ባይሆንም ቀብቁ. (የቀን ብርሃን ቁጠባ) ተፅዕኖ በገሃድ እኮ አለን!” ብሎ አብራራ። መስ ተገረመ። ስለ ጨረቃዋ ወይም ስለ በጊዜ-መጨለሙ ከአወራ ይበልጥ ተደምሞ “ምንድነው ቀብቁ.? ስለጨለማው ነው?” ዓይንዎቹን በጨለመ መንገዱ አተኩሮ ጠየቀው፨
“አዎን! በክረምቱ ጨለማ ቀድሞ ይመጣ አለ። እንደ አሁኑ አስራሁለት ሰዓት ይጨልምብን አለ። በበጋው ደግሞ ማታ አንድ ሰዓት ተኩል ስትወጣ ከቶ ደንገዝገዝ እንጂ ጭልምልም አይልም። ይህ ልዩነት በመጋቢት ብቻ እሚታረቅ እና አስራሁለት ሰዓት ጨለማ አስራሁለት ሰዓት ሌሊት እሚሆን ነው። እስከ እዛ ግን እንደ ወቅቱ ይለያይ የቀን እና ጨለማ መጠን ይዛባ እና ከእኩልነት እሚለያይ ይሆን አለ። ይህን አይተህ ለምሳሌ በበጋ መብራት ኃይል በወጥ ሰዓት የመንገድ መብራትዎች እንዳያበራ መጠበቅ አለብህ። እንደ ቢንያም ፍራንክሊን። ክረምት ደግሞ በጊዜ መንገዱ እንዲበራ ህገደንቤ (ፕሮቶኮል) መዘጋጀት አለበት። አንዱ የቀብቁ. ህገደምቤ ነው።” በማለት አብራራ። መስ በመደመም አድምጦ “ይደንቅ አለ! ይህን እንደ እዚህ አላሰብኩትም ነበር!” በማለት ወደ ቤት ገቡ። ‘ተፈጥሮን እማ ተፋትተን በብዙ ተጎድተን አለ እንጂ፤’

እቤት እንደ ገቡ፣ እራስአቸውን በጠላ እና ፋንዲሻ መስተንግዶዎች እሚ ከበበችልአቸው። መስ እሚን በተመለከተ ቅጽበት ግን በፊቷ የሃዘን ጥላ እንደወደቀ ተረዳ። ነገር ካገኛት እርግጠኛ እስኪሆን ተረጋግቶ ለማጤን እና በልጆች ፊት ላለማንሳትም በዝምታ አለፈው። እሚ የፊቷ ለዉጥ ተደብቆ ያለ መስሎዋት በልቧ እየተብከነከነች፣ እራት ማሰናዳቱን ተያያዘች። በእርግጥ ቤቱ በብዙ ባለሙያዎች የተሞላ ነው። በቀረ ጮለቅ፣ ሁሉም እሚደንቅ ባለሙያነት ከእናትአቸው አስተምህሮት ቀምመው ይዘው ወይም እየያዙ ነበር። ናሆምም መብሉን ማሰናዳት ይችልአለ። ቤተሰቡ ያለው እንስትዎች ከእሚ በቀረ፣ ገና የስምንት አመቶቿ ጢዩ እና እሷ እምትንከባከባት ጮለቅ ናቸው። ይህን እሚ እምታበላሸው እና እንስትዎቹ እስኪአድጉ እምትፈዝዝበት አላደረጋትም። ተባእትዎቹን ከእሷ የሚገኝ ማድ-ቤት-ሙያ ሁሉ ያስተማረችው ገና ከልጅነታቸው ነበር። ሁሉም እኩል ብቁ ሆነው አሉ፨
የ እሚ አንድ ምርጥ እናትአዊ ገጸባህሪ ናሆምን እንደ አስገረመው እና ሰሞኑን አንድ ሃሳብ እንዲአብሰለስል እንደ ሰጠው ነው። ‘ሃገርአችን እንዲቀየር እናትዎች መቀየር እና መሪ መሆን አለብአቸው። ልጅ ሲአሳድጉ በጓሮ እና ጓዳ ሙያ ግልአቸውን አስችለው እንዲለማመዱ እንዲሰለጥኑ ቢአድጉ፣ እሚረከበው አዳጊ ዜጋ አንድ ድባብ እሚፈጥር ይሆን ነበር። ሁሉም ወጣት ኢትዮጵያአዊ፣ በሃያ ዓመትዎች ወደ ማኅበርአዊ ትርጉምአማ ዐውድ ብቅ ሲል የእናት እና እኅት አክብሮት እና ፍቅር እሚአወጣ ይሆን አለ። እሚአገኘውን ገቢ በብልህ መንገድ እንዲጠቀም የጓዳ እና ማዕድቤት ዕዉቀት እና ብልሃት ይተውለት አለ። እሚአገባትን እንስት መረዳት እና ማክበር ይችል አለ። ችግሮቿ በአንድ ጣራ ኖረው እንደ ረቂቅ ሁሉ እሚሰወርበት እንደ አይሆን ተሞክሮው ያስታውሰው አለ። ትዳርዎች ዉስጥ ከእዚህ የተነሳ ከፍተኛ የመስመር እና መበልጸግ ኋኝነትአዊነት ሊከሰት ይችል አለ። እናቶች ከሰለጠኑ የቅርብ ወደፊትአችን ሠለጠነ፤’
ናሆም አባቱን መስ በተገቢ ስለ ተካው ብዙ አይጨነቅም እንጂ፣ የአባትም ልጅን ወደ ጓሮ ወስዶ በለጋ እድሜው በቆሎ እና ድንች እንዲተክል አድርጎ፣ ከአካሉ እኩል ሂወቱን ማሳደግ እንደ አለበት ያስብ ነበር። ተክልዎችን ህፃን ልጅ በልጅነቱ ተክሎ፣ ተፈጥሮውን እንደ እሚፈልገው አድርጎ በማጥናት እንደ ፍላጎቱ እንዲአሳድገው እንዲአርመው እንዲጠብቀው እና ሲአልቅ ቀጥፎ ለቤተሰብ ማዕድነት አንድ ምሽት መድቦ በእዛ ሂደት ልጁን ቢአንጸው፣ ዉጤቱ ትዉልድ ቀያሪ ሊሆን እንደ እሚችል ሰሞኑን አብሰልስሎ ነበር። የአ፣ ነገርን በመወጠን፣ ቀጥሎ በመንከባከብ፣ እና አሳድዶ ለፍሬ ማድረስ ድረስ፣ መጣጣር እንደ እሚገባ ያስተምር አለ። በትኩረት፣ በፍላጎት፣ በቡረቃ፣ ጨዋታ፣ እና ሀሴት ተሆኖ፣ ከምርአዊ ትምህርት በ ተግባር እሚአስተምረው ዕንቁ ስነልቦና ይህ የጓሮ ትትረት እንደ አለ ያምን አለ። ኃላፊነት መዉሰድ እሚችል ዜጋ ከቤተሰቡ እንዲአድግ፣ ዓለም በግል ኃላፊነት እንደ እምትሰራ እና በግል እንክብካቤ ፍሬ እንደ እምትሰጥ ለማሳወቅ የእናት ሚናን በትልቁ መሳል እንዳለበት አሰበ፨
ይህን በእሚአስብበት ሰሞን መነሻ የነበረው እሚአደንቀው አንድ ኢትዮጵያአዊ ነበር። ድንቁ፣ ባለሞገስ ስብእናአማው፣ ታጋይ እና አንፋሽ (ኢንስፓየረር) የ ሆነው፣ የሃገር ሽማግሌው፣ ሻለቃ፣ ኃይሌ ገብረሥላሴ ከጓደኛው፣ ሥራ ፈጣሪው፣ ቴዎድሮስ ሽፈራው ጋር፣ በ ናሁ ትመ. ጣቢአ ላይ ይህን የጓሮ አትክልት ጉዳይ ሀበሻዎች እንዲከውኑት አሳሠበ። ከተሜ ኢትየጵያዎች ጓሮአቸውን በመኮትኮት ስለግብርና ለማወቅ እና ሙያውን ማክበር ለመቻል፣ ሥራ ፈጣሪነት በቀላሉ እንዲለምዱ፣ ይህን ሃሳብ አቅርቦ አሳሰበ። “ኃይሌ ፉክክር” እሚሰኝ ተግባሬት አቅርቦ ለጓሮ ምርጥ አትክልተኛ ከመቶሃምሳሺህ ብር ጀምሮ እስከ አስረኛ ለወጡት እንደእሚሸልም አሳወቀ። ናሆም በሰማው የሻለቃው እሯጭኛ (አትሌት) ትንተና ተማርኮ በወጠነው ሃሳብ ደግ ድምዳሜ ጫነበት። ሀበሻ ለ ልጅዎቹ ይህን በእርግጥ ማስተማር ነበረበት። አሁን ግን አንቀላፍቶ ስለነበር እራሱ እንዲማር እድል ተፈጠረለት፨
ጓዳን በማስተማር ከጓዳ እሚበልጥ አለ። ሙሉ ዓለምን እና ስብእናን – ከአንድ (ኩሽና) አንፃር አድርጋ እሚ ልጆችዋን አስተማረችአቸው። ኃላፊነት መዉሰድ የለመዱት ገና በለጋ እድሜ ሆነ። እቤት ማስተዳደር ከሙያ አንፃር ችለው አለ። ቤተሰብ አስተዳዳሪ ለመሆን አይከብድአቸውም። እራስዎችአቸውን ሲአውቁ አብሮ ኃላፊነት መዉሰድ እና ግልን መንከባከብ ከእራስዎችአቸው ጋር እሚረዱአቸው ማንነትዎችአቸው ሆኑ። እሚ ደግሞ ሃሳቧ ሁሉ፣ አንድ ልጅ በግሉ ኃላፊነት መዉሰድ ከቻለ እና እራሱን ከአስተዳደረ፣ ሁሉም በጋራ ነፃ ወጣ፣ እሚል ነበር። ያ ተሳክቶላት እየሰመረ ነው። በደግ መጠን ብልሃት እና ለግል ማሰብ መቻል በሁሉ ታዳጊ ማየት እና በእዛም መኩራት ጀምራ አለች፨
ብሩ በተሸላሚነት ብቻ ሳይሆን ከእዛም በላይ በመወደድ መከበር እና መታፈር እሚአስከብራት ልጅ ሆኖ በክረምቱ የመሰናዶ ትምህርት ማብቂያ ፈተና ዉጤት ለመመልከት እንኳ እማይሰጋ፣ ግን ለዉጤት ጥራት ብዙ በመጨነቅ ሆኖ እየተሰናዳ ነው። መጨናነቁ ግን እሚአይለው የእሚአልመውን የዉጭ ሃገር ትምህርት ዕድል ገና ከመጀመሪአ ዲግሪ ጀምሮ ለማግኘት ስለ ነበር በጸና ጥንካሬ ለእንከንየለሽ ዉጤት አሳድዶ እሚኳትን ሆነ። ከዮስ ጋር በአስረኛ ክፍል ምንም ‘ቢ’ በአለማግኘት በመስቀል፣ አለፉ። አሁንም በእሚአገኙት አጋጣሚ ሁሉ ስለ ተለያዩ ጉዳይዎች ዓለምን እና ነፃ ትምህርት ዕድልዎቹን ያስሱ አለ። እሚገቡበትን ያቅዱ አለ። የቱ ኅዋአዊከተማ እና ከተማ ምርጡ ነው? ነፃ ትምህርት ዕድል የት በምርጡ መንገድ ይገኝ አለ? የቱ ክፍለትምህርት ሥራ አስቀጣሪ እና ስራ ፈጠራ አመቻች ነው? ሁሉን ይጎረጉሩ አሉ፨
ናሆምም አብልጦ ለተሻለ የቤተሰቡ እና ግሉ ወደፊት እሚጨነቅ እና ምንም ጉድለት ያላስመለከታት ሆኖ አለ። የእሚ አያያዝ በእነ ቢግ እና ባቤ እንኳ አልተዛነፈም። የቤት ስራውን እና የስነልቦና አበለፃጸጉን በብልሃት ስለያዘች፣ እርሷ በእማታውቀው ቀለም-ዓለም፣ ሁሉም በግሉ ስኬትን አመጣላት። እንደ አቀደችው፣ ኃላፊነት ይዘው ሲአድጉ አባትአቸውን አይጨምር እንጂ በመቀራረብ እና በቤተሰብ ፍቅር አድገውላት እና በማደግ ላይ ናቸው። አሁን ከመጣው ስምጥ ጣጣ በቀረ ሁሉ ሰላም ነው። እንዲህ ከአደጉ ሌላው ሂወት አዲስ ፈተና አይሆንም። በእራስሰር (አዉቶማቲክአሊ) ሁሉ ይሰምር አለ እምነቷ ነው። ምንእንደ እሚሰሩ አትወቅ እንጂ በደብተር ተከብበው እንዲቀመጡ ሰዓት አበጅታ በጸጥታ ትተውአቸው አለ። ብሩ በዉጤት በጊዜ ሲሸለም የስነስርአት ማስያዝ አሳክታ እንደ ያዘች አምና በመርካት፣ ከስነአሰራርአዊ (ፕሮሲጀራል) ትትረቱ ጎን ይዘቱን ግን በትልቁ ልጅ ላይ ጣለችበት። እርሱ ደግሞ፣ ኃላፊነት ተረክቦ ታናናሽዎች ማስጠናቱን ብዙ አልከወነም። ናሆም ዉሎው በቤተመጽሐፍትዎች ብቻ ሆነ። ወንድሙ ጋር ገና አራት እና አምስትኛ ክፍል ላይ በትምህርቱ ይዘት ያልተካተቱ ሁሉ ነገርዎች በመጎርጎር እና በማብሰልሰል በሃሳብዎች ይከራከሩ እና ይጣሉ ሆነ። እሚ ተሸላሚ ስለሆኑ አይጨንቃትም ነበር። ናሆም የሰመጠ የሊቅአዊነት ፍቅሩ እና ብቃቱ በመጨረሻ ታምኖለት ተቀባይነት አገኘ እና በታላቅ ወንድሙ ጥረቱ የግድ ከመቃኘት ነፃ ተደረገ፨
በሰባትኛ ክፍል ይህ ሲደረግለት ጭራሽ የትምህርትቤቱ አንድኛ – ዘጠናዘጠኝ አማካይ ያገኘ ባይተዋሩ ተማሪ – ሆኖ አረፈው። ሁሉን አልፎ በእዚህ ስኬት ጎዳና ሲአዘግም፣ በእዚህ ሰሞን፣ የእሚ ብልህ እናትአዊነት ስራ በ ህይወቱ አሻራ እንደ አለው ሲአውጠነጥን የወንድሞቹም ሁኔታ ተመሳሳይ ሆኖ ታየው። በሁሉ የኑሮ ገጽታዎች ላይ ነበር እሚታይ ጥረቷ የሰገገው። ድንገት ሲአስተውል በርግጥ እንደ ሌላዎች በመጫወት እና በሩጫ መፈንጠዝ ለዕድልዎች ተለቅቀው ስለ አላደጉ ይህ አስተዳደግ ብድር ከፍሎ እያስመለከተ እንደ ሆነ አመነ። እሚጫወቱት በብስል መንገድዎች እንጂ ወጥቶ እንደ ብዙዎቹ የመንገድ አዳጊዎች እና ታዳጊዎች ዕለት አውድሞ መመለስ አልነበረም። ስነስርኣትዎች በቆፍጣናዋ እሚ መከበርአቸው በቂ አመክዮነት ሆኖ ሳይጮኽባቸው ልጅዎቹም ስርኣት የማክበር መመሪአ ሆና ትታይአቸው ሁሉ ነበር። አጥኑ ብላ በማለፍ መለያየት የለም። ጎብዙ ብላ ዝም የለም። ጉብዝና በ ትምህርቱ ባይገባትም በሂወት ግን ስለ እሚገባት ታስመለክትአቸው እና ለትምህርቱ ነፀብራቅአዊ ግብዓት እንደ እሚሆን ታምን ነበር። ስለ እዛ አያያዟ ደግሞ ቤተሰቡ ሁሉ ተጠቃሚ ሆነው እንደ ተገኙ አሁን ናሆም በመመርመር ሆኖ እየተመለከተው መጣ። ያንን ኃይሌን ያደመጠበት ቀን ሲአብሰለስል ፍሬ ጉዳዩን ወደ እናት ሚና አጥልሎ ደመደመው፤ ሁሉ የሀበሻ እናት በተለየ ወንድ ልጅዎችዋን በቀረበ አስተዳደግ ስብእናውን ከጡት ማጥባት ጀምራ ማበልጸግ ከቻለ ች ታዳጊነት ላይም ከመንጋአማው አባካኝ አካሄድ ከገደበች እሚወጣው ድንቅ ዜጋ ሊሆን እንደ እሚችል፨

ይህ ሁሉ በድህነትም ተኾኖ በአኗኗር የተከበረ ብሂል በመሆኑ ብቻ የተነሳ ስምረት የሰጠ ጥበብ እና ቤተሰቡ ግን አሁን ሁሉም ያላወቀው አደጋ ተጋርጦበት እሚን ብቻ እያብከነከነ ያለ ስልጣኔ ነው። ቢሆንም ምሽቱ ግን በቀሩት ዘንድ ደምቆ ቆየ። የገጠሩ ደግ የቀድሞ-ጎረቤት ልጅዎችሽን አዘጋጂ ያላት ለፈጣን አገልግሎትአቸው እንጂ ለእረጅም ፍሰተንዋይ (ኢንቨስትመንት) አልነበረም እና ለቅጽበት በአቋራጭ ብታስኬድአቸው ኖሮ ትገላገል እንደ ነበር ደጋግማ ማሰብዋን ቀጥላ አሰበ ች። ወዲአው ግን ታላቅ ፀጸት ተሰማት። “ልጅ መዉለዴ ስለወለድኳቸው እንደ ልቤ ለማድረግ አይደለም። እንደ ፈለጉት እንዲኖሩ ልንከባከብአቸው እንጂ። ችግሬን እንዴት ልጭንብአቸው አሰብኩ! ኧረ ይቅር በለኝ!” ወዲያው ተጸጽታ ተመለሰች። ከሆዷ መነጋገሩ ቀጠለ። የሰው መሆንን ሥጦታ በጥቂት ልስጥአቸው እንጂ እንዴት የኔ ድህነት መጠቀሚአ አድርጌ መጪ ጊዜአቸውን ከአባትአቸው ላመሳስል አሰብኩ በእሚል ስሜት እራስዋን አንገበገበች። አናፂ፣ ግንበኛ፣ መኪና እረዳትዎች ቢሆኑ በጊዜ ብትገላገልአቸው መጨረሻአቸው ግን ምን ይሆን እንደ ነበር አስባ አዘነ ች። በእነዛ መንገድ ስኬት ቢገኝም በተማርን መደበኛ አስተዳደግ ባለፍን ማለትአቸው አይቀሬ ይሆን ነበር። ጥቂት ወጣ የእሚል አካሄድ ጋር መጋፈጥም ከስኬኬክ ሊያስጥልአቸው ይችል እና እንደ አባትአቸው ጠፍተው ይቀሩ ይሆን ነበር።፤ ምንአልባት። የያዘችው አካሄድ ምርጡ የእናትነት መስዋእትነት እንደ ሆነ በማሰብ መልሳ ለመደሰት ሞከረች። ማሰቡ ግን እማይፋታ ሆነ። በ ሌላ ሁኔታ መጠመድ ፈለገች፨
የ መስ መደባለቅ በአንድ ጎን ድንቅ ደስታ ነበር። የጢዩ ፀሐይ ህልም ቤቱን በጋለ ቁስአዊ ሙቀት እና የቤተሰብ መሟሟቅ እንደ አሰመረው አስተውላ ጉዳይዋን በመተው በመደሰቱ ለማተኮረወ ፈለገች። የእርሱ መቀላቀል ከሌላ በዐድ ድንጋጤ ጋር እንዲሁ ቤተሰቡን አብሮ መቀላቀል ጋር ተጓዳኝ ሆኖ የእሚ ደስታን በእዚያም በእዚህ ብትል እማይለቅቅ ሆኖ በመመላለስ መደሰቷን ከፊል አደረገው፨
መስ በሥጦታዎቹ ለቤቱ ልዩነት ፈጣሪ ስለሆነ ወደ አልተለመደው ደስታው ለጊዜው ደግማ አመዘነች። ነገርግን መስ እንደ አቀደው ከሆነ ገና ያቀረበ ው የገጸበረከቱን መግቢአ ብቻ ነበር። ገና ያሰበው ደስታ አለ። በክረምት እረፍቱ ቆይታው፣ ጊዜ ወስዶ እሚከወን ሊሆን እሚችል ተጨማሪ እቅድ ዋና ያለው ሥጦታው ሆኖ በልቡ ያለ ነው። ይህ ምስጢር ያደረገው ነበር። ሁሉም እርሱን እሚወድደው በብዙ አመክዮ ነው። አባት ስለ እሚጓጉ ለልጆቹ እንደ አባት በመሆን በደስታ ስለ እሚንከባከብአቸው አንዱ መነሻ የአባትአቸው ከእነ እርሱ መለየት እና መጥፋት ነው። ግን በመሪነት እና አስተማሪነት እንዲሁ ደግሞ ከፍተኛ ተሰጥዖ እና ዕዉቀት ስለ አለውም እሚደነቅ ክሂሎት እና ሙያ አጋሪ በመሆን ደግሞ ለእሚ አጋዥ ጓደኛ ነበር። ቤተሰቡ ደግሞ ምንም ሃብት ስለ ሌለው፣ እሚ ‘በድሃ ቤት የቤተሰቡ ሃብቱ እያንዳንዱ ግለሰቡ ነው’ በእሚል ልጆቹን በማሰልጠን የግል ሃብትዎችአቸው እንዲሆኑ እንድትታትር አንዱን ድጋፍ እና ጉትጎታ እሚሰጠው እርሱ ነበር። የሙያ፣ ክሂሎት እና የዕዉቀት ክፍያዎች ይከፍልላቸው ነበር። “ነፃነት በስብእናዎቻቸው አስርጸውባቸው የልጆቼን ነገ ካሳመሩማ እሰማህአለሁ!” ብላ በቅን መተባበር እና ናፍቆት እሚ ስለምታደምጠው፣ በእሚሰጠው አመራር መስ በልቧ ልዩ ተፈቃሪነት ተችሮት አለ። የወታደርአዊ ማንነቱን በማጋለጥ እነርሱ እንዲጠቀሙበት ከጎኗ እራሱን በማከል ለልጆቿ ከአባት በላይ የምርጥ አባት ደንብንም እሚወጣ ድንጋጌ ነበር። ልስነስርኣት በማስረጹ በተለየ አግዟት አለ። አባት-አልባ ልጅዎች ሆነው እንዳይባክኑ እና እንዳያሸንፏት ቆፍጣና ህላዌ ይዞ እንደ አባት የልጆቹን ሂወት ያበራላት የነብስ አጋርዋም ነበር። ሲቀጥል ዛሬ ደግሞ እንዳሳየው እማይናቅ የቁስ መሰረትም ለቤተሰቡ ሆኖት ነበር። ቤት ከማሟላት እና ነፃ ኩሽና፣ ከጓሮ ማቋቋም ጨምሮ፣ ብዙ ግዙፍአዊ (ማቴሪያል) አስተዋጽዖዎችን በየአመቱ እረፍት በመዉሰድ ክረምቱን ሲያሳልፍ አበርክቶልአቸው አለ። ስለዚህ የእርሱ ቤተሰቡን መቀላቀል ዘንድሮ ተቀናቃኝ ዱብዕዳ ቢአገኝም ሁሌም ግን ዘርፈቀለምአዊ (መልቲ ከለርድ) ነው፨
በጠቅላላ ለቤተሰቡ ምሠሶ እንደ ሆነውም፣ እንዲሁ ለእራሱም ሂወት የቆመ ብቸኛው ሰው እራሱ ብቻ ነው። እራሱን በተለያዩ መንገዶች በማስተዳደር ከልጅነት ጀምሮ በእርሻ ተጠምዶ በማደግ በጎን ደግሞ ከአቻዎቹ ልቆ ዘመንአዊ ትምህርት በመማር ለመለወጥ ይተጋ ነበር። በመማሩ ተስፋውን ገፍቶ መካነአእምሮመካ ለመግባት ሲደርስ ግን አመቺ ሁኔታ ጠፋ። አሳዳጊ አክስትአቸው ስትሞት፣ ከቤተሰቡ በድህነት ምክንያት ተለያዩ። እሚ ተድራ እርሱ ደግሞ ወደ አዲስአበባ ስራ ፍለጋ እራሱን ሸኘ። ወዲአው ከመዳሯ ግን እሚ በትዳር ደስታ አጥታ ከባለቤቷ መቃረኑን ተያያዘች። በተለየ፣ ባሏ ከርሷ ይልቅ እሚወድደው ብቸኛው ስራ አጋሩ፣ የልብወዳጁ፣ እና አብሮት ያደገው መክዩ በቢጫ ወባ ህመም ተይዞ በገጠሩ የቅዳሜ እና እሁድ ህክምና ስላልተገኘ፣ ድንገት በሞት ሲለየው የለየለት ንክ ሆነ። ወዲያው ከወትሮው በተለየ ልዩ-ሰካራም ሆነ። ቀድሞም ለመክዩ የሃሳብ ጉትጎታ ተረትቶ እንጂ ትዳር ፍላጎቱ አልነበረም። የማረስ ፍቅሩም ከቶ ተሰለበበት። ሂወቱን ተጠየፈ። ቀንን መሰንበት ከባድ ስራ ሆነ። ቤተሰቡን ጥሎ ብዙ ጊዜ ከተማ በመመላለስ ኖረ። ቆይቶ ወደ ከተማ ጠቅልለው አብረው እንዲገቡ በመከራ እና በሰፊ ግለማጉተምትሞ ወሰነ። ለቤተሰቡ ምርጡ መዋጮው ሆኖ ታየው። ግን ኢውለታ ነበር። በከተማ ባይተዋር ነበር ያደረጋቸው እና። እዛ የከተማ ድንበር አልፈው ነጹት ቤት እንደ ገቡ ትንሽ አብሮአቸው ቆየ። የከተማ ፍቅሩ ግን፣ አልረካም። በላጭ ከተማ ፈለገ። እሚን ተለይቶ ወደ ትልቅ ከተማዎች ልዩልዩ ሥራዎችን በመሞከር መንቀሳቀስ ተያይዞ በዓመት አንድ ሁለቴ እየተመላለሰ ለሁለት ሦስት ቀን እየጎበኛት ይጠፋ ጀመረ። በመጨረሻ በኢመደበኛ አኳኋን እንደ ተለያዩ ሁሉ በይፋ እንዲለያዩ ቆርጣ አሳወቀች። መልሶ በመጥፋት በይቅርታ መጠየቅ አሁንም መልሶ በመምጣት ልብዋን እየአባባ ስለሚአስቸግራት መኖሩ ይቀጠል ነበር። መልሶ ከአንድ ሰሞን በቀር መቆየት ይሳነው፣ ምንም እርዳታ ማድረግ ቀርቶ ስለአያያዟ እንኳ ሳይጠይቅ በወጣበት መቅረቱን አበዛ። ለእርሱ የነበራትን ታማኝነት እና ሃቀኛነትዋን ይፈታተን ጀመረ። ጮለቅ እንደ ተጸነሰች ግን፣ “ለመቆየት ተስማማ ወይም አታንገላታኝ” አለች ው። በማግስቱ አንድአንድ ሰውዎች ዘግይቶ ሲመሰክሩ ወደ ሱዳን ሳይሆን አይቀርም ያሉትን ጉዞውን አደረገ። አሁን ሁለት ዓመትዎች ጀርባ ም ስለ እርሱ ብዙም አይሰማም። የት ይሁን በምን ሁኔታ፣ ጭራሽ ይኑር ወይም ይሙት ማንም በቤተሰቡ እሚያውቀው ታጣ። መስ ግን ለእሚ ደግ ምትክነትን በከፊልነት ከዉኖ ነበር፨
እርሱም ግን ከእዚህ የበረከት ዉጣ ዉረድ ጎን ተጓዳኝ ዉጣ ዉረድዎችን መጀመሪአ ቀምሶ የመረረ ጊዜን ቀበር። ነገርግን አንድ ወቅት በግል ጊዜው፣ ጥርስ ነከሰ እና አሰበ። ስለ ወደፊቱ በንቅዓት ለመመርመር እና ለማስላት አንድ ትልምም ለመቅደድ ብቻውን ተቀምጦ አዉጠነጠነ። ኑሮ በወሰደኝ ስጓዝ ከምገኝ ወደ አንድ የህይወት ወደብ ገብቼ ባልንደላቀቅ እንኳ ሰክኜ ልኑር ብሎ በቁርጥ ወሰነ። ሲመለከት፤ በትምህርት መግፋት ከአልቻለ፣ በጊዜአዊ ስራ ወደፊቱ ቋሚ እና ብሩህ ሆኖ እሚታየው አልነበረም። ወዲአው የዉትድርና እና ጣምራመንግስቱ (ፌደራል) ህግዘብ ምልመላ ዜና ሲሰማ ፈርጣማ አካሉ እና ንቁ ስብእናው እንደ እሚደግፈው፣ ከተመረቀ በመበርታት ሰርቶ በግል እሚሰሩም ተያያዥ ስራዎች እንደ ነበሩ በበቂ ጥናት አጥንቶ ወደ ምልመላው ተመዘገበ። ተመለመለ። ከፍተኛ ድካም ባለበት ስልጠና አልፎ፣ የጣምራ መንግስት ህግዘብ (ፖሊስ) ሆነ፨
በ ተመቸ አጋጣሚ ሁሉ በጎን ምንጊዜም በግል ጥረቱ መነገድ መሞከር ግን አላቋረጠም። እንደ ባልደረባዎቹ ባለመታየቱ ተደስቶ ከከተማ ከተማ ሲዞር፣ መዝናናት አያበዛም። ነጠል ብሎ፣ በእሚጓዙበት አዲስ ከተማ ሲገባ የከተማውን ርካሽ ነገር ያጠያይቅ አለ። ሹፌሮች፣ እረዳቶች፣ ዘበኛዎች፣ ቡና አፍይዎች፣ አስተናጋጆች፣ እሚቀዋለሉ ነዋሪዎች በመቅረብ በመላ ከተጨዋወተ በኋላ ስለከተማው እና ጎረቤት ገጠሮቹ ብዙ እየጠያየቀ ያጠና አለ። አንዱ የሰጠውን መረጃ ይዞ ለሌላው ቡና አፊ ሄዶ እሚያቅ መስሎ የተነገረውን በመንገር ተጨማሪ ይጠይቅበት አለ። ብዙ መረጃዎች ከሰበሰበ በኋላ፣ በመጠኑ የረከሰ ምርትአቸውን በመግዛት ወደ አዲስአበባ ሲመለስ መርካቶ ወይም እንደ ቁሱ ዓይነት አንድ ደንበኛ ው ዘንድ ሄዶ ያስረክብ አለ። ቡና፣ ማር፣ እጅግ ብዙ አይነት ሰብልዎች፣ በርጩማዎች፣ ሌላ ጣዉላዎች፣ ሸቀጥዎች፣ የተለያዩ ልብስዎች እና ጫማዎች፣ ህልው እንስሳዎች፣ ቅመማቅመምዎች፣ ዘመንአዊ መሳሪአዎች፣ ወዘተ. ብቻ እሚነገድ ያልነካው ነገር የለም። ይህም አጋጣሚዎች ሲአገኝ ብቻ ነው። ደግነቱ በምንም ኪሳራ ከቶ አያገኘውም። ከረከሰበት ወደ እሚወደድበት ማሻገር የንግዱ መርኅ ስለ ሆነ መቶ እና ሁለትመቶ ብርዎች እንኳ አያጣበትም። አጋጣሚ-አዳኝ ስለሆነ ወጪ የለውም። ማጓጓዙም ሆነ ምኑቅጡ የንግድ ወጪም የለም። ንግዱ ደግሞ ትርፍ አያጣም ማለት ነው። ከምንም በላይ ከሰዎች ስለ ተግባባ እና በ ድረ-ሰብእ ሃብት ስላልደኸየ እርካታ እና ትርፍ ላለማጣቱ መነሾ ሆነ። አሁን ደግሞ ከዚህ ክረምት መልስ በጣምራመንግስት ፍሬጉዳይዮች ዙሪአ በመንቀሳቀስ ሲአገለግል ከርሞ ደግ ልምድዎች ስላካበተ በቅርቡ ስራ በጀመረው በኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር መስመር አገልጋይ ሆኖ ተመድቦ እሚሰራ ተደርጎ አለ። ባቡሩን በክልልዎች ህግዘብዎች መተዳደር እማይተው የጣምራመንግስቱ ድርሻ ሃላፊነት በመሆኑ አንድ የመንቀሳቀሻ ዕድሉ ሊሆንለት ነው። የባቡሩን ደህንነት ለማጀብ ሲመላለስ ግን በጎን መነገድን ከአሁኑ እየአቀደበት ነው፨
ለ ብሩ ደግሞ መስ ብዙም ስምጥ ግንኙነት አያመነጭም። አምና እንኳ መጠነኛ ሠቤ (ድሮይድ) ስልክ ሲገዛለት ብዙ እንደ እሚቀራረቡ ቢገምትም የአ አልሆነም። ብሩ ከናሆም እና እሚ በቀር ለማንም ቁጥብ እና እራሱን በማራቅ አስከባሪ ነው። በዝምታ እና ልዝብተኛነቱ ስለሚበረታ ብዙ እሚሰምጥ ቁርኝት አይጋብዝም። ዩሱፍ ብቸኛ ብሩ ፈልጎ እሚቀርበው ሰው ነው። አሁንም ያባት እጦት ስነልቦና ሸብቦት እንዲህ አድርጎት ከሆነ ማወቅ አይቻልም። በ መስ ግን በመጠኑ ከመደሰት በዘለለ እንደ ቀሩት ስለ እማይቦርቅ ያባቱ ጎኑ አለማደግ ከምር ጎድቶት ሊሆን እንደ እሚችል ያስገምት አለ። ሰው አለማመን እሚከሰተው መቅረብ ያለበት ሰው ቀርቦ እማይገኝ ከሆነ በሚከሰተው መጎዳት ሌላን ማመን ስለሚአስጨንቅ ነው፤ አንዱ ምክንያት። ብቻ ከቅርርብ በዘለለ በኃላፊነት ቸልታ እና ትምህርት ወይም ስነምግባር ላይ ስጋት እሚባል ነጥብ አስመልክቶ ስለ እማያውቅ የእሚ ስጋት ባህሪ ው ነው በእሚል ቀለል ብሎላት አለ። በመጠኑም ቢሆን ግን መስ ቢያንስ እንደ ደግ አጎት ግን በብሩ እሚወደድ ነው፨
ለ ናሆም ደግሞ ከማንም እሚለይ ነው። መስ የእብስልስልታአዊ (ኢንተለክቹዋል) ጓደኛ፣ ሂወት አሰልጣኝ፣ መካሪ እና አማካሪ፣ አባት፣ ወንድም፣ መደበኛ ጓደኛ ጭምር ነው። በብዙ ቅርርብ እሚተሳሰሩ ናቸው፨
ለ እነ ቢግ እና ታናናሽዎቹ የጸና አባትአዊ ምትክ ነው። በቆይታው መደሰት በመኄጃው ማልቀስ ድረስ እሚስማማአቸው ብቸኛ ህይወትን አብሪ ዓዉራአቸው (አልፋ) ነው። እሚመኩት፣ ነፃነት እሚምጉት፣ ግልትምምን እሚአዳብሩት፣ ደስታአቸው እማይከነክን አቅም ይዞ እሚጨለጠው፣ የወንድነት ምሳሌን እሚአገኙት፣ በመስ እንከን የለሽ አባትአዊ መቀላቀል ነው። መስ ደግሞ በግል የራሱ ቤተሰብ ገና ስለ ሌለውም እስከ አሁን ሰክኖ ባለመቋቋሙም፣ ያሉት ሙሉ ቤተሰብ እነ እርሱ ብቻ ነበሩ። ቤተሰቦቹ ስለሆኑለት እርሱም በሰፋ አስተሳሰብ አድማሱ እና ቅንስብእናው የቤተሰቡን አላባልዎች እንደ ወለደአቸው ማስተናገድ እና ከተጨበጠ አቅሙ በመዝለል ድጋፍ መስጠት እንጂ ማነስን አድርጎ አያውቅም። ከስብሰባ፣ ስልጠና ወይም ጉዞ አበል ሲቀበል ለእሚ ሸርፎ በመላክ፣ ለልጆቿ እንድትተርፍ ጥቂት እገዛ የአደርግ ነበር። በተለይ በአካል እንዲበለጽጉ ፍራፍሬዎች እንድትገዛ አብሮም ስለበሽታ ተከላካይ እና ገንቢ መብል ጥበብ እንድታውቅ አብሮ ይሰብካት ነበር። እንደ ጤፍ ያለ አንድ ሰብል ብቻ ለቀለብ ፍጆታ ከመግዛት ጤፉን ቀንሳ በረከሱ ሰብልዎች ስነአመጋገብአዊ ፍትህ ወይም ትርፍ አጊንታ እንድትደመም እሚአስችል ጉትጎታ በስሌትዎቹ ይነግራት ነበር። “ለልጅዎችሽ ዛሬ ባንቺ ሚዛን መደረግ ያለበት ግዴታ እንደ ሀበሻ ሳይሆን እንደ ተማረ መመገብ እና በአካል እንዳይቀነጭሩ ይልቅም እንዲገዝፉ እና እንዲቆነጁ ማድረግ ነው። ወደፊት በስነልቦና እንዳይጎዱ ማድረግ ቻልሽ። ወደፊትአቸውን አጸፏዳሽላቸው። የእናትነት ነገር ደግመለ ወደፊትን ማስመር እንጂ እንደ በግ እና ከብት አጥብቶ ማሳደግ ብቻ አይደለም። ሲአድጉ ደግሞ እራስአቸውን በጭንቀት ባለመዋጥ እሚአበለጽጋቸው የዛሬው የማለዳ አመጋገብአቸው ነው። አድገው ልባም ይሆኑልሻል። ያመሰግኑሽ አለ… ሌላው አለም እሚያድገው አንድም በእዚህ የሰላ አያያዝ ነው..አይዞሽ እህቴ…” በማለት ባለመታከት ሲአበረታታት ነበር። የአካል ግዝፈትን ከመብል ጋር አገናኝቶ በእዛ መጠን መጨነቅ የጀመረው በእርግጥ በህግዘብ ስልጠና ወቅት ከብዙ አካባቢዎች የመጡ የምእራብ ኢትዮጵያ ዜጋዎች ጋር ተገናኝቶ ግዙፍ አካልአቸው ከአመጋገብአቸው ጋር እሚገናኝበት ምስጢርን በመመልከት እና አብሮአቸው በተወያየ እና ባስረዱትም ጊዜ ነበር። እዚአ፣ በባህልአቸው በመመገብ ሂደት ያለው የሀበሻ ተራው የእንጀራ ፍቅር አይደለም። ያ የይዘት ጥቅም እንደሰጣቸው ከአቻ ሰልጣኝዎቹ ተማረ። ከመሀል ሀገር የተለየጀ ሆኑ። መሀከልሀገር ግን በሽሮ እና እንጀራ የተጠለፈ ቅንጭር ትዉልድ አምራች ነው። ልእለብዙሃኑ መሀልሀገር ኢትየጵያአዊ በኬንያዊያን እንኳ እሚናቅ እሚንቋሸሽ ሰውነት ያለው ነው። የአንጎል እና አካል መበልጸግ ከአመጋገብ ሲቀዳ እና የመሀከልሀገር ኢትየጵያ ደግሞ በእንጀራ አያያዝ ተሸንፎ መብሉ ንጥረነገርዎች ስለ እሚአጣ በአመጋገብ ሊወገድ እሚችል አካል መቀንጨር ድረስ የደረሰ ስነአመጋገብአዊ ቀውስ ሲፈጠር አስተዉሎ አስተዋዩ መስ ይናደድ ቀጠለ። ከእዛም፣ ይህ ቁጭት-ሃሳቡ ጠርቶ በልቡ መቀመጥ ጀምሮ፣ ምንም ቢከብደው እሚን ለአመል ያክል ደግፎ ስነልቦናአዊ ዝግጅትዋን ከመኮርኮር እና ማሳመን ቦዝኖ አያውቅም። ሂወቱ ላይ የተመለከተውን ሁሉ በመቀመር ወደ ልጅዎች እና መጭ ትዉልድ ማዞር እማይደራደርበት የማን መሆኑ አካል ነው። ‘ምንም ይሁን ምን፣ የሂወት ልምድ ተቀምሮ ወደ ታናሽ ትዉልድ ከአልወረደ ታናሹ ትዉልድ ከዜሮ ጀማሪ ነው፤’ ይል ነበር። ያ ትዉልድ ደግመለ ከአዲስ እሚጋጋጥ በመሆኑ ሃገር እንኳ እማይታድግ ነው ይል ነበር። ይህ የሃገርአችን አያያዝ መሆኑን እና ወጥ አያያዝ በጋራ ህይወትአችን እንደሌለ ያምን ነበር። “ገ መች የደርግ ታሪክ እንኳ ገብቶን በጎበጎው ቀሸለ? መች ቀኃሥ. መሠረትአቸው ቀጠለ?” በማት ይበሳጭ እና ከመንገድዳር እየመጡ በይዘትየለሽ ማእረግ ሃገር እናስተዳድር ብለው በእሚያከስሩን ስነዉሳኔኛዎች (ፖለቲሻንስ) ተበሳጭቶ ሃሳቡን ይዘጋ አለ። ነገ፣ ዕድል ሲገኝ እነእርሱን ለመቃወም እሚጓዝበትን መንገድ ሁሉ አድፍጦ ይቀምርበት እና ይቀመጥ አለ። ለጊዜው ወደ ታናሾቼ እንደመንግስት ባይደረስም እኔ ልድረስ ይል አለ። ወደ እሚ ስልክ ያነሳ አለ፤ በእሚቻለው ሁሉ። እሚ ደግሞ ለልጆቿ መጪአቸውን ከመደገፍ እና ማበርታት በዘለለ ማድረግ እምትችለው ምንም ስለሆነ፣ ዉርስ እምትሰጠው ስለሌላት እና ለልጅ መብቃት እሚመከር ሁሉ ስለሚአንሰፈስፋት፣ ከልቧ ሆና ያጣችውን በልጆቿ የመመልከት ህልሟም አግዟት የእምትመከረውን ትሰማ እና በትኩረት እና ብልሃት ትተገብር አለ ች፨
ገና ፋሲካይት ሊገቡ ጀምሮ፣ የ አካልአቸውን መጠንከር በተግባር እሚ በተመለከተች ወቅት ሰውነትአቸው እንዲበረታ፣ ጤና እንዲአገኙ፣ አንጎልአቸው እንዲታነጽ፣ እና ቆዳአቸው በተፈጥሮ እንዲዋብ ዋጋ መክፈሉን ከ እዛ ወዲአ አበክራ ተያያዘች። ጤና-ቅጥያ (ሄልዝ-ኤክስቴንሽን) አገልግሎት ሰባኪዎችም ስለመብል አልሚነት እንጂ ተራ የሆድ መጥገብ ብቻ እሚመራው አመጋገብ አካልቦናዊ (ፊዚዮሎጂካል) ጉዳቱን ነግረው ሲአስተምሯት አድምጣ ልጅዎች በተለየ መንገድ አጥጋቢ ሳይሆን የለማ በመመገብ ለጣዕም እንዳይጨነቁ አድርጋ አሳደገች። ይህን አጥብቃ እንዳቶድቅበት የተያያዘችው ደግሞ አንድ ክረምት ላይ መስ የሊቀሊቃውንት (ፕሮፌሰር) በፍቃዱ ድጋፌ ከጋዜጠኛ ፍቅርተ መኮንን ጋር በ ኢሳት ትመ. የከወነውን ሆድአባቢ ዉይይትአዊ ቃለመጠይቅ ቅጂውን ከአንድ ሀገርወዳድ እና ደግ ነገሮች አንዴ ተወርተው በአየር እንዳይቀሩ በግሉ ከእሚታትር እና በጡመራ ገጹ በእሚከትብ ወጣት ጦማሪ ድረገጽ አጊንቶት አውርዶ ካመጣላት እና ካስደመጣት በኋላ ነበር። ምሁሩ፣ ልጆች ቤተሰብአዊ አመል ሆኖ በሆድ ሞይ እንጂ በአልሚ መንገድ ተመግበው ስለማያድጉ አንዱ የኢትዮጽያ ምጣኔሃብት ዉድቀት ምንጭ ሆኖ እሚከሰት ጉዳይ የቅንጭር ኢትዮጵያአዊነት ጉዳይ እንደሆነ በመረጃ ለወጣቷ ጋዜጠኛ እሚአብራራበት ነው። እንኳን ኋላቀሩ ገጠር፣ ከተማ ውስጥ የ2012 ዓም. ኢትዮጽያ እንኳ፣ አርባ እጅ ከተሜ ታዳጊዎቿ ቀንጭረው አሉ አለ። ማለትም፣ ገና ከአሁኑ ከተመረተው ከተሜ ታዳጊ አርባ እጁ፣ አካል እና አንጎሉ የተዳፈነ ደግ ጥቅም በመደበኛው አካሄድ እማይሰጥ ክፍለማህበረሰብ እንደሆነ አረዱ። እና ገና አድጎ ወደፊት ከእሚመጣው ወጣት፣ ይህ ግማሽ እሚጠጋው ወጣት እጅ፣ ገና ስራ ፈጣሪ እማይሆን እና የሀገር እዳ የመሆን ያክል እንደማይሳካለት ተደርጎ እንዳደገ ሊቀትምህርቱ አብራሩ። ይህን በቀኃሥ. ከ1950ዎቹ ወዲህ ዘምኖ የተቀየረ የግብርና አያያዝዛችን በደርግ ስልጣንመዉረስ ትልምአግጣጫ (ፖሊሲ) እና ኢህአዴግ. እዉርነት እንደተውንው፣ ዛሬ ሰማኒያ እጅ ግብርና-መር ሃገር ምጣኔሃብት ብዙ ገቢ ከግብርና ምርቶች ዉጭ-ሽያጭ ቢሰጠንም ያንቀላፋው መንግስት ግን ለግብርናው ከትርፉ መልሶ እሚሰጠው ስለሌለ የሦስትሺህ ዘመኖች ግብርና ሽልፍኖት እንደኋላቀርነቱ እንዳልተነካ፣ ወዘተ. ሊቀሊቅአዊ ምስክርነት ሲሰጡ፣ እሚ ምኑም ምሁርአዊው የመረጃ ትንታኔ አልገባትም። መብል አልሚ ባለመሆኑ ግን ልጆችን እንደእሚያቀነጭር የተናገረው ልቧን ሰንጥቆት ተከፍታ እና ተረድታው ነበር። ይህን ንግግር በመስ ተስ. ሰምታ የሊቀሊቆቹ ድምጽ አየሽማግሌም ድምጽ ስለነበር “ ለነገሩ እሚሞቱ አዛውንት ናቸው አይዋሹም!” በእሚል ለማመን አልቦዘነችም። “አመጋገብ ለልጅ እሚአጠግብ ተራ መብል ሳይሆን፤ ለነገ የአካል እና ስነልቦና ወለል ስለሚሆናቸው ሳትሰንፉ አልሚ አልሚውን ስጡ ነው! አይ ማወቅ ደጉ! መች ስሰንፍ ልገኝ ከንግዲህ እናቴ!” እሚ ድጋሚ ስታረጋግጥ ምላሿ ያ ነበር። “ሲያቅተኝ እንኳ የወደቅኩት በነገው የብዙ ልጆቼ መጭ ሂወት እና ባገሬ ምጣኔሃብት ላይ ነው በእሚል እጋጋጣታለኋ እንግዲህ!” ጨምራ ያን ካለች በኋላ መልሳ ግን ክው አለች። “እኔ ምለው ግን መስ? የሃገሪቷ ወደፊት ገና ካሁኑ ጨፍግጓል በልጆች አመጋገብ ብለው ምነው ምጣኔሃብት እሚሉትን ነገር ለመታደግ ይሄ ትልምአግጣጫዎች እና ህጎች አላቋቋሙ? ጤና-ቅጥያዎች እሚሰሩት ጥቂት ምክር እንጂ ገና ምኑ ተነካ እንዲህ ከሆነ? ለምን ጥቂት የሠመጠ አያያዝ በጉዳዩ አይዘረጉም ከእሚያደነቁሩ ህዝብ?… አንተ ባትኖር መች እሰማቸው ነበር እኔ ራሱ ለነገሩ?” ብላ ጠይቃም ነበር። “አንቺ መሪ እክቶኚ ይሆናላ!” መስ አሽሟጥጦ አለፈ። ብቻ የአመጋገብ ፈላስፋ የሆነው፣ እውቅ ተመራማሪ ባይሆንም ነበር። በቂ መረጃ እና ተሞክሮ ስለያዘ እና ነገን ላሻሽልበት፣ አኗኗርአችን ወጥመዱ በእዛ ነው እሚሰ ረው ብሎ ስላመነ ብቻ። ስነአመጋገብ አማካሪነትን የተቀዳጀው፣ ደግ አላሚ ከመሆኑ ብቻ ነበር። ይህን ሁሉ መሰረት እና ድጋፍ እሚቸረው መስ እንግዲህ ይህ ነው። ማጥናት እና ለመማር ሃገር ማሠስን እሚወድድ፣ በአንክሮትአዊ (ክሪቲካል) ማውጠንጠን ነገር እሚአሰላ፣ ከፍተኛ ወደፊትን የመሳል አቅም ያለው፣ ወደፊትን በስምጥ ሃልዮ ማጠንጠን እና ማስላቱ ጀርባ፣ የወደፊቱን ምስል በምናቡ ስሎ ለመረጠው የነገ ዉስጥ ዉጤት ዛሬ በአንድ ያገኘው አጋጣሚ አንፃር ተደብቆ በትጉህ መታተር የሚፋለምለት፣ እሚስለው ወደፊት ክፉ ጎን እና ብሩህ ጎን ከአለው ክፉው እንዳይመጣበት ብሩህ የሆነው ጎን እንዲገጥመው እሚንቀሳቀስ፣ ቆጣቢ የሆነ፣ ይህ ብቻ ከእልፍዎች አጠገቡ ከእሚኳትኑ ለይቶት በአሁን ወቅት እየከፈለው ሊአኮራው የደረሰ ሃልዮታው (አቲትዩድ) መለያው የሆነለት፣ ከጥበቃ ወደ አፍ እሚሻገር አኗኗር ለእርሱ ወለሉ እንዳይሆን አዲስ ወለልን እየጣለ ያለ…ድሃ ኢትዮጵያአዊ ነው። ወደ ቤተሰቡ ይህ ብርቅ ወዳጅ እና አባል ዓዉራነቱን ተላብሶ ሲቀላቀል፣ አብሮት ሃዘን ስለተቀላቀለአቸው፣ እሚ በተከፋ ልቧ እንደ ተሰነጠቀ ሆና በማስመሰል እየተሳካላት ፈገግ ፈገግ ስትል ምሽቱ አብቅቶ ወደ መኝታ ተኼደ፨

፨፨፨ ፨፨፨ ፨፨፨

By Binyamhailemeskel

Hey there! If you want to know about me, I just like fun, commonsense wisdom, and human love. Let us live a bright today changing tomorrow into brighter.
Regards,

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s