Categories
My Outlet (የግል ኬላ)

ምእራፍ-፪

መስፍን ጎንለጎን ምእራፍ ፪፨

፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
፪ ዓዉራውን መቀበል

የምእራፉን ተአዶ. (PDF).

ደቡብምስራቅ መስመር ላይ ከአዲስአበባ 300 ኪሜ.ዎች ተምዘግዝጎ እሚገኝ ወጣት ሰፊ ከተማ ፋሲካይት ነው። ከሁሉ ቀድሞ ታላቅ እና ልዑል ለኢትዮጵያ እሚገባ ሃሳብ በሆነው በደርጉ (መንደር-)ሰፈራ መርሐግብር እንደ አንድ መንደር ተጠንስሶ ዛሬ ዐምደ ከተማ ባይሆን እንኳ እማይከፋ ከተማ ሆነ። በብሔረሰብ መለኪያ ሁሉን እየመዘነ እንደጎዳ መንግስተ-ኢህአዴግ ለእዚህ እና መሰል ከተማዎች ያስቆጠረው ዉለታም አለ። ከከተማው ራቅ ብሎ ከሰማይ እንደ ወረደ ናዳ ከደቡብምስራቅ መዉጫው አንድ ኅዋአዊከተማ (ዩንቨርስሲቲ) ዋና ቅጥሩን አድርጎ ከኢህአዴግ. ወደ ብልግና መቀየር ቀደም ብሎ ተሰርቶላቸው ነበር። ግን ወግ ያየ መንገድ እንኳ ገና ከተማው አልነበረውም። ዓዉራ መንገዱ፣ ብቸኛው ዘመንአዊ መንገድ እንኳ፣ ደግ አይባልም። ቤተመስተናገጃ (ሆስፒታል) እንኳ የለም። መለስተኛ-ቤተጤና በጫካ መሀከል አራዊት እሚአክም ይመስል ከከተማው እርቆ አራት ኪሜ.ዎች አልፎ አለ። ከተማው እንድትሰፋ እና መሀከል ሆኖ እንዲያገለግል ነው የራቀው ቢባልም አጠገቡ ግን ተራራ እና በሃያ አመቶች በእዛ አግጣጫ ያልሰፋ ከተማ ስለሆነ ህክምናውን አቅራቢያ ማግኘት አይቻልም። ሦስት ቤተመድኃኒትዎች ብቻ በከተማው አሉ። መንገድዎች በክረምት ጨቅዪ ናቸው። ከተማው መዝናኛ ማዕከል ወይም ይፋ መጽሐፍቤት(ዎች) አያቅም። የከተማው ቤተመዘክር ዉስጥ ታሪክ፣ ከባቢ ተፈጥሮ ወይም ባህሉ ተመዝግቦ ለእይታ አልተቀመጠለትም። ነዋሪዎቹ (ወይም ጎብኚዎች እና ለምሳሌ ዘጠና ዓመቶች ኋላ ያለ መጭው ዘመን) ከተማውን ማን እንደመሰረተው እና ማን ምን እያደረገለት እዚህ እንደደረሰ እሚያቁበት ይፋ እድል ከቶ የለም። የከተማው ታሪክ በማዘጋጃው እንደ አንዱ ስራው ተደርጎ ላልተመዘገበ ከታሪኩ ባሻገር መጪው ጊዜውም ገና ባይመጣም ሲመጣ እንኳ ታሪክ እማይሆን ነው። ወጣትዎች፣ ህፃንዎች፣ ጎልማሳዎች፣ አካላዊ ተስኖ ያለባቸው፣ ወይም ማንኛውም ክፍለ ማህበረሰብ እሚገለገልበት ልዩአማአዊ (ስፔሻላይዝድ) መስተናገጃ ተቋምዎች፣ ማዕከልዎች ወይም ሥፍራዎችም አያቅም፤ በከተማው እሚተላለፉ እነእዚያ ዜጋዎች እና ጭራሽ መስራቾች መሀል ሆነው እሚኖሩ ግን ብዙ ናቸው። የአየርላንድ መንግስት ከአየርላንድአዊያን፣ የሰበሰበው የራሱ ሃገር መተዳደሪአ ግብርን ሰንጥሮ፣ ለእዚህ ሀበሻ ከተማ፣ ከተማ ፍሳሽ ማስተናገጃ ስነስርአት አበጅቶለት አለ። ትልቁ የተጠና ከተማአዊ ቀለም ያ ጥረት ብቻ እንደ ሆነ አለ፨
ብቸኛ አንድኛ ደረጃ ትምህርትቤት – መስኮት ትምህርትቤት – በተዋህዶ እምነት ዓለምአዊ እኩያ ቤተትምህርት ግንባታ – መልከብርሃን መነሻ ደረጃ ትምህርትቤት – እገዛ ትንፋሽ አጊንቶ አለ። በቀረ፣ ሰፊው እና የተጨናነቀው መስኮት መነሻ-ደረጃ ቤተትምህርት፣ ብዙ እየፈለጉ የያዙት ባይተዋሩ አሽከራቸው ነው። ናሆም ከጭንቅንቁ እሚዛመድ አንድ ገጠመኙ ግን ለአንድ የሂወት መርኅ አድርሶት ነበር። የተዓግ. (የተባበሩት አሜሪካ ግዛቶች = USA) ኢተድ. (ኢመንግስታዊ ተራዶ ድርጅት = NGO) ለትምህርትቤቱ ከአስረከበው ልዩልዩ ለቤተመጽሐፍ የተወሰኑ ሥጦታ መጽሐፍዎች ነበሩ። ሸላሚ ደቦነቶች (ኮሚቲ) ከቤተመጽሐፎቹ ሥጦታ መጽሐፍ መርጠው በምትኩ የሽልማት ግዢ ወጭ አስወጥተው ተማሪዎች ሲሸልሙ እና ናሆም ትምህርትቤቱ ጭንቅንቅ አድርጎት አመቱን ማጠናቀቁ ስለነበር፣ በሽልማት ቀን ሄዶ ሳይቀበል ቀረ። ደጉ ምርጥ መጽሐፎች በሙሠኛዎቹ ተሰረቅኩኝ ስላለው፣ መጽሐፍ ሽልማቱ ዳግም አጓጉቶት ለመጠየቅ በንጋታው ሲመለስ፣ በህቡዕ ክልከላቸው ዛሬነገ ዉሰድ ብለው ሊቀደቦነቱ (ቼር ኦፍ ኮሚቲ) እንዲመላለስ ሲአደርጉት በመጨረሻ በመበሳጨት ንቋቸው ተወው። እሚያከብራቸው ጎልማሳ መምህሮቹ ግን ባዩት ቁጥር እሚአፍሩ ሆነው በመጨነቅአቸው ደግመው ሲያስጨንቁት፣ የልፋት ሽልማቱን ተነጥቆ ገና የመጨነቅ እና መሳቀቅ ነገር ላይ መዉደቁ አንድ ፍልስፍና እንዲያሳድግ አረገው። መመረቅ። ‘ወደፊት ስለእርሱ እነግርአችሁ አለሁ፤’ እሚያፍሩት እና እሚያስጨንቁት መምህሮቹ፣ ሲገናኙ ምንም እንዳልተፈጠረ መቁጠር ጀመረ። እማያውቀው መንገደኛ እንዳለፈው በዝምታ በመምህሮቹ መታለፉ ተስማማው። ከአሉታአዊ ኩነቱ ተመረቀ፨
‘መመረቅ ማለት ከገጠመ አንድ ከንካኝ፣ ሰላም ነሺ፤ ወይም አስፈንጣዥ ሁሉ፤ ጉዳይ አንድ መዝጊያ ድምዳሜ (በቀላል ሊቀበሉት) አድርጎ አበጅቶ ጉዳዩን መጠቅለል ነው። እና ወደ ዕሙንአዊነት (ሪአሊቲ) ለቀጣዩ ኑሮ ተመልሶ መግባት ነው፤ ሃሳብ ይዞ ከመብከንከን፣ ዘግቶ ወደ ነዋሪነት ማዝገሚአ ጎዳና፤’ መመረቅ የሂወት ትልቅ መርኅ ነው። በኑሮ ግብግብ ሂደት፤ በአረዳድ፤ ወይም አተያይ ዉስንነት፤ የሰው ዘር በጭንቀት ሲጠቃ፣ ነፃነትን አለመልቀቂያ እና ከሁኔታዎች ጋር አለመጣበቂአ ማምለጫ ሽንቁር፤ መመረቅ ነው። የደምድሞ መሻገር ቅኔ። ናሆም ዉጤቱ ሲያረሰርሰው፣ ዘረሰው ሁሉ ያስፈልገዋል ብሎ ያስብ ሁሉ ነበር። ካልሆነ፣ ሰው በገጠመው አንድ ደግ ወይም ክፉ ኩነት ሲብከነከን በነገሩ አንጎሉ ይተበተብ እና ሂወትን ይዘነጋ አለ። ሂወት ግን ስነሂወትአዊ (ባዮሎጂካል) ነው። አዎንታአዊነት ብቻ አኗኗር ነው። መብከንከን አዎንታአዊነት ገፋፊ ነው እና መመረቅ ትልልቆቹ የመኖር ጥበቦች መሀል ነው፤ የነገሩ አብከንካኝነት ባልተገባ ረጅም ቆይታ ወይም ዘላለም መቆየት ጭራሽ ልብን ይቦረቡር እና ከኩነቱ ጎጂ (ወይም ጠቃሚ ሁሉ) ገጽታ ሌላ ወደ አዲስ እንዳናማትር ያጠምደናል። ያ፣ ቋሚ ቅጣትን እራስ ላይ ማቋቋም ነው። ‘መመረቅ ግን በሂወት መራመድ እንዲቻል የገጠመን ረግጦ ወደ አዲስ ምዕራፍ ለመሻገር የኑሮ እግርዎች መላክ ነው።’ በሰው ወይም ነገር ላይ ቅናት መንፈስም ላለመያዝ ያግዝ ሁሉ አለ። ስለ እምንመረቅ፨

ወደእዚህ ብዙ የጎደለው ከተማ እሚ በረከትን ተከትላ ልጆቿን አስከትላ ስትመጣ፣ ከተሜ አኗኗር ይከብድ እንደሆነ ቅንጣት መረጃ አልያዘችም። እንደ ገጠር ነበር የመሰላት። ጭራሽ ቀድማ ማቀድ ጽንሰሀሳቡን እንኳ አታውቅም። በረከት ግን በገጠራማው የከተማው አዋሳኝ የሠፈራ ሁዳድ ሲኖር ወደ ከተማዋ ወጣገባ በማለቱ ብርቅርቅታዋ አነሆለለው። በሁዳድ ፱ ገጠር መንደር የነበረውን መሬት ቀድሞም እየሸረፈ በመሸጥ አስቸገሮ ነበር። “አንድ ቀርጥ ቸበቸብክ። በምን እንኑር?” እሚ አንድ ቀን በግና ጥያቄውን ለኮሰች። በረከት አንድ ነገር ለምዶ ነበር። መንደሩ ዉስጥ ካሉ ነዋሪዎች ወጣት እሚሰኙት መሀከል ነበር። እርጅና የገጠማቸው እና አቅም ያነሰአቸው ዜጋዎች መሬትን በመጋዞ ዉልዎች ማሳረስ በስፋት ስላለመዱ፣ አዛውንት በበዛበት መንደር ወጣት የነበረ በጉልበቱ ብቻ መራርጦ እኩል፣ እኩልታምሾ፣ ድረስ ያርስ ነበር። ይህን ሲያደርግ ከርሞ፣ በሬዎቹን በመቀነስ ደግሞ ሲሸጥ ወይም እህሉ በቤቱ ሲትረፈረፍ ነገን ስለማያስብ፣ ድካሙን ለመቀነስ አስቦ፣ ወደ ሢሶ መጋዞ ይዞር ነበር። በሂደት፣ ትንሽ ቢሰራም ኑሮ በመቅለሉ ሲቀጥል፣ በሬዎቹን ተዘናግቶ ሸጦ ከመጋዞ ወረደ። በስምምነት ተቀጥሮ (ጉልበት ብቻ ሸጦ) ማረስ ጀመረ። ብዙ ሰብሎች ማግኘቱ ዞሮዞሮ በቂ ነበር። በረከት በእዚህ አኗኗር በመስመጡ ግን፣ የገቢው ዋና ምንጭ የራሱ ሁለት ተኩል ቀርጥ መሬት ሳይሆን ጉልበት አገልግሎቱ እና ክፍያው ሆኖለት ነበር። ጉልበቱ በቂ ገቢ አግኝቶለት በተከታታይ ስለተደሰተ ግን የግል መሬቱን ዋጋ ከናካቴውም መናቅ ቸላማለት፣ ከእዛም መቦጫጨቅ ጀመረ። እሚ ግን በንህላልነቱቱ በግና መሬቱን እየቆረሰለ እንዳይሸጥ ስታሳስበው በቂ ገቢ ስለ እሚአገኝ መልሶ ተከራካሪ እና አሸናፊ ነበር። “በደንብ እየተበላ አይደል እንዴ!” አለ። “ዛሬ አልፎ ወደፊት ልጆችህ ስ? እ! ከመቃብር አጽም ስትሆን ወጥተህ ለሽማግሌዎቹ እያረስህ ልትረዳቸው ነው? እነ እርሱ መማር ነው ያለባቸው! እንደ አንተ የብድር በሬዎች ቂጥ ስር ሲሯሯጡ አይኖሯትም! የእኔ ልጆች አር ሲወጣ እየተመለከቱ ፈሳቸው ሲፈሳባቸው እየቻሉ ጥማዶች ተከትለው ለማረስ አይፈልጉም! አንተ አፅም ሆነህ ለማረስ ብትመጣ ደግሞ እንኳ በሬዎች ደግሞ አፅም ይፈራሉ።” እሚ በስሜት ስትነድድ እና ስትናገር ድንገት ትልቅ እሚሰኝ ጥፊ ተጣለባት። “በግራ ነው በቀኝ?” እራስዋን እየጠየቀች ተንደፋድፋ ለጥቂት ከመዉደቅ ብትተርፍም ስታፈጥጥበት ብዥብዥ እሚል ምስል ብቻ ስለምታይ ደግሞ ለማጥቃት ከጅሎ እንደሁ ዓጥርቶ አይቶ ለማወቅ አዳገታት። በእርግጥ ለመጀመሪአ ጊዜ በእጁ ሲማታ ነበር። የተጋቡ ሰሞን አለምክንያት በእርግጫ ብጤ ሰክሮ አቅምሷት ነበር፨
ባይስማሙም፣ ከከፋ የመራራቅ አባዜ በዘለለ አካልአዊነት በመሀከልአቸው ጠብዎች በተለይ እስከእዛ ሰሞን ግን ተዋውቆ አያውቅም ነበር። ብቻ ያን ሰሞን አልፎ፣ መሬቱ እየተነደለ መሸጡ ቀጥሎ ትንሽ ሰንብተው፣ ያነሰው መሬት ለልበሙሉ ግብርና ጥረት ማስተናገጃነት ስላነሰ በመስነፍ ወደቀ። “ደግ እሚሰኝ ነው” ብሎ በመጮኽ ሚስቱ እንድታምን የተከራከረበትን ክፍያ ተቀብሎበት ቀድሞም እየሸራረፈ ለሸጠለት ጎረቤታቸው አንድፊቱን የቀረውንም ሸጦት እንደ መጣ አረዳት። ያኔ ጠንከር አድርጋ መልስምት ሞከረች። “በስካር ነው የነገደው። እባክአችሁ ዉሉ ይመለስለት፣ የልጆች እናት ባዶ ቀረሁ…” በብርቱ ማስተዛዘን ሽማግሌዎች፣ ቄስዎች እና መሬታቸውን የገዛው ጎረቤትአቸውን አቶ በርናባስ፣ አንፃርአዊ የሁዳድዎቹ ከበርቴውን ተለማመጠች። ብሩን መልሰህ ዉሰድ በሚል አብዝታ ጠየቀች፣ አስለመነች። ቀና ምላሽ የለም። በመጨረሻ “ልጅዎች ማሳደጊአ የለኝም” ብላ ስለ ልጅ አምላክ እና ከቶ በእማያውቃቸው በነበሩት እናቱ ስም ለምና ገዢ ጎረቤትዋ ላይ ስታለቅስበት፣ የበረከትን ወፈፌነት እና ሰካራምነት ወትሮም ተገንዝቦ፣ በግዢው ቤተሰብ የማፈናቀሉ ጎንዮሽ ወንጀል ቦርቡሮ እየተሰማው ተጨንቆ ስለነበር ልቡ መደንደን ፈራ። “እናቴ ከአረፈች ስምንት አመቷ ነበር መሰለኝ። በቃ በእናቴ ስም ስለለመንሽ ብቻ፣ ልጅዎችሽ እንዳያስጨንቁሽ በእሚል ለስምንት አመትዎች ከባልሽ ቀስ በቀስ ጠቅልዬ ከገዛሁት መሬት፣ እኩሌታው ምርት ያንቺ ይሆንልሽ አለ። ከቀረ ሰፊ እርስቱ ስለቀላቀልኩት እና አንድነት ስለእማርስ ምንም እርሻውን ልቆጣጠር ቅብጥርስዮ የለም። እኔ በአህያዎች ጭኜ ምርቱን በተመረተ ቁጥር እልክልሽ አለሁ። ግን ወቅቱ ሲአበቃ፣ ስምንት ዓመትዎች ኋላ፤ ስጦታ ዉሌ ቀጥሎ ተረፈምርት እንኳ መቃረም አትችይም። ባልሽን እስከ እዛ አደብ አስይዥ እና ልጅዎችሽን አስተካክለሽ ለገቢ እንዲሆኑሽ አድርሺ። ኑሮሽን እንደ እዚያ አብጂ፤ በራስሽ ጠንክሪ ድሃ እንስት!” ብለው ትልቅ ድጋፍ እና አግጣጫ ቸሯት። እሚ ቋሚ ቅርሱ አንዴ ስላመለጠ፤ አማራጩ ታላቅ ደስታ እና ድጋፍ ሆኖ ታያት፤ ከበቂ በላይ የስምንት ዓመቶች ዋስትና መቷል። አመስግና ተመለሰች፨
ወዲያው፣ በረከት የገጠር ኑሮ ሲመረው፣ የጉልበቱ ሥራ አይታክተው መስሎት እንደ አልቆየ ማረስ ከቶ ሲያስጸይፈው፣ የከተማ ሰውዎች ኑሮ አነሁልሎት በመመላለሱ ደግሞ ከተማ ሲያደስተው፣ አንድ ሆነ። በመጨረሻ፣ ግለኛው በረከት አንድ ነገር ጉልህ የሆነ መስሎ በመጥራት ታየው። የከተማ ነዋሪዎች ልጅዎች እንደአሉአቸው ተረዳ። ለካ ከተሜ ከልጆቹ ጋር እዛው ከትቶ እሚኖር ነው፤ ግንዛቦት አደረገ። ከመጠጥ እና መዝናናቱ ጎን ያም በመጠኑ ሊኮረጅ እንደ እሚችል አዉጠነጠነ እና በእዛም ነሁልሎ ተሳበ። ከጥፊው ጋር ተያይዞ ስትበግን እና ስትቀየመው ሰንብተው ስለነበር የእሚ ከጥፋቱ ጎን የተለቀመ ገጸበረከት ሳይነገረው እንዳለ፣ ጠቅልለው፣ የገጠሩን ቤት ንብረት በትንሽ ገንዘብ በመለወጥ፣ ያነሆለለችው ፋሲካይት ዉስጥ፣ ሰሜንምስራቅ ፍጹም ዳርቻ ላይ፣ መስሪአቤትዎች ብቻ ከተማውን ገድበው በሰፈሩበት እና በተለየ ማታ ኮራ እያሉ ከእሚራመዱ ጅብዎች በቀረ ነዋሪ በሌለበት መንደር እርካሽ ሰፋ ያለ ባዶ መሬት ገዝተው መጡ። ለበረከት የከተማው በር ላይ መገኘቱ በቂ ነበር እና ሙሉው ቤተሰብ በስሩ ሆነው አብረው እረኩ። እዚያ ያቆሙት ቤት በአስለቀቁት ሜዳ ላይ በቅለው ያደጉ ዛፍዎች ተመንጥረው ከአጠራቀሙት እንጨትዎች ነበር። አንድ ሰፋ ያለ ሳሎን፣ ዉስጥኛ በሩ ወደ መኝታ ቤት እሚከትት የሆነ፣ ከመኝታ ክፍሉም በበር ክፍተት በር ባይንጠለጠልም መጋረጃ ተሰቅሎበት ወደ አነስተኛ ጓዳ ገባ-ወጣ እሚአስችል ስርአት ተበጅቶለት ተሰራ። ከመኝታ ቤቱ ወደ ጓሮ አሳላፊ በር ደግሞ በሰፊው ተበሳለት። ከቤቱ አካልዎች ሁሉ ናሆም የጀርባ ጣውላ በሩን ብቻ ይወድድ አለ። የተላገው በዉብ መልክ ነው። ከፍ ብሎ መሰቀሉ ደግሞ በምሁር የተገነባ ያክል ነው። ደፉ ለእንቅስቃሴ ቆፍ ሆኖ ደግ ፈተናነት በእርግጥ አለበት። ለጎሜንበር (ዊልቸር) ተጠቃሚ ግን ኪነህንፃአዊ ጥያቄ እሚአጭር ስለ ሆነ አንድ መንገድ በሃሳቡ ሳለ። “ማንም ጎሜመንበር ተጠቃሚ እዚህ አይደርስ!” ብቻ ግን፤ ወደ ታች ወይም ጎን መከፈት ከቻለ በቂ አካቶትአዊነት (ፓርቲሲፓቶሪነስ) ሁሉ ያለው ይሆናል። ዞሮዞሮ፣ “ድንቅ በር ነው” ይለው ነበር። እሚ እና ቤተሰቦቿ በባይተዋሩ ቤት ከኖሩ ግን ስኬት በልጆቿ ሳይጠፋ በበርናባስ ገጸበረከት ደግ እሚሰኝ አኗኗርን ይጎነጫሉ፨

ሁሌ እሚወድደውን እና እሚማጸንበትን፣ በንጉሥ ምንይልክ ካልዕ ዘመን የተገነባ እና በቀኃሥ. (ቀዳምአዊ ኃይለ-ሥላሴ) ታድሶ በተለየ በስሉሥ ዐብይ ጉልላቶቹ እና ቀለምየለሽ ጥርብ ድንጋዮች በቆሙ ግድግዳዎቹ ከመደበኛ ማራኪነት በላይ ዉበት የተሸከመው፣ በሰሜን ከተማው መውጫ ፈቀቅ ብሎ ተቀምጦ አሁን ከተማው ሰፍቶ በእቅፉ ወደመሀል የሰበሰበው፣ እና ሰሜንአዊ ጫፍ አላማ (ሳይን) ለከተማው የሆነው፣ ደብረ ምኅረት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስትያንን ተሳለመ። ዉዳሴ ማርያም እንዳደረሰ ኪዳን በማድረሱ ግን ሳይካፈል ወደ ቤት ተመለሰ። ኋላ ሽርጉድ ስለእሚበዛበት ቀድሞ ጊዜ-ክምችት ላይ መጠንቀቅ ከወነ። ቤት ተመልሶ፤ ቀለም ያልተቀባ፣ እሚ እበት ስለለቀለቀችው ተፈጥሮአዊ ዉበት የያዙ ጭቃ ግድግዳዎች አልፎ ወደወል መኝታ ክፍላቸው ገባ። ባቤን ለይቶ ለመቀስቀስ ጣረ። የቅድም እግር ላይ አንድ እጅ አክሎ፣ በብሩ ሆድ አካባቢ ላይ ስለ ጫነ፣ ብሩ ቀድሞ መንቃት የለበትም። ባቤም መንቃት አልቻለም። ናሆም ባቤን ለመቀስቀስ እና ብሩን ላለማንንቃት በዝግታ ጎንበስ ሲል፣ ከጀርባው ቁጡ ድምጽ በከፍታ ጉልበት ገፍቶ ጸጥታውን አስወጣ። “ስእ!! ገና በጧት ጡት መታገል። ኢይ! በቃሽ!” ጮለቅ ባትሰማም የእሚ ኮናኝ ድምጽ በጣሪአው ሁሉ እየተነዳ ሲራመድ ተሰማ። አድማጩ ጮለቅ ነበረች። ይህን ሰምቶ በንዑስ መባነን ሆኖ፣ ባቤ ግን ይባስ ብሎ እግሩን ለማከክ ፈለገ። ብሩ እጁን ከአንገቱ አካባቢ አዉርዶ በሆዱ ሲጭን የባቤን እግር ስለአገተው፣ በደመነብስ እያስለቀቀ ሲፈራገጥ ብሩም ነቃ። ፊቱ የተገተረ ናሆም ላይ ዓይንዎች በንቃት-ትንቅንቅ ጠበብ ዘርጠጥ እያደረገ አፈጠጠ። ናሆም ራስቅል ወደ ትከሻ በማስረግ ትከሻዎች ወደ ጆሮዎች በመቆልቆል፣ በከፍታ ድምጽ ከት ብሎ ሣቀ። ብሩ ወደ እራሱ ተመለሰ እና ባቤ ሆዱን መትቶበት እግሩን ሲመነጭቀው አፈፍ አድርጎ ያዘው። አሁንም የበለጠ ለማስለቀቅ ሲታገል እንደ ታሰረ እንስሳ ይመስል ነበር። “እንደ ከራዲዮን እኔ ላይ ወጥቶ አይተኛም እንዴ¡¡¡” በመናደድ እና ተስፋ መቁረጥ የእጅከፍንጅ ምርኮውን ለመቅጣት በመመቻቸት ቀና አለ። አሁንም በህልሙ ሳይክል እሚነዳ ይመስል የተጠመደ እግሩን ለመመንጨቅ መታገሉን ተመልክቶ “ተወው ባክህ” በማለት ናሆም ቀጣዩ ድርጊት እንዲቀር ለመነ። መልሶ ደግሞ ፍፃሜውን ለማየት ጓጉቶ፣ በመንታልብ በመፈገግ እንዲቀር ለመነ። ወደ ሰውነቱ እይ ‘አንተም ፍረድ እስቲ’ በእሚል ስነልቦና ግብዣ ብሩ ሆዱን እየጠቆመ ጋብዞት ተመለከተ። የባቤ ድንበር ጣሽነትን በደግ መጠን ቁንጥጫ አጸፋ መመለስ ተያያዘ። በመጠኑ በመጮኽ እና ክዉታ ታግዞ ባቤ ነቃ። የታላላቆቹን ፍጥጫ ማስተዋል ጋር ከእግሩ ንዘረት ጎን ተፋጠጠ። በጉርምርምታ እየተራገመ በደመነብስ ተቻኩሎ ወረደ። አብሮት፣ የወል ዥጉርጉር ጥቁር እና ቀይ ብርድልብስአቸው እንደ መቀነት እየተጎተተ ሲከተለው ካነቀው ሰውነቱ አላቅቆ አሽቀንጥሮ መለሰላቸው እና በባዶ እግሮች ወለል እየደበደበ ወደ ዉጭ ወጣ። ደመነብሱ ሲአበቃ አለአመክዮ ከቤቱዉጭ እራሱን አግኝቶ አስተዋለ። ወደ ቤት በማጉረምረም ተመልሶ፣ ለአመል የቆመች ግን ትልቅ አገልግሎት እምትሰጥ መጋረጃ እንደ ጠላት አሽቀንጥሮአት ወደ ጓዳው ዘለቀ። በእጀታው ሲጨብጡት ከማፍሰሻው በስተ ግራ ጫፉ የተቦደሰ ሎሚ-ቀለም አሀዱ-ሊትር ላስቲክ-ጆክ ዉስጥ፣ ዉኀ እስከ ወገቡ ሞልቶ በመቆናጠር እንደ ነበረው በእንቅልፍ ተጽዕኖ እና ንዴት መሀከል ሆኖ መሬትዋን በደንብ ድምድም እያደረገ ቤቱን በማንዘር ወጣ። ‘እናት ምድር!’
ከሚቆጣ ባቤ በቀር ቤቱን ማንም ቢራመድ ስለ እማያነዝር በህብር ተደምመው ተመለከቱት። ከጓሮ መዉጫው በር ሲደርስ፣ ምድሩን ድምድም እሚአደርገውን ቆም አደረገ። ናሆምን በመርገም ፊት፣ ክፉ ዉሻ አይቶ ክው እንዳለ እና ከእግሬአዉጭኝ ቀድሞ ጥቂት እንደ አፈጠጠ ድመት ሆኖ ተመለከተው። የተናነቀው ቃል ዘግየት ብሎ በእሚራገም ፊቱ ፈሰሠ “ሂ…!ሂ…! የ..ሆነ! ቆንጥጠህ ቢሆን….ም ቀድመህ ቀስቅሰኝ አላልኩህም!” ናሆም ከት ብሎ ሣቀ። “መቆንጠጡ ካልቀረ ምን ልዩነት አለ!” ባቤ በስውር እየተራገመ፣ በከፍታ ጉልበት ወለል እየደበደበ ወጣ። ‘በእርግጥ፤ ወንዞችን ጠልፈው አምስት ሺህ አመቶች ጀምረው ሲሰለጥኑ ዉሃን “እናት ዉሃ!” አሉ ቻናዎች! መብል እና ሃይል አመንጪ ነው፤ ህይወት አብሪ። ሦስትሺህ አመቶች ተከትሎ እንኳ፣ የዋና ወንዛችንን መብት አክራሪ (ተርባይን) በመምታት እንዲወሰን እና ይዘቱን እንዳንነካው በአቂያቂይ የ ታህግ. (ታላቁ ህዳሴ ግድብ) ድርድሮች በሚል ፈሊጥ ያስወሰንን ይመስል አለ እንጂ፣ ከባቤ እግሮች ቀጥሎ እርግጥም፦ ቻይናን እና ግብጽን ሃገር ያረገው ፈሳሽ ‘እናት ዉሃ፤’
ጸጉርዋ ስር ፈልቅቃ በላከቻቸው ጣትዎች ቅሏን በፍቅር እያከከች የዕለት መቅደጃዋን ሻካራ ድምጽ ጢኖም አሰማች “ህማ? ህልም ምንድን ነው?” “እንጃባሽ!”
ከ ጮለቅ አፍ ጡቷን መንከሱ ሲበዛ ለመጨረሻ ጊዜ እንደ ገመድ መዝዛ ነጠቀች እና በመቀመጥ ሆና፣ ስለአደጋ አደረሰ፣ ተደስቶ የእሚአሾፍባት ጨቅላ ፊትን አየች። ንፁህ ጮለቅ ላይ መናደድዋን ከቶ ያልተበደለች ያክል ዉጣው ዞር አለች። “ምን አይተሽ ነው?” “ትልቅ ፀሐይ እዚህ ሲገባ አየሁ። ሁላችንን አቀፈን።” “ደግሞ…ፀሐይ ነው የእሚአቅፈው?” የጮለቅ ሽንት ጨርቅ እርሶ ከሆነ አንድ መዳፍ ልካ በቆዳ ስሜቷ አሰሠች። ተነሳች። ምርአዊነት ዉስጥ ሆና ወደ ጓዳ ዘለቀች። ተመልሳ ፈገግታ አብዝታ ወደ ጢዩ በደስታ ወጣች “እ…! መብራቱ ዛሬ መምጫው አይደል እንዴ! እሱን ማየትሽ ይሆን አላ!” መልሳ ቀጨመች። “የት ወሰደው ጆኩን ያ ልጅ! ልጅሽን አጫውች!” ወደ ዉጭ የባቤ ዱካዎችን አነፈነፈች።
ጢዩ ወደ ጮለቅ እማይጨነቅ ፍልቅልቅ ፊት ለጫወታ ፍጆታ አቅርባ አስጠጋችላት። “መስ ሊመጣ ነው ዛሬ! መስ ሊመጣ ነው ዛሬ! መስ ሊመጣ ነው ዛሬ! ጮለቅ! ኬክ ይገዛልናል! መስ ሊመጣ ነው ዛሬ!…” እያንድአንዱን ቃል ፊቷ ከጮለቅ ፊት ቅርብ ብሎ እየተወዛወዝ ስታወራ፣ ደረቅ እና ትኩስ ዓይናርዎች ከሞላጎደል ደረቅ ንፍጥ ከሚያስመለክት አፍንጫ ጋር ታግዞ ታላቅ ደስታ ለጮለቅ ፈጠረላት። ከእሚጸዳ ቆሻሻው ጀርባ እንደ ፈርጥ እሚአበራ ቅን-ደስታ በጢዩ ፍልቅልቅ ፊት ይፈስስ ስለ ነበር፣ ለጮለቅ እማይነጥፍ ዕለትአዊ የመዝናናት ፍጆታዋ ነበር። ብዙ ጊዜ ትጥገብ እንጂ ጮለቅ ተጨማሪ መጫወቻ ከጢዩ ፊት በላይ አትጠይቅም። ከፊቷ ባሻገር ጢዩ በመተረት፣ ስእሎች በማስጠናት እና እንቆቅልሽ ትረካዎች በማከል ጮለቅን ታዝናናት አለች። ምክትል እናቷ። በአካል እሚነካት ስለሌለ በዝምታ እምታጤን የግል ደስተኛ ጨቅላ ነበረች፨

<p class="has-text-align-justify" value="<amp-fit-text layout="fixed-height" min-font-size="6" max-font-size="72" height="80">ናሆም እና ብሩ ሁለቱ የጓዳ እና መኝታቤት መስኮቶችን ተከፍተው ወደ ቤት ማሰናዳት ገቡ። ቀሪው መስኮት ሳሎን ከበሩ እኩል ተከፍቶ እንዲሁ ሰፊ ፅዳት ሆነ። ያልነቃ ብቸኛ ው ቤተሰብ አባል የጋራ ብርድልብሱ ለብቻው ሆኖለት የቤቱ ብቸኛው በአናፂ ባለሙያ የተሰራው አልጋው ላይ ከመደበኛ እራስጌ አግጣጫ ስቶ ወደ ጎን፣ በእሚ የተላጨ አናቱን አድርሶት ተኝቶ አለ። ናሆም ትራሱን ወደ ጊዜአዊ እራስጌ አምጥቶ አስገባለት። ብሩ፣ ብቸኛ ተንቀሳቃሽ ስልክ በቤቱ ለመያዝ የታደለ፣ አስራሁለትኛ ክፍል ፈጽሞ በብሔርአዊ ፈተና ዉጤት ልዩ ጭንቀት ይዞት ከወዲሁ እሚብሰከሰክ የሆነው፣ ሞላጎደል ዝምተኛ እና ግል ዛቢያው ተስማምቶት እሚዞርበት፣ የቤቱ በኩር፣ ጸጉር በተለየ መልኩ ሉጫ ሆኖ ያደገለት እና ከሁሉ ቀላ እሚል ቆዳ እና ሽል መልክ ሁሉ ያገኘው፣ እንደ ወትሮው ከሥራው ቀድሞ ወደ ተሱ. (ተስ. = ተንቀሳቃሽ ስልክ) ገባ። ናሆም እንቅልፍክፍሉን እየቃኘ ማጽዳቱን ሲያያዝ ከጀርባው የብዙነሽ በቀለ እንደሆነ እሚታወቅ ጥንትአዊ ዘፈን ምትሃትአዊ የኦርኬስትራ መግቢኣ ቅንብሩን በጣሪአው እየአሯሯጠ መርጨት ጀመረ። “ጭንቅ ጥብብ” እስክትል እና የመሳሪያዎች ቅንብሩ ዉበት “ድርን” ብሎ “እያልኩልህ” እሚለውን ልትል እስኪ ፈቅድላት ድረስ፣ እማይመለጥ የኦርኬስትራ ስውር ልዕለ-ጉልበት የሆነ መግቢኣው የተገኘውን የቀልብ አሃዝ ሁሉ ገዛ። ናሆም ወደ ጓዳ ገብቶ በአፍጢሙ የተደፋ ከሁሉ እሚረዝም የክትዕቃ – ሽንጣም ብርጭቆ – አንስቶ ወጣ። መናኛ ቻይና ስሪት ተሱ.ን ከጥጋቱ ጠረጴዛ አነሳ። ያለው ዐውራ ድምጽማውጫ አካሉን በብርጭቆው ቀዳዳ ልክ አድርጎ ድምፁ በብርጭቆው እንዲንቆረቆር አስቀመጠው። በተሱ. መደበኛ አቀማመጥ ከሆነ ድምፁ በጠራ መልኩ መስተናገድ እሚችል አልነበረም። በብርጭቆው ጉድጓድ እየተስተናገደ ግን በበላጭ ጥራት መጉላት እና ማስተጋባት እንዲችል ታገዘ። ዉጭአዊ ተጽዕኖ (ኢፌክት) ሆኖ በብጁው (ከስተማይዝድ) የድምፅ ቅንብር አልፎ ለጆሮ በአነሰ ጉርበጣ መዉጣት ጀመረ። ያ ሲሆን የብዙነሽ ምትሃትአዊ ድምጽ ክወና ልክ መፍሠስ ጀምሮ ነበር። ‘…እ…እ…እ…’።<br>በመቆም ለመጥረግ እንዲአመች የእንጨት እጀታ ጨምሮለት ቁም መጥረጊአ ያደረገውን፣ ከዘንባባ ቅጠልዎች እነቢግ ያዘጋጁት መጥረጊአን ሰሞኑን ተለዉጦ ስለነበር፣ ከአረጀው የበለጠ ሊያገለግል ተነሳ። እነ ጢዩ ወደ እንግዳመቀበያ ክፍል እንዲወጡ ናሆም በመጠነኛ ዳንስ ሆኖ አዘዘ። ጮለቅ በብሩ ጥንቁቅ እቅፋት ሆና በእማይደክም የጢዩ ፊት ዥዋዥዌ እየተዝናናች ወደ ሳሎን ከግድግዳ በግማሽ እርምጃ የአክል ራቅ ብሎ በተዘረጋ ሽንጣም መከዳ እራስዋን አገኘች። “እኔን አታስታቅፉ…ኝም!?” ስለ እምታውቀው፣ ጢዩ መልስ ሳትጠብቅ እንደ ወትሮው ላመሏ ያክል ብሩን ጠየቀች። “ማሪያም አስወልዳ ታሳቅፍሽ!” ብሩ ህፃኗን አስረክቦ ተመለሰ። በአጭር የእግሮች፣ ድንክነቱ ላይ ተንጣልሎ ወደ እሚአገለግለው መከዳ ተጠግታ ከሥሩ መሬቱ ላይ ለዛ ኢላማ በምትጎዘጉዘው መጠነኛ ምንጣፍ በመንበርከክ ተመቻችታ፣ ክንድዎቿ ተጣጥፈው በመከዳው ጫፍ ተደራርበው አረፉ። የጮለቅ አለአግባብ መንቀሳቀስ እምቅአደጋ (ሪስክ) በዛ እየተገደበ፣ የጢዩ ፊቷም በአገጭ በኩል እሚቀመጥበት ልሙድ መካንጊዜ ነበር። “እ..ህ…ህ…ህ… የኔ ቆንጆ እ… ሸጋ…….ልቤ ወዶኻል …እ… እ… እንዳትረሳኝ…እ…አደራህን…..” አብራ እና ሲአመልጥም ሙጉ.ን (ሙግ. = የ ሙዚቃ ግጥም/ ሊሪክስ) በመከተል ስትልላት አሁንም አሁንም ጮለቅ የዓመት እና ሁለት ወር እድሜ ገደቧን ዘንግታ በጉልህ እሚታይ አዲስ ዓለም ዉስጥ ሰምጣ መቦረቅ ትያያዝ አለች፨<br>ብሩ ከናሆም መጥረጊአን ተክቶ ተቀበለ እና ወለል ወሰደ። ናሆም ልምዱ ስለ እሚአግዘው ወደ ጣሪአ ዞረ። በፊት ጣሪአው ተንፍሶ በተሰፋበት እቅጭ የቀዶጥገና ሥፍራ ቀድዶ፣ ክምቹ ቆሻሻውን በቆሻሻው ባልዲ አስተናገደ። ለቀሩት ሦስት የኮርኒስ ጡቶችም ህክምናው ዘመተ። በኋላ መልሶ እንደነበር በእሚ መርፌ ቀዳዳዎቹ ተሰፉ። አልፎአልፎ የእሚጎበኟቸው አይጥዎች አዲሱ መንደራቸው ዳግም ፈርሶ፣ ናሆም በመቀጠል አዳዲስ ልዩልዩ ቅርጽ (በተለይ የልብ) እና ቀለሞች ያሏቸው ሻካራ ላስቲኮች ነፍቶ እንዲያብረቀርቁ ሰቀለ። ብሩ ሁሉን መኝታ ካነጠፈ፣ ግድግዳዎች እንዳይቀረፉ በጥበብ ቆሻሾቻቸው በጋራ ከተለቀሙ፣ እና ወለል ከተጠረገ ኋላ ሁለገብ ጽዳት እና መጠነኛ እድሳቱ ቤቱን ደመቅ አደረገ።<br>ቆሻሻውን ለሁለገቡ የቆሻሻ ባልዲ አጉርሶ ወደ ጓሮ ማቃጠያው ምሥ ጉድጓድ ሊደፋ ብሩ ዞረ። ለእሚ እገዛ እራሱን ሊያክል፣ ባቤ ብሩን ከመንገዱ ተለይቶት ወደ ኩሽና አጠመዘዘ። እሚ ከጓዳ ወደ ኩሽና በመመላለስ ቁርስ ማበጀቱን አፋፋመች። ነገርግን፣ እንደ ሁሌ ደስታ እሚሰማት አልሆነም። የመስ መምጣት ምንጊዜም ደስታ እና ደስታ ብቻ ነው። ግን ዛሬ ክፍት እሚል ድባብ ገና በጠዋቱ ሰፈረባት። ጭራሽ ጭንቅ እያደረጋት ሲብስ የባቤ እግር በኩሽናው ሜዳ የነበረ የኑግ ዱቄት አነስተኛ ጣሣ ደፋባት። የባቤ ጥፋት ስላልነበረ ለመልቀሙ ብቻ ዕዝ አድርጋ ጭንቀቷን በሆንብሎንታ ላለመሸበር በእሚል በግድየለሽነት አለፈችው እና በማብሰሉ ልትጠመድ አሰበች።<br>“እሚ! ህልሜ ትዝ አለኝ እንደ ገና! ያየሁት እኮ ፀሐይ ብቻ አይደለም ስ!” ጢዩ ወደ ጓሮ ኩሽናው እየገባች፣ ትሁት ፊቷ ታጥቦ እንደረጠበ እጆች በደረት አድርጋ በእርጋታ ሆና ጨዋታ ጀመረች። ግን መልሱ ጩኸት ሆነ። “ልጅትዋ ስ!” ክዉ ያለች ጢዩ ግንባር ቋጥራ ክዉታውን መከተች። “ብሩ አለ!!” ድንገት ቁመቷን ሰሞኑን መዝዛ ያለችው የሴቶች በኩሯ፣ ነጭ የእሚ ክሮች ያበጁት የዳንቴል ሹራቧን በመሰል ከአጠራት እና ከቁርጭምጭሚት እማይደርስ ጥቁር ሱሪዋ አቀራረበችው እና ወደ እርጋታዋ ተመለሰች። ቀናአዊነቷን ለበስ አድርጋ “እና እሚ እይስ! አንቺ ነጠላ ስትጥይም አይቼ ነበር! ያን ልነግርሽ ነው የመጣሁት። ግን እሚ! ህልም ቆይ ምንድን ነው?” እሚ ወደ ልዩ ኢተንቀሳቃሽ ወንበሯ ተቀመጠች እና ጢዩን ዘነጋ ች። በመሰል የተተከለው ጠረጴዛ ላይ ቅርንፉድ ለመፍጨት ቂጥዋን ለአመል ያክል ስለመንጠራራት ከፍ አድርጋ ከ ናሆም-መደርደሪያ ላይ ጠርሙስ ለቀመች። ጢዩ ጠረጴዛውን ቀረብ ብላ በሆዷ ስትንጠለጠልበት እግሮቿ ምድርን ተሰናበቱ። መልሳ በማረፍ ያመለጠ ቅርንፉድ አንስታ መልስ እየጠበቀች ሆና አስፈጨችው። “ሂጅ ባክሽ ልጅቷ ጋር! ምንም የለም እዚህ! ሁሉን እኛ ነን እምንሰራው!” ባቤ ተቃውሞ እና ገሠጻውን ጀመረ። በአጉልቶ ምላስ ማሳየት ደግሞ ምራቅ ጭኖበት በማስመልከት፣ ጢዩ አብሽቃ ተከላከለች። ባቤ ቁጣውን ወደ ስድብ እያዞረ “ደረቅ፣ ፍየል ጸጉር፣…” ማለቱን ሲቀጥል እሚ ሁለቱንም ስትቆጣ፣ ጢዩ በስውር ተፍታበት ተመለሰች። ባቤ ለመምታት እንደእሚፈልግ የምራቁን ኤክዚቢት አስመለክቶ አሳሰበ። እሚ ግን 'ታላቅ ይታገሳል’ እሚል የተለመደ ምክሯን ሰጠች፨<br>ከዋናው ቤት በስተ ቀኝ ከጓሮ እሚገኘው ኩሽና ከዉጭ እና ዉስጥ እንዲቆለፍ አድርገው በጸዳ እና ብልኅ ድባብ እነ መስ እንደአዲስ ያበጁት ሁለት አመቶች ቀድሞ ነበር። ከአፈርአማው ወለል ግድግዳዎቹ ተመዝዘው፣ በእሚ ራስቅል አካባቢ ድረስ ባለአካልአቸው ጭቃ ምርጊት ያስተናገዱት ናቸው። ሦስት-በ-ሦስት ሜትሮች ዙሪአውን ገድበው ተገጣጥመውለት፣ የኩሽና ስፋቱን አበጅተው አሉ። ከሜትር እና ኩርማን አካባቢ ልስን በላይ ያለው የግድግዳ ቅርጽ ግን፣ አልፎአልፎ የቆሙ ምሰሶዎች እስከ ጣራው ደርሰው ጣሪአ ሲሸከሙ ይታያል። ሳይለሰን እና እንጨቶች ሳይገጠገጠበት የሳጣራ አካል ብቻ ሸፈነው። ሁለት ጎንዎች ግን ንፋስ እና ዉሽንፍር ስለ በክረምት እሚአጠቃአቸው ስለሆነ ደረቅ ላስቲኮች ጨምረው አሉ። ባሉት ላስቲክየለሽ የጣራስር ሁለቱ ግድግዳዎች ደግሞ፣ ቤቱ በብርሃን እና ጭስ የማመላለስ ትጉህ-አገልግሎት ይሰጥ አለ። የእነመስ ንድፍ የሆነው ኩሽና ተጨማሪ የይዘቶች ዝግጅትም አሉት። ካንዱ የግድግዳ ሆድእቃ፣ እንደ ልዕለ-ጉጥ ወደ መሀከል ቤቱ አስግጎ እሚሰነዘር አካል አለ። እርብራብ ተበጅቶ በላዩ የታነፀ መደርደሪአ አለ። ከግድግዳው ወደ ጣሪአ ሳይሆን ወደ ቤቱ መሀከል እሚፈልቅ እንጨት የወለሉ መሳለመሳ (ፓራለል) ሆኖ ትልቅ ጣውላ ተነጥፎበት ሲዘጋጅ፣ መስ በናሆም ሃሳብ አመንጪነት ስላነፀው፣ በኋላ በስሙ ተሰየመለት፤ የናሆም-መደርደሪአ። ብዙ ወጥቤት ቁሳቁስዎች እሚሸከም ሲሆን እሚን ያስደነቀ አሽከርነት እሚሰጥ በመሆን ሁሌም ትደመምበትአለች። በተቃራኒው አግጣጫ ያለው ግድግዳም በመሰል የእነ መስ እና ናሆም ምርምር ያደገ ክወና ያቆመው ዉስጤታአዊ (ኢንቴሪየር) ክፍለ ኩሽና አለው። በእሚ ወገብ ከፍታ የቆመ የማንደጃዎች አገልግሎት ማእከል ያቀርብ አለ። እንደዛው ግድግዳው የእሚሸናው እሚመስለው ይህ አካል፣ አንድ ጎኑ ላይ እንጀራ ምጣድ ተንጠልጥሎበት አለ። ጎኑ በብልሃት ከምጣድ በጥገኛነት እሳት እሚገለገል መጠነኛ የማብሰያ ክፍተት የአለበት ቅርጽ አሳድገው አብሳይ ሆኖ አለ። ከተንጠለጠለ ምጣድ እና ማብሰያው ሥር በነበረው ክፍተት፣ ጥቂት ከማንአንሼአዊ ከፍታ ላይ ወለል ቅርጽ ተበጅቶ እንጨት እየተኛበት ለነዲድ እሚታዘዝበት ቅርጽ አለ። ያ ሆድዕቃ ክፍል በበር መዘጋት እና መከፈት ቻይ ሆኖ እሳት በተቀነሰ ኦክስጅን ቅጥልጥል (ኮምበስሽን) ማገዶ ይቆጥብ ነበር። ንፋስ አጠናግሮት ስለ አጋጋለው በከንቱ እማይበዛው እሳት በተከበበ ክፈፉ ሙቀት አምቆ ጭምርም ቶሎ ያበስል አለ። አመድ በአቆረ ጊዜ ደግሞ ተከፍቶ ወደ ዉጭ እንዲአፈስስ፣ ፊት ቅርፁ ዝቅ ብሎ ዘመም እንዲል እሚአስችል ስነእንቅስቃሴ (መካኒክስ) እንደ ቁልፍ ተገጥሞለት አለ። አመዱ ያለንክኪ እየተናደ ከስር በእሚነጠፍ አጭር ላስቲክ በመናድ ወደ ሰፊ ባልዲ ይንሸራተት አለ። ባልዲ ው እንደ አሻ መንቀሳቀስ እሚችል ነው። ይህ ግድግዳ የደገፈው ማብሰያ ሰፊ ቅርጽ ሙሉ ግድግዳውን አልሰረቀም። ከጥጋት ወደ ተወሰነ ቦታ አብቂ ነው። በቀረው ክፍተት ደግሞ፣ እነ መስ ያበጁ፣ ጫፍአቸው በወለል ሆድ በተተከሉ ማገርዎች ላይ ቋሚ እግር አጊንቶ በመነጠፍ የተመታ ጣውላ፣ አሁን ቅርንፉድ እያስፈጨ፣ ጠረጴዛ ሆኖ ያገለግል አለ። በመሰል እግሮቹ በወለል የተጎረሱ እና ከጠረጴዛው ተገቢ መመጣጠን መስተጋብር ያለው አንድ ወንበርም አለ። እሚ ወይም አብሳይ በእርሱ ተቀምጦ መክተፍ ወይ እሚበስልን መጠበቅ ይችል አለ። እሚ ተቀምጣ በመንጠራራት ብቻ ደግሞ ንዑስ መደርደሪአ ከጀርባዋ እንዳለው ዐብዩ ናሆም-መደርደሪአ ስለተበጀ ዘወትርአዊ እና ቀላል ቁሳቁስዎችን መድረስ ትችል አለች። ብዙ ጊዜ እንዳነሳችው መፍጫ ጠርሙስ፣ ዘይትዎች፣ ቅቤ፣ ቅመማቅመምዎች፣ ትንንሽ መክተፊአ፣ ቢላዋዎች፣ ማንኪያ፣ ጭልፋ፣ ትንንሽ ድስትዎች፣ ማማሰያዎች፣ ወዘተ. በእዛ አነስተኛ መደርደሪአ፣ በጋራ ታጅበው ለሎሌነት ቅጥር በመስከን ይጠባበቁ አሉ። በሌላ ግድግዳ ደግሞ ብዙ ሚስማሮች ልዩልዩ ተንጠልጣይ ቁሳቁሶችን አቅፈው አሉ። ጣባዎች፣ ቤተሰቡ እሚወድዳቸው የሆነው እና በተለይ በገጠሩ በመርከሳቸው በስፋት የተገዙት ብዙ አይነት ሌላ የሸክላ ድስትዎች እና ቁሳቁሶች፣ ጦቅየ፣ ወዘተ. አሉ። በእርግጥ የዘመንአዊ መኖሪያ ቤት ኩሽና አይሁን እንጂ ሃሳብ እና አያያዘጀ ግን የድንቅ ልባሞች ቤተማዕድ ነበር። ሁሌም ጽዱ እና አቀማመጡ ትክክል ያለ ሲሆን በአያያዙ ወጥ እና ተገማች ከመሆኑ የተነሳ ጮለቅ ብቻ እንጂ ሁሉም ለምደውት ነበር፨<br>የእሚ ቁርስ ቤተሰቡ ተስማምቶ በመርከሱ ከገዛው ከቀይ ጤፍ፣ በአማራጭነት ከተረፈው ብር ደግሞ ከተገዛው በቆሎ፣ ጥቂት ማሽላ፣ መዓዛ ቀያሪ እሚአክል በስሱ ታምሶ ከገባበት አብሽ፣ የደረቀ ጥቂት መጥበሻ ቅጠል እና በሶብላ፣ ቦለቄ እና ገብስ ድብልቅዎች የተበጀ አልሚ-ዱቄት እሚዘጋጀው ልማደኛው ግን ያልተለመደ ቢሆንም ደግ ጣዕም ያለው አካል ገንቢ ገንፎ ነበር። ከጎኑ፣ አሁንም እሚ ከገሬዎች እምትገዛው እርካሹ ማር እያገለገለ የማር ሻይ ተጥዶ ደረሰ። በመጠበቅ ሆና ለሌላ ወቅት ያዘጋጀችው ቅርንፉድ ሲደቅቅ ወደ ብልቃጥ ታጉሮ ለእምቅ (ፖቴንሻል) አገልግሎት ተበጀ። ባቤ በመላላክ መመገቢያዎችን ከያሉበት መደርደሪያዎች እየተዋሰ በመኖሪአ ክፍሉ ዋና ጠረጴዛ ተራበተራ አስተካክሎ አሽከርነትአቸውን ለእምቅ አገልግሎት አሰናዳ። መብሉ ተጠናቅቆ ሲበቃው፣ ባቤ ዜናውን ዐዋጅ በማጮኽ አበሰረ። እነ ናሆም፣ ጽዳቱን ሁሉ ፈጽመው ስለነበር በቅጥሩ እየተጨዋወቱ፣ በመተጣጠቡ ተረዳድተው ወደ ሳሎኑ ተሰበሰቡ። እንደ ቤተሰቡ ኢዘማሚ ጠረጴዛ ባህል ሆኖ፣ ማንም ከጎደለ መመገብ እሚጀመር አይደለም። እሚ ገንፎውን በሰፊ ጣባ መሰል ሸክላ ትሪው ልትገለብጥ እና ወደ ማባያ ስራው ለመዞር የኩሽና እረዳቱ ባቤን ማረጋገጫ ጠየቀች።<br>ባቤ ትሪውን በማንጠፉ አዎንታአዊ መልስ አስተላልፎ፣ ወደ ቀጣይ ተግባሩ ዞረ። ከሁሉ እንቅልፍአም ታናሹን ሊቀሰቅስ ወደ መኝታ ክፍል ዘመተ። እነ ናሆም ረዘም ከአሉት ወንበርዎች የተለመደ መቆያ ወንበርዎች ይዘው የመጨረሻ መሰናዶው እስኪፈፀም በመጠባበቅ ደምብ፣ ወደ ሙዚቃ ምቾት ተዛወሩ። አሁን ድምጹ ቀነስ ተደርጎ ከማሟያው (አክሰሰሪ) ሽንጣም ብርጭቆ ጋር ስልኩ ወደ ሳሎኑ ጠረጴዛ ወጣ። የሀመልማል አባተ “ይዳኘኝ የአየ” ወዲአው ተከፈተ። በሙዚቃ ምርጫ ሁለቱም ስለ እሚግባቡ ብዙ ጠብ የለም። ብሉይ (ክላሲካል) እንጂ በተስ. አገልግሎት ሱቆች ስለተሸጠ ብቻ ወደ ተሱ. ተገልብጦ እሚደመጥ ዘፈን የለም። መዘፈን ስለተቻለ እንዲሁ የተመረተ ምርትም በትዉስታ ማኅደርሩ ታቁሮ አይደመጥበትም። ታናናሽ ታዳጊዎቹም በድንቅ ዘፈንዎች ታጅቦ የማደግ እድል ከእዚህ የተነሳ ገጥሞአቸው አለ። ገና በጨቅላነት በቤቱ ሁለት ታላላቆች የእሚመራረጡ ምርጥ ብሉይ ዘፈንዎች ብቻ ይሰሙ ነበር። ከሞላጎደል። እነ ጥንትአዊ አስቴር አወቀ፣ እነ ብዙነሽ፣ ሂሩት፣ ኤልያስ ተባበል፣ ጥንትአዊ ጥላሁን ገሰሠ፣ ምንይልክ ወስንአቸው፣ ወዘተ. እሚኮመኩሙ ሆኑ። ከብዙ መስፈርቶች አብሮ የድምጽ ትግበራ ጥበብ የረቀቀበት ዘመንን ሲኮመኩሙ አሁንም ተዘውታሪ ብሉይ ኪኖችንም አይከታተሉም፤ አቅም በፈቀደ። ጥቂት እንደ አደመጡ እሚ ባቤ በሰተረው ሰፊ ትሪ ላይ በጨርቅ ታግዛ ያመጣችውን ጠይም ገንፎ ከሸክላው ድስት አፈሰሰች። ተመልሳ ስትወጣ ባቤ የሻይ ብርጭቆዎች እና የቤቱ አይነተኛ ዉሃ መጠጫ መርቲ ጣሣዎችም አደለ እና ተከተላት። ጥቂቱ ብርጭቆ አካል፣ በክብረበዓል እንጂ አዘቦት ዉስጥ ለማገልገል አይቀጠርም። ከሙዚቃው ጋር ትኩሱ እንፋሎት እና ሽታው ሁለቱን አድማጭዎች አወደአቸው። ብሩ በሌባ ጣቱ ጠንቆል አድርጎ ሰረቀ። “ተው!” ናሆም ተቃወመ። ምላሱ ላይ ጠረገው። 'ኤክ' የባቤ ከጧቱ ባያሌው ረግበው የቀነሱ ኮቴ ድምድምዎች አብዛኞቹ በታዳጊዎቹ በቀለጡ ላስቲኮች እና እርጥብ እንጨቶች መቅረጽ የተፈበረኩ ሹካ እና ማንኪያዎች ይዘው ደረሱ። በእየስፍራው ገንፎውን ጠነቋቁሎ ሰካሰካ አደርገአቸው እና ወንድምዎቹን ተገላምጦ ተመልሶ ወጣ። “እሺ እሱባለውን እከፍትአለሁ!” ብሩ ጣቱን መልሶ ለመጠንቆል ካበጀ በኋላ ፍቃድ እየጠበቀ ተደራደረ። ናሆም “ዘፈን ማሞቂአ አይደለም” እሚሰኝ የሃገር መዉደድ እንደ ሆነ በታሳቢነት የተዘለለ የየሺ ሙዚቃ በገሃድ አምርሮ ስለተቸ የ አኪለስ ቁርጭምጭሚቱ ሆኖ የሰሞኑ መጠቂአው ነው። ‘አስቀያሚ የሹፈት ሙግ.’ “አትከፍትም” በመቀየም ስሜት ናሆም ተናገረ። “እንዲያ ከሆነ!…እ?” ወፈር አድርጎ በሌባጣቱ ጠይም ገንፎ ቧጠጠ። ምላሱን ጎልጉሎ በማንጠፍ በላዩ አንሸራተተው። እሚ የቅቤ፣ እና ምጥሚጣ፣ እቃዎች ይዛ መጥታ ገንፎው አቅራቢያ ንዑስ-መካን ላይ አስቀመጠች። ባቤ ቂጥቂጥ መከተሉን ዘወትርአዊ አመክዮ አስችሮት የበርበሬ ብልቃጥ አምጥቶ እንዲሁ አስቀመጠ። እሚ በአንድ ገበታ ሁሉን አሟልቶ አንዴ የማቅረብ ባህል ወሳኝ፣ ከኩሽና ዉጭ ደግሞ መብል ማብሰል ከቶ ወንጀል፣ ብላ በእምታምነው መርኋ መሰረት፣ ወደ ኩሽና ተመልሳ ሻይ ማምጣት ዞረች። በእናትነት እና ኑሮ ቀለሟም አማካይነት የኩሽና እና ጠረጴዛ ፍልስፍዋ ከህይወት መርሆቿ አንዱ የሆነ ነው። ባቤ ወንድሞቹን አሁንም ገልመጥ አድርጎ ተመለከተ እና አብሯት ተከትሎ ዉሃ ለማምጣት ባቤ ሄደ። እራሱን ለመቻል እና ወደ ጉርምስና ከቶ ለመግባት እሚጥረው ባቤ ማፍጠጡ የመናቅ መሆኑ ተፈጥሯዊ ስለሆነ ማናቸውም ምንም አላሉም። ‘አለማፍጠጥ ግን የስልጣኔዎች ሁሉ መጨረሻ ነው፤ ለእዛ ሲባል የስልጣኔ መጀመሪያም ሆነ። ወደፊት ስለ እዛ እነግራችሁ አለሁ፤’<br>ብሩ አሁንም ጥቃት አመቻቸ። በሹፈት ፈገግታ ታጅቦ፣ ናሆምን በግንባሩ ተመለከተው። “አቦ አቁም አታበሳጨኝ!” “ዘፈን ማሞቂያ አይደለም እወድሽ አለሁ እኮ ማለቴ ወድጄሽ ነው ያሟሟቅኩት…” እየአለ ወደ ስልኩ ሌባጣቱን በአማራጭነት ሰደደ። ናሆም በእየሻይቤቱ ያንን ዘፈን አንድ ሰሞን ሲሰማ “እንዲህ ያለ ሙግ. ላይ ታረፈ በቃ! ጭንቀታም ሙገኛ (ሊሪሲስት) … በአረንጓዴ ሀገር ስንራ፣ በኢፍትሕአዊነት ትዉልድ ሲበደል፣ የዘመነ ዓለም ዕዉቀትአዊ አመራር በምድሩ ሲሰለብ፣ እና የሃገርዎች ጭራ ሲኮን፣ ነፍስ አስጸያፊው የአፈር ማሞገሱ ዘፈንአችን አነሠ? … ጭራሽ የሃገር ዘፈን ለመዝፈን ያክል ብቻ እንደ እሚዘፈን እና ዘፈን መሳለቂያ እንደ ሆነ ታመነ?!” ብሎ ነበር። የናሆም አረዳድ ሙገኛው ሲገጥም ማንጎራጎሩን ስለሃገር የግድ እንዲሆን ለማስቻል ሲል ብቻ ሲጠበብ ሲጠበብ፣ ሳቢ መነሻ-ሃሳብ ስለአጣ ይህ ስነልቦናውን ገልብጦ በመሳደብ የጀመረበት ነው እሚል ነበር። “…'ማሞቂያ አይደለም’ ነው ያለው ግን! ጓዴ?” ብሩ አአልፎአልፎ ለክርክርቴ (አርጊመንት) ፍቅሩ በናሆም ሃሳብ ባይስማማም ቢስማማም በመቃረን እሚለውን ለመስማት ይዘጋጅ ስለ ነበር ሻይቤቱ ዉስጥ ሲጠጡ ተከራክሮት ነበር። ናሆም ከሻይቤቱ መስኮተድምጽ (ራዲዮን) እሚወጣውን 'ዘፈን?’ አንገፍጋፊ አድርጎ እንዲጠላው ጭራሽ አባሰበት። “ለምን እንደ እዛ ገጠመ? ዘፈን ማሞቅ ስለፈለገ እና ግን ያን ማድረጉን ስለፈራ ግን አማራጭ ስለአጣ፣ ስለ ሁሉ የዘፈን ጭብጥዎች እና ዘውጎች (ጀነርስ)፣ አቀንቅኖ ስለሃገር መተው ስለ ገበያው እሚጠላ ብሎ ገመተ፣ 'ዘፈን ማሞቂአ ነው’ በሚል በስውር ሲናገር ያመለጠው ዳራ (ትራክ) ነው፤” ናሆም በወቅቱ ያንጎራጉሩ ከነበሩት እነ አቡሽ ዘለቀ ይሻላሉ ይል ነበር። አንደ ልዕለ-ታሪክኛው፣ ዝሜ-ዘርፈህብርአዊነት (ፕሮ-መልቲቲዉድ-ነስ) ታጋይ መሪ ቴዲ አፍሮ፣ ስብእናአዊ አመራሩን በሙግ. ተከትለው ማህበረሰብአዊ ችግሮችን ማቀንቀን አሳይተው ከነበሩት ጥቂቶች ናቸው። ሙሰኛዎች በዙ፤ እኛን ምንነካን በማለት በግልጽ አቀነቀኑ! ለዚህ እርምጃ ናሆም የድጋፍ ልቡ ቀለጠ። ሲጀምር ሀገሩ ችግር እንዳለበት እንጂ፣ ምን እንደሆነ ግን አብጠርጥሮ እማያውቀን ችግር ህዝቡ እንዲያስበው፣ ሃቀኛ ዘፋኝ ካለ ያን ይዘፍናል። ከአፈሩ ለምነት ይልቅ ስለአፈሩ ጥበበምርምር (ሳይንስ) ያቀነቅን ነበር ብሎ ይሟገት ነበር።<br>ብሩ የናሆም ቁንጽል ክርክርቴ፣ አብጋኝ ኢአመክዮአዊነት ከማጤን የተነሳ እንደሆነ ገመተ። ኢአመክዮአዊነት የቀሰቀሠው ንዴት፣ ናሆምን ሲያበግን ከተመለከተ ግን፣ ነጥቡን እያስተዋለ ወደ ማፌዝ ይገባ እና የስሜት ነገሩን ለማብረድ ይጥር አለ። ሁሌም ብሩ ይህን አድርጎ እንደታላቅነቱ አቀዝቃዥ ተሳታፊነትን ይወጣ ነበር። “ልማትአዊ ዘፈን ትወድድአለህ ማለት ነዋ!” በማለት አሾፈበት። “መልማት ስለ እማልጠላ!” ብሎ መለሰለት። 'ገና መልማት ጫፉ ሳይነካን ልማትአዊነትን አዛብተን ተገንዝበን የት ይሆን የታዳጊዎች ተስፋ!’ ስለዛ ብቻ ብቻ ግን አይደለም የወቅቱን ሙዚቃ ዓለም ሞላጎደል የእሚአጥላላው። ‘በ ግልዮሽአዊ (ኢንዲቪጁዋል) ድምፅ-ቀለም እሚዋብ ዘፋኝ ከገበያው ጠፍቶ አለ፤ ጥንትአማነት (ኦሪጂናሊቲ)፣ በተለየ በሃሳብዎች፣ ከቶ የለም ማለት ተቻይ ነው፤ በስልትም ያው ነው… ቀላሉ ሥራ ድምጽ ዉህደት እንኳ መሳሪአዎች በአሃዝአዊነት (ዲጂታላይዜሽን) ቢመነደጉም ኋሊትአዊ ለውጥ አድርጎ ለጆሮ እረባሽ ሆኖ አለጥራት በእየጢሻው እሚዋሃድ ነው፤ ለገበያ ሲባል ችግርን ማጋለጥ እና መሟገት ቀርቶ፣ ህዝብ ማታለል እንደ ባህል ሰርጾ አለ፤ ዜማ ሹፈት ሆኖ ግን ሹፈትነቱ በምትዎች ጫጫታ ተደብቆ ተዘንግቶ አለ። በወርቅአማ እሚሰኝ ዘፈን ወቅትአችን በነበሩት ሃቀኛ ሙዚቃዎች፣ ምትክ የጃምቦ ማወራረጃ ጩኸትዎች ብቻ ነው ያሉት እንጂ እማይጮኽ ደግሞ ከቶ አይደመጥም…፤’<br>ብሩ ናሆምን ጨምሮ ለማበሳጨት ሳይችል ወዲአው ሁሉ ተሰናድቶ አበላሉ በይፋ ሊታወጅ ደረሰ። ገንፎው ዙሪአ በሁለት አነስትኛ ጣባዎች በአንዱ ለብ የተደረገ ቅቤ ከምጥሚጣ ጋር፤ በሌላው እሚ እሚቀናት ተልባ በዉሃ ተለውሶ ለአማራጭ ማጣቀሻነት ቀረበ። ብሩ፣ ናሆም፣ የተቀሰቀሰው ቢግ፣ ባቤ እና ጢዩ ጠረጴዛውን ግርማሞገስ አልብሠው በእሚ የእራስ-አቀማመጥ መሪነት ለመብሉ ተዘጋጁ። ቢግ ሁሉም እንዲቋደስ ለማስቻል ቀድሞ አቡነዘበዘማያት በይፋ እንደ ተለመደው አደረሰ። ትኩስ መብልአቸውን ከፈለጉት ማባያ እየቀቡ በመመገብ ተያያዙት። በህብረት ይሁን እንጂ ሁሉም በእርጋታ እና ክብር ይመገብ ነበር፤ እንደ ምንጊዜውም ባህልአቸው። ጮለቅን የታቀፈች እሚ ገበታ ምግባርዎች ማስተማሯ ከጥንት ስለጀመረ በጨዋታ መነታረክ ካልሆነ በቀረ በስነስርኣት መመገቡ፣ ሁሉ ልማዱ አድርጎላት ስላለ በምንም ድርጊትአቸው አትበሳጭም። ሳይቋረጥ በእሚላክላት የገጠሩ፣ ስሙ ወንድሜ እና ሀሴት ተብሎ በእሚፈታው በአቶ በርናባስ ስጦታ ስትንበሸበሽ ገሚሱን ወዲአው ትሸጥ ነበር። በመስ እማይነጥፍ ስብከት መሰረት ለልጅቿ እሚጠግን የተመጣጠነ መብል ለማሰናዳት ብዙ ሌላ ጥራጥሬዎች እና ቅመማ ቅመምዎች ለዉጣ ትሸምትበት አለች። አሁን ከልጆቿ በኩርዎቹ ደግሞ ለኃላፊነት መድረስ ሊጀምሩ ነው። እንደ አጋጣሚ፤ ነገርግን፤ ሁለቱም እንደመንትያ እሚቀራረቡት ታዳጊ ወጣቶቿ፣ የመቀጠር ሥራን ከወዲሁ የተጣሉት ምክረሃሳብ ነበር። አይፈልጉትም። ዘመኑ በግል አግዝፎ መበልጸግ እሚአዋጣ እንደ አደረገ እሚአምኑ ወጣትዎች ሆኑባት። ይህ አንዱ የጭንቀት ምንጭ ቢሆንባትም ምንም ማድረግ ሳትችል፣ ሁኔታው እንደ ከበባት ነው። አቶ በርናባስ እንዳሉት ቶሎ ደርሠው ከባዶነቱ ሊያወጧት አይችሉም። እና ምን ይደረግ? በቀረ ከመጨነቅ መፍትሔ ላይ መመራመሩ አልቀናትም። ልጆቹ የፈጠራ ስራን አንዴ ቀንቶ ካገኙ ላይላቀቁት ግን እንደእሚናፍቁ አረጋግጠዋል። “ስለ ዘሽ. (ዘመንአዊ ሽንትጨርቅ = ዳያፐር) አስተዉይ እስቲ!” ወጣቶቹ አቋምአቸውን አንድ ቀን ደግሞው ሲያረጋግጡ ለምሳሌ ብለው ያነሱት ነበር። የዘሽ. ቀውስ ንግዱ አንድ አብነትአቸው ነበር። እሚ ሽንትጨርቅ ከነጠላዎች ተጠቅማ ነው ያሳደገችአቸው። ግን እንደእሚገኝ እንድታይ ብቻ ብሎ፣ ብሩ ጮለቅ እንደ ተወለደች አንድ ዘሽ. ገዝቶ አበርክቶ ነበር። እሚ ተደንቃ የጮለቅን ቂጥ አሸገችበት። ባለማመን ብትሆንም ስለተብራራላት ብቻ የጮለቅን ወገብ አስራበት ለሰዓት ያክል ቆየ። ወዲአው ተቀምጠው እየተጨዋወቱበት፣ የእሚ አራስቤት ብቸኛነትን ለመግፈፍ ቁጥር መቁጠር አስተምረዋት ያስለመዷት የካርድ ጨዋታን፣ አብረዋት ተያይዘው እና አብረውም አጥሚት ተጋብዘው ሲጎነጩ ነበር። ዘሹ.ን እሚ ደጋግማ ዞር እያለች ትመለከት ነበር። ጨዋታአቸው ገና ጥቂት ከመሄዱ እና እሚ ሚስትዎችአቸው ማንም በሌለበት በድንገት ቢወልዱ፣ ቶሎ እንግዴ ልጁን እንደ ገመድ ከልጁ ሆድ ክንድ እሚጠጋ ያክል ከፍ ብለው መቋጠር ከዛ መቁረጥ ከእዛም ሚስትአቸው ብድግ ብላ ዱብዱብ ስትል የእርግዝና ተረፈ ምርቱ ሁሉ ተጠራርጉ በብልቷ ሾልኮ እንደ እሚአመልጥ እና መዉለዱ እንደ እሚፈጸም ስታብራራልአቸው ጨዋታው በሣቅ ጦፈ። ባቤ አጠገብአቸው የካርዱን ጨዋታ እየለመደ ያደምጥ ስለነበር “ኤክ! ኤክ!” ብሎ መቀፈፉን አሳወቀ። እሚ ፈገግ ብላ “ጭራሽ ከእዛ ቀድሞ ለመዉለድ ስታምጥ ሚስትህ አሯን ነው ቀድማ ዱብ አድርጋ እምትጥልልህ እኮ ገና!” ብላ ከት ብለው እንዲስቁ አደረገች። እንደባቤ ናሆምም ተፀይፎ ገሸሽ ሲል፣ ሀኪም መሆን እሚመኘው ብሩ አስቀድሞ ያጠናው ክፍለ-ማዋለድ ህክምና መረጃ ስለነበር፣ ባለመገረም “ምን ይሄ ተፈጥሮአዊ ስርኣት አይደል እንዴ? አር የሰው ልጅ ስነስርኣት (ሲስተም) ነው! ምኑ ይደንቃል! እደጉ እንጂ!” ብሎ ጥላቻአቸውን ወዲአው በተገቢ ስልጣኔ ሞረደ። ዘመንአዊ አመለካከትዎች አነፀ። ሁሉም ተስማምተው መፀየፍ የቅጽበት ገሃድን ማጋነን ነው በእሚል ወደ ጨዋታው ተመለሱ። የብሩ አዲስ ዘሽ. በጮለቅ ገላ እንደ ተጣበቀ ዘልጎ ሳይቆይ ግን ወዲያው ካገልግሎት ዉጭ ተደረገ፨<br>የህፃኗ አር እና ሽንት ካካሏ ሲመዘዝ እሚ ሳታይ ዘግየት ብሎ በመጥፎ መዓዛው መሪነት ከካርድ ጨዋታው ተመልሳ ፈተሸችው። የእለቱ ተረኛ አጣቢ ባቤ ተጠርቶ ዘሹ.ን አጥቦ እንዲአመጣ በእሚ ታዘዘ። ሁለቱ ወጣትዎች መሣቁን ከወኑ እና እቃው ከአሽከርነት እሚባረር፣ ተጠቅመህ-ወርውር ቁስ እንደሆነ አሳወቋት። ብዙ ገንዘብ እንደ ወጣበት አስተውላ "በላተኛ ሱቅ!” መዳፏ ፊት አበስ አድርጎ በሃዘን በመያዝ ሆና ካርድዎች አብራ ሳታስተውል በመዘቅዘቅ እያሳየችአቸው አወገዘች፨<br>ብሩ እና ናሆም የሱቅ ሥራ ሳይሆን የአምራቾች ምትሃትአዊ ንግድ እንደ ሆነ እና አንድ ጨቅላ እስኪአድግ ብዙ ኢትዮጵያዎች በወር ሺህ ብርዎች በማውጣት እልፍ ፍሰተንዋይ (ኢንቨስትመንት) ቂጥ ለማሸግ እንደ እሚአፈስሱ አብራሩላት። እሚ ከእርሷ አያያዝ አነፃጽራ ስለልዩነቱ ማቀድ ገብታ አናቷ ዞረ። አንድ ጨርቅ ስንቴ እንደ እሚታጠብ እና ዳግ-እሚአገለግል (ሪ-ሰርቭ) እንደሆነ ታውቅ አለች። አንዴ የተገዛው ዘሽ. ወዲአው ሲወረወር አይታ ደግሞ ክዉ አለች። በቀን አንድ ቢጠቀሙ እንኳ ምን ያክል የወጪ ግንድ እንደ ሆነ ታይቶ ከበዳት። “አይ! አንተ ሞኝ ሆነህ ስለ ገዛህ እንጂ ይይህ የሀበሻ እናት ሳይሆን የፈረንጅ ብቻ ነው!” ከከንካኝ ሃሳቧ መዉጫ እና የአጠቃቀሟ ግብረመልስ መሠል ቃል ካርድ እያማረጠች በመጠመድ ሰጠች። ብዙዎች ይህን ሲጠቀሙ እንደእሚገኙ አብራርቶ ብሩ ዘመኑን አስተማራት። እሚ የወቅቱ እንስቶች እና ቤተሰብ መሪዎች ቀዉሰዋል አለች። ብዙ ወጪ ለዘሽ. እንደሚበትኑ እና አልሚ ነገር ለልጆቻቸው በምትኩ መመገብ እንዳልቻሉ አስባ መቀበሉ ከበዳት። ለዘሽ. ብዙ በማውጣት ነገ አልደላኝ ነበር በእማይል ቂጥ ፈንታ የደለበ እና ጤናአማ ሰውነት ያጣ ትዉልድ እንደ እሚአድግ በመብገን የታያትን አቀረበች። እነ ብሩ ህዝቡ መቀወሱ ላይ ተስማምተው፤ ሽንትጨርቅ የማጠብ ስንፍና እና በምትኩ እንቁላል ማር፣ ወተት፣ ቅቤ…አለ መግዛቱ የዘሽ. ገበያው ቀን እንደ ሆነ እንድታምን አደረጓት። “እና እኔ እምነለው ከእናንተ ቶሎ ሥራ አንፈልግም ማለቱ ምን አገናኘው?” በሌላ ትንግርት ሆና ጠየቀች። እነ ናሆም ተያዩ። ፈገግ ብለው ፍረወይኒ መብራቱ እምትሰኝ ኢትየጵያአዊ በ ሲኤንኤን የዓመቱ ጀግና ሽልማት መሸለምዋን አነሱላት። “ለገጠር ተማሪዎች፣ ጎጆ ዉስጥ በቀላል እሚመረት እና እንስት ከሆኑ በነፃ የእሚሰጥ የ ወርት. (ወርአበባ መጥረጊአ = ሞዴስ) እንዲሰጥአቸው በተግባሮት ነድፋ ብዙ ወጣት ኢትዮጵያዎች በነፃነት እንዲማሩ ስላገዘች መቶሺህ የአሜሪካ ዶላርዎች ተሸለመች።” ብሩ አብራራ። እሚ ፍቺው አይገባትም። ናሆም ፈገግ ብሎ ቀጠለ። “ለምሳሌ በቀላል በጎጆ አምርቶ ለባለ አነስተኛ ገቢ እንስትዎች ይህን መነገድ ይቻል አለ!” ብሩ ቀበል አድርጎ አንድ አረዳድ እንደ አለው ያክል ቀጠለበት “ወይም ደግሞ እንደ ተጠቀምሽው እጅግ ዘመንአዊ ያልሆነ ሽንትጨርቅ በጎጆ አምርቶ…” ብሩ ከአፉ መነተፈው “…ለ አነስተኛ ገቢ ቤተሰብዎች” ናሆም መልሶ ከአፉ ነጥቆ ቀጠለ “…ወይም ሃበደታም ቢሆኑም ላልቀወሱ ልጅ አሳዳጊዎች ሁሉ መሸጥ እሚቻል ነው።” “የወይን ፍሬ እንደ ስሟ የሆነችን እንስት፣ በጎስራ ከተንዠረገገ ለድሃ እናትዎች ተያያዡን የቀላል ወጪ ዘሽ. ሥራ ልትሰራ ብትችልም…” ናሆም ሃሳቡን ቀጥሎ አንጠለጠለ እና ዝም ያለ ወንድሙን ተመለከተ። ብሩ ደመደመለት “…ማለት ብቻ ዘመኑ አንድ ነገር ለፈጠረ ሰፊ ገበያ አለው ነው እምንልሽ! እሚነቃ እና አስሶ እሚሰራ ነው እሚአስፈልገው..” ወንድሙን በጨረስኩ መንፈስ ተመለከተው። “ስለ እዚህ ተቀጥሮ መስራት አንፈልግም ነው! በመነገድ የዘሽ. ንግድ ገቢን እራስ እስኪአምም ድረስ ስለሽው ነበር። እማይቀለረጥ ገቢ አለበት። የተማረ ወይም ያሰላሰለ አንድ ነገር አቅዶ ከተነሳ… በሰማይ ሁሉ ለመጓዝ የቀና ዘመን ነው! ሥራ! ሥራ! ሥራ! የሥራ ዘመን ደግሞ ከተቀጣሪነት አይሻም ነው እምንልሽ።”<br>በግራቀኝ እየወረወሩባት ሲወያዩ ሁሌ እሚአሳምኗት እና በእማታስተውለው መፍዘዝ ሰምጣ ፈገግ ብላ በመነሁለል ሁሌ ታምንልአቸው አለች። ብትስማማም ለአመል ያክል ግን ትቃወም እና ሥራ እንዲቀጠሩ መክራ ዘወር ትል ነበር። ሃሳቡ ቢጥምም ገቢ ግን ቶሎ ማግኘት ስለ አለብአቸው መልሳ ትጨነቅ አለች። መልሳ ደግሞ ዞሮ ዞሮ እራስ ከቻሉ፣ የገጠሩ ገጸበረከት በቀነ-ገደቡ በእዚህ ዓመት ማብቂአ ሲቋጭ ገቢ ቢቀንስም፤ በሁለት ዓመትዎች በወጥነት የተቋቋመ ምትክ ምንጭ ስለ አጊንታ አለች ትተውአቸው አለች፨<br>በ አዲስአበባ፣ አውሮፓ፣ ሰሜን አሜሪካ እና ፋሲካይት ትልቅ የባህል ልብስ ድረ-ንግድ እንደ ትጉህ ሸረሪት የዘረጋች ወጣቷ ቀልጣፋ ሥራ ፈጣሪ ሐረግ ቸርነት፣ ሁለትሺህ ብር በወር ትከፍላታለች። ቆንጽላ፤ ግን ከእሚ አንድ ሰራተኛነት አንፃር በዛ አለ እሚሰኝ፤ እምታቀርብላትን ከነጋዴዎች እሚሰበሰብ ጥጥ ተረክባ፣ ፈትላ፣ ለመሸመን ሲደርስ ታስረክባት አለች። ባለፈው የፋሲካ ሰሞን ስትጎበኛት ድንገት ተነስቶ እንደ ተወያዩት፣ አሁን ደግሞ መስከረም ላይ ተቀጣጥረው፣ መጪው ዓመት መደወሪአ ገዝታ መሸመን ልታስጀምራት እና ከቤት መዉጫ አመክዮ ለሌላት እሚ ሦስትሺህ እና አምስት መቶ ብርዎች ደመወዝ ለመክፈል ቅኗ እና ባለሳቂታ ስብእና ወጣት ነጋዴ ዕቅድ ይዛላት አለች፨<br>ቀልጣፋዋ ሐረግ ከብዙ የገጠር እንስትዎች ጋር ይህ ብልህ የድረ-ንግድ ገና ስትጀምር አስተሳስሯት ነበር። ከቅናሽ ክፍያአቸው ብዙ አተረፈች። ስትረዳአቸው ሲረዷት ትልቅ አትራፊ ሆና ንግዷ ዘለገ። አሰፋችው። በቀጣዩ ሥራ በግሏ ንድፍ ተምራ እና አጥንታ ተመለሰ ች። ነድፋ፣ ሰፍታ እምታቀርበው ዘመንአዊ የባህል ልብስዎች ልዩልዩ ቅጥ (ስታይል) ሲሆን ገበያው ከኢኅአዴግ. የህዳር ፳፱ በዓል ጋር በተለየ ይደምቅላት ነበር። በእምትሰጠው ጉርሻ ብዙ መንግስት መስሪአቤትዎች ከእርሷ የብሔረሰብ ልብስዎች እሚሉትን ይገዙ ነበር። ሁሉን አቃለሁ በማለት ቀለምዎች በመዘበራረቅ ልብሱን ስትሰጥ ይረኩ ነበር። ለማድመቂአ ሚሊየንዎች ሲበተኑ፣ ክፍያዋ ከፍ ተደርጎ ከመንግስት ካዝና ይወጣ እና ከፊሉ በከፋይዎቹ ስምምነት ለጉርሻ ተመላሽ ይሆን አለ። በሂደት ግን ተሰጥዖ እና ዘመንአዊ ዕዉቀት ከብልሃት ጋር ስለነበራት የልብስ ንድፎቿ እና ሥራዋ፣ በመንደር እሚቀር አልሆነም። በንግድ ድር መገንባት ክሂሎቷ፣ የተረፈችውን ይዛ ወደ ሰፊ ሽል ንግድ ዓለም እራስዋን ገፍታ አሹልካ ተፈናጠጠች። ደግ ገቢ በዘመንአዊ ባህል-ልብስ ቅጥ ንግዷ በመሰብሰብ ዳግመኛ ወደ አዲስ መሰላል አደገች። የመንደሩን ንግድ አብዝታ በመቀነስ ወደ አዲስአበባ አተኮረች። በደግ ብልሃቷ የአዲስአበባ ገበያ ከፍተኛ ሃብታሞች ሰርጎችን እስከመቆጣጠር እና ብዙ አሻራ በመደበኛውም ገበያ እንድታሳርፍ ፈቀደላት። ደግ ንድፈኛ (ዲዛይነር) ተብላ ብዙ ሽልማቶች እና ቄንጥ (ፋሽን) ዉድድሮች አሸነፈች። በሂደት ግን ንግዱ አዲስአበባ እሚቀር አልሆነም። በቀጣይ በረራዋ ደግሞ ወደ ባህር ማዶ ዞረች። ልክ እንደ አፍሪቃ የመጀሪያዎቹ ሴት ሚሊየነሮች፤ እንደ ቶጎዎቹ እንስት ባህል ልብስ አምራቾች የሃበሻ ብዙ ሃበሻዎች ከሃገር ሲወጡ ባህል ልብስ ስለእማይዙ እና ቤተሰብ እዛ ስለ እሚአፈሩ ለበዓልዎች ግን ልብሱን መፈለግ ይጀምሩ አሉ። ከነቤተሰብአቸው እሚሆን አቅርቦት እምብዛም ስለ እማይኖር፤ የእርሷ አቅርቦት ከደቡብአፍሪቃ በመነሳት ወደ ዐረብዎች፣ አዉሮፓ፣ እና ሰሜን አሜሪካዎች በዝግመት እየተንሰራፋ ደረሰ። ይህ የምጣኔሃብት ግዛቷ ትንሽ ሰውዎች ጨምሮ አስቀጠራት። ግን ከገጠር በቅላ፣ ሃገር ወዳድ የሆነችዋ ሐረግ፣ ሃገረሰብእዔውን (ካንትሪሳይድ-ሜን) ለመጥቀም ሥራዋ ዘመንአዊ እዉቀት ፈላጊ ካልሆነ፣ በገጠር እሚገኝ ድሃ እንዲሰራው ታደርግ ነበር። እሚን ሁለት ዓመትዎች በፊት ስታገኝ በወሬ እንጂ ያኔ እሚ ከተማ ከገባች አምስት አመቷ ነበር። እሚ ለደጉ ጎረቤቷ በርናባስ ገጠር በመሄድ በፋሲካ ሳምንት በያመቱ ጉብኝት ታደርግ ነበር። አመቱን እማያራዝሙ እንደ ሆነ ገልጸው በቤተሰብነት ግን የእሚቀርቡአት ጎረቤት ከወጣቷ ነጋዴ ጋር በገጠሩ ሰራተኛ ስታፈላልግ በሰፊ ጆሮአቸው ወሬውን ገብቶ ስለ ነበር እንደ ምትክ ገቢ ቢሆናት ብለው ከሐረግ ጋር አገናኙዋት። “እኔ መሬቱን እሻው አለሁ። ገቢዬ አሽቆልቁሎ አለ። ለልጅዎቼ ከተማ ቤት ልገዛ ደግሞ ሳንቲም እየአጠራቀምሁ ነው። ላአንቺ አልሆንም። ባልሽ በደለሽ መሬቱ አልቅሰሽበት አይቀናኝም ብዬ ስለ እናቴም መለመንሽን አይቼ ነው የምረዳሽ። ይቺ ወጣት ፈታይ ትፈልግ አለች። አንቺ ደግሞ በስንቱ ሙያ የተካንሽ ነሽ።” ብለው አበረታቱአት እና አገናኙዋት። እሚ ከተሜ ናት በሚል ወጣቷ እንቢ አለች። ግን ሁሉ የእሚ ነገር ሲነገራት ዞሮዞሮ ሰው መርዳቱ ስለ እሚገድዳት ፈትና ስታረካት ቀጠረቻት፨<br>ይህ ገቢ የገጠሩ ገጸበረከት በአዲሱ አመት ሲቋጭ እንደ ተለመደው ባይሆንም ለመኖር ያክል ምንጭ ነው። ያቀደችው ደግሞ ጠላ እና አረቄ አብሮ በመሸጥ ከተማ መግባትዋን በገቢ ብዝበዛ ልትጠቀምበት ነው። ከተማው በባህል መጠጡ አቅርቦት ተምበሽብሾ የእሚ ችክን ያለ ሙያ ገበከው ቢወርድበትም ለዋናው ገቢ አጋዥ ከሆነ በቂ ነው ብላ አቅዳለት አለች። መስ ደግሞ በወር መቶ እና ሁለትመቶ ብርዎች ሳይልክላት አያልፍም። እግዜር ከደገፈው መስም ይህን ሊአቋርጥ ካልቻለ መብራት እና ዉሃ እንኳ ሊሸፍን ይችል አለ። ካደረሳት ደግሞ ኮፍያዎች በመስራት ስለ ተካነች በቻይና ክርዎች በምትታታቸው ኮፍያዎች ገቢ ጭምር ጥቂት ይስተካከል አለ። ስለ እዚህ እሚ በመጪ ጊዜዋ የገጠሩ ገፀበረከት ጠፋ ብላ ስጋት ገብቶዋት አታውቅም። እንደ እምትረካበት ልጆቿ ድሃ ቤተሰብ ሆነውም በብልሃቷ እንደ ደላው ቤተሰብ ነገአቸው ላይ ብቻ አተኩረው በስርኣት እያደጉላት ነው፨<br>የጧት መብሉ እንደ አለቀ ቁሳቁስዎችን የመንከባከብ ስራው በሁለት ቀን አንዴ የቢግ ስለ እሚሆን ሰብስቦ በጥንቃቄ ወደ ጓሮ ዞረ። ከዉጭው ኩሽናው ስር ወደ ጊቢ ዉጭ ፍሳሹ እሚጓዝ መስመር የተሸለመ በፍርግርግ እንጨትዎች ለዕቃዎች ማጠቢአነት የተቋቋመ ከፍታ ላይ፣ ከስሩ ባለአንድ ብቻ ደረጃ በመሰቀል ወጥቶ፣ ቢግ ዕቃውን ሁሉ ቆሻሻው ሳይደርቅበት ወዲአው አጠበ፨<br>ሳይታሰብ ሰዓቱ ስለረፈደ የመስን መምጣት ሁሉ ይጠባበቅ ጀመረ። ብሩ ቤቱን ከወንድሙ ጋር አሰናድቶ ወደ ሲጨርስ ሌላዎቹን ተለይቶ ወደ ጓደኛው ዮስ እንደ እሚሄድ አሳውቆ ወጣ። ባቤ መስኮተድምጽዋን ከፍቶ የክረምቱ አንድ ግል ሥራውን ሰሞኑን ጥራጥሬዎች በማሰስ ለቃቅሞ ከወረቀትዎቹ ጋር ይዞ ሲቀመጥ፣ ናሆም የጣለበትን ቤትስራ ደግሞ ለመንትያነት የቀረበው፣ ብዙ እማይበልጠው ቢግ ተያያዘ። የእንግሊዝኛ መማሪአ ወረቀትዎች ናሆም ራሱ ከእሚወድደው ኢንትርሚዲየት ኢንግሊሽ ግራመር፦ የካምብሪጅ ኅዋአዊከተማ እትመት ድንቅ መጽሐፍ ቀምሞ አበጅቶለት ነበር። መጽሐፉ ለናሆም፣ እንግሊዝኛ ለመማር ከተፃፉ እና ከገጠመው መጽሐፍዎች ድንቁ እና አንድኛ እሚለው ነበር፤ በአንድ ገፅ አንድ ምዕራፍ – በመቶሰማኒአ ገፅዎች መቶሰማኒአ ምእራፍዎች ከአስደማሚ አቀራረብ ፍፁምነት ጋር። ‘ይህን አንብቦ በእንግሊዝኛው ላይ ያልጎበዘበት ቢኖር አላምንም፤' ቢግ መሰረትአዊ ንግግርዎች መከወኛ ሰዋሰው በማጥናት ብዙ ሳይቸገር ስለለመደ ፣ በእዚህ ወር ቢግ መሃከለኛ የቋንቋውን አቅም በመሰነጣጠር ላይ ነው። ከአራት ወደ አምስትኛ ክፍል ገና ቢዛወርም እንግሊዝኛ ው ግን፣ ለማስተማር ፊቱ ከእሚቆሙ መምህሮች እሚሻል ሆኖለት ነበር። ቢግ በእርግጥ በግሉ እንደ ቀሩት ልጅዎች ብሩ በተለየ ደግሞ ናሆም እየረዱት እማይሞክረው እና እማይደሰትበት ምርምር ብጤ ነገር አልነበረም። ናሆም በልጅዎች ወደ ዐዋቂ ሰውነት ማንቃት ወይም ማደግ እምንለው ደረጃ መድረስ የተካነ ስነልቦናአዊ አገነዛዘብ ነበረው። ይህ ወደ ታናናሽዎቹ ልዩነት ሆኖ እንዲመጣልአቸው የተወው ነበር፨<br>ናሆም ጆን ፊኒስን ድንገት በቤተመጽሐፉ የዉጭ ስጦታ መጽሐፍዎች መሀከል አጊንቶት አገላበጠ እና በፍቅር ወደቀበት። ፊኒስ (ሰቨን ቤዚክ ሂዉማን ጉድስ) ላይ እንደ አለው፣ ህፃን ሰው፣ ነብሱ ያልነቃ ገና ሂወትን ከአካባቢው በዝግመትአዊ አጢኖት (ኦብዘርቬሽን) ብቻ እሚለማመድ፣ ወጣኝ ዘረፍጥረት ነው ይል ነበር። አካባቢው ምንም ካስተማረው ያን ምንምን በብቃት መሆን ይችል አለ። ነገርግን የ ፊኒስ ዳግምርምር (ሪሰርች) ልቦና (ኮንሰንትሬሽን)፣ የህፃን ሰውዎች አንጎል ማደግ ምንጩ፣ ተተግባሪአማ አመክዮአዊነት (ፕራክቲካል ሪዝኔብልነስ) ማጥናት መቻልአቸውን አስምሮ ማሳወቅ ነበር። ከተግባር-ተኮር አመክዮ ብቻ፣ ልጅ እንደ ሰው መሆን ይማር አለ። ከእሚነገረው ቃልዎች ይልቅ የተግባር አመክዮን የማነፍነፍ፣ መመርመር፣ እና አብነት የ ማድረግ ተሰጥዖ በህፃን ሰው ሁሉ እንደ አለ አስረዳ። ወደ አንድ ገጸባህሪይ ልጅን እሚቀርፀው ይህ የተተግባሪ አኳኋን ማጤኛ አመክዮ ስጦታው ወይም አቅሙ እንደ ሆነ አሳየ፨ ናሆም በእዚህ የ ፊኒስ አገነዛዘቡ ልቡ ፈካ።ልጅዎች በመጥረብ እንደ ተፈለገው ማጎንቆል እንደ እሚቻል በፊትም ያዉጠነጥን እና የተዝረከረከ አያያዝ እንደ አለ በጠቅላላው በመቃኘት ስለ ሃገሩ ይበሳጭ ነበር። ፊኒስ ግን ለሰመጠ ምናብአዊ ግዛቱ ከእንግሊዝ ተሻግሮ በመጽሐፉ ሊአዋየው ጓዱ ሆነለት። አገነዛዘቡ ሰፍቶ ሂስ ሁሉ በዘርፉ ተመራማሪዎች እንዲሰነዝር አበቃው። ይህ ልጅነት በእርግጥ ለ አነሱ ፈላስፋዎች ሌላ አናሽ መገለጫዎች ታይቶአቸው እሚዘለል ነጥብ ም ነው። ደቂቅ-ስነልቦና (ቻይልድ ሳይኮሎጂ) እነ እዚህን ንዑስ-እሳቤዎች ለመገፍተር በቂ የጥናት እና አስተምህሮት ብቃት ቢኖረውም እንደ አለመታደል ግን አፈንጋጭነቱ በመሀልአችን አለ። ለምሳሌ፣ በእዉቀቱ ስዩም፣ የጭራቅ ተረት ግጥሙን ነግሮ ‘አዉዉ መጣ' ምናምን ነገር በማለት ልጅዎች እሚአሳዩት አንድ ያለመንቃት ተፅዕኖን ሀበሻ መታገሉ እንደ ተገቢነት የተለመደ ነገር አድርጎ ማጥናቱን ይናገር አለ። ግን ይህ ንዑስ-ስነልቦናትንታኔ (ሰብስታንዳርድ ሳይኮአናሊሲስ) እንጂ ከቶ ምርጥ አገነዛዘብ አይደለም። ማለትም፤ ስህተት ነው። በናሆም ታታሪ፣ ጥበበምርምርአዊ (ሳይንቲፊክ) ገሃድ አሳሽ፣ አዉጠንጣኝ ምናብ እንደ ተደረሰበት ከሆነ ምርጡ መንገድ የህፃን አንጎልን ለማንቃት ተግባር ትምህርት እንዲሆን ማድረግ ብቻ ነው። አድጎም ልጅ ምግባርአዊ (ቢሄቭድ) እንዲሆን ተግባር የዓለሙ መገናኛ መንገድ እንደ ሆነ በትግበራ እንዲማር ተደርጎ ማደግ አለበት። የልጅ አመክዮ አቅም መገንባት እና ዓለምን መረዳት ከተተግባሪ ነገርዎች መሀል አመክዮ ወይም ፍች የመፈለግ ተሰጥዖው ነው እና። ይህ የሃገር ምርጡ ማዕድን ዕንቁ ነው ብሎ ናሆም ወዲአው አመነ። ይህን ያሰመጠ አረዳድ የከወነበት ሃገር ካለ፣ የመጪጊዜ ዕድሉን መቆጣጠር ይችል አለ። ይህ የገባው ልጁን በፈለገው መንገድ ይቀርጽበት ስላለ። አዳጊው ትዉልድ ለምሳሌ አንድ ተግባር በነፃ እንደ እማይገኝ፣ በአንድ መንገድ ስብእናው እንዲሟሽ ገና በጊዜ ማድረግ ይችል አለ። ለልጅ ቶሎ በጨቅላነት በትግበራ ዉስጥ ፍቺ ማስተማ በመቻሉ። 'እንዴት? በዋነኛነት ጨቅላ-ስነልቦናኛዎች (ቻይልድ ሳይኮሎጂስትስ) የአብራሩት አለ፤' ለናሆም በመሰረትአዊነት ግን፣ በግል የግል ዓለምን መቆጣጠር እንደ አለብአቸው በተግባር መርቶ ማሳወቁ እነ እርሱን ቶሎ ማንቂአው መንገድ ነው። ለምሳሌ መጫወቻ እራሱ መርምሮ በመገጣጠም እና በመሰካካት እየተገነባ እሚአጫውት አድርጎ፣ አመክዮአዊነትን ወደ ልጅ ያመጣ አለ። በዘመኑ ይህን ሃሳብ አገልጋይ መጫወቻዎች ማጫወቱን ብዙዎች ቢአዘወትሩትም ፍቺው ግን መጫወቻ ብቻ እንደ ሆነ ስለ እሚአቁ ጨቅላው ካደገ የምስጢሩ ነገር ይረሳ አለ። ግን ማፍረስ መገንባቱ የ ፊኒስ ሃሳብ ፍች – የኃላፊነት ጽንሰሐሳብን ከተተግባሪ አመክዮ ዉስጥ በጨዋታ መሀል ለልጅ አንጎል ማስነፍነፍ፣ የግል ጥረትን ምንመሆንን እንደ ሃሳብ ወደ አንጎል ከትግበራው ማስመጠጥ፣ ብቻ ዓለምን ማስተማር እና ወደ ዐዋቂነት ቶሎ ማብቂያ ጎዳና – ነው። ነገርግን ያባትአዊነት ፍቅር መግለጫ የሆነው እና ሲአለቅሱ ለእናትነት ደግሞ ማታለያ ብለን እምንረዳው መጫወቻ ስለ ሆነ የበለፀገ አንጎል ከመገንባት ይከለክለን አለ። ምክንያቱም ሳይታወቅም ቢሆን ከትግበራ አመክዮን በጥቂቱ ባቅሙ የመሰረተው የአንጎል፣ ልጁ መዳኽ ከአቆመ ይወገድ አለ። አይተካም። ለምሳሌ ገና ጥቂት ከፍ ሲሉ ግን፣ አዲስ መላ በእዚህ ነቢብ እንደምታ መሰረት ግን ነበር። ህፃኑ አንድ አትክልት ተንከባክቦ ማሳደግ እና እራሱ ኮትኩቶ፣ አርሞ፣ አዘጋጅቶ ዐዋቂ እንዲመግብ እና አብሮ እንዲመገብ ማድረግ፣ ወይም በፍቅር ሌላ መጫወቻ ለ ምሳሌ አንድ ጫጩት አሳድጎ በግሉ ለወግ ፍሬ ማብቃት፣ ወይም መሰል አንድ መጫወቻ እሚቀርብለት ሲሆን እግረመንገዱን ም ታዳጊው አመክዮን ከተግባር እንደ ንብ ቀስሞ ስብእናው ከ ምናብቴ (ፋንታሲ) ወደ ተግባር ይተሳሰር አለ። እራሱን መገንዘቢአ መንገዱ ከተጨባጭ እና ሰርቶ ፍሬ መልቀም ይተሳሰር አለ ነው። ሲአድግ ዓለም ከእዛ አገነዛዘብ አትሸሽበትም። ተግባር እና ዉጤቱ፤ መነሾ እና አመክዮው ከመድረሻው፤ እሚሰነታትር አንጎል በተፈጥሮው ይካን አለ። ስኬትን ማግኘት ችግር ከመጠንቆል እና ማውጣት፣ መፍትሔውን ከማብላላት እና መተግበር ቀልሎ ይታየው አለ። የስኬትአማ ሃገር ትዉልድ ገና ከመዋእለቀን (ዴይኬር) ጀምሮ ይህን በስፋት እሚማር የሆነበት ነው፨<br>የናሆም ምናብ ይህን በስፋት አብሰልስሎ አብላሎት (ኢንተርናላይዜሽን) ከዉኖበት ከትዉልድ አረዳድ አንጎልአዊነቱ (ሜንታሊቲ) ያዋሃደው ነበር። በሃሳቡ መሰደር እና መብላላት ተደስቶ የግንዛቤ ግዛቱን ቀጥሮት ወደ ታናናሽዎቹ ማበልፀግ አተኮረ። ፈጥኖ ኃላፊነት መቀበል ችለው በጥገኛነት እማያስቸግሩ እንደ እሚሆኑ ስላመነ፤ ማንም ዘላለም ለእማያቅፈው አዲስ ተወላጅ ዘረሰው ሰው ይህ ቶሎ እንዲውል ወሰነ። ‘የ ስብእና ነፃነት ጎህ መቅደድ ማለት ነው፤' ልእለንቅኣት ያለው ልጅ ማፍሪአው መንገድ ነው። አድጎ ይህን ለመከወን ከእሚጥር እና ቀውስ ሊገጥመው ከእሚችል ልጅ የተሻለ ስኬት አምጪ ልጅ ማቁላያው መንገድ ነው። ጅቡ እና ጭራቁ ሳይኖሩ በ አሙ መጣ እና አዉዉ ማታለሉ ህፃኑን አድጎ ፈሪ ግን ፈርቶም ትርጉም እማያገኝ ያደርገው አለ። ግለ-አርነት (ሰልፍ-ፊሪደም) በጠለቀ ስነልቦና ስላልሰረፀ ዘገይቶ መታሰስ አለበት። ለእራሱ ግለአርነት በሂወት ማለዳ ከተግባርአዊ እንቅስቃሴ አመክዮ መኖር በግል ተንቀሳቅሶ ያጤነ ግን እንዲይዝ የተደረገው ግልአዊ አቅሙን ነው፤ ሊአውም በጊዜ ስለ ሆነ ሥር በቀላሉ በእሚሰድድ መልኩ። ሲአድግ እንደ ፈርቶ አደገው ያሳዳጊ መሃይምነት ጎርፍ አስተዳደጉን ያጨቀየበት ሳይሆን፣ ጭራሽ ግን በአለ አስፈሪ ስብእና ይሆን አለ፨<br>ናሆም ይህን በሰፊ ማብላላት አዉጠንጥኖበት የአምን ነበር። በደግ መጠን እሚም። በደግ ስፋት መስም። የ ጆን ፊኒስ የተፈጥሮ ህግ ፍልስፍና ፍቺ በመደበኛ አኗኗር በእነ እሚ ቤተሰብ ተደርሶበት “የ ወደፊት ተስፋም-መንገድም” ነበር። ገሃድ መቼም እና የትም ገሃድ ነበር እና። ገሃድ በፈላስፋ እና ዓይንዎች ባልጨፈነ መደዴ እኩል በገሃዱ ሃዲድ እሚአሳፍር ነበር እና፤ ከስምጠት ልዩነት በቀረ። የእሚ ቀላል አኗኗር፣ በመስ እና ናሆም ምክርዎች የተብላላ ሆኖ ለልጆቿ መስዋእት ስለነበረች ምርጡ የተባለ ልጅ ማሳደግ መንገድ የእርሷ መንገድ ነበር፤ ብዙ ገንዘብ እስከ አልጠየቀ ድረስ። ስነልቦና ደግሞ ወጪው ዜሮ ጋር ይዋደድ ስለ ነበር አልከበዳትም፨<br>ባቤ በስእልዎች እነ ቢግ እና ጢዩ በአትክልትዎች እና ታሪክ አያያዝዎች ኃላፊነት መዉሰድን እና የመመርመር ጥበብን በስዉር ይማሩ እና ሰው መሆንን በእራስአቸው ይገነቡ ነበር – በእዚህ ዓመት። የቢግ መሰል አመትአዊ ተግባሬት (ፕሮጀክት) የእሚ ዘመን የልጅ ተረቶች መልቀም እና መፃፍ ሆኖ ወደ ሰባአንድ ተረትዎች ደርሶለት ነበር። የእሚ ልብ ዓመቱን ሙሉ አጫዋች አጊንቶ ባለመታከት ተረት በማስታወስ እና አንድአንድ ም በመፍጠር ተጠምዶ ነበር። ጎረቤት በሌለበት አዋዋዮቿ ልጆቿ ስለ ነበሩ እማይታክት ጓደኛምነት እናትነትን አነባብሮ ነበራት። ቢግ ጥራዝ-ተረትዎቹን ያበጀው ያምና ሊቅአዊ-ዓመት (አካደሚክ ዪር) ማብቂአ ደብተርዎች ያተረፉት ወረቀቶቻቸውን ገንጥሎ እንዲአዋጡ አድርጎ በህብረወረቀትዎች በሰፋው መጽሔቱ ተይቦ ነው። ብጁ-መጽሔቱ ባለኮሌታ ሽፋን እና መዘጊአ እንዲሆን ጠንካራ ካርድ ተጀቦደበት። በመዘጋት በስነቁልፍ ቀመሩ ተቆልፎ ወደ ጓዳው የላይ-ግድግዳ ተንጠልጣይ ግል ሻንጣው ለወደፊት አገልግሎት ተኝቶ ነበር። በናሆም በቀላል ቅጽበትዎች ከማዳበሪአዎች የተዘጋጀው ሻንጣ በመቆለፍ እና በመንጠልጠል ለታዳጊዎቹ ብርቅ አገልግሎት ይቸር ነበር። ከእዚህ ተግባሬት መጠናቀቅ ኋላ ሲመለስ፣ ሰሞኑን ቢግ በእንግሊዝኛው እንዲያተኩር ተደርጎ ነበር፨<br>ከ እንግሊዝኛው ጎን ደግሞ፣ የህፃናት ሰብልዎች ጥናት ከጢዩ ጋር ይተገብር ነበር። ናሆም የታዘዘውን የቢግ አዲስ የጥራጥሬዎች በተቀራረበ ዘርግንድ መሰደር እና አጎነቋቆል መንገድዎች እና እሚፈጁት ጊዜ ዳግምርምር ሥራውን ጎበኘለት። ደግ መማር ቢግ ከተግባሬቱ እንደ አገኘ ተረዳ። ስለ እቅጭ የሰብል ባህሪዎቹ በዝርዝሩ እራሱ ናሆም እንኳ አያቅም ነበር። ግን የጥናትአዊ ስነአሰራሩ በደንበኛ ተመራማሪ መንገድ ስለ ተወሳሰበ እና በቀጥተኛ ግልፅ ትርጉምአማ ቅንብር ስለ ተዘጋጀ አጠናኑ በቂ አመክዮ እንደ ገነባ አስረዳው። ስምጥ ጉዳዩን በፍላጎቱ ቢግ አድጎ ከመረጠው እስኪቀጥል ለጊዜው ይህ ቅኔ ለናሆም በቂ ሆነ። ቢሳሳት እንኳ፤ እርሱ ገና መች የግብርና ዲግሪ እንኳ አገኘ? አላማው በተግባር ዉስጥ አመክዮ መልመድ እና እራስ ማወቅን፣ አሰበጣጥሮ ቶሎ ነገርዎች በማገናኘት አብላልቶ ማስጨበጥ ነው። ቶሎ ከእናት ስነልቦናአዊ ጉያ መፈልቀቅ ነው። ለእዛ ደግሞ ይህ አንድ አረዳድ ተከትሎ የስነጥራጥሬ ዓለሙን መሰብሰቡ ትልቅ በቂ ክሂሎትአማአዊነት (ቴክኒክ) ነው። ናሆም በተመለከተው አስተያየቱን አዎንታአዊ ድርጎ ተሻገረ። ወደ ነብሳት መሰል ዳግምርምሩ መሻገሪአ አረንጓዴ መብራት ተሰጠው፨<br>'ሃዘንቴ (ሳዲስት) መሆን የለም። በሰው መቅናት እና መመቃኘት ስሜት ማሳደግ የለም። መተባበር እና ሰው መሆን ይለመድ አለ። በግል ኃላፊነት ለኑሮ መዉሰድ እንዲበዛ፣ ምራቅ ያስውጥ አለ። ይህ በለጋ እድሜ በዚህ ብልሃት ተከውኖ ወደ ብርሃን ፍጥነት (ጊዜ) ብስለት ትዉልዱን ይመልሰው አለ፤' ናሆም ይህን ወደ ጠቅላላ አረዳድ ቀይሮ እሚአስበውን የሽል ዓለም ናፍቆት በታናሹ ላይ ተመልክቶ ወረቀቱን መለሰለት። ቢግ ከበርጩማ ወንበርዎቹ መሀል ያለ መጠነኛ ጠረጴዛው ላይ ያሉ ሌላ ወረቀትዎቹን ጨምሮ ወደ ጓዳው በመደሰት አዘገመ፨<br>እሚ ሞላጎደል በሰብል ምርትዎች መርከስ እማትታማዋ ፋሲካይት ዉስጥ እንዳትቸገር እሚደጉማትን ዕድአዊ ሥራ፤ ሰሞኑን በያዘችው የልቃቂት ማበጀት ትንቅንቅ ትላንት ስላጠናቀቀች፣ እና በደሞዝ ልትለዉጠው ማስረከቢአውን ቀን ብቻ ስለ እምትጠባበቅ፣ በናሆም ዉብ ንድፍ ላይ ለግል ገበያዋ አንድ አበሻ ቀሚስ መጥለፍ ስለ ተያያዘች ወደ እርሱ ተመለሰች። ጢዩ እምታጫውታት ጮለቅ ወደ ቁርስዋ ዞረች። ጢዩ በማሳቁ መሀከል የጮለቅ አፍ ሲለጠጥ፣ ወተት፣ እንቁላል፣ ገብስ፣ ጨው፣ ዘይት፣ ቅቤ፣ እና ዉኀ ምስጀት (ረሲፒ) ተዋህዶ በስሎ፣ ቀዝቀዝ ብሎ የቀረበላትን በመመገብ ተጠምዳ ቆየች። እሚአቅፋት ስለሌለ እና የጢኖ ፍቅር ከማንም ይልቅ ስለ እሚአስቦርቃት በነፃነት በማደግ ላይ ነች። እምትሰማው የጢዩ እንቆቅልሽ እሚገባት ይመስል በዐዋቂ ማእረግ እያደመጠች መብሉን መዉሰድ ቀጠለች። ናሆም ቢግ በቀጣይ ማስቸገር ዙሩ ያቀረበለት እንግሊዝኛ ጥያቄዎችን በመመለስ አግዞት ሲአበቃ የሁለትኛ ጧት ዕቅዱ ደግ ፍፃሜ ሆነ። የመጨረሻ ጧት ዕቅዱን አሰበ። ‘መስተንግዶ መስ፤' ከመብል ኋላ የተበላሸ ስፍራ ካለ ቤቱን ፈተሸ። በሳሎኑ ወደ አንድ ጥጋት አዝምሞ ያለው፣ ዉራጅ (ሰከንድሀንድ) ሆኖ በርካሽ እሚ በሽንጥ ግተራ መወገን ያስገዛችው ደገኛ እሚባለው የሁዳድ ፍልሰት ዉጤት ከሆኑ ቅርስ መሰብሰብዎች ዋና የሆነው የቤት እቃ፣ በባለሙያ የተዘጋጀ የሆነው በደግ ከፍታ እሚአጅቡት ስምንት ቀጭን ዘለግ ያሉ ወንበርቹ ጭምር እሚፎክረው መመገቢአ ጠረጴዛ ያልተበላበት ይመስል አምሮበት አለ። ሁሉም መሆን ከእሚችለው አቅመ ዉበት ላይ ነው። ዉጭውም በቀደመው ቀን መጠነኛ መስተንግዶ አግኝቶ ያንን ያንጸባርቅ አለ። የእጅ ሰዓቱን ተመለከተ፨ናሆም እና ብሩ ሁለቱ የጓዳ እና መኝታቤት መስኮቶችን ተከፍተው ወደ ቤት ማሰናዳት ገቡ። ቀሪው መስኮት ሳሎን ከበሩ እኩል ተከፍቶ እንዲሁ ሰፊ ፅዳት ሆነ። ያልነቃ ብቸኛ ው ቤተሰብ አባል የጋራ ብርድልብሱ ለብቻው ሆኖለት የቤቱ ብቸኛው በአናፂ ባለሙያ የተሰራው አልጋው ላይ ከመደበኛ እራስጌ አግጣጫ ስቶ ወደ ጎን፣ በእሚ የተላጨ አናቱን አድርሶት ተኝቶ አለ። ናሆም ትራሱን ወደ ጊዜአዊ እራስጌ አምጥቶ አስገባለት። ብሩ፣ ብቸኛ ተንቀሳቃሽ ስልክ በቤቱ ለመያዝ የታደለ፣ አስራሁለትኛ ክፍል ፈጽሞ በብሔርአዊ ፈተና ዉጤት ልዩ ጭንቀት ይዞት ከወዲሁ እሚብሰከሰክ የሆነው፣ ሞላጎደል ዝምተኛ እና ግል ዛቢያው ተስማምቶት እሚዞርበት፣ የቤቱ በኩር፣ ጸጉር በተለየ መልኩ ሉጫ ሆኖ ያደገለት እና ከሁሉ ቀላ እሚል ቆዳ እና ሽል መልክ ሁሉ ያገኘው፣ እንደ ወትሮው ከሥራው ቀድሞ ወደ ተሱ. (ተስ. = ተንቀሳቃሽ ስልክ) ገባ። ናሆም እንቅልፍክፍሉን እየቃኘ ማጽዳቱን ሲያያዝ ከጀርባው የብዙነሽ በቀለ እንደሆነ እሚታወቅ ጥንትአዊ ዘፈን ምትሃትአዊ የኦርኬስትራ መግቢኣ ቅንብሩን በጣሪአው እየአሯሯጠ መርጨት ጀመረ። “ጭንቅ ጥብብ” እስክትል እና የመሳሪያዎች ቅንብሩ ዉበት “ድርን” ብሎ “እያልኩልህ” እሚለውን ልትል እስኪ ፈቅድላት ድረስ፣ እማይመለጥ የኦርኬስትራ ስውር ልዕለ-ጉልበት የሆነ መግቢኣው የተገኘውን የቀልብ አሃዝ ሁሉ ገዛ። ናሆም ወደ ጓዳ ገብቶ በአፍጢሙ የተደፋ ከሁሉ እሚረዝም የክትዕቃ – ሽንጣም ብርጭቆ – አንስቶ ወጣ። መናኛ ቻይና ስሪት ተሱ.ን ከጥጋቱ ጠረጴዛ አነሳ። ያለው ዐውራ ድምጽማውጫ አካሉን በብርጭቆው ቀዳዳ ልክ አድርጎ ድምፁ በብርጭቆው እንዲንቆረቆር አስቀመጠው። በተሱ. መደበኛ አቀማመጥ ከሆነ ድምፁ በጠራ መልኩ መስተናገድ እሚችል አልነበረም። በብርጭቆው ጉድጓድ እየተስተናገደ ግን በበላጭ ጥራት መጉላት እና ማስተጋባት እንዲችል ታገዘ። ዉጭአዊ ተጽዕኖ (ኢፌክት) ሆኖ በብጁው (ከስተማይዝድ) የድምፅ ቅንብር አልፎ ለጆሮ በአነሰ ጉርበጣ መዉጣት ጀመረ። ያ ሲሆን የብዙነሽ ምትሃትአዊ ድምጽ ክወና ልክ መፍሠስ ጀምሮ ነበር። ‘…እ…እ…እ…’።
በመቆም ለመጥረግ እንዲአመች የእንጨት እጀታ ጨምሮለት ቁም መጥረጊአ ያደረገውን፣ ከዘንባባ ቅጠልዎች እነቢግ ያዘጋጁት መጥረጊአን ሰሞኑን ተለዉጦ ስለነበር፣ ከአረጀው የበለጠ ሊያገለግል ተነሳ። እነ ጢዩ ወደ እንግዳመቀበያ ክፍል እንዲወጡ ናሆም በመጠነኛ ዳንስ ሆኖ አዘዘ። ጮለቅ በብሩ ጥንቁቅ እቅፋት ሆና በእማይደክም የጢዩ ፊት ዥዋዥዌ እየተዝናናች ወደ ሳሎን ከግድግዳ በግማሽ እርምጃ የአክል ራቅ ብሎ በተዘረጋ ሽንጣም መከዳ እራስዋን አገኘች። “እኔን አታስታቅፉ…ኝም!?” ስለ እምታውቀው፣ ጢዩ መልስ ሳትጠብቅ እንደ ወትሮው ላመሏ ያክል ብሩን ጠየቀች። “ማሪያም አስወልዳ ታሳቅፍሽ!” ብሩ ህፃኗን አስረክቦ ተመለሰ። በአጭር የእግሮች፣ ድንክነቱ ላይ ተንጣልሎ ወደ እሚአገለግለው መከዳ ተጠግታ ከሥሩ መሬቱ ላይ ለዛ ኢላማ በምትጎዘጉዘው መጠነኛ ምንጣፍ በመንበርከክ ተመቻችታ፣ ክንድዎቿ ተጣጥፈው በመከዳው ጫፍ ተደራርበው አረፉ። የጮለቅ አለአግባብ መንቀሳቀስ እምቅአደጋ (ሪስክ) በዛ እየተገደበ፣ የጢዩ ፊቷም በአገጭ በኩል እሚቀመጥበት ልሙድ መካንጊዜ ነበር። “እ..ህ…ህ…ህ… የኔ ቆንጆ እ… ሸጋ…….ልቤ ወዶኻል …እ… እ… እንዳትረሳኝ…እ…አደራህን…..” አብራ እና ሲአመልጥም ሙጉ.ን (ሙግ. = የ ሙዚቃ ግጥም/ ሊሪክስ) በመከተል ስትልላት አሁንም አሁንም ጮለቅ የዓመት እና ሁለት ወር እድሜ ገደቧን ዘንግታ በጉልህ እሚታይ አዲስ ዓለም ዉስጥ ሰምጣ መቦረቅ ትያያዝ አለች፨
ብሩ ከናሆም መጥረጊአን ተክቶ ተቀበለ እና ወለል ወሰደ። ናሆም ልምዱ ስለ እሚአግዘው ወደ ጣሪአ ዞረ። በፊት ጣሪአው ተንፍሶ በተሰፋበት እቅጭ የቀዶጥገና ሥፍራ ቀድዶ፣ ክምቹ ቆሻሻውን በቆሻሻው ባልዲ አስተናገደ። ለቀሩት ሦስት የኮርኒስ ጡቶችም ህክምናው ዘመተ። በኋላ መልሶ እንደነበር በእሚ መርፌ ቀዳዳዎቹ ተሰፉ። አልፎአልፎ የእሚጎበኟቸው አይጥዎች አዲሱ መንደራቸው ዳግም ፈርሶ፣ ናሆም በመቀጠል አዳዲስ ልዩልዩ ቅርጽ (በተለይ የልብ) እና ቀለሞች ያሏቸው ሻካራ ላስቲኮች ነፍቶ እንዲያብረቀርቁ ሰቀለ። ብሩ ሁሉን መኝታ ካነጠፈ፣ ግድግዳዎች እንዳይቀረፉ በጥበብ ቆሻሾቻቸው በጋራ ከተለቀሙ፣ እና ወለል ከተጠረገ ኋላ ሁለገብ ጽዳት እና መጠነኛ እድሳቱ ቤቱን ደመቅ አደረገ።
ቆሻሻውን ለሁለገቡ የቆሻሻ ባልዲ አጉርሶ ወደ ጓሮ ማቃጠያው ምሥ ጉድጓድ ሊደፋ ብሩ ዞረ። ለእሚ እገዛ እራሱን ሊያክል፣ ባቤ ብሩን ከመንገዱ ተለይቶት ወደ ኩሽና አጠመዘዘ። እሚ ከጓዳ ወደ ኩሽና በመመላለስ ቁርስ ማበጀቱን አፋፋመች። ነገርግን፣ እንደ ሁሌ ደስታ እሚሰማት አልሆነም። የመስ መምጣት ምንጊዜም ደስታ እና ደስታ ብቻ ነው። ግን ዛሬ ክፍት እሚል ድባብ ገና በጠዋቱ ሰፈረባት። ጭራሽ ጭንቅ እያደረጋት ሲብስ የባቤ እግር በኩሽናው ሜዳ የነበረ የኑግ ዱቄት አነስተኛ ጣሣ ደፋባት። የባቤ ጥፋት ስላልነበረ ለመልቀሙ ብቻ ዕዝ አድርጋ ጭንቀቷን በሆንብሎንታ ላለመሸበር በእሚል በግድየለሽነት አለፈችው እና በማብሰሉ ልትጠመድ አሰበች።
“እሚ! ህልሜ ትዝ አለኝ እንደ ገና! ያየሁት እኮ ፀሐይ ብቻ አይደለም ስ!” ጢዩ ወደ ጓሮ ኩሽናው እየገባች፣ ትሁት ፊቷ ታጥቦ እንደረጠበ እጆች በደረት አድርጋ በእርጋታ ሆና ጨዋታ ጀመረች። ግን መልሱ ጩኸት ሆነ። “ልጅትዋ ስ!” ክዉ ያለች ጢዩ ግንባር ቋጥራ ክዉታውን መከተች። “ብሩ አለ!!” ድንገት ቁመቷን ሰሞኑን መዝዛ ያለችው የሴቶች በኩሯ፣ ነጭ የእሚ ክሮች ያበጁት የዳንቴል ሹራቧን በመሰል ከአጠራት እና ከቁርጭምጭሚት እማይደርስ ጥቁር ሱሪዋ አቀራረበችው እና ወደ እርጋታዋ ተመለሰች። ቀናአዊነቷን ለበስ አድርጋ “እና እሚ እይስ! አንቺ ነጠላ ስትጥይም አይቼ ነበር! ያን ልነግርሽ ነው የመጣሁት። ግን እሚ! ህልም ቆይ ምንድን ነው?” እሚ ወደ ልዩ ኢተንቀሳቃሽ ወንበሯ ተቀመጠች እና ጢዩን ዘነጋ ች። በመሰል የተተከለው ጠረጴዛ ላይ ቅርንፉድ ለመፍጨት ቂጥዋን ለአመል ያክል ስለመንጠራራት ከፍ አድርጋ ከ ናሆም-መደርደሪያ ላይ ጠርሙስ ለቀመች። ጢዩ ጠረጴዛውን ቀረብ ብላ በሆዷ ስትንጠለጠልበት እግሮቿ ምድርን ተሰናበቱ። መልሳ በማረፍ ያመለጠ ቅርንፉድ አንስታ መልስ እየጠበቀች ሆና አስፈጨችው። “ሂጅ ባክሽ ልጅቷ ጋር! ምንም የለም እዚህ! ሁሉን እኛ ነን እምንሰራው!” ባቤ ተቃውሞ እና ገሠጻውን ጀመረ። በአጉልቶ ምላስ ማሳየት ደግሞ ምራቅ ጭኖበት በማስመልከት፣ ጢዩ አብሽቃ ተከላከለች። ባቤ ቁጣውን ወደ ስድብ እያዞረ “ደረቅ፣ ፍየል ጸጉር፣…” ማለቱን ሲቀጥል እሚ ሁለቱንም ስትቆጣ፣ ጢዩ በስውር ተፍታበት ተመለሰች። ባቤ ለመምታት እንደእሚፈልግ የምራቁን ኤክዚቢት አስመለክቶ አሳሰበ። እሚ ግን ‘ታላቅ ይታገሳል’ እሚል የተለመደ ምክሯን ሰጠች፨
ከዋናው ቤት በስተ ቀኝ ከጓሮ እሚገኘው ኩሽና ከዉጭ እና ዉስጥ እንዲቆለፍ አድርገው በጸዳ እና ብልኅ ድባብ እነ መስ እንደአዲስ ያበጁት ሁለት አመቶች ቀድሞ ነበር። ከአፈርአማው ወለል ግድግዳዎቹ ተመዝዘው፣ በእሚ ራስቅል አካባቢ ድረስ ባለአካልአቸው ጭቃ ምርጊት ያስተናገዱት ናቸው። ሦስት-በ-ሦስት ሜትሮች ዙሪአውን ገድበው ተገጣጥመውለት፣ የኩሽና ስፋቱን አበጅተው አሉ። ከሜትር እና ኩርማን አካባቢ ልስን በላይ ያለው የግድግዳ ቅርጽ ግን፣ አልፎአልፎ የቆሙ ምሰሶዎች እስከ ጣራው ደርሰው ጣሪአ ሲሸከሙ ይታያል። ሳይለሰን እና እንጨቶች ሳይገጠገጠበት የሳጣራ አካል ብቻ ሸፈነው። ሁለት ጎንዎች ግን ንፋስ እና ዉሽንፍር ስለ በክረምት እሚአጠቃአቸው ስለሆነ ደረቅ ላስቲኮች ጨምረው አሉ። ባሉት ላስቲክየለሽ የጣራስር ሁለቱ ግድግዳዎች ደግሞ፣ ቤቱ በብርሃን እና ጭስ የማመላለስ ትጉህ-አገልግሎት ይሰጥ አለ። የእነመስ ንድፍ የሆነው ኩሽና ተጨማሪ የይዘቶች ዝግጅትም አሉት። ካንዱ የግድግዳ ሆድእቃ፣ እንደ ልዕለ-ጉጥ ወደ መሀከል ቤቱ አስግጎ እሚሰነዘር አካል አለ። እርብራብ ተበጅቶ በላዩ የታነፀ መደርደሪአ አለ። ከግድግዳው ወደ ጣሪአ ሳይሆን ወደ ቤቱ መሀከል እሚፈልቅ እንጨት የወለሉ መሳለመሳ (ፓራለል) ሆኖ ትልቅ ጣውላ ተነጥፎበት ሲዘጋጅ፣ መስ በናሆም ሃሳብ አመንጪነት ስላነፀው፣ በኋላ በስሙ ተሰየመለት፤ የናሆም-መደርደሪአ። ብዙ ወጥቤት ቁሳቁስዎች እሚሸከም ሲሆን እሚን ያስደነቀ አሽከርነት እሚሰጥ በመሆን ሁሌም ትደመምበትአለች። በተቃራኒው አግጣጫ ያለው ግድግዳም በመሰል የእነ መስ እና ናሆም ምርምር ያደገ ክወና ያቆመው ዉስጤታአዊ (ኢንቴሪየር) ክፍለ ኩሽና አለው። በእሚ ወገብ ከፍታ የቆመ የማንደጃዎች አገልግሎት ማእከል ያቀርብ አለ። እንደዛው ግድግዳው የእሚሸናው እሚመስለው ይህ አካል፣ አንድ ጎኑ ላይ እንጀራ ምጣድ ተንጠልጥሎበት አለ። ጎኑ በብልሃት ከምጣድ በጥገኛነት እሳት እሚገለገል መጠነኛ የማብሰያ ክፍተት የአለበት ቅርጽ አሳድገው አብሳይ ሆኖ አለ። ከተንጠለጠለ ምጣድ እና ማብሰያው ሥር በነበረው ክፍተት፣ ጥቂት ከማንአንሼአዊ ከፍታ ላይ ወለል ቅርጽ ተበጅቶ እንጨት እየተኛበት ለነዲድ እሚታዘዝበት ቅርጽ አለ። ያ ሆድዕቃ ክፍል በበር መዘጋት እና መከፈት ቻይ ሆኖ እሳት በተቀነሰ ኦክስጅን ቅጥልጥል (ኮምበስሽን) ማገዶ ይቆጥብ ነበር። ንፋስ አጠናግሮት ስለ አጋጋለው በከንቱ እማይበዛው እሳት በተከበበ ክፈፉ ሙቀት አምቆ ጭምርም ቶሎ ያበስል አለ። አመድ በአቆረ ጊዜ ደግሞ ተከፍቶ ወደ ዉጭ እንዲአፈስስ፣ ፊት ቅርፁ ዝቅ ብሎ ዘመም እንዲል እሚአስችል ስነእንቅስቃሴ (መካኒክስ) እንደ ቁልፍ ተገጥሞለት አለ። አመዱ ያለንክኪ እየተናደ ከስር በእሚነጠፍ አጭር ላስቲክ በመናድ ወደ ሰፊ ባልዲ ይንሸራተት አለ። ባልዲ ው እንደ አሻ መንቀሳቀስ እሚችል ነው። ይህ ግድግዳ የደገፈው ማብሰያ ሰፊ ቅርጽ ሙሉ ግድግዳውን አልሰረቀም። ከጥጋት ወደ ተወሰነ ቦታ አብቂ ነው። በቀረው ክፍተት ደግሞ፣ እነ መስ ያበጁ፣ ጫፍአቸው በወለል ሆድ በተተከሉ ማገርዎች ላይ ቋሚ እግር አጊንቶ በመነጠፍ የተመታ ጣውላ፣ አሁን ቅርንፉድ እያስፈጨ፣ ጠረጴዛ ሆኖ ያገለግል አለ። በመሰል እግሮቹ በወለል የተጎረሱ እና ከጠረጴዛው ተገቢ መመጣጠን መስተጋብር ያለው አንድ ወንበርም አለ። እሚ ወይም አብሳይ በእርሱ ተቀምጦ መክተፍ ወይ እሚበስልን መጠበቅ ይችል አለ። እሚ ተቀምጣ በመንጠራራት ብቻ ደግሞ ንዑስ መደርደሪአ ከጀርባዋ እንዳለው ዐብዩ ናሆም-መደርደሪአ ስለተበጀ ዘወትርአዊ እና ቀላል ቁሳቁስዎችን መድረስ ትችል አለች። ብዙ ጊዜ እንዳነሳችው መፍጫ ጠርሙስ፣ ዘይትዎች፣ ቅቤ፣ ቅመማቅመምዎች፣ ትንንሽ መክተፊአ፣ ቢላዋዎች፣ ማንኪያ፣ ጭልፋ፣ ትንንሽ ድስትዎች፣ ማማሰያዎች፣ ወዘተ. በእዛ አነስተኛ መደርደሪአ፣ በጋራ ታጅበው ለሎሌነት ቅጥር በመስከን ይጠባበቁ አሉ። በሌላ ግድግዳ ደግሞ ብዙ ሚስማሮች ልዩልዩ ተንጠልጣይ ቁሳቁሶችን አቅፈው አሉ። ጣባዎች፣ ቤተሰቡ እሚወድዳቸው የሆነው እና በተለይ በገጠሩ በመርከሳቸው በስፋት የተገዙት ብዙ አይነት ሌላ የሸክላ ድስትዎች እና ቁሳቁሶች፣ ጦቅየ፣ ወዘተ. አሉ። በእርግጥ የዘመንአዊ መኖሪያ ቤት ኩሽና አይሁን እንጂ ሃሳብ እና አያያዘጀ ግን የድንቅ ልባሞች ቤተማዕድ ነበር። ሁሌም ጽዱ እና አቀማመጡ ትክክል ያለ ሲሆን በአያያዙ ወጥ እና ተገማች ከመሆኑ የተነሳ ጮለቅ ብቻ እንጂ ሁሉም ለምደውት ነበር፨
የእሚ ቁርስ ቤተሰቡ ተስማምቶ በመርከሱ ከገዛው ከቀይ ጤፍ፣ በአማራጭነት ከተረፈው ብር ደግሞ ከተገዛው በቆሎ፣ ጥቂት ማሽላ፣ መዓዛ ቀያሪ እሚአክል በስሱ ታምሶ ከገባበት አብሽ፣ የደረቀ ጥቂት መጥበሻ ቅጠል እና በሶብላ፣ ቦለቄ እና ገብስ ድብልቅዎች የተበጀ አልሚ-ዱቄት እሚዘጋጀው ልማደኛው ግን ያልተለመደ ቢሆንም ደግ ጣዕም ያለው አካል ገንቢ ገንፎ ነበር። ከጎኑ፣ አሁንም እሚ ከገሬዎች እምትገዛው እርካሹ ማር እያገለገለ የማር ሻይ ተጥዶ ደረሰ። በመጠበቅ ሆና ለሌላ ወቅት ያዘጋጀችው ቅርንፉድ ሲደቅቅ ወደ ብልቃጥ ታጉሮ ለእምቅ (ፖቴንሻል) አገልግሎት ተበጀ። ባቤ በመላላክ መመገቢያዎችን ከያሉበት መደርደሪያዎች እየተዋሰ በመኖሪአ ክፍሉ ዋና ጠረጴዛ ተራበተራ አስተካክሎ አሽከርነትአቸውን ለእምቅ አገልግሎት አሰናዳ። መብሉ ተጠናቅቆ ሲበቃው፣ ባቤ ዜናውን ዐዋጅ በማጮኽ አበሰረ። እነ ናሆም፣ ጽዳቱን ሁሉ ፈጽመው ስለነበር በቅጥሩ እየተጨዋወቱ፣ በመተጣጠቡ ተረዳድተው ወደ ሳሎኑ ተሰበሰቡ። እንደ ቤተሰቡ ኢዘማሚ ጠረጴዛ ባህል ሆኖ፣ ማንም ከጎደለ መመገብ እሚጀመር አይደለም። እሚ ገንፎውን በሰፊ ጣባ መሰል ሸክላ ትሪው ልትገለብጥ እና ወደ ማባያ ስራው ለመዞር የኩሽና እረዳቱ ባቤን ማረጋገጫ ጠየቀች።
ባቤ ትሪውን በማንጠፉ አዎንታአዊ መልስ አስተላልፎ፣ ወደ ቀጣይ ተግባሩ ዞረ። ከሁሉ እንቅልፍአም ታናሹን ሊቀሰቅስ ወደ መኝታ ክፍል ዘመተ። እነ ናሆም ረዘም ከአሉት ወንበርዎች የተለመደ መቆያ ወንበርዎች ይዘው የመጨረሻ መሰናዶው እስኪፈፀም በመጠባበቅ ደምብ፣ ወደ ሙዚቃ ምቾት ተዛወሩ። አሁን ድምጹ ቀነስ ተደርጎ ከማሟያው (አክሰሰሪ) ሽንጣም ብርጭቆ ጋር ስልኩ ወደ ሳሎኑ ጠረጴዛ ወጣ። የሀመልማል አባተ “ይዳኘኝ የአየ” ወዲአው ተከፈተ። በሙዚቃ ምርጫ ሁለቱም ስለ እሚግባቡ ብዙ ጠብ የለም። ብሉይ (ክላሲካል) እንጂ በተስ. አገልግሎት ሱቆች ስለተሸጠ ብቻ ወደ ተሱ. ተገልብጦ እሚደመጥ ዘፈን የለም። መዘፈን ስለተቻለ እንዲሁ የተመረተ ምርትም በትዉስታ ማኅደርሩ ታቁሮ አይደመጥበትም። ታናናሽ ታዳጊዎቹም በድንቅ ዘፈንዎች ታጅቦ የማደግ እድል ከእዚህ የተነሳ ገጥሞአቸው አለ። ገና በጨቅላነት በቤቱ ሁለት ታላላቆች የእሚመራረጡ ምርጥ ብሉይ ዘፈንዎች ብቻ ይሰሙ ነበር። ከሞላጎደል። እነ ጥንትአዊ አስቴር አወቀ፣ እነ ብዙነሽ፣ ሂሩት፣ ኤልያስ ተባበል፣ ጥንትአዊ ጥላሁን ገሰሠ፣ ምንይልክ ወስንአቸው፣ ወዘተ. እሚኮመኩሙ ሆኑ። ከብዙ መስፈርቶች አብሮ የድምጽ ትግበራ ጥበብ የረቀቀበት ዘመንን ሲኮመኩሙ አሁንም ተዘውታሪ ብሉይ ኪኖችንም አይከታተሉም፤ አቅም በፈቀደ። ጥቂት እንደ አደመጡ እሚ ባቤ በሰተረው ሰፊ ትሪ ላይ በጨርቅ ታግዛ ያመጣችውን ጠይም ገንፎ ከሸክላው ድስት አፈሰሰች። ተመልሳ ስትወጣ ባቤ የሻይ ብርጭቆዎች እና የቤቱ አይነተኛ ዉሃ መጠጫ መርቲ ጣሣዎችም አደለ እና ተከተላት። ጥቂቱ ብርጭቆ አካል፣ በክብረበዓል እንጂ አዘቦት ዉስጥ ለማገልገል አይቀጠርም። ከሙዚቃው ጋር ትኩሱ እንፋሎት እና ሽታው ሁለቱን አድማጭዎች አወደአቸው። ብሩ በሌባ ጣቱ ጠንቆል አድርጎ ሰረቀ። “ተው!” ናሆም ተቃወመ። ምላሱ ላይ ጠረገው። ‘ኤክ’ የባቤ ከጧቱ ባያሌው ረግበው የቀነሱ ኮቴ ድምድምዎች አብዛኞቹ በታዳጊዎቹ በቀለጡ ላስቲኮች እና እርጥብ እንጨቶች መቅረጽ የተፈበረኩ ሹካ እና ማንኪያዎች ይዘው ደረሱ። በእየስፍራው ገንፎውን ጠነቋቁሎ ሰካሰካ አደርገአቸው እና ወንድምዎቹን ተገላምጦ ተመልሶ ወጣ። “እሺ እሱባለውን እከፍትአለሁ!” ብሩ ጣቱን መልሶ ለመጠንቆል ካበጀ በኋላ ፍቃድ እየጠበቀ ተደራደረ። ናሆም “ዘፈን ማሞቂአ አይደለም” እሚሰኝ የሃገር መዉደድ እንደ ሆነ በታሳቢነት የተዘለለ የየሺ ሙዚቃ በገሃድ አምርሮ ስለተቸ የ አኪለስ ቁርጭምጭሚቱ ሆኖ የሰሞኑ መጠቂአው ነው። ‘አስቀያሚ የሹፈት ሙግ.’ “አትከፍትም” በመቀየም ስሜት ናሆም ተናገረ። “እንዲያ ከሆነ!…እ?” ወፈር አድርጎ በሌባጣቱ ጠይም ገንፎ ቧጠጠ። ምላሱን ጎልጉሎ በማንጠፍ በላዩ አንሸራተተው። እሚ የቅቤ፣ እና ምጥሚጣ፣ እቃዎች ይዛ መጥታ ገንፎው አቅራቢያ ንዑስ-መካን ላይ አስቀመጠች። ባቤ ቂጥቂጥ መከተሉን ዘወትርአዊ አመክዮ አስችሮት የበርበሬ ብልቃጥ አምጥቶ እንዲሁ አስቀመጠ። እሚ በአንድ ገበታ ሁሉን አሟልቶ አንዴ የማቅረብ ባህል ወሳኝ፣ ከኩሽና ዉጭ ደግሞ መብል ማብሰል ከቶ ወንጀል፣ ብላ በእምታምነው መርኋ መሰረት፣ ወደ ኩሽና ተመልሳ ሻይ ማምጣት ዞረች። በእናትነት እና ኑሮ ቀለሟም አማካይነት የኩሽና እና ጠረጴዛ ፍልስፍዋ ከህይወት መርሆቿ አንዱ የሆነ ነው። ባቤ ወንድሞቹን አሁንም ገልመጥ አድርጎ ተመለከተ እና አብሯት ተከትሎ ዉሃ ለማምጣት ባቤ ሄደ። እራሱን ለመቻል እና ወደ ጉርምስና ከቶ ለመግባት እሚጥረው ባቤ ማፍጠጡ የመናቅ መሆኑ ተፈጥሯዊ ስለሆነ ማናቸውም ምንም አላሉም። ‘አለማፍጠጥ ግን የስልጣኔዎች ሁሉ መጨረሻ ነው፤ ለእዛ ሲባል የስልጣኔ መጀመሪያም ሆነ። ወደፊት ስለ እዛ እነግራችሁ አለሁ፤’
ብሩ አሁንም ጥቃት አመቻቸ። በሹፈት ፈገግታ ታጅቦ፣ ናሆምን በግንባሩ ተመለከተው። “አቦ አቁም አታበሳጨኝ!” “ዘፈን ማሞቂያ አይደለም እወድሽ አለሁ እኮ ማለቴ ወድጄሽ ነው ያሟሟቅኩት…” እየአለ ወደ ስልኩ ሌባጣቱን በአማራጭነት ሰደደ። ናሆም በእየሻይቤቱ ያንን ዘፈን አንድ ሰሞን ሲሰማ “እንዲህ ያለ ሙግ. ላይ ታረፈ በቃ! ጭንቀታም ሙገኛ (ሊሪሲስት) … በአረንጓዴ ሀገር ስንራ፣ በኢፍትሕአዊነት ትዉልድ ሲበደል፣ የዘመነ ዓለም ዕዉቀትአዊ አመራር በምድሩ ሲሰለብ፣ እና የሃገርዎች ጭራ ሲኮን፣ ነፍስ አስጸያፊው የአፈር ማሞገሱ ዘፈንአችን አነሠ? … ጭራሽ የሃገር ዘፈን ለመዝፈን ያክል ብቻ እንደ እሚዘፈን እና ዘፈን መሳለቂያ እንደ ሆነ ታመነ?!” ብሎ ነበር። የናሆም አረዳድ ሙገኛው ሲገጥም ማንጎራጎሩን ስለሃገር የግድ እንዲሆን ለማስቻል ሲል ብቻ ሲጠበብ ሲጠበብ፣ ሳቢ መነሻ-ሃሳብ ስለአጣ ይህ ስነልቦናውን ገልብጦ በመሳደብ የጀመረበት ነው እሚል ነበር። “…’ማሞቂያ አይደለም’ ነው ያለው ግን! ጓዴ?” ብሩ አአልፎአልፎ ለክርክርቴ (አርጊመንት) ፍቅሩ በናሆም ሃሳብ ባይስማማም ቢስማማም በመቃረን እሚለውን ለመስማት ይዘጋጅ ስለ ነበር ሻይቤቱ ዉስጥ ሲጠጡ ተከራክሮት ነበር። ናሆም ከሻይቤቱ መስኮተድምጽ (ራዲዮን) እሚወጣውን ‘ዘፈን?’ አንገፍጋፊ አድርጎ እንዲጠላው ጭራሽ አባሰበት። “ለምን እንደ እዛ ገጠመ? ዘፈን ማሞቅ ስለፈለገ እና ግን ያን ማድረጉን ስለፈራ ግን አማራጭ ስለአጣ፣ ስለ ሁሉ የዘፈን ጭብጥዎች እና ዘውጎች (ጀነርስ)፣ አቀንቅኖ ስለሃገር መተው ስለ ገበያው እሚጠላ ብሎ ገመተ፣ ‘ዘፈን ማሞቂአ ነው’ በሚል በስውር ሲናገር ያመለጠው ዳራ (ትራክ) ነው፤” ናሆም በወቅቱ ያንጎራጉሩ ከነበሩት እነ አቡሽ ዘለቀ ይሻላሉ ይል ነበር። አንደ ልዕለ-ታሪክኛው፣ ዝሜ-ዘርፈህብርአዊነት (ፕሮ-መልቲቲዉድ-ነስ) ታጋይ መሪ ቴዲ አፍሮ፣ ስብእናአዊ አመራሩን በሙግ. ተከትለው ማህበረሰብአዊ ችግሮችን ማቀንቀን አሳይተው ከነበሩት ጥቂቶች ናቸው። ሙሰኛዎች በዙ፤ እኛን ምንነካን በማለት በግልጽ አቀነቀኑ! ለዚህ እርምጃ ናሆም የድጋፍ ልቡ ቀለጠ። ሲጀምር ሀገሩ ችግር እንዳለበት እንጂ፣ ምን እንደሆነ ግን አብጠርጥሮ እማያውቀን ችግር ህዝቡ እንዲያስበው፣ ሃቀኛ ዘፋኝ ካለ ያን ይዘፍናል። ከአፈሩ ለምነት ይልቅ ስለአፈሩ ጥበበምርምር (ሳይንስ) ያቀነቅን ነበር ብሎ ይሟገት ነበር።
ብሩ የናሆም ቁንጽል ክርክርቴ፣ አብጋኝ ኢአመክዮአዊነት ከማጤን የተነሳ እንደሆነ ገመተ። ኢአመክዮአዊነት የቀሰቀሠው ንዴት፣ ናሆምን ሲያበግን ከተመለከተ ግን፣ ነጥቡን እያስተዋለ ወደ ማፌዝ ይገባ እና የስሜት ነገሩን ለማብረድ ይጥር አለ። ሁሌም ብሩ ይህን አድርጎ እንደታላቅነቱ አቀዝቃዥ ተሳታፊነትን ይወጣ ነበር። “ልማትአዊ ዘፈን ትወድድአለህ ማለት ነዋ!” በማለት አሾፈበት። “መልማት ስለ እማልጠላ!” ብሎ መለሰለት። ‘ገና መልማት ጫፉ ሳይነካን ልማትአዊነትን አዛብተን ተገንዝበን የት ይሆን የታዳጊዎች ተስፋ!’ ስለዛ ብቻ ብቻ ግን አይደለም የወቅቱን ሙዚቃ ዓለም ሞላጎደል የእሚአጥላላው። ‘በ ግልዮሽአዊ (ኢንዲቪጁዋል) ድምፅ-ቀለም እሚዋብ ዘፋኝ ከገበያው ጠፍቶ አለ፤ ጥንትአማነት (ኦሪጂናሊቲ)፣ በተለየ በሃሳብዎች፣ ከቶ የለም ማለት ተቻይ ነው፤ በስልትም ያው ነው… ቀላሉ ሥራ ድምጽ ዉህደት እንኳ መሳሪአዎች በአሃዝአዊነት (ዲጂታላይዜሽን) ቢመነደጉም ኋሊትአዊ ለውጥ አድርጎ ለጆሮ እረባሽ ሆኖ አለጥራት በእየጢሻው እሚዋሃድ ነው፤ ለገበያ ሲባል ችግርን ማጋለጥ እና መሟገት ቀርቶ፣ ህዝብ ማታለል እንደ ባህል ሰርጾ አለ፤ ዜማ ሹፈት ሆኖ ግን ሹፈትነቱ በምትዎች ጫጫታ ተደብቆ ተዘንግቶ አለ። በወርቅአማ እሚሰኝ ዘፈን ወቅትአችን በነበሩት ሃቀኛ ሙዚቃዎች፣ ምትክ የጃምቦ ማወራረጃ ጩኸትዎች ብቻ ነው ያሉት እንጂ እማይጮኽ ደግሞ ከቶ አይደመጥም…፤’
ብሩ ናሆምን ጨምሮ ለማበሳጨት ሳይችል ወዲአው ሁሉ ተሰናድቶ አበላሉ በይፋ ሊታወጅ ደረሰ። ገንፎው ዙሪአ በሁለት አነስትኛ ጣባዎች በአንዱ ለብ የተደረገ ቅቤ ከምጥሚጣ ጋር፤ በሌላው እሚ እሚቀናት ተልባ በዉሃ ተለውሶ ለአማራጭ ማጣቀሻነት ቀረበ። ብሩ፣ ናሆም፣ የተቀሰቀሰው ቢግ፣ ባቤ እና ጢዩ ጠረጴዛውን ግርማሞገስ አልብሠው በእሚ የእራስ-አቀማመጥ መሪነት ለመብሉ ተዘጋጁ። ቢግ ሁሉም እንዲቋደስ ለማስቻል ቀድሞ አቡነዘበዘማያት በይፋ እንደ ተለመደው አደረሰ። ትኩስ መብልአቸውን ከፈለጉት ማባያ እየቀቡ በመመገብ ተያያዙት። በህብረት ይሁን እንጂ ሁሉም በእርጋታ እና ክብር ይመገብ ነበር፤ እንደ ምንጊዜውም ባህልአቸው። ጮለቅን የታቀፈች እሚ ገበታ ምግባርዎች ማስተማሯ ከጥንት ስለጀመረ በጨዋታ መነታረክ ካልሆነ በቀረ በስነስርኣት መመገቡ፣ ሁሉ ልማዱ አድርጎላት ስላለ በምንም ድርጊትአቸው አትበሳጭም። ሳይቋረጥ በእሚላክላት የገጠሩ፣ ስሙ ወንድሜ እና ሀሴት ተብሎ በእሚፈታው በአቶ በርናባስ ስጦታ ስትንበሸበሽ ገሚሱን ወዲአው ትሸጥ ነበር። በመስ እማይነጥፍ ስብከት መሰረት ለልጅቿ እሚጠግን የተመጣጠነ መብል ለማሰናዳት ብዙ ሌላ ጥራጥሬዎች እና ቅመማ ቅመምዎች ለዉጣ ትሸምትበት አለች። አሁን ከልጆቿ በኩርዎቹ ደግሞ ለኃላፊነት መድረስ ሊጀምሩ ነው። እንደ አጋጣሚ፤ ነገርግን፤ ሁለቱም እንደመንትያ እሚቀራረቡት ታዳጊ ወጣቶቿ፣ የመቀጠር ሥራን ከወዲሁ የተጣሉት ምክረሃሳብ ነበር። አይፈልጉትም። ዘመኑ በግል አግዝፎ መበልጸግ እሚአዋጣ እንደ አደረገ እሚአምኑ ወጣትዎች ሆኑባት። ይህ አንዱ የጭንቀት ምንጭ ቢሆንባትም ምንም ማድረግ ሳትችል፣ ሁኔታው እንደ ከበባት ነው። አቶ በርናባስ እንዳሉት ቶሎ ደርሠው ከባዶነቱ ሊያወጧት አይችሉም። እና ምን ይደረግ? በቀረ ከመጨነቅ መፍትሔ ላይ መመራመሩ አልቀናትም። ልጆቹ የፈጠራ ስራን አንዴ ቀንቶ ካገኙ ላይላቀቁት ግን እንደእሚናፍቁ አረጋግጠዋል። “ስለ ዘሽ. (ዘመንአዊ ሽንትጨርቅ = ዳያፐር) አስተዉይ እስቲ!” ወጣቶቹ አቋምአቸውን አንድ ቀን ደግሞው ሲያረጋግጡ ለምሳሌ ብለው ያነሱት ነበር። የዘሽ. ቀውስ ንግዱ አንድ አብነትአቸው ነበር። እሚ ሽንትጨርቅ ከነጠላዎች ተጠቅማ ነው ያሳደገችአቸው። ግን እንደእሚገኝ እንድታይ ብቻ ብሎ፣ ብሩ ጮለቅ እንደ ተወለደች አንድ ዘሽ. ገዝቶ አበርክቶ ነበር። እሚ ተደንቃ የጮለቅን ቂጥ አሸገችበት። ባለማመን ብትሆንም ስለተብራራላት ብቻ የጮለቅን ወገብ አስራበት ለሰዓት ያክል ቆየ። ወዲአው ተቀምጠው እየተጨዋወቱበት፣ የእሚ አራስቤት ብቸኛነትን ለመግፈፍ ቁጥር መቁጠር አስተምረዋት ያስለመዷት የካርድ ጨዋታን፣ አብረዋት ተያይዘው እና አብረውም አጥሚት ተጋብዘው ሲጎነጩ ነበር። ዘሹ.ን እሚ ደጋግማ ዞር እያለች ትመለከት ነበር። ጨዋታአቸው ገና ጥቂት ከመሄዱ እና እሚ ሚስትዎችአቸው ማንም በሌለበት በድንገት ቢወልዱ፣ ቶሎ እንግዴ ልጁን እንደ ገመድ ከልጁ ሆድ ክንድ እሚጠጋ ያክል ከፍ ብለው መቋጠር ከዛ መቁረጥ ከእዛም ሚስትአቸው ብድግ ብላ ዱብዱብ ስትል የእርግዝና ተረፈ ምርቱ ሁሉ ተጠራርጉ በብልቷ ሾልኮ እንደ እሚአመልጥ እና መዉለዱ እንደ እሚፈጸም ስታብራራልአቸው ጨዋታው በሣቅ ጦፈ። ባቤ አጠገብአቸው የካርዱን ጨዋታ እየለመደ ያደምጥ ስለነበር “ኤክ! ኤክ!” ብሎ መቀፈፉን አሳወቀ። እሚ ፈገግ ብላ “ጭራሽ ከእዛ ቀድሞ ለመዉለድ ስታምጥ ሚስትህ አሯን ነው ቀድማ ዱብ አድርጋ እምትጥልልህ እኮ ገና!” ብላ ከት ብለው እንዲስቁ አደረገች። እንደባቤ ናሆምም ተፀይፎ ገሸሽ ሲል፣ ሀኪም መሆን እሚመኘው ብሩ አስቀድሞ ያጠናው ክፍለ-ማዋለድ ህክምና መረጃ ስለነበር፣ ባለመገረም “ምን ይሄ ተፈጥሮአዊ ስርኣት አይደል እንዴ? አር የሰው ልጅ ስነስርኣት (ሲስተም) ነው! ምኑ ይደንቃል! እደጉ እንጂ!” ብሎ ጥላቻአቸውን ወዲአው በተገቢ ስልጣኔ ሞረደ። ዘመንአዊ አመለካከትዎች አነፀ። ሁሉም ተስማምተው መፀየፍ የቅጽበት ገሃድን ማጋነን ነው በእሚል ወደ ጨዋታው ተመለሱ። የብሩ አዲስ ዘሽ. በጮለቅ ገላ እንደ ተጣበቀ ዘልጎ ሳይቆይ ግን ወዲያው ካገልግሎት ዉጭ ተደረገ፨
የህፃኗ አር እና ሽንት ካካሏ ሲመዘዝ እሚ ሳታይ ዘግየት ብሎ በመጥፎ መዓዛው መሪነት ከካርድ ጨዋታው ተመልሳ ፈተሸችው። የእለቱ ተረኛ አጣቢ ባቤ ተጠርቶ ዘሹ.ን አጥቦ እንዲአመጣ በእሚ ታዘዘ። ሁለቱ ወጣትዎች መሣቁን ከወኑ እና እቃው ከአሽከርነት እሚባረር፣ ተጠቅመህ-ወርውር ቁስ እንደሆነ አሳወቋት። ብዙ ገንዘብ እንደ ወጣበት አስተውላ “በላተኛ ሱቅ!” መዳፏ ፊት አበስ አድርጎ በሃዘን በመያዝ ሆና ካርድዎች አብራ ሳታስተውል በመዘቅዘቅ እያሳየችአቸው አወገዘች፨
ብሩ እና ናሆም የሱቅ ሥራ ሳይሆን የአምራቾች ምትሃትአዊ ንግድ እንደ ሆነ እና አንድ ጨቅላ እስኪአድግ ብዙ ኢትዮጵያዎች በወር ሺህ ብርዎች በማውጣት እልፍ ፍሰተንዋይ (ኢንቨስትመንት) ቂጥ ለማሸግ እንደ እሚአፈስሱ አብራሩላት። እሚ ከእርሷ አያያዝ አነፃጽራ ስለልዩነቱ ማቀድ ገብታ አናቷ ዞረ። አንድ ጨርቅ ስንቴ እንደ እሚታጠብ እና ዳግ-እሚአገለግል (ሪ-ሰርቭ) እንደሆነ ታውቅ አለች። አንዴ የተገዛው ዘሽ. ወዲአው ሲወረወር አይታ ደግሞ ክዉ አለች። በቀን አንድ ቢጠቀሙ እንኳ ምን ያክል የወጪ ግንድ እንደ ሆነ ታይቶ ከበዳት። “አይ! አንተ ሞኝ ሆነህ ስለ ገዛህ እንጂ ይይህ የሀበሻ እናት ሳይሆን የፈረንጅ ብቻ ነው!” ከከንካኝ ሃሳቧ መዉጫ እና የአጠቃቀሟ ግብረመልስ መሠል ቃል ካርድ እያማረጠች በመጠመድ ሰጠች። ብዙዎች ይህን ሲጠቀሙ እንደእሚገኙ አብራርቶ ብሩ ዘመኑን አስተማራት። እሚ የወቅቱ እንስቶች እና ቤተሰብ መሪዎች ቀዉሰዋል አለች። ብዙ ወጪ ለዘሽ. እንደሚበትኑ እና አልሚ ነገር ለልጆቻቸው በምትኩ መመገብ እንዳልቻሉ አስባ መቀበሉ ከበዳት። ለዘሽ. ብዙ በማውጣት ነገ አልደላኝ ነበር በእማይል ቂጥ ፈንታ የደለበ እና ጤናአማ ሰውነት ያጣ ትዉልድ እንደ እሚአድግ በመብገን የታያትን አቀረበች። እነ ብሩ ህዝቡ መቀወሱ ላይ ተስማምተው፤ ሽንትጨርቅ የማጠብ ስንፍና እና በምትኩ እንቁላል ማር፣ ወተት፣ ቅቤ…አለ መግዛቱ የዘሽ. ገበያው ቀን እንደ ሆነ እንድታምን አደረጓት። “እና እኔ እምነለው ከእናንተ ቶሎ ሥራ አንፈልግም ማለቱ ምን አገናኘው?” በሌላ ትንግርት ሆና ጠየቀች። እነ ናሆም ተያዩ። ፈገግ ብለው ፍረወይኒ መብራቱ እምትሰኝ ኢትየጵያአዊ በ ሲኤንኤን የዓመቱ ጀግና ሽልማት መሸለምዋን አነሱላት። “ለገጠር ተማሪዎች፣ ጎጆ ዉስጥ በቀላል እሚመረት እና እንስት ከሆኑ በነፃ የእሚሰጥ የ ወርት. (ወርአበባ መጥረጊአ = ሞዴስ) እንዲሰጥአቸው በተግባሮት ነድፋ ብዙ ወጣት ኢትዮጵያዎች በነፃነት እንዲማሩ ስላገዘች መቶሺህ የአሜሪካ ዶላርዎች ተሸለመች።” ብሩ አብራራ። እሚ ፍቺው አይገባትም። ናሆም ፈገግ ብሎ ቀጠለ። “ለምሳሌ በቀላል በጎጆ አምርቶ ለባለ አነስተኛ ገቢ እንስትዎች ይህን መነገድ ይቻል አለ!” ብሩ ቀበል አድርጎ አንድ አረዳድ እንደ አለው ያክል ቀጠለበት “ወይም ደግሞ እንደ ተጠቀምሽው እጅግ ዘመንአዊ ያልሆነ ሽንትጨርቅ በጎጆ አምርቶ…” ብሩ ከአፉ መነተፈው “…ለ አነስተኛ ገቢ ቤተሰብዎች” ናሆም መልሶ ከአፉ ነጥቆ ቀጠለ “…ወይም ሃበደታም ቢሆኑም ላልቀወሱ ልጅ አሳዳጊዎች ሁሉ መሸጥ እሚቻል ነው።” “የወይን ፍሬ እንደ ስሟ የሆነችን እንስት፣ በጎስራ ከተንዠረገገ ለድሃ እናትዎች ተያያዡን የቀላል ወጪ ዘሽ. ሥራ ልትሰራ ብትችልም…” ናሆም ሃሳቡን ቀጥሎ አንጠለጠለ እና ዝም ያለ ወንድሙን ተመለከተ። ብሩ ደመደመለት “…ማለት ብቻ ዘመኑ አንድ ነገር ለፈጠረ ሰፊ ገበያ አለው ነው እምንልሽ! እሚነቃ እና አስሶ እሚሰራ ነው እሚአስፈልገው..” ወንድሙን በጨረስኩ መንፈስ ተመለከተው። “ስለ እዚህ ተቀጥሮ መስራት አንፈልግም ነው! በመነገድ የዘሽ. ንግድ ገቢን እራስ እስኪአምም ድረስ ስለሽው ነበር። እማይቀለረጥ ገቢ አለበት። የተማረ ወይም ያሰላሰለ አንድ ነገር አቅዶ ከተነሳ… በሰማይ ሁሉ ለመጓዝ የቀና ዘመን ነው! ሥራ! ሥራ! ሥራ! የሥራ ዘመን ደግሞ ከተቀጣሪነት አይሻም ነው እምንልሽ።”
በግራቀኝ እየወረወሩባት ሲወያዩ ሁሌ እሚአሳምኗት እና በእማታስተውለው መፍዘዝ ሰምጣ ፈገግ ብላ በመነሁለል ሁሌ ታምንልአቸው አለች። ብትስማማም ለአመል ያክል ግን ትቃወም እና ሥራ እንዲቀጠሩ መክራ ዘወር ትል ነበር። ሃሳቡ ቢጥምም ገቢ ግን ቶሎ ማግኘት ስለ አለብአቸው መልሳ ትጨነቅ አለች። መልሳ ደግሞ ዞሮ ዞሮ እራስ ከቻሉ፣ የገጠሩ ገጸበረከት በቀነ-ገደቡ በእዚህ ዓመት ማብቂአ ሲቋጭ ገቢ ቢቀንስም፤ በሁለት ዓመትዎች በወጥነት የተቋቋመ ምትክ ምንጭ ስለ አጊንታ አለች ትተውአቸው አለች፨
በ አዲስአበባ፣ አውሮፓ፣ ሰሜን አሜሪካ እና ፋሲካይት ትልቅ የባህል ልብስ ድረ-ንግድ እንደ ትጉህ ሸረሪት የዘረጋች ወጣቷ ቀልጣፋ ሥራ ፈጣሪ ሐረግ ቸርነት፣ ሁለትሺህ ብር በወር ትከፍላታለች። ቆንጽላ፤ ግን ከእሚ አንድ ሰራተኛነት አንፃር በዛ አለ እሚሰኝ፤ እምታቀርብላትን ከነጋዴዎች እሚሰበሰብ ጥጥ ተረክባ፣ ፈትላ፣ ለመሸመን ሲደርስ ታስረክባት አለች። ባለፈው የፋሲካ ሰሞን ስትጎበኛት ድንገት ተነስቶ እንደ ተወያዩት፣ አሁን ደግሞ መስከረም ላይ ተቀጣጥረው፣ መጪው ዓመት መደወሪአ ገዝታ መሸመን ልታስጀምራት እና ከቤት መዉጫ አመክዮ ለሌላት እሚ ሦስትሺህ እና አምስት መቶ ብርዎች ደመወዝ ለመክፈል ቅኗ እና ባለሳቂታ ስብእና ወጣት ነጋዴ ዕቅድ ይዛላት አለች፨
ቀልጣፋዋ ሐረግ ከብዙ የገጠር እንስትዎች ጋር ይህ ብልህ የድረ-ንግድ ገና ስትጀምር አስተሳስሯት ነበር። ከቅናሽ ክፍያአቸው ብዙ አተረፈች። ስትረዳአቸው ሲረዷት ትልቅ አትራፊ ሆና ንግዷ ዘለገ። አሰፋችው። በቀጣዩ ሥራ በግሏ ንድፍ ተምራ እና አጥንታ ተመለሰ ች። ነድፋ፣ ሰፍታ እምታቀርበው ዘመንአዊ የባህል ልብስዎች ልዩልዩ ቅጥ (ስታይል) ሲሆን ገበያው ከኢኅአዴግ. የህዳር ፳፱ በዓል ጋር በተለየ ይደምቅላት ነበር። በእምትሰጠው ጉርሻ ብዙ መንግስት መስሪአቤትዎች ከእርሷ የብሔረሰብ ልብስዎች እሚሉትን ይገዙ ነበር። ሁሉን አቃለሁ በማለት ቀለምዎች በመዘበራረቅ ልብሱን ስትሰጥ ይረኩ ነበር። ለማድመቂአ ሚሊየንዎች ሲበተኑ፣ ክፍያዋ ከፍ ተደርጎ ከመንግስት ካዝና ይወጣ እና ከፊሉ በከፋይዎቹ ስምምነት ለጉርሻ ተመላሽ ይሆን አለ። በሂደት ግን ተሰጥዖ እና ዘመንአዊ ዕዉቀት ከብልሃት ጋር ስለነበራት የልብስ ንድፎቿ እና ሥራዋ፣ በመንደር እሚቀር አልሆነም። በንግድ ድር መገንባት ክሂሎቷ፣ የተረፈችውን ይዛ ወደ ሰፊ ሽል ንግድ ዓለም እራስዋን ገፍታ አሹልካ ተፈናጠጠች። ደግ ገቢ በዘመንአዊ ባህል-ልብስ ቅጥ ንግዷ በመሰብሰብ ዳግመኛ ወደ አዲስ መሰላል አደገች። የመንደሩን ንግድ አብዝታ በመቀነስ ወደ አዲስአበባ አተኮረች። በደግ ብልሃቷ የአዲስአበባ ገበያ ከፍተኛ ሃብታሞች ሰርጎችን እስከመቆጣጠር እና ብዙ አሻራ በመደበኛውም ገበያ እንድታሳርፍ ፈቀደላት። ደግ ንድፈኛ (ዲዛይነር) ተብላ ብዙ ሽልማቶች እና ቄንጥ (ፋሽን) ዉድድሮች አሸነፈች። በሂደት ግን ንግዱ አዲስአበባ እሚቀር አልሆነም። በቀጣይ በረራዋ ደግሞ ወደ ባህር ማዶ ዞረች። ልክ እንደ አፍሪቃ የመጀሪያዎቹ ሴት ሚሊየነሮች፤ እንደ ቶጎዎቹ እንስት ባህል ልብስ አምራቾች የሃበሻ ብዙ ሃበሻዎች ከሃገር ሲወጡ ባህል ልብስ ስለእማይዙ እና ቤተሰብ እዛ ስለ እሚአፈሩ ለበዓልዎች ግን ልብሱን መፈለግ ይጀምሩ አሉ። ከነቤተሰብአቸው እሚሆን አቅርቦት እምብዛም ስለ እማይኖር፤ የእርሷ አቅርቦት ከደቡብአፍሪቃ በመነሳት ወደ ዐረብዎች፣ አዉሮፓ፣ እና ሰሜን አሜሪካዎች በዝግመት እየተንሰራፋ ደረሰ። ይህ የምጣኔሃብት ግዛቷ ትንሽ ሰውዎች ጨምሮ አስቀጠራት። ግን ከገጠር በቅላ፣ ሃገር ወዳድ የሆነችዋ ሐረግ፣ ሃገረሰብእዔውን (ካንትሪሳይድ-ሜን) ለመጥቀም ሥራዋ ዘመንአዊ እዉቀት ፈላጊ ካልሆነ፣ በገጠር እሚገኝ ድሃ እንዲሰራው ታደርግ ነበር። እሚን ሁለት ዓመትዎች በፊት ስታገኝ በወሬ እንጂ ያኔ እሚ ከተማ ከገባች አምስት አመቷ ነበር። እሚ ለደጉ ጎረቤቷ በርናባስ ገጠር በመሄድ በፋሲካ ሳምንት በያመቱ ጉብኝት ታደርግ ነበር። አመቱን እማያራዝሙ እንደ ሆነ ገልጸው በቤተሰብነት ግን የእሚቀርቡአት ጎረቤት ከወጣቷ ነጋዴ ጋር በገጠሩ ሰራተኛ ስታፈላልግ በሰፊ ጆሮአቸው ወሬውን ገብቶ ስለ ነበር እንደ ምትክ ገቢ ቢሆናት ብለው ከሐረግ ጋር አገናኙዋት። “እኔ መሬቱን እሻው አለሁ። ገቢዬ አሽቆልቁሎ አለ። ለልጅዎቼ ከተማ ቤት ልገዛ ደግሞ ሳንቲም እየአጠራቀምሁ ነው። ላአንቺ አልሆንም። ባልሽ በደለሽ መሬቱ አልቅሰሽበት አይቀናኝም ብዬ ስለ እናቴም መለመንሽን አይቼ ነው የምረዳሽ። ይቺ ወጣት ፈታይ ትፈልግ አለች። አንቺ ደግሞ በስንቱ ሙያ የተካንሽ ነሽ።” ብለው አበረታቱአት እና አገናኙዋት። እሚ ከተሜ ናት በሚል ወጣቷ እንቢ አለች። ግን ሁሉ የእሚ ነገር ሲነገራት ዞሮዞሮ ሰው መርዳቱ ስለ እሚገድዳት ፈትና ስታረካት ቀጠረቻት፨
ይህ ገቢ የገጠሩ ገጸበረከት በአዲሱ አመት ሲቋጭ እንደ ተለመደው ባይሆንም ለመኖር ያክል ምንጭ ነው። ያቀደችው ደግሞ ጠላ እና አረቄ አብሮ በመሸጥ ከተማ መግባትዋን በገቢ ብዝበዛ ልትጠቀምበት ነው። ከተማው በባህል መጠጡ አቅርቦት ተምበሽብሾ የእሚ ችክን ያለ ሙያ ገበከው ቢወርድበትም ለዋናው ገቢ አጋዥ ከሆነ በቂ ነው ብላ አቅዳለት አለች። መስ ደግሞ በወር መቶ እና ሁለትመቶ ብርዎች ሳይልክላት አያልፍም። እግዜር ከደገፈው መስም ይህን ሊአቋርጥ ካልቻለ መብራት እና ዉሃ እንኳ ሊሸፍን ይችል አለ። ካደረሳት ደግሞ ኮፍያዎች በመስራት ስለ ተካነች በቻይና ክርዎች በምትታታቸው ኮፍያዎች ገቢ ጭምር ጥቂት ይስተካከል አለ። ስለ እዚህ እሚ በመጪ ጊዜዋ የገጠሩ ገፀበረከት ጠፋ ብላ ስጋት ገብቶዋት አታውቅም። እንደ እምትረካበት ልጆቿ ድሃ ቤተሰብ ሆነውም በብልሃቷ እንደ ደላው ቤተሰብ ነገአቸው ላይ ብቻ አተኩረው በስርኣት እያደጉላት ነው፨
የጧት መብሉ እንደ አለቀ ቁሳቁስዎችን የመንከባከብ ስራው በሁለት ቀን አንዴ የቢግ ስለ እሚሆን ሰብስቦ በጥንቃቄ ወደ ጓሮ ዞረ። ከዉጭው ኩሽናው ስር ወደ ጊቢ ዉጭ ፍሳሹ እሚጓዝ መስመር የተሸለመ በፍርግርግ እንጨትዎች ለዕቃዎች ማጠቢአነት የተቋቋመ ከፍታ ላይ፣ ከስሩ ባለአንድ ብቻ ደረጃ በመሰቀል ወጥቶ፣ ቢግ ዕቃውን ሁሉ ቆሻሻው ሳይደርቅበት ወዲአው አጠበ፨
ሳይታሰብ ሰዓቱ ስለረፈደ የመስን መምጣት ሁሉ ይጠባበቅ ጀመረ። ብሩ ቤቱን ከወንድሙ ጋር አሰናድቶ ወደ ሲጨርስ ሌላዎቹን ተለይቶ ወደ ጓደኛው ዮስ እንደ እሚሄድ አሳውቆ ወጣ። ባቤ መስኮተድምጽዋን ከፍቶ የክረምቱ አንድ ግል ሥራውን ሰሞኑን ጥራጥሬዎች በማሰስ ለቃቅሞ ከወረቀትዎቹ ጋር ይዞ ሲቀመጥ፣ ናሆም የጣለበትን ቤትስራ ደግሞ ለመንትያነት የቀረበው፣ ብዙ እማይበልጠው ቢግ ተያያዘ። የእንግሊዝኛ መማሪአ ወረቀትዎች ናሆም ራሱ ከእሚወድደው ኢንትርሚዲየት ኢንግሊሽ ግራመር፦ የካምብሪጅ ኅዋአዊከተማ እትመት ድንቅ መጽሐፍ ቀምሞ አበጅቶለት ነበር። መጽሐፉ ለናሆም፣ እንግሊዝኛ ለመማር ከተፃፉ እና ከገጠመው መጽሐፍዎች ድንቁ እና አንድኛ እሚለው ነበር፤ በአንድ ገፅ አንድ ምዕራፍ – በመቶሰማኒአ ገፅዎች መቶሰማኒአ ምእራፍዎች ከአስደማሚ አቀራረብ ፍፁምነት ጋር። ‘ይህን አንብቦ በእንግሊዝኛው ላይ ያልጎበዘበት ቢኖር አላምንም፤’ ቢግ መሰረትአዊ ንግግርዎች መከወኛ ሰዋሰው በማጥናት ብዙ ሳይቸገር ስለለመደ ፣ በእዚህ ወር ቢግ መሃከለኛ የቋንቋውን አቅም በመሰነጣጠር ላይ ነው። ከአራት ወደ አምስትኛ ክፍል ገና ቢዛወርም እንግሊዝኛ ው ግን፣ ለማስተማር ፊቱ ከእሚቆሙ መምህሮች እሚሻል ሆኖለት ነበር። ቢግ በእርግጥ በግሉ እንደ ቀሩት ልጅዎች ብሩ በተለየ ደግሞ ናሆም እየረዱት እማይሞክረው እና እማይደሰትበት ምርምር ብጤ ነገር አልነበረም። ናሆም በልጅዎች ወደ ዐዋቂ ሰውነት ማንቃት ወይም ማደግ እምንለው ደረጃ መድረስ የተካነ ስነልቦናአዊ አገነዛዘብ ነበረው። ይህ ወደ ታናናሽዎቹ ልዩነት ሆኖ እንዲመጣልአቸው የተወው ነበር፨
ናሆም ጆን ፊኒስን ድንገት በቤተመጽሐፉ የዉጭ ስጦታ መጽሐፍዎች መሀከል አጊንቶት አገላበጠ እና በፍቅር ወደቀበት። ፊኒስ (ሰቨን ቤዚክ ሂዉማን ጉድስ) ላይ እንደ አለው፣ ህፃን ሰው፣ ነብሱ ያልነቃ ገና ሂወትን ከአካባቢው በዝግመትአዊ አጢኖት (ኦብዘርቬሽን) ብቻ እሚለማመድ፣ ወጣኝ ዘረፍጥረት ነው ይል ነበር። አካባቢው ምንም ካስተማረው ያን ምንምን በብቃት መሆን ይችል አለ። ነገርግን የ ፊኒስ ዳግምርምር (ሪሰርች) ልቦና (ኮንሰንትሬሽን)፣ የህፃን ሰውዎች አንጎል ማደግ ምንጩ፣ ተተግባሪአማ አመክዮአዊነት (ፕራክቲካል ሪዝኔብልነስ) ማጥናት መቻልአቸውን አስምሮ ማሳወቅ ነበር። ከተግባር-ተኮር አመክዮ ብቻ፣ ልጅ እንደ ሰው መሆን ይማር አለ። ከእሚነገረው ቃልዎች ይልቅ የተግባር አመክዮን የማነፍነፍ፣ መመርመር፣ እና አብነት የ ማድረግ ተሰጥዖ በህፃን ሰው ሁሉ እንደ አለ አስረዳ። ወደ አንድ ገጸባህሪይ ልጅን እሚቀርፀው ይህ የተተግባሪ አኳኋን ማጤኛ አመክዮ ስጦታው ወይም አቅሙ እንደ ሆነ አሳየ፨ ናሆም በእዚህ የ ፊኒስ አገነዛዘቡ ልቡ ፈካ።ልጅዎች በመጥረብ እንደ ተፈለገው ማጎንቆል እንደ እሚቻል በፊትም ያዉጠነጥን እና የተዝረከረከ አያያዝ እንደ አለ በጠቅላላው በመቃኘት ስለ ሃገሩ ይበሳጭ ነበር። ፊኒስ ግን ለሰመጠ ምናብአዊ ግዛቱ ከእንግሊዝ ተሻግሮ በመጽሐፉ ሊአዋየው ጓዱ ሆነለት። አገነዛዘቡ ሰፍቶ ሂስ ሁሉ በዘርፉ ተመራማሪዎች እንዲሰነዝር አበቃው። ይህ ልጅነት በእርግጥ ለ አነሱ ፈላስፋዎች ሌላ አናሽ መገለጫዎች ታይቶአቸው እሚዘለል ነጥብ ም ነው። ደቂቅ-ስነልቦና (ቻይልድ ሳይኮሎጂ) እነ እዚህን ንዑስ-እሳቤዎች ለመገፍተር በቂ የጥናት እና አስተምህሮት ብቃት ቢኖረውም እንደ አለመታደል ግን አፈንጋጭነቱ በመሀልአችን አለ። ለምሳሌ፣ በእዉቀቱ ስዩም፣ የጭራቅ ተረት ግጥሙን ነግሮ ‘አዉዉ መጣ’ ምናምን ነገር በማለት ልጅዎች እሚአሳዩት አንድ ያለመንቃት ተፅዕኖን ሀበሻ መታገሉ እንደ ተገቢነት የተለመደ ነገር አድርጎ ማጥናቱን ይናገር አለ። ግን ይህ ንዑስ-ስነልቦናትንታኔ (ሰብስታንዳርድ ሳይኮአናሊሲስ) እንጂ ከቶ ምርጥ አገነዛዘብ አይደለም። ማለትም፤ ስህተት ነው። በናሆም ታታሪ፣ ጥበበምርምርአዊ (ሳይንቲፊክ) ገሃድ አሳሽ፣ አዉጠንጣኝ ምናብ እንደ ተደረሰበት ከሆነ ምርጡ መንገድ የህፃን አንጎልን ለማንቃት ተግባር ትምህርት እንዲሆን ማድረግ ብቻ ነው። አድጎም ልጅ ምግባርአዊ (ቢሄቭድ) እንዲሆን ተግባር የዓለሙ መገናኛ መንገድ እንደ ሆነ በትግበራ እንዲማር ተደርጎ ማደግ አለበት። የልጅ አመክዮ አቅም መገንባት እና ዓለምን መረዳት ከተተግባሪ ነገርዎች መሀል አመክዮ ወይም ፍች የመፈለግ ተሰጥዖው ነው እና። ይህ የሃገር ምርጡ ማዕድን ዕንቁ ነው ብሎ ናሆም ወዲአው አመነ። ይህን ያሰመጠ አረዳድ የከወነበት ሃገር ካለ፣ የመጪጊዜ ዕድሉን መቆጣጠር ይችል አለ። ይህ የገባው ልጁን በፈለገው መንገድ ይቀርጽበት ስላለ። አዳጊው ትዉልድ ለምሳሌ አንድ ተግባር በነፃ እንደ እማይገኝ፣ በአንድ መንገድ ስብእናው እንዲሟሽ ገና በጊዜ ማድረግ ይችል አለ። ለልጅ ቶሎ በጨቅላነት በትግበራ ዉስጥ ፍቺ ማስተማ በመቻሉ። ‘እንዴት? በዋነኛነት ጨቅላ-ስነልቦናኛዎች (ቻይልድ ሳይኮሎጂስትስ) የአብራሩት አለ፤’ ለናሆም በመሰረትአዊነት ግን፣ በግል የግል ዓለምን መቆጣጠር እንደ አለብአቸው በተግባር መርቶ ማሳወቁ እነ እርሱን ቶሎ ማንቂአው መንገድ ነው። ለምሳሌ መጫወቻ እራሱ መርምሮ በመገጣጠም እና በመሰካካት እየተገነባ እሚአጫውት አድርጎ፣ አመክዮአዊነትን ወደ ልጅ ያመጣ አለ። በዘመኑ ይህን ሃሳብ አገልጋይ መጫወቻዎች ማጫወቱን ብዙዎች ቢአዘወትሩትም ፍቺው ግን መጫወቻ ብቻ እንደ ሆነ ስለ እሚአቁ ጨቅላው ካደገ የምስጢሩ ነገር ይረሳ አለ። ግን ማፍረስ መገንባቱ የ ፊኒስ ሃሳብ ፍች – የኃላፊነት ጽንሰሐሳብን ከተተግባሪ አመክዮ ዉስጥ በጨዋታ መሀል ለልጅ አንጎል ማስነፍነፍ፣ የግል ጥረትን ምንመሆንን እንደ ሃሳብ ወደ አንጎል ከትግበራው ማስመጠጥ፣ ብቻ ዓለምን ማስተማር እና ወደ ዐዋቂነት ቶሎ ማብቂያ ጎዳና – ነው። ነገርግን ያባትአዊነት ፍቅር መግለጫ የሆነው እና ሲአለቅሱ ለእናትነት ደግሞ ማታለያ ብለን እምንረዳው መጫወቻ ስለ ሆነ የበለፀገ አንጎል ከመገንባት ይከለክለን አለ። ምክንያቱም ሳይታወቅም ቢሆን ከትግበራ አመክዮን በጥቂቱ ባቅሙ የመሰረተው የአንጎል፣ ልጁ መዳኽ ከአቆመ ይወገድ አለ። አይተካም። ለምሳሌ ገና ጥቂት ከፍ ሲሉ ግን፣ አዲስ መላ በእዚህ ነቢብ እንደምታ መሰረት ግን ነበር። ህፃኑ አንድ አትክልት ተንከባክቦ ማሳደግ እና እራሱ ኮትኩቶ፣ አርሞ፣ አዘጋጅቶ ዐዋቂ እንዲመግብ እና አብሮ እንዲመገብ ማድረግ፣ ወይም በፍቅር ሌላ መጫወቻ ለ ምሳሌ አንድ ጫጩት አሳድጎ በግሉ ለወግ ፍሬ ማብቃት፣ ወይም መሰል አንድ መጫወቻ እሚቀርብለት ሲሆን እግረመንገዱን ም ታዳጊው አመክዮን ከተግባር እንደ ንብ ቀስሞ ስብእናው ከ ምናብቴ (ፋንታሲ) ወደ ተግባር ይተሳሰር አለ። እራሱን መገንዘቢአ መንገዱ ከተጨባጭ እና ሰርቶ ፍሬ መልቀም ይተሳሰር አለ ነው። ሲአድግ ዓለም ከእዛ አገነዛዘብ አትሸሽበትም። ተግባር እና ዉጤቱ፤ መነሾ እና አመክዮው ከመድረሻው፤ እሚሰነታትር አንጎል በተፈጥሮው ይካን አለ። ስኬትን ማግኘት ችግር ከመጠንቆል እና ማውጣት፣ መፍትሔውን ከማብላላት እና መተግበር ቀልሎ ይታየው አለ። የስኬትአማ ሃገር ትዉልድ ገና ከመዋእለቀን (ዴይኬር) ጀምሮ ይህን በስፋት እሚማር የሆነበት ነው፨
የናሆም ምናብ ይህን በስፋት አብሰልስሎ አብላሎት (ኢንተርናላይዜሽን) ከዉኖበት ከትዉልድ አረዳድ አንጎልአዊነቱ (ሜንታሊቲ) ያዋሃደው ነበር። በሃሳቡ መሰደር እና መብላላት ተደስቶ የግንዛቤ ግዛቱን ቀጥሮት ወደ ታናናሽዎቹ ማበልፀግ አተኮረ። ፈጥኖ ኃላፊነት መቀበል ችለው በጥገኛነት እማያስቸግሩ እንደ እሚሆኑ ስላመነ፤ ማንም ዘላለም ለእማያቅፈው አዲስ ተወላጅ ዘረሰው ሰው ይህ ቶሎ እንዲውል ወሰነ። ‘የ ስብእና ነፃነት ጎህ መቅደድ ማለት ነው፤’ ልእለንቅኣት ያለው ልጅ ማፍሪአው መንገድ ነው። አድጎ ይህን ለመከወን ከእሚጥር እና ቀውስ ሊገጥመው ከእሚችል ልጅ የተሻለ ስኬት አምጪ ልጅ ማቁላያው መንገድ ነው። ጅቡ እና ጭራቁ ሳይኖሩ በ አሙ መጣ እና አዉዉ ማታለሉ ህፃኑን አድጎ ፈሪ ግን ፈርቶም ትርጉም እማያገኝ ያደርገው አለ። ግለ-አርነት (ሰልፍ-ፊሪደም) በጠለቀ ስነልቦና ስላልሰረፀ ዘገይቶ መታሰስ አለበት። ለእራሱ ግለአርነት በሂወት ማለዳ ከተግባርአዊ እንቅስቃሴ አመክዮ መኖር በግል ተንቀሳቅሶ ያጤነ ግን እንዲይዝ የተደረገው ግልአዊ አቅሙን ነው፤ ሊአውም በጊዜ ስለ ሆነ ሥር በቀላሉ በእሚሰድድ መልኩ። ሲአድግ እንደ ፈርቶ አደገው ያሳዳጊ መሃይምነት ጎርፍ አስተዳደጉን ያጨቀየበት ሳይሆን፣ ጭራሽ ግን በአለ አስፈሪ ስብእና ይሆን አለ፨
ናሆም ይህን በሰፊ ማብላላት አዉጠንጥኖበት የአምን ነበር። በደግ መጠን እሚም። በደግ ስፋት መስም። የ ጆን ፊኒስ የተፈጥሮ ህግ ፍልስፍና ፍቺ በመደበኛ አኗኗር በእነ እሚ ቤተሰብ ተደርሶበት “የ ወደፊት ተስፋም-መንገድም” ነበር። ገሃድ መቼም እና የትም ገሃድ ነበር እና። ገሃድ በፈላስፋ እና ዓይንዎች ባልጨፈነ መደዴ እኩል በገሃዱ ሃዲድ እሚአሳፍር ነበር እና፤ ከስምጠት ልዩነት በቀረ። የእሚ ቀላል አኗኗር፣ በመስ እና ናሆም ምክርዎች የተብላላ ሆኖ ለልጆቿ መስዋእት ስለነበረች ምርጡ የተባለ ልጅ ማሳደግ መንገድ የእርሷ መንገድ ነበር፤ ብዙ ገንዘብ እስከ አልጠየቀ ድረስ። ስነልቦና ደግሞ ወጪው ዜሮ ጋር ይዋደድ ስለ ነበር አልከበዳትም፨
ባቤ በስእልዎች እነ ቢግ እና ጢዩ በአትክልትዎች እና ታሪክ አያያዝዎች ኃላፊነት መዉሰድን እና የመመርመር ጥበብን በስዉር ይማሩ እና ሰው መሆንን በእራስአቸው ይገነቡ ነበር – በእዚህ ዓመት። የቢግ መሰል አመትአዊ ተግባሬት (ፕሮጀክት) የእሚ ዘመን የልጅ ተረቶች መልቀም እና መፃፍ ሆኖ ወደ ሰባአንድ ተረትዎች ደርሶለት ነበር። የእሚ ልብ ዓመቱን ሙሉ አጫዋች አጊንቶ ባለመታከት ተረት በማስታወስ እና አንድአንድ ም በመፍጠር ተጠምዶ ነበር። ጎረቤት በሌለበት አዋዋዮቿ ልጆቿ ስለ ነበሩ እማይታክት ጓደኛምነት እናትነትን አነባብሮ ነበራት። ቢግ ጥራዝ-ተረትዎቹን ያበጀው ያምና ሊቅአዊ-ዓመት (አካደሚክ ዪር) ማብቂአ ደብተርዎች ያተረፉት ወረቀቶቻቸውን ገንጥሎ እንዲአዋጡ አድርጎ በህብረወረቀትዎች በሰፋው መጽሔቱ ተይቦ ነው። ብጁ-መጽሔቱ ባለኮሌታ ሽፋን እና መዘጊአ እንዲሆን ጠንካራ ካርድ ተጀቦደበት። በመዘጋት በስነቁልፍ ቀመሩ ተቆልፎ ወደ ጓዳው የላይ-ግድግዳ ተንጠልጣይ ግል ሻንጣው ለወደፊት አገልግሎት ተኝቶ ነበር። በናሆም በቀላል ቅጽበትዎች ከማዳበሪአዎች የተዘጋጀው ሻንጣ በመቆለፍ እና በመንጠልጠል ለታዳጊዎቹ ብርቅ አገልግሎት ይቸር ነበር። ከእዚህ ተግባሬት መጠናቀቅ ኋላ ሲመለስ፣ ሰሞኑን ቢግ በእንግሊዝኛው እንዲያተኩር ተደርጎ ነበር፨
ከ እንግሊዝኛው ጎን ደግሞ፣ የህፃናት ሰብልዎች ጥናት ከጢዩ ጋር ይተገብር ነበር። ናሆም የታዘዘውን የቢግ አዲስ የጥራጥሬዎች በተቀራረበ ዘርግንድ መሰደር እና አጎነቋቆል መንገድዎች እና እሚፈጁት ጊዜ ዳግምርምር ሥራውን ጎበኘለት። ደግ መማር ቢግ ከተግባሬቱ እንደ አገኘ ተረዳ። ስለ እቅጭ የሰብል ባህሪዎቹ በዝርዝሩ እራሱ ናሆም እንኳ አያቅም ነበር። ግን የጥናትአዊ ስነአሰራሩ በደንበኛ ተመራማሪ መንገድ ስለ ተወሳሰበ እና በቀጥተኛ ግልፅ ትርጉምአማ ቅንብር ስለ ተዘጋጀ አጠናኑ በቂ አመክዮ እንደ ገነባ አስረዳው። ስምጥ ጉዳዩን በፍላጎቱ ቢግ አድጎ ከመረጠው እስኪቀጥል ለጊዜው ይህ ቅኔ ለናሆም በቂ ሆነ። ቢሳሳት እንኳ፤ እርሱ ገና መች የግብርና ዲግሪ እንኳ አገኘ? አላማው በተግባር ዉስጥ አመክዮ መልመድ እና እራስ ማወቅን፣ አሰበጣጥሮ ቶሎ ነገርዎች በማገናኘት አብላልቶ ማስጨበጥ ነው። ቶሎ ከእናት ስነልቦናአዊ ጉያ መፈልቀቅ ነው። ለእዛ ደግሞ ይህ አንድ አረዳድ ተከትሎ የስነጥራጥሬ ዓለሙን መሰብሰቡ ትልቅ በቂ ክሂሎትአማአዊነት (ቴክኒክ) ነው። ናሆም በተመለከተው አስተያየቱን አዎንታአዊ ድርጎ ተሻገረ። ወደ ነብሳት መሰል ዳግምርምሩ መሻገሪአ አረንጓዴ መብራት ተሰጠው፨
‘ሃዘንቴ (ሳዲስት) መሆን የለም። በሰው መቅናት እና መመቃኘት ስሜት ማሳደግ የለም። መተባበር እና ሰው መሆን ይለመድ አለ። በግል ኃላፊነት ለኑሮ መዉሰድ እንዲበዛ፣ ምራቅ ያስውጥ አለ። ይህ በለጋ እድሜ በዚህ ብልሃት ተከውኖ ወደ ብርሃን ፍጥነት (ጊዜ) ብስለት ትዉልዱን ይመልሰው አለ፤’ ናሆም ይህን ወደ ጠቅላላ አረዳድ ቀይሮ እሚአስበውን የሽል ዓለም ናፍቆት በታናሹ ላይ ተመልክቶ ወረቀቱን መለሰለት። ቢግ ከበርጩማ ወንበርዎቹ መሀል ያለ መጠነኛ ጠረጴዛው ላይ ያሉ ሌላ ወረቀትዎቹን ጨምሮ ወደ ጓዳው በመደሰት አዘገመ፨
እሚ ሞላጎደል በሰብል ምርትዎች መርከስ እማትታማዋ ፋሲካይት ዉስጥ እንዳትቸገር እሚደጉማትን ዕድአዊ ሥራ፤ ሰሞኑን በያዘችው የልቃቂት ማበጀት ትንቅንቅ ትላንት ስላጠናቀቀች፣ እና በደሞዝ ልትለዉጠው ማስረከቢአውን ቀን ብቻ ስለ እምትጠባበቅ፣ በናሆም ዉብ ንድፍ ላይ ለግል ገበያዋ አንድ አበሻ ቀሚስ መጥለፍ ስለ ተያያዘች ወደ እርሱ ተመለሰች። ጢዩ እምታጫውታት ጮለቅ ወደ ቁርስዋ ዞረች። ጢዩ በማሳቁ መሀከል የጮለቅ አፍ ሲለጠጥ፣ ወተት፣ እንቁላል፣ ገብስ፣ ጨው፣ ዘይት፣ ቅቤ፣ እና ዉኀ ምስጀት (ረሲፒ) ተዋህዶ በስሎ፣ ቀዝቀዝ ብሎ የቀረበላትን በመመገብ ተጠምዳ ቆየች። እሚአቅፋት ስለሌለ እና የጢኖ ፍቅር ከማንም ይልቅ ስለ እሚአስቦርቃት በነፃነት በማደግ ላይ ነች። እምትሰማው የጢዩ እንቆቅልሽ እሚገባት ይመስል በዐዋቂ ማእረግ እያደመጠች መብሉን መዉሰድ ቀጠለች። ናሆም ቢግ በቀጣይ ማስቸገር ዙሩ ያቀረበለት እንግሊዝኛ ጥያቄዎችን በመመለስ አግዞት ሲአበቃ የሁለትኛ ጧት ዕቅዱ ደግ ፍፃሜ ሆነ። የመጨረሻ ጧት ዕቅዱን አሰበ። ‘መስተንግዶ መስ፤’ ከመብል ኋላ የተበላሸ ስፍራ ካለ ቤቱን ፈተሸ። በሳሎኑ ወደ አንድ ጥጋት አዝምሞ ያለው፣ ዉራጅ (ሰከንድሀንድ) ሆኖ በርካሽ እሚ በሽንጥ ግተራ መወገን ያስገዛችው ደገኛ እሚባለው የሁዳድ ፍልሰት ዉጤት ከሆኑ ቅርስ መሰብሰብዎች ዋና የሆነው የቤት እቃ፣ በባለሙያ የተዘጋጀ የሆነው በደግ ከፍታ እሚአጅቡት ስምንት ቀጭን ዘለግ ያሉ ወንበርቹ ጭምር እሚፎክረው መመገቢአ ጠረጴዛ ያልተበላበት ይመስል አምሮበት አለ። ሁሉም መሆን ከእሚችለው አቅመ ዉበት ላይ ነው። ዉጭውም በቀደመው ቀን መጠነኛ መስተንግዶ አግኝቶ ያንን ያንጸባርቅ አለ። የእጅ ሰዓቱን ተመለከተ፨

፨፨፨ ፨፨፨ ፨፨፨

By Binyamhailemeskel

Hey there! If you want to know about me, I just like fun, commonsense wisdom, and human love. Let us live a bright today changing tomorrow into brighter.
Regards,

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s