Categories
My Outlet (የግል ኬላ)

ምእራፍ ፩

መስፍን ጎንለጎን ምእራፍ አንድ፨

፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
፩ ቀን መቀበል

የምእራፉን ተአዶ. (PDF) ያግኙ።

ሌላ ሰኞ ገባ። ዉስጡ፣ የእሚ ቤተሰብ ህልው ሆኖ አለ። የአዲሱ ሰኞ ጎኅ የእሁድ ጨለማ ማፈናቀሉን ሊያጠናቅቅ ሲል፣ ከሁሉ ቀድሞ፣ ናሆም ልክ ነቃ። አንጠራራ። ‘ኡኽ አዲሱ ዕለት። እንተቃቀፍ አልክ? በሁለትኛ ማንጠራራት እና መመቻቸት፣ የነፍስ እጅዎቼን ዘርግቼ ነዋ!’ ከእንቅልፍ፣ ቀድሞ በዉጋገን፣ የዕድሜዘመኑን በር ከፍቶ ገቢ ቀን ሲአንኳኳ እሚቀበል ቀን-ተቀባይ ይባላል። የኑሮ መንገድ አበጂ ስለሆነ፣ ቀንመቀበል ከቀን-መቀላቀል በሂወቱ ይለያል። ሌቋሆ. (=ሌላ ሃቂትዎች (ፋክተርስ) ቋሚ ሆነው) ቀን-ተቀላቃይ ከቀን-ተቀባይ አናሽ የቀን ፍቅር አለው፣ ቀን-ተቀባይ ከቀኑ በላጭ የቀን ክፍያ አለው። ዘማች ጊዜ አጠንክሮለት በሄደው የማለዳ ቅኔ አረዳዱ፣ በደግ ዐዋቂ ልቡ ተቀርጾ የመቼም መርኁ ነበር፨
ማንም ያየው፤ መጠነኛ ሰውነት አለህ እሚለው፣ የ ፲፰ ዓመቱ፣ ከጥራዝነጠቅ ርእዮት የነቃ፣ ብልኅ እና የልጅዐዋቂ፣ አስተዋይነት በሆንብሎንታ (ደሊበሬትሊ) እሚገነባ (ምናብ ዉስጥ ነብሱ ሰምጦ ያልጠፋ እና በሞገደኛ ህላዌ ያልታሠረ)፣ ገጠር በኩራዝ ብርሃን ታጅቦ ወለል ምንጣፍ ላይ ዓለምን ሌሊት ተወልዶ የተቀላቀለ፣ ብዙ ሳይቆይ በቤተሰቡ ድንገቴ ኢንጽረቴ (ወደፊትን አጥርቶ ያላጠና) ዉሳኔ-ትግበራ፣ ጠይም ሀበሻ መልክ እንደ ቤተሰብዎቹ አብዛኛዎቹ አባልዎች ለቆዳው የደረሰው፣ ማለት እሚቻል አባትአልባ፣ በቀረ በትምህርትቤት መሸለም እና ላይ-መምህርዎች በግሉ ዘባች ሊቅኛ (አካደሚክ) እዉቀቱ የእሚያስከበረው፣ ተማሪቤቱ የመብሰል አቅሙን ፈተና ሆኖ ያልተገዳደረው፣ አይነተኛ የ፳፩ኛው ክዘ. ክፍለሀገር ኢትዮጵያአዊ ታዳጊ። ሰሞኑን ግን፤ የሰውነት ንጥረነገሩ ሁሉ እየፊናው በጡንቻ እድገትአቸው መነሾነት አካላቱን ሁሉ በቂም መሰል ጥቃት ማፈነዳዳት ተያይዞበት ያለው ናሆም፣ እንደ ወትሮው በአዲስ ጎኁ ነብሱን ልኮ በሂወት ተመዘገበ፨
እንደ ሁልጊዜ ልምምዱ፣ መስ በገነባው አልጋ ሰዉነቱን አንጥፎበት፣ ወደ ጣሪአ ተመለከተ። ኢንጽረቴ አኗኗሩ በድንገት ተሳክቶ፣ የተለመደ እማይባለው የከተው አኗኗራቸው ሁሉም እየጠቀመ ነው፦ እድሜ ለመስ እና በርናባስ። እርሱም እየተሸለመ ነው፦ የጠሩ ዓይንዎች፣ ወደርየለሽ ልቦና (ኮንሰንትሬሽን) ትምህርትአዊ ስኬት እና ደስተኛነት፣ ፈርጣማ እና ጠንካራ ሰዉነት፣ በጠቅላላው ብሩህ የታዳጊ መንገድ ዉስጥ እየተቋቋመ ነው። ወደ ላይ እንደ ተመለከተ፣ መልሶ ዓይንዎቹን ጨፈን አደረገ። ዊ…ቅ.. ዊ…ቅ.. ዊ…ቅ። የጓሮ በራቸው ሥር እሚጨዋወቱ እንቁራሪቶችን እና ጠንካራ ፀጥታን አብሮ አደመጠ። እንቁራሪትዎቹ ለአዳራቸው፣ ወደ በሩ ቀረብ ብለው ነበር ማለት ነው። ከአስተዉሎቱ ወደ እራሱ ተመልሶ፣ ዓይኖቹን በመጠኑ ለስስ ሥራ፤ በስሱ መልሶ ከፈተአቸው፦ በአዉቆታ (ኢንተንሽን) መደሰት ስሜት ዉስጥ እራሱን አብልጦ ገባ ገባ አደረገ። ለቅጽበት ምክትል ጣሪአው፣ አደፋ ጨርቁ ኮርኒስን አጢኖት፣ ወዲያው አንድ ብሎ ሰየመዉ፨
ወደ ሁለትኛ አሰሳ ሳይመጣ፣ በምንም ወደ አልደፈረሰ ማለዳ ጸጥታ ሳቢ ምትሃት ደግሞ ተስቦ ገጽታውን ለማጣጣም በላቀ ነፃነት ወደ ገጸ-ጠዋቱ ሰምጦ አተኮረ። ‘ግን ላስተዋለው፣ ከማንም ቀድሞ መንቃት፣ ህይወት ለዋጭ ልእለምትሃት ነው። ግለትምምን (ኮንፊደንስ) ሲቸርስ! ስለዛ ወደፊት ባለመንገር ዉስጥ እነግራችሁ አለሁ’፨
የተኛበት ቀጭን ፍራሽ፣ ቀጭን ደማቅ አረንጓዴ አንሶላ ተደርቦበት አለ። ግን፣ አንሶላ እና ግል-ብጁ (ሰልፍሜድ) ፍራሹ መሃል፣ “አጣጪ” ብሎ የሰየመው የቀይ በሬ ቁርበት ተነጥፎበት አለ። ግልብጁው አለቅጥ በመመቸቱ፣ በድሎቱ ስለሰነፈ፣ መድላቱን አስተካካይ ይህ ቁርበቱ ሆነለት። ደንበኛ ምቹ እና ተገቢ አልጋ ከቁርበቱ ተደማምሮ ለጀርባ መሸከሚያ አሽከርነት በቃ፨
ከ ቅጽበቶች እርጋታ እና የማለዳ ድባብ አስተዉሎት ተመለሶ፣ በባህርዛፍ እንጨቶች እና ጠፍሮች በመስ አራት አመቶች ቀድሞ ከተዘጋጀው አልጋ ላይ ጀርባውን አነሳ። ቂጡ ላይ አካሉን ቆለለ። ከሉልአዊው ስደተኛዎች ተቋም ለስደተኛ የተለገሰውን ድንቅ እሚባል – አንድአንድ ሰራተኛዎቹ ሲአነብቡት “ዩኤንኤጭሲአር” እሚሉት ‘Unhcr’ እሚል ስመ-አርማ ያለውን፣ በእርካሽ ዋጋ ስታገኘው፣ እሚ ተሯሩጣ ለደጋአማ ከተማው ስትል የገዛችው – ዳልቻው ብርድልብስ፣ ተንሸራትቶ ከደረቱ በመሸብለል ወደ ብልቱ ተሰበሰበ እና ተቆለለ፨
ወትሮም፣ ከመረጠው አነዋወር ጥበብ ተነስቶ እርጋታን ለስብእናው አከናንቦ በእርጋታ በእየሰከንዷ እሚንቀሳቀስ ሰው ሆኖ አለ እና፣ አሁንም እንደ ምንግዜው፣ ሰክኖ የቤቱን ግራቀኝ ተመለከተ። እሚ በመሬቱ ፍራሽ ከተኛው የቤተሰቡ መንጋ መሀከል ናት። በስተ ቀኟ፣ በጨቅላዋ ጮለቅ ስር-አንገት እቅፋት፣ አንገቷ በወጪገቢ ትንፋሽ ጋል ብሎላት፣ ማን መሆኗ ሙሉኛ (ፉሊ) በብድር ለንዋም ተሰጥቶ እስኪመለስላት እንደ ጠፋች ናት። ድንገት ቀጭን ድምፃማ ድንክዬ ፈስ ጢጥ አደረገች። ከጀርባዋ፣ ጢዩ ግንባርዋን ማጅራቷ ላይ አገናኝታባት ተወሽቃባት አለች። ቂጥ አፈንድዳ፣ በታጠፈ ጉልበቶቿ የእናቷን ጀርባ መልሳ ጎስማ ነክታ፣ አሁን ስራ የሰራው የእሚ ቂጥ ላይ የእግሮቿ ቁመት አልቆ አለ። በጡቶቿ አቅራቢያ አንገቷ ስር ጮለቅ፣ በጀርባዋ ባለፍየል ጭራ መሰል ጸጉር ጉንጉናማዋ ጢዩ ከእናትአቸው ትክአልባ ስነልቦናአዊ ከለላ መስርተው፣ በብቃት ሰላም እየሳቡ መሽገውባት አሉ። በመደቡ፣ ሁሉ ሰላም እና የበቂ ፍች ያለው ነበር። ‘አቤት እናት፦ ለጨቅሎቿ ሁሉን እምታውቅ እና የምኑም መፍትሔ የሆነችው ፍጥረት’፨
ወደ ሌላው ጥጋት በእርጋታ ናሆም ዞረ፤ ራቅ ብሎ እነ ቢግ ፍራሽ ላይ ብሩ፣ ቢግ እና ባቤ በእየፊናአቸው በዉጥንቅጥ አግጣጫዎች በመጋደም መኖራቸውን በዉሰት ከለቀቁ መሀል ነበሩ። ማንም በጊዜ ቢነቃ እና ቢያይአቸው፣ እንደ ረቂቅአዊ (አብስትራክት) ስእል ነፃ ቅጥ (ፍሪ ስታይል) በእየቀኑ ተቀያይሮ ያስመለክቱት አለ። ፈገግ አለ። ‘ደግ ምስል መቅረጫ መሳሪአ ያገኘሁ ቀን ይህን ወደ ማህደር መቀየር አለብኝ፤’ ባቤ እንደ ለመደው ግራ እግሩ፣ ብሩ ሆድ ላይ ስለተጫነ፣ ቀድሞ መንቃት አለበት። ብሩ ከቀደመው ግን፣ ስለ ኢህግአዊ ድንበርጣሽነቱ የእግሩን ሥጋ ይዞ ምዝልግልግ ያደርግለታል። ትላንት ጨምሮ ሰሞኑን ያን አድርጓል። ባቤ ባለአስራሁለት አመትዎች እድሜ ተናዳጅ፣ ብሩህ፣ ግለትምምንአማ፣ ግልዮሽኛ (ኢንዲቪጁዋሊስቲክ) ወፈር ወደማለት ያለ ጎረምሳው፣ ይህ ሁሌም ንዋሙን-አብራሪ የሆነ መመዝለግ ሰሞኑን እየጠነከረበት በጠባ ቁጥር መብገን እየለመደ ነው። ብሩ ግን ቀድሞ ስለሚነቃ እንጂ ተኝቶ በቡጢ እና እርግጫዎች በሁለቱም ጎንዎች በጎረምሶቹ በየተራ ሲነደል አይሰማውም። ሲነቃ፣ በሰላማዊነት እንግድነት ብቻ የጠየቁት እጆች እና እግሮችን፣ እርምጃ ይቸርአቸው አለ። ‘ትልቅ እንቅልፋም፣ ጉዱን አላወቀ’፨
ወደ ጥርስ መወልወል እና ፀሎት ከመሄድ እና ተግባርአዊ ዕለት ከመጠንሰስ፣ ቀድሞ እስከ እረፋዱ እሚቋጩ ስስ ዕቅድዎች አሠሳ ወደ ራሱ ትኩሮት ተመልሶ ቀጠለ። ‘ሁለትኛው ሁለገብ ጽዳት ነው፤’ ወደ ሦስትኛ ዐብይ ጉዳይ ሲመለስ የቢግ እንግሊዝኛ ጥያቄ እና የባቤ ሰሞንኛ ንትርክ ትዝ አለው እና በእነዛ ጸና። ቀጥሎ አሰበ። ‘የትላንቷ አዉሎነፋስ፤’ ምሣሰዓት ጀርባ ደግሞ የተሲዓት ተግባር ከእርሱ ከተፈለገበት መረመረ። ቢመረምር ምንም አላገኘም። ‘ማታ ስ?’ ሦስትኛው የዕለት ክፍለጊዜ? ምንም ግዴታ አልያዘበትም! ‘የመስ ፊት፤’
ናሆም ይህን ሲከውን፣ የተግባርዎች ዕቅድ ነደፋ ለማዳበር እንጂ የሚአስበው እሚዉለውን ሙሉ ወይ ከፊል አዋዋል አይደለም። ያ፣ መርሐ-ግብር (=ተግባር መምሪያ) እሚሉት ሳይሆን አይቀርም። መርሐግብርን ከእዛ አንፃር ግን ከባድ እና ኢተፈጥሮአዊ ብጤ ስለሆነ አይከተለውም። ቀድሞም ማንም ዕለትን አይቆጣጠረውም። እርሱም ያንን አለ-መብቃት ይቀበል አለ። ‘እኔ እግዚእአብሔር አይደለሁም፤’ ብቻ ግን ስስ ቁምነገር ያሥሳል። ‘እማውቀው፣ ከእኔ በድርጊት እሚፈጸም ምን ምን ይጠበቅብኝ አለ?’ ይህ ነው የእርሱ መነሻ። ምንም ተቆጣሪ ተግባር ሰግጎ ካልጠበቀው፣ ዕለቱን ‘በደስታ ሆኜ መቋጨት’ ብሎ፣ ምድር እንድትቀበለው እግርዎች ወደ ወለል ይልካል። የሆኑ ግዴታ ተግባሮች፣ ሰግገው ለመደረግ ሲጠብቁት ካስተዋለ፣ አንደኛ እነሱን መቁጠር እና ግዴታዎች እንዳሉ ማስታወስ፣ ሁለተኛ በዕለቱ መቼ እና እንዴት ብከውናቸው ከሁሉ ቀላል እና ስኬትአማ ይሆኑልኝ አለ ብሎ ማቀድ እና ድርጊቶቹን ለምርጡ አከዋወን ጥምረት ማመሳቀል ብቻ ነው። ምርጡ የአጋጣሚዎች ስብጥር ንድፍ ተበጀ ማለት ነው። ኃላፊነት እንዳይተው፣ በቅድመንቃቱ (ፕሮአክቲቭ) መነሾነት ደስተኛ እንዲሆን፣ በተግባር ስኬት እንዲያቀርብ፣ እራሱ ላይ አተኩሮ በልቦናአማነት (ማይንድፉልነስ) ለመኖር ስለእሚአበቃው ይህን ዘወትር ይከውን አለ፨
ይህ ልምምዱ፣ ያኗኗር ስኬት አሳፍሶት ነበር። በእሚጠበቅበት የቀን ድርጊትዎች፣ የመጨነቅ እና ያለማሳካት ኋኝነትአዊነትዎችን (ፓሲቢሊቲስ) በእዚህ እንዲነጥፉ ያደርግ አለ። በዘፈቀደ አከዋወን ዕለቱ ስለእማያልፍ፣ አለመዛል እና አለመድከም እንዲችል አድርጎት ነበር። ለምሳሌ ይህ የዕለት ስስ ዳሰሳ እሚለው አደብ-ጊዜ፣ አንድ ተግባር ብሎ እከሌን መጠየቅ ካለው፣ ሁለተኛው ገበያ መዉጣት ከሆነ፣ ሁለቱን አጣምሮ ለመከወን እራሱን እንዲአበጅ እና ኋላ “ኡ! የአን ረሳሁ! ወይ! ምነው አብሬ የአን ይሄን ባደረግሁ!” እንዳይል ይፈቅድለት አለ። ዕለት በስሱ ማሰብ ለርሱ አንዱ ይህ የማስተጋበር ትልም እንጂ በመርሐግብር መታሰር አይደለም፨
ብዙዎች ግን፣ ቀላል የዕቅድ ጥበቡ፣ ለዕለትአዊ ስኬት እና ደስታ እሚረዳ አይደለም፣ ሂወትን መቆጣጠር አይቻልም፣ ያን ግዴታ በእዛ ደቂቃ በእዚህ ደቂቃ ሳደርግ ካልተገኘሁ ሞቼ ልገኝ አስብሎ ከሰው ያራራቃል፣ በሚሉ ተቃውሞዎች የሃሳቡን ጥቃት ሰርተውለታል። አስረኛ ክፍል እንደ ገባ፣ ይህን እሚጠላ፣ የስነህይወት መምህር፣ መምህር አጉናው ድጋፌነህ፣ የጸረ-ዕለት-ዕቅድ ተከራካሪ ሆኖ ገጥሞት ተፋለመው። በመሰላቸው ጊዜ መስራት እንደ አለባቸው እሚአስረዱ ብዙ ምክርዎች ከዘረዘረ በኋላ መናገር ቀጠለ እና “በዘፈቀደ መኖር ይሻላል ማለቴ አይደለም። ግን ሰው በዕቅድ፣ መሐግብር ምናምን እሚተበተብም ዘረፍጥረት (ስፒሺስ) ደግሞ አይደለም። ባሻቹህ ሰዓት አጥኑ። ደስ ስላላችሁ ብቻ፣ ስኬት ያኔ ይጨምራል። እራስ ማስገደድ ዉስጥ ግን መሰበር እንጂ ስኬት የለም። ስትደበሩ፣ መርሐግብሬ ነው በሚል ፈሊጥ ከመታሰር እና ጥናቱን ከመጥላት ይልቅ ወጣ በሉና ተጫወቱ። ስትመለሱ በራሱ ጊዜ ማጥናቱ ስቧችሁ ታቀረቅሩ እና ስኬትአማ ትሆኑ አለ። ባጭሩ፤ የሰው ልጅ ትልቅ ነው። በመርሐግር አይጠፈነግም።” አለ። ሲጨርስ፣ ናሆም እጁን አዉጥቶ ነበር። እድል ተሰጠው። “መቼም ማጥናት ከደበረኝስ?” “የትላንቱን ቤትስራ ያልሰራ አለ?” ወደ ማስተማሩ ተቀየሰ፨
‘አጎቴ መስ ግን ማቀድን እንዳፈቅር አድርጎ ሚስጥሩን አስተማረኝ። ባቋራጭ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን ስንሄድ፣ ያስተማሪውን መምህር አጉናው አዲስ ርካሽ ኪራይ ቤት አሳይቼው መምህሩ ያለውን ነገርኩት። ‘ይሄ ያልተማረ አስተማሪ’ ብሎ ተቆጣልኝ። ድንገት ዞር አለ እና ‘ቆይ ግን እርካሽ እንደሆነ የት አወክ?’ ብሎ ጠየቀኝ። ‘ጎረቤቱ ያለው ልጅ ለማንም ሳይናገር ርካሽቤት ሊፈልግለት እና ሃያብር ሊሰጠው ተነጋግረው፣ አገኘሁልህ ብሎ ወደ እዛ መራው። ቤቱ ሃምሳ ብር ስለቀነሰ ገባበት እና አስርብር ሰጥቶ በአርባ ብሩ ፈንታ ማርክ እጨምርልህ አለሁ አለው። ልጁ እንቢ አለ። መምህሩ እንደውም ተወው አለ እና አብሶ አበሳጨው። ልጁ ተናድዶ ወሬውን ለሁሉ ተማሪ አስወራበት እና ከፍተኛ ድሃ አስባለው። ገናም ቀድሞ ከነበረበት ትንሽ ብቻ እርካሽ ቤት ፈለገለት እንጂ ከሁሉ እርካሽ ግን እንዳልነበረ አሳወቀው። ጎረቤቱ የነበሩት አከራይዋ አያና ቤት ተከራይ ካመጣ አስር ብር እንደ እምትሰጠው ስለነገረችው ስድሳ ብር አልሞ እዛ ወደ እሷ ጋር ቀጥታ እንደ ወሰደው ነገረው። ‘ማርክ ምን ያደርግ አለ? እንደውም ተወው! ሀገርአቀፍ ተፈታኝ ነኝ። እንከፍ ድሃ!’ ብሎ እስከ እብደት አበሳጨው።’
መስ ይህን ሰምቶ ልጁን አደነቀ። ናሆምም ትንሽ አክሎ ነገረው። “ያኔ መምህሩን ስጠይቀው በመጀመሪያ እኔ ማቀድን ወግኜ አልነበረም። መጠየቅ ከቻልኩ፣ ነገርግን ሳልጠይቅ ካለፍኩ፣ ከእውነት ስለእሚአፋታኝ፣ ለዛስል ብቻ፣ ጥያቄ ሲታየኝ መጠየቅ ፈለግኩ። መጠየቅ እሚአስችል የሃሳብ ክፍተት ተመልክቼ ሳልጠይቅ ካለፍኩ ‘የዓለም ከሃዲ’ ነኝ ብዬ አምናለሁ። እማይጠየቅ ነገር ደግሞ እምብዛም የለም። ከምንም አለመጣበቅ የመጠየቅ አቅም ቁልፉ ነው። ከምኑም ካልወገኑ፣ ምኑንም መጠየቅ ይቻል አለ። በእኔ ጥያቄ እሚመለስ ፍሬነገር ምን እንደእሚሆን አላውቅም። ህይወቴን እሚአበራ ነገር ሊገጥመኝ ይችላል። ወይ ደግሞ እሚአደምጥ ወይም እሚመልስ ደግሞ አንድአች ከፍተኛ መንቃት ሊመዝዝበት ይችል አለ። ስለዚህ አንድ ክፍተት የተመለከተ ሰው፣ ይህን መጋጨት ወይም አለመገለጥ ለማሳወቅ እንኳ ብቻ መጠየቅ ግዴታው ነው። ለምን የጥያቄ ሃሳብ እንደ ቀረበለት አያውቅም። ደደብ ወይም ጎበዝ ነኝ ሳይል ብቻ በማመዛዘን ሆኖ፣ ተገቢ መካንጊዜ (ስፔስታይም) ዉስጥ ወይም-ይልቅ ዐውድ ወይም ድባብ ዉስጥ ሆኖ መጠየቅ ይገባው አለ። ለምሳሌ ሰው ሞቶ ሲቀበር ለምን በሣጥን ይከተት አለ ብሎ የተገረመ ሰው ጥያቄውን ሰው ሲቀበር ከእሚያለቅሱ ቤተሰቦች ላንዱ ሄዶ ‘ሣጥኑ ምን ይሰራለት አለ?’ ብሎ መጠየቅ ተገቢ አይደለም። ግን ዞር ብሎ ለሌላ ሀዘንተኛ ላሎነ ሰው ወይም ለአስመሳይ ለቀስተኛ ግን ቢጠይቅ አመክዮው ይገለጥለት ይሆን አለ። ብቻ በተገቢ ሥፍራ ማንም ምንም መጠየቅ ቢከውን፣ እሚጎዳ ማን አለ? ማንም የለም። ባለ መጠየቅስ? ምንአልባት፣ ሁሉም!”

ከስስ ዕለት ቅኝቶቹ መልስ፣ ፈርጣማው ናሆም ፈለግዎቹን በግል ወደ አነጸው ላስቲክ መጫሚአ ከተተ። የተመረጡ የጀሪካን ላስቲክዎች ጣሣ ዉስጥ አቅልጠው፣ በሸክላ ጭቃ ዱካቸውን በማተም ባዘጋጁት ቅርፅ የቀለጡትን ላስቲኮች አፍስሰው፣ ብዙ መጫሚአዎች ለቤተሰብዎቹ ያዘጋጁ ነበር። ከእንደማንኪያ እና ሌላ ቁሳቁስዎች መሀል። በምቹ ጫማው የተተከለ አካሉን አንቀሳቅሶ፣ አልጋውን ተገቢ የማንጠፍ መስተንግዶ አደረገለት። ዝግታ እንደ ያዘው ወደ በሩ አመራ። በክረምቱ ሁሉ አየር እና ምድር ዓለሙ ሲረጥብ፣ የቤቱ ግድግዳ እንጨቶች በቋሚነት ለወርዎች ሲርሱ፣ ቤቱ እርጥበት መጥጦ ይሸበሸብ፣ ይከብድ አለ። ገናም፣ ወደ ጨቀየ፣ ላቆጠ ምድር በቀላል ኢምንት ኢምን እያለ ስለእሚሰርግ፣ የቤቱ በር እና መስኮትዎች እንደ ልብ ገጥመዉ አይዘጉም። ግን በሩ አብሮ ካመትአመት በመስመጥ መሬት እሚፍቅ ሆኖ እንዳይሰርግ፣ ከፍባለ ደፍ ከወለሉ ተጣልቶ ርቆ ተገጥሞ ነበር። ደፉን ወርዎች ኋላ ጮለቅ እየዳኸች እንኳ መሻገር እና ዉጭ መዉጣት አትችልም። ወደ ሠላሳአራት ሴሜ.ዎች ከፍታ ድረስ ነበር። በእርሱ አናት ላይ በሩ የተንጠለጠለ እና ሲዘጋ ልክክ ብሎ እሚገጠምበት ነው። በመከፈት እና መዘጋት ድንቅ ሎሌነት እንዲይዝ ይህ ኪነህንፃአዊ (አርኪተክቸራል) ብልሃት አስችሎት ነበር፨
በዝግታ እሚንቀሳቀሰው ናሆም በረከት፣ መቀርቀሪአውን ከተሰካበት የግድግዳ ብስ በቀላል ጉልበት መንጨቅ አደረገ እና በአየሩ ለቀቀው። በሩ አካል ላይ በተያያዘበት አጭር ጠፍር በእራስሰር (አዉተለማቲካሊ) ተንጠለጠለ። በሩ አለቅጥ እንዳይበለቀጥ በመዳፍ ገደበው። ቆመ። ዉጭን ተመለከተ። ብርሃን አብዝቶ ገፍቶ አልደረሰም። ሌላ ሥፍራ የማታ ጀምበር ሆኖ ወደ እዚህ የማለዳ ጀምበር አልሆነም። ሌላ ቦታ ጀምበር ሲርቅ ገና እዚህ ወደ ሰማዩ ይሰቀል እና ይበራ አለ። ለዓይንዎች ግን ድንግዝግዝ ዉጋገኑ በቂ ሆነለት፨
ከዉጭ ዘመንአዊ መቀርቀሪአው ስክት ብላ ታገለግል አለች። ተጠቀማት እና ዉጭውን ተቀላቀለ። የተንጣለለ ጊቢ፣ ሞላጎደል ባዶ፣ በእሾሃማ ኮሽም ዛፍዎች መተቃቀፍ፣ ዘብነት እና ለአመል ቆም ቆም ባሉ አቅመቢስ አጋፋሪ እንጨትዎች መናኛ አጥር ተከልሎ አለ። ቀዝቃዛ አየር አስገድዶት ወደ አፍንጫው በጉልበት ተማገ እና ወደ “ያን ትተህ እኔን አጢን” አመጣው። ፊቱን የወረረ ህቡዕ ቅዝቃዜ ፍልቅልቅነት ቸረው። ‘የማለዳ ሥጦታ፤’ ፈገግ አለ። ዙሪአገባውን እየተመለከተ አካል እንቅስቃሴ ዉስጥ ተጠመደ። እሚወድደው ቅዝቃዜን ደጋግሞ በተሰማው መንገድ ሁሉ አብሮት እያጣጣመ ቆየ፨
በመደበኛነት ደጋማ እሚገልፃት ፋሲካይት፣ በማለዳው ናሆም አድናቆት እሚቸረው አሸብራቂ ቅዝቃዜ አላት። በተለይ ቤትአቸው፣ ከከተማው ሙቀት ፈንጠር ብሎ፣ ከብዙ መንግስት መስሪአቤትዎች የተርታ መንደር ጀርባአቸውን እየተመለከተ ሲታነፅ፣ በብቸኛነቱ ጭምር ለመቀዝቀዝ የተፈረደበት ነበር። በድባብም በጭስ ብክለትአልባነትም። ጭራሽ ከጓሯቸው ራቅ ሳይል እንኳ የከተማ አጎራባች መጠነኛ ጫካው መነሻው ስላለበት ነፋሻማነቱ በቤታቸው የጠና ነው። ናሆም ደግሞ መቀዝቀዝ ጥሎበት ይወድድ ስለነበር አቀማመጡን ቤተድቅ (ማንሽን) ባይሆንም እምብዛም አይጠላውም። ቅዝቃዜ እሚጠላ ይቃረነው አለ እንጂ የከተማዋ አንድኛ ዉበት መቀዝቀዝዋ ሁለተኛ የሰው እና ከተማ አቅሙ ህገክፍፍሉ (ሬሾ) አለቅጥ አለመብዛቱ እንደ ሆነ ይከራከር አለ። ማለዳውን ከተተኛ ቅዝቃዜው ዉበት ግለት ግን እማይቀመስ ነው ብሎ ይመልስ አለ። በማለዳ መንቃቱን ለማብሰልሰል እንኳ እሚፈቅድ ስለሌለ ሃሳቡ ሁሌ አሸናፊ ይሆንለት ነበር፨
እንቅስቃሴውን ከዉኖ ከደቂቃዎች ማለዳ አጢኖት (ኦብዘርቬሽን) ኋላ፣ በልዩልዩ ጭርጭርታዎች ወፍዎች ማዜም ሲአበዙ፣ ‘እሚአደርጉትን በማቀድ ስለዕለቱ ሲወያዩ’ ብርሃን ሌላ ዓለም ምሽት አንግሶ እዚህ መሞቅ ሲጀምር ወደ ቤት ተመለሰ።የ “ቀ” ፊደል ዘር “ቋ”ን ጨምሮ በአማርኛ ባይኖር ለልጆቻችን ደግ ነው። የቋንቋው መሰረተ ድምጽ አስጨናቂ ስነልቦና አምጪ እና በቀላሉ ልክ ጀ እና ዠ አንድ እንደሆኑት በ “ከ” ዘር ሊለወጥ እሚችል ነው። ስለ አማርኛ ገበታ ወደፊት ነግራችኋለሁ፤’ ልብስ ቀየረ። በግል ያልተበጀ መጫሚአ ለወጠ። የጅ ሰዓቱን እሚገምተውን ለማረጋገጥ ተመለከተ። አስራሁለት ሰዓት ሊል ሁለት ደቂቃዎች ቀሩ። ቀንን ተቀብሎ አለ። አሁን ገብቶበት አለ። ስለ እዚህ በቀን ወደመሰንበት ሳይሆን ንቁ እና ደስተኛ በመሆን ብቻ ወደመኖር ይገባ አለ። ጉልበትየለሽ ጠዉላጋ ጨረርዎች ለ አመል ያክል ከደካማ ፀሐይ እየሞቀ ወደ ቤተክርስትያን በከባቢ ዓለሙ ግል ቅኝግዛት ማንም በሌለበት በብቸኛነት ይዞ፣ አለ ድካም ያስለቀቀውን ባዶ ጎዳናዎች እንደቅኝ ገዢ ለብቻው ይዞ ነጎደ፨

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

By Binyamhailemeskel

Hey there! If you want to know about me, I just like fun, commonsense wisdom, and human love. Let us live a bright today changing tomorrow into brighter.
Regards,

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s